ኅብረ-ብዕር · 6 7 ኅብረ-ብዕር ጨ01 ጤጋ05 dፎ2007 የምንወግነው...

25
ያበጠው ይፈንዳ ቅፅ 01 g ቁጥር 05 g የካቲት 2007 g ዋጋ፡15.00 ኅብረ-ብዕር

Upload: others

Post on 05-Sep-2019

54 views

Category:

Documents


6 download

TRANSCRIPT

ያበጠው ይፈንዳ

ቅፅ 01 g ቁጥር 05 g የካቲት 2007 g ዋጋ፡15.00

ኅብረ-ብዕር

ሁሉም ጣቱን ወደራሱ ይቀስር

መልእክተ ህብር

ማኔጅንግ ዳሬክተር ብንያም ከበደ

ዋና አዘጋጅአመለወርቅ ጌታቸውአድራሻ: የካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤት ቁጥር 1076

አምደኞች ኩምሳ ጉዲና

መዝናኛታገል ሰይፉ

ስፖርት አብዱልሰመድ መሐመድ

ሪፖርተሮችደምሰው በነበሩ

ኤደን ኡታላተስፋዬ ቱፋ

ፌቨን አብርሃም

ግራፊክስና ሌይአውት ዲዛይን

ፀሐፊአይናለም ከፈለኝ

ህትመት ክትትልና ቁጥጥርዮናስ አዲሱ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁ. 160

ስልክ 011 5 57 12 88e-mail: [email protected]

አታሚ ሴንትራል ማተሚያ ቤት

አድራሻ: ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03የቤት ቁ. 414

ኅብረ-ብዕርበማህበራዊ፣ በፖለቲካና በሥነ-ጥበብ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በየ15 ቀኑ ለህትመት የምትበቃ መጽሔት

አሳታሚ: በሜቲ የህትመት፣ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ እና የማስታወቂያ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

የካቲት 2007ቅፅ 01 g ቁጥር 05

Think Design

0912 780 118

ከምርጫ ቦርድ ብንጀምር ምርጫው ለሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች እኩል የመጫወቻ ሜዳ እንዲኖር የማድረግ ቁልፍ ኃላፊነት የተጣለው በቦርዱ ላይ ነው፡፡ ምርጫውን ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ ለማስኬድ ትላልቅ ተግባራት ተከናውነው፣ ነገር ግን ጥቃቅን የሚባሉ ህፀፆች ከታዩ የተሰሩትን ትላልቅ

ሥራዎች ዋጋ ይቀንሳሉ፡፡ መልካም የተባሉ የምርጫ ሂደቱ ውጤቶችን ያበላሻሉ። ይሄም በመሆኑ የምርጫ ቦርድ ከወዲሁ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል፡፡

ምርጫ ቦርድ ገና ከጅምሩ በምርጫ ማስፈፀሙ ሂደት ላይ ወገንተኝነት የሚታይባቸው ወይም ከዚህ ቀደም በተደረጉ ምርጫዎች ላይ በአስፈፃሚነት ተመድበው ችግሮች የታዩባቸው ካሉ እንዲወገዱ በማድረግ ገና በጠዋቱ የማጥራት ስራውን ሊጀምር ይገባል፡፡

ከተለያዩ የአለማችን ክፍል የውጭ ታዛቢዎች በምርጫው ሂደት ላይ እንዲገኙ ማድረግ ብቻውን የምርጫውን ትክክለኛነት አያሳይም፡፡ ዋናውን ምስክርነት የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን በሚገባ በመገንዘብ በሁሉም መስክ ቦርዱ እንከን የማይወጣለት ምርጫ እንዲሆን ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በሌላ በኩል ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለምርጫ ማስፈፀሚያ የተመደበላቸው በጀት እየዘገየ ስለሚለቀቅላቸው የፖለቲካ ስራችንን መስራት አልቻልንም የሚል ቅሬታ ሲያሰሙ ይደመጣል፡፡ ገዢው ፓርቲ በሚያከናውናቸው ስራዎች ከህዝቡ ጋር በቀላሉ መገናኘት ስለሚችል (Governing Party እንደመሆኑ) የሚድያ ተደራሽነት ችግርና የበጀት እጥረት ሊገጥመው እንደማይችል የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ለተፈፎካካሪ ፓርቲዎች ግን ለምርጫው ማስፈፀሚያ የተመደበው በጀት በጊዜው ካልተለቀቀላቸው በምርጫ ፉክክሩ ላይ የራሱ ተፅዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ምርጫ ቦርድ በፅኑ ሊገነዘብ ይገባል። በአጠቃላይ በምርጫው ሂደት ላይ “30 ሚሊዮን ህዝብ በመራጭነት ተመዘገበ” ማለቱ ህዝቡ በመብቱ ምን ያህል እንደተጠቀመ የሚያሳይ ቢሆንም ለምርጫው ፍትሀዊነት ግን እንደ ማስረጃ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ትኩረት መደረግ ያለበት ምርጫው ፍፁም ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ነው።

በመገናኛ ብዙሀን በኩል ያለውን ስንመለከት ደግሞ ምርጫውን ለማድመቅም ሆነ ለማደብዘዝ ይህ ነው የማይባል ትልቅ ሚና አላቸው። በተለይ የህዝብ የሆነው “ኢብኮ” (ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ኢትዮጵያ ሬዲዮ) አሁን በተደጋጋሚ እያሳየንና እየነገረን እንዳለው ይሄን ያህል ብዛት ያለው ሰው ተመዝግቦ የመራጭነት ካርድ ወሰደ ማለቱ ብቻ ፋይዳ የለውም። ይልቁንም ዲሞክራሲውን የሚያዳብርና ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን አቅጣጫ የሚያስይዙ ሚዛናዊ ቁም ነገሮች ለህዝብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የመገናኛ ብዙሀን ያለፉትን ምርጫዎች ጥንካሬና ድክመት እየገመገሙ ሚዛናዊ መረጃዎች ሊያቀርቡ ይገባል።

በሌላ በኩል ደግሞ ቀደም ብለው መጀመር የነበረባቸው የፓርቲዎች የምርጫ ክርክር ፕሮግራሞች መዘግየት ይታይባቸዋል። ተፎካካሪ ፓርቲዎች በፖሊሲዎቻቸው፣ በፕሮግራሞቻቸው ላይ ቀደም ብለው ክርክር ቢጀምሩ ህብረተሰቡ በስሜትና በሙሉ ፍላጎት የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ ያነሳሳዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሰፊ የማገናዘቢያ

ግዜ አግኝቶ የምርጫ ካርዱን ለማንና ለምን እንደሚያውል የማሰቢያ ጊዜ እንዲኖረው ይረዳል። በመሆኑም የፓርቲዎች የክርክር መድረክ የምርጫውን ዲሞክራሲያዊነት ማሳያ መሆኑን መገናኛ ብዙሀን ሊገነዘቡት ይገባል።

ሌላው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግን የሚመለከት ጉዳይ ነው። ኢህአዴግ ምርጫው ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማድረግ “የምርጫ ስነ-ምግባር መመሪያ” (Code of Conduct) አውጥቼ አባሎቼን እያሰለጠንኩ ነው ብሏል። ይህ የሚደገፍ መልካም ተግባር እንደሆነ ይታመናል፡፡ ሆኖም ግን እስከዛሬ ድረስ አንድም ችግር አልተፈጠረም ማለት አይቻልም። ተፎካካሪ ፓርቲዎች “ወከባ ተካሄደብን፣ ተፅዕኖ ተፈጠረብን” ሲሉ ይደመጣል፡፡ ገዢው ፓርቲ ደግሞ የስነ-ምግባር መመሪያውን ተከትሎ ጥፋተኛ የሆነ አንደም አባሉን በገሀድ ሲቀጣ እና ሲያባርር አልተስተዋለም። በምርጫው ሂደት በተፎካካሪዎች ላይ ወከባ የሚፈጥር ወይም ጫና የሚያሳድሩ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ካሉ ጉዳቱ ለተፎካካሪዎች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለገዢው ፓርቲው ጭምር ነው። ምክንያቱም ፍትሀዊ ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ የገባውን ቃል ተአማኒነት ያሳጣልና።

የምርጫው ዲሞክራሲያዊነት መገለጫ ዋነኛ አካል የሆኑት ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ለሂደቱ መሳካት የሚጠበቁባቸው በርካታ ነገሮች አሉ።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች መቸም ምርጫ ውድድር ውስጥ ከገቡ አሸንፈን መንግስት እንሆናለን በሚል እምነት እንደሆነ አያጠያይቅም። ይህ ማለት ከ90 ሚሊዮ በላይ የሆነውን ህዝብ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ዓላማ ሠንቀዋል ማለት ነው። አሁን የሚታየው ሐቅ ግን ይህንን አላማቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው። ምክንያቱም የፓርቲው አመራሮች እርስ በእርሳቸው አለመተማመንና አለመግባባት እየፈጠሩ ለደጋፊዎቻቸው ተስፋ አስቆራጭ፤ ለተፎካካሪዎቻቸው ደግሞ በሜዳው በስፋት የመጫወት እድል እየፈጠሩ ነው። ይሄ ፓርቲያቸውን ክፉኛ ይጎዳል። ዛሬ “ቀበና ቢሮ” ተቀምጠው መስማማት አቅቷቸው ነገ አራት ኪሎ ቤተመንስት ሲገቡ የሚጠብቃቸውን ሠፊና ዘርፈ ብዙ ኃላፊነት በስምምነትና በመግባባት ፈፅመው 90 ሚሊዮን ህዝብ ሊመሩ ይችላሉ ብሎ ለመገመት ያዳግታል።

በፓርቲዎች ውስጥ ልዩነቶች ሲፈጠሩ የውስጥ አለመግባባታቸው ምክንያት የገዢው ፓርቲ እንደሆነ በመግለፅ ችግሮቹን ወደ ሌሎች መለጠፉ ብዙም አያስኬድም። ይሄ ሆኗል እንኳን ቢባል ችግሩ ከፓርቲዎቹ አመራሮች ውጪ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ገዢው ፓርቲ በቀላሉ ሊከፋፍላቸው የሚችሉ አመራሮችን ይዞ ተፎካካሪ ፓርቲ መሆን የትም አያደርስምና። ይህ ደግሞ የገዢው ፓርቲ ድክመት ሳይሆን የተፎካካሪዎቹ ፓርቲዎች አመራር አባላት ብቃት ማነስ ወይንም በቀላሉ መፈረካከስና የአላማ ፅናት ያለመኖር ነው።

በአጠቃላይ መጪውን ምርጫ የተሳካ፣ ፍፁም ዲሞክራሲያዊና ፍትሀዊ ለማድረግ አንዱ የሌላውን ድክመት እያነሱ ከማብጠልጠል ይልቅ ሁሉም የየራሱን ኃላፊነትና ግዴታ ሊወጣ ይገባል። የምርጫ ቦርድ፣ የመገናኛ ብዙሀን፣ ገዢው ፓርቲና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከቅንነት፣ ከእውነተኛነትና ከህዝብ ታማኝነት የመነጨ ተግባር ማከናወን አለባቸው። ሁሉም ራሱን ሊመረምር ይገባል! ሁሉም ጣቱን ወደ ራሱ ይቀስር። g

አብይ ጉዳይ ይህ አምድ በእንግሊዘኛ Cover Story የሚባለው ሲሆን በተመረጠ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትንታኔ፣ ማብራሪያ የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ በጉዳዩ ላይ በቂ ጥናት በማድረግ ወቅታዊ አብይ አጀንዳ ላይ በመመርኮዝ መረጃ የሚቀርብበት ነው።

ሙግትይህ አምድ ማንኛውም አይነት ሀሳብና አመለካክት በነጻ የሚስተናገድበትና በሀሳቡ ላይ የተለያዩ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሚሟገቱበት ሲሆን በዚህ አምድ ላይ የሚጻፉት ጽሁፎች የመጽሄቱ አቋም የሚወክሉ ሳይሆን የእያንዳንዱ ጦማሪን አመለካከት የሚገልጹ ናቸው። በዚህ አምድ ላይ አንኳር የሆኑና ሙግት አዘል እሰጣ-ገባዎች የሚስተናገድበት ነው።

መልህቀ-ፖለቲካ በሀገራችንም ሆነ በአለማቀፍ ደረጃ መሰረታዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በማንሳት ምርምርና ጥናት ላይ የተመሰረተ ጥልቅ የሆነ የፖለቲካ ትንታኔና አተያይ የሚቀርብበት አምድ ነው።

እኔ የምለውማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሁሉም ዘርፍ ሀሳቡን፣ አስተያየቱን፣ ጥቆማውንና ትዝብቱን የሚገልጽበት አምድ ነው።

24 ስኬት

36 ሙግት

ያበጠው ይፈንዳ?

ከሳሙኤል አባይነህ

6

10

16

28

42

44

8ዜና

መልዕክቶቻችሁ

ኅብረ-ኪንየፈረንጁ መምህር ጥያቄዎች

ታገል ሰይፉ

እግረኛውወይ የሃውልት ብዛት!

ከብላታ

መዝገበ ወንጀልአፈር በልታ ከሞት የተረፈች ነፍስ

በፈንታሁን ጌታሁን

ኅብረ-ስፖርት

እኔ የምለውየሽብር ታሪክ ራሱን ሲደግም!

ግዛቸው አበበ

40 ህገኛ

“ህግ ይኖራል ተተክሎሥርዓት ይኖራል ተዛውሮ”

20 አብይ ጉዳይ 12 ኅብረ-እንግዳ

በአያቱ የወጣው ኮሜዲያን“አይኔን አታስቁት ጥርሴስ ልማዱ ነው”

ኮሜዲያን በረከት በቀለ (ፍልፍሉ)

“ብዙ የተከፈቱ በሮች እያሉ የምናስበውየተዘጋችውን አንዷን በር ብቻ ነው”

ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ

ማውጫየካቲት 2007

ቅፅ 01 g ቁጥር 05

30 መልህቀ ፖለቲካ

“40”አሳጋራ ክፍል ሁለት

ሃይለየሱስ (ዳምቡሽ) ከደብረታቦር

ይድረስ ለገዢው ፓርቲይድረስ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች

ይድረስ ለገለልተኛ ኢትዮጵያውያንዮሴፍ ወ.ደግፌ

6 7

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

እኔ የምለውእኔ የምለው

የሽብር ታሪክ ራሱን ሲደግም!

ከዓመታት በፊት ወይም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1980ዎቹ ዓመታት የአሜሪካ መንግስትና አልቃይዳ (ያኔ

ሙጅሃዲን ይባል የነበረው) በጣም ወዳጅ ነበሩ። በዚህ ወዳጅነት ውስጥ ደግሞ የቢል ላደንና የጆርጅ ቡሽ ቤተሰብ በጣም የተቀራረቡ ወዳጆች ሆነው ነበር። ይህ ወዳጅነት የአፍጋንን ኮምኒስት መንግስትና በአጋርነት ጦሯን ወደ

አፍጋን የላከችውን ሶቭየት ሕብረትን ለመውጋት የተፈጠረ ስምምነት የነበረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቡሽ ቤተሰብና በቢን ላደን መካከል ሰፊ የቢዝነስ ግንኙነት የነበረ መሆኑም ይታወቃል።

በዚህ ወዳጅነት የተነፋው የሕብረት ኳስ በአፍጋን ምድር ብዙ ደም ካፋሰሰ በኋላ ኳሱ ከታቀደለት ሜዳ ውጭ ተጉዞ ዋሽንግተንና ኒው ዮርክ ላይ ነጥሮ 9/11 የተባለውን የሽብር ድራማ ሰርቶ ፍጻሜ ላይ ደርሷል። ከዚያ በኋላ አሜሪካ

ጦሯን ወደ አፍጋን ልካ የአፍጋናውያንን ሕይወት ያጨለመ ጦርነት አካሂዳ እሷም የዘራችውን እያጨደች ቆይታለች።

ይህ ታሪክ ትምህርት መስጠት ሲገባው በሚስተር ኦባማ ተመሳሳይ “የስህተት ታሪክ” ተደግሞ ለማየት በቅተናል። ባራክ ኦባማ የሶርያው የአሳድን መንግስት ከስልጣኑ ለማስወገድ ባካሄደው ጣልቃ ገብነት ከዓለም አደገኛ አሸባሪዎች ጋር ግንባር ፈጥሯል። የአልዘዋህሪው አልቃይዳ፣ ሳዑዲ

ዓረቢያ የምትረዳቸው ታክፊሪዎች፣ በኢራቁ ግብግብ ወቅት አሜሪካ ራሷ አሸባሪ ብላ የፈረጀችው አልኑስራ ግንባር እና እንደ አዲስ ተደራጅቶ እንቅስቃሴ የጀመረው ‘ኢስላሚክ ስቴት’ (ISIS) በኦባማው ጸረ-በሽር አልአሳድ ጦርነት ውስጥ ተሳታፊዎች ናቸው። እነዚህ ቡድኖች የሚያደርጉት ጦርነት፣ የሚፈጽሙት ሰቆቃ እና የሚያደርሱት መጠነ ሰፊ ጥፋት ሁሉ በሚዲያዎች ላይ (ቪኦኤንና ዶቸቨለን ጨምሮ) “ጸረ አሳድ ተዋጊዎች” ወይም “የሶርያ አማጽያን” ወይም “የዲሞክራሲ ጠበቆች” እየተባሉ እየተወደሱ ገጽታቸውን ለማስዋብ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ሲነገርላቸው ከ3 ዓመታት በላይ አልፈዋል። አስገራሚው ነገር የኢትዮጵያ የግልና የመንግስት ሚዲያዎች ተስማምተው ከሰሩት ስራ አንዱ ይህ በሶርያ ምድር ሽብርን የሚፈጽሙ ቡድኖችን ‘የነጻነት ታጋይ’ ወይም ‘ለዲሞክራሲ የሚፋለሙ’ አስመስለው እያወሩልን መክረማቸው ነው።

ቪኦኤና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ወጣቶች ከአሜሪካ ወደ ሱማሊያ ሄደው አልሸባብን ሊቀላቀሉ ሲሉ ተይዘው ለፍርድ ቀረቡ እያሉ ብዙ ዜና አሰምተውናል። ወደ ሱማሊያ ለመሄድ ሲነሱ እዚያው በአሜሪካና በአውሮፓ ምድር ተይዘው ነው ለፍርድ የሚቀርቡት። በጣም የሚገርመው ነገር ከአሜሪካ፣ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ፣ ከጀርመንና ኬሎች የአውሮፓ አገራት ወጣት ወንዶችና ሴቶች፣ በዕድሜ የጎለመሱትም ጭምር ወደ ሶርያ ሲሄዱ ግን ክትትል ተደርጎ ሲያዙ አልተሰማም። አሁን ወደ እየ አገራቸው ለመመለስ ሲሞክሩ ግን ክትትሉ ጠንክሯል፤ ተይዘው ለፍርድ ቀርበው የታሰሩም አሉ።

ለሶስት ዓመታት ያህል የሶርያ መንግስት ሶርያ ውስጥ የሚዋጉት ግለሰቦች ከ80 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የመጡ አሸባሪዎች ናቸው የሚል መግለጫ ሲሰጥ የአሜሪካ መንግስት በየሚዲያዎቹ ‘በሶርያ ውስጥ የሚዋጉት ሶርያውያን ብቻ ናቸው’ ብሎ ነገሩን መሸፋፈኑ አይዘነጋም። ‘‘ኢስላሚክ ስቴት’’ (ISIS) ዓለም አቀፍ ስጋት መሆን የሚያስችለው አንድ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ግን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት በሶርያ ከ50 በላይ ከሚሆኑ አገራት የተውጣጡ አክራሪዎች ተሰባስበው በመዋጋት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ስጋቱን ማስተጋባት ጀምሯል።

ወደ ሶርያ ሲሄዱ ‘በሰላም ያድርሳችሁ’ የተባሉት አክራሪዎች የሶርያው ጦርነት አሳድን ከማስወገድ ይልቅ በተቃራኒው አሳድን እያጠነከረ መምጣቱን አዩ። የኦባማ፣ የሄላሪ ክሊንተን፣ የእንግሊዙ ዴቪድ ካሜሩን “Assad Must Go” ፉከራ የሚዲያ ላይ ጩኸት ከመሆን አለመዝለሉንም ተረዱ። ስለዚህ ቀስ በቀስ ከሶርያ መውጣት ጀመሩ። ብዙዎቹ ወደ ኢራቅ ገብተው ውጊያውን ሲያጧጡፉ የቀሩት ወደ ቱርክ የስደተኛ ካምፖች መዝለቅ ጀመሩ። በዚህ ጊዜ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግስታት ኡኡታ ማሰማት ጀመሩ። ቱርክም ድንበሯን ዘግታ እውነተኛ አደጋ ያንዣበበባቸው እናቶችንና ሕጻናትንም ጨምሮ በምድሯ ወደሚገኙት ስደተኛ ካምፖች እንዳይደርሱ አደረገች። ከየምድራቸው ተውጣጥተው ወደ ሶርያ የሄዱት ወጣቶችና ጎልማሶች ወደ አሜሪካና ወደ አውሮፓ ከተመለሱ በሶርያ ያደርጉት የነበረውን የሽብር ስራ እዚህም ይደግሙታል የሚል

ጭንቀት ሃያላኑን ይንጣቸው ጀመረ። የISIS/ISIL አሸባሪዎች ሶርያ ውስጥ በኢምንት የእምነት

ትምህርት ልዩነት ሙስሊሞችን በጅምላ ሲቀሉና ሲረሽኑ፣ ከነሱ እምነት ለየት ያለ የእስልምና ትምህርት ይካሄድበታል ያሉትን መስጊድ ሲያፈራርሱና ሲያቃጥሉ፣ የአሳድ ደጋፊ ነው ያሉትን ሁሉ ሲገድሉ፣ ቤተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን በቦምብ ሲያፈራርሱና ሲያቃጥሉ፣ ቀሳውስቱንና መነኩሴዎችን ሲገድሉና አፍነው ሲወስዱ፣ ህጻናት በተለያዩ ምክንያች የጥይትና የጩቤ ሰለባ ሲያደርጉ፣ ‘ጀሃዳዊ ሴቶች’ በሚል ስም ሴቶችን ከቱኒዝያና ከሌሎች ዓረብ አገራት በጅምላ እያስመጡ የጾታ ስሜታቸው ማርኪያ ሲያደርጉ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ምንም ቅሬታ አድሮባቸው ተቃውሞ አሰምተው አያውቁም። ሚዲያዎቻቸውም እንደዚሁ ይህን ሁሉ በዝምታ አልፈውታል። የአጥፍቶ ጠፊ የመኪና ቦምቦች የሶርያን ወታደሮች ቤተሰቦችን በጅምላ ሲጨርሱ፣ አለዋይቶችን ሲፈጁ በሚዲያዎች ላይ ‘የአሳድ ደጋፊዎች ጥቃት ደረሰባቸው’ እየተባለ እንደ ድል ዜና መነገሩን አንረሳውም።

እነዚህ አክራሪዎች በእምነት፣ በፖለቲካ ወይም በዘር (ጎሳ) ልዩነት ሊቀጡ ይገባል ያሏቸውን ከፎቆች እየወረወሩ ይገድሉ ነበረ። በእነዚሁ ልዩነቶች ሰዎችን ማረድ የዕለት ተዕለት ድርጊት ከመሆን አልፎ ሕጻናትና ልጆችን ሰብስበው ሰው ሲታረድ እንደ ትርኢት እንዲያዩ ማድረጋቸው ዓለምን ጉድ ሰአሰኝቷል። ከዚህም አልፈው በመሄድ ዕድሜያቸው 9 እና 10 የሚሆናቸው ‘የጅሃዲስቶች’ ልጆች እጆቹ የተጠፈሩበትን ሰው እንዲያርዱ ሲያደርጉም ታይተዋል።

‘ጅሃዲስቶቹ የቆረጡትን ጭንቅላት ደሙ እየተንጠባጠበ፣ በእግራቸው እየለጉና እየተቀባበሉት እንደ ኳስ እየተጫወቱበት ሲዝናኑም ታይተዋል። ሴቶችን በባሎቻቸውና በወንድሞቻቸው ፊት በመድፈር ‘ሌሎቹ ሙስሊሞች’ ያሏቸውን ለማዋረድ ሞክረዋል። የሶርያ አክራሪ አሸባሪዎች ከተሞችን በሮኬትና በላውንቸር በዘፈቀደ በመደብደብ ‘ከእኛ ጋር ያልሆነ ሁሉ የኣሳድ ደጋፊ ነው’ እያሉ ብዙ ሰው ጨርሰዋል።

እዚህ ላይ አንድ ነገር ማውሳት ይገባል። የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት በሶርያ ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች መጠነ ሰፊ እርዳታ ለግሰዋል። “Non-Lethal Aid” እየተባለ ዶላርና ሌሎችንም እርዳታቸዎች ለግሰዋል። የጦር መሳሪያ እርዳታ አላደረግንም ብለውም ይከራከራሉ። በለገሱት ዶላር ወይም ISIS/ISIL ነዳጅ ዘይት ሲሸጥላቸው በሚከፍሉት ዶላር ላይ ‘በዚህ ገንዘብ የጦር መሳሪያ መግዛት አይቻልም’ ብለው ጽፈው ከሆነ እንጃ!

አሜሪካ ለሳዑዲ ዓረቢያና ለኳታር የላከችው ጦር መሳሪያ ISIS/ISIL አልደረሰም ማለትም አይቻልም። ሲጠቀሙበት እየታዩ ነው። ዞሮ-ዞሮ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት የወዳጆቻቸውን የሶርያ አማጽያን አሰቃቂና አሳፋሪ ስራ የነሱን ስም የሚያጠቁር እንዳይሆን ለመከላከል ሲሉ፣ ‘‘ኢስላሚክ ስቴት’’ እና ሌሎች ሶርያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ሰቆቃ ሲፈጽሙ የሚያሳዩ ፊልሞችን ቀርጸው በዩ-ቲዩብ፣ በፊስቡክና በሌሎችም ማሕበረዊ ገጾች ሲያቀርቡ የአሜሪካና የአውሮፓ

ግዛቸው አበበ[email protected]

ወደ ገፅ፡ 14

ነፃአውጪ

አሸባሪ

8

ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

መልዕክቶቻችሁ

ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢብኮ) ሃይ! ባይ የለውም እንዴ?

ይህን አስተያየት መላክ የነበረብኝ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

(ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን) እንደሆነ ይገባኛል። ሆኖም ግን “ኢብኮ” ከሚፈልገው

ሀሳብ ወጣ ያለ አስተያየት ሲያስተናግድ ስላላየሁ እኔም ደብዳቤዬን ብልከው

ውጤት አይኖረውም በሚል ወደ እናንተ ልኬዋለሁ። ወደ እናንተ የላኩበት

ምክንያት ደግሞ ኅብረ-ብዕር መጽሄት ተቃዋሚ/ደጋፊ ሳትል የሁሉንም

አስተያየት በነጻ ስለምታስተናግድ መልእክቴ በእናንተ በኩል እንደሚደርስ

እርግጠኛ ሆኜ ነው።

ወደ ዋናው ጉዳዬ ልግባና የ “አንድነት” እና የ “መኢአድ” ፓርቲ አመራር

አባላትን መከፋፈልና የእርስ-በእርስ ጭቅጭቅ አስመልክቶ “ምርጫ ቦርድ”

ውሳኔ ሊሰጥ አንድ ቀን ሲቀረው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜና

አልተመቸኝም።

የዜናው ይዘት ለህግ በለሙያዎችና ለተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ቃለመጠይቅ

በማድረግ የ “ምርጫ ቦርድ” ውሳኔ ምን ሊሆን ይገባል በሚለው አስተያያት

መሰብሰብ ነው። አስተያየት ሰጪዎች ከፊሎቹ ለእገሌ ወገን መፍረድ አለበት …

አንዳንዶቹ ደግሞ ፓርቲዎቹ ሙሉ-በሙሉ መታገድ አለባቸው የሚል ከምርጫ

ቦርድ ውሳኔ በፊት ቀድመው ይፈርዳሉ።

በመሰረቱ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜ አየሰጠ ገደቡን እያረዘመ

በረጅም ትዕግስት ሲጠብቃቸው እየተስተዋለ ለውሳኔ አንድ ቀን ሲቀረው ያቺን

አንድ ቀን መታገስ አቅቶት ኢቲቪ ተቻኩሎ የውሳኔ ዜና ማቅረቡ በፍጹም

ተቀባይነት የለውም። ለራሱም ቢሆን ተአማኒነቱን ይቀንስበታል። የምርጫ ቦርድ

ውሳኔ ላይም ተጽእኖ መፍጠር ይሆናል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትልቅ

ስህተት ነው የሰራው። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሃይ! ባይ የለውም እንዴ?

ዕፀገነት እርቅይሁን ከላምበረት

ይድረስ ለህብር ብዕር መጽሔት

ህብር ብዕር መጽሔት ቅጽ ቁጥር 04፣ ጥር 2007 መልሀቀ ፖለቲካ

በሚለው አምዳችሁ ስር አንድ የህወሐት ነባር ታጋይ እውነተኛ ታሪክ

የመጀመሪያውን ክፍል “40” በሚል ርዕስ ያቀረባችሁትን ጽሁፍ አንብቤ

የተሰማኝን ስሜት እንደሚከተለው እገልጻለሁ።

በዚህ ጽሁፍ ላይ ታጋዩ ወደ በረሀ ለመውጣት ሲወስን ከእናቱ፣ ከቤተሰቦቹ

የሚያገኘውን ፍቅር ትቶ ሳያሳውቃቸው መሄዱን ሲመርጥ፣ እናት በመሆኔ

በእናትና በልጅ መሐል ያለውን ፍቅር ስለማወቅ እጅግ በጣም ተሰምቶኛል።

ወልደው ያሳደጉትን እናቱን፣ የሚወዳቸውን ወንድሞቹን፣ ቤተሰቦቹንና

ጎረቤቶቹን፣ አፈር ፈጭቶ ያደገባትን ከተማ ሲሰናበት፣ ስንብቱ ደግሞ እሱ

ብቻ የሚያውቀው ሌሎች ግን የማያውቁት፣ በሰላም ግባ ተብሎ ሳይሸኝ

መሆኑ ምን ያህል ህሊናን የሚሞግትና የሚያስተክዝ ፈታኝና የእናትን ልብ

በሀዘን የሚሰነጥቅ እንደሆነ ከማንም በላይ እኔና እኔን መሰል ከሆኑ እናቶች

በላይ የሚገነዘብና የሚረዳ ያለ አይመስለኝም።

ታዲያ በደርግ ዘመን የነበረው ሁኔታ በእናትና በልጆች መሐል የሚኖርን

ህያው ፍቅርን ትቶ ለመለየት የሚያስገድድ መሆኑን ከሚያስገነዝበው

የመጀመሪያው ክፍል ላይ የቀረበው ታሪክ ልቤን የነካና ህሊናዬ ውስጥ

እንዲያድር ያደረገ ነው። ያ ክፉ ዘመን ተመልሶ ላይመጣ ማለፉ ደስ

ይለኛል።

ውድ የህብር ብዕር አዘጋጆች፤ ይህን መሰል ታሪኮች አዲሲቱን ኢትዮጵያ

ለመገንባት በምናደርገው ርብርብ ስንቅ ስለሚሆኑ እያፈላለጋችሁ ለንባብ

እንደምታበቁ ተስፋ በማድረግ እሰናበታለሁ። በዚሁ ቀጥሉበት እላለሁ።

አንዲት እናት - ከአ/አበባ

ኧረ ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ

በመጪው ምርጫ ላይ መብቴን ተጠቅሜ አንድነት ፓርቲን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ ወስጄ ነበር። ሆኖም ግን በአንድነት የአመራር አባላት መሀከል የተፈጠረው መከፋፈል ወሽመጤን ነው የበጠሰው። በጣም አዋርደውናል። ገሀድ የወጣ ይሄንን አይነት መከፋፈል … ያውም ለምርጫው መቶ ቀን ገደማ ሲቀረው በጣም ያሳዝናል። የቅንጅትን መንፈስ ይዛችሁ ለውጤት ታበቁናላችሁ ብለን በጉጉት ስንጠብቅ ይሄን አይነት መፈረካከስ በጣም ያሳዝናል። ተዋርዳችሁ … አዋረዳችሁን! ወያኔዎች በውስጣቸው መከፋፈል እያለ እንኳን ልዩነቶቻቸውን በውስጣቸው አየተፋጩበት ወጣ ሲሉ ግን በአንድ ድምጽ ይናገራሉ። የእኛዎቹ አመራሮች ግን የጓዳ ምስጢራቸውን ሳይቀር ሬድዮ ፋና ስቱዲዮ ውስጥ ይለፈልፉታል።

በአሁኑ ምርጫ ላይ ቢቻል መንግስት ተቀይሮ አልያም እነ አዲስ አበባን እንድነት ይቆጣጠራል የሚል እምነት ነበረኝ። ነገር ግን የአመራሩ መከፋፈል ሀሳቤን አጨልሞታል። ፓርቲው እኮ ፓርቲ የሆነው በአመራሩ ብቻ አይደለም። በፓርቲው ስር የተሰባሰቡ መላ አባላቱን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ መከፋፈላቸው በጣም ያሳዝናል። አሁንም ቢሆን የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት ጊዜው አልረፈደም … ቀረብ ብላችሁ ተወያይታችሁ ችግሮቻችሁን በመፍታት እኛን ደጋፊዎቻችሁን አረጋጉን። ኧረ ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ!

ፍሬሰንበት ለማ ከ አ/አበባ

ክልሎችንም ግምት ውስጥ አስገቡ

ኅብረ-ብዕር መጽሄት ሁሉንም አይነት አስተያየቶች ማስተናገዷ በጣም ጥሩ ነው። ሆኖም ግን ትኩረታችሁ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ይመስላል። ኢትዮጵያ ማለት አዲስ አበባ ብቻ አድርጋችሁ እያሰባችሁ ከሆነ ተሳስታኋል። ምክንያቱም እኔ ነዋሪነቴ አዋሳ ከተማ ነው። መጽሄቷ ግን በምኖርባት ከተማ ላገኝ አልቻልኩም። አዲስ አበባ ለስራ ስመጣ ደግሞ አገኛታለሁ። ስለዚህ ስርጭታችሁን ብታስተካክሉና ክልሎችንም ግምት ውስጥ ብታስገቡ ጥሩ ነው።

እዮብ ኩማሎ ከሀዋሳ

ከዝግጅት ክፍሉ

አቶ እዮብ ለአስተያየትዎ እናመሰግናለን። ሆኖም ግን እንደሚታወቀው የዛሬው ገና 5ተኛ እትማችን ነው። ከመጀመሪያው እትማችን በመነሳት በየጊዜው ልምድና ትምህርት እየወሰድን ነው። ስርጭቱንም በተመለከተ ከጊዜ ወደጊዜ የተሻለ አሰራር በመፍጠር መጽሄቷ ለክልሎችም እንድትደርስ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን። ዛሬ የሰጡንን አስተያየት ደግሞ ግምት ውስጥ በማስገባት በክልል ስርጭት ላይ የበለጠ ጠንክረን ለመስራት እንሞክራለን።

+251 942 199191 [email protected] Hibre Bier23456, አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

10 11

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ዜናዜና

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተለያዩ የክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን አስታወቀ።

ፓርቲው በተለይ በደብረማርቆስ ከተማ ባደረገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ተነስቶ ተክለሐይማኖት አደባባይ ድረስ በመጓዝ ሲሆን በዚህም ጊዜ ልዩ ልዩ መፈክሮች ተደምጠዋል።

በደብረማርቆስ ከተማ አንድነት ፓርቲ ያደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የተሳካ እንዲሆን ፓርቲው ቀደም ብሎ በከተማው በሚገኙ የንግድ ተቋማት፣ የገበያ ማዕከላት፣ በተለያዩ ካፌዎችና ሬስቶራንቶች ቅስቀሳ ያካሄደ ሲሆን በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎችም በመኪና በመዘዋወር ደጋፊዎች በተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንዲገኙ ጥሪ አድርጓል። g

ኢፍዴኃግ መ.ኢ.አ.ድ.

የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲ ሀይሎች ግንባር (ኢፍዴኃግ) አባል ድርጅቶች ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ የግንባሩ አባላት ህገ-ወጥ የምርጫ ምልክት መውሰዳቸውን አወገዘ።

በግንባሩ ስር የሚገኙት ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ በተገኘ ሰርተፊኬት ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን በግለሰብ ደረጃ ከግንባሩ ላፈነገጡት አባላት የምርጫ ምልክት መሰጠቱ አግባብ አለመሆኑን ለምርጫ ቦርድና ለሚመለከተው አካል ግንባሩ ቢያሳውቅም መፍትሄ አለመገኘቱ በጉባዔው ላይ ተጠቅሷል።

ጉባዔው በማስከተልም አንዳንዶቹ በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት የተባረሩ ቢሆንም ከወጡ በኋላ ለሚሰሩት ህገ-ወጥ ስራ አስቸኳይ መፍትሄ የሚሰጥ በመጥፋቱ ችግሩ ሊባባስ መቻሉን ገልጿል። g

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥር 15 ቀን 2007 ዓም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፓርቲውን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ አወገዘ።

ፓርቲው በዚህ መግለጫው ላይ በቴሌቪዥን የተላለፈው ዘጋቢ ፊልም የፓርቲውን አመራር አባላት ሳያነጋግሩና በተለያዩ ጊዜ የተሰጡ ቃለመጠይቆችን ቆራርጦ በማቀነባበር የተሰራ በመሆኑ አግባብ አይደለም ብሏል።

በማያያዝም ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎችን ምንም አይነት የውስጥ ችግር ሳይኖርበት ችግር አለ በሚል ቦርዱ ራሱ በፈጠረው መንገድ ሁለት የፓርቲውን አባላትና አንዳንድ ጥቅመኞችን በመያዝ ጫና በመፍጠር ፓርቲውን ለማፍረስ በሂደት ላይ ነው ብሏል። g

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መስራችና የአመራር አባል ከነበሩት አንዱ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ለአንድ የአገር ውስጥ መጽሄት ሰሞኑን ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል።

በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ ለ ዶ/ር ያዕቆብ ከቀረበላቸው ጥያቄዎች መሀከል “አንድነት ከመኢአድ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰማያዊ ፓርቲ ጋርም የመዋሃድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነበር። የወደፊት እጣ ፈንታው ብቻውን ከመቀጠል ሁኔታ ጋር እንዴት ያዩታል?” የሚል ነበር።

ለዚህ ጥያቄ ዶ/ር ያዕቆብ ምላሽ ሲሰጡ “እነኚህ ፓርቲዎች ተሰባስበው እንዲያውም ተዋህደው አንድ አይነት ህብረት እስካልተፈጠረ ድረስ ምርጫ ቢገቡም ምንም አይነት ውጤት አያመጡም” ብለዋል። ዶ/ሩ በማያያዝም የአሁኑ ምርጫ ጥቂት ጊዜያት እንደቀረው አውስተው በዚህ ወቅት ምንም የሚታይ ትብብርም ሆነ ውህደት ባለመኖሩ በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎች ውህደት ፈጥረው ኢህአዴግን በሰላማዊ መንገድ ይፋለማሉ ማለት በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

መጽሄቱ እርሳቸው የነበሩበት የቅንጅትን ያለፉ ስድስት አመት ጉዞ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ያዕቆብ ምላሽ ሲሰጡ “ነጻ ምርጫ ቢኖር ኖሮ ቅንጅት እንደገና አሁንም ነፍስ ዘርቶ ይወጣ ነበር” ብለዋል። g

ዶ/ር ያዕቆብ ኢፍዴኃግ ኅብረ-ብዕር

ህብረ-ብዕር መጽሄታችን በየአስራ አምስት ቀኑ

በያላችሁበት ቦታ በአድራሻችሁ እንድትደርሳችሁ የምትፈልጉ

አንባቢያን

በስልክ ቁጥር:(0942) 199191(0911) 688973

በኢሜይል አድራሻ[email protected]

ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ከዝግጅት ክፍሉ

የምንወግነው ለሀቅ ነው!

12 13

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ኅብረ-እንግዳኅብረ-እንግዳ

ኅብረ-ብዕር፡ በረከት (ፍልፍሉ) ልጅ እያለህ ወይም ተማሪ እያለህ ምን መሆን ነበር የምትመኘው?

በረከት፡ ት/ቤት እያለን አብረውኝ የሚማሩት ተማሪዎች “ወደፊት ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ሲባሉ አብዛኛው ተማሪ ዶክተር የሚል ምላሽ ነበር የሚሰጠው፡፡ እኔ ደግሞ ይሄ ሁሉ የወደፊት ዶክተር ስራ እንዳያጣ በሚል ምኞቴ ታማሚ መሆን ነበር፡፡

ት/ቤት ውስጥ አስተማሪ ጥያቄ ሲጠይቅ መልስ ለመስጠት ትሽቀዳደም ነበር ይባላል እውት ነው?

እውነት ነው፡፡ ግን እንደዚያም ቸኩዬ ብዙ ጊዜ የጥያቄውን መልስ አላገኘውም፡፡ በብዛት የተሳሳተ መልስ ነው የምሰጠው፡፡

በዚያን ጊዜ ተሳስተህ ከመለስካቸውና ከምታስታውሰው አንዱን ልትነግረኝ ትችላለህ?አንድ ጊዜ መምህራችን ከዱር እንሰሳት አምስቱን ጥቀሱ ይሉናል፡፡ እንደተለመደው ተሽቀዳድሜ እጄን አወጣና ሦስት አንበሳና ሁለት ጅብ ብዬ የመለስኩት ትዝ ይለኛል፡፡

በትምህርትህ ምን ያህል ጐበዝ ነበርክ?ሁልጊዜ ከክፍል አንደኛ ነበር የምወጣው

ታጠና ነበር ማለት ነው?አንደኛ ነው የምወጣው ያልኩህ እኮ ትምህርት ሲያልቅ ከተማሪዎች ሁሉ ቀድሜ ነው ከክፍሌ የምወጣው ማለቴ ነው፡፡

ቂ-ቂ-ቂ (ረጅም ሳቅ) ቀልዶችን ብዙ ግዜ ከየት ነው የምታገኘው?በቁፋሮ ቂ-ቂ-ቂ … የእኔ ቀልድ የሚቀርበው እዛው መድረክ ላይ ከማየው በምፈጥረው ነገር ነው፡፡ መድረክ ላይ ብቻ ሳይሆን ከጓደኞቼ ጋር ስጫወትም ከምናወራው ነገር በመነሳት ነው ቀልድ የምፈጥረው፡፡

ለዛሬ ኮሜዲያን መሆንህ የሴት አያትህ አስተዋፅኦ አለበት ይባላል፡፡ እውነት ነው?

በጣም እውነት ነው፡፡ አያቴ ቀልደኛ ነበረች፡፡

ከአያትህ ቀልዶች የምታስታውሰውን ብትነግረኝ?

የእሷ ተወርቶ አያልቅም፡፡ ከሁሉም የማይረሳኝ ግን ገንዘቧን ስታስቀምጥ በትንሽ ቦርሳ አድርጋ ጡቶቿ ውስጥ ነው የምትደብቀው፡፡ ታዲያ እኔ ስትተኛ እጠብቅና ቦርሳውን ከወሸቀችበት ቀስ ብዬ አውጥቼ ያለውን ብር ከወሰድኩ በኋላ ልክ ብር አስመስዬ ጋዜጣ ቆርጬ ቦርሳው ውስጡ አስቀምጣለሁ፡፡ አይኗ በደንብ ስለማያይ ሲነጋ ቡና ልትገዛ ሱቅ ትሄድና ለባለ ሱቁ የ3 ብር ቡና ስጠኝ ብላ ቦርሣዋን ከፍታ

ስትከፍል ባለሱቁ “ምነው እማማ ዛሬ ደግሞ በወረቀት ነው እንዴ የሚገዙት?” ይላታል፡፡ በዚህ ግዜ “ጉድ የሰራኝ እሱ ነው” ብላ ተናዳ ወደቤት ትመለሳለች። ከዚህ ጊዜ በኋላ ቦርሳዋን ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም … ቡሃቃ ሳይቀር ፈትሻለሁ፡፡ ለብዙ ጊዜ አላገኘሁትም፡፡ አንድ ቀን ተኝቼ በጠዋቱ ወደኔ ትመጣና እንጀራ እናቴ መሞቷን ትነግረኛለች፡፡ አስከትላም አንዴ ቀና በል ስትለኝ “ምን ፈልገሽ ነው?” አልኳት “ቀና በል ገንዘብ ላውጣ” ብላ ከራሴው ትራስ ስር ቦርሣዋን ያወጣችው ትዝ ይለኛል፡፡

ብዙ ጊዜ ኮሜዲያን ለቅሶ ለመድረስ ሲሄዱ ሀዘናቸውን ሌላው ሰው አይረዳቸውም ይባላል። አንተስ በዚህ በኩል የገጠመህ ነገር አለ?

አዎ፡፡ አንድ ጊዜ ምን ሆነ መሰለህ? አንድ በጣም የምወደው አርቲስት ይሞትና መሸትሸት ሲል ለቅሶ ለመድረስ ሄድኩኝ። ሟቹን ከልብ እወደው ስለነበር ድምፅ አውጥቼ ተንሰቅስቄ ነው ያለቀስኩት፡፡ ለቅሶ ቤት ውስጥ የነበረው ሰው በሙሉ ሴቶች አፋቸውን በነጠላ፣ ወንዶቹ በኮሌታቸው አፍነው በሳቅ ይንተከተካሉ፡፡ ሁሉም ሰው የኔ ለቅሶ የምር አልመሰለውም፡፡ ከሰው መሃል አንዲት ልጅ ብቻ ናት የማለቅሰው የእውነት መሆኑ ገብቷት ያፅናናችኝ፡፡ ለቅሶዬን ጨርሼ እምባዬን ጠራርጌ እራት ሳነሳ የሟቹ ሚስት መጥታ “ውጣልኝ ሃዘኔን አታበላሽብኝ” ብላ ጮኸችብኝ። ምን አደረግኩ ብዬ ግራ ተጋባሁ። ሴትየዋ ግን አሁንም “ከቤቴ ውጣልኝ” እያለች ያነሳሁትን ምግብ ልትቀማኝ ስትል ወጡ እኔና እሷ ልብስ ላይ እንዳለ ይፈሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለቅሶ በስልክ ነው የምደርሰው፡፡

አሜሪካ ሄደህ ለሁለት ዓመት ያህል ቆይተህ ነው የተመለስከው። ቆይታህ እንዴት ነበር?

ቤት ውስጥ …ቂ-ቂ-ቂ-ቂ

ቂ-ቂ-ቂ-ቂ(ረጅም ሳቅ) ምን ምን ስራዎችን ሰርተህ ነው የተመለስከው?

በዚሁ በኮሜዲ ስራ ወደ 20 የሚጠጉ ስቴቶች (የአሜሪካ ግዛቶች) ተጉዣለሁ። በእነዚህ

ቦታዎች ላይ የመድረክ ስራ አቅርቤያለሁ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ እየተከፈለኝ በየቤቱ እየተጠራሁ አስቅ ነበር፡፡

በረከት ከሚለው ስምህ ይልቅ አንተ የምትታወቀው ፍልፍሉ በሚለው መጠሪያ ነው፡፡ ለመሆኑ ፍልፍሉ የተባልከው ለምንድነው?

ድሮ በቀበሌ ኪነት ውስጥ ሌሎች ድራማ ሲሰሩ እኔን አያሰሩኝም ነበር፡፡ ይሄ ጅል ነው አይችልም ይሉኝ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ሌሎች የሰሩትን መገምገም ብቻ ነበር ስራዬ፡፡ በዚህ ጊዜ አሪፍ የተባለውን ድራማ ወይም ጭውውት አቃቂር አወጣለታለሁ፡፡ አንድ ጊዜ ሙሉ የተባለች ልጅ የተጨበጨበለትና እንከን የለውም የተባለ ድራማ ሰርታ መጣች። ታዲያ እኔ ድራማው ያለበትን ጉድለት ተናገርኩኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጅቷ ይሄ እንዴት ነው ፈልፍሎ ስህተት የሚያወጣው ደንበኛ ፍልፍሉ ነው አለች፡፡ በቃ ከዚያ ጊዜ በኋላ ፍልፍሉ ተባልኩኝ፡፡

ፍልፍሉ የሚለው የቅፅል ስምህ በመለመዱ ምክንያት የገጠመህ ችግር የለም?

አንዳንድ ቦታ የኮሜዲ ስራ ሰርቼ ቼኩን ፍልፍሉ በቀለ ብለው ያዘጋጁ ገጥመውኛል፡፡ ግን ፍልፍሉ በሚል ስም መታወቅያ ስለሌለኝ ገንዘቡን ለማውጣት ስለማልችል ቼኩን በረከት በሚለው ስም እንዲቀየር ያደረግኩባቸው ጊዜያት አሉ፡፡

ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ አንድ መቶ ሃምሳ የሚሆኑ አርቲስቶችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ለጉብኝት ወደ ትግራይ ተጉዘው ነበር፡፡ አንተም በዚህ ቡድን ውስጥ ነበርክ፡፡ ታዲያ በወቅቱ ከአምቡላንስ ጋር የተገናኘ ሁለት አጋጣሚዎች ነበሩህ ሲባል ሰምቻለሁ ጉዳዩ ምን ነበር?

አንደኛው ደጀና የሚባል አካባቢ በጉብኝት ላይ እያለን እኔንና አርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬን ተርብ ይነክሰናል፡፡ እኔን የነከሰኝ እጄ ላይ ነው። በጉብኝት ቦታዎች ሁሉ አምቡላንስ ይከተለን ስለነበር አንቡላንስ ውስጥ ገብቼ የመጀመሪያ ዕርዳታ የወሰድኩበት ነው፡፡ ሁለተኛው አጋጣሚ ደግሞ ከሀገረ ሰላም ወደ መቀሌ እየመጣን በነበረበት ጊዜ ነው፡፡

ምን ገጠመህ፤ ታመምክ ወይስ እንደገና ተርብ ነከሰህ?

በፍፁም፡፡ ምን መሰለህ የሆነው እኔ ሰለሞን አስመላሽ፣ ጆኒ ካናዳ፣ ነዋይ ደበበና ቤን ሆነን

የሐገረሰላምን ጉብኝት ጨርሰን በላንድክሩዘር ወደ መቀሌ እየሄድን ነው፡፡ በዛ ላይ ጨልሟል፡፡ መቀሌ ለመግባት በግምት 60 ኪ.ሜ ያህል ሲቀረን የኋላ ጐማ ፈነዳና ብጥስጥሱ ወጣ፡፡ ጐማ እየቀየርን እያለን አንድ አምቡላንስ አላርም እያበራ ሲመጣ ከሩቁ አየሁት። ወደ መንገዱ ገባ ብዬ ምልክት ሰጥቼ አቆምኩት። አምቡላንሱ ውስጥ ያሉት የህክምና ባለሙያዎች ሰው የተጐዳ መስሎአቸው ወዲያውኑ አቆሙና “ምነው ደህና ናችሁ?” ሲሉን እኔም ፈጠን ብዬ “አምቡላንስ የተጐዳ ሰው ብቻ ነው እንዴ የሚረዳው? በሉ ይሄን የተጐዳ ጐማ ውሰዱና እርዳታ ስጡት” አልኳቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ በጣም ነበር የሳቁት፡፡

መቼም ባለትዳር መሆንህንና ሁለት ልጆች እንዳሉህ ሁሉም ያውቃል፡፡ የልጆችህ ስም ለየት ያለ ነው ይባላል ለመሆኑ ስማቸው ማን ማን ነው?

ትልቁ ወንድ ልጄ “የ” ይባላል ዕድሜው 4 ዓመት ነው ትንሿ ሴት ልጄ ደግሞ “አብ የሳላት” ስትሆን ዕድሜዋ ገና 6 ወሯ ነው፡፡

“አብ የሰላት” የሚለው አብ ወይም እግዚአብሔር የሰራት ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው ፡፡ የመጀመሪያው ልጅህ ስም “የ” የሚለው ግን ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ ምን ማለት ነው?

እንደምታውቀው የኔ ስም በረከት ነው፡፡ ከፊት የልጄ ስም ሲጨመር “የበረከት” የሚል ይሆናል፡፡ ይሄ ማለት የኔ ልጅ ማለት ነው፡፡ አልካድኩትም፡፡ በዛ በላይ ደግሞ ወደፊት ሲያድግ ስሙን ሲፅፍ እስክርቢቶና ወረቀት አይጨርስም፤ በቃ ይሄ ነው፡፡

የኮሜዲ ስራ ከሌለብህ ያለህን ትርፍ ግዜ የት ነው የምታሳልፈው?

ብዙ ግዜ ከቤቴ አልወጣም፡፡ ልጆቼን ሳጫውት ነው የምውለው። እንደምታውቀው የድሮ ልጅ የእናቱን ጡት ነው የሚጠባው፡፡ የዛሬ ልጅ ግን የአባቱን ኪስ ነው የሚጠባው። አብሬያቸው ስውል ወጪው ራስ ያማል፡፡

እቤት ውስጥ ከልጆችህ ጋር የምትውለው እያስጠናሃቸው ነው ወይስ እያጫወትካቸው?

ወይ ማስጠናት እውቀቱ ከየት ይመጣል? ቤት በገባሁ ቁጥር ትልቁን ልጄን “A” የምትለዋን ፊደል አስጠናዋለሁ፡፡ ከዚያ መቀጠል ስለማልችል በነጋታውም “A” እለዋለሁ፡፡ በቃ በየዕለቱ “A” እንዳልኩት ነው፡፡ በኋላ ላይ

ልጁም እቤት ስገባ አባዬ ቀረና ሚስተር “A” መጡ ማለት ጀመረ፡፡

ተጨንቀህ ወይም ተቸግረህ የሰዎችን እገዛ ወይም እርዳታ በምትፈልግበት ጊዜ በኮሜዲያንነትህ የገጠመህ ነገር የለም?

መቼም ሳትሰማ አትቀርም፤ አንድ ጊዜ ድብደባ ተፈፅሞብኝ ነበር፡፡ ታዲያ በዚያን ግዜ ግንባሬን ክፋኛ ተፈንክቼ ደም በጣም ይፈሰኝ ነበር፡፡ ሆስፒታል ውስጥ በስትሬቸር እየተገፋሁ ወደ ራጅ ክፍል ስገባ ራጅ ክፍል ያለው ሐኪም “ከአንገትህ ቀና በል” ሲለኝ ለራጅ መስሎኝ ቀና እላለሁ፤ እንደዛ ደም እየፈሰሰኝና ስቃይ ላይ እያለሁ ሞባይሉን ለአንዱ ሰጥቶ እቅፍ አድርጐኝ ፎቶ እንነሳ ያለኝን አልረሳውም፡፡

መድረክ ላይስ የገጠመህ ተመሳሳይ ነገር የለም?

አንድ ጊዜ አዳማ ከተማ መድረክ ላይ እየሰራሁ ከተመልካች መሃል አንድ ልጅ እየሮጠች ወደ መድረኩ ላይ ትወጣና እቅፍ አድርጋኝ ጡቴን በጣም ትነክሰኛለች፡፡ ንክሻዋ ኃይለኛ ስለነበር ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮህ ሰው ቀልድ እያቀረብኩ መስሎት ይስቃል፡፡ እኔ ንክሻው አሞኛል፡፡ ተመልካቹ በጩኸቴ እያጨበጨበ ይስቃል፡፡ ልክ ስራዬን እንደጨረስኩ እዛው አዳማ ሆስፒታል ሄድኩኝና ዶክተሩ ጋ ቀረብኩ፡፡ “ምንህን ነው የሚያምህ?” ሲለኝ ግራ ጡቴን እንደሆነ ነገርኩት። ቀና ብሎ ሲያየኝ እኔ ነኝ፡፡ የማሾፍ መስሎት “እስከዛ ድረስ በቀኝ ጡትህ አጥባ” ያለኝ ትዝ ይለኛል፡፡

ባለፈው ታህሳስ ወር የኪነ-ጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በትግራይ ያደረጉት ጉብኝት ላይ መሳተፍህን ምክንያት በማድረግ በአንዳንድ ድረ-ገፆች ስድብ አዘል አስተያየት እየተሰጠብህ ነው። ያንተ ምላሽ ምን ነበር?

እነዚህ የሚሳደቡ የዲያስፖራ ጋዜጠኞች አፍ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ትግራይ እኮ ኢትዮጵያ ናት፡፡ የራሳችን አገር ናት፤ እኛ ትግራይ እያለን እኮ እነሱ ኤርትራ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከኛ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሻዕቢያ ጋር ሲሞዳሞዱ አልነበር እንዴ? እና በነሱ ብሶ የገዛ አገራችሁን ለምን ጐበኛችሁ ቢሉኝ “አይኔን አታስቁት ጥርሴስ ልማዱ ነው” ብዬ ነው የማልፋቸው፡፡

ስለ ቃለ-ምልልሱ በጣም እናመሰግናለን። እኔም በጣም አመሰግናለሁ።

በአያቱ የወጣው ኮሜዲያን“አይኔን አታስቁት ጥርሴስ ልማዱ ነው”ኮሜዲያን በረከት በቀለ (ፍልፍሉ)

የተወለደው አዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ ያሳደጉት የአባቱ እናት (አያቱ) ናቸው፡፡ እኚህ ሴት አያቱ ቀልደኛ ቢጤ ስለሆኑ እሱም የእሳቸውን እየሰማ ደንበኛ ጨዋታ አዋቂ ሆነ፡፡ በ1993 ዓ.ም በሚማርበት ምስራቅ ድል ት/ቤት ውስጥ አስቂኝ ቀልዶችን ማቅረብ ጀመረና ዕለት ተዕለት ይህ ቀልደኛነቱን እያዳበረ አሁን በአገራችን ታዋቂ ኮሜዲያን ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህ የዛሬ እንግዳችን ብዙዎቻችን “ፍልፍሉ” በሚል የቅፅል ስም የምናውቀው ኮሜዲያን በረከት በቀለ ነው፡፡ የህብረ-ብዕር ዘጋቢ አነጋግሮታል፡፡

14

ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ኅብረ-እንግዳ

ፖለቲከኞች ‘ፊልሞቹ ፈጠራ ናቸው’፣ ‘የአሳድ ፕሮፓጋነዳ ነው’ እያሉ የሽብሩን ስራ ለራሳቸው ስም ሲሉ ሲሸፋፍኑና ሲከራከሩ ነበር።

በሌላ በኩል በኦባማ ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ቪዲዮዎችን እየተከታተለ ማሕበራዊ ድር-ገጾቹ በአስቸኳይ እንዲያስወግዱአቸው የሚያስገድድ አሰራር በሰፈነበት በዚህ ዘመን የሽብር ስራዎችን የሚያሳዩን አሰቃቂ ቪዲዮዎች ያለ ከልካይ መለቀቃቸው ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቶ እዚህ ላይ ደርሰናል። ISIS/ISIL ከአሜሪካ መንግስት ጋር በይፋ ተጣልቶ የአሜሪካዊ ጋዜጠኞች ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የሚያሳዩት ቪዲዮዎች ሲለቀቁም መጀመሪያ ላይ ‘ፈጠራ ናቸው’፣ ‘ይመረመራሉ’ ወዘተ ተብሎላቸው ነበር። አሁን ግን ለመሸፋፈንና ለክርክር በማይመች መንገድ የቪዲዮዎቹ እውነተኛነት ተረጋግጧል። ይህ ደግሞ በአሜሪካና በአውሮፓ መንግስታት አይዞህ ባይነትና እርዳታ የሚንቀሳቀሱት ቡድኖች ሶርያ ውስጥ የሰሩትን ሰቆቃ ለተመልካች ያቀረቡባቸው ቪዲዮዎች ሃቀኛ መሆናቸውን የሚያረገግጥ ነው።

አውሮፓውያኑና አሜሪካውያኑ መንግስታት ይህን ሁሉ ከምንም ባለመቁጠር የበሽር አል አሳድን አምባገነንነት ብቻ አጉልተው በመናገር፣ በዚያ ምድር የሚፈጸመው ሁሉ “ጸረ አሳድ” ውጊያ (ፍትሐዊ ጦርነት) ተደርጎ ብቻ ይነገር ነበረ። ሚዲያዎቻቸውም ይህንኑ በመከተል የሽብሩን ስራ ሁሉ ሸፋፍነው ‘የሶርያ አማጽያን’ የአሳድን ጦር ወይም የአሳድን ደጋፊዎች ተዋጉ ሲሉን ከርመዋል።

ድሮ አልቃይዳና (ሙጂሃዲንና) ቢን ላደን ‘ጀግና ተዋጊ’ ሲባሉ ከርመው በኋላ ላይ ‘አሸባሪ’ የተባሉት በአሜሪካ ላይ ፊታቸውን ሲያዞሩ ነበር፤ አሁንም ‘‘ኢስላሚክ ስቴት’’ (ISIS) ሶርያ ውስጥ ያሻውን ነገር ሲፈጽም ሲመሰገን ከርሞ አሸባሪ ለመባል የበቃው አባላቱን ከሶርያ መልሶ ወደ አሜሪካና አውሮፓ ሊያስገባ ሲል መሆኑን ልብ ማለት ጥሩ ነው። ሚዲያዎች ይህን ቡድን በሰፊው ማብጠጠል የጀመሩት ደግሞ በአሜሪካ ጋዜጠኞች ላይ እንስሳዊ ሰቆቃውን ከፈጸመ በኋላ ነው። ከጆርጅ ቡሽ መማር ያልቻለው ኦባማ ከራሱ ስህተት ትምህርት ለመውሰድ ተገድዷል። የአሜሪካ የስለላ ድርጅት የ ‘‘ኢስላሚክ ስቴት’’ (IS) አባላት አሜሪካና በአንዳንድ የአውሮፓ አገራት ሳይገቡ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ ማሰማት ጀምረዋል። ታሪክ ራሱን በከፋ መልኩ መድገም ጀምሯል፤ የ9/11 ታሪክ ራሱን ይደግም ይሆን?

ሁለት የአሜሪካ ጋዜጠኞችን በማረድ የገደለው የ ISIS/ISIL አባል እንግሊዛዊ፣ ተባባሪዎቹ ካናዳውያን መሆናቸውን አይተናል። እንግሊዛዊውን ሰው በማረድ የገደለው የ ISIS/ISIL አባል ደግሞ አሜሪካዊ ነው። እንግሊዝ እስከ 500 የሚደርሱ ዜጎቿ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጉዘው በመዋጋት ላይ መሆናቸውን ብታምንም፤ ካሊድ ሞሐመድ የተባሉት የእንግሊዝ ፓርላማ አባል ላለፉት ሶስት ዓመታት ወደ ‘ውጊያ’ የሄዱት እንግሊዛውያን ከ1500 በላይ መሆናቸውንና የሄዱት ደግሞ ወደ ሶርያ መሆኑን በመግለጽ የመንግስታቸውን መሸፋፈን ተችተዋል።

የአሜሪካው ሴናተር ጆን መኬይን አምና (2013) ወደ ሶርያ በስውር ገብቶ እንደነበር ሲ.ኤን.ኤንን የመሳሰሉ ሚዲያዎች ነግረውናል። መኬይን ራሱ በኩራት ስለ ድብቅ ጉብኝቱ መግለጫ ሰጥቶ እንደነበርም ይታወሳል። ጆን መኬይን ያኔ ሶርያ ውስጥ

ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ በሚዲያዎች ላይ ከተለቀቁት ፎቶዎች ውስጥ አንዱ መኬይን ከአምስት የኢስላሚክ ስቴት ተዋጊዎች ጋር የሚታይበት ነበረ። አሁን አሜሪካ የኢስላሚክ ስቴት ጠላት መሆኗን አውጃ የአየር ድብደባ ስትጀምር ድርጅቱ የመኬይንና የአባላቱን የያዘውን ፎቶ በየድረ-ገጹ በመልቀቅ እየተሳለቀ ነው።

አስገራሚውና አሳዛኙ ነገር የዚህ ቡድን ማንነትና ምንነት በግልጽ ስላልተነገረ በዚህ ድርጅት (ኢስላሚክ ስቴት) አማካኝነት የተፈጸሙት ሰቆቃዎች የእስልምናንና የሙስሊሞችን ስም ለማጥፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆናቸው ነው። ኢስላሚክ ስቴት እንዴት ወደ ሕልውና መጣ?

አልቃይዳ በአሜሪካ የተቋቋመና የአሜሪካ መሳሪያ ለመሆን ጥቅም ላይ የዋለ ቡድን እንደሆነው ሁሉ ብቅ ብቅ በማለት ላይ ያሉ አንዳንድ መረጃዎች የኢስላሚክ ስቴት ተመሳሳይ ምንጭ እንዳለው እያሳዩ ነው። የኢስላሚክ ስቴት መሪ የሆነው “አቡ በከር አል-ባግዳዲ” በእስራኤል የስለላ ድርጅት በሞሳድ የተመለመለና ለአንድ ዓመት በሞሳድ የሰለጠነ ሰው መሆኑን ቀደም ብሎ በስኖውደን አማካኝነት ይፋ የተደረጉት መረጃዎች አጋልጠዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቡ በከር አል-ባግዳዲ የሚመራው ‘ኢስላሚክ ስቴት’ በአሜሪካ፣ በእንግሊዝና በሳዑዲ ዓረቢያ ስፖንሰርነት የተቋቋመና የተደራጀ መሆኑን ካናዳዊው የሰብዓዊ መብቶች ጠበቃ ኤድዋርድ ኮሬን ከ “ፕረስ ቲቪ” (Press TV) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልለስ ላይ ገልጸዋል። ካናዳ ኦንታሪዮ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት “ኤድዋርድ ኮሬን” አሜሪካና እንግሊዝ ለኢስላሚክ ስቴት ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የጦር መሳሪያም እያቀበሉት ኖረዋል ይላሉ። ኮሬን ጨምረው ሲናገሩም ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኩዌት እና ኳታር የዚህ ድርጅት ዋና ደጋፊ መሆናቸውን ጨምረው በማጋለጥ እነዚህ አገራት (በተለይ አሜሪካ፣ እንግሊዝና አስራኤል) ይህን ድርጅት ያቋቋሙትና ያደራጁት ከመላው ዓለም አክራሪዎችን አሰባስበው የአሳድን መንግስት ለመገልበጥ በወጠኑት ስትራቴጂ መሆኑን በመናገር ከየአገራቱ አክራሪዎች ወደ ሶርያ ሲጎርፉ የታየው ለዚህ ስትራቴጂ ስኬት ነው ብለዋል።

‘‘ኢስላሚክ ስቴት’’ (IS) አደገኛ ድርጅት ከመሆኑም በላይ በጣም የናጠጠ ሃብታም ድርጅትም ነው። ያለው ሃብት ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህን ሃብት ያካበተው ነዳጅ ዘይት በመሸጥ ነው። ይህ ድርጅት የሶርያንና የኢራቅ-ኩርድ ግዛትን የነዳጅ ምንጮች ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት ነዳጅ ዘይት በሰፊው ይሸጥ እንደነበር የታወቀ ነው። ከዚህ ድርጅት የተሸጠን ነዳጅ ከተሸከሙ መርከቦች አንዷ ወደ አሜሪካ ግዛት ተጠግታ ከኢራቅ መንግስት ጋር ውዝግብ መፈጠሩና አንድ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ከኢራቅ መንግስት የቀረበን ክስ መሰረት አድርጎ መርከቧ ነዳጁን እንዳታራግፍ መወሰኑ ይታወሳል። ይህ አጋጣሚ የአሜሪካ ካምፓኒዎች ‘ኢስላሚክ ስቴት’ ከሶርያና ከኢራቅ የዘረፈውን ነዳጅ ዘይት እየገዙ ድርጅቱን ከበርቴ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ የሚያረጋግጥ ነው።

የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ሽብርን እየተዋጋን ነው በማለት እያደናቆሩን ወደ 10 ዓመታት ቆጥረን እዚህ ላይ ደርስናል። ከዚያስ?!

ሰላም ለዓለማችን!!

ከገፅ፡ 7

ጥራት ፍጥነት

ውበትThink Design

?

ድርጅትዎተወዳዳሪ ወይስ ተመራጭ

እንዲሆን ይሻሉ

ውድድሩን ለእርሶ ትተናል

እንዲሆኑ ግን እኛ እንሰራለን

+ 2 5 1 9 1 2 7 8 0 1 1 8

........................................................................................................................................................................................................................................................................

........................................................................................ ........................................................................................ ........................................................................................

. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ ደ ው ለው እ ና ው ራ

ጥራት ፍጥነት

ውበት

LogoBusiness Card

Flier, Brochure & PosterBusiness Catalog

MagazineID card

Letter Head

16 17

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ኅብረ-ኪንኅብረ-ኪን

አሁን ስድስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ነን፡፡ ዓመተምህረቱን ለጊዜው አልመዘገብነውም፡፡

ነገር ግን እነ ጀማነሽ ሰለሞን ተማሪ፤ እነ ደበበ ሰይፉ ደግሞ አስተማሪ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ ክፍለ ጊዜው ግን የአቶ ደበበ አልነበረም፡፡ የአንድ ፈረንጅ መምህር እንጂ…

በወቅቱ ክፍለጊዜውን የተካፈሉት ተማሪዎች መምህሩ ሰዓታቸውን አክብረው መድረሳቸውን ለመገንዘብ ጊዜ አልፈጀባቸውም … እንደገቡ ማስተማር መጀመራቸውን ለማወቅ ግን በጣም ዘግይተዋል፡፡

ወደው አይደለም፡፡ ካሁን አሁን አስተማሩን በማለት አቆብቁበው ሲጠብቋቸው ዕቃ እንደጠፋበት ሰው ወለሉ ላይ አቀርቅረው ጥቂት ከተንጐራደዱ በኋላ “እስቲ በአማርኛ ቋንቋ ቀጭን ሴትን የሚያወድስ ወይም የሚያቆላምጥ አንድ ቃል ፈልጉልኝ” አሉ።

በዚያን ሰዓት ሁለት ነገር ተፈጠረ … ተጠራጣሪዎቹ ተማሪዎች ጥያቄውን ከሰሙ በኋላ በጥርጣሬ ኮስተር አሉ፡፡ በእነሱ ቤት ይህ ፈረንጅ በአንዲት ሀበሻ ፍቅር የሚነደፍበት ምክንያት ካገኘ በኋላ ውበትዋን የሚገልፅበት አማርኛ አጥቶ ተቸግሯል፡፡

የዋሆቹ ተማሪዎች ደግሞ በየዋህነት ፈገግ አሉ፡፡ አንዳንድ መምህራን ማስተማር ከመጀመራቸው በፊት ክፍሉን ለማነቃቃት ለተማሪዎቻቸው ከሚያቀርቧቸው አዝናኝ ዓይነት ጥያቄዎች አንዱ እንደተወረወረላቸው አስበው ነው፡፡

እናም የጥያቄውን አዝናኝነት በሚመጥን ፈገግታ ፈታቸው እያበራ ቀጭን ሴትን አሳምሮ የሚገልጥ የተለየ ቃል ፍለጋ በተለያየ ተመስጦ ተበታተኑ፡፡

ጥቂት ደቂቃዎች በዚህ ሁኔታ አለፉ፡፡ አሁን ከተበተኑበት ተመስጦ ባዶ ሃሳባቸውን ተመልሰዋል፡፡ ከዚያም በ “እንዴት ይጠፋናል?” ስሜት እርስ በርሳቸው ተያይተዋል፡፡

ያችን ቃል ወደተራቡት የመምህሩ ዓይኖች ግን ቀና ለማለት አልደፈሩም፡፡ ይልቁንስ ባዶው አየር ላይ አፍጥጠው ወጥመድ ውስጥ የገባች ድንቢጥ መሰሉ፡፡

እዚያ ወጥመድ ውስጥ ከገቡት ድንቢጦች መሃል አንድ እሳት የላሰ ድንቢጥ ብቻ ከእሳቱ ተሰማ … አንደበት የሰማውን የፍቅር ዘፈን አስታውሶ እጁን አነሳ፡፡

‹‹አገኘህ?›› አሉት መምህሩ‹‹አዎ!?››‹‹ንገረኝ››‹‹ችቦ አይሞላም ወገቧ››‹‹ምናልክ!?›› አሉት ነጭ ግንባራቸውን ስብስብ አድርገው፡፡ ምን እንዳለ ደግሞ ነገራቸው፡፡ እንደዚህ ያለ ረጅም ቃል

በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ መኖሩን የተጠራጠሩት እኒህ ፈረንጅ ደግመው ጠየቁት “በዕርግጥ ይሄ አንድ ቃል ነው?” በማለት፡፡

አሁን እሳቱ ጠፍቶ አመዱ ቡን አለ፡፡ ከሶስት ራሳቸውን የቻሉ ቃላት ተፈትሎ የተሰራ የአማርኛ ሀረግ መሆኑን እያመነታ ገለፀላቸው፡፡

ብዙዎቹ ተማሪዎች የመምህሩ ጥያቄ የቀጭን ሰው ክብደትን ያክል ቀላል እንዳይደለ ልብ ያሉት ይሄን ጊዜ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ

ጥያቄው የትምህርቱን መጀመር እስካሁን አላመላከታቸውም፡፡ ቅድም ፈገግ ያሉት ተማሪዎችም የጥያቄው አዝናኝነት ቀዝቀዝ

እያለባቸው መጣ፡፡ አንዳንዶቹ በጭንቀት ወደ ኮርኒሱ ቀና አሉ፡፡ ሌሎቹ በሃፍረት ወደ ጠረጴዛዎቻቸው አቀረቀሩ፡፡

የተቀሩት በክፍሉ መስኮቶች አሻግረው ወደውጭ ይመለከቱ ጀመር፡፡ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በወፍራም ሰዎች መካከል የሚርመሰመሱ ቀጫጭን ሰዎች ይታዩዋቸዋል፡፡ እነኚያን ቀጫጭን ፍጥረቶች ለማድነቅ የተፈጠረ አንድ አማርኛ እንኳ አብሯቸው እልፍ ሲል አለመመልከታቸው ከፋ እንጂ!…

በዚህ እየተገረሙ ሳሉም “በቃ ተውት” የሚለው የመምህራቸው እንግሊዝኛ ከንቱ ፍለጋቸውን አስተዋቸው፡፡

እናም አሻቅበው ከተሰቀሉበት ኮርኒስ አወረዳቸው … አቀርቅረው ከተደፉበት ጠረጴዛ አነሳቸው … ተወርውረው ከወጡበት መስኮት መለሳቸው…

ያም ሆኖ ታዲያ ፈረንጁ መምህር ገና በደንብ ያልወረደ በደንብ ያልተነሳ እና በደንብ ያልተመለሰ ነገር የቀራቸው ይመስል እንደገና አቀርቅረው ከተንጐረደዱ በኋላ “እስቲ ደሞ አሁን በአማርኛ ቋንቋ ቀጭን ሴትን የሚያንኳስስ እና የሚሰድብ ቃል አምጡልኝ” አሉ።

የሚገርም ነው፡፡ ይሄን ቃል ለማምጣት የተማሪዎቹ ዓይኖች እንደ ቅድሙ ወደጣራው አልወጡም ወደጠረጴዛው አልወረዱም ወደ ደጅም አልበረሩም፡፡

ልክ የፊሽካ ድምፅ ሲሰማ ፈጥኖ እንደሚንቀሳቀስ የጅምናስቲክ ቡድን በአንድነት እና በቅፅበት እጆቻቸውን ሽቅብ ወረወሩ፡፡

መምህሩ እጃቸውን ያላወጡ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ ወደላይ ከተመዘዙት ጣቶች መካከል ለአንዳንዶቹ እነኚያን ቃላት ይጠቁሟቸው ዘንድ ዕድል ሰጧቸው፡፡

‹‹አንተ››‹‹ስልባቦት››‹‹አንቺስ››‹‹ሲምቢሮ!››‹‹እዛጋ!››‹‹ኮሳሳ!››‹‹እዚህስ!››‹‹ቀጫጫ››‹‹በቃ!››‹‹ሌላም አለ››‹‹ይበቃል! ይበቃል››

በርሳቸው ይበቃል የወረዱት የዋህ እጆች ማስታወሻ ደብተሮቻቸውን መግለጥ ጀመሩ፡፡ በነሱ ቤት አሁን መምህራቸው የክፍሉን መነቃቃት ካረጋገጡ በኋላ አዝናኝ ጥያቄያቸውን አብቅተው የዕለቱን ትምህርት ለመጀመር ተዘጋጅተዋል፡፡

መምህሩ ግን ገና አልበቃቸውም አሁንም በክፍላቸው ወለል ላይ ጥቂት ከተንጐራደዱ በኋላ ከተደፋ አንገታቸው ቀና በማለት ‹‹እስቲ ደሞ አሁን ወፍራም ሴትን የሚያሞግስ ወይም የሚያቆላምጥ አንድ አማርኛ ፈልጉልኝ››

አሁንም ጭንቅ ሆነ፡፡ ጣራው ታየ ጠረጴዛው ተዳሰሰ፡፡ ደጁ ተፈተሸ በዚያን ሰዓት በቅጥር ግቢው ውስጥ ወዲያ ወዲህ ከሚሉት ቀጫጭን እግሮች መካከል ጐልተው የሚታዩዋቸው

ታገል ሰይፉ

ብዙ ወፋፍራም ሰዎች ነበሩ፡፡ ወፍራምነታቸው አሳምሮ የሚገልጥ አንድ ቃል

ማግኘት ከወፍራም ሰው ክብደት በላይ ከብዶ ተሰማቸው እንጂ…

በዚህ እየተገረሙ ሳለም “እሱን ተውትና …” የሚለው የመምህራቸው ድምፅ ካሻቀቡበት አወረዳቸው ከተደፉበት አነሳቸው ከወጡበት መለሳቸው…

“እሱን ተውትና ወፍራም ሴትን የሚያንኳስስና የሚሰድብ አንድ ቃል አምጡልኝ፡፡”

ተማሪዎቹ እንደፈረደባቸው እጆቻቸውን ሽቅብ ወረወሩ መምህሩም እንደገና ከእነኛ የትየለሌ እጆች መካከል ለአንዳንዶቹ አንዳንድ እድል ሰጧቸው፡፡

‹‹አንቺ››‹‹ወደል››‹‹አንተስ››‹‹ድብልብሌ››‹‹እዚህ ጋ››‹‹ዘረጦ››‹‹እዛስ››

‹‹ግንድ እግር››‹‹በቃ››‹‹ሌላም አለ መምህር›› ‹‹ይበቃል ይበቃል››በፈረንጁ ይበቃል የወረዱት የዋህ እጆች

ማስታወሻ ደብተራቸውን ገለጡ፡፡ ትምህርቱ ግን አሁንም አልተጀመረም፡፡

“አያችሁ…የማድነቅ ባህል ስለሌላችሁ ቋንቋችሁ እንኳን የበለፀገው በስድብ ቃላት ነው” በሚለው የመምህሩ የመጨረሻ ቃል ተደመደመ እንጂ፡፡ ….

የፈረንጁ መምህር ጥያቄዎች

ለፈገግ…

የስስት ነገር ሲነሳ ከፊታችን ድቅን የሚሉት ጋቭሮቮዎችና ስኮትላንዶች

ናቸው። ለዛሬ ትንሽ ልጅ አስከትሎ ወደ አንድ ፀጉር አስተካካይ ጐራ ስላለ አንድ እስኮትላንዳዊ

ልናጫውታችሁ ነው፡፡ ሰውዬው ጐፈሬው የተቆለለ ቁመቱ ረዘም ያለ፣ ትከሻውም ከበድ ያለ ሰው ነው፡፡

ዕድሜውም ቢሆን ቀላል አይባልም፡፡ 40ዎቹን ጨርሶ ወደ 50ዎቹ በመጓዝ ላይ ሳለ እግረ መንገዱን በዚህ

ፀጉር ቤት በኩል ሲያልፍ ዘው ይላል፡፡ ያንን ትንሽ ልጅ እንዳስከተለ፡፡ ….

ከዚያም ልጁን ወረፋ ጠባቂዎች ከሚቀመጡበት ወንበር ላይ ያስቀምጠውና እሱ ወደ ፀጉር ማስተካከያው ወንበር ያመራል፡፡ መጀመሪያ የአናቱን ጐፈሬ እንዲያራግፍለት ከዚያም ፂሙን በቀጭኑ እንዲላጨው ቀጭን ትዕዛዝ ያስተላልፋል፡፡ ከዚያም ፊቱን በክሬም ፀጉሩን በቅባት እንዲያሰማምረው ጭምር …

ባለሙያው በታዘዘው መሠረት አጨዳውን ከጐፈሬው ይጀምራል፡፡ ሰውዬው በማስተካከያ ቦታው ላይ የተደላደለው ጀርባውን ለትንሹ ልጅ ሰጥቶ ቢሆንም

ልቡም አይኑም ያለው በልጁ ላይ ነበር፡፡ የእግሩን ንቅናቄ በፊት ለፊቱ መስታወት መሀከል

አሻግሮ እየተመለከተ “አንተ ልጅ እግርህ ይረፍ ዋ! … የምን መቁነጥነጥ ነው? …”ይለዋል፡፡

ባለሙያው አጨዳውን ቀጥሏል፡፡ የአናቱ ጎፈሬ እየተገነደሰ እግሩ ስር ይከመራል፡

፡ ሰውዬው እየተንከባለለ እግሩ ስር የሚያርፈውን የፀጉር ክምር

አቀርቅሮ እየተመለከተ “ዋ !” ማለቱን

አላቆመም፡፡የእግሩ ውዝዋዜ ከወንበሩ ጋር ሲጋጭ

በሰማ ቁጥር “ባጐነብስም እኮ አይሃለሁ … ዋ … ብቻ ዛሬ …”

እናም ባለሙያው ፀጉሩን … ሰውየው እግሩን እየከረከመ ….እየከረከመ…መጨረሻ ላይ ሁሉም ነገር ተጠናቀቀና ከአጨዳው ወንበር ብድግ አለ፡፡

ከዚያም ወደ ትንሹ ልጅ ዘወር ብሎ “አሁን ደግሞ የአንተ ተራ ነው…”

ልጁም የሚወዛወዝ እግሩን አቁሞ ይቆምና ተወርውሮ ከአጨዳው ወንበር ላይ ጉብ ይላል፡፡

ሰውየው ወደ አስተካካዩ ዞሮ ልጁ እንዴት መቆረጥ እንዳለበት ከነገረው በኋላ ወደ ልጁ ጎንበስ ብሎ “እንግዲህ አንተ እስክትጨርስ እዛ ጋ ካለችው ሱቅ ዕቃ ገዝቼ እመጣለሁ … ታዲያ እስክመለስ ንቅንቅ የለም … ዋ…” ብሎት ወጣ፡፡

ፀጉር አስተካካዩም በተባለው መሠረት ልጁን አሰማምሮ ከጨረሰ በኋላ ሌሎች ደምበኞቹን ማስተናገድ ይቀጥላል፡፡

አንዱን ጨርሶ ሌላ ይተካል …. ሰውየው አይመጣም፡፡ ሌላውን ጨርሶ ሌላውን … ሰውየው አይመጣም፡፡

በጣም ሲቆይበት ጊዜ ቁጭ ብሎ እግሩን ወደሚያወዛውዘው ትንሽ ልጅ ዘወር ብሎ

“አንተ ልጅ … አባትህ በጣም ቆየ እኮ …” ቢለው “አባቴ አይደለም” “ምንህ ነው ታዲያ?”“ምኔም አይደለም … ወደ ቤቴ ስሄድ

መንገድ ላይ አገኘኝና ፀጉርህን በነፃ መስተካከል ከፈለክ ከእኔ ጋር እንሂድ ብሎኝ ወደዚህ አመጣኝ”

20 21

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

አብይ ጉዳይአብይ ጉዳይ

ይድረስ ለገዢው ፓርቲ ይድረስ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች

ይድረስ ለገለልተኛ ኢትዮጵያውያን

(ዮሴፍ ወ.ደግፌ)[email protected]

ጉዳዩ፡ “ቤት በጥበብ ይሰራል፣ በማስተዋልም ይጸናል”

ቤት በጥበብ እንጂ በጠብ እንደማይሰራ፣ በማስተዋል እንጂ በስሜታዊነት እንደማይፀና፣ በመፅሐፍ ቅዱስ በመፅሐፈ

ምሳሌ ምዕ. 24 ቁ.3 ላይ ያስተምራል… “ቤት በጥበብ ይሰራል” በሚልበት ጊዜ ሰዎች በጋራ የሚመሰርቷቸውን ቤተሰባዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሀገራዊና የተለያዩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ህብረቶችንና ተቋማትንም ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። የጋራ ቤትን ለመገንባት የጋራ ራእይ ማውጣት፣ አላማን መንደፍ፣ ግቦችን መተለም የሚያስፈልግ ሲሆን … በሂደት በሰዎች መካከል የአመለካከት ልዩነት ሊፈጠር ስለሚችል … አላማንና ግቦችን የማያስት እስከሆነ ድረስ፣ በመቻቻል በመደራደር መስራት (Compromising) ጥበብና ማስተዋል ደግሞም ስልጡንነትና ዲሞክራሲያዊ አካሄድ ነው፡፡ …በተቃራኒ ሀሳቦች በመደራደር የዳበረ ውይይት … በሳል ውሳኔን በማመንጨት … መተማመንን በማዳበር… ህብረትን አንድነትን በማጠናከር እንዲሁም አሰራርን በማጠናከር ሂደትን የማፋጠን አቅሙ ከፍተኛ ነው … ልዩነትን አቻችሎ መስራት የአብሮነት ውዴታ ግዴታም ነው፡፡

ካናዳዊ የባህርይ ጥናት ሳይኮሎጂስት (Behav-ior psychologist) አልበርት ባንዲራ ባደረገው የማህበራዊ ባህርይ ጥናት (social Behavior

study) ሰዎች ከሚያደርጉዋቸው 20 ውይይቶች 17ቱ (85%) ግብብነት የሌላቸው የሚቃረኑ ሃሳቦች (negative communications) እንደሆኑ አረጋግጦአል። … ይህም የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሮአዊ ሰውኛ (Humanistic) ነው ወደሚል መደምደሚያ ይወስዳል። ታዲያ ሰዎች በጋራ አጀንዳ ላይ እየተደራደሩ ከመኖር ውጭ ምን የተሻለ ምርጫ አላቸውና ነው በመጣላት የሚበታተኑት?

ከዓለም ህዝብ 10% በታች የሚሆኑት ምዕራባውያን በጋራ እየተደራደሩ በመሰራት “ባለመግባባትም ቢሆን ተገባብተው” (agree to disagree) ሁለንተናዊ አቅማቸውን በማሳደግ በኢኮኖሚ በፖለቲካና በወታደራዊ የበላይ ሆነው አለምን ይመራሉ … አፍሪካውያን ግን ዛሬም ድረስ ካልተግባባን መጨራረስ ያለብን ይመስል እንደ አይጥና ድመት እየተጠባበቅን በጦርነት እንደቅርጫ ስጋ እየተከፋፈልን እየተበታተንን አቅም በማጣት እንዳክራለን፡፡ በተራ አለመግባባት ችግር ምክንያት በከፋ መቃቃር፣ በጸብ፣ በቂምና በጥላቻ በመለያየት፣ ብዙ የተወጠነበትንና የተደከመበትን ቤተሰባዊ፣ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ሀገራዊ ህብረት በቀላሉ በማፍረስ፣ አንዳችን አንዳችንን አጥፍተን በ “ሰላም” ለመኖር እንጥራለን፣ (አንዱ አንዱን አጥፍቶ በሰላም ለመኖር አይችልም እንጂ) በተለይ ኢትዮጵያውያን በጋራ አጀንዳ ላይ

እየተደራደርን ተግባብተን መስራት ለምንድነው የሚያቅተን?

የተለየ የግል አላማ ከሌለ በስተቀር የሀሳብ ልዩነቶች በተሻለ አማራጭና መፍትሔ አምጪነት እንጂ፣ በአፍራሽነት በመመልከት፤ በጋራ አጀንዳ ላይ ለድርድር እንቢተኛ መሆን ኢ-ዲሞክራሲያዊነት ወይም አምባገነንነት ነው፡፡ በራዕይ በዓላማና እንዲሁም በግብ አንድ ሆነው ሳለ … በሃሳብ ልዩነቶቻቸው ላይ መደራደር እያቃታቸው ጥበብንና ማስተዋልን በማጣት በግትርነትና በስሜታዊነት በየግዜው በመሰነጣጠቅ ከሚፈርሱትና ከሚበታተኑት የኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ህብረቶች መካከል፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የገዢው ፓርቲ ኢሊቶችን፣ የዲያስፖራ ጊዜያዊ ፖለቲካ ማህበራትን፣ የዲያስፖራ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲዎችን፣ የዲያስፖራ የኢትዮጵያ ስፖርት ማህበራትን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ክርስቲያናዊ መንፈሳዊ ህብረቶች ጭምር ለአብነት ያህል መጥቀስ ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በቤተሰብም ሆነ በት/ቤት ውስጥ እድገታችን እንዲሁም ደግሞ የመንግስታቶቻችን የአገዛዝ ባህርይ በውይይት፣ ድርድር ሳይሆን፣ ‹በግዢና በተገዥነት›... “በበላይና በበታችነት” … “ትእዛዝ በመስጠትና መመሪያ በመቀበል”

በአለቃና በምንዝር፣ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ስሜታዊ እድገታችን ተጨፍልቆ በባህርያችን ላይ ትልቅ ተፅእኖ በማሳደሩ በውይይት በክርክርና በመደራደር የጋራ ስምምነት ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሞት ያህል ይከብደናል፤ ለመግባባት አለመቻላችን ከግል አልፎ ሀገራዊ ጉዳትና ጠባሳ እየተወ ይታያል፡፡ ድርጅታዊ ተቋም ካለንም ተቋማዊ ህገ-ደንብ (መተዳደሪያ ደንብ) (By-law) በማይፈቅደው … ጠቅላላ አባላት (ጉባዔ) ሳያውቀው (ሳያፀድቀው) ከ‹‹እኛ ጋር ያልሆነ ሁሉ ይቃወመናል›› በማለት… በአመለካከት የተለዩንን ሰዎች እንደ ጠላት በመፈረጅ፣ ወደ ተከላካይነትና አጥቂነት እንቀየራለን … የእኛን ሀሳብ የሚጋራ ደካማ ደጋፊ (Cliques) ካገኘንም በብልጣብልጥነት ለመክረም እንገደዳለን እንጂ “ይቅርታ ተሳስተናል ታርቀን ተራርመን እንደገና አብረን እንቀጥል” ሞት ቢመጣ አንልም፡፡ በመሆኑም ብዙ የታቀደለትንና ለመገንባት ዘመናት የፈጀንበትን ህብረት ህብረት/ተቋም በአንዲት ጀንበር አፍርሰን ቁጭ እንላለን፡፡ ለመፍታትም አንጥርም፤ ማንም ምንም ቢል ግድ አይሰጠንም፡፡ ምክንያቱም ከራሳችን በስተቀር ማንንም አንሰማም… ማንንም አናምንምና ነው፡፡ ከዚህ ከተጠናወተን የባህርይ በሽታ ለመፈወስ ብዙ ትውልድ የሚፈጅብን ይመስለኛል፡፡

ጆርጅ ፓትሰን የተባሐው ሰው “if everyone thinking alike, then somebody is not think-ing” ይላል፡፡ ሰው ሁሉ ተመሳሳይ ሀሳብ ቢኖረው ኖሮ፣ ሌላው ሰው ማሰብ አያስፈልገውም ነበር… ምክንያቱም የአንድ ሰው ሀሳብ ለሰዎች ሁሉ በቂ ስለሚሆን ነው… ሰዎች ከአስተዳደግ ተጽእኖ፣ ከመንፈሳዊ እምነት ተጽእኖ፣ ከህይወት ልምድ ተጽእኖ፣ ከትምህርት ዝግጅት ተጽእኖ Genera-tion gap ወዘተ… የተነሳ ተመሳሳይ አመለካከት ሊኖራቸው በፍፁም ስለማይችል በድርድር ጥበብ በማስተዋልም በጋራ መስራት ይገባቸዋል፡፡

የዚህ ፅሁፍ አላማ የግል እይታን እንደ ዜግነት አስተዋፅኦ ማቅረብ ሲሆን 1/ የየፖለቲካችን አይዶሎጂዎች/ እምነቶች/ መርሆዎች እንደተጠበቁ ሆነው በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግን ከቡድናዊ ወይም የፓርቲ አመለካከት ነፃ በመውጣት በጋራ የምንመራባቸው የጋራ ሀገራዊ ፖሊሲዎች መቅረፅ እንደሚያስፈልገን ማስገንዘብ ነው፡፡ 2/ በዋና ዋና ብሔራዊ ሀገራዊ አጀንዳዎቻችን ላይ የአንድን የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን ራእይ አላማና ፍላጎት ብቻ በማብጠልጠል የተለየ አመለካከት ያለውን ወገን ከጨዋታ ውጪ ማድረግ ለማንኛችንም የማይበጅ ዘላቂ ስምምነት ላይ የማያደርሰን ዘላቂ ሀገራዊ ልማትና በዋናነትም ዘላቂ ሰላም የማያመጣልን መሆኑን ማስገንዘብ ነው፡፡ 3/ የጋራ ብሔራዊ ፖሊሲያዎችን (የጋራ ብሔራዊ አጀንዳዎችን) ለመቅረፅ ብሔራዊ መግባባት እንደሚያስፈልገን ማስገንዘብ ነው፡፡ 4/ አክራሪ

(ፅንፈኛ) የፖለቲካ አመለካከቶችን በጋራ ብሔራዊ ራእይ ለማጥበብ እንዲቻል ፖለቲካኞቻችን ወደ ማእከላዊ የፖለቲካ አመለካከት (Centrism: Centre Left or Centre Right) መምጣት እንደሚገባቸው ማስገንዘብ ነው፡፡ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሁሉም የጋራ ውሳኔ የሚሰጥበት ብሔራዊ የጋራ አጀንዳ ቢኖረን በትንሽ በትልቁ የፖለቲካ ንትርካችን ይቀንሳል የፖለቲከኞቻችን ውጥረት ይቀንሳል የብልፅግና ጉዞ ዘመንም ያጥራል 5/ የጋራ ብሔራዊ አጀንዳ ለመቅረፅ በፖለቲካ አይዶሎጂ ወገናዊነት ውስጥ የሌሉ ገለልተኛ ሰዎች በሙስና ውስጥ የሌሉ ሰዎች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሰዎች ለሀገር ትንሽ አስተዋፅኦ በማድረግ የሚታወቁ ሰዎች ከገዢውና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በህብረት እንዲሰሩት ማስገንዘብ ነው፡፡

“እንደ እባብ ብልህ እንደ እርግብ የዋህ(?)”

10,200 ኪሎ ሜትር ያህል በመጓዝ በዓለም ላይ በርዝመቱ 1ኛ የሆነውን ታላቁን የአባይን ወንዝ መሰረት አድርጎ የተገነባው የግብፅ ህይወት የአስዋን ግድብ ተገንብቶ ለግብጽ መጠነ ሰፊ ጥቅም መስጠት ከጀመረ ግማሽ ምእተ አመት (50 ዓመት) ሲሞላው ኢትዮጵያ በተባለችው ምድር ላይ የሚኖረውና የአባይ ምንጭ 86% ያህል መነሻ የሆነው ህዝብ ግን የ2ሺ ዓመታት መፅሐፍ ቅዱሳዊ እምነቱ እንደሚናገረው “እንደ እባብ ብልህ እንደ እርግብ የዋህ ሁን” ሆኖ ያልተገኘ ምንዱባን ህዝብ ነው፡፡ ርግብነቱ (?) አለን ብንል እንኳን ብልህነቱ የት አለ? ፈጣሪ የሰጠውን የተፈጥሮ በረከቶች በመጠቀም ከርሃብና ከእርዛት ሳይወጣ ለብዙ ሺ ዓመታት በድህነትና በጦርነት አዙሪት ውስጥ ሲዋትት ይገኛልና፡፡ ይበልጥ ደግሞ በግሎባላይዜሽን ዘመን ላይ አባይን በጋራ ለመገደብና ለመጠቀም የህብረት ችግር መታየቱ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡

በሺ ዓመታት ረጅም ታሪክዋ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው መሪዎች ህዝብ የስልጣናቸው ምንጭ ስላልሆነ ከራሳቸው አመለካከት በላይ ለሀገር ማሰብ ያልቻሉ፤ በስልጣን ሹኩቻ በመናቆር አንዱ በአንዱ መቃብር ላይ የራሱን መንግስት በኃይል የሚገነባ፣ የአመራር ጥበብና ማስተዋል የሌላቸው፣ ጀብደኞች ፣ ግትሮች፣ ራስ ወዳድዎች፣ በአጠቃላይ አምባገነኖች በመሆናቸው የተነሳ በጦርነት የደቀቀች ድንቁርና ርሀብና ድህነት የተንሰራፋባት ሀገርን ደግሞም እርስበርስ ጥላቻንና ክፋትን ቂም በቀልን እንጂ ሌላ ምንም ውርስ አላስረከቡንም፡፡ በመሆኑም በራሳችን ችግር ምክንያት፤ አባይንም ይሁን ሌሎች በረከቶቻችንን ለመጠቀም ባለመቻላችን፤ ለዘመናት በከንቱ በመባከን የተራቆተ ህዝብ ስለሆንን ሊታዘንልን እንኳን የማይገባን ነን፡፡ ሌላው አለም ስለ እህል ማሰብ ትቶ ትልቅ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ጐሎባላይዜሽን

ዘመን ላይ በአለም ፊት ርሀብተኛ፣ ተመፅዋች፣ ስደተኛ፣ የድርቅና የጦርነት ምሳሌ ነን፡፡

“ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” እንዲሉ አባይንም ይሁን ሌሎች ተፈጥሮአዊ ሀብቶቻችንንና የሰው ኃይል ሀብታችንን ሳንጠቀምባቸው በድህነትና በጦርነት አዙሪት (Vicious Cir-cle of poverty & war) ለዘመናት ስንዳክር እዚህ ደርሰናል፡፡ እህል ሆኖ ሊጠቅመን ባልቻለ ታሪክም በባዶ ሜዳ ላይ ስንፎክርና ስናቅራራ የበረከት ምንጮቻችን ለዘመናት በከንቱ ባከኑ፤ ወንዞቻችንም በከንቱ ወረዱ፤ ከዚህ አንፃር እርዛትን እንደ ብልፅግና፣ ርሀብን እንደ ጥጋብ በመቁጠር፤ ለዘመናት እያለቅን ከንቱነታችንን ለአለም ያረጋገጥን የመሆናችንን እንቆቅልሽ በእፍረትም በድፍረትም በመናገር ለመፍታት መነሳታችን ዛሬ እንኳን ካልሆነ መቼ ሊሆን ነው?

“ኢትዮጵያውያን አብረው መብላት እንጂ አብረው መስራት አይችሉም”

እንደ ቋንቋ/ዘርና ሃይማኖት ወዘተ ልዩነታችን ሁሉ የአመለካከት ልዩነታችንም በጋራ ሀገራዊ ግንባታ ላይ ጥንካሬያችን ስለሆነ እጅግ አስፈላጊያችን ነው፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያውያን በትንሹም ይሁን በትልቁ በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ዘወትር በከፋ የአለመግባባት ልዩነት (ቅራኔ) ውስጥ ስለምንገባ፣ በህብረት (በአንድነት) ለመስራት ፈፅሞ አለመቻላችን … ከመጥፎ ባህርይነት ወደ መጥፎ ፖለቲካ ባህልነት እየተቀየረ መጥቶአል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለሺ ዓመታት የዘለቁ ታላላቅ ቀደምት ሃይማኖቶች ተከታይ እንደመሆኑ መጠን ከእኛ በላይ በጥሩ ስነ-ምግባር የታነጸና ደግሞም በታሪክ ህዝብ በዓለም ላይ የሚገኝ አይመስለንም፡፡ ነገር ግን እኛ እንደምንለው ሳይሆን፤ ትላንትና ነፃነታቸውን ያገኙ ሀገሮች በአጭር ዘመን ውስጥ የማደጋቸውን ምስጢር የእኛን ያለማደግ ምክንያት ያጋልጣል፡፡

ነፃነታቸውን ካገኙ 50 ዓመት የሞላቸው ሀገሮች ከሞላ ጎደል በስምምነት ሰርተው ለውጥ ሲያመጡ፣ እኛ ሺ ዓመታት ቀደምት ብንሆንም ተስማምተን በጋራ ለመስራት ባለመቻላችን፣ ዛሬ በአለም ላይ ከአንድ ሀገር በስተቀር የምንቀድመው የለም፡፡ እርግጥ በጋራ ጠላት (የጦርነት ታሪኮች) ውጤታማነት በአለም የታወቅን ለመሆናችን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነገር ግን ወደ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ስንመጣ የአለም መጨረሻ ነን፡፡ ይህም ‹‹እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ›› ፖሊሲያችን ውጤት ነው። በዋናነትም መሪዎቻችን ለእግዚአብሔር ሆነ ለህዝብም ባስቸገረ ማንነት፣ ያለ ህዝብ ፍላጎት ተጭነው በመግዛት፣ ሀገርን በፍትህ በመምራት ወደ ብልፅግና ለማምጣት አለመቻላቸው፤ በስልጣን በመሻኮት እጅግ በከፋ የጥላቻና የቂም በቀል

22 23

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

አብይ ጉዳይአብይ ጉዳይ

ኩሬ ውስጥ በመዘፈቅ፤ እርስ በርስ በመጠፋፋት ፖሊሲያቸው፣ በጦርነት በመጠመድ አንደኛው በሌላኛው ላይ ስልጣኑን በሃይል ለመመስረት የሚያደርገው ትግል፣ ትውልዶች በጦርነት እሳት በከንቱ አለቁ፣ የሀገሪትዋ ሀብትም ወደመ። መልካም አስተዳደር በማጣት ምክንያት የመጡ 3 ቀውሶች በቀላል ምሳሌዎች ፡

1 ኢኮኖሚ ለሺ ዓመታት በአንድ ማረሻ በበሬ እያረስን የሺ

ዓመታት የጦርነት ታሪካችንን እንደ ሀገራዊ ልማት ለዘመናት ስንደልቅ ነፃነታቸውን ካገኙ ሃምሳ ዓመት ያልሞላቸው የአፍሪካ ሀገሮች ቢያንስ ከርሀብ ወጥተዋል፡፡ እኛ ግን አሁንም ድረስ እንራባለን፡፡ በFAO የ2013 መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ በየአመቱ በአማካኝ ከ16 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የምግብ እህል እርዳታ ጠባቂ ነው፡፡ ከህዝባችን 93 በመቶ የሚሆነው ለመኖር የሚያስፈልጉት ሶስት መሠረታዊ ነገሮች፣ (በቂ ምግብ ልብስና መጠለያ ቤት) ሳይሟላለት የሚኖር ነው፡፡ በምግብ ራስን ያለመቻል ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የስልጣኔ መሰረት የሆነውን የቴክኖሎጂ ልማት ብንመለከት፣ በአፍሪካ ሀገሮችና በኢትዮጵያ መካከል ለምሳሌ በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ በኢንተርኔት አቅርቦት፣ በስልክ አቅርቦት በመኖሪያ ቤትና በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡

2 ከፍተኛ ትምህርት የኡጋንዳው ማካራሬ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተ 115

ዓመታት ያለፈው ሲሆን የእኛው ‹‹አንጋፋ›› አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግን ገና 65 ዓመት አካባቢ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ትላንትና ነፃነቷን ካገኘችው ኡጋንዳ ጋር ስንወዳደር ለ50 ዓመታት (3 ትውልድ ያህል) ከከፍተኛ ትምህርት ወደኋላ እንድንቀር ተደርጓል፡፡ ከኡጋንዳ አንፃር እንኳን ስንወዳደር የመጀመሪያው ትውልድ ከ120 አመታት በፊት ኮሌጅ/ዩኒቨርስቲ መግባት የነበረበት ሲሆን ‹‹አንጋፋው›› አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በአሁኑ ሰዓት 3ኛ ትውልድ ሳይሆን ቢያንስ 6ኛ ትውልድ በስተማር ላይ መገኘት ነበረበት፡፡ ከ120—150 ዓመታት በፊት ኮሌጅ/ ዩኒቨርስቲ የገባ የመጀመሪያ ትውልድ ቢኖረን ኖሮ የተሻለ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ይኖረን ነበር፡፡

3 ፖለቲካየፖለቲካ ባህላችን የጦርነት ታሪክ ነው።

በፖለቲካ ሽኩቻ አዲስ ገቢው መንግስት በአሮጌው መንግስት መቃብር ላይ የቀድሞውን እያፈረሰ የራሱን አዲስ አገዛዝ በኃይል የሚመሰርትበት ዘላቂ ሰላም ብልፅግናና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን በመከባበርና በማቻቻል ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ድርድር የማይደረግበት ዛሬም በግሎባላይዜሽን ዘመን ‹‹የማን ቤት ጠፍቶ

የማን ሊበጅ የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ›› የሚለውን ጥንት የተላለቅነበትን የመጠፋፋት ዘፈን የምናቀነቅን በመሆኑ የፖለቲካ ባህላችን በሽተኛ መሆኑን ያጋልጣል፡፡ (ይህ ግን ህዝባችን በዓለም የተደነቀበትን በአንድነት በሰላምና በፍቅር በሃይማኖት ተቻችሎ ተከባብሮ የሚኖርበትን ፅናት አይመለከትም)

ብሔራዊ መግባባት (National con-sensus)

በዓለም አንጋፋ የታሪክ ባለቤትነት በሃይማኖት በስነ ምግባር በመልካም ሰብእና በመታነፅ በሰው አክባሪነት በእንግዳ ተቀባይነት ወዘተ ቅፅሎች ሁሉ እንዳሉ ናቸው ብንል ይህ ማንነት ግን ተግባብተን በጋራ ለመስራት አላስቻለንም፡፡ ባህርያችን በስራችን መሆኑን አላስተዋልንም የአለመተማመን ክስረት ውስጥ የገባ እንደ እኛ አይነት ህዝብ በዓለም ላይ ያለ አይመስልም፡፡ የምንከተለው ሃይማኖትም ስለ ፍቅር ቢሰብክም፣ ፍቅራችን ግን የግብዝነትና የለበጣ በመሆኑ፣ በፍቅር መሸናነፍ ቀርቶ ተራ ሰውኛ መግባባት ላይ እንኳን ለመድረስ አልቻልንም፡፡ የረዥም ዘመን ባለታሪክነትና ሃይማኖተኛነት በጋራ ጥቅማችን ላይ መስማማት የምንችልበትን አቅም ሊፈጥርልን አልቻለም ‹‹ኢትዮጵያውያን አብረው መብላት እንጂ አብረው መስራት አይችሉም›› የሚሉት ስድባዊ አባባል እርግጥም እውነትነት አለው፡፡

ብሔራዊ መግባባትን በተመለከተ ነግ በእኔ ነውና የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ያለጠላትነት በሰላም ለደርግ ባለሥልጣናት ምህረትና ይቅርታ ማድረጉ በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ ተጨማሪም ብሔራዊ መግባባት ለማድረግ 1ኛ/ ከ40 ዓመታት ወዲህ የሞት የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ካሳ መክፈልና ይቅርታ መጠየቅ ይገባል፡፡ 2ኛ/ ለፖለቲካ እስረኞች ምህረትና ይቅርታ ማድረግም ይገባል፡፡ 3ኛ/ ገዢውና ተቃዋሚ ፓርቲዎች (በአይዲዮሎጂ ቢለያዩም፣ ተሳሳይ የሀገር እድገት አላማ አላቸው) ብሔራዊ መግባባት ስለሌላቸው፣ ጦርነት ቀረሽ ፖለቲካዊ ጭቅጭቃቸው ፖለቲካዊና መረጋጋትና እድገት እንዳይኖር ያደርጋል ምሳሌ 1/ የባህር በር፣ ጠ/ሚር መለስ ‹‹ወደብ ሸቀጥ ነው›› በማለታቸው፣ ኢህአዴግ የባህር በር አጀንዳን የዘጋ ይመስላል፡፡ ተቃዋሚዎች ደግሞ ‹‹ሀገሪቷ የባህር በር የማግኘት ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና አለም አቀፋዊ መብት አላት›› ይላሉ፡፡ ታዲያ ይሄን ተራራ የሚያህል የብሔራዊ ፖሊሲ ልዩነት ሳይፈታ (ብሔራዊ መግባባት ሳይኖር) ኢህአዴግ እራሱን ለማጥፋት ነው በምርጫ መሸነፍም ቢሆን የፖለቲካ ስልጣንን ለተቃወሚ ፓርቲ የሚያስረክበው? ምሳሌ 2/ የመሬት ፖሊሲ፣ ‹‹መሬት የግል ይሁን የመንግስት?›› የሚለው ብሔራዊ ጥያቄ በተቃዋሚ

ፓርቲዎችና በኢህአዴግ መካከል የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቅ ፖሊሲ ልዩነት ሳይፈታ ነው (ብሔራዊ መግባባት ሳይኖር) ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣንን ለተቃዋሚ ፓርቲ የሚያስረክበው? ስለሆነም ብሔራዊ መግባባት የግድ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡

የኑሮ ልዩነት ችግርና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል

ዛሬ ዛሬ አብረን ለመቁረስ እንኳን እንዳንችል የሰማይና የምድር ያህል ያራራቀን የገቢ ልዩነታችን ያሰፈራናል፡፡ እንደቀድሞው ዘመን በጋራ የማንበላበት አንድ ምክንያት የሀብታችን ምንጩ ስለ ‹‹ማይታወቅ›› ስለምናፍርበት ይሆን? የደሀና የሀብታም ኑሮ ልዩነት እጅግ የመስፋት ችግር (Eco-nomic Inequality) በተመለከተ እጅግ በጣም ጥቂቶች (<o.0002%) ከአውሮፓ/ ከአሜሪካ ስታንዳርድ (ደረጃ) በላይ ሲኖሩ … (93%) ህዝብ ደግሞ በእርዛት መኖር ሀገራዊ መሰረታዊ ችግራችን ነው፡፡ በዚህች ደሀ ሀገር ውስጥ የገቢ ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል መራራቅ ችግር ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ችግር መኖር ‹‹መንግስተ ሰማይም ሲኦልም እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው›› የሚሉን ደግሞ የውጭ ታዛቢዎች (ነጮች) ናቸው፡፡ እንዲሁም የምግብ ዋስትና ችግር የመልካም አስተዳደር ችግር (የፍትህ መዛባት ችግር) የሙስና ችግር (ባቋራጭ ሀብታም የመሆን ችግር) የስራ አጥነት ችግር በመስፋፋቱ የተነሳ ህዝቡ ኑሮና ብልሀቱ እየተጣረሰበት በሰላም ሊኖር አይችልም፡፡ የደሀና የሀብታም የኑሮ ልዩነት ችግር (income gap ) ለመፍታት ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል የግድ ስለሚያስፈልግ tax & economic policy መሻሻል አለበት፡፡

ድህነት አለመግባባትን ያባብሳልአለመግባባታችንን ከሚያባብሱ ነገሮች ውስጥ

ድህነት ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የሚኖራት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትዋ ግን ከ2 ሺ ሜጋ ዋት የማይበልጥ በመሆኑ፤ በዚህና በሌሎች የድህነት መስፈርቶችም ጭምር የድህነታችን ልክ ሲለካ በዓለም ላይ ከመጨረሻ 2ኛው እጅግ ደሀ ሀገር እንደሆንን በቅርቡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በ2014 /2015 ባደረገው ጥልቅና ሰፊ የጥናት መረጃ ጠቁሟል (Global Multidimensional pover-ty index (GMP) www.ophi.org.uk) ሀገሪቱ ግን የኤሌክትሪክ ኃይል ለአፍሪካና ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ኤክስፖርት በማድረግ በቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ የማግኘት አቅም አላት፡፡ አባይ ቢገደብና 6ሺ ሜጋዋት በማመንጨት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅማችንን ወደ 8ሺ ሜጋ ዋት ከፍ ቢል 1/ የሀገር ውስጥ ሀይል ፍላጎት በእጅጉ

ይሻሻላል፡፡ (ቢያንስ መብራት ተቋረጠብን ማለት ይቀራል) 2/ የውጭ ኢንቨትመንት እንዲስፋፋ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በእጅጉ ወሳኝ መሆኑ የውጭ ኢንቨስተር ከፖለቲካ መረጋጋት ቀጥሎ የሚጠይቀው ‹‹ምን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አላችሁ›› መሆኑ 3/ የሌክትሪክ ኃይል ወደ ውጭ ኤክስፖርት በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማግኘት ሀገራዊ ግንባታና ተጨማሪ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ለማመንጨትም የአባይ አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ ባለመሆኑ ነው፡፡

ሌላው የድህነታችንን ትልቁ መግለጫ የገቢ ንግድ (Import) እና የውጭ ንግዳችን (Export) ነው፡፡ … የኢትዮጵያ መንግስት የብሔራዊ ባንክ በ2012 /2013 ባወጣው የሀገሪቱ የገቢና የውጪ ንግድ ስታትስቲክስ መሰረት፤ የሀገራችን የገቢና የውጭ ንግድ ሬሽዮ (ንጽጽር) በዓለም ላይ ካሉት የመጨረሻ ደካማ ሀገሮች ተርታ ነው፡፡ ይኸውም ወደ ውጪ የምንልካቸው ምርቶች ከውጭ ከምናስገባቸው እቃዎች ጋር በዋጋ ሲነፃፀር Export : import ratio 1 እጅ ለ3 እጅ ነው፡፡ በአሀዝ ሲታይ በ2012/2013 ሀገሪቱ ወደ ውጭ የላከችው ምርቶች ዋጋ በድምሩ ወደ 3.5 (ሦስት ተኩል) ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን፣ ከውጭ ያስመጣቻቸው እቃዎች ዋጋ ደግሞ በድምሩ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ስሌት መሰረት ከውጭ የምናስመጣቸውን እቃዎች ያለ ንግድ ጉድለት (trade Deficit) ለማከናወን ወደ ውጭ የምንልካቸውን እቃዎች በመጠን በጥራትና በሽያጭ ዋጋ ከሶስት እጥፍ በላይ ማደግ አለበት፡፡

አባይ ለብሔራዊ መግባቢያነት የአባይ ግድብ ግንባታን መቃወም ግን ምን

አይነት የፖለቲካ ስልት ነው? እንዲያውም የአባይ ግድብ ግንባታ የከረረውን የጥላቻ ፖለቲካችንን ውጥረትን ያረግባል፡፡ ስርነቀል የእድገት ለውጥ ለማምጣት የኃይል አቅርቦት በእጅጉ የሚያስፈልጋት ታላቅ ደግሞም ታናሽ ደህ ደግሞም ሀብታም ሀገር ኢትዮጵያ በመንግስት ስታትስቲክስ መሰረት አሁን ባለችበት የ2ሺ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፤ እንኳን የውጭ ኢንቨስትሮችን ለልማት ለመጋበዝ ቀርቶ የሀገር ውስጥ ፍጆታን ለሟሟላት ፈፅሞ አትችልም፡፡ የአባይ ግድብ ግንባታ ለሀገሪትዋ ሁለገብ የልማት ስራዎችና የሀይል ምንጭነት እጅግ መሰረታዊ ከመሆኑ በመለስ ለብሔራዊ ፖለቲካ መግባቢያነት ከሚረዱን ግብአቶች ውስጥ አንድ መሆኑን በቅንነት ያለመረዳት ችግር ያለ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ይህንን የተረዳን ቢሆን ሮሮ ከቡድናዊ ፖለቲካዊ አመለካከታችን ውጭ መሆን ነበረብን፡፡ ግድቡን ማንም ይገንባው ባለን አቅም መረባረብ እንጂ ገዢውን ፓርቲን ከመጥላት ችግር መያያዝ የለበትም፡፡ ይልቁንም አባይ ቢገደብ ለብሔራዊ

መግባቢያነት በር ይከፍታል ብሎ ማሰብ ይበጃል፡፡ በማስተዋልና በጥበብ መመላለስ ማለት

አባይን ተቃዋሚ ፓርቲ ገደበው ገዢው ፓርቲ ገደበው የተሰራውን ስራ መቀበል (acknowl-edge) ማድረግ ነው የሚገባው። በአባይ ግድብ ስራ መነሻነት በመከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ፖለቲካዊ ባህል ሊጀመር ይችላልና፡፡ እውነትም አባይ ተገድቦ የኢትዮጵያ ህዝብም ተጠቅሞ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ኢህአዴግም በፖለቲካዊ መቻቻል መልካም ግንኙነት ቢመሰርቱ አባይ ለብሔራዊ መግባቢያነት ቢሆን ትልቅ ድል ታላቅ ገድልም ነው፡፡ ስለሆነም አስተውለንና ተግባብተን በብሔራዊ ጉዳይ በጋራ ለመስራት ካልቻልን በስተቀር፣ አንድ የፖለቲካ ምሁር እንደጠቀሰው ‹‹if we are political depressed we will find it much harder to cope with political stalemates and our frustration lead us to wrong decision/action›› በፖለቲካዊ ድንዛዜ ውስጥ ገብተናል፤ ወይም ከጥንት የተጠናወተን የእርስ በርስ ክፋት፣ ጥላቻና ቂም በቀል ዛሬም የግሎባላይዜሽን ዘመን ላይም አለቀቀንም? ወይም ደግሞ ዘወትር ‹‹እኔ የምለው ብቻ ትክክል ነው›› (my way is the highway) የምንል ራስ ወዳድ ግትሮች ነን፡፡

ምኑን አወቅን?ጥላቻ በሰላም በጋራ ሊያኖር የሚያስችል

መርዝ … ቂም ወደ ተለመደው እርስ በርስ ጦርነት የሚወስደን አቋራጭ መንገድ … በቀል የህይወት መጋዝ መሆኑን በግሎባላይዜሽን ዘመን ካልተረዳን መቼ ነው የምንረዳው? መልካም መንፈስና አእምሮ ያለው ሰው ምንጊዜም ገለልተኛነትን በማራመድ ሰውን ሁሉ እኩል የሚያይ ነው፡፡ … ከወገናዊነት ነፃ መሆን ሚዛናዊ አስተሳሰብን የምናራምደው የጋራ ችግራችንን በጋራ በሰላም የምንፈታበት ሁሉም የሚያሸንፈበት (Win-Win Resolution) መንገድ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ መቻቻልን ዛሬ ካልሰራን መቼ ነው የምንሰራው? የምንገኝበት ዘመንም ይህን ግድ እንደሚለን እንዴት አልተገነዘብንም? ይህንን ለማወቅም ሆነ መቻቻልን እውን ለማድረግ የአስተሳሰብ ልቀት የሚያስፈልግ ሲሆን በአስተሳሰብ ለመላቅ ደግሞ MA ወይም PhD ዲግሪ መጫን አያስፈልግም፡፡ ጥላቻን ክፋትን ምቀኝነትን ገብጋባነትንና ምዝበራን ቂም በቀልን ወዘተ በማስወገድ በምትካቸው ንፁህ አዕምሮና ንፁህ ልብን መፍጠር ብቻ ነው፡፡ በዚህም ከማይበጅ ጥላቻ አመለካከት ነፃ እንወጣለን፡፡

ኦሮሚያንና ኦጋዴንን እንደ ኤርትራ ማስገንጠል ቀርቶ ኤርትራም፣ ኢትዮጵያም፣ ኦሮሚያም፣ ሶማሌም፣ ጅቡቲም፣ ሱዳንም፣ ደቡብ ሱዳንም፣ ኬንያም፣ ኡጋንዳም፣ የምስራቅ አፍሪካ ህዝብ ሁሉ የጋራ ችግርን በጋራ ለመፍታት፤ ከድርቅ

(ርሀብ) ከጦርነት ነፃ ለማውጣት፤ ጠንካራ ሶሺዮ ኢኮኖሚያዊ ህብረት በመመስረት በሂደትም ፖለቲካዊ ቁርኝት በማምጣት በሰላም እና በብልጽግና የምንኖርበት ዘመንና ምድር መፍጠር ካላወቅን ምኑን አወቅን? ዛሬም እንደትላንቱ ህዝቦችን በመከፋፈል የምናጋጭ ይህም ሁላችንንም ይዞ የሚጠፋ ስራ መሆኑን ካለወቅን ምኑን አወቅን ? ይህ የአእምሮ ጉድለት (Personality Disor-der) መሆኑን ካላወቅን ምኑን አወቅን? ዘላቂ ሰላም ለቀጠናው ማምጣትን ካላወቅን ምኑን አወቅን? በቋንቋና በባህላችን ራሳችንን በማስተዳደር፤ ለጋራ ጥቅምም አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የጋራ ትብብር ማድረግ ካላወቅን ምኑን አወቅን? ይህ ትውልድ ከመንግስቱ ኃይለማርያም፣ ከኢሳያስ አፈወርቂ ትውልዶች ‹‹ከራስ በላይ እግር›› አስተሳሰብ ነፃ ካልወጣ ምኑን ነፃ ወጣ? ከጥላቻና ‹‹እኔ የምለው ብቻ ትክክል ነው›› አስተሳሰብ ነፃ መውጣት ዋና ነው፡፡

በእውነት ገና ብዙ አልገባንም … የመንፈስና የአእምሮ ነፃነትን አልተቀዳጀንም፤ … የስሜታችን ባሪያዎች ስለሆንን ሰዎችን ነፃ ልናወጣ ቀርቶ ራሳችንንም ነፃ ሳንወጣ ዘመናችንን ጨርሰን ወደ መቃብር እንወርዳለን … የመሬት ሆድ ውስጥ ገብተን ለዘላለም ፀጥ ከማለታችን በፊት ሰውን መውደድ ሰላምና ፍቅርን መውደድ እንደሆነ በቅድሚያ እንወቅ፡፡ ፍቅርንና ሰላምን ካልሰበክን በስተቀር እንደለመድነው በማይጠቅም ደምሳሽ ጦርነት እርስ በርስ መጠፋፋት ብቻ ነው ዛሬም ያለን አማራጭ፡፡ የቱን እንምረጥ? … ሰላምን ፍቅርን ወይስ ጥላቻና ቂም በቀል የሚወልደውን እርስ በርስ መጠፋፋት? ህዝቦችን አንዱን ብሔር ካንዱ ኦሮሞን ከአማራ፣ ትግሬንም አማራንም ከኤርትራ፣ ወዘተ እርስ በርስ ጠላት እንዲሆኑ ማድረግ ከንቱነት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ‹‹በጥባጭ እያለ ማን ንጹህ ውሃ ይጠጣል›› እንደሚባለው አይነት ህይወት መኖር የለብንም፡፡ ይህ ትውልድ በቅን አስተሳሰብ፣ በሰላም ወዳድነት፣ በጸዳ አእምሮ (Corruption Free Mind) እንጂ በጉልበት (በጦርነት) የማያስብ መሆን አለበት፡፡

ብናስተውል መልካም ይሆናል … አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በሰራነው በደል ቀርቶ በተናገርንበት ነገር ሁሉ የምንጠየቅበት ዘመን ነው፡፡ ሰው ከትግሬም፣ ከኤርትራም፣ ከአማራም፣ ከኦሮሞም ከየትም ይወለድ አመለካከት ባግባቡ በሰለጠነ መንገድ መተቸት አለበት፡፡ ‹‹ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም ለመጪው ይታሰብበታል እንጂ›› እንዲሉ መጭውን ዘመን እያሰብን እርስ በርስ መልካም እናደርግ፡፡ ሁሉም ህዝቦች በሰላምና በብልጽግና ይኖሩ ዘንድ እንስራ አንዱን አጥፍቶ ሌላውን ማልማት በግሎባላይዜሽን ዘመን አይቻልምና፡፡ g

ተከታዩን ፅሁፍ በቀጣዩ ዕትም ይጠብቁ >>>

24 25

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ስኬትስኬት

ኅብረ-ብዕር፡- በቅድሚያ ለቃለ መጠይቁ ፈቃኛ ሆነህ ውድ ጊዜህን ስለሰጠኸን ከልብ እናመሰግናለን።

ብሩክ፡- እኔም አመሰግናለሁ።

ከልጅነትህ እንጀምርና ብሩክ የትና መቼ ተወለደ?

የተወለደኩት አዲስ አበባ ጋንዲ ሆስፒታል ነው (ሳቅ)። 17ኛ ዓመቴን ሳከብር እንደውም ጋንዲ ሆስፒታል ሄጄ ነበር ያከበርኩት። የተወለድኩት በ1974 ዓ/ም ነው። በአጠቃላይ ተወልጄ ያደግኩት አዲሱ ገበያ በመባል በሚታወቀው ሰፈር ነው። አሁንም አልለቀኩትም እዛው ነኝ ( ሳቅ)።

ብሩክ እስቲ ስለቤተሰብህ ንገረን?ቤተሰቤ በኑሮ ደረጃ ደህና የሚባል ነበር። አባቴ የራሱ የሆነ የታይፕ ትምህርት ቤት ነበረው። ት/ቤቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ መኪና ፅህፈት ት/ቤት ይባል ነበር። አባቴ ለ30 ዓመታት ያህል ታይፕ አስተምረዋል። ታዲያ ብዙ ፀሐፊዎች ማፍራት ችሏል። የአስር ዓመት ልጅ እያለሁ አብሬው እሰራ ነበር። እናቴ የቤት እመቤት ናት። ልጆች ስድስት ስንሆን እኔ ደግሞ የመጨረሻ ልጅ ነኝ። አራት ወንድሞች እና አንድ እህት ነው ያለኝ፡። ትልቅ ቤተሰብ ነው የነበረን። እናቴና አባቴ አሁን በህይወት የሉም።

በቅርብ ከሚያውቁህ ሰዎች እነደሰማሁት ልጅ እያለህ አልቃሻ ነበርክ ይባላል። እውነት ነው?

አዎ፤ እናቴ የስለት ልጅ ነህ ትለኝ ነበር። ታላላቆቼ እምብዛም ከስር ከስሯ ውር-ውር አይሉም ነበርና “ከስሬ የማይጠፋ ልጅ ስጠኝ” በማለት ተስላ ነበር አሉ። ታድያ ስለቷ ተሳክቶላት ከስሯ አልወጣ እያልኩ ቀሚሷን ይዤ ነበር የምከተላት። ቅፅል ስሜ “ጅራት” ነበር (ሳቅ)። አንድ ጊዜ ልብሷን ይዤ ስከተላት ሳላይ የወጥ ድስት ውስጥ ወድቄባት ከእዛ አውጥታ ወደ ሊጥ ባልዲ ውስጥ ከታኛለች። እድለኛ ሆኜ ብዙ አልተጐዳሁም።

ትምህርት ላይ እንዴት ነበርክ?የሚገርምሽ ድሮ “ቤተልሔም” የሚባል የህዝብ ት/ቤት ነበር። በጣም የሚወደድ ስለነበር እዛ ት/ቤት የሚገባው በዕጣ ነበር። ታዲያ አባቴ “ቤተልሔም” ትምህርት ቤት ካልገባ በማለቱ ሁለት ዓመት ያለ ትምህርት ተቀምጫለሁ። ሁለቴ እጣው አልወጣልኝም

በሦስተኛ ተሳክቶልኝ እስከ 8ተኛ እዛው ተማርኩ። አሞኝ እስከ አቋረጥኩበት ጊዜ ደግሞ ዘጠነኛ ክፍል “የካቲት አስራ ሁለት” ወይም “መነን” ነው የተማርኩት።

ዘጠነኛ ክፍል እያለህ ነው ህመሙ የጀመረህ ማለት ነው?

አይደለም፡፡ ህመሙ የጀመረኝ በ12 ዓመቴ ነው። በሽታው የ ማ ይ ታ ወ ቅ በ መ ሆ ኑ መድሃኒት አላገኘሁም። “ብርድ ነው፣ ነርቭ ነው፣ . . .” እየተባልኩ ማስታገሻ እየተሰጠኝ ህመሙ ግን እየባሰብኝ ሄደ። ዘጠነኛ ክፍል ሁለተኛ ሴሚስተር ልጀምር ስል የቀኝ እግሬን አመመኝ። ከ ዛ ጨ ር ሶ መራ መ ድ አቃተኝ። ያኔ 17 ዓመቴ ነበር። ከዛ እየቀጠለ ሁለቱም እግሬ፣ ቀጥሎ የጀርባ አጥንቴ እስከ አንገቴ ድረስ አጥንቶቼ መተጣጠፍ አቃታቸው።

የበሽታውን ስም አሁንም አላወከውም?ካመመኝ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ነው ስሙን ራሱ ያወቅኩት። Achilosing Spendal-ity (አቺሎሲን ስፒንዳሊቲይ) ይባላል። የበሽታውን ምንነት ያሳወቀኝ ዶክተር ምንም ማድረግ እንደማይቻል ነግሮኝ ተስፋ ቆርጬ ነበር።

ሥዕል እንዴት ጀመርክ?ከ7 ዓመቴ ጀምሮ ሥዕል እስል ነበር። የአባቴ ጓደኞች ሰአሊ ነበሩ የነበሩ ሲሆን አባቴም ይሞካክር ነበር። አባቴም ለስዕል የቀረበ በመሆኑ ቀለሞች እና ወረቀቶች ያመጣልኝ ነበር። እናቴም በአንድ ወቅት እስራኤል ሃገር ሄዳ ስትመለስ የተለያዩ ስጦታዎችን ይዛልን መጣች። ሁሉም ሌላ ነገር ላይ ሲሻሙ እኔ የመሣያ ቀለም ነበር የደረሰኝ። እዛው ሽሚያው ሳያልቅ መሣል ጀመርኩ። መጀመሪያ የሳልኩት የኢየሱስን ምስል ነበር።

ካመመህም በኋላ ስዕል ትሰራ ነበር?ከታመምኩ በኋላ ያሳለፍኩት ጊዜ እጅግ ከባድ ነበር። ከመንቀሳቀስ በአንዴ ወደ አለመንቀሳቀስ

መምጣት እንዴት ይከብዳል መሰለሽ? ደግሞ ስለ አካል ጉዳተኛ እየሰማሁ ያደግኩት ነገር መልካም አይደለም። አካል ጉዳተኛ ተስፋ የሌለው፣ የማይጠቅም አድርጌ አስብ ስለነበር ተስፋ ቆርጬ ሥዕሌን መሳል አቆምኩ። ዘጠኝ ዓመት ዝም ብዬ መጨረሻዬን እጠብቅ ነበር፡፡ ቤተሰቤ እና ጓደኞቼ ፀበል እንድሄድ ያበረታቱኛል። ፀበል ለሰባት ወር ቆየሁ። በዚህ ጊዜ ብዙ ከእኔ የባሱ ሰዎችን ተመለከትኩ፤ የተለያዩ መፅሐፍትን ሳነብ መነሳሳት ፈጠረልኝ። እህቴን ወደቤት እንድትመልሰኝ ነገርኳት። ወደ ቤት እንደተመለስኩ መሣል ጀመርኩ። ይሁን እንጂ የሥዕል ሃሳቦች አልመጣልህ እያለኝ እቸገር ነበር።

“ብሩክ ጠንካራ ነው … ፅናቱ ይገርማል እንደውም ለሌሎች መፅናኛ ነህ” ይሉሃል፤ በዚሀ ጉዳይ ላይ ምን ትላለህ?

አዎ! እራሴን መሆን ከቻልኩ በኋላ ጠንክሬያለሁ፡፡ ብሩክ ብዙ እድሎች (የተከፈቱ በሮች) አሉት። የተዘጋው መንቀሳቀሱ ብቻ ነው፡፡ የሰው ልጅ ማንነቱ የሚታየው በጭንቅለቱ ከሆነ ብሩክ ያቃተው መንቀሳቀስ ብቻ ነው፡፡ ግን ማሰብ ይበልጣል ብዬ ነው የማምነው፡፡

“ብዙ የተከፈቱ በሮች እያሉ የምናስበው የተዘጋችውን አንዷን በር ብቻ ነው”

ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ

የዛሬው የህብረ-ብዕር እንግዳችን ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ ይባላል። ሰአሊ ብሩክ በብዙዎች ዘንድ በፅናቱ ምሳሌ መሆን የቻለ ወጣት ነው። የስዕል ስራዎቹም ድንቅና ተወዳጅ ናቸው። ለአምስት ጊዜ ያህል የስዕል ኤግዚቪሽን ማቅረብ ችሏል፡፡ ብሩክ ምንም እንኳን የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም፣ የገጠመውን የአካል ጉዳት አሸንፎ መግነን ችሏል። ሪፖርተራችን ኤደን ኡታላ አነጋገራዋለች።

26 27

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ስኬትስኬት

ታነባለህ?አዎ! አነባለሁ። የተለያዩ መፅሐፍት በተለይም የሰዎችን ግለ ታሪክ እና ስነ-ውበታዊ መፃህፍትን አነባለሁ። ኢንተርኔትም እጠቀማለሁ፡፡

የስዕል ኢግዚቢሽን አዘጋጀተህ ታውቃለህ?አዎ፤ አምስት ኢግዚቢሸኖችን አዘጋጅቻለሁ። የኢግዚቢሸኖቼ ተመልካቾች የሚሰጡኝ አስተያየቶች የሚገርሙ ነበሩ። የምጠቀማቸው ቁሳቁሦች በጣም ይገርማቸዋል። ለምሳሌ የመጀመሪያውን ኤግዚቢሽኔን ያቀረብኩት ከተሰባበሩ መስታወቶች የተሰሩ አርቶችን ነበር። በዚህ ፕሮግራም ላይ እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ተገኝተው ነበር። ብዙ አስተያየት ሰጥተውኛል። የሚገርመው ሁለተኛውንም ኤግዚቢሽኔንም አይተውልኛል። በጣም አስደስተውኛል። ሰው በእኔ ስራ በጣም ደስተኛ ነው። በቅርቡ ደግሞ በቾክ የሰራዋቸውን ነበር ያቀረብኩት።s ይህ ሰራዬ አስተማሪዎችን የሚወክል ነው።s

አንተ የምትሠራቸው ሥዕሎች ምን አይነት ናቸው ?

ሪሊፍ፣ አብስትራክት፣ ኢንስታሌሽን (ኮልኮሌ) እና ቅርፃ ቅርፅ ነው የምሰራው፡፡

ሥዕሎችህን መሸጥ እንደማትፈልግ አውቅ ነበር። አሁን መሸጥ ጀምረሀል?

አዎ፡፡ በስራዬ ዙሪያ 3 ዕቅዶች ነበሩኝ፡፡ እቅድ አንድ ሙዚየም ማስቀመጥ እና ገቢ ማግኘት፣ ሁለተኛው እቅዴ በውሰት በመስጠት ገቢ ማግኘት ሲሆን ሶስተኛው እቅዴ በመሸጥ ገቢ ማግኘት ነበር። ሁለቱ አልሆኑልኝም። የተሳካልኝ ሶስተኛው ነው። በዚሀ መሰረተ አሁን ስራዎቼን እየሸጥኩ አገኛለሁ። ደግሞም ስራዬ የሚቀጥል ስለሚሆን ማስቀመጫ ቦታ እቸገራለሁ። በዚህ መሀል ስራዬ ሊጐዳብኝም ይችላል። በዚህ ምክንያት ቀደሞ የነበረኝን ያለመሸጥ ሀሳቤን ልቀይር ችያለሁ።

በቅርቡ ህክምና ጀምረሀል … እንዴት ነው መላ ያለ ይመስልሀል? አሁን ለውጥ አለህ?

አዎ ህክምና ጀምሬያለሁ። እስከ አሁን አንዴ ኦፕራሲዮን ተደርጌያለሁ። እግዚአብሄር ይመስገን በፊት መቀመጥ አልችልም ነበር፡፡ አሁን መቀመጥ እችላለሁ ፡፡ ነገር ግን አሁንም ሶስት ኦፕሬሽን ይቀረኛል፡፡ አሁን መራመድ ብችልም እግሬን ማጠፍ አልችልም፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ጉልበቴን እሰራለሁ፤ ጉልበቴ ከተሰራ በኋላ ደረጃ መውጣትም እጀምራለሁ።

እጅግ መልካም ዜና ነው ብሩክ እንኳን ደስ ያለህ፡፡

አመሰግናለሁ፡፡

የህክምናህን ወጪ ማን ነው የሚሽፍንልህ?በፊት ቤተሰቤ ነበር የሚያግዘኝ። አሁን ግን አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ባዘጋጀሁት

ኤግዚቢሽን ላይ ሥዕሎቼ በጨረታ ተሽጠው ባገኘሁት ገቢ ነው እየታከምኩ ያለሁት።

አንዱ ሥዕል እስከ ስንት ትሸጠልህ?(ሳቅ…) ከፍተኛው 80,000 ብር ዝቅተኛው ደግሞ 40,000 ብር ነበር የተሸጠው።

ሥዕሎችህ ምን ላይ ያተኩራሉ? ማለቴ የሚያስተላልፉት መልዕክት ይዘቱ ምንድነው?

እኔ ብዙ ግዜ የምሥለው ያለፍኩበትን የሕይወት፤ መንገዶቼን የሚገልፅ ነው። በእኔ ህይወት ውስጥ ደግሞ ብዙ ሰዎች አሉ … የኔን አይነት ታሪክ ያላቸው። በተለያየ መንገድ ፈተና የገጠማቸው። ያንን ግን አሸንፈው ወይም እየታገሉ የሚገኙ ማለት ነው።

እሺ ብሩክ ሰዎች ካንተ ህይወት ምን መማር አለባቸው ትላለህ?

እኔ የሚገርመኝ አብዛኛዎቻችን ያለንበትን ሁኔታ አንደወደውም። የማንወደውን ያለንበትን ሁኔታ ለመለወጥ ከመስራት ይልቅ መሸሽ እንመርጣለን። ብዙ የተከፈቱ በሮች እያሉ የምናስበው የተዘጋችውን አንዷን በር ብቻ ነው። የተሳካለት ሰው ማለት ተቸግሮ የማያውቅ ማለት አይደለም። ይልቁንም ችግሩን ተጋፍጦ ያሸነፈ ማለት ነው። ታዲያ ፈተና ሲበዛ የበለጠ መስራት እንጂ መሸነፍ … እጅ መስጠት አያስፈልግም። እኔ መፈጠሬን እወደዋለው። በ1974 ዓ/ም እግዚአብሔር እኔ እንድወለድ ሲያደርግ አላማ አለው ብዬ አምናለው። ስለዚህ ራሴን ሆኜ ሰርቼ ማለፍ እፈልጋለው።

ስለነበረን ቆይታ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ እኔም አመሰግናለው። እንደውም ከሥዕሌ ልበላችሁ።

28

ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

እግረኛው

ዛሬ እንኳ በሰላምታ ልጀምር እስኪ፤ “እንዴት ሰንብታችኋል ወዳጆቼ?” ስራዬ መጓዝ ተጉዞም ነገር መለቃቀምም አይደል?... ገና ማለዳው ላይ ከቤቴ

ወጥቼ ዋናው የመኪና መንገድ ላይ ስደርስ ባየሁት ነገር በጣም ነው የተገረምኩት፡፡ ምን መገረም ብቻ የጮሌው ጊዮርጊስን ያየሁት ነገር አስደነገጠኝም … አናደደኝም፡፡ ማን እንዳደረገው ባላውቅም የእግረኛው መንገድ ላይ ቆሻሻ ተከምሮ በእግሩ የሚጓዘው ሰው በመኪና መንገዱ ላይ ከተሽከርካሪ ጋር እየተጋፋ ይሄዳል፡፡ አሁን ይሄ ምን ይባላል? በአንድ በኩል ሽታው ለጤና ጠንቅ ነው፡፡ በሌላ በኩል ቆሻሻው የእግረኞችን መንገድ ዘግቶ ሰው በመኪና መንገድ ሲሄድ ለአደጋ ይጋለጣል፡፡ አሁን ይሄን ማሰብ ያቅታል? ከቤቴ እንደወጣሁ ያየሁት የቆሻሻ ክምር አንድ ነገር አስታወሰኝ፡፡ ከ3 ሣምንት በፊት አንድ የቅርብ ዘመዴን ልጠይቃት ወደምትኖርበት አፓርታማ ሄጄ ነበር፡፡ ታዲያ በአፓርታማው የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ሁለት ትላልቅ የቆሻሻ ገንዳዎች አሉ፡፡ እሷን ለመጠየቅ በሄድኩ ግዜ ገንዳዎቹ ሞልተው ቆሻሻው መሬት ላይ ሁሉ ተከምሮአል፡፡ በዛ ላይ ሽታው አይጣል ነው፡፡ ታዲያ ይችን ዘመዴን ‹‹እንደዚህ ክፉኛ እየሸተታችሁ እንዴት ትኖራላችሁ?›› ብዬ ስጠይቃት በሰለቸ ድምጿ ‹‹አዬ… ብላታ ለምደነዋል፡፡ ገንዳዎቹ ሞልተው መሬት ተከምሮ ሽታው ልባችንን ካጠፋው በኋላ ነው ማዘጋጃ ቤት መጥቶ የሚያነሳው … ብናመለክት ሰሚ አጣን … ብላታ የዚህን ጉዳይ ይተዉት›› አለችኝ፡፡ ደግሜ እንዳነሳላትም አልፈለገችም፡፡ አሁን ይህ በኔ ሰፈር መንገድ ላይ የተከመረውን ቆሻሻ ስመለከት መቼም አይነሳም በሚል ተስፋ ቆረጥኩ፡፡ ‹‹የጮሌው ጊዮርጊስን እላችኋለሁ መንገዱን በሙሉ ይሄንን ነገር ሳሰላስል ተጓዝኩት፤ ጤና ጣቢያ ተቋቋመ፣ ክትባት ተሰጠ፣ በሽታን ለመከላከል ዘመቻ ተጀመረ… ይሄ ሁሉ የመንግስት የመግለጫ ጋጋታ ምን ሊሰራ? ምነው ብላታ! … በሽታን ለማጥፋት እየሰራን ነው እያሉ ዋናውን የበሽታ

ምንጭ እንደመታሰቢያ ሃውልት መሃል መንገድ ተከምሮ ሲያዩት ዝም ማለታቸው ደነቀኝም … ገረመኝም››። ትልቁ መንግስት ትላልቅ ራዕዮች ይዞ እየሰራ እያለ በየመስተዳድሩ ያለው ትንንሹ መንግስት ግን እነዚህን እንኳን በቅጡ መስራት ሲያቅታቸው አሳዘነኝ። ይሄን እያሰላሰልኩ ሳላስበው ብዙ ተጓዝኩና አራት ኪሎ አካባቢ ስደርስ ቡና ልጠጣ ብዬ ወደ አንድ ካፌ ጐራ አልኩኝ፡፡ ወሬ ለመቃረም እንዲመቸኝ ብዬ ውጭ በረንዳ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ የጮሌው ጊዮርጊስ ይወደኝ የለ? … ከጐኔ የተቀመጡት የማላውቃቸው ሰዎች ከካፌው ፊት ለፊት ስለሚታየውና በጅምር ስለቆመው ፎቅ

የሞቀ ወሬ ይዘዋል፡፡ … ጠቆር፣ ወፈር ያለውና ሙሉ ልብስ ከነክራቫቱ የለበሰው ጐልማሳ ሰውዬ በእጁ ወደ ጅምሩ ፎቅ እያመለከተ ‹‹ይኸው ባንክ ወርሶት ከቆመ አምስት ዓመት አለፈው … ጉዳዩ ምን እንደሆነ አላውቅም ከጊዜ ብዛት የተገጠመው የመስኮት መስታወት ሁሉ እየተሰባበረ ነው›› ይላል። ትንሽ ከሳ ያለና ሸሚዝ ከጅንስ ጋር የለበሰው ጐልማሳ በበኩሉ ‹‹ምን ዋጋ አለው? ለከተማ ውበት ይሆናል ተብሎ የታሰበው ህንፃ ስራው ሳያልቅ ቆሞ እየፈረሰ የከተማው አስቀያሚ ገፅታ ሆኗል፡፡ መንግስት ግን ለምን አንድ ነገር አድርጐ በጅምር የቆሙ ህንፃዎችን ቶሎ እንዲያልቁ አያደርግም? … በከንቱ እየባከነ ያለው እኮ የሀገር ሀብት ነው›› … ብቻ እየተቀባበሉ በጅምር ስለቆሙት ህንፃዎች ያወራሉ፡፡ ሦስተኛው ሰውዬ በተራው የከተማው

ዋና የግንባታ ኃላፊ ይመስል አዲስ አበባ ውስጥ ሰፈር እየጠቀሰ የቆሙ ህንፃዎችን ብዛት ይቆጥራል፡፡ በዚህ ጊዜ ደንገጥ አልኩኝና ‹‹የጮሌው ጊዮርጊስ … ሰውየው ምን ነካው? የሚያወራው ስለፎቅ ነው ወይንስ ስለሃውልት?›› አልኩኝ … ግን ለራሴ በውስጤ ነው ያወራሁት፡፡ ነገሩን ሳስበው በጣም አስገረመኝ፡፡ ፎቆቹ በጅምር የቆሙበት የተለያየ ምክንያት ሊኖር ይችላል፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን ችግሩ ተፈትቶ ለምን አገልግሎት አይሰጡም ነው? መቸም እኔ ብላት ያየሁትን የሰማሁትን እንዲህ ሞጫጭሬ እወቁት! ብዬ ከመጮህና በጮሌው ጊዮርጊስ ስም ተማፅኜ ኧረ አርሙት ከማለት ባለፈ አቅምም ስልጣንም

የለኝም፡፡ ወደ አመሻሽ ላይ በመጣሁበት ሁኔታ ወደ ቤቴ አቅጣጫ ቀይሬ ስመለስ ሌላ ጉድ አየሁ፡፡ ለህንፃ ግንባታ ተብሎ በቀለም ተዥጐርጉሮ የታጠረው ቆርቆሮ ለእግረኛ ተብሎ የተሰራውንም መረማመጃ ወደ ውስጥ አጠቃሎታል፡፡ ከአጥሩ ውጭ ለህንፃው ግንባታ የሚያስፈልጉ አሸዋና ጠጠር ደግሞ በመኪናው መንገድ ላይ ተከምረው አደባባይ መስለዋል ‹‹የጉድ ያለህ!... ምነው ብላታ አሁንስ በዛ … የጮሌው ጊዮርጊስን ሃይ ባይ ያጣች ከተማ ሆናለች›› አልኩኝ። ደግሞም እውነቴን ነው፤

የእግረኛን መንገድ በአጥር ከልሎ ህዝቡ መሄጃ ሲያጣ የመኪናው መንገድ ላይ አሸዋና ጠጠር ተከምሮ መኪኖች እየተጨናነቁ አደጋ ሲፈጠር የከተማው አስተዳደር ዝምታ ይገርማል! እውነት እውነት እላችኋለሁ ቆሻሻው መሃል አደባባይ፣ አሸዋና ጠጠሩ መሃል አደባባይ ላይ ተከምረው … ህንፃዎች በጅምር ቆመው ሲታዩ ምን ይባላል? አይ አዲስ አበባ ጥንት የተሰሩልሽ ሀውልቶች እንዳይበቁ ቆሻሻውም፣ አሸዋና ጠጠሩም፣ ጅምር ህንፃውም ሀውልት ሆነው በየአደባባዩ መታየታቸው እንዴት ገፅታሽን ያበላሸው ይሆን? ወይ የሃውልት ብዛት እያልኩኝ ቤት ደረስኩኝ፡፡ ነገ በማለዳ ወደ መስተዳደሩ ሀላፊ ቢሮ ሄጄ ቅሬታዬን ዘርግፌ ለመናገር ወስኛለሁ። እንግዲህ ለዛሬ ይብቃኝ … ቸርም በጐም ሁኑልኝ፡፡ g

ወይ የሃውልት ብዛት!

ከብላታ

30 31

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

መልህቀ-ፖለቲካመልህቀ-ፖለቲካ

“40”አሳጋራ ክፍል ሁለት

በማግስቱ በማለዳ ተነስተን እንደተለመደው የመሬት ላይ አልጋችን የሆነውን ምንጣፍ አጣጥፈን ስልፍ በመያዝ ዝግጁነታችንን አረጋገጥን። በማስከተልም ራቅ ወዳለ አካባቢ ሄደን ተፀዳዳንና ወደ ሰንዓፈ

ሬስትራንት ሄደን ምግብ መመገብ ጀመርን። እዛው ምግብ ቤት ውስጥ እያለንም መሳርያ የታጠቁ ሁለት ታጋዮች ወደ ነበርበት ቦታ ይመጣሉ። ፋኑስ እንግዶች አስተዋወቀን። ፋኑስ ስራው የከተማ ውስጥ ታጋዮች (ምልምሎች) “ስርዒት” ተብሎ የሚታወቀውን የከተማ መረብ መከታተል ስለሆነ አለባበሱ ከእኛ ከአዲሶቹ ምልምሎች የተለየ ባለመሆኑ ወደኛ ከመጡ ሁለት የታጠቁ ታጋዮች ጋር በአለባበስ ፈጽሞ አይመሳሰልም። ፋኑስ ከእንግዶቹ ጋር ሲያስተዋውቀን እኛን ወደ ዘመቻ ጣቢያ (መዋፊሪ) ሊወሰዱን እንደመጡ ገልፆልናል። በመሆኑም ሁላችንም ሌላ አዲስ ጉጉት ስለፈጠረብን ቀኗ የተለየች ልዩ ቀን ሆናብናለች። ጉዛችን ከሰዓት በኋላ እንደሆነ ተገለፀለን።ግን የምንነሳበትን ትክክለኛ ሰዓት የሚያውቀው መሪው ብቻ ነው። ይህም አንዱ የጐሪላ ታክቲክ ነው። ማንኛውም የታጋዮች እንቅስቃሴ በከፍተኛ ምስጢርና የደህንነት እርምጃዎች የታጀበ ነው።

የሰንዓፈ ሬስቶራንትን ለመሰናበት የመጨረሻውን የምሳ ፕሮግራም አጠናቀቅን። እኛን የተቀላቀሉን ሁለቱ እንግዶች ሓርነትና ስራጅ ይባላሉ። መንትዬዎች ይመስላሉ። የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ ይመሳሰላል። ሓርነት ፀጉሩ ጀብጅብ ራስታ አይነት ነው። ከሰውነቱ ጋር የተጣበቀ ሸሚዝና አጭር ሱሪ ለብሷል። የያዘው መሳርያ ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የተሰራ ጋንዴ ነው። ያምርበታል። ስራጅ ጠቆር ያለ ሲሆን ሉጫ ፀጉር ያለው ጎፈሬ ነው። መልከመልካምና በጣም የተረጋጋ ወጣት ነው። ሸሚዝና ረዥም ሱሪ አድርጓል። የታጠቀው ካርባይን የሚባለውን የእሜሪካ ሰራሽ መሳርያ ነበር።

በድንገት እንድንሰለፍ ተነገረንና ተሰለፍን። መዘጋጀታችንን ለማረጋገጥ ሓርነት ጮክ ብሎ ጥያቄ አዘል በሆነ ሁኔታ “ዝግጁ?” አለን። “አዎ ዝግጁ!“ አልን በአንድ ድምፅ። ፋኑስ በነበሩት ሁለት ቀናት እነዚህ እነዚህን የመሰሉ ነገሮችን አስተምሮናል። ቀን በብርሀን የሚደረግ ጉዞ ስለሆነ ሳትጠጋጉ በመካከላችሁ ከ20 ሜትር በላይ በሆነ ርቀት መጓዝ አለባችሁ ተባልን። ይህ የሚደረገው ጠላት ከርቀት እንቅስቃሴያችን እንዳይለይ እና በድንገት የተኩስ እሩምታ ቢያደረግ እንኳን የሚያደርስብን ጉዳት አነስተኛ እንዲሆን እንደሚጠቅም ተነገረን። የእያንዳንዷ መመርያ ጥቅምና አላማዋን በተመለከተ ትምህርት እየተሰጠን ነን። አሁን ጉዞ ተጀመረ። መጀመርያ ሓርነት ብቻውን ተንቀሳቀሰ። ስራጅ ከኛ ጋር ቆሟል። ሓርነት ከ20-25 ሜትር ያህል ከራቀን በኋላ ከፊት የተሰለፍኩት እኔ ነበርኩኝ እና ስራጅ “ተነስ” ሳትጠጋው አሁን ያለውን ርቀት ጠብቀህ ተከተለው ብሎ አዘዘኝ። ተነሳሁኝ። ጉዞ ጀመርኩኝ። ከኋላዬ የነበረው ተከትሎኝ ሊመጣ ሲነሳ

ስራጅ “ቆይ” አለው። እኔም 20 ሜትር አካባቢ ከራቅኹኝ በኋላ የሚከተለው ሌላው ሰልፈኛ ጉዞ እንዲጀመር ተደርጐ ሁላችንም በዚህ መንገድ ተራርቀን ጉዞ ተጀመረ።

የሰልፉ ርዝመት እንደ ትምህርት ቤት ሰልፍ ተጠጋግተን ቢሆን ኖሮ ከ15 ሜትር የማይበልጥ ሲሆን አሁን ግን ተራርቀን በመጓዛችን እስከ 200 ሜትር ርዝመት ያለው ሰልፍ ሆነ። አንዱ ፈጠን ብሎ አንዱ ቀስ በማለቱ ምክንያት ተራርቆ የመጓዙ ስርዓት ሲበላሽ ከፊት ሓርነት ከኋላ ስራጅ መልዕክት ያስተላልፉና አንዱ ለአንዱ በመናገር በሰልፈኛው መካከል ይተላለፋል። “ተፈናተት” ሳትጠጋጉ ተራርቃችሁ ሰልፋችሁን አሳምሩ ለማለት አጭር የወታደራዊ ትዕዛዝ ቃል ነው።በተደጋጋሚ የሚተላለፍ መልዕክት ነው።

በዚህ መንገድ በውርጫማውና ነፋሻማ የሰንዓፈ አካባቢ ብዙም ሳንጓዝ የገደል አፋፍ ላይ ደረስን። መውረጃ የሌለው በሚመስለው ገደል ቁልቁል ተዳፋት ቀጭን የእግረኛና የእንስሳ መንገድ ይዘን ሰልፋችንን አሳምረን መውረድ ጀመርን።

ተዳፋቱ አንዴ እንኳን ለመቆም እረፍት የማይሰጥ ቁልቁል እንድትንደረደር የሚያደርግ ስለሆነ ከመሬት የስበት ሃይል ጋር እየታገልን ሳንቆምም ሳንወድቅም መጓዝን ተያያዝነው። ቁልቁለቱ መጨረሻ ያለው አይመስልም። ጨረሰን ስንል ትንሽ ትንፋሽ ሳይሰጠን እንደገና አዲስ የቁልቁለት መንገድ እንጀምራለን። በዚህ በዛሬው ጉዟችን አይን ሲታይ የፋኑስ የማታው ጉዞ ምን አላት? የሚያስብል ነበር። የዚህ መጨረሻው የማይታወቅ የቁልቁለትና ገደላማ ቦታ የሁለት ሰአት ጉዞ በኋላ አዲስ ምልምሎች ጉልበታችን አካባቢ የመዳከምና ወለም የማለት አዝማሚያ መፈጠር ጀመረ። የሰልፋችን የርቀት ስርዓቱም ወጣ ገባ መሆን ጀመረ። “አብሩኽ” ቁጢጥ ብላችሁ በያላችሁበት ቁጭ በሉ የሚል መልዕክት ከኋላ ከስራጅ ተላለፈ። መልዕክቱ በሰልፉ መበጣጠስ ምክንያት ፊት ወዳለነው ሊደርስ አልቻለም። ከፊትም ሓርነት “አብሩኽ” የሚል ተመሳሳይ መልዕክት አስተላለፈ። እኔም ተቀብዮ ወደ ኋላዬ ሳስተላልፍ ከኔ ቀጥለው ከተሰለፉት 3 ሰዎች በኋላ መልዕክቱ ሊቀጥል ባለመቻሉ ተመልሶ ተቋርጧል የሚል መልዕክት ከኋላዬ ካለው ሰው መጣ። እኔም ለሓርነት አስተላለፍኩ። ሓርነት ከፊት ወደ ኋላ መምጣት ጀመረ። እኔን አልፎኝ ተጉዞም ከእይታዬ ውጭ አቀበቱን ፉት ብሎት ወጣ። በግምት ከ20 ደቂቃ በኋላ ሓርነት ከፊት ስራጅ ከኋላ የተቋረጠውን ሰልፍ ያስተካከሉት ይመስላል። ሓርነት ወደላይ በወጣበት ፍጥነት ቁልቁለቱንም በፈጣን እርምጃ ተጉዞ ጊዜ ሳይወሰድበት ወደፊት ተመለሰ።

እንደገና በሰልፉ መሀል ሓርነት ተዘጋጅ የሚል መልዕክት አስተላለፈ። ተዘጋጅ፣ ተዘጋጅ፣ ተዘጋጅ… እያለ መልዕክቱ በሰልፉ ቅደም ተከተል መሰረት እስከ ስራጅ ደረሰ። ስራጅም “መንቀሳቀስ እንችላለን” የሚል መልዕክት አስተላለፈ። መልዕክቱ እኔጋ ደርሶ ለሓርነት ደረሰና “ተበገስ” የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ። ጉዞ

ሃይለየሱስ (ዳምቡሽ)ከደብረታቦር

ለማስታወስ ያህል በክፍል አንድ ላይ ጸሀፊው ታሪኩን ያቆመው ፋኑስ ለአዳር

ከመረጠላቸው እንግዳ ማረፊያ ቤት ውስጥ ገብተው ተሽከል ይዘው መተኛታቸውን

በመግለጽ ነበር።

32 33

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

መልህቀ-ፖለቲካመልህቀ-ፖለቲካ

እንደገና ተጀመረ። እኔም “ተበገስ” የሚለውን መልእክት ከኋላዬ ላለው አስተላልፊ መንቀሳቀስ ጀመርኩኝ። “ተበገስ” ማለት “ጉዞ ጀምር” ማለት ነው። እየተማርን ያለነው ትግርኛና ትግርኛም ያልሆኑ የጐሪላ ቋንቋ ናቸው። በቀላሉ መግባባት የሚያስችሉ አጭርና ግልጽ ቃላቶች ናቸው። የተበጣጠሰው ሰልፋችን ከተሰተካከለ በኋላ ቁልቁል መጓዛችንን ቀጠልን።

መንገዱ አያልቅም። መዳረሻውን ሳታውቅ ስትጓዝ ይርቅብሃል አይደል የሚባለው? የተያያዝነው መንገድ ግን የማናቀው መዳረሻ ብቻ በመሆኑ ሳይሆን የእውነትም ሩቅ ነው። ቁልቁለቱ ረጅም ነው። ቁልቁለት ሲባል ከላይ ከፒያሳ ወደ ለገሀር የቸርችል ጎዳናን መጓዝ አይነት ቁልቁልት አይደለም። ቁልቁለቱ ስትወርድ ከኋላህ የሚገፋህ ሃይል ያለ የሚመስል ወይም ከፊት ከእግርህ በታች ገደሉ ና እያለ የሚስብህ አይነት ቁልቁለት ነው። ቁልቁል እየወረድን በሄድን ቁጥር ሁለት ነገሮች እየተለዩ አየሁኝ። ቅዝቃዜው እየሸሸ ሙቀት እየጨመረ ነው። የአካባቢው እፅዋትም እንዲሁ እየቀነሰና አይነታቸውም እየተቀየረ ነው። ከደጋማው ወደ ቆላ ብቻ ሳይሆን ወደ ታላቁ የስምጥ ሸለቆ እየወረድን መሆኑ በግልፅ ያስታወቃል። ጉልበታችን እየከዳን መጣ። ሮጠን ቁልቁለቱን ወርደን ጨርስን ማየትን ተመኘሁ። ግን ብቻህን ያዋጣኛል የምትለውን ማድረግ የለም። ጐሪላነትት ሁሉ ነገር በቡድን አንድ ላይ መወጣትን ይጠይቃል። አንዱ አንዱን እንዲረዳ እንዲደግፍ ይጠበቅበታል።

ከሦስት ሰዓት ጉዞ በኋላም ቁልቁለቱ አላለቀም። የሚያልቅም አይመስልም። ፊት በመሆኔ የበለጠ መገንዘብ የምችለው የሓርነትን እንቅስቃሴ ነው። ይህ ጉዞ ለሱ ምኑም አይደለም። እኔና ከኋላዬ ያሉት የኔ ብጤዎች ጀሌዎች ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ ስላለን በዚህ ሰዓት የምናስበው አንድ እንደሚሆን ገመትኩኝ። በዚህ ሀሳብ ላይ እያለሁ አንድ ነገር ተፈጠረ። መውረጃ የሌለው ቦታ ላይ ደረስኩኝ። ከፊት ሓርነት ይህን ገደል አልፎት እየተጣደፈ ቁልቁል ጉዞውን ቀጥሏል፤ ቆምኩኝ። አተኩሬ ስመለከት ህፃን ሁኜ የምፈራውና በህልሜም ስቃዥ የሚያስፈራኝ ገደል አይነት ነው። ሓርነት ይህን እንዴት ወረደው አልኩኝ። ተራርቀን ስለሆነ የምንጓዘው እንዴት እንደወረደው ማየት አልቻልኩም። አሁንም ቆሚያለሁኝ። ከኋላዬ የነበረው ተከትሎኝ ደረሰብኝ። “ምነው?” አለኝ። “ገደል ነው። እንዴት እንደሚወረድ አልገባኝም” አልኩት። እሱም አየና “ሓርነት እንዴት ወረደው?” ብሎ ጠየቀኝ። “እኔ እንጃ” አልኩት። እግሬ በላብ ተጠመቀ። ሓርነት ዞር ብሎ ሲያየን እዛው ገደል የሆነብን መንገድ ላይ መቆማችንና ሁለት መሆናችን አይቶ “አይዟችሁ ቀስ ብላችሁ ውረዱ” እያለን በወረደው ፍጥነት ወደኛ ተመለሰ። እንዴት መወረድ እንዳለብን ታች ሆኖ ቢያስረዳንም የሚሞክር ታጣ።

ከኋላ የነበሩት እየደረሱብን አራት አምስት የምንሆን ገደሉ ገድቦን ቁመናል። ሓርነት ስለገባው ምንም ሞራላችንን ሳይነካ እኛ ገደል ያልነውን ከመቅፅበት ወጥቶት እኛ ወደ ቆምንበት ቦታ ወጣ። “ጦጣ ወይስ ሰው ነው?” አልኩኝ በውስጤ። እጄን በመያዝ አይዞህ እያለ እንድንወርድ ጋበዘኝ። በአንድ በኩል እልህ ይዞኝ በሌላ በኩል የምፈራውና የማልወደው ገደል መወረድ ገጥሞኝ እየተቀጠቀጥኩኝ ቁጭ ብዬ እየታከኩኝ መውረድ አይሉት መንከባለል ወረድኩኝ … ወይም አወረደኝ። እንደዚህ እያደረገ አንድ ባንድ አወረደን። አንዱ ካንዱ እያየ እያሻሻለ በትንሽ ድጋፍ መወረድ ጀመረ። ሓርነት አይደክመውም። ይወጣል።ይወርዳል። እንዲያውም ከነሙሉ ትጥቁ። ቀናሁኝ። ስልጠናዬን ጨርሼ እኔም እንደሓርነት የማይደክመው ብረት የምሆነው መቼ ነው ብዬ አስብኩኝ። መሰናክሉን አልፈን ሁላችንም እንደተሰባሰብን ጉዞዋችንን ቀጠልን።

አሁንም መንገዳችን ፈታኙ ቁልቁለት ነው። ቀኑ እያለቀ ምሽቱ ሊረከብ መሆኑን የሚያመላክተው እኛ ቁልቁል ወደ ምስራቅ ፀሀይ ደግሞ ወደ ምዕራብ እየቀረች ከጀርባችን ያለው ገደል ከልሏት እየሸሸችን እንደሆነ ይታየኛል። ቁልቀለቱም እያለቀ ይመስላል። የያዝነውን መንገድ በድንገት

ለቀን ወደ ግራ በኩል ታጠፍን። ከገደሉ በክረምት ወቅት በሚፈሱ ትናንሽ ሸንተረሮች ምክንያት

የተፈጠረች ውሃ የሌላት የወንዝ ቦይ ውስጥ ገባን። ከገደሉ የሚፈሰው ውሃ በፍጥነት አፈሩንና ድንጋዩን እየጠራረገ በሚሄድ ጎርፍ የተፈጠረ ስለሆነ ይመስለኛል የወንዙ ቦይ መልክ የሌለው ወጣ ገባ ያለ፤ አንዱ ቦታ አሸዋ ሌላኛው ጋር ደግሞ ከላይ እየተደረመሱ በሚመጡ ድብልብል ትላልቅ ድንጋዮች የተሞላ ነበር። በቁልቁለት መንገድ የተዳከመው ጉልበታችን ሌላ ፈተና ገጠመው። አንዴ አሸዋው ውስጥ ገባ ወጣ ማለት አንዴ ደግሞ በናዳው ተንከባለው የመጡት ድብልብል ድንጋዮች ላይ እየተሰቀልን መወረድ መውጣትም ነበረብን። በዚህ መንገድ ትንሽ ከተጓዝን በኋላ የወንዙ ቦይ እየተሻሻለ አሸዋውን ብቻ እየረገጥን መጓዛችንን ቀጠልን።

በዚህ መንገድ እየተጓዝን እያለን አቅጣጫው ከፊት ከመሆኑ በቀር ማን እንደሆነ የማይታይ አንድ ሰው “ቁም! ማን ነህ?” የሚል ድምጽ አሰማ። ሓርነት ወደ ኔ ተመልሶ “አብሩኽ” . . . ወደ ኋላ መልዕክት ተላላፈ። ሓርነት “ቁም” ብሎ ካዘዘን ሰው ጋር መልዕክት ተነጋገረና ቁጢጥ ብሎ ቁጭ አለ። ከአንድ አስር ደቂቃ በኋላ አንድ ሙሉ በሙሉ የታጠቀ ታጋይ ብቅ አለ። ከሓርነት ጋር ተሳሳሙ። ትንሽ እየተሳሳቁ ካወሩ በኋላ ሓርነት “ተበገስ” የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ። ተነስተን ጉዞ ጀመርን። ቁጥቋጦ የበዛበት ቦታ ላይ ደረሰን። አሁንም በቁጥቋጦው መሀል እየተሸለኮለክን ጉዟችን ቀጠልን። የቀን ብርሃን ለጨለማ ለማስረከብ የቀረው ጊዜ ትንሽ ደቂቃዎች መሆኑ ያስታውቃል። ጥቅጥቅ ያለው ቁጥቋጦ ሙሉ ብርሀን አያገኝም። ከእኛ ቀደም ብለው የተሰባሰቡ በርከት ያሉ ሰልጣኞች ወዳሉበት ስፍራ ደርሰናል። ቦታው አሳጋራ ይባላል። (ተሓህት “ደደቢት” ላይ ከተመሰረተች በኋላ ከምእራብ ወደ ምስራቅ ጫፍ በመሄድ “ዲማ”፣ “ወረዓትለ” እና “አሳጋራ” የተባሉ በደጋውና በአፋር ስምጥ ሸለቆ መሀከል የሚገኙ ቦታዎች ላይ “ቤዞች” መስርታ ነበር።)

የስምጥ ሸለቆው ጫፍ ላይ እንገኛለን። እረፍት እንድናደርግ ከተነገረን ከደቂቃዎች በኋላ ራት እንድንበላ ታዘዝን። የተቀበሉን ታጋዮች ሁሉም በፍቅር “እንኳን ደህና መጣችሁ” … “ደከማችሁ አይደል?” … “ትለምዱታላችሁ” አሉን። ሁሉም ታጋይ ሲያገኘን ከሰላምታ በኋላ የሚለው ይህን ተመሳሳይ ነገር ነበር። ከምግብ በላይ ያማረኝ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት ነበር። ይህ ምርጫ የኔ ብቻ አልነበረም … የሁላችን ነበር። የፈለግነውን መጠን ውሃ ባናገኝም ለሁላችንም በፕላስቲክ ኩባያ ውሃ ታድሎን ጠጣን። የራት ፕሮግራም አለቀ። ጨለማው ያዝ አደረገ።

ተሰለፉ ተባልን። “ደግሞ ወዴት ልንሄድ ነው?” አልኩኝ … በሃሳቤ። ደክሞኛል። ቁልቁለቱን ብቻ ለአራት ሰዓታት ያህል የተጓዘው ጉልበቴ ዝሏል። በዚህ ሰዓት ያማረኝ ጋደም ማለት … መተኛት ነው። ቢሆንም ለማንጠፍ ጉልበት ያለኝ አይመሰለኝም። ብቻ ባለሁበት ቦታ ላይ መጋደም አሰኝቶኛል። ይህ ስሜት የኔ ብቻ አልነበረም። በጉዞ ላይ ያለነው የሁላችንም ነው። ቢሆንም ምንም ማድረግ አይቻልም። ወታደራዊ ትዕዛዝ ነው። እየተንቀራፈፍን በዝግምታ እንደምንም ተነስተን ተሰለፈን። ቁጢጥ ብለን ለመቀመጥም አቅም አጣን። አዲስነታችንና እንግድነታችንን አይተው አንዳንዶቹ “አይዟችሁ” ይሉናል። አለመቆጣታቸውና ትዕግስታቸው ጥሩ ቢሆንም “አይዟችሁ” የሚለው ቃል ግን ወደ ሀይል ቁሳዊ አካል የሚቀይር ሞራል ግን አልነበረንም።

ከከተማና ከትምህርት ቤት … ከአባትና እናት እንክብካቤ ወጥቶ ከፍ ወዳለ የትግል ወኔና ወታደራዊ ዲስፕሊን በቀጥታ ገብቶ ራስህን ማዘጋጀትና ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ መሆኑ በተግባር እያየሁት ነው። “ድራር ለይቲ - ተካ ሴሮ” የሚል መልዕክት በዛ በጨለማ ተጠጋግተን በተሰለፍንበት መስመር ተላለፈ። “ድራር ለይቲ” በቀጥታ ወደ ትግርኛ ቢቀየር የሚኖረው ትርጉም የሌሊት ራት (ምግብ) ማለት ነው። በወታደራዊ ትርጉም ሌሊት የሚደረግ እንቅስቃሴ የይለፍ ቃል

ስለሚያሰጠይቅ የሚሰጥ ኮድ ነው። የዛሬ ሌሊት ድራር ለይቲ ተካ ሴሮ ነው። ሁለት ቃል መሆን አለበት። ማን ነህ? ቁም ስትባል ስምህን ከገለፅክ በኋላ ድራር ለይቲ ትጠየቃለህ። ያኔ አንተ ተጠያቂው “ተካ” ትላለህ። ጠያቄው ደግሞ “ሴሮ” ነኝ ብሎ እለፍ ይልሃል። ከተሳሳትክ አደጋ ላይ ትወድቃለህ። ይህ ሁሉ ያኔውኑ ቢነገረንም ደክሞኝ ስለነበረ በአጠቃላይ ካልሆነ በዝርዝር ያወቅሁትና የገባኝ በነገታው ጠይቄ ነበር። ተሰልፈን መጓዝ አይሉት መጓተት አይነት ጉዞ አድርገን ብዙ ሳንሄድ ተሸክላችን ቦታ ላይ ደርሰን ቦታ ቦታ ተመድቦልን ተኛን።

ዛሬ የገበሬ ቤት የለም። በርሃ ላይ ነን። የአፋር አካባቢ ስለሆነም ብርድ የሚባል የለም። በማታ የአፋር አካባቢ ደስ የሚል የአየር ሁኔታ አለው። ወዲያውኑ እንቅልፍ ወሰደኝ። ተኝቼ ወይስ ወድቄ እንደአድርኩኝ መለየት አልችልም። በጠዋት 12 ሰዓት ተነሱ ተባልን። የት እንዳለሁ የአወቅሁት ከእንቅልፍ ስባንን ነው። በጣም ደስ የሚል እንቅልፍና እረፍት አግኝቻለሁ። አእምሮዬም ተነቃቅቷል። ልነሳ ስል ግን እግሬ ተያይዟል። ት/ቤት ያለማሟቅያ ስንሮጥና እግር ኳስ ስንጫወት እንደሚይዘን አይነት “እስትራፖ” (የጡንቻ መሸማቀቅ) ይዞኛል።

ተነስተን ከተፀዳዳን በኋላ ለ30 ደቂቃ የሚሆን ሩጫ እንድንሮጥ ተደረገ። አዲስ ምልምሎች ናቸው ደክሟቸዋል ተብለን ሌሊት ዋርድያ (ጥበቃ) ተርታ ውስጥ አልተካተትንም። የስፖርት ፕሮግራሙም ቀለል ያለ ተደርጐልን የአካል እንቅስቃሴው አለቀ። ትላንት ምሽት ከጉዞ ስንገባ አቀባበል ወደ ተደረገልን ስፍራ ደርሰን በቡድን ቡድን ተለያይተን ቁርስ በላን።

ምግቡ ታጋዮች ራሳቸው ያዘጋጁት ቂጣና ሻይ ነበር። ቂጣው አልፎ አልፎ በጣም ያረረ ነው። ሻሂውም ጥቁር ነው። በሻይ ቅጠል የተፈላ ሳይሆን ስኳር አሳርሮ የተዘጋጀና በጣም ከልክ በላይ ስኳር ያለው ነው።ስትጠጣው ከንፈርህን የሚያጣብቅ ነው። የቆዩት ታጋዮች አጫጭደው ሲጨርሱት ትላንት የገባነው አዲሶቹ ታጋዮች ግን ነካ ነካ እያደረግን እንደነገሩ ጨረስነው። “አትበሉም እንዴ?” አሉን ሁሉም። “በላን” አልናቸው። “ምስ ደሞም እዮም” ተባባሉ እየተሳሳቁ። በታጋዮች ቋንቋ “ደማቸው እንዳለ ነው” ማለት ነው። የቤታቸው ደም ገና አልተቀየረም ያገኙትን መብላት እንደሁኔታው መኖር ገና እየተላመዱ ነው ማለት ነው። እኛም እንደናንተ የመጀመርያ አንድ ቀን ሁለት ቀን እንዲሁ ተቸግረን ነበርን አሉን። እኛም እርስ በርሳችን የትላንትና ከአራት ሰዓት በላይ የቁልቁለት መንገድ ጉዟችንና በተለይም የገደልዋን ነገር አንስተን አንዱ አንዱን እየተረበ መሳሳቅ ጀመርን። እዛ ለቆዩትም የሆነውን እያወራናቸው ተሳሳቅን። በአንዴ ተዋወቅን። በዚህ ሁኔታ እያለን ተዘጋጁ የሚል ትዕዛዝ መጣ። ቀጥሎም “ተሰለፉ” ተባልን። ተሰለፍን። ሁላችንም ዝግጁ መሆናችንንና ንብረቶችን በሙሉ መያዛችን ቁጥጥር ተደረገ። ንብረት የሚባለው የምግብ መሳርያ እቃዎቻችን እና በጐናችን የምናስረው “ኩሹኽ” ብቻ ናቸው። ዝግጁ መሆናችን ከተረጋገጠ በኋላ ጉዞ ጀመረን።

ጉዞው በቁጥቋጦ መሀል ስለሆነ በጣም ሳንራራቅ በቅርብ ርቀት ሁነን ነው የምንጓዘው። ፀሀይ ፍንጥቅጥቅ ብላ የወጣች ብትሆንም በቁጥቋጦ መሀል ሾልኮ ከሚመጣው ጨረር በስተቀር ሙቀትዋ አልተሰማንም። ጥቂት እንደተጓዝን አንድ ትልቅ ዛፍ ስር በሚገኝ ጥላ ላይ እንድቀመጥ ተደረገ። ሌሎቹም ቡድኖች በተመሳሳይ በሰልፍ እየመጡ ቦታ ቦታችንን ያዝን። የመጀመርያ ስብሰባ መሆኑ ነው።

ከአብዛኞቻችን በእድሜ ገፋ ያደረጉ ሁለት ታጋዮች ፊት ለፊታችን ቆሙ። የግራ እግራቸው ቀጥ ብሎ እንደቆመ ቀኝ እግራቸው ብድግ አድርገው መሬቱን ድምፅ በሚያሰማ አኳሃን መተው በተጠንቀቅ ቆም አሉ። ወታደራዊ ስነ ስርዓት ነው። እንድንቆም ሁላችን ታዘዝን። “ደው በል” ነው ትዕዛዙ። ቀጥሎም “ሰጥ በል” ተባልን። “ተጠንቀቅ” ማለት ነው። በወታደራዊ ቋንቋ ተጠንቀቅ ማለት ቀጥ ብለህ ቁም ማለት ነው።

ነባሮቹ ያደረጉትን ለማድረግ እያየን ልክ እንደእነሱ አደረግን። “ዝክረ ሰማእታት” አለ ጮክ ብሎ። ከሁለቱ አንዱ ለሰማእታት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት አደረግን። ተሓህት በዚህ ወቅት የነበሯትን ሰማእታት ታጋዮች በሙሉ በስማቸው ያውቋቸዋል። የት ቦታና እንዴት እንደተሰዋ ያውቃል። ትላንት ማታ ድራር ለይቲ ተብሎ ተካ ሴሮ የተባልነው ተካ የሚባል የተሰዋ ጓድ ለማስታወስ ሲሆን የተሰዋበት ቦታም በአዲግራትና በአድዋ መከከል በሚገኝ ሴሮ በተባለ ተራራማ አካባቢ በተደረገ ውጊያ መሆኑን ለማስተዋስ ነው።

ከህሊና ፀሎቱ በኋላም እንድናሳርፍ ታዘን “ቁጭ” በሉ ተባልን። ቁጭ አልን። የውሎአችን ፕሮግራም ተነገረን። ጠዋት ወታደራዊ ትምህርት ከሰዓት በኋላ ደግሞ ፖለቲካዊ ትምህርት አንደሚሰጠን ተነገረን። የወታደራዊ አሰልጣኛችን ግርማይ ጃብር ይባላል። ግርማይ ጃብር ከኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅቶች ተቀላቅሎ የቆየና የጎሪላ ውጊያ ተሞክሮ ያገኘ ነው። አጭር መግለጫና ብዙ የተግባር ስልጠና ልምምድ ማድረግ ይወዳል። ድሮስ ቢሆን ውጊያ በተግባር የሚፈፀም እንጂ መቼ በወሬ ሆነና?! አሰጋራ ላይ ከወሰድኳቸው ስልጠናዎች የማልረሳው ቢኖር ደፈጣ ውጊያ ለምን እንደሚደረግና ምን አይነት የመሬት ገፅታ እንደሚመረጥ ያገኘሁት እውቀት ነው።

ግርማይ ጃብር ይህንን ሲያስተምረን በአሳጋራ ባሉ ኮረብታማ መሬቶች ላይ በተግባር ቦታ እየያዝና አጥቅተን ስናፈገፍግ … እያንዳንድዋን እንቅስቃሴያችንን እየተቆጣጠረ እርምት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሲያገኝ ያለመታክት ያሰለጥነን ነበር። ግርማይ ጃብር በስልጠና ወቅት ቀልድ አይወድም። ሁሉም ነገር በውጊያ ውስጥ እንዳለን ታሳቢ አድርገን ፈጥነን መሮጥ በሚያስፈልግበት ጊዜ እንድንፈጥን ተኝተህ እንደ እባብ በሆድህ እየተሳብክ መንቀሳቀስ በሚያስገድድበት ሁኔታም ማድረግ ያለብን መሆኑን አበክሮ በተደጋጋሚ ይገልፅልናል። ስንፍናም ካሳየን ወታደራዊ ቅጣት ይቀጣናል። ቀልድ የለም። “የዛሬ ድካምና ላብ ነገ ደምና ህይወት ታድናለች!” መፈክራችን ነበር።

የፖለቲካ ትምህርት አሰልጣኝ ገብረመስቀል ይባላል። በማሳጠርም ብዙዎች ገሬ ብለው ይጠሩታል። ገሬ በወቅቱ ፋሽን የነበረችውን የሌኒን ዓይነት ኮፍያ ያደርጋል። ሲያስተምር ጥሩ የቋንቋ ችሎታውን ተጥቅሞ አፍ ያስከፍታል።የገሬ ትምህርት በዋናነት የሚያጠነጥነው ገበሬውን ማክበር፣ መውደድ፣ ንብረቱን መንከባከብ እንዳለብን እያሳቀ ደጋግሞ ይነግረን ነበር። የገበሬን ቅል ውሃ ለመጠጣት ስንጠቀምበት ቢሰበር ቅል ምንም ዋጋ የላትም ብለን ወይም በወፍ ዘራሽ ራሱ የሚበቅል ነው ብለን ዝም ማለት አይገባም። ይቅርታ መጠየቅም ብቻ አይበቃም። መክፈል አለብን። ገበሬ ንብረቱን የሚነካበት፣ የሚያበላሽበት አይወድም።ሚስቱ ሹሩባ ተሰርታ አምራ ስናያት እንዳላየን መሆን ይጠበቅብናል። አለበለዚያ ገበሬው አንድ ምልክት ከታዘበ መሳርያ የታጠቅን ስለሆነ ዝም ቢልም በውስጡ እኛጋ እምነት አያሳድርም። ቂም ከያዘ አይለቅም። ገብረመስቀል መልእክቱን የሚያስተላልፈው ኪነጥበብ በተላበሰና ፈገግ እንድንል እያደረገ ነው። ገበሬውን ህዝባችንን ከጎናችን ማሰለፍ የምንችለው አሳምነን እና አሳምነን ብቻ እንደሆን ትኩረት ሰጥቶ አስተምሮናል። ገበሬው የትግላችን የጀርባ አጥንት በመሆኑ የትግላችን አሸናፊነት የሚወሰነው ገበሬውን ምን ያህል ከጎናችን ማሰለፍ ችለናል የሚለው ትልቅ ጉዳይ በተግባር ሲረጋገጥ ነው።

በዚህ መንገድ ለአንድ ሳምንት ቆይተናል። አሁንም ምግቡን አልለመድነውም። የጣሳ ቅቤ በሁሉም ምግብ ላይ ስለምንጠቀም የፕላስቲክ ኩባያ ተጠቅመን ውሃ ለመጠጣት ሽታው ሁሉ ያስቸግራል። ለቆዩት ግን ምንም አይላቸውም። የጎሪላ ነገር ሆኖ አሳጋራን ትተን ሌላ ቦታ ለመቀየር ተዘጋጁ የሚል ትእዛዝ ተላልፎልና። ትእዛዙን ምሳ እንደበላን ነበር የሰማንው። የአሳጋራን ቁጥቋጦችዋንና የዋርካው ትምህርት ቤታችንን ጥለን ጠቅልለን ለመውጣት ተዘጋጀን። g

35

የምንወግነው ለሀቅ ነው!

መልህቀ-ፖለቲካ

36 37

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ሙግትሙግት

መሳለሚያ አካባቢ የምትኖረው ታላቅ እህቴ እስከ የዛሬ 10 ዓመት ድረስ ባለትዳርና የ3 ልጆች እናት የነበረች ስትሆን በአሁኑ

ወቅት ግን በህይወት የቀሯትን ሁለት ልጆችዋን ለብቻዋ እያሳደገች ትገኛለች፡፡ የልጅነት ባለቤቷ የዛሬ ሁለት ዓመት በእግዜሩ በሽታ የሞተባት ሲሆን፣ የመጀመሪያ ልጇ ግን በጥይት አረር ከሞተ ይኸው አስር ዓመቱን ሊያስቆጥር ነው፡፡

ወቅቱን ወደ ኋላ ሄዳችሁ ቆጥራችሁት ከሆነ ምርጫ 97ትን ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ትርምስ ውድ ህይወታቸውን ካጡት የድሀ ልጆች አንዱ ነበር፤ የእህቴ ልጅ፡፡ የፖለቲካው ግለቱ በጣም አተኩሶ የነበረበት ወቅት ነበርና እሱም

እንደማንኛውም ወጣት በለውጡ ማዕበል አብሮ እየከነፈ ነበር፡፡ አቤት ለልደቱ አያሌው እና ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የነበረው ፍቅር! ልክ እንደ ደም ልገሳ እድሜም እየተቀነሰ የሚለገስ ቢሆን ኖሮ አይኑን ሳያሽ ጎምዶ እንደሚሰጣቸው አልጠራጠርም፡፡

እኔ ደግሞ የ “እዛ ትውልድ” (ማለትም የኢህአፓው ወቅት) ስሪት ነኝና ከእድሜዬም ሆነ ከተሞክሮዬ ያካበትኩትን ልምድ በማቃመስ ትንሽ ሰከን እንዲል እመክረው ነበር፡፡ “ተው ትንሽ ረጋ በል!... ሁሉም ነገር ውሸት ነው!” … በማለት የልምዴን ላካፍልህ ስለው “ወይ ፍንክች! በቃ ያበጠው ይፍንዳ!” ባይ ነበር…

ታዲያ እንደፈራሁት በዚያን በሁከቱ ሰሞን ተሲያት ላይ እህቴ ወደ እኔ ዘንድ ደውላ “እሪ!”

እያለች ጩኸቱን ታቀልጠዋለች … ኧረ ምንድነው ጉዳዩ? ብዬ ሰጠይቃት፣ ሳግ እየተናነቃት የልጇን ስም ትጠራልኛለች፡፡ ታዲያ እሱ ምን ሆነ? ስል “በግርግሩ ውስጥ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ተወስዷል” ስትለኝ ከፉኛ ደነገጠኩ … አዞረኝ…። እህቴ ወደ ጠራችው ሆስፒታል እየበረርኩ ስደርስ ማረፉ ተነግሯት ኖሮ ከጎረቤቶቿ ጋር ኡኡታውን ስታቀልጠው ደረስኩ…። ልጅ የሞተባትን እናት እንዴት ማፅናናት ይቻላል?! ያውም ከአጠገቧ ወጥቶ ድንገት በጥይት አረር ለሞተ ልጅ!

ብቻ … የማይቻል የለም ያ ቀን አልፎ ይኸው 10ኛ ዓመቱን ልንዘክረው ተቃርበናል፡፡ መጥፎ ዘመን … መጥፎ ወቅት! ሟቹ የእህቴ ልጅ “በቃ ያበጠው ይፈንዳ!” ይላት የነበረው እስከአሁን

ያበጠው ይፈንዳ?በህሊናዬ ታቃጭላለች፡፡ የሚያሳዝነው ብቻ ሳይሆን የሚቆጨው ጉዳይ ግን “ያበጠው ሲፈነዳ” የፍንዳታው ገፈት ቀማሽ ድሀዋ ወላጅ እናቱ እና ሁለት ታናናሽ እህቶቹ መሆናቸው ነው፡፡ ስለዘመነ ምርጫ 97 ወቅት ሲነገር እንደቀላል “192 ሰዎች ገደማ ሞተዋል” ሲባል ያንገበግበኛል … ምክንያቱም እኛ ቤት የሞተው ቁጥር ሳይሆን ስም ያለው … የሚዳሰስ ሰው ነውና! ልጅ ነው የሞተበትን!

“ወደ እዛ ወደ መጥፎ ዘመን ለምን ተመለስክ? ለምን አልሸር ያለውን ቁስል ትነካካዋለህ?” ለምትሉኝ አንባቢዎቼ እንዳስታውስ ያደረገኝ የያኔውን ክፉ ወቅት የሚያስታውሱኝ አንዳንድ ምልከቶች ስለታዩኝ ነው። ዘንድሮም አንዳንዶች በቅንነት ልበለው በጅልነት “ያበጠው ይፈንዳ!” ሲሉ ስሰማ ምስኪኑ የእህቴ ልጅ ፊቴ ላይ ድቅን … ድቅን ቢልብኝ ነው፡፡ ያበጠው ሲፈነዳ፣ የሚፈነዳው የእንቅስቃሴው መሪዎቹ ላይ ሳይሆን እንደ የእህቴ ልጅ ምስኪኑ ዜጋ ላይ መሆኑ ነው፡፡

ያ! ብላቴና … ያ! ትሁቱ የእህቴ ልጅ … እንደእዛ ይመካባቸው የነበሩት የቀድሞው የቅንጅት አመራሮች በቀብሩ ላይ እንኳን አልተገኙለትም፡፡ እድሜውን ከራሱ ላይ ቀንሶ ሊለግሳቸው እሰከመፍቀደ ያምናቸው የነበሩት አመራሮች፣ ሌላው ቢቀር ወደ መሣለሚያ ብቅ በማለት ምስኪኗን እናቱ “ነፍስ ይማር!” አላሏትም፡፡ ወቅቱ እብደት የነገሰበት እና መረጋጋት ያልሠፈነበት ስለነበር፣ “ለምን በትኩስ መጥተው አልጠየቁም” ብዬ አምርሬ አልተቀየምኳቸውም ነበር፡፡ ነገር ግን “እኛ አመፅ በመቀስቀሳችን ጥፋተኞች ነን” በማለት ለማረሚያ ቤት ይቅርታ ጠይቀው የወጡ ወቅት ግን የተወሰኑት እንኳን ድሃ እናቱን ሀዘን ይደርሷታል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ማንም ዝር ሳይል የልጇን ሰባት ዓመት በለቅሶ ዘከረችው። ያበጠው ሲፈነዳ፣ የፈነዳው እነ እህቴ ቤት እንጂ ዋነኞቹ አመራሮች ዘንድ አልነበረም፡፡

ይኸው እህቴ ልጇን ካጣች በኋላ ያኔ ይመካባቸው የነበሩት ፖለቲከኞች በይቅርታ ከማረሚያ ቤት ወጥተው ኑሮዋቸውን ሲያጣጥሙ ይታያሉ፡፡ ኢንጀነር ኃይሉ ሻውል “ላፍቶ ሞል” የተባለ ትልቅ የገበያ ማዕከል አስገንብተው ዛሬ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ሚሊየነር ሆነዋል፡፡ … ዶ/ር ብርሃኑ ነጋም ወደ ፔንሲልቪያ (አሜሪካ) አቅንተው የፈረንጅ ልጆችን እያስተማሩ ደመወዛቸውን በዶላር ያገኛሉ፡፡ አንድም ልጅ አልሞተባቸውም። … ልደቱ አያሌውም ቢሆን ወደ እንግሊዝ ሀገር በመሄድ የማስትሬት ዲግሪውን ጨርሶ ሀገሩ ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡ ሙሼ ሰሙም ቢሆን በዳሽን ባንክ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚሠራና ከውፍረቱ የተነሳ አንገቱን እንኳን አዙሮ ማየት የማይችል ሆኗል፡፡ …

እነ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያምም በእድሜ ላይ እድሜ ጨምረው ኑሮ ቀጥለዋል …. እነ አቶ አየለ ጫሜሶም የቅንጅትን ስሙን እና ምልክቱን ይዘው ነጋ ጠባ በቴሌቪዥን የምናያቸው ሆነዋል። ያ ምስኪኑ፣ ደሀው የእህቴ ልጅ ግን “ውጣና ታገል!” ተብሎ ሲነገረው እውነት መስሎት እንደ ብላቴናው ዳዊት ድንጋይ እና ወንጭፍ ይዞ ወጣ …። ዛሬ ላይ የሞቱን አስረኛ አመት ለመዘከር ደርሰናል፡፡

የዛሬው መጣጥፌ ዓላማ ከ10 ዓመት በፊት የነበረውን ሁኔታ አንስቼ ለመብከንከን ሳይሆን፣ “ከነበረው አሳዛኝ ታሪክ ምን እንማራለን? ምን አገኘን? ምንስ አጣን?” የሚለውን ለመመልከት ነው፡፡

በጀመሪያ ደረጃ አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ በየትኛውም መስፍረት ብጥብጥ ወይም አመፅ (አብዮት) መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ብዬ አላምንም፡፡ ከሀገራችንም ሆነ ከዓለም አቀፉ ተሞክሮ ግርግር እና ብጥብጥ መጨረሻቸው የንፁሃን ዜጎቸ ህይወት መጥፋት፣ የሃገር እድገት ማቆልቆል … ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ቆም ብለን የ1997ቱን ሁኔታ ስናስታውሰው ያ ዴሞክራሲያዊ ሂደት በብልሀት እና በማስተዋል ተመርቶ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ በሀገራችን ይኖር የነበረው የዲሞክራሲ ሁኔታ አሁን ከደረሰበት የላቀ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችል እነደነበር ይሰማናል፡፡

ፓርላማችን 99.6% በገዢው ፓርቲ ብቻ ከመያዝ ይልቅ ተቃዋሚዎች የሚመሩት ወይንም ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉበት ሁኔታ … ስልጣን የሚጋሩበት መሆን ይችል ነበር፡፡ እንደ ዘንድሮው ምርጫ የተቃዋሚዎች ትንፋሽ የማይሰማበት ከመሆን ይልቅ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ጎልተው የሚወጡበት ደማቅ የምርጫ ሂደት ይሆን ነበር፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድፍን ሀገሪቷን መቆጣጠር ባይችሉ እንኳን የተወሰኑ ክልሎችንና ትላልቅ ከተሞችን ማስተዳደር የሚያስችላቸው የህዝብ ውክልና ማግኘት በቻሉ ነበር፡፡ አበው ሲተርቱ “ብልጥ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል” ይላሉ፡፡ የእኛዎቹ ፖለቲከኞች ግን የተሰጣቸውን ስልጣን ተቀበለው ለቀጣዩ በጥበብ እና በትዕግስት ባለመመራታቸው፣ እጅ ውስጥ የገባውንም እድል አሳልፈው ሰጥተዋል። የሀገራችንም የፖለቲካ እድገት “ከርሞም ጥጃ” የሚሉት አይነት ሆነ ፡፡

እዚህ ላይ ገዢው ፓርቲ የሠራቸው እጅግ ብዙ ስህተቶች ሣይነሱ መታለፍ የለባቸውም፡፡ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መሽመድመድ አንዱ ኃላፊነት ሊወስድ የሚገባው ኢህአዴግ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ እንዲረዳ በማለት ለአበባ ኢንደስትሪው ሳይቀር ሚሊዮኖች ወጪ የሚያደርገው መንግስት ዲሞክራሲው እንዲስፋፋ እና እንዲጎለብት በማለት ለፖለቲካ ፓርቲዎች

የገንዘብ ድጎማ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር፡፡ መቼስ የፖለቲካ ስራ ለመስራት ገንዘብ ዋነኛው ነው ባይባልም፣ ወሳኝነቱ ግን አያጠያይቅም፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት (ኢህአዴግ አላልኩም) የፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ ምርጫ ሊካሄድ ሁለት ወራት ሲቀሩት ብቻ መልቀቅ ሳይሆን ከምርጫ ወቅት ውጪም ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ሊያመቻች ይገባል፡፡

ለኢህአዴግም ቢሆን 23 ዓመታት ስልጣን ላይ ቆይቶ ዘንድሮም ፓርላማው 99.6% በአባላቱ ታጨቆ ሲመለከት፣ በህዝብ ድምፅ ያገኘው በመሆኑ ባያፍርበትም እንኳን የሚያኮራው አለመሆኑ ግን ግልፅ ነው፡፡ ጣቱን ሁሌ ወደ ውጪ ከመቀሰር ይልቅ፣ “እኔስ ዲሞክራሲው እንዲጎለብት ምን አይነት አስተዋፅኦዎች አበርክቻለሁ?” ብሎ ራሱን መጠየቅ ይኖረበታል።

ለፖለቲካ ፓርቲዎቸ ከሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በፍትሀዊነት ሊያገለግሉ ይገባቸዋል፡፡ የኢህአዴግ ጉባዔዎችን ለቀናት… በስፋት የሚዘግበው የመንግስት ሬዲዮና ቴሌቪዥን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ስብሰባዎች በስፋት የሚዘግበው በመሀከላቸው መከፋፈል እና ድብድብ ሲከሰት ብቻ ነው፡፡ ይኼ አካሄድ እየዳኸ ያለውን ዴሞከራሲያችንን ሽባ የሚያደርግ ነው፡፡

የፋይናንስ ችግር የገጠማቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ወደ ዲያስፖራ ፊታቸውን እንዲያዞሩ የተገደዱበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ይሄኔ ፅንፈኛው ዲያስፖራ እኩይ መርዙን በዶላር ጠቅልሎ ያጎርሳቸዋል፡፡ በዚሀ ምክንያት ፖለቲካችን ከቤቱ ወጥቶ “ዱር አደር” እየሆነ ነው፡፡ የሀገራችንን ፖለቲካ ከፅንፈኛ ዲያስፖራ ተፅዕኖ ለመታደግና ወደ ትክክለኛ ሀዲዱ ለመመለስ ገዢው ፓርቲ ትልቅ ሃላፊነት አለበት፡፡ በሀገር ውስጥ ያሉት ህጋዊና ሠላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተዳከሙና በሞቱ ቁጥር ተጠቃሚ የሚሆኑት መሠረታቸውን ኤርትራ አድርገው አመፅ የሚያራግቡት እነ “ግንቦት 7” ናቸው፡፡ መንግስት የተለያዩ የኢኮኖሚው አንቀሳቃሽ ዘርፎችን እንደሚደጉመው ሁሉ፣ ዘንድሮም ዳዴ ከማለት ያልወጣውን ዲሞክራሲያችንን ሊያበረታታው ይገባል፡፡

ከፍ ሲል ወደ አነሳሁት ወደ መንደርደሪያ ሀሳቤ ስመለስ የትኛውም አይነት ሰበብ ወይንም ምክንያት የአመፅን አማራጭ ቅቡል አያደርገውም፡፡ ይህንን አስረግጬ እንድናገር የሚገፋፋኝ የ1997 ምርጫን ተከትሎ በነበረው ግርግር ቤተሰቤ ያጣው የአንድ አፍላ ወጣት ልጅ ህይወት ነው፡፡ እኛ ቤት የገባው መሪር ሀዘን ማንም ቤት እንዲገባ አልመኝም፡፡ ስለዚህም ደግሜ ደጋግሜ ስለሰላም፣ ስለመስከን

ከሳሙኤል አባይነህ

38 39

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

መዝገበ ወንጀልሙግት

እና ስለረመረጋጋት እሰብካለሁ፡፡ “ያበጠው ይፈንዳ!” የሚለው አባባል ዕውርና

ጨካኝ መሆኑን የተረዳሁት የእህቴን ልጅ በጥይት ያጣሁ ወቅት ነው፡፡ የያኔው ቁስል ከመጠገን ይልቅ እነዲያመረቅዝ የሚያደርገው ምክንያት የእኛውን ብላቴና አይነት ወጣቶችን “አይዟችሁ… አትፍሩ … ውጡ!” ይሏቸው የነበሩ ሰዎች ዛሬ ላይ የተመቸ ሕይወት ሲመሩ ስመለከት ነው፡፡ እንደውም አንዳንዶቹማ ዘንድሮ ላይ በድጋሚ የ ”አበጠው ይፈንዳ!” አይነት መልዕክት ሲያራግቡ ስመለከት ውስጤን ያመዋል፡፡ እነሱ አሳብጠው ሊያፈነዱት የሚሹት የአመፅ እሳት ሲቀጣጠል ነበልባሉ የሚፈጀው የእነሱን ልጆች ሳይሆኑ የእኛ የድሃ ልጆችን ነውና! ስለዚህም ዝም አልልም ብዬ ይህችን መጣጥፍ ለህዝቤ አነሆ ለማለት ተነሳሁ።

ከሀገራችንም ተሞክሮ እልፍ በማለት የአለማችንን ወጣ ገባ ብንዳስስም የምንማረው ተሞክሮ ከአመፅና ከአብዮት ዲሞክራሲ የማይወለድ መሆኑን ነው፡፡ የድፍን ዓለምን ቀልብ ወደ ሳበችው ወደ ሶሪያ ብንመለከት “ለውጥ” እና “ዲሞክራሲን” እናዋልዳለን በማለት የጎዳና አመፅን የመረጡት ኃይሎች ያተረፉት ነገር ቢኖር ሀገራቸውን ማፈራረስና እነ ISISን የመሠሉ አሸባሪዎች መፈንጫ ማድረግ ነው፡፡ ሶርያ ዛሬ ላይ ልጇች ት/ቤት የማይሄዱባት፣ በየትኛውም ቦታና ሰዓት ፈንጂ የሚፈነዳባት፣ ከሚልየን በላይ የሚቆጠሩ ዜጎቿ በጎረቤት ሀገራት በስደተኛ ካምፖች ውስጥ በድንኳን የሚኖሩባት፣ ቤተክርስቲያኖቿም ሆኑ መስጊዶቿ የፈራረሱባት እንደው በጠቅላላው ተስፋ ያጣች ምድር ሆናለች፡፡ አመፅ፤ እልቂት እና ውርደት እንጂ የናፈቀችውን ዲሞክራሲ አላዋለደላትም፡፡

እዚሁ ቅርባችን ያለችው ግብፅም በአመፁ ካገኘችው ይልቅ ያጣችው ይበልጣል፡፡ ዛሬም ሀገሪቷን እየመራት የሚገኘው የጄኔራል ልብሱን መኝታ ቤቱ ውስጥ አስቀምጦ ሳሎን ላይ ሱፍ ለብሶ የተቀመጠ ወታደር ነው፡፡ አክራሪው “የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት” እዚህም ሆነ እዚያ የንፁሀን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል፡፡ ሀገሪቷ በየዓመቱ በቱሪዝም ኢንደስትሪዋ ትዝቀው የነበረው ዶላር በብጥብጡ እና በአመፁ ሳብያ ከተቋረጠ ከራርሟል፡፡ አዎን ግብፅ ካገኘችው ይልቅ ያጣችው ሚዛኑን ደፍቷል፡፡

ከአረቡ ዓለም ወጣ በማለት ወደ ወደምስራቀ አወሮፓዋ ሀገር ዩክሬን ብመለከትንም ዲሞክራሲን ያዋልዳል የተባለው አመፅ የነበራትን ያሳጣት መሆኑነ እንታዘባለን፡፡ ዛሬ ላይ ዩክሬን “ክሪሚያ” የተባለውን ትልቁን ክልሏን ለራሽያ አስረክባ በቆዳ ስፋቷም ሆነ በሉዓላዊነቷ አንሳ ትገኛለች፡፡ ሌሎች ምስራቃዊ ክልሎቿም ካልተገነጠልነ አያሉ ነወ።

መጀመሪያ ላይ አመፅ በዋና ከተማዋ በኪየቭ ሲጀምር ምን ያህሉ የዩክሬን ዜጋ የመጨረሻው ውጤት እንዲህ አሳዛኝ ይሆናል ብሎ የገመት እንደነበረ አላውቀም፡፡ ነገር ግን አብላጫው

የዩክሬን ዜጋ የኪየቭ አብዮት ሀገሪቷን እንዲህ እንደሚበጣጥሳትና ሉዐላዊነቷን ለአውሮፓ ኅብረት እና ለራሺያ እንደሚያስረክብ ቢያውቁ ኖሮ ያንን መንገድ ይመርጡታል ብዬ አልገምትም፡፡ አብላጫው የዩክሬን ዜጋ ለአብዮቱ (አመጽ) ሲቀሰቅሱና ሲደግፉ ዲሞክራሲን ያዋልድልናል ብለው በማመን ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ቆም ብለው ሂሳባቸውን ሲያወራርዱ ግን ትልቁ ግዛታቸው የነበረችው ክሬሚያን ከማጣታቸው በተጨማሪ እነ “ሉሀንስክ”፣ “ዶኔትስክ” እና “ኦብላስትስ” የተባሉ ሠፋፊ ግዛቶቿን ልታጣ ጫፍ ላይ መደረሷን ይገነዘባሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ዛሬ ላይ ዩክሬን የወደፊት እጣ ፈንታዋ ላይ ለመወሰን ሳይቅር የአውሮፓ ህብረት ይሁንታን ለመጠየቅ ተገዳለች፡፡ በአመፅ አብዮቱ መንገድ ዩክሬን ከሠረች እንጂ አላተረፈችም፡፡

የአመፅን (የአብዮት) ውጤቶችን ለመገምገም ፊታችንን ወደ አፍሪካዋ ሊቢያ ስናዞርም የምናየው ተመሳሳይ እውነታ ነው፡፡ ሊቢያውያን ካተረፉት ይልቅ ያጡት በእጅጉ ሚዛን ይደፋል።

በግብጿ ታህሪር አደባባይ አብዮቱን ይመሩ የነበሩት ሴቶች ዛሬ ላይ ራዕያቸው ተጨናግፎ በየጎዳናው የአስገድዶ መደፈር ሠለባ መሆናቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይተርኩታል፡፡ የሮይተር ፋውንዴሽን ጥናት እንደሚያመላክተው ግብፅ በአረቡ አለም ለሴቶች ቁጥር አንድ ሲኦል እንደሆነች መስክሯል፡፡ ይህ ማለት የሴቶችን መብት ይረግጣል ከሚባለው ከሳዑዲ አረብያ በከፋ ሁኔታ! በቴሌቭዥን መስኮት ስንከታተል የነበረውን የግብፅ ታህሪር አደባባይ አብዮት እንቅስቃሴ ይመሩ የነበሩት ሴቶችን እንኳን አልታደጋቸውም፡፡ ምክንያቱም አመፅና አብዮት ይዞት ከተነሳው ዓላማ በቀላሉ አፈትልኮ ሊወጣ ይችላልና!

ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮዎች መለስ በማለት ወደ ሀገራችን ሁኔታም ስንመለከት በአመፅና በግርግር ተጠቃሚ የሚሆኑት እኩይ አላማቸውን መጠቀሚያ ለማድግ የሚፈልጉ ብቻ መሆናቸውን መረዳት አይከብድም ፡፡ በቅርቡ የአምቦ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች “የአዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ግዛቶች መስፋፋት እንቃወማለን” በማለት ባስነሱት ህግን ያልተከተሉ ግርግሮች አምቦ ምን አገኘች? ምንስ አጣች?

ህግን ያላማከለ ግርግር ተነስቶ ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸውን አጡ፣ ትላልቅ የንግድ ተቋማት ተዘረፉ፣ ባንክ ሳይቀር ተቃጠለ፣ ዜጎች ለፍተው እና ጥረው ያፈሩት ሀብት ወደመ፣ የከተማዋ ፍርድ ቤት ከነሙሉ ሰነዶቹ በእሳት ጋየ! ከእዚህ ሁሉ ሞት እና ውድመት በኋላ ሰከን ተብሎ በውይይት ሲፈተሽ የተናፈሰው ወሬ ውሃ የማይቋጥር ውሸት ሆኖ ተገኘ፡፡ የአምቦ ነዋሪዎችና የአምቦ ከተማ ግን በእጅጉ ከሰሩ። ገና ከመነሻው አጀንዳውን ይዘው የተነሱት ዋነኞቹ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ሣይቀሩ

ፍርድ ቤት ለማቃጠል እና ህይወት እንዲጠፋ አልመው የነበረ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን የአመፅ እንቅስቃሴ በተፈጥሮው በቀላሉ ሊጠለፍ የሚችል በመሆኑ እንቅስቃሴው ሲጀመር መጨረሻውን መገመት ይከብዳል፡፡ ለዚህም ነው የአመፅ ጥሪንና እንቅስቃሴን ልናወግዝና “እንቢየው” ልንል የሚገባን፡፡

ኢትዮጵያን በተመለከተ ደግሞ ብጥብጥና አመፅ እንዲነሳ የሚሹ ሀገሮች መኖራቸውን የማያውቅ ግለሰብ ያለ አይመስለኝም፡፡ በሀገራችን ግርግሩ ቢነሳ የኤርትራ መንግስት እንዴት ቤንዚን ሊያርከፈክፍበት እንደሚችል መገመቱ አይከብድም፡፡ መምጫዋ እንደ የጌታ ቀን የማትታወቀዋ ግብፅም ያንን አጋጣሚ በመጠቀም ምን ያክል መሠሪ ስራ ለመስራት እንደምትችል መገት አያዳግትም፡፡

ከሃይማኖት አክራሪዎች ጀምሮ ጠባብ ብሄረተኝነትን የሚያራግቡ ወገኖች ግርግሩን ወደ ከፋ እልቂት ሊያደርሱት እንደሚችሉም ለመገመት አዋቂ መጠየቅ አያሻም፡፡ እዚህች ሀገር ላይ የትኛውም አይነት ግርግር ቢከሰት አልሸባብ ምን ያክል ፈንጂዎችን እነደሚያሰርግና እንደሚያጠምድ፣ የስንት ንፁሀን ዜጎችን ደም እንደሚያጎርፍ ለመገመት ልዩ እውቀት የሚጠይቅ አይደለም።

እነዚህን አስፈሪ ሁኔታዎች በህሊናዬ ስስልና የዛሬ 10 ዓመት በሞት የተለየኝን የእህቴን ልጅ ሳስታውስ አመፅ፣ እልቂት፣ አብዮት የሚሏቸውን ነገሮች…. እጠየፋቸዋለሁ፡፡ አይደለም እንደዚህ በፅሁፍ ማቅረብ ይቅርና ጥሩንባ ይዘህ መሀል ጎዳና ላይ ስለአመፅ አስከፊነት ተናገር ቢሉኝ አደርገዋለው፡፡ ለሀገሬም ሆነ ለህዝቤ ያለኝ ፍቅር ግድ ይለኛልና… እኛ ቤት የገባው ሞት እናንተ ጋር እንዳይደርስ እፈልጋለሁና፡፡ ልክ እንደ የእኔ እህት የእናንተም እህቶች ልጃቸውን ቀብረው ነጠላ ከመዘቅዘቁ ይጠብቃችሁ።

ኑ ተነሱና በጋራ የአመፅ ጥሪዎችን እናውግዝ! ቤታችንን … ሀገራችንን ከእሳት እንታደግ! “ያበጠው ይፍንዳ!” የሚሉ ወገኖችን ስትሰሙ፣ “ያበጠው እንዲፈነዳ የምትመክሩት የድሃው ቤት ውስጥ ነው ወይንስ የአመፁ መሪዎች ቤት?” ብላችሁ ጠይቋቸው፡፡ ግብፆች፣ ሶርያዎች፣ ሊቢያዎች፣ ዩክሬኖች፣ ወይንም ደግሞ የአምቦ ነዋሪዎች ሣይቀር “ያበጠው ይፈንዳ!” በሚል በተቀሰቀሱት አመፅና ግርግር ተጠቀሙ? ወይንስ ከሠሩ?” ብላችሁ ጠይቁልኝ፡፡

እኔም ሆንኩኝ ቤተሰቤ የ ”ያበጠው ይፈንዳ!” አመለካከት ተጠቂ ነንና “ያበጠ አይፈንዳ!” ብዬ ማስተማር እወዳለሁ፡፡ የ “አበጠው ይፈንዳ!” መጨረሻው የንፁሀን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ እና ሀገርን ወደ ከፍተኛ ፍዳ ማጋፋት ስለሆነ “የአበጠው ይፈንዳ!” የሚለውን ወደ “የአበጠው አይፈንዳ!” ….. “ያበጠው በሰከነ ውይይት ይሟሽሽ” … “ያበጠው በሰከነ መንፈስ ይፈታ!” ወደሚል እንለውጠው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ g

40 41

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ህገኛህገኛ

ውድ አንባቢያን ባለፉት አራት የህብረ ብዕር መፅሄት እትሞች እየተማማርን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ቅፅ 01 ቁጥር 02 የህዳር

2007 እትም ላይ “የዜግነት ክብር” በሚል ርዕስ ያቀረብኩት ፅሁፍ ላይ በርካታ አንባብያን እጅግ ጠቃሚ አስተያየት በኢሜል አድራሻዬ አድርሰውኛል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ አንድ የመሰጠኝን አስተያየት ግን ለዛሬ ፅሁፌ መግብያነት ልጠቀምበት ወድጃለሁ፡፡ የፀሃፊው አስተያየት “ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለምን እንደ ዜጋ አልተቆጠሩም?” የሚል ተቆረቋሪነት የተንፀባረቀበት አስተያየት ነው፡፡ ለአንባቢዎች ያለኝን ክብር ለማሳየት ያኽል መልስ መስጠት አለብኝ ብዬ ስላመንኩ ዜግነት/ኢትዮጵያዊነት በትውልድ ቢሆንማ ኖሮ ጁቡቲና ኤርትራም እኮ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አገሮቹ እንደ አገር፣ ዜጎቻቸው እንደዜጋ ውልደታቸው ከኢትዮጵያ ነውና በማለት ለዛሬ እስኪ በመልካም አስተዳደር ሳንካና የአስተዳደርና ስነ ስርአት ህግ አለመኖር ጥቂት ልበላችሁ፡፡

ሕዝብ በመንግሥት ተቋማት መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና የሚገባውን አገልግሎት ሳይጉላላ እንዲያገኝ ይፈልጋል። በአሁኑ ጊዜ በመላ አገሪቱ የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩ ሁላችንንም ያግባባናል ብዬ አገምታለሁ፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግር ዋነኛ ጠንቅ የሆነው ሙስና መጠኑ ቢለያይም አነስተኛው የአስተዳደር እርከን ከሆነወ ቀበሌ ጀምሮ የፌዴራል መንግሥት መዋቅር ውስጥ ቤቱን ሰርቷል፡፡ አንድን አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጡ መመርያዎችና ደንቦች የሚፈጥሯቸውን ክፍተቶች በመጠቀም ባለጉዳዮችን በማጉላላት በሕገ ወጥ መንገድ መጠቀም፤ በመሬት አስተዳደር፣ በግንባታ ፈቃድ፣ በብቃት ማረጋገጫ፣ በንግድ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ አሠራሮች፣ ማስረጃ በማረጋገጥ፣ በኮንዶሚኒየም ቤቶች አሰጣጥ፣ መታወቂያ አሰጣጥ፣ መውጫና መግብያ ኬላዎች ላይ ባለ ፍተሻ፣ ጨረታዎች፣ ግዥ ወዘተ ተገልጋዩ ሕዝብ በሕግ የተከበረለት መብት ተጥሶ የሙሰኞች ሲሳይ እየሆነ ነው፡፡ አንገታቸውን ደፍተው የሚሠሩ ትጉሃን ሠራተኞችን የሚያሳቅቁ ድርጊቶች ይፈጸማሉ፡፡ ህዝባዊነትና አገራዊ ስሚት በርካሽ ጥቅም መለካት፣ የተሿሚዎች ብቃት ማነስ፣ የሕዝብ አገልጋይነት መንፈስ መኮስመን፣ ደንታ ቢስነትና በራስ ያለመተማመን የመሳሰሉት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚያሰፉ የውድቀት ሸለቆዎች ሲሆኑ፤ የ “አስተዳደር ሕግ” አለመኖሩ ግን ችግሩን በስርአት ለመዋጋት የሚደረገው ጥረት አልፈስፍሶታል፡፡ በመሆኑም በዛሬው ፅሁፌ በ “መልካም አስተዳደር” እና የ “አስተዳደር

ሕግ” መሃል ያለውን መስተጋብር አንስቼ “ለምን ይህ የአስተዳደር ህግ እንዲኖረን አልተፈለገም? ባለቤቱስ ማን ነው?” በሚሉት ጉዳዮቸ ላይ መሞገት አፈልጋለሁ፡፡

በየጊዜው የምናነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፈጣን፣ ተጨባጭና በስርአት የታገዘ ዕርምጃ ያስፈልገዋል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሰት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው “የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚን በልማታዊነት በመቀየር ላይ በተመሠረተ ትግል ነው” ብሏል፡፡ ውሳኔው ወደ ድርጊት የሚቀየርበት ህጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ያስፈልገዋል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ፣ ምንም እንኳ “ብቸኛ አማራጭ ነው” ባይባልም ወንጀል ነክ ላልሆኑ አስተዳደራዊ ሳንካዎች ራሱን የቻለ የአስተዳደርና ስነ ስርአት ህግ መኖር አጋዥ መፍትሄ ሊሆን ይችላል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ የመጡት የአስተዳደር አካላት ባቋቋሟቸው ሕጎችና በሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች መሰረት ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ ከስልጣናቸው በማለፍ የዜጎችን መብቶች እንዳይነኩ የተለያዩ የቁጥጥር ስርዓቶች በተለያዩ የህግ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በአጠቃላይ የቁጥጥር ስርዓቶቹ ውስጣዊና ውጫዊ በመባል በሁለት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ሲሆን የመጀመሪያው የአስተዳደር አካላቱ በራሳቸው የውስጥ አሰራር የሚያደርጉትን ቁጥጥር የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው የቁጥጥር ዓይነት ደግሞ በሕግ አውጭው ክፍል፣ በእንባ ጠባቂ ተቋም፣ ከመደበኛው የዳኝነት አካላት ውጭ ባሉ የአስተዳደር ፍርድ ቤቶች (Administra-tive Tribunals) እንዲሁም የአስተዳደር አካላት ውሳኔዎች በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚከለሱበትን ሁኔታ የሚያጠቃልል ነው፡፡

ዳይሲ የሚባል የእንግሊዝ ፀሐፊ የአስተዳደር ህግ “የመንግስት ባለስልጣናትን ወይም ኃላፊዎችን የህግ ኃላፊነታቸውን የሚወስን፣ ግለሰቦች ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ባላቸው ግንኙነት ግዴታቸውን የሚያስፈጽሙበትን ስርዓት የሚመለከት ነው” በማለት ይገልፀዋል፡፡ የአስተዳደር ህግ፣ የአስተዳደር አካላትን ተግባርና ስልጣን የሚቆጣጠር ህግ ነው፡፡ የመንግስት አስተዳደር ስራን የሚቆጣጠር የህግ ዘርፍም ነው፡፡ ግለሰቦች ከአስተዳደር አካላት ጋር ባለቸው ግንኙነት ያላቸውን መብትም ያመለክታል፡፡ በመሆኑም የአስተዳደር ህግ ዋና ዓለማ የአስተዳደር አካላትን ስልጣን መቆጣጠር ነው፡፡ የአስተዳደር ህግ ዜጎችን ከመንግስት ባለስልጣናት የማን አለብኝነት እርምጃ

ወይም ህገወጥ

ድ ር ጊ ት ይ ጠ ብ ቃ ል ፡

፡ የመንግስት ባለስልጣናት በግለሰቦች መብት ውስጥ ከህግ ውጭ ጣልቃ እንደይገቡ መጠበቁ የአስተዳደር ህግ ዋናኛ ትኩረት ነው:: በአጠቃላይ የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር ክፍሉ ያለ አግባብ ወይም ከህግ ውጭ በዜጎች መብት ውስጥ ጣልቃ ሲገባ፣ ግለሰቦች መብታቸውን የሚያስከብሩበትን ስርዓት በማስቀመጥ የግለሰቦች መብት እንዲከበር ያደርጋል ማለት ነው፡፡

በአለማችን ያሉት አገራት ከሞላ ጎደል ከወንጀል መለስ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ ራሱን የቻለ የአስተዳደርና ስነ ስርአት ህግ ይጠቀማሉ፡፡ አገራት እንደሚከተሉት የሕግ ስርዓት እና ውስጣዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች የአስተዳደር አካላትን ውሳኔዎች ሕጋዊነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ ስርዓቶችን ዘርግተዋል። የተዘረጉት ስርዓቶች የአንዱ ከሌላው የሚለይበት ባህሪ ቢኖረውም፤ በተለይ የአስተዳደር ውሳኔዎችን በአስተዳደራዊ ህግና ስርአት ቁጥጥር እነዲውሉ ተደርጓል፡፡ በዘመናችን በመንግስት አካላት መካከል አንዱ ሌላውን የመቆጣጠር (Check and Balance) አሰራር በተወሰነ ደረጃ በተለያዩ አገራት እየተሰራበት የሚገኝ ቢሆንም፣ የአስተዳደር ህግ የቁጥጥር ስርአት በሶስቱ የመንግስት አካላት መካከል የተደረገውን የስልጣን ክፍፍል በማያፋልስ መልክ ተፈጻሚ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ የመጣውን የመንግስት ተግባራት ለማከናወን በሕግ አውጭው አካል በሚወጡ ሕጎች የሚቋቋሙ የመንግስት አካላት በተቋቋሙበት ሕግ መሰረት መስራታቸው የሚረጋገጥበት የቁጥጥር ስርዓት በበቂ ሁኔታ ካልተዘረጋ የዜጎች መብት ከመጣሱም በላይ የሕብረተሰቡን ጥቅም ለማስጠበቅ የታቀዱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖሊቲካዊ ፖሊሲዎች አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ በዚሁ መሰረት የአስተዳደር አካላት በስልጣናቸው ልክ መስራታቸውንና የዜጎችን መብቶች አለመጣሳቸውን ለማረጋገጥ በውሳኔያቸው ሕጋዊነት ላይ ቁጥጥር ማድረጉ የአስተዳደር ሕግ ዋነኛ ጉዳይ ነው፡፡

“ህግ ይኖራል ተተክሎ ሥርዓት ይኖራል ተዛውሮ” ለዚህ ሲባልም የአንግሎ አሜሪካን የሕግ ስርዓት

አካል የሆነችውን ዩናይትድ ኪንግደም (UK) የአስተዳደር አካላት በሕግ ከተሰጣቸው ስልጣን ክልል ውጭ ወጥተው የግለሰቦችን መብት የሚጋፋ ውሳኔ እንዳይሰጡ ወይም በስልጣን ክልላቸው ውስጥ ብቻ የሚሰሩበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ በዩናይትድ ኪንግደም በተለያዩ ትሪቡናልስ፣ በፓርላማ ኮሚሽነሮች ወይም እንባ ጠባቂዎች (Parliamentary Commissioner/ Ombuds-men) እንዲሁም በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚደረግ የአስተዳደር ውሳኔ የሚከለሰበት የዳበረ አሰራር አላት፡፡ የአስተዳደር ትሪቡኖች፣ የአስተዳደር አካላት የሰጧቸውን ውሳኔዎች ፍሬ ነገር (Sub-stance and Merit) ጭምር በመመርመር ውሳኔ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ የአስተዳደር ትሪቡኖች ስለሚሰጡት ውሳኔ ምክንያት መስጠት እንዳለባቸው እ.ኤ.አ በ1992 በወጣው Tribu-nals and Inquiries Act ክፍል 10 ግልፅ ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡

በአስተዳደር አካላት እና በአስተዳደር ትሪቡናሎች በሚሰጡ ውሳኔዎች የዜጎች መብት እንዳይጣስ በመጠበቅ በዩናይትድ ኪንግደም ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኙ የዜጎችን ከበሬታ ያገኙ ተቋማት ናቸው፡፡

የኔዘርላንድን ልምድ ስናይ ደግሞ የአስተዳደር አካላት ከሚሰጡት ውሳኔ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ አቤቱታዎች የሚታዩበትን መስፈርቶች የሚመለከቱ መርሆዎችን ያካተተ አጠቃላይ የአስተዳደር ሕግ (General Administrative Law Act ወይም Algemene Wet Bestuursrecht) እ.ኤ.አ በ1994 አውጥታለች፡፡ በመሆኑም በዚህ አገር አጠቃላይ የአስተዳደር ሕግ መሰረት በአስተዳደር አካላት በተሰጠ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያላቸው ሰዎች በቅድሚያ በአስተዳደር አካላቱ ውስጥ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ጉዳያቸው በአስተዳደር አካሉ በድጋሚ እንዲታይ የመቃወሚያ ማስታወቂያ ስነስርዓትን (Notice of Objection Procedure) ከተጠቀሙ በኋላ በዚህ ደረጃ በተሰጠው ውሳኔ ካልተስማሙ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት የሚያቀርቡበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡

በፈረንሳይ የአስተዳደር አካላት የተሰጣቸውን ስልጣን በስራ ላይ በሚያውሉበት ወቅት ከሕግ ውጭ እንዳይሰሩ እና የዜጎችን መብት እንዳይጥሱ ለመቆጣጠር ከመደበኛ የዳኝነት አካላት ውጭ የሆኑ እራሳቸውን ችለው የተዋቀሩ የአስተዳደር ፍርድ ቤቶች ጭምር በማደራጀት ትታወቃለች፡፡ በዚህ ስርዓት የአስተዳደር አካላት በሰጧቸው ውሳኔዎች “መብቴ ተነክቷል” የሚሉ ሰዎች ወይም ቡድኖች በቅድሚያ በአስተዳደር አካላቱ ውስጥ ያሉትን መፍትሄዎች ካሟጠጡ በኋላ ለአስተዳደር ፍርድ ቤቶች አቤቱታቸውን የማቅረብ ዕድል አላቸው፡፡

በአስተዳደር አካላት በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመጀመሪያ የሚያዩት የአስተዳደር ትሪቡናሎች ናቸው፡፡ የአስተዳደር ትሪቡናልስ በሰጧቸው ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያላቸው ሰዎች አቤቱታቸውን ለአስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ለማቅረብ ይችላሉ፡፡ የአስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶቹ በአስተዳደር ትሪቡናሎች የተሰጡ ውሳኔዎችን ሙሉ ለሙሉ እንደገና በማየት መዳኘት ስልጣን አላቸው፡፡ የአስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በሚሠጡት ውሳኔ ያልተስማማ ወገን በአስተዳደር ፍርድ ቤቶቹ እርከን የመጨረሻ ወይም ከፍተኛ ወደ ሆነው ኮንሴዴታ አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል፡፡ ይህ በፈረንሳይ በአስተዳደር ጉዳይ የመጨረሻ የዳኝነት ስልጣን ያለው የአስተዳደር ዳኝነት አካል በይግባኝ ሰሚ የአስተዳደር ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ ወደ ማየት ሳይገባ ቅሬታ የቀረበበትን ውሳኔ የሚመረምርባቸውን አጠቃላይ መስፈርቶች ወይም መርሆዎች (Unwritten Gen-eral Principles of Law) ከረጅም ጊዜ ልምዱ በመነሳት አዳብሯል፡፡

በአገራችን ኢትዮጵያ አስፈላጊነቱ ባያከራክርም የአስተዳደርና ስነ ስርአት ህግ የለም፡፡ መርሁ ግን ህገ መንግስታዊ ነው፡፡ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ከሚመራባቸው ዋና ዋና መሠረታዊ መርሆች በሕገመንግስቱ አንቀፅ 12 የመንግሥት አሠራርና ተግባራት ለህዝብ ግልጽና የሚያስጠይቁ መሆን እንዳለባቸው ይደነግጋል። የኢፌዲሪ ሕገመንግስት ፌዴራላዊ የሆነ የአስተዳደር ሥርዓትን የሚመሠርት እንደመሆኑ መጠን በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት (በክልልና ፌደራል መንግስት) እንደየተጨባጭ ሁኔታቸው ሕግ የማውጣት፣ ህግ የማስፈፀም እንዲሁም ሕግ የመተርጎም ሥልጣናት አሏቸው። ነገር ግን የሁሉም እርከኖች የመንግሥት አሠራርና ተግባራት ለህዝብ ግልጽና የማያጠያይቁ መሆን አለባቸው፡፡ መንግስት የሚያወጣቸው ዕቅዶችም ሆኑ ፖሊሲዎች ዜጎችን ያሳተፉ መሆን ይገባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውም የአስተዳደር አካል ከተሰጠው የሥልጣን ገደብ የሚተላለፍ ከሆነ ወይም የተጣለበትን ኃላፊነትና ግዴታ የማይዋጣ ሆኖ ሲገኝ ተጠያቂ መሆኑን ሕገ መንግሥቱ በግልጽ የደነገገው በመሆኑ የሕገ-መንግሥቱ መሠረታዊ መለያ ከሆኑ ጉዳዮች አንደኛው ነው። ግን ምን ያደርጉታል … መርሁ መርህ ሆኖ ውሃ እንዲበላው ተፈረደበት እንጂ፡፡ ይህ መርህ ተግባራዊ ከሚሆንባቸው መደላድሎች አንዱ የአስተዳደር ሕግና ስነ ስርአት የለማ፡፡

በመልካም አስተዳደር ህዝቦች ምንም ልዩነት ሳይደረግባቸው ተሳትፎ እንዲኖራቸው የማድረግ መሰረት ነው፡፡ ሕዝቦች ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ ተሳታፊዎች መረጃ ማግኘትና ሀሳብን

በነፃ የመግለፅ እንዲሁም የመደራጀት መብትን መንግስት ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡ በመልካም አስተዳደር ግልፅነት የመርሁ አስኳል ነው፡፡ ግልፅነት፣ ማንኛውም ውሳኔና አፈፃፀም በግልፅ የተቀመጡ የህግ ስርአቶችንና ደንቦችን ተከትሎ መፈፀም ማለት ነው፡፡

ከሁሉም በላቀ ግን ማንኛውም የአስተዳደር አካል ከተሰጠው የሥልጣን ገደብ አልፎ ከሰራ ወይም ስልጣኑን ካባከነ ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ ተጠያቂነት የመልካም አስተዳደር መሰረታዊ መገለጫ ነው፡፡ የመንግስት መስሪያቤቶች ብቻ ሳይሆኑ በተቻለ መጠን የግል ሴክተሩ ውስጥ ያሉ አደረጃጀቶችም ለህዝቡና ለባለድርሻዎቻቸው ተጠያቂ መሆን አለባቸው፡፡ ይሁንና ተጠያቂነት ያለግልፅነትና ያለ ህግ የበላይነት ተግባራዊ ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ የሕግ የበላይነት አንዱ መሠረታዊ መገለጫ ባለሥልጣኖች እንደፈለጉት ያለ ገደብ የሚወስኑበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረግ የመወሰን ሥልጣናቸውን መገደብ ነው፡፡

ማንኛውም የሥልጣን አካል ወይም ባለስልጣን ለመወሰን ስልጣን ባለው ጉዳይ ላይ ሲወስን በውሣኔ አሰጣጡ ሂደት ሊከተላቸው የሚገቡ ስርዓቶች፣ ሊጥሳቸው የማይችሉ መሠረታዊ መብቶች አሉ፡፡ ስለሆነም የመወሰን ስልጣን ቢኖረውም በሚወስንበት ጊዜ ሊከበሩ የሚገባቸው የሥነ ሥርዓት ህጎችና ደንቦች ቀደም ብለው የተዘጋጁና ሁሉም ሰው የሚያውቀቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ እነዚህ ህጎች በግልጽነት ተግባራዊ መደረግ አለባቸው፡፡

Philip Hamburger የተባለ ፀሃፊ “Is Admin-istrative Law Unlawful?” በሚለው መፅሃፉ እንዳረጋገጠው ሕግ አስፈጻሚው የአስተዳደር ህግና ስርአት እንዲኖር አይፈልግም ብቻ ሳይሆን በቁጥጥር መልክ አጠቃላይ ስራየን እንደፈለግኩት ሊያሰራኝ አይችልም ብሎ ስለሚያምን ለተግባራዊነቱ ብዙም ትኩረት ላይሰጥ ይችላል፡፡ ምንም እንኳ የአስተዳደር ህግና ስርአት ለህግ አስፈፃሚው ጭምር የሚጠቅም አካላቱን የሚመለከትና አደረጃጀታቸው፣ ስልጣናቸውና ኃላፊነታቸውን የሚወስን ህግ በመሆኑ ስራቸው በስርአት እንዲመራ ማድረግ የሚያስችል ቢሆንም፡፡

ተጠያቂነት የሚኖርበት ስርአት ለመዘርጋት ደግሞ ጠንካራ የሆነ፣ በህግ የበላይነት የሚያምን፣ የላቀ ስነ-ምግባር ያለው ቁርጠኛ አመራር ወሳኝ የመሆኑ ያክል የአስተዳደር ህግና ስርአት መኖር ወንጀል ነክ ባልሆኑ የዜጎችን የመልካም አስተዳደር፣ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥና የፍትህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ያግዛል፡፡

ህግ ይኖራል ተተክሎ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ አይደል የአበው አባባል፡፡ቸር እንሰንበት፡፡ g

42 43

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

መዝገበ ወንጀልመዝገበ ወንጀል

አፈር በልታ ከሞት የተረፈች ነፍስ ደብረብርሃን ከተማ ለሥራ በሄድኩበት ወቅት መልከ መልካምና ቁመናው ያማረ ወጣት የፖሊስ አባል አገኘሁኝ። ከዚህ ወጣት የፖሊስ አባል ቢሮ ጎራ ብዬ እራሱን እንዲያስተዋውቀኝ ጠየኩት። እርሱም “ኢንስፔተር አካሉ ብርሃኑ እባላለሁ የደብረ ብርሃን ከተማ ፖሊስ

ወንጀል ምርመራ የሥራ ሂደት ባለቤት ነኝ” በሚል ትውውቅ የሄድኩበትን ሥራ ጀመረኩና የተለዩ የወንጀል ድርጊቶችንና ፖሊስም እነዚህን ወንጀሎች ለመግታትና ለመከላከል እያደረገ ያለውን ጥረት እያመጣ ያለውንም ውጤት የተወሰኑ የምርመራ መዝገቦችን አገላብጦ አስረዳኝ።

ሥራዬን እንደጨረስኩም የሚፈፀሙ ወንጀሎች ውስብስብነት አስገርሞኝ አንድ ጥያቄ አነሳሁለት እንዲህም አልኩት “በምርመራ ሥራ የማትረሳው ገጠመኝ አለ ወይ?” የኢንስፔክተር አካሉ መልስ “የወንጀል ድርጊት ውስብስብ ነው። መርማሪው ደግሞ በውስብስብ ወንጀሎች ስለሚጠመድ ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ግድ ይለዋል። የተሻገራቸውን ውስብስብ መንገዶች ደግሞ ብዙዎቹን ያስታውሳቸዋል። እኔም የማስታውሰውን ልነግርህ እችላለሁ” ብሎ ይህንን የወንጀል ድርጊት ገለፀልኝ።

የምንጃር ወረዳ ፖሊስ የሥራ ሂደት በነበረበት ወቅት በምንጃር ወረዳ አራርቲ ከተማ አንዲት /ስሟ አይገለፅም/ የደርግ ተፈናቃይ ወታደር አግብታ ስትኖር የ8 ወር ነብሰጡር መሆኗን ታበስረዋለች፡፡ ባለቤቷም ልጅ ወልዶ ለመሳም ካለው ጉጉት የተነሳ 9 ወር ደርሶ አዲስ የሚወለደው ሕፃን ናፈቀው፡፡ ይሁን እንጂ ዘጠኝ ወሩም አልደረሰ … ሕፃኑም በሰላም ወደዚች ዓለም አልመጣም። “ምች” በሚባል ሕመም በእናቱ ማህፀን ከስሞ ቀረ። አባት ደግሞ ይህንን አምኖ አልተቀበለም።

እንዲያውም ከሌላ የምትወልዳትን የ4 ዓመት ሕፃን ልጇን እንደሚበቀላት መዛት ጀመረ። የባለቤቷ ፀባይም ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መጣ። ሕፃኗንም ዓይንሽን ለአፈር አላት። ሲወጣ ሲገባ የሚለው ነገር ቢኖር “የእኔ ልጅ ሞቶ የአንቺ ልጅ አታድግም” ሆነ የንግግር መጀመሪያው።

ሕፃኗ ጡት አልጣለችም፤ የእናቷን ጡት ስትጠባ ከደረሰ ከእቅፏ ቀምቶ መሬት ላይ ይወረውራታል። በሕፃኗ ላይ ጡት ብቻ አይደለም ማዕቀብ የተጣለባት፤ ከምግብም ታቅባ በረሀብ እንድትሞት በእንጀራ አባት ተወስኖባታል። በእርሱ ፊት ጡትም ሆነ ምግብ ደፍሮ የሚሰጣት የለም። እናትም የእራሷን ሕይወት ለመታደግና በሰላም ለመኖር የሕፃኗን ግፍና በደል አምና ተቀብላለች። ሕፃኗም ከሰውነት ተራ ወጣች፣ ከሳች መነመነች፤ ሕይወቷም ያለው እናቷ በድብቅ በምታደርግላት ጉርሻና ቅምሻ ነው። ይህ ደግሞ ዘለቄታ ሊኖረው አልቻለም፡፡ እንዴት ብሎስ በአንድ ቤት ውስጥ ሆኖ በድብቅ ይኸን ማከናወን ይቻላል። የተደበቀ ነገር ደግሞ ሆን ብሎ ጎልቶ ይወጣል።

ከዕለታት አንድ ቀን እናት ልጇን ከጎኗ አስቀምጣ ምግብ ስታበላ የሕፃኗ የእንጀራ አባት ይደርሳል። በዚህን ጊዜ አለንጋ ሳያነሳ ቁንጥጫም ሳያስፈልገው ሦስተኛ እግር ሆኖ በሚያገለግለው ክራንች ይመታታል። ህፃኗም ተዝለፍልፋ ትወድቃለች። እናትም የባሏ ተባባሪ ሆና ጩኸት ሳታሰማ ፊቷ ላይ ተዝለፍልፋ የወደቀችውን ልጇን አንስታ ባሏንም አስከትላ ወደ አንድ ጫካ ታመራለች። ከጫካው እንደደረሱም አንድ የቀበሮ ጉድጓድ ስላገኙ ሁለት ሆነው የያዙትን አስክሬን ቀብረው ተመለሱ፡፡ ይኸን ሲፈጽሙ ከፈጣሪ በስተቀር ማንም አላየም፤ የሰማም የለም።

ድርጊቱ በተፈፀመ በሁለተኛው ቀን የሕፃኗ የክርስትና እናት በእንግድነት ይሄዳሉ። በቆይታቸውም ሕፃኗን ያጧታል። የተወሰነ ሰዓት ጠብቀው ሕፃኗ ያለመኖሯን ሲያረጋግጡ የሆዳቸውን በሆድ አድርገው ቤት ለእምቦሳ ብለው ከገቡበትን ቤት ደህና ሰንብቱ ብለው ተሰናብተው ወጡ። ያመሩት ግን ወደቤታቸው አይደለም፤ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንጂ። ፖሊስ ጣቢያ እንደደረሱም

ከዚያ በፊት በሕፃኗ ላይ ይደርስባት የነበረውን ስቃይ አስረድተው ከቤት ያለመኖሯ ሚስጢር ገልፀው ቀብረዋት ይሆናል የሚል ጥርጣሬያቸውን ለፖሊስ ጠቆሙ።

ፖሊስም ይህ ጥቆማ እንደደረሰው ይዋል ይደር ሳይል ጉዳዩን ለማጣራት ወደቦታው ሄደ። እናት የተባለችውን ግለሰብም በቁጥጥር ሥር አውሎ ለምርመራ ወደ ጣቢያ ወሰዳት። የሰጠችው መልስ ግን “እንዴት ልጄን እገድላታለሁ፣ በዚህስ ለምን እጠረጠራለሁ” በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ አበዛች። ለማሳደግ አቅም ስላጣሁ ናዝሬት ሰድጃታለሁ የሚል መልስ ለመርማሪ ፖሊሱ ቃሏን ሰጠች። ይኸን የማዘናጊያ ቃላት ግን የሰማት አልነበረም። በምን፣ በማን የሚሉ ጥያቄዎች ተከተሉ። ለነዚህም ጥያቄዎች አንዲት ዘመዷ አሳፍራ እንደላከቻት ተናገረች። ላከች ወደ ተባለችው ሰውም ፖሊስ የመኪናውን ሞተር አስነስቶ በረረ። ሴትዮዋንም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዟት መጣ ከሕፃኗ እናት ጋርም ፊት ለፊት አገናኛቸው። በእናቷ ፊትም ልጅቱን እንደምታውቃትና ተገቢውን እንክብካቤ ስለማታደርግላት በሀዘኔታ አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ እንደምትሰጣት፣ ናዝሬት ልካለች የተባለው ግን ውሸት እንደሆነ አስረዳች። የእርሷም ጥርጣሬ ከክርስትና እናቷ ጋር ተመሳሳይ ሆነ።

የሕፃኗ እናት ድፍረት አጣች አንደበቷም ታሰረ። ባለቤቴ የምትለው ሰውም ሚስቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መሆኗን ሲሰማ ከአካባቢው ተሰወረ። ወንጀሉ በተፈፀመ በሦስተኛው ቀን እናት ወድቆ መፈራገጥ መላላጥ እንደሆነ ስትረዳ ልጅዋ በእንጀራ አባቷ ተመትታ መሞቷንና ሰው ሳያይ ጫካ ወስደው በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ መቅበራቸውን ለፖሊስ አስረዳች። የተቀበረችበትን ቦታም መርታ አሳየች! ከቦታው ደርሰው የተዳፈነችበትን አፈር ሲቆፍሩ በውስጡ ሣር እና ቅጠል ተሞልቶ ተገኘ። ሣርና ቅጠሉም ከቀበሮው ጉድጓድ ውስጥ እንዲወጣ ተደረገ፡፡ ጉድጓዱ ጥልቀት ስለነበረው በውስጡ ያለውን ትዕይንት በቀላሉ ለመለየት አልተቻለም። በውስጡ የተባለው የሕፃን አስክሬን ይኑር ወይም ሌላ አውሬ ይኑር በውል አልታወቀም፡፡

በቦታው የደረሱት ፖሊሶች የተቻላቸውን ሁሉ አድርገው ምንም ሳይዙ ለመመለስ ሲያቅማሙ ከመካከላቸው አንደኛው ነገሩ አልዋጥለት አለ። የቀበሮውን ጉድጓድ መጨረሻ ለማግኘት በደረቱ እየተሳበ ተመልሶ ገባ በጨለማ ከተዋጠው ጉድጓድ ውስጥ ሙታለች ተብላ የተጣለችውን ሕፃንም በሕይወት አግኝቶ በገባበት መንገድ ተመልሶ ሕፃኗን ይዞ ወጣ። ሕፃኗም ከጉድጓዱ ወጥታ ንፁህ ዓየር ተቀብላ እራሷን እንድታውቅ ከተደረገ በኋላ እናቷን ስታይ ድርጊቱን ፈጽማብኛለች ብላ የማትገምተው ሕፃን በእናቷ አንገት ዘላ ተጠመጠመች። ፖሊስም ሁኔታው አረጋግቶ ወደ ሆስፒታል ሄዳ ስትመረመር ለሶስት ቀን ስትቆይ ውስጥ ያለውን መረሬ አፈር ስትበላ እንደቆየችና የተመገበችው አፈርም በሕክምና ጥበብ ከሆዷ ውስጥ ታጥቦ እንዲወጣ ተደረገ። የሕፃኗ ጤንነትም በአስተማማኝ ሁኔታ ተመለሰ። ለዚህ ወንጀል ተባባሪ የሆነችው እናትም ሕግ ፊት እንድትቀርብ ሆኖ ሕፃኗም አንዲት እናት ልጅም የለኝም መሀን ነኝ እንደወለድኳት ተንከባክቤ ላሳድጋት ብላ ስለጠየቀች እና ወላጅ እናትም ከዚህ በኋላ እኔ እናት ልሆናት አልችልም ሕፃኗም እያደገች ስትመጣ እናትነቴን አምና አትቀበልም እኔም እናቷ ልሆን አልችልም እርሷም ልጄ አይደለችም ብላ ለማሳደግ ላመለከተችው ግለሰብ በፊርማ አስረከበቻት።

የሕፃኗ ጉዳይ በዚህ ቢደመደምም ፖሊስ ግን አሁንም የዜጎችን ሕይወት ከሞት እየታደገ የሕዝቦችን ንብረትም ከውድመት እየጠበቀ ይገኛል። እነዚህን ፖሊሶቻችንን ልናመሰግናቸውና ልናከብራቸው ይገባል። g

ምንጭ ፖሊስና ርምጃው

በፈንታሁን ጌታሁን

44 45

የምንወግነው ለሀቅ ነው!ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ኅብረ-ስፖርትኅብረ-ስፖርት

የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ወር 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር መቼ እንደተጀመረ፣ በስንት ተሳታፊ ሀገሮች እንደተጀመረና ውድድሩ እንዴት የአሁን ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደቻለ በአጭር በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ እድገት ከ1950-1960

የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ሀሳብ የተጠነሰሰው እ.ኤ.አ በ1956 የፊፋ ሦስተኛ ጉባዔ ሊዝበን ላይ በተካሄደበትና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ምስረታ በረቀቀበት

ጊዜ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ አህጉራዊው ውድድር በፍጥነት እንዲካሄድ ዕቅድ ተይዞ እ.ኤ.አ ጥር 1957 የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በሱዳን ካርቱም እንዲዘጋጅ ተደረገ፡፡ በወቀቱ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መስራች በነበሩት ሀገሮች፤ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ግብፅና ደቡብ አፍሪካ መካከል ውድድሩ እንዲካሄድ ቢደረግም፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ሲከተለው በነበረው የአፓርታይድ ፖሊሲ ምክንያት ደቡበ አፈሪካ ከመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጪ ተደርጋለች፡፡ አንደኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርም ያለምንም ማጣሪያ ጨዋታ በሦስቱ መስራች ሀገሮች መካከል ተካሄደ፡፡ ኢትዮጵያም የደቡብ አፍሪካን ከውድድር መውጣት ተከትላ ለፍፃሜ ሱዳንን በግማሽ ፍፃሜ ካሸነፈችው ግብፅ ጋር ለመጫወት ቀረበች፡፡ በፍፃሜው ጨዋታም ግብፅ ኢትዮጵያን 4ለ0 አሸንፋ የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት መሆን ችላለች፡፡ አራቱም ጐሎች የተቆጠሩት በአንድ ተጨዋች ሲሆን፣ እሱም ግብፃዊው አጥቂ ሙሀመድ ዲያብ ኢል አታራ ነው፡፡

ከሁለት ዓመት በኋላ በ1959 ግብፅ ሁለተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ነበረች፡፡ በዚህኛውም ውድድር ሦስቱ ሀገሮች ብቻ ነበር የተሳተፉት፡፡ ግብፅም ኢትዮጵያን አሸንፋ ለፍፃሜ ጨዋታ የቀረበችውን ሱዳንን በማሸነፍ በሀገሯ ዋንጫውን ለሁለተኛ ጊዜ አንስታለች፡፡

ኢትዮጵያ የ1962ቱን ሦስተኛ የአፍሪካ ዋንጫ በአዲስ አበባ ማዘጋጀቷ ይታወሳል፡፡ እዚህኛው ውድድር ላይ 9 ተወዳዳሪ ሀገሮች እንዲሳተፉ ጥረት ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዘጠኙም ቀጥታ ወደ ዋናው ውድድር እንዲቀላቀሉ አልተደረገም፡፡ አዘጋጇ ኢትዮጵያና የሁለት ጊዜዋ ሻንፒዮናዋ ግብፅ ያለምንም ማጣሪያ ቀጥታ የአፍሪካን ዋንጫ ውድድር ሲቀላቀሉ፣ የተቀሩት ሰባት ሀገሮች የማጣሪያ ጨዋታ በመሀከላቸው አካሄዱና ከሰባቱ ሀገሮች ናይጄሪያና ቱኒዚያ የመጨረሻውን አራት ቡድን ተቀላቀሉ፡፡

ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ለፍፃሜ ብትደርስ ደፋ ቀና ያለችበትን ሦስተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ለግብፅ አሳልፋ አልሰጠችም፡፡ ኢትዮጵያ በሜዳዋና በደጋፊዋ ፊት ግብፅን በጭማሪ ደቂቃ 4 ለ2 አሸንፋ ዋንጫውን አንስታለች፡፡

የጋናውያን የበላይነት በ1960ዎቹጋና ወደ አፍሪካ እግር ኳስ መድረክ የመጣችው

የ1963ቱን አራተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ በመሆን ነው፡፡ በፍፃሜ ጨዋታም ሱዳንን 3ለ0 በማሸነፍ ሻንፒዮን መሆን ችላለች፡፡ ጋና በድጋሚ ከሁለት ዓመት በኋላ ከ1965 ብሔራዊ ቡድኗ ውስጥ ሁለት ተጫዋቾች ብቻ አካታ ቱኒዚያ ያዘጋጀችውን የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ በማንሳት የግብፅን ታሪክ መጋራት ችላለች፡፡ ጋና በ1968ቱና በ1970ው የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ ለፍፃሜ ደርሳ ዋንጫዎችን ሣታነሳ ቀርታለች፡፡

በ1968 ውድድር ወቅት የማጣሪያ ጨዋታ ካደረጉ 22 ቡድኖች 8 ቡድኖች እንዲያልፉና ውድድሩ ሰፋ እንዲል ተደረገ፡፡ ማጣሪያውን ያለፉት 8 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተደልድለው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ እንዲያደርጉና ከሁለቱ ምድብ አንደኛና ሁለተኛ የሆኑ ቡድኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተቀላቅለው ከዚያም ለፍፃሜ እንዲቀርቡ ስርዓት ተቀርጾ እስከ 1992 ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ከ1968ቱ ዝግጅት ጀምሮ ውድድሩ በቋሚነት በየሁለት ዓመቱ በሙሉ የአመተ ምህረት ቁጥር አቆጣጠር እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡ የአፍሪካው ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የቴሌቪዥን ሽፋን ያገኘው ሱዳን ባዘጋጀችው የ1970 ውድድር ላይ ነው፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተፎካካሪዎች በ1970ዎቹ ውስጥ

በ1970ዎቹ በተካሄዱት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውስጥ ስድስት የተለያዩ ሀገራት ዋንጫውን አንስተዋል፡፡ እነርሱም በቅደም ተከተል ሱዳን፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ዛየር፣ ሞሮኮ፣ ጋና እና ናይጄሪያ ናቸው፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍፃሜ ጨዋታ ዛየር እና ዛምቢያ በጭማሪም ደቂቃ ሳይቀር 2ለ2 ሆነው ባለመሸናነፋቸው በሌላ ቀን እንዲጫወቱ ቀጠሮ ተይዞላቸው እንዲለያዩ ተደርጓል፡፡ በተያዘላቸው ቀጠሮ መሠረት ከሁለት ቀን በኋላ ዛየር 2ለ0 አሸንፋ ዘጠነኛውን የአፍሪካ ጭንጫ ማንሳት ችላለች፡፡ በዛየር በኩል አራቱንም ጐሎች ከመረብ ያገናኘው አጥቂው ሙላምባ ነዳየ ነበረ፡፡ ከዚህ ውድድር ሦስት ወር በፊት ዛየር ለዓለም ዋንጫ ውድድር ያለፈች አንደኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ነበረች፡፡

የናይጄሪያና የካሜሮን የበላይነት በ1980ዎቹ

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ የ1980ውን የአፍሪካ ዋንጫ በሀገሯ አዘጋጅታ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችላለች፡፡ ዋንጫውን ማንሳት የቻለችው አልጀሪያን በፍፃሜ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው፡፡ ከአራት ዓመት በኋላም ለፍፃሜ ብትደርስም በካሜሮን ተሸንፋ ዋንጫውን ሳትነሳ ቀርታለች፡፡ የ1984ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለካሜሮናውያኑ የማይበገሩት አንበሶች የመጀመሪያው ዋንጫቸው ነበር፡፡ ካሜሮን ከሁለት ዓመት በኋላ ግብፅ ባዘጋጀችው ውድድር ላይ ለፍፃሜ ቀርባ ነበር፡፡ ነገር ግን ዋንጫ በተደጋጋሚ የማንሳት ብቃት ባላት ግብፅ ተሸንፋ ዋንጫውን አጥታ በሁለተኛ ደረጃነት አጠናቃለች፡፡ በዚህ ቁጭት ያደረባቸው የካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ሞሮኮ ባዘጋጀችው የ1988 ውድድር ላይ ለሦስተኛ ጊዜ ለፍፃሜ በመቅረብ ናይጄሪያን 1ለ0 አሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችላለች፡፡ ናይጄሪያም በ1980ዎቹ ውስጥ አራት ጊዜ ለፍፃሜ ብትደርስም ሁለት ጊዜ በካሜሮን እየተሸነፈች ዋንጫውን ሳታነሳ ስትቀር፤ እንዲሁም ለሦስተኛ ጊዜ ከ1990 ውድድር አዘጋጅ አልጄሪያ ጋር ለፍፃሜ ቀርባ ድል ሳይቀናት ቀርቷል፡፡

የተሳታፊ ሀገሮች ብዛት የተስተካከለበት የ1990ዎቹ ውድድሮች

ሴኔጋል ባዘጋጀችው የ1992 ውድድር ላይ 12 ሀገሮች በሦስት ምድብ ተመድበው እንዲጫወቱ የሚያዝ ሥርዓት የተዘረጋበት ጊዜ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ የተወዳዳሪ ሀገሮች ብዛት ስለጨመረ ውድድሩ እጅግ ፉክክር የበዛበት ነበር፡፡ የ1992 የአፍሪካ ዋንጫንም አይቮሪኮስት ጋናን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፋ

ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ያነሳችበት ሰዓት ነው፡፡ በድጋሚ ከሁለት ዓመት በኋላ የ12 ቡድኖችና

የሶስት ምድብ ድልድል መርሀ ግብር ተግባራዊ ሆኖ ውድድሩ በቱኒዚያ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ አዘጋጇም ቱኒዚያም ገና በመጀመሪያው ዙር ተሸንፋ በጊዜ ከውድድሩ ውጭ የሆነችበት የአፍሪካ ዋንጫ ነው፡፡ ቱኒዚያ ያዘጋጀችውንም 19ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ናጄሪያ ዛምቢያን 2ለ1 በማሸነፍ አንስታለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ በሀገሪቷ የነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ከወደቀና ለዓመታት በካፍ የተጣለባት ቅጣት ከተነሳላት በኋላ የ1996ቱን የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅ በመሆን ወደ ውድድሩ መጥታለች፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አሁን ወዳለበት 16 ተሳታፊ ሀገሮችና የ4 ምድብ ድልድል ስርዓት የተቀየረው ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 20ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጊዜ ነው፡፡ ይሁን እንጂ 20ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የተካሄደው በ15 ሀገሮች መካከል ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ናይጄሪያ በሀገሯ ፖለቲካዊ ምክንያት በመጨረሻ ሰዓት ከውድድሩ እራሷን በማግለሏ ነው፡፡

በዚህ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ በፍፃሜ ጨዋታ ቱኒዚያን 2ለ0 አሸንፋ እራሷ ያዘጋጀችውን ዋንጫ አንስታለች፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ቡርኪናፋሶ ባዘጋጀችው ውድድር ላይ ደቡብ አፍሪካ በድጋሚ ለፍፃሜ ብትቀርብም በግብፅ ተሽንፋ ዋንጫውን ሳታነሳ ቀርታለች፡፡ በዚህ ጊዜ ግብፅ ለአራተኛ ጊዜ ነው ዋንጫውን ያነሳችው፡፡

ግብፅ በተከታታይ ሻንፒዮን የሆነችባቸው የ2000ዎቹ ውድድሮች

የ2000ውን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ ዚምባቡዌ ብተመረጥም የኋላ ኋላ ግን ጋና እና ናይጄሪያ በጥምረት የውድድሩ አዘጋጅ ሀገሮች ሆነዋል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ካሜሮንና ናይጄሪያ ለፍፃሜ የቀረቡ ሲሆን፡፡ ካሜሮን በፍፁም ቅጣት ምት አሸናፊ ሆና የዋንጫው ባለቤት ሆናለች፡፡ የማይበገሩት አንበሶች የሚል ቅፅል ስም የወጣለት የካሜሮን ብሔራዊ ቡድን በድጋሚ የ2002ቱን የአፍሪካ ዋንጫ በማንሳት በተከታታይ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ካነሱት ግብፅ እና ጋና ጋር ታሪክ ለመረጋራት በቅተዋል፡፡ ካሜሮን የ2002ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችው ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ የቀረበችውን ሴኔጋልን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፋ ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ቱኒዚያ ባዘጋጀችው ውድድር ላይ ካሜሮንና ሴኔጋል ከሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ተሰናብተዋል፡፡ አዘጋጇ ሀገር ቱኒዚያም ሞሮኮን 2ለ1 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች፡፡

ከ2006 እስከ 2010 ድረስ ደግሞ የተዘጋጀውን ሦስቱን የአፍሪካ ዋንጫ ጠራርጋ የወሰደችው ድሮ

የተባበሩት አረብ ሪፕብሊክ በመባል የምትታቀው የአሁኗ ግብፅ ነች፡፡ ግብፅ የ2006ቱን የአፍሪካ ዋንጫ እራሷ አዘጋጅታ በፍፃሜ ጨዋታም አይቮሪኮስትን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፋ ነው ዋንጫውን ያነሳችው፡፡ ጋና ባዘጋጀችው የ2008 ውድድር ላይ ደግሞ ግብፅ ካሜሮንን 1ለ0 አሸንፋ በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ ልትነሳ በቅታለች፡፡ አሁንም አንጐላ ያዘጋጀችውን የ2010 የአፍሪካ ዋንጫ በማንሳት በተከታታይ 3 ጊዜ ሻንፒዮን የሆነችበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳችው ግብፅ ለፍፃሜ የቀረበችውን ጋናን 1ለ0 አሸንፋ ነው፡፡ በ2004 ቱኒዚያ ላይ በአልጄሪያ 2ለ1 ከተሸነፈች ወዲህ ሦስት ጊዜ በተከታታይ ዋንጫውን እስካነሳችበት 2010 ድረስ ግብፅ 19 ጨዋታዎችን ያለምንም ሽንፈት ተጉዛለች፡፡ የአህጉሩን ዋንጫ 7 ጊዜ በማንሳትም ጭምር ሪከርድ እንደያዘች ነው፡፡ እንዲሁም ግብፅ የአህጉራቸውን ዋንጫ ለተከታታይ ሦስት ጊዜ ካነሱት ሜክሲኮ፣ አርጀቲና እና ኢራን ጋር በመቀላቀል ሌላ አዲስ ሪከርድ ለመያዝ ችላለች፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች በ2010ቹ ዓመታት ውስጥ

የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከዓለም ዋንጫ ውድድር ፕሮግራም ጋር እየተጋጨ ሲመጣ መጋቢት 2010 ላይ የአፍሪካ ዋንጫ ከ2013 ጀምሮ በጐደሎ ዓመተ ምህረት ቁጥር እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡ በዚህም ሳቢያ በ12 ወራት ውስጥ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡ ይህም 27ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ጋቦንና ኢኳቶሪያል ጊኒ ጥር 2012 ሲያዘጋጁ፤ 28ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ጥር 2013 ላይ ማዘጋጀቷ አይዘነጋም፡፡ የ2012 ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ዛምቢያ ባልተጠበቀ መንገድ ብርቱካናማ ለባሾችን የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን በፍፁም ቅጣት ምት በማሸነፍ ሻንፒዮን ሆናለች፡፡

የቅረብ ጊዜ ትውስታ ያለው የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን በጥሩ መልክ ነበር ያስተናገደችው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ከሦስት ዓመት በፊት የ2010 የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ስለነበረች በሜዳ ጥራት በኩል ምንም አይነት እንከን ያልገጠመው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ነው ማለት ይቻላል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መስራቿም ኢትዮጵያ

ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሠችበት የአፍሪካ ዋንጫ ነበር፡፡ 29ኛውንም የአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ የፍፃሜ ተጋጣሚዋን ቡርኪናፋሶን 1ለ0 አሸንፋ የዋንጫው ባለቤት መሆኗ አይዘነጋም፡፡

ሌላው በዚህ ወር እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ እንድታዘጋጅ የተወሰነው ጥር 29 /2011 ነበር፡፡ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ግን በ2014 የተፈጠውን የኢቦላ በሽታ በመፍራት ውድድሩ እንዲራዘምላት ካፍን ብትጠይቅም ሀሳቧ ውድቅ ተደርጐ ከውድድሩ ውጭም ተደርጋ በአሁኑ ሰዓት አስተናጋጅ ለሆነችው ኢኳቶሪያል ጊኒ በጊዜው ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በኢኳቶሪያል ጊኒ ሁለት ከተሞች እየተካሄ ነው፡፡ g

ከ1ኛው እስከ 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ድረስ ኮከብ ተጨዋች ተብለው የተሸለሙ

1ኛ. አድ-ዲባ (ግብፅ) 2ኛ. ማሆድ ኤል-ጐሃሪ(ግብፅ)3ኛ. መንግስቱ ወርቁ (ኢትዮጵያ)4ኛ. ሃሰን ኤል-ሻዝሊ (ግብፅ)5ኛ. ኦሴ ኮፊ (ጋና)6ኛ. ካዛዲ ሙዋምባ (ኮንጐ ቢሻሳ)7ኛ. ሎረንት ፓኩ (ኮትዲቫር) 8ኛ. ፍራንሷ ሜፔሌ (ኮንጐ ብራዛቪል)9ኛ. ናዳዪ ሙላምብ (ዛየር)10ኛ. አህመድ ፋራስ (ሞሮኮ)11ኛ. አብዱል ራዛቅ (ጋና)12ኛ. ክርስቲያን ቹኩው (ናይጄሪያ)13ኛ. ፋውዚ አል-ልሳዊ (ሊቢያ)14ኛ. ቴዎፊል አቤጋ (ካሜሮን)15ኛ. ሮጀር ሚላ (ካሜሮን)16ኛ. አዚዝ ቦደርባላ (ሞሮኮ)17ኛ. ራባህ ማጀር (አልጄሪያ)18ኛ. አብዲ ፔሌ (ጋና)19ኛ. ረሺድ የኪኒ (ናይጄሪያ)20ኛ. ካሉሻ ቧልያ (ዛምቢያ)21ኛ. ቤኔድኮት ማካርቲ (ደቡብ አፍሪካ)22ኛ. ሎረን (ካሜሮን)23ኛ. ሪጐበርት ሶንግ (ካሜሮን)24ኛ. ጄ-ጄ ኦካቻ (ናይጄሪያ)25ኛ. አህመድ ሃሰን (ግብፅ)26ኛ. ሆስኒ አብድራዞ (ግብፅ )27ኛ. አህመድ ሀሰን (ግብፅ)28ኛ. ክርስቶፎር ካቶንጐ (ዛምቢያ)29ኛ. ጆናታን ፒትሮፓ (ቡርኪናፋሶ)30ኛ. ?

46

ኅብረ-ብዕር ቅፅ 01 ቁጥር 05 የካቲት 2007

ድረ-አይን

PHARMACURE Plc.

Manufacturerand

Supplier ofHigh Quality,

Affordable Drugs

Tel: +251 116 604 820 | Fax: +251 116 604 825 P.O.Box: | 5542 E-mail: [email protected] Ababa, E thiopia