በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhicይገኛል፡፡ በዚህም...

82

Upload: duongbao

Post on 03-Feb-2018

298 views

Category:

Documents


18 download

TRANSCRIPT

Page 1: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 2: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው

ሶላትንም በቀን ጫፎች (ጠዋትና ከቀትር በኋላ) ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፤

መልካም ሥራዎች ኃጢኣቶችን ያስወግዳሉና፤ ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው፡፡

(ቁርኣን 11፡-114)

Page 3: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ዛኢባተ የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት

መለኮታዊው መንገድየአዲስ ሙስሊሞች መመሪያ መጽሐፍ፡- ሐሰን ላም (ክፍል 1፣ 2 እና 3)፣ ረምዚ አጀም (ክፍል 4)የአምልኮ የመጀመሪያ መመሪያዎች ፡- ረምዚ አጀም (ማሊኪ)፣ ሰማሕ ማሪ (ሐነፊ)፣ ነጃም ኻጃ (ሐንበሊ)፣ ሰኢማ ዲን (ሻፊዒ)የሰላት ምስላዊ መመሪያ (ዲቪዲ)የሰላት ድምጾች (በድምጽ)የመምህሩ መመሪያ ፡- ሰኢማ ዲን የመምህራን ስልጠና ትምህርት፡- ነዲም ሜሞንየመምህራን ማጎልበቻና ማረጋገጫ ፕሮግራም ፡- ቀይሰር አሕመድ

Page 4: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው

መንገድ

Page 5: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

© Zayed House for Islamic Culture 2015

Published byZAYED HOUSE FOR ISLAMIC CULTUREP.O. BOX 16090, AL-AIN, UNITED ARAB EMIRATESTEL 800555 FAX +971 3 7810633WWW.ZHIC.AE [email protected]

ISBN 978-9948-22-056-5

Commissioned by Zayed House for Islamic Culture, UAE. Produced by Razi Group, Canada, under the supervision of Tabah Foundation, UAE.

ALL RIGHTS RESERVED. Aside from fair use, meaning a few pages or less for nonprofit educational purposes, review, or scholarly citation, no part of this publication may be reproduced, stored in a retrieval system, or transmitted in any form or by any means, electronic, mechanical, photocopying, recording, or otherwise, without the prior permission of the Copyright owner.

ZHIC has no responsibility for the persistence or accuracy of URLs referred to in this publication, and does not guarantee that any content on such websites is, or will remain, accurate or appropriate. All information is correct as of November 2009, but ZHIC does not guarantee the accuracy of such information thereafter.

Printed in UAE© Zayed House for Islamic Culture 2015

አሳታሚዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋምፖ.ሳ.ቁ 16090፣ አል ዓይን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችስልክ 800555 ፋክስ +971 3 7810633ድረ ገፅ፡ WWW.ZHIC.AE ኢ ሜይል፡ [email protected]

የዚህ መጽሐፍ ህትመት ወጪ የተሸፈነው ተቀማጭነቱ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሆነው ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም (Zayed House for Islamic Culture) ነው፡፡ የመጽሐፉ ዝግጅት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሚገኘው ጣባህ ፋውንዴሽን ተጠባባቂነት፣ ካናዳ በሚገኘው

ራዚ ግሩፕ ተካሄደ፡፡

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ በህግ በተፈቀደው መሠረት ከትርፍ ጋር ተያያዥነት ለሌላቸው ትምህርታዊ ዓላማዎች፣ ለሒሳዊ ዳሰሳ፣ ወይም ለምሁራዊ ሥራዎች ማጣቀሻነት ካልሆነ በስተቀር፣ ከቅጂው ባለመብት በጽሑፍ የተሰጠ ፈቃድ ሳይገኝ ከዚህ ህትመት ውስጥ አንዲትም አንቀፅ ቢሆን ማባዛት፣ በቤተ መዛግብት ማኖር፣ በኤሌክትሮኒክ፣ በሜካኒካዊ መንገድ፣ በፎቶኮፒ፣ በድምፅ

መሣሪያ በመቅዳት፣ ወይም በሌላ በማንኛውም ቅርፅ ወይም መንገድ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡

በዚህ ህትመት ውስጥ የተጠቀሱ ድረ ገፆችን ዘውታሪነት ወይም በውስጣቸው የሚገኙ መረጃዎችን ትክክለኝነት በተመለከተ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ምንም ዓይነት ኃላፊነትን አይወስድም፤ እንዲሁም በእነዚህ ድረ ገፆች ስለሚገኙ ማናቸውም ይዘቶች ትክክለኛነት ወይም ተስማሚነት ዋስትና አይሰጥም፡፡ በዚህ ህትመት ውስጥ ያሉ መረጃዎች እስከ ኖቬምበር 2009 ባለው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ ናቸው፤ ያም ሆኖ ከዚህ በኋላ ባለው ጊዜ የመረጃዎቹ ይዘትም ሆነ ትክክለኛነትን

በተመለከተ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ዋስትና አይሰጥም፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ ታተመ

© ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም 2015

Page 6: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ሁለተኛ እትም

መለኮታዊው

መንገድ

የአምልኮ የመጀመሪያ መመሪያዎች

የኢማም መሐመድ ቢን ኢድሪስ አልሻፊዒይ (ረ.ዐ) አስተምህሮ ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀ

ሳኢማ ዲን

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም አል ዓይን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች

Page 7: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ስለ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ለተወሰነ ዓላማ የተቋቋመ፣ ከልዑል አልጋ ወራሹ ሸንጎ ጋር ተቀራርቦ

የሚሠራ ነፃ ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ የተመሠረተው በቀድሞው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ገዢ ሸይኽ ዛይድ

ቢን ሡልጣን አል ናህያን ሲኾን፣ እ.አ.አ በ2005 በክቡርነታቸው ሸይኽ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ነህያን፣

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዚደንት እና የአቡዳቢ ገዢ በይፋ ተመርቆ ሥራውን ጀምሯል፡፡

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ኢስላማዊ ባህልን በማስፋፋት በተለያዩ ብሄሮች መካከል የግንኙነት ድልድይ

በመገንባት ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ተቋሙ ስለኢስላም እና ኢስላማዊ ባህል የማወቅ ፍላጎት

ያላቸው አዳዲስ ሙስሊሞችና ግለሰቦችን በደስታ ይቀበላል፡፡ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም አዳዲስ

ሙስሊሞች ከማኅበረሰብ ጋር ውህደት ለመፍጠር የሚረዳቸውን ርዕይና አቅጣጫ በመስጠት በበርካታ

ቋንቋዎች ለማስተማር ያለመ ልዩ ትምህርታዊ መርኃ ግብር አበልጽጓል፡፡ በተጨማሪም፣ የቁርአን የቃል ጥናት

እና የአረብኛ ቋንቋ፣ የሐጅ አገልግሎቶች፣ የህዝብ ቤተ መጻሕፍት፣ እንዲሁም ባህላዊና በአንድ ጭብጥ

ላይ የተመሠረቱ የጉዞ ሁነቶችና ስፖርቶችን የመሳሰሉ ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ያካተቱ ልዩ መርኃ

ግብሮችን ያቀርባል፡፡

ጥቂት ስለ ሸይኽ ዛይድ

ሸይኽ ዛይድ እ.አ.አ በ1918 በአል ዓይን ከተማ ተወልደው አብዛኛውን

የህፃንነት ጊዜያቸውን በዚያው አሳልፈዋል፡፡ የአቡዳቢ ገዢ ሆነው በርካታ

የስኬት ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ፣ እ.አ.አ በ1971 በአዲስ መልክ

የተመሠረተውና ዋና ከተማይቱን አቡዳቢን ጨምሮ የሰባት ኤሚሬቶች

ፌደሬሽን የሆነው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መሪነትን ጨብጠዋል፡

፡ ሸይኽ ዛይድ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን እጅግ ፈጣን ለውጥ

በሚታይበት ወቅት ላይ በመምራት፣ ለአያሌ አሥርት ዓመታት ከባድ

ችግሮችን ላሳለፈው አካባቢ ሀብት፣ ትምህርትና መልካም ዕድሎችን

አስገኝተዋል፡፡ ሸይኽ ዛይድ በህዝቡ እና በአገሩ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት

የነበራቸውና፣ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ የአብሮ መኖር፣

የመቻቻል እና የመከባበር ባህል እንዲዳብር ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሰው

ነበሩ፡፡ ሸይኽ ዛይድ እ.አ.አ. በ2004 ከዚህች ዓለም የተለዩ ሲኾን፣

አቡዳቢ ውስጥ ከሚገኘውና በስማቸው ከሚጠራው ታላቅ መስጂድ

አጠገብ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ በዙፋናቸውም ላይ የበኩር ልጃቸው

የተከበሩ ሸይኽ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ተተክተዋል፡፡

Page 8: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መልዕክት ከዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም

ለአላህ (ሱ.ወ) ክብር ይገባውና በተባበሩት ዐረብ ኤመሬቶች ውስጥ ኢስላምን የሚቀበሉ ሰዎች ቁጥር

በእጅጉ እየጨመረ መጥቷል ፡፡ የዛይድ ኢሰላማዊ ባህል ማዕከል ከምስረታው አንስቶ ኢስላምን ለሚቀበሉ

ሰዎች አስፈላጊውን እገዛና ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉበትን ሁኔታዎች እያመቻቸ

ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ- ትምህርት ማዘጋጀት አስፈላጊ

ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከዚህ በመነሳት ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ይህን በማኅበረሰቦችና ባህሎች መካከል የሚታይ የግንዛቤ

ክፍተት ለማጥበብ ወይም ለመዝጋት በሚደረገው ጥረት ላይ መሪ ሚና ለመጫወት የሚጥር ተቋም

ነው፡፡ ዓላማችን ውጤታማ የባህል ልውውጥ ሐሳቦችን በማራመድ፣ ህዝቦች በተሻለ ሁኔታ እርስ በእርስ

እንዲተዋወቁና አንዳቸው የሌላውን እሴት እንዲያደንቁ መርዳት ነው፡፡ የዚህ ጥረት አንዱ ክፍል በልዩ ልዩ

ርዕሰ ጉዳዮች ዐውድ የተሰናዱና ለዚህ ዓላማ ጠቀሜታ ያላቸው ስራዎችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ዓለምን

ከኢስላም እና ከአንድ ቢሊዮን ከሚበልጡት ተከታዮቹ ጋር ማስተዋወቅ ነው፡፡

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ከኢስላም ጋር ተዋወቁ! የተሰኘውን ይህን ተከታታይ ቅፅ ሲያቀርብ ከፍተኛ

ደስታ ይሰማዋል፡፡ በተከታታይ ቅፆች የሚቀርቡት ስራዎች በዘመናችን እጅግ የተዛባ ግንዛቤ ሰለባ በሆኑት

ህዝቦች ዙርያ ለየት ያሉ እይታዎችን ያቋድሳሉ፡፡ ቅፆቹ የዘመናችንን የተለዩ ተግዳሮቶች ተረድቶ ተገቢ

አፀፋ በመስጠት ዓላማ በመገናኛ ብዙኃን ውጤቶች ላይ የተካሄዱ ዙርያ መለስ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ

የተዘጋጁ ናቸው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚገኘው ጧባህ ፋውንዴሽን

እና ካናዳ የሚገኘው ራዚ ግሩፕ ይህ ልዩ እና ኪናዊ አቀራረብ የተላበሰ ፕሮጀክት እጅግ ስኬታማ ይሆን

ዘንድ ላደረጉት ያልተቆጠበ ጥረት ምስጋናውን ለማቅረብ ይወዳል፡፡ በዚህ ቅፅ ውስጥ የቀረቡት ሥራዎች

ስለ ኢስላማዊ መርኆች እና ስለ ሙስሊም ህዝቦች አንባቢያንን በማሳወቅ ረገድ በጣም ጠቃሚ እንደሚሆኑ

ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህ አነስተኛ ጥረት የእርስ በርስ መግባባት፣ መልካም ፈቃድና ፍሬያማ የአብሮ መኖር

ድልድይ ከመገንባት አኳያ የመጀመርያው እርምጃ ነው፡፡

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም

Page 9: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 10: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ስለደራሲዋ

ሳኢማ ዲን በአሁኑ ጊዜ መምህርትና የሎቲ ትሪ ድርጅት ምክትል የመምሪያ ኃላፊ ናት፡፡ በተጨማሪም የራዚ

ቡድን (www.razigroup.com) በትምህርት ተቋም ውስጥ የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ አማካሪም

ናት ከአምስት ዓመታት በፊት ካናዳ በሚገኘው ፒል ዲስትሪክት ትምህርት ቤት መምህርት ነበረች፡፡

ሳኢማ በኢዱኬሽን የመጀመሪያ ዲግሪዋን የተከታተለችው ቶሮንቶ በሚገኘው ኦንታሪዮ ኢንስቲትዩት ሲሆን ከዚያ

መልስ ኢስላማዊ እውቀትዋን ማዳበር ጀመረች፡፡ ደራሲዋ በአሁኑ ጊዜ በብራምፕተን ከባለቤቷና ከሁለት ልጆቿ ጋር

ትኖራለች፡፡

Page 11: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የአነባበብ መፍቻዎች

ی/آ/ا አሊፍ አ

ب ባ በ

ت ታእ ተ

ث ሣ ሠ

ج ጂም ጀ

ح ሐ ሐ

خ ኻ ኸ

د ዳል ደ

ذ ዛል ዘ

ر ራ ረ

ز ዘይን ዘ

س ሲን ሰ

ش ሺን ሸ

ص ሷድ ሷ

ض ዷድ ደ

ط ጧ ጠ

ظ ዟ ዘ /በጥርስና ምላስ/

ع ዓይን ዐ

غ ገይን ገ

ف ፋ ፈ

ق ቃፍ ቀ

ك ካፍ ከ

ل ላም ለ

م ሚም መ

ن ኑን ነ

ه ሃእ ሀ

و ወው ወ

ي ያ የ

Page 12: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የዐረብኛ ምሕጻረ ቃላት

(ሱ.ወ)፡- (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ከሁሉ ነገሮች የጠራና የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ፡፡

(ሰ.ዐ.ወ)፡- (ስል-ላሁ ዐለይሂ ወሰልለም) የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን፡፡

(ረ.ዐ)፡- (ረዲየል-ላሁ ዐንሁ፣ ረዲየል-ላሁ ዐንሃ፣ ረዲየ-ላሁ ዐንሁም) መልካም ስራውን ይቀበለው፣ መልካም ስራዋን ይቀበላት፣ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው፡፡

(ዐ.ሰ)፡- (ዐለይሂ አስ-ሰላም) የአላህ ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን፡፡

Page 13: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ማውጫ

ሰንጠረዦችና ስዕላዊ መግለጫዎች 1

መቅድም 3መግቢያ 4

ክፍል አንድ፡- ለሶላት መዘጋጀት 6ምዕራፍ 1 ንጽሕናና እምነት 8

ውሃ ለንጽሕና 8ምዕራፍ 2

አካላዊ ንጽሕናን ማሟላት 9የሃፍረተ ገላን ንጽህና መጠበቅ 9

ምዕራፍ 3ለአምልኮታዊ ተግባር ንጽሕናን ማሟላት 11ዉዱእ እና አፈጻጸሙ 11ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች 15ዉዱዕ ማድረግ የሚያስፈልገው 15ጉስል (መላ ሰውነትን መታጠብ) 16የግዴታ ትጥበት ምክንያቶች 17በትልቁ እድፈት (ሐደስ) ላይ ሆነን ልንፈጽማቸው

የተከለከሉ ተግባራት 17

ምዕራፍ 4የወር አበባ 18የወር አበባ የሚጀምርበት ጊዜና የሚከለከሉ ነገሮች 18የወር አበባ መቼ ይጠናቀቃል፣ ሲጠናቀቅስ ምን

ይደረጋል? 18የወር አበባ ካበቃ በኋላ የሚኖር የደም መፍሰስ 18መደበኛ ያልሆነ የደም መፍሰስ 18ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ የወር አበባ 19

ክፍል ሁለት፡- ስግደት (ሶላት) 20

ምዕራፍ 5

ግዴታ ሰላቶች 22የሶላት ወቅቶች፣ ሥያሜዎቻቸውና የአፈጻጸም

ዑደታቸው 22

ሶላትን በወቅቱ መስገድ 24የሶላት ወቅትን ማሳለፍ 24

ምዕራፍ 6የሶላት ጥሪ 25

ምዕራፍ 7እንዴት እንሰግዳለን? 26

ሁለት ዙር (ረከዓ) ሶላት አስጋገድ 27 ሦስት ዙር (ረከዓ) ሶላት አሰጋገድ 33

አራት ዙር (ረከዓ) ሶላት 33

ምዕራፍ 8በሕብረት ስለ መስገድ 34

በሕብረት የሚሰገደው እንዴት ነው? 34

ምዕራፍ 9ሌሎች ስግደቶች 35

እንዲሰገዱ የሚመከሩ ሱንና ሶላቶች 35 35የጁምዓ ሶላት 35

የዒድ ሶላት 36የተራዊሕ ሶላት 36የመንገደኛ ሶላት 36

Page 14: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል ሶስት፡- የረመዷን ፆም 38

ምዕራፍ 10ግዴታዎችና ቅድመ-ሁኔታዎች 40መጾም ያለበት ሰው 40የማይጾመው ሰው 40ጾምዎ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ 40

ምዕራፍ 11ፆምን መግደፍና

የሚያስከትላቸው ውጤቶች 41ፆምን ማካካስ 41ያለ ሥርየት መቀጮ (ከፍፋራህ) ፆምን መተካት 41ካሣ (ፊድያ) 42

ምዕራፍ 12የረመዷንን ቀን እንዴት እንፆማለን 43

ምዕራፍ 13የተፈቀዱና የተከለከሉ

የፆም ዓይነቶች 44የተፈቀዱ የፆም ዓይነቶች 44የተከለከሉ የፆም ቀናት 44

ማጠቃለያ 46

የቃላት መፍቻ 48

የጸሎት ቃላት ድምጾች 52

Page 15: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 16: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ሠንጠረዦችና ስዕላዊ መግለጫዎች 1

ሠንጠረዦችና ስዕላዊ መግለጫዎች

መግቢያሠንጠረዥ የመለኮታዊው ህግ መሰረታዊ ድንጋጌ

ክፍል ሁለት፡- ሶላት

ምዕራፍ 5 የግዴታ ሶላቶችስዕል የሰላት ዙር (ረከዓ)ስዕል አምስቱ የግዴታ ሰላቶች

ምዕራፍ 6 የሶላት ጥሪስዕል አዛንና ኢቃማ

ምዕራፍ 7 የአሰጋገድ ሥርዓትስዕል የሰላት ዙር (ረከዓ) በስዕል

ምዕራፍ 9 ሌሎች ሶላቶችስዕል የፊትና የኋላ ሱና ሶላቶች

Page 17: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 18: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መቅድም 3

«ነገሮችን ቀላል አድርጉ፡፡ አታክብዱ፡፡»1 ይህ መጽሐፍ የሚከተለው ታላቅ የትምህርት መሠረት በዚህ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ላይ ጥገኛ ነው፡፡ ታዋቂው ምሁር ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒ ይህን ሐዲስ አስመልክተው ሲናገሩ፤ «አባባሉ ለአዳዲስ ሙስሊሞች እጅጉን ተስማሚ ነው» ብለዋል፡፡

ይህ የመማሪያ መጽሐፍ እስልምናን አዲስ ለሚቀላቀሉ ሰዎች የተዘጋጀ በመሆኑ ይህን የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) መመሪያ በልባቸን አኑረናል፡፡ ኢብኑ ሐጀር ከላይ የጠቀሱትን ሃሳብ በማጠናከር «ስለዚህ እውቀት ደረጃ በደረጃ ሲመጣ ነው የሚሻለው፡፡ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ከጅምሩ ቀላል ከሆነ ለሚማረው ሰው የሚማርክ ይሆናል፡፡ በፍቅር እየተቀበለው እንዲመጣም ያስችለዋል» ብለዋል፡፡

ይህ «መለኮታዊው መንገድ፡-የአምልኮ የመጀመሪያ መመሪያዎች» የተሰኘው አነስተኛ መጽሐፍ እንደ ግብ ይዞ የተነሳው አዳዲስ ሙስሊሞችና ለእስልምና ተግባራት ጀማሪ የሆኑ ነባር ሙስሊሞች አምስት ወቅት ሶላትና የረመዷን ጾምን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በፈጸሙት መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መተግበር እንዲችሉ በቂ መመሪያዎችን መስጠት ነው፡፡2

ይህን ከዳር ለማድረስም በዝግጅቱ ወቅት የሚከተሉትን ውሳኔዎች መውሰድ አስፈልጓል፡-ሀ.ነባር እውቀትን የሚጠይቁ ጉዳዮችና አገባባዊ ትርጓሜ ያላቸው የዐረብኛ ቃላት በጥቂቱ ብቻ እንዲኖሩ ተደርጓል፡፡ለ.ግዴታና የሚበረታቱ ተግባራት በመካከላቸው ምንም ልዩነት ሳይኖር አንድ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ሐ.አልፎ አልፎ ወይም በተለየ ሁኔታ ለሚያጋጥሙ ጉዳዮች የሚሆኑ መልሶች አልተካተቱም፡፡መ.ከአምልኮ ተግባራት ጋር የተያያዙ ማረጋገጫዎች፣ ምክንያታዊነቶች፣ ጥቅሞች እና የመደንገጋቸው ጥበቦች እንዲካተቱ አልተደረገም፡፡ሠ.ምክሮችና ተያያዥነት ያላቸው ነጥቦች በመጽሐፉ ውስጥ እጥር ምጥን ባለ ቋንቋ እንዲጠቃለሉ ተደርጓል፡፡ ለአብዛኛዎቹ እስልምናን የተቀበሉ ሰዎች ተግዳሮት የሚፈጥርባቸው ነገር ቢኖር ቁርኣን ከመቅራታቸውና ውዳሴዎች ከመማራቸው ጐን ለጐን ዉዱእና ሶላትን መማር ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ቀላል ለማድረግ የምስልና የድምጽ ማስተማሪያዎችን በማዘጋጀት ከመጽሐፉ ጋር አያይዘን አቅርበናል፡፡ አክለንም በአባሪ ገጽ ላይ የዕለታዊ ተግባራት ውዳሴዎችና ጸሎቶችን ከትክክለኛ አነባበባቸው ጋር በጥንቃቄ በማዘጋጀት አቅርበናል፡፡

ይህን መመሪያ ብቁ ከሆነ ሙስሊም መምህር ጋር ሆነው እንዲማሩት ቢበረታታም ቀለል ባለ የአቀራረብ ስልትና በጥንቃቄ የተዘጋጀ በመሆኑ ራሱን በራሱ ለሚያስተምር ሰውም ምቹ ነው፡፡ በእውነቱ ይህ መጽሐፍ ሶላትና ፆምን በትክክለኛ ሁኔታ ለመተግበር መንገዱን ያመቻቻል የሚል ተስፋ አለን፡፡ ሌሎች መሠረታዊ ማስተዋወቂያ ትምህርቶች «መለኮታዊው መንገድ፡- የአዲስ ሙስሊሞች መመሪያ መጽሐፍ» በተሰኘው ተጓዳኝ መጽሐፍ ውስጥ ተካተዋል፡፡

መቅድም

Page 19: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ:የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት4

መግቢያ

እስልምና የተሟላ እምነት ነው፡፡ አስተምህሮቶቹም መንፈስ ላይ ብቻ ያተኮሩ ወይም አዕምሮን ብቻ የሚያናግሩ መግለጫዎች አይደሉም፡፡ በእስልምና አዕምሮ፣ ሰውነትና ነፍስ ፈጣሪያችንን ለማላቅ አንድ ላይ ይዋሃዳሉ፡፡

ከሌሎች እምነቶች አንጻር እኛ ልዩ በሆነ ስፍራ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ የሆነው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሰጡ የነበሩትን አስተምህሮዎች በትክክል ማወቅ የምንችል በመሆናችንና በዚህም ምክኒያት በእርግጠኝነትና በራስ መተማመን እርሳቸው ሲያመልኩበት በነበሩበት ሁኔታ ፈጣሪን ማምለክ የምንችል በመሆኑ ነው፡፡ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያመልኩ በነበሩበት ዘዴ አላህን ማምለክ መማር ማለት በዚህች ምድር መንፈሳዊ ምሉዑነትንና በመጪው ዓለም ደግሞ ዘልዓለማዊ ሕይወትን የመጐናጸፊያ ቁልፍን ማግኘት እንደማለት ነው፡፡ ይህ ቁልፍ ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ በምሁራን ሰንሰለት ተጠብቆ እኛ ዘንድ ሊደርስ ችሏል፡፡

በዚህ የምሁራን ሰንሰለት አማካኝነትም አላህ (ሱ.ወ) የቁርኣንንና የነብዩን ፈለግ (ሱንና) በጽሑፍም ሆነ በአተረጓጐም ምንም ዓይነት ብልሽትና መበረዝ ሳይኖርባቸው ጠብቆ አቆይቷቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ብቁና ለተገቢው ጥያቄ ትክክለኛና አጥጋቢ ምላሽ ከሚሰጡና የእውቀት መነሻቸው ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ከሰሐቦቻቸው የተመዘዘ ከሆኑት ምሁራን እውቀትን መቅሰም እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- “… ¾Tታ¨<lU wƒ§’<. ¾°¨<kƒ”

vKu?„‹ ÖÃl::” (አን-ነሕል፡ 43)

ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን አንስቶ እስከአሁን ድረስ ትክክለኛ እስላማዊ የአምልኮ ተግባራትን የሚጠብቅና የሚያስተላልፍ የትምህርት ባህል ሁልጊዜ ሲፈጠር ኖሯል፡፡ ምሁራንና የእነርሱ ደቀመዛሙርት የመለኮታዊውን ሕግ መመሪያዎችና ከሁለቱ ዋነኛ የሃይማኖታችን ምንጮች ከሆኑት ቁርአንና ሱና የተውጣጡትን ህግጋቶች በጥንቃቄ መዝግበው አስተላልፈዋል፡፡ እነዚህ ህግጋቶችና ከሁለቱ ዋነኛ ምንጮች ተጨምቀው የተውጣጡበት ዘዴ በመዝሀብነት ወይም “መንገድነት” ተጠብቋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ተከታይነት ያላቸው አራት ኢስላማዊ የሕግ ትምህርት ቤቶች (መዝሃቦች) አሉ፡፡ እነርሱም የኢማም አቡ ሐኒፋ፣ የኢማም ማሊክ፣ የኢማም አሽ-ሻፊዒይና የኢማም አሕመድ ኢብን ሐንበል ትምህርት ቤቶች (መዝሃቦች) ናቸው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡላችሁ ትምህርቶች የተወሰዱት ከእውቁና ታላቁ የጋዛ ምሁር ኢማም አቡ ዐብዱላህ ሙሐመድ ኢብን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይ (አላህ ይዘንላቸውና) [እ.ኤ.አ ከ767-820 / እ.ሂ.አ ከ150-204] እስላማዊ የሕግ ርዕዮት (መዝሃብ) ነው፡፡

የዚህ አነስተኛ መጽሐፍ ዓላማ አዲስ ወደ እስልምና የተቀላቀሉ ሰዎችና እስልምናን መተግበር የጀመሩ ነባር ሙስሊሞች የአምስት ወቅት ሶላቶችንና ዓመታዊውን የረመዷንን ወር ፆም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሠሩበት መንገድ እንዲተገብሩ በቂ መመሪያ መስጠት ነው፡፡

Page 20: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መግቢያ 5

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል «እውቀትን ለማግኘት ለተጓዘ አላህ የጀነትን መንገድ ያገራለታል፡፡»3 ይህንን እውቀት ለመፈለግ በምታደርጉት ጥረት ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ የመጀመሪያውን እርምጃ እየተራመዳችሁ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ እንደ ሌሎች መጽሐፍት አንዴ አንብበን የምናስቀምጠው እንዳልሆነ አስታውሱ፡፡

የአምልኮ ተግባራችሁን በትክክል መተግበር እንደምትችሉ እርግጠኛ እስክትሆኑ ድረስ መጽሐፉን ደጋግማችሁ አንብቡት፡፡አንዳች ጥያቄ አሊያም የተለየና በመጽሐፉ

ያልተዳሰሰ ጉዳይ ካጋጠማችሁ አስተማሪያችሁ መልሱን ማግኘት እንደምትችሉት የት እንደሆነ ይጠቁማችኋል፡፡

የዚህ መጽሐፍ አዘጋጆችና አርታኢያን ከመጽሐፉ ተጠቃሚ እንድትሆኑና መልዕክቱም ለመረዳትና ለመተግበር ቀላል እንዲሆንላችሁ ከልብ ዱዓ (ጸሎት) ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ የሚገኝ መልካም ነገር ሁሉ ከአላህ ነው፡፡ አንዳች ስህተት ቢኖር ከኛ ነው፡፡እርሱን የሚያስደስተውን ነገር እንከውን ዘንድ አላህ ስኬትን ያድለን፡፡ አሚን!

አዲስ ወደ እስልምና ለገባ ሰው መሰጠት የሚገባቸው ዋነኛ ትምህርቶች ካለነርሱ የኢስላም ህልውና የማይረጋገጥባቸው

መሠረታዊና አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን ነው፡፡ – (ሸይኽ ሐቢብ አሕመድ መሽሁር)

ኢስላማዊው ሕግ የሰዎችን ተግባራት በአጠቃላይ እንደሁኔታቸው በአምስት ክፍሎች አስቀምጧቸዋል፡፡

ድንጋጌ ዐረብኛ መግለጫ

የግዴታ ተግባር ፈርድ/ዋጂብመተግበራቸው ግድ የሆኑ ቢሠሩ ምንዳ የሚገኝባቸው ባይተገበሩ ተጠያቂ የሚያስደርጉ

ተግባራት ናቸው፡፡

የተወደደ ተግባር ሱንና/መንዱብበመተግበራቸው ምንዳ የሚገኝባቸው ባይተገበሩ ተጠያቂ የማያስደርጉ ተግባራት

ናቸው፡፡

የተፈቀደ ተግባር ሙባሕምንዳ የማያስገኙ የማያስኮንኑም፤ በመልካም እሳቤ ከተተገበሩ ግን ምንዳን ሊያስገኙ

የሚችሉ ተግባራት፡፡.

የተጠላ ተግባር መክሩህየማይበረታቱና ቢሠሩ ተጠያቂ የማያደርጉ፤ ነገር ግን የራቃቸው ሰው ምንዳ

የሚያገኝባቸው ተግባራት፡፡

የተከለከለ ተግባር ሐራምክልክል የሆኑና በመሠራታቸው ተጠያቂ የሚያስደርጉ ተግባራት፤ የራቃቸው ሰው

ምንዳ ያገኝባቸዋል፡፡

Page 21: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 22: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ለሶላት መዘጋጀትእና”} ÁS“‹G< JÃ! ¨Å fLƒ uqT‹G< (KSqU vcv‹G<) Ñ>²?. ò„‰‹G<”. እЉ‹G<”U

እeŸ ¡`•‹ እÖu<:: ^f‰‹G<”U (u¨<H) አብc<:: እÓa‰‹G<”U እeŸ l`ßUßT>„‹

(እÖu<)... (አል-ማኢዳህ፡-6)

Page 23: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ:የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት8

ንጽሕናና እምነት

«ንጽሕና የእምነት ግማሽ ነው»4

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህንን ሐዲስ መናገራቸው ለተከታዮቻቸው ውስጣዊና ውጫዊ ንጽሕና ምን ያህል

ከፍ ያለ ግምት እንደሚሰጠው ግልጽ ያደርጋል፡፡

የእስልምና ተግባራትን መፈጸም በቀጠልክ ቁጥር አላህን ለመገዛት አካላዊና የአካባቢ ንጽህናን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል በዝርዝር ትረዳዋለህ፡፡ንጽሕናን በተመለከተ በእስልምና ሁለት ዓይነት ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነርሱም አካላዊ ንጽሕናና መንፈሳዊ ንጽሕና ናቸው፡፡ ሁለቱም ውሃን በመጠቀም የሚተገበሩ ናቸው፡፡

ውሃ ለንጽሕና

ውሃውንም በርሱ ሊያጠራችሁ …. ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውስ) (አል-አንፋል፡-11)

ለአካላዊና መንፈሳዊ ንጽህና የሚያስፈልገው ውሃ ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ውሃው የዝናብ፣ የባህር፣ የወንዝ፣ የጉድጓድ፣ የበረዶ ወይም የቧንቧ ይሁን ተፈላጊው ውሃው ነጃሳ (ቆሻሻ) እስካልገባበት ድረስ አሊያም ጣእሙ፣ መልኩ ወይም ጠረኑ እስካልተለወጠ ንጹሕ ነው ብሎ በማሰብ ለትጥበት መጠቀም ይቻላል፡፡ በተፈጥሮ ውሃው አረንጓዴ ያለበት፣ በጭቃ የደፈረሰ ወይም ጨዋማ ቢሆንም ለትጥበት መጠቀም ይቻላል፡፡

ልብ ይበሉ፡-ውሃው፡ ስለመቆሸሹ፡ ምንም ዓይነት አሳማኝ

ማስረጃ ከሌለህ ውሃው ንጹህ ነው ብለህ በመቀበል ልትጠቀምበት

ትችላለህ፡፡ ውሃን ልንጠቀምበት አንችልም የሚያስብለን፡-

መልኩ፣ ጣዕሙ ወይም ጠረኑ ከተለወጠ ብቻ ነው፡፡

1

Page 24: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 1፡- ለሶላት መዘጋጀት 9

2

ልብስህንም አጥራ (አል-ሙደሲር፡-4)

ሶላት ከመስገድህ በፊት አካላዊ ንጽሕናህን መጠበቅህ ግድ ነው፡፡ ይህም ማለት ሰውነትህ፣ ልብስህና የምትሰግድበት ቦታ ከነጃሳ ማለትም እንደ ደም፣ ሽንትና ሰገራ ከመሳሰሉት ቆሻሻ ነገሮች የጸዱ መሆን አለባቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች በመለኮታዊው ሕግ የቆሸሹ ነገሮች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ በመሆኑም አምልኮታዊ ተግባር ከመፈጸም በፊት ሊወገዱ ይገባል፡፡ አካላዊ ንጽሕና እነዚህን ነገሮች በውሃ የማስወገድን ተግባር ያጠቃልላል፡፡

ልብ ይበሉ፡-ምናልባት ንጹሕ ስለሆኑና ስላልሆኑ ነገሮች

ስናስብ አእምሮ ላይ ውልብ በማለት ግራ ሊያጋቡን ወይም

ሊያስጨንቁን ይችሉ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ በእኛ ሃይማኖት

ማስረጃ እስካልተገኘላቸው ድረስ ሁሉም ነገሮች በተፈጥሯቸው

ንጹሕ ናቸው የሚለውን አቋም ይውሰዱ፡፡

የሀፍረተ ገላን ንጽህና መጠበቅ

…አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል»(አት-ተውባህ፡ 108)

ዓይነ ምድርንም ሆነ ፈሳሽ ሽንትን ካስወገድን በኋላ ሃፍረተ ገላዎቻችንን ማጽዳት ግዴታ ነው፡፡ ወደ ሶላት ከመግባታችን በፊት እነዚህ የአካል ክፍሎቻችን ስለመጽዳታቸው እርግጠኞች መሆን አለብን፡፡

የብልትንም ሆነ የሰገራ መውጫ ንጽሕናን ለመጠበቅ ተመራጩ መንገድ በቅድሚያ በወረቀት መጠቀምና ኋላም በውሃ ማጠብ ነው፡፡ ምናልባት እነዚህ የቆሸሹ ነገሮች በሰውነት ወይም በልብስ ላይ ቢረጩ የተረጩበትን ማበስ (መጥረግ) ብቻ በቂ ስላልሆነ ቦታውን በውሃ ማጠብ ግዴታ ነው፡፡ በውሃ ከማጠባችን በፊት ውሃ ሽንትም ሆነ ዓይነ-ምድር ከሰውነታችን ሙሉ በሙሉ ተወግዶ መጠናቀቁን እርግጠኛ መሆን

አካላዊ ንጽሕናን ማሟላት

Page 25: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ:የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት10

አለብን፡፡ በተለይ የሚወጣው ነገር ከሰውነታችን ሙሉ በሙሉ መወገዱን እዚያው መጸዳጃ ቤት በመቆየትና በሆዳችን አካባቢ ያሉ ጡንቻዎችን በማኮማተርና ቀስ አድርገን በመጭመቅ እንዲሁም በማለብ ማረጋገጥ አለብን፡፡ በተለይ ወንዶች መሽኒያቸውን በመጫን የሚወጣው ነገር በደንብ መውጣቱንና መንጠባጠብ ማቆሙን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ተግባር "ኢስቲብራእ" የሚባል ሲሆን ማድረጉ ግዴታ ነው፡፡

1 ወደ መፀዳጃ ቤት ሲገባ ግራ እግራችንን በማስቀደም «ቢስሚላህ አሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል-ኹቡሢ ወልኸባኢሥ» እንላለን፡፡ ትርጉሙም «በአላህ ስም አላህ ሆይ! ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ» ማለት ነው፡፡

2 ስንጸዳዳ ንጽሕናችንን ጠብቀን መሆን አለበት፡፡ 3 ከዚያ በወረቀት እናደራርቃለን (እስቲብራእ

እናደርጋለን)

4 በቀኝ እጃችን ውሃ በመጨመር በግራ እጃችን ውሃ ሽንትና ሰገራ የወጣበትን አካላችንን በደንብ እናጥባለን፡፡

5 ሁል ጊዜ ሁለት እጆችህን መታጠብ አትርሳ፡፡

6 ከመጸዳጃ ስንወጣ ቀኝ እግራችንን ማስቀደምና ይህንን ዱዓ ማድረግ አለብን «ጉፍራነከ» ትርጉሙ፡- «ጌታዬ ሆይ! ምህረትህን እለምንሃለሁ» ማለት ነው፡፡

ከስድስተኛው መቶ ዘመን ጀምሮ የግል ንጽህናችንን እንድንጠብቅ ኢስላም ሲያስተምረን ቆይቷል፡፡ ሃፍረተ ገላችንን በውሃ ማጠብ ያለውን ጥቅም የሕክምና ምንጮች ማሳወቅ የጀመሩት ግን ገና በቅርቡ ነው “

Page 26: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 1፡- ለሶላት መዘጋጀት 11

አካላዊ ንጽሕናህን አንድ ጊዜ መጠበቅህን ካረጋገጥክ በኋላ ሥግደትህን በተሟላ መንገድ ለመፈፀም ማተኮር ትችላለህ፡፡ ሶላት ከአላህ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝህ መንገድ ነው፡፡ በመሆኑም ንጹህ ሆነህ መቅረብህ ለዚያ ታላቅ ግንኙነት ብቃት እንዲኖርህ ያደርጋል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ንጽሕና (ጡሃራ) የሌለውን ሶላት አላህ አይቀበልም፡፡”5

መንፈሳዊ ንጽህና ማለት ከራስህ ላይ መንፈሳዊ ዕድፈትን (ሐደስ) ማስወገድ ነው፡፡ "ሐደሥ" በተለያዩ ሕጋዊ የሆኑ ሁኔታዎች ይፈጠራል፡፡ የሐደስ ሁኔታ አንድ ጊዜ ከተከሰተ ሶላትንና ሌሎች መሰል አምልኮታዊ ተግባራትን እንዳይፈጸሙ ይከላከላል፡፡ ይህ ሐደስ አነስተኛ ወይም ትልቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ትልቁ ሐደስ ሊጸዳና ሊወገድ የሚችለው ሙሉ አካልን (ሰውነትን) በመታጠብ ነው፡፡ ይህ መሰሉ ቆሻሻ የማስወገድ ተግባር "ጉስል" በሚል ስያሜ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ሥርዓት በአላህ ፈቃድ ወደ ኋላ ላይ በዝርዝር እንመለስበታለን፡፡

ትንሹ ሐደስ ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ምክንያት የሚከሰት ነው፡፡ ለምሳሌ አየር ከታች በኩል ሲወጣ ወይም ሽንት በመሽናት፡፡ ይህም የሚወገደው በአነስተኛው ትጥበት (ውዱዕ) ነው፡፡

ልብ ይበሉ ውሃ በጠፋበት አሊያም መጠቀም በማይቻልበት

ሁኔታ የሶላት ወቅት ከደረሰ ለሶላት የሚያበቃ መንፈሳዊ

ንጽሕና የሚደረግበት ሌላ አማራጭ አልለ፡፡ ይኸውም ደረቅ

አፈርን መጠቀም ሲሆን "ተየሙም" ይባላል፡፡

ዉዱእ እና አፈጻጸሙዉዱእ መደረግ ያለበት በንጹሕ ውሃ ነው፡፡ ዉዱእ በምታደርጉበት ጊዜ ውሃ ወደ ቆዳችሁ አልፎ እንዳይገባ የሚከለክል አንዳች ነገር ማለትም እንደ ቅባት፣ የመዋቢያ ኬሚካሎች (ሜካፕ)፣ ቀለም፣ የጥፍር ቀለም ካለ በቅድሚያ ሙልጭ አድርጋችሁ በማጠብ ማስወገድ ይግገባል፡፡ ዉዱእ በምታደርጉበት ጊዜ ከዚህ በታች ያለውን መመሪያ ሳታዛንፉ ተራውን ጠብቃችሁ መከወን አለባችሁ፡፡

ለአምልኮታዊ ተግባር ንጽሕናን ማሟላት3

Page 27: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ:የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት12

1 ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ርረሒም (በአላህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ርኅሩኅ በሆነው እንላለን፤

2 ዉዱእ ስለማድረግ በልብ ማሰብ (ንያ ማድረግ) ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሃሳብ ማለትም በልብ ውስጥ ዉዱእ ለማድረግ ንያ ማሳደር ያለብን ገና የውዱእ ዝግጅት በምናደርግበት ጊዜ ነው፡፡ እሳቤያችንም እጃችንን ከመታጠብ ጀምሮ እግራችንን እስከምንታጠብ ድረስ በልባችን መኖር አለበት፡፡

ልብ ይበሉ፡- የልብ ውሳኔ (ንያ) ሥራችን አምልኮ ሆኖ

እንዲቆጠር ያደርጋል፡፡ ማንም ሰው እጆቹን ወይም እጆቿን

ሊታጠቡ ይችላሉ ይሁን እንጂ ምንዳ የሚያገኘው ግን

ለአምልኮ ንያ (እሳቤ) ያደረገ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

«ሥራ የሚለካው በኒያህ ነው» ብለዋልና፡፡6

3 እጅን ሦስት ጊዜ መታጠብ፡፡ ይኸውም ከእጅ አንጓ ጀምሮ የጣቶችን አጽቅ በደንብ አድርጎ ማጠብ፡፡ ብሎም ከቀኝ መጀመር መዘንጋት የለበትም፡፡

4 ውሃን በአፍና አፍንጫ በመሳብ ሦስት ጊዜ መጉመጥመጥና አፍንጫ ውስጥ ያለን ቆሻሻ ማስወጣት፡፡ ይህንን ስንፈጽም በተመሳሳይ ጊዜ ከአፋችን ውስጥና ከአፍንጫችን ውሃውን እናስወጣለን

ደንቡን ጠብቆ ዉዱእ ያደረገ ወንጀሉ ከጥፍሩ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ከሰውነቱ ይወገዳል ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)፡፡ “

Page 28: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 1፡- ለሶላት መዘጋጀት 13

5 ፊትን ሦስት ጊዜ መታጠብ፡፡ ፊታችን የምንለው ከፀጉራችን መጀመሪያ እስከ አገጫችን፤ ከቀኝ ጆሮ ግንዳችን እስከ ግራ የጆሮ ግንዳችን ያለውን በሙሉ በውሃ ማጠብ ነው፡፡ ጉንጫችንና አገጫችን ላይ ያለው ፂም ጥቅጥቅ ያለ ከሆነ ላይኛውን የፂማችንን ክፍል ማዳረስ በቂ ነው፡፡

6 ሁለት እጆችን እስከ ክርን መገጣጠሚያ ድረስ ሦስት ጊዜ በውሃ ማጠብ፡፡ ታዲያ ከቀኝ እጅ መጀመርዎንና የጣቶችን መሐል በደንብ አድርገው ማዳረስዎን ያረጋግጡ፡፡

7 ፀጉርን ሦስት ጊዜ ማበስ፡፡ ሁለት እጅን ውሃ በማስነካት ከግንባርዎ የፀጉር መጀመሪያ እስከ ማጅራትዎ የፀጉርዎ ማብቂያ በውሃ አብሰው ወደፊት መመለስ፡፡ ፀጉርዎ ረጅምና የተቆጣጠረ ከሆነ ወደ ኋላ አብሰው ባይመለሱ ይመረጣል፡፡

8 ጆሮን ሦስት ጊዜ ማበስ፡፡ ሁለት እጅን ውሃ በማስነካት ግራና ቀኝ ጆሮዎቻችን ውስጥ አመልካች ጣቶቻችንን በማስገባት በአውራ ጣቶቻችን ደግሞ የኋላኛው የጆሮአችንን ክፍል በመጥረግ ለሶስት ጊዜያት ማበስ፤ ሶስቱንም ጊዜ አዳዲስ ውሃ መጠቀም፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ!» ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)…. (አል-ማኢዳህ፡ 6)

Page 29: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት14

9 ሁለቱን እግሮቻችንን ለሶስት ጊዜያት ማጠብ፡፡ ከቀኝ እግራችን በመጀመር ግራ እግራችንን ማስከተል፡፡ የእግራችንን ላይኛና ውስጠኛ ክፍል እንዲሁም ከእግራችን ጣቶች ጫፍ እስከተረከዛችን ያሉትን በደንብ ማጠብን መዘንጋት የለብንም፡፡ በተለይም በጣቶቻችን መካከል ውሃ መድረሱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ልብ ይበሉ፡- ለዉዱእ የተሰጡት ማብራሪያዎች ለሴቶችም ለወንዶችም ልዩነት የላቸውም፡፡ ሴት ልጅ ፀጉሯን በምታብስበት ጊዜ ግን ጸጉሯን ገልጣ ሙሉ ለሙሉ እንዳታብስ በመከናነቢያዋ ስር የፀጉሯን የተወሰነ ክፍል ብቻ ማበስ በቂ ነው፡፡

አሸሃዱ አላኢላሃ ኢለላህ ዋሕደሁ ላሸሪከላህ ወአሸሃዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ፡፡ አላሁመጅአልኒ ሚነተዋቢን ወጅአልኒሚነል ሙተጠሂሪን፡፡

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም ብዬ እመሰክራለሁ፡፡ አንድና አጋር የለውም፡፡ ሙሐመድ የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ! በጸጸት ከኃጢአት ተመላሽ ከሆኑት መካከል አድርገኝ፡፡ ከወንጀል ንጹሕ (የጠሩ) ከሆኑት ሰዎች መካከል አድርገኝ፡፡

ዉዱእ አድርገን ካበቃን በኋላ የሚከተለውን ዱዓእ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ለዉዱእ ማድረጊያ ቦታ ባልተዘጋጀበት በሕዝብ መፀዳጃ ቦታ ላይ ዉዱእ ማድረግ ያስቸግራል፡፡ በተለይም እግርን ለመታጠብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላ አማራጭ አጥተን በእንደዚህ ዓይነት ቦታ ዉዱእ ካደረግን ውዱዕ ስናበቃ ቦታውን በሥርዓቱ ማጽዳትና መወልወል ይኖርብናል፡፡ እኛ በፈፀምነው ስህተት በኃይማኖታችን ላይ መጥፎ አመለካከት እንዳናሳድር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

Page 30: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 1፡- ለሶላት መዘጋጀት 15

ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች የሚከተሉት ነገሮች ዉዱእን ያበላሻሉ፡-

1 ከሁለቱ ቆሻሻ ማስወገጃ (ቀዳዳዎች) የሚወጣ አንዳች ነገር (ፈስንም ጨምሮ)

2 ጭልጥ ያለ እንቅልፍ መተኛት፣ ራስን መሳት ወይም ስካር

3 ሃፍረተ-ስጋን በእጅ መንካት

4 ባእድ በሆኑና የጋብቻ ትስስር በሌላቸው ወንድና ሴት መካከል የሚደረግ ንክኪ ያለምንም ወሲባዊ ስሜትና ሳያስቡት ቢሆንም እንኳን፡፡

ልብ ይበሉ፡- እስልምና እነዚህን ድርጊቶች አሳፋሪና ቆሻሻ

ተግባራት እንደሆኑ አድርጐ አይቆጥርም፡፡ ሆኖም እነዚህ

ከላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮች ከተከሰቱ ሕግ አውጪው (አላህ)

ውዱዕ እንድናደርግና ለሶላት ዝግጁ እንድንሆን በጥበቡ

ስለደነገገ ነው፡፡

ዉዱዕ ማድረግ የሚያስፈልገውበሚከተሉት ጊዜያት ዉዱእ እንዳደረጉ እርግጠኛ ይሁኑ፡-

1 በሰላት ወቅት

2 ቁርኣንን ሲነኩ

3 ጠዋፋ ሲያደርጉ (በካዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ሲዞሩ)

ውዱዕ ሳይኖር አላህን አንዳች ነገር መጠየቅ (ዱዓ ማድረግ) እንደሚቻለው ሁሉ ቁርኣንንም በቃል መቅራት የተፈቀደ ነው፡፡“

Page 31: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት16

ጉስል (መላ ሰውነትን መታጠብ)

ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት) ጀናባ ብትኾኑ ገላችሁን ታጠቡ፡፡ (አል-ማኢዳህ፡- 6)

አነስተኛው እድፈት (ሐደስ) በውዱእ እንደሚወገደው ሁሉ ትልቁ እድፈት በጉስል (መላ ሰውነትን በመታጠብ) ይወገዳል፡፡

ጉስል (ለአምልኮታዊ ጉዳይ ሰውነትን መታጠብ) መላ አካልን የመታጠብ ሥርዓት እንደመሆኑ ልክ እንደ ውዱዕ ሁሉ በንጹህ ውሃ ይፈጸማል፡፡ በሰውነታችን ላይ ውሃው ቆዳችንን ዘልቆ እንዳይገባ የሚያግድ አንዳች ነገር ካለ መላ ሰውነታችንን ከመታጠባችን በፊት ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ «ቢስሚላሂ አር-ራሕማኒ አር-ረሒም» «እጅግ አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም» ብለን እንጀምራለን ፡፡

ገላችንን መታጠብ ስንጀምር የሚከተሉትን መመሪያዎች አንዘንጋ፡-

1 ቢስሚላሂ አር-ራሕማኒ አር-ረሒም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ በሆነው በአላህ ስም ማለት ያስፈልጋል፡፡

2 ትጥበትን የሚያግዱ ነገሮችን ከሰውነት ማስወገድ

3 ትልቁን ዕድፈት (ሐደስ) ለማስወገድ የልብ ውሳኔ (ኒያህ) በማድረግ ብልቶችንና አካባቢያቸውን ማጠብ፡፡

4 ዉድእ ማድረግ

5 የግዴታ ትጥበት ለመፈጸም የልብ ውሳኔ (ኒያህ) በማድረግ ጭንቅላት ላይ ሦስት ጊዜ ውሃን ማፍሰስ፡፡

ከሻወር ስር ሆኖ መታጠብ ይመረጣል አለዚያ ፀጉራችንን በምንታጠብበት ጊዜ በእጃችን እየፈተግን ውሃ በደንብ ማዳረሱን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

6 ቀጥሎ በሰውነታችን ላይ ውሃ ማፍሰስ፡፡ በዚህ ዓይነት የቀረውን የሰውነታችንን ክፍል ሦስት ጊዜ ማጠብ፡፡ በዚህ ጊዜ እያንዳንዷን የሰውነታችንን ክፍል ማዳረስ ይኖርብናል፡፡ ሰውነታችንን በምንታጠብበት ጊዜ ሰውነት ማሽያ ቡርሾችን ወይም ፎጣዎችን ብንጠቀም በደንብ እንዲዳረስ ይረዳናል፡፡ ካልሆነም በእጃችንም ቢሆን በውሃ አዳርሰን ማጠብ፡፡ በቀኝ ጐናችን ጀምረን በግራ በኩል መጨረስ ይወደዳል፡፡

አንድ ሰው ወደ እስልምና ሲገባ መጀመሪያ የሚያደርገው ነገር ጉስል (ሰውነቱን መታጠብ) ነው “

Page 32: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 1፡- ለሶላት መዘጋጀት 17

የግዴታ ትጥበት ምክንያቶች

ቀጣዮቹ ምክንያቶች ሲከሰቱ ሰውነትን መታጠብ ግድ ነው፡-

1 ስሜት ሰጭ በሆነ ሁኔታ ተኝተውም ሆነ ነቅተው የዘር ፈሳሽ ከብልት ከወጣ፣

2 የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ በኋላ

3 የወር አበባ ሲቆም፣

4 የወሊድ ደም ሲቆም፣

5 ወደ እስልምና ሲገባ (አንድ ሰው ኢስላምን ሲቀበል)፣

ልብ ይበሉ፡-የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው የግዴታ ትጥበትን

ካከናወኑ በኋላ በስሜት ውስጥ ሆኖ የዘር ፈሳሽ ከብልት

ከወጣ በድጋሚ መታጠብ ግድ ይሆናል፡፡

በትልቁ እድፈት (ሐደስ) ላይ ሆነን ልንፈጽማቸው የተከለከሉ ተግባራት

በምንም ዓይነት መንገድ ግዴታ የሆነን ትጥበት ሳይፈጽሙ የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም አይቻልም፡-

1 ሶላት መስገድ፣

2 መስጂድ ውስጥ መቆየት፣

3 ቁርኣንን መቅራት፣

4 ቁርኣንን መንካት፣

5 ጠዋፍ ማድረግ (ካዕባን ለሰባት ጊዜ መዞር)፣

6 ሱጁድ የሚያስወርድ የቁርኣን አንቀጽ ሲቀራ ሱጁድ ማድረግ፡፡

የሚያፀዳ የሆነ ጉስል ተቀባይነት የሚያገኘው የልብ ውሳኔ (ኒያ) ሲኖርና መላ ሰውነት በንፁህ ውሃ

ሲታጠብ ነው።“

Page 33: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት18

የወር አበባ4

ለትልቅ ዕድፈት (ሐደስ) ከሚያበቁ ሁኔታዎች አንዱ የወር አበባ ነው፡፡ ከወር አበባ በኋላ እንዴት ትጥበት በማድረግ መጽዳት እንደሚቻልም ተምረናል፡፡ ይሁን እንጂ ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ዝርዝር ጉዳዮችን መማር ጠቃሚ ነው፡፡

የወር አበባ ቀን ቆጥሮ በየወሩ ከሴቶች ብልት የሚፈስ ደም ነው፡፡ ማንኛዋም ለአቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት ከ9 የጨረቃ ዓመት ጀምሮ አርጅታ እስከሚቋረጥባት ጊዜ ድረስ ወር ቆጥሮ ይመጣል፡፡ አነስተኛው የወር አበባ ቆይታ ጊዜ አንድ ቀን ከነሌሊቱ ነው፡፡

የወር አበባ የሚጀምርበት ጊዜና የሚከለከሉ ነገሮች

የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ ፍልቅ የሚል ደም ይሆናል፡፡ ምንም ጥቂትና የፈዘዘ ቢሆንም፡፡

የወር አበባ ደም ማየት እንደተጀመረ ከቀጣዮቹ ድርጊቶች መቆጠብ ያስፈልጋል፡-

1 ከግብረ ሥጋ ግንኙነት

2 ከሶላት

3 ከፆም

4 ከጠዋፍ (ካዕባን ከመዞር)

5 ቁርኣንንና ቁርኣን የተቀመጠበትን መያዣም ከመንካት 6 መስጂድ ውስጥ መቆየት

የወር አበባ መቼ ይጠናቀቃል፣ ሲጠናቀቅስ ምን ይደረጋል?

የወር አበባ ማብቃቱ የሚታወቀው፡-

1 ሴቷ የወር አበባው ደም ሙሉ በሙሉ ማብቃቱን በትክክል ስታረጋግጥ፡፡

2 ድንግል የሆነችም ሆነ ያልሆነች ሴት ንጹህ የሆነ (ብዙውን ጊዜ ነጭ) ፈሳሽ ከብልቷ መውጣቱን ስትመለከት፡፡

የወር አበባ ደም ማቆሙን ስታረጋግጪ ገላሽን በመታጠብ ግዴታ የተደረጉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን ማከናወን አለብሽ፡፡ ሌላው ቀርቶ በቀጣዩ ቀን ወይም ከዚህ ስግደት በኋላ ሊመጣ ይቻላል የሚል ጥርጣሬ ቢኖርሽ እንኳን መስገድ አለብሽ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደሞ ከመጣ እስኪቆም ትጠብቂና መጥራቱን ስታረጋግጪ ገላሽን በመታጠብ ሶላትሽን ትጀምሪያለሽ፡፡ ቢደጋገምም ይሄንኑ ሂደት መከተል ያስፈልጋል፡፡

የወር አበባ ካበቃ በኋላ የሚኖር የደም መፍሰስ

የወር አበባ መጥቶ ከሄደ በኋላ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ድጋሚ የወር አበባ አይመጣም፡፡ ከዚያም አያንስም፡፡

መደበኛ ያልሆነ የደም መፍሰስ

አንዲት ሴት ከ15 ተከታታይ ቀናት በላይ ከብልቷ ደም የሚወጣ ከሆነ የተወሰነው እንደወር አበባ (ሐይድ) የሚታይ ሲሆን የተወሰነው ደግሞ እንደ በሽታ ደም (ኢስቲሃዳ) ይቆጠራል፡፡ ሆኖም በርግጥ የወር አበባ ከሆነ አምልኮታዊ ተግባራት የተከለከሉ ሲሆን የበሽታ ደም (ኢስቲሓዳ) ከሆነ የተፈቀደ ይሆናል፡፡የበሸታ ደም (ኢስቲሓዳን) በተመለከተ በአንዲት ሴት ላይ አራት ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡

Page 34: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 1፡- ለሶላት መዘጋጀት 19

ሁኔታ 1 ለመጀመሪያ ጊዜ የደም መፍሰስን የምታይ ሴት ለወትሮው የተለመደ የወር አበባ ጊዜ የነበራት ሆኖ በተለምዶው መጠን አንዴ በከባዱ ከፈሰሰ እንደ ወር አበባ ደም ይቆጠራል፡፡ ቀለል ያለ ደም ከሆነ እንደ በሽታ ደም (ኢስቲሓዳ) ይቆጠራል፡፡ በከባዱ የሚፈሰው ደም አነስተኛው አንድ ቀንና ሌሊት ሲሆን ከፍተኛው ከ15 ቀናት አይበልጥም፡፡ ሆኖም ግን የሚፈሰው ደም ምንነቱ ካልለየ የወር አበባ ጊዜ ተብሎ የሚወሰደው አንድ ቀን ከአንድ ሌሊት ሲሆን የቀሩት የወሩ ቀናት እንደ በሽታ ደም (ኢስቲሃዳ) ይቆጠራሉ፡፡

ሁኔታ 2 ማንኛዋም ሴት የራሷ የሆነ ቋሚ ሁኔታ አላት፡፡ ይህ ማለት የወር አበባዋ መቼ መጥቶ እንደሚሄድና ለምን ያህል ቀናት እንደሚቆይ ታውቃለች ማለት ነው፡፡ ስለሆነም አንዲት ሴት መደበኛ ሁኔታዋን ካወቀች መደበኛው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ሶላት መስገድ የለባትም፡፡ ሆኖም ከመደበኛው ጊዜ በላይ ከቆየ ግን ትጥበት በማድረግ ደም እየፈሰሳትም ቢሆን ልትሰግድ ይገባታል፡፡

ሁኔታ 3 መደበኛ ጊዜውን ጠብቆ የወር አበባዋ የማይመጣባት ሴት የደሙን የተለያዩ ሁኔታዎች በመመልከት ማለትም ቀለሙን ውፍረቱንና ጠረኑን በማየት መለየት ይኖርባታል፡፡

ለምሳሌ 20 ቀን ሙሉ ደም የሚፈሳት ከሆነ አሥሩን ቀን ጥቁር ደም አሥሩን ደግሞ ቀይ ደም ከሆነ ጥቁር ደም ያየችባቸውን ቀናት እንደ የወር አበባ ቀናት በመቁጠር የቀሩትን ቀናት የበሽታ ደም (ኢስቲሐዳ) አድርጋ መቁጠር ይኖርባታል፡፡

ሁኔታ 4የወር አበባዋን መምጫ የማታስታውስ ሴት ሁኔታዋን ገምግማ እርግጠኛ ስትሆን ሕጉን ሥራ ላይ ታውላለች፡፡ ይሁን እንጂ የወር አበባዋ ያቆመበትን እርግጠኛ

ጊዜ ከተጠራጠረች ሃይማኖታዊ ግዴታዎቿን መፈጸም ያለባት ሲሆን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ግን ማድረግ አይፈቀድላትም፡፡

ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ የወር አበባ

የወር አበባ ከ15 ቀናት በላይ የሚቆይ አይሆንም፡፡ ከዚያ ካለፈ ከብልቷ ግድግዳ የሚወጣ የበሽታ ደም (ኢስቲሐዳ) እንጂ የወር አበባ ነው አይባልም፡፡ ለማንኛውም ለእንዲህ ዓይነቱ ችግር ሐኪም ማናገሩ ይመከራል፡፡

ልብ ይበሉ፡-ሁልጊዜ በተከታታይ ደም የሚፈሳት ሴት

ከእያንዳንዱ ሶላት በፊት ከዚህ በታች ያለውን መመሪያ

ትከተል፡- :

•ከአካሏና ከልብሷ ላይ ደሙን በማጠብ ታስወግድ፡፡

•ደሙ የሚወጣበት ቦታ ላይ ጨርቅ ወይም ሌላ ቁስ

ታድርግበት፡፡

•ከዚያም ውዱዕ ታድርግና ወዲያው ትሰገድ፡፡

እንደ አንሷር ሴቶች የሃይማኖታቸውን ጉዳይ ምንም ሳያፍሩ መማር የሚፈልጉና የሚገነዘቡ መልካም ሴቶችን

አላየሁም -ዓኢሻ ቢንት አቡበከር (ረ.ዐ)“

Page 35: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 36: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ስግደት(ሶላት)አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ…

(አል-በይዪናህ፡- 5)

Page 37: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት22

ግዴታ የሆኑ ሶላቶች5

ሙስሊሞች በሁሉም ወቅት ፈጣሪያቸውን እንዲያስታውሱ ይበረታታሉ፡፡ ይህን እንዲያደርጉ ለማገዝም ልዩ የሆኑ በቀን ውስጥ ለአምስት ጊዜያት የሚፈጸሙ ተግባራት ተደንግገዋል፡፡ እነርሱም የአምስት ወቅት ሶላቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ፈርድ (ግዴታ) የሆኑ ሶላቶች መስገድ ለአንድ ሙስሊም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ተግባሩ ነው፡፡ የፍርዱ ቀን ሲመጣ ከሌሎች ጥያቄዎች በፊት ሙስሊም የሚጠየቀው ስለ ሶላቱ ነው፡፡

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) “አሰጋገዴን አይታችሁ ስገዱ” በማለት ተከታዮቻቸውን አስተምረዋል፡፡ እርሳቸው እንዴት መስገድ እንዳለባቸው ያስተማራቸው ደግሞ ጂብሪል (ዐ.ሰ) ነው፡፡ ዛሬ ሙስሊሞች በዚህ በተማሩት መሠረት መስገድ ቀጥለዋል፡፡ በምዕራፍ 7 የምንማረውም ስለዚሁ ስለሶላት ይሆናል፡፡

ልብ ይበሉ፡-ሙስሊም ወንድም ሆነ ሴት ለአቅመ አዳም

(ለአቅመ ሄዋን) ከደረሱ በኋላ በማንኛውም ሸሪአዊ ጉዳዮች

ተጠያቂ (ሙኻለፍ) ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም የአምስት ወቅት

ሶላትን ወቅቱንና ደንቡን ጠብቀው ሊሰግዱ ይገባል፡፡ ሶላት

እንዳይሰገድ ሊያቅበው የሚችለው በሴቷ ላይ የሚመጣው

የወር አበባና የወሊድ ደም ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም ደሞች ከቆሙ

በኋላ ሶላት የመስገድ ግዴታነት እንደገና ይጸናል፡፡

የሶላት ወቅቶች፣ ሥያሜዎቻቸውና የአፈጻጸም ዑደታቸው

…ሶላት በምእመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትናአን-ኒሳእ 103

እያንዳንዱ የግዴታ ሶላት የራሱ የሆነ 1.መጠሪያ ስያሜ 2.የሚሰገድበት የተወሰነ ሰዓት 3.የአፈጻጸም ዑደቶች አሉት፡፡

በተጨማሪም ድምጻችንን አጉልተን ቁርኣንን የምናነብባቸውና ድምጻችንን ዝቅ አድርገን የምናነብባቸው የሶላት ወቅቶች አልሉ፡፡

የሰላት ዑደት

Page 38: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

23ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

አምስቱ የግዴታ ሶላቶች

የየዕለቱ የአምስት ወቅት ሶላት መስገጃ ሰዓት ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ሶላትህን ጊዜው መግባቱን

ስታረጋግጥ ስገድ፡፡ ትክክለኛውን የሶላት ወቅት ያለህበትን አካባቢ ወቅቶች ያገናዘበ ልዩ የጊዜ ሰሌዳ ይኑርህ፡፡ “

ሱብሒየንጋት ሶላት

ዙህርየቀትር ሶላት

ዐስር የቀትር በኋላ ሶላት

መግሪብየፀሐይ መጥለቅ ሶላት

ዒሻእየምሽት ሶላት

2 ረከዓ የሚሰገድበት • መስገጃ ወቅቱ የሚጀምረው እውነተኛ የንጋት ወጋገን (ፈጅር) ሲወጣ

• ወቅቱ የሚያበቃው ፀሐይ ከአድማሷ መውጣት ስትጀምር

• ድምጽን በማውጣት ቁርኣን የሚነበብበት

4 ረከዓ የሚሰገድበት•መስገጃ ወቅቱ የሚጀምረው ፀሐይ ከአናት ዘንበል ስትል

•ወቅቱ የሚያበቃው የነገሮች ጥላ ከራሳቸው ጋር እኩል ሲሆን

•ድምጽ ሳይወጣ ቁርኣን የሚነበብበት

4 ረከዓ የሚሰገድበት•መስገጃ ወቅቱ የሚጀምረው የዙህር ሶላት ወቅት ሲያበቃ

•ወቅቱ የሚያበቃው ፀሐይ ስትጠልቅ

•ድምጽ ሳይወጣ ቁርኣን የሚነበብበት

3 ረከዓ የሚሰገድበት•መስገጃ ወቅት የሚጀምረው ፀሐይ ስትጠልቅ

•ወቅቱ የሚያበቃው ቀዩ ወጋገን ሲጠፋ

•የመጀመሪዎቹ ሁለት ረከዓዎች ድምጽን በማጉላት ቁርኣን የሚነበብበት

4 ረከዓ የሚሰገድበት•መስገጃ ወቅቱ የሚጀምረው የመግሪብ ሶላት ማብቂያ ላይ

•ወቅቱ የሚያበቃው እውነተኛው የንጋት ወጋገን ሊወጣ ሲል

•የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ረከዓዎች ድምጽን በማጉላት ቁርኣን የሚነበብበት

Page 39: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት24

ሶላትን በወቅቱ መስገድ

ሰውዬው ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ቀርቦ «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የትኛው ሥራ ነው ይበልጥ የልቅና ባለቤት የሆነውን አላህን የሚያስደስተው?» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «ሶላትን በወቅቱ መስገድ»7 አሉት፡፡

ማንኛውንም ሶላት በተደነገገለት ጊዜ መስገድ የግድ ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ ሶላትን ወቅቱ እንደገባ መስገድ ይመከራል፡፡

አንድ ሶላት ተቀባይነት እንዲያገኝ ቢያንስ ወቅቱ ከማለፉ በፊት ሰጋጁ አንድ ዙር (ረከዓ) ማግኘት አለበት፡፡ እንዲህ ከሆነ ወቅቱ ተገኘ ሊባል ይችላል፡፡ ያለምንም በቂ ምክንያት ሶላትን ማዘግየት አይፈቀድም፡፡

ሰውዬው ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህን ይበልጥ የሚያስደስተውና አላህ

የሚወደው ተግባር የትኛው ነው?» ሲል ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ «ሶላትን በወቅቱ መስገድ» አሉት፡፡“

የሶላት ወቅትን ማሳለፍ

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «ሶላቱን ያለምንም ምክንያት ከወቅቱ የሚያሳልፍ ንብረቱንና ቤተሰቦቹን እንዳጣ ሰው ነው»8 ብለዋል፡፡

የግዴታ ሶላት ወቅትን በመዘንጋትና በመርሳት ያሳለፈ ሰው ባስታወሰበት ወቅት ሶላቱን መስገድ አለበት፡፡

ወቅቱን በዘነጋና በረሳ ሰው ኃጢኣት የለበትም፡፡ ሆን ብሎ ያሳለፈ ግን እንደ ከባድ ኃጢኣት ይቆጠርበታል፡፡ ንስሐ (ተውባህ) ማድረግም ይኖርበታል፡፡

Page 40: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

25ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

የሶላት ጥሪ6

በዓለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች በሙሉ በቀን ውስጥ ለአምስት ጊዜያት ያህል የሚያደርጉት ጥሪ አንድ ዓይነት ሲሆን ልዩ የኢስላም ምልክት ተደርጐ ይቆጠራል፡፡ ይኸው የሶላት ጥሪ አዛንና ኢቃማህ በመባል ይታወቃል፡፡

አዛን የሚደረገው የሶላት ወቅት ሲገባ ነው፡፡ ኢቃማህ ደግሞ የግዴታ ሶላት ሊሰገድ ሲል የሚደረግ ሲሆን አንድ ሰው ለብቻው ቢሰግድ እንኳ ማድረጉ ግዴታ ነው፡፡

አዛን

አዛን ሰዎች የሶላት ወቅት መድረሱን እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል፡፡

አላሁ አክበር (አራት ጊዜ)

አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለልላህ (ሁለት ጊዜ)

አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ (ሁለት ጊዜ)

ሐይየ ዐለስ-ሶላህ (ሁለት ጊዜ)

ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ (ሁለት ጊዜ)

አስ-ሶላቱ ኸይሩን ሚነን-ነውም (ሁለት ጊዜ)

(ይህ በሱብሒ ወቅት ብቻ የሚባል ነው)

አላሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

ላ ኢላሀ ኢልለሏህ (አንድ ጊዜ)

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም ብዬ እመሰክራለሁ

ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ

ወደ ሰላት ኑ

ስኬት ወደተመላበት ሕይወት ኑ

ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ነው፡፡

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም

ኢቃማህ

ኢቃማህ የግዴታ ሶላት ለመጀመር የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡

አላሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለሏህ (አንድ ጊዜ)

አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ (አንድ ጊዜ)

ሐይየ ዐለስ-ሶላህ (አንድ ጊዜ)

ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ (አንድ ጊዜ)

ቀድ ቃመቲ ሶላህ (ሁለት ጊዜ)

አላሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

ላ ኢላሀ ኢልለሏህ (አንድ ጊዜ)

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም ብዬ እመሰክራለሁ

ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ

ወደ ሶላት ኑ

ስኬት ወደተሞላበት ሕይወት ኑ

በርግጥ ሶላት ተጀምሯል

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም

Page 41: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት26

መስገድ ከመጀመርዎ በፊት ሶላትዎ ትክክለኛ መሆኑን ከዚህ በታች የሰፈሩትን ሁኔታዎች በመፈተሽ ያረጋግጡ፡-

1 ወቅቱ መግባቱን፡- ሶላት መሰገድ ያለበት በትክክለኛው ወቅት ነው፡፡

2 አካላዊ ንጽሕና፡- የምንሰግድበት ልብስ ገላችንና መስገጃችን ንጹህ መሆኑን፡፡

3 መንፈሳዊ ንጽሕና፡- ለሶላት ስንዘጋጅ ከትንሹ እድፈት (ትንሹ ሐደስ) ለመጽዳት ውዱዕ ማድረግ ያለብን ሲሆን ከትልቁ እድፈት (ትልቁ ሐደስ) ለመጽዳት መላ ሰውነትን መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

ልብ ይበሉ፡-ሴት ልጅ የወር አበባ ላይ ከሆነች፣ እስክትጸዳ

ሶላትና ጾምን ከመሳሰሉት የአምልኮ ተግባራት ነጻ

ትደረጋለች፡፡ በወር አበባ ወቅት ያልሰገደቻቸው ሶላቶችም

ከወር አበባ ስትጠራ እንድታካክስ አትገደድም፡፡ የረመዷን

ወር ፆምን ግን ያመለጣትን ጊዜ ቆጥራ ረመዷን ከወጣ በኋላ

ትፆማለች (ታካክሳለች)፡፡

4 ሐፍረተ-ገላን መሸፈን፡- በሶላት ወቅት ሐፍረተ ገላን (ዐውራህን) የመሸፈን ግዴታ አለብን፡፡ የወንድ ልጅ ሐፍረተ ገላ የሚባለው ከእንብርት እስከ ጉልበት ድረስ ያለው አካል ሲሆን፥ ለሴት ልጅ ግን ከእጇና ከፊቷ ውጭ ያለው ሰውነቷ በሙሉ ስለሆነ በልብስ መሸፈን አለበት፡፡ የምንለብሳቸው ልብሶች የሰውነትን ቅርጽና ቆዳ የሚያሳዩ መሆንም የለባቸውም፡፡

5 አቅጣጫን ማስተካከል (ቂብላህ)፡- መካ ወደ ሚገኘው የተቀደሰው መስጊድ ወይም ከዕባህ የፊትን አቅጣጫ በማስተካከል ለሶላት መቆም፡፡ በአካባቢህ ያለው መስጊድ ያለውን የቂብላህ አቅጣጫ በማጤን ወይም ከታማኝ ምንጮች በማረጋገጥ አቅጣጫህን (ቂብላህን) ማስተካከል ትችላለህ፡፡

6 ኒይያህ፡- የኒይያህ ወይም ቁርጠኛ ውሳኔ ማድረጊያ ቦታ ልብ ነው፡፡ አሁን ልትሰግደው ያሰብከውን ሶላት ለመስገድ መዘጋጀትህን በልብህ ስታስብ «አላሁ አክበር» የሚለውን ቃል በምላስህ መድገም ያስፈልጋል፡፡

በምላስ የሚደረገው ኒይያህ «አላሁ» በሚለውና «አክበር» በሚለው ቃል መሐል መጠናቀቅ አለበት፡፡

በግዴታ ሶላት ወቅት ኒይያው ውስጥ የምትሰግደውን የሶላት ዓይነት፣ የረከዓው ብዛት መካተት ያለበት ሲሆን ግዴታ ያልሆነ ሶላት ከሆነ የምትሰግደውን ሶላት የተለየ ጊዜ በማሰብ ኒያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ከመደበኛ ሶላት በፊትና በኋላ ሱና ሶላቶችን መስገድ፡፡

እንዴት እንሰግዳለን?7

Page 42: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

27ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

ሁለት ዙር (ረከዓ) ሶላት አስጋገድ

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «እኔ ስሰግድ እንዳያችሁት ስገዱ»9 ብለዋል፡፡

ከሶላት በፊት መስማት በሚቻል መጠን ድምጽን በማውጣት ኒይያህ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ቁርኣንን ድምጽ አውጥቶም ይሁን ሳያወጡ ለማንበብ የሶላቶቹ ዓይነትና የሶላቱ ዙሮች (ረከዓዎች) ይወስናሉ፡፡

1 ሶላት ለመጀመር ቀጥ ብሎ መቆም

2 «አላሁ አክበር» በሚሉት ሁለት ቃላት መሐል እሳቤ (ንያ) ማድረግ፡፡ ይኸውም የምንሰግደውን ሶላት በስሙ መጥራት፣ የግዴታ ከሆነ ግዴታ (ፈርድ) ሱንና ከሆነ ሱንና ማለት፡፡ ከኢማሙ ኋላ የምትሰግድ ከሆነ ኢማሙን ተከትለህ ለመስገድ እሳቤ (ንያ) አድርግ፡፡ ከዚያም ሁለት እጆችህን ወደ ትከሻህ ከፍ በማድረግ የመክፈቻውን ተክቢራ (አላሁ አክበር) ካልክ በኋላ ከደረት በታችና ከእምብርት በላይ ባለው ስፍራ እጆችን አነባብሮ (በግራው ላይ ቀኙን ደርቦ) ማስቀመጥ፡፡

3 ቀጥሎ የመክፈቻውን ዱዓ ማድረግ ይኸውም፡-«ወጀህቱ ወጅሂ ሊለዚ ፈጠረስ ሰማዋቲ ወል-አርደ ሐኒፈን ሙስሊመን ወማ አነ ሚነ-ል-ሙሽሪኪን፡፡ ኢንነ ሶላቲ ወኑሱኪ ወመሕያየ ወመማቲ ሊላሂ ረቢ-ል-ዓለሚን፡፡ ላ ሸሪከ ለሁ ወቢዛሊከ ኡሚርቱ ወአነ ሚነ-ል-ሙስሊሚን»

አንድ ሙስሊም ወንድም ሆነ ሙስሊም ሴት እድሜያቸው ለአቅመ አዳም (ሄዋን) ሲደርስ ግዴታ በሆኑባቸው

ተግባራት ተጠያቂዎች (ሙኧልለፍ) ይሆናሉ፡፡ በዚህ ጊዜ አምስቱን የግዴታ ሶላቶች መስገድ አለባቸው፡፡ “

Page 43: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት28

“ፊቴን፡- ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው ፍጹም የጠራና ብቸኛ የሆነው አምላክ አዞርኩ፡፡ እኔ በሱ ላይ ከሚያጋሩት አይደለሁም፡፡ ስግደቴም፣ ጸሎቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም፣ የዓለማት ጌታ ለሆነው ለፈጣሪዬ ነው፡፡ በዚህም ታዝዣለሁ፡፡ እኔ እርሱን ከሚታዘዙት ሙስሊሞች ነኝ፡፡”

4 የመክፈቻውን ምዕራፍ (ፋቲሓን) ከቁርኣን መቅራት ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒምአልሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን፤ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም፤ ማሊኪ የውሚድ-ዲን፤ ኢይያከ ነዕቡዱ ወኢይያከ ነስተዒን፤ ኢህዲነስ-ሲራጠ-ል-ሙስተቂም፤ ሲራጠል-ለዚነ አንዐምተ ዐለይሂም፤ ገይሪል መግዱቢ ዐለይሂም ወለድ-ዷሊን፡፡ አሚን፡፡

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ምሥጋና ለአላህ ይገባው፡፡ የዓለማት ጌታ ለሆነው፡፡ እጅግ በጣም ርኅሩኅ እጅግ በጣምአዛኝ፡፡ የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው፡፡ አንተን ብቻ እንግገዛለን፡፡ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ የነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፤ በነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን፡፡

የመክፈቻው ምዕራፍ ፋቲሐ ቁርኣን ውስጥ ካሉ አጫጭር ምዕራፎች አንዱ ነው፡፡ በሁሉም የሶላት ዙሮች (ረከዓዎች) የሚነበብ በመሆኑ ዐረብኛውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመልመድ ሞክር፡፡ አለዚያ በትልቁ በመጻፍ በምትሰግድበት ጊዜ ፊት ለፊትህ አኑረህ ማንበብ ትችላለህ፡፡

Page 44: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

29ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

ልብ ይበሉ፡-ኢማምን ተከትለህ የምትሰግድ ከሆነ የመክፈቻውን ምዕራፍ (ፋቲሓን) ማንበብ ይኖርብሃል፡፡

ፋቲሓን ስትጨርስ ደግሞ "አሚን" ትላለህ፡፡ ይህ ማለት አላህ ሶላትህን እንዲቀበልህ እየጠየቅክ ነው ማለት ነው፡፡

5 ቀጥሎ ከቁርኣን የተወሰነ ክፍል ማንበብ፡፡ ይህም አንዱ ሙሉ ምዕራፍ ወይም ከዚያ ያነሰ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ቀጥሎ አንድ ምዕራፍ ቀርቧል፡-ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒምቁል ሁወልላሁ አሐድ፤ አልላሁ አስ-ሰመድ፤ ለም የሊድ፤ ወለም ዩለድ፤ ወለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሐድ፡፡ትርጉም፡- በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነውበል እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፡፡ አልተወለደም፡፡ ለርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡

6 ማጎንበስ (ሩኩዕ ማድረግ)፣ በመቀጠል ሁለት እጅህን ወደ ትካሻህ በመውሰድ «አላሁ አክበር» ብለህ ማጐንበስ ነው፡፡ መዳፎችህ ጉልበቶችህን ሲደገፉ እግሮችህ ቀጥ ብለው ይቆማሉ፡፡

7 እዚያው እንዳጎነበስክ ድምጽህን ቀንሰህ ሦስት ጊዜ ይህን ትላላህ ሱብሓነ ረቢየ-ል-ዐዚም ኃያሉ ጌታዬ ከሁሉ ነገር ጠራ

አንዴ የሰላቱን መክፈቻ "አላሁ አክበር" ብለህ ከጀመርክ በኋላ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ለምሳሌ መናገር፣ መብላትና ከልክ ያለፈ መቁነጥነጥ ሶላቱን ያበላሸዋል፡፡ “

Page 45: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት30

8 ካጎነበስክበት ትነሳለህ (ቀና ትላለህ)፡፡ እጅህንም ወደ ትከሻህ ስትወስድ እንዲህ ትላለህ፡- ሰሚዐል-ላሁ ሊመን ሐሚዳህ

አላህ የሚያመሰግኑትን ቃል ይሰማልቀጥ ብለህ ከቆምክ በኋላምረብበና ለከ-ል-ሐምድጌታችን ሆይ ምሥጋና ላንተ የተገባ ነው፡፡ በል

ልብ ይበሉ፡-ኢማምን ተከትለህ የምትሰግድ ከሆነ ሁለቱንም

ሐረጎች ማለትም «ሰሚዐል-ላሁ ሊመን ሐሚዳህ» እና

«ረበና ለከ-ል-ሐምድ» ማለት ይኖርብሃል፡፡

9 በግንባር መሬት መንካት (ሱጁድ)፡- ቀጥለህ በቆምክበት ሆነህ «አላሁ አክበር» ካልክ በኋላ ሱጁድ ታደርጋለህ (በግንባርህ መሬት ትነካለህ)፡፡ በቅድሚያ ጉልበትህ መሬት ይነካል፡፡ ከዚያም ሁለት እጆችህ፣ ግንባርህና አፍንጫህ፡፡ በግንባርህና በመስገጃ ቦታህ መሐል ሊጋርድ የሚችል አንዳች ነገር አለመኖሩን አረጋግጥ፡፡

10 ሱጁድ ላይ ሆነህ ሦስት ጊዜ የሚከተለውን በል ሱብሓነ ረቢየ-ል-አዕላ ትርጉሙ፡- ከሁሉም በላይ የላቀው ጌታዬ ጥራት ይገባው፡፡

ባሪያዬ ወደ እኔ ከሚቃረብባቸው መልካም ሥራዎቹ ሁሉ እንደ ሶላት የምወድለት ነገር የለም፡፡ (ሐዲስ አል-ቁድስ)“

Page 46: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

31ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

11 ግንባርህንና እጆችህን ከሱጁድ ማንሳት፡- «አላሁ አክበር» በማለት ተስተካክለህ መቀመጥ፡፡ ሁለቱ እጆችህ በሁለቱ እግሮችህ ጭኖች ላይ ያርፋሉ፡፡ የእጆችህ ጣቶች ሁሉም ተስተካክለው ተዘርግተው ጭንህ ላይ ያርፋሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ረቢ ኢግፊር ሊ ረቢ ኢግፊር ሊ ጌታዬ ሆይ! ማረኝ ጌታዬ ሆይ ማረኝ! በል፡፡

12 በድጋሚ «አላሁ አክበር» በማለት መሬት ላይ ትደፋለህ፡፡ በዚህም ወቅት ቀደም ሲል በቁጥር 10 ላይ ብለኸው የነበረውን ትደግመዋለህ፡፡

አሁን የሶላትህን አንደኛ ዙር (ረከዓ) አጠናቀሃል

ማለት ነው፡፡

13 የመጀመሪያውን ዙር (ረከዓ) ሶላትህን እንዳጠናቀቅክ ለሁለተኛው ዙር ከሱጁድ ተነስተህ «አሏሁ አክበር» በማለት ትቆማለህ፡፡ ትርጉሙ አላህ ታላቅ ነው ማለት ነው፡፡

14 ሁለተኛውን ዙርም ልክ የመጀመሪያ ዙር ላይ ከ4-12ኛው ተራ ቁጥር የነበረውን ድርጊት ቅደም ተከተሉን ጠብቀህ በመድገም መቀመጥ፡፡

በሶላት ላይ ሆነህ ደረትህ ከመስገጃ አቅጣጫህ (ከቂብላህ) አቅጣጫ አለመዘንበሉን እርግጠኛ ሁን“

Page 47: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት32

15 ሁለት ዙር (ረከዐህ) ከሰገድክ በኋላ በስዕሉ ላይ እንደሚታየው ለ"ተሸሁድ" ትቀመጣለህ፡፡ "ተሸሁድ" ማለት (ምስክርነት) ነው፡፡ እንደሚከተለው ይነበባል፡- «አት-ተሒያቱ አል-ሙባረካቱ አስ-ሶላዋቱ አጥ-ጠይባቱ ሊላህ አስ-ሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢይዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካትሁ አስ-ሰላሙ ዐለይና ወዐላ ዒባዱላሂ አስ-ሷሊሒነ አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለልልላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ» ትርጉም፡-«ክብር፣ ታላቅነት፣ ሶላትና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው፡፡ አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም እዝነቱና በረከቶቹ በርስዎ ላይ ይሁኑ፡፡ ሰላም ለኛና ለደጋጎቹ የአላህ አገልጋዮች ይሁን፡፡ ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ አለመኖሩን እመሰክራለሁ፡፡ ሙሐመድ የአላህ ባሪያና መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡»

በተሸሁድ (ምስክርነት) ወቅት የግራ እጅ መዳፍ ግራ ታፋ ላይ ጣቶች ደግሞ ጉልበት መታጠፊያ ላይ ተዘርግተው ሊያርፉ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የቀኝ እጅ መዳፍ በቀኝ ታፋ ላይ ያርፋል፡፡ ልክ ተሸሁድ ጋር ስትደርስ ማለትም «ኢልለልላህ» (አላህ ብቻ) በምትልበት ወቅት የቀኝ እጅ አመልካች ጣትህን በሥዕሉ ላይ በምታየው መሠረት ትቀስራለህ፡፡ ይኸውም ቀጥ አድርገህ ማቆም ሲሆን ማንቀሳቀስ አይኖርብህም፡፡«የአምስት ወቅት ሶላትን የሚሰግድ ከቤቱ ፊት ለፊት ጅረት ውሃ እንደሚፈስለትና በዚያ ውሃ በቀን አምስት ጊዜ እንደሚታጠብ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው ከቶም ቆሻሻ አይኖረውም፡፡ የአምስት ወቅት ሶላትም ውሃ ሰውነትን ከቆሻሻ እንደሚያጠራው ሁሉ ወንጀልን ያጸዳል፡፡» ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

16 በማጠናቀቂያው የምስክርነት (የተሸሁድ) አቀማመጥ ላይ ካለህ ቀደም ሲል ያለውን ካልክ በኋላ ቀጣዩን የኢብራሂሚያ ጸሎት አክልበት፡-«አላሁምመ ሶልሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶልለይተ ዐላ ኢብራሂም ወዐላ

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ (አል-አሕዛብ 56)“

Page 48: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

33ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

አሊ ኢብራሂም ወባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂም ወዐላ አሊ ኢብራሂም ፊ-ል-ዓለሚነ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ»

ትርጉሙ፡- «አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እዝነትህን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው ኢብራሂምንና ቤተሰቦቻቸውን ብሩክ እንዳደረግካቸው ሁሉ ሙሐመድና ቤተሰቦቻቸውን ብሩክ አድርጋቸው አንተ በዓለማት ሁሉ ምስጉንና ኃያሉ ነህና» ማለት ነው፡፡

17 ይህንን በሥርዓቱ እንዳጠናቀቅክ ወደ ቀኝህ በመዞር ‹አስሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላህ› (የአላህ ሰላምና በረከት በናንተ ላይ ይሁን) በል፡፡ ቀጥለህም ወደ ግራህ በመዞር ይህንኑ ደግመህ በል፡፡

አሁን ሁለቱንም የሶላት ዙሮች (ረከዓዎች) አጠናቅቀሃል፡፡

የአምስት ወቅት ሶላትን የሚሰግድ ከቤቱ ፊት ለፊት ጅረት ውሃ እንደሚፈስለትና በዚያ ውሃ በቀን አምስት ጊዜ እንደሚታጠብ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው ከቶም ቆሻሻ አይኖረውም፡፡ የአምስት ወቅት ሶላትም ውሃ ሰውነትን ከቆሻሻ እንደሚያጠራው ሁሉ ወንጀልን ያጸዳል፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ሦስት ዙር (ረከዓ) ሶላት አሰጋገድ

ሦስት ዙር (ረከዓ) ሶላት በምትሰግድበት ጊዜ ሁለቱን አከታትለህ ትሰግድና ለመጀመሪያው ምስክርነት (ተሸሁድ) ትቀመጣለህ፡፡ በተሸሁድ ወቅት ከመነሳትህ በፊት ‹አላሁመ ሶልሊ ዐላ ሙሐመድ› የሚለውን ዱዓ ብቻ ካልክ በኋላ ተነስተህ በመቆም የቀረህን አንድ ዙር (ረከዓ) ታክላለህ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን እንደቀድሞዎቹ ከፋቲሐ በኋላ የሚቀራ አንቀጽ አይኖርም፡፡ ከዚያም

(ለምስክርነት) ለተሸሁድ ተቀምጠህ ሶላትህን ታጠናቅቃለህ፡፡

አራት ዙር (ረከዓ) ሶላት

በአራት ዙር (ረከዓ) ሶላት ሁለቱን ዙሮች (ረከዓዎች) በመስገድ ለምስክርነት (ለተሸሁድ) ትቀመጣለህ፡፡ በተሸሁድ ወቅት «አላሁምመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ» የሚለውን ዱዓ ብቻ ካልክ በኋላ ተነስተህ በመቆም የቀሩህን ሁለት ዙሮች (ረከዓዎች) ታክላለህ፡፡ በዚህ ወቅት ስትነሳ እጆችህን ወደላይ በማድረግ አላሁአክበር ትላለህ፡፡ ከፋቲሐ በኋላ የምታስከትለው ሌላ የቁርኣን አንቀጽ አይኖርም፡፡ ፋቲሃን (የመክፈቻ ምዕራፍ) ስታነብ ድምጽህን ዝቅ ታደርጋለህ፡፡ አራቱን ዙሮች (ረከዓዎች) ከጨረስክ በኋላ ሶላትህን ታጠናቅቃለህ፡፡

Page 49: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት34

በሕብረት ስለ መስገድ8

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «ለብቻ ከመስገድ በጀማዐ (በሕብረት)

መስገድ በ27 ደረጃ የላቀ ነው» 10ብለዋል፡፡ ለወንድ ልጅ

አምስት ወቅት ሶላትን በመስጊድ በጀማዐ መስገዱ ነው

የታዘዘው፡፡ ለአቅመ አዳም/ሄዋን የደረሱ ሰዎች ካሉ፤

አንዱ ወንድ ኢማም ሆኖ ሌሎቹ ተከታዮች ሆነው መስገድ

አለባቸው፡፡

በሕብረት የሚሰገደው እንዴት ነው?

1 በህብረት በምትሰግድበት ጊዜ ወንድ ከሆንክና

እና ብቸኛ ከሆንክ ከኢማሙ በቀኝ ጎን በመቆም

ትከተለዋለህ፡፡ ሌሎች የሚሰግዱ ሰዎች ካሉ ከእነርሱ

ጋር ትከሻህን ገጥመህ ቁም፡፡ ሴቶች ደግሞ ከወንዶች

ኋላ ነው የሚቆሙት፡፡

2 ኢማሙ ለማሰገድ «አላሁ አክበር» ሲል ኒይያህ

(እሳቤህን) አስተካክል፡፡

3 የመክፈቻውን ተክቢራ ልክ ኢማሙ ሲጨርስ

ተከትለህ በል፡፡

4 ሶላቱ ድምጽ ሳይወጣ ቁርኣን ከሚቀራባቸው

ሶላቶች አንዱ ከሆነ ብቻህን ስትሰግድ እንደምታደርገው

ሁሉንም ነገር ፈጽም፡፡ ከኢማም ጋር በምትሰግድበት ጊዜ

ተመሳሳይ ነገር አድርግ፡፡ ኢማሙ ከፋቲሐ ቀጥሎ ሌላ

ምዕራፍ ሲያነብ አንተ ማንበብ አያስፈልግህም፡፡

5 አንተ ተከታይ እንደመሆንህ በምንም ዓይነት

ሁኔታ ኢማሙን ቀድመህ አንዳች እንቅስቃሴ ማድረግ

አይኖርብህም፡፡

Page 50: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

35ክፍል 2፡- ስግደት (ሶላት)

እንዲሰገዱ የሚመከሩ ሱንና ሶላቶች

ከግዴታ ሶላቶች ጎን ለጎን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሱንና ሶላቶችን ይሰግዱ ነበር፡፡ እነዚህን የሱና ሶላቶች መስገድ የሚመከር ሲሆን አንዳንዴ ነዋፊል ሶላቶች በመባል ይጠራሉ፡፡ አንተ ፈልገህ የምትሠራቸው ከሆነ በመሥራትህ ከአላህ ምንዳን ታገኝበታለህ፡፡

እነዚህ የሱንና ሶላቶች የሚሰገዱት ድምጽን ዝቅ አድርጐ ነው፡፡ ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ የሱንና ሶላት መቼና እንዴት እንደሚሰገዱ የሚያሳይ ነው፡፡

ልብ ይበሉ፡-ከመደበኛው የሚቀድም ሱና (ቀብሊያ) የግዴታ

ሶላት ወቅት ካልገባ በስተቀር አይሰገድም፡፡ ሱና ሶላቶችን

እቤት ውስጥ መስገድ ይወደዳል፡፡

ዊትር

ከኢሻእ ሶላት በኋላ ከፈጅር (ንጋት) ሶላት በፊት ባለው በማንኛውም ሰዓት የሚሰገድ ሱና ሶላት ነው፡፡ ዊትር ሶስት ዙር (ረከዓ) ያለው ሲሆን ሁለቱን ዙሮች (ረከዓዎች) ከተሰገዱ በኋላ አሰላምቶ አንዷን ዙር ረከዓ ለብቻዋ ማምጣት ይቻላል፡፡

በሁሉም ዙሮች (ረከዓዎች) የመክፈቻ ምዕራፍ (ፋቲሃ) የሚነበብ ሲሆን አስከትሎም ሌላ የቁርኣን ምዕራፍ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ከረመዷን አጋማሽ ጀምሮ በዊትር ሶላት ወቅት የመጨረሻው ዙር (ረከዓ) ሲሰገድ ከሩኩዕ በኋላ የሚደረግ ጸሎት (ቁኑት) አልለ፡፡ የጸሎቱ ሙሉ መልእክት በመጨረሻዎቹ ገጾች ይገኛል፡፡

የጁምዓ ሶላትእናንተ ያመናችሁ በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ…. (አል ጁሙዓህ 9)

የጁምዓ ሶላት ኢማሙን ጨምሮ ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ከተገኙ ተሰብስበው የሚሰግዱት ሶላት ነው፡፡ ሴትም ሆነ ወንድ የጁምዓ ሶላትን በመስጊድ የሰገደ የዙህር ሶላትን አይሰግድም፡፡

በጁምዓ ሶላት ሁለት ዲስኩሮች (ኹጥባ) በኢማሙ ይደረጋሉ፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጐ ሁለት ዙር (ረከዓ) ሶላትም ያሰግዳል፡፡

በአጠቃላይ የጁምዓ ሶላት በአንድ አካባቢ በከተማም ሆነ በጐጥ በቋሚነት በሚኖሩ ሰዎች ላይ ግዴታ ነው፡፡ ሴቶች ካልመጣችሁ ተብለው አይገደዱም መምጣታችው ግን መልካም ነው፡፡

ሌሎች ሶላቶች9

ከመደበኛው የሚቀድም ሱና

(ቀብሊያ) መደበኛ ሶላት

ከመደበኛው በኋላ የሚከተል

ሱና (ባዕዲያ)

2 ዙር (ረከዓ) ሱብሒ የለም

4 ዙር (ረከዓ) ዙህር አራት ዙር (ረከዓ)

2 ዙር (ረከዓ) ዐስር የለውም

የለም መግሪብ ሁለት ዙር (ረከዓ)

2 ዙር (ረከዓ) ዒሻእ ሁለት ዙር (ረከዓ)

Page 51: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት36

ዒድ ሶላትየዒድ ሶላቶች በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰገዳሉ፡፡ አንደኛው የረመዷን ወር ሲያበቃ የሚሰገድ ሲሆን ሁለተኛው በዙል-ሒጃ 10ኛው ቀን ይሰገዳል፡፡

በነዚህ ዒዶች ሁለት ዙር (ረከዓ) የሚሰገድ ሲሆን ተክቢራ (አላሁ አክበር) በብዛት ይባላል፡፡ እንዲሁም ከሶላቶቹ በኋላ ዲስኩር (ኹጥባ) ይሰማል፡፡

የተራዊሕ ሶላት

ተራዊሕ በረመዷን ወር ምሽት ከኢሻእ ሰላት በኋላና ከዊትር በፊት የሚሰገድ የ20 ዙር (ረከዓ) ሶላት ነው፡፡ ተራዊህ ሶላት በየሁለት ረከዓው እየተሰላመተ ነው የሚሰገደው፡፡ በየዓመቱ የረመዷን ወር ምሽቶች በዓለም ዙሪያ ያሉ መስጊዶች በተራዊሕ ሶላት ሰጋጆች

አሸብርቀው ይታያሉ፡፡ ይህ ሶላት የረመዷን ወር ልዩ መገለጫ ነው፡፡

የመንገደኛ ሶላትአንድ ሰው አገር አቋርጦ የተጓዘ እንደሆን ወደ አገሩ እስኪመለስ አራት አራት ዙር (ረከዓ) የሆኑትን ሶላቶች እያሳጠረ ሁለት ሁለት ረከዓዎች በማድረግ እንዲሁም የዙሁርን ሶላት ከዐሥር የመግሪብን ደግሞ ከዒሻ ጋር በማጣመር መስገድ ይችላል፡፡

81 ኪ.ሜ የምትጓዝ ከሆነና የምትጓዝበት ምክንያት ለመልካም ተግባርና ለትክክለኛ ዓላማ ከሆነ ከከተማህና ከቤትህ ከወጣህ በኋላ ሶላትን ማሳጠርና ማቆራኘት መጀመር ትችላለህ፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ይበልጥ ማብራሪያ ከፈለግህ በአካባቢህ የዕውቀት ባለቤት (ዓሊም) በመጠየቅ የበለጠ ማብራሪያ ማግኘት ትችላለህ፡፡

የግዴታ ሶላትን ለማሰገድ ከሁሉም የሚመረጠው ከሰገጆቹ መካከል በሶላት ዙሪያ የተሻለ እውቀት (ዒልም)ያለው ነው፡፡ “

Page 52: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 53: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 54: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 55: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 56: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 57: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 58: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የረመዷን ፆምእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ፥ በናንተም ላይ ተጻፈ፥ (ተደነባ)፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (አል-በቀራህ ፡-183)

Page 59: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት40

ግዴታዎችና ቅድመ-ሁኔታዎች10

የረመዷን ወር መፆም ከእስልምና ምሶሶዎች አንዱ ነው፡፡ በዚህ የፆም ወር ሙስሊሞች በቀን ላይ መብላት፣ መጠጣትና ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ ተከልክለዋል፡፡ የረመዳን ፆም የሚጀመረው አንድም ጨረቃ መውጣቷ ታይቶ ሲረጋገጥ ሲሆን ጨረቃ መውጣቷ ካልተረጋገጠ ደግሞ የሻዕባን ወር 29 ወይም 30 ቀናት ከሞላ በኋላ ነው፡፡ የረመዷን ወር በዓመቱ ካሉት ወራት ይበልጥ የተከበረና በየቀኑ የሚሠራ መልካም ሥራም እጥፍ ድርብ ምንዳ የሚገኘበት ነው፡፡

መጾም ያለበት ሰው

ማንኛውም እድሜው ለአቅመ አዳም (ሄዋን) የደረሰ ጤነኛና በቂ ምክንያት የሌለው እስከሆነ ድረስ

የረመዳንን ወር የመፆም ግዴታ አለበት፡፡

የማይጾመው ሰው

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሰዎች ረመዷንን ከመጾም ነፃ ተደርገዋል፡-

1 መዳኑ የሚያጠራጥር በሽተኛ

2 በእርጅና ምክንያት መፆም የማይችል አረጋዊ

3 መዳን በሚችል ሕመም የተያዘ በሽተኛ

4 ከ81 ኪ.ሎ ሜትር በላይ የሆነ መንገድ የሚጓዝ መንገደኛ

5 በእርግዝና ላይ ያለችና የምታጠባ ሴት

6 የወር አበባ ዑደት ላይ ያለች ሴት

7 ከወሊድ በኋላ የሚመጣ ደም ያለባት ሴት

ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱት ሰዎች ከጾም ይቅርታ የተደረገላቸው ሲሆን ከ3-7 የተዘረዘሩት ካሉበት ሁኔታ እንደወጡ ፆማቸውን የማካካስ ግዴታ አለባቸው፡፡

ልብ ይበሉ፡-በወር አበባና በወሊድ ደም ላይ ካለሽ መፆም

የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖም ግን በነዚህ ወቅቶች ያለፉትን የፆም

ቀናት የረመዷን ወር ከወጣ በኋላ ባሉ ጊዜያት ማካካስ

ግዴታሽ ነው፡፡

ጾምዎ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ

ፆምዎ ተቀባይነት እንዲኖረው፡፡

1 ከወር አበባና ከወሊድ ደም ነፃ ይሁኑ

2 ጐህ ከመውጣቱ በፊት ንያ (እስቤ) ያድርጉ

3 ፆምዎን ሊያጠፉ ከሚችሉ ነገሮች ከጐህ ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ይቆጠቡ፡፡

Page 60: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 3፡- የረመዷን ፆም 41

በሥርዓት መቀጮ (ከፍፋራህ) ፆምን መተካት

የረመዳንን ወር መፆም ግዴታ እንደመሆኑ ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ሆን ብሎ ፆምን መግደፍ እንደ ከባድ ኃጢኣት ይቆጠራል፡፡ በአጠቃላይ አንድ ሰው ያለበቂ ምክንያት ሆነ ብሎ ፆሙን ካጠፋ ያንን ቀን ከምግብ በመቆጠብ መዋል ይኖርበታል፤ ያጎደፈውንም ቀን መተካት ይኖርበታል አንድ ሰው በፆሙ ወቅት ሆነ ብሎ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከፈፀመ የማካካሻ ፆም የመፆም ግዴታ አለበት፡፡

እንዲሁም ለሁለት ተከታታይ ወራት በመፆም ሥርየት ማግኘት ይችላል፡፡ ይህን የማይችል ከሆነ 60 ድሆችን የመመገብ ግዴታ አለበት፡፡

ያለ ሥርዓት መቀጮ (ከፍፋራህ) ፆምን መተካት

አንድ ሰው ፆሙን እየፆመ ሳለ በአዕምሮ መዛባትም ሆነ ሳያስበው ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አንዱን ካደረገ ፆሙን መተካት እንጂ የቤዛ ክፍያ (ከፍፋራህ)አይኖርበትም፡፡

1 ዉዱእ እያደረገም ሆነ ገላውን ሲታጠብ ውሃ ወደ ጉሮሮው ከወረደ

2 ከሽቶና ከምራቅ ውጪ ያሉ ንጥረ ነገሮች በአንድ ዓይነት ቀዳዳ ወደ አካሉ ከደረሱ፡፡

3 ብልትን በመነካካት ፍትወትን ካስወጣ

4 ወሲባዊ ግንኙነት ከፈፀመ

5 የረመዷን ወር መግባቱን በመዘንጋት ወይም ወሩ ሻዕባን እንደሆነ በማሰብ ሳያውቅ መብላት፡፡ ወይም አዲስ ሙስሊም ሆኖ የፆምን ሕግጋት ባለማወቅ ከበላ

አንድ ሰው ከላይ የተዘረዘሩትን ጥፋቶች ሆን ብሎ ቢፈጽም እንኳን ፆም ላይ መሆኑን እንዳስታወሰ ድርጊቱን በማቆም ጾሙን ይሙላ፡፡ እዲሁም ያቋረጠውን ቀን በመፆም ያካክስ፡፡

ፆምን መግደፍና የሚያስከትላቸው ውጤቶች11

Page 61: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት42

ፆምን ማካካስ

አንድ ሰው ከረመዳን ወር ላይ የገደፈው ቀን ቢኖር ረመዷን እንደወጣ ወዲያውኑ ያጠፋውን ቀን በመፆም ማካካስ አለበት፡፡ያለበቂ ምክንያት ዛሬ ነገ እያለ ከዘገየ ካሳ (ፊድያ) መክፈል አለበት።

ካሣ (ፊድያ) ከዚህ በታች ባሉት ምክንያቶች ጾሙን ያሳለፈና ዳግመኛ መፆም ያልቻለ ለእያንዳንዱ ቀን አንዳንድ ምስኪን መመገብ ይኖርበታል፡፡

የአደም ልጅ መልካም ተግባሩ በሙሉ ለራሱ ነው፡፡ አንድ ጥሩ ሥራ ቢሠራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ ድረስ ተባዝቶ ምንዳ ሊያገኝ ይችላል፤ ከፆም በስተቀር፡፡ ፆም ለኔ ነው የምመነዳውም እኔው ነኝ፡፡ ሐዲስ አል-ቁድሲ

1 ዕድሜው የገፋ ከሆነ

2 በቀላሉ መዳን የማይችል በሽታ ያለበት

3 በእርግዝና ወይም በማጥባት ምክንያት የፆም ጊዜው ያለፋት እናት፣ በመፆሟ ጽንሱ የሚጎዳ አለያም የምታጠባው ልጅ ለረሃብ ይጋለጥብኛል ብላ የፈራች፡ ያጠፋቸውን እያንዳንዱን ቀን ከማካካስ በተጨማሪ አንድ አንድ ድሃ መመገብ ይኖርባታል፡፡

Page 62: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ክፍል 3፡- የረመዷን ፆም 43

የረመዷንን ቀን እንዴት እንፆማለን12

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «ምንዳ (አጅር) እንደሚያገኝ አምኖ አስተንትኖ የረመዳንን ወር የፆመ ያለፈውን ኃጢኣቱን አላህ ይምረዋል»11 ብለዋል፡፡

1 የረመዷንን ቀን ለመፆም ምሽቱን ኒያ (እሳቤ) ማድረግ አለብህ፡፡

2 ጐሕ ከመውጣቱ በፊት ስሁርን ተመገብ፡፡

3 ከንጋት እስከ ምሽት ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች ታቀብ፡፡

4 ቀኑን ሙሉ መልካም ተግባራትን ብቻ ሥራ

5 ፀሐዩዋ እንደጠለቀች ወዲያው ፆምህን ግደፍ (አፍጥር)

6 በእርጥብ ወይም በደረቅ ቴምር ካልሆነም በውሃ ፆምህን ግደፍ (አፍጥር)፡፡

በምታፈጥርበት ጊዜ ከዚህ በታች ያለውን ዱዓ አድርግ «አላሁምመ ለከ ሱምና ወዐላ ሪዝቂከ አፍጠርና ፈተቀበል ሚና ኢንነከ አንተ ሰሚዑ-ል-ዓሊም» «አላህ ሆይ! ላንተ ስንል ፆምን አንተ በሰጠኸን ሲሳይም እንገድፋለን

(እናፈጥራለን)፡፡ ፆማችንን ተቀባይነት ያለው አድርግልን፡፡ አንተ ሰሚና አዋቂ ነህ፡፡»

7 የመግሪብን ሶላት በወቅቱ ስገድ ቀጥለህም ምግብህን ተመገብ፡፡

8 ከዒሻእ ሶላት በኋላ የተራዊሕ ሶላትን ስገድ፡፡

Page 63: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት44

የተፈቀዱና የተከለከሉ የፆም ዓይነቶች 13

ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቀናት መፆም የተፈቀደ ነው

1 የዐረፋን ቀን መፆም ሐጅ የማያደርጉ (የዙልሒጃን ዘጠነኛ ቀን)

2 ከዐረፋ ቀን አስቀድመው ያሉትን የዙልሒጃን ስምንት ቀናት መፆም

3 የሙሐረምን ወር 10ኛ ቀን መፆም

4 የሙሐረምን ዘጠነኛ ቀን መፆም

5 የቀሩትን የሙሐረም ቀናት መፆም

6 የረጀብን ወር መፆም

7 የሸዕባንን ወር መፆም

8 የሸዋል ወርን ስድስት ቀናት መፆም

9 ሰኞ ቀንን መፆም

10 ሐሙስ ቀንን መፆም

11 በጨረቃ አቆጣጠር በየወሩ ሦስት ቀናትን መፆም

የተከለከሉ የፆም ቀናት

ማንኛውም ሙስሊም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቀናት መፆም አይፈቀድለትም፡-

1 ዒድ አል-ፈጥር

2 ዒድ አል-አድሐና አያመ ተሽሪቅ (ከዒድ በኋላ ያሉትን ሦስት ቀናት)

Page 64: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 65: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት46

ማጠቃለያ

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «አላህ ደግ ነገር የሻለትን ሰው

የሃይማኖት እውቀት ይሰጠዋል»12 ብለዋል፡፡ አንተ

ሁለት ጊዜ የአላህን ጸጋዎች አግኝተሃል፡፡

አንደኛው አላህ ወደ ሃይማኖቱ የመራህ በመሆኑ

ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እርሱን ለማምለክ ቀናውን

ጐዳና እንድታውቅ እውቀት ሰጥቶሃል፡፡ ይህ መማሪያ

በአላህ ፈቃድ ለሕይወት ዘመንህ ሁሉ ጠቃሚ ነው፡፡

«መለኮታዊው መንገድ» አላህን ለመገዛት መሠረታዊ

የሆኑ መመሪያዎችን ከማስገንዘብ ውጪ ሌሎች ዝርዝር

ጉዳዮችን አይነግርህም፡፡ ሆኖም እነዚህን መማሪያዎች

በአጭሩ ለማስገንዘብ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው፡፡

በተጨማሪም ለላቁ ኢስላማዊ እውቀቶች በር

ይከፍትልሃል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የተጠቀሱ መረጃዎች

ጥቅማቸው በራሳቸው ብቻ የተወሰነ አይደለም

የዕውቀትን ሰንሰለት ከትውልድ ወደ ትውልድ

የማድረስ ባሕልን ለማስቀጠል ጭምር እንጂ፡፡

በዚህ መጽሐፍ የምታነብባት እያንዳንዷ መመሪያ ከነቢዩ

ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ድርጊቶች ጋር የተሳሰረች

ናት፡፡አሁን ከአራቱ መዝሀቦች የአንዱን መሠረታዊ

ትምህርት በመማርህ እስላማዊ እውቀትህ ይበልጥ

እንዲሰፋ የሚያደርጉ መምህራንን የምትፈልግበት ደረጃ

ላይ ትገኛለህ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የምታገኛቸው መረጃዎች የውቅያኖስን ያህል

የሰፉ ናቸው፡፡ ከዚያም ውስጥ የተወሰነው ትክክለኛና

ጠቃሚ ሲሆን የተወሰነው ግን አይጠቅምህም፡፡

የትኛው ጠቃሚ ነው? የሚለውን ለመለየት ተመራጩ

መንገድ የመረጃው ሠንሠለት ያልተቋረጠ የሆነውን

ዕውቀት በአላህ ፈቃድ ማረጋገጥ ነው፡፡

እንግዲህ ሃይማኖትህን በተመለከተ ከዚህ ያነሰ መረጃን

ያለመቀበል መርህ ሊኖርህ ይገባል፡፡

አስታውስ የተማርካትን እያንዳንዷን ጥቂት እውቀት

ማስታወስና ከሁሉም በላይ ደግሞ በተግባር መለወጥ

Page 66: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

ማጠቃለያ 47

ይገባል፡፡ ሃይማኖታዊ እውቀት ጥቅም ላይ ሊውል

የሚገባው የእውቀት ዓይነት ነው፡፡ስለሆነም የተማርከውን

ወደ ተግባር ለውጠው፡፡ ያንን ብታደርግ ይበልጥ ዕውቀትህን

ለመጨመር ቀላል ይሆንልሃል፡፡ እንዲህ የሚል አባባል

ተጠቅሷል፡- “ያወቀውን የሚተገብር አላህ ዕውቀትን

ይጨምርለታል” 13

አንዳንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን በአንድ ጊዜ እየተማርክ

እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል፡፡ ሆኖም ታገስ፡፡ ፍጹምነትን

አሁኑ በራስህ ላይ ለማምጣት አትጠብቅ፡፡ እውነተኛ ሁን፡፡

ባደረከው የተባረከ ምርጫ በየዕለቱ ምቾት እየተሰማህ

እንደሚሄድ እወቅ፡፡

በችግርህና በምቾትህ ጊዜያት ሁሉ ፊትህን ወደፈጣሪ

አዙር ያኔ ሸክምህን የሚያቀልልህ ወዳጅ እንዳለህ

ትገነዘባለህ፡፡

ሁሌም በምትሠራው ሥራ አላህን በማስደሰት ምንዳ

እንደምታገኝ አስብ፡፡ አስቸጋሪም ቀላልም ነገር ከአላህ

ነው ብለህ ነገርህን ወደ አላህ ካስጠጋህ አላህ ከባዱን

ነገር ቀላል ያደርግልሃል፡፡

«… አላህ በናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል በናንተም ችግሩን

አይሻም…..» (አል-በቀራህ፡ 185)

1.ይህ ሃይማኖት የችግር ሃይማኖት አይደለም፡፡ እኛ

በቁርኣንና በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ

ሃይማኖት ገር እንደሆነ ባማረ መልኩ ተገልፆልናል፡-

«ሃይማኖት ገር ነው ማናችሁም ይህንን ዲን አያጠብቀውም

የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ፡፡ ጽናትን ተላበሱ፡፡

የቻላችሁትን ያህል ሥሩ፡፡ የመልካም ሥራ ምንዳችሁን

እንደምታገኙ ብስራት አላችሁ፡፡ በጧት፣ በምሽትና

ከሌሊቱም በተወሰነው ክፍል የጌታችሁን እርዳታ ጠይቁ»

ይህ መመሪያ ሃይማኖትህን ይበልጥ ለማወቅ

በምታደርገው ጉዞ ከምታነብባቸው በርካታ መጽሐፍት

የመጀመሪያው ነው፡፡

አላህ መልካም ሥራህን ይቀበልህ፡፡

አሚን

Page 67: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት48

የቃላት መፍቻ

ሐደስ፡- መንፈሳዊ ዕድፈት ሐደስ መለስተኛና ከፍተኛ በሚል በሁለት ይከፈላል፡፡ መለስተኛው ዉዱእ በማድረግ

የሚወገድ ሲሆን ከፍተኛው መላ ሰውነትን መታጠብን ይጠይቃል፡፡

ሐዲስ፡- የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተመዘገቡ አባባሎችና ድርጊቶች ከቁርኣን ቀጥሎ ሁለተኛው የእስልምና እውቀት

ሐዲስ ነው፡፡

ሐዲስ-አል-ቁድስ፡- ቃሉ የአላህ ሆኖ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተላለፉት፡፡ ይህ ከቁርኣን የሚለይ ነው፡፡

ሐጅ፡- ከእስልምና መሠረቶች አንዱ ሲሆን መካ በመሄድና የአላህን ቤት በመጐብኘት የሚፈጸም ሃይማኖታዊ ተግባር

ሐላል፡- በሸሪዓ (በኢስላማዊ ሕግ) የተፈቀደ ነገር

ሐራም፡- በሸሪዓ (በኢስላማዊ ሕግ) ያልተፈቀደ ነገር

ሐይድ፡- የወር አበባ

መዝሀብ፡- በኢስላማዊ ሕግ ላይ ተመስርቶ፣ ተቀባይነት ያገኘና ሃይማኖታዊ ክንውኖች የሚፈጸሙበት መንገድ፡፡

መግሪብ፡- ፀሐይ ስትጠልቅ የሚሰገድ የግዴታ ሶላት፡፡

መክሩህ፡- በኢስላማዊ ሕግ መሠረት የተጠላ ተግባር፡፡

መንዱብ፡- በኢስላማዊ ሕግ መሠረት የሚበረታታ ተግባር፡፡

መስጂድ፡- የሙስሊሞች የአምልኮ ቤት፤ እንዲሁም የማህበረሰቡ (ኡማው) ማዕከል፡፡

መካ፡- ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተወለዱበት የዐረቢያ ዋና ከተማ፡፡

ሙባሕ፡- በኢስላማዊ ሸሪዓ ሕግ ትዕዛዝ ቢሠራም ባይሠራም ጉዳት የማያመጣ የተፈቀደ ነገር፡፡

ሙአዝዚን፡- ሶላት እንዲሰገድ ኢስላማዊ ጥሪን የሚያስተላልፍ ሰው፡፡

ሙሐረም፡- በኢስላማዊ የወራት አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር፡፡ የሂጅራን አቆጣጠር ተመልከት፡፡

ሙከልለፍ፡- ሃይማኖታዊ ተግባራትን እንዲፈጽም ግዴታ የተጣለበትና ባይፈጽም ደግሞ ተጠያቂ የሚሆን ሰው፡፡

ሙስሊም፡- እስልምናን ሸሃዳ በመያዝ የተቀበለ ሰው፡፡

ሱጁድ፡- ግንባርን ከመሬት ጋር በማገናኘት መስገድ፡፡

ሶላት፡- ከአምስቱ የእስልምና መሠረቶች አንዱ የሆነው የስግደት አምልኮ፡፡

ፆም፡- ጐህ ከመውጣቱ ቀደም ብሎ ጀምሮ ፀሐይ እስክተገባ ድረስ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከመጥፎ ነገሮች መታቀብ፡፡

የረመዷንን ወር መጾም ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት አንዱ ነው፡፡

ሰሑር፡- የዕለቱ ፆም ከመጀመሩ በፊት ሌሊት የሚበላ የምግብ (ማሳሪያ) ሱንና፡-

1. የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ድርጊቶችና ፈለገ ሕይወታቸው፡፡

2. ቢሠራ ምንዳ (አጅር) የሚገኝበት ባይሠራ ግን ቅጣት የማያስከትል የአምልኮ ተግባር፡፡

ሱራ፡- የቁርኣን ምዕራፍ፡፡ በቁርኣን ውስጥ 114 ምዕራፎች አልሉ፡፡

Page 68: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የቃላት መፍቻ 49

ረጀብ፡- በኢስላማዊው የወራት አቆጣጠር ሰባተኛው ወር፡፡ የሂጅራ አቆጣጠርን ተመልከት፡፡

ረመዷን፡- በኢስላማዊው የወራት አቆጣጠር የተከበረ ወር ሲሆን በዚህ ወር ነበር ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ቁርኣን

የወረደላቸው፡፡ ሙስሊሞች ጐሕ ከመውጣቱ በፊት ጀምረው ፀሐይ እስክትጠልቅ ይጾማሉ፡፡

ረከዐህ፡- አንድ ዙር ስግደት፡፡ ማለትም አንድ ሰው ለሶላት ቆሞ ፋቲሐን ቀርቶ ሩኩዕና ሱጁድ የሚያደርግበት ዙር ነው፡፡

የሶላት አሰጋገድ ሥርዓትን ተመልከት፡፡

ሸዕባን፡- በኢስላማዊ የወራት አቆጣጠር ስምንተኛው ወር፡፡

ሸሪዓ፡- ኢስላማዊ ሕግ፡፡

ቂብላህ፡- ፊትን ወደ መካ በማዞር ሶላትን የመስገጃ አቅጣጫ፡፡

ቂያስ፡- ኢስላማዊ የሸሪዐህ ሕግን ለማበጀት የሚያገለግል የማንጸሪያ መንገድ ሲሆን ዋና ዋና ከሚባሉት የኢስላማዊው

ሕግ ምንጮች አንዱ ነው፡፡

ቁርኣን፡- የእስልምና ቅዱስ መጽሐፍና የአላህ ቃል ሲሆን በጅብሪል (ዐ.ሰ) አማካይነት ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

የተወረደ፡፡

በስመላ፡- ሙስሊሞች ማንኛውንም ተግባራት ሲጀምሩ የሚጠቀሙት ቃል፡፡ ትርጉሙም «በአላህ ስም እጅግ በጣም

ርኅሩኅና በጣም አዛኝ ማለት ነው፡፡»

ተሐጁድ፡- ከእኩለ ሌሊት በኋላ ሱብሒ ከመድረሱ በፊት የሚሰገድ ሱንና ሶላት፡፡

ተክቢር፡- «አላህ ትልቅ ነው» ብሎ ማወጅ፡፡

ተክቢራት፡- የተክቢር አብዢ ቃል፡፡

ተራዊሕ፡- በረመዷን ወር ከዒሻእ ሶላት በኋላ የሚሰገድ ሱንና ሶላት፡፡

ተሸሁድ፡- ሶላት በሚሰገድበት ጊዜ ከሱጁድ በኋላ የመቀመጥ ስርዓት፡፡

ተየሙም፡- ውሃ በሌለበት ወይም መጠቀም በማይቻልበት ጊዜ የሚደረግ ደረቅ ዉዱእ፡፡

ነጃሳ፡- ቆሻሻ

Page 69: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት50

አደብ፡- ክቡር ባሕሪና የላቀ ሥነ-ምግባር፡፡

አዛን፡- በእስልምና ለሶላት የሚደረግ ጥሪ፡፡

አያህ፡- የቁርኣን አንቀጽ፡፡

ኢፍጣር፡- በቀኑ መጨረሻ ፆምን የመግደፍ ሥርዓት፡፡

ኢጅማዕ፡- ታዋቂ ሙስሊም ምሁራን በአንድ ኢስላማዊ ጉዳይ የሚኖራቸው ተመሳሳይ አቋም ሲሆን የኢስላማዊ ሸሪዓ

ሕግ አንዱ ምንጭ ነው፡፡

ኢማም፡- በሶላት ወቅት ተከታዮቹን የሚመራ፡፡

ኢቃማህ፡- ሁለተኛውና ሶላት ሊጀመር መሆኑን ማብሰሪያ ጥሪ፡፡

ኢስላም፡- አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሰጣቸውና እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቆይ የመጨረሻው ሃይማኖት፡፡

ኢስቲብራእ፡- ከመጸዳዳት በኋላ የቀረውን ቆሻሻ (ነጃሳ) ከአካል የማስወገድ ተግባር ነው ለበለጠ መረጃ ነጃሳ

የሚለውን ቃል ተመልከት፡፡

ኢስቲሓዳ፡- ያልተለመደ ከሴት ብልት የሚወጣ ደም፡፡ ይህ ደም እንደ ወር አበባ ደም የሚቆጠር አይደለም፡፡

ኢስቲኻራ፡- ሁለት ነገሮች ለመምረጥ በምንቸገርበት ጊዜ ከአላህ ምሪት ለማግኘት የሚሰገድ ሶላት፡፡

እ.ሂ.አ (እንደ ሂጅራ አቆጣጠር)፡- ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና የተሰደዱበት ጊዜ መነሻ በማድረግ

የተጀመረ ዘመን አቆጣጠር ሲሆን ሥራ ላይ የዋለው በሁለተኛው ኸሊፋ በኡመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) የአስተዳደር

ዘመን ነው፡፡

ከዕባ፡- መካ የሚገኝ ቅዱስ መስጊድ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድና እውነተኛውን አምላክ ለማምለክ የተገነባ፡፡

ከፍፋራህ፡- የረመዷን ፆምን በመግደፍ የሚከፈል ማስተሰሪያ ቅጣት፡፡

ዐረፋ፡- ከሐጅ ተግባራት አንዱና ዋነኛው የሚፈጸምበት መካ አቅራቢያ የሚገኝ ሜዳማ ሥፍራ፡፡

አስር፡- ከቀትር በኋላ የሚሰገድ ሶላት፡፡

ዐውራህ፡- ሐፍረተ ገላ፡፡

ዒሻእ፡- ምሽት ላይ የሚሰገድ ሶላት

ዒድ፡- ዓመታዊ ወይም የዓመቱ አጋማሽ በዓል፣ በኢስላም ሁለት ዒዶች አሉ፡፡

ዒድ አል-አድሐ፡- ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ለመሰዋት የተዘጋጁበትን ጊዜ ለማሰብ የሚከበር በዓል ሲሆን

የሚውለውም በሐጅ ወቅት ነው፡፡

ዒድ አል-ፈጥር፡- የረመዳን ጾም ማብቂያ ላይ የሚከበር በዓል፡፡

Page 70: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የቃላት መፍቻ 51

ኹጥባ፡- ከጁሙዐህ ሶላት በፊትና ከዒድ ሶላት በኋላ የሚኖር ሃይማኖታዊ ዲስኩር፡፡ ጁምዓን ተመልከት፡፡

ዉዱእ፡- ሶላት ለመስገድ ሲባል እጅን ፊትን ራስን እግርን ማጠብ፡፡

ዊትር፡- ከዒሻእ ሶላት በኋላ በጎደሎ ቁጥር በፈቃደኝነት የሚሰገድ ሱንና ሶላት፡፡

ዙህር፡- የእኩለ ቀን ሶላት፡፡

ዙልሒጃ፡- በሂጅራ የወር አቆጣጠር 12ኛው ወር ሲሆን፣ የሐጅ ተግባር የሚፈፀምበትና ዒድ የሚከበርበት ወርም ነው፡፡

ዚክር፡- አላህን ማስታወስ፡፡

ጁሙዐህ፡- የዓርብ ዕለት የሕብረት ስግደት

ጂን፡-ከእሳት የተሠሩ ለሰዎች የማይታዩ ፍጡራን፡፡ ጂኖች ልክ እንደ ሰዎች ሁሉ በሠሩት ሥራ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡

ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ሙስሊሞች ሲሆኑ ከፊሉ ደግሞ ከሃዲያን ናቸው፡፡

ጠዋፍ፡- ከዕባን መዞር፡፡ ከጥንት ጀምሮ ሲፈጸም የኖረ ሃይማኖታዊ ተግባር ሲሆን ኢሰላምም ተቀብሎት (አንዳንድ

ማሻሻያዎችን በማከል) እንዲሠራበት አድርጓል፡፡

ፈጅር፡- የንጋት ሶላት፡፡

ፈርድ፡- በእስልምና ሕግ ግዴታ የሆነ ተግባር፡፡

ፋቲሐ፡- የቁርኣን መክፈቻ ምዕራፍ፤ የመላው ቁርኣን ልብ ነው ተብሎም ይቆጠራል፡፡

ፊድያ፡- ፆምን የገደፈ ሰው የሚከፍለው ማስተሰሪያ፡፡

Page 71: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት52

የመጸዳጃ ቤት ሥርዓት

ወደ መጸዳጃ ቤት ከመግባትህ በፊት«ቢስሚላህ አላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነ-ል-ኹብሲ ወል-ኸባኢስ» በል፡፡ትርጉም፡- በአላህ ስም ጌታዬ ሆይ ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ከሽንት ቤት በሚወጣበት ወቅት፡-«ጉፍራነከ»ትርጉም፡- ጌታዬ ሆይ! ምህረትህን እለምንሃለሁ፡፡

ዉዱእዉዱእ ከመጀመርህ በፊት፡-

«ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም»

እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝና በሆነው አላህ

ስም፡፡

ዉዱእ ስታጠናቅቅ

«አሸሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሁ ላ

ሸሪከ ለሁ ወአሸሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ

ወረሱሉሁ አላሁምመ ኢጅዐልኒ ሚነት-ተዋቢን

ወጅዐልኒ ሚነ-ል-ሙተጠሂሪን»

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ

የለም፡፡ እርሱም አጋር የሌለው ብቸኛ ነው ብዬ

እመሰክራለሁ፡፡ ሙሐመድ ባሪያውና መልዕክተኛው

መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ከዘወትር

ተጸጻቾቹና ከተጥራሩ ባሪያዎች አንዱ አድርገኝ፡፡

ምዕመናንን ወደ ሶላት ለመጥራት

አዛን

አላሁ አክበር (አራት ጊዜ)

አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለልላህ (ሁለት ጊዜ)

አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉልላህ (ሁለት ጊዜ)

ሐይየ ዐለስ-ሶላህ (ሁለት ጊዜ)

ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ (ሁለት ጊዜ)

አስ-ሶላቱ ኸይሩን ሚነን-ነውም (ሁለት ጊዜ

በሱብሒ ወቅት ብቻ ነው የሚባል)

አላሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

ላ ኢላሀ ኢልለልላህ (አንድ ጊዜ)

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ሌላ ጌታ የለም

ብዬ እመሰክራለሁ

ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብዬ

እመሰክራለሁ

ወደሶላት ኑ

ወደ ተሳካ ሕይወት ኑ

ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ነው

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም

በአዛኑ ወቅት

ሙአዚኑ የሚለውን ተከትለህ ትደግማለህ፡፡ ሆኖም

ሙአዚኑ «ሐይየ ዐለስ-ሶላህ» በሚልበትና

«ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ» በሚልበት ወቅት ብቻ

አንተ ማለት ያለብህ «ላ ሐውል ወላ ቁውወተ

ኢልላ ቢልላህ» ነው

ትርጉም፡- ብልሃትም ሆነ ጉልበት ያለው ለአላህ

ብቻ ነው

በድምጽ የተዘጋጀው ማገዣ ትርጉሞችና አነባበባቸው

የጸሎት ቃላት ድምጾች

Page 72: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የጸሎት ቃላት ድምጾች 53

ከአዛን በኋላ

ከሙአዚኑ እየቀጠልክ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን

ካልክ በኋላ አላህ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

እና በቤተሰቦቻቸው ላይ በረከቱን

እንዲያወርድባቸው ቀጥሎ ያለውን ጸሎት (ዱዓ)

ታደርጋለህ፡-

«አላሁምመ ረብበ ሃዚሂድ-ደዕወቲ ታምመቲ

ወስ-ሶላቲ-ል-ቃኢመቲ አቲ ሙሐመዲን

አል-ወሲለቲ ወል-ፈዲላህ ወብአሥሁ መቃመን

ማሕሙደን አል-ለዚ ወዐድተሁ ኢንነከ ላ

ቱኽሊፉል-ሚዓድ»

ትርጉም፡-

‹‹የዚህ ምሉዕ ጥሪያችን እና የዚህ የሚቆመው

ሶላት ጌታ የሆንክ አላህ ሆይ! በጥሪው (በፀሎቱ)

በረካ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዝንተ

ዓለማዊ የማማለድ መብቶች፣ ማዕረግና በጀነትም

እጅግ ከፍተኛውን ደረጃ ስጣቸው፡፡ ቃል

ወደገባህላቸው ከፍተኛ ደረጃም ከፍ አድርጋቸው

በእርግጥም አንተ ቃልህን አታጥፍምና፡፡»

ኢቃማ

አላሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለልላህ (አንድ ጊዜ)

አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉልላህ (አንድ ጊዜ)

ሐይየ ዐለስ-ሶላህ (አንድ ጊዜ)

ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ (አንድ ጊዜ)

ቀድ ቃመቲ ሶላህ (ሁለት ጊዜ)

አላሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

ላ ኢላሀ ኢልለልላህ (አንድ ጊዜ)

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም

ብዬ እመሰክራለሁ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ

ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ

ለሶላት ተሰብሰቡ

ለእውነተኛ ነፃነት ተሰብሰቡ

በርግጥ ሶላት ተጀምሯል

አላህ ትልቅ ነው

ከአላህ በስተቀር በርግጥ አምልኮ የሚገባው ሌላ

ጌታ የለም

ወደ ሶላት መግባትተክቢራ

አላሁ አክበር

“አላህ ትልቅ ነው”

የመክፈቻ ጸሎት

«ወጀህቱ ወጅሂየ ሊለዚ ፈጠረ አስ-ሰማዋቲ

ወል-አርደ ሐኒፈን ሙስሊመን ወማ አነ ሚነ-ል-

ሙሽሪኪን፡፡ ኢንነ ሶላቲ ወኑሱኪ ወመሕያየ

ወመማቲ ሊላሂ ረቢ-ል-ዓለሚን፡፡ ላ ሸሪከ ለሁ

ወቢዛሊከ ኡሚርቱ ወአነ ሚነ-ል-ሙስሊሚን»

ትርጉም፡-

“ፊቴን፡- ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው ፍጹም

የጠራና ብቸኛ የሆነው አምላክ አዞርኩ፡፡ እኔ በሱ ላይ

ከሚያጋሩት አይደለሁም፡፡ ስግደቴም፣ ጸሎቴም፣

መኖሬም፣ መሞቴም፣ የዓለማት ጌታ ለሆነው ለፈጣሪዬ

ነው፡፡ ብቸኛ ነው፡፡ አጋር የለውም በዚህም ታዝዣለሁ፡፡

እሱን ከሚታዘዙት ሙስሊሞችም ነኝ፡፡”

በአላህ መጥጠበቅ

“አዑዙ ቢልላሂ ሚነሸ-ሸይጧኒር-ረጂም” ትርጉም፡-

«እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለሁ፡፡»

“ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም”

Page 73: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት54

ትርጉም፡-

«በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ

በሆነው»

ፋቲሐ

አልሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን፤ አር-ረሕማኒር-

ረሒም፤ ማሊኪ የውሚድ-ዲን፤ ኢይያከ

ነዕቡዱ ወኢይያከ ነስተዒን፤ ኢህዲነስ-ሲራጠ-ል-

ሙስተቂም፤ ሲራጠል-ለዚነ አንዐምተ ዐለይሂም፤

ገይሪል መግዱቢ ዐለይሂም ወለድ-ዷሊን፡፡ አሚን፡፡

ትርጉም፡-

«ምሥጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ (ብቻ)

ይግገባው፤ እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ፤

የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው፤ አንተን ብቻ እንገዛለን፤

አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን፤ ቀጥተኛውን

መንገድ ምራን÷ የነዚያን በነርሱ ላይ በጎ

የዋልክላቸውን፤ በነርሱም ላይ ያልተቆጣህባቸውንና

ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን፡፡»

ማጐንበስ (ሩኩዕ) ላይ

“ሱብሐን ረብቢየል ዐዚም”

ትርጉም፡-

«ከሁሉም በላይ ትልቅ ለሆነው ጌታዬ ጥራት

ይገባው» ይባላል፡፡

ከሩኩዕ ሲነሱ የሚባለው ዱዓ

“ሰሚዐልላሁ ሊመን ሐሚደህ”

“ረብበና ወለከል ሐምድ”

ትርጉም፡-

«አላህ በርግጥ የሚያመሰግነውን ሰው ሰማ ጌታችን

ሆይ! ምስጋና (ሁሉ) ላንተ ይግባህ፡፡»

ሱጁድ ላይ የሚባለው ዱዓ

“ሱብሓነ ረብቢየል አዕላ”

ትርጉም፡-

«ከሁሉም በላይ ልዑል ለሆነው ለጌታዬ ጥራት ይገባው»

ከሱጁድ ሲቀመጡ የሚባለው ዱዓ

«ረቢ ኢግፊር ሊ ረቢ ኢግፊር ሊ»

«ጌታዬ ሆይ ማረኝ ጌታዬ ሆይ ማረኝ»

ተሸሁድ

«አት-ተሒያቱ አል-ሙባረካቱ አስ-ሶላዋቱ

አጥ-ጠይባቱ ሊላህ አስ-ሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-

ነቢይዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካትሁ አስ-ሰላሙ

ዐለይና ወዐላ ዒባዱላሂ አስ-ሷሊሒነ አሽሀዱ አን

ላ ኢላሀ ኢለልልላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን

ዐብዱሁ ወረሱሉህ»

ትርጉም፡-

«ክብር፣ ታላቅነት፣ ሶላትና መልካም ነገሮች ሁሉ

ለአላህ ናቸው፡፡ አንቱ ነቢይ ሆይ! የአላህ ሰላም

እዝነቱና በረከቶቹ ለርስዎ ይሁን ሰላም ለኛና

ለደጋጎቹ የአላህ አገልጋዮች ይሁን፡፡ ከአላህ

በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ፡፡

ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ እና አገልጋዩ

መሆናቸውን እመሰክራለሁ»

«አላሁምመ ሶልሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶልለይተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢብራሂመ ወባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢብራሂመ ፊ-ል-ዓለሚነ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ»

«አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው

እዝነትህን እንዳወረድክላቸው ለሙሐመድና

ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው ኢብራሂምንና

ቤተሰቦቻቸውን ብሩክ እንዳደረግካቸው

ሙሐመድና ቤተሰቦቻቸውን ብሩክ አድርጋቸው

አንተ በዓለማት ሁሉ ምስጉንና ኃያሉ ነህና»

ማሰላመት (ማጠናቀቅ)

‹አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወረሕህመቱላህ›

Page 74: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የጸሎት ቃላት ድምጾች 55

‹አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላህ›

ትርጉም፡-

የአላህ ሰላምና በረከት በናንተ ላይ ይሁን

ከሶላት በኋላ የሚኖር ዚክር

አየተ-ል-ኩርሲይ «አልላሁ ላ ኢላሀ ኢልላ ሁወ-ል-ሐይዩ-ል-

ቀዩም ላ ተእኹዙሁ ሲነቱን ወላ ነውሙን ለሁ ማ

ፊስ-ሰማዋቲ ወማ ፊ-ል-አርዲ መን ዘል-ለዚ

የሽፈዑ ዒንደሁ ኢልላ ቢኢዝኒሂ የዕለሙ ማ በይነ

አይዲሂም ወማ ኸልፈሁም ወላ ዩሒጡነ

ቢሸይኢን ሚን ዒልሚሂ ኢልላ ቢማ ሻኣ ወሲዐ

ኩርሲይዩሁስ-ሰማዋቲ ወል-አርዲ ወላ የኡዱሁ

ሒፍዙሁማ ወሁወ-ል-ዐአሊይዩ-ል-ዐዚም»

ትርጉም፡-

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው

ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም

አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ

ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ

በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?

(ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው

ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ

ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም

(አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡

ጥበቃቸውም አያቅተውም እርሱም የሁሉ በላይ

ታላቅ ነው፡፡

ይቅርታን መጠየቅ

«አስተግፊሩላህ» (ሦስት ጊዜ)

አላህ ሆይ! ይቅር በለኝ

አላሁምመ አንተ ሰላም…

«አላሁምመ አንተስ-ሰላሙ ወሚንከስ-ሰላሙ

ተባረክተ ያ ዘ-ል-ጀላሊ ወል-ኢክራም»

ትርጉም፡-

አላህ ሆይ! ሰላም አንተ ነህ፤ የሰላም ምንጭም

አንተው ነህ፤ የተባረክህም ነህ፤ የልቅናና የክብር

ባለቤትም ነህ፡፡

አላሁምመ ላ ማኒዐ

«ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ

ለሁ-ል-ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ

ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁምመ ላ ማኒዐ ሊማ

አዕጠይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ

ዘ-ል-ጀድዲ ሚንከ-ል-ጀድዲ»

ትርጉም፡-

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ

የለም፡፡ እሱ ብቸኛና ተጋሪ የሌለው ነው፡፡

ሉዓላዊነትና ምሥጋና ለርሱ ብቻ ነው፡፡ በሁሉም

ነገር ላይ ቻይ ሙሉ ሥልጣን ያለው ነው፡፡ አላህ

ሆይ! አንተ የሰጠኸውን ነገር የሚከለክል፤

የከለከልከውን ነገር የሚሰጥ የለም፡፡ ካንተም ዘንድ

በዘሩ በጨዋነቱና በክብሩ ራሱን ወይም ሌላን ሰው

የሚፈይድ የለም፡፡

ሱብሓነልላህ አልሐምዱ ሊልላህ

«ሱብሓነልላህ»

ለአላህ ጥራት ይገባው

«አልሐምዱ ሊልላህ»

ምሥጋና ሁሉ ለአላህ ነው

«አላሁ አክበር»

አላህ ትልቅ ነው

ከላይ የተጠቀሱትን ባላቸው ቅደም ተከተል 33

ሰላሳ ሦስት ጊዜ ማለት ያስፈልጋል አስከትሎም

Page 75: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት56

«ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ

ለሁ-ል-ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ

ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር»

ትርጉም፡-

ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም፡፡

እርሱ ብቸኛና ተጋሪ የሌለው ነው፡፡ ሉዓላዊነትና

ምሥጋና ለርሱ ብቻ ነው፡፡ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ

(ሙሉ ስልጣን ያለው) ነው፡፡

ቁኑት

«አላሁምመ ኢህዲኒ ፊ መን ሀደይት ወዓፊኒ ፊ

መን ዐፈይት ወተወልለኒ ፊ መን ተወልለይት

ወባሪክ ሊ ፊ መን አዕጠይት ወቂኒ ሸርረ ማ

ቀደይት (በዚህ ጊዜ ወደ ላይ ተዘርግቶ የነበረውን

የእጃችን መዳፍ ወደታች እንዲያዘቀዝቅ

እናደርጋለን፤ የሚቀጥለውን ስንል እንደነበረው

እንመልሳለን) ፈኢንነከ ተቅዲ ወላ ዩቅዳ ዐለይከ

ወኢነሁ ላ የዚልሉ መን ዋአለይት ወላ የዒዝዙ

መን ዓደይት ተባረክተ ረብበና ወተዓለይት

ፈለከ-ል-ሐምዱ ዐላ ማ ቀደይት አስተግፊሩከ

ወአቱቡ ኢለይክ»

«አላህ ሆይ (ቀጥተኛውን መንገድ)

እንደመራሃቸው ሰዎች እኔንም ምራኝ፡፡ ጤነኛ

እንዳደረግካቸው ሰዎች እኔንም ጤነኛ አድርገኝ፡፡

እንደተንከባከብካቸው ሰዎች እኔንም ተንከባከበኝ፡፡

በምትሰጠኝ ነገር ሁሉ በረካ አድርግልኝ፡፡

ከደነገግካቸውም መጥፎ ነገሮች ሁሉ ጠብቀኝ፡፡

በርግጥ ነገሮችን ሁሉ የምትደነግገው አንተ ነህ፡፡

ባንተ ላይ ግን አይደነገግብህም፡፡ በእውነትም አንተ

ወድደህ ከፍ ያደረግከውን (ያከበርከውን) ሰው

የሚያዋርድ አንተ ያዋረድከውንም የሚያከብር

ከቶም የለም ጥራትና ክብር እንዲሁም ሉዓላዊነት

የተገባው ላንተ ነው፡፡ ጌታችን (ወንጀላችንን)

ይቅር እንድትለንም አንተኑ ይቅርታ እጠይቅሃለሁ፡፡

ወደ አንተም በንስሐ እመለሳለሁ፡፡»

የረመዳን ጾምጾሙን ስትጀምር እንዲህ ትላለህ/ትያለሽ

«ነወይቱ ሰውመ ገዲን ሚን ሸህሪ ረመዳን፡፡»

ወይም

«ወቢሰውሚ ገዲ ነወይቱ ሚን ሸህሪ ረመዳን»

የነገውን የረመዷን ወር ጾም ለመጾም አስቤያለሁ

ፆም ሲገደፍ (ሲፈጠር)

«አላሁምመ ለከ ሱምና ወዐላ ሪዝቂከ አፍጠርና

ፈተቀበል ሚንና ኢንነከ አንተ ሰሚዑ-ል-ዐሊም»

ጌታዬ ሆይ ላንተ ስንል ጾምን፤ ባንተም ምግብ

ጾማችንን ገደፍን፤ ጾማችንን ተቀበለን፤ በእውነት

አንተ ሰሚና አዋቂ የሆንክ ጌታ ነህ

ወይም

«አላሁምመ ኢንኒ ለከ ሱምቱ ወቢከ አመንቱ

ወዐለይከ ተወከልቱ ወዐላ ሪዝቂከ አፍጠርቱ»

ጌታዬ ሆይ ላንተ ስል ጾምኩ፤ በአንተም አመንኩ፤

ባንተ ላይ ተመካሁ፤ ባንተም ምግብ ጾሜን ገደፍኩ

በተጨማሪም

«አላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ቢረሕመቲከ አል-ለቲ

ወሲዐት ኩልለ ሸይኢን አንተ ኢግፊር ሊ»

ጌታዬ ሆይ! ያንተን እዝነት እጠይቅሃለሁ ሁሉንም

ነገር ባካበበው ምሕረትህ ጌታዬ ሆይ! ትምረኝ

ዘንድ እጠይቅሃለሁ፡፡

በረመዳን ለይለተል-ቀድር ሲያጋጥም የሚደረግ ልመና

«አላሁምመ ኢንነከ ዐፉዉን ቱሒቡ-ል-ዐፍወ

ፈዕፉ ዐንና»

ጌታዬ ሆይ! በርግጥ ይቅር ባይ ነህ፤ አንተ

ይቅርታን ወዳጅ ነህና ይቅርታ አድርግልን፡፡

Page 76: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የጸሎት ቃላት ድምጾች 57

የዕለት ተዕለት ዱዓ

ጠዋት ከእንቅልፍ በምንነቃበት ጊዜ «አልሐምዱ ሊልላሂ አል-ለዚ አሕያና በዕደ ማ አማተና ወኢለይሂን-ኑሹር»

ከሞትን በኋላ ላነቃን ለአላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው

ሲተኛ የሚባል ዱዓ«ቢስሚከል-ላሁምመ አሙቱ ወአሕያ»

ጌታዬ ሆይ በስምህ እሞታለሁ በስምህ እነቃለሁ፡፡

የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከመፈፀም በፊት«ቢስሚላህ አላሁምመ ጀንኒብና አሸ-ሸይጧን ወጀንኒቢ ሸይጧነ ማ ረዘቅተና»

በአላህ ስም ጌታዬ ሆይ ሁለታችንንም ከሸይጧን ጠብቀን የምትሰጠንንም ልጅ ከሸይጧን ጠብቅልን፡፡

ልብስ ሲለበስ የሚደረግ ዱዓአልሐምዱ ሊልላሂ አል-ለዚ ከሳኒ ሀዛ (አሥ-ሠውበ) ወረዘቀኒ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላ ቁውወቲን”

“ከኔ ችሎታና ኃይል ውጭ ይህንን ልብስ (የልብሱን ዓይነት ገልጸህ) ላለበሰኝና ለለገሠኝ አላህ ምስጋና ይገባው፡፡”

ልብስ በሚወለቅበት ጊዜ “ቢስሚልላህ “በአላህ ስም” ከምግብ በፊት የሚባል ዱዓ

“ቢስሚልላህ”

“በአላህ ስም”

ከምግብ በኋላ የሚደረግ ዱዓ“አልሐምዱ ሊልላሂ አልለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላ ቁውወቲ”

“ያለኔ ብልሃትና ኃይል ይህንን ምግብ ለለገሠኝ አላህ ምስጋና ይገባው፡፡”

ቤት ሲገባ የሚደረግ ዚክር“ቢስሚልላሂ ወለጅና፥ ወቢስሚልላሂ ኸረጅና ወዐላ ረብቢና ተወክከልና፡፡”

“በአላህ ስም (ወደ ቤታችን) ገባን፤ በአላህ ስምም (ከቤታችን) ወጣን፤ በጌ ታችንም ተመካን»

ከቤት ሲወጣ የሚደረግ ዚክር“ቢስሚልላሂ፥ ተወክከልቱ ዐለልላሂ፥ ወላ ሐውል ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ”

“በአላህ ስም (እጀምራለሁ)፡፡ በአላህ ላይም እመካለሁ፡፡ ከአላህ እርዳታ በስተቀር ብርታትና ኃይል የለም፡፡”

እንስሳት (መኪና፣ አውሮፕላን...) ላይ ሲወጡ የሚባል ዱዓ

“ቢስሚልላሂ ሱብሓነል-ለዚ ሰኽኸረ ለና ሀዛ ወማ ኩንና ለሁ ሙቅሪኒን ወኢንና ኢላ ረብቢና ለሙንቀሊቡን፤

“በአላህ ስም፣ ያ ይህንን የማንችለው ስንሆን ለኛ ያገራልን ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡”

ለጉዞ ሲወጡ የሚባል ዱዓአልላሁምመ ኢንና ነስአሉከ ፊ ሰፊሪና ሀዘል-ቢርረ ወት-ተቅዋ ወሚነ-ል-ዐመሊ ማ ተርዷ አልላሁምመ ሀውዊን ዐለይና ሰፈረና ሀዛ ወጥዊ ዐንና ቡዕደሁ አልላሁምመ አንተስ-ሷሒቡ ፊስ-ሰፈር ወልኸሊፈቱ ፊል አህሊ አልላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ወዕሣኢስ-ሰፈሪ ወከአበቲ-ል-መንዞሪ ወሱኢ-ል-ሙንቀለቢ ፊል-ማሊ ወል-አህሊ፡፡”

በተጨማሪ ከጉዞ ሲመለሱ ይህንኑ ዱዐ ካደረጉ በኋላ የሚቀጥለውን ማስከተል ‹አኢቡነ ታኢቡነ አቢዱነ ሊረቢና ሃሚዱን› ይባላል፡፡

Page 77: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት58

አላህ ሆይ! በዚህ ጉዟችን መልካም መሥራትን፣ አንተን መፍራትን፣ የምትወደውን ነገር እንድንፈጽምም እንጠይቅሃለን፡፡ አላህ ሆይ! ይህን ጉዟችንን አመቻችልን፤ በአጭር ጊዜም የምንቆርጠው አድርገን፡፡ አላህ ሆይ! አንተ በጉዞ ላይ ጓደኛ (ባልደረባ) ነህ፡፡ የቤተሰብም ምትክ (ዋቢ) ነህ፡፡ አላህ ሆይ! እኔ ከጉዞ ጣጣ ከአመላካከት ለውጥና በንብረትና በቤተሰብ ላይ መጥፎ ነገር ደርሶ ከመመለስ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡” ተመላሽ ነን፣ ተውበተኞች ነን፣ ተገዥዎች ነን፣ ለጌታችን አመስጋኞች ነን፡፡

ከጉዞ ሲመለሱ

በየትኛውም ጊዜ ከሩቅ ሀገር ሲመለሱ“አላሁ አክበር (3 ጊዜ) ካሉ በኋላ የሚቀጥለውን ያስከትሉ፡-

ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር አኢቡነ ዓቢዱነ ሊረቢና ሓሚዱን

ከአላህ በስተቀር አምልኮት የሚገባው ሌላ አምላክ የለም ብቸኛና አጋር የሌለው ንግሥና የሱ ነው፡፡ ምስጋናም የሱ ነው፡፡ እሱ በሁሉም ነገር ቻይ ነው፡፡ ተመላሽ ነን፣ ተውበተኞች ነን፣ ተገዥዎች ነን፣ ለጌታችን አመስጋኞች ነን፡፡

መስጂድ ሲገባ የሚባል ዱዓ

“አዑዙ ቢልላሂ-ል-ዐዚም፥ ወቢ ወጅሂሂ-ል-ከሪም፥ ወሱልጧኒሂ-ል-ቀዲም፥ ሚነሽ-ሸይጧኒር-ረጂም፡፡” (ቢስሚላሂ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊልላሂ) (አላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ)

“ታላቅ በሆነው አላህ፤ በተከበረው ፊቱ እና መጀመሪያ በሌለው ሥልጣኑ አሳሳች ከሆነ ሰይጣን እጠበቃለሁ (በአላህ ስም፣ የአላህ ሰላምና ሰላምታ በመልዕክተኛው ላይ ይስፈን) (ጌታዬ ሆይ የምህረት በርህን ክፈትልኝ)

ከመስጂድ ስንወጣ የሚባል ዱዓ

“ቢስሚልላህ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊልላህ አለሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊከ”

“በአላህ ስም የአላህ ረሕህመትና ሰላም በመልዕክተኛው ላይ ይሁን ጌታዬ ሆይ ረድኤትህን እጠይቃለሁ”

ወደ ገበያ ቦታ (ሱቅ) ሲገቡ የሚሉት ዱዓ"

“ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁ-ል-ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ዩሕዪ ወዩሚቱ ወሁወ ሐይዩን ላ የሙት ቢየዲሂ-ል-ኸይሩ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር፡፡”

“ከአላህ በስተቀር አምልኮት የሚገባው ጌታ እንደሌለ እመሰክራለሁ፡፡ አንድ ነው፡፡ ሸሪክ (አጋር) የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ነው፡፡ ምስጋና ለርሱ የተገባ ነው፡፡ ሕይወት የሚሰጠውም በሞት የሚወ ስደውም እርሱ ነው፡፡ ሕያውና ሞት የማይነካው ነው፡፡ በጐ ነገር ሁሉ በእጁ ይገኛል፡፡ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡”

የሶላተል ኢስቲኻራ (አማራጭ ለመውሰድ የሚሰገድ ሶላት) ዱዓ

“አልላሁምመ ኢንኒ አስተኺሩከ ቢዒልሚከ ወአስተቅዲሩከ ቢቁድረቲከ ወአስአሉከ ሚን ፈድሊከ-ል-ዐዚም ፈኢንነከ ተቅዲሩ ወላ አቅዲሩ ወተዕለሙ ወላ አዕለሙ ወአንተ ዐልላሙ-ል-ጉዩብ፡፡ አልላሁምመ ኢን ኩንተ ተዕለሙ አንነ ሀዘ-ል-አምረ ኸይሩን ሊ ፊ ዲኒ ወመዓሺ ወዐቂበቲ አምሪ -አው ቃለ ዓጂሊሂ ወኣጂሊሂ- ፈቅዱርሁ ሊ ወየስሲርሁ ሊ ሡምመ ባሪክ ሊ ፊሂ፤ ወኢን ኩንተ ተዕለሙ አንነ ሀዘል አምረ ሸርሩን ሊ ፊ ዲኒ ወመዓሺ ወዓቂበቲ አምሪ -አው ቃለ ዓጂሊሂ ወአጂሊሂ- ፈስሪፍሁ ዐንኒ ወስሪፍኒ ዐንሁ ወቅዱር ሊየ-ል-ኸይሩ ሐይሡ ካነ ሡምመ አርዲኒ ቢሂ፡፡”

Page 78: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

የጸሎት ቃላት ድምጾች 59

“በዕውቀትህ (በጐውን ነገር) እንድትመርጥልኝ እጠይቃለሁ፡፡ በችሎታህም (እተማመናለሁ በጐውን ምርጥልኝ)፡፡ ከታላቁ ትሩፋትህም እጠይቅሃለሁ፡፡ አንተ እንጂ እኔ ወሳኝ አይደለሁም፡፡ አንተ ዐዋቂ ነህ፡፡ እኔ ግን መሃይም ነኝ፡፡ አንተ የሩቅን ዐዋቂ ነህ፡፡ አላህ ሆይ! ይህ ጉዳይ (ጉዳዩን ይጥቀስ) ለኔ፣ ለሃይማኖቴ፣ ለሕይወቴና ለመጨረሻዬ በጐ ከሆነ ወስንልኝ፤ አቅልልኝም፤ ረድዔትህንም ሙላልኝ፡፡ ይህ ጉዳይ ለኔ፣ ለሃይማኖቴ፣ ለሕይወቴና ለመጨረሻዬና ለሕይወቴ መጥፎ ሆኖ የሚገኝ መሆኑን የምታውቅ በመሆኑ (መጥፎ ከሆነ) ከኔ አስወግደው፡፡ እኔንም ከርሱ አርቀኝ፡፡ ምንም ይሁን ምን መልካም ነገርን ወስንልኝ፡፡ ከዚያም እኔ (ውሳኔውን) እንድወድ (እንድቀበል) አድርገኝ፡፡”

ለጉዳይ (ሐጃ) የሚደረግ ዱዓ

ላ ኢላሀ ኢልለልላህ አል-ሐሊም አል-ከሪም ሱብሓነልላህ ረብቢ-ል-ዐርሺ-ል-ዐዚም አልሐምዱ ሊልላሂ ረብቢ-ል-ዓለሚን አስአሉከ-ል-ሙጂባቲ ረሕመቲከ ወዐዛኢመ መግፊረቲከ ወል-ገኒመተ ሚን ኩልሊ ቢርሪን ወስ-ሰላመቲ ሚን ኩልሊ ኢስሚን ላ ተዶዕ ዘንበን ኢልላ ገፈርተሁ ወላ ሀምመን ኢልላ ፈረጅተሁ ወላ ሐጀተን ሂየ ለክ ሪዷ ኢልላ ቀደይተሃ ያ አርሐመር-ራሒሚን

ከአላህ በስተቀር በርግጥ አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም እርሱ በእርግጥ እጅግ በጣም ታጋሽ ቸር ነው፡፡ የታላቁ ዐርሽ ጌታ የሆነው አላህ ጥራት ተገባው፡፡ የዓለማት ጌታ ለሆነው አላህ ምስጋና ተገባው፡፡ ጌታዬ ሆይ! እዝነትህንና ታላላቅ ምህረቶችህን የሚያመጡ ነገሮችን መብቃቃትን፣ ከሁሉ ሃጢአቶች መጠበቅን እጠይቅሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ማንኛውንም ሀጢኣት የማርክልን፤ ከማንኛውም ጭንቀት ነፃ ያወጣኸን፤ ማንኛውንም ጉዳዮች ያንተ ፈቃድ ሆኖ የፈጸምክልን ካልሆነ በስተቀር ከአዛኞች በላይ እጅግ አዛኝ የሆንከው ጌታ ሆይ አትተወን፡፡

አጫጭር የቁርኣን ምዕራፎች ሱረቱል ኢኽላስ (የፍፁምነት ምዕራፍ)

“ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም”“ቁል ሁወልሏሁ አሐድ አልሏሁስ-ሶመድ ለም የሊድ ወለም ዩለድ ወለም የኩን ልለሁ ኩፉወን አሐድ”

ትርጉም ፡- «እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው በአላህ ስም (እጀምራለሁ)፡፡» በል፡- እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደም፡፡ ለርሱም አንድም ቢጤ የለውም፡፡»

ሱረቱ አል-ፈለቅ (የተፈልቃቂው ጎህ ምዕራፍ)

“ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም”“ቁል አዑዙ ቢረብቢ-ል-ፈለቅ ሚን ሸርሪ ማ ኸለቅ ወሚን ሸርሪ ጋሲቂን ኢዛ ወቀብ ወሚን ሸርሪን-ነፍፋሣቲ ፊ-ል-ዑቀድ ወሚን ሸርሪ ሐሲዲን ኢዛ ሐሰድ”

ትርጉም፡-«እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው በአላህ ስም (እጀምራለሁ)»«በል፡- በተፍልቃቂው ጎህ ጌታ፤ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፤ ከሌሊትም ክፋት በጨለመ ጊዜ፤ በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከሆኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፤ ከምቀኛም ክፋት፣በተመቀኘኝ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)፡፡»

ሱረቱ አን-ናስ (የሰዎች ምዕራፍ)

“ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም”“ቁል አዑዙ ቢረብቢን-ናስ መሊኪን-ናስ ኢላሂን-ናስ ሚን ሸርሪ-ል-ወስዋሲ-ል-ኸንናስ አል-ለዚ ዩወስዊሱ ፊ ሱዱሪን-ናስ ሚነ-ል-ጂንነቲ ወን-ናስ”

Page 79: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት60

ትርጉም፡-«እጅግ በጣም ርኅሩኅ፣ በጣም አዛኝ በሆነው በአላህ ስም (እጀምራለሁ)»«በል-በሰዎች (ፈጣሪ) ጌታ እጠበቃለሁ፣ የሰዎች ሁሉ ንጉሥ በሆነው፣ የሰዎች ሁሉ አምላክ በሆነው፣ ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች (ሠይጣን) ክፋት፣ ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከሆነው፣ ከጋኔኖችም ከሰዎች (ሠይጣናት እጠበቃለሁ) በል፡፡»

Page 80: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-
Page 81: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት62

1ኢማም አልቡኻሪ፣ ሶሒሕ አልቡኻሪ

2ኢብን ሐጀር አልአስቀላኒ፣ ፈትሑል ባሪ

3ኢማም ሙስሊም፣ ሶሒሕ ሙስሊም

4ዝኒ ከማሁ

5ዝኒ ከማሁ

6ኢማም አልቡኻሪ፣ ሶሒሕ አልቡኻሪ

7ኢማም አቡዳዉድ፣ ሱነን

8ኢብን ሒባን፣ ሶሒሕ

9ኢማም አልቡኻሪ፣ ሶሒሕ አልቡኻሪ

10ዝኒ ከማሁ

11ኢማም ሙስሊም፣ ሶሒሕ ሙስሊም

12ኢማም አልቡኻሪ፣ ሶሒሕ አልቡኻሪ

13አቡኑዓይም፣ አልሒልያ

14ኢማም ሙስሊም፣ ሶሒሕ ሙስሊም

ማስታወሻዎች

Page 82: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - ZHICይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ-