የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ...

24
የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) መተዳደሪያ ደንብ

Upload: vuanh

Post on 07-Mar-2018

382 views

Category:

Documents


21 download

TRANSCRIPT

Page 1: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)

መተዳደሪያ ደንብ

Page 2: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 2 of 24

መግለጫ

ድር ባሕላዊ የማህበረሰብ ስብስብ ወይም የቀብር ማህበር ሆኖ ሙትን ለመቅበር የሚያግዝ

ድርጅት ነው፡፡ ‘የቀደሙት አያቶቻችን በእድር ተደራጅተው፣ በየወሩ መዋጮ እያዋጡ፣ የቀብር

ስርዐትንና የሙታ ቤተሰብን በሐዘንና በእዝን ወቅት ያግዙና ይረዱ ነበር᎓᎓

እኛም በኪውንስላንድ የምንኖር፣ አንድ ባሕል፣ አንድ ልምድ፣ ያስተሳሰረን የዚህ ሕብረተሰብ አባላት

የእድርን ጠቃሚነትን ከቀደምት አያቶቻችን ተረድተንና ‘ሞት’ የማይወገድ ክስተት መሆኑነ ተገንዝበን “የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩውንስላንድ” /ኢመእኩ/ አቋቁመናል᎓᎓

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩውንስላንድ በእዚህ አኳያ ለሟች አባል ቤተሰብ የገንዘብ እርዳታ

ድጋፍ፣ መንፈሳዊ ድጋፍ እንዲሁም የማሕበራዊ ድጋፍ ይሰጣል᎓᎓ ይህም እርዳታና ድጋፍ ተገቢ በመሆኑ፣

የሟች አባል ቤተሰብ ሐዘኑንና እዝኑን ተረጋግተውና ተጽናንተው እንዲወጡት ይረዳል᎓᎓

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩውንስላንድ /ኢመእኩ/ በዘር፣ በጾታ፣ በሀይማኖትና በፖለቲካ እምነት

ልዩነት ሳይኖር ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ ቃለ በመግባት፤ ሐምሌ 19 /2006

(July 26 /2014) ተመሰረተ᎓᎓

ቦታው፦ ብርዝቤን፣ ኪውንስላንድ

አውስትራሊያ᎓᎓

Page 3: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 3 of 24

ዝርዝር

ክፍል 1 የእድር ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና ሐሳቦች

ክፍል 2 የአባልነት መደቦች

ክፍል 3 የአባልነት መስፈርቶች

ክፍል 4 የአባልነት ግዴታዎች

ክፍል 5 የማህበሩ አገልግሎቶች

ክፍል 6 የአባልነት ክፍያዎች

ክፍል 7 የአባልነት ድጋፎች

ክፍል 8 የአባልነት ድጋፎች አፈጻጸም

ክፍል 9 የሐዘን መግለጫ

ክፍል 10 የእድሩ ማህበር የሂሳብ መዝገብ

ክፍል 11 የበጀት አመት

ክፍል 12 የአባልነት መቋረጥ

ክፍል 13 የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያዎች፣ የአገልግሎትና የአባልነት ክፍያ ለውጦች

ክፍል 14 የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት

ክፍል 15 የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ተግባር

ክፍል 16 ጠቅላላ ስብሰባ

ክፍል 17 አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ

ክፍል 18 ልዩ ውሳኔ

ክፍል 19 ዘገባና የዘገባ መጽሐፍ

ክፍል 20 ውክልና

ክፍል 21 የሒሳብ ምርመራ

ክፍል 22 ሚስጥር መጠበቅ

ክፍል 23 የእድሩ መፍረስ

ኮንትሮልን ይዘው ይጫኑ ለቀጣዩ መልዕክት

Page 4: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 4 of 24

ክፍል 1 የእድር ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና ሐሳቦች 1፡1 አባባሎች

በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መደናገርንና የቃላት አሳሚነትን ለመቀነስ የተወሰኑ መሰረታዊ የሆኑ ቃላት

ትርጉሞች ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህ ቃላትና አባባሎች ለዚህ መተዳደሪያ ደንብ ጥቅም እንዲውሉ ታስበው

ነው፡፡

1. “ዳኛ ” የማህበሩን ተግባራት የሚያስተዳድርና በበላይነት የሚመራ ሹም ማለት ነው፡፡

2. “ስራ አመራር ኮሚቴ” በማሕበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ተመርጦ ማሀበሩን የሚመራ አሰተዳዳሪያዊ አካል

ሲሆነ የሚመረጡትም በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

3. “አባል” ማለት ማህበሩን በበጐ ፍቃደኝነት የተቀላቀለ ሲሆን በመተዳደሪያ ደንብ መሰረተ

የአባልነት ግዴታውን አሟልቶ የተገኘ ነው፡፡

4. “ልዩ ውሳኔ” ማለት በጠቅላላ ጉባኤ (አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤን ጨምሮ) የሚተላለፉ ውሳኔ ነው፡፡

5. “የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ” ማለት በዓመት አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የሚጠራ የማህበሩ ሁሉም

አባላት፣ ከእንግዶች ጋር የሚገኙበት ስብሰባ ነው፡፡

6. “የአባልነት መዋጮ” ማለት ‘ለሐዘን ድጋፍ’ በጥቅም ላይ የሚውል ወርሐዊ ወይም አመታዊ

የአባልነት መዋጮ ማለት ነው፡፡

7. “የምዝገባ ክፍያ” ማለት አንድ ግለሰብ የማህበሩ አባል ለመሆን አንድ ጊዜ የሚከፍለው ክፍያ

ማለት ነው፡፡

8. “የአባልነት ድጋፍ ” ማለት አንድ አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሐዘን ወቅት የሚያገኘውን

‘የሐዘን ድጋፍ’ ይገልጻል ፡፡ ይህም ድጋፍ የገንዘብ ድጋፍን፣ መንፈሳዊ ድጋፍን እንዲሁም

የማሕበራዊ ድጋፍን ይጨምራል፡፡

9. “ባልና ሚስት” ማለት የማህበሩ አባላት የሆኑ በሕጋዊ ጋብቻ ወይም በዲፋክቶ ግኑኝነት ውስጥ

የሚገኙ ጥንዶች ማለት ነው፡፡

10. “ቤተሰብ” ማለት ባልና ሚስት፣ አድሜአቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆችና በአንድ ጣራ ስር

በእድሩ የተሸፈኑ ሌሎች ሰዎቸን ይጨመራል፡፡

11. “ሐዘን” ማለት አንድ ሰው በሞት ሲለይ የሚሰማ ስሜት ነው፡፡ ሐዘን በዚህ አኳያ በሞት የመለየት

ስሜት እስከሚታገስልን ድረስ የምናልፍበት ሒደት ነው፡፡

12. “እዝን”ማለት የሐዘን ውጫዊ መግለጫ ነው፡፡

Page 5: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 5 of 24

1፡2 ስም

የማህበሩ ስም “የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ” (ኢመእኩ) ወይንም “The Ethiopian

Burial Society in Queensland”/EBSQ/ Co-op Ltd በእንግሊዘኛ ይባላል፡፡

1፡3 አርማ

ይህ አርማ ሙሉ እውቅና ያለው የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) አርማ ነው፡፡

1፡4 ማህተም

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) ማህተም፣ የድርጅቱ ሕጋዊ ማህተም በመሆን

በሕጋዊ ሰነዶች ላይ የማህበሩን ሰመና ሕልውና ያረጋግጣል፡፡.

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ ዋና ፀሐፊ ይህን የእድሩን መሀተም በኃላፊነትና በጥንቃቄ

በመያዝ፣ በአገልግሎት ላይ ይጠቀምበታል፡

Page 6: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 6 of 24

1፡5 የማህበሩ አላማዎች

በጋራ እሴት፣ ባሕልና የአስተዳደጋችን መንፈስ ተሰባስበን ባሕላዊ የእድር አገልግሎትን ለመሰጠት ሲሆን

የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት እናከናውናለን፡-

1. በአባል ወይም በቤተሰቡ ላይ በሞት ምክንያት ሐዘን ሲደርስ የችግሩ ተካፋይ በመሆን ‘የሐዘን

ድጋፍ’ ይሰጣል፡፡

ይህ ‘የሐዘን ድጋፍ’ የማህበራዊ እርዳታ ድጋፍን፣ የመንፈሳዊ እርዳታ ድጋፍንና የገንዘብ እርዳታ

ድጋፍን – የሟችን አስከሬን ለመቅበር – ይጠቀልላል፡፡

2. በአባላትና በመላው ማህበረሰብ መካከል ወዳጅነትን ለማጠናከር የሚጠቅሙ “የቤተሰብ ቀን”

የመሳሰሉ ዝግጅቶችን ማከናወንና የእድሩን የገንዘብ አቅም ለማጐልበት በሚደረጉ አገልግሎቶች

እንዲሁም ስጋት በሌለባቸው የኢንቨስትመንት ተግባራት መሳተፍ - በአውስትራሊያ ውስጥ

ብቻ ፡፡

ክፍል 2 የአባልነት መደቦች

2፡1 የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) መደበኛ አባላትን አካቶ የሚከተሉትን የአባልነት መደቦች ዝርዝር አሉት᎓᎓

ይህም እነዚህን ይጨምራል፦

(ሀ) ረዳት አባላት

(ለ) የዘላለም አባላት

(ሐ) የክብር አባላት

2፡2 የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) መደበኛ አባላት መጠን ገደብ የለውም᎓᎓

አባል ለመሆንም የዘር፣ የጾታ፣ የሀይማኖትና የፖለቲካ እምነት ልዩነትን የሚቃወም ምንም አጋች መስፈርት

በእድሩ ማህበር መተዳደሪያ ሕግ ውስጥ የለም - ከ18 ዓመት እድሜእና በላይ በስተቀር᎓᎓

Page 7: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 7 of 24

ክፍል 3 የአባልነት መስፈርቶች

3፡1 አንድ አመልካች የአባልነት ማመልከቻ ቅጽን በመሙላትና ቅጹ ላይ በመፈረም ለመረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) መስጠት ይኖርበታል፡፡ የአባልነት ማመልከቻው በስራ አመራር ኮሚቴ ወርሐዊ ስብሰባ ተወስኖ አባሉ እንዲገባ ይደረጋል፡፡

3፡2 የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ በኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) ሊቀመንበር

ወይም ፀሐፊ ሊፈረምበት ይገባል፡፡

3፡3 የአባል ዝርዝር፣የጋብቻ ሁኔታ፣የጥገኛ ቤተሰብ አባላት ዝርዝርና መሰል ግላዊ መረጃዎች

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) ሕጋዊ ሰነዶች ናቸው፡፡

3፡4 የአዳዲስ አባላት ማመልከቻ ሕጋዊ የሚሆነው የአባልነትና የምዝገባ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ሲከፈል

ነው፡፡

3፡5 አባላት ከኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ ጋር

የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ ቅጂ ይሰጣቸዋል፡፡

3፡6 ማንኛውም ፍላጐት ያለው ግለሰብ የማመልከቻ ቅጽን (እዝል 1) በመሙላት ለኢትዮጵያውያን

መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) የስራ አመራር ኮሚቴ ያቀርባል፡፡ የስራ አመራር ኮሚቴውም

ማመልከቻውን ስለመቀበል ወይም ውድቅ ስለማድረግ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡ የስራ አመራር ኮሚቴው

ማመልከቻውን ውድቅ ካደረገው ምክንያቱን ለማቅረብ አይገደድም፡፡ ውሳኔውንም እንደገና እንዲታይ

የመጠየቅ መብት የለም፡፡ የማመልከቻ ክፍያውም ሙሉ በሙሉ ለአመልካቹ ይመለሳል፡፡

3፡7 አባላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎቸ ሲከሰቱባቸወ ለማህበሩ ማሳወቅ አለባቸው፦

ሀ. የአድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ ስምና ኢሜሎች ሲለወጡ

ለ. ተጠቃሚ ሲለወጥ

ሐ. የጋብቻ ሁኔታ ሲለወጥ፡፡

3፡8 የተጋቡ/ዲፋክቶ ጥንዶች የአንድ ቤተሰብ የአባልነት ክፍያ ይፈጽማሉ፡፡

Page 8: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 8 of 24

3፡9 ፍቺ በሚፈፀምበት ወቅት እያንዳንዱ ወገን አባልነቱን መቀጠል የሚችል ሲሆን፤ እያንዳንዳቸው

የአባልነት ክፍያ ድርሻቸውን የመክፈል ሐላፊነት አለባቸው፡፡

3፡10 አንድ አመልካች እድሜው 18 አመት ከሞላውና በእድሩ ማህበር መቀላቀል ከፈለገ ስለእድሜው

ማስረጃ ሊያቀርብ ይገባል፡፡

3፡11 ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች ወላጆች ከማመልከቻቸው ጋር የልጆቻቸውን እድሜ የሚገልጹ

ማስረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው፡፡

3፡12 አባልነት በማንኛውም ሁኔታ የሚተላለፍ አይደለም፡፡

ክፍል 4 የአባልነት ግዴታዎች

4፡1 የእድሩ ማህበር ሙሉ ለሙሉ የሚንቀሳቀሰው በበጐ ፍቃደኞች ሲሆን እነዚህ በጐ ፍቃደኞች

የእድሩ ማህበር የስራ አመራር ኮሚቴ አባል ለመሆን በየሁለት ዓመት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ተመርጠው፣

ለሁለት ዓመት ያገለግላሉ፡፡

ሆኖም ግን በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው/ የተመረጠችው የስራ አመራር ኮሚቴ አባል አንድ

ዓመት አገልግሎ/ አገልግላ ከስራ አመራር ኮሚቴ አባልነት መወገድ ከፈለገ/ ከፈለገች በሕግ የተጠበቀ

መብት አለው/ አላት፡፡

4፡2 አባላት ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር በአንድ አባል የቀብር ስርዐት መርሐግብር ላይ መሳተፍ

አለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ ለሚስት/ለባል/ለእህት/ወንድም እንዲሁም ለአያት፣ አጐት፣ አክስት፣

የአጐት/አክስት ልጅ ቀብር መገኘትን ያካትታል፡፡

ክፍል 5 የማህበሩ አገልግሎቶች

5፡1 ሟች ግለሰብን በኩዊንስላንድ/አውስትራሊያ እንዲቀበር በቤተሰቦች ከተወሰነ፣ ማህበሩ የቀብር

አገልግሎትን በአካባቢው በሚገኝ የቀብር አገልግሎት አስፈፃሚ ወኪል በኩል እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡

Page 9: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 9 of 24

በሟች ቤተሰቦች አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አንደ የእድሩ አባል ዕምነት የመታሰቢያ አገልግሎት ኘሮግራም

ይከናወናል፡፡

5፡2 የሟች ቤተሰቦች አስክሬናቸውን በአውስትራሊያ ውስጥ ወይም ወደውጭ አገር መላክ ከፈለጉ

ማህበሩ ይህንን ተግባር በአገር ውስጥ በሚገኙና አለምአቀፋዊ የቀብር ስርዐት አስፈጻሚ ወኪሎች በኩል

ጋር አንድ በሆነ ተመሳሳይ ወጪ ይህንን ተግባር ያከናውናል፡፡

5፡3 ከቤተሰብ ጋር በመተባበር ማህበሩ ስለሟች ታሪክ መግለጫ ከፎቶ ጋር ያዘጋጃል፡፡

5፡4 ማህበሩ በአባላቶቹ ምትክ በመሆን በመቃብር ላይ የሐዘን መግለጫ አበባ ለማስታወሻ

ያስቀምጣል፡፡ እንዲሁም “የእዝን እርዳታ” (በክፍል 9:9.1 በተጠቀሰው መሰረት) ይሰጣል፡፡

5፡5 የእድሩ አገልግሎት የሚጠናቀቀው ሁሉም ሐዘንተኞች የቀብረ ስርዐቱ እንደ ተፈጸመ፣ በሟች ቤት

ውስጥ ተገኝተው ባሕላዊ ጠበል ጻዲቅ ከተቀመሰ በኋላ ነው፡፡

ክፍል 6 የአባልነት ክፍያዎች

6፡1 እድሜያቸው ከ18 አመት በላይና ከ ከ18 አመት በላይ ለሆኑ ጥንዶች የሚከፈል አመታዊ

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የአባልነት ክፍያ … $240.00 የአውስትራሊያን ዶላር እና

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) የመመዝገብያ ክፍያ… $100.00

የአውስትራሊያን ዶላር ይጨምራል፡

ይህ ክፍያ(የአመታዊ የአባልነት ክፍያና የመመዝገብያ ክፍያ) በሶስት ወራቶት ውስጥ ተከፍሎ ማለቅ

አለበት፡፡ አንድ አባል ይህን ከፍሎ ካልጨረሰ የእድሩን ጥቅም አያገኝም፡፡

6፡2 ከመጀመሪያው ክፍያ (የአባልነትና የመመዝገብያ ክፍያ) በኋላ የአባልነት ክፍያዎች በየወሩ ወይም

በየሩብ አመቱ ወይም በየአመቱ ይከፈላሉ፡፡

6.3 የእድሩ ማህበር አንድ የ$25.00 AUD መቀጫ ክፍያ አለው፡፡ ይህ የመቀጮ ክፍያ የእድሩ ማህበር

አባል በዓመት የሚጠበቅበትን ክፍያ ወቅትን አሳልፎ ለአራት ወር ያህል ሳይከፍል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ

በስተቀር የእድሩ ማህበር ምንም አይነት መቀጫ በማህበሩ አባላት ላይ አይጥልም፡፡

Page 10: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 10 of 24

6:4 የእድሩ አባል በስራም ሆነ በግለሰብ ምክንያት ውጭ ቆይቶ ወደ ኩዊንስላንድ በሁለት ዓመት ውስጥ

ከተመለሰ፤ በአባልነቱ እንደጸና ይቆያል፣ መመዝገቢያ ክፍያም እንደ አዲስ ኣባል አይከፍልም፡፡

ክፍል 7 የአባልነት ድጋፎች

7፡1 የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ ‘የሐዘን ድጋፍ’ ለእድሩ አባልና ቤተሰቡ ይሰጣል፡፡

ይህም፦ የገንዘብ እርዳታ ድጋፍን – የሟችን አስከሬን ለመቅበር – ፣ የመንፈሳዊ እርዳታ ድጋፍንና

የማህበራዊ እርዳታን ድጋፍን ያጠቀልላል፡

7፡2 የእድሩን ማህበር የገንዘብ እርዳታ ድጋፍ መጠን፣ የመንፈሳዊ እርዳታ ድጋፍንና የማህበራዊ እርዳታ

ድጋፍ አይነት በኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ ስራ አመራር ኮሚቴ ይወሰናል፡፡

7፡3 ከእድሩ ማህበር አላማና ተግባር ውጭ በቀር ለማንኛውም የእድሩ ማህበር አባል የብድር (ወለድ

ወይንም አራጣ ያለው) ክፍያ የእድሩ ማህበሩ አይሰጥም፡፡

7፡4 የእድሩን ማህበር ‘የዋና ገንዘብ አክሲዮን ወይንም ድርሻ’ (shared capital) እና ‘የንግድ ትርፍም’

(business surplus) ስሌለው ለድጎማ ሰጪ ድርጅቶች እርዳታ አይሰጥም፣ ለማህበሩ አባላትም

አያከፋፍልም፡፡

ክፍል 8 የአባልነት ድጋፎች አፈጻጸም

8፡1 አዲሱ አባል እርሱ ወይም እርሷ በሞት ጊዜ የአባልነት ድጋፎችን ለመቀበል ብቁ የሚሆኑት ለ6 ወር በኣባልነት ተመዝግበው ሲቆዪ ነው፡፡

8፡2 በሞት ጊዜ የሚፈጸም ክፍያ የሚከፈለው እድሜያቸው 18 አመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ወይም

በአባልነት ማመልከቻ ቅጽ ላይ ተጠቃሚ ተብሎ የተሞላ/የተሞላች ለአቅመ አዳም/ሔዋን ያልደረሰ/ች ልጅ

ሕጋዊ አሳዳጊ ለሆነ ግለሰብ ነው፡፡ ተጠቃሚ ያልተወሰነ ከሆነ ደግሞ በሕግ ለተወከለ ሰው ይከፈላል፡፡

Page 11: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 11 of 24

8፡3 ከአራት ወራት በላይ የአባልነት መዋጮ ውዝፍ እዳ ያለባቸው አባላት ማንኛውንም የእድሩን

አገልግሎቶች መቀበል አይችሉም፡፡ ነገር ግን ከአቅም በላይ ችግሮች ሲያጋጥም የስራ አመራር ኮሚቴው

ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

ክፍል 9 የሐዘን መግለጫ

9፡1 አንድ አባል ሲሞት ከኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) $1000 የአውስትራሊያ ዶላር የእዝን እርዳታ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የቤተሰብ አባል ጥያቄ ካቀረበ ይህ አስተዋጽኦ ከእዝን እርዳታ የማይበልጥ ዋጋ ያለው

ገንዘብ አባሉ ለመረጠው በጐ አድራጐት ድርጅት እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

9፡2 ከአባል ጋር የሚኖር የቤተሰብ አባል ሲሞት የስራ አመራር ኮሚቴው ለአባሉ የሐዘን መግለጫ

ካርድን ይልክለታል፡፡

9፡3 የቅርብ የቤተሰብ አባል (ወላጅ፣ እህት፣ወንድም፣ ባል፣ ሚስት) ከአባል ጋር የማይኖሩ በሚሞቱበት

ወቅት የስራ አመራር ኮሚቴው የሐዘን መግለጫ ካርድን ለአባሉ ይልክለታል፡፡

ክፍል 10 የእድሩ ማህበር የሂሳብ መዝገብ

10.1 የእድሩ ማህበር በአንድ ሕጋዊ እውቀና ባለው ገንዘብ አስቀማጪ ተቋም (financial

institution) ውስጥ በእድሩ ስም የሂሳብ መዝገብ መክፈት ይገበዋል፡፡

የእድሩ ማህበር የእድሩን መመዝገቢያና የዓመት ክፍያ ከፍለው ላጠናቀቁ የእድሩ ማህበር አባላት ሕጋዊ

የሆነ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

10.2 ገንዘብ አውጪ ሰነድን (cheque) በመጠቀም ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የእድሩ ማህበር ‘የሐዘን ድጋፍ’

የገንዘብ እርዳታ ይሰጣል፡፡ ይህ ገንዘብ አውጪ ሰነድ (cheque) በሦስት የተመደቡ የስራ አመራር ኮሚቴ

አባላት (ዳኛ፣ገንዘብ ያዥና የገንዘብ ሹም) መፈረም ይኖርበታል፡፡

10.3 በገንዘብ ማግኛ ገቢዎችና በገንዘብ ማዋል አገልግሎቶች (ኘሮሞሽን /ኢንቨስትመንት) የተገኙ

ገቢዎች በኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) የተለየ ሒሳብ ተመዝግበው፤

Page 12: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 12 of 24

“በድንገተኛ እርዳታ ወጪ” ስር አባል ላልሆኑ ግለሰቦች ሲሞቱና የማህበሩን እድገት ደረጃ ከፍ ለማድረግ

በጥቅም ላይ እንዲውል የእድሩ ማህበር ያደርጋል፡፡

ክፍል 11 የበጀት አመት

11.1 የእድሩ ማህበር የበጀት አመት (financial year) የሚጀምረው በየዓመቱ አፕሪል 1 ሲሆን

የሚጨረስው በማርች 31 ላይ ነው፡፡

የበጀት አመት ካለፈ በአምስት ወራቶች ውስጥ የእድሩ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት አለበት፡፡

ክፍል 12 የአባልነት መቋረጥ

12.1 አባልነት ከሚከተሉት ምክንያቶች መካከል በአንዱ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

1. አንድ አባል በአደጋ ወይም በተፈጥሮ በሚሞትበት ወቅት፡፡ ቀሪው የቤተሰብ አባል አባልነቱን

ይቀጥላል፡፡

2. አባሉ በበጐ ፍቃደኝነት አባልነቱን ሲያቋርጥ

3. አባሉ በስነ- ስርዐት ጉድለት ምክንያት ከአባልነት ሲሰናበት፤

4. አባሉ ወርሐዊ ክፍያን ሳይከፈል ሲቀር፤

12.2 አንድ አባል የአባልነት መዋጮን መክፈል ከነበረበት ቀን ለ3 ወራት ያህል ሳይከፍል ከቆየ ውዝፍ

ቀሪውን ከመቀጫ ጋር እንዲከፍል ተጨማሪ 30 ቀናት ይሰጡታል፡፡

12.3 በ4ኛው ወር የመጀመሪያ ቀን አባልነቱ እንደሚቋረጥ ማስጠንቀቂያ ተጽፎ ከ$25.00 መቀጫ ጋር

አደራ ደብዳቤ ይላክለታል፡፡ ይህ አባል ውዝፍ ክፍያ መቀጫውን በ30 ቀናት ውስጥ ካልከፈለ፤

ከአባልነቱ ይሰረዛል፡፡

Page 13: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 13 of 24

12.4 የአባልነት መወገድ ‘በስነ-ስርዐት ጉድለት ሳቢያ’ ከሆነ በኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር

በኩዊብስላንድ የስራ አመራር ኮሚቴ ይወሰናል፡፡

የእድሩን ማህበር አባል የይግባኝ መብት በመጠበቅ፤ ይግባኝ ባዩ አባልና የማህበሩ የስራ አመራር ኮሚቴ

ከአባልነት መገለል ጋር የተያዘ የመከራከሪያ ሀሳባቸውን እንዲገልጹ በጹሁፍ ወይንም በቃል እድል

ይሰጣቸዋል፡፡

በእያንዳንዱ የይግባኝ ጥያቄዎች ክስ ላይ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊብስላንድ የስራ አመራር

ኮሚቴ ውሳኔ የጸና ይሆናል፡፡

የይግባኝ ጥያቄ ክስ ላቀረበው/ ላቀረበችው አባል የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊብስላንድ የስራ

አመራር ኮሚቴ ውሳኔን የሚገልጽ ህጋዊ ደብዳቤ ይላክለታል / ይላክላታል፡፡

ክፍል 13 የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያዎች፣ የአገልግሎትና የአባልነት ክፍያ ለውጦች

13.1 የአባልነት ክፍያ ከአባልነት መመዝገቢያም ጭምር፣ በሞት ጊዜ የሚፈጸም ክፍያና የእዝን እርዳታ

ክፍያ 2/3ኛ አባላት ሐሳብ አቅርበው በጠቅላላ ጉባኤ ሊሻሻልና ሊቀየር ይችላል፡፡

13.2 የመተዳደሪያ ደንብ ድንጋጌዎች በ 1/3ኛ የስራ አመራር ኮሚቴ ወይንም 2/3ኛ የእድሩ ማህበር

አባላት ሐሳብ በሚያቀርቡበት ወቅት ሊሻሻል ወይንም ሊለወጥ ይችላል፡፡

13.3 የመተዳደሪያ ደንብ ሕጐች በጠቅላላ ጉባኤ 2/3ኛ ብልጫ ድምጽ ከጸደቀ ወዲያውኑ ተፈፃሚ

ይሆናል፡፡

13.4 የልዩ ውሳኔ ስብሰባ ከተከናወነ በሶስት ወራት ውስጥ የተሻሻለው ወይንም የተለወጠው

የመተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ተቀባይነት አግኝቶ እንዲመዘገብ ለኩዊንስላንድ መንግስት - የንግድ ክፍል

(Queensland Government: Office of Fair Trading) - ማሳወቅ ይገባል፡፡

ክፍል 14 የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት

Page 14: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 14 of 24

የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ሰባት ቋሚ አባላትን የያዘ ሲሆን እነሱም ፡-

1. ዳኛ

2. ምክትል ዳኛ

3. ፀሐፊ

4. ገንዘብ ያዥ

5. ገንዘብ ሹም

6. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም

7. የንብረት ሹም

14.1 በምርጫ ግዜ የእያንዳንዱ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል የስራ ተግባራት የሚገልጽ ጽሑፍ ለአባላት

እንዲሰራጭ መደረግ አለበት፡፡

14.2 በማህበሩ ውስጥ ባላቸው መልካም አቋም የተነሳ ሁለት እጩ አባላት ለስራ አመራር ኮሚቴ

አባልነት ይጠቆማሉ፡፡

እጩውን/ እጩዋን አባልን የጠቆመ የእድሩ ማህበር አባል በምን ምክንያት እጩውን/ እጩዋን

እንደጠቆመ በስብሰባው ላይ ለተገኙ የእድሩ ማህበር አባለት አጭር ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

በተጠቆሙት ሁለት የእድሩ ማህበር አባለት እጩዎች ላይ ድምፅ ይሰጥና ብልጫ ድምፅ ያገኘው አባል

የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል ሆኖ ይመረጣል፡፡

በቂ ድምጽ ብልጫ አግኝቶ/ታ ያልተመረጠው/ችው እጩ ፍቃደኛ ከሆነ/ች ፣በድጋሚ እጩ ሆኖ/ና በስራ

አመራር ኮሚቴ አባል ምርጫ ሂደት ላይ መሰተፍ ይችላል/ ትችላለች፡፡

ሰባት የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት በግልጽና መድልዎ

በሌለበት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይመረጣሉ፡፡

አዲሰ የተመረጡት የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት የስልጣንና የሓላፊነት ክፍፍል አድርገው

ለኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ አባላት ያሳውቃሉ፡፡

14.3 እያንዳንዱ የስራ አመራ አባል ኮሚቴው የሚሰጠውን ስራዎች የማከናወን ሐላፊነት አለበት፡፡

Page 15: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 15 of 24

14.4 እያንዳንዱ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ ከስራ አመራር ኮሚቴ

አባልነቱ ሊሰናበት ይችላል፦

ሀ. ተቀባይነት በሌላቸው ምክንያቶች የተነሳ ሦስት ተከታታይ ስብሰባዎች ላይ ካልተገኘ

ለ. የስራ አመራር ኮሚቴው ሳይፈቅድለት ወክሎ ከተገኘ

ሐ. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተጠቀሰውን የአባልነት ግዴታዎች ሳያሟላ ከቀረ፡፡

14.5 የስራ አመራር ኮሚቴ አባልነት ‘ስንብት ውሳኔን’ እንደገና እንዲታይ የመጠየቅ መብት የለም፡፡

14.6 አንድ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል በገዛ ፍቃዱ ስራውን ሲለቅና ወይም የሚጠበቅበትን ስራ

ከአላከናወነ፤ የስራ አመራር ኮሚቴው በምትኩ ሌላ ያስመርጣል፡፡

14.7 የስራ አመራር ኮሚቴ ጉዳዮችን በሚገባ ለማከናወን በየአራት ወራት አንድ ጊዜና እንደ አስፈላጊነቱ

ሊሰበሰብ ይችላል፡፡ የስብሰባው ቃለጉባኤዎችም ሊያዙ ይገባል፡፡

14.8 የስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባ ምልአተ ጉባኤ ሆነ (ሞልቷል) የሚባለው ከግማሽ በላይ የስራ

አመራር ኮሚቴ አባላት ሲገኙ ብቻ ነው፡፡

14.9 ምልአተ ጉባኤ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ካልሆነ፦

1. ይህ ስብሰባ የልዩ ስብሰባ ጥሪ ከሆነ - ለሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ይደረጋል፡፡

2. በሌላ ምክንያቶች ግን - ስብሰባው በሚቀጥለው ሳምንት በተመሳሳይ ቀን ጊዜና ቦታ እንዲከናወን

ሊተላለፍ ይችላል፡፡

3. ለ2ኛ ጊዜ ተጠርቶ በሚከናወነው ስብሰባ ወቅት በስብሰባው መገኛ ጊዜ በግማሽ ሰዓት ውስጥ

ምልአተ ጉባኤ ካልሆነ፣ በተገኙት ተሰብሳቢዎች ምልአተ ጉባኤ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

ክፍል 15 የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ተግባር

Page 16: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 16 of 24

15.1 የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት የሚመረጡት በጠቅላላ ጉባኤ አመታዊ ስብሰባ ወቅት ነው፡፡

እነርሱም ዳኛ፣ ምክትል ዳኛ፣ ፀሐፊ፣ ገንዘብ ያዥ፣ ገንዘብ ሹም ፣ የኘሮሞሽን /ኢንቨስትመንት ሹም እና

የንብረት ሹም ናቸው፡፡

የዳኛ ተግባር

1. ዳኛው ማህበሩ ስኬታማ በሆነ መልኩ ሥራውን እንዲያከናውን፣ ግቦቹን እንዲያሳካ፣ ሁሉም

አባላት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ በድርጅቱ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግና በዚህ መተዳደሪያ ድንብ

ውስጥ የሰፈሩት ደንቦች ሳይዛቡ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ተግባራዊ መሆናቸውንም

ይቆጣጠራል።

2. ዳኛው አዳዲስ አባላት በድርጅቱ የመልካም አቀባበል ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ አለበት፡፡

ዳኛው እንደስሙ ሁሉንም ስብሰባዎች ሥርዓትን ጠብቆና ደንቡን ተከትሎ ይመራል፡፡

3. ዳኛው ስብሰባዎችን በሊቀመንበርነት በሚመራበት ወቅት፣ በተነሱ ክርክሮች ላይ ሳያዳላ

ክርክሮችን እልባት ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡

4. ዳኛው በተጨማሪም ከስብሰባ ውጪ አስፈላጊ የሆኑ ሐላፊነቶች አሉበት፡፡ ዳኛው በድርጅቱ

ሕጋዊ እንቅስቃሴዎች ድርጅቱን የሚወክል ሲሆን ተገቢ የሆኑ መግለጫዎችን ለመስጠት ወይም

ድርጊቶችን ለማከናወን የድርጅቱ አፈቀላጤ በመሆን ያገለግላል፡፡

5. ዳኛው በገንዘብ ያዥ በወጪ ደብዳቤዎችና በሂሳብ ወጪ ሰነዶች ላይ ዋና ፈራሚ በመሆን

ያገለግላል፡፡ በዚእም አኳያ እስከ $1000.00 የሚደርሱ ተገቢና ሕጋዊ ወጪዎች ላይ የመፍቀድ

ሥልጣን አለው፡፡

6. ዳኛው በተጨማሪም ለሟች ግለሰብ የቤተሰብ አባላት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ክፍል 7:7.1–

7.2 ላይ እንደተጠቀሰው የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የስራ አመራር ኮሚቴ

‘የሟችን አስከሬን ለመቅበር’ የተመደበውን የገንዘብ እርዳታ ለመፍቀድ ሥልጣን ካላቸው ሦስት

ፈራሚዎች ውስጥ ( ዳኛ፣ገንዘብ ያዥና የገንዘብ ሹም) መካከል አንዱ ነው፡፡

7. ዳኛው ከተቀሩት የስራ አመራር ኮሚቴ አባሎች ጋር በመመካከር አስቸኳይ የስራ አመራር ኮሚቴ

ስብሰባ እንደአስፈላጊነቱ ሊጠራ ይችላል ፡፡

8. ዳኛው በህገ ደንቡ ላይ ያልተካቱ ለእድሩ ማህበር እድገት ጠቃሚ የሆኑ ገንቢ ሀሳብ በእድሩ

ማህበርና አሰራር ላይ ሲቀርብ በሰራ አመራር ኮሚቴ ላይ ያወያያል፡፡

Page 17: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 17 of 24

ገንቢ ሀሳቡ በጠቅላላ ጉባኤ ላይ አጀንዳ ለመሆን በሰራ አመራር ኮሚቴው ወይንም በማህበሩ

አባላት መደገፍና መፈረም ይኖርበታል በእድሩ መተዳዳሪያ ደንብ ክፍል 13:2 መሰረት፡፡

የምክትል ዳኛ ተግባር

1. ምክትል ዳኛው ከዳኛው ጋር በመተባበር ይሰራል፡፡ ዋናው ስተዳዳሪው በማይገኝበት ወቅት

ተክቶት ስብሰባ ይመራል፣መደበኛ ስራዎችንም ያከናውናል።

2. ምክትል ዳኛው ከተቀሩት የስራ አመራር ኮሚቴ አባሎች ጋር በመመካከር አስቸኳይ የስራ

አመራር ኮሚቴ አመራር ስብሰባ እንደአስፈላጊነቱ ሊጠራ ይችላል።

3. የዳኛው ሓላፊነተና ሥራ ለረⶵም ጊዜ ሲቋረጥ፤ አዲስ ዳኛ በአጠቃላይ ስብሰባ እስኪመረጥ

ድረስ ምክትል ዳኛው በጊዜያዊነት አስተዳዳሪ ሆኖ ይቆያል፡፡

የፀሐፊ ተግባር

1. ፀሐፊው የማህበሩ አስተዳደር ክፍል አባል ነው፡፡ ፀሐፊው ከአስተዳዳሪው ጋር በመመካከር

የሁሉንም የድርጅቱን የስብሰባ አጀንዳዎች ያዘጋጃል፡፡

2. ፀሐፊው የአባሎችን ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ሰነዶችንና ሐይሎችን የአባላትን ሙሉ ስሞች፣

አድራሻ፣ የስልክ ቁጥርና ኢሜሎች ይይዛል፡

3. ፀሐፊው በ1እያንዳንዱ የማህበሩ ስብሰባዎች በመገኘት የስብሰባውን ውይይት ሒደት

ማስታወሻዎች በጽሁፍ በመያዝ ቃለጉባኤ ያይዛል፡፡

4. ፀሐፊው ሁሉንም ገቢ የልውውጥ ደብዳቤዎች በመቀበል ያስቀምጣል፤ ሁሉንም ወጪ

ደብዳቤዎችን በመመዝገብ ይልካል፡፡

5. ፀሐፊው የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤዎችን ለአባላት ይልካል፡፡ ፀሐፊው በዚህ የስብሰባ ጥሪ

ደብዳቤ ውስጥ የስብስባውን ቀን፣ ቦታውን፣ የስብሰባ ሰዓቱንና አጀንዳዎችን በግልጽ ለአባላት

ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

Page 18: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 18 of 24

የገንዘብ ያዥ ተግባር

1. ገንዘብ ያዥ የማህበሩን የገንዘብ አስተዳደር ጤናማ በሆነ የገንዘብ አስተዳደር አሰራር የመያዝ

ሐላፊነት አለበት እንዲሁም የድርጅቱን መልካም የገንዘብ ምንጮችን ለማሻሻል እድሎችን

ይኸውም ቀላል የሆኑ ለስጋት የማይዳርጉ ኢንቨስትመንቶችን ያዘጋጃል፣ ይገመግማል፡፡

2. ገንዘብ ያዥ ገንዘብን ይቀበላል፣ ያወጣል እንዲሁም ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም የገንዘብ

ምዝገባዎችን ይይዛል እንዲሁም ሒሳቦችን በሚመለከት ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

3. ገንዘብ ያዡ መዝግቦ የሚይዛቸው ሰነዶች ትክክል ለሞሆናቸውና ምንም ዓይነት ልዩነትና ስህተት

እንዳልኖረ ለማረጋገጥ የፋይናንስ ሐላፊው ከሚይዘው ሰነዶች ጋር መጣጣማቸውን በየወቅቱ

ማመሳከር ይኖርበታል።

4. ገንዘብ ያዥ በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የበጀት ሪፖርትን ማቅረብ አለበት፡፡

5. ገንዘብ ያዥ ስለተክክለኛ የገንዘብ አስተዳደር ኘሮቶኮሎች እርግጠኛ ካልሆነ ጉዳዩን ወደ እድሩ

አስተዳዳሪ ይመራል፡፡

6. ገንዘብ ያዥ የአባልነት ክፍያዎችን ይይዛል፣ ይቆጣጠራል እንዲሁም ይመዘግባል፡፡ እርሱም

በተጨማሪም በየአራት ወራት ለአባላት ሕጋዊ የክፍያ ደረሰኞችን ይልካል፡፡

7. ገንዘብ ያዥ በተጨማሪም ለሟች ግለሰብ የቤተሰብ አባላት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ክፍል

7:7.1– 7.2 ላይ እንደተጠቀሰው የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የስራ አመራር

ኮሚቴ ‘የሟችን አስከሬን ለመቅበር’ የተመደበውን የገንዘብ እርዳታ ለመፍቀድ ሥልጣን ካላቸው

ሦስት ፈራሚዎች ውስጥ (ዳኛ፣ገንዘብ ያዥና የገንዘብ ሹም) መካከል አንዱ ነው፡፡

8. ገንዘብ ያዥ መደበኛ የአባልነት ክፍያን በወቅቱ ለማይከፍሉ የእድሩ ማህበር አባላት በቃል

እንዲሁም ሕጋዊ ደብዳቤ በመላክ ያሳውቃል፣ያሳስባል፡፡

9. ገንዘብ ያዥ በኘሮሞሽን /ኢንቨስትመንት የተገኙ የገንዘብ ገቢዎች በኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር

በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ) የተለየ ሒሳብ ተመዝግበው፤ “በድንገተኛ እርዳታ ወጪ” ስር አባል

ያልሆኑ ግለሰቦች ሲሞቱና የማህበሩን እድገት ደረጃ ከፍ ለማድረግ በጥቅም ላይ እንዲውል

ያደረጋል፡፡

Page 19: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 19 of 24

የገንዘብ ሹም ተግባር

1. የገንዘብ ሹም የማህበሩ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ አሰራር ሒደቶች ሕጋዊነትን የተከተሉ

መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

2. የገንዘብ ሹም ከአባላትና ሌሎች ድርጅቶች የሚገቡትን ክፍያዎችና የማህበሩ ወጪዎች በሙሉ

ያረጋግጣል፡፡

3. የገንዘብ ሹም የፋይናንስ ሪፖርትን ማዘጋጀት አለበት፡፡ በተጨማሪም በየ6 ወሩ የማህበሩን

በጀት ማዘጋጀት አለበት፡፡ የገንዘብ ሹም ግኝቶቹን የአባላትና የማህበሩን ውዝፍ እዳዎች

ጨምሮ ለስራ አመራር ኮሚቴ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡

4. የገንዘብ ሹም በተጨማሪም ለሟች ግለሰብ የቤተሰብ አባላት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ክፍል

7:7.1– 7.2 ላይ እንደተጠቀሰው የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የስራ

አመራር ኮሚቴ ‘የሟችን አስከሬን ለመቅበር’ የተመደበውን የገንዘብ እርዳታ ለመፍቀድ

ሥልጣን ካላቸው ሦስት ፈራሚዎች ውስጥ (ዳኛ፣ገንዘብ ያዥና የገንዘብ ሹም) መካከል አንዱ

ነው፡፡

5. የገንዘብ ሹም በተጨማሪም በዓመት አንድ ጊዜ ለሚደረገው አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ

የገቢና የወጪ ሪፖርቶችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም ተግባር

1. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም የቤተሰብ ቀን በዓመት አንድ ጊዜና የአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ

ቀን የመዝናኛ ዝግጅትን ያዘጋጃል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የገንዘብ ማግኛና ማሰባሰቢያ

ድግሶችን ያከናውናል፡፡

2. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም የድጎማ እርዳታ ( fund) በእድሩ ማህበር ስም ይጠይቃል፡፡

ይህን የድጎማ እርዳታ ( fund) ጥያቄ በእድሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አቅርቦ

ያስወስናል፡፡

3. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም ከፖለቲካ ድርጅቶች የሚሰጡ እርዳታዎችን አይቀበልም፣

አይሰጥምም፡፡

Page 20: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 20 of 24

4. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም ስራዎችንና እቅዶችን ለማከናወን የእድሩን ማህበር ስራ

አስፈፃሚ ኮሚቴና የእድሩ ማህበር አባላትን የሞራልና የሰው ሐይል ድጋፍ እገዛን መጠየቅ

አለበት፡፡

5. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም ማህበሩንና መተዳደሪያ ደንቡን ለሕዝብ ለማስተዋወቅ ሰፊ

ሚና ይጫወታል፡፡

6. የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም የማህበሩን በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት የሥራ አስፈፃሚው

ኮሚቴ ሲያፀድቅና እውቅና ሲሰጥ ያሰራጫል፡፡

በተጨማሪም የማህበራዊ ግንኙነተ ሹም የማህበሩን ኔትወርክ ሥርአትን ድረገጽን ጨምሮ

ይቆጣጠራል፡፡

የንብረት ሹም ተግባር

1. የንብረት ሹም የማህበሩን ንብረቶች የመቆጣጠርና የማስተዳደር ሥልጣን አለው፡፡

2. እያንዳንዱ የማህበሩ ንብረት በፋይል ተይዞ ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ሊቀመጥ

ይገባል፡፡

3. የማህበሩን ንብረቶች መስጠት፣ መመለስና ማከራየት የሚቻለው የስራ አመራር

ኮሜቴው ባስቀመጠው የአሰራር ደንቦች መሰረት ነው፡፡

4. የንብረት ሹሙ ለኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ ወቅታዊ ፍላጐቶች

አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በሚመለከት ሐሳብ ያቀርባል፡፡

ክፍል 16 ጠቅላላ ስብሰባ

16.1 ጠቅላላ ስብሰባዎች በማንኛውም ጊዜ ሊከናወን የሚችል ሲሆን በእድሩ ተግባራት ላይ መሰረት

ያደረገ መሆነ አለበት፡፡ ጠቅላላ ጉባኤ ድርጅቱ በተቋቋመ እስከ 3 ወራት ባሉት ጊዝያቶች ውስጥ

የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያው ጠቅላላ ጉባኤ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ሊጠራ ይችላል፡፡

የእድሩ ፀሐፊ ለእያንዳንዱ አባል በ14 ቀናት ውስጥ የጥሪ ደብዳቤ በጹሑፍ በመላክ በሚከተሉት

ምክንያቶች የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባን መጥራት ይችላል፦

Page 21: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 21 of 24

1. በስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባ እንዲጠራ ትዕዛዝ ሲሰጥ

2. ቢያንስ 1/3ኛ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ፈርመው ጥያቄ ሲያቀረቡ

3. የሰራ አመራር ኮሚቴ አባላትን እጥፍ ቁጥር ያላቸው ከአንድ አባል ጋር ተጨምሮ የማህበሩ

አባላት በጽሑፍ በመፈረም ጥያቄ ሲያቀርቡ

16.2 የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባን ለማካሄድ ምልአተ ጉባኤ ሊሟላ ያስፈልጋል፡፡ ለጠቅላላ ጉባኤ ምልአተ

ጉባኤ ሆነ የሚባለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር በሁለት ተባዝቶ አንድ ሲደመርበት ይሆናል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ሁሉም የኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ የስራ አመራር ኮሚቴ

አባላት ከሆኑ፤ ምልአተ ጉባኤ ሆነ የሚባለው ከአጠቃላይ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ቁጥር ላይ አንድ

ሲቀነስ ነው፡፡

16.3 ለጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው የስብሰባ መገኛ ጊዜ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ምልአተ ጉባኤ ካልሆነ፦

1. ስብሰባው በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ያልተጠራ ከሆነ ለሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ይደረጋል፡፡

2. በሌላ ምክንያቶች ግን ስብሰባው በሚቀጥለው ሳምንት በተመሳሳይ ቀን ጊዜና ቦታ እንዲከናወን

ሊተላለፍ ይችላል፡፡

3. ለ2ኛ ጊዜ ተጠርቶ በሚከናወነው ስብሰባ ወቅት በስብሰባው መገኛ ጊዜ በግማሽ ሰዓት ውስጥ

ምልአተ ጉባኤ ካልሆነ በተገኙት ተሰብሳቢዎች ምልአተ ጉባኤ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

16.4 ለሁሉም ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባዎች ቃለጉባኤ ይያዛል᎓᎓

ክፍል 17 አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ

17.1 በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ አባላት፣ የስራ አመራር

ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ፡፡

17.2 አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የእድሩ ማህበር የበጀት አመት እንዳለቀ ሊጠራ ይገባል፡፡ ፀሐፊው

ለእያንዳንዱ አባል የስብሰባ ስፍራ፣ቀን፣ ቦታና አጀንዳዎችን በመግለጽ ከስብሰባው ቀን 14 ቀናት በፊት

የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ መላክ አለባት፡፡

Page 22: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 22 of 24

በኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ ጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ ላይ የሚከተሉት ተግባራት

ይከናወናሉ፦

1. ያለፈውን ዓመት የሥራ እንቅስቃሴዎችና ስኬቶች በሚመለከት ውይይት ማድረግ፤

2. የተመረመረ ወይም የተረጋገጠ የፋይናንስ መግለጫዎችን በስብሰባው እንዲጸድቁ ማቅረብ፤

3. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ

4. ለሚቀጥለው የበጀት ዓመት ኦዲተር ወይም አረጋጋጭ መሾም፡፡

17.3 አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ምልአተ ጉባኤ መሆን አለበት፡፡ የአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ

ምልአተ ጉባኤ የሚባለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር በሁለት ተባዝቶ አንድ ሲደመርበት

ይሆናል፡፡

17.4 የአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለጉባኤ ከአጠቃላይ ስብሰባ ቃለጉባኤ ተለይቶ መያዝ አለበት፡፡

ክፍል 18 ልዩ ውሳኔ

18.1 ልዩ ውሳኔ የሚባለው በአጠቃላይ ስብሰባ (አመታዊ አጠቃላይ ስብሰባን ጨምሮ) ወቅት በ 2/3ኛ

አባላት ድምጽ የተላለፈ ውሣኔ ነው፡፡

የታቀደውን የልዩ ውሳኔ ስብሰባ አጀንዳ ቦታና ጊዜ የጠቀስ ደብዳቤ ለኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር

በኩዊንስላንድ አባላት ከ14 ቀን በፊት መሰጠት አለበት፡፡

በልዩ ውሳኔ ስብሰባ የሚወሰኑ ውሳኔዎች፦

1. ድርጅትን ማቋቋም

2. የተቋቋመውን ማህበር ስም መለወጥ

3. የማህበሩን ሕጐች መቀየርና ማሻሻል

4. ማህበሩን ማፍረስን ይጨምራል፡፡

18.2 ለልዩ ውሳኔዎች የስውር ድምጽ አሰጣጥ አይፈቀድም፡፡

Page 23: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 23 of 24

ክፍል 19 ዘገባና የዘገባ መጽሐፍ

19.1 የዘገባ መጽሐፍ በእድሩ ማህበር ፀሐፊ ይያዛል፡፡ የተመዘገቡት ውሳኔዎች በተግባርና በጥቅም ላይ

እንዲሉ የእድሩ ማህበር ፀሐፊ ያደረጋል፡፡ የዘገባ መጽሐፍ የእድሩ ማህበር ክንውኖችን በአጭር ዝርዝር

ያሳያል፡፡

19.2 የስብሰባ ዘገባ (የስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባ፣የጠቅላላ ስብሰባና የአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ)

በየአንዳንዳቸው የዘገባ መጽሐፍ መያዝ ይኖርበታል፡፡

19.3 የኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ አባል የእድሩን ማህበር ዘገባ ማየትና መመርመር

ከፈለገ በዳብዳቤ የወቅቱን የስራ አመራር ኮሚቴ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡

ክፍል 20 ውክልና

20.1 የማህበሩ አባላት ሌላ ግለሰብን ወይም አባልን የመወከል ሥልጣን አላቸው፡፡

20.2 በወኪል ድምጽ ለመስጠት የሚቀርብ ጥያቄ ለማህበሩ ዳኛ ወይንም ፀሐፊ በጽሑፍ ተደርጐ

ከታቀደው ስብሰባ 3 ቀን (72 ሰዓት) በፊት መቅረብ አለበት፡፡

ክፍል 21 የሒሳብ ምርመራ

21.1 የማህበሩ ገቢና ወጪ በተመሰከረለት የሒሳብ አዋቂ /ኦዲተር/ በየዓመቱ ከአጠቃላይ ስብሰባ በፊት

ሊመረመር ይገባል፡፡

21.2 ሕጋዊ የምርመራ ሪፖርቶች ለማህበሩ አባላት በቀጣይ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ይቀርባል ወይም

በማህበሩ ድረ ገጽ ላይ ከቀጣዩ አጠቃላይ ስብሰባ በፊት ሊቀርብ ይገባል፡፡

ክፍል 22 ሚስጥር መጠበቅ

Page 24: የኢትዮጵያውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ (ኢመእኩ)ebs-q.org/ConistituionAmharic.pdf · Page 4 of 24 ክፍል 1 የእድር ማህበሩን

www.ebs-q.org Page 24 of 24

22.1 የአባላት የግል መረጃ ዝርዝር የግል ሚስጥር በመሆኑ በአባላትና በሌሎች መካከል የሚደረጉ

መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ግንኙነቶች በከፍተኛ ሚስጥር መያዝ አለባቸው፡፡

22.2 የኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ አባል በእድሩ ማህበር ውስጥ ያሉትን የራሱን

መረጃዎችና ዝዝሮች መመርመርና ትክክል ያልሆኑ መረጃዎችን እንዲሰተካከሉ የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ክፍል 23 የእድሩ መፍረስ

23.1 የእድሩ ማህበር እዳዎቹን ለመክፈል ባለመቻሉና ከምልአተ ጉባኤ ቁጥር በታች የሆኑ አባላት ሲቀሩ

የማህበሩ መፍረስ ግዴታ ነው፡፡ የማህበሩ መፍረስ የማይቀር ከሆነ በዚህ ወቅት ቀሪ የማህበሩ አባላት

የቀረውን የእድሩ ማህበር ንብረት ተጠቅመው የማህበሩን እዳዎች ለመመለስ የሚቻላቸውን ጥረት

በማድረግ፤ ማህበሩን ከማስቆም ጋር የተገናኙ ልውውጦችን በመሉ መዝጋት አለባቸው፡፡

23.2 እድሩ በሚፈርስበት ወቅት ሆነ በሌለም ወቅት የእድሩ ማህበር ‘የብድር ገንዘብ’ ተመን ክፍያ

(nominal value) ለማህበሩ አባለት አይሰጥም፣አያከፋፍልም፡፡

23.3 የቀረውን የኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ ሐብት (ጥሬ ገንዘብም ጨምሮ) እንዴት

መከፋፈል እንዳለበት ለመወሰን ስብሰባ መካሄድ አለበት፡፡

የእድሩ ማህበር መፍረስ በስብሰባው ውሳኔ ከጸደቀ የቀረው የኢትዮጵውያን መረዳጃ እድር በኩዊንስላንድ

ሐብት(ጥሬ ገንዘብም ጨምሮ) ለተመሳሳይ በጎ አድራጊ ድርጅት ወይንም ድርጅቶች ተላልፎ መሰጠት

ግዴታ ነው፡፡

_ _ _ ተፈፀመ _ _ _