2014–2015 · 2014. 8. 19. · a student’s guide to rights and responsibilities (የተማሪ...

24
የስቴት ህጎች፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ደንቦች፣ እና የMontgomery County የትምህርት ቦርድ እና የMontgomery County Public Schools (MCPS) የአስተዳደር ደንቦች መቀየር ይችላሉ እናም በዚህ ፅሁፍ በሰፈሩት መግለጫዎችና መጣቀሻዎች ላይ የበላይነት አላቸው። የተማሪ ስም ___________________________________ አድራሻ ______________________________________ ስልክ _______________________________________ Rockville, Maryland Amharic በMontgomery County Public Schools www.montgomeryschoolsmd.org መብቶችና ሀላፊነቶች 2014–2015 የተማሪ መመርያ ስለ

Upload: others

Post on 17-Nov-2020

5 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

የስቴት ህጎች፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ደንቦች፣ እና የMontgomery

County የትምህርት ቦርድ እና የMontgomery County Public Schools (MCPS)

የአስተዳደር ደንቦች መቀየር ይችላሉ እናም በዚህ ፅሁፍ በሰፈሩት መግለጫዎችና

መጣቀሻዎች ላይ የበላይነት አላቸው።

የተማሪ ስም ___________________________________

አድራሻ ______________________________________

ስልክ _______________________________________

Rockville, Maryland

Amharic

በMontgomery County Public Schools

www.montgomeryschoolsmd.org

መ ብ ቶ ች ና ሀ ላ ፊ ነ ቶ ች

2014–2015የ ተ ማሪ መመ ር ያ ስ ለ

Page 2: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

የትምህርት ቦርድ 850 Hungerford Drive, Rockville, Maryland 20850 301-279-3617ኢሜይል: [email protected]/boe

Mr. Christopher S. Barclay (ሚ/ር ክሪስቶፈር ኤስ. ባርክሌይ)ዲስትሪክት 4

Mr. Michael A. Durso (ሚ/ር ማይክል ኤ. ዱርሶ)ዲስትሪክት 5

Mrs. Patricia B. O’Neill (ወ/ሮ ፓትሪሽያ ቢ. ኦ'ኔይል)ም/ፕረዚደንትዲስትሪክት 3

Dr. Joshua P. Starr (ዶ/ር ጆሹዋ ፒ. ስታር)የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ

Mr. Larry A. Bowers (ሚ/ር ላሪ ኤ. ባወርስ)Chief Operating Officer (ዋና ስራ አስኪያጅ)

Dr. Kimberly A. Statham (ዶ/ር ኪምበርሊ ኤ. ስታታም)የት/ቤት ድጋፍና መሻሻል ም/የበላይ ተቆጣጣሪ

Dr. Maria V. Navarro (ዶ/ር ማሪያ ቪ. ናቫሮ)የስርአተ ትምህርት ዋና መኮንን

Mrs. Rebecca Smondrowski ዲስትሪክት 2

Dr. Judith R. Docca (ዶ/ር ጆዲት ዶካ)ዲስትሪክት 1

Mr. Philip Kauffman (ሚ/ር ፊሊፕ ካውፍማን)ፕሬዚደንትሁለ-ገብ/ተወካይ

Ms. Dahlia Huh (ወ/ይ ዳህሊያ ሁህ)ተማሪ አባል

የት/ቤት አስተዳደርwww.montgomeryschoolsmd.org

ራእይ

ለአያንዳንዱና

ለማንኛውም ተማሪ

እጅግ የላቀውን ህዝባዊ

ትምህርት በማቅረብ

ትምህርት እንዲሰርፅ

እናደርጋለን።

ተልእኮ

እያንዳንዱ ተማሪ

በኮሌጅም ሆነ በስራ

ስኬታማ እንዲሆን

አካዴሚያዊ፣ የችግር

አፈታት ፈጠራ፣ እና

የማህበራዊ ስሜት

ችሎታዎች ይኖሩታል።

የአላማ ፍሬ ነገር

ሁሉም ተማሪዎች

በወደፊት ኑሮአቸው

እንዲለሙ/እንዲበለፅጉ

ማዘጋጀት።

አይነተኛ እሴቶች

ትምህርት

ግንኙነቶች/ዝምድናዎች

ክብር

ልቀት

ፍትህ

Ms. Shirley Brandman (ወ/ይ ሺርልይ ብራንድማን)ሁለ-ገብ/ተወካይ

Page 3: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

© (የአሳታሚው መብት የተጠበቀ) ኦገስት 2014

Montgomery County Public Schools

Rockville, Maryland

በMontgomery County Public Schools

www.montgomeryschoolsmd.org

መ ብ ቶ ች ና ሀ ላ ፊ ነ ቶ ች

2014–2015የ ተ ማሪ መመ ር ያ ለ

Page 4: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

2014–2015 የትም/ቤት ቀን መቁጠርያ Montgomery County Public Schools2014ኦገስት 25 ለተማሪዎች የመጀመርያ የትምህርት ቀን

ሰፕተምበር 1 በአል-Labor Day (ወዛደር ቀን) ፅ/ቤቶችና ትም/ቤቶች ዝግ ናቸው

ሰፕተምበር 24ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን K–12።ፕላን ማድረጊያ/ማርክ መስጫ/እረፍቶች

ተማሪዎች ከምሳ በኋላ ይሰናበታሉ

ሰፕተምበር 25 Rosh Hashanah (የእብራይስጥ አዲስ አመት)ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት የለም(ማሳሰቢያ: Yom Kippur ቅዳሜ ኦክቶበር 4, 2014 ይውላል)

ኦክተበር 17 የMSEA ስብሰባ/የMCAAP የፎል ወራት ስብሰባ ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት የለም

ኦክተበር 30 የመጀመርያ ማርክ መስጫ ወቅት ማጠናቀቂያ

ኦክተበር 31 የመምህራን የባለሙያ ቀን ለተማሪዎች ትምሀርት የለም። የተወሰኑ የ10-ወር ሰራተኞች ይሰራሉ

ኖቨምበር 4 በአል—የምርጫ ቀን ፅ/ቤቶችና ትም/ቤቶች ዝግ ይሆናሉ

ኖቨምበር 10ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን K–8። የወላጅ ስብሰባዎች።

ተማሪዎች ከምሳ በኋላ ይሰናበታሉ

ኖቨምበር 11ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን K–8። የወላጅ ስብሰባዎች።

ተማሪዎች ከምሳ በኋላ ይሰናበታሉ

ኖቨምበር 12 ሪፓርት ካርድ የሚሰራጭበት

ኖቨምበር 26 በቅድሚያ ስንብት፣ K–12 ቅደመ Thanksgiving በአል

ኖቨምበር 27–28 በአላት-Thanksgiving ፅ/ቤቶችና ትም/ቤቶች ዝግ ይሆናሉ

ዲሰምበር 24-25 በአላት-ገና ፅ/ቤቶችና ትም/ቤቶች ዝግ ይሆናሉ

ዲሰምበር 26፣ 29፣ 30፣ 31

የዊንተር እረፍት ለተማሪዎችና መምህራን ትምህርት ቤት ዝግ ነው

2015ጃኑዋሪ 1 በአል—አዲስ አመት በአል ቀን ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጃኑዋሪ 2 የዊንተር እረፍት ለተማሪዎችና መምህራን ትምህርት ቤት ዝግ ነው

ጃኑዋሪ 16 ሁለተኛ ማርክ መስጫ ወቅት ይጠናቀቃል

ጃኑዋሪ 19 በአል—Dr. Martin L. King, Jr.- የዶ/ር ማርቲን ኤል ኪንግ ጁንየር ቀን ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጃኑዋሪ 20 የመምህራን የባለሙያ ቀን ለተማሪዎች ትምህርት የለም። የተወሰኑ የ10-ወር ሰራተኞች ይሰራሉ

ጃኑዋሪ 29 ሪፓርት ካርድ የሚሰራጭበት

ፌብሩዋሪ 16 በአል—የፕሬዚደንት ቀን ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ፌብሩዋሪ 27 ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን K–12። ፕላን ዝግጅት/ማርክ አስጣጥ ተማሪዎች ከምሳ በኋላ ይሰናበታሉ

ማርች 26 ሶስተኛ ማርክ መስጫ ወቅት ይጠናቀቃል

ማርች 27 የመምህራን የባለሙያ ቀን ለተማሪዎች ትምህርት የለም

ኤፕረል 3 በአል—ስቅለተ አርብ ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ይሆናሉ

ኤፕረል 6 በአል—ፋሲካ ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ኤፕረል 7–10 የስፕሪንግ እረፍት ለተማሪዎችና መምህራን ትምህርት የለም

ኤፕረል 14 ሪፓርት ካርድ የሚሰራጭበት

ሜይ 25 በአል—Memorial Day (ያርበኞች ቀን) ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጁን 12 ለተማሪዎች የመጨረሻ የትምህርት ቀን ተማሪዎች ከምሳ በኋላ ይሰናበታሉ

ጁን 15 የመምህራን የባለሙያ ቀን

ጁን 23 የአመቱ አጠቃላይ ሪፓርት ካርድ የሚላክበት

የትም/ቤት መጠባበቂያ ቀን መቁጠርያ፣ 2014–2015በአስቸኳይ ሁኔታ ምክንያት የትምህርት አመት ቢስተጓጎልና ትም/ቤቶች ቢዘጉ፣ የትምህርት አመቱ እንዲራዘም ይደረጋል።ትም/ቤቶች ... ቢዘጉ የትምህርት አመቱ በ... ይራዘማል5 ቀኖች 1 ቀን በጁን 15 20156 ቀኖች 2 ቀን ጁን 15 እና 16 20157 ቀኖች 3 ቀኖች ጁን 15፣ 16፣ እና 17 20158 ቀኖች 4 ቀኖች ጁን 15፣ 16፣ 17፣ እና 18 20159 ቀኖች 5 ቀኖች ጁን 15፣ 16፣ 17፣ 18፣ እና 19 2015

Page 5: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 e

የ ተ ማ ሪ ዎ ች መ ገ ልገ ያ ዎ ች

ከMCPS ጋር ምንግዜም ይገናኙ www.montgomeryschoolsmd.orgለስርአት አቀፍ መረጃና የአስቸኳይ ሁኔታ ማስታወቂያዎች፡-

• MCPS በTwitter: www.twitter.com/mcps• MCPS በስፓኒሽም: www.twitter.com/mcpsespanol• የMCPS ማስጠንቀቅያ: www.montgomeryschoolsmd.org/alertMCPS• የQuickNotes ኢሜይል መልእክቶችና የዜና መግለጫዎች፡- www.mcpsQuickNotes.org• የMCPSን Information Service (የመረጃ አገልግሎት) ይጠይቁ

−ስልክ፡ 301-309-MCPS (6277) −ኢሜይል፡ [email protected]

• የMCPS ቴሌቪዥን (www.mcpsITV.org፤ Comcast 33 እና 34, RCN 89, Verizon 36)• የተቀረፀ የአስቸኳይ ሁኔታና የአየር ሁኔታ መረጃ:- 301-279-3673

የMontgomery County የወጣት ችግር ሁኔታ መገናኛ (Youth Crisis Hotline of Montgomery County) . . . . . . . . . 301-738-9697

Montgomery County Crisis Center(የMontgomery County የቀውስ ሁኔታ ማእከል) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .የቀውስ/ችግር ማእከል 240-777-4000

አጣቃላይ የአስቸኳይ ሁኔታ መገናኛ 301-738-2255የደህንነትና የፀጥታ አስጊ ሁኔታ ለማስታወቅ

MCPS Safe Schools 24-Hour Hotline (የMCPS ትም/ቤቶች ደህንነት የ24 ስአት አስቸኳይ መገናኛ) . . . . . . . . . . . . 301-517-5995የMCPS የደህንነትና የፀጥታ መምርያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 301-279-3066Montgomery County Police Department Family Crimes Division (የፖሊስ መምርያ የቤተሰብ ወንጀል ክፍል) . . . . 240-777-5400Montgomery County Police Nonemergency (አስቸኳይ ያልሆነ ፖሊስ) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 301-279-8000Montgomery County ፖሊስ:- አደንዛዥ እፅና የወንብድና ጥቆማ አስቸኳይ መገናኛ . . . . . . . . . . . . . . . . . . 240-773-TIPS (8477)የMontgomery County የጤናና የህዝብ አገልግሎቶች መረጃ መስመር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 240-777-1245The Cyber Tipline (የኮምፒውተር መጠቆሚያ) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .1-800-843-5678

በት/ቤት ውስጥ በኮምፒውተር ተገቢ ያልሆነ ተግባር በዚህ አስታውቁ [email protected]

ጠቃሚ መጣቀሻዎችCountywide Student Government (ካውንቲ አቀፍ የተማሪ አስተዳደር)(www.montgomeryschoolsmd.org/departments/studentaffairs)

• የተማሪ ጉዳዮች አስተባባሪ (Coordinator of Student Affairs) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-444-8620ተማሪ የቦርድ አባል (www.montgomeryschoolsmd.org/boe/members/student.aspx)

• የትምህርት ቦርድ ፅ/ቤት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-3617የ2ኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ተባባሪ የበላይ ተቆጣጣሪ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-315-7379የመካከለኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ተባባሪ የበላይ ተቆጣጣሪ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-315-7370የኤሌሜንታሪ ትም/ቤቶች ተባባሪ የበላይ ተቆጣጣሪ . . . . . . . . . . . . . 301-315-7362, 301-315-7374, 301-315-7364 እና 301-315-7360የማህበረሰብ ተሳትፎና ሽርከና ፅ/ቤትOffice of Community Engagement and Partnerships . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-3074የቤት ስራ ቀጥተኛ/አስቸኳይ ስልክ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 301-279-3234 ወይም በቴክስት 724-427-5445Section 504 Compliance Officer (የሰክሽን 504 ተቆጣጣሪ መኮንን) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-315-7335የህዝብ ግንኙነት ተቆጣጣሪ መኮንን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-3126ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ለሆነ እንቅስቃሴ ክፍያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-517-5000

የMCPS የድረገፅ መገልገያዎችWeb address: www.montgomeryschoolsmd.org• ይፈልጉ:

• የMCPS የት/ቤት ማውጫ• የMCPS የሰራተኞች ማውጫ• College and Career Information (የኮለጅና የስራ መረጃ) • CyberSafety• Course Bulletin (የት/ቤት የኮርስ መፅሄት)• የዲፕሎማ መስፈርቶች• የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግምገማዎች• የቤት ስራ ቀጥታ መስመር Live (ህያው)• ማርክ አሰጣጥና ዘገባ• መመርያዎችና ደንቦች• ልዩ ፕሮግራሞች• ስልታዊ የፕላን መዋቅር• የተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች• የተማሪ አገልግሎት ትምህርት• የበላይ ተቆጣጣሪው የአመራር ፕሮግራም

Page 6: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች
Page 7: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

የ ተማ ሪ መብቶች ና ሃ ላ ፊ ነ ቶች መመር ያ 2 0 1 4 – 2 0 1 5 i

ማ ው ጫ

መግቢያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

ነፃ ህዝባዊ ትምህርት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

የተማሪ ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

የብቸኝነት/የግል ጉዳይ መብት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

ክትትል (በክፍል ውስጥ የተገኙና ያልተገኙ መቆጣጠሪያ) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

ተፈቅዶላቸው የቀሩ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

ያለፈቃድ የቀሩ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

በቀሪነት ወቅት ያመለጡ ስራዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

ክብሮች፣ ከፍተኛ-ደረጃ፣ የክፍል ማዝለል (AP) ኮርሶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

ማርክ አሰጣጥና ዘገባ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የተማሪዎች አስተዳደር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የመምህራን ድጋፍ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የተማሪዎች አስተዳደር ስልጣን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የመጠየቅና የመናገር መብት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ንግግር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ስሞታዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ቴክኖሎጂ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

ህትመቶችና የህትመት ውጤቶች - የታተመና ያልታተመ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

ት/ቤት የሚደግፋቸው ህትመቶችና ምርቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

ት/ቤት ያልደገፋቸው ተለጣፊ ማስታወቂያዎች፣ በራሪዎች፣ እና ተመሳሳይ ቁሳቁሶች . . . . . . . . . . . 4

የተከለከሉ ነገሮች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

ፖሊቲካ ነክ ነገር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

በፖሊቲካ ዘመቻ ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

የመሰብሰብ ነፃነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

ያገርወዳድነት እንቅስቃሴዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

የሃይማኖት ነፃነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

ክበቦች፣ ቡድኖች፣ እና የተማሪ ድርጅቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

ትም/ቤት የሚደግፋቸው ድርጅቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

የትም/ቤት ድጋፍ የሌላቸው የተማሪ ድርጅቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

አድልዎ-የለሽ/ከአድልዎ ነፃ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

ልብስና አለባበስ/የግል እንክብካቤ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

ፆታዊ ወከባ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

የተማሪ ዘገባዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7

ፈልጎ መያዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7

የትም/ቤት ደህንነትና ፀጥታ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7

ተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8

ዲሲፕሊን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8

ይግባኝ-የቅሬታ ቅደም ተከተል—ህጋዊ ሂደት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8

በትም/ቤት ደረጃ ውሳኔ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8

በርእሰ መምህሩ/ሯ ውሳኔ ይግባኝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8

በትም/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ ውሳኔ ላይ ይግባኝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8

ተጨማሪ/አባሪ—MCPS Regulations (ደንቦች) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9–11

የቃላት ፍቺ ዝርዝር እና ማስታወሻዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .12

Page 8: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች
Page 9: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 1

መ ግ ቢ ያ

ይህች መለስተኛ መፅሃፍ ተማሪዎች በMontgomery County Public Schools (MCPS) ለየሚያገኟቸው መብቶችና ሃላፊነቶች መመርያ ናት። ይህች መለስተኛ መፅሃፍ ተምሪዎችን የሚመለከቱ ህጎችና ደንቦች ባጭሩ የምታጠቃልል ናት። በማንኛውም የተወሰነ ሁኔታ የተማሪ መብቶች ወሳኝና ዘላቂ መግለጫ አይደለችም። ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ በየክፍሉ መጨረሻ የተጣቀሱትን የተወሰኑ ህጎች፣ መመርያዎች፣ እና ደንቦች ያንብቡ። የትምህርት ቦርድ (የቦርዱ) መመርያዎችና የMCPS ደንቦች በwww.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy ይገኛሉ በተጨማሪ፣ የያንዳንዱ ት/ቤት የሚድያ ማእከልና የት/ቤቶች አስተዳዳሪዎች የነዚህ ሰነዶች ቅጅዎች ይኖሯቸዋል።

የስቴት ህጎች፣ የሜሪላንድ ትምህርት ቦርድ ውስጠ-ደንቦች፣ እና የMontgomery County የት/ቦርድ መመርያዎችና የMCPS የአስተዳደር ደንቦች በማንኛውም ወቅት መለወጥ ይችላሉ እናም በዚህ ህትመት በሚገኙ መግልጫዎችና መጣቀሻዎች የበላይነት አላቸው።

¡ ነፃ ህዝባዊ ትምህርትበMontgomery County የሚኖሩ እድሜአቸው 5 አመትና ከዚያም በላይ የሆነ እናም ከ21 አመት በታች የሆኑ በህዝብ ትም/ቤቶች ያለ ክፍያ የመማር መብት አላቸው።

በMontgomery County የሚኖሩ አካለ ስንኩላን ከተወለዱበት እለት ተማሪው/ዋ 21 አመት በሚሞላው/ት ወቅት የነበረ(ች)በት የትምህርት አመት እስከሚያልቅ ድረስ ተገቢ ትምህርት በነፃ የማግኘት መብት አለው/አላት።

¡ የተማሪ ተሳትፎስለያንዳንዱ ኮርስ አጠቃላይ አለማዎችና አፈፃጸማቸውም ስለሚገመገምበት መስረት ተማሪዎች መረጃ ይሰጣቸዋል። ተማሪዎች በትምህርት ክፍል እንቅስቃሴዎች የመሳተፍና በትም/ክፍል ደንቦች፣ ግዴታዎች፣ እና ያፈፃጸም ሂደቶች የመገዛት ሃላፊነት አለባቸው።

በትምህርት ቀን ለመደበኛ ፕሮግራም ተለዋጭ ወይም ተጨማሪ እና/ወይም ከትምህርት ቀን ውጭ ለፈቃደኛ ተማሪዎች ጥቅም እንዲውሉ ለማድረግ፣ ከመምህራን ጋር በመመካከር፣ ተማሪዎች ሰሚናሮች፣ ስብሰባዎች፣ ወይም በተመረጡ ርእሶች አጫጭር ኮርሶች እንዲከናወኑ ሃሳብ ማቅረብ ይችላሉ።

ተማሪዎች ከርእሰ መምህራን እና ከአስተዳደር አባላት ጋር ፕሮግራሞችን ፕላን በማድረግ ተባብረው ይሰራሉ። ፕሮግራሞች ከቦርዱ ስልታዊ የፕላን መዋቅርና ከት/ቤቶች መስረታዊ የትምህርት ተልእኮ ጋር የተሳሰሩ፣ ለአድማጮች እድሜና ብስለት የተመጣጠኑ፣ እና በአዋዛጋቢ ርእሶች አቀራረብ ሚዛን የጠበቁ ሆነው መገንባት አለባቸው።

የተማሪ ወኪሎች ተማሪዎችን በሚመለከቱ አበይት የቦርድ መመርያዎች ክለሳ ወይም ማዳበር ላይ መሳተፍ አለባቸው። ይህ አይነቱ ተሳትፎ ሀላፊነት በሚሰማው ፅ/ቤት፣ መምርያ፣ ወይም ኮሚቴ (በስብሰባዎች የተማሪ ወኪሎችን የሚያካትት) ወይም በማዳበር ወይም በክለሳ ሂደት ባሉት በርካታ ደረጃዎች ባንዱ የተማሪ አስተዋፅኦ በመጋበዝ ሊከናወን ይችላል። በአካባቢ ት/ቤት ተማሪዎችን በሚመለከቱ መመርያዎችና ደንቦች የክለሳ ወይም የመዳበር ተግባሮች ተማሪዎች ተመሳሳይ የመሳተፍ መብት አላቸው። ተማሪዎችን የሚመለከቱ አበይት የአካባቢ ት/ቤት መመርያዎች ወይም ደንቦች ከመዳበር ወይም ከመከለሳቸው በፊት ለተማሪ ትችት ቅጅዎች፣ ለተማሪ አስተያየት በቂ ግዜ በመስጠት፣ ለተማሪዎች አመች በሆኑ ቦታዎች ይለጠፋሉ።

በስቴት ደረጃ ተፈላጊ የሆኑት የComprehensive Health Education Curriculum (አጠቃላይ የጤና ትምህርት ስርአተ ትምህርት) የቤተሰብ ኑሮና የሰው ፆታዊነትና የህመም መካላከልና መቆጣጠር ህዋሶች ውስጥ ተማሪው እንዳይሳተፍ የተማሪው ወላጆች/ሞግዚቶች ከጠየቁ፣ ለተማሪው ተለዋጭ እንቅስቃሴዎች ይቀርቡለታል።

መጣቀሻዎች:- Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)COMAR 13A.04.18.04 Program in Comprehensive Health

Education (አጠቃላይ የጤና ትምህርት ፕሮግራም)

¡ የብቸኝነት/የግል ጉዳይ መብትየተማሪ የብቸኝነት/የግል ጉዳይ በት/ቤት አስተዳደር አባላት ይከበራል።

የተማሪውን ትኩረት ወደ ተማሪው ማርኮች፣ ሃማኖት፣ የግል መርሆዎች፣ ወይም አካላዊ ሁኔታው ላይ በመሳብ እንቅስቃሴው የተማሪውን የብቸኝነት/የግል ጉዳይ መብት የሚጥስ መሆኑ ወላጁ/ሞግዚቱ ወይም ተማሪው ካመነበት ተማሪዎች ወይም ወላጆቻቸው/ሞግዚቶቻቸው አስተማሪው ለእንቅስቃሴው ተለዋጭ እንዲያቀርብ የመጠየቅ መብት አላቸው።

ስለ ቤተሰብ ክውነቶች ወይም የግል ልምዶች፣ ዝምድናዎች፣ ምርጫዎች፣ ባህርዮች፣ ውሳኔዎች፣ ወይም ችግሮች፣ ወይም ራሳቸውን ወይም ቤተሰቦቻቸውን ከሌሎች ጋር ሳያወዳድሩ፣ ተማሪዎች በትምህርት ክፍል ውይይት፣ በስራ ትእዛዞች፣ ወይም በሌላ መንገድ የትምህርት አላማዎቻቸውን የማሟላት መብት አላቸው።

ተማሪዎች የተለጠፈ ማስታወቂያ ባላቸው በህዝባዊ ስፍራዎች በድምፃዊና በቪድዮ ካሜራ ክትትል/ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይችላል፣ ስለሆነም ማንኛውም ተማሪ በእንደዚህ አይነቱ ድምፃዊ ወይም የቪድዎ ክትትል/ቁጥጥር በተገኘ ማስረጃ መሰረት የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል። በነዚህ ሁኔታዎች ተማሪዎች የብቸኝነት/የግል ጉዳይ ይከበራል ብለው መጠበቅ የለባቸውም።

መጣቀሻዎች: Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)

¡ ክትትል (በክፍል ውስጥ ተማሪው/ዋ መገኘቱ/ትዋን መቆጣጠሪያ)

በየቀኑ መከታተል ለተማሪው ስኬት እና በትምህርት መካንንም ለማስመስከርና በኮርሶች ክሬዲት ለመቀበል ወሳኝ ነው። ተማሪዎች ትም/ቤት እንዲከታተሉ እና ወደ ትም/ቤትና የመማርያ ክፍሎች በወቅቱ እንዲደርሱ ይጠበቅባቸዋል።

ተፈቅዶላቸው ካልሆነ በስተቀር፣ በትምህርት ቀን ተማሪዎች ወደ መማርያ ክፍሎችና ወደ ተፈላጊ እንቅስቃሴዎች መሄድ አለባቸው። የትምህርት ክትትል በተማሪው/ዋ ሪፖርት ካርድ አማካኝነት ለወላጆች/ሞግዚቶች ይገለፃል። አንድ ተማሪ በትምህርት ቀን አራት ሰአት ወይም ከዚያ በላይ ከተገኘ/ች ሙሉ ቀን እንደተገኘ/ች ይቆጠርለ(ላ)ታል። አንድ ተማሪ በትምህርት ቀን ቢያንስ ለሁለት ሰአት፣ ግን ከአራት ሰአት በታች ከተገኘ/ች ግማሽ ቀን እንደተገኘ/ች ይቆጠርለ(ላ)ታል።

እንዳንድ ያካባቢ ትም/ቤት ስራ ሂደት፣ አንድ ተማሪ ከትም/ቤት ቀሪ ከሆነ/ች፣ ትም/ቤት ቀሪው(ዋ)ን በተመለከተ ክትትል ያደርጋል።

ፈቃድ ያላቸው መቅረቶችበሚከተሉት ምክንያቶች ብቻ ተማሪዎች ከትም/ቤት መቅረት ይችላሉ፡-

• የቅርብ ዘመድ ከሞተ• ህመም (ህመሙ ስር የሰደደ ወይም ከመጠን በላይ መቅረት የሚያስከትል

ከሆነ ርእሰ መምህሩ/ሯ ከወላጁ/ሞግዚቱ የህኪም ወረቀት ሊጠይቅ/ልትጠይቅ ይችላል/ትችላለች።)

• የፍርድ ቤት መጥሪያ• የሃይማኖት በአል• የስቴት አስቸኳይ ሁኔታ• መታገድ• አደገኛ የአየር ሁኔታ (ተማሪው/ዋ ከቤት ወደ ት/ቤት ለመመላለስ የአየር

ሁኔታ የሚያሰጋ ከሆነ)

Page 10: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

2 2 0 1 4 – 2 0 1 5 A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች )

• መደበኛ ትራንስፖርት ሲጠፋ (ለምሳሌ፣ አውቶቡሱ ካልመጣ)• የርእሰ መምህር ፈቃድ

ከነዚህ ምክንያቶች ባንዱ ተማሪው/ዋ ከት/ቤት ከቀረ/ች፣ ተማሪው/ዋ ከወላጁ/ጇ/ሞግዚቱ/ቷ ት/ቤት ከተመለሰ/ች በሶስት ቀን ውስጥ ማስታወሻ ማምጣት ይገባዋል/ይገባታል። ለምሳሌ፣ አንድ ተማሪ ሮብና ሃሙስ ከት/ቤት ቢቀር/ብትቀር እና አርብ ቢመለስ/ብትመለስ፣ ስለመቅረቱ/ቷ የሚያብራራ ማስታወሻ በሚቀጥለው ማክሰኞ ገቢ ማድረግ አለበ(ባ)ት። አለዝያ፣ መቅረቱ ያልተፈቀደ ተብሎ ይታሰባል። ተማሪው/ዋ ከ18 አመት ወይም ከዚያ በላይ ወይም ባለትዳር ከሆነ/ች፣ ተማሪው/ዋ የእድሜ ሙላት መጠይቅ ከሞላ/ች በኋላ የራሱ/ሷ/ን ማስታወሻ መፃፍ ይችላል/ትችላለች። አንድ ተማሪ የእድሜ ሙላት መብቱ(ቷ)ን እያስከበረ/ች እንደጥገኛ ልጅ ከወላጆቹ/ቿ/ሞግዚቶቹ/ቿ የሚኖር/የምትኖር ከሆነ፣ ተጨማሪ የቀሪ ማስታወቂያዎች ለወላጆች/ሞግዚቶች ሊላክ ይችላል።

ወላጁ/ጇ/ሞግዚቱ/ቷ (ወይም ተማሪው/ዋ የእድሜ ሙላት ከደረሰ/ች) ከአምስት ቀኖች በፊት ካመለከቱ/ተ/ች ርእሰ መምህሩ/ሯ ተማሪው/ዋ ለሌላ ስራ ወይም እንቅስቃሴ ከት/ቤት እንዲቀር/እንድትቀር መፍቀድ ይችላል/ትችላለች። ከሚከተሉት እንዱን ለማከናወን ተማሪው/ዋ ከት/ቤት ከቀረ/ች ርእሰ መምህሩ/ሯ ብዙውን ግዜ ይቅርታ ማድረግ/መፍቀድ ይችላል/ትችላለች፡-

• የኮሌጅ ግቢ ለመጎብኘት• በኮሌጅ የመተዋወቅያ ፕሮግራም ለመሳተፍ• ስራ ለመቀጠር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ• የተፈቀደ የጋራ ትምህርት ፕሮግራም አካል የሆነ ስራ • በግዚያዊ፣ በቋሚ ስራ ለመሳተፍ

የቤተሰብ እረፍቶች በአብዛኛው አይፈቀዱም። ከተለመደው ውጭ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ግን፣ ርእሰ መምህሩ/ሯ መቅረቱን ይቅርታ ማድረግ ይችላል/ትችላለች።

ፈቃድ የሌላቸው ቀሪዎችከላይ ከተጥቀሱት ውጭ የተፈፀመ መቅረት ፈቃድ የሌለው ቀሪ ነው። አንድ ተማሪ የትምህርት ቀን ካመለጠው/ጣት እና ፈቃድ ከሌለው/ላት፣ ተማሪው/ዋ በያንዳንዱ ባመለጠው/ጣት የትምህርት ክፍል ያልተፈቀደ ቀሪ ይኖረዋል/ይኖራታል። አምስት ህጋዊ ያልሆነ ቀሪ ያስመዘገቡ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የቀሪዎቻቸውን ምዝገባ ይግባኝ ወድያውኑ እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል፣ እነሱ ወይም ወላጆቻችደው/አሳዳጊውቻቸው ቀሪው ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል እምነት ካላቸው፣ እና/ወይም ከአማካሪዎቻቸድው/አስተዳዳሪዎቻቸው ጋር በመሆን የክትትል ጣልቃ ገብነት ፕላን ማዘጋጀት። የይግባኝ እና/ወይም የክትትል ጣልቃ ገብነት ፕላን በተማሪው፣ በወላጅ/አሳዳጊ፣ ወይ በአማካሪ/አስተዳዳሪ ቡድን ሊቀሰቀስ ይችላል። ተማሪው የክትትል አቤቱታ ዘገባ ወይም የክትትል ጣልቃ ገብነት ፕላን ካላጠናቀቀ እና/ወይም ከህግ ውጭ መቅረት ከቀፀለ፣ ተማሪው በያዘው ኮርስ የመውደቅ ውጤት የማግኘት አደጋ ላይ እንደሚገኝ ይታሰባል።

የቀሩበት ህጋዊ ይዘት የፈለገውን ይሁን ያመለጣቸውን ስራ ለማስተካከል መጣር ለተማሪዎች እጅጉን አስፈላጊ ነው። ተማሪዎች ከቀሩበት ሲመለሱ መምህራን ተመጣጣኝ፣ ግን የተለየ ስራ ወይም ተግባር ሊሰጧቸው ይችላሉ። ከህግ ውጭ ስለተከናወኑ ቀሪዎች፣ ርእሰ መምህሩና የአመራሩ ቡድን ባፀደቁት ሂደት መሰረት፣ አስተማሪዎች ለጎደሉት ስራዎች ወይም ግምገማዎች እውቅና መንሳት ይችላሉ።

ተማሪው/ዋ ያለፈቃድ በቀረ(ች)በት ቀን ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች የመካፈል እድል ርእሰ መምህሩ/ሯ መንሳት ይችላል/ትችላለች። እያንዳንዱ ት/ቤት በየቀኑ የመከታተል ልምድ ለማበራታት፣ ክትትልን ለመቆጣጠር፣ እርምጃዎችንም ለመውሰድ የሚያስችል የስራ ቅደም ተከተል ያቋቁማል።

በቀሪ ወቅት ያመለጠ ስራየቀሩበት ሁኔታ ህጋዊነት የፈለገውን ይሁን፣ ተማሪዎች ያመለጣቸውን ስራ የማካካስ ህላፊነት አላቸው። ቀሪነቱ በፈቃድ ከሆነ ወይም የመታገድ ውጤት ከሆነ ያመለጠውን ስራ መምህሩ/ሯ በማካካስ ረገድ ያግዛል/ታግዛለች። ቀሪነቱ ያልተፈቀደ ከሆነ፣ አስተማሪው/ቷ ተማሪውን ያመለጠውን በማካካስ በኩል ማገዝ፣ ፈተና መስጠት፣ ወይም ወቅቱ ለደረሰ ስራ የግዜ ማራዘምያ መስጠት የለበ(ባ)ትም። ምንም እንኳን አስተማሪው/ዋ ተማሪው ላመለጠው ማካካሻ በሚያደርገው ማገዝ ባይኖርበ(ባ)ትም፣ ቀሪውን ኮርስ ማሟላት ይችል ዘንድ ተማሪው ስራውን ማካካስ ይኖርበታል።

መጣቀሻዎች፡- Regulation IKA-RA: Grading and Reporting (ማርክ አሰጣጥና ዘገባ)Regulation IOA-RA: Gifted and Talented Education (ተስጥኦና የላቀ

ችሎታ ላለው/ላላት ትምህርት) Regulation IQB-RA: Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምህርት

ውጭ እንቅስቃሴዎች)Regulation JEA-RA: Student Attendance (የተማሪ ክትትል)Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)Maryland Student Records System Manual (የሜሪላንድ የተማሪ

ዘጋባዎች/ሰነዶች ስርአት መመርያ)MCPS High School Course Bulletin (የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የኮርስ መፅሄት)

ክብሮች (Honors)፣ ከፍተኛ ደረጃ፣ እና የክፍል መዝለል (AP) ኮርሶችርእሰ መምህራን የHonors፣ AP፣ እና የከፍተኛ ደረጃ ኮርሶች ፈተና ለመቀበል ችሎታ፣ ተነሳሽነት፣ ወይም እምቅ ችሎታ ያለቸው ተማሪዎች በሞላ ይህን ለማከናወን እድሉ ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ። እያንዳንዱ ት/ቤት ጥብቅ ፕሮግራምና ከፍተኛ ደረጃ የኮርስ ስራ ለመከታተል ችሎታ ወይም ተነሳሽነት ላለው ለያንዳንዱ ተማሪ ለHonors፣ AP፣ እና የከፍተኛ ደረጃ ኮርሶች ክፍት ምዝገባ ያቀርባል። ያላቸው መሆኑን ተማሪ ጥንካሬ ገፅታ በሚከተሉት በርካታ መስፈሮች አማካይነት ጥብቅ ግምገማ በማድረግ ማወቅ ይቻላል፡-

• ኮርስ ለመውሰድ የቅድሚያ መስፈርቶች የዕውቀት ደረጃ (A፣ B፣ ወይም C ማርኮች)

• የወላጅ/ሞግዚት ማሳሰብያዎች• መደበኛ የፈተና ውጤቶች፣ እንደአግባቡ• ፈታኝ ስራዎችን ለመፈፀም ፈቃደኛነት• የተማሪ ፍላጎት ወይም ተነሳሽነት• የመምህር/አማካሪ ማሳሰቢያዎች• የስራ ናሙናዎችና የተማሪ ሰነዶች

ማርክ አሰጣጥና ዘገባየማርክ አሰጣጥና ዘገባ ትግባሬዎች ፍትሃዊ፣ ትርጉም ያላቸው፣ እና ለሁሉም ተማሪዎች ጥብቅ የአፈፃፀም መመዘኛዎች ደጋፊ ይሆናሉ። ማርኮች በመላ የት/ቤት ስርአት ውስጥ ፅኑ ትርጉም ይኖራቸዋል፣ በስርአተ ትምህርቱ እንደተመለከተውም በክፍል ደረጃና በኮርስ በሚጠበቁት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የቦርድ መመርያ IKA ይመልከቱ: ማርክ አሰጣጥና ዘገባ፣ በ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy።

ከ1ኛ-5ኛ ክፍሎች፣ ማርኮች ከክፍል ደረጃ መመዘኛዎች አንፃር የአካዴሚ ግኝትን ያንፀባርቃሉ። እውቀታቸውን፣ ሂሳዊና የፈጠራ አስተሳሰብ ችሎታዎቻቸውን፣ እና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎቻቸውን በቃል፣ በፅሁፍ፣ እና በትርእይቶችና በምርቶች ለማሳየት እንዲችሉ በርካታና የተለያዩ እድሎች ለተማሪዎች በመስጠት አስተማሪዎች ግንዛቤን ይቆጣጣራሉ።

ከ6ኛ-12ኛ ክፍል፣ ማርኮች ከክፍል ደረጃ መመዘኛዎች አንፃር የአካዴሚ ግኝትን ያንፀባርቃሉ። በመካከለኛ ም/ቤቶችና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ6ኛ-12ኛ ክፍሎች፣ ለማርክ አሰጣጥ፣ ዳገመ-ማስተማር/ዳገመ-ግምገማ፣ እና ለቤት ስራ፣ አስተማሪዎች የMCPS “Procedures” (የስራ ሂደቶች) ተግባራዊ ያደርጋሉ።

አስተማሪዎች ለስራ ወይም ለግምገማ የሚሰጡት ማርክ ከ50 በመቶ ያላነሰ ነው። ተማሪው የስራዎች/ተግባሮች መሰረታዊ መስፈርቶች አለማሟላት ወይም ተማሪው በአካዴሚያዊ ወራዳነት ተጠምዷል ብሎ አስተማሪው ካመነበት አስተማሪው ዜሮ መስጠት ይችላል።

አስተማሪዎች ማስረከቢያ ወቅትና የግዜ ገደብ ይወስናሉ። አስተማሪዎች ማስረከቢያ ወቅትንና የግዜ ገደብን እንዲለዩ ይጠበቅባቸዋል፤ ቢሆንም፣ ማስረከቢያ ወቅትና የግዜ ገደብ እንድ ላይ የሚወድቁበት ወቅት ሊኖር ይችላል። ከማስረከብያ ወቅት በኋላና በግዜ ገደብ (deadline) የቀረበ ስራ ከማርኩ አንድ ደረጃ ወይም ከማርኩ 10 በመቶ በላይ ላይቀነስ ይችላል። ከግዜ ገደብ በኋላ ገቢ የተደረገ ስራ ዜሮ ተብሎ ይመዘገባል።

መምህራን ተጨምሪ እውቅና (credit) አይሸልሙም።

እነዚህ ሂደቶች ለወላጆች/ሞግዚቶች እና ተማሪዎች በMCPS ድረገፅ www.montgomeryschoolsmd.org/info/grading፣ እና በት/ቤቶች ፅ/ቤቶች ይገኛሉ።

Page 11: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 3

¡ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (Student Service Learning (SSL))

ለሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምርያ ዲፕሎማ ለማግኘት የሚሰሩ ተማሪዎች ሁሉ ለምረቃ የሚያስፈልጉትን ክሬዲት፣ ኮርሶች፣ እና ከብቃቶች በተጨማሪ የአገልግሎት ትምህርት ሰአቶች መፈፀም አለባቸው። የአገልግሎት-ትምህርት ሰአቶች ከ5ኛ ክፍል መጨረሻ በኋላ ካለው የሰመር ወራት ጀምሮ መጠራቀም ይችላሉ። ተማሪዎች ከምረቃ በፊት 75 የአገልግሎት-ትምህርት ሰአቶች መፈፀም አለባቸው። የMCPS SSL(የተማሪ እገልግሎት-ትምህርት) ፕላን ዝርዝሮች በwww.mcpsssl.org ወይም በማንኛውም የመካከለኛ ወይም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የSSL አስተባባሪ በመገናኘት ሊገኙ ይችላሉ።

መጣቀሻዎች፡- Annotated Code of Maryland, Education, Sections 13A.03.02.07MCPS Student Service Learning Coordinator (የSSL አስተባባሪ)፡

301-279-3454

¡ የተማሪዎች አስተዳደርተሳትፎተማሪዎች የተማሪዎች አስተዳደር ድርጅት የማቋቋምና የመሳተፍ መብት አላቸው። ተማሪዎች በተማሪ አስተዳደር ድርጅት አማካኝነት በት/ቤት ጉዳዮች ድምፃቸውን የማሰማት መብት አላቸው። ተማሪዎች ተጠያቂነቱ ለተማሪዎች የሆነ ውጤታማ የተማሪ አስተዳደር ድርጅት ለመፍጠር የመስራት ሃላፊነት አለባቸው። በህጋዊ መንገድ ት/ቤት የተመዘገበ፣ በአኣካዴሚ ብቁ፣ እና የት/ቤቱ መተዳደርያ ደንብ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተማሪ በተማሪዎች አስተዳደር ለሚገኝ ቦታ መወዳደርና ቦታውን መያዝ ይችላል። ተመሪዎች ያስተዳደር ቦታ ይዘው ለመቀጠል በአካዴሚም ብቁ ሆነው መቀጠል አለባቸው። ይህም ማለት የምርጫ ቦታ ለመያዝ ተማሪው ምንግዜም 2.0 አማካኝ ውጤት እንዲኖረውና በሪፖርት ካርዱም ከአንድ የበለጠ የመውደቅ ማርክ እንዳይኖረው ያስፈልጋል። በተማሪዎች አስተዳደር መሳተፍ የአገልግሎት ትምህርት ሰአቶች ማግኘት ያስችላል።

የመምህራን ድጋፍየት/ቤት አስተዳደር አባላት የተማሪን በተማሪ አስተዳደር የመሳተፍ መብት ይደግፋሉ። የተማሪዎች አስተዳደር ተማሪዎች በት/ቤት ስራ አፈፃጸም ድምፅ የሚሰጣቸው መሆኑን ርእሰ መምህሩ/ሯ ዋስትና ይሰጣል/ትሰጣለች።

በስፕሪንግ ወራት፣ ስለሚመጣው አመት የአማካሪ ምደባ በሚመለከት የተማሪ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከርእሰ መምህሩ/ሯ ጋር ይገናኛል እናም አማካሪው ከመሰየሙ በፊት የተማሪዎች አስተዋፅኦ ጥንቁቅ ግንዛቤ ይሰጠዋል።

የት/ቤት አስተዳደር አባላት የተማሪ አስተዳደር አስፈላጊ አቅርቦቶችና የክፍል አገልግሎት እንዲያገኝ ያግዛሉ።

አስተዳደሩ ባፀደቀው የተማሪ አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ በማለት ከትምህርት ክፍል የቀሩ ተማሪዎች የተፈቃደ ቀሪነት ይሰጣቸዋል ያመለጧቸውን ስራዎች የማካካስ ሃላፊነትም ይኖራቸዋል።

የተማሪዎች አስተዳደር ስልጣኖችእንዳስፈላጊነቱ በት/ቤት ሰራተኛ/አማካሪ ከሚሰጥ ምክር ጋር፣ ተማሪዎች የተማሪዎች አስተዳደር መተዳደርያ ደንብ ፅሁፍ ወይም በስራ ለይ ያለውን የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያዎች የማዘጋጀት ሃላፊነት አለባቸው። ሁሉም የመተዳደርያ ደንቦች የርእሰመምህሩ(ሯ)ን የውሳኔ መስጠት ስልጣን የሚያውቅ አንቀፅ ማካተት አለባቸው። ህግ፣ መምርያ እስካልጣሰ፣ ወይም በርእሰ መምህሩ/ሯ አስተያየት፣ ከት/ቤቱ ስኬታማ ግብረት ጋር በሚመጠን ጣልቃ እስካልገባ ድረስ፣ የተማሪዎች አስተዳደር መተዳደርያ ደንቡን ወይም ማሻሻያዎቹን ርእሰ መምህሩ/ሯ እንዲያፀድቅ/እንድታፀድቅ የመጠበቅ መብት ተማሪዎች አላቸው። ያልፀደቀበት ምክንያቶች ለተማሪዎች በፅሁፍ ይገለፅላቸዋል የአስተዳደሩን ቅሬታዎች አስመልክተው የመተዳደርያ ደንቡን ለመከለስ እድል መሰጠትም አለባቸው።

ተማሪዎች፣ በተማሪዎች አስተዳደር አማክይነት፣ በተማሪ አስተዳደር ለሚቀርቡ ማሳሳቢያዎች በአምስት የትምህርት ቀኖች ውስጥ ከት/ቤቱ አስተዳደር መልስ የመቀበል መብት አላቸው። ማሳሰብያዎች ተቀባይነት ካላገኙ ወይም ከተለወጡ አስተዳደሩ፣ በጽሁፍም ሆነ በቃል፣ ምክንያቶች ይሰጣል። ማሳሰቢያዎቹ በርካታ ወይም ውስብስብ ከሆኑ፣ የት/ቤቱ አስተዳደር፣ ከተማሪዎች አስተዳደር ተወካዮች ጋር በመመካከር፣ የቃል ወይም የፅሁፍ መልስ የሚሰጥበትን ተቀባይነት ያለው ግዜ ይወስናል።

የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ፣ የተማሪዎች አስተዳደር አማካሪ፣ እና ርእሰ መምህሩ/ሯ በየወቅቱ እየተገናኙ ስለ ተማሪዎች አስተዳደር ድርጅት ግስጋሴና ቅሬታዎች ይመካከራሉ።

መጣቀሻዎች፡Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)Regulation IQD-RA: Academic Eligibility for High School

Students Who Participate in Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት)

Regulation IQD-RB: Academic Eligibility for Middle School Students Who Participate in Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት)

MCPS Student Affairs (የተማሪ ጉዳዮች): 301-444-8620 (www.montgomeryschoolsmd.org/departments/studentaffairs/ )

¡ የመጠየቅና የመናገር ነፃነትንግግርየስቴት ወይም የካውንቲ ስርአተ ትምህርት በሚያስገድዱት ገደብ የተከበረ ሆኖ፣ ተማሪዎች በአዋዛጋቢ ርእሶች ስለሚኖሩ የተለያዩ አስተያየቶች የመሰጠት መብት፣ እና አማራጭ አስተሳሰቦችን አመዛዝነው አስተሳሰባቸውን ለመቅረፅ ግላዊ አስተያየቶች የመግለፅ መብት አላቸው። ተማሪዎች የተለያዩ አስተሳሰቦች የማክበርና እያንዳንዱ ሰው የግል አስተያየት እንዲኖረውና የመግለፅም መብት እንዳለው የማወቅ ሃላፊነት አለባቸው። ተማሪዎች በኮርሶቻቸው የሚቀርቡ ርእሶችን በጥሞና የማገናዘብ ሃላፊነት አለባቸው፤ በውይይት ርእሶች የሚገለፁ የተለያዩ አስተያየቶችን ለማበልፀግ የራሳቸውን አስተያየቶች ለመጨመር መማርያ ክፍል በሚካሄዱ ውይይቶች የመሳተፍ ሀላፊነት አለባቸው። ከአወንታዊ ትምህርትና ከስራ አካባቢ የሚያስተጓጉል፣ እና የጋራ መከባበር መንፈስ ከማዳበር ግብ ጋር የማይጣጣም፣ መረንና ስድ ቋንቋ ከመጠቀም የመቆጠብ ሃላፊነትም አለባቸው፣

አቤቱታዎችተማሪዎች ከት/ቤት አስተዳዳሪዎች የመገናኘትና አለመግባባቶችን ማጣራትና በአቤቱታ መነሻ በሆኑ ርእሶች የመረጃ መለዋወጫ መድረክ የማቅረብ ሃላፊነት አለባቸው። የት/ቤት ግብረቶችን እስካልረበሹ ድረስ፣ ተማሪዎች አቤቱታዎችን ከትምህርት ግዜ ውጭ የማሰራጨት መብት አላቸው። አቤቱታዎቹ የተማሪዎች ወይም ሌሎች የት/ቤቱ ህብረተሰብ አባላት ጤንነት ወይም ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባሮች እንዳያበረታቱ እና ስም አጥፊ ወይም ባለጌ አለዚያም በት/ቤቱ ግብረቶች ከፍተኛ ቀውስ የሚያመጡ እንዳይሆኑ ተማሪዎች የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው። ይህን ሃላፊነት ለማሟላት ካልቻሉ የት/ቤቱ አስተዳደር የአቤቱታዎችን መሰራጨት ማቆም ይችላል። በት/ቤት ደረጃ፣ መልሱን በመለጠፍ ወይም አመንጭው የሚታወቅ ከሆነ ለአመንጭው በመላክ ተማሪዎች በአምስት ቀኖች ውስጥ መልስ የማግኘት መብት አላቸው

ቴክኖሎጂተማሪዎች ለትምህርት ጉዳዮች በMCPS በሚቀርበ ቴክኖሎጂ የመጠቀም መብት ያላቸው በMCPS Regulation IGT-RA፣ User Responsibilities for Computer Systems, Electronic Information, and Network Security በተገለፀው መሰረት ብቻ ነው። የኮምፒተር መሳርያ፣ የኮምፒውተር አገልግሎቶች፣ እና የድር መጋናኛዎች ወደ ት/ቤቶችና ፅ/ቤቶች የሚቀርቡት ከMCPS ተልእኮ ጋር ለፀኑ ጉዳዮች ብቻ ነው። ሁሉም እንቅስቃሴዎች/ተግባሮች MCPS ሊቆጣጣራቸው ይችላል ታይተውም ሊመዘገቡ (logged) ይችላሉ። ተማሪዎች መረጃዎችንና መገልገያዎችን ከስርቆሽ፣ ከተንኮለኛ አደጋ፣ ያልተፈቀደ ዳሰሳ፣ ጣልቃ ብልሽት እና ጥፋት መከላከል፣ እናም አግባብ ያላቸውን የስቴት፣ ያካባቢ፣ የፌደራል ህጎች ማክበር አለባቸው። ተማሪዎች የትም/ቤት ኮምፒውተሮች በሚጠቀሙበት የግል/የራስ ጉዳይ መብት የላቸውም ወይም እንዲኖርም መጠበቅ የላባቸውም። ተማሪዎች በMCPS Regulation IGT-RA ደንቦች እና ኤሌክትሮኒክ መገናኛዎችን በሚመለከት ሌሎች ህጎችና ገደቦች መሰረት ራሳቸውን እንዲጠብቁ/እንዲቆጣጠሩ ሀላፊነት አለባቸው።

Page 12: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

4 2 0 1 4 – 2 0 1 5 A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች )

የተከለከለ ፅሁፍ/ህትመትየፅሁፎች/ህትመቶች ስርጭት በርእሰ መምህሩ/ሯ በሚከተለው ሁኔታ ይከለክላል።

• ይዘቱ ህጎችን፣ የMontgomery County የትምህርት ቦርድ መመርያዎች፣ ወይም የMCPS ደንቦች ጥሷል።

• ይዘቱ በከፍተኛ ደረጃ የትም/ቤት እንቅስቃሴዎችን ሊረብሽ ወይም ረብሻ ሊያስከትላል ይችላል ተብሎ ይገመታል። "በከፍተኛ ደረጃ ረብሻ" ማለት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በት/ቤት ጣልቃ መግባት ወይም ከስነ ስርአት ውጭ የሆነ ተግባር ማስከተል ሲሆን፣ ይህም ረብሻ መቀስቀስን፣ ከትም/ቤት ባድማ መቅረትን፣ የቁጭ-በል አድማዎች፣ ንብረት ማጥፋት እና ጥሎ መውጣትን ያካተተ ነገር ግን በነዚያ ያልተወሰነ ነው።

• ይዘቱ፣ በሙሉም ይሁን በመጠነኛ ከፊል፣ በትርእይትም ይሁን በመግለጫ የተማሪዎችን ወይም የሰራተኞችን ጤንነትና ደህንነት አደጋ ላይ መጣልን የሚያደፋፍር ሲሆን ይህም ከህግ ውጭ ወይም ከመጠን በላይ አልኮል፣ አደንዛዥ እፅ ወይም ሌሎች አስካሪዎች መውሰድን፤ ሁከትን፤ በመጠጤ ዕድሜ ዉስጥ የሚፈፀም ግብረስጋን፤ ህገወጥ አድልዎን፤ ወይም ህገወጥ ተግባሮችን የሚያካትት ግን በነዚህ ያልተወሰነ ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህ መመርያ ሃላፊነት የተላበሱ ክርክሮች ወይም ውይይቶች የያዙ የመረጃ ቁሳቁሶች ህትመት ወይም ስርጭት አይከለክልም።

• ይዘቱ፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያሳይ ወይም የሚገልፅ እና በMCPS Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች) የተገለፁትን ሶስቱን የብልግና መስፈሮችን የሚያሟላ ከሆነ ብልግና ነው።

• ያልተፈቀደ፣ ሃሰተኛ፣ ወይም ተንኮለኛ ነገር በህትመት፣ በፅሁፍ፣ ምልክቶችንና ስእሎችን በመሳሰሉ ሌሎች ማቅረቢያዎች አንድን ግለሰብ ለህዝባዊ ንቀት፣ ጥላቻ፣ ወይም ፌዝ፣ ሆን ተብሎ ወይም በጀብደኝነት እና/ወይም በግድየለሽነት የተከናወነን የሚያካትት ይዘት ስም አጥፊ ይባላል። ይህ በMCPS Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች) በተጨማሪ ተገልፆአል።

ርእሰ መምህሩ/ሯ አንድን ተማሪ ህትመት ከማሰራጨት ካቆመ(ች)ው፣ ህትመቱንና ስርጭቱም ይፈቀድ እንደሆነ ለመወያየት ስብሰባ ይደረጋል። ርእሰ መምህሩ/ሯ በሁለት የትምህርት ቀኖች ውስጥ ለውሳኔው ምክንያቶች የሚገልጽ ውሳኔ ለተማሪው በፅሁፍ ይሰጠዋል/ትሰጠዋለች። በውሳኔው ላይ ይግባኝ ሊባል ይቻላል። የይግባኙ ቅደም ተከተል በዚች መለስተኛ መፅሀፍ ውስጥ (ገፅ 8) የይግባኝ-አቤቱታ አቀራረብ—ህጋዊ ሂደት (Appeals-Complaint Procedure—Due Process) ተገልጿል።

የፖሊቲካ ቁስማንም ሰው፣ ህገ መንግስታዊ ያልሆነ፣ ህገ ወጥ፣ የስቴት ምርጫ ህጎች የሚፃረር፣ ወይም፣ በርእሰ መምህሩ/ሯ አስተያየት/አስተሳሰብ፣ ለትምህርት አካባቢ የረብሻ አደጋ ያመጣል ተብሎ የተገመተ የምርጫ ዘመቻ ፅሁፍ/ህትመት ማሰራጨት አይችልም። የዘመቻ ቁሶች የፈቃድ መስመር ያስፈልጋቸዋል (MCPS Regulation KEA-RA: Participation in Political Campaigns and Distribution of Campaign Materials ይመልከቱ)። ይህ ውሳኔ ይግባኝ ሊባልበት ይቻላል። የይግባኙ ቅደም ተከተል በዚች መፅሀፍ (ገፅ 8) በይግባኝ-አቤቱታ አቀራረብ—ህጋዊ ሂደት (Appeals-Complaint Procedure—Due Process) ተገልጿል።

እነዚህን ደንቦች እስከተከተሉ ድረስ ሌላ የፖለቲካ ቁስ ማሰራጨት ይቻላል።• ለሁሉም ሰው ከመስጠት ይልቅ፣ ቁስን ፍላጎት ላላቸው ሰዎች አቅርብ።

ይህን ህግ ሳይጥሱ ስርጭት ማድረግ የሚያስችሉ ጥቂት መንገዶች እነዚህ ናቸው፡- ፍላጎት ላላቸው ብቻ ማሰራጨት፣ መግለጫ ቦታ ማዘጋጀት፣ ወይም ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ መለጠፍ።

• አንድ ተማሪ የፖለቲካ ቁሶችን የእግረኛ መንገዶች እና በካፊቴሪያ፣ የተመለከቱ የቤት ውስጥ መተላለፊያዎች፣ ወይም የተማሪ አስተዳደር ክፍሎችና ስፍራዎች ላይ ሆኖ ማሰራጨት ይችላል። ተማሪዎች በመማርያ ክፍሎች፣ በሚድያ ማእከል፣ ወይም በሌሎች የት/ቤት ክፍሎች በትምህርት ቀን የፖሊቲካ ቁሶችን ማሰራጨት አይችሉም፣ ከነዚህ በስተቀርa. ክፍሉ ለፈቃደኛ መሰብሰብያ ጥቅም የሚውል ከሆነ፣ ወይም b. ቁሱ እንደ መደበኛ የመማርያ ፕሮግራም ወይም የተማሪዎች የፈቃደኛ

መድረክ ወይም ሴሚናር አድርገው ካልያዙት በስተቀር።• የፖሊቲካ ቁስ ሁልግዜ ከትምህርት ግዜ ውጭ ብቻ አሰራጩ።

ህትመቶችና የህትመት ምርቶች—የታተመ እና ያልታተመአንድ ህትመት/ምርት ባንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ስፖንሶርድ ሆነ የሚባለው በአንድ ሰው ወይም ቡድን በገንዘብ ወይም በጉልበት ተደግፎ ምርቱን ሲያመርተው ነው። ት/ቤት ስፖንሶር ለሚያደርጋቸውም ሆነ ለማያደርጋቸው ህትመቶች/ምርቶች የተለያዩ ህጎች አሉ። የCablecast ጥያቄዎች የሚሸፈኑት በተለየ የMCPS Regulation IID-RA፣ Programs to be Cablecast on the MCPS Education Channels ነው።

ት/ቤት ስፖንሶር የሚያደርጋቸው ህትመቶችና የህትመት ምርቶችት/ቤት ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ህትመቶች፣ እንደ ጋዜጦች፣ አመታዊ መፃህፍት፣ እና የስነፅሁፍ መፅሄቶች እና ት/ቤት ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ምርቶች፣ በት/ቤት ውስጥ ለመገልገል የተነደፉ እንደ የት/ቤት ቲያትሮች እና የቴሌቪዥን ትእይንቶች እንዲበረታቱ ይደረጋል። እያንዳንዱ ህትመት/ምርት ባለሙያ አማካሪ ይኖረዋል። አማካሪያቸው እስካፀደቀው ድረስ፣ ተማሪዎች ት/ቤት ስፖንሶር ያደረጋቸው ህትመቶች ወይም ምርቶች ይዘት የመምረጥና የማዳበር መብት አላቸው። አማካሪው የሆነን ነገር ለህትመት ወይም ለምርት ውድቅ ቢያደርገው፣ ተማሪዎች ለርእሰ መምህሩ/ሯ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ።

ት/ቤት ስፖንሶር በሚያደርጋቸው ህትመቶች/ምርቶች የንግድ ማስታወቂያዎች እነዚህን ህጎች ይከተላሉ።

• ህዝባዊ እውቅና የሌላቸው ግለሰቦች ስሞች እና/ወይም ስእሎች የያዙ ማስታወቂያዎች ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል (ህዝባዊ እውቅና ያላቸው ግለሰቦች ዝነኛ አርቲስቶች፣ ስፖርተኞች ወዘተ... እና የመንግስት ሃላፊነት ቦታ የያዙ ናቸው)። የኩባንያ የንግድ ምልክት የያዝዙ ማስታወቅያዎችም ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል።

• ማስታወቂያ ከዜና ታሪክ ወይም ከህትመቱ ሌላ ክፍል ጋር የሚያደናግር ከሆነ፣ ማስታወቂያ የሚል መለያ ይደረግበታል።

• ማስታወቂያዎች ስፖንሶር በሚያደርጓቸው ሰዎች ወይም ኩባንያዎች ስም/ስሞች መቅረብ አለባቸው።

• ከተቻለ፣ ከማስታውቂያዎቹ በፊት ማስታወቂያው የአዘጋጁን፣ የት/ቤቱን፣ የMCPS፣ የትምህርት ቦርድን አስተያየት ወይም መመርያዎች እንደማያንፀባርቅ የሚገልፅ መግለጫ አስቀድሞ ይሰፍርበታል።

ት/ቤት ስፖንሶር ስለሚያደርጋቸው ህትመቶችና ምርቶች ተጨማሪ መረጃ፣ MCPS Regulation JFA-RA፣ Student Rights and Responsibilities (የተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች) እና MCPS Regulation CNA-RB, Advertising ይመልከቱ።

ት/ቤት ስፖንሶር ስለማያደርጋቸው ተለጣፊዎች፣ በራሪዎች፣ እና ተመሳሳይ ቁሳቁሶችፅሁፎቹ ስፖንሶር ያደረጋቸውን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እስከሰፈረባቸው፣ ወይም የሚሸጡት አለዚያም የሚስራጩት ህትመቶች የታተሙት MCPS በተመዘገቡ ተማሪዎች እስከሆነ ድረስ፣ የት/ቤቱ አስተዳደርና መምህራን የት/ቤቱ ስፖንሰር ያላደረጋቸውን ፅሁፎች ተማሪዎች እንዲያሰራጩ ይፈቅዳሉ።

በሚቀጥለው ክፍል ከተገለፁት የተከለከሉ ፈርጆች አንዱ ጋ የሚመደቡ እስካልሆነ ድረስ፣ ተማሪዎች የተለያዩ ህትመቶችን/ፅሁፎችን በማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ ግድግዳዎች ወይም ሌሎች በዘልምድ የተማሪ ማስታወቂያ መለጠፊያነት የሚውሉ ስፍራዎች ሊለጥፉ ይችላሉ።

በሚቀጥለው ክፍል ከተገለፁት የተከለከሉ ፈርጆች አንዱ ጋ የሚመደቡ እስካልሆነ ድረስ፣ ተማሪዎች በራሪዎችን ወይም መለስተኛ ፅሁፎችን በማንኛውም የትምህርት አመት ግዜ ውስጥ በጠረጴዛዎች፣ የመፅሄት አቃፊዎች፣ ወይም በት/ቤቱ የተመለከቱ ስፍራዎች ማስቀመጥ ይችላሉ።

የተለያዩ ህትመቶች/ፅሁፎች በት/ቤቱ በየውቅቱ ሊወገዱ ይችላሉ። አንድ ፅሁፍ/ህትመት የተወገደው ይዘቱ ከህጎች አንዱን በመጣሱ ከሆነ ተማሪው/ዋ የፅሁፍ መግለጫ ይደረግለ(ላ)ታል።

የንግድ ማስታወቂያዎች ወይም መግለጫዎች፣ የፖሊቲካ ዘመቻ ፅሁፍ/ህትመት፣ እና የሃይማኖት ፅሁፍ/ህትመት በተጨማሪ በተመለከቱ ደንቦች ይገዛሉ። (MCPS Regulation KEA-RA፣ Participation in Political Campaigns and Distribution of Campaign Materials (በፖሊቲካ ዘመቻ ተሳትፎና የዘመቻ ቁሳቁሶች ስርጭት) እና MCPS Regulation CNA-RA፣ Display and Distribution of Informational Materials and Announcements (የመረጃ ቁሳቁሶችና ማስታወቂያዎች አቀራረብና ስርጭት በተጨማሪ ይመልከቱ።)

Page 13: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 5

ተሳትፎ በፖሊቲካ ዘመቻዎችከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የወላጅ/የሞግዚት ፈቃድ፣ የርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም የሱ/ሷ ተወካይ ማፅደቅ፣ እና በፖሊቲካ ተመራጭ ወይም ድርጅት ጥያቄ ታክሎበት በፖሊቲካ ዘመቻ እንቅስቃሴ መሳተፍ ይችላሉ። ተቀዳሚ (primary) ወይም አጠቃላይ ምርጫ ልክ ከመካሄዱ በፊት ባለው የሁለት ሳምንት ግዜ ውስጥ ለእንደዚህ አይነቱ ተሳትፎ በአንድ የትምህርት አመት በድምሩ ሶስት የትምህርት ቀኖች ፈቃድ ለተማሪዎች ሊሰጥ ይችላል። በፖሊቲካ ዘመቻዎች የተማሪ አገልግሎት ሰአቶች ለማትረፍ እንዲቻል፣ ለህዝባዊ ቦታ ምርጫ ለሚሰለፍ ግለሰብ አገልግሎት ከመሰጠቱ በፊት ተማሪዎች MCPS Form 560-50 ማስሞላት አለባቸው።

መጣቀሻዎች፡Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)Regulation KBA-RB: Educational Purposes and Administration of

the MCPS Web (የMCPS ድረገፅ ትምህርት አላማዎችና አስተዳደር)Regulation KEA-RA: Participation in Political Campaigns and

Distribution of Campaign Materials (በፖለቲካ ዘመቻዎች ተሳትፎ እና የዘመቻ ቁሶች ስርጭት)

Regulation IGT-RA: User Responsibilities for Computer Systems, Electronic Information, and Network Security (የኮምፒውተር ስርአቶች አጠቃቀም፣ ኤሌክትሮኒክ መረጃ፣ እና የድር መዋቅር ደህንነት)

Regulation IID-RA: Programs to be Cablecast on the MCPS Education Channels (የCablecast ፕሮግራሞች በMCPS የትምህርት ቻነሎች)

¡ የመሰብሰብ ነፃነትተማሪዎች ተሰብስበው ለነሱ አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ውይይቶች ለማካሄድና በሰላማዊ መንገድ ለመሰላፍ የመሰብሰብ መብት አላቸው። እንቅስቃሴው በትምህርት ቀን፣ ከትምህርት ቀን ውጭ፣ ወይም በምሳ ሰአት ይፈቀድ እንደሆነ፣ ምን አይነት ቁጥጥርም ያስፈልግ እንደሆነ ለማወቅ፣ ተማሪዎች ከት/ቤቱ ርእሰ መምህር ጋር የመመካከር ሃላፊነት አለባቸው። ተማሪዎች ከት/ቤቱ ሰራተኞች አባላት ጋር ተባብሮ የመስራትና እንቅስቃሴው ስርአት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ተቀባይነት ያላቸው እርምጃዎች የመውሰድ ሃላፊነትም አለባቸው።

መጣቀሻዎች፡-Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)

¡ ያገር ወዳድ እንቅስቃሴዎችተማሪዎች በት/ቤት በሃገር ወዳድ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እና/ወይም ለማየት እድል ይኖራቸዋል።

ተማሪዎች በሃገር ወዳድ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እንዳይገደዱ፣ ወይም ባለመሳተፋቸው እንዳይቀጡ ወይም እንዳያፍሩ መብት አላቸው።

አንድ ተማሪ በሃገር ወዳድ እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሌሎችን ሊያቋርጥ/ልታቋርጥ አይ(ት)ችልም።

መጣቅሻዎች- Annotated Code of Maryland, Education Article, Section 7-105Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)

¡ የሃይማኖት ነፃነትተማሪዎች በት/ቤት ስፖንሶርድ የሆኑ ሃይማኖት አልባ ለሆኑና የሃይማኖት ተግባራት የማያካትቱ እንቅስቃሴዎች ማካሄድ ይችላሉ። ተማሪዎች የሃይማኖት እምነቶች በኮርሶች በማይናፈሱባቸው የአካዴሚያዊ አካባቢዎች ወይም ት/ቤት ስፖንሶር በሚያደርጓቸው እንደ ምረቃ ወይም ስብሰባዎች በመሳሰሉ አካባቢዎች የመሳተፍ መብት አላቸው። ተማሪዎች፣ የሌሎችን መብቶች እስካልነኩ ድረስ ወይም የት/ቤት እንቅስቃሴ እስካልረበሹ ድረስ፣ ት/ቤት ስፖንሶር ያላደረጋቸው የፀሎት ቡድኖችን ጨምሮ፣ የሃይማኖታቸውን ተግባሮች በት/ቤት ማክበር ይችላሉ። ተማሪዎች የMCPS መመርያዎች የሚያሟሉ የሃይማኖት ሙዚቃዎችን የሚያካትቱ የበአል ሙዚቃ ትርኢቶች የመሳተፍ ወይም የመከታተል መብት አላቸው። ከተገኘ፣ ተማሪዎች፣ የሃይማኖት ገፅታዎች ውይይት የሚደርጉባቸው የታሪክ ወይም የሃይማኖት መወዳደርያ ጥናቶች በሚካሄዱባቸው ተመራጭ (elective) ሰሚናሮች መከታተል ይችላሉ። በነዚህ ትምህርቶች የሚቀርቡት በሃቅ የተመስረቱና የተወሰኑ ሃይማኖታዊ አስተያየቶች የማያራምዱ መሆን አለባቸው።

የሃይማኖት ቁሶች ስርጭት የፖሊቲካ ቁሶቹን አይነት ተመሳሳይ መመርያዎች ይከተላል።

መጣቀሻዎች፡Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)Regulation IKB-RA: Homework Procedures (የቤት ስራ ቅደም

ተከተሎች)

¡ ክበቦች፣ ቡድኖች፣ እና የተማሪ ድርጅቶች

ተማሪዎች በክበቦች፣ ቡድኖች፣ እና የተማሪ ድርጅቶች የመሳተፍ መብትና በተሳትፎ ችሎታቸው ተፅእኖ ባላቸው ከት/ቦርድ መመሪያዎች እና ከMCPS ደንቦች ጋር የመተዋወቅ ሃላፊነት አለባቸው።MCPS

ት/ቤት ስፖንሶር ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከመደበኛ ትምህርት ውጭ (extracurricular) ለሆነ ክፍያ ከተማሪዎች ይፈለጋል።

MCPS ሁለገብ የሆነና በት/ቤቶች መካከል የሚካሄድ ክፍት የአትሊቲክስ ፕሮግራም የMCPSና የMaryland Public Secondary School Athletic Association (የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች አትሌቲክስ ማህበር) መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ሁሉም ተማሪዎች ያቀርባል። በት/ቤትች መካከል ባለው አትሌቲክስ የሚካፈሉ ተማሪዎች በMCPS የአትሌቲክስ ድረገፅ (www.montgomeryschoolsmd.org/departments/athlet ics/) የሚገኙትን ከጤናና ደህንነት ጋር የተያያዙ መረጃዎች እንዲያነቡ ይጠበቅባቸዋል።

ት/ቤት ስፖንሶር የሚያደርጋቸው ድርጅቶችበተወሰኑ ት/ቤት ስፖንሶር ያደረጋቸው ድርጅቶች ለመሳተፍ፣ ተማሪዎች በአካዴሚ ብቁ ሆነው መገኘት አለባቸው። በክለቦች፣ ቡድኖች፣ ወይም የት/ቤት ድርጅቶች ለሃለፊነት ቦታዎች ለመመረጥ ወይም ለመሾም ወይም የአመራር ቦታ ይዘው የሚገኙ ተማሪዎች ግብረገባዊ፣ ህጋዊ፣ እና ተገቢ ባህርይ ማሳየት ያለባቸው ሲሆን ይህም ሁሉንም መምርያዎች፣ ደንቦች እና የቅጥር ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ ቅደም ተከተሎችን ይጨምራል። የዲሲፕሊን ህጎችና ደንቦች በመጣስ ምክንያት ርእሰ መምህራን ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ ማእቀብ የማድረግ ስልጣን ይዘው ይቀጥላሉ። የተፈቀደላችው የተማሪ ድርጅቶች በት/ቤት መገልገያዎች የመጠቀም መብት አላቸው። ይህም፣ በማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ የድምጽ ማጉያዎች (public address (PA) system)፣ እና ማባዣዎች ተቀባይነት ያለው አጠቃቀምን ያካትታል።

ት/ቤት ስፖንሶር የማያደርጋቸው የተማሪ ድርጅቶችከዚህ የሚከተሉትን ሃላፊነቶች እስካሟሉ ድረስ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ግዜ ውጭ ስብሰባ የማካሄድ መብት አላቸው።

• ስብሰባው የደህንነት ወይም የፀጥታ አደጋ ስጋት አያስከትልም። • ስብሰባዎች በፈቃደኝነት የተመሰረቱና በተማሪዎች የተነሳሱ እንጂ ት/ቤት

ስፖንሶር እንዳደረጋቸው ክበቦች ሆነው መቅረብ ወይም መያዝ የለባቸውም።• የት/ቤት ሰራተኞች ስብሰባዎችን ስፖንሶር አያደርጉም ወይም አያራምዱም፤

ቢሆንም፣ የት/ቤት አስተዳደር አባል ለደህንነት ተቆጣጣሪ መሆን ይችላል።• የት/ቤት ተቀጣሪዎች ስብሰባዎች አይመሩም ወይም አይሳተፉም፣ የሃይማኖት

ስብሰባዎችም ቢሆኑ።

Page 14: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

6 2 0 1 4 – 2 0 1 5 A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች )

• ስብሰባው በት/ቤቱ ውስጥ ከትምህርት እንቅስቃሴዎች ስነስርአታዊ አፈፃጸም ጋር በተጨበጠና በከፍተኛ ደረጃ ጣልቃ ይገባል ተብሎ ተቀባይነት ባለው ሁኔታ የማይገመትና የማይቻል ነው።

• የት/ቤት አባል ያልሆኑ ሰዎች ስብሰባዎች ሊመሩ ወይም በተከታታይ መሳተፍ አይችሉም።

• የህዝብ/የመንግስት ገንዘብ ስብሰባዎች ላይ ወጪ አይደረግም (የመሰብሰቢያ ቦታ ማቅረቢያ ዋጋ በስተቀር)።

መጣቀሻዎች፡- Policy IOB: Education of Students with Disabilities (የአካል ጉዳት

ያላቸው ተማሪዎች ትምህርት)Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)Regulation IQD-RA: Academic Eligibility for High School

Students Who Participate in Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ለሚሳተፉ የ2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ተማሪዎች የአካዴሚያዊ ብቃት መስፈርቶች)

Regulation IQD-RA: Academic Eligibility for High School Students Who Participate in Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ለሚሳተፉ የመካከለኛ ደረጃ ትም/ቤት ተማሪዎች የአካዴሚያዊ ብቃት መስፈርቶች)

Director Systemwide Athletics (ስርአትአቀፍ የአትሌቲክስ ስራ መሪ): 301-279-3114

¡ አድልዎ-የለሽተማሪዎች በጋራ የመከባበርና በተመሳሳይ ሁኔታ የመያዝ መብት በተገነባ ምግባር ራሳቸውን የማካሄድ ሃላፊነት አለባቸው።

ሁሉም የጥላቻ/ሁከት ተግባሮችና ህገወጥ አድልዎ በተለይም በዘር፣ በቀለም፣ በብሄር፣ በሃይማኖት፣ በፆታ፣ በእድሜ፣ በትዳር ይዞታ፣ በማህበራዊ-ኤኮኖሚያዊ ይዞታ፣ በፆታዊ ዝንባሌ፣ በፆታ፣ በአካላዊ ይዞታ፣ ወይም በአካል ጉዳት የተመሰረቱት ተቀባይነት የሌላቸውና በትግስት የማይታለፉ ናቸው።

ት/ቤቶች ለመማርያ ደህና ቦታዎች ይሆኑ ዘንድ ተማሪዎች ከደካሞች መበደል፣ ከወከባ፣ እና ከማስፈራራት ነፃ የሆነ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው። ደካማን መበደል፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ትምህርትን ያወዛግባል የአክዴሚ ክንውንን፣ ስሜታዊ ጤንነት፣ እና የት/ቤትን አየርም አሉታዊ ተፅእኖ ያስከትልባቸዋል።

• የMCPS Form 230-35: Bullying, Harassment, or Intimidation Reporting (ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት) ሰነድን ጨምረው፣ ት/ቤቶች በይንዳንዱ ት/ቤት ማመልከት ሂደቶችን ለተማሪዎች ያሳውቃሉ። ዘገባዎች ለት/ቤቱ ርእሰመምህር ነው ገቢ መሆን ያለባቸው።

• የደካማ መበደል፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ክውነቶች በMCPS ይደፋፈራሉ ይደገፋሉም።

• ርእሰ መምህራን ወይም ተወካዮች ሁሉንም የደካማ መበደል፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ዘገባዎች ወድያውኑ አጣርተው እንደአግባቡ ማስተካከያ እርምጃዎችና ውጤቶች ተግባራዊ ያደርጋሉ።

• ርእሰ መምህራን በደካማ መበደል ውስጥ የተካተቱ ተማሪዎችን ወላጆች/ሞግዚቶች ወድያውኑ ያስታውቋቸዋል።

• በምርመራው መደምደምያ፣ የደካማ መበደል፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ቀጥሎ እንደሆነ ለማየት ግላዊና ተናጠላዊ ውይይቶች ከሁለቱም ከተበደለው ተማሪና ከበዳዩ ተማሪ ጋር ይከናወናሉ።

• ለተበደለው ተማሪ፣ ለበዳዩ ተማሪ እና ለተመልካቾች የድጋፍ አገልግሎቶች የሚገኙላቸው ይሆናሉ።

(Regulation JHF-RA, Bullying, Harassment, or Intimidation ይመልከቱ)

መጣቀሻዎች፡Policy ACB: Nondiscrimination (አድልዎ-አልባነት)Regulation ACA-RA: Human Relations (የህዝብ ግንኙነቶች)Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች) Regulation CNA-RA: Display and Distribution of Informational

Materials and Announcements (የመረጃ ቁሶችና ማስታወቂያዎች ማሳያና ስርጭት)

Regulation JHF-RA: Bullying, Harassment, or Intimidation (የደካማ መበደል፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት)

የዩናይትድ ስቴትስ ህገ መንግስት አንደኛው ማሻሻያ

Section 1983 of the Civil Rights Act of 1871 (የ1871 ስቪል መብቶች አዋጅ ክፍል 1983)

Title VI of the Civil Rights Act of 1964 (1964 ሲቪል መብቶች አዋጅ አርእስት 4)

Title IX of the Education Amendments of 1972 (የ1972 የትምህርት ማሻሻያ አርእስት 9)

Section 504 of the Rehabilitation Act of 1973 (የ1973 ማገገሚያ አዋጅ ክፍል 594)

The Americans with Disabilities Act of 1990(የ1990 የአካል ጉዳትያላቸው አሜሪካኖች አዋጅ)MCPS R.E.S.P.E.C.T. Make it Real:(MCPS -መከባበር በተግባር፡)

www.montgomeryschoolsmd.org/staff/respect www.montgomeryschoolsmd.org/info/bullying/

Director Systemwide Athletics (ስርአት አቀፍ የአትሊርቲክስ ስራ መሪ): 301-279-3114

¡ ልብስና ግላዊ እንክብካቤበማህበረሰቡ የአለባበስ መመዘኛዎችና በአካባቢ ት/ቤት የዲሲፕሊን መመርያ በሚሰጠው የራስ አጠባበቅ፣ ተማሪዎች ለት/ቤት በአግባቡ የመልበስና ራሳቸውን የመንከባከብ ሃላፊነት አለባቸው። በሚከተሉት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር ተማሪዎች በአለባበስና ራስን በመንከባከብ ፈሊጥ ረገድ ላይቀጡ ይችላሉ፡-

• በት/ቤት እንቅስቃሴዎች ረብሻ የመቀስቀስ አዝማምያ ካለው፤• በት/ቤት እንቅስቃሴዎች ረብሻ የሚያስነሳ ከሆነ፤• ጤና ወይም ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ፤• ያንድ ኮርስ ወይም እንቅስቃሴ ተቀባይነት ያለው መስፈርት የማያሟላ ከሆነ፤• ከወንበዴዎች ጋር ግንኙነት ካለው፤• አፈ ፀያፍ፣ ያልታረመ፣ ስድ፣ ራቁት፣ ወይም ፆታዊ የግብረ ስጋ ባህርይ፤

ወይም• ትምባሆ፣ አልኮል፣ ወይም ኣደንዛዥ እፆች የሚያራምድ ከሆነ።መጣቀሻዎች፡- Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)

¡ ፆታዊ ወከባፆታዊ ወከባ በMCPS Policy ACF ተወስኗል፣ ፆታዊ ወከባ፣ ተቀባይነት የሌላቸው ፆታዊ መቀራረቦች፣ የፆታ ችሮት ጥያቄዎች፣ እና/ወይም ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ሁኔታዎች የሚከናወኑ የቃል፣ የፅሁፍ፣ እና ፆታዊ ባህርያት ያላቸው አካላዊ ተግባሮች፡-

• ለዚህ አይነቱ ተግባር እጅ መስጠት፣ በግልፅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ፣ ለቅጥር፣ ለትምህርት፣ ወይም በሌሎች የት/ቤት እንቅስቃሴዎች ተሳትፎ እንደ ዋጋ/መካካሻ ሆኖ መታየት።

• ለዚህ አይነቱ ተግባር በአንድ ግለሰብ እጅ መስጠት ወይም እምቢታ የፆታ ጥያቄ የቀረበለት ግለሰብን የሚነካ በበዳዩ የፔርሶኔል ወይም የአካዴሚ እርምጃ ሲወሰድ።

• እንደዚህ አይነቱ ድርጊት በግለሰቡ ስራ እና ወይም አካዴሚያዊ ክንውን ከመጠን በላይ ጣልቃ ሲገባ ወይም የሚያስፈራ፣ አሉታዊ፣ ወይም ጎጂ ስራ ወይም የትምህርት አካባቢ ሲፈጥር።

በተማሪዎች ወይም በመምህራን ላይ ፆታዊ ወከባ በተማሪዎች መፈፀም ተገቢ አይደለም እናም የቦርድ መመርያዎችንና የMCPS ህጎችን ይጥሳል። በአስተዳደር አባል በተማሪ ላይ የተፈፀመ ፆታዊ ወከባ ለት/ቤት አስተዳደር አባል ወይም ለት/ቤት ርእሰ ማምህር መመልከት አለበት። የፆታዊ ወከባ አቤቱታ በርእሰ መምህሩ ላይ ከሆነ፣ አቤቱታው መመዝገብ ያለበት ለDr. Susan F. Marks, acting associate superintendent, Office of Human Resources and Development, 45 West Gude Drive, Suite 2100, Rockville, Maryland 20850 ነው። በ301-279-3204 ትገኛለች።

መጣቀሻዎች፡Regulation ACF-RA: Sexual Harassment (ፆታዊ ወከባ)Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)

Page 15: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 7

¡ የተማሪ ዘገባዎችርእሰ መምህራን ለሁሉም ተማሪዎች መዛግብት መያዝ አለባቸው። የተማሪ መዝገብ በMCPS ፎርሞች የተመዘገቡ መሰረታዊ መረጃዎች የያዘ የጥርቅሞሽ ማህደር አለው። ባንዳንድ ሁኔታዎች፣ ሚስጢራዊ ማህደር ሊፈጠር ይችላል። የት/ቤት ሰራተኞች ሚስጢራዊ ማህደር ሲፈጥሩ ወላጆችን/ሞግዚቶችን ማሳወቅ አለባቸው።

አንድ ተማሪ እና የሱ/ሷ ወላጆች/ሞግዚቶች ከት/ቤት ሰራተኞች ጋር በሚደረግ ስብሰባ የተጠራቀመ የተማሪ መዝገብ የማየት መብት አላቸው። ከተጠየቁ፣ የት/ቤት ሰራተኞች ለተማሪው/ዋ እና ለሱ/ሷ ወላጆች/ሞግዚቶች የተጠራቀመ መዝገብ ማብራራትና መግለፅ ይችላሉ።

ከትምህርት አመት መጀምርያ በ30 ቀኖች ውስጥ፣ የማውጫ መረጃ ተብለው ስለሚቆጠሩት የመረጃ አይነቶች MCPS ህዝባዊ ማስታወቂያ ይሰጣል። መረጃው ስም፣ የቴሌፎን ቁጥር፣ የትውልድ እለትና ቦታ፣ እና ሌሎች መረጃዎች ያካትታል። የቤት አድራሻዎችና የቴሌፎን ቁጥሮች ሊሰጡ የሚችሉት ለወላጆች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የቀድሞ ተማሪዎች ድርጅቶች፣ ወይም ለሆነ የሚሊታሪ ቅርንጫፍ ብቻ ነው። ወላጆች/ሞግዚቶች እነዚህን መረጃዎች በሙሉ ወይም በከፊል የማውጫ መረጃ እንዳይሆኑ ማስቀረት ይችላሉ። ተማሪው ይህን መርጃ ካስቀረ፣ እንደማንኛውም በተማሪ መዝገብ የሚገኝ መረጃ፣ በምስጢር ይያዛል።

አንድ ተማሪ የእውቅና እድሜ ሲደርስ፣ ተማሪዎች እና ወላጆች/ሞግዚቶች የተማሪ መዛግብትን በሚመለከት እኩል መብት ይኖራቸዋል። ቢሆንም ፣ ተማሪው በሱ/ሷ ወላጆች/ሞግዚቶች ጥገኛ እስከሆነች ድረስ፣ የተማሪው/ዋ እድሜ የፈላገውን ይሁን፣ ወላጆች/ሞግዚቶች የተማሪውን/ዋን መዝገብ ማየት ይቀጥላሉ።

መጣቀሻዎች፡ Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች) Regulation JOA-RA: Student Records (የተማሪ መዛግብት)

¡መፈተሽና መያዝበእጅ ከተገኘ የወንጀል ጥፋት ወይም ሌላ የስቴት ህግ ወይም የMCPS ህጎች ወይም ደንቦች በመጣስ የሚያስጠይቅ ነገር ይዟል/ይዛለች ተብሎ ተቀባይነት ያለው ጥራጣሬ ካለ፣ ርእሰ መምህሩ/ሯ፣ ረዳት ርእሰ መምህሩ/ሯ፣ የፀጥታ ጓድ አባል፣ ወይም በት/ቤት ስፖንሰር በተደረገ ሽርሽር የተሰየመ መምህር ተቀባይነት ያለው የተማሪ ፍተሻ በት/ቤት ግቢ ወይም ት/ቤት ስፖንሶር ባደረገው የሽርሽር ቦታ ማከናወን ይችላሉ።

የተማሪውን ሰውነት፣ ንብረት፣ ማስቀመጫ ሳጥን፣ ወይም የተለየለት ቦታ እንዲፈትሽ ስልጣን ያለው ሰራተኛ ከመፈተሽ በፊት ተማሪውን ለማሳወቅ ተቀባይነት ያለው ሙከራ ያደርጋል።

ህጋዊ ያልሆኑ ነገሮች በሚያዙበት ሁኔታ ሁሉ ፖሊስ ይጠራል። እነዚህ ነገሮች ለህግ አስከባሪ አካል ይረከባሉ። ሌሎች ነገሮች በሙሉ ለተማሪው/ዋ ወይም ለወላጅ/ሞግዚት ተቀባይነት ባለው ግዜ ውስጥ ይመለሳሉ።

መጣቀሻዎች፡- Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች) Regulation JGB-RA: Search and Seizure (ፈትሾ መያዝ)Annotated Code of Maryland, Education Article, Section 7-308

www.montgomeryschoolsmd.org/departments/security/

¡ የት/ቤት ደህንነትና ፀጥታአወንታዊ የመማርያ አካባቢ ለመንከባከብ የተማርዎችና የሰራተኞች ደህንነት ወሳኝ ነው። የት/ቤቶቻችን ደህንነትና ፀጥታ የሁሉም ሰው ጉዳይ ነው። ለአስቸኳይ ግዜ ሁኔታ ዝግጁ ለመሆንና ለት/ቤት ደህንነት ቅድመ ዝግጁነት፣ ሁሉም ት/ቤቶች የት/ቤት አስቸኳይ ሁኔታ ፕላን አዳብረዋል። አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ የሚጠይቅ መተንበይ የማይቻል፣ ፕላን ያልተደረገ ሁኔታ ነው። አስቸኳይ ሁኔታዎች የቦምብ ማስፈራራት፣ የወንጀል ተግባር፣ አደጋዎች፣ እሳት፣ የአደገኛ ቁሱች አድራጎቶች፣ ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን የሚያካትቱ በነሱ ግን ያልተወሰኑ ናቸው። በት/ቤት ለሚደርስ አስቸኳይ ሁኔታ ምላሽ እንዲሆን Lockdown, Evacuate, and Shelter (ዝጋ/ቆልፍ፣ ጥለህ ውጣ፣ መጠለያ አግኝ) (LES) የሚባሉ ቅደም ተከተሎች ተዘጋጅተዋል እናም የት/ቤት አስቸካኳይ ሁኔታ ዝግጁነት ፕላን አካል ናቸው። ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ኣባላት፣ እና ወላጆች/ሞግዚቶች የእነዚህ ቅደም ተከተሎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ወሳኝ ነው።

ዝጋ/ቆልፍ (Lockdown) በMCPS መገልገያ ለሚደርስ አስቸኳይ ሁኔታ ለመግለፅ ስራ የሚውል ቃል ነው። ዝጋ/ቆልፍ በህንፃ ውስጥ ወይም ውጭ አደጋ በማንዣበብ ላይ እንዳለና ወደ አስቸኳይ ዝጋ/ቆልፍ ሁኔታ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የአስተዳደር አባላትን የሚያስጠነቅቅ ነው። ሁሉም ተማሪዎች በአንድ አዋቂ ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ይጠይቃል። ተማሪዎችና የሰራተኛ አባሎች በፍጥነት ወደ አንድ ሊጠበቅ የሚችል ቦታ እንዲሄዱ፣ ፀጥ እንዲሉ፣ እና የአስተዳደር አባል ትእዛዝ እንዲከትሉ ያስፈልጋል። ለቀህ ውጣ (Evacuate) በት/ቤት ውስጥ ለሚደርስ አስቸኳይ ሁኔታ ለመግለፅ ስራ ላይ የሚውል ቃል ነው። የእሳት መልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ወይም በአስተዳደር የሚመራ የለቀህ ውጣ የድምፅ ማጉያ ማስታወቂያ አማካይነት ሁሉም ተማሪዎችና የሰራተኛ አባሎች ህንፃውን ለቀው እንዲወጡ ይጠይቃል። መጠለያ አግኝ (Shelter) በMCPS መገልገያ ወይም ባቅራቢያው ለሚደርስ አስቸኳይ ሁኔታ መኖሩን አስተዳደር አባላትን ለማስጠንቀቅ ስራ የሚውል ቃል ነው። ሁሉም ተማሪዎች መኖራቸው እንዲደረጋገጥና በአዋቂ ቁጥጥር ስር ህንፃ ውስጥ እንዲሆኑ ይጠይቃል። ሶስት አይነት የመጠለያ ማስጠንቀቂያዎች አሉ፡- የህዝብ ደህንነት (Public Safety)፣ አስከፊ ያየር ሁኔታ (Severe Weathe)፣ እና የአደጋኛ ንጥረነገሮች በውጭ መለቀቅ (Outside Hazardous Materials Release)።

ስም ሳይገልፁ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ወላጆች/ሞግዚቶች የደህንነትና የፅጥታ ስጋታቸውን ሊያመልክቱ እንዲችሉ፣ Safe Schools Hotline በቀን 24 ሰአት በሳምንት ለ7 ቀኖች ሰራተኛ ተመድቧል በጠሪ መታወቂያም አይገለገልም። ያስታውሱ፣ በት/ቤቶች ደህንነትና ፀጥታ ሁሉም ሰው ደንታ አለው፣ እነዚህም ስጋቶች ሃላፊነት ላለው አዋቂ ወይም ለSafe Schools Hotline በውቅቱ መመልከት አለባቸው።

MCPS Safe Schools 24-Hour Hotline: 301-517-5995

በቀን 24 ሰአት በሳምንት ለ7 ቀኖች ሰራተኛ የተመደበባቸው ተጨማሪ አስቸኳይ መስመሮች፡

Montgomery County Police (ፖሊስ)—አስቸኳይ ሁኔታ ላልሆነ፡- 301-279-8000አደገኛ እፅና የወንበዴ መጠቆሚያ አስቸኳይ መስመር፡- 240-773-8477

Montgomery County Health and Human Services (ይጤናና ስብአዊ አገልግሎቶች) Information Line (የመረጃ መስመር) (ከሰኞ እስከ አርብ 8:30 a.m.–5:00 p.m.): 240-777-1245

MCPS Department of School Safety and Security (የት/ቤት ደህንነትና ፀጥታ መምርያ): 301-279-3066

www.montgomeryschoolsmd.org/departments/security/

መጣቀሻዎች፡-Regulation EKA-RA: Emergency and Disaster Preparedness

(ለአስቸኳይ ሁኔታ እና ለውድመት ዝግጁነት)Regulation EKC-RA: Bomb Threats/Explosive Devices (የቦምብ ዛቻ/

ፈንጂ መሳርያዎች) Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)

¡ ተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎችየመካከለኛና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በMCPS ንብረትና MCPS ስፖንሰር በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎች መያዝ ይችላሉ። መጠቀም በማይፈቀድባቸው ወቅቶች መሳርያው መጥፋቱንና ከእይታ ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የተማሪው ሃላፊነት ነው። የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በምሳ ሰአት በተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎች መጠቀም ይችላሉ።

የኤሌሜንትሪ ተማሪዎች በትምህርት ቀን በት/ቤት ግቢ ውስጥ ተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎች እንዲይዙ አይፈቀድላቸውም።

ከወላጅ/ሞግዚት በፅሁፍ በቀረበ ተጠይቆና በርእሰ መምህሩ/ተወካዩ ከፀደቀ፣ የኤሌሜንታሪ ት/ቤት ተማሪ በት/ቤት ግቢ በትምህርት ቀን ተንቅሳቃሽ የመገናኛ መሳርያ መያዝ ይችላል። በነዚህ ታሳቢዎች ግንዛቤ በመመስረት መሰረት ርእሰ መምህሩ/ተወካዩ ደንቦችን ማውረድ ይችላል፡- ከ እና ወደ ት/ቤት ደህንነት፣ ከግቢ ውጭ የሚደረግ ግንኙነት፣ ከትምህርት ሰአት በኋላ እንቅስቃሴዎች፣ ወይም የህክምና ጉዳይ። በርእሰ መምህሩ/ተወካዩ ግላዊ አስተሳሰብ ሌሎች ታሳቢዎች ሊገናዘቡ ይችላሉ ለማንኛውም ከደንብ የማውረድ ጥያቄ በወላጅ/ሞግዚት፣ ተማሪ፣ እና በርእሰ መምህር ወይም ተወካይ መገናኘት ያስፈልጋል።

Page 16: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

8 2 0 1 4 – 2 0 1 5 A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች )

ማንም ተማሪ በማንኛውም ወቅት በተንቃሳቃሽ መገናኛ መሳርያው አድርጎ አፈ ፀያፍ፣ ባለጌ፣ ስድ ወይም የሰውን ብቸኝነት በሚጎዳ መጠቀም አይችልም። የነዚህ ምሳሌዎች ፎቶግራፎች ወይም የቴክስት መልእክት ያካትታሉ፣ በነሱ ግን አይወሰንም።

ይህ ደንብ ተግባራዊ የሚሆነው በትምህርት ሰአት የቅዳሜ ት/ቤትና የተራዘመ አመት ተማሪዎች ላይ ነው።

መጣቀሻዎች፡Regulation COG-RA: Portable Communication Devices (ተንቃሳቃሽ

መገናኛ መሳርያዎች)

¡ ዲሲፕሊንተማሪዎች ለትምህርት አስፈላጊ የሆነ ስነስርአት ያለው፣ ደህና፣ ዲሲፕሊን የተሞላ አካባቢ መብት አላቸው። ዲሲፕሊንን በሚመለከት የተማሪ መብቶችና ሃለፊነቶች በMCPS Code of Conduct (የስነምግባር ህግ) ውስጥ ተዘርዝረዋል።

¡ ይግባኝ-የቅሬታ ቅደም ተከተል - ህጋዊ ሂደት

ይህ ክፍል ስለያንዳንዱ/ዷ የአቤቱታ፣ ያድልዎ ቅሬታ፣ እገዳ ወይም ስንብት ያላስከተለ የዲሲፕሊን እርምጃ ጥያቄ ያለው/ያላት ተማሪ ጉዳይ አያያዝ መረጃ ለመስጠት የተተለመ ነው። የዚህ አይነት አያያዝ ለማረጋገጥ፣ የት/ቤት ህጎች ከቦርድ መመርያዎችና ከMCPS ደንቦች እንዲሁም በስራ ላይ ያሉ የታተሙ ህጎችና ደንቦች ጋር የሚስማሙ መሆን አለባቸው። ካውንቲ አቀፍና ያካባቢ የሁለቱም የዲሲፕሊን ህጎች መታተምና ለወላጆች/ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር አባላት መዳረስ መቻል አለባቸው።

በት/ቤት ደረጃ ውሳኔA. አንድ ተማሪ ችግር ወይም አቤቱታ፣ የአድልዎ ቅሬታን ጨምሮ፣

ካለው/ካላት፣ 1 የሚከተሉት መብቶች አሉት/አላት—1. በመግባባት ደረጃ መፍትሄ ለማግኘት2 ከርእሰ መምህሩ/ሯ

ወይም ተውካዩ/ይዋ ጋር መገናኘት፣ ወይም2. ርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም ተወካዩ/ይዋ በአግባቡ አቤቱታውን

እንዲመለከት/እንድትመለከት በፅሁፍ መጠየቅ። ተማሪው/ዋ A.1 ቢመርጥ፣ ነገር ግን በመግባባት ሂደት ወይም በቀረብው መፍትሄ ካልተደስተ/ች፣ ወይ ኣቤቱታ ከቀረብልት እለት 15 ቀኖች ካለፉ፣ ርእሰ መምህሩ/ሯ አቤቱታውን በአግባቡ እንዲመለከተው/እንድትመለከተው ተማሪው/ዋ በፅሁፍ ማስመዝገብ ይችላል/ትችላለች።

B. ርእሰ መምህሩ/ሯ የተማሪው(ዋ)ን አቤቱታ በአግባቡ በሚ(ምት)መለከትበት ወቅት፣ ተማሪው/ዋ አቤቱታውን የሚደግፉ ምስክሮችና መረጃዎች የማቅረብ መብት አለው/አላት። ርእሰ መምህሩ/ሯ ከተማሪው/ዋ የፅሁፍ አቤቱታ ከተቀበለ(ች)በት በ10 የትምህርት ቀኖች ውስጥ የፅሁፍ ውሳኔ ሰጥቶ/ታ ቅጂውን ለአመልካቹ/ቿ ያስተላልፋል/ታስተላልፋለች።

የርእሰ መምህሩ/ሯ ውሳኔ ይግባኝA. ይግባኝ አቀራረብ

ተማሪው/ዋ በተሰጠው ውሳኔ ካልተደሰተ/ች፣ ተማሪው/ዋ ከርእሰ መምህሩ ውሳኔ 10 የትምህርት ቀኖች ውስጥ ውሳኔውን ለዋና ተቆጣጣሪው ተወካይ በፅሁፍ አቤት ሊልበት/ልትልበት ይችላል/ትችላለች። ይግባኙ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፡1. የአቤቱታውና የርእሰ መምህሩ ውሳኔ ድህረ እይታ

እንዲደረግባቸው ጥያቄ2. ሁሉም ተፈላጊ ሃቀኛ መረጃዎች3. የሚጠየቀው መድህን

B. የይግባኝ ድህረ እይት1. የት/ቤት ዋና ተቆጣጣሪ ወይም ተወካዩ ጉዳዩንና የተያያዙ

መረጃዎችን ድህረ እይት ያደርጋል።2. ይግባኙ ከደረሰ በ10 የትምህርት ቀኖች ውስጥ፣ የት/ቤቶች

ዋና ተቆጣጣሪ ወይም ተወካዩ ውሳኔ ወስዶ ተማሪው(ዋ)ን እና ርእሰ መምህሩን በፅሁፍ ያስታውቃቸዋል።

የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ ውሳኔ ላይ ይግባኝተማሪው/ዋ በት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማለት መብት አለው/አላት። ውሳኔው የMontgomery County የትምህርት ቦርድ ፅ/ቤት በመገናኘት ይግባኝ ማለት ይቻላል (Suzann _ M _ [email protected] or fax to 301-279-3860)።

መጣቀሻዎች:-Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ

መብቶችና ሃላፊነቶች)Policy BLB: Rules of Procedure in Appeals and Hearings

(የይግባኝና የችሎቶች ቅደም ተከተል ህጎች)Policy BLC: Procedures for Review and Resolution of Special

Education Disputes (የልዩ የትምህርት ክርክሮች የድህረ እይትና መፍትሄ ቅደም ተከተል)

MCPS Division of Pupil Personnel Services (የተማሪ ፐርሶኔል አገልግሎቶች ክፍል): 301-315-7335

1 MCPS በዘር፣ ቀለም፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣ ትውልድ፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የጋብቻ ይዘት፣ የማህበራዊ-ኤኮኖሚያዊ ይዘት፣ የፆታ ዝንባሌ፣ የፆታ ማንነት፣ አካላዊ ይዘት፣ ወይም ስንኩልነት መሰረት አድልዎ ይከለክላል። የአድልዎ በደል ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች Ms. Lori-Christina Webb, Executive Director to the Chief Academic Officer, Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive, Room 129, Rockville, Maryland 20850, 301-279-3128፣ ወይም Student Affairs Office (የተማሪዎች ጉዳይ ፅ/ቤት 301-444-8620 በመገናኘት ምክርና እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

2 በፆታዊ ወከባ ቅሬታ ምርመራ ወቅት፣ አመልካቿ ከተከሳሽ ወካቢ ጋር ፊት ለፊት መገናኘት ወይም በምንም ሁኔት መጋጠም አይፍለግባትም።

Page 17: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 9

ተጨማሪ / አ ባ ሪ—MC P S R E GU L A T I O N S ( ደ ን ቦ ች )www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy/

MCPS Regulation ABA-RA: Community Participation in Decision-Making at the Local School (በአካባቢ ት/ቤት ውሳኔ አወሳሰድ የማህበረሰብ ተሳትፎ)

ደንቡ ዜጎች በMCPS ስኬታማ ግብረት ቀጥተኛ ግድአለኝነት እንዳላቸው ያውቅላቸዋል፣ በተለይም ያካባቢው ት/ቤት፣ እናም ዜጎች በአካባቢ ውሳኔ አወሳሰድ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው መመርያና ቅደም ተከተሎች ይቀይሳል። የአካባቢ ት/ቤት የዲሲፕሊን ፕላን ለህብረተሰብ ተሳትፎ አንዱ የዚህ አይነቱ አስፈላጊ መስክ ነው።

MCPS Regulation ABC-RA: Parent and Family Involvement (የወላጅና የቤተሰብ ተሳትፎ)

ደንቡ ጠንካራ የቤት-ት/ቤት ሽርክና ለማረጋገጥ ለት/ቤት፣ መስክ/ሜዳ፣ እና የማእከላይ ፅ/ቤት ሰራተኞች ከወላጆች/ሞግዚቶች ጋር የሚሰሩበት መመርያዎች ያስቀምጣል እናም የያንዳንዱ ተማሪ ተነሳሽነት፣ ፅናት፣ ክንውን፣ እና በራስ መተማመን የሚያበለፅግ አካባቢም ያራምዳል።

MCPS Regulation ACF-RA: Sexual Harassment (ፆታዊ ወከባ)

ደንቡ ፆታዊ ወከባ ምን እንደሆነ ይገልፃል እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠርም እንዴት እንደሚመለከትና እርዳታና ድጋፍ የሚገኝበትን ቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል። ተማሪዎችና ሰራተኞች የዚህ አይነት ስነምግባር እንዳይገጥማቸው ለማረጋገጥ MCPS መውሰድ ያለበትን እርምጃዎች ይለያል።

MCPS Regulation CNA-RA: Display and Distribution of Informational Materials and Announcements (የመረጃ ንጥረ ነገሮችና ማስታወቂያዎች ማሳያና ስርጭት)

ይህ ደንብ የንግድ ማስታወቂያ ንጥረ ነገሮች እና/ወይም መግለጫዎች አፈቃቀድና ስርጭት ወይም የምርቶች እና ወይም አገልግሎቶች ሽያጭ መመርያዎች ይሰጣል።

MCPS Regulation CNA-RB: Advertising (ማስታወቂያ)ደንቡ በMontgomery County Public Schools በሞላ የማስታወቂያና የስፖንሶሮች እውቅና ቅድመ ሁኔታዎች አስፍሯል። ደንቡ ማስታወቂያዎች የት እንደሚቀመጡ/እንደሚሰፍሩ እና ለምን ያህል ጊዜ ይገልፃል፣ የቅድመ ሁኔታዎች ይዘት ያስቀምጣል፣ ወደ ማስታውቂያ ውል ለመግባት መምርያዎች ይሰጣል።

MCPS Regulation COB-RA: Reporting a Serious Incident (ከባድ ክውነት ዘገባ)

ደንቡ በት/ቤት ንብረት ወይም ከት/ቤት እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ከባድ ክውነት ሲያጋጥም መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

MCPS Regulation COC-RA: Trespassing or Willful Disturbance on MCPS Property (በMCPS ንብረት በደል ወይም የማን አለብኝ ረብሻ)

ይህ ደንብ በMCPS ንብረት በደል በሚያደርሱ ሰዎች የት/ቤት ሰራተኞች ስልጣን ያስቀምጣል ህጉንም ለማስከበር ቅደም ተከተሎች ይሰጣል። በሰነዱ እንደተቀመጠው፣ ከትም/ቤት የታገዱ ተማሪዎች በርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም በእርሱ/ሷ ተወካይ ካልተፈቀደ በስተቀር በት/ቤቱ ግቢ እንዲደርሱ አይፈቀድላቸውም።

MCPS Regulation COE-RA: Weapons (የጦር መሳርያዎች) ይህ ደንብ በMCPS ንብረት አደገኛ ወይም ገዳይ ተብለው የሚገመቱ መሳርያዎች መያዝ የሚከለክለውን ህግ ያስቀምጣል እናም የህጉ መጣስ ሲታይም መከተል የሚባቸው ቅደም ተከተሎችንም ያስቀምጣል። የጦር መሳርያዎችም እንደዚህ ይገላፃሉ "... የእካል ጉዳት የሚያስከትሉ መሳርያዎች። ይህም የሚተኮሱ መሳርያዎች፣ ጩቤዎች፣ እና ማንኛውም እንደ የጦር መሳርያ የሚያገለግል።"

MCPS Regulation COF-RA: Alcohol, Tobacco, and Other Drugs on (በMontgomery County Schools ንብረት አልኮል፣ ትምባሆ፣ እና ሌሎች እፆች)

ይህ ደንብ በሀኪም ትእዛዝ ካልተፈቀደ በስተቀር በት/ቤት ግቢ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ የአልኮል መጠጦች ወይም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ንጥረ ነገሮች መብላት፣ መያዝ፣ ወይም ማሰራጨት ህገ ወጥ የሚያደርገውን የስቴት ህግ ያስቀምጣል እናም እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም የት/ቤት አስተዳዳሪዎች ምን አይነት ቅደም ተከተሎችና መቀጮዎች ስራ ላይ እንደሚያውሉ ያስቀምጣል።

MCPS Regulation COG-RA: Portable Communication Devices (ተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎች)

ይህ ደንብ በMCPS ንብረት የሚገኙ ወይም MCPS-ስፖንሶር በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የተንቀሳቃሽ የመገናኛ መሳርያዎች አያያዝና አጠቃቀም ቅደም ተከተሎች እና መቀጮዎች ያስቀምጣል።

MCPS Regulation ECC-RA: Loss of or Damage to Property (የMontgomery County Public Schools ንብረት መጥፋት ወይም ጉዳት)

ደንቡ፣ በአደጋና በተንኮል በሁለቱም ለደርሰ ጉዳት፣ የተሰረቀ ንብረት፣ በእሳት የጠፋ ወይም የተበላሸን ጨምሮ የጠፋ ንብረት መለየትና ማመልከት፤ የተሰረቁ ወይም የወደሙ ነገሮችን ከት/ቤት ንብረት ዝርዝር መሰረዝ፤ እናም ለጠፋ ንብረት መተኪያ ማግኘት ቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል።

MCPS Regulation ECG-RA: Student Driving and Parking Facilities (የተማሪ መኪና መንጃና ማቆምያ መገልገያዎች)

ይህ ደንብ ርእሰ መምህራን በየአመቱ ያሉትን መገልገያዎችና የተማሪዎችን የማቆሚያ ፍላጎቶች እንዲገመግሙ ያለባቸው ሃላፊነት ያስቀምጣል እንዲሁም ለተማሪዎች የማቆሚያ መገልገያዎች የመመደቢያ መስፈርቶችን ያስቀምጣል። ያካባቢ ት/ቤት ህብረተሰብ ለማቆሚያ ግድፈቶች ተገቢ የዲሲፕሊን እርምጃ የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በት/ቤት ግቢ ተሽከርካሪዎችን መንዳትና ማቆምን በሚመለከት ተማሪዎች ለሁሉም ህጎችና ለአካባቢ ት/ቤት ደንቦች ተጠያቂ ናቸው።

MCPS Regulation ECI-RA: Display of the United States and Maryland Flags (የዩናይትድ ስቴትስ እና የሜሪላንድ ሰንደቅ አላማዎች ማሳያ)

ደንቡ የሰንደቅ አላማዎች ማሳያ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል የመክፈቻ/መስቀያ ተግባሮች አፈቃቀድ እና ተማሪዎች በነዚህ ተግባሮች የሚተባበሩበትን ሃላፊነት ይደነግጋል። ደንቡ ያለመሳተፍ ቅጣቶችን ይከለክላል።

Page 18: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

1 0 2 0 1 4 – 2 0 1 5 A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች )

MCPS Regulation EEA-RA: Student Transportation (የተማሪ ትራንስፖርት)

ደንቡ ለያንዳንዱ የክፍል ደረጃ የእግር ጉዞ መጠን ያስቀምጣል እናም ተማሪዎችን በማጓጓዝ፣ ተገቢ ዘገባዎችን በመያዝ፣ እና ተገቢ የደህንነት ጥንቃቄዎች መወሰዳቸውን በማረጋገጥ ርእሰ መምህሩ/ሯ መከተል ያለበ(ባ)ትን መርሆች ይዘረዝራል። ያውቶቡስ ነጅ የዲሲፕሊን ችግሮችን በማመልከት መከተል ያለበትን ቅደም ተከተል ያስቀምጣል ርእሰ መምህሩም የተማሪ ዲሲፕሊን በሚጋባ የመከታተል ሃላፊነቱን ይገልፃል። የልዩ ትምህርት ተማሪዎች እና የአካለ ጎደሎ ተማሪዎች ትራንስፖርትም ተመልክቷል።

MCPS Regulation EKA-RA: Emergency and Disaster Preparedness (የአስችኳይ ሁኔታ እና የውድመት ዝግጁነት)

ይህ ደንብ በMCPS ስፍራዎች ለሚገኙ ሁሉም ሰዎች ደህንነት የሚሰጡ ሁለገብ ያካባቢ ቀውስ ፕላኖች መዳበርና እንክብካቤ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

MCPS Regulation EKC-RA: Bomb Threats/Explosive Devices (የቦምብ ዛቻዎች/ፈንጂ መሳርያዎች)

ይህ ደንብ የቦምብ ዛቻ ለMCPS ሰራተኞች ሲተላለፍ ወይም በMCPS ግቢ ፈንጅ መሳርያ ሆኖ የሚጠረጠር ሲገኝ መተግበር ያለባቸውን ቅደም ተከተሎች ያቀርባል።

MCPS Regulation IGO-RAGuidelines for Incidents of Alcohol, Tobacco, and Other Drug Abuse Involving Students (ተማሪዎችን የሚያካትት የአልኮል፣ ትምባሆ፣ ሌሎች እፆች አጠቃቀም ክውነቶች መምርያ)

ይህ ደንብ አልኮል፣ ትምባሆ፣ ሌሎች እፆችን በሚመለከት ከተምሪዎችና ወላጆች ጋር ስለሚካሄድ ግንኙነት ቅደም ተከተል ያስቀምጣል፤ እርዳት የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች መለየት፤ ተማሪዎችን የሚያካትቱ ትግባሬውች አመዘጋገብ፤ እና የሚጠረጠሩ ቁሶች አያያዝ።

MCPS Regulation IGT-RA: User Responsibilities for Computer Systems, Electronic Information, and (ለኮምፒውተር ስርአቶች፣ ኤሌክትሮኒክ መረጃዎች፣ እና አውታረ መረብ ጥበቃ)

ይህ ደንብ እንደ የOutlook ሂሳብ አያያዝና ከአይነተኛ የስቴት፣ የአካባቢ፣ እና የፌዴራል ህጎች የማክበሩ ጥያቄ የመሰሉ ተገቢ የኮምፒውተር አውታረ መረቦች አጠቃቀም ቅደም ተከተሎችና የሚጠበቁ ውጤቶች ያስቀምጣል።

MCPS Regulation IID-RA: Programs to be Cablecast on the MCPS Education Channels (በMCPS የትምህርት ቻነሎች Cablecast የሚሆኑ ፕሮግራሞች)

ይህ ደንብ የተቀረፁ ወይም ህያው ፕሮግራሞች በMCPS የትምህርት ቻነሎች በኬብል መዘርጋት (cablecast) እንዲደረጉ ለሚጠይቁ ት/ቤቶችና ከት/ቤት ጋር የተያያዙ ድርጅቶችና መምርያዎች መከተል ያለባቸውን ቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

MCPS Regulation IKA-RA: Grading and Reporting (ማርክ አሰጣጥና ዘገባ)

ይህ ደንብ የማርክ አስጣጥና የዘገባ ሂደቶችን በመመዘኛ ከተመሰረተ ስርአተ ትምህርትና የMCPS እና የሜሪላንድ ስቴት ግምገማዎች ጋር በማቀናጀት የተማሪን ክንውን በትክክል የሚያንፀባርቁ ማርኮች ያራምዳል።

MCPS Regulation IKB-RA: Homework Procedures (የቤት ስራ ቅደም ተከተሎች)

ይህ ደንብ ለቤት ስራ ቅደም ተከተሎችና የሚሰጡ ስራዎች ዝርዝር መመርያዎች ይሰጣል። የተመለክቱ የሃይማኖት በአላትን የትምሀርት ቦርድ በተቀበለው የቀን መቁጠርያ እንደተመለክቱት አድርጎ ያብራራቸዋል እንዲሁም በሃይማኖት በአል ምክንያት ከት/ቤት ፈቃድ ያገኙ ተማሪዎች ያመለጣቸውን ስራ ለማካካስ እድል እንዲኖራቸው አስፈላጊነቱን ያብራራል።

MCPS Regulation IKC-RA: Grade Point Averages (የማርክ ነጥብ አማካዮች) (GPA) እና Weighted Grade Point Averages (የተመዘነ የማርክ ነጥብ አማካዮች) (WGPA)

ይህ ደንብ የማርክ ነጥብ አማካዮች እና የተመዘነ የማርክ ነጥብ አማካዮች አውሳሰንና ለአሁንና ለወደፊት ቀጣሪዎች እንዲሁም እንደ ማመልከቻና የመቀበያ ሂደት አካል የሚጠይቁት ከ2ኛ ደረጃ በላይ ላሉ የትምህርት ተቋሞች ዘግቦ ለማስተላለፍ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

MCPS Regulation IOA-RA: Gifted and Talented Education (ተሰጥኦ እና የላቀ ችሎታ ያለው ትምህርት)

ይህ ደንብ የተሰጥኦ እና የላቀ ችሎታ ያለው ትምህርት መመርያ ተግባራዊ ማድረጊያ ቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

MCPS Regulation IQA-RA: Administration of the High School Interscholastic Athletic Programs (የ2ኛ ደረጃ ትም/ቤት የትም/ቤቶች አትሌቲክ ፕሮግራሞች አስተዳደር)

ይህ ደንብ መካከል በMontgomery County 2ኛ ደረጃ ትም/ቤቶች የሚከናወን አትሌቲክስ የካውንቲ-አቀፍ የት/ቤቶች ፕሮግራምች አስተዳደር ስልጣን ያብራራል። የ2ኛ ደረጃ ትም/ቤት አትሌቲክስ ገፅታዎች የሚመለከቱ ፕሮግራሞች፣ ህጎች፣ እና መመርያዎች በMCPS High School Athletic Handbook (የ2ኛ ደረጃ ትም/ቤት አትሌቲክስ መፅሃፍ/የእጅ ማስታወሻ) ተካትተዋል፣ ይህም በርእሰ ማምህሩ/ሯ ፅ/ቤት እና በያንዳንዱ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት የሚድያ ማእከል ይገኛል።

MCPS Regulation IQB-RA: Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምሀርት ውጭ እንቅስቃሴዎች)

የመደበኛ ውጭ እንቅስቃሴዎች ፕሮግራም መቋቋምና መንከባከብ መስፈርቶች በዚህ ደንብ ተቀምጠዋል።

MCPS Regulation IQD-RA: Academic Eligibility for High School Students Who Participate in Extracurricular Activities (ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ለሚሳተፉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት)

ይህ ደንብ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብቃት ቅደም ተከተሎች ያስቅምጣል።

MCPS Regulation IQD-RB: Academic Eligibility for Middle School Students Who Participate in Extracurricular Activities(ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ለሚሳተፉ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት)

ይህ ደንብ ለመካከለኛኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብቃት ቅደም ተከተሎች ያስቅምጣል።

MCPS Regulation ISB-RA: High School Graduation Requirements (ይ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ምረቃ ቅድመ ሁኔታዎች)

ይህ ደንብ የስቴት እና የካውንቲ የምረቃ ቅድመ ሁኔታዎችን አፈፃፀም ቅደም ተከተሎች ያትማል።

Page 19: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች ) 2 0 1 4 – 2 0 1 5 1 1

MCPS Regulation JEA-RA: Student Attendance (የተማሪ ክትትል)

ይህ ደንብ ለክትትል ተግባራዊ የሚሆኑ የህጉ አግባብ ያላቸው ክፍሎች ያስቀምጣል፣ ቀሪዎችን ይቅርታ የማድረግና የመመዝገብ ሃላፊነትን ያስቀምጣል፣ ክትትልን ለማሻሻልና ከተማሪዎችና ከወላጆች/ሞግዚቶች ለመከታተል ቅደም ተከትሎችን ይነግራል።

MCPS Regulation JEC-RA: Student Withdrawals from Classes and School (የተማሪ ከትምህርት ክፍልና ከት/ቤት መውጣቶች)

ይሀ ደንብ ከግል መማራ ክፍሎች ለመውጣትና ከት/ቤት ለዘለቄታው መውጣት ተማሪዎች መከተል ያለባቸው ቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል። እንደዚህ ለመሰሉት እርምጃዎች የግዜ ገደቦች ይገልፃል ለማርኮችና ለክሬዲቶች አስጣጥም መመርያዎች ያስቀምጣል።

MCPS Regulation JEE-RA: Transfer of Students (የተማሪዎች ዝውውር)

ይህ ደንብ ተማሪው ከነበረው የክትትል ሰፈር ውጭ ሌላ ት/ቤት እንዲከታተል ለሚቀርብ ጥያቄ ቅደም ተከተል አስቀምጧል።

MCPS Regulation JFA-RA: Student Rights and Responsibilities (የተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች)

ይህ ደንብ ስለ ተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች መመርያ አፈፃፀም ቅደም ተከተሎች ይሰጣል።

MCPS Regulation JGA-RA: Classroom Management and Student Behavior Interventions (የመመርያ ክፍል አስተዳደር እና በተማሪ ስነምግባር ጣልቃ መግባት)

ይህ ደንብ መማርን ለመንከባከብ አመች ለሆነ አካባቢ የተቀየሱ ዘላቂ የሆኑ የመማርያ ክፍል ዲሲፕሊን እና የቁጥጥር ቅደም ተከተሎች ለመመስረት ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል። ይህ ደንብ ከዚህ ሰነድ ጋር እና በMontgomery County የትምህርት ማህበር እና በMontgomery County የትምህርት ቦርድ መካከል ካለው ስምምነት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ የርእሰ መምህሩ/ሯን ሃላፊነቶች በሚመለከት ዝርዝር መመርያ ይሰጣል።

MCPS Regulation JGA-RB: Student Discipline (የተማሪ ዲሲፕሊን)

ይህ ደንብ ገደብና ስንብትን የሚገዛውን የስቴት ህግ ስራ ላይ ያውላል፣ የMCPS ሰራተኛ ሃላፊነቶች የሚገልፁት ቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል፣ በሂደቱ የተማሪዎች መብቶችን ያብራራል፣ እና ለአቤቱታዎች መንገድ ይሰጣል። ከተማሪ አካለ-ጎዶሎነት የተያያዙ እገዳ እና ስንብትን በሚመለከት ቅደም ተከተሎች ተካትተዋል።

MCPS Regulation JGB-RA: Search and Seizure (ፍተሻ እና መያዝ)

ይህ ደንብ ህግ ወይም የMCPS ህግ ወይም ደንብ በመጣስ ጥርጣሬ ተማሪዎች እና/ወይም ንብረታቸው ለፍተሻና ለመያዝ ሲዳረጉ መወሰድ ያለባቸው ዝርዝር መመርያዎችን ያስቀምጣል። እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሲሆን መከተል የሚያስፈልጋቸው ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

MCPS Regulation JHF-RA: Bullying, Harassment, or Intimidation (በደል፣ ወከባ፣ እና ማስፍራራት)

ይህ ደንብ ት/ቤቶች ለመማርያ ሰላማዊ ቦታ ይሆኑ ዘንድ ከበደል፣ ወከባ፣ እና ማስፍራራት ነፃ የሆነ አካባቢ ለመንከባከብ MCPS የገባበትን ግዴታ ይገልፃል። ደንቡ "በደል፣ ወከባ፣ እና ማስፍራራት"ን ይገልፃል እንዲሁም መከላከያና ጣልቃ አገባብ፣ መዘዞችና መፈወሻ እርምጃዎች፣ እናም የበደል፣ የወከባ፣ እና የማስፍራራት ተግባራት ማመልከቻ ቅደም ተከተል ደረጃዎችን ያስቀምጣል።

MCPS Regulation JHG-RA: Gangs, Gang Activity, or Other Similar Destructive or Illegal Group Behavior Prevention (ወንበዴዎች፣ የውንብድና እንቅስቃሴ፣ ወይም ተመሳሳይ አፍራሽ ወይም ህጋዊ ያልሆነ የቡድን ስነ ምግባር መከላከል)

ደንቡ አካዴሚያዊ ክንውን እና ማህበራዊ እድገት የሚኖሩት ተማሪዎችና ሰራተኞች ሰላም ሲሰማቸው ነው የሚለውን የMCPS እምነት ይገልፃል። ወንበዴዎች፣ የውንብድና እንቅስቃሴ፣ ወይም ተመሳሳይ አፍራሽ ወይም ህጋዊ ያልሆኑ የቡድን ስነ ምግባሮች (ውንበዴ-ነክ ስነምግባሮች) ከት/ቤቶች ሰላማዊ ግብረት ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ። ደንቡ ወንበዴዎች፣ የውንብድና እንቅስቃሴ፣ የመክላከያ ተግባሮች፣ እና የጣልቃገብ እንቅስቃሴዎችን ይገልፃል። የመከላከል፣ የጣልቃ አገባብ፣ መዘዞች፣ የማመልከቻ ቅደም ተከተሎች፣ የምርመራ ቅደም ተከተሎች እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል

MCPS Regulation JIA-RA: Honor Societies and Honor Rolls in Secondary Schools (የክብር ማህበሮች እና የክብር መዝገብ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች)

ይህ ደንብ በመካከለኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የክብር መዝገብ፣ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደግሞ የክብር ማህበር ለማቋቋም ቅደም ተከተሎች ይሰጣል።

MCPS Regulation JNA-RA: Curricular Expenses for Students (የትምህርት ወጪዎች ለተማሪዎች)

ይህ ደንብ የአኤኮኖሚ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይወሰዱ/ሳይታዩ፣ ለሁሉም ኮርሶች የተሟላ ቀረቤታ፣ ለነዚያ ኮርሶች የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ እና የትምህርት ፕሮግራም ለሁሉም ተማሪዎች የሚቀርብበት ቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

MCPS Regulation JNA-RB: Collection of Student Financial Obligations (የተማሪ ፋይናንሳዊ ግዴታዎች አሰባሰብ)

ይህ ደንብ ተማሪ ፋይናንሳዊ ግዴታዎች አሰባሰብ መመርያዎች ያስቀምጣል (የMCPS ንብረት በመጥፋቱ ወይም በመበላሸቱ ለመተካት ወይም ለመጠገን፣ ወይም ለMCPS ያልተከፈሉ የተማሪ እዳዎች ለመክፈል)

MCPS Regulation JOA-RA: Student Records (የተማሪ መዛግብት)

ይህ ደንብ ስለ ተማሪዎች መረጃ አሰባሰብ፣ እንክብካቤ፣ እና ስርጭት ሃላፊነቶች ከነቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል።

MCPS Regulation KBA-RB: Educational Purposes and Administration of the MCPS Web (ትምህርታዊ አላማዎችና የMCPS ድረገፅ አስተዳደር)

ደንቡ ለMCPS ድረገፅ ቅርፅና ይዘት መዋቅር ይሰጠዋል ድረፅጉ የMCPSን ትምህርታዊ አላማ ማገልገሉን ያረጋግጣል የMCPSን ሰራተኞችና ተማሪዎችን የግል/የራስ ጉዳይ ለመጠበቅ መቆጣጣርያዎች ያስቀምጣል።

MCPS Regulation KEA-RA: Participation in Political Campaigns and Distribution of Campaign Materials (በፖሊቲካ ዘመቻ ተሳትፎ እና የምርጫ ቁሶች ስርጭት)

የተማሪዎች በፖለቲካ ዘመቻ እንቅስቃሴ ተሳትፎ እንዲሁም ለተሳትፎ ፈቃድ የማግኛ ቅደም ተከተሎች በዚህ ደንብ ተቀምጠዋል።

Page 20: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

1 2 2 0 1 4 – 2 0 1 5 A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ( የ ተማ ሪ መምር ያ ለመብቶች ና ለ ሃ ላ ፊ ነ ቶች )

የ ቃ ላ ት መ ግ ለ ጫ ና ማ ስ ታ ወ ሻ ዎ ች

chronic (ዘላቂ/የማይጠፋ)ክትትል የሚደረግበት ዘላቂ የስነምግባር ተደጋጋሚ ሞዴል

collaboratively (በመተባበር)ከሌሎች ጋር አብሮ በመስራት የተፈፀመ

commencement (ምረቃ)በአክዴሚያዊ አመት ማክተሚያ ዲግሪ የመሸለም ወይም ዲፕሎማ የመስጠት ስነስርአት

compelled (የተገደደ)የሆነ ነገር ለማከናወን መገደድ ወይ መገፋት

continuum (ተከታታይ/የማያቋርጥ)ቢያንስ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ አማራጮች ያሉት ተከታታይ ክውነት

controversial (አወዛጋቢ)በርካታ ውይይት፣ አለመግባባት፣ ወይም ጭቅጭቅ የሚያስከትል

cumulative (ጥርቅሞሽ)መሰብሰብ፣ በአብዛኛው ደረጃ በደረጃ

designee (ስዩም)ላአንድ ቦታ የተሰየመ ወይም የተመረጠ ግለሰብ

discretion (የሂሊና ነፃነት)በራስ አስተሳሰብ የመወስን ወይም እርምጃ የመውሰድ ስልጣን ወይም መብት

forum (መድረክ)ስብሰባ ወይም መሰብሰቢያ ቦታ

indecent (ባለጌ)ባጠቃላይ ተቀባይነት ባገኙ የመልካም ስነምግባር መለኪያዎች አንፃር አስቀያሚ መሆን

infractions (ህገ ወጥነቶች)ህግን ወይም መመርያን የመጣስ ተግባር

intoxicants (አስካሪዎች)አልኮል ወይም የተወሰኑ እፆች

lewd (አፈ ፀያፍ)አፈ ቅድ ወይም ባለጌ

libelous (ስም አጥፊ)በቃል ወይም በአካላዊ መንቀሳቀስ ሳይሆን፣ በፅሁፍ፣ በህትመት፣ በስእሎች፣ ወይም በሌላ በሆነ መንገድ የሌላን መልካም ስም ሆን ተብሎ የተጠነሰስ ሃሰት ወይም ያልተረጋገጠ ጉዳት

malicious (ምቀኛ)ሆን ተብሎ ያለምንም አላማና መነሻ ጉዳት

materially (በመጠኑ/በርካታ)አስፈላጊ ደረጃ ድረስ፤ በሚያሳስብ ሁኔታ

obscene (ፀያፍ)ለመልካም ግብረገብና ስነምግባር አስቀያሚ፤ ባለጌ

precede (መቅደም)ቀድሞ መሄድ

profane (አፈ ፀያፍ)ያልታረመ፤ ስድ፤ ምግባረ ብልሹ፤ ፀያፍ፤ ባለጌ

socioeconomic (ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ)በህብረተሰብና በአኮኖሚያዊ ታሳቢዎች ማካከል ያለ ግንኙነትን የሚመለከት

substantially (በአመርቂ ሁኔታ)በቂ/በርካታ ወይም ከፍተኛ መጠን፣ ብዛት፣ ግዝፈት

supersede (መተካት)በስልጣን፣ በሃላፊነት፣ በውጤታማነት፣ በተቀባይነት መተካት

tampering (መነካካት/ጣልቃ መግባት)ጣልቃ መግባት፣ በተለይ ለመቀየር፣ ለመጉዳት፣ ወይም ለማበላሸት

vulgar (ስድ/ያልታረመ)ያልታረመ፤ ስድ፤ ምግባረ ብልሹ፤ ፀያፍ፤ ባለጌ

Page 21: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች
Page 22: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች
Page 23: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች
Page 24: 2014–2015 · 2014. 8. 19. · A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES (የተማሪ መምርያ ለመብቶችና ለሃላፊነቶች) 2014–2015 e የተማሪዎች

Rockville, Maryland

ህትመት በDepartment of Materials Management for the

Department of Student Services (የቁሳቁስ እስተዳደር መምርያ ለተማሪዎች አገልግሎት መምርያ)

ትርጉም በLanguage Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual Programs Office of Curriculum and Instructional Programs

1696.14ct • Editorial, Graphics & Publishing Services • 9/14 • 1,527