awramba times issue 171

22
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ በ ገፅ 11 በ ገፅ 19 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003 ዋጋ 7፡00 ብር ‹‹ወደዚህ የመጣሁበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው። አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ስንዘጋጅ አሜሪካ ከጀርባችን መሆኗን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የእናንተ ድጋፍና ምክር ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ወሳኝ ነው። … ኢትዮጵያውያን ነጻነት እና ዴሞክራሲ እንዲጎናጸፉ እንፈልጋለን። … ማርክሲስት - ሌኒኒስት አይደለንም። ነገሮችን በአዎንታዊ መንገድ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን።››..... በዳዊት ከበደ.... የመለስና የ‹‹ሲ.አይ.ኤ››ው አባል ምስጢራዊ ውይይት ፎቶ በሲሳይ ጉዛይ በ ገፅ 3 የመንግስት ተቋማትን ገመና ያጋለጠው ሪፖርት የዩ.ኤስ አሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሴክሬታሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ለማድረግ የፊታችን ሰኞ አዲስ አበባ እንደሚገቡ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ለአውራምባ ታይምስ በላከው መግለጫ እስታወቀ፡፡ ሂላሪ ክሊንተን በሁለት ቀን ቆይታቸው በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትና የአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ፡፡ በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙ ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብለት 1 ነጥብ 45 ቢሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ያለአግባብ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለጀነሬተር ኪራይ ከፍሏል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሕገ-ወጥ መንገድ ብዛቱ አምስት ሺህ የሚሆን ጥራዝ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ አሳትሞ ሒሳብ ሰብስቧል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተመደበው ከፍተኛ ሀብት ለሌላ ዓላማ ውሏል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ያጸደቀው በጀት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉን፣ ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በ2002 በጀት ዓመት ሒሳብ ላይ ባከናወነው ኦዲት በርካታ የሒሳብ አያያዝ ግድፈቶችን ማግኘቱንም አስታውቋል። ሂላሪ ክሊንተን ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ በ ገፅ 21 በ ገፅ 19 የብርቱካን የመኸር ጊዜ እርሳቸው “በኢትዮጵያ ከታዩ ሥርዓቶች ውስጥ ይህንን ሥርዓት በቀላሉ ማሸነፍ ይቻላል” ብለው ያምናሉ። የኢህአዴግ ህልውና የተመሰረተው በራሱ ጥንካሬ ላይ ሳይሆን በተቃዋሚዎች ድክመት እና ሕብረት ማጣት ላይ እንደሆነ ይገልፃሉ። አዎን፣ የዛሬ ትንታኔያቸው ማጠንጠኛ ብርቱካን ናት። ከፖለቲካው እርቃ ትቆያለች የሚል እምነት የላቸውም። “በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ አንዲት መልካም ፍሬ የምታፈራ የምታምር ድንቅ ዛፍ ተተክላ በጥሩ ሁኔታ በቅላለች፤ ብዙ ውሽንፍርና ውርጭ ተቋቁማ ፍክት ብላ አብባለች” በማለት ይተርኩና ሲደመድሙም፣ “እናም በፍሬው ለቀማ ላይ ወ/ሪት ብርቱኳን ቅርጫቷን ይዛ ብቅ አትልም ብሎ መጠርጠር የማይታሰብ ነው” ይሉናል። አቶ አብርሃም ያየህ የብተና ፖለቲካ የወለደው አዲስ ምዕራፍ! የብተና ፖለቲካ የወለደው አዲስ ምዕራፍ! ኢትዮጵያውያኑ የተስፋ ፍሬዎች በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው የተሳሳተ አመለካከት በአለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር) በፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) በ ገፅ 14 -15 ከሰሞኑ ‹‹የኢህአዴግ ደጋፊ አርቲስቶች ማኅበር›› ሳይቋቋም አይቀርም! በ ገፅ 4 የአሲድ ጥቃት የተፈፀመባት አረፈች ‹‹የሠራዊት እና ሠራዊቱ ድራማ›› የኪነ-ጥበብ ‹‹ባለሙያዎች›› እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስብሰባ ቅሬታዎች በርክተውበታል ለ20 ዓመታት ተፈትኖ የወደቀ አካል በቃህ ሊባል ይገባዋል! መውጫው መንገድ ፀንቶ መታገል ብቻ ነው! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

Upload: tigist-muluken

Post on 11-Mar-2015

331 views

Category:

Documents


11 download

TRANSCRIPT

Page 1: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

በ ገፅ 11

በ ገፅ 19

4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003 ዋጋ 7፡00 ብር

‹‹ወደዚህ የመጣሁበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው። አዲስ አበባን ለመቆጣጠር

ስንዘጋጅ አሜሪካ ከጀርባችን መሆኗን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የእናንተ ድጋፍና

ምክር ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ወሳኝ ነው። … ኢትዮጵያውያን ነጻነት

እና ዴሞክራሲ እንዲጎናጸፉ እንፈልጋለን። … ማርክሲስት - ሌኒኒስት

አይደለንም። ነገሮችን በአዎንታዊ መንገድ እንድትገነዘቡልን

እንፈልጋለን።››..... በዳዊት ከበደ....

የመለስና የ‹‹ሲ.አይ.ኤ››ው አባል ምስጢራዊ ውይይት

ፎቶ በሲሳይ ጉዛይ

በ ገፅ 3

የመንግስት ተቋማትን ገመና ያጋለጠው ሪፖርት

የዩ.ኤስ አሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሴክሬታሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ለማድረግ የፊታችን ሰኞ አዲስ አበባ እንደሚገቡ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ለአውራምባ ታይምስ በላከው መግለጫ እስታወቀ፡፡

ሂላሪ ክሊንተን በሁለት ቀን ቆይታቸው በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት

ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትና የአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ፡፡ በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙ ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብለት 1

ነጥብ 45 ቢሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ያለአግባብ

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለጀነሬተር ኪራይ ከፍሏል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሕገ-ወጥ መንገድ ብዛቱ አምስት

ሺህ የሚሆን ጥራዝ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ አሳትሞ

ሒሳብ ሰብስቧል

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር

የተመደበው ከፍተኛ ሀብት ለሌላ ዓላማ ውሏል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሕዝብ ተወካዮች ም/

ቤት ያጸደቀው በጀት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉን፣

ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል

ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በ2002 በጀት ዓመት

ሒሳብ ላይ ባከናወነው ኦዲት በርካታ የሒሳብ አያያዝ

ግድፈቶችን ማግኘቱንም አስታውቋል።

ሂላሪ ክሊንተን ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ በ ገፅ 21

በ ገፅ 19

የብርቱካን የመኸር ጊዜ

እርሳቸው “በኢትዮጵያ ከታዩ ሥርዓቶች ውስጥ ይህንን ሥርዓት በቀላሉ ማሸነፍ ይቻላል” ብለው ያምናሉ። የኢህአዴግ ህልውና የተመሰረተው በራሱ ጥንካሬ ላይ ሳይሆን በተቃዋሚዎች ድክመት እና ሕብረት ማጣት ላይ እንደሆነ ይገልፃሉ። አዎን፣ የዛሬ ትንታኔያቸው ማጠንጠኛ ብርቱካን ናት። ከፖለቲካው እርቃ ትቆያለች የሚል እምነት የላቸውም። “በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ አንዲት መልካም ፍሬ የምታፈራ የምታምር ድንቅ ዛፍ ተተክላ በጥሩ ሁኔታ በቅላለች፤ ብዙ ውሽንፍርና ውርጭ ተቋቁማ ፍክት ብላ አብባለች” በማለት ይተርኩና ሲደመድሙም፣ “እናም በፍሬው ለቀማ ላይ ወ/ሪት ብርቱኳን ቅርጫቷን ይዛ ብቅ አትልም ብሎ መጠርጠር የማይታሰብ ነው” ይሉናል።

አቶ አብርሃም ያየህ

የብተና ፖለቲካ የወለደው አዲስ ምዕራፍ!

የብተና ፖለቲካ የወለደው አዲስ ምዕራፍ!

ኢትዮጵያውያኑ የተስፋ ፍሬዎች

በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው የተሳሳተ አመለካከት

በአለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር) በፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

በ ገፅ 14 -15

ከሰሞኑ ‹‹የኢህአዴግ ደጋፊ አርቲስቶች ማኅበር›› ሳይቋቋም አይቀርም!

በ ገፅ 4

የአሲድ ጥቃት የተፈፀመባት አረፈች

‹‹የሠራዊት እና ሠራዊቱ ድራማ››የኪነ-ጥበብ ‹‹ባለሙያዎች›› እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ

ስብሰባ ቅሬታዎች በርክተውበታል

ለ20 ዓመታት ተፈትኖ የወደቀ አካል በቃህ ሊባል ይገባዋል!መውጫው መንገድ ፀንቶ መታገል ብቻ ነው!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

Page 2: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

ኮፒ ኤዲተርƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹cKV” VÑe

ታዲዎስ ጌታሁን SpÅe õeNደሳለኝ ስዩም

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ0911629281

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

የማስታወቂያ ክፍሉ ስልክ0911629281

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

በድንገት ተቀጣጥሎ የአረብ አገራትን ማዳረስ የጀመረው ሕዝባዊ አብዮት ለ42 ዓመታት ያህል የአፍሪካዊቷ ሊቢያ

አድራጊ ፈጣሪ በነበሩት ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ላይም ሲቀጣጠል ሰውየው በተቃወሟቸው ዜጎቻቸው ላይ የግድያ ብይን በይነው ዕልቂት አወጁ፡፡ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በጋዳፊና ደጋፊዎቻቸው ላይ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ወታደራዊ ድጋፍ ለተነሱባቸው የሀገሪቱ ኃይሎች በማቅረብ የተጠበቀውን ፍልሚያ ጀመሩ።

ምንም እንኳ በጋዳፊ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የበገነው የዓለም ሕዝብ ለጥምር ኃይሉ ያለውን ድጋፍ ቢገልጽም፣ አሜሪካውያን ግን ከራሳቸው ብሔራዊ ፍላጎትና ጥቅም ጋር የተያያዘ አንድ መጠይቅ ወዲያውኑ አቀረቡ፡፡

የሕዝቡን ፍላጎት በሚያንሸራሽሩ የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን አማካይነት የቀረበው ጥያቄ፣ ‹‹በዚህ ከፍተኛ ወጪ በሚጠይቅ ወታደራዊ ግዳጅ የአሜሪካ ፍላጎትና ጥቅም ምንድነው?›› የሚል ነበር፡፡ የተለዩ አመክንዮዓዊ መሰረቶችን በመዘርዘር የሚነቅፍ ነው የጥያቄው አንደምታ። እናም ሳይውል ሳያድር የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ምላሽ ተሰማ።

በመገናኛ ብዙኃንም ቀርበው፣ ‹‹አዎ፤ በዘመቻው ተሳትፈናል። ይህን ያደረግነውም አምባገነኖች ሕዝባቸውን ሲጨፈጭፉ የሞራል እና ዓለም አቀፍ ሰላም የማስጠበቅ ግዴታ ስላለብን ነው› ሲሉ ገለፁ፡፡

ሌላው የማይዘለል ነጥብ ደግሞ ፍጹም ዴሞክራሲያዊነት በተንፀባረቀበት ሁኔታ በዘመቻው ላይ ከራሳቸው የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ሳይቀር ተቃውሞ

የገጠማቸውን ያህል፣ የፓርቲያቸው ተቀናቃኝ ከሆነው ሪፑብሊካን ፓርቲ ድጋፍ የቸሯቸውም ነበሩ፡፡

ጥያቄው፣ ይህ ተሞክሮ ለአገራችን መሪዎች ምን ያስተምራል የሚል ነው። ከዚህ ጋር አያይዘን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለሥልጣናት እና በሚዲያዎቻቸው ሲገለፅ የነበረን ስናስታውስ ልዩነቱንና ለልዩነቱ ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች በግልፅ ያመላክተናል ብለን እናምናለን።

እንደሚታወሰው ሁሉ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ዘምቷል በሚል አል-ጃዚራ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ሌሎች ሚዲያዎች ምስል እያስደገፉ ጉዳዩን ለዓለም ሕዝብ አቀረቡ። የኢህአዴግ መንግሥት ምላሽ ግን ሁነቱን ሙሉ ለሙሉ ያስተባበለ ሆኖ ተከሰተ። ዘግይቶ ግን የአል-ሻባብ መሪ በኢትዮጵያ ላይ ‹‹ጅሃድ አውጀናል›› በማለቱ ቀደም ሲል የነበረው ማስተባበያ ተቀየረ። ይህንኑ ተከትሎ በየደረጃው ያሉ ሹማምንት አቋማቸውን ቀይረው አዲሱን መግለጫ ማቀንቀን ጀመሩ።

‹‹አድርገናል፤ ያደርግነውም ለዚህ ዓላማ ሲባል ነው›› በሚል ለሕዝብ በታማኝነትና በግልፅ የመንገር አሰራር የሌለ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ሁኔታውን ሚዛናዊ ለማድረግ እንዳያስችል እንኳ በሥርዓቱ ውስጥ ከላይ እስከታች የሚገኙ ሹማምንት በምንም መልኩ ይገለፅ ከማስተጋባት ውጪ በዚህ ላይ የተለየ ኃሳብ አለኝ በሚል የአማራጭ አቅጣጫ ሲያመላክቱ አናይም። ይህም ለማንኛውም ዜጋ አሳሳቢ አካሄድ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ‹‹ከእኛ ጋር ያልሆኑ ሁሉ ከእኛ በተቃራኒ የቆሙ ናቸው›› ከማለት አልፎ፣ የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውን ወገኖች በሚያነሱት ኃሳብ ወይም በሚያራምዱት የፖለቲካ ርዕዮት-ዓለም ምንነት ሳይሆን

በመሰረተ ልዩነቱ ብቻ ሲታገሉት ይስተዋላል።

ቆጥረን የማንጨርሳቸው ሆኖም አካሄዳቸው በትውልዱ አስተሳሰብ እጅግ አደገኛ ጫና የሚያሳርፉ ክንውኖችን መሪዎች ሲገልፁ፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሲያራግቡ፣ ከላይ ያለው አመራር አቋሙን ሲቀይር ወዲያው ብዙ የተባለለትን ሁነት አፈር አልብሶ አዲሱን መዝሙር መዘመር ለገዢው መንግስት ጠቅሞታል የሚል መከራከሪያ ቢቀርብ እንኳ ሕዝቡን ውዥንብር ውስጥ እየከተተ መቀጠሉ አጠያያቂ አይደለም። በተለይ አንዳንዶቹ ጉዳዮች መዘዛቸው በቀላሉ የማይመዘዝ መሆኑን ማስተዋል ይገባል። የመሪዎች ኃሳብ መዋዠቅ ምናልባት ድርጅታዊ ጠቀሜታን ‹‹ያስገኛል›› ተብሎ ታምኖበት ተወስዶ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ግን ያ የሚያስከትለው አገራዊ ምስቅልቅል እጅግ እጅግ ያሳስበናል!

ከዓመታት በፊት ማቆጥቆጥ የጀመረውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ለመከላከል መደረግ ስለሚኖርበት የቁጥጥር ሥርዓት ከአንዳንድ የነፃ ፕሬሶች፣ ከምሁራኑ እና ከሕዝቡ ይቀርቡ ለነበሩ አማራጮች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፣ ‹‹የሚመራን ገበያው ነው፤ የምንከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲም ይህንኑ መሰረት ያደረገ ነው›› ሲሉ የሰጡት ምላሽ አሁን ድረስ በጆሮአችን የሚያቃጭል ነው፡፡ በኋላም በየደረጃው ያሉ የመንግሥታቸው ባለሥልጣናት ይህንኑ በጠነከረ አፅንኦት ሲገልፁ ተደመጡ፡፡

አይደለም የተለየ ኃሳብ ያቀረበ፣ ከዚህ የተለየ ኃሳብ ሲነሳ የነበረው ምላሽ በጠንካራ ተቃውሞ የታቃኘ ነበር። ቆይቶ ግን፣ ማለትም ከአምስት ወራት በፊት፣ በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ በተደረገ የዋጋ ትመና ለዓመታት የተቀነቀነው ወደ ጎን ተደረገ።

ያንንም ተከትሎ ላለፉት አምስት ወራት ከላይ እስከታች የነበሩ የገዢው መንግሥት ሹማምንት ስለዋጋ ተመኑ በማይታጠፍ አቋም ሲከራከሩ ቆዩ። አሁንም ከላይ ያለው አቋሙን ቀየረ፡፡ እናም ከአምስት ወራት በኋላ ወደ ‹‹ገበያው ይመራናል›› ተመለስን። እንዴት? በምን አግባብ? ቀጣዩስ ጉዞ? በሚለው ላይ የተለያዩ ኃሳቦች ሲንሸራሸሩ ግን እያየን አይደለም። አይተመን? አዎ! ይተመን? አዎ! ወደ በፊቱ እንመለስ? አዎ፡፡ አዎ፣ አዎ፣ አዎ ተብሎ የት ይደረሳል? ...

‹‹ኢትዮጵያ ሬዲዮኖችን ታፍናለች› የሚል ክስ ይቀርብባት የጀመረው በቅርብ ጊዜያት አይደለም። ከላይ ያሉት ‹‹ሐሰት ነው›› አሉ። በየደረጃው የሚገኙት ‹‹በሬ ወለደ ነው›› ሲሉ ቆዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግን ‹‹አቅሙ እስካለን ድረስ እናደርገዋለን፤ እንዲያውም ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ›› ሲሉ ደግሞ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ሳይቀር እያጣቀሱ ሚዲያዎችን መሸበብ የተለመደና የሚገባ መሆኑ ተዘከረልን። ሁላችንም እንደምናውቀው ዛሬ አገራችን ሬዲዮ ጣቢያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ከሰሐራ በታች ድረ-ገጾችን በማፈን ከአናቶች አናት ላይ ተቀምጣለች።

ቀደም ሲል እንደጠቀስነው፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መሰል ተሞክሮዎችን መደርደር እንችላለን። ዋናው መልዕክታችን የተባለውን ሁሉ እንደወረደ የሚያስተጋቡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ‹‹ሕዝባቸውን›› በሁለንተናዊ መንገድ እጅግ አስከፊ በሆነ መልኩ መጉዳታቸው አይቀርምና ከተግባራቸው ለመታቀብ ቆም ብለው ያስቡ ነው፡፡ ለሕሊናቸውም፣ ለሕዝቡም ታማኝ ሊሆኑ ይገባቸዋል ብሎ ማሳሰብ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹ለእኔ ምንም አይነት ትርጉም የለውም…ምክንያቱም ጥቂት ሰዎችን በማሰርና በመፍታት አገራዊ መግባባት መፍጠር

አይቻልም… በእነዚሁ ሰዎች የፍርድ ሂደት ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ የለም። ህዝቡ ይቅር

አልተባባለም››ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ አቃቤ ህግ

‹‹አሁን በኢትዮጵያ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር የእነዚህ ሰዎች መፈታት ያለው

ተፅዕኖ ምን ይመስላል?›› በሚል የደርግ ባለሥልጣናትን በማስመልከት ከሰንደቅ ጋዜጣ

ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ።

‹‹ ‘ራቁቱን የተወለደ ዳባ መች አነሰው’ ይባላል። ባያተርፍም ከደጅ ጥናትና ከጉቦ

ተላቀን መኪኖቻችንን በአግባቡ መስራታቸው በራሱ ለእኛ ሀብት ነው።››

አቶ ፀጋ አስማረየተባበሩት የነዳጅ ኩባንያ የቦርድ ሊ/መንበር ‹‹የነዳጅ ስራ በኢትዮጵያ አትራፊ አይደለም

እየተባለ ይነገራል። እውነት አትራፊ አይደለም?›› በሚል ከሪፖርተር ጋዜጣ

ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ።

የመሪዎች ሀሳብ መዋዠቅ የሚያስከትለው አገራዊ ምስቅልቅል እጅግ እጅግ ያሳስበናል

ማን ምን አ ለ

‹‹ጥሩ አይደለም! ይሄ ግልጽ ነው። ተወልጄ ያደግኩባትን እናት አገሬን አጥቻለሁ።

ከወገኔ ተለይቻለሁ።››

ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም የቀድሞ የኢህድሪ ፕሬዚዳንት

ግንቦት 13 ቀን ከኢትዮጵያ የለቀቁበትን 20ኛ ዓመት አስመልክቶ ከጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ጋር በኢትዮፒካ

ሊንክ የሬዲዮ ፕሮግራም ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ሥለስደት ከተናገሩት።

Page 3: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003 3

በዳዊት ከበደ

ጊዜው መጋቢት 1982 ዓ.ም ነው፤ የደርግ መንግሥት ሊወድቅ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ገደማ ቀርቶታል። በወቅቱ ከትግራይ በረሃዎች ሱዳን በመግባት ከካርቱም ኤርፖርት ወደ ሮም፤ ቀጥሎም ወደ ዋሽንግተን ዲ.ሲ ያቀኑት አቶ መለስ፣ የጉዞአቸው ዓላማ ጣሊያን ሮም ከተማ ውስጥ ከደርግ ጋር ለመደራደር እንደሆነ ቢገለፅም፣ ዋነኛ የአጀንዳቸው ዓላማ ግን የሚመሩት ድርጅት (ሕወሓት) ከሶሻሊዝም ርዕዮተ-ዓለም ወጥቶ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን (በአጠቃላይ ምዕራቡ) የምትፈልገውን አይዲዮሎጂ ለመከተል መወሰኑን ማሳመን፣ ብሎም ከልዕለ ኃያሏ አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ድጋፍ ማግኘት ነበር።

ዕለተ ማክሰኞ መጋቢት 25 ቀን 1982 ዓ.ም ጧት በሰሜን ምዕራብ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ጽ/ቤት ውስጥ የያኔው የሽምቅ ተዋጊው ቡድን መሪ፣ የአሁኑ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ በወቅቱ የአሜሪካን ከፍተኛ የደህንነት ባለሥልጣን ከነበሩትና (ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩት) ፖል ሄንዝ ጋር ምስጢራዊ ውይይት እያደረጉ

ነው። ውይይቶቹ ሕወሓት ስለሚከተለው አይዲዮሎጂ፣ በኢትዮጵያ ስለሚገኙ ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች አሰላለፍ፣ ስለቀጣይ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ፣ እንዲሁም ስለአቶ መለስ የግል ጉዳዮች እንዲሁም በሌሎች ወታደራዊ፣ ርዕዮተ-ዓለማዊና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ ናቸው። ወደ ቃለ-

ምልልሱ ከማምራቴ በፊት ግን ስለ ፖል ሄንዝ ጥቂት ልበላችሁ።

ፖል ሄንዝ ማን ናቸው?ኢትዮጵያን ከዳር

እስከዳር ጎብኝተዋል። አገሪቱን አብጠርጥረው ከሚያውቁ ጥቂት አሜሪካውያን መካከል ተጠቃሽ ናቸው (በዚህ ረገድ የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ባልደረባ ፕ/ር ዶናልድ ሌቪንም ይጠቀሳሉ)።

በፕሬዝዳንት ካርተር የሥልጣን ዘመን የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ ምክትል አማካሪ፣ እንዲሁም እ.አ.አ በ1970ዎቹ በኢትዮጵያ የሲ.አይ.ኤ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል - ዶ/ር ፖል ሄንዝ።

ሰውየው በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ግጭት ወቅት ‹‹ወራሪዋ ኤርትራ ናት!›› በሚል አቋማቸው

ይታወቃሉ። ከአምስት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሠራዊት ሶማሊያ ሲገባም የኢትዮጵያን እርምጃ በይፋ ደግፈዋል። ለዚህም ይመስላል በርካታዎቹ የአገራችን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሰውየውን ‹‹የአቶ መለስ አስተዳደር ጠበቃ›› ሲሉ ይሸነቁጧቸው የነበረው።

ፖል ሄንዝ አወዛጋቢ መጽሐፎችን በመጻፍም ይታወቃሉ። እ.አ.አ. በ1981 በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በካቶሊካዊያን ሊቃነ-ጳጳስ ጆን ፖል ዳግማዊ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አስመልክተው፣ “The Plot to Kill the Pope” በሚል ርዕስ የጻፉት መጽሐፍ በዓለም

በ ገፅ 15

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ከዓለም ሲኒማ ተመልካቾች የተሰበሰበ

በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው 1. ግሩም ኤርሚያስ የተዋጣለት 2. አማላይ ነው በተለይ ለእንደእኔ ትውልደ 3. ኢትዮጵያዊ ይመቻል በጥራት ስለሰራችሁት 4. አመሰግናለሁ ፊልም ማለት እንደዚህ ነው 5. ሁለት የተለያዩ ስቶሪዎች በፍቅር 6. አይቻለሁ ግሩም እኔን በጣም ነው ያማለለኝ 7. አስተዋውቁኝ እኔና ጓደኞቼ የእውነት ማለናል፡፡ 8.

ምስጋና ለዓለም ሲኒማ

ከባለሙያዎች የተሰጠ አርቲስት መርዓዊ ስጦት - ዘመኑን የዋጀ ፊልም አርቲስት ሠይፉ አርአያ - የወጣቶችን ልብ የሚማርክ ዘመናዊ ፊልም አርቲስት ጌትነት እንየው - በጣም የሚጣፍጥ ቀለል ያለ ታሪክ አርቲስት ቢኒያም ወርቁ - በሁሉም መስክ የተዋጣለት ፊልም ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ - በባለሙያዎች የተሰራ ምርጥ ፊልም የሜዳሊያ ደራሲ አማኑኤል መሀሪ - ምርጥ ፕሮዳክሽን ሊያዩት የሚገባ

የአማላዩ ፊልም እውነታዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የተቀረፀ - በCanon 5D እና 7D የተቀረፀ- በከፍተኛ በጀት የተዘጋጀ፣ 7 ወራትን የፈጀ - በየጊዜው መረጃዎችን በጋዜጣዊ መግለጫ ያበሰረ - ለቀለም እርማት ሥራ ወደ ለንደን የተጓዘ - ከተመረቀ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ በ21 እይታ የታየ- ተመልካቾችንና ባለሙያዎችን ያስማማ ምርጥ ፊልም - አማላዩ-

በእምቢልታ ሲኒማ፣ በኤድና ሞል፣ በአለም ሲኒማ፣

በዩፍታሄ ሲኒማ፣ በፓናሮሚክ ሳምንቱን ሁሉ ይገኛል

‹‹አማላዩ›› ከካም ግሎባል ፒክቸርስ አማላዩ ሮማንቲክ ኮሜዲ

ስለ ‹‹አማላዩ›› ፊልም ተመልካቾች ምን ይላሉ

ፎቶ በ

ሲሳይ

ጉዛይ

የመለስና የ‹‹ሲ.አይ.ኤ››ው አባል ምስጢራዊ ውይይት

በ ገፅ 16

ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮደብረብርሃን፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ወልዲያ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣

አላማጣ፣ ማይጨው፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር

የአቶ አንለይ ገላዬ የ6ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ

የሐዘን መግለጫአንለይ ስምህን ለዘላለም ህያው ያደረጉትን መልካም ሥነ-ምግባርህን፣ ቅንነትህንና አለኝታነትህን ይዘህ ከተለየኸን እነሆ ስድስት አመታት ቢያልፍም የመልካምነትህ መገለጫ የሆኑ በጎ ስራዎችህ ምሳሌ ሆነው ለዘላለም ከኛ ጋር ትዘልቃለህ። አንተን ማጣት ለኛ ትልቅ ሞት ነው። ይሁን እንጂ የአምላክ ፍቃድ በመሆኑ ለወዳጅ ዘመዶችህ መፅናናትን እመኛለሁ።

ከወንድምህ አንተነህ ገላዬ

Page 4: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003ፊ ቸ ር4

ይግባኝ የሌለው ቅጣት

ብርቅየዋን ወፍ ፍለጋ ወይስ መቃብር ቁፈራ!/የአብዮታዊ ዴሞክራሲና የልማታዊ መንግስቱ ጋብቻ/

ጠ/ሩ በጽሑፋቸው ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግሥታትን መገንባት ለአፍሪካ አማራጭ እንደሌለው ያወሳሉ። ይሁንና አንድ የሳቱት ነገር ልማታዊ መንግሥታት መቶ በመቶ በሚያስብል አኳኃን ከዴሞክራሲ ጋር ጸበኞች ናቸው። ልማታዊ መንግሥት የሚለው እሳቤም የሚታወቀው ከጨቋኝ መንግሥታት ጋር ተያይዞ ነው።አሊያም ደግሞ በአውራ ፓርቲነት ሀገራቱን ለረዥም ጊዜ በመምራት ሥልጣንን የሙጥኝ ያሉ መንግሥታት ናቸው። ልማታዊ መንግሥታት በአማካኝ ከ30 ዓመት በላይ በስልጣን ላይ የቆዩና ተቀዋሚው እጅግ የተዳከመባቸው መሆናቸው ይነገርላቸዋል። ዋይት፣ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግሥት ብርቅዬ ወፍ እንደማለት ነው›› ሲል የሁለቱ ነገር አልተገናኝቶም መሆኑን ያረዳናል። አይተዋወቁም። ይህን ጠ/ሩም የሚያምኑት ነው። በፅሑፋቸው ብርቅዬ ዝርያ ነው ሲሉ ገልፀውታል። ተንታኞች እንደሚሉት ግንባሩ ከዚህ ቀደም ከነበረው ሪከርድ ጋር ልማታዊ መንግሥትነት ሲታከልበት ሌላ አይዶሎጂያዊ መጣረዞችን በማስከተል በልማታዊ መንግሥትነት ሰበብ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ቁጥጥሮሹን እንደሚያጠናክር ይጠበቃል። ይህም በልማታዊ መንግሥታት የሚታየው የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን በማፈን ልማትን እናስገኛለን ዘይቤ የሚያጠናክር ይሆናል። በተለይ በ2002ቱ ምርጫ ያለተፎካካሪ ወንበሩን

መጠራረጉን ተከትሎ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት በመታወጁ የዴሞክራሲ ሂደቱን ይበልጥ ፈተና ውስጥ የሚከተው ይሆናል።ልማታዊ መንግሥትን በተመለከተ የሚቀርቡት ፅሁፎች በጠቅላላው በሚያስብል ደረጃ የመንግሥቱን አምባገነንነት እንደየመንግሥት ነፃነትና ጥንካሬ (Autonomy) አድርገው ባለው ከፍተኛ ኅብረተሰቡ ውስጥ ዘልቆ የመግባትና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ያያይዙታል። ይህም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገባቸው የመሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችንና ነፃነቶችን ማገድ አንዱ ለልማት ሂደት መከፈል ያለበት ነው የሚለውን በመከራከሪያነት እንዲያቀርቡ አድርጓቸዋል። ይህም ቻንግ እንደሚለው የእነዚህን ሀገራት መንግሥት ቅቡልነት የተመሰረተው በኢኮኖሚ እድገቱ በሚያስመዘግቡት ውጤት መሆኑን ይጠቅሳል። በዚህም ልማታዊ መንግሥታት አምባገነን ናቸው የሚል መደምደሚያ አስገኝቶላቸዋል። ይህም ‹‹የሞላ ሆድ ትንታኔ›› ዋነኛው አካል ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም በ2002ቱ ምርጫ የተስተዋለ ሲሆን ጠ/ሩ ከአድዋ የምርጫ ጣቢያ ሆነው ለውጭ ጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ‹‹አስቡት እስኪ በየት ሀገር ነው በየዓመቱ በአማካይ 11 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያስመዘግብ መንግሥት በምርጫ የሚሸነፈው›› በሚል በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ የተንጠላጠለ የፖለቲካ ቅቡልነትን ድርጅታቸው እንደሚከተል አስቀምጠዋል። ግንባሩና ባለስልጣናቱ በተደጋጋሚ በሚያወጧቸው ሰነዶችና መግለጫዎች በደሃ ሀገር ዴሞክራሲን መገንባት አስቸጋሪ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚህም

የአብዮታዊ ዴሞክራሲና የልማታዊ መንግስቱ ጋብቻ

ከስድስት ዓመታት በፊትበሚሊዮን የሚቆጠርና ከተለያዩ

የአገሪቱ ክፍል የመጣ ሕዝብ ወደ መስቀል አደባባይ መክተት የጀመረው የድጋፍ ሰልፉ ከተጠራበት ሰዓት እጅግ ቀደም ብሎ ነው። እድምተኛው በጀርባ ከታዘሉ ሕጻናት ምርኩዝ እስከያዙ አዛውንቶች ያለውን የዕድሜ ዙርያ መለስ ያካትታል።

በእያንዳንዱ ታዳሚ ፊት ላይ የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሰፈፈ ቢሆንም ቁርጠኝነቱ ወዳልተፈለገ ቁጣ የሚያመራ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ስርዓት የሚመራ እንደነበር በየትኛውም ምክንያት ይሁን በስፍራው የተገኙ ወገኖች ሁሉ የሚመሰክሩት ታሪካዊ እውነታ ነው - ሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም ያ ሕዝብ ለምን ወደ አደባባይ ወጣ ለሚለው አጭርና ቀላል ጥያቄ (ምርጫው) ሊካሄድ ሳምንት ሲቀረው ሕዝባዊ ሰልፉን ለጠራው የቀድሞው ‹‹ቅንጅት›› ድጋፉን ለማሳየት ነው የሚለው ምላሽ ብቻውን በቂ አይደለም የሚል የመከራከርያ ኃሳብ ይቀርባል።

በሰልፉ ሁለንተናዊ ዓላማዎችና ግቦች ዙርያ የተደረጉ ጥናቶች፣ በተለያዩ ባለሙያዎች የቀረቡ ትንታኔዎች፣ በሰልፉ ጠሪዎችም ሆነ ያለአንዳች አሸማቃቂ ጫና በአደባባዩ በተገኙ ታዳሚዎች የሚሰጡት ምክንያቶች ግልጽና ተመሳሳይ ናቸው። ሲጠቃለሉ ‹‹በኢትዮጵያ ሰማይ ስር እጅግ ስር የሰደደና ዜጎችን አንገት የሚያስደፋ ድህነት፣ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ገፈፋ፣ የአገርንና የሕዝብን ኃብት የሚዘርፍ የአስተዳደር ልሂቃን ዝቅጠት፣ የሕዝብን ፈጽሞ የማይገሰሱ መብቶች በዘፈቀደ የሚደፍር የካድሬ ስርዓት ተጠየቅ አልባነት፣ ወዘተ … ›› የሚሉ ይሆናሉ።

ሰልፉን የጠሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አጋር ተጋባዦች የማይታጠፍ ያሉትን የቁርጠኝነት ቃላቸውን ሰጡ። በተከታታይ በነበሩት ቀናትና ወራት ‹‹እኛ ብንሰዋ እንኳ ትግሉን ዳር የሚያደርሱ ለነጻነት ትግሉ የቆረቡ አሉ።›› የሚሉ አማላይ ቃል ኪዳኖች ተደረደሩ። በተለይ ዋንኛው ተቃዋሚ ፓርቲ የነበረው ‹ቅንጅት› በምርጫ ማኒፌስቶው ላይ ስለ ራዕዩ ሲያትት፡-

‹‹የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ሙሉ ለሙሉ የተከበሩባት ኢትዮጵያን፣ ለሕዝቡ ፍላጎት መሟላት በኃፊነትና በተጠያነት መንፈስ የሚሰራ አመራር፣ በሁሉም ደረጃ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ስርዓት የሚሰራ መልካም አስተዳደር፣ በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ያለውና ራሱን ከኋላ ቀርነትና ድህነት ለማውጣት አብሮ የሚሰራ ሕዝብ ማየት ነው።›› ያለበት አቋም ከጀርባው ብዙዎችን ያሰለፈ እንደነበር ይታመናል።

በዚያ ላይ ለብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ አገሪቱ በታሪክ ዘመኗ አጋጥሟት የማያውቀው ወደብ አልባነት የተቋጨበት መንገድ በደባ የተሞላ እንደሆነ ማመኑ፣ 70 ሺህ ያህል ልጆቹን እንደገበረበት የሚታመነው የ1990 ዓ.ም የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ባድመን ያሳጣው መሆኑና መሪዎቹ እውነታውን ሸፍጠው የገለጹበት ሁኔታ፣ ተማሪዎች በቂ ምግብ መመገብ ባለመቻላቸው በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ በጠኔ የሚወድቁባት አገር በርካታ የመንግስት ሹማምንትና እነሱን መስለው የሚያድሩ ወገኖች በብርሐን ፍጥነት በኃብት ማማ ላይ መቆናጠጣቸው… የፈጠረው ቁጭት ግስጋሴው የተፈለገው ግብ ላይ ሳይደርስ የሚያናጥበው እንደማይኖር የሚያመለክት ነበር። …

የብተና ፖለቲካ የወለደው አዲስ ምዕራፍ!

ከስድስት ዓመታት በኋላ… ከአንድ ዓመት በፊት ያስተናገደው

እንዳለ ሆኖ ከ15 ቀናት በፊት ይኸው አደባባይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ለድጋፍ የወጡ ሰልፈኞችን አስተናግዶ ነበር። በዚህ ጥሪ ላይ ያልተገኙ የአንዳንድ መ/ቤት ሰራተኞች ምክንያታችሁን ግለጹ ሳይቀር የተባለለትን ታሪካዊ አጋጣሚ፤ የፖለቲካ ተንታኞች የአንድ ክንውን ጥላ ሆኖ የሚያገለግል መባቻ መሰረት እንደተጣለ ይጠቁማሉ። ምክንያቶቻቸው ሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም ሚሊዮኖችን ወደ አደባባይ ያወጣ ሕዝባዊ ጥያቄ እንዳለ መሆኑ፣ እንዲያውም በባሰበት ሁኔታ መገኘቱ እንደሆነ ይናገራሉ። ተጨማሪ መገለጫዎችንም ያነሳሉ።

በወቅቱ ሕዝቡን አደራጅተው በነጻነት ንቅናቄ ያንቀሳቀሱት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መክነዋል። ከመሪዎቹ አንደበት ይወጡ የነበሩ ከግባችን ሳንደርስ አንመለስም መግለጫዎች ቋንቋቸው ተለሳልሷል፣ ተቀይሯል። የሚያዚያ 30/97ቱን ሰልፍ የጠራው ፓርቲ ሊቀ መንበር የነበሩት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የ2002ቱን የፓርቲዎች የስነ ምግባር ደንብ ፈርመው ከጠ/ሚ/ር መለስ ጋር ሞቅ ባለ ወዳጃዊ ስሜት ከተጨባበጡ በኋላ ‹ተምረናል፣ አውቀናል› ሲሉ ተደምጠዋል።

በአንድ ወቅት በሕይወቴ የማይረሳኝ ሲሉ ያወደሱትን ዕለትና የትግል መስመሩን በመንቀፍ አሁን ገና መስመሩን እንዳገኙት ገልጸዋል። እንደወ/ሪት ብርቱካን ያሉ ተምሳሌታዊ የፖለቲካ መሪዎች ነጻ አስተያታቸውን ለመስጠት ሳይቀር ራሳቸውን እንዲሸብቡ የሚያደርጋቸው ነገር ያለ መሆኑን የሚያሳብቅ አስተያየት ሲሰነዝሩ በሚዲዎች እየተደመጠ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ላይ ቀርበው በሰሜን አሜሪካ የውርስና ቅርስ ማሕበር ያደረገላቸውን ግብዣ መቀበላቸውን የገለጹት ወ/ሪት ብርቱካን ከዚያ ውጭ በምንም ጉዳይ ላይ ጥያቄ እንዳያቀርብላቸው አስቀድመው ቃል እንዳስገቡት ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ ለአድማጮቹ ይፋ አድርጓል።

አሁን ስማቸው መዘርዘር የማያስፈልግና ያደርጉታል ተብለው የማይታሰቡ፤ በአሁኑ ወቅት እየተንቀሳሱ ያሉ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለቃለ መጠይቅ ሲጠየቁ በተደጋጋሚ ሰበብ አስባቦችን እየደረደሩ ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን መግለጻቸው አልቀረም። በሕዝቡ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ላይ መግለጫ የሚሰጡት የመስቀል ወፍ እንደሚባለው ዓይነት ከስንት ጊዜ አንዴ ነው። ለመሆኑ አሉ? የሚል ጥያቄ እየቀረበባቸው ነው።

ብዙዎች በመግቢያችን ላይ ባየነውና በነባራዊው ሁኔታ መካከል ያለው የዓመታት ርቀት ስድስት ዓመት ብቻ መሆኑን አምነው መቀበል ያዳግታቸዋል። ፖለቲካዊ አስተሳሰቡ

በፍጹማዊ ተቃርኖ መጠለፉና ሌሎቹም መገለጫዎች የኢሕአዴግ የብተና ፖለቲካ ስልቶች የፈጠሩትን አዲስ አይነት ምዕራፍ

አመላካች ናቸው ይላሉ።ባለብዙ ፊቶቹየአገራችንን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች

በቅርበት የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኞች፣ የታሪክ፣ የባሕል፣ የፍልስፍና፣ የኪነ ጥበብ፣ የሜዲያ፣ የኢኮኖሚ እና የሌሎች መስኮች ጠበብቶች ከዚያ ሕዝቡ በትክክል ምን እንደሚፈልግ ይፋ ካደረገበት ታሪካዊ ምዕራፍ ወዲህ የነበሩት ጊዜያት የኢህአዴግ የተለያዩ

ፊቶች እየተገለጡ የተስተዋሉባቸው ናቸው ይላሉ። በተለይ ‹ወይ ሁሉንም ማግኘት ካልሆነ ግን ሁሉንም ማጣት› የሚለውን አስተሳሰብ መመርያው እንዳደረገ ይታመናል።

ይህም ኢህአዴግ ወደስልጣን የመጣበትን 20ኛ ዓመት[ከሕዳሴው ግድብ መገንባት ጋር አቆራኝቶ] ምክንያት በማድረግ በአብዮት አደባባይ በጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ አንድምታ እየተከተለ ያለውን አቅጣጫ ያመላከተበት እንዲሁም ላለፉት ተከታታይ አስር ዓመታት የዘራውን ሁሉንም የመጠቅለል ተምኔታዊ ሩጫ በብቸኝነት ያጠናቀቀበት ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

የ1992ቱ አጠቃላይ ምርጫ ከመካሄዱ ስድስት ወራት ቀደም ብሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢሲኤ አዳራሽ በተደረገ ውይይት ላይ ረ/ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ‹‹ … ኢህአዴግ ብዙ ፊቶች አሉት። በአንድ በኩል ፀጥታ አስከባሪ ነው፤ በአንድ በኩል ዳኛ ነው፣ በአንድ በኩል ፖሊስ ነው፣ በአንድ በኩል ምርጫ ቦርድ ነው። ብዙ ፊቶች አሉት። እነዚህን ፊቶች ማለፍ በጣም አስቸጋሪ ነው። በየክ/ሀገሩ የተሰማሩ ካድሬዎች ኢህአደግን ምን እንደሚፈጥርና እንደሚሰራ ሳይነገራቸው ያውቃሉ።…›› ሲሉ የተናገሩት የብተና ፖለቲካ እንቅስቃሴ የጠራ ምስሉን ያገኘው አሁን መሆኑ ይገለጻል።

የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መረራ ኢህአዴግ ይህን ሁሉ የሚያደርገው በፖለቲካ ሳይንቲስቶች ቋንቋ ‹ዜሮ ሰም ዜሮ ፖለቲክስ› ማለትም እስከመጫረሻው ሁሉንም አግኝ ያለበለዚያ ሁሉንም እጣ› አስተሳሰብ በመጠመዱ ነው በሚለው ይስማማሉ።

ብዙዎች የ2002ቱ ምርጫ ውጤት ኢህአዴግ ያሉትን ፊቶች አሟጦ የተጠቀመበት በመሆኑ ግንቦት 20/2003ትን ሲያከብር የተቆናጠጠው እርካብ በእርግጥም ተጨባጩን ሁኔታ በማሳየት የፖለቲካ አወቃቀሩ ያሰፈነውን መንፈስ የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። በእነዚህ ወገኖች እምነት በ2002ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ ወቅት የነበሩት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁለንተናዊ መስተጋብሮች መገለጫና ከመገለጫው ምንነት አንፃር ይከሰታል ተብሎ ያልተጠበቀው መቶ በመቶ ሊባል የሚችል ውጤት ለ20ኛው ግንቦት 20 ‹ሕዝባዊ የድጋፍ ማዕበል› እንደጥላ ሆኖ አገልግሏል። አዲሱን ምዕራፍ ስለወለዱት ስልቶች ከሚጠቀሱት የተወሰኑት፡-

ማስራብ! የማሕበራዊ ሳይንስ አጥኚዎች ‹አንድ

አገር ወኪሎቹን ለመምረጥ ከሚሰለፈው ሕዝብ ዳቦ ለመግዛት የሚሰለፈው የሚበዛባት ከሆነች በእርግጥ ችግር አለ› ይላሉ። ለስንዴ ሰልፍ፣ ለስኳር ሰልፍ፣ ለዘይት ሰልፍ፣ ለአትክልትና ፍራፍሬዎች ሰልፍ፣ ሰልፍ፣ ሰልፍ… ከሆነ አንድ ሕዝብ ከገዢዎች ተጽዕኖ ነጻ የሚያወጣውን ኃይሉን አጥቷል ተብሎ ይታመናል። ሁኔታውን ከዚህ የሚያከፋው ግን በእርዳታ የመጣን የምግብ እህል ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል መሆኑን የወቅቱ የመድረክ ሊቀ መንበር አቶ ገብሩ አስራት ይገልጻሉ።

አቶ አስራት በትግራይ አከባቢ ስርዓቱን ይቃወማሉ ተብለው የሚታሰቡ ዜጎችን የምግብ እህል እርዳታ እንዳገኙ

በማድረግ ተጽዕኖ መ ፍ ጠ ር የገዢው ፓርቲ የተለመደ ስልት ሆኗል ይላሉ። ኢትዮጵያን አስመልክቶ በሚነሱ ፖለቲካዊ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በድረ ገጾችና ዓለም አቀፍ ሽፋን ባላቸው የቴሌቭዥን ስርጭቶች ላይ ሙያዊ አስተያየቱን በመስጠት የሚታወቀው የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር ሲራጅ ችግሩ አለ የሚለው ‹ማስረጃዎች አሉ።› ሲል በመጀመር ነው።

‹‹ገዢው ፓርቲ የእርዳታ እህልን ህዝቡን ለማስፈራርያና ለማስገደጃ እንደሚጠቀምበት ብዙ መረጃዎች አሉ። ይህ ሙስና ብቻ ሰይሆን ዜጎች ለመብታቸው እንዳይታገሉ ህይወታቸውና ኑሯቸው ከገዢው ፓርቲ ጋር እንዲቆራኝ ያስገድዳቸዋል።›› እንደፖለቲካ ተንታኙ እምነት አንድ ፓርቲ ሁሉንም የመንግስ አካላት መቆጣጠሩ አንሶ ለተራበው ምስኪን ሕዝብ የመጣውን የነፍስ አድን የእርዳታ እህል በመቆጣጠር የሚያስርበው ከሆነ የአገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ አደጋ ላይ ይወድቃል።

በምርጫው ዋዜማ ዘ-ኢኮኖሚስት አስራሚ የተባለለት ዘገባ አስነብቦ ነበር። ‹‹ተጨማሪ አምስት አመታት - ውጤቶቹ የሚያጠራጥሩ አይደሉም። በጣም ድሃና የተራቡ ማሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ብቻ እንጂ›› ዘ-ኢኮኖሚስት ‹ውጤቶቹ የሚያጠራጥረ አይደሉም› ያለው ምርጫ ኢህአዴግን 99.6 በመቶ ውጤት ‹እንዲያገኝ› አስቻለው። ይሄ ውጤት እንዴት ሊገኝ ቻለ? በ1979ኙ የብሔራዊ ሸንጎ ምርጫ በአንድ ፓርቲ ሙሉ ለሙሉ አሸናፊነት ከተጠቀቀ በኋላ የዚህ አይነት አሃዝ ምን ያመለክተል? የሚሉ ጥያቄዎች እንዲንሸራሸሩ መንገድ ከፍቷል።

ፕሮፓጋንዳአንጋፋው ፖለቲከኛ አብርሐም ያየህ

አዲሱን ምዕራፍ ስለከፈቱት የኢህአዴግ ስልቶች ከአውራምባ ታይምስ ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹ዳጎስ ያለ መጣፍ የሚወጣው ነው።› ሲሉ ነው የጀመሩት። ‹‹ኢህአዴግ በዋናነት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ስልቶች አንዱ ህዝቡ ከራሱ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ውጪ ሌላ የተቃዋሚዎችም ይሁን የሌላ ዜጋ ድምጽ እንዳይሰማ በተቻለው ሁሉ ማፈን ነው።›› የሚሉት አቶ አብርሐም አፈናውን ተቋቁመው በብዙ መከራ የሚሰራጩ

ሃሳቦች ካሉ ደግሞ በግብር ከፋዩ ህዝብ ገንዘብ የተቋቋሙት የአገሪቱ ሚዲያዎች የገዢው ፓርቲ ንብረት ይመስል በህዝብ ሚዲያ እየተጠቀሙ የተቃዋሚውን ሃሳብ በማዛባትና ሌላ ትርጉም በመስጠት መዝመት፣ የተነሳውን ሃሳብ በሌላ ሃሳብ መሞገት ሳይቻል ሲቀር ደግሞ ሃሳቡን በሰነዘረው ድርጅት ወይም ግለሰብ ላይ ከሃሳቡ ጋር ግንኙነት የሌለው ጉዳይ እያነሳ

አቅጣጫ ለማሳት መዝመት የግንባሩ ተደጋጋሚ ስልት እንደሆነ ይገልጻሉ።

አንድ ስርዓት 99.6% ሕዝብ መርጦኛል ብሎ የሚፎክር ከሆነ ሚዲያን

የሚፈራበትና የሚያፍንበት ምክንያት ምንድነው? የሚል ጥያቄም ይነሳል።

በኦሃዮ ዴይተን ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ‹የውጭ ታዛቢዎችና መንግስታት ይቅሩና ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር ትውውቅ የሌለው ማንኛውም ሰው የዚህ አይነት ውጤት ሊገኝ

የሚችለው ተቃዋሚዎች ከታፈኑ ወይም ከሌሉ ብቻ ነው ብሎ መደምደሙ አይቀርም።› ሲሉ ሁኔታውን የገለፁበት መንገድ ብዙዎች የሚጋሩት ሆኗል።

ፕ/ር መሳይ ለውጤቱ አስተዋጽኦ አድርገዋል ያሏቸውን ነጥቦች ከዘረዘሩ በኋላ ‹በዚህም ተባለ በዚያ የከፍተኛ ድምፅ ልዩነተ ድል አገሪቷ በኢህአዴግ የመንግስት ስርዓት ስር መውደቋን ያሳያል።›› ብለዋል። ቀደም ሲል በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከፍተኛ ኢኮኖሚስት ሆነው ያገለገሉት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ይህን ያህል ውጤት አግኝቻለሁ ብሎ የሚያምን ፓርቲ ለምን መረጋጋት አቅቶት በፕሮፓጋንዳ እንደተጠመደ የገለጹት ገነባሁ የሚለው ስርዓት የመቶ በመቶ ውጤት ‹እያመጣበት› የሕጋዊ ተቀባይነት እጦት ስለሚያስነሳበት ነው በሚል ነው።

አብርሐም ያየህ ኢህአዴግ ዛሬ እያደረገው ያለውን ስንመለከት ስርዓቱ የሚፈራው ከሱ ቁጥጥር ውጭ ያሉትን ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆን ወክሎኛል፣ ኮንትራት ሰጥቶኛል፣ ወዘተ የሚለውን ህዝብ ጭምር እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም ይላሉ። መከራከርያቸውን ሲያቀርቡም አንድ በራሱ የሚተማመን ስርዓት አገር ቤት ያሉትን የግል ሚዲያዎች ማሳደድና ስም ማጥፋት አልበቃ ብሎት የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ራዲዮኖችን፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን፣ የተለያዩ ድረ-ገጾችን፣ ወዘተ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የድሃው ሕዝብ ገንዘብ እያፈሰሰ ያገር ሃብት አላግባብ ማባከን ባላስፈለገው ነበር ሲሉ ነው።

ይህ የሚዲያ አፈና ህዝቡ በሁለት መንገድ እንዲጎዳ ያደርገዋል። አማራጭ ሃሳብ እንዳያገኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በስሙ ተለምኖ ከለጋሾች የሚመጣውንና ህዝቡ ራሱ ፈሰስ ባደረገው ታክስ አማካኝነት የተገኘውን ገንዘብ አፈናዉን ለሚያከናውኑለት የውጭ ባለሙያዎች በመክፈል የሕዝቡን አንጡራ ገንዘብ አላግባብ በማባከን ነው። በመሆኑም ለአገር ልማት መዋል የነበረበት ገንዘብ ከሕዝብ ፍላጎትና ምርጫ ውጭ ለሆነ አፈና በከንቱ እየባከነ መገኘቱ ብዙዎችን የሚያስቆጭ ሆኗል።

በሌላ በኩል መሰረታዊ የተባሉ ሸቀጦች የዋጋ ተመን በወጣላቸው ወቅት መመርያውን የተቹትን ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ነጻ ኃሳባቸውን የገለጹ ወገኖችን ‹የሕዝብ ጠላት› ያስመሰሉ ፕሮፓጋንዳዎች በመንግስት ሜዲያዎች ይወርዱባቸው የነበረውን ውግዘቶች የተከታተሉ ወገኖች ግንቦት 20

በውብሸት ታዬ

ሳምንት ግንቦት 27/2003 ለህትመት በበቃችው አውራምባ ታይምስ ቁጥር 170 ‹‹ፊቸር›› አምድ ላይ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ልማታዊ መንግሥት

ከየት ወዴት ያደርሳታል?›› በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ እነሆም በዛሬው ዕትም የጽሑፉን ተከታይ ክፍል የፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ባለሙያ የሆነው ተጋባዥ ጸሐፊያችን ዘሪሁን አዲሱ ያቀርብልናል፡፡

በዘሪሁን አዲሱ

Page 5: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5

ማስታወቂያ

ፊ ቸ ር

የዴሞክራሲ ነጻነቶችን በዳቦ ለመቀየርና ለማዘግየት ያልማሉ።የአፍሪካ መንግሥታት ም ራሳቸው የመብት ቅደም ተከተል ተግባራዊ በማድረግ የልማት መብት (The Right to Development) መቅደም አለበት የሚል እምነት እንዳለ ተንታኞች ይናገራሉ። ይህ ተመሳሳይ ምክረ-ሃሳብ በልማትና በዴሞክራሲ መካከል ያለው ግንኙነት በአንዱ መታቀብ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በማውሳት የአፍሪካ መንግሥታት ጨቋኝነታቸውን ለማስተባበል ይሞክራሉ። ይህም አመለካከት ከፍተኛ እድገት ባመጡ ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ መንግሥታት ምክንያት ተጠናክሮ ነበር።ይሁንና ሁዋንግ ቻይና ላይ በሰራው ጥናት የቻይና ተዓምራዊ የኢኮኖሚ እድገት የታየው በ1980ዎቹ መንግስቱ የተሻለ ነፃ በነበረበት ወቅት መሆኑን አስቀምጧል።በሁለተኛነት የዴሞክራሲና የልማታዊ መንግሥትን ግንኙነት የሚያሳየው የመቃብር ቆፋሪው ምክረ-ሃሳብ የሚሉት ነው። ይህም መንግሥት የሚፈጥረው በኢኮኖሚ ጠንካራ የሆነ ማኅበረሰብ የተሻለ የሊበራል የፖለቲካ ስርዓትን በመጠየቅ የመንግስቱን ስልጣን ይገዳደራል የሚለው ነው። ክርሰቶፈር ዴንት እንደሚለው በታይዋን መንግስቱ በ1980ዎቹና በኋላ በኢኮኖሚ የጠነከረው ክፍል በመግስት ላይ ጫና በማሳደር ፖሊሲዎች ውስጥ አጃቸውን ማሰገባታቸውን ይገልጻሉ። በዚህም መንግሥት ለውጦችን በመፍራት ባለኃብቱንና የተማረውን ክፍል እንደሚያገል ይገልጻል።በተመሳሳይ ሁኔታ በኢትዮጵያ የኢህአዴግና የባለኃብቱና የተማረው ክፍል ግንኙነት የዚሁ ግልባጭ ነው። ኢህአዴግ ገና ስልጣን ላይ ከመምጣቱ ጀምሮ ባለኃብቱንና የተማረውን ክፍል በጤናማ አይን እንደማያይ በተደጋጋሚ ተስተውሏል።ይህም ለስልጣኑ አስጊ አድርጎ በመመልከቱ ነው። ግንባሩ በሰነዱ ላይ እንዳሰፈረው ‹‹በግል ባለኃብቱ ላይ ጥርጣሬ በመኖሩ የመንግሥት ድርሻ ሊበራሊዝም በሚያስቀምጠው መልኩ እንዳይሆን ተፈልጎ ነው›› የሚል ጥርጣሬውን ያትታል።በተለይ በምርጫ 97 ወቅት ባለኃብቱ ድጋፉን ለቅንጅቱ መስጠቱን ተከትሎ የሁለቱ

በተከበረ ማግስት ይነሳ መባሉን ከአዲሱ አቋም ጋር ያያይዙታል።

ማደፍረስበኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታዩት

የፖለቲካ አወቃቀር ችግሮች አንዱ የሆነውን የዴክራሲ ሂደት ሰበዝ በመጥቀስ ‹ምን መደረግ አለበት?› ሲሉ የሚጠይቁት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የኢፌዴሪ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ ናቸው። አምባሳደሩ በ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ መሰረት የጣለው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዕሴት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት የመቶ በመቶ አይነት ውጤት ሲቋጭ መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥያቄ ውስጥ እንደሚገቡ አሳስበዋል። የሕግ የበላይነትና የመልካም አስተዳዳር ዕጦት መስፈንንም ከዚሁ ጋር አያይዘውታል።

አምባሳደሩ በስርዓቱ ከነበራቸው ከፍተኛ ኃላፊነት አንፃር አገሪቱ ተቃዋሚዎችን እያጣች መሆኗ አሳስቧቸው ምን ቢደረግ ይሻላል? ሲሉ በምርጫው ማግስት ለንባብ ያበቁት ይህ ሚዛናዊ የተሰኘ ፅሁፋቸው ብዙ ነገሮችን መቀስቀሱ አልቀረም። ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ከሌላ ጊዜው በተለየ ሁኔታ ‹ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሱ እየታፈነ ነው› በሚል ድምፃቸውን ማስማት የጀመሩትም ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው።

የኒውስዊክ የውጭ ጉዳዮች ረዳት ማጄንግ ኤዲተር የሆኑት ጆናታን ቴፐርማን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ነው ያሉትን በፕሬሶች ላይ በሕግ ሽፋን የሚፈፀም አፈና፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ የሚወሰድ እገዳ እንዲሁም የምርጫ መጭበርበር ከጠቃቀሱ በኋላ አገራቸው (አሜሪካ) ይህ ሁሉ የዴሞክራሲ አፈና ክስ በሚቀርብባት አገር መሪዎች ላይ እያሳየች ያለችው ወዳጃዊነት (አፈናዎቹን ችላ በማለት) ሊታረም እንደሚባው በአፅንኦት ገልፀዋል። የዜጎች ድምጽ እንይሰማ ማፈን ያለውን መዘዝም በአበክሮ ገልጸዋል።

አቶ አብርሐም በውጭ አገራት የሚደረገውንና አሳፋሪ ያሉትን የአፈና ስልት ሲገልጹ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ በውጭ አገር ያለውን ወገኑን የተለየ ሃሳብ እንዳይሰማ ከሚደረጉ የተለያዩ የአፈና ስልቶች ደግሞ አንዱ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲደረጉ በመጀመሪያ የስርዓቱ ደጋፊ ናቸው የሚባሉ ሰዎችና በተለይ የትግራይ ተወላጆች በተጠሩት ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ እንዳይገኙ በስርዓቱ ኤምባሲዎች ባሉ ካድሬዎችና የስለላ ሰዎች አማካኝነት ማስጠንቀቂያ ይተላለፋል። ብዙ ሰዎች በድብቅ እያገኙ የሚነግሩኝ ይህንኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ስብሰባ በጠራንበት ቀንና ሰዓት የስርዓቱ ኤምባሲዎች ደግሞ በትግራይ ልማት ወይም በሌላ ምክንያት አሳበው ሌላ ስብሰባ ይጠራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ጥቂት ረብሸኞች ወደ እኛው ስብሰባ ይላኩና ስብሰባው ሲጀመር ረብሸኞቹ ሁካታና ጫጫታ በማድረግ ስብሰባውን ለማወክ ይሞክራሉ። ከዚህ የተነሳ ብዙ ጊዜ በፖሊስና በተሰብሳቢው ህዝብ እየተጎተቱ ሲባረሩና ሲዋረዱ ተመልክቻለሁ። ›› ሲሉ የአደፍራሽት ስልቱን ይጠቁማሉ፡፡

በእርግጥ የዚህኛው ስልት አዋጪነት አጠራጣሪ የሆነ ይመስላል፡፡ ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው እንዲሉ፣ ከዚህ ስልት በተቀሰመ ተሞክሮ መሰረት በቅርቡ በውጭጉዳይና ም/ሚ/ር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በተጠራ ስብሰባ ላይ ተቃዋሚዎች ያደረሱት ከፍተኛ እንቅፋት ተጠቃሽ ነው። ስብሰባው እንዲበተን በማስገደድ ጭምር ተቃዋሚዎቹ በልዑካኑ ላይ ያደረሱት

ኪሳራ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡

መፈናፈኛ ማሳጣትየኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር

የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የተቃውሞውን ጎራ ከተቀላቀሉ በኋላ በ2002 ምርጫ ዋዜማ ወደትውልድ አከባቢያቸው በመሄድ ስለወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ መረጃ ለማሰባሰብ ሞክረው እንደነበር ይገልፃሉ። የዶ/ሩ መረጃ አሰባሰብ ፖለቲካዊ አንድምታውን በጠራ ሁኔታ የሚያመለክት ነው ተብሎለታል። ምክንያቱም የመረጃ አሰባሰብ ስልታቸው ሁሉን አቀፍ የሚባለው አይነት ስለነበር ነው።

ነጋሶ ‹የኦህዴድ/ኢህአዴግ ካድሬዎችን ጨምሮ ከነጋዴዎች፣ ከአከባቢ ሽማግሌዎች፣ ከመንግስት ሰራተኞች፣ ከቀበሌ ኅላፊዎች፣ በግል ሙያ ከተሰማሩ ግለሰቦች፣ ከኃይማኖተ አባቶች፣ ወዘተ ጋር ተገናኝቻለሁ› ያሉ ሲሆን በዚህ ግኝታቸውም ገዥው ፓርቲ የአከባቢውን ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ በመቆጠር ተቃዋሚዎችን መፈናፈኛ እንዳጣቸው ታዝበዋል። ይህ የቁጥጥር ስርዓት እስከየት እንደሚዘልቅ ሲገልፁም ‹…ኦህዴድ/ኢህአዴግ በአከባቢው ሊፎካከሩት ለሚችሉ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ላለመፍቀድ የቆረጠ ይመስላል።…› ካሉ በኋላ ‹…ወደ አከባቢው የሚመጡ ግለሰብ ጎብኝዎችን እስካለመቀበል ይደርሳል ብለዋል።

የት እንደሄዱ፣ ማንን እንደጎበኙና ምን እንዳሉ ለማረጋገጥ በጎብኝዎች ላይ ምስጢራዊ ክትትል እንደሚደረግ አልፎ አልፎ ጎብኝዎች ለጥያቄ እንደሚጠሩ ከዚህ አልፎ በተቃዋሚ አባላት ላይ የሚፈፀመውን እስር፣ አፈና፣ ትንኮሳ፣ በጥቅማጥቅም መደለል የቢሮ ማዘጋት ወዘተ ጠቃቅስዋል።

ተቃዋሚዎችን መስራት እና ማስረግ

ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በመስራት ይከሰሳል። እነዚህ ‹ተቃዋሚዎች› የተለየ አማራና ሞጋች ኃሳብ ያላቸው ሳይሆኑ ሰርተፍኬት ይዘው በየቤታቸው የተቀመጡ፣ ኑ ሲባሉ የሚመጡ፣ ሂዱ ሲባሉ የሚሄዱ ገዢው ፓርቲ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ሕጋዊነት የሚያላብሱ ተብለው ይጠራሉ። ምሳሌ ሲጠቀስም በምርጫ መጠናቀቅ ማግስት ተቃዋሚዎች ቅሬታ ማቅረብ የሚጀምሩ ከሆነ እነዚህኞቹ ተጠራርተው ኢህአዴግን ‹እንኳ ደስ ያለህ› የሚል መግለጫ ያወጣሉ።

አቶ አብርሐም ያየህ ስርዓቱ የተቃዋሚዎቹን ደካማ ጎን የሚጠቀምበት መንገድ በዋናነት በተቃዋሚዎቹ ጉያ ውስጥ በተወሸቁና የስርዓቱ ተቃዋሚ በመምሰል ጭምብል ባጠለቁ ሰርጎ ገቦች አማካኝነት ነው ይላሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ስርዓቱ ተቃዋሚዎችን ለማዳከም ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ የተቃዋሚዎችን ስስ ብልትና ደካማ ጎን በሚገባ አጥንቶ በሰርጎ ገቦቹ አማካኝነት በዚያ ቀዳዳ ሾልኮ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርሰው አደጋ መሆኑ ይነገራል። ቀድሞ የገዢው ፓርቲ ታማኝ ጋዜጠኛ የነበረውና አሁን በስደት አውሮፓ የሚኖረው ተስፋዬ ገ/አብ ይህንን በማስመልከት በቅርቡ ባሰራጨው አንድ መጣጥፍ ላይ፣ “መለስ ዜናዊ ሃያ አመታት በስልጣን የቆየው የተቃዋሚዎችን ደካማ ጎን በትክክል ማወቁ እና ያንን ደካማ ጎናቸውን በአግባቡ ሊጠቀምበት በመቻሉ ነው” ሲል ገልጿል።

የቁርጡ ቀን ልጆችበሚዲያው ውስጥም ስርቱን

የሚያብጠለጥሉ መስለው የሚታዩና ወሳ የሚባል ቀን ሲመጣ ካባቸውን የሚገለብጡ እንዳሉ ይገለጻል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚገኙ ጋዜጦች፣ ድረገጾች፣ ራዲዮኖችና በመሳሰሉት እንሚጠቀሙ ብዙዎች ያውቃሉ፡፡ የዚህ ዓይነቱ ስልት ለምሳሌ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ በኤርትራ በኩል ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር በተለይ ከአርበኞች ግምባር፣ ከኦነግ፣ ከኦብነግና ከመሳሉት ጋር አንድ ተጨባጭ ግንኙነት ማድረግ ከጀመረ ሰርጎ ገቦቹ ብቅ ይሉና መደብደብ ይጀምራሉ። አብርሐም ያየህ የዚህ አይነቶቹን የቁርጥ ቀን ልጆች ‹‹ቀደም ሲሉ ወያኔን በመስደብና በማዋረድ

የ”ጸረ-ወያኔ” ጭምብል ያጠለቁ ስለሆነ ብዙ ሰው ሰርጎ ገቦቹ የሚቀባጥሩት ሁሉ ከአገር ወዳድነትና ከተቆርቋሪነት የመነጨ እየመሰለው አብሯቸው ይነጉዳል። በዚህ አሰራር በየጊዜው በተቃዋሚው ጎራ የሚፈጠረውን ትርምስ ቆጥሮ ለመጨረስ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡›› ይላሉ፡፡

ሮቦቶችን ማምረትብዙ ኢትዮጵያውያን

ለወገናቸው አንድ ነገር ለማድረግ ፈልገው የገዢው ፓርቲ አባልነት ጉዳይ እንደቅድመ ሁኔታ ሲቀርብላቸው ያዝናሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደገባ ካባረራቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሕራን አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በአንድ ወቅት ከአውራምባ ታይምስ ጋር

ባደረጉት ቃለ ምልልስ ‹‹ከሁሉም የሚያንገበግበኝ ለአገሬ ያለመስራቴ ነው።›› ብለው ነበር፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አዲሱን ‹የኢህአዴግን የኢትዮጵያን› ታሪክ የሚያስተምሩ ሁለት ካድሬዎች ተልጀው እንነበር ኢትጵያ ከየት ወዴት በሚለው መጽሐፋቸው ገልጸውታል፡፡

ይህ አስተሳሰብ የተዛባ የታማኝነት ትንታኔ በመያዝ እሺ እና አዎ እንጂ ለምን? እንዴት? እና አይሆንም የሚሉ ቃላት ከአንደበታቸው የማይወጣ ሮቦቶችን በታማኝነት ስም እንደሚያሰባስብ በተደጋጋሚ ተገልጿል። እነዚህ ግለሰቦች የተለየ ሃሳብም ሆነ ዕምነት ማንጸባረቅ ስለማይፈቀድላቸው የዴሞክራሲ ትግሉን ጎታች ማሽኖች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ቀደም ሲል የጠቀስናቸው ምሑር ኢህአዴግ የሚፈልገው በጭንቅላት አስበውና አመዛዝነው ሳይሆን በኮምፒውተር ፕሮግራም እየተደገፉ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ሮቦቶች ያሉ ሰብአዊ ሮቦቶችን መፍጠር ነው ይላሉ። እነዚህ ሮቦቶች ከሌላው ሮቦት የሚለዩበት ነገር ቢኖር በብረት፣ በሽቦና በፕላስቲክ ሳይሆን በአጥንት፣ በስጋ፣ በጅማትና በደም የተገነቡ መሆናቸው

ብቻ ነው ሲሉ በምጸት ይገልጻሉ። መገለጫቸውንም፡-

‹‹ታማኞቹ›› ከተገጠመላቸው መርሃ ግብር/ፕሮግራም ውጪ ከራሳቸው ጭንቅላት አመንጭተው አንዲት ነገር እንኳ መጨመር ወይም መቀነስ የማይችሉ አሳዛኝ ፍጡራን ናቸው። ሮቦቶቹ፣ መለስ የሚወዱትን ይወዳሉ፤ መለስ የሚጠሉትን ይጠላሉ። መለስ ሲስቁ ይስቃሉ፤ መለስ ሲቆጡ ይቆጣሉ። መለስ ለምን ጠሉ? ለምን ወደዱ? መለስ ለምን ሳቁ? ለምንስ ተቆጡ? ብሎ መጠየቅና መመራመር ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም ይሉታል።

የፖለቲካ ተንታኞች እንዲህ ይላሉ። የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ሙሉ ለሙሉ የተከበሩባት ኢትዮጵያን፣ ለሕዝቡ ፍላጎት መሟላት በኃፊነትና በተጠያነት መንፈስ የሚሰራ አመራር፣ በሁሉም ደረጃ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ስርዓት የሚሰራ መልካም አስተዳደር፣ በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ያለውና ራሱን ከኋላ ቀርነትና ድህነት ለማውጣት አብሮ የሚሰራ ሕዝብን ማየት በምኞት ደረጃ አማላይ ራዕይ ቢሆንም የተቀናቃኝ ወገንን ጫና የሚቋቋሙ አመራሮችና አደረጃጀት ከሌለ ግን አሁን የተወለደው አዲስ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ የሚገለጠው የባሰ የማይሆንበት ማስረጃ የለም።

ኢህአዴግ የሚፈልገው በጭንቅላት አስበውና አመዛዝነው ሳይሆን በኮምፒውተር ፕሮግራም እየተደገፉ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚያከናውኑ

ሮቦቶች ያሉ ሰብአዊ ሮቦቶችን መፍጠር ነው ይላሉ። እነዚህ ሮቦቶች ከሌላው ሮቦት የሚለዩበት ነገር ቢኖር በብረት፣ በሽቦና በፕላስቲክ ሳይሆን በአጥንት፣

በስጋ፣ በጅማትና በደም የተገነቡ መሆናቸው ብቻ ነው

በ ገፅ 7

Page 6: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 20036

ቭላድሚር ኢሊች ኡልያኖቭ፣ ኮምስኮ በስተደቡብ በምትገኘው ሲምበርስኪ (በኋላ ኡልያኖብስኪ ተብላ በተጠራችው) አነስተኛ ከተማ ነው የተወለደው። ቤተሰቦቹ መካከለኛ ገቢ ያላቸውና ምሁራን የነበሩ ሲሆን፣ አባቱ የታወቀ የትምህርት ቤት ኃላፊ ነበር። ቭላድሚር ኢሊች አስራሰበት ዓመቱ እያለ ታላቅ ወንድሙ የራሺያን ዛር (በኢትዮጵያ ‹‹አፄ›› አቻው መጠሪያ ነው) በመግደል ሴራ ላይ ተሳትፈሀል ተብሎ በስቅላት በመሞቱ በቤተሰቡ ላይ ጥቁር ደመና አጠላ። እርሱም በሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመሳተፉ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ከዩኒቨርስቲ ይባረራል፤ ወዲያውም ‹‹ሌኒን›› የሚለውን መጠሪያ በመያዝ ቭላድሚር ኢሊች የሙሉ ጊዜ አብዮተኛ ለመሆን በቃ።

ከዚያ በኋላ የሌኒን አስተሳሰብ እና ጉልበት ሁሉ በአስደናቂ መንገድ ወደአንድ አቅጣጫ ያተኮረ ነበር፤ ይኸውም አብዮቱን ወደመቀስቀስ። ሁሉም መጠነ ሰፊ ፅሁፎቹ፣ እጅግ በረቀቀ መልኩ ፅንሰ-ሀሳባዊ የሆኑትን ጨምሮ፣ አብዮታዊ ዓላማዎችን ለመደገፍ (ለማጠናከር) የተፃፉ ነበሩ። በተለይም ፅንሰ-ሀሳብን በተመለከተ ካበረከታቸው ሁለት ወሳኝ አስተዋጽኦዎች ረገድ ይህ ሐቅ ነበር፡- የአብዮታዊ ፓርቲ ፅንሰ-ሀሳብ እና የካፒታሊስት አምፔሪያሊዝም ፅንሰ-ሀሳብ ሁለቱ አስተዋጽኦዎቹ ናቸው።

የራሺያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (RSDP) የተሰኘው ማርክሲስት ፓርቲ በ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ አካባቢ በራሺያ ይቋቋምና አንፃራዊ በሆነ መልኩ ትናንሽ ከሆኑ ኢንዱስትሪዎች ሠራተኞችን ይመለምል ጀመር። ሆኖም ከጀርመኑ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (SDP) በተቃራኒው ይኼኛው ሕጋዊ አልነበረም፡- የዛሪስት ፖሊስ በከፍተኛ ሁኔታ ይከታተለዋል፣ አመራሮቹ ኗሪነታቸው ከሀገር ውጪ ነበር፣ እንዲሁም ሠራተኛውን መደብ በማደራጀት እና በመደገፍ ረገድ ስኬታማነቱ አነስተኛ ነበር። ማርክሲዝም ከመምጣቱ አስቀድሞ በራሺያ ጠንካራ የአብዮት ባህል ነበር፤ እንዲሁም ሌኒን ማርክሲስት ከመሆኑ በፊት አብዮተኛ ነበር።

የሌኒን ከፍተኛ ወኔ እና የማደራጀት ብቃት ብዙም ሳይቆይ በፓርቲ ውስጥ የመሪነት ስም ያሰጠው ሲሆን ከሀገር እንዲወጣም አድርጎታል። ይሁንና ከጊዜ ወደጊዜ በራሺያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲው እምነት እያጣ የመጣው ሌኒን አጠቃላይ የፓርቲው ፕሮግራም እና ስትራቴጂ የተሳሳተ እንደሆነ ያምናል። የፓርቲው አመራር አብዮት በመፈንዳቱ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ የለውም፤ ሆኖም ራሺያ በሌሎች ሀገራት በማንኛውም መልኩ ቀድሞ ሊፈነዳ ለሚችለው አብዮት ከመብቃቷ በፊት በቅድሚያ በረጅም የካፒታሊስት የጊዜ ሂደት ውስጥ ማለፍ እንደሚገባት ያምናል። ሌኒን በዚህ አይስማማም፤ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት እየሆነ ያለው ምንም ይሁን ምን ፓርቲው በተቻለ ፍጥነት በራሺያ አብዮት ማካሄድ እንዳለበት አፅንኦት ይሰጣል።

ሌኒን የጀርመንን ሶሸል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሞዴል ያደረገ ግዙፍ የብዙሃን ፓርቲ በመገንባቱ ስትራቴጂ ላይም አይስማማም። በራሺያ የነበሩት ሁኔታዎች በጭራሽ የተለዩ ነበሩ፤ የፓርቲው ሕገ-ወጥ መሆን፣ ለፓሊስ ጥቃት በሰፊው ክፍት መሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ክፍያ እና የሥራ ሁኔታዎችን የሚመለከቱ የሠራተኞች ጥያቄዎችን ለመደገፍ እጅግ የተገደበ መሆኑ። የሌኒን አማራጭ መንገድ ትልቅ ቦታ

የፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎችበግዛው ለገሠ

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

ሌኒን እና የአብዮታዊ ፓርቲ ፅንሰ-ሀሳቡ ቭላድሚር ኢሊች ሌኒን /1870-1924/

በሚሰጠው ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ በሚሰጠው “What Is To Be Done? (1920)” የተሰኘ ሥራው ላይ የተገለፀ ነበር። በዚህ ሥራውም ሠራተኛው መደብ የሚመራው አካል ሳይኖር በራሱ መንገድ እንዲሄድ ከተተወ ሊያጎለብት የሚችለው ከተፈላጊው “አብዮታዊ ንቃተ-ህሊና” ይልቅ “የሠራተኛ ማህበር ንቃተ-ህሊና” ብቻ እንደሆነ ይከራከራል። እናም ሠራተኛው የሚያስፈልገው ነገር፣ አስፈላጊውን አብዮታዊ ንቃተህሊና የያዘ የአዲስ ዓይነት ፓርቲ አመራርና ከዚህ ንቃተህሊና ጋር አብሮ የሚሄድ ፅንሰ-ሀሳብ እና ታክቲኮች ነበሩ።

ስለዚህም ሌኒን በአብዮታዊ እንቅስቃሴዎች የሰለጠኑ ሙሉ ለሙሉ በማርክሲስት ፅንሰ-ሀሳብ ላይ የሚመረኮዙ ትጉህ ፕሮፌሽናል አብዮተኞች የሚመሩት አነስተኛ ፓርቲ ይመሰረት ዘንድ ሀሳቡን አቀረበ። የፓርቲው አደረጃጀት “በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት (democratic centralism)” መርህ ላይ መሠረት የሚያደርግ ይሆናል። ይህም ግልፅ ውይይት እና አስተያየት የሥልጣን እርከንን ተከትሎ የሚጓዝበት ነው፤ ነገር ግን አንድ ጊዜ ከላይ ውሳኔ ከተላለፈ ያለማንገራገር በመላው ፓርቲ ተፈፃሚ መሆኑ የግድ ነው። ይህ አዲሱ ፓርቲ የወዝአደሩ ፊታውራሪ (vanguard) ይሆናል፤ ማለትም ከሠራተኛው መደብ የተነጠለ አይደለም፣ ይልቁንም ልሂቅ (መሪ) ነው - ይበልጥ ንቃተህሊና ያደረበት የመደቡ ክፍል። በተጨማሪም ሌኒን ምንም ያህል ኢ-ሞራላዊነት ቢታይበት አብዩታዊ ግቡን ለማፋጠን የሚደረግ ማንኛውም ነገር ምክንያታዊ ወይም ተቀባይነት ያለው አንደሆነ አፅንኦት ይሰጣል። በሌላ አገላለፅ በመጨረሻ የሚገኘው ግብ እርሱን ለማሳካት የተተገበሩትን ሁሉ ትክክለኛ ያደርጋቸዋል (the end justifies the means)።

የሌኒን እሳቤዎች

የራሺያን ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ አመራር ለሁለት ሰነጠቁትና የእርሱ አንጃ በኋላ “ቦልሼቪክስ” የተባለውን ፓርቲ ለማቋቋ ተገነጠሉ። እርሱ ጥሎት የመጣው ፓርቲ “ሜንሼቪክስ” በሚል ይታወቅ ጀመር። የተወሰኑት ፈጣን አብዩት ለማመጣት የመስራትን የሌኒን እምነት በበጎ የተቀበሉት ቢሆንም የእርሱ አምባገነናዊ አመራር ሊዋጥላቸው አልቻለም ነበር። በዚህ ጉዳይ ጎልቶ የሚታወቀው እንደ ፀሐፊ እና አብዮተኛ የራሱ ስምና ዝና የነበረው ሊዮን ትሮትስኪ ነበር፤ ትሮትስኪ አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ ወደ ቦልሼቪክስ ተመለሷል።

የሌኒን ለማርክሲስት ፅንሰ-ሀሳብ ያበረከተው ሁለተኛው ዋነኛ አስተዋፅዖ የማርክስ ትንበያዎች ክሽፈትን በተመለከተ ሲሆን በተመሣሣይ ሰዓትም የዓለም አብዮት ለምን በራሺያ መጀመር እንዳለበት የሚያስረዳ ትንታኔ ያቀርባል። ከማርክስ በተቃረነ መልኩ፣ ካፒታሊዝም በአደጉ ካፒታሊስት ሀገራት ውስጥ የመውደቅ ወይም የመፈራረስ ብልጭታ አይታይበትም ነበር፤ መደባት ፅንፍና ፅንፍ እየሆኑ አልነበረም፤ መካከለኛው መደባት እያደጉና የሠራተኛው መደባት ደግሞ ይበልጥ እየበለፀጉ ነበር። ይህንን ጉዳይ በሚመለከተው ዋና ሥራው (Imperialism, the Highest Stage of Capitalism - 1916) ሌኒን መፍትሔ ያቀርባል። የ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ዋነኛ የዓለም ኃይላት አፍሪካን እና ሌሎች በቅኝ ግዛት ያልተያዙ የዓለም ክፍሎችን ለመቀራመት የሚፎካከሩበት ጊዜ ነበር። የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በመሠረታዊ መልኩ በቅኝ ግዛት ባለቤትነት ላይ ያነጣጠረ ጦርነት ነው፤ በዚህም በአሸናፊ ሀገር ውስጥ ያሉ ካፒታሊስቶች የብዝበዛ ተግባራቸውን እና ትርፋቸውን ሊያስፋፉ የሚችሉበት ነበር። ይህ የኢምፔሪያሊስቶች መስፋፋት ካፒታሊዝምን ወደከፍተኛ ደረጃው እንዳመጣው ሌኒን ይከራከራል፤

ይህም ማርክስ አስቀድሞ ሊመለከተው ያልቻለው ነበር። እናም ካፒታሊዝም ያላደገውን የዓለም ክፍል በከፍተኛ መጠን ይበዘብዛል፤ ከዚያም የሚያገኘውን ትርፍ የሀገር ውስጥ የሠራተኛ መደቡን በከፍተኛ የኑሮ ደረጃና በማህበራዊ ዋስትና ለማባበል ወይም ዝም ለማሰኘት ጥቅም ላይ ያውለዋል። በዚህ አማካኝነትም የቅኝ ተገዢው ዓለም ተበዝባዥ ብዙሃን አዲሱ የወዝአደር ወይም የሠራተኛ መደብ ሆነዋል። ስለዚህ የኮሚኒስት አብዮት በአደገው የምዕራብ ዓለም የመከሰቱ ነገር እርግጠኛ የሚኮንበት አልነበረም።

በርግጥም በተለየ መልኩ ለአብዮት ዝግጁ የነበረች ሀገር ራሺያ እንደሆነች ሌኒን መከራከሪያውን ያቀርባል። በኢኮኖሚዋ ያደገች አልነበረችም፣ ሠራተኞቹም በማባበያ አልተያዙም፣ እንዲሁም በአብዛኛው በውጭ ካፒታል የሚደጎመው ኢንዱስትሪዋ በካፒታሊስት ኢምፔሪያሊዝም ሰንሰለት ውስጥ ‘ደካማው ማስተሳሰሪያ’ ነበር። እናም በራሺያ የሚካሄድ አብዮት በተቀረው ዓለም ሊንሰራፋና በአጠቃላዩ ሥርዓት ላይ መደርመስን ሊያስከትል የሚችል ሂደትን ይጀምር ይሆናል።

የዛሪስት ሥርዓት በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ውጥረት በፌብርዋሪ ወር 1917 ተደረመሰ፤ የሌኒን ቦልሼቪክስም ትሮትስኪ ተቀላቅሎበት በኖቬምበር ወር ሥልጣኑን ተቆናጠጠ (በወቅቱ በጥንቱ የራሺያ የቀን አቆጣጠር መሠረት ኦክቶበር ወር ነበር፤ በዚህም “የኦክቶበር አብዮት” ይባላል)። የቦልሼቪክ ፓርቲ “የሶቪየት ሕብረት ኮሚኒስት ፓርቲ” የሚል ስያሜውን ያዘ። አንዴ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ፣ ሌኒን አርሶአደሩን እና ሠራተኛውን መሬት እና ፋብሪካዎችን እንዲቆጣጠሩ አበረታታቸው፤ እርሱም ሁሉንም ተቃዋሚ ፓርቲዎች አፈናቸው (ገደባቸው)። “What Is To Be Done?” መፅሐፉ ላይ የሰፈሩት የአብዮታዊ ፓርቲ መርሆዎች የገዢውም ፓርቲ መርሆዎች ሆኑ። ከዚህም አልፈው ሌኒን በ1919 በመሠረተውና ሁሉም አባል ፓርቲዎች የእርሱን አስተምህሮዎች እና የእርሱን የፓርቲ አደረጃጀት እንዲቀበሉና ለሶቪየት ሕብረት አመራር እውቅና እንዲሰጡ በማድረግ ቁጥጥሩን ባሳረፈበት “Communist International” (“ኮምኢንተርን”

በመባልም ይታወቃል) የዓለም የኮሚኒስት ፓርቲዎች ስብስብ ላይም መርሆዎቹ ተፈፃሚ ሆነው ነበር። የእርስ በርስ ጦርነት እና የውጭ ኃይል ጣልቃገብነት ይኑርባት እንጂ ሌኒን በ1924 ህይወቱ ሲያልፍ ሶቪየት ሕብረት ተመስርታ ቆይታ ነበር።

የሌኒን ማርክሲዝም-ሌኒኒዝም በመባል የሚታወቀው የማርክስ ፅንሰ-ሀሳብ ብቸኛ ትርጓሜ እና ማፋፊያ ነበር ኋላ የሶቪየት ሕብረት እና የሁሉም የተከታይ ኮሚኒስት ሥርዓቶች ኦፊሴላዊ አስተምህሮ ለመሆን የበቃው (ምንም እንኳን በቻይና እንደሆነው ሁሉ አንዳንድ ጊዜ ሀገር በቀል ንጥረ ነገር ቢጨመርበትም)። ‘ኮሚኒዝም’ በማለት የሚታወቀው የማርክሲዝም ዓይነት ሲሆን እስከ 1960ዎቹ ድረስም ብቸኛው

ያልተበረዘው የማርክሲዝም ዓይነት ነበር። ብቸኛው ትክክለኛ ማርክሲዝም የሚል ስም ማግኘቱ በቀላሉ የሌኒን ስኬት ውጤት ነው። ማርክሲዝም-ሌኒኒዝም በርግጥም በማርክስ የኋላ ሥራዎች እና በተለይም በኤንግልስ ታዋቂ ማብራሪያዎች ላይ የተመረኮዘ ድፍድፍ የሚሰኝ የማርክሲዝም ዓይነት ነው። በኢኮኖሚ ወሳኛዊነት (determinism) ላይ ከፍተኛ አፅንዖት በመስጠት በጣም የተዋቀረ ነው። ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ከላይ የሚነሳ ግትር ቁጥጥርን ከሚያካትተው የፓርቲ አደረጃጀት መርህ አንስቶ ፓርቲው ወሳኝ የሚባሉትን ማህበራዊ አደረጃጀቶች እስከሚቆጣጠርበትና የትኛውም ተቃዋሚ እስከሚገደብበት የህብረተሰብ አደረጃጀት መርህ የሚደርስ ነው። ይህም አምባገነናዊ የአንድ ፓርቲ መንግስትን በመፍጠር በሁሉም የተቀሩት የኮሚኒስት ሥርዓቶችም የሚታይ ነበር።

ከማርክሲስት አንፃር ይህንን ምክንያታዊ የሚያደርገው በማርክስ ፅንሰ-ሀሳብ ላይ የተገለፀው “የወዝአደሩ አምባገነናዊነት” ነው፤ ይህም ሙሉ ለሙሉ ኮሚኒዝም እስከሚሰፍን ድረስ ሠራተኛው መደብ የሚገዛበት (ሥልጣን የሚይዝበት) ጊዜያዊ የሂደት ደረጃ እንደሆነ ተመልክቷል። በሌኒን ፅንሰ-ሀሳብ ፓርቲው ወዝአደሩ ነውና፣ የወዝአደሩ ፊታውራሪ ነውና በተቀረው ሠራተኛ ስም የመግዛት መብት አለው። ሌሎች ምክንያታዊ አድራጊ ሀሳቦችም ከዲሞክራሲ መሠረቶች አንፃር ቀርበው ነበር። መድብለ ፓርቲ ሥርዓት የመደብ ክፍፍልን ያንፀባርቃል ተብሏል፤ ይህ ደግሞ በኮሚኒስት ሀገራት ዘንድ አይገኝም፤ እናም ኮሚኒስት ፓርቲው ብቻውን የሕዝቡን ፍላጎቶች መወከል ይችላል። እንደዚህ ባሉ መከራከሪያዎች ምክንያት ነበር የኮሚኒስት ሥርዓቶች ከሊበራል ዲሞክራሲዎች በተለየ እራሳቸውን “ሕዝባዊ ዲሞክራሲ” በማለት የሚጠሩት፤ ይህም ሕዝቡ እውን የሆነ ሥልጣን ስላልነበረው የይስሙላ እንደሆነ ተደርጎ ተቀባይነትን አላገኘም።

በሌላ በኩል የኮሚኒስት ሥርዓቶች “የሠራተኞች መንግስታት” ነን ቢሉም እራሳቸውን የኮሚኒስት ህብረተሰብን ከማምጣቱ ግብ ረጅም እርቀት ላይ እንደሚገኙ አድርገው ይመለከታሉ። ሌኒን በ1917 ሥልጣን ሲጨብጥ የሌሎች ሀገራት ሠራተኞች

የራሺያን መሪነት ካልተከተሉ በቀር የእርሱ አብዮት ሊሳካ እንደማይችል አምኖ ነበር። በርግጥ ይህ ሊሆን አልቻለም። ከማርክሲስት እሳቤ አንፃር ሁሉም ኮሚኒስት ሀገራት በሽግግራዊው የወዝአደሩ አምባገነንነት ሂደት ውስጥ ሰጥመው ቀርተዋል (ይህም ማርክሲስቶች አንዳንድ ጊዜ ግራ አጋቢ በሆነ መልኩ ከመጨረሻው የሂደት ደረጃ፣ ከኮሚኒዝም በመለየት “ሶሻሊዝም” በማለት በሚጠሩት ማለት ነው)፤ እናም በጠላት ካፒታሊስት ሀገራት እስከተከበቡ ድረስ እጅግ ጠንካራ መንግስት ይዘው መቀጠል ይገባቸዋል። የተቀረው ዓለም የራሱን አብዮት ሲያካሂድና የቀደመውን ሲደርስበት ብቻ ነው የሰው ዘር ወደእውነተኛው የኮሚኒስት ህብረተሰብ በአንድነት

የሚያድገው።በየትኛውም ቦታ ባለ

የኮሚኒስት ሥርዓት ላይ የሌኒን የፊታውራሪ ፓርቲ ፅንሰ-ሀሳብ እስካሁንም ተፅዕኖ አለው። ይሁንና ቢያንስ ከ1960ዎቹ ጀምሮና በተለይም ከአውሮፓዊ ኮሚኒዝም መፈረካከስ (1989-91) አንስቶ በብዙ የምዕራቡ ማርክሲስቶች ሲተች ቆይቷል። ማርክስ በሠራተኛው ስም ሥልጣን ስለሚይዙ ልሂቃን የማይጨበት እሳቤ ሳይሆን፣ አጠቃላዩ የሠራተኛ መደብ ትምህርት መማርና ለአብዮቱም ግለ-ንቃተህሊና ኖሮት ዝግጁ መሆን እንደሚያስፈልገው በግልፅ አስተምሯል። በተጨማሪም ሜንሼቪኮች ራሺያ ትክክለኛ የወዝአደር አብዮት ለማካሄድ እጅግ ኋላ ቀር እንደነበረች ባስረገጡ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ትክክል እንደነበሩ ብዙዎች አሁን ድረስ ይከራከራሉ። ሆኖም እነዚህ ሁሉ በማርክሲዝም ውስጥ አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው።

ይሁንና ግን ኢምፔሪያሊዝምን የሚመለከተው ፅንሰ-ሀሳብ በማርክስ ትንበያዎች አለመሳካት ላይ የሚሰነዘሩ ተቃውሞዎችን መክቷልና በሁሉም ማርክሲስቶች ዘንድ የተሰጠውን ቦታ አልለቀቀም። የምዕራቡ የቅኝ አገዛዝ ሥርዓት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ቢያከትምም እስካሁን ድረስ ተቀባይነቱ ሰፊ ነው። ለዚህም መከራከሪያው ምንድነው፣ በግላጭ ይካሄድ የነበረው የፖለቲካ ቁጥጥር ያለፈ ቢሆንም ሦስተኛው ዓለም አሁንም ድረስ በምዕራቡ ካፒታሊስት ተፅዕኖ እያደረበትና እየተበዘበዘ ነው፤ የአሁኑ ግን የሚለየው ይበልጥ ጥበባዊ በሆኑ ኢኮኖሚያዊ ዘዴዎች አማካኝነት መሆኑ ብቻ ነው። ሆኖም የተወሰኑ ሀገራት፣ በተለይም የሩቅ ምስራቅ ሀገራት በ20ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ አካባቢ እየበለፀጉ ሲመጡ ፅንሰ-ሀሳቡ የተወሰነ ኃይሉን አጥቷል፡- ፅንሰ-ሀሳቡ የኋለኞቹ ቀናት ኢኮኖሚያዊ ኢምፔሪያሊዝም ይህንን (መበልፅግን) ሊከለክል እንደሚችል ይጠቁማል።

በቅርብ አሥርት ዓመታት የኮሚኒዝም ክሽፈቶች ወይም ለስኬት አለመብቃት የሌኒንን ዝና ሸርሽሮት ቆይቷል፤ ያም ሆኖ ግን ሌኒን የዘመናዊ ኮሚኒዝም መስራች እንደመሆኑ መጠን የሃያኛው ክፍለዘመን እጅግ ወሳኝና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት መካከል የሚመደብ መሆኑ አልቀረም።

ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ከላይ የሚነሳ ግትር ቁጥጥርን ከሚያካትተው የፓርቲ አደረጃጀት መርህ አንስቶ ፓርቲው ወሳኝ

የሚባሉትን ማህበራዊ አደረጃጀቶች እስከሚቆጣጠርበትና የትኛውም ተቃዋሚ እስከሚገደብበት የህብረተሰብ አደረጃጀት መርህ

የሚደርስ ነው። ይህም አምባገነናዊ የአንድ ፓርቲ መንግስትን በመፍጠር በሁሉም የተቀሩት የኮሚኒስት ሥርዓቶችም የሚታይ ነበር።

““

Page 7: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ አቤቶ ወግአቤ ቶክቻው[email protected]

ሰ ሞ ን ኛአንድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ሰሞንኛ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ከዕሁድ እስከ ዕሁድ የሚያገለግል ሰው››

ሲል ይተረጉመዋል። እኔም የሰማሁትን ላሰማዎ፣ ያየሁትን ላሳይዎ፣ ትጉ ሰሞነኛ አገልጋይዎ መሆንን ወደድሁ።

እን ዴ ት ሰነ በታችሁ ! ? እኔ ሰሞነኛ አገልጋያችሁ፤ ያ ው እንደተለመደው እንዳለሁ አለሁ፡፡ ያውም በፅኑ እ ን ደ ተ ጋ ሁ

አለሁላችሁ፡፡ የሆነው ሆኖ፣ ልክ እንደአርቲስቶቻችን ‹‹እንደሚታወቀው›› እያልኩ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሰኞ ትጉ መሆኔን መደስኮር ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ የሚታወቀውማ የታወቀ ነውና ወደማይታወቀው ነገር ነው ማለፍ ያለብኝ፡፡

ስለዚህ እኔ ሰሞነኛ አገልጋያችሁ፤ የያዝነው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን በሆነው ዕለተ ሰኞ የነበረኝ ትጋት ከዚህ በፊት የማይታወቅልኝ ትጋት መሆኑን የምነግራችሁ ለአገልግሎቴ ‹‹የምስጋና ቀን›› እንድትሰይሙልኝ ፈልጌ አለመሆኑን አስቀድሜ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ፡፡ ለኔ አገልግሎት የምስጋና ቀን ከሰየማችሁልኝማ፣ አርቲስቶቻችን የኪነ-ጥበብ ቀን እንዲሰየምላቸው ካቀረቡት ጥያቄ ጋር ሲደመር፣ በዚህች አገር አንድም ስየማ-አልባ ቀን አይኖርም ማለት ነው፡፡ ስም ሳይሰጠው እንዲሁ ‹‹የሥራ ቀን›› የሚባል ሊጠፋ እኮ ነው።

የኪነ-ጥበብ ቀን፣ የስኳር ቀን፣ የዘይት ቀን፣ የእገሌ ቀን፣ ወዘተ እያልን ከቀጠልን የዓመቱን ቀናቶች በማክበር (ይቅርታ ለመፎጋገር) ካዋልነው፣ አገሪቱ በአጠቃላይ የሥራ ፈቶች ልትሆን ነው፡፡ እኔ ደግሞ ሀገሬ የሥራ ፈትነትና የሥራ ፈቶች እንድትሆን አልፈልግም፡፡ ጎበዝ! ዓባይን በገንዘባችንም በጉልበታችንም ገድበን ሀገሪቱን ወደላቀ ዕድገት እናሸጋግራታለን ብለን ቆርጠን በተነሳሳንበት ወሳኝ ወቅት፣ ከዓመቱ

የሥራ ቀናቶች አንዱን፣ የሆነ ዓይነት በዓል ለማክበርና ሥራ ለመፍታት መጠየቅ፣ በዓባይ ጉዳይ ላይ ‹‹አባይ›› (ላላ ተደርጎ ይነበብ) መሆን አይደለም እንዴ!?

ጎበዝ! ስለሰኞ ቀን ትጋቴ ለማሳወቅ ስል የዘበራረቅሁ ከመሰላችሁ፣ ‹‹እንደአርቲስቶቻችን ከመዘባረቅ ይሰውርህ›› ብላችሁ እንደምታልፉኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሆኖም እንደዚያ እስከምባል የምጠብቅ አይደለሁም፡፡ ንቁ ነኛ! ንቁ ብቻ ሳልሆን፣ ‹‹ነቄ››ም ነኝና በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ እዘልቃለሁ፡፡

እናላችሁ! ዕለተ ሰኞ ለእኔ ከትጋቶች ሁሉ የላቀ ትጉ አድርጎኝ ነው ያለፈው። እንደሚታወቀው እንደሌላው ስንከወከው አርፍጄ ደከምከም ሲለኝ ለመነቃቃት ያህል ቡና ቢጤ ነገር ፉት ማለት ፈልጌ ወደ አንዱ ሆቴል ጎራ ስል፣ ሕዝቤ ሁሉ ዓይኑን ቴሌቪዥን ላይ ተክሎ በትኩረት ይከታተላል፡፡

ይኼን ጊዜ እኔ ሰሞነኛ አገልጋያችሁ ‹‹ኢቴቪ ያልለመደበትን ምን ዓይነት ሰበር ዜና ይዞ ቢቅርብ ነው›› ብዬ ዓይኔን ወደ ቴሌቪዥኑ! ማመን አልቻልኩም፡፡ የሆነ ነገር ያጥበረበረኝ ስለመሰለኝ ዓይኖቼን በመዳፎቼ አሻሽቼ መልሼ ወደ ቴሌቪዥኑ ላክኋቸው፡፡ አልተሳሳትኩም፤ እሳቸው ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ናቸው፡፡ ዘና ብለው የአርቲስቶቻችንን ድራማ እየኮመኮሙ አየኋቸው፡፡ ይኼኔ ደስ አለኝ፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ፤ በጣም ነው ደ…ስስስስ ያለኝ፡፡

ይህቺን አገር ለማቅናት ካለአንዳች እረፍት 20 ዓመት ሙሉ ቀና ደፋ፣ ላይ ታች ሲሉ ካለመታከት ሲባክኑ የኖሩት ጠቅላይ ሚኒስትራችን፣ እንዲህ ጊዜ አግኝተው ‹‹እፎይ›› ብለው ድራማ እየተመለከቱ ሲዝናኑ ሳያቸው ደስ ያላለኝ መቼ ደስ ሊለኝ ነው!? እናም ደስ ነው ያለኝ፡፡

ከዚያስ!? አትሉኝም፡፡

ከዚያማ፤ በአገራችን አሉ የሚባሉት አርቲስቶቻችን በጠቅላይ ሚኒስትራችን ፊት መድረኩ ላይ ተረማመዱበት፡፡ አንዱ ብዕር፣ ሌላው ወረቀት፣ ሌላው ቡርሽ፣ ሌላው ካሜራ፣ እንደው በጥቅሉ የሙያ መገለጫ መሣሪያቸውን ይዘው፣ አንዷን አርቲስት በፈረደባት ኢትዮጵያ መስለው፣ በጠቅላይ መሪያችን የአመራር ዘመን የሀገራችን ኪነ-ጥበብና የኪነ-ጥበብ ሰዎች ያሉበትንና የሚገኙበትን ደረጃ እየተዋነዩ ገለጡላቸው፡፡ ገለጡላቸው ብቻ ሳይሆን፣ ዓይናቸውን በዓይናቸው እያሳዩ አሳቋቸው፡፡

ይኼኔ እኔ ሰሞነኛ አገልጋያችሁ፣ ‹‹እሰይ! አርቲስቶቻችን ጠቅላይ ሚኒስትራችንን አሳቋቸው›› ብዬ በእሳቸው ደስታ መደሰቴን ገልጬ ሳልጨርስ፣ አንዱ የኔ ቢጤ የቴሌቪዥን ተመልካች ‹‹መች አሳቋቸው፤ አስፋሸኳቸው፣ አሳቀቋቸው እንጂ›› ሲል ተናገረ። እዚህ ላይ ባይሳሳትም ምናልባት ሊሳሳት እንደሚችል ጠቆምኩት። ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንኳን ብዕር፣ ወረቀት፣ ቡርሽ፣ ጊታር፣ ክራር ምናምን ታጥቆ በባዶ መድረክ ለሚጯጯህ አርቲስት ይቅርና የሌላቸውን አለን እያሉ በሩቁ ለሚያቅራሩ የባዕዳን ኒዮ-ሊበራል ‹‹አቀንቃኞች›› ፉከራ የማይሳቀቁ መሆናቸውን አውቃለሁና ምንም ላለማለት ወስኜ ዝም አልኩ፡፡

በቃ! የዚያን ክፉ አሳቢ አነጋገር ችላ አልኩና ድራማቸውን አጣጣምኩ፡፡ ድራማው እንዳለቀ አርቲስቶቻችን ጥያቄ ነው የሚሉትን ጥያቄ ሁሉ ሲያዥጎደጉዱት ‹‹ለእኔ ብዬ›› ከልብ አደመጥኩ፡፡ የኋላ ኋላ ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንደ ልማዳቸው ሊያውም በወርሃ ግንቦት የመጨረሻ ቀን መድረኩን ተቆጣጠሩት፡፡ ምን መድረኩን ብቻ፣ አርቲስቱን ሁሉ ተቆጣጠሩት፡፡ ታዲያ ይኼ ደስ አይልም!?

ግን ምን ዋጋ አለው!? ከእኔ

ጋር ታድመው የአርቲስቶቻችንን እና የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ውይይት በቴሌቪዥን የሚከታተሉ አንዳንድ ሰዎች ግን ሻዕቢያና ተላላኪዎቻቸውን ነጭ ለባሾች ይመስል ምንም ነገር የሚጥማቸው አልሆኑም፤ ምን አለፋችሁ፤ ከውይይቱ የማይነቅሱትና የማይነቅፉት ምንም የቀራቸው ነገር አልነበረም፡፡ ታዲያ እኔስ ማነኝና ‹‹እህ›› ብዬ ሰማኋቸው፡፡ ልብ ብዬ አዳመጥኩና ነገራቸውን ሰነቅሁላቸው፤ ሰነቅሁ ሰነቅሁና ይኸው ለእናንተ አቀብላቸው ዘንድ አገልግሎት ላይ አዋልኳቸው፡፡ እናም፣ ከሰማሁላቸው አንዳንዱን፣ አለፍ አለፍ እያልኩ ልንገራችሁ፡፡

ታስታውሱ እንደሆን፣ ድራማውን በሚታይ ጊዜ ወረቀት ስለተወደደ ከሀገር ለመሰደድ ግድ መሆኑ የሚጠቀስበት ትዕይንት ነበር። ወዲያውም ‹‹ይኸው ነው የኛ ነገር፤ እንዲህ ወረቀት ተወደደ ብሎ ከሀገር ይወጣል፣ ከወጣ በኋላ ደግሞ የለየለት ተቃዋሚ ይሆናል፤ ወደልማት አይሰማራም? ከዚህ በላይ ነጭ ለባሽ የታለ?›› የሚል ‹ልማታዊ› ትችት አብረውኝ ቴሌቪዥን ከሚመለከቱት ሰዎች መካከል ተሰነዘረ። ምላሽ ግን አላጣም፣ ‹‹ነጩን ያለበሰው ማን ሆነና?›› የሚል ‹ፀረ-ልማታዊ› የመልስ ምት ከወዲያ ተሰነዘረ። ጊዜው መጥፎ ነበርና ስንዘራው በአጭሩ ሲቋጭ፣ እኔ ሰሞንኛ አገልጋይዎ ደግሞ ድምፅ አውጥቼ ‹‹ኡፍ…!›› አልኩኝ።

ትንሽ ቆይቶ ግን ሌላ ጥቆማ ብቅ አለልዎ፤ ‹‹የድራማው ደራሲ እኮ አጠገባቸው ነው›› የሚል። ይኼኔ ያ ልማታዊ ትችት ሰንዛሪው ‹‹ድሮም እኮ የዚህ መንግስት ችግሩ የቅርቡን ችላ ብሎ የሩቁ ላይ ማተኮሩ ነው›› እያለ ፀረ-ልማታዊ ተቺው ላይ ማፍጠጥ ጀምሯል። እኔ ደግሞ ምን ቀን እዚህ ቤት አመጣኸኝ፣ ምነው ጆሮዬን በደፈነው እያልኩኝ የሚባባሉትን ላለመስማት እየጣርኩልዎት ነው። በዚህን ጊዜ የእጅ ስልኬ ተንጫረረችና

በድጋሚ ‹ኡፈይ…› አልኩኝ፡፡ ስልኬን አንስቼ ጆሮዬ ላይ

ስደግነው፣ ደዋዩ ከወዲያኛው ጫፍ ከዚያው ከአርቲስቶቹ ስብሰባ መሀል እንደሚገኝ ነገረኝና ‹‹ስብሰባችንን እየተከታተልክ ነው ወይ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ እኔም ልብ ብዬ እያየሁ መሆኑን አስረገጥኩለት፡፡ ‹‹አምባሳደሩ ሰብሳቢያችን ‹ሁለት ደቂቃ ቀረ› ብሎ ሲናገር ምን እንደተባለ ልነግርህ ነው የደወልኩልህ›› አለኝ፡፡ ‹‹አምባሳደሩ›› ሲል ግር ብሎኝ ነበር። ኋላ ግን የመድረኩ መሪ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በአምባሳደር ማስታወቂያዎች ስለሚታወቅ መሆኑ ትዝ አለኝ።

ታዲያ ‹ሁለት ደቂቃ› እያሉ ሰዓት እንዲቆጠብ ማድረግ በዛሬ ጊዜ ምን አስብሎ እንደሆን መስማት እንደምፈልግ ገለፅኩለትና ቀጠለ። እናም ሠራዊት ‹‹አፈ-ጉባኤ ተሾመ ቶጋ›› እየተባለ በገዛ የሙያ አጋሮቹ ሲወረፍ እንደነበር አጫወተኝ። ለካንስ እሳቸውም አምባሳደር ናቸውና። እናልዎ አርቲስት፣ አምባሳደርና አፈ-ጉባኤ ሠራዊት ይህን ቢሰማ ምን ይል ይሆን?

ብቻ ይህ አርቲስት-ነክ ወዳጄ የዘነጋው ነገር የአሁኑ አፈ-ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ መሆናቸውን ነው። አዎ፣ ናቸው! በፓርላማው ከታዩ ሰነባበቱ እንጂ፣ አሁንም አፈ-ጉባኤ ናቸው። እስካሁን ምንም መረጃ የለኝማ!

እናላችሁ! እኔ ሰሞነኛ አገልጋያችሁ፤ በዚህና በዚያ ነገር እየገረመኝ ሳለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከነዚሁ አርቲስቶች የወርቅ ብዕር ተሸለሙ። ታዲያ ይኼን ጊዜ፣ ‹‹አርቲስቶቹ ምን እያሉ ነው፣ በኮፒ ራይት ምናምን ገቢያችን ተመናመነ፣ መታከሚያ አጣን፣… እያሉ አልነበር እንዴ? ታዲያ ይህን የወርቅ ብዕር ከየት አምጥተው ነው?›› የሚሉ ጥያቄዎች ሳላስበው አመለጡኝ። ያ አብሮን እየተመለከተ ሲያፌዝ የነበረው ሰውዬም ዞር ብሎ ገረመመኝና፣ ‹‹በጥቃቅንና አነስተኛ

ካተረፉት የተረፋቸው ነው›› ብሎ ሰለቀ።

አሁን እያሰብኩት መጠየቅ ጀምሪያለሁ፣ ‹‹መቼ ነው ደግሞ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁት?›› አልኩት። ፌዘኛው መልስ አያጣም ለካስ፣ ‹‹እንደነሱ የልማት አርበኛ አለ እንዴ? ድህነትን ‹‹ጃስ›› ብሎ በማስፈራራት ሊያጠፉት የሞከሩት እነሱው አልነበሩ እንዴ?›› በእውነት ነው የምላችሁ አንዳች ቂም አርግዞባቸዋል። የከንፈሩን አነካከስ ብትመለከቱት ዘጠኝ ወር ሁሉ የሚጠብቅ አይመስላችሁም። ቀጠለ፣ ቀጠለና በመጨረሻም፣ ‹‹በቅርቡ የኢህአዴግ ደጋፊ አርቲስቶች ማኅበር እንደሚመሰረት አትጠራጠር›› ብሎኝ አረፈው።

ይልቁንስ እጅግ የሚደንቀው፣ አርቲስቶቹ ከርዕሰ መስተዳደር ጋር ይቅርና ከቀበሌ የሥራ ሂደት ባለቤት ጋር የሚያወሩ እንኳን አለመምሰላቸው ነበር። የነበረው ‹‹ሰፋጣ›› አልገረማችሁም? እንዴት ነው ነገሩ፣ ሰውየው እኮ የሀገር መሪ ናቸው፡፡ ለዚያውም በኑሮ ውድነቱ ምክንያት መሪር ሐዘን ውስጥ የገባ የ80 ሚሊዮን ሕዝብ መሪ። ታዲያ ለ80 ሚሊዮኖቹ መሪ፣ እፍኝ የማይሞሉ አርቲስቶች በኩርማን አዳራሽ ሰብሰብ ብለው፣ ለዚያውም ድፍን የአገር ሰው በሰፊው ሚዲያ እያያቸው ‹‹ዛሬ በእጃችን በመዳፋችን ገብተዋል። ጥያቄችንን ካልመለሱ አንለቅዎትም›› ዓይነት ንግግር መተርተር ምን የሚሉት መሳፈጥ ነው!? እኔ ይህንን ብልም አንድ ወዳጄ ግን፣ ‹‹ዝም በላቸው ያውሩ፣ ሰውየው እንኳን በጥቂቶች መዳፍ ይቅርና በ80 ሚሊዮን መዳፍም ሊገቡ አልተቻለም›› አይለኝ መሰልዎ።

በሉ እንግዲህ ጎበዝ፣ እኔ ሰሞነኛ አገልጋያችሁ፣ አንዴ ካመረርኩ መመለሻ የለኝምና ብሰናበታችሁ ነው የሚሻለው፡፡ ደህና ሰንብቱልኝ አቦ!!

ግንኙነት እጅግ ሻክሮ ታይቷል። በሺህዎችም ዘብጥያ ወርደው ነበር።ሌፍትዊች እንደሚለው ድህነት ቅነሳ በመጀመርያ የፖለቲካ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ፖለቲካው በተመሰቃቀለበት፣ የእድገት አንድነት በሌለበት የተቋማት ነፃነትና የኅብረተሰቡን ፍላጎት በማያካትቱበት ሁኔታ ልማት እንደማይመጣም ይሞግታል።ይህም ፖለቲካን ወደቀደመ ስፍራው የመመለስ የሚጠይቅ ስራ ነው። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች የጨዋታ ሕግ የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ ለልማትና ዴሞክራሲ ሚናው ቀዳሚ መሆኑን ያስቀምጣሉ። በፖለቲካው ጨዋታ ውስጥ ሁለት ዓበይት የተለያዩ ነገር ግን እጅግ የተቆራኙ ደረጃዎች ይጠቀሳሉ። እነዚህም የጨዋታ ሕግ (ተቋማት) እና በጨዋታው ሕግ ውስጥ ያለው ጨዋታ ናቸው። የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት በጨዋታው ሕጎች ስምምነት የተመሰረተ ነው። ስለሕጎቹ አይነትና ባህርያትና እንዴት እንደሚቀየሩ መስማማት የጨዋታው ጅማሮ ነው። የጨዋታው ሕጎች ምን አይነት ተቋማትና ሂደቶች ስለመኖሯቸው የሚናገሩ በመሆናቸው ለጨዋታው ወሳኝ ናቸው።የጨዋታውን ሕጎች በተመለከተ ኢህአዴግ ሁሌም የሚያወጣቸው ሕጎች ከፍተኛ የሆነ አለመስማማታና ብሎም ኃይለኛ ተቃውሞ የሚያስተናግዱ ናቸው። ከሕገመንግስቱ ጀምሮ የፀረ-ሽብር ሕግ፣ የሚዲያ ነጻነት አዋጅ፣ የሲቪክ ማሕበረሰቡ በተመለከተ የወጡትና ሌሎች በርካታ ሕጎች ከፍተኛ የሆነ ሀገራዊ የስምምነት እጦት የሚታይባቸው ናቸው። እንደ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ፀረ-ሙስና ፓርላማው እንዲሁም የፍትሕ አካላቱ በተቀዋሚዎችና በፖለቲካ ክበቡ ውስጥ ባሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ አለመተማመን የነገሰባቸው ሆነው ይስተዋላሉ። ይህም የዴሞክራሲ ሂደቱን ክፉኛ አቀጭጮታል።

ተግዳሮቶቹኢህዴግ ከሽግግር መንግስቱ ጀምሮ ልማታዊ መንግሥት ለመሆን በርካታ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አካሂዷል። ግንባሩ እንደሚለው ‹‹ከኢህአዴግ ያለፉ አመለካከቶች የተሸጋገሩ ቅሪቶች፣ ከነባራዊ ሁታዎች የመነጩና በከፊልም ቢሆን ከልማታዊ መንግሥታት ልምድ የተገኙ አመለካከቶች አንድ ላይ ተደርገው ጉራማይሌ አስተሳሰብ የተያዘበት ወቅት ነበር ማለት ይቻላል ... በወቅቱ ከጠራ የልማታዊነት አመለካከት የመነጩና ለዚሁ ዓላማ በአግባቡ ጥቅም ላይ የዋሉ አልነበሩም›› ይላል።ለዚህም ግንባሩ የጠራ አቋም ማጣቱና ልማታዊ መንግሥት የሚፈልጋቸውን ነገሮች አሟልቶ አለመያዙ ዋነኛ ችግሩ ነው። ምንም እንኳን ጥቂት እድሎች ቢኖሩም፣ በርካታ አጥኚዎች የኢሲያ የልማታዊ መንግሥታት በ21ኛው ክ/ዘመን መደገማቸውን ይጠራጠራሉ። ተንታኞች ይህንን ‹‹ያለመቻል ምክረ-ሃሳብ›› ይሉታል። ለዚህም የተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶችን ያነሳሉ። በአብዛኛው የሚያነሱት አንዱ ነጥብ የቀዝቃዛው ጦርነትን ማብቃት ተከትሎና የግሎባላይዜሽን መስፈን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደየዓለም ባንክ፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ንግድ ድርጅት በኩል ኒዮሊበራሎች ፖሊሲዎቻቸውን ለማስፈፀም ቀላል እንደሆነላቸውና የካፒታል ዝውውርን ያወሳሉ። የኢተዮጵያ መንግሥት የተለያዩ የመዋቅራዊ ማሻሻያዎችን በመውሰድ በተወሰነ ደረጃ ገበያውን ክፍት የማድረግ ተግባር በዓለም ባንክና በዓለም የገንዘብ ፈንድ ተፅዕኖ አካሂዷል። አንዳንዶች በቅርቡ የተካሄደው የብር ምጣኔ ከዶላር አንጻር መቀነስን ከዚሁ ጋር ያያይዙታል። አሁን ደግሞ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በሂደት ላይ ነው። ይሁንና ድርድሩን በጥንቃቄ ካላካሄደና ከፍተኛ የሆነ የቀረጥ ቅነሳ ካስተናገደ እንዲሁም አዳጊና ትኩረት የሚሹ ኢንዱስትሪዎቹንና ዘርፎቹን ከውጭ ውድድር ካልተከላከለ የልማታዊ መንግሥትን በተግባር ለማዋል ይቸግረዋል።ሌላው ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ የዴሞክራሲ መስፋፋትን ተከትሎ እንደቀድሞው ኢኮኖሚያዊ እድገት ከዴሞክራሲ ይቀድማል የሚለው እሳቤ በአብዛኛው ውድቅ መሆንና ይልቁንም ዴሞክራሲ ለኢኮኖሚ እድገት ቅድመ ሁኔታ ነው የሚለው ሃሳብ መስተጋባትንና ሁለንተናዊ ተቀባይነት ማግኘትን ያነሳሉ። ለዚህም አሁን በአረቡ ዓለም የሚስተዋለው አመፅ አንዱ የዚህው ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ደግሞ ለግንባሩ እጅግ ግዙፍ የሆነ ፈተና

እንደሚሆን ይጠበቃል። ዴሞክራሲያዊ ለውጦችን ማድረግ ካልቻለና ሰብዓዊ ነፃነቶችን ካልተንከባከበ የልማት እስክስታውም ሊገታ እንደሚችል ተችዎች ያስረዳሉ። ኢዴጂ በትክክል እንዳስቀመጠው፣ ትላልቅና ጨቋኝ መንግሥታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት የሚያስመዘግቡ ቢሆን ኖሮ፣ የአፍሪካ መንግሥታት ቀዳሚ በሆኑ ነበር። እንደእርሱ የአፍሪካ መንግሥታት ልማታዊ ለመሆን የሚያስቡ ከሆነ ያላቸው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው - ዴሞክራሲን በመቀበል ላይ ብቻ የተመሰረተ።ሶስተኛው፣ ተቋማትን የመኮረጅ አስቸጋሪነት ነው። ተንታኞች እንደሚሉት የኢሲያው ተቋማት በአንድ ወቅት ሀገራቱ የፈጠሯቸውና የራሳቸው ሂደት ውጤት በመሆናቸው ሊደገሙ እንደማይችሉ ሶስት ምክንያቶችን ያነሳሉ። የመጀመሪያው የተቋማት ችግር ሄዊት እንደሚለው፣ ‹‹አራቱ ነብሮች›› በልዩ ተቋማቸው፣ ዓለም አቀፍና ጂኦግራፊያዊ ሁኔታዎች ምክንያት ሊደገሙ እንደማይችል ይሞግታል። ሌላው ከኢሲያውያን ልዩ የሆነው ማኅበራዊ ባህልና ልማድ በዋናነት ይጠቀሳል። ይህም ሀገራቱ በከፍተኛ ደረጃ በኮንፊሺያን እሴቶች (Confician Values)፣ ትምህርት፣ ጠነካራ ሰራተኝነትና ታታሪነት (Meritocracy) እንዲሁም እጅግ የጠነከረ የትርፋማነትና የቢዝነስ ፍቅር የመሳሰሉ ማኅበራዊ እሴቶች መገለጫቸው ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም ብቃትንና ውጤትን መሰረት ያደረገ የቢሮክራሲ መዋቅር ለመዘርጋት አስችሏቸዋል፡ተንታኞች ልሂቃኑ የአርበኝነትና ሀገራዊ ብሄርተኝነቱ የሳሳ ከመሆኑ ጋር ተያያዞ ይህ በአፍሪካ እጅግ እንደሚጎድል ያስቀምጣሉ። ከዚሁ ጋር የሚያያዘው ሌላው ተቋማቱ የተፈጠሩበት ሁኔታ እጅግ የተለየና በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ተፅዕኖ መነሻ በመሆኑ ተደጋሚነታቸውን አጠራጣሪ ማድረጉን ነው። በኢትዮጵያ ምን አልባት ከመከላከያው በስተቀር የዚህ ነጸብራቅ የሆነ ተቋም ማግኘት አዳጋች ነው።አራተኛው የመንግሥታት አመራር አቅም ማነስ ነው። አቅም የመንግስታቱን ውጤታማነት የሚወስን ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከኢሲያውያኑ ጋር ሲነፃፀር ትልቅ የአቅም ውስንነት ይስተዋልበታል። ከበጀቱ ወደ 35% የሚሆነውን የሚያገኘው በእርዳታ ላይ ጥገኛ በመሆን ነው።በአምስተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የመንግስታቱ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በነበራቸው ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎች መነሻ የፖሊሲ ነፃነታቸውን አስጠብቀው ከፍተኛ የሆነ የእርዳታ መጠን አግኝተዋል። በዚህ በኩል ከእነዚህ ሀገራት ጋር የሚስተካከል ባይሆንም በፀረ-ሽብር አጋርነቱ መንግሥት ጠቀም ያለ እርዳታ ያገኛል። ነገር ግን አብዛኛው በብድር የሚገኝና በተለያዩ ፕሮግራሞች ስር እንደ ለፀረ-ሽብር ዘመቻው፣የምግብ ዋስትና፣ ሴፍትኔት ወዘተ የሚያልፍ በመሆኑ በቀጥታ በበጀት ውስጥ የማይካተትና በኢኮኖሚው ውስጥ የሚያልፍ አይደለም። ከዚሁ ጋርም የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቹን ነፃነት የማስጠበቅ ፈተናው ከኢሲያውያኑ ጋር ሲነፃፀር እጅግ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሀኔታና የመንግስቱ ጂኦፖለቲካዊ ጠቃሚነት ደካማ መሆን ምክንያት የፖሊሲ ነፃነቱን ማስጠበቅ ትልቅ ፈተናው ነው።ኢትዮጵያን በተመለከተ ውስብስብ የሆነው የመሬት ጉዳይ ነው። እነዚህ የኢሲያ ሀገራት በውጭ ድጋፍ ከፍተኛ መሬትን ለገበሬው የማከፋፈልና ዋስትናውን የማረጋገጥ ስራ አስቀድመው ሰርተዋል። ይህም የኢኮኖሚ አቅማቸው አንዱ ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ይህንን ለማድረግ ትልቅ ፈተና ይሆንበታል። ግንባሩ በመሬት ላይ ባለው አቋም ምክንያት የገበሬው የመሬት ዋስትና መረጋገጡ ላይ ጥርጣሬ አለ። ደሳለኝ ራህመቶ፣ ‹‹The Peasant and the State: Studies in Agrarian Change in Ethiopia 1950s-2000s›› በሚል ጥናታዊ መፅሐፉ የኢትዮጵያ መንግሥት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ቢሰጥም፣ ገበሬው ስጋት እንዳለው ያስቀምጣል።በእርሱ እምነት የመሬት ዋስትና የሚረጋገጠው ባለይዞታው መሬቱን ለፈገው አላማ የመጠቀመና ኢንቨስት ማድረግ ሲችል፣ መንግስትን ጨምሮ የባለቤትነት መብቱ በየወቅቱ እንደተፈለገ የማይነሳ መሆኑ ሲሰማውና መሬቱን ከማንም ጣልቃገብነት ነፃ በሆነ መልኩ (መንግሥትን ጨምሮ) ማስተላለፍና ለሶስተኛ ወገን ጥቅም ለማግኛነት መዋዋል የቻለ እንደሆነ ያሳስባል።ሌላው ትልቁ የልማታዊ መንግስቱ ፈተና የኢንዱስትሪ ፖሊሲው ይሆናል።ባለፉት ሃያ ዓመታት የኢንዱስትሪው ከጠቅላላ ኢኮኖሚው ከ13%

የዘለለ ሽፋን የለውም። ይህ ደግሞ በኢሲያ ከታዩት ልማታዊ መንግሥታት በእጅጉ ወደኋላ የቀረ ነው። መንግሥት የግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት እንደሚከተል ይታወቃል። ይሁንና ኢኮኖሚው መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት አልቻለም። የውጭ ንግድ መሩም ቢሆን በዋነኛነት የተመሰረተው በግብርና ምርቶች ላይ በመሆኑ፣ አስተማማኝነቱ የሚያወላዳ አይደለም። ይህም ከኢሲያውያን የተኮረጀ ቢመስልም፣ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ይስተዋልበታል። በተለይ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ትኩረት ካልተሰጠና የግል ባለኃብቱን ካልሳበ፣ የኢኮኖሚው ዘላቂነትና ጥንካሬ አጠያያቂ ይሆናል። የመዋቀራዊ ሽግግር ኢኮኖሚው እያሳየ ባለመሆኑ፣ ለኢንዱስትሪው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት፣ ታዳጊና ስትራቴጂክ የሆኑ ዘርፎችንና ኢንዱስትሪዎችን በመለየት ጥበቃ በማድረግና ማበረታቻ በመስጠት መደገፍ አስቸኳይ ይሆናል።ጠንካራ የሆነና ሁሉን አቀፍ ፖሊሲዎችን የማውጣት አቅም ያለው ቢሮክራሲ ለመገንባት የትምህርት ሥርዓቱ ወሳኝነት ያለው ነው። ኢሲያውያኑ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ኮምፒውተርና ኢንጂነሪንግ ትምህርች ከፍተኛ የሆነ ትኩረት በመስጠት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙያተኞችን አፍርተዋል። መንግሥት ከዚህ በመነሳት የ70/30 የትምህርት ፖሊሲ ዘርግቷል። ነገር ግን አደገኛ የሆነ የጥራት ችግር ይስተዋልበታል።የቴክኖጂ ሽግግሩም እጅግ ደካማ ነው። ብርሃኑ አበጋዝ እንደሚለው፣ መንግስቱ የኢሲያን በተለይም የቻይናን የልማት ሞዴል ለመከተል ያልማል። ይሁንና የቁጠባና ኢንቨስትመንት መሳሳት፣ የቴክኖሎጂ ልሂቅ በጥራትና በብዛት አለማፍራትና የእርሻ ምርት አስተማማኝ አለመሆን ሞዴሉን ለመተግበር እንደማያስችለው ይገልፃል።

ልማታዊ መንግሥት ና ትችቶቹሀገራቱን በተመለከተ የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ. የ1997ቱን የገንዘብ ቀውስ ተከትሎ ባወጣው ሪፖርቱ፣ የኢሲያውያን እድገት በራሳቸው መንገድ ከሙከራቸውና ከስህተታቸው በመማር በራሳቸው የታሪክ ምራፍ ያስመዘገቡት የኢኮኖሚ እድገት በመሆኑ ተዓምር ሊባል እንደማይችል አስፍሯል። የኖቤል ተሸላሚው ኢኮኖሚስት ፖል ክሩግማን እንደሚለው፣ ሀገራቱ በተዓምራዊው የኢኮኖሚ እድገታቸው ወቅት የኢኮኖሚ ኃብታቸው ምርታማነት ደካማ የነበረ ቢሆንም፣ የካፒታል ክምችትን በመጨመርና ከፍተኛ የሆነው የሰው ኃይል ተሳትፏቸው ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት እንዲያስመዘግቡ እንደረዳቸው በመግለጽ ምንም ተዓምር እንዳልሰሩ ይሞግታል።ሌላው ደግሞ ሀገራቱ የኪራይ ሰብሳቢነት ባሕሪ የተላበሱ መሆናቸው ነው። ይህ ከፖለቲካ ልሂቁና ቢሮክራሲው ጋር በቅንጅት የተያዙ የቢዝነስ ተቋማት (Crony/Alliance Capitalism) ይጠቀሳሉ። የተባበሩት መንግሥታት የልማት ኮንፍረንስ (UNCTAD) እ.ኤ.አ 2009 ባወጣው ሪፖርቱ፣ የአፍሪካ ሀገራት ልማታዊ መንግሥታት መሆን እንዳለባቸው ቢገልፅም፣ በተለመደው በኢሲያውያን መንገድ እንዳልሆነና የመልካም አስተዳደርንና ዴሞክራሲን ባቀፈ መልኩ መሆን እንዳለበት አበክሮ አሳስቧል። ይህም የኖርዲች ሞዴልን የሴልቲክ ነብሮችን ጨምሮ መሆን እንደሚገባው ሲያስቀምጥ መንግስታቱ የፖለቲካና የቴክኒክ አቅማቸውን መገንባት እንዳለባቸው አስፍሯል።‹‹TINA››በአንድ ወቅት የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት ማርጋሬት ታቸር ከነፃ ገበያ ውጭ ‹‹ምንም አማራጭ የለም›› የሚለውን፣ የኒዮሊበራሊዝም መፈክር እስከ መሆን የበቃውን ድምጸት አሰሙ። ጠ/ሩም ‹‹TINA›› ማቆም እንዳለበትና አፍሪካውያን (በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ማለት ነው) ሌላ አማራጭ መፈለግ እንዳለባቸው በማጠቃለያቸው ላይ መክረዋል። ልማታዊ መንግሥትንም ‹‹አዲስ ጅማሮ›› ሲሉ ጠርተውታል። ይሁንና ሁሉም ሊባል በሚችል አኳኋን አፍሪካውያን ልማታዊ መንግሥትን ከድህረ-ቅኝ ግዛት ጀምሮ በተግባር ላይ ለማዋል ሞክረዋል - ምንም እንኳን ባይሳካለቸውም።ማካንድዋሬ እንደሚለው፣ ልማታዊ መንግሥታት ለአፍሪካ አዲስ አይደሉም።በዕቅድም ይሁን በፍላጎትና በተግባር፣ አፍሪካ ብዙ ልማታዊ መንግሥታትን አይታለች።የኢትዮጵያ መንግሥት ልማትን ከዴሞክራሲ ጋር አቀናጅቶ የማይሄድ ከሆነ፣ አጠቃላይ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ-ኃብታዊ እንዲሁም በተለይ ፖለቲካዊ ቀውስ ማስከተሉ የማይቀር ይሆናል።ግና ሚዲያው ልማታዊ መንግስታችን ማለቱን ተያይዞታል። ዴሞክራሲያዊ የሚለው ግን ለሚዲያ ፍጆታ እንኳን ጥቅም ላይ ሲውል አይስተዋልም። ኢህአዴግ ብቸኛው ተጨዋች መሆኑን ከቀጠለ የጨዋታው ውጤት ውሎ አድሮ የዜሮ ድምር ጨዋታ መሆኑ አይቀርም። ጠ/ሩ እንዳሉተ ‹‹TINA›› አልፎበታል፤ አማራጭ ያስፈልጋል። ነገር ግን አማራጭ የሌለው አንድ ጉዳይ አለ - ዴሞክራሲ!

የአብዮታዊ ዴሞክራሲና...

ከሰሞኑ ‹‹የኢህአዴግ ደጋፊ አርቲስቶች ማኅበር›› ሳይቋቋም አይቀርም!

Page 8: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 20038

፪ሀገር ማለት ቀላል አይደም

ከክብር ሁሉ ይበልጣልየናት ያባት የዘመድ

የሚስትን ፍቅር ያቀልጣል(አበባው መላኩ)

ሰላም ለእናንተ ይሁን!ባለፈው ሳምንት የሀገር

አደራ ለተሸከሙት የተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች ጥያቄዎችን ሰንዝሬ ነበር። የይደር ጥያቄዎቼን ለዚህ ሳምንት እንደማቀርብም ገልጨ ነበር።

እነሆም ይህንን ሳምንት በአበባው መላኩ ግጥም ጀመርኩት - ሀገርን ማገልገል ለሀገር አደራ መብቃት ምንኛ ከባድ እንደሆነ ይገልጥልኛል ብየ ተስፋ በማድረግ!

ሀገርን መረከብ አንድ ነገር ነው። ትውልድን መረከብም አንድ ነገር ነው። እንደ እናንተ ሁለቱንም መረከብ ደግሞ የበለጠ ከባድ እዳ ነው። ብርቱ ልትሆኑ ይገበል። ይህንንስ እዳ ወደ እናንተ መግፋቴ ስለምን ነው ቢሉ … ባለፈው ሳምንት እንዳነሳሁት የአለባበስ፣ የአመጋገብ፣ የአነጋገር፣ የነገሮች አከነዋወን ወዘተ ሀገራዊ እሴቶችን (እስከዛሬም መጥተዋልና) አስጠብቆ መሄድ የሃይማኖት አባቶች በተለይም የኦርቶዶክስ አባቶች እዳ ነው። ብሎም የዜጎች ሥነ-ምግባር፣ ሥነ-ልቦናና ሞራል ሁሉ መገንባት የእናንተው እዳ ነውና ብርቱ ጫንቃ ያስፈልጋችኋል እላለሁ።

ባለፈው ሳምንት በጠቀስኩት ‹‹The Ethiopian Orthodox Church Tradition›› መጽሐፍ ላይ ደራሲዋ

... የመቅደላ ሰማዕታት፣ የመተማ ሰማዕታት፣ የአድዋ ሰማዕታት፣ የ5 ዓመቱ (ከ1928 - 33 ዓ.ም) ሰማዕታት፣ የቀይ ሽብር ሰማዕታት፣ የ97 ሰማዕታት ... ብቻ ብዙ ነው። እነዚህ ብዙ ሰው የሚያውቃቸው የሰማዕትነት ወቅቶች ናቸው። ግን ደግሞ ብዙ ሰው የማያውቃቸውና ያልሰማቸው የትላንትም ሆነ የዛሬ የሰማዕትነት ወቅቶች፣ ተገቢው የታሪክ ሽፋን ሳይሰጣቸው በየመንደሩ ተድበስብሰው ቀርተዋል።

የሆነው ሆኖ፤ ሰማዕትነት ትልቅ የልብ ፍጆታ የሚጠይቅ፣ በመኖርና በመሞት መካከል የሚደረግ ወደር የለሽ ትንቅንቅ ነው። አብዛኛውን ጊዜ አብዛኛው ሰው ‹‹ሰማዕት›› የሚለውን ቃል እንደወረደ ሲጠቀምበት ነው የኖረው። ቃሉ የፅርህ ወይም የግሪክ ሲሆን፣ ትርጉሙ ደግሞ ‹‹መስካሪ›› ማለት ነው። ‹‹ሰማዕታት›› ሲሆን ደግሞ ‹‹መስካሪዎች›› ተብሎ ይተረጐማል።

የቃሉ ትርጉም እምብዛም አለመታወቅ አርበ-ሰፊ የሆነ ስህተት እንዲሰራ ምክንያት ሆኗል። ኢትዮጵያ እንደ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አሊያም እንደ አገር ሆና በመንግስት መተዳደር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ብዙ ትውልዶች ተፈጥረው አልፈዋል። ከትውልዶቹ መሐልም ብዙዎች ስለ አንዲት አገራቸው ሰማዕት ሆነው (መስክረው) አልፈዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ዜጋ ስለሞተለት (ስለሞተበት) ነገር በቂ እውቀትና እምነት ሳይኖረው በቀይ ሽብር ተኩስ ስለተገደለ ብቻ ‹‹ሰማዕት›› የሚለው የ/ክብር ስም ሲሰጠው ኖሯል።

ይህ ግን ስህተት ብቻ ሳይሆን ረቀቅ ያለ ነውር ጭምር መሆኑን ይህ ጽሑፍ ሊያስገነዝበን ይገባል። የትርጉም ስህተት ያመጣውን የሰማዕትነት መፋለስ ፈር ማስያዝም ሌላኛው አዎንታዊ እርምት ነው። ‹‹ሰማዕት›› የሚለው

ኮሜንተሪ

ቃል ትርጉሙ ‹‹መስካሪ›› የሚል ከሆነ፣ ሳይመሰክሩ የሞቱ ነገር ግን በቀይ ሽብር አሊያም በአድዋ ጦርነት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ሁሉ የሰማዕትነት ክብር ይገባቸዋል? እውነትን ማድበስበስ እንደማይቻል ሁሉ፣ በአድዋ ጦርነት ወይም በቀይ ሽብር ወቅት ትክክለኛውን የሰማዕትነት አክሊል የተቀዳጁ ብዙ ‹‹መስካሪዎች›› እንደነበሩ አይካድም።

እነዛ ሰማዕታት የሰማዕትነትን ክብር የተጐናፀፉት በግርግር ሳይሆን በትክክለኛው የሰማዕትነት መንገድ ነው። ለምሳሌ በቀይ ሽብር ዘመን የነበረው ትውልድ፣ ህይወቱ በግርግር የታጀበ ነበር። አፈሙዝ በባረቀ ቁጥረ ኅብረተሰቡ ይደነግጥ ነበር። ያ ድንጋጤ ደግሞ የራሱን ወከባና ግርግር ይፈጥራል።

በዚያ ግርግር ውስጥ በፍርሃት እየራደ ወደ ቤቱ ሊገባ ሲሮጥ የተገደለ አንድ ዜጋ፣ በቀይ ሽብር ስም ስለተገደለ ብቻ ‹‹ሰማዕት›› ሊባል አይችልም። ምክንያቱም ምንም ዓይነት ምስክርነት ሳይሰጥ ወይም የስርዓቱን አስከፊነት ለወገኖቹ እየመሰከረ ስላልሞተ በጭራሽ ሰማዕት አይባልም። የደርግ መንግስት የአራት ኪሎ ቤተ-መንግስት ወንበር ላይ ለመቀመጥ ፈልገው ውጊያ የሚከፍቱ ቡድኖችን ለማጥቃት ሲል በብዙ ወጣቶች ነፍስ ላይ ዕጣ ተጣጥሏል።

ወጣቶቹ ህይወታቸውን የገበሩት ውጊያውን ሳይፈልጉና የደርግን የወቅቱን አቋም ሳያምኑበት ከሆነ፣ በርግጥም የሰማዕትነትን ክብር ይላበሳሉ የሚል ቅንጣት ታህል ግምት የለኝም። ሰማዕትነት የመመስከር ጥበብን ከጠየቀ ወጣቶቹ (ተገዳዮቹ) ገለልተኛ ነበሩ።

ወጣቶቹ የሞቱት ስለደርግ መንግስት መልካም ገፅታም ይሁን መጥፎ ጐን ሳይመሰክሩ በመሆኑ በየትኛውም አገባብ ሰማዕት ይሆናሉ የሚል በቂ የማሳመኛ ነጥብ መያዝ አይቻልም። ግን በማያውቁት ነገር በግፍ ተገደሉ ሊባል ይችላል።

ደርግ በወቅቱ ሲገለገልበት የነበረው ሥርዓት ‹‹የቄሳርን ለቄሳር ስጡ›› የሚለውን አልነበረም። የኢህአፓን አባላት ነፍሳችሁን ለኢህአፓ ሳይሆን ለኔ ስጡ እያለ ነበር እርምጃውን ሲያፋፍምባቸው የነበረው።

ሁሉም የአገሪቱ ህዝብ የሱን አስተዳደር እንዲደግፍ ብርቱ ፍላጐት ስለነበረው የጠብመንጃ አፈ-ሙዝ በሚጠቀምበት ወቅት ጥቂት የማይባሉ ዜጐች አምፀውበታል። ብዙሃኑ ዜጋ የደርግን ሥርዓት መጥፎነት ሲመሰክርም እንዲሁም ሌሎችም በትጥቅ ሲቃወሙት እንደነበርም እናውቃለን። እነዛ ዜጐች የሥርዓቱን ብልሹ ገፅታ በአደባባይ ሲመሰክሩ በመሞታቸው ‹‹ሰማዕታት›› ሊባሉ ይገባል። በተለያዩ መንግስታት ዘመን ለአገር የማይበጁ ውሳኔዎች ሲተላለፉ ቀድመው በመነሳት፣ ለተቀረው ህዝብ አገራዊ ሞራል በመፍጠር የሚታወቁት የዩኒቨርስቲ (በተለይ የአዲስ አበባ) ተማሪዎች፣ የምስክርነት ስራ በማከናወናቸው ሊጨፈጨፉ ችለዋል። የነሱና የሌሎች ዜጐቻችን ሰማዕትነት ለሰከንድ እንኳን ጥርጣሬ የሚፈጥር አይደለም። ብሎ ከማንኛውም አገራዊ ስሜት ካለው ሰው ህሊና ውስጥ ተፍቆ የሚወጣ አይደለም። ከራሳቸው ኑሮ ይልቅ የአገራቸውን ህልውና ያስቀደሙ በመሆናቸው ‹‹መስካሪዎች›› አልናቸው።

አብዛኛው ሰው የተወለደበትን ቀበሌና መንደር ይወዳል። አንዳንዱ ፍቅሩን ሲያጠነክረውም፣ እትብቴ ከተቀበረችበት ስፍራ አልርቅም ብሎ እዚያው ኖሮ እዚያው የሚቀበርም አለ። የአገር ፍቅር ግን የተለየ ነው። ሁሉም ማለት ባይቻልም፣ አብዛኛው ዜጋ የአገሩን ምድር፣ እፅዋቱን፣ ወንዙን፣ ተራራውንና ሸለቆውን አያውቅም። ሆኖም አገሩን በዓይነ-ህሊናው ማየትና መተለም ይችላል። አገሬን እወዳለሁ ሲልም በዚህ መልኩ የሚያያትን አገር ማለቱ ነው። የሰማዕትነቱን ፅዋ

ለመጐንጨት ሲያስብም አገሩን በዓይነ-ህሊናው እያሰበ ነው። ለአንዲት አገር የሚከፈል ምስክርነት የሚመነጨው ከእውነተኛው ህሊና በመሆኑ፣ አንድን ዜጋ የትኛውም ዓይነት ነውጥ ፈጣሪ የቦንብ ፍንዳታ ከሰማዕትነት ጉዞው አያሰናክለውም።

አንድ ሰው ሰማዕት ለመሆን ከመሬት መነሳት ብቻ በቂ መስፈርት አይሆንለትም። ለሚሞትለት ዓላማ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል።፡ በዛ ግንዛቤ ላይ ተመስርቶ ነው የመመስከር ተግባር ሊፈፅም የሚችለው።

በሌላ በኩል ሰማዕትነት ፈርጀ ብዙ ነው። ሰማዕትነት በአገር ጉዳይ ላይ ብቻ የሚወሰን የምስክርነት ውጤት አይደለም። በኛ አገር ስታንዳርድ ያየነው እንደሆነ፣ ሙሉውን ማለት ይቻላል ሰማዕትነት የሚያያዘው ከአገር ጋር ብቻ ነው (ከሃይማኖት ውጪ)።

ለልጆቻቸው፣ ለሚወዱት ሰው፣ ላፈቀሩት ሰው ... ትልቅ መስዋዕትነት ከፍለው የሚያልፉ ሰዎች፣ በርግጥም በመደባቸው ‹‹ሰማዕት›› የማይባሉበት ምክንያት የለም። የአገር ፍቅር ሳይኖረው የሔደበትን ጉዳይ ሳያምንበትና በግዳጅ ጦር ሜዳ ሔዶ፣ በኢትዮጵያ ስም ከሚሞት ደንታ ቢስ ሰው ይልቅ፣ የውሻውን ጥቅም አውቆና አምኖበት ለውሻው ሲል የሚሰዋ የውሻ አሳዳጊ ክብርና ሞገስ ያገኛል።

... ሌላው በዚህ በሰማዕትነት ጉዳይ ላይ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት የቡድን ቡድን አቋም አለ። ያኔ ኢህአዴግ ደርግን ለማውረድ የትጥቅ ትግል በሚያካሂድበት ዘመን፣ በደርግ አማካይነት ህይወታቸውን ያጡ የኢህአዴግ አባላት አሉ። ኢህአዴግ ደርግ የገደላቸውን አባላቱን ‹‹ለቆሙለት ዓላማ የተሰው ሰማዕታት ናቸው›› ይላቸዋል።

ወደ ደርግ ሲመጣ ደግሞ፣ ደርጉ ለስርዓቱ ተቆርቋሪ ናቸው ያላቸውን አባላቶቹን ከኢህአዴግ

ጋር ያፋልማቸው ነበር። ከኢህአዴግ ጋር ሲፋለሙ የሞቱትን ሰዎች አባሎቹን ‹‹ለቆሙለት አላማ የተሰዉ ሰማዕታት ናቸው›› ይላል ደርጉ። ምክንያቱም የደርግ መንግስት ቦታውን እንዳይለቅ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት አባሎቹ ለስርዓቱ ብለው ስለተፈጁ ደርጐች ‹‹ሰማዕታት›› ሲሉ ጓዶቻቸውን ያቆላምጧቸዋል። አሁን ሁለት አይነት ሰማዕትነት ሊፈጠር ነው ማለት ነው። ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ የራሳቸው ሰማዕታት አሏቸው። ደርግም እንደዛው።

ኢህአዴግ ለደርግ መንግስት ወግነው የደርግን አቋም በማንፀባረቅ ውጊያ ያካሄዱትንና አፈር የበሉትን የደርግ ሟቾች ‹‹ሰማዕታት›› ብሎ አይጠራቸውም፣ ‹‹ሰው በላ›› ስርዓት አራማጅ በማለት ይኮንናቸዋል እንጂ። ደርግም በበኩሉ የኢህአዴግን ሟቾችና ኢህአዴግ ‹‹ሰማዕታት›› ናቸው ብሎ ያመነባቸው አባሎቹን ‹‹ጠላቶቼ አሳዳጆቼ›› ይላቸዋል እንጂ ሰማዕታት አይላቸውም።

በዚያን ዘመን በደርግ መንግስት አማካይነት ጥቅም ያገኙ የነበሩ ቤተሰቦች ድጋፋቸውን በጭብጨባም ሆነ በፉጨት የሚሰጡት ሰማዕታት ለሚሏቸው ለራሳቸው ቡድኖች እንጂ፣ በተቃራኒ አሰላለፍ ተሰልፎ ለሚያጠቃቸው ለኢህአዴግ ቡድን አልነበረም።

የኢህአዴግና የደርግ ቤተሰቦች በየራሳቸው አቋም የየራሳቸውን ‹‹ሰማዕታት›› አፍርተዋል። ሁለቱም በየፊናቸው የኔ ነው ትክክል ሲሉም ይደመጣል። ለምሳሌ፡- እናቴ የደርግ፣ አባቴ የኢህአዴግ አባል ሆነው በየራሳቸው ህይወት የየራሳቸውን ‹‹ሰማዕታ›› ቢፈጥሩ፣ እኔ የየትኛውን ቡድን ሰማዕታት ነው መቀበል ያለብኝ? ምክንያቱም ሁለቱም ‹‹የኔ ነው ትክክል›› እያሉ ዘወትር ይነግሩኛልና። ግን ክፉ አጣብቂኝ ይመስለኛል። እዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ የባቢሎን ግንብ ሲናድ ከስር ርብራብ መሆን ይቀል ይሆን?

ስለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሞራል አስተምህሮ ሰርፀ ፍሬ የተባሉ ካህንን በመጥቀስ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ተርቤ ነበር አበላችሁኝን፤ ታርዤ ነበር አለበሳችሁኝን፤ ታምሜ ነበር ጎበኛችሁኝን›› ብሎ ጌታ በማቴዎስ ወንጌል በተናገረው መሰረት በጎ ምግባርን ያስተምራሉ።

ዳሩ ወ/ሮ ክሪስቲን በመጽሐፋቸው ይጥቀሱም አይጥቀሱም ቤተክርስቲያኗ በምን መሠረት እንዳለች ለምናውቅ በጎ ሥነ-ምግባርን ማስተማር ተግባር እንደሆነ ማወቅ አይሳነንም።

እኔም ይህንኑ አወቅሁ ለማለት አይደል ጥያቄ ለመሰንዘር የደፈርኩት! አዎ! ቃላዊና ተግባራዊ አስተምህሮዎችን ማስማማት እንዴት ተሳናችሁ ስል ባለፈው ሳምንት ጥቂቱን ጥያቄ አቅርቤአለሁ። እነሆ ዛሬም የቀሩኝን እጠይቃለሁ።

መድሆች ገንዘብ ካልከፈሉ

ልጆቻቸውን ክርስትና ማስነሳት ላይችሉ ነውን? በእርግጥ ይህ ነገር ጎፋ ገብርኤል አካባቢ ባለች እናት ደርሶ ስማቴን ገለጥኩ እንጅ ምን ያክል ስፋትና ጥልቀት ያለው ጉዳይ መሆኑን አልመረመርኩትም።

ግን እንደመንፈሳዊነት አንዲትም ነፍስ ማዘን የለባትምና ቤተክርስቲያኒቱ ወይስ አገልጋዮቹ ካህናት ይህንን ደስ የማይል ደንብ ያወጡት? ሲተገበርስ ስለምን ችላ ተባለ? በእውነት የመንፈስ ቅዱስን ኃብትና ልጅነት በገንዘብ ለመሸጥ ማሰብስ ተገቢ ነው? መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለኔ ደግሞ ይህንን ስልጣን ስጡኝ አለ። ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፡- የእግዚአብሔርን ስጦታ

በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ካንተ ጋር ይጥፋ። ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም። እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንስሐ ግባ!››

የሐዋ. ሥራ 8 ፥ 18-23በታላቁ መጽሐፍ የመንፈስ

ቅዱስን ስጦታ በገንዘብ ሊገዛ ያሰበ እንዲህ ከተገሰፀ ሊሸጥ ያሰበስ ምን ይጠብቀው ይሆን?

ሰዎች በአለማዊ ኑሮ የሰለቻቸው እያንዳንዱን ነገር በገንዘብ የመግዛት ኑሮ በመንፈሳዊ

ሕይወትም ሲገጥማቸው ምን ሊያስቡ የሚችሉ ይመስላችኋል? ፀሐይን ፈጥሮ በነፃ ብረሃን ስለሰጠ አምላክ ለመስበክ ገንዘብ የምንጠይቅ ከሆነ ነገራችን ወዴት ወዴት ነው? የእግዚአብሔር አምላክነት ወይስ የኛን ጥበብና ገንዘብ ወዳድነት እያገለገልን ያለነው?

‹‹መጽሐፉ ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋል ይላል። ይሁን እንጂ አብያተ-ክርስቲያናትን ሳንቲም መሰብሰቢያ ካደረግናቸው

ነገሮች ሁሉ ወዳልተፈለጉ አቅጣጫዎች ያመራሉ።››

የጋግራን እሪታ ገፅ 49

ሠቤተክርስቲያኒቱ በዚች

አገር ቀደምትም ይሁን ዘመናዊ የሥልጣኔ ታሪክ ውስጥ የራሷ ሆነ ጉልህ አሻራ እንዳላት የታወቀ ነው። ይህንን አዎንታዊ አስተዋጽኦ ጠብቆ ለማቆየት ይበልጥም ለሀገሪቱ ለማገልገል

በታዲዎስ ጌታሁን

በግርግር ‹‹ሰማዕታት›› የተባሉ ዜጐች አሉ

ጥያቄዎች ለአባቶቼደሳለኝ ሥዩም

[email protected]

በ ገፅ 23

እንደመዝለቂያ‹‹የቡከን ፀብና የግንቦት

ደመናገለል ገለል ይላል ነገሩ ሲጠናከላይ አንድ ድግር፣ ከታች

አንድ ድግርእንደዚህ ሲል ያልቃል

የደካማ ምድር››- // -

አባቶቻችን፣ አያት ቅድመ አያቶቻችን ከዘመናቸው አልፈው የተተኪውን ትውልድ አመለካከት በመቅረፅ ረገድ የተጠቀሙበት ጥበባዊ ሥልት መሆኑ ይታመናል - ሥነ-ቃል።

አበው በሥነ-ቃሎቻቸው ክፋትን ከደግነት፣ እምነትን ከክህደት፣ ጀግንነትን ከፍርሃት ወዘተ ጋር እያነፃፀሩ ልጆቻቸው (ተተኪው ትውልድ) የቱን መምረጥና መሆን እንደሚገባቸው አመላክተውበታል። በአጭር አነጋገር፣ ትውልድን አንፀውበታል። ገንብተውበታል።

እነሆ ይህ ታላቅ ጥበባቸው ከትውልድ ወደትውልድ እየተላለፈ ለእኛም ተርፏል፣ ለእኛም ደርሷል። ለዚህ ጽሑፍ መዝለቂያነት አስቀድሜ የነቀስኳቸው ሥነ-ቃሎች ፈሪና ፍርሃት የሚያስከትሉትን ተዋራጅነት የገለጡባቸው ጥበባዊ ኃብቶቻቸው ናቸው።

አ በ ው - በ ፈ ሪ ነ ት ና በጀግንነት መሀከል ያለውን ወይም የሚኖረውን ክብርና ውርደት ለይተው ድንበር አበጅተውበታል። ሐቀኝነት፣ የእምነት ፅናት፣ ደፋርነት ወዘተ በማኅበረሰባችን ዘንድ የሚያሰጠውን የሰውነት ደረጃ በማሞገስ፣ መልመጥመጥ፣ ፍርሀትና ውርደት ወዘተን በማንኳሰስ፤ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ‹‹የእኛ ጉዳይ›› መሆኑን አመላክተውናል። እንዲያ ከሆነ ዘንዳ እያንዳንዱ ክብር ያሰጠኛል ያለውን (ፍርሀትን ወይም ድፍረትን) መምረጥ የራሱ ጉዳይ ነው። በሌላ አነጋገር፣ በአንዱ ምርጫ ሌላው የሚያገባው ነገር

በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን

የኪነ-ጥበብ ሰዎቻ ችንና የግንቦት ደመናሀገራዊ

ማንነትንና አንድነትን ብሎም የጋራ

መገለጫን መገንባት የሚቻለው በእምነትና

በእውነት ነው። እምነትም እውነትም

የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮዎች ናቸው። ከእነዚህ ትምህርቶች የሚጣረሱ ተግባራት

ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ በቅለው ሲገኙ

ያስቆጫል።

በሌላ በኩል ሰማዕትነት

ፈርጀ ብዙ ነው። ሰማዕትነት

በአገር ጉዳይ ላይ ብቻ

የሚወሰን የምስክርነት

ውጤት አይደለም። በኛ አገር

ስታንዳርድ ያየነው እንደሆነ፣

ሙሉውን ማለት ይቻላል

ሰማዕትነት የሚያያዘው

ከአገር ጋር ብቻ ነው

Page 9: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ምክክር ለሥነ-ጥበብ፣ ምክር ለአርቲስቶቹ9ኮሜንተሪ

እለቱ ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተዘጋጀ አንድ የውይይት መድረክ ነበር። በዚሁ እለት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከተለያዩ የሥነ-ጥበብ ሙያተኞች (የፊምና የመድረክ ተዋንያን፣ ደራስያን፣ ሰዓሊያን፣ ድምፃውያን፣ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች፣ ቀራፂያንና ሌሎችም) ጋር በግንባር ተገናኝተዋል። የዚህ መድረክ አዘጋጅ የሆነው ኮሚቴ መጠሪያ ስም ትንፋሽ የሚጨርስና ትንሽ ረዘም ያለ ነው። ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሕብረ ሥነ-ጥበባት ምክክር መድረክ አመቻች ጊዜያዊ ኮሚቴ›› ይባላል። ከዚህ በኋላም ኮሚቴው እያልኩ የማነሳው ይህንኑ ስመ ዘርፋፋ ኮሚቴ ነው።

ኮሚቴው በእለቱ ባሰራጨው በራሪ ወረቀት ላይ ይህን መድረክ ማዘጋጀት ያስፈለገበትን ዓላማ ገልጿል። በዚሁ መግለጫ መሰረት በአሁኑ ሰዓት የአገሪቱ ሥነ-ጥበብ እየገጠሙት ያሉ ችግሮች በርከት ያሉና አንዳንዶቹ የራሱ የሥነ-ጥበቡ ማሕበረሰብ ሊፈታቸው የሚገቡ ቢሆንም በይበልጥ እንቅስቃሴውን እየጎዱ ያሉት ችግሮች ግን በትምህርት፣ በሕግ፣ በፖሊሲ፣ በተቋማዊ አደረጃጀት፣ በሥራ አፈፃፀም፣ በማበረታቻና በትኩረት ማጣት የተንተራሱ በመሆናቸው በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከርና በችግሮቹ ላይ የጋራ መፍትሔን ለማፈላለግ ነው።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማሕበር አባል በመሆኔ በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ለመታደም ችያለሁ። በዚህ ፅሁፍ የሰፈረው አስተያየት ግን የማሕበሩ ሳይሆን የግል ሀሳቤ ብቻ መሆኑን ለማስታወስ እወዳለሁ።

በቅድሚያ የኢትዮጵያ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንዲህ በጋራ መሰባሰብና መቀናጀት

መቻል በራሱ የሚያስመሰግን ነው። ከዚህ ቀደም ደራሲያን ለብቻቸው፣ ሙዚቀኞች፣ ተዋንያን፣ ሰዓሊያንና ሌሎች የጥበብ ቤተሰቦች በየፊናቸው ለሀገሪቱ ለሥነ-ጥበብ ሥራ እውቅናና ድጋፍ እንዲሰጥ የተናጠል ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር አይዘነጋም። በዚህ ወቅት ግን ይህን የተናጠል ጥረታቸውን በማቀናጀት የጋራ ድምፃቸውን በአንድነት ለማሰማት መቻላቸው በእውነትም ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ነው። ሙዚቃ በተናጠል ከክራር ብቻ ሊገኝ ቢችልም መሰንቆው፣ ዋሽንቱ፣ ከበሮውና እምቢልታው ሲታከልበት ምን ዓይነት ሕብረ-ዜማ እንደሚኖረው የሥነ-ጥበብ ሙያተኞች የሚገነዘቡት ቁም ነገር ነው። የተባበረ ድምፅ እንዲሁ ያምራል፤ የበለጠም ይደመጣል።

ኮሚቴው በዚህ መልኩ ከመደራጀቱ በተጨማሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የምክክር መድረክ (ጉባኤ) ማዘጋጀቱ ሌላው እንደበጎ እርምጃ የሚታይ ክንዋኔ ነው። ምክክሩ በራሱ ግብ ባይሆንም ለሚፈለገው የአጭርና የረጅም ጊዜ ግብ እንደ አንድ መልካም ጅምር የሚታይ ነው። የእለቱ የውይይት መድረክ እንደመጨረሻ ግብ እንዳይወሰድ ግን እሰጋለሁ። ኮሚቴው በበለጠ ተጠናክሮ የሥነ-ጥበብ ማሕበረሰቡን ድምፅ በአንድነት የሚያስተባብር የጋራ መድረክ ሆኖ መቀጠል፣ አልያም በተመሳሳይ አደረጃጀት መተካት መቻል አለበት። የሥነ-ጥበብ ማሕበረሰቡ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ባይወገዱም ቢያንስ ከፊል ችግሮቹን መቀነስ እንዲቻል እንዲህ ያለው ሕብረትና የጋራ መድረክ አስፈላጊ ነው።

መንግስት ለሥነ-ጥበቡ እድገት ድጋፍ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት ደጋግሞ ማስታወስና ማሳሰብ ይገባል። በሕገመንግስቱ አንቀጽ 91 ላይ በግልፅ እንደሰፈረው መንግስት ባህል ነክ

ዓላማዎችን የመደገፍና የመርዳት ኃላፊነት አለበት። በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 3 ላይ የሰፈረውን ብቻ ብንወስድ ‹‹መንግስት አቅም በፈቀደ መጠን ኪነ-ጥበብን፣… የማስፋፋት ግዴታ አለበት›› ይላል። ይህም ብቻ አይደለም። በሕገመንግስቱ አንቀፅ 29 ላይ ማንኛውም ሰው በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ-ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶች እንዳሉት በግልፅ አስፍሯል። መብቱ በዚህ ብቻ አይወሰንም። በሕገመግንስቱ አንቀጽ 39 ላይ ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ በቋንቋው የመናገር፣ የመፃፍ፣ ቋንቋውን የማሳደግ እና ባሕሉን የመግለፅ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት እንዳለው የሚያብራራ ጉልህ ሀሳብ ሰፍሮ ይገኛል።

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሕገመንግስታዊ ነፃነትና መብት የሚተገበረው በሥነ-ጥበብ ሥራና በሥነ-ጥበብ ሙያተኞች አማካኝነት ነው። የጥበብ ቤተሰቦች እነዚህን ሕገመንግስቱ የሰጣቸውን ተደራራቢ መብቶች በአግባቡ ለመጠቀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ የገጠሙትን ችግሮችና በርካታ ውጣ ውረዶች ‹‹አቤት›› ለማለትና መፍትሔውን ለመሻት ነበር ከጠቅላይ ሚነስትሩ ጋር ይህን የምክክር መድረክ ያካሄዱት። የሕትመት ዋጋ መናር፣ የቅጂ መብቶች አለመከበር፣ ለሥነ-ጥበብ ሙያው ተመጣጣኝ ዋጋ አለማግኘት፣ የሀገሪቱ የጥበብ ሰዎች በመዋጮ መታከምና በመዋጮ መቀበር፣ ለሥራቸው ተገቢ ማስታወሻና መታሰቢያ መጥፋት፣ የሥነ-ጥበብ ማሳያ ማዕከላት እጥረት፣ የቀረጥና የግብር ጫና፣ የሥነ-ጥበብ

የልማት ችግሮች የመሳሰሉት በዚሁ መድረክ ላይ ተነስተዋል። እነዚህን የዘርፉን ችግሮች ለማስገንዘብ የሚያስችል አጭር ድራማም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሥራ ባልደረቦቻቸው ቀርቧል።

እርግጥ ነው የእለቱን መድረክ ‹‹የምክክር መድረክ›› ነበር ከማለት ይልቅ ‹‹የጥያቄና መልስ›› ነበር ማለቱ ይቀላል። ጥያቄዎች እንዲያነሱ አስቀድመው ከተመረጡት መካከል እጅግ የተወሰኑት ጥያቄያቸውን በግልፅና በአግባቡ ለማቅረብ ችለዋል። ብዙዎቹ ግን የራሳቸውን ማንነትና ሥራዎች ሲያስተዋውቁ፣ የወጡ የወረዱበትን ሜዳና ገደል ሲተርኩ፣ ከዚህ ቀደም ሕገወጥ ቅጂ ፈፃሚዎችን አሳዶ ለመያዝ ያደረጉትን ጀብዱ ሲዘረዝሩ ይህን ወርቃማ ግዜ በከንቱ አባክነውታል። የውይይቱ አስተናባሪ የነበረው ሠራዊት ፍቅሬም እነዚህን ‹‹ጥያቄ አቅራቢዎች›› ወደ ዋና መንገዳቸው ለመመለስና የተሰጣቸውን ውስን ሰዓት በአግባቡ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ደጋግሞ ሲወተውት አይተናል። ከዚህ የምረዳው ነገር አስቀድሞ የጥያቄ አቅራቢዎቹ አመራረጥ ችግር እንደነበረበት ነው። ነገር ግን ጥያቄዎቹ ከተለያዩ የጥበብ ዘርፎች እንዲካተቱ ጥረት መደረጉን እገነዘባለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ሀሳባችሁን ለመግለፅ ይቸግራችኋል ብዬ አልገምትም፤ የጥበብ ሰዎች እንደመሆናችሁም በእናንተ ፍጥነት ለመሄድ ያስቸግራል›› እንዳሉት ሳይሆን አብዛኛዎቹ ጠያቂዎች ግለ-ታሪካቸውን፣ ተጋድሏቸውን፣ የግል ገጠመኛቸውን ሲዘረዝሩና ‹‹አብሲት ጥዬ፣ ንፍሮ ቀቅዬ›› ሲሉ የወከሉትን ሙያተኛ የልብ ሀሳብ ሳያስተላልፉ እራሳቸውንም፣ የጥበብ ማሕበረሰቡንም ትዝብት ላይ ጥለውት አልፈዋል። ረዳት ፕ/ር ኃይማኖት አለሙ፣ ታጠቅ ታደሰ፣ እሸቱ ጥሩነህ፣ ሰርፀ

ጥያቄዎች ለአባቶቼ

ፍሬስብሀትን የመሰሉ ጥቂት ጠያቂዎች በተሻለ ደረጃ የጥበብ ቤተሰቡን ሀሳብና የልብ ትረታ ለማንፀባረቅ ሞክረዋል። የተቀሩት ግን መብታችንን ማስከበር ሳይሆን እንደደካማ ጠበቃ በላያችን ላይ አስፈርደዋል።

በጉባኤው ላይ የደራሲያንን ችግሮች የተመለከቱ ጥያቄዎች አለመቅረባቸው ደግሞ በግሌ ያሳዘነኝ ጉዳይ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለወረቀት ዋጋ ውድነት የሰጡት ምላሽ በቀጥታ የደራሲያንን ችግሮች የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው አልነበረም። በሕትመት ዋጋ መናር ላይ የሰጡት ምላሽ በድራማው ላይ ከተንፀባረቀው ቃለ-ተውኔት ላይ ተነስተው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወረቀት ዋጋ ችግር የዓለም ገበያ የፈጠረው መሆኑን፣ የመፅሐፍ የግዥ ዋጋን ለመቋቋም በጋራ ገዝቶ የማንበብ ልምድን ማዳበር እንደሚቻል የሰጡት ምላሽም መንግስት ለዘርፉ ያለው አመለካከት የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነና ገና ብዙ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን እንድገነዘብ አድርጎኛል። ዛሬ የመንግስት ተቋም የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚያሳትማቸው መፅሐፍት ዋጋ እንኳ 150፣ 200 እና 300 ብር ይደርሳል። ይህ ዋጋ እንኳን የንባብ ልምድ የሌላቸውን ሊስብ ቀርቶ የማንበብ ልምድ ያላቸውንም የሚገፈትር ነው። ለምሳሌ አንድ መካከለኛ ገቢ አለው የምንለው ዜጋ የማንበብ ፍላጎት ቢኖረው እጁ ላይ ባለው ገንዘብ ምግብ ገዝቶ ከመብላትና መፅሐፍ ገዝቶ ከማንበብ አንዱን እንዲመርጠ ይገደዳል፡፡ መፅሐፍ ለማሳተም ከየትኛም ዘመን በላይ አስቸጋሪ የሆነው ዛሬ ነው። እርግጥ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የወረቀት

በሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል)[email protected]

በ ገፅ 14

። ። በመጨረሻ አባይ ከነግሳንግሱ ከተፍ አለ። አገሬውን በየቀየው፣ ሰራተኛውን በየመስሪያ ቤቱ፣ ምዕመኑን በየአብያተ-መቅደሱ እየከተረ ሲያመካክረው፤ ሰልፍ እያስወጣ ሲያሸልለው፤ የቴሌቭዥን ካሜራ ፊት እየገተረ ሲያስደነፋው የሩቅ ታዛቢ የመሆን ጊዜ አበቃ። እንደተጠበቀው ግዙፉ ደመራ ላይ የሚጨምራቸውን ችቦዎች ከየስፍራው የሚለቃቅመው ረጅም እጅ ከደጅ ደርሶ በሩን አንኳኳ። ማንስ ቢሆን ከዘመን ትኩሳት እንደምን ሊያመልጥ

ይቻለዋል? አገር ስትናጥ እኔ አልነቃነቅም የሚለውስ የቱ ፌዘኛ ነው? ለነገሩ እንዲህ ባለ የስሜት ሰደድ መንቀልቀል ብርቃችን አይደለም። ግለቱን ቀዝቅዘን፣ ውክቢያውን ሰክነን ማስተዋል አልለመድንም እንጅ። አሁንም አንዳንዶቻችን ወደን ተነስተን፣ አንዳንዶቻችን ከዳር እንደቆምን ተገፍተን የሚተመውን ሠራዊት ተቀላቀልን። ምድርን የሚያናውጥ አስገምጋሚ ጩኸት ለመፍጠር ትንንሽ ድምጾቻችን አዋጣን። መፈክር አስተጋባን። ዝማሬ ተቀብለን አጨበጨብን። ሲጨፈር እስክስታ ወረድን። ሲቅራራ ተነሽጠን ፎከርን። ሙዳየ-ምፅዋት ሲዞር በአሳር የተገኙ ሳንቲሞቻችንን ወረወርን። የግርግሩ ምቾት ቢስማማንም ቅሉ፣ እርምጃችንን ግራ መጋባት አላጣውም። አጠቃላይ የሰፈነው መንፈስ ለጥያቄዎቻችን የማያምታታ መልስ ሊሰጥ ስላልቻለ መወናበድ አልቀረልንም። የጠራ ትርጉም ፍለጋ አብረውን የሚራመዱ ጓዶቻችንን ስናጤን ውዥንበረ ከሁላችንም ናላ በላይ የሚሽከረከር የዚህ ‹‹ህዝባዊ ንቅናቄ›› አንድ መገለጫ መሆኑ ተገለጠልን።

የአገራችን ብሩህ መፃኢ ቀናት መድህን መሆኑ እየታወጀለት ያለው ታላቅ ግድብ መገንባት አግባብነት ላይ ጥያቄ የሚያነሳ አመዛዛኝ ሰው አለ ለማለት ያስቸግራል። ሆኖም

በልገሳና በቦንድ ግዥ የስምምነት ውሳኔዎች የሚደመደሙ ስብሰባዎች ሲበተኑ ጆሮአችንን ጣል አድርገን የወሬ መረባችንን ብንዘረጋ የምናጠምዳቸው ስሜቶች ከኩራትና እርግጠኛነት ይልቅ ምሬት፣ ብሶት፣ ቁጣና ጥርጣሬን የሚያንፀባርቁ ናቸው። ይህ በአደባባይ ከሚሰበከውና በሚዲያ (የመንግስቱን ማለቴ ነው) ከሚተረከው ዜጎች ከመቼውም በበለጠ አንገታቸውን ቀና ሊያደርጉ እንደተዘጋጁ፣ ልዩነታቸውን ወደ ኋላ ትተው በአንድነት እንደተነሳሱ፣ ቁርጠኝነታቸውን አስረግጠው ያለአንዳች ቅሬታ ያልተሸራረፈ ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሰጡ ከሚያትተው ትረካ ጋር አይገጥምም። ተራና የተለመደ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ነው ተብሎ እንዳይታለፍ ደግሞ የአባይ ነገር ምን ያህል ሆዳችንን ሲበላን እንደኖር የምናውቀው ነው። ለእናቱ እጦት ባይታዋር የሆነ መና ልጅ እያልን ስንወቅሰውና ስናወግዘው ትውልዶች መተካካታቸው አይታበልም። ታዲያ በማንነታችን ቅንብር ውስጥ የማይናቅ ስፍራ ያለው ይህ ወንዝ ረብ ይኑረው፤ ወደ መነሻው ዞሮ አጉራሹን ያጉርስ፣ አልባሹን ያልብስ የሚል ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመር ሚዲያው የሚጮኸውን ያህል ማህበረሰበዊ ፈንጠዝያ ቢያስከትል የሚገርም አይሆንም። የእውነታው በሁለቱ አፅናፎች መኃል መዋለል ስለጉዳዩ አፋችንን ሞልተን ከመናገር አቅቦናል። በእርግጥ ግልፅና የተሰመረ ወሰን የሌላቸው፣ በሁለት አጋማሾች መኃል ሲያሻቸው ወደፊት እየገፉ፣ ቆይተው ወደ ኋላ እየሸሹ እንዴ ሙልት አንዴ ጉድል በሚል የአስተሳሰብ ተቃርኖዎች የተቀለመ ዝብርቅርቅ ስዕልን ያበረከተልን የመጀመርያው

አገራዊ አጀንዳ አባይ አይደለም። ርቀን ሳንሄድ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውጥንቅን እናስታውስ።

የዳር ድንበሩ መደፈር ያስቆጣው ጀግና ህዝብ ‹‹ቀፎው እንደተነካ ንብ›› ከጫፍ እስከ ጫፍ ተጠራርቶ ተነስቶ ወደ ጦር ግንባር ሲዘምት ስንቅ ብቻ ሳይሆን እልልታም ሰልቀናል። ግጥም ገጥመን አንብበናል። አነብንበናል። በሙዚቃ ተኮርኩረናል። ጀብድ እያደነቅን አውግተናል። ሬዲዮውና ቴሌቭዥኑም ‹‹ልጆቹን መርቆ ልኮ›› ብሎልናል። የድጋፍ ሆታችንን አግንኖልናል። ሰልፋችንን አግዝፎልናል። መከፋፈል ሳያምረን፣ ቅራኔዎቻችንን ዘንግተን የመሰረትነውን ኅብረት አሞካሽቶልናል። እንዲያም ሆኖ ግን ከዚህ ስምሙ ማዕቀፍ ያፈነገጡና አብረው የማይሄዱ፣ ጥቂት ልንላቸው የማንደፍር ትዕይንቶችንም ታዝበናል። ዘማች ልጆቻቸውና ባሎቻቸው የሚቆዩበተን የቀበሌ ፅ/ቤት ከበው በዋይታ ያወኩ እናቶችና ልጅ ያዘሉ ሚስቶች በፖሊስ ዱላ ተነርተው ሲበተኑ አይተናል። ያለፈቃዳቸው ወደ ሞት አውድማው የተላኩ እድለ ቢሶችን የሚመለከቱ ሀተታዎችን /ሀሜታዎችን ሰምተናል። አሰምተናል። ስለጦርነቱ መንስኤና ትክክለኛ ሂደት የሚሰጠንን ይፋዊ መረጃ ለማመን አመንትተናል። መሻሽቶ በየጎጆዎቻችን ስንወሸቅ እንደግለሰብም እንደሀገርም የምንገብረውን ጥሪት የትየሌለነት አስልተን አጉተምትመናል። በማኅበረሰብ ደረጃ ቀርቶ በግል እንኳ ወጥ አቋም መያዝ ተስኖን ተተረማምሰናል። ‹‹የሀገርን አቅጣጫና ህልውና የሚነኩ ታላላቅ ጉዳዮች ሲከሰቱ መበየንን፣

የለም ማለት ነው።ይህንን ሁሉ ያልኩት

በወርሃ ግንቦት መጨረሻ የሀገራችን የኪነ-ጥበብ ሰዎች ነን ተብዬዎች እንደግንቦት ደመና ‹‹ደሞ ገለሌ›› ባይ ሆነው መገኘታቸው በእጅጉ ስላስገረመኝ ነው። ስላሳዘነኝ ነው። ስላሳዘኑኝም ነው። እንዴትና በምን ልትሉ ትችላለችሁ። በቅደም ተከተል ላስረዳ፡-

-ሀ-ባለፈው ሰኞ ግንቦት 30

ቀን 2003 ዓ.ም ከ‹‹ፅኑ መነፋፈቅ›› በኋላ የሀገራችን አርቲስቶች ከጠ/ሚ/ር መለስ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን አይታችኋል፤ ያላያችሁ ሰምታችኋል። ያላያችሁም፣ ያልሰማችሁም ይኸው እኔ ነገርኳችሁ። ድፍን 20 ዓመታት ከጠ/ሚ/ር መለስ ጋር መገናኘትን ሲናፍቁ የኖሩት አርቲስቶቻችን ፊት ለፊት ተቀምጠው ተወያያተዋል።

ለውይይት መቀመጥ መልካም ነው። መወያየትን

የመሰለ ብልህነት የለም። እኔም አርቲስቶቻችን ከአቶ መለስ ጋር ለምን ተወያዩ አልልም። አ ል ቃ ወ ም ም ። ል ቃ ወ ም ም አልችልም። መብታቸውም ነው። ሕገመንግስታዊ መብትቸውም መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ።

የእኔ ጉዳይ፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎቻችን መብታቸውን ተግባራዊ ሲያደርጉ፣ የሌላውን መብት ለመደፍጠጥ ለምን ይቃጣሉ ነው። የሌላውን መብት ለመደፍጠጥ መቃጣታቸው ብቻ ሳይሆን መደፍጠጣቸው ተገቢ አይደለም ነው። የዚህንም እንዴትነት ላስረዳ።

-ለ-የኢትዮጵያ ብሔራዊ

ኅብረ-ሥነ-ጥበባት ምክክር መድረክ ተብዬውን ውይይት ያስተባበረው ከአንድ ወር በፊት በድንገት ብቅ ያለ ኮሚቴ መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል። የውይይቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ተብዬዎች ታዲያ አንድ አሳፋሪ ውሳኔ ወሰነው ተግባራዊ ማድረጋቸው ነው ለዚህ መጣጥፍ

ዋንኛ መነሻ የሆነኝ። ያ ውሳኔ በሀገሪቱ ከሚገኙ ፕሬሶች መሀል፣ ‹‹የፖለቲካ›› ያሏቸው የግል የህትመት ውጤቶች በውይይቱ ላይ እንዳይገኙ የሚከለክል ነው።

ለምን? መንግሥትን ይተቻሉ፤ ያብጠለጥላሉ፤ ይዳፈራሉ። በመንግሥት አይወደዱም። ስለዚህ እነሱ የፖለቲካ ናቸው ያሏቸውን ጋዜጦችን ገለል አድርገን ከመንግሥት ጋር እንሞዳመድ አይነት ነው ውሳኔያቸው። ይሁንላቸው። ይሞዳሞዱ። ይመቻቸው። ነገር ግን፣ ማንና ምን ስለሆኑ ነው የንግግርና የመፃፍ ነፃነትን ወደጎን የሚገፉት? ሀሳብን በመግለፅ ነፃነትስ ጣልቃ ገብተው እነእከሌ ይምጡ እነእከሌ ይቅሩ ለማለትስ ምን መብት አላቸው?

መንግሥት ይስማን፣

በቃልዲን ይበልጣል [email protected]

የኪነ-ጥበብ ሰዎቻ ችንና የግንቦት ደመና

የሁለት ‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄዎች›› ወግ

በ ገፅ 23

ዘማች ልጆቻቸውና ባሎቻቸው የሚቆዩበተን የቀበሌ ፅ/ቤት ከበው በዋይታ ያወኩ እናቶችና ልጅ ያዘሉ ሚስቶች በፖሊስ ዱላ ተነርተው ሲበተኑ አይተናል። ያለፈቃዳቸው ወደ ሞት አውድማው የተላኩ እድለ ቢሶችን የሚመለከቱ ሀተታዎችን /ሀሜታዎችን ሰምተናል።

በ ገፅ 23

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ሀሳባችሁን ለመግለፅ

ይቸግራችኋል ብዬ አልገምትም፤ የጥበብ ሰዎች እንደመሆናችሁም

በእናንተ ፍጥነት ለመሄድ ያስቸግራል›› እንዳሉት ሳይሆን

አብዛኛዎቹ ጠያቂዎች ግለ-ታሪካቸውን፣ ተጋድሏቸውን፣

የግል ገጠመኛቸውን ሲዘረዝሩና ‹‹አብሲት ጥዬ፣ ንፍሮ ቀቅዬ›› ሲሉ የወከሉትን ሙያተኛ የልብ

ሀሳብ ሳያስተላልፉ እራሳቸውንም፣ የጥበብ ማሕበረሰቡንም ትዝብት

ላይ ጥለውት አልፈዋል።

Page 10: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 200310

በአቤል ዓለማየሁ

የጥበብ ባለሙያዎች ያሉባቸውን ቅሬታ እና ችግሮች ለመግለፅ ለረዥም ጊዜያት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ተገናኝተው ለመወያየት ይፈልጉ ነበር። ባለፈው ሰኞ እድሉን አገኙና ፊት ለፊት ተፋጠጡ። እንደ ብዙዎቹ ተሳፊዎችና ታዛቢዎች ገለፃ ግን ሀሳባቸውን በአግባቡ ሳያስረዱ እና እርባና ቢስ ጥያቄ ሳያቀርቡ ስብሰባው ተደምድሟል። መድረኩን የመራው ሠራዊት ፍቅሬ በእለቱ ማምሻውን ‹‹ሒሮሺማ›› የሚል ፊልሙን በብሔራዊ ቴያትር ያስመርቅ የነበረ ሲሆን ከፊልሙ ይልቅ ግን ስለመራው ስብሰባ በአዳራሹ በሁሉም ጠርዝ ትችታዊ አስተያየቶች ይሰሙ ነበር።

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና የቅጂና ተዛማጅ መብቶች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ይፍሩ ማኅበራቸውን ወክለው ለስብሰባው ላይ ለመናገር 18ኛ ዝርዝር ላይ ተካተው የነበረ ቢሆንም እድል ስላልተሰጣቸው ጥያቄያቸውን ማቅረብ ሳይችሉ አዳራሹን መሰናበታቸውን ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል። ‹‹የሙዚቃ ማኅበር እና የሙዚቃ ባለሙያዎች በርካታ የችግር ዘመናትን አሳልፈናል። ይህንንም በሰላማዊ ሰልፍ፣ እና በመሰል ጥረቶች ለመግለፅ ሙከራ ብናደርግም ችግሮቹ ስላልተፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እናቀርባለን የሚል ሀሳብ የነበረን ቢሆንም የመድረክ መሪው (አቶ ሰራዊት ፍቅሬ) እድሉን ስላልሰጡን ሳናቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተነስተው ሄደዋል›› ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ደራሲን ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ በበኩላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥበብ ባለሙያዎችን አክብረው መገኘታቸን አመስግነው ‹‹ነገር ግን እኛ እድሉን አምክነነዋል›› ሲሉ ገልፀዋል። ‹‹ነገ በጋራ አብረው ሊሰሩ የሚችሉ የጥበብ ባለሙያዎችን ከምንም ሳይቆጥሩ የተወሰኑ ሰዎች፣ የተወሰኑ መልዕክት አስተላልፈው ስብሰባው ተጠናቋል›› በማለት ቅሬታቸውን ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው ማኅበራቸውን ወክለው ከአደራሹ የተገኙ ቢሆንም ቃል እንዲተነፍሱ እድል የሰጣቸው እንዳልነበር አስታውሰው 61 ዓመት ያከበረ ማኅበር ሀሳብ እና የደራሲያን ድምፅ ሳይሰማ በመቅረቱ በኮሚቴው ላይ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ሰዓሊያን፣ ቀራጺያንና ግራፊክስ ዲዛይነሮች እና መሰል ሙያ ያላቸውን ባለሙያዎች ያካተተው የኢትዮጵያ ቪዥዋል አርቲስትስ አሶሴሽን በበኩሉ ድምፁን የሚያሰማበት እድል ሳይሰጠው ከአዳራሹ በመውጣቱ ቅሬታውን ገልጿል። ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ምክክር ለማድረግ የተቋቋመው ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኅብረ ሥነ ጥበባት ጊዜያዊ የምክክር መድረክ አመቻች ኮሚቴ›› አባል ሆኖ ይሳተፉ እንደበር የገለፁት የአሶሴሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ስዩም አያሌው ጥያቄ ለማቅረብ በዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም መድረክ መሪው እድል ስላልሰጧቸው በስዕል ጥበብ ዙሪያ ያሉ ድምጾች ሊሰሙ እንዳልቻሉ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል።

በስብሰባው ላይ የነበረውን ተውኔት ከተጫወቱ ባለሙያዎች መሀከል አንዱ የሆነው አንጋፋው ፋንቱ ማንዶዬ ‹‹ስብሰባው ላይ የተነሱትን ችግሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቀበላቸውና በመነጋገር እንፈታቸዋለን ማለታቸው በጎ ጎን ነው›› በማለት የገለፁ ሲሆን በጥያቄ አቀራረቡ ላይ ለሁሉም ማህበራት ባለመዳረሱ እንደ ችግር ቢገልፀውም በቀጣይ በማኅበሩ ተወካያቸው አማካኝነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማቅረብ እንደሚፈቱ እምነት ይዟል።

የፋንቱን ሀሳብ በስብሰባው ላይ የተካፈለ አንድ የጥበብ ባለሙያ ይቃረነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከአሁን በኋላ ዳግመኛ ማግኘት የሚታሰብ አይመስለውም። ‹‹የነበረንን ዕድል እንድንጠቀም መድረክ መሪው ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ እድል ሊሰጥ ይገባው ነበር። አቶ መለስም ጊዜ ሰጥተው እስከ መጡ ድረስ ታጋሽ ሆነው የሁሉም

የሙያ ማህበራት ሀሳብን መስማታቸውን ሳያረጋገጡ መውጣት አልነበረባቸውም›› ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

ለአውራምባ ታይምስ ሀሳቧን የገለፀች ስሟን መግለፅ ያልፈለገች አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በመድረክ መምራቱ በኩል ሁሉንም ባማከለ መልኩ ዕድል እንዲያገኙ ካለማድረጉም በላይ በርካታ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች እያሉ በሞኖፖል የምክክር መድረኩን መቆጣጠሩን እንዳሳዘናት ገልፃለች። በስብሰባው የተካፈለ አንድ ሰዓሊ በበኩሉ ከአዳራሹ ሲወጡ ተሰብሳቢዎች ‹‹የሠራዊትና ሠራዊቱ ድራማ›› በማለት ተቃውሟቸውን ይገልፁ እንደነበር ገልጾ

የታየውም ይኸው ነው ብሏል። በጉዳዩ ዙሪያ መልስ እንዲሰጠን ለሠራዊት ፍቅሬ ወደ እጅ ስልኩ ደጋግመን ብንደውልም፣ የፅሁፍ መልዕክት ብንልክም መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

አቶ ዳዊት ይፍሩ ለተፈጠረው ችግር ጣታቸውን ወደ ምክክር አመቻች ጊዜያዊ ኮሚቴው ይጠቁማሉ። ‹‹ኮሚቴው ምን ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እንደተሰናዳን አስቀድሞ ስለሚያውቅ ቅደም ተከተሉን መጠበቅ ሲገባው ለአንድ ሙያ ማኅበር ሁለት እና ከዚያ በላይ ጊዜ እድል ከመስጠት ይልቅ ስብጥር ማድረግ ነበረበት›› በማለት ኮሚቴውንም ሆነ መድረክ መሪውን

‹‹የሠራዊት እና ሠራዊቱ ድራማ››የኪነ-ጥበብ ‹‹ባለሙያዎች›› ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ዙሪያ ቅሬታዎች በርክተዋል

ተችተዋል። ያለ ባለሙያ ፈቃድ ስራውን

በሬዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን ማቅረብ ስህተት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዳዊት በቀድሞ ጊዜ ግን ክፍያ ያስገኝ እንደነበር አንስተው ይህን መጤን እንዳለበት፣ አንጋፋ ሙዚቀኞች ችግር ውስጥ ሲገቡ በምፅዋት መርዳትና መቅበር እንዲቀር መንግስት እርዳታ እንዲያደርግ ሀሳብ የማንሸራሸር ሀሳብ ይዘው የነበረ ቢሆንም ዕድል ተነፍጓቸዋል።

ከህፃናት መዋያ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ የሥነ ሥዕል ሙያ እንዲሰጥ፣ መካከለኛ የእውቀት ደረጃ ላይ ያሉ ሰዓሊያን ወደ ከፍተኛ የእውቀት

ደረጃ እንዲሸጋገሩ የሚያደርገው የትምህርት ዕድል መቆሙን፣ የውጪ ትምህርት ዕድል መቅረቱን፣ በግብርና በቅጂ መብት ዙሪያ ስላሉ ችግሮች ጥያቄ መሰንዘር አስበው እንደነበር የገለፁት አቶ ስዩም አያሌው ለዚህም ሲሉ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርተው በመወያየት ጥያቄ ቢያዘጋጁም መታፈናቸውን ገልፀዋል፤ በኮሚቴው። ‹‹መንግስት በኪነ ጥበብ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት የመጀመሪያው ስብሰባ ላይ ለሁሉም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሀሳብ መሰማት የነበረበት ቢሆንም ከሞላ ጎደል ዕድል ተደጋግሞ የተሰጣቸው ግን የፊልም እና የፎቶ ግራፍ ማኅበሮች ናቸው›› ብለዋል። ‹‹ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ ጥያቄ አቅርበዋል እሳቸው እናንተን አይወክሉልምን?›› ብለን የቪዥዋል አርቲስትስ አሶሴሽን ፕሬዝዳንት አቶ ስዩምን ጠይቀናቸው አቶ እሸቱ የማህበራቸው አባል እንዳልሆኑ በመግለፅ ጥያቄያቸውም ሊወክላቸው እንደማይችል ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው በለጠ የሚቆጫቸው በምክክሩ የማህበራቸው አፍ መሆን ሳይችሉ መቅረታቸው ብቻ ሳይሆን ወቅታዊውን ዕድል ለራሳቸው ጥቅም ባዋሉት በዚህ ጊዜያዊ የምክክር ስብሰባ ሳቢያ በሌሎች ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ዕድል ማጨለማቸው ነው። የህትመት ዋጋ መናር ለአሳታሚዎች ትልቅ ችግር መሆን በዋናነት ሊጠይቁት ያሰቡት የነበረ ጥያቄ እንደነበር ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል። ተወካዮች በአዳራሹ ጥያቄ ከማቅረባቸው በፊት ተገናኝተው ጥያቄውን ይለማመዱት እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። የጊዜያዊ የምክክር ኮሚቴውን ሰብሳቢ አቶ ቶማስ ጌታቸውን ምላሽ ለማድመጥ ወደ እጅ ስልካቸው ብንደውልም ስለማይነሳ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

p Ç T@ S ´ “ —ፎቶ፡- ሲ

ሳይ ጉ

ዛይ

ደርግ ስልጣን የያዘበትን አንደኛ አመት መስከረም ሁለት 1968 ዓ.ም ሲከበር ‹‹ታላቁ የአብዮት በዓል አከባበር-በስዕል››

የሚል ርዕስ ሰጥቶ እንደዚህ ዘግቦታል

አዲስ ዘመን ጋዜጣና ‹‹ልማታዊ›› ዘገባዎቹ በሁለቱ መንግስታት

ኢህአዴግ አዲስ አበባ የተቆጣጠረበትን የግንቦት 20 በዓል አስመልክቶ አከባበሩን ‹‹የግንቦት 20 ሀያኛ አመት የድል በዓል

አከባበር-በፎቶግራፍ›› ሲል እንዲህ አቅርቦታል

ነገስ?

Page 11: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç T@ S ´ “ —

ጳውሎስ ኞኞ ይሰራበት በነበረው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የ‹‹አንድ ጥያቄ አለኝ›› አምድ የካቲት 1964 ዓ.ም. እትም ላይ ‹‹እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በብዛት የሌለው ስም የቱ ነው?›› የሚል ጥያቄ ቀርቦለት፣ ‹‹ኞኞ ነው›› ሲል መልሷል። የተጠየቅከው አንተ ብትሆን ደግሞ ‹‹ማንዶዬ›› የምትል ይመስለኛል።አዎ፣ ማንዶዬ የተለመደ ስም አይደለም። አባቴ የደቡብ ሰው ነው፤ የወላይታ። የስሙ አቻ የአማርኛ ቃል ‹‹ማንን ተክቼ›› እንደ ማለት ነው። አንተን የሚያስታውስ ‹‹እሁድ የእቁብ ጠላ›› የሚለውን ኮሜዲያዊ የሙዚቃ ስራን አይዘነጋም።የዘፈኑ የዜማና የግጥም ደራሲ ንጉሱ ረታ ይባላል። በወቅቱ ጠጪ ስለነበርኩ፣ ይመለከተኝ ስለነበር ለእኔ ሲሰጠኝ ደስ ብሎኝ ተጫወትኩት። በርካታ ጣሳ ጠላ ትጠጣ እንደነበር ሰምቻለሁ። ምን ያህል ትጠጣ ነበር?ኦው! ጠዋት ተነስቼ ጠላ ነበር የምጠጣው። [ይጠጣ የነበረው ዶሮ ማነቂያ ውስጥ በሚገኘው ሾፌር ሰፈር ነበር።]

ጠዋት ከ40 በላይ ብርጭቆ ትጠጣ ነበር አሉ …ያኔ በብርጭቆ አይለካም እንጂ ከዚያ በላይ ጠጣ ነበር። ጠላ የምንጠጣው ጠዋት ጠዋት ብቻ ነበር። ከዚያ በኋላ ወደ ካቲካላ፤ ጠጅ እንቀጥላለን። እስከ ምሽት ድረስ መጠጣት ነበር። [በወቅቱ የሁለት ጣሳ ጠላ ዋጋ ስሙኒ ነበር።]

ከ60 ዓመት የሕይወት ተሞክሮህ አንፃር ስታየው፣ ‹‹ባልፈጠር ያመልጠኝ ነበር›› የምትለው ነገር ምንድን ነው?መጠጥ ካቆምኩ 24 ዓመት ደፍኖኛል። በፊት ብሞት መጠጥ ገደለው እንጂ እግዚአብሔር ገደለው አይባልም ነበር። ኖሬ ይህን በማየቴ ደስ ይለኛል። በመኖሬ ብዙ የሰው ፍቅር አግኝቻለሁ። ባልፈጠር ይህ የሕዝብ ፍቅር ከየት ይገኝ ነበር? ከሰውነትህ አካላት መካከል ቢቀነስም አይጎዳኝ የምትለው አለ?ሁሉም የሰውነት አካላት ጠቃሚ ናቸው። ኧረ! ይቀነስ የምለው የለም። የፊት ገፅታህ ቁጡ ያስመስልሀል። ዝምታህም የሚያስጨንቅ አይነት ነው ልበል? ብዙዎች እንደዚያ ይሉኛል። ከመናገር ይበልጥ ማዳመጥ ደስ ይለኛል። ብዙ

ክርክር አልችልም። የማውቀውን ነገር እንኳን ‹‹አይደለም›› ቢሉኝ ከምከራከር ይልቅ አምኜ ብለያይ ብዬ ስለማምን እተወዋለሁ። ዝም እና ኮስተር በማለቴ ብዙ ሰዎች የምጫወት አይመስላቸውም። ድሮ ድሮ ጠጅ ቤት ውስጥ ዝም ስለምል ተደባዳቢ መስላቸው ነበር። አንድ ሽማግሌ ከቀረቡኝ በኋላ፣ ‹‹ለፀብ የተዘጋጀህ እንጂ ተጨዋች ሰው አትመስለኝም›› ሲሉ ተዋውቄያቸው ለብዙ ዘመን ጓደኛ ሆነናል።

የ‹‹እኔ›› የምትለው መልካም ነገር ምንድን ነው? በጎ ነገሮችን ለመስራት እሞክራለሁ። በጓደኞቼ ላይ አንዳንድ ችግሮች ሲመጡ በአቅሜ መተባበር እፈልጋለሁ። ሜሪ ጆይ የተራድኦ ድርጅት ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እሰጣለሁ። የቀይ መስቀል አባል ነኝ። ይህን መሰል በሆኑ በጎ ሥራዎች ላይ ብካፈል ደስተኛ ነኝ።

የመኖሪያ አካባቢ በድርቅና በመሰል ችግሮች ሳቢያ ‹‹ለኑሮ አመቺ አይደለም›› ሲባል ሰፈራ ይደረጋል። የሙያ ሰፈራ ቢኖር ወደ ምን መስፈር ትፈልጋለህ?ወደ ሌላ ሙያ ብዘዋወር መስራት የምችል አይመስለኝም። እንደገና ልጅ ብሆን ግን እግር ኳስ ተጨዋች ብሆን ደስ ይለኛል። ከሰራኸው ቲያትር ውስጥ እንደው ቢቻልና በተመሳሳይ ሰዓት ‹‹ተዋናይ ሆኜ ብትሰራው፣ ተመልካች ሆኜ ባየው›› ብሎ ያስመኘህ አለ?በ1964 ዓ.ም ‹‹ጤና ያጣ ፍቅር›› የሚል ሙዚቃዊ ድራማ ሰርተን ሲጠናቀቅ የነበረው ጭብጨባ በጣም ከፍተኛ ነበር። ተመልካችም ሆኜ የማየው ቢሆን እሱን መርጥ ነበር። ሌላው ቀርቶ በፊልም ተቀርጾ እንኳን ባየው ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን አልተደረገም።

ምላሽ ባለማግኘትህ ብቻ አምነህ የተቀበልከው ነገር አለ?አለ። እሱም በመስሪያ ቤታችን (በአዲስ አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ) ያለውን የሠራተኛ ደረጃ አመዳደብ ነው። አንድ ጊዜ ኤክስፐርት ያደርጉሀል፣ ሲፈልጉ ተዋናይ ያደርጉሀል። እናም ሳላምንባቸው ብዙዎቹን ነገሮች ተቀብያለሁ። ‹‹ለምን?›› ብትለኝ እነሱ ማሟላት አለብህ የሚሉኝን የትምህርት ሰርተፍኬት ስለማላሟላ ነው። እኔ ትምህርት ያቆምኩት 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ላይ ስለሆነ ያሉኝን መቀበል ነው። በችሎታ /በሙያ ፈትነው ኤክስፐርት፣ ተዋናይ ስድስት ተብዬ ነበር። እንደገና በቢ.ፒ.አር ተራ ተዋናይ ተብዬ ወደ

ታች ስወርድ በዚህ ምክንያት ጡረታ ወጥቻለሁ። [ጡረታ 1,067 ብር ያገኛል]

ባለፈው ሰኞ የጥበብ ‹‹ባለሙያዎች›› ከጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ባደረጋችሁት ስብሰባ ላይ አንተ የተሳተፍክበት ተውኔት አቅርባችኋል። ‹‹ልቤን የጭብጨባ ቡፌ አጥግቦት ሆዴ ባዶ መሆኑን እያወቅኩ ይኸው እስከዛሬ ዘለቅኩ›› የሚል የጥበብ ሰዎች ኑሯችሁ አሳዛኝ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ ተውኔት ከአፍህ ወጥቷል። ይህ መሰል ነገር ተደጋግሞ ይነሳል። እናንተ የሙያው ፀባይ ታዋቂ ያደርጋችኋል፣ ጭብጨባ ይቸራችኋል። አንድ የሕክምና ዶክተር፣ አካውንታንት፣ ሥራ አስኪያጅ አይጨበጨብላቸውም እንጂ ትልቅ ነገር ይከውናሉ። የእናንተ ታዲያ ምን ስለሆነ ነው ተደጋግሞ የሚነሳው?

የቴሌቪዥን ድራማ፣ ፊልም እና ሌሎች የጥበብ ውጤቶችን ስንሰራ የሚከፈለን ገንዘብ አነስተኛ ነው። ይህ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ የቅጂ መብት በአግባቡ አለመከበር ነው። በእኛ ሥራ ምንም ነገር ሳይሰሩ ትልቅ ሀብታም የሆኑ ሰዎች አሉ። አሁን በህይወት የሌለ አረብ አገር ይኖር የነበረ አንድ ጓደኛችን፣ ‹‹የሚገርማችሁ የእናንተ ድራማ ሲተላለፍ እዚያ እሸጥ ነበር። ገንዘቡ የቤት ኪራይ ለመክፈል ይረዳኝ ነበር›› ብሎኛል። እሱ ግልፅ ስለሆነ ነገረን እንጂ ብዙዎች ተጠቃሚ የሆኑ አሉ። ይህ ደግሞ ተገቢውን ህይወት እንዳንመራ አድርጎናል እንጂ፣ ‹‹እኛ ከሌላው ህዝብ የተለየን ነን›› ማለት አይደለም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሙሉ መጠሪያ ስማቸውን ታውቀዋለህ? [እየሳቀ] አታስቸግረኝ … በእውነት ጥራ ብትለኝ አልችለውም። [እንደምንም ሞክረው ብዬው ዝግ እያለ ቀጠለ] ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ አክሱም ወይጨጌ እንደዚህ የሚል አለበት እና አዎ እንደዚያ ነው …·ረ ይጠፋኛል። [ለማንኛውም ፋንቱ እኔ ልሞክር… ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣… ኦው! ፋንቱ የቀረ ካለ ተባበረኝ፤ እንሞላዋለን፣ ስለ ትብብርህ አመሰግናለሁ።]

ለ42 ዓመታት በኪነ-ጥበብ ውስጥ ቆይታ ያደረገ

አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው። ‹‹እሁድ የእቁብ ጠላ›› እና

ከፀሐይነሽ በቀለ ጋር የተጫወተው ‹‹የት ሄደሽ ነበር … ››

የሚሰኙት ኮሜዲያዊ ዜማዎች (ሙዚቃዊ ድራማዎች) አይረሴ

አድርገውታል። 40 ገደማ የሚሆኑ የመድረክ ቲያትሮች ላይ

ተሳትፏል። ‹‹የቅጂ መብት አለመከበር ተገቢውን ጥቅም

እንዳናገኝ አድርጎናል›› የሚለው ፋንቱ ማንዶዬ፣ አንዳፍታ የአቤል ዓለማየሁን ጥያቄዎች ይመልሳል።

አ ፍታ1‹‹በቢ.ፒ.አር ተራ ተዋናይ ተብዬ

ወደ ታች በመውረዴ ጡረታ ወጥቻለሁ››ፋንቱ ማንዶዬ [አርቲስት]

“ኦዉሽ” ነጠላ ግጥም ተለቀቀየአረንቻታ ማስታወቂያ ባለቤትና የአርከባስ መፅሔት ዋና አዘጋጅ

የሆነው ጀሚል ሰኢድ በብዕር ስሙ ኪፍያፍ (ሃጅ) “ኦውሽ” የተሰኘ ለአባይ ዶክመንተሪ ቅኔ ሲዲ አሣተመ። ግጥሙን ታዋቂ ምሁራን ገምግመውታል። ማጀቢያ ሙዚቃውን ድምፃዊ ማሚላ (አውአውባዴ)፣ ቅንብሩን ካሙዙ ካሣ ሰርተውታል። ሲዲው በነፃ የሚሠራጭ እንደሆነና ሙሉ ወጪው ሃያ ሺህ ብር መሆኑን የገለፀው ጀሚል (ኪፍያፍ) በቀጣይነት ክሊፕ ተሰርቶለት በመላው አለም እንደሚሰራጭ፤ በቀጣይም ሙሉ ስራውን ለህዝብ እንደሚያቀርብ እና ለህትመት የተዘጋጁ መፅሐፎቹን እንደሚያሳትም ገልጿል።

“ዘኪዮስ” እና “ፔሌማ” ፊልሞች ይመረቃሉ በሱራፌል ተምትም ተደርሶ በሄሮን ስቱዲዮ የቀረበው “ዘኪዮስ”

የተሰኘ ፊልም ነገ በ8፡00 ሰዓት በአለም ሲኒማ በልዩ ሁኔታ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ይመረቃል። የፊልሙ ጭብጥ አንድ በቁመቱ ድንክ የሚባል ሰው ለህይወት ስኬት ሲታትር የሚያሳይ ሲሆን በርካታ የማህበራዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

ሸዋፈራሁ ደሳለኝ፣ ፍቅርተ ጌታሁን፣ ሞዴል ሰብለ ወንጌል ፀጋ፣ አለምሰገድ ተስፋዬ ገነነ አማረ እና ሌሎችም ከ120 በላይ አርቲስቶች የተካፈሉበት ይህ ፊልም ከ600 ሺህ ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

እንዲሁም በባሮክ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው የደራሲና ዳይሬክተር ሜሊ ተስፋዬ “ፔሌማ” ልብ አንጠልጣይ ፊልም የፊታችን ሰኞ ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር፣ በአለም ሲኒማ በዮፍታሔ ሲኒማ፣ በሴባስቶፖል እና በሌሎችም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል።

ፊልሙ “አዋቂ ጠንቋይ” ጋ የሚሄዱ ሦስት ጓደኛሞች ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን መልካም የመሰለ ክፉ ነገር ሁሉ መጨረሻው ውድ ዋጋ የሚያስከፍል ስለመሆኑ የሚያስቃኝ መሆኑን ፕሮዳክሽኑ ገልጿል።

በፊልሙ ላይ ማክዳ ሃይሌ፣ ማስረሻ ደጌ፣ ሄለን ቸርነት፣ ናትናኤል ጌታቸው እና ሌሎችም ተውነውበታል።

‹የአቤ ቶኪቻው ስላቆች› በመጽሐፍ መልክ ቀረበአቤ ቶኪቻው የተሰኘ የብዕር ሥም በመጠቀም በአገሪቷ ፖለቲካዊ

ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ በመጻፍ የሚታወቀው አበበ ቶላ በተለያየ ጊዜ ያቀረባቸውን 27 ስላቃዊ መጣጥፎች በመፅሐፍ መልክ ታትመው ለአንባብያን ቀረቡ።

ከእነዚህ 27 ሰላቃዊ መጣጥፎች መሀል አብዛኞቹ በሳምንታዊዋ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ለንባብ የቀረቡ መሆናቸውን ፀሐፊው ገልጿል። አበበ ቶላ ‹‹ስላቆች ከአቤ ቶኪቻው›› በሚል ርዕስ ለአንባቢያን ያቀረበው ይህ መፅሐፍ ባለ 152 ገፅ ሲሆን በ26 ብር ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የብልጽግና ቁልፍ ቁጥር 4 ታተመ በምንኖርበት የውድደር ዓለም ላይ ዕድገትን በመሻት ተግተው

ለሚሰሩ፣ የተሻሉ የዕድገት ስልቶችን በአማራጭነት የያዘ ነው የተባለለት ‹‹የብልፅግና ቁልፍ ቁጥር 4›› መፅሐፍ ለህትመት በቃ።

የመፅሐፉ አዘጋጆች በኢተርፕሬነርሽፕ አሰልጣኝነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ወሮታው በዛብህና የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙ ናቸው።

‹‹የብልፅግና ቁልፍ ቁጥር 4›› መፅሐፍ ባለ 149 ገፅ ሲሆን፣ ለገበያ የቀረበው በ29 ብር ከ99 ሳንቲም ነው።

“የንፁሐን ሰቆቃ በጓንታናሞ” እና “ሰውየው ማነው” መፅሐፎች ለገበያ ቀረቡ

የታሪኩ ባለቤት ሙራት ኩርናዝ ከሔልመት ኩን ጋር በመተባበር “የንፁሐን ሰቆቃ በጓንታናሞ” የሚል ርዕስ ያለውና ንፁህ ሰው ለአምስት ዓመታት በጓንታናሞ እስር ቤት ያሳለፈውን ስቃይ በዝርዝር የሚተርክበት እውነተኛ ታሪክ መፅሐፍ በቢኒያም አለማየሁ ተተርጉሞ ለገበያ ቀረበ። መፅሐፉም 239 ገፆች አሉት።

በተያያዘ ዜና በቺካጎ አሊኖስ ዲፖል ዩኒቨርስቲ የታሪክ ፕሮፌሰር በሆኑት ዶ/ር ቶማስ ሞካይቲስ የተፃፈው ‹‹Osama Bin Laden biography›› በመሐመድ ኢብራሂም ሲራጅ አመካኝነት ‹‹ሰውየው ማነው›› በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለህትመት በቅቷል።

ለበርካታ ዓመታት የዓለም ህዝብ የመነጋገሪያ ርዕሥ የነበረውና በቅርቡ በአሜሪካዊያን ኮማንዶዎች ፓኪስታን ውስጥ የተገደለውን የኦማሳ ቢንላደንን የህይወትና የህልፈት ታሪክ ያካተተው ‹‹ሰውየው ማነው?›› መፅሐፍ 230 ገጾች ያሉት ሲሆን ለአንባቢያን የቀረበው በ35 ብር ዋጋ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

Page 12: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

የብርቱካን የመኸር ጊዜ

የቢስ አትክልትና ፍራፍሬ አክሲዮኖች

በፍጥነት በመሸጥ ላይ ናቸው።

እርሶም ፈጥነው የዚህ ግዙፍና ትርፋማ

አክሲዮን ባለቤት ይሁኑ!!!

12 እ ን ግ ዳ

ከቅ ን ጅ ት መሰባበር በ ኋ ላ ሁ ለ ት ኃ ይ ሎ ች ጎ ል ተ ው

ወጥተዋል። አንዱ በሰላማዊ ትግል እቀጥላለሁ ያለው፣ በወ/ት ብርቱካን የሚመራው የአንድነት ፓርቲ ሲሆን ሌላው ደግሞ በሰላማዊ መንገድ መታገል ያበቃለት ስለሆነ ሁሉንም አማራጮች መጠቀም ግድ ይላል የሚል አቋም የያዘው፣ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው የግንቦት-7 ንቅናቄ ነው። እነዚህ ሁለት የተለያዩ የትግል ስልቶች የያዙ ኃይሎች አንዳንድ የሚመሳሰሉባቸው የጀርባ ታሪክም አላቸው። የሁለቱም ኃይሎች መሪዎች ታዋቂ የቅንጅት አመራር አባላት የነበሩና ለቅንጅቱ መፈጠር ወሳኝ አስተዋጽኦ የነበረው የቀስተደመና ፓርቲ አመራር አባላት የነበሩ ናቸው። ሁለቱም ኃይሎች በአገር ቤትም ይሁን ከአገር ውጭ ባለው የቅንጅት ደጋፊ ሕዝብ፣ በተለይም በወጣቱ ትውልድ፣ ጠቀም

ያለ ተቀባይነት ያላቸው ኃይሎች ናቸው።

ሌላው የሚያመሳስላቸው ነገር ደግሞ ሁለቱም ኃይሎች

ነገ ሰኔ 5 ቀን ከሰኞ ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀመራል።

በዓለም ሲኒማ ኤድናሞል ሲኒማአምባሳደር ሲኒማእምቢልታ ሲኒማ

ዮፍታሄ ሲኒማ እንዲሁም በመላው አገሪቱ

በተመሳሳይ ሆኔታ የሁለት ጎራ ሰለባ መሆናቸው ነው። በአንድ

በኩል በቅንጅቱ መሰባበር ምክንያት ሲፈነድቅ የቆየው የወያነ ሥርዓት የነዚህ ኃይሎች ተጠናክሮ መውጣት አስደንግጦታል። በሌላ በኩል ደግሞ

በእነዚህ ኃይሎች መበለጣቸው የተረዱ የተለያዩ የተቃዋሚ ኃይሎች (ተቃዋሚዎችን ለመቃወም የተቋቋሙ ተቃዋሚዎች ልንላቸው እንችላለን) በተለያየ መንገድ በአንድነት ፓርቲና በግንቦት-7 ንቅናቄ ላይ ሲዘምቱና አሉባልታ ሲነዙ ይስተዋላሉ። ስለዚህ አንድነት ፓርቲና ግንቦት-7 ከሁለት አቅጣጫ ጦርነት እንደተከፈተባቸው መገንዘብ ያስፈልጋል።

እንግዲህ የወ/ት ብርቱካን ለዳግም እስር መዳረግ ስንፈትሽ ይህንን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ መሆን አለበት። ከዚያ በፊት ግን የወያነ ሥርዓት አመራር የሚፈራውን ኃይል ለማጥቃት ምን ያህል ርቆ እንደሚሄድ እንመልከት።

ሥርዓቱ አንድን ተቃዋሚ ግለሰብ ወይም ኃይል ሲያሳድድ ካየን ተሳዳጁ ግለሰብ ወይም ኃይል ለሥርዓቱ አስጊ ሆኖ ተገኝቷል ማለት ነው። ለምሳሌ የግንቦት-7 መሪዎች በሌሉበት የሞት ፍርድ ሲወሰንባቸው፤ ማየት ያለብን የፍርድ ሂደቱን ሳይሆን ሰዎቹ ሥርዓቱን የሚፈታተን አንድ ነገር በእጃቸው ጨብጠዋል ማለት ነው። በተረፈ ከውጭ አገር በሪሞት ኮንትሮል መንግስት ሊገለብጡ ሞክረዋል ብሎ መክሰስ አስቂኝ ኮሜዲ ካልሆነ ሌላ ትርጉም የለውም።

በዚህ አጋጣሚ እኔም አንዱ እማኝ ነኝ። በአንድ ወቅት ሥርዓቱ እኔን በአስጊነት ፈረጀኝና ወደ ተጠጋሁባት አገር (ዴንማርክ) ድረስ ዘልቀው “በጦር ወንጀለኛነትና በሰብዓዊ መብት ገፈፋ” የምፈለግ መሆኔን ጠቅሰው ከሰውኛል። ይህን ያደረጉት፣ ማንም ሰው ሊረዳው እንደሚችል፣ እኔ በጦር ሜዳ ተገኝቼ ሰው ስልገደልኩ ወይም የመንግስት

አቶ አብርሃም ያየህ

የብርቱካን የመኸር ጊዜ

በ ገፅ 20

ከህወሓት ጋር ተሰልፈው በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ጀግንነት

የፈጸሙ ታጋይ ሴቶች (የታገሉለት ዓላማ ውሃ በልቶት መቅረቱ ቢያሳዝንም) ዛሬ

የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እናውቀዋለን። በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ ውስጥ

ስንት ሴቶች አሉ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ምንም የሚል ሆኖ እናገኘዋለን።

Page 13: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

እ ን ግ ዳ

14

ዓ ለም አቀፍ

በአለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር)

‹‹ሲድ›› (‹‹SEED››) እንደአስተማሪዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ አርቲስቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የዩኒቨርስቲ ተቋማት ተማሪዎች እና የማኅበረሰብ መሪዎች ያሉ ላቅ ያሉ ሥራዎችን ላከናወኑ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች እውቅና መስጠት ዓላማው ያደረገ፣ ዳያስፖራ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እ.አ.አ በ1993 የተመሰረተ፣ ወገንተኛ ያልሆነ የሲቪክ ማኅበር (ወይም መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት - መያድ) ነው፡፡

በግንቦት 21/2003 ዓ.ም፣ በዋሽንግተን ዲሲ ጆርጅ ታወን ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ ማዕከል ውስጥ ‹‹ሲድ›› ባዘጋጀው ዓመታዊ የ‹‹ሲድ›› ሽልማት የዕራት ፕሮግራም ላይ ፕ/ር አለማየሁ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ይህም ኮመንታሪ በወቅቱ ያደረጉት ንግግር ሆኖ ሰፋ ባለ መልኩ ራሳቸው ያዘጋጁትና እኛ ወደ አማርኛ የመለስነው ነው፡፡

የ‹‹ሲድ›› ሥራ አስፈፃሚ ቦርድና የቦርዱ ሊቀ-መንበር ፕ/ር መላኩ ላቀው እኔን አንዱ የ2011 ተሸላሚ አድርገው በመምረጣቸው አመሰግናለሁ።

የድርጅቱ ስያሜ በራሱ አነቃቂ ነው። ፍሬዎች ይበቅላሉ፣ ያቆጠቁጣሉ፣ ሥር ሰድደውም ያድጋሉ። ቆይቶ የሚያምር አበባ ሆነው ፈክተው ለቀጣይ ትውልዶች አዳዲስ ፍሬዎችን ያራግፋሉ። ላለፉት አስራ-ዘጠኝ ዓመታት ‹‹ሲድ›› አድጓል፣ አድጎም አብቦ ፈክቷል፡፡ በዚህም ምሽት እውቅና በሚሰጣቸው እጅግ ከፍተኛ ስራ ባከናወኑ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ፊት የ‹‹ሲድ››ን ፍሬዎች እንመለከታለን።

ለኢትዮጵያዊነትና ለሰብዓዊነት የራሳቸውን ጥቂት አስተዋጽኦዎች ለማድረግ ያሹ ኢትዮጵያውያንን እውቅና ለመስጠት ያለመ እንደ‹‹ሲድ›› ያለ ድርጅት በመኖሩ ኮርቻለሁ፡፡ እናም ሁላችንም ‹‹ሲድ››ን ልናከብረውና ርዕዩተ-ዓለም፣ ፖለቲካዊ ድጋፍ፣ ብሄር፣ ዜግነት፣ ሃይማኖት፣ ዘር ወዘተ የማይለይ የኢትዮጵያውያንንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን አስተዋጽ እውቅና ለመስጠት ግቡ ያደረገንና ወገንተኛ ያልሆነ የሲቪክ ማኅበር ለመመስረትና ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል እንዲቀጥል ለማድረገ ያለሙ የድርጅቱን አባላትና የድርጅቱን ቦርድ እንኳን ደስ አላችሁ ልንላቸው ይገባል።

ግለሰቦች በኅብረት በመሰባሰብ በሰቪክ ተቋማት አማካኝነት ምን ሊያሳኩ እንደሚችሉ የሚያሳይ አንፀባራቂ ምሳሌ ነው - ‹‹ሲድ››።

ለመላ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አስተዋፅኦዎችን አበርክተው እውቅና ከሚሰጣቸው ሰዎች መካከል እኔ አንዱ ሆኜ በመመረጤ ኩራት ይሰማኛል፣ ምስጋናዬም ታላቅ ነው፡፡ ወ/ሮ አበበች ጎበና ወላጆቻቸውን በሞት ከተነጠቁና አሳዳጊ ከሌላቸው ህፃናት እና ጾታዊ ጥቃት ከተፈፀመባቸው ሴቶች ጋር በተያያዘ የህይወት አድን ስራቸው በበርካቶች ‹‹አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ›› ተብለው ይጠራሉ። ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ በርካታ የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቶችንና ሌሎች አያሌ የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት የሆኑ አትሌቶችን አሰልጥነዋል። ፕ/ር ረዳ ተ/ሃይማኖት ለፖልዮ መጥፋት ነጥረው የወጡ አስተዋጽኦዎችን ያበረከቱና በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ዝቅተኛ የጤና አገልግሎት ካሉባቸው ስፍራዎች በአንዱ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ድጋፍ አድርገዋል። አቶ እዝራ ተሾመ ለፓሊዮ መወገድ የላቁ አስተዋጽኦዎችን በማድረጋቸው (እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ድሃ ሴቶችንና ህፃናትን ለማጠናከር ድጋፍ በማድረጋቸው) በበርካቶች የሚታወቁ ናቸው።

እንዲሁም ካለፉ በኋላ በዛሬዋ ምሽት በስራዎቻቸው እውቅና የሚሰጣቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን አሉ። ፕ/ር ሁሴይን አህመድ የተለየ ጉብዝና የነበራቸው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የእስልምናን የአስተሳሳሪነት ሚና ብርሃን የፈነጠቀ ቀዳሚ የምርምር ስራ ያበረከቱ ነበሩ፡፡ ዶ/ር መላኩ ኢ. በየነ ከአሜሪካን ዩኒቨርስቲ በመጀመርያ የተመረቁ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ በ1930ዎቹ በኢጣሊያ ወረራ ላይ የፓን-አፍሪካ ንቅናቄን ያደራጁ

እየተመለከቱ ወደ ፊት ይቀዝፋሉ - ይሸመጥጣሉ። በያኔው ትውልድ ውስጥ ያለን የተወሰንነው ነገሮች እንዲከሰቱ እንፈልጋለን። አብዛኞቻችን እንዲሁ ተቀምጠን ነገሮች እንዲሆኑ እንመኛለን። የእኛዎቹ ወጣቶች ግን እንዲሆን ያደርጉታል! ያ ነው እንግዲህ ድልድይ ልንሰራለት የሚገባን ልዩነት፡፡

ከረዥም ጊዜ በፊት የያኔው ትውልድ አባላት ወደሐሰባዊነት መንገድ ጀምረን በኃላ በመንገዳችን የሆነ ስፍራ ላይ መድረሻው ‹‹እውናዊነት›› ወደተባለ አቅጣጫ ዞርን። እዛም በስግብግነት፣ ሥልጣን፣ ኃብት፣ ዝና እና የተቀረውን በጠቅላላ በመቅደሱ ላይ ማምለክ ጀመርን።

በመጨረሻም የሄድንበት የእውናዊነት ጎዳና ከንቱ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ጨለምተኞች ሆንንና ሁሉም ለራሱ ጠቅም ብቻ በቆመበት ዓለም ውስጥ፣ ብርቱው ብቻ በህይወት ይቆያል ስንል ደመደምን፡፡ ለደካሞችና ራሳቸውን መከላከል ለማይችሉ ስቃይ ግድ የለሾች/ራስ ወዳዶች ሆንን፤ ከጉስቁልናቸው አይኖቻችንን አዞርን፤ ለጥልቅ ስቃትይ ለቅሶአቸው ጆሮአችንን ደፈንን፤ ሥልጣን በያዙ ለተፈፀሙባቸው ኢ-ፍትሃዊነቶች አንደበታችን ታሰረ።

አሁን መነሻችን ወደ ሆነው ሃሳባዊነት መመለስ አለብን፤ ‹‹የለየለት›› ሽሙጠኛው ጆርጅ ካርላይን ‹‹እያንዳንዱ ጨለምተኛ ሰው ውስጥ የተበሳጨ ሃሳባዊ ሰው አለ›› ሲል ተናግሮ ነበር። ምናልባት ያን የተበሳጨ /የተናደደ/ ሃሳባዊ በጨረፍታ በራስዎ ውስጥ ተመልክተው ሊሆን ይችላል። ሃሳባዊ በመሆኑ የሚያሳፍር ምንም ነገር የለም። ያለፈው ክ/ዘመን የዓለማችን ታላላቅ የፖለቲካና የሞራል መሪዎች ሃሳብያውያን ነበሩ፡፡ ታላቅ ተላሚዎች ነበሩ ምክንያቱም ልክ እንደ ወጣቶች በይበልጥ የተሻለ ነገን በአይነ ህሊና መመሰል እና ማለም ይችሉ ነበርና።

ጋንዲ ለቅኝ አገዛዝ አለቆቻቸው እንዲህ ሲሉ ነበር የተናገሩት፡- ‹‹በመጨረሻ ሕንድን ለቅቃችሁ ትወጣላችሁ ምክንያቱም እንግሊዛውያኑ 350 ሚሊየን ህንዳውያን አንተባበርም ብለው እምቢኝ ካሉ እነዚያን ህንዳውያን እንዲሁ በቀላሉ መቆጣጠር አይቻላቸውም።›› ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ‹‹አንድ ቀን በቀዩ የጆርጅያ ጉብታዎች ላይ የቀድሞ ባሪያዎች ልጆችና የቀድሞ ባሪያ አሳዳሪዎች ልጆች በወንድማማችነት ጠረጴዛ በአንድነት እንደሚቀመጡ›› አልሞ ነበር። ኔልሰን ማንዴላ ‹‹መቼም መቼም ይህች ውብ ምድር ከእንደገና አንዱ ሌላኛውን የሚጨቁንባት ምድር አትሆንም›› ሲሉ ቃል ገብተዋል። እነዚህ ሃሳብያውያን በጊዜያቸው መሳቂያ ነበሩ። በመጨረሻ ግን ድል የእነርሱ ሆነች፤ በእነርሱም ትግል፣ አመራር እና መርሆዎች ዓለም የበለጠች የተሻለች ስፍራ ሆነች።

በተጨማሪ ሃሳባዊ መሆን ማለት ዝግጁ፣ ጊዜ ያለፈባቸውን አመለካከቶች፣ እምነቶችና ፍርሃቶች ለመቀየርና ለመለወጥ መቻል እና ፍቃደኛ መሆን ማለት ነው፡፡ የጋንዲን አስተምህሮ ለመገንዘብ ረዥም ጊዜ ወስዶብኛል፡- ‹‹በዓለም ውስጥ ለመመልከት የምትፈልገውን ለውጥ ሁን።›› ዛሬ እኔ የማስበው ከሰብዓዊነት አንፃር እንጅ ከብሄር ወይም ከዜግነት (አገር) አነፃር አይደለም። በአንድ ወቅት በጭካኔ ፊት ዝምታን መርጬ ነበር፡

እውነት ነው የማልመለስ የጭቆና፣ ኢ-ፍትሃዊነተ እና አምባገነንነት ተቺ ነኝ። አንዳንዶች በማደርጋቸው ጥረቶች መሳለቃቸውና እኔን የዋህ ማለታቸው የሚያጠራጥር አይደለም። ካለአንዳች ጥርጥርም ጥቂት ሃሳባውያን ዓለምን ሊቀይሩ እንደማይችሉ ማወቅ እንደሚገባኝ አውቃለሁ። ሆኖም ግን ‹‹በጥልቀት የሚመረምሩና የቆራጥ ዜጎች ስብስብ ዓለምን መለወጥ መቻሉን በጭራሽ አትጠራጠር፤ እርግጥም ብቸኛው ዓለምን የለወጠው ያ ነው›› ሲል ትዝብቱን ባስቀመጠው ማርጋሬት ሚድ ተረታሁ።

ከዚህም በተጨማሪ አንድን መጥፎ ሁኔታ ለሌሎች መልካምነት ማዋልና መጠቀም ማለትም ነው - ሃሳባያዊነት፡፡ ከበርካታ ዓመታት በፊት፣ ባለቤቴ ገና በዕንጭጭነቱ ደረጃ ላያ ያለ፣ ሥር ያልሰደደ የጡት ካንሰር እንዳለባት በየዓመቱ በምታደርገው ‹‹ናኖግራም›› አማከኝነት ታወቀና ስኬታማ ህክምና ወስዳ ከካንሰሩ ነፃ ሆነች፡፡ ምንም እንኳን ባለቤቴ እጅግ ስኬታማ ህክምና ግልጋሎት ብታገኝም፣ እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ሴቶች ግን በቋሚነት ‹‹ናኖግራም›› ባለማድረጋቸው እና የጡት ካንሰር እንዳለባቸው ተመርምረው አንዴ ካወቁ በኃላ በሽታው እንዳለባቸው እውነታውን ከአጋሮቻቸውና ከወዳጆቻቸው በመሸሸግ ከንቱ ሞትን ይሞታሉ፡፡ እርሷም ስለጡት ካንሰር ያለውን የንቃት ለማሳደግና እንዴት ብዙ ህይወት እንዳይቀጥፍ ማድረግ ይቻላል የሚለውን አስመልክታ ‹‹ለኢትዮጵያውያን እህቶቼ ደብዳቤ›› ለመፃፍ ወሰነች፡፡ የተወሰኑ መልካም ያሰቡ የመሰላቸው ሰዎች ግን በበሽታው መያዝ የሆነ የሚያሳፍር ነገር አለው ብለው በገደምዳሜ በማመላከት ሁኔታዋን አደባባይ እንዳታወጣ መከሯት፡፡ እርሷ ራሷ የማትመለስ ሃሳባዊ ነችና በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የጡት ካንሰርን ሥር-ሳይሰድድ በህክምና በእንጭችነቱ መቅጨት የሚቻል የመሆኑን እውነታ ካወቁ፣ ሁሌም የጡት ካንሰርን መርታት ቻላቸዋል የሚል ዕምነት ነበር የነበራት፡፡ ስለጡት ካንሰር አለመነጋገር ከጡት ካንሰር በበለጠ ብዙ እህቶቻችንን እና እናቶቻችንን ይገድላል፡፡ መረጃ በመስተት በጡት ካንሰር ላይ ሁላችንም እንዝመት!

አስቀድሜ ያወሳሁትን የትውልድ ልዩነት ማስወገድ ያስፈልገናል፡፡ ልክ እንደኛዎቹ ወጣቶች አንድ አይነት ቋንቋ የምንናገር ከሆነ ያን ማድረግ እንችላለን፡፡ እርስ በእርሳችን ስንማማር ነው ልነቱን መቅረፍ የምንችለው፡፡ ስለነገውና ሊያሳኩ ስለሚችሏቸው ታላላቅ ነገሮች ሊያስተምሩን ይችላሉ፤ እኛም ስላለፈው፣ እኛ ፈፀምናቸው ስህተቶች እንዴት ማሳወገድ እንደሚችሉ፣ እና በትክክል ስለፈፀምናቸው ነገሮች እናስተምራቸዋለን፡፡

አንዳንዶች የእኔ ድልድይ-ገንቢ ሃሳቦች ተግባራዊ ሊሆኑ የማይችሉ፣ የማይሳኩ፣ የማይመስሉ እና የህልመኞች ነገሮች ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን እላለሁ፣ ምላሹንም በጥያቄ እሰጣለሁ፡- ‹‹የፈለገው ቢሆን ታዲያ ፍፁም፣ ሁሉም ከተሟላላት ኢትዮጵያ ታዲያ ምንድን ነው የሚጠበቀው?!?

በሁሉም ሃሳብያውያን ትግል ውስጥ ልክ ጋንዲ እንዳስተማሩት ውጤቱ ሁሌም አንድ አይነት ነው፡- ‹‹መጀመርያ ትኩረት አይሰጡህም፤ በመቀጠል ይስቁብሃል፤ ከዚያም ይፋለሙሀል፤ በመጨረሻ ግን አሸናፊ ትሆናለህ፡፡››

ከእኛዎቹ ወጣቶች ጎን ከሆንን በእርግጠኝነት ድሉ የእኛ ነው፡፡ ካላመናችሁኝ በቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ . . . ካሉ ወጣቶች ጋር አውሩ፡፡ እላለሁ፡- በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የወጣቱን አብዮት እንቀላቀል፡፡

ለሁላችሁም፣ እና በተለይ ደግሞ እዚህ ምሽት ለተገኛችሁ ወጣቶች የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝ ሁላችንም ለታፈኑ ድምፃቸው ልንሆን፣ ልንቆምላቸው ያስፈልገናል የሚለው ነው፡፡ በቦብ ማርሌይ ቃላት ‹‹Get up, stand up, stand up for your rights (and their rights too)! Don’t give up the fight!›› እላለሁ፡፡ ለውጥ አንድ በአንድ ሰውን በመለወጥ ለውጥ እውን እንዲሆን እናድርግ፡፡

‹‹ሲድ››ን እና እኛን ብላችሁ እዚህ ዛሬ የተገኛችሁትን በጠቅላ አመሰግናለሁ!

‹‹የሆነ ሌላ ሰው ከጠበቅን፣ አሊያም ሌላ ጊዜ የምንጠብቅ ከሆነ ለውጥ አይመጣም፡፡ እኛኑን ነበር እየጠበቅን የነበረው፡፡ የምንሻው ለውጥ እኛው ራሳችን ነን፡፡››

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ

/አለማየሁ ገብረማሪያም፣ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናንዲኖ

የፖለቲካል ሳይንስ ፕሬፈሰር ሲሆኑ ሎስ አንጀለስ በሚገኝ አንድ ተቋም ውስጥ

የህግ አማካሪና ጠበቃም ናቸው/

ኢትዮጵያውያኑ የተስፋ ፍሬዎችነበሩ፡፡

ከእነዚህ ታላላቆችና ጀግኖች መካከል ራሴን ባገኘሁበት ወቅት፣ ‹‹የምጠብቃቸው ቃሎች፣ ከማሸለቤ በፊት የምጓዛቸው ማይልሶች አሉኝ›› የሚሉት የባለቅኔው ሮበርት ፎርስት ቃላት ነበሩ የታወሱኝ፡፡

እነዚህ ግለሰቦች ለእኔ፣ እዚህ ለሁላችንም እዚህ ለተገኘን፣ እና ለመጪዎቹ ወጣት ኢትዮጵያውን ትውልዶች ታላቅ ምሳሌዎቻችን ናቸው።

በዚህ ምሽት ኩራት ብቻ አይደለም የሚሰማኝ፤ ተባርኬያለሁም። በጥረቷ ላገኘችው የላቀ የአካዳሚ ውጤት እና የማኅበረሰብ ግልጋሎት ሽልማት ከምትቀበለው ልጄ አቢጌል ጋር ይህን መድረክ እጋራለሁ። ለመማር አስርት ዓመታት የወሰዱብኝን እርሷ በአስራዎቹ ዕድሜዋ ተክናቸዋለች። ሰው የሚኖርበትን ማኅበረሰብና ዝቅተኛ ዕድል ያላቸውን በኃላፊት (ሞራል)፣ ግዴታ፣ ቁርጠኝነትና በከፍተኛ የአክብሮት ስሜት ግለሰባዊ ኃላፊነትን መውሰድን ያካትታል - እውነተኛ ዴሞክራሲዊ ዜግነት። ወጣቶች ከራሳቸው፣ እንዲሁም ከዕለታዊ ሁከቶችና ብስጭቶች ባሻገር ሲመለከቱ ለመልካምና ለሰብዓዊነት ግዙፍ ኃይል እንደሚሆኑ ከልጄ አቢጌል ተምሬያለሁ።

በዚህ ምሽት ጥቂት ቃላትን ከልቤ ለመናገር እፈልጋለሁ። ከአእምሮዬ በመነጩ ጽሁፎችና ንግግሮች ብዙዎቻችሁ ታውቁኛላችሁ። በየሳምንቱ በኮመንታሪዎቼ የመረጃ፣ ስታቲስቲክስና ማስረጃ ቋንቋን እናገራለሁ። መልዕክቴን ለማስተላለፍ በተቻለኝ አቅም መረጃን በአሳማኝ ትንታኔና መከራከሪያ ደውሬ ለማቅረብ እጥራለሁ። ሆኖም ግን ከልብ ማውራት በጣም አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም የፍሬ-ነገሮች እና የቁጥር መረጃዎችን ጥልቅ ጠለል ድረስ መዝለቅን እና ከእውነታ ሥረ-መሰረት መናገርን ይጠይቃልና።

እውነታው የኢትዮጵያ ወጣቶች የሀገሪቱ የወደፊት ተስፋዎች መሆናቸው ነው፡፡ ከ80 ሚሊየን የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ውስጥ 70 በመቶ የሚጠጋው ወጣት ነው ተብሎ ይገመታል (ከዚያ ውስጥ 50 በመቶ ከ15 ዓመት በታች ነው)፡፡ አንድ ቆየት ያለ የኢትዮጵያ ምሳሌያዊ አነጋገር ይታወሰኛል፡- ‹‹የዛሬ ፍሬዎች የነገ አበባዎች››። ለእኔ ዛሬ በጣም ወሳኙ ጥያቄ በኢትዮጵያ ውስጥና በዳያስፖራ በሚገኙ በእነዚህ የወደፊት አበቦች ዙሪያ ያጠነጥናል።

የቀደመው ትውልድ አባላት ደጋግመን የምንጠይቀው አንድ ጥያቄ አለ፡- ‹‹የእኛዎቹን ወጣቶች ለነገ ለማዘጋጀት ምን ማስተማር እና ማድረግ እንችላለን? ወደ ተሻለች ነገ ልንመራቸውስ እንዴት ይቻለናል?››

ለእኔ ግን፣ ‹‹ዛሬ ከወጣት ኢትዮጵያውን ምን ልንማር እንችላለን?›› የሚለው ነው ትክክለኛው ጥያቄ፡፡

በሁሉም ስፍራ የሚገኙ አብላጫዎቹ ወጣት ኢትዮጵያውያን አንድ የጋራ ‹‹ላዕላይ የሞራል ልዕልና››ን (VIRTUE) ይጋራሉ - ሐሳባዊነትን (IDEALISM)።

መቋጫ የሌላቸው ጦርነቶች፣ ቡድናዊና አንጃዊ ግጭቶች እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ቢኖሩም፣ ዓለምን የተሻለች አድርገን መለወጥ እንችላለን ብለው ያምናሉ። ወጣቶች ነፃነት፣ ሰላም እና እኩል ዕድል ይፈልጋሉ። በርትዕ-አልባነት እና በኢ-ፍትሃዊነት እጅግ ስሜታቸው ይቆስላል፣ ይቆጣሉ። በገንዘብና በሙስና የተጨማለቀ፣ ቅጥፈት ብቻ ነው ብለው በሚወስዱት ፖለቲካ ውስጥ ላለመሳተፋቸው ዋንኞቹ ምክንያቶች ናቸው ብለው ለሚያምኗቸው ኢ-ታዓማኒነት (ቅጥፈት) እና ግብዝነት ያላቸው ትዕግስት ኢምንት ነው፡፡ መንታ ምላስ ይጠየፋሉ።

‹‹እኔ እንደምናገረው እንጂ እኔ እንደማደርገው አታድርግ›› በሚለው የቀደመው ትውልድ አመለካከት አይስማሙም። ወኔና የላቀ የሞራል መርሆ ሳይመለከቱብን ሊቀር፣ እና ለቁርጥራጭ ብር ስንሰጥ ሲመለከቱን ይበሳጫሉ።

‹‹የትውልድ ልዩነት› ከሚለው ምሳሌያዊ አባባል ባሻገር ስመለከት የአስተሳሰብ፣ አመለካከት እና የዕይታ ልዩነት እንጂ የዕድሜ ልዩነት አይታየኝም።

ወጣቱ ‹‹ማድረግ እንችላለን›› የሚል አመለካከት ነው የለው፡፡ ለእኛ ለአብዛኞቻችን የቀድሞ ትውልድ አባላት ግን ‹‹ማድረግ አንችልም›› የሚል አመለካከት አለን፡፡ ነገሮችን ለማድረግ ምክንያት ያገኛሉ፤ እኛ ደግሞ ላለማድረግ ማመካኛ።

እኛ እናንገራግራለን፤ እነርሱ ግን ተግባራዊ ናቸው። እኛ እንቆዝማለን፤ እነርሱ ያስባሉ። እኛ የቦዩ ጭለማ ሲታየን፣ እነርሱ ግን ከቦዩ ወዲያ ማዶ ጫፍ ያለውን ብርሃን ይመለከታሉ። በኋላ መመልከቻ መስታወታችን እየተመለከትን ስናሽከረክር እነርሱ ግን በፊት መስታወት

‹‹የሆነ ሌላ ሰው ከጠበቅን፣

አሊያም ሌላ ጊዜ የምንጠብቅ ከሆነ

ለውጥ አይመጣም፡፡ እኛኑን ነበር

እየጠበቅን የነበረው፡፡ የምንሻው

ለውጥ እኛው ራሳችን ነን፡፡››

፡ ዛሬ ግን ለተጠቂዎች እሟገታለሁ። በብሄር ማዕከልነት ሌሎች ሲጎዳኙ ተመልክቼአቸዋለሁ፤ እኔ ግን ዛሬ ጥብቅ ወዳጃዊ ትስስርት ማስፋፋት እሻለሁ። የመጨረሻ ተስፋዬም በኢ-ሰብዓዊነት ላይ ዓለም አቀፍ አንድነትን ማደራጀት ነው።

በ1997 ዓ.ም ከደንዳናው እውናዊ ‹‹ልባስ›› ሰብሬ ወደ ሃሳባዊው ዓለም ገባሁ። በዚያ ዓመት በኢትዮጰያ የተካሄደውን የግንቦት ምርጫ ተከትሎ 193 ያልታጠቁ ሰልፈኞች በመንግስት ወታሮች በአደባባይ ተገደሉ፤ 163 ተተኩሶባቸው የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው፡፡ ከሰላሳ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችም ታሰሩ። የድህረ-ምርጫው ክስተቶች በሚሊኒየኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ጨለምተኝነትና ተስፋ መቁረጥ አዘቅጥ ውስጥ ዘፈቃቸው። በእኔ ላይ ግን ተቃራኒ ውጤት ነበረው።

የተፈፀመው ግድያ ህሊናዬን ቆጠቆጠው። የአፓርታይድ ፖሊሳች 69 ያልታጠቁ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ሰልፈኞችን በመጋቢት 1960 የገደሉበት በደቡብ አፍሪካ ስለተፈፀመው ሻርፕቪሌ ጭፍጨፋ አሰብኩኝ።

በወቅቱ ለቫርፕቪሌ ሰለባዎች ድምፄን እንዳላሰማላቸው ገና ልጅ ነበርኩ፡፡ ዛሬ ግን በእነዚያ 193 ኢትዮጵያውያንና ለሌሎች በሺህዎች ለሚቆጠሩ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ሰለባዎች ድምፄን ለማሰማት እንዲያዳግተኝ ዕድሜዬ እጅግ አልሄደም፡፡

በዚህ መልኩ ነው ሃሳባዊ የሆንኩት። ዜጎች የመንግሥታቸውን ተግባሮች በሰላማዊ መንገድ መቃወም እንደሚችሉ፤ እንጂ በመቃወማቸው የማይጨፈጨፉባት ኢትዮጵያ ልትኖረን እንደሚችል ወደ ማመን መጣሁ። አንድ ሰው በሥልጣን ላይ ያሉትን በመቃወሙ/ሟ የፖለቲካ እስረኛ ወይም የመንግሥት የጠቃት ዒላማ መሆን የለበትም። በኢትዮጵያ ውሰጥ በትረ-ሥልጣኑን የጨበጠ ለሕግ ማጎንበስ እንጂ ልክ የሕግ የበላዮች ሆነው ዙፋኑ ላይ መቀመጥ የለባቸውም። በሌላ አገላለፅ፣ የሕግ የበላዮች አይደሉም - የሕግ ትሁትና ተማኝ አገልጋይ እንጂ። ህጋዊ ሂደትን ባልተከተለ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ግሰብ ሕይወቱ፣ ነፃቱ ወይም ንብረቱ ሊነፈግ አይገባም ብዬ ማለም ጀመርኩ።

የመንግሥትን እንቅስቃሴዎች እየተከታተለና እየተቆጣጠረ ሙስናን የሚያጋልጥ ነፃ ፕሬስ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖር ይግድ ነው እስከማለት የደረሰ ህልም ጭምር ነበረኝ። ፍትህን የሚያስተዳድርና ሥልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙትን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ ገለልተኛ የፍትህ አካል መኖር አለበት። ምርጫዎች ነፃና ፍትሃዊ መሆን አለባቸው፤ ለአሪቱ መጪ ጊዜ ሙግቶች ማዕከላዊ ሚና እንዲጫወቱ ሊፈቀድላቸው ይገባል። ረዥሙን ታሪክ ለማሳጠር፣ አንዳንዶች እንደሚሉት ተስፋ የቆረጠ ሃሳባዊ ሆንኩኝ።

ሃሳባዊ ስትሆን በዕምነቶችህ ትፀናለህ። የምታምንበትን ትሰብካለህ፣ ታስተምራለህ፡፡ እናም ዴሞክራሲን፣ ሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነትን በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እንዲሁም በየትኞቹም የዓለም አገራት ውስጥ ለማጠናከር እስከተቻለኝ እጥራለሁ። ድምፃቸውን ለማያሰሙ ድምፄን ላሰማላቸው ‘ሞክራለሁ - ምንም’ንኳ አንዳንዶች ‘ኔን በበረሃ በከንቱ እንደሚጮኽ ድምፅ ቢያስቡም።

Page 14: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15ዳ ሰ ሳ

በፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

በቅድሚያ ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ፣ ከሁለት ሳምንት በፊት ‹የሕንድ-አፍሪካ ወዳጅነት ከኢትዮጵያ አንፃር› በሚል ርዕስ አውራምባ ታይምስ ላይ የሰፈረ ፅሁፍ ሲሆን በፅሁፉም ውስጥ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው “በነፃ ገበያ መርህ እዚህ አምርተህ እዚሁ ሽጥ የሚባል ነገር የለም። አምርቶ የፈለገበት መሸጥ ይችላል” ማለታቸው ተገልፅዋል። ይህን አባባላቸውንም በመመርኮዝ ከረዥም ዓመታት ጀምሮ በአገራችን የተስፋፋውን ስለ ነፃ ገበያ ያለንን የተሳሳተ አመለካከት ለመዳሰስ ነው።

ይህ አባባል በሳይንስና በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ባልተደገፈ መረጃ፣ በተለይም ተጠሪነቱ ለጠቅላላው ተመጋቢው ሕዝብ ከሆነ ባለስልጣን አፍ መውጣት የሌለበት እጅግ አደገኛና አሳሳች፣ እንዲሁም ደግሞ ልቅነትን የሚያስፋፋና ሊታለፍ የማይችል አነጋገር ሆኖ ስላገኘሁት ነው። ትምህርት ቤት ገብተን የምንማረው ዝም ብሎ የሚነገረንን እንደ ዕምነት ለመቀበልና እሱን መልሰን ለማስተጋባት ሳይሆን፣ ከኮመን-ሴንስም ሆነ ከሳይንስ አንፃር አንድ ነገር ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን በመመርመር የራሳችንን ፍርድ ለመስጠትምና ትክክለኛውን መንገድ ለማሳየት ነው።

በተለይም ባለፉት ስድሳ ዓመታት የኒዎ-ክላሲካል፣ ወይም በዘመኑ አባባል የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚክስ ትምህርት የበላይነትን ከተቀዳጀ ወዲህ፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ምሁራንን በማሳሳት ለብዙ የሶስተኛው ዓለም አገራት ድህነትና ኋላ-መቅረት ዋና ምክንያት እንደሆነ፣ በየአገሩ የሰፈኑት ተጨባጭ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆኑ እሱን የሚቀናቀኑ አያሌ መጽሐፍትም ያረጋግጣሉ። በተለያዩ አዋቂዎች ታትመው የወጡትን የተለያዩ አስተሳሰቦችን ያዘሉና፣ በየአገሩ የሰፈኑትን በጣም አስከፊ ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ማወዳደርና እንዲሁም ደግሞ ማውጣትና ማውረድ ባልተለመደበት አገር ከአንድ ወገን የሚቀርቡ ትምህርቶችን እንደ ዕውነተኛ ወስዶ እነሱን መስበኩ እንደልማድና ዕምነት ይወሰዳል።

ዛሬ በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠውና እንደቀኖና የተወሰደው የኒዎ-ክላሲካል ትምህርት ከመፍለቁ በፊት ብዙ የአውሮፓ መንግስታት፣ ኋላም አሜሪካ ህብረ-ብሔርን (Nation-State) መገንባት የቻሉት የኔዎ-ክላሲካል ፅንሰ-ሀሳብን መሰረት በማድረግ ሳይሆን፣ በጊዜው እንደዚሁ ዓይነቱ ፅንሰ-ሀሳብ በፍጹም አይታወቅም ነበር - የመርከንታሊዝምን ወይም ቀጥተኛና ንቁ የሆነን የኢኮኖሚ ፖሊሲ መመሪያ በማድረግ ነበር። የኋላ ኋላ ሌሎች ፅንሰ-ሀሳቦች ቢፈልቁም ከአስራ አምስተኛው ክፍለ-ዘመን እስከ አስራዘጠናኛው ክፍለ-ዘመን ማገባደጃ ድረስ የብዙ አውሮፓ መንግስታት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በማኑፋክቱር ግንባታ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ የውስጥ ገበያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት፣ ከተማዎችን በማስፋፋት፣ የካናል ሲይስተሞችንና የባቡር ሃዲድን በመስራትና በመገንባት ሕዝቡን ማስተሳሰር ነበር።

በ18ኛው ክፍለ-ዘመን የአዳም ስሚዙ የነፃ ገበያ መመሪያ ተቀባይነት እንዲኖረው በተለይ እንግሊዝ ከፍተኛ ትግል ብታካሂድም፣ የጀርመን ፈላስፎች፣ የህብረተሰብ ሳይንስ ምሁሮችና ኢኮኖሚስቶች በመቃወምና የራሳቸውን ፅንሰ-ሀሳብ በማፍለቅና በማስፋፋት ጀርመን በጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት ላይ እንድትገነባ መሰረት ጥለው አልፈዋል። የዩሊታሪያን አስተሳሰብ ከተስፋፋ በኋላ የነፃ ገበያ ፍልስፍና እንዳለ እንግሊዝ አገር ተግባራዊ ቢደረግም ከፍተኛ ህብረተሰብአዊ ቀውስ በመፈጠሩና ድህነትም ስልተስፋፋ በጊዜው የድህነት ፖሊሲን መዋጊያ (Poor Law) በማውጣት ሊሰራ የሚችል ሰው ሁሉ ሥራን ሳያማርጥ በዝቅተኛ ደሞዝ እንዲሰራ ተገደደ። ልቅ የሆነ የነፃ ገበያ ፖሊሲ ውድቅ ከተደረገ በኋላ እንግሊዝም ሆነች ሌሎች የአውሮፓ አገራት በመንግስት የተደገፈን የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዲከተሉ ተገደዋል።

በሌላ ወገን ግን በ19ኛው ክፍለ-ዘመን በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይና በጀርመን መካከል የነፃ ንግድ ስምምነት ቢደረግም፣ ይህ ዓይነቱ የነፃ ንግድ ስምምነት በጀርመንና በፈረንሳይ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት

ስላደረሰ ሁለቱም አገሮች ስምምነቱን በማፍረስ ወደ ውስጥ ያተኮረ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ተገደዋል። የኢኮኖሚ ታሪክን ሊትሬቸርና፣ በተለይም በኋላ በማርክስ የተደረሰውን የዳስ ካፒታልን ሥራና የሹምፔተርን የኢኮኖሚ ዕድገት መጽሐፍና እንዲሁም ሌሎች ትችታዊ አመለካከት ያላቸውን መጽሐፎች ላገላበጠ የሚረዳው በአውሮፓ ውስጥ የተካሄደው የኢኮኖሚ ግንባታ በፍጹም አዳም ስሚዝም ሆነ በኋላ የወጣው የትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ እንደሚነግሩን አይደለም። ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊታይ የቻለው በስምምነት ላይ ወይም ደግሞ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ጥቅም በማስቀደምና ኢኮኖሚያዊ አርቆ አሳቢነትን መመሪያ በማድረግ አይደለም።

የካፒታሊዝም ዕድገት፣ ወይም ደግሞ በማሳመር የነፃ ገበያ ተብሎ ስም የተሰጠው ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ብዙ ውጣ ውረድን አሳልፎ እዚህ የደረሰና በተወሰኑ ህብረተሰቦች ውስጥ ብቻ ተግባራዊ የሆነ ክንውን ነው። ይሁንና በሪኔሳንስ አማካይነት የተካሄደው ጭንቅላትን የማደስ ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ ለግለሰብዓዊ ፈጠራ መንገዱን እንዳመቻቸ የማይታበል ሀቅ ነው።

ነፃ ገበያ ወይስ ካፒታሊዝም!ነፃ ገበያ የሚለው ፅንሰ-ሀሳብ ብቅ

ከማለቱ በፊት ብዙ ህብረተሰቦች ከሞላ ጎደል የገበያን ኢኮኖሚ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ አዳብረዋል። ገበያ ከህብረተሰቦች ዕድገትና ከሥራ-ክፍፍል መዳበር ጋር የተያያዘ ነው። ሕዝቦች እንደማህበረሰብ ሲደራጁና ፍላጎታቸውም እያደገ ሲመጣ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተመሳሳይ ምርት ስለማያመርቱ፣ ፍላጎቱን ለማሟላት ሲባል አንደኛው የህብርተሰብ ክፍል ማምረት የማይችለውን ለማግኘት ሲል ከሌላው ጋር መገበያየት ተገደደ። በገበያ ውስጥ በሚደረግ የተለያዩ አምራቾች ግንኙነትና፣ በኋላ ደግሞ በነጋዴዎች አማካኝነት እያንዳንዱ ግለሰብ፣ በመጀመሪያ ዕቃን በዕቃ (Natural Exchange)፣ በኋላ ደግሞ ገንዘብ የዕቃዎች ወይም እህል መለዋወጫ መሣሪያ ሆኖ ሲዳብር ተጠቃሚው የፈለገውንና የቻለውን በመግዛት ፍላጎቱን ያሟላ ነበር።

እንደዚህ ዓይነቱ የገበያ ልውውጥ እንደ አገር በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ውስጥ በተወሰነ ክልል በመካሄድና በማደግ፣ በኋላ ደግሞ በተለያዩ አገራት መካከልም በመስፋፋት የሩቅ ንግድ እየተባለ ለሚጠራው በር ከፈተ። በሩቅ ንግድ አማካኝነትም በተለያዩ ማህበረሰቦች ዘንድ የዕቃ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን የባህልም ግንኙነት በመፈጠር፣ በጋብቻና በመዋለድ ለአንዳንድ አገሮች የህብረተሰብዓዊ ለውጥ እምርታን አምጥቷል። በተለይም በእንደዚህ ዐይነቱ ልውውጥ ተጠቃሚና፣ ህብረተሰብአዊ ለውጥን በማምጣት የሩቅ ንግድ ዓይነተኛ ሚና የተጫወተባቸው አገራት የምዕራብ አውሮፓ አገራት ናቸው። በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ነው በሩቅ ንግድ አማካኝነት ቀስ በቀስ የሥራ ክፍፍል መዳበር የቻለውና፣ ነጋዴዎችም ብዙ ገንዘብ በማከማቸትና የዕደ-ጥበብ ሥራዎችን በመቆጣጠርና የፊዩዳሉን መደብ በዕዳ በመተብተብና ልዩ የፍጆታ አጠቃቀም በማስለመድ ቀስ በቀስ ወደ ኢንዱስትሪ ከበርቴነት ሊለወጡ የቻሉት።

በአውሮፓ የኢኮኖሚ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ከፊሉ የነጋዴ መደብ ወደ ኢንዱስትሪ ከበርቴነት ሲቀየር ዝም ብሎ ሀብት ማጋፈፍ ብቻ ሳይሆን ሥራው በባህላዊ እንቅስቃሴና በከተማ ግንባታዎች ሥራ በመሰማራት የህብረተስቡ አኗኗር በዕውቅ (Rationalize) ላይ እንዲገነባና እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ጀመረ። በዕውቅ ላይ ያልተመሰረተው የፊዩዳሉ ሥርዓት፣ በከተማዎች ግንባታ፣ በዕደ-ጥበብ ሙያ መስፋፋትና በንግድ ማበብ መልክ እየተዳከመና ለሌላና ለተሻለ የአኗኗር ሥርዓት መንገዱን እንዲለቅ ተገደደ። ፍልስፍና፣ ድራማና አርክቴክቸር ሲያብቡ፣ በተለይም የከበርቴውና የአርስቶክራሲው የአኗኗር ስልት ከራስ በማለፍ ህብረተሰቡ ሊተሳሰር የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያዘጋጁ ተገደዱ። በነሼክስፔር፣ በሼሊና የኋላ ኋለ ደግሞ በጀርመን ክላሲኮች የድራማና የክላሲካል ሙዚቃ አማካኝነት በማደግ ላይ የነበረውን የከበርቴ መደብና የአርስቶክራሲ አገዛዝ ጭንቅላት እንዲታነጽ በማድረግ የከበርቴው ሰብዓዊነት ቀስ በቀስ ሊስፋፋ ቻለ። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከህብረተሰብዓዊ ዕድገት ተነጥሎ ሊታይ የማይችል ሆኖ ተቀባይነትን በማግኘት ሥራዎች በሙሉ ጥበብንና (aesthetic) ስርዓትን እንዲይዙ ተደረጉ።

ከዚህ በተረፈ በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ በየጊዜው የሕዝብ ቁጥር እያደገ ሲሄድና ፍላጎትም ሲጨምር ብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገራት በአንድ ዓመት ውስጥ ሶስት ጊዜ ሊያመርቱ የሚችሉበትን ሁኔታ (The Three Field Farming System) አዳበሩ። በተጨማሪም በበሬ ከማረስ

ይልቅ በፈረስ እየታገዙ በማምረት ምርት ሊያድግ የሚችልበት ሁኔታ ተዘጋጀ። በአገር ውስጥ ምርት ብቻ የሕዝብ ፍላጎት ማሟላት ባልተቻለበት አገራት ውስጥ መንግስታት ከውጭ እህል በማስመጣት የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት የተገደዱበት ጊዜ ነበር።

ይህንን ጉዳይ ፕሮፌሰር ሚስኪሚን ሃርይ “The Economy of Later Renaissance Europe, 1460-1600” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ በዝርዝር ያስረዳሉ። በተጨማሪም ፕሮፌሰር ጞልድትዋይት “The Economy of Renasissance Florence” በሚለው መጽሐፋቸው የኢጣሊያን ኢኮኖሚ በዘፈቀደ ሳይሆን በዕውቅ ላይ የተገነባና፣ ጣሊያንም በተለይ በኢንዱስትሪ ምርት አይላ ትገኝ እንደነበር ነው የሚነግሩን። ከነዚህ መጽሐፍትም ሆነ ከሌሎች አያሌ የኢምፔሪካል ጥናቶች መረዳት የሚቻለው፣ በነፃ ገበያ አማካኝነት ሁሉም እንደፈለገው እህሉን ውጭ እያወጣ መቸብቸብ ይችላል የሚል ሳይሆን፣ በዕውቅና በመጀመሪያ ደረጃ የየህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት ያስፈልጋል የሚለውን መመሪያ በመውሰድ ነው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ህብረተሰብአዊ ግንባታ ሊካሄድ የተቻለው። ማንም እንደፈለገው መሸጥ ይችላል እየተባለና የውጭ ምንዛሪ ለመቃረም ሲባል በአገር ውስጥ የሚመረትን ምርትም ሆነ ፍራፍሬዎች እየሟጠጡ ወደ ውጭ በመላክና መሬትን ለውጭ እንቬሰተሮች በማከራየት አልነበረም በአውሮፓ ምድር ውስጥ ካፒታሊዝም ማደግ የቻለው።

ካፒታሊዝም እያደገና እየተወሳሰበ ሲመጣ በሸቀጥ ልውውጥ መነጋገድ በቂ ሆኖ አልተገኘምና የግዴታ በመንግስት የተደገፈ የወረቀት ገንዘብና ሳንቲም በብዛት በመታተም የካፒታሊዝምን ዕድገት ማፋጠን ተቻለ። የወረቀት ገንዘብ የበለጠ ተቀባይነትን እያገኘ ሲመጣም የሰው በሰው ግንኙነትም እየተለወጠ መጣ። ገንዘብ የህበረተሰብአዊ ግንኙነት መለኪያ ሆነ። ተራ የገበያ ኢኮኖሚ ወይም የነፃ ገበያ የሚለው አባባል አዲስ በተፈጠረው የሀብት ቁጥጥርና የህብረተሰብ ግንኙነት አማካኝነት ወደ ካፒታሊዝምነት ተለወጠ። ካፒታሊዝምም ህብረተሰብአዊ ሥርዓትን መግልጫና ብዙ ነገሮችን ያካተተና የያዝ ሆነ። ለዚህ ነው ማርክስም ሆነ ሹምፔተር ካፒታሊዝምን ዝም ብለው ነፃ ገበያ ወይም የገበያ ኢኮኖሚ ብለው የማይጠሩት። ምክንያቱም እንደዚህ ዓይነቱ አባባል ያልተሟላና ብዙ ነገሮችን ስለማያካትት ነው። የእነ አዳም ስሚዝ አገላለጽ ታሪካዊ አይደለም፤ የማርክስም ሆነ የሹምፔተር እንዲሁም የሌሎች የታሪክን ዕድገት ያካተተና ያለምርት ኃይሎች ዕድገት (Production Forces)፣ ማለትም ያለቴክኖሎጂ ምጥቀት ሊገለጽ አይችልም።

አዲሱና የተሻሻለው የቴክኖሎጂ ለውጥ አሰራር አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ የተወሰኑ በተኖችን (ቁልፎችን) ብቻ በመንካት የምርትን ሂደት እንዲያፋጥን አስቻለው። በዚያውም መጠን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት የሰው ኃይል ትርፍ (Redundant) እየሆነ እንደመጣ እንመለከታለን። በቴክኖሎጂዎች ምጥቀትና ውድድር አማካኝነት የካፒታል ክምችትና የኢንዱስትሪና የባንክ ካፒታል እየተቆላለፉ በመምጣት፣ ፋይናንስ

እስከመነጠቅ ይደርሳል። ይህ ዐይነቱ ህግ ጠቅላላውን የገበያ ሂደት የሚመለከትና ብዙ ነገሮችን የሚያካትት ነው።

በካፒታሊስት አገራት እንደኛ አገር ኑግን፣ ተልባን፣ ሰሊጥን፣ ሱፍንና ሌሎች ነገሮችን የውጭ ካረንሲ ለመቃረም ሲባል እስከነነፍሱ አይላክም። ይህንን የሚያደርግ ስለኢኮኖሚ ዕድገት ምንነትና በኢንዱስትሪዎች መሀከል ስለሚኖረው ውስጣዊ ግኑኝነት የማያውቅ መሆን አለበት። እንደዚህ የሚያደርግ መንግስት በዚያውም መጠንም የውስጥ ገበያን ዕድገት ይዘጋል። ነጋዴው እዚያው ቀጭጮ እንዲቀር ያደርገዋል። በአጠቃላይም ህብረተሰብአዊ ለውጥ እንዳይመጣ መንገዱን ሁሉ ያፍናል። የሕዝቡን የፈጠራ ሥራ ከማፈኑም የተነሳ ኑሮ የተዘበራረቀ እንዲሆን ያደርጋል። በሌላ በኩል የኢኮኖሚው ኤጀንቶችን የፈጠራ ችሎታና በየጊዜው እንደገበያው መለዋወጥ ከሁኔታው ጋር ሊኖር የሚችለውን መጣጣምና በፍጥነት መጓዝ ማጤን ከማስፈለጉ ባሻገር ለውድድሩ መጧጧፍ የጊዜ ኢኮኖሚና ቦታ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታሉ። ከነዚህ ነጥቦች ስንነሳ በአገራችን ምድር የሚነዛው ስለገበያ ኢኮኖሚ ሳይንሳዊ ባህርይ የሌለው በተራ ችርቻሮ ላይ የተመረኮዘና ተዋንያኖችን የበለጠ የሚያንቀዠቅዥና አጭበርባሪ የሚያደርጋቸው ነው። እነ አቶ ተፈራ እንደዚህ ዓይነቱን ኢኮኖሚ ነው የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ እያሉ የሚነግሩን። እግዚአብሔር እንዳይሰማዎት!!

ካፒታሊዝም፣ ሳይንስና እንዲሁም ቴክኖሎጂ !!አንዳንድ ስለኢኮኖሚ ዕድገት

የሚጽፉትንም ሆነ የሚያወሩትን የኒዎ-ክላሲካል የኢኮኖሚ ምሁራንና፣ እንዲሁም ስለ ኢኮኖሚ እናውቃለን ብለው አፋቸውን የሚሰዱትን አንዳንድ የወያኔ ደጋፊዎችን ስንመለከትና ስናዳምጣቸው እነዚህ ስዎች ስለምን እንደሚያወሩ ነው ግራ የሚገባን። በታሪክ ውስጥ የገበያ ኢኮኖሚ ከግብታዊ ባህርዩ ከተላቀቀና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከተሸጋገረ ወዲህ መሰረታዊ ምርምርና ከዚያ በኋላ ደግሞ ይህንን ቀስ በቀስ ተግባራዊ ማድረግ የካፒታሊዝም ዓይነተኛ ባህርይ ሊሆኑ በቅተዋል።

በመጀመሪያ ደረጃ ሳይንስ መዳበር የቻለው በታላላቅ ተመራማሪዎች፣ በአስራ አምስተኛው፣ በአስራስድስተኛውና በአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ሲሆን፣ ወደ ቴኮኖሎጂ ማፍለቂያነትና ወደ ተግባራዊነት እየተለወጠ ሊመጣ የቻለው ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ሳይንሳዊ ግንኝነት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊነትና ቴክኖሎጂዎችን ፈጥሮ ወደ ምርት ማምረቻ መሣሪያነት መለወጥ የታቸለው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ምርት በዕውቅ መመረትና ምርትን ማሳደግና እንዲሁም የተለያዩ ምርቶችን ማምረት የተቻለውና ቀስ በቀስም ዛሬ ለማየት የበቃነውን ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀት ማየት የተቻለው። በአንዳንዶች አባባል ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው በቴክኖሎጂ አማካኝነት ተፈጥሮን እስከተወሰነ ደረጃ መቆጣጠርና በተፈጥሮ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ነገሮችን በልዩ መሣሪያዎች መመርመርና ማየት የተቻለው። ስለሆነም ሰለ ገበያ ኢኮኖሚ ወይም ስለ ካፒታሊዝም በምናወራብት ጊዜ ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም ደግሞ በየጊዜው ከሚካሄድ ፈጠራ (Innovation) ውጭ ማየትና ማተት ስህተት ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛ ነው።

ከዚህ ስንነሳ በአገራችን ምድር ኢኮኖሚው በአስራአንድ በመቶ አድጓል፣ የነፃ

ገበያ ኢኮኖሚ እያካሄድን ነው የሚለው ተራ አባባል ሳይንሳዊ መሰረት የለውም። ይህ ዓይነቱ አነጋገር የኢኮኖሚ ፖሊሲ አውጭዎቻችንን የዕውቀት ደረጃ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ እንደዚህ ዓይነቱ የሸቃዮች ኢኮኖሚ የቱን ያህል በሚሊዮን የሚቆጠረውን ታዳጊ ወጣት አእምሮውን እንደሚያበላሽው ነው መረዳት የሚቻለው። እንደዚህ ዓይነቱ ግራ መጋባትና አላዋቂነት የፈረንጆች መጫወቻ፣ መሳቂያና መሳለቂያ እንድንሆን አድርጎናል። የተለያዩ ግን ደግሞ ሳይንሳዊ ይዘት የሌላቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚባሉ ነገሮች ተግባራዊ እየሆኑ ከፍተኛ የሆነ የውንብድና ሥርዓት ተዘርግቷል። ድህነት ተስፋፍቷል። ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሳይሆን፣ ገንዘብ ከዚህና ከዚያ በመቃረምና ትላልቅ ኢኮኖሚያዊ መሰረት የሌላቸው ሆቴል ቤቶችና ቡና ቤቶች በመስራት ውድ እናት አገራችን ወደ አስረሽ ምችውነት ተለውጣለች። ስለዚህም ከዚህ ዓይነቱ ጉድ ለመውጣት በአንድ ላይ ሆነን ፈጣሪን በመማፀን ታትረን መስራት አለብን።

/ዶ/ር ፍቃዱ በቀለ፣ በጀርመን የ‹‹ዴቨሎፕመንት›› ኢኮኖሚክስ መምህርና ተመራማሪ ናቸው/

በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው የተሳሳተ አመለካከትካፒታል የኢንዱስትሪን ዕድገትና የቴክኖሎጂን ምጥቀት መወሰን ቻለ። በተጨማሪም፣ የኢንዱስትሪ ካፒታል እየመጠቀ የመጣውን ያህልና፣ የካፒታል ክምችት ያደገውን ያህል፣ በአንድ በኩል መጠነኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወይም ባህላዊ የዕደ-ጥበብ ሥራዎች እየተዳከሙና እየጠፉ ሊመጡ ችለዋል። ከዚህም በላይ የመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ዕድገት፣ መኖርና ያለመኖር በትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ውስጠ-ኃይል የሚወሰን መሆን ቻለ። ምክንያቱም መጠነኛና ማዕከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተለዋዋጭ ዕቃዎችንና(Spare parts) መጠገኛዎችንም ሆነ ዋና ዋና ክፍሎችን አምራች ስለሆኑ፣ ለምሳሌ የመኪና ገበያ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ ትናንሽ ኢንዱስትሪዎችም ይዳከማሉ ማለት ነው።

ይህም የሚያመለክተው የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እርስ በራሳቸው የተያያዙና (Value-added Chain) አንደኛው በሌላኛው ላይ የተመካና፣ የአንደኛው መዳከም ወይም መጠንከር በሌላው ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል ማለት ነው። ይሁንና ግን በዘመነ-ግሎባላይዜሽን፣ ለምሳሌ የአንድ መኪና የተለያዩ ክፍሎች እዚያው ፈጣሪው አገር ብቻ አይመረቱም። የማምረቻን ዋጋ ለመቀነስ ሲባል የተወሰነው የመገጣጠሚያ ክፍል በተለያዩ አገሮች በመመረት የመጨረሻ መጨረሻ ዋናው አምራች አገር ምርቶቹን በመገጣጠም የመጨረሻውን ምርት ውጤት ገበያ ላይ ይቀርባል። ስለሆነም የዛሬው የገበያ ኢኮኖሚ ወይም ደግሞ ካፒታሊዝም ከሶስት መቶና አራት መቶ ዓመት በፊት ከነበረው በብዙ መቶ እጅ ልቆ የሚገኝ ነው።

ውድድርና የካፒታሊዝም ዕድገት !

የገበያ ኢኮኖሚ ወይም ካፒታሊዝም እንደ አገራችን በተራ ነጣቂነት ወይም ዓይን ባወጣ ዘራፊነት የሚደነገግና ውስጠ-ኃይል የሚያገኝ አይደለም። ማርክስ እንደሚለውና በትክክልም እንደሚያረጋግጠው ውድድር (Competition) የካፒታሊዝም ዋና አንቀሳቃሽ ኃይል ነው። ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀትም የሚታየው በውድድር አማካኝነት ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ በከፍተኛ ምርምርና ፈጠራ እየታገዙ ማምረት ያስፈልጋል። እያንዳንዱ በገበያ ላይ ምርት እያመረተ የሚያቀርብ ካፒታሊስት ተወዳዳሪውን በመርዝ ወይንም በአንዳች ነገር ህይወቱን ለማጥፋት ወይም ለመግደል ተንኮል የሚያብሰለስል ሳይሆን፣ በምን መንገድና እንዴት አድርጌ ምርት ባመርት ተወዳዳሪዬን ለማሸነፍ እችላለሁ፣ ወይም የበለጠ የገበያ ድርሻ ይኖረኛል ብሎ ታጥቆ በመነሳት የኢንቨስትመንት ስትራቴጂውን ይቀይሳል።

ከዋጋ አንፃር የማምረቻ ዋጋን በመቀነስና ምርትን በነፍስ ወከፍ ሲተመን በማሳደግ (Productivity)፣ እንዲሁም ደግሞ ምርቱ ጥራት እንዲኖረው በማድረግ ብቃትቱን በማሳየት በገበያ ውስጥ ለመቆየት ጥረት ያደርጋል። በየጊዜው የምርቱን ሁኔታ ይለዋውጣል። ለምሳሌ በአንድ ወቅት የተወሰነ ምርት፣ መኪና ወይም ማቀዝቀዣ የተወሰነ የፍጆታ ዘመን ነው ያላቸው። በመጀመሪያው ወቅት አዲስ ምርት ገበያ ላይ ሲወጣ እንደብርቅ ይታያል። ቀስ በቀስም ሰው እየለመደው ሲሄድ ገዝቶ ይጠቀማል። በገበያ ላይ የመሸጡ ኃይል እያደገ ይመጣል። ሌላው ተመሳሳይ ምርት የሚያመርት ካፒታሊስት ውበቱንና የአጠቃቀሙን ዘዴ በመለወጥ ተመሳሳይ ምርት ለገበያ ያቀርባል። የድሮውም ምርት ገበያ ላይ ተገዢነቱ እየቀነሰ በመምጣት ከገበያ ላይ እየተስፈናጠረ ይወጣል። በዚህ መልክ በስድሳኛውና በሰባኛው ዓ.ም ይመረቱ የነበሩ መኪናዎችም ሆነ ማቀዝቀዣዎች ዛሬ በፍጹም አይገኙም። በተጨማሪም የኃይልን አጠቃቀምና የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ ሲባል በተለይም ረዥም ዕድሜ ያላቸው ምርቶች በጥራትም ሆነ በአጠቃቀም ደረጃ እጅግ እየተሻሻሉና ለምችቶም አጋዥ እየሆኑ መጥተዋል።

ውድድር ለካፒታሊዝም ዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል የሆነውን ያህልና፣ የገበያ ኢኮኖሚ የሚለው ተራ አነጋገር በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውን ያህል፣ ይህ ዓይነቱ በውድድር ላይ የተመሰረተ የገበያ ኢኮኖሚ ከሕግ ውጭ የሚሰራ ነው ማለት አይደለም። በአምራችና በነጋዴ መካከል ያለው ግንኙነት በአንድ ወገን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በነጋዴውና በተጠቃሚው መካከል ያለው ግንኙነት በሕግ ላይ ተመርኩዞ የሚንቀሳቀስ ነው። በመጀመሪያ አምራቹ ካለምንም ማጭበርበር ምርቱን አምርቶ ለነጋዴው ያቀርባል። ነጋዴው በአምራቹ ላይ ሙሉ ዕምነት አለው ማለት ነው። የሚያጭበረብር ነጋዴ በሕግ ተጠያቂ ብቻ ሳይሆን፣ ምናልባት በምርቱ አጠቃቀም ላይ የተወሰነ መደበኛ አሰራርን ተከትሎ ያልተሰራ ምርት አደጋ የሚያደርስ ከሆነ አምራቹ እንደ አደጋው ዓይነት ፈቃዱን

በመጀመሪያ ደረጃ

ሳይንስ መዳበር የቻለው

በታላላቅ ተመራማሪዎች፣

በአስራ አምስተኛው፣

በአስራስድስተኛውና

በአስራሰባተኛው ክፍለ-

ዘመን ሲሆን፣ ወደ

ቴኮኖሎጂ ማፍለቂያነትና

ወደ ተግባራዊነት

እየተለወጠ ሊመጣ የቻለው

ከአስራስምንተኛው ክፍለ-

ዘመን ጀምሮ ነው።

Page 15: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 200316

ዙሪያ በከፍተኛ ቅጂ ተሸጣል። መጽጽፉ የያኔዋን ሶቭየት ኅብረት የስለላ ድርጅት ‹‹ኬጂቢ››ን ተጠያቂ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በኢትዮጵያ ታሪክና ፖለቲካ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ በርካታ መጽሐፎችን ለንባብ አብቅተዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፖል ሄንዝ፣ ከህልፈታቸው በኋላ የዛሬ 23 ዓመት ከአቶ መለስ ጋር ያደረጉት ምስጢራዊ ውይይት በዋሽንግተን ፖስት አማካኝነት ይፋ ተደርጓል። ፖል ሄንዝ በወቅቱ ከውይይቱ በኋላ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ በማጠቃለያው ላይ አቶ መለስን እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጽዋቸው፡- ‹‹አጭር ቀጠን ያለ፤ ዕድሜው በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ የሚገመት፤ በጣም አጫሽ፤ ጥሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ፤ ነገሮችን በጥሞና የሚመረምር፣ የተረጋጋና በራስ የመተማመን መንፈስ የሚነበብበት፤ ስንገናኝ አለባበሱ ቀለል ያለ (ኢ-መደበኛ የሚባል) ነበር፤ አንዳንዴ ዘና የሚያደርጉ ጨዋታዎችን ወርወር ያደርጋል፤ ዘና ባለ መልኩ ለመወያየት የማይከብድና እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የአንደበተ ርቱዕነት ጸጋ የተላበሰ ሰው።››

ውይይቱ በከፊልይህ የሁለቱ ወገኖች ምስጢራዊ ውይይት

የተጀመረው አቶ መለስ በሰጡት ቀጣዩ አስተያየት ነበር፡-

አቶ መለስ፡- ስለ ኢትዮጵያ የፃፍካቸውን በርካታ ነገሮች የማንበብ ዕድል አግኝቻለሁ። ባነሳኻቸው በርካታ ነጥቦች ላይም እስማማለሁ። አንድ ያየሁት ችግር ግን አለ፤ ለምንድነው ‹‹ማርክሲስት›› ብለህ የምትጠራን?

ፖል ሄንዝ፡- ምክንያቱም እናንተው ራሳችሁ ማርክሲስት ስለመሆናቸሁ በተደጋጋሚ በመግለፃችሁ ነዋ! አንተ ራስህ አልባንያን እንደሞዴል በመውሰድ ለነገዋ ኢትዮጵያ ብቸኛው አማራጭ እሱ እንደሆነ በይፋ በመግለፅ ትታወቀለህ ... ማርክሲስት አይደለንም ካላችሁ ነገሩን ለማጥራት ብዙ ሥራ መስራት ይጠበቅባችኋል።

አቶ መለስ፡- እኛ ማርክሲስት-ሌኒኒስት አይደለንም። ይህንኑ በትግራይ ምድር ተግባራዊ የማድረግ ዕቅድም የለንም። የድርጅታችን ስያሜም ቢሆን ማርክሲስት-ሌኒኒስት ስለመሆናችን ምንም የሚጠቁመው ነገር የለም። በድርጅታችን ውስጥ ማርክሲስቶች አሉ። ይህ እውነት ነው። እኔ ራሴ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ወቅት በማርክሲዝም መጠመቄን አልክድም። በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ድርጅታችን በማርክሲዝም አመለካከት ተጠምቆ ትግል መጀመሩ ይታወቃል። ነገር ግን በሂደት የተማርነው ነገር ቢኖር ያረጀ ያፈጀ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም ውጤት አልባ መሆኑን ነው። ... በዘመናዊው ዓለም እየሆነ ስላለው ነገር በቂ መረጃ አለን።

ፖል ሄንዝ፡- አልባኒያን እንደምታደንቁ የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ። የአልባኒያ ሞዴል ኮሚኒዝም በትግራይ ለማስፈንስ ትፈልጋላችሁ?

አቶ መለስ፡- የአልባኒያ ሞዴል ኮሚኒዝም የማስፈን ፍላጐት የለንም፤ የሶቪየትም ሆነ የቻይና ሥርዓት የምናሰፍንበት ምንም ምክንያት የለም። ዘመኑ እየተቀየረ በመሆኑ አልባኒያውያንም ቢሆኑ አንዳንድ ሥርዓቶቻቸውን እየለወጡ ነው።

ፖል ሄንዝ፡- አልባኒያ ሄደህ ታውቃለህ? ከአልባኒያውያንስ ጋር ግንኙት አላችሁ?

አቶ መለስ፡- አልባኒያ አልሄድኩም። ከአልባኒያ ጋር ምንም አይነት ግንኙነትም የለንም። አልባኒያውያን በአገራቸው ያሰፈኑትን አይነት ሥርዓት እኛ ትግራይ ውስጥ እንድናሰፍን ለምን እንደሚፈለግ አይገባኝም።

ፖል ሄንዝ፡- የነገዋን ኢትዮጵያ እንዴት ትገልፃታለህ?

አቶ መለስ ፡- ደርግ በአገሪቱ የዘረጋው ሥርዓትም ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ አለበት። አለበለዚያ አገሪቷን ከማጥፋት ወደኋላ አይልም። በሁሉም አቅጣጫ ለነፃነታቸው እየተፋለሙ ያሉ ድርጅቶች አንድ ላይ ተሰባስበው ስለአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ መምከር አለባቸው። የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረትና ሁሉም ፓርቲዎች (ቀኝ ዘመም ይሁኑ ግራ ዘመም) አንድ ላይ እንዲሰባሰቡ ሀሳብ አቅርበናል። በዚህ አገራዊ ጉዳይ ማንም ሊገለል አይገባም የሚል እምነት አለን። የሚመሰረተው ጊዜያዊ መንግሥት አገሪቱ የምትመራበትን ሕገመንግሥት በመቅረፅ አገሪቷ በአዲስ መልክ ወደ መልካም አቅጣጫ ማምራት አለባት። ሕዝቦቿ የራሳቸውን መብት በራሳቸው እንዲወስኑ መብቱ ሊሰጣቸው ይገባል። ... የአማራ የበላይነት ማክተም አለበት።

ፖል ሄንዝ፡- የአማራ የበላይነት ስትል አልገባኝም? ያንተ አመለካከት ይህ ከሆነ በቅርቡ በትጥቅ ትግል የተቆጣጠራችኋቸው አካባቢዎች አሉ (ላስታ፣ ጋይንት፣ ሳይንት፣ መንዝ፣ መራቢቴና ሌሎችን መጥቀስ ይቻላል)። በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች አማሮች አይደሉምን?

አቶ መለስ፡- እነዚህ የተጨቆኑ አማሮች ናቸው። ስለአማራ የበላይነት ስንነጋገር የሸዋ አማራ ማለታችን ነው። ባለፉት መቶ ዓመታት በተለምዶ የሸዋን የበላይነት የሚያንፀባርቅ የአስተዳደር ሥርዓት ነበር በአዲስ አበባ የነበረው። እንደዚህ አይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች አስተሳሰባቸውን መቀየር አለባቸው። ደርግም ከመጀመሪያ ጀምሮ ሥራ ላይ ያዋለው ይህንኑ አስተሳሰብ ነው። አንዱ ሕዝብ በሌላው ሕዝብ ላይ የበላይነቱን የሚያሳይበት ሁኔታ ማክተም አለበት።

ፖል ሄንዝ፡- በቅርቡ የኢህአዴግን ፖለቲካዊ መርህ የሚያትት ሠነድ አንብቤ ነበር። ሆኖም ግን ያነበብኩት አሁን አንተ ከምትነግረኝና ቆመንለታል ከምትሉት ዓላማ ጋር አይመሳሰልም። ሠነዱ የማርክሲዝም-ሌኒኒዝም መንፈስ ይንፀባረቅበታል።

አቶ መለስ፡- በዚህ ሠነድ እኛን መፈረጅ

የለብህም። መዳኘት ያለብን ትግራይን ጨምሮ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ላይ እየሆነ ባለው እውነታ ነው። መጥተህ ብትጎበኘንና ስለኢትዮጵያ የሥልጣን ሽግግር የሚያትተውን መለስተኛ ፕሮግራማችንን እንድታነብ ልጋብዝህ (አቶ መለስ ሠነዱን በውይይቱ መሀል ለፖል ሄንዝ ይሰጧቸዋል)።

ፖል ሄንዝ፡- ድርጅታችሁን ‹‹ግንባር›› ብላችሁ ነው የምትጠሩት። ግንባር ደግሞ የተለያዩ ድርጅቶችን ያቀፈ ፓርቲ የሚጠቀምበት ስያሜ ነው። ከሕወሓት ውጪ ያሉት ድርጅቶች ምንድናቸው?

አቶ መለስ፡- በአሁኑ ጊዜ ሌላ ድርጅት የለም። ትግራይ ውስጥ ስማችን (ሓርነት) ንቅናቄ የሚል ትርጉም ነው ያለው። ወያኔ የሚለውን አገላለፅ የምንጠቀምበት ምክንያት ትግራይ ውስጥ ታሪካዊ ትርጓሜ ስላለው ነው። ትርጉሙ ደግሞ በውጭ ኃይሎች ላይ የሚካሄድ ሕዝባዊ አመፅ ማለት ነው ... በ1943 ተመሳሳይ ትግል ተካሂዷል - ትግራይ ውስጥ። ትግሉ የሸዋን ጭቆናና የበላይነትን የሚቃወም ነው የነበረው። ደርግም ‹‹ወያኔ›› ብሎ ነው የሚያጣጥለን። አኛ ግን ስያሜውን እንወደዋለን። እኛ በፖለቲካ ደረጃ የተባበርን ንቅናቄ ነን። ነገር ግን የተለያዩ ሀሳቦችና አመለካከቶች እንዲንሸራሸሩ እንፈቅዳለን። በውስጣችን በግልፅና በነጻነት የመወያየት ባህል አለ።

ፖል ሄንዝ፡- ኢህዴን ይህ ነው የሚባል ነፃነት የለውም። በራሱ መቆም የሚችልም አይደለም የሚባል ነገር ሰምቻለሁ ... ሰዎች ሕወሓት ጠፍጥፎ የፈጠረው ድርጅት እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እውነት ነው?

አቶ መለስ፡- ኢህዴን እንደሕወሓት በደንብ የተደራጀ ንቅናቄ ነው ባይባልም፣ እኛ ጠፍጥፈን የፈጠርነው ድርጅት ግን አይደለም። በደቡብ ትግራይ የሚገኙ ጭቁን አማራዎችን የሚወክልና የእነዚህን ጭቁኖች ተስፋ የሰነቀ ንቅናቄ ነው። ዋና ጽ/ቤቱም በሰቆጣ ይገኛል።

ፖል ሄንዝ፡- ከኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ ምን ይመስላል?

አቶ መለስ፡- ከኢህአፓ ጋር ያለን ግንኙነት መልካም የሚባል አይደለም። ድርጅቱ በአብዮቱ ማግስት ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ እንደነበር ዕሙን ነው። ነገር ግን በቀይ ሽብር ወቅት ብዙ ጉዳት ደርሶበታል። ከዛ በኋላ ጥንካሬያቸውን ጠብቀው መቀጠል አልቻሉም። እነሱ ማለት የደርግ ሌላኛው ገፅታ ናቸው። የአማራ የበላይነትን ይደግፋሉ። ... ማርክሲስቶች ናቸው። አቋማቸው የኢትዮጵያውያንን የእኩልነት መርህ ይፃረራል። አመለካከታቸውን እስካልቀየሩ ድረስ ከእነሱ ጋር ትብብር መፍጠር ያስቸግረናል። ሕዝቡም ይደግፋቸዋል ብዬ አላስብም።

ፖል ሄንዝ፡- ከመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ጋርስ ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል?

አቶ መለስ፡- መኢሶኖች (እነሱ እንደሚያወሩት ሳይሆን) ኢትዮጵያ ውስጥ የድጋፍ መሰረት የላቸውም፤ ተዋጊዎችም የሏቸውም። በመርህ ደረጃ ከእነሱ ጋር ለመስማማት አንቸገርም። ምናልባትም ትብብር ልንመሰርት እንችል ይሆናል።

ፖል ሄንዝ፡- ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋርስ?

አቶ መለስ፡- በጣም አስቸጋሪዎች ቢሆኑም ከእነሱ ጋር በቀላሉ መተባበር የምንችል ይመስለኛል። በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብዙም እምነት የለንም። የአመራር ማዕከላዊነት የሚባል ነገር አያውቁም። ከድርጅታቸው ጋር በሆነ ነገር ላይ እንስማማና አባሎቻቸው ደግሞ ስለዛ ነገር ምንም የማያውቁ ሆነው እናገኛቸዋለን። ከኢትዮጵያ ውጪ ብዙ ነገር ያወራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ያን ያህል ጠንካራ አደረጃጀት አላቸው ብለን አናምንም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎችም ያን ያህል ከቁምነገር አይቆጥሯቸውም። አንዳንዶቹ አመራሮች መገንጠልን ይደግፋሉ። ነገር ግን ነፃ ኦሮሚያን መፍጠር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ አይገነዘቡም።

ፓል ሄንዝ፡- ስለመገንጠል ምን ታስባለህ?አቶ መለስ፡- እኛ የምንታገለው ለመገንጠል

አይደለም። በኢትዮጵያ አንድነት እናምናለን። ያ ማለት ግን የሸዋ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት አንሻም። ከጥቂት ሳምንታት በፊት እዚህ ለሚኖሩ ኤርትራውያን ያደረግከው ንግግር አንብቤዋለሁ። የተናገርከውን እደግፈዋለሁ። ኢትዮጵያዊነት ይበልጥ ዋጋ እንዳለው የገለፅክበት መንገድም ይስማማኛል። ይህ ግን በዴሞክራሲያዊ መርህ መቃኘት አለበት። ነፃነትንና ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ዋስትና ባገኘ መልኩ መሆን አለበት። ብቸኛው አማራጭ መሆን ያለበት ፌደሬሽን ነው። ፌዴሬሽንን እንደግፋለን። ደርግ ያደረሰውን ጉዳት መጠገን ያለብን በዚህ መንገድ ብቻ ነው።

ፖል ሄንዝ፡- ከኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር (ሕግሓኤ) ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ ምን ይመስላል። ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ትነጋገሩበታላችሁ?

አቶ መለስ፡- ከኢሳይያስ ጋር ሁሌ እንነጋገራለን። የማያስማሙን ጉዳዮች የሉም። በ1970ዎቹ ያለምንም ችግር አብረን ብዙ ሰርተናል። በ1984 ግን አለመግባባት ተፈጠረና ግንኙነታችን ተቋረጠ። ያልተግባባንበት ዋናው ምክንያት በሶቭየት ሕብረት ላይ በያዝነው የተለያየ አቋም ምክንያት ነው። እነሱ አሁንም ሶቭየት ሕብረትን እንደሞዴል አድርገው ይቀበላሉ። ሶቭየት ከደርግ ይልቅ እነሱን ብትደግፍ ውጤታማ ትሆናለች ብለው ያምናሉ። የእሷን ሥርዓትም በኤርትራ ምድር ላይ ተግባራዊ ማድረግ ይፈልጋሉ። ይህ ግን በጣም ቀሽም የሆነ እሳቤ ነው። ያለውን ነባራዊ እውነታ መሰረት አድርገን የራሳችንን ሞዴል ነው ሥራ ላይ ማዋል ያለብን፤ ይህ ደግሞ በትግራይ ምድር በተጨባጭ ስላየነው የእነሱ ምርጫ የተሳሳተ ነበር። የእኛ ደግሞ ትክክል ነበር።

ፓል ሄንዝ፡- ስለዚህ የመገንጠላቸውን ጉዳይ እንዴት ትመለከተዋለህ?

አቶ መለስ፡- የኤርትራ ሕዝብ ደርግን እጅግ ስለሚጠላ መገንጠልን እንደሚፈልግ እርግጥ ነው። ሕግሓኤ አስመራን እንደተቆጣጠረ ሕዝቡ ወዲያውኑ መገንጠል እንደሚፈልግ ይታመናል። ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ ፈታኝ ሁኔታ እንደሚገጥማቸው ኢሳይያስ ቢገነዘብም፣ ሕዝቡ በከባድ ሁኔታ ግፊት ያደርግበታል። እናም ይህ ለኢሳይያስ ትልቅ ፈተና መሆኑ አያጠያይቅም።

ፖል ሄንዝ፡- ስለዚህ በመገንጠላቸው ጉዳይ ላይ የእናንተ አቋም ምንድነው የሚሆነው?

አቶ መለስ፡- እኛ ጉዳዩን የምንመለከተው በመጀመሪያ ደረጃ ከትግራይና ከኢትዮጵያ ጥቅም አንፃር ነው። ከኤርትራ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን። ትግራይ የባሕር በር እንዲኖራት እንፈልጋለን። ይህ ደግሞ የሚሆነው በኤርትራ በኩል ነው። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆነችም አልሆነችም ወደብ ያስፈልገናል። ኤርትራ ውስጥ ብዙ የትግራይ ተወላጆች አሉ። እንደ ውጭ አገር ዜጋ ሊታዩብን አይገባም ብለን እናምናለን። በኤርትራና በትግራይ መካከል የጠበቀ ቁርኝት አለ። ተመሳሳይ ባህልና ታሪክ አላቸው። እናም ከዚህ አንጻር እዛ በሚገኙ የተለያዩ ቡድኖች መካከል ልዩነት ሊፈጠር ይችላል የሚል ብርቱ ሥጋት አለን።

ፖል ሄንዝ፡- የሮም ድርድር (ከደርግ ጋር) እንዴት ነበር?

አቶ መለስ፡- ውይይቱ አስደሳች አልነበረም። ጣሊያኖች ደርግን እንደሚደግፉ በግልፅ ተስተውሏል። ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ቢሮ የመጣውና ውይይቱን የመራው ኃላፊ በአሻግሬ ይግለጡ (የደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር) አማካኝነት የሚቀርበውን ሀሳብ ነበር

የሚደግፈው። ከዛ ይልቅ ከሚስተር ሮሲ (በአዲስ አበባ የቀድሞው የጣሊያን አምባሳደር) ጋር የነበረን ቆይታ ይበልጥ መልካም ነበር። ሰውዬው ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ በቅርብ ያውቃል። ነገር ግን በውይይቱ ላይ ይህ ነው የሚባል ሚና አልነበረውም። ስለዚህ አቋማቸው ትክክል እንዳልሆነ ገልፀንላቸው ስብሰባውን ረግጠን ለመውጣት ተገደናል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቀጣይ ውይይት ማድረግ ይቸግረናል።

ፖል ሄንዝ፡- ስለዚህ ከዚህ በኋላ ከደርግ ጋር ድርድር የማድረጉ ጉዳይ የሚቻል አይደለም ማለት ይቻላል?

አቶ መለስ፡- በእኛ እምነት ደርግ እውነተኛ ድርድር የማድረግ ፍላጎቱ ዝቅተኛ ነው። ደርግ መወገድ ነው ያለበት። ከእሱ ጋር ሥምምነት ላይ መድረስ የሚቻል አይመስለኝም። በጀመርነው ትግል ገፍተንበት አገራችንን ነፃ ማውጣት አለብን። ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የምዕራብ መንግሥታት ድጋፋቸውን ሊሰጡን ይገባል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በተለይ አሜሪካን ትልቅ ሚና መጫወት ትችላለች። ለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካን አቋም ምን ይመስላል?

ፖል ሄንዝ፡- አሜሪካ ሁሌም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ታከብራለች። ዘመናዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ትሻለች። አሜሪካ ያላት አቋም ይኸው ነው። ሶቭየት ኅብረት ለመንግሥቱ አስተዳዳር የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጓ ተገቢ እንዳልሆነ አሜሪካ ታምናለች። እኔ በግሌ የአሜሪካን መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ አቋም አልያዘም የሚል ግምት አለኝ። ምናልባት አንብበኸው ከሆነ ከሶስት ሳምንት በፊት በአሜሪካን ኮንግሬስ ለአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ያቀረብኩት ሪፖርትም ይህንኑ ያትታል … ተስፋ አደርጋለሁ አሜሪካ ይበልጥ በዚህ አቋሟ እንደምትገፋበት።

አቶ መለስ፡- አሜሪካ በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ሚና መጫወት ትችላለች። የደርግ ሥርዓት እየተዳከመ ነው። በዚህ ሁኔታ ብዙ ጊዜ አይቆይም። አሜሪካ ተነሳሽነቱን ወስዳ ልታግዘንና ኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ መንግሥታዊ አስተዳደር እንዲኖር ከጎናችን ልትቆም ይገባል። የአሜሪካን መንግሥት ኃላፊዎች በዚህ ዙሪያ ጠንከር ያለ አቋም የማይወስዱት ለምንድነው?

ፖል ሄንዝ፡- በአሜሪካን መንግሥት ቦታ ሆኜ መናገር ይከብደኛል። ላለፉት አስር ዓመታት በመንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ አልነበርኩም። ስለዚህ እንደአንድ ባለሥልጣን ሆኖ ለጥያቄህ መልስ መስጠት ከባድ ነው። አሁን የምነግርህ የግሌን ሀሳብ ነው። እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በአሜሪካን ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጣት አንገብጋቢ ርዕሰ ጉዳይ አይደለችም። አሜሪካን ቅድሚያ የምትሰጣቸው በርካታ አገሮች አሉ። ምስራቅ አውሮፓ፣ ቻይና እና በከባድ ቀውስ ውስጥ ያለችው ሶቭየት ኅብረት ተጠቃሽ ናቸው። የመካከለኛው ምስራቅ እና የላቲን አሜሪካ አገሮች ጉዳይ ይበልጥ በአሜሪካን ዘንድ ቅድሚያ ይሰጠዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ጉዳይ ለአሜሪካን ያን ያህል አንገብጋቢ አይደለም።

አቶ መለስ፡- ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ የአፍሪካ ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መወሰድ ያለበት አይመስለኝም። በዓለም ላይ ትልቅ ሥትራቴጂካዊ አንደምታ ያለው ርዕሰ ጉዳይ ነው። የሰብዓዊነትና የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይም ጭምር ነው። … አሜሪካን ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ትወደሳለች። በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሕዝቦች አሜሪካን እንደ ብቸኛ ተስፋቸው አድረገው ይመለከቷታል። አሜሪካን በአካባቢው የተንሰራፋው ድርቅ የሚያሳስባትን ያህል፣ ድርቅ በድጋሚ እንዳይከሰት ለማድረግ የሚያስችል ፖለቲካዊ ግፊት ማድረግ ግድ ይላል። … ለመሆኑ እስራኤል ለደርግ መንግሥት የምታደርገውን ድጋፍ አሜሪካን ተገቢ ነው ብላ ትቀበላለች?

ፖል ሄንዝ፡- አሜሪካን ተገቢ ነው ብላ አታምንም። በአሜሪካን አስተዳደርም ሆነ በኮንግሬስ ውስጥ ያሉ ኃላፊዎች እስራኤል ከደርግ ጋር ባላት ግንኙነትም ሆነ በምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ ደስተኞች አይደሉም። ድጋፉ ተገቢ ነው ብሎ የሚያምን አንድም የኮንግሬስ አባል አላጋጠመኝም። አይሁድ የሆኑ የኮንግሬስ አባላት ሳይቀሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ነው ያላቸው። እስራኤል ውስጥም ቢሆን ተቃውሞ አለ ምክንያቱም የደርግ መንግሥት ያበቃለትና ከወራት በላይ ሊዘልቅ እንደማይችል ነው የሚታመነው። … ለመሆኑ አዲስ አበባን ስትቆጣጠሩ ሕዝቡ እንዴት የሚቀበላችሁ ይመስለሀል?

አቶ መለስ፡- ጉዳዩ እኛንም ያሳስበናል። በተደራጀና በተቀናጀ አኳኃን ነገሮችን እናስተካክላለን፤ ምን እንደምናደርግም እናውቃለን። ውጤታማ እንድንሆን የናንተን ድጋፍ እንሻለን። ምዕራብያውያን ከጀርባችን እንዲሆኑ እንፈልጋለን። ወደዚህ የመጣሁበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው። አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ስንዘጋጅ አሜሪካን ከጀርባችን መሆኗን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የናንተ ድጋፍና ምክር ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ወሳኝ ነው። መለስተኛ ፕሮግራማችን እንደሚያትተው ዓላማችን ግልጽ ነው። ኢትዮጵያዊያን ነጻነትና ዴሞክራሲ እንዲጎናጸፉ እንፈልጋለን። አምባገነናዊ ሥርዓት ማስፈን አንፈልግም። ማርክሲስት-ሌኒኒስትም አይደለንም። ነገሮችን በአዎንታዊ መንገድ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን። ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ አሜሪካን ትልቁን የኃላፊነት ሚና መወጣት አለባት።

ፖል ሄንዝ፡- ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ያላችሁ ዝግጁነት ምን ይመስላል? ደርግ ሲወድቅ አዲስ አበባ ውስጥ ምን የሚፈጠር ይመስለሀል?

አቶ መለስ፡- የከተማዋ ነዋሪዎች በጣም ተጨንቀዋል፤ እኛም ጉዳዩ በጣም አሳስቦናል። ሕዝቡ ከስጋትና ፍርሀት ይልቅ በተደራጀ ሁኔታ በሰላምና መረጋጋት በኩል አብሮን እንዲሰራ እናደርገዋለን። ከዚህ በፊት በተቆጣጠርናቸው ከተሞች ያደረግነው ይህንኑ ነው፤ ውጤታማም ሆነናል። ሕዝቡ ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ጀርባ የአሜሪካን ድጋፍ እንዳለን ካወቀ ይቀበለናል፤ መደበኛ ስራውንም በተረጋጋ ሁኔታ ይቀጥላል።

ፖል ሄንዝ፡- አሁን ከሕዝቡ ጋር እንዴት ነው እየተገናኛችሁ ያላችሁት?

አቶ መለስ፡- የሬዲዮ ፕሮግራም አለን። በይበልጥ ወደ ርዕሰ ከተማዋ እየተቃረብን ስንመጣ ደግሞ ዓላማችን ምን እንደሆን (በሬዲዮ ፕሮግራሞቻችን አማካኝነት) ለሕዝቡ ግልጽ እናደርግለታለን።

የመለስና... በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብዙም እምነት

የለንም። የአመራር ማዕከላዊነት የሚባል ነገር

አያውቁም። ከድርጅታቸው ጋር በሆነ ነገር ላይ

እንስማማና አባሎቻቸው ደግሞ ስለዛ ነገር ምንም

የማያውቁ ሆነው እናገኛቸዋለን። ከኢትዮጵያ ውጪ

ብዙ ነገር ያወራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ያን

ያህል ጠንካራ አደረጃጀት አላቸው ብለን አናምንም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎችም ያን ያህል

Page 16: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

17ተጠየቅ

የአፍሪካ ሕብረት ግራንድ ሆቴል ፕሮጀክትና የሠራተኞቹ ውዝግብ

ለፊሊፒንስ ዜጋ ሠራተኞች የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ ቁሶች ይሰጣሉ- ኢትዮጵያዊያን ግን ለሥራ ላይ አደጋ የተጋለጡ ናቸው- የሠራተኛ ማኅበሩ 6 አመራሮች ታግደዋል- ለታገዱት አመራሮች ደመወዛቸው እንዲከፈል ፍርድ ቤት አዟል-

በሱራፍኤል ግርማ

ዋና መሥሪያ ቤቱን አዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ሕብረት እያስገነባ የሚገኘውን ዘመናዊ ሆቴል በተቋራጭነት የያዘው ‹‹ሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ማኔጅመንት ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማ›› በስሩ የሚያሰተዳድራቸው ሠራተኞቹ ካቋቋሙት የሠራተኛ ማኅበር ጋር ውዝግብ ውስጥ ይገኛል።

በሠራተኛ ማኅበሩ አመራሮች ገለፃ መሠረት፣ በድርጅቱና በማኅበሩ መካከል ለተፈጠረው ውዝግብ ዋንኛ ምክንያት ‹‹ሠራተኛው ከተደራጀ የመብት ጥያቄ ማንሳት ይጀምራል›› የሚል ስጋት ነው።

በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩት ቅሬታ አቅራቢዎች የሠራተኛ ማኅበር ማቋቋም ያስፈለጋቸው ከእነሱ ጋር በተመሳሳይ የሥራ መስኮች ላይ የተሰማሩ (ግንበኛ፣ የብረት ሠራተኛ፣ ፌራዩ፣ ወዘተ) የፊሊፒንስ ዜጎች ከሚያገኙት የሥራ ላይ ደህንነት ያነሰውን እንኳን ኢትዮጵያውያን ሊያገኙ ባለመቻላቸው መሆኑን ይናገራሉ። ኢትዮጵያዊ ሠራተኞቹ ሴፍቲ ጫማን ጨምሮ የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት ሳይሟሉላቸው እንደሚሰሩና በእኩል ሥራ ላይ ከተሰማሩ የውጭ ዜጎች እጅግ ያነሰ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው ይገልፃሉ።

በሕጉ መሠረትም ማኅበር የመመስረት ጥያቄያቸውን ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን እንጨት፣ ብረታብረት፣ ሲሚንቶና የመሳሰሉት ሠራተኛ ማኅበራት ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን አቀረቡ። ፌዴሬሽኑም ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች በሙሉ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዕውቅና እንዲሰጣቸው በ17/08/2003 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

የከተማው አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ደግሞ በበኩሉ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በሚያዘው መሠረት የሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ሠራተኞች ተሰብሰበው ማኅበር ማቋቋማቸውንና የሥራ አመራር ምርጫ እንዳካሄዱ ከፌዴሽኑ የደረሰው ደብዳቤ እንደሚያስረዳ በመግለፅ ለማኅበሩ ዕውቅና መስጠቱን ሚያዚያ 19 ቀን 2003 ዓ.ም አስታውቋል።

በተጠቀሰው ቀን ቢሮው ለማኅበሩ የሰጠው የምሥክር ወረቀት ‹‹ሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ማኔጅመንት ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር መሠታዊ የሠራተኞች ማኅበር በሕግ ታውቆ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተመዘገበ ነው›› የሚል ሲሆን፣ የማኅበሩ የሥራ አስፈፃሚ እና የኦዲት ኮሚቴ አባላት የሥልጣን ዘመናቸው እስከሚያልቅበት ሚያዚያ 19/2007 ዓ.ም ድረስ የማኅበሩን ሥራ ለማከናወንና ለማስፈም እንደሚችሉ ለድርጅቱ አስገንዝቧል።

ሆኖም የሠራተኛ ማኅበሩ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ የሠራተኞቹን መብት ለማስከበር እንቅሰቃሴ ማድረግ ሲጀምር ድርጅቱ ጫና መጀመሩን የማኅበሩ ለቀመንበር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ታዬ ይገልፃሉ።

‹‹ድርጅቱ በስሩ ያሉት ሠራተኞች ያቋቋሙትን ማኅበር ለማፍረስ ቆርጦ ተነስቷል፤ በአመራሮቹ ላይም የተለያዩ ሕገ-ወጥ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል›› የሚሉት አቶ ቴዎድሮስ በምሳሌነት ለእሳቸው የተሰጠውን የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ያቀርባሉ።

ሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ማኔጅመንት ሰርቪስስ ሚያዚያ 25 ቀን 2003 ዓ.ም የሠራተኛ ማኅበሩ ሊቀመንበር ለሆኑት አቶ ቴዎድሮስ በጻፈው ማስጠንቀቂያ፣ ዘወትር ማለዳ እንደሚደረገው ሁሉ ሚያዚያ 20 ቀን 2003 ዓ.ም የአፍሪካ ሕብረት ግራንድ ሆቴል ፕሮጀከት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ውይይት በሚያደርጉበት ወቅት የማኅበሩ ሊቀመንበር ‹‹ተገቢነት የጎደለው›› ድርጊት መፈፀማቸውን ገልጿል።

በፅሁፍ ማስጠንቀቂያው ላይ የተዘረዘሩት የማኅበሩ ሊቀመንበር ‹‹ጥፋቶች››፤ የሠራተኛውን መብት ለማስከበር ማኅበር ማቋቋማቸውን፣ መብቱን ለማስከበር የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከማኅበሩ ጎን እንዲቆም መጠየቃቸው እና መብቱ እንዲከበርለት የሚፈልግ ሠራተኛ የማኅበሩ አባል እንዲሆን ማስገንዘባቸው ናቸው።

የፅሁፍ ማስጠንቀቂያው በማከልም ‹‹… እስከዛሬ ድረስ በድርጅቱና በሠራተኛው መካከል የነበረውን መልካም የሥራ ግንኙነት ለማደፍረስ

የተደረገ ነው›› የሚል ሲሆን፣ ድርጊቱ ሥነ-ምግባር የጎደለውና የሠራተኞችን የሥራ ተነሳሽነት ከመቀነሱ በተጨማሪ የድርጅቱን ስም፣ ክብርና ዝና እንደሚያጎድፍ በማተት ሊቀመንበሩን ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ በፅኑ አሳስቧል።

ነገር ግን አቶ ቴዎድሮስ ማስጠንቀቂያውን አይቀበሉትም። ‹‹የማኅበሩ ዓላማ ግልፅነው፡፡ ለባዕዳን እየተሰጠ ያለው የሥራ ላይ ደህንነት ለኢትዮጵያውያንም እንዲከበር እና የሚፈፀምብን የጉልበት ብዝበዛ እንዲቆም ነው እየጠየቅን ያለነው›› በማለት ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፣ ድርጅቱ ያስተላለፈባቸውን ማስጠንቀቂያ እንዲያነሳላቸው ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።

በደብዳቤያቸው፣ ማንኛውም የማኅበሩ አባል መሆን የሚፈልግ ሠራተኛ ከሥራ ሰዓት ውጪ መመዝገብ እንደሚችል ከመግለፅ ባለፈ ድርጅቱን የሚጎዳ ድርጊት አለመፈፀማቸውን ከማስገንዘባቸው በተጨማሪ፣ ‹‹ደግሞም በጥፋትነት የተጠቀሱብኝ ነገሮች ሊያስወቅሱኝ ሳይሆን ሊያስመሰግኑኝ ነው የሚገባው›› በማለት ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከዚህ ባሻገር ማኅበሩ ዓላማዎቹ፤ ሠራተኛውን ከአሰሪው ጋር በማቀራረብ ችግሮችን በተገቢው ጊዜ መፍታት፣ ሠራተኛው መብትና ግዴታውን አውቆ ከድርጅቱ ጋር ተባብሮ የሚሰራበትን መንገድ ማመቻቸት እና ማንኛውም የማኅበሩ አባል የድርጅቱን ንብረቶች እንደራሱ በመመልከት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማስገንዘብ መሆናቸውን ለሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ማኔጅመንት ሰርቪስስ በፅሁፍ በመግለፅ ድርጅቱ ያስተላለፈውን ማስጠንቀቂያ ተቃውሟል።

በሠራተኛ ማኅበሩና በድርጅቱ መሐል የተፈጠረው ውዝግብ ሊፈታ ባለመቻሉ ማኅበሩ ጉዳዩን ወደ አዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ወስዶታል። ማኅበሩ ዕውቅና ካገኘበት ቀን አንስቶ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ምንም ዓይነት ድጋፍ ከአሰሪው አካል እየተደረገላቸው አለመሆኑንና በሠራተኛውና በማኅበሩ አመራር ላይ አግባብ ያልሆነ ርምጃ እየተወሰደ ስለመሆኑ አቤቱታ ያቀረቡት አባላቱ ቢሮው ከድርጀቱ ጋር እንዲያስማማቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር።

የ‹‹አስማማን›› ጥያቄ የቀረበለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮም ስለ ሠራተኛ ማኅበር መብትና ግዴታ ለመወያየት የሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ማኔጅመንት ሰርቪስስ የሥራ ኃላፊዎችና የሠራተኞቹ ማኅበር አመራሮች ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ.ም ከቢሮው እንዲገኙ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

ነገር ግን የቢሮውን ጥሪ አክብረው የተገኙት የማኅበሩ አመራሮች እንጂ የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች አልነበሩም። ‹‹ሜፖ›› ከመንግስት የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ በተወካዮቹ አማካኝነት ለመወያየት ፈቃደኛ ካለመሆኑ ባሻገር የሠራተኛውን መብት ለማስከበር እየተጉ የሚገኙ የሠራተኛ ማኅበሩ አመራሮችን ከሕግና መመሪያ ውጪ ወደ ባሕር ዳር ለማዛወር ከውሳኔ ላይ ደርሷል።

ግንቦት 2 ቀን 2003 ዓ.ም ከድርጅቱ ‹‹ኩባንያው በሥሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንደሚያሰተዳድር ይታወቃል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል ፕሮጀክት ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የብረት ሠራተኞችን እንድንልክለት ጠይቆናል። ስለዚህ እርስዎ ከግንቦት 04 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ባሕር ዳር የተዛወሩ መሆኑን እንገልፃለን›› የሚል ደብዳቤ የደረሳቸው አመራሮች ውሳኔውን በቸልታ አላለፉትም።

በድንገት የተላለፈውን የዝውውር ውሳኔ ‹‹የሠራተኛውን መብት የጣሰና ከባሪያ ባልተናነሰ ሁኔታ እንደሚመለከቱን ማሳያ ነው›› ሲሉ ከመተቸታቸውም በላይ ለሚመለከታቸው አካላት ‹‹አቤት›› ብለዋል።

አቤቱታ ከቀረበላቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ድርጅቱን በፅሁፍ አስጠንቅቋል።

በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቀጥር 377/96 አንቀጽ 178 እና 179 ለሥራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አልግሎት በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ.ም የቢሮው የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች የአዋጁን አፈፃፀም እና በማኅበሩ አመራር ላይ እየተወሰደ ያለውን ርምጃ ለመቆጣጠር በድርጅቱ ወስጥ ተገኝተው ነበር።

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሠራተኞችን መብት እየጣሰ መሆኑ የተነገረውን ድርጅት በጠንካራ ቃላት ቢያስጠነቅቅም ጉዳዩን አስመልክቶ ለአውራምባ ታይምስ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም፡፡

በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት በድርጅቱ ላይ የተወሰደ ሕጋዊ ርምጃ ስለመኖሩ እና የኢትዮጵያ ዜግነት የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሊሰማሩባቸው በሚገቡ የሥራ መስኮች ላይ ተሰማርተው ስለመገኘታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ መረጃ እንዳለው ለማጣራት ሙከራ አድርገን ነበር፡፡

ነገር ግን ተፈላጊውን መረጃ በመስጠት ፋንታ ‹‹ሚዲያ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አገባው? ጉዳዩን ለሕዝብ እንዲደርስ ማድረግም ጥቅም የለውም፡፡ ምናልባት በዘገባው ባለሀብቱ ሊጎዳ ይችላል፤ ይኼ ደግሞ የመንግስት የልማት አቅጣጫ አይደለም›› ባሉት የቢሮው የሥራ ኃላፊዎች ማንገራገር የተነሳ ሙከራችን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሜፖ ኮንትራክቲንግ ኤንድ ማኔጅመንት ሰርቪስስ ኃ/የግ/ማ የሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን አቶ ፈቃደሥላሴ ወርቁ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቀናቸው፣ በአሁኑ ሰዓት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ገልፀውልናል።

በሌላ በኩል ሠራተኞቹ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ሲሆን፣ መዝገባቸውን እየተመለከተ የሚገኘው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ-1 የሥራ ክርክር ችሎት ያለ ደመወዝ ለታገዱት የማኅበሩ አመራሮች ድርጅቱ ያልከፈላቸውን ደመወዝ እንዲ ከፍል ሰኔ 1 ቀን 2003 ዓ.ም ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ለሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ የአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍልም ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሚያቀርብ ይገልፃል፡፡

ተቆጣጣሪዎቹ በድርጅቱ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በግልፅ እየተጣሰ መሆኑን እንደተገነዘቡ ቢሮው ገልጿል። በተለይም፣ ‹‹መሠረታዊ የሥራ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ በሚል ርዕስ›› የሚጀምረው ደብዳቤ በድርጅቱ ውስጥ የሥራ ሁኔታዎችን የሚደነግግ የውስጥ ደንብ እና ሠራተኞችን ከቦታ ቦታ አዘዋውሮ ስለሚያሰራበት ሁኔታ የሚገልፅ መመሪያ ስለመኖሩ ተቆጣጣሪዎቹ ላቀረቡት ጥያቄ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የሰጡት ምላሽ አዋጁን እንደሚጥስ በማስታወስ የኃላፊውን አዋጅ የጣሱ ምላሾች ዘርዝሯል።

የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን መሠረት ያላደረጉት የሜፖ ምላሾች ‹‹ሠራተኛውን የሚቀጥረውና ደመወዝ የሚከፍለው ድርጅቱ ነው፤ ስለዚህ ማንኛውንም ሠራተኛ በተፈለገው ቦታ በማንኛውም ጊዜ ማዛወርና ማሰራት እንችላለን። ደንብና መመሪያም የለንም››፤ እንዲሁም በድርጅቱ ስለተቋቋመው መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበርና በድርጅቱ መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ለመወያት ከቢሮው የተላፈውን ጥሪ አስመልክቶ፣ ‹‹ቢሮው ያለበትን ቦታ አናውቅም፤ ደግሞም ቅድሚያ የምንሰጠው ለሥራችን ነው›› የሚሉት ሲሆኑ፣ ሕጋዊ ዕውቅና ያገኘውን የሠራተኛ ማኅበሩን አመራሮች እንደማያውቅ መግለፁና የሠራተኞቹ መብት ከግምት ውስጥ ሳይገባ በዘፈቀደ ወደ ባሕር ዳር እንዲዛወሩ መወሰኑም አዋጁን የጣሰ ሆኖ ተገኝቷል።

ቢሮው ለድርጅቱ በግንቦት 5 ቀን 2003 ዓ.ም የፃፈውን ማስጠንቀቂያ ያጠቃለለውም ‹‹ይህ ደብዳቤ በደረሳችሁ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንድታደርጉ። ይህ ካልሆነ ግን የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆናችንን እንገልፃለን›› በሚል ማሳበቢያ ነው።

ምንም እንኳን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

‹‹ልጄ ሆይ የአባትህን

ትዕዛዝ ጠብቅ

የእናትህንም ሕግ አትተው››

ምሳ 6፤20

ግንቦት 28 ቀን 2003

ዓ.ም 4ኛ ዓመት ልደትህን

ላከበርከው ባቡሹ ፓቼ እንኳን

አደረሰህ!

ስታድግ ወላጆችህን ፓቼንና

አልሚን ብቻ ሳይሆን

ከአንተ ብዙ የምትጠብቀውን

አገርህን እንደምታኮራት

መከታም እንደምትሆን

እተማመንብሃለሁ!

ተሻለ ሰይፉ

Page 17: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 200318

ሴት

ከዚህ ቀደም ባቀረብነው ፅሁፍ ላይ አንዳችን በአንዳችን ልብ ውስጥ እንድንቆይ ማድረግ ስላለብን ነገር በመጠኑ ዳሰናል።

ለዛሬ፣ በዚህ በወጉ ሳይጠናኑ የሚገቡበት ትዳር እንደአሸን በሚፈፀምበት እና ወራት ባልተቆጠሩ ጊዜያት ውስጥ ፍቺ በሚፈፀምበት ወቅት ‹‹ለምን?›› ብለን ጠይቀን ላልተመለሱልን ጥያቄዎች እንደምን ይህ እክል እንዳይፈጠር ቀድመን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን የሚለውን እንመልከት። ሁሉንም እንስቶች በተዘዋዋሪ የሚመለከት ቢሆንም ባለትዳር እንስቶችን ማዕከል አድርገን 10ቱን ወርቃማ ሕግጋት እንፈትሽ።

የትዳር አጋርሽን እንደምታምኝው ግለጭለት። በአንቺ የመታመን ስሜት 1. አቋን ሳላላ እንዲኖር ያስችለዋል። በጣም ማመን ማለት ግን ችላ ትይዋለሽ ማለት አይደለም።

የሚያደርጋቸውን ነገሮችና ያለበትን ቦታ የመሳሰሉ ነገሮችን ከመቆጣጠር 2. ተግባር ተቆጠቢ። ባለትዳር ወንድ የት ነህ? ምን እያደረክ ነው? ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብሃል? ከማን ጋር ነህ? የሚሉ ጥያቄዎች በጥርጣሬ መልክ ሲቀርቡለት ይበሳጫል። የብስጭቱ ምላሽ ደግሞ ወደአንቺ መጋባቱ አይቀርም።

አስቢለት፣ ተንከባከቢው። ይህንንም በተግባር አሳይው። ይህ ማለት ግን 3. በራሱ ነገሮችን ማከናወን የማይችል በሚያስመስል መልኩ እንዳይሆን ተጠንቀቂ።

አይኑን ሸፍኚው። ይህ ማለት ከአንቺ አንዳች ነገር አጥቶ ያን ጉዳይ 4. ሌላ ቦታ የሚፈልግበትንና የሚመራመርበትን ቀዳዳ አትክፈች። አሁንም አንድ ነገር ተጠንቀቂ። ይህ አንቺ ዋጋ የሌለሽ እሱ ደግሞ አድራጊ ፈጣሪሽ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ካየው ይልቅ ያላየው ነገር ያጓጓዋልና ለምንም ነገር አዲስ እንዳይሆን አድርጊው።

ለቤተሰቦቹ አክብሮት አሳዪ። ይህ ምናልባት እነሱ ለአንቺ ጥሩ ስሜት 5. የሌላቸው ቢሆን እንኳ መፈፀም ያለበት ጉዳይ ነው። አሉታዊ ጎኖቻቸው ላይ ያተኮረ ንግግር አታድርጊ። በእርግጥ የሚሰማሽን ደብቂ ማለት አይደለም። ችግሮች ቢኖሩ እንኳ ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ባለሽ እምነት ላይ አፅንኦት ስጪ። ለምሳሌ ‹‹ባክህ… እነሱ ምንም ባደርግ ሊወዱኝ አይችሉም…›› ከማለት እና በእሱም ላይ

10ቱ

ወርቃማ ሕጎች ለትዳርሽ

የተዛባ አመለካከት ከማሳደር ይልቅ የእነሱ ባንቺ ላይ ያለው አሉታዊ አመለካከታ በደንብ ስላላወቁሽ እንደሆነና ቢያውቁሽ ነገሮች ሁሉ መልካም እንደሚሆኑ አድርገሽ አስረጅው። እንዲያ ካልሆነ ምን አልባትም በቤተሰብ ምክንያት ብቻ ትዳራችሁ ወደማብቃቱ ሊደርስ ይችላል።

በችሎታቸው፣ በስልጣናቸው ወይም በክብራቸው ከሱ ስለሚሻሉ ሰዎች 6. ስታወሪ ተጠንቀቂ። በተለይ እነዚህ ሰዎች የቅርብ ጓደኞቹ ከሆኑ የመናቅ እና ከእነሱ የማነስ ስሜት ልታሳድሪበት ትችያለሽ።

ፍቅር የየራሱ መገለጫዎች ቢኖሩትም ለልጅሽ፣ ለአባት እናትሽ ወይ 7. ለሌላ ሰው ያለሽ ፍቅር ለእሱ ካለሽ የሚበልጥ አድርገሽ አትግለጪ። ‹‹ከእሱ ቀጥሎ›› በይ። እሱ ላንቺ ምን ያህል እንደሆነ ማወቁ በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥርለታልና አንቺም ለእሱ ምን ያህል እንደሆንሽ አድርጎ እንዲያስብ ታደርጊዋለሽ።

ራስሽን ገንቢ። አንብቢ፣ ከልምድ ቅሰሚ። ያንንም በሕይወት ውስጥ 8. ተግብሪ። ካሰብሽበት ዕውቀት ከተለያየ አቅጣጫ ይገኛል። ትርኪ ምርኪ የሚሰኙ ፅሁፎችን፣ የራዲዮና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን ከመከታተል ይልቅ እውቀት የሚገኝባቸውን ምረጪ። እንዲያ ስል ደግሞ ምንም አይነት አዝናኝ የራዲዮና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን አትመልከቺ ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ጠለቅ ያለ መረጃ ያላቸውን ነገሮች ባወቅሽ እና ማወቅሽን እሱ ባወቀ ጊዜ በአንቺ እንዲተማመንብሽና እንዲያደንቅሽ እንዲሁም በሰዎች ፊት ሁሉ እንዲኮራብሽ ታደርጊዋለሽና ነው።

በባለትዳርና በላጤ ሴቶች መካከል ያለውን ልዩነት ለዪ። ሁለቱ የተለያዩ 9. ምዕራፎች ናቸው። ‹የትዳር ህይወት እስር ቤት ነው› ማለት ሳይሆን ከዚያኛው የሚለየው የራሱ ስርዓት፣ ሕግና ፍልስፍና አለው። ለምሳሌ ላጤ ሆነሽ ተቃራኒ ጾታ ያላቸውን እያቆላመጥሽ ‹ዬ› እያልሽ ብትጠሪ ያን ያህል ትኩረት ላይስብ ይችላል። ወደትዳር ስትመጪ ግን ይህ አጠራር ለሌሎች ሲውል ብዙ ምቾት ላይሰጥ ይችላልና ተጠንቀቂ።

ራስሽን አትጣይ። በአለባበስ በንፅህና ተዋቢ። ግን ደግሞ 10. ስርዓት ያለው፤ ቢቻል እሱን ሊያስደስተው የሚችል አይነት ቢሆን ይመረጣል። እንዲያ ስልሽ ለእሱ ብቻ እንጂ ለሌሎች ወይንም ለአንቺ እይታ ግድ አይኑርሽ ማለቴ አይደለም፤ አለባበስሽ ለትዳር አጋርሽ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንዳይረበሹበት አድርጊው ማለቴ እንጂ። በአገራችን ባይለመድም፤ የምትጠቀሚያቸው ነገሮች የተለያዩ አይሁኑ። ማለትም አንድን ሽቶ የምትጠቀሚ ከሆነ ያንቺ መለያሽ እሱ ይሁን። የምትጠቀሚያቸው ነገሮች ውሱን መሆን እና አለመብዛት እሱ ያንቺን ነገሮች የትም ሲሄድ እንዲለይና ‹ይሄ የእሷ ነው› ብሎ እንዲያስብ ታደርጊዋለሽ።

ከላይ የተዘረዘሩት እኔ ለአንቺ ትዳር ይሆናሉ ያልኳቸው ሐሳቦች መሆናቸውን አትርሺ። በእያንዳንዱ ስኬታማ ትዳር ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ወርቃማ ሕጎች ሊኖሩ ይችላሉ። ያን የተገበሩትም እስከመጨረሻው ስኬታማ ሆነዋል። ስለዚህ ከላይ ያስቀመጥኳቸው 10 ሕጎች ብቻ እንዳልሆኑ ልብ ልትይ ይገባል። አንቺ በትዳር ውስጥ ያለሽን ልምድ ከዚህ ጋር አክይበትና ተግብሪው።

በተለይ ለአንቺ የህይወትሽ ረዥሙ ክፍል በትዳር የቆየሽበት ሊሆን ይችላልና ያን ረዥም ጊዜሽን በማይመች ሁኔታ እንዳታሳልፊው ሊረዳሽ ይችላል - ይረዳሻልም። ሳምንት ለሴቶች የሚሆን ከሌላ አቅጣጫ የተቃኘ የ10ቱ ወርቃማ ሕግጋትን እንመለከታለን።

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

ያድምጠን፣ ያወያየን ብለው ጉብ ቂጥ ሲሉ የነበሩ ሰዎች፣ የሌላውን መብት ለመንፈግና የአምባገነኖችን መዳፍ ለማስፋት መጣራቸው ያሳፍራል፤ ያሳዝናል።

-ሐ-እንደው ለነገሩ ነው እንጂ እነዚህ

የግል ጋዜጦች፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ተብዬዎቹ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባለመገኘታቸው የቀረባቸው ነገር የለውም። እንደውም የኪነ-ጥበብ ሰዎች ተብዬዎቻችንን ማንነትና ምንነት የመለየት መልካም ዕድል ነው የገጠማቸው።

እንደውነቱ ከሆነ የኪነ-ጥበብ ሰዎች አጎንብሱ ሲባሉ የሚያጎነብሱ መሆን የለባቸውም። እስከውቀው ድረስ እንኳንስ የእነሱ የራሳቸው፣ የሌላ ሰው አንገት መድፋት የሚያስቆጫቸው መሆን ነበረባቸው። ለምን? ብለው መጠየቅና ሞጋች መሆን ነበር የሚገባቸው። ይህ ለምን ባይነት ነው ብዕራቸውን፣ ቡርሻቸውን፣ ካሜራቸውን ወዘተ እንዲያንቀሳቅሱ ብርታትና ኃይል የሚሆናቸው። ከያኒ የሚል ሥምን የሚያሰጣቸውና የሚያጎናፅፋቸው ‹‹ለምን?›› ማለት ነበር ብዬ አምናለሁ።

ለምን አለማለት ግን ራሱን የቻለ ሞት ነው። ለምን የሚል ጠያቂን በመንቀፍና በማግለል ከሹም ጋር ለመሿሿም መሯሯጥ ከአንድ አገር የኪነ-ጥበብ ሰው የሚጠበቅ ተግባር አይደለም። ሊሆንም አይችልም። እንዲያ ከሆነ ከያኒው በሕዝብ መሀል የለም ወይም አልነበረም ማለት ነው። ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዊሣ (ሎሬት) ‹‹የከያኒ ሞት ጅማሬ›› ሲሉ የገለፁት እንዲህ ያለውን ሁኔታ ይመስለኛል። የፀጋዬን አባባል ቃል በቃል ልጥቀሰው፡-

‹‹የሕዝቡ ሙቀት ካልሞቀህ፣ በሕዝቡ ሕዝባዊነት ውስጥ ካልታቀፍክ፣ የእሱን ሕይወት አትተረጉምም። የደራሲ (ከያኒ) ሞት የሚጀምረው ከሕዝቦች አካል ውጪ ከተለየ በኋላ ነው … ››

መሪዎች የሚወዱትን በመውደድ፣ የጠሉትን በመጥላት፣ ያገለሉትን በማግለል አጓጉል ለመሞዳሞድ ሲባል ፕሬሶች ነገራቸውን እንዳይዘግቡ መከልከል፣ የመፃፍና የመናገር ነፃነትን ለመገደብ ተባባሪ መሆን፣ ለኪነ-ጥበብ ሰዎች ነን ባዮች ሁሉ ራሱን የቻለ ‹‹ሞት ነው›› ብዬ አምናለሁ።

-መ-እርግጥ ነው በዚህ ጉዳይ

ላይ የሀገሪቱ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ሁሉ ተወቃሽ መሆን እንደሌለባቸው አምናለሁ።የክልከላው ውሳኔ የተሰጠው የብሔራዊ ሥነ-ጥበባት ሰብሳቢ በተባለው ኮሚቴ ነው። ኮሚቴ ማለት እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ‹‹ራስ/ጭንቅላት›› ማለት ነው። ራስ

ደግሞ የሰውነት ክፍሎችን ሁሉ የሚያዝ ዋንኛ አካል ነው። የሁሉም አካል መሪ የሆነው ራስ (አናት) ከተበላሸ የተቀረው አካል ጤነኝነት እንደሚታወክ መናገር አያስፈልገኝም።ከአናቱ ‹‹ጤነኛ›› ያልሆነ ኪነ-ጥበብ ደግሞ እንዳለ አይቆጠርም። ደካማነትን እንጂ ብርታትን አያስገኝም። ውድቀትን እንጂ ዕድገትን አያመጣም። ማስመረር እንጂ ማስተማር አይችልም። መበታተንን እንጂ አንድ መሆንን አያተርፍም። ስለዚህም ይመስለኛል አበው፡-

‹‹ከላይ አንድ ድግር - ከታች አንድ ድግር፣

እንደዚህ ሲል ያልቃል- የደካማ ምድር›› ይሉ ብሒል ያኖሩልን።

ይህ ማለት በብሔራዊ ኅብረ-ሥነ-ጥበብ ውይይት አመቻች ኮሚቴዎች ውሳኔ ሰጪነት የተላለፈው አሳፋሪ ተግባር የሚያሳየው የሀገራችንን ኪነ-ጥበብ ደካማነት ነው ማለት ነው። የሀገራችን ኪነ-ጥበብ ደካማ ሆነ ማለት፣ የባለሙያዎቹንም ድክመት ነው የሚያጋልጠው። ደካማ የኪነ-ጥበብ ሰው ደግሞ እንኳን ለሌላው፣ እንኳን ለብዙሃኑ፣ እንኳን ለሀገሩ፣ ለራሱም የሚበጀውን ማወቁን እጠራጠራለሁ።የሆነውም፣ በውይይታቸው የታየውና የተሰማውም አንድና አንድ ዕውነት ደግሞ ይኸው ደካማነታቸው ነው። በጥቂቱ ላስረዳ፡-

-ሠ- የኪነ-ጥበብ ሰዎቻችንን

የ‹‹ናፈቋቸውን›› ጠ/ሚ/ር መለስ ቁጭ አድርገው ድራማ አሳዩአቸው። እኔም ድራማቸውን በቴሌቪዥን መስኮት አየሁላቸው። እናንተ አንባቢዎቼም አይታችሁታል ብዬ እገምታለሁ። ድራማው ካለቀ በኋላ የማይጠየቅ ጥያቄ ደረደሩላቸው።

አቶ መለስም ‹‹እዩ!›› የተባሉትን ድራማ አዩ። ጥያቄአችን ነው ያሉትንም በጥሞና ሰሙ። በመጨረሻም የኪነ-ጥበብ ሰዎቻችን አስተካክለው ያላቀረቡትን ጥያቄ እያስተካከሉላቸው መልስ ሰጡበት። በመልሳቸው መኃል ካሳዩአቸው ‹‹አርቲ ቡርቲ›› ድራማ መሀል አንድ ነገር ትዝ አላቸውና - ‹‹ቅድም›› አሉ። በወረቀት መወደድ የተነሳ የኪነ-ጥበብ ሰዎቻችን ለመሰደድ ማሰባቸውን (እኔ የገባኝ እንደዛ ነው) ነቅሰው አስታወሱና፣ ቅልብጭ ያለ ትንታኔዊ ምላሽ ሰጧቸው።ይህ ምላሻቸው ታዲያ የጎጃሙ አለቃ ገብረሀና ተብለው በታሪክ የሚታወቁትን ሰው አባበል ነው ያስታወሰኝ።

በአፄው ዘመን አለቃ ገብረሐና ጎጃም ክፍለ ሀገር አንድ ወረዳ የሚስተዳድሩ ቀኛዝማች ቤት ይሄዳሉ አሉ። አለቃ ገብረሐና ከቀኛዝማቹ ጋር እያወሩ ሳለ የወረዳው ነዋሪዎች ሰብሰብ

ብለው ይመጡና ተበደልን ያሉትን ነገር ሁሉ ዘርዝረው ያስረዳሉ። በመጨረሻም ከመማረራቸው የተነሳ ሀገር ለቀው ለመሰደድ መወሰናቸውን ይገልፃሉ። ይኼን ጊዜ አለቃ አቤቱተኞቹን፣ ‹‹ባላገር እውነትሽን ነው የምትይኝ? እውነትሽን ከሆነ’ማ ነይ ሳሚኝ›› አሉ አሉ።

ጠ/ሚ/ር መለስም ለአርቲስቶቻችን በወረቀት መወደድ የተነሳ ‹‹ልንሰደድ ነው›› አይነት ጥያቄ ሲያቀርቡ ‹‹እውነትሽን ነው አርቲስት? እውነት ከሆነ ነይ ሳሚኝ›› ይላሉ ብሎ ጠብቄ ነበር። ወይም ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ›› ይሏቸዋል ብዬ ገምቼ ነበር።

እሳቸው ግን በሰከነ መንፈስ ‹‹የወረቀት ዋጋ ሰማይ ተሰቅሏል ማለት ኪነ-ጥበቡ ወገቡን ተመቷል ማለት አይደለም። የኪነ-ጥበብ ሰው ማንበብና መፃፍ አቆማለሁ አይልም›› የሚል ‹‹ምን ነካችሁ!!!?›› አይነት መልስ ነው የሰጧቸው። ከገባቸው ማንበብ፣ ማንበብ አሁንም ማንበብ እንደሚገባቸው ነው የመከሯቸው።

በመጨረሻየመጀመሪያውም የመጨረሻውም

እውነት ይኼው ይመስለኛል። ማንበብ ያስፈልጋል። ዕውነትን ማወቅ ያስፈልጋል። በማንበብ ዕውነትን ለይቶ እውቀትን ማዳበር የሚሻ ወይም የቻለ ሰው የመፃፍና የመናገር ነፃነትን ለመገደብ አይቃጣም። የክልከላ ተባበሪ ሆኖ አይሆንም። ሊሆንም አይችልም። ምክንቱም ህሊናው አይፈቅድለትም።

የብሔራዊ ኅብረ-ሥነ-ጥበባት ምክከር መድረክ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ግን ያደረጉት ተቃራኒውን ነው። በጠሩት የውይይት መድረክ ላይ ‹‹የፖለቲካ›› ብለው የፈረጁአቸውን ፕሬሶችን በጠሩት ስብሰባ ላይ መገኘት የለባቸውም የሚል።

ይህ ምን ማለት ነው? የኪነ-ጥበብ ሰው ነን ከሚሉ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ አግላይነት ይጠበቃል? አይጠበቅም። እንዲህ አይነቱን እሳቤ ይዞ ህዝብን አዝናናለሁ፣ አስተምራለሁ፤ በጥበብ ዕውቀትን አቀብላለሁ ማለት ይቻላል? አይቻልም። የሚቻልም አይመስለኝም። ለማንኛውም እኔ ማለት የምፈልው ‹ልቦና ይስጣችሁ! ልቦና ይስጠን›› ነው። ዋናው ልብ ነው። ፈሪም ፍርሃቱን ደፋሩም ድፍረቱን ይዞ የሚኖረው በልቡ ነው ብዬ አምናለሁ። እናንተ ከፈራችሁ አትፃፉ አትናገሩ። ፕሬሱ ግን ያለችውን ጠባብ መሬት ቀስ በቀስ ለማስፋት የሚወጣውን እና እየተወጣ ያለውን ቅን ተግባር ለማሰናከል ተባባሪ አትሁኑ ማለት ነው የምፈልገው። ቢያንስ ይህንን በማድረግ መረጃ የሚፈልገው ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ባለመፃረር ዕርዱት ማለት ነው የምፈልገው።አበቃሁ።

ማለትም አንድን ሽቶ የምትጠቀሚ ከሆነ ያንቺ መለያሽ እሱ ይሁን። የምትጠቀሚያቸው ነገሮች

ውሱን መሆን እና አለመብዛት እሱ ያንቺን ነገሮች የትም ሲሄድ እንዲለይና ‹ይሄ የእሷ

ነው› ብሎ እንዲያስብ ታደርጊዋለሽ።

በሱራፍኤል ግርማ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመጋቢት ወር ላይ የቀረበለትን የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ረቂቅ አዋጅ ጉልህ ማሻሻያ ሳያደርግበት አፀደቀ። ም/ቤቱ ረቂቁን ያፀደቀው ከትናንት በስቲያ ሲሆን፤ ረቂቁን ሲመረምሩ የቆዩት በም/ቤቱ የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳዳር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብና ሪፖርት አቅርበዋል።

በቋሚ ኮሚቴዎች ሪፖርት መሠረት፣ በአዋጁ ላይ የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አመራሮች ከቋሚ ኮሚቴዎቹ ጋር፣ እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።

ከውይይቱ የተገኙት ጭብጦችም፣ ለረጅም ጊዜ በመንግስት ሠራተኞች ብቻ ተወስኖ የቆየውን የጡረታ ሽፋን በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ማስፋፋት የኢንዱስትሪ ሰላምና መረጋጋት የሚያመጣ መሆኑ፣ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማሩት ዜጎች የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋን

እንዲኖራቸው ማድረግ በሕገ-መንግስቱ የተደነገገውን የዜጎች የማኅበራዊ ዋስትና የማግኘት መብት እንደሚያረጋግጥ እንዲሁም ከዘርፉ የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮ ገንዘብ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ምንጭ ሊሆን መታመኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ምንም እንኳን የማኅበራዊ ጉዳዮች እና የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በረቂቁ ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ ማሻሻያዎች እንደተካተቱበት ቢገልፁም ከም/ቤቱ አባላትም ሆነ ሌሎች ወገኖች ትችት የተሰነዘሩበት አንቀፅ 26 ማሻሻያ አልተደረገበትም።

ስለተመላሽ የጡረታ

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ጉልህ ማሻሻያ ሳይደረግበት ፀደቀ

መዋጮ የሚተነትነው ይህ የአዋጁ ክፍል በርካታ ተቃውሞ የገጠመው፣ በተለይም በሁለተኛው ንዑስ አንቀጽ ከ10 ዓመታት ያነሰ አገልግሎት ፈፅመው በራሳቸው ፈቃድ ሥራቸውን ሲለቁ ምንም ዓይነት የጡረታ ክፍያም ሆነ ለጡረታ ክፍያ ከደመወዛቸው የሚያዋጡት ገንዘብ እንደማይመለስላቸው በመደንገጉ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም አንድ የግል ድርጅት ሠራተኛ፣ ከ10 ዓመት ያላነሰና 20 ዓመት ያልሞላ አገልግሎት ፈፅሞ በራሱ ፈቃድ ሥራውን ከለቀቀ ወይ ከ20 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በአዋጁ ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውጪ ከሥራ ከተሰናበተ የአሰሪውን ድርሻ ሳይጨምር ሠራተኛው ራሱ ባዋጣው መጠን ብቻ የጡረታ መዋጮው እንዲመለስለት አንቀጽ 26 ላይ ተገልጿል።

ምንም እንኳን ረቂቅ አዋጁ መጀመሪያ ለም/ቤቱ በቀረበ ጊዜ አንቀጽ 26 ላይ ያሉትን ድንጋጌዎች ‹‹የሠራተኛውን ገንዘብ መውረስ ነው›› በሚል የሕዝብ ተወካዮቹ ነቅፈውት የነበረ ቢሆንም ከትናንት በስቲያ ረቂቁ በፀደቀበት ጊዜ ግን ይኼን ጉዳይ ያነሳ የፓርላማ አባል አልነበረም።

ከ20 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በአዋጁ

ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውጪ ከሥራ ከተሰናበተ የአሰሪውን

ድርሻ ሳይጨምር ሠራተኛው ራሱ ባዋጣው መጠን ብቻ የጡረታ

መዋጮው እንዲመለስለት አንቀጽ 26 ላይ ተገልጿል።

Page 18: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ዜ ና ዎ ች 19

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ባለቤታቸው ቢል ክሊንተን በስምንት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያን ባይጎበኙም፣ ከፕሬዝዳንትነት ከተሰናበቱ በኋላ ከአራት ዓመት በፊት ‹‹ከክሊንተን ፋውንዴሽን›› የሥራ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ አገራችንን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ሂላሪ ክሊንተን፣ የኦባማ አስተዳደር ሥልጣን ከተረከበ ወዲህ ወደኢትዮጵያ ከመጡ የአሜሪካን ባለሥልጣናት መካከል በከፍተኛ መንግሥታዊ የሥልጣን ዕርከን ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

ሂላሪ ክሊንተን...

ለዘመናት በጭቆናና በችጋር ፍዳውን ሲያይ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የፍትሕና የዕድገት ፀሐይ ቀን በኢትዮጵያ ምድር እንድትወጣ ተስፋ ሰንቆ ነበር። በርካታ የሚያማልሉ ተስፋዎች ደግሞ እውን ሆነው ለማየት እንደተለመደው በጉጉት መጠበቁን ቀጠለ። የኢህአዴግ የአገዛዝ ዓመታት እየተደራረቡ ሲያልፉ፤ የዚያኑ ያህል የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭቆናና ድህነት እጥፍ ድርብ እየሆነ መጣ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓለም አንቅሮ የተፋው አብዮታዊ ዴሞክራሲና እርሱን መሠረት አድርገው የሚነደፉ ደካማ ፖሊሲዎች መሞከሪያ ጣቢያ ሆነ። ከ20 የመከራ ዓመታት በኋላ ማሳረጊያው የአንድ ፓርቲና የአንድን ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነትን ማንገስና አፈናና ድህነትን ማባባስ ሆነ።

ብዙ የተተረከለት የልማት መስመርና የኢኮኖሚ መስፈንጠር ውጤት ምን እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሀብና በጭንቅ ውስጥ ወድቆ በተግባር እየመሰከረ ነው። ኢህአዴግ መሬት ባልረገጠ፣ በተዝረከረከና የኢትዮጵያ ሕዝብ እውቅናና አመኔታ በነሳቸው ፖሊሲዎች ኢትዮጵያን ለ20 ዓመት ሲያተራምስ መቆየቱ ሳይበቃው፣ አሁን ደግሞ ሕዝቡን ወደ ፍፁም የኢኮኖሚያዊ ድቀትና የአፈና አዘቅት ውስጥ ከቶታል።

ላለፉት አምስት ወራት እየተካሄደ ያለው ‹‹መንግስታዊ›› ቧልት የዚሁ ጉዳይ ሁነኛ ማሳያ ነው። በቁጥጥር ፍቅር ልክፍት የወደቁት አምባገነን መሪዎቻችን ኢኮኖሚውን፣ ፖለቲካውን፣ ማህበራዊውንና የኪነ-ጥበብ ዘርፉንም ሳይቀር በአንድ በውል በሚቆጣጠሩት ቋት ውስጥ ለመክተት ከላይ ታች እየረገጡ ይገኛሉ። በዚሁ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ የመቆጣጠር አባዜያቸው ሕዝብን፣ በተለይ የንግዱን ማህበረሰብና ባለሞያዎችን ሳያማክሩ በሥራ ላይ ባዋሉት እውር ድንብር ውሣኔ ድሮም ቋፍ ላይ የነበረውን ‹‹የነፃ ገበያ›› የባሰ ውዥንብር ውስጥ ጥለውታል። ሕዝቡ ባልተጠናው የዋጋ ገደብ ምክንያት የኑሮ ውድነት ባደቀቀው ቁስሉ ላይ ጨው ተነስንሶበት በህይወትና በሞት መሀከል ይገኛል። አብዛኛው የንግዱ ማህበረሰብም በኢህአዴግ የናጠጡ የንግድ ተቋማት ተገፍትሮ ከጨዋታ ውጭ እየሆነ ይገኛል። የቀረው የንግዱ ማሕበረሰብም ቢሆን ኢህአዴግ በየጊዜው በሚፈጥረው ትርምስ ለራሱም ሆነ ለሀገር ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ እንዳያደርግ ተገድቧል። ኢህአዴግ በሚከተለው ዝርክርክ የፊስካልና የሞኒተሪ

ፖሊሲ በዓለም አቀፍ ገበያ ከነዳጅና የሸቀጦች ዋጋን መጨመር ጋር ተያይዞ የብርን ዋጋ ወደ ገለባነት ደረጃ እየቀየረው ይገኛል። የዚህ ሁሉ የተተረማመሰ አሰራርና የተሳሳቱ ፖሊሲዎች ውጤትን የሚሸከመው ከባድ የችጋር ጫና ያጎበጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ገዢዎቻችን ለሚያደርሱት የኢኮኖሚ ድቀት ይቅርና ለሚቀጥፉት ህይወትም እንኳን የሚጠየቁበት ሥርዓት አልተገኘም።

በባከኑት 20 ዓመታት ውስጥ የደረሰውና እየደረሰ ያለው የኢኮኖሚ ድቀት ገዢዎችን አገር የመምራት ብቃት ፈጽሞ እንደሌላቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። አገር መምራት ባለመቻላቸው በሚፈፅሙት የመደነባበር ተግባር አገራችንን ያልተጠኑና ከሃገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይሄዱ ፖሊሲዎች መፈተሻ አድርገዋታል። የዚህ ሁሉ ገፈት ቀማሽ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹‹ይህ ሁሉ አይበቃህም›› ተብሎ በሰሞነኛ የማማለያ ፕሮፓጋንዳቸው መድረሻ አሳጥተውታል። ሰሞነኛውም ፕሮፓጋንዳ በዋናነት አባይ ላይ ያተኮረ መሆኑን ሁሉም የሚረዳው እውነት ነው።

አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በፕሮግራሙ እንዲሁም በቅርቡ ባወጣው የስትራቴጂ ሰነድ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ አባይን አይደለም ሌሎቹም ወንዞቻችን ተገድበው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም መዋል እንዳለባቸው ያምናል። ልዩነታችን እንደ ሶማሊያው ዘመቻ፣ እንደ ውሃ ማቆርና እንደ ዋጋ ተመኑ ሁሉ ሕዝብ ሳይመክርበት፣ በሚገባው ሁሉን አቀፍ ጥንቃቄ ሳይደረግበትና ኢትዮጵያውያን የዘርፉ ባለሙያዎች በወጉ ሳይመክሩበት ‹‹የምንላችሁን ብቻ ተቀበሉ›› በሚል ዘመቻ መጀመሩን ነው። እንዲሁም ለግድቡ መስሪያ ሌሎች አዋጭ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶች ባለመነደፋቸውና አሳታፊ ውይይት ባለመደረጉ በአጠቃላይ ሕዝቡ ይቅርና የጉዳዩ ባለቤቶች ነን ባዮቹ የኢህአዴግ መሪዎች እንኳን ዕለት ተዕለት ውዥንብር ውስጥ ገብተዋል። በዚህ ሁኔታ ነው የኑሮ ውድነት ያደቀቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከየትም ብሎ ገንዘብ እንዲያመጣ ጫና እየተደረገበት ያለው። ገንዘብ ሰብሳቢውም በሙሰኛነቱ የሚታወቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት መሆኑ ለሕዝቡ ትልቅ ራስ ምታት ነው። ያም ሆኖ እንደ መንግሥት ፕሮፓጋንዳ ከሆነ ግድቡ ተሰርቶ ከአሁኑ ሥራ ላይ የዋለ ይመስላል። ግድቡ ለፍፃሜ ቢበቃስ እንደተባለው 5250 ሜጋ ዋት ያመነጫል ወይ? የሚገኘው የኃይል

አቅርቦት የኢትዮጵያን ሕዝብ ከአምስት ዓመት በኋላ ከድህነት እንደሚያወጣው መናገሩ ሌላ ሕዝብን መደለያ ተውኔት ነው። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ለዘመናት በድህነት አረንቋ የተዘፈቁ አገሮች አንድ ግድብ በመገንባት ከድህነት ሊወጡ አይችሉም። ይህ መሰሉ ውዥንብር ያስፈለገው የሕዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና የመንግሥት ላይ ያለው ብሶት ገንፍሎ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት በፕሮፓጋንዳ ብዛት ለማምከን ነው።

ከዚህም በላይ ሕዝቡ የሚያደርገው መዋጮ በነፃነትና በንፁህ ፍላጎት መሆኑ ቀርቶ ያለ እምነቱና ያለ ፍላጎቱ የወር ደመወዙን እንዲያዋጣ እየተገደደ ይገኛል። ይህም አልበቃ ብሎ በውል ላልተረዳው የኢህአዴግ ሰሞነኛ የማዘናጊያ ፕሮፓጋንዳ በእድር፣ በቀበሌና በመሥሪያ ቤት ጭምር ተጠፍንጎ እንደደርጉ ‹‹የእናት ሀገር ጥሪ›› ያለፈቃዱ ሰልፍ እንዲወጣ እየተገደደ ነው። ሀገሪቷ የምትመራው በሰሞነኛ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ፕሮፓጋንዳ ነው።

ከሃያ ዓመታት የአፈና አገዛዝ በኋላ ሥርዓቱ በሁሉም አቅጣጫ የመለወጥ ፍንጭ ፈጽሞ አይታይበትም። በዚህ ዓመት በተለያየ ወቅት፣ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የአፈናና የወከባ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ሕዝቡ በሚገባ ያውቀዋል። አሁን ደግሞ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው መረን የለቀቀ ተግባር ሁነኛ ማሳያ ነው። በገሀድ እንደሚስተዋለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግን ደግፎ ካልሆነ በስተቀር የተለየ ሃሳብ ማራመድ እንደማይቻል ተደጋግሞ ታይቷል። ያለው አምባገነናዊ አገዛዝ ተማሪዎች የተመደበችላቸውን ውሱን በጀት ሳይቀር መንጠቅ፣ ነጥቆም ጥያቄ ሲነሳ በጭካኔ ማፈን፣ ተፈጥሯዊ መብቱ አድርጎታል። ከግንቦት 22/2003 ዓ.ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው አፈና በአስቸኳይ መቆም አለበት። ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች ሰብአዊ ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው በአስቸኳይ ይመለሱ። ተማሪዎች በተመደበላቸው ውሱን የምግብ በጀት ላይ ጥያቄ ማንሳትና ቅሬታም ማቅረብ እንደ ከፍተኛ ወንጀል ተቆጥሮ አሰቃቂ የሆነ ድብደባ፣ እንግልትና የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው መደረጉ ሥርዓቱ አሁንም የሕዝብን መብት ረግጦ ለመቀጠል እንደወሰነ ያሳያል። ከሁሉም የከፋው ነገር ለተማሪዎችና ለመምህራን እውቀት መገበያያ ብቻ ሊያገለግል ይገባ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ማዕከል

የሥርዓቱ ደጋፊዎች ፈቃዳቸውን ሁሉ የሚፈጽሙበትና ደም የማፍሰስ ሱሳቸውን የሚያረኩበት መድረክ መሆኑ እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው። ተማሪዎቹ እንኳንስ ባጀታቸውን በሚመለከት ይቅርና አጠቃላይ ሀገራዊ ጉዳዮችን በሚመለከተ የተቃውሞ ሰልፍ ቢጠሩ ሕገመንግስታዊ መብታቸው ነው። በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 30 ንዑስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተቀምጧል። ኢህአዴግ ሕገመንግሥቱን ካወጣ ከ16 ዓመታት በኋላ ላወጣው ገዥ-ሰነድ ‹‹አልገዛም›› ማለቱን ደጋግሞ በተግባር አስመስክሯል።

በተግባር ላለፉት ሃያ ዓመታት የታየው አሁንም ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልፅ ሆኖ የወጣው ጉዳይ ኢህአዴግ አገርን ለመምራት ብቃትም ሆነ በጎ ፈቃድ እንደሌለው ነው። ሀገራችን ልትሸከም ከምትችለው በላይ የግርድፍ ፖሊሲዎች መሞከሪያ መሆኗን በቃ እንላለን። ሕዝቡ የተቃውሞ ሃሳቡን እንዳይገልጽ የሚደረግበት አፈና በአስቸኳይ ሊቆም ይገባዋል። የግንቦት ሃያ የሃያ ዓመት ትሩፋቶች አፈና፣ ረሃብና ሰቆቃ መሆን ባልተገባቸው ነበር። ሀገራችን ከምትገኝበት የውድቀት አፋፍ ልትወጣ የምትችለው በኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበረ ብርቱና ሰላማዊ ትግል ነው። ለኢህአዴግ ሀገራችንን መተው ከነአካቴው ከአፋፉ ወደ ገደሉ እንዲጨምራት ሆን ብሎ መፍቀድ ነው።

ኢትዮጵያውያን ባለፈው ታሪካችን የምናውቀው አንድ ክፍለ ሀገር ወይም የተወሰነ አካባቢ በረሀብ ሲጠቃ ነበር። አሁን ዕድሜ ለሃያ ዓመታት የኢህአዴግ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አገዛዝ ችጋር በየአንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማጀት ቤቱን ሰርቷል። ከዚህ ድህነት የነፃነት እጦት መውጫው መንገድ ሕዝቡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ሰው ተናጋሪ ሆኖ መታገልና የኢህአዴግ አገዛዝ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ከጫንቃው ሲያወርድ ብቻ ነው። አንድነት ሕዝቡ በፀና ሰላማዊ ትግል ከሚገኝበት ቅጥ ያጣ ድህነት እና ጭቆና ነፃ ለመውጣት የሚያደርገውን ትግል አበክሮ ይደግፋል።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሰኔ 2 ቀን 2003

ዓ.ም.

አዲስ አበባ

በሱራፍኤል ግርማ

ከአንድ ወር በፊት የአሲድ ጥቃት የተፈፀመባት ትዕግስት መኮንን ከብዙ ስቃይ በኋላ ህይወቷ ማለፉን ቤተሰቦቿ ለአውራምባ ታይምስ አስታወቁ። የወጣት ትዕግስት ነፍስ ከስጋዋ የተለየችው ሐሙስ ሌሊት በግምት ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል አስክሬን መመርመሪያ ክፍል የሚገኘው አስከሬኗ ለቤተሰቦቿ ባለመሰጠቱ ምክንያት ሥርዓተ ቀብሯ እስከትላንት ድረስ አልተፈፀመም ነበር።

በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናት ስቃይዋ ተባብሶ እንደነበር የገለፁልን ቤተሰቦቿ በተፈጥሯዊ መንገድ ለመተንፈስ ባለመቻሏ የተነሳ ኦክስጅን ተገጥሞላት

በመሬት ሊዝ ሽያጭ የመንግስትን ጥቅም

አሳጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች ተፈረደባቸውበኤልያስ ገብሩ በሙስና ወንጀል ክስ

የተመሰረተባቸው አምስት ተከሳሾች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በዋለው ችሎት እስከ ሰባት ዓመት ከመንፈቅ በሚደርስ ፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ወሰነ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ውስጥ 1ኛ ተከሳሽ ሳምሶን በቀለ መኃንዲስ፣ 2ኛ ተከሳሽ ገነት ማሞ የሊዝ አፈፃፀም መምሪያ ኃላፊ ሆነው አገልግለው ነበር። በወቅቱም ከቢዝነስ ወደ መኖሪያ ቤት የተቀየረውን ቦታ አስረካቢ በመሆን 2ኛ ተከሳሽ የሊዝ ውሉ ለቢዝነስ 50 ዓመት መዋዋል ሲገባት አራቱንም ቦታዎች ወደ 99 ዓመት መኖሪያነት በመቀየር እና የሊዝ ውል መዋዋላቸውን የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል።

በዚሁ ክ/ከተማ የመሬት ልማት ቡድን መሪ የነበረው 3ኛ ተከሳሽ ዮሴፍ ከበደ በክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ውስጥ በሚያገለግልበት ወቅት በ1997 ዓ.ም የተሰጠውን ሥልጣን ከመጠን አሳልፎ በመገልገል ቦታው ለንግድ አገልግሎት ብቻ የሚፈቀድ መሆኑን እያወቀ የክፍለ ከተማው ቦርድ ሳይወስን ቦታው ለመኖሪያነት ተቀይሮና የሊዝ ዘመኑ ከ50 ዓመት ወደ 99 ዓመት ተለውጦ ሲቀርብ ፈቃድ እንዲሰጥ ማድረጉ በክሱ ላይ ተመልክቷል።

በተመሳሳይም በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች አብደላ ነስሩ እና መሐመድ ሁሴን በጨረታ ያስነሷቸው አራት ቦታዎች ከላይ እንደተገለፀው የሊዝ ዘመኑ እንዲለወጥ አድርገዋል።

በዚህም መሠረት ግንቦት 7 እና 8 ቀን 1998 ዓ.ም ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆኑና የእያንዳንዳቸው ስፋት 320 ካሬ ሜትር የሆኑ ሁለት ቦታዎችን 5ኛ ተከሳሽ፣ እንዲሁም ጠቅላላ ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የሊዝ ስፋታቸው 360 እና 320 ካሬ ሜትር የሆኑ ሁለት ቦታዎችን 6ኛ ተከሳሽ እንዲወስዱ መደረጉ በክሱ ላይ ተገልጿል።

በአጠቃላይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች መንግስት በሊዝ ቢሸጥ ሊያገኘው የነበረው 4,158,77.20 ብር የሚያወጡ ቦታዎችን ለ5ኛ እና ለ6ኛ ተከሳሾች በመስጠት በመንግስትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው በማስረጃ መረጋገጡን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስረድቷል። እንዲሁም 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በወንጀሉ ሥራና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን በግብረ አበርነት በፈፀሙት በሥልጣን አለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

በመሆኑም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ ሊከላከሉ ባለመቻላቸው 1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በብር 7500፣ 6ኛ ተከሳሽ በሌሉበት በሰባት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራትና በብር 15,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በኤልያስ ገብሩ

የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በከባድ የዕምነት ማጉደል ወንጀል ክስ የመሰረተበት ግለሰብ በአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና በብር አራት ሺህ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ

‹‹ሌጋተም›› በተሰኘ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ቡድን እና ‹‹ኦሚዲያር ኔትዎርክ›› በተባለ ተቋም አማካኝነት የሚዘጋጀው አፍሪካ አዋርድስ ፎር ኢንተርፕሪነር ሺፕ እ.አ.አ አቆጣጠር ሜይ 31 ቀን 2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በዘንድሮው ውድድር ላይ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ሥራ ፈጣሪዎች ተሳታፊ የሚሆኑበት እድል መመቻቸቱ

ወንጀል ችሎት ግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጠ።

አስማማው ዶላ የተባለው ተከሳሽ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን፣ በዱራሜ ዲስትሪክት የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ውስጥ የከስተመር ኬር አድቮኬት ሆኖ የሰራ እንደነበር የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል።

ግለሰቡም በሥራ ላይ በነበረበት

ወቅት ተገቢ ያለሆነ ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በግንቦት ወር 2001 ዓ.ም ለመሸጥ ከተረከባቸው 510 የቢል ሂሳብ ውስጥ ብር 7,002.28 በማጉደል የፈፀመው ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል በማስረጃ በመረጋገጡ ከላይ የተገለፀው የፍርድ ውሳኔ እንደተላለፈበት ታውቋል።

በከባድ የዕምነት ማጉደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ ተፈረደበት

ለ20 ዓመታት ተፈትኖ የወደቀ አካል በቃህ ሊባል ይገባዋል!መውጫው መንገድ ፀንቶ መታገል ብቻ ነው!

(ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

ተገልጿል። ውድድሩ ለአራተኛ ጊዜ

በተከፈተበት ወቅት አዘጋጆቹ፣ በአፍሪካ ውስጥ በከፈቷቸው የንግድ ድርጅቶች አማካኝነት የሥራ እድል ለፈጠሩ ኢንተርፕረነሮች እውቅና ሰጥተዋል። ኢንተርፕረነሮች ሥስራ ፈጣሪ ከመሆናቸው የተነሳ ለኢኮኖሚ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ እና

ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚ እድገት የእነሱ መኖር ወሳኝ መሆኑን የገለፁት አዘጋጆች በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ዘርዝረዋል።

በዚህም መሰረት፤ የአመራር ብቃት፣ ያላቸው የረዥም ጊዜ የቢዝነስ ስትራቴጂ፣ ትርፋማነት ወዘተ ኢንተርፕረነሮቹ ከሚመዘኑባቸው ውስጥ

ዋንኞቹ መስፈርቶች ናቸው። በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ

የንግድ ድርጅቶች ማመልከቻቸውን እ.አ.አ እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በwww.africaawards.com መላክ የሚችሉ መሆኑና በውድድሩ ብልጫ ያሳዩ እስከ 100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸለሙ ተገልጿል።

አፍሪካዊያን ሥራ ፈጣሪዎች ይሸለማሉ

እንደነበር ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በብቸኝነት

ሲያስታምማት የነበረው ታናሽ ወንድሟ ዮሐንስ ታደሰ በደረሰበት መሪር ሐዘን የተነሳ ራሱን ስቶ ሆስፒታል መተኛቱን ከደረሰን መረጃ መረዳት ችለናል።

በወጣቷ ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው እሁድ ሚያዚያ 30 ቀን 2003 ዓ.ም ሲሆን፣ ወንጀሉን ከግብረአበሮቹ ጋር ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረው ደግሞ ባለቤቷ አቶ ምናለ አቻም ነው። አሲዱ የተደፋባት በጭንቅላቷ፣ በጀርባዋ፣ በእጅና እግሯ እንዲሁም በከፊል ፊቷ ላይ ሲሆን በተለይም በጭንቅላቷ እና በዓይኗ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ነበር።

ትዕግስት ተኝታ ትታከምበት በነበረው የካቲት 12 ሆስፒታል የቃጠሎ

ክፍል ውስጥ አግኝተን ያነጋገርናቸው የህክምና ባለሙያዎች፣ ከአሲድ ጥቃቱ በፊት ራሷን እንዳትከላከል ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ስለተፈፀመባት እና በዚሁ የተነሳ መንቀሳቀስ የማትችል የነበረች በመሆኑ የጉዳቱ አሰቃቂነት ከዓመታት በፊት የአሲድ ጥቃት ሰለባ ከነበረችው ካሚላት በእጅጉ አስከፊ መሆኑን ባለፈው ሳምንት ገልፀውልን እንደነበር ይታወሳል።

ጥቃቱን እንደፈፀመባት የሚጠረጠረው ግለሰብ እስካሁን ያልተያዘ ሲሆን ቤተሰቦቿ ጥቃት ፈፃሚው ከነግብረ አበሮቹ ለፍትህ እንዲቀርብ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለመንግስት ተማፅኖአቸውን አቅርበዋል።

የአሲድ ጥቃት የተፈፀመባት አረፈች

Page 19: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003ጤ ና20

ማስታወስ ለሰዎች የመኖር ሕልውና ወሳኝ ነው። በአዕምሮ አማካኝነት ያለፉ ጊዜያት፣ እውነታዎች እና ክስተቶች ይቀመጣሉ፣ ይለያሉ። ከማሰብና ንቁ ከሆኑ የአዕምሮ የተግባር ሂደቶች ጋር የተገናኙ የተቀነባበሩ ሁነቶች በድጋሚ የሚፈጠሩት በአዕምሮ ውስጥ ነው። ትውስታዎች አጭርና ረዥም ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ። የአጭር ጊዜ ትውስታ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በተደረጉ ሁኔታዎችና ክስተቶች ላይ፣ እንዲሁም የረዥም ጊዜ ትውስታ ደግሞ ከረዥም ጊዜ በፊት በተደረጉ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል።

መርሳት ለምን?የመርሳት ችግር አምኔዥያ

በመባል በሳይንሱ ዓለም ይጠራል። ሥር ከሰደደ የአዕምሮ ሕመም ምልክትና በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ችግሩም ከፊል/ አጠቃላይ፣ ቋሚና ጊዜያዊ ሊሆን ቢችልም፣ ሶስት የአምኔዥያ አይነቶች አሉ። ትራንሲየንት ግሎባል አምኔዥያ፣ ችግሩ አጠቃላይ ነው። ሁሉንም ትውስታዎች በጊዜያዊነት ያጠፋቸዋል። አንቲሮግሬድ አምኔዥያ ደግሞ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተከስተው የነበሩ ሁኔታዎችን መልሶ ማስታወስ ያለመቻል ውጤት ነው። ይኼም ከባድ አደጋ ከደረሰ በኋላ ሊያጋጥም ይችላል። በሶስተኛውና ሪትሮግሬድ አምኔዥያ ላይ ችግሩ የሚመጣው ከባድ አደጋ ከመድረሱ በፊት ሲሆን ከአደጋው በኋላም ወደ ማስታወስ ዓለም መመለስ ይቻላል።

የመርሳት ችግር ከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሆኖ በሰዎች ዘንድ ይከሰታል። በእርጅና ወቅት የተለመደ ነገር ነው። ብዙ ጊዜ ድንገተኛ የመርሳት ችግር አዕምሮ በተለያዩ ከባባድ ምክንያቶች/ሁኔታዎች ሲጎዳ ቋሚና ጊዜያዊ ሆነ ይመጣል።

‹‹አልዛይመር››በሕክምና ሁኔታዎች

ከሚመጡ ችግሮች መካከል የአልዛይመር (በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነርቭ ሥርዓት በሽታ ሲሆን፣ ውጤቱም በሂደት የመርሳት፣ የመናገር፣ የመንቀሳቀስ እና በግልፅ ማሰብ ያለመቻል ችግርን ያስከትላል) በሽታ ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በዚህ በሽታ ምክንያት የመርሳት ችግር በሂደት እየተከሰተ ቋሚ እስከመሆን ይደርሳል። ሁኔታው ጊዜያዊ ከሆነ ደግሞ ከትውስታዎች ጋር የተገናኘውን የአንድን ሰው ከፊል ልምድ ብቻ የመጉዳት አቅም አለው። በሽታው የማስታወስ ችሎታን በማዛባት ትውስታን የሚቆጣጠሩ የአዕምሮ አወቃቀሮችን ያጠፋል። ይኼም ለአጭር ጊዜ የማስታወስ ችግር የሚዳርግ ቢሆንም የረዥም ጊዜ የማስታወስ ችሎታ ግን እንደነበረ ይቆያል።

ድንገተኛ የመርሳት ችግር የሚከሰተው አዕምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በከባድ ሁኔታ ሲጎዳ ብቻ አይደለም። በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የኮሌስትሮል መጠን ከፍተኛ ለሆነባቸው ሕሙማን በተመሳሳይ መልኩ የሚሰጠው ሕክምና የጎንዮሽ ጎዳት በማስከተል ለችግሩ ሊዳርግ ይችላል። ለድንገተኛ የመርሳት ችግር የደም ዝውውር በድንገት መቆም (ስትሮክ)፣ ለረዥም ጊዜና ለዕድሜ ልክ በተደጋጋሚ የሚከሰቱት እንደ ማጅራት ገትር እና ኤፕሌፕሲ (የሚጥል በሽታ)ን የመሳሰሉ በሽታዎች ዋነኛ ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው።

አለመጋለጥሥር የሰደደ የአልኮል መጠጥና

የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት፣ ከባድ አካላዊ ጎዳቶች፣ እርጅና፣ ጫናና ውጥረት፣ ዲሜንሺያ (አዕምሮ ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት አዕምሮ

በብቃት ያለመስራትና በሂደት ማስታወስ ያለመቻል ችግር)፣ የሥነ-ልቦናና የዕንቅልፍ መዛባት፣ መድኃኒቶች፣ የተመጣጠነ ምግብና የቫይታሚን እጥረት፣ ለመርዛማ ነገሮች ለረዥም ጊዜ ተጋላጭ መሆን፣ ኢንፌክሽንና ለረዥም ጊዜ በሽታዎች የሚሰጡ የሕክምና ሁኔታዎች ለችግሩ የሚያጋልጡ መሆናቸው ይገለፃል።

መርሳት እስከምን ድረስ?መረጃዎችን፣ ስሞችን፣

መልዕክቶችንና የነገሮችን ዓላማ እስከመርሳት ያደርሳል። ነገሮችን በቀላሉ መርሳት፣ መኪና መንዳት እና ዳቦ መጋገርን የመሳሰሉ የተለመዱ ተግባራትን ማከናወን አለመቻል፣ ግራ መጋባት፣ በትንሽ በትልቁ መበሰጫጨትና ንቃት እየቀነሰ መምጣት የችግሩ ምልክቶች ናቸው - ከሰው ሰው ቢለያይም። ምልክቶቹም ብዙ ጊዜ በሂደት እየተከሰቱ የሚኼዱ ሲሆን፣ ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉት ሁኔታዎች የምልክቶቹን መጠን እንደሚወስኑ መረጃዎች ያስረዳሉ። በተለይ ደግሞ ችግሩ በትልልቅ ሰዎች ላይ ሥር የሰደደ ከባድ በሽታ ይሆናል። ከምልክቶች መካከል በጣም የሚያስጨንቀው ሰዎች አንድን ነገር ለማድረግ መርሳታቸው አይደለም። አንዳንድ ሕሙማን የነገሮችን ስያሜ የመቀላቀል ችግር አለባቸው። እንዲሁም ነገሮችን በአግባቡ ተረድተው ንግግር ለማድረግ ሲቸገሩ ይታያል። ስለዚህ በችግሩ ሳቢያ ቀላል ውሳኔዎችን ለማድረግ ያልቻሉ ሰዎች የሆነ ነገራቸው በትክክል እያሰራ ባለመሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ምክር በከፍተኛ ሁኔታ ያስፈልጋቸዋል።

ምርመራና ሕክምና በሽታው ላይ የሚታየውን

አንድ ምልክት ብቻ መሰረት

በማድረግ ‹‹ግለሰቡ በመርሳት ችግር እየተሰቃየ ነው›› ብሎ መወሰን ከባድ መሆኑ ይገለፃል። ሁኔታውን ለመመርመር የሕክምና ዶክተሩ/ባለሙያው ስለታማሚው ቅድመ-ሕክምና ታሪክ ጠለቅ ብሎ ሊያውቅ የግድ ነው። ታማሚውም በሂደት የተለያዩ አይነት የኒውሮሳይኮሎጂካል ምርመራዎችን በማድረግ በማስታወስ ተግባሩ ላይ ትኩረቱን ያሰጣል። ሌሎች እንደ ኤሌክትሮኢንሲፋሎግራፊ፣ ኤም.አር.አይ እና ሲቲ ስካንን የመሳሰሉ ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች ለመርሳት ችግር ትክክለኛውን የምርመራ ውጤት ሊሰጡ ይችላሉ። ለአጭር ጊዜ የሚከሰተው ዋነኛ ችግር ከሰከንዶች ጀምሮ ደቂቃዎች ሊያስቆጥር ይችላል።

የችግሩ መንስዔው ወደትክክለኛው ቦታ ካልተመለሰ በስተቀር መርሳት ሊድን እንደማይችል መረጃዎች ያስረዳሉ። በዚህም መሰረት ሕክምናው በችግሩ ዋነኛ ምንጭ ላይ ይበልጥ የተመካ ነው። የመርሳት ችግሩ የከባድ ሕመም ምልክት ከሆነና ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ተለይቶ ከታወቀ ችግሩን ወዲያውኑ መመለስ ይቻል ይሆናል። … ከእርጅና ጋር ተያይዞ የመጣው ችግር የማይድን ቢሆንም፣ የመከላከል እርምጃዎችን በመከታተል በምልክቶቹ ላይ መሻሻልን ማምጣት ይቻላል።

ቀላል የመርሳት ችግሮችን የመድኃኒትነት ጠቀሜታ ያላቸውን እፅዋቶችን በመጠቀምና የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ማከም መፍትሔ ነው። የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ፣ ምቾቱን የጠበቀ በቂ ጥልቅ ዕንቅልፍ ማግኘት፣ ለችግሩ በዋነኝነት የሚያጋልጡ ነገሮችን በማወቅና ከእነሱ በመራቅ የሕመምተኞችን አጠቃላይ የጤና ሁኔታ ማሻሻል

ይቻላል። እንዲሁም ችግሩን ለማከም የቤተሰብ ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ፣ የሕሙማን ቤተሰብ አባላት የታማሚዎቻቸው የጤና ችግር እንዲሻሻል ምን ማድረግ እንደሚኖርባቸው ለማወቅ ከሕክምና ባለሙያዎች ወሳኝ ምክሮችን መቀበል ይገባቸዋል።

ምግብና እንቅስቃሴበጣም የተለመደው ዓይነት

የማስታወስ ችግር በጭንቅላት ላይ በሚደርስ ከባድ ጉዳት የሚመጣ ነው። ለዚህም ሰዎች የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው። ለምሳሌ መኪና በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የደህንነት ቀበቶ እና ሞተር ብስክሌት በሚነዱበት ወቅት ደግሞ ተገቢውን የግጭት መከላከያ የራስ ቆብ (ሄልሜት) ማድረግ ተገቢ

ነው። ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የያዙ

ምግቦችን መመገብና ጫናን መቀነስ የሁኔታዎቹን ምልክቶች ለመከላከል ይረዳሉ። ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ድንገተኛ ለሆነ የደም ዝውውር መቆም ችግር (Stroke) የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለማስታወስ ችግር በቀላሉ ተጋላጭ ናቸው። በመሆኑም ህሙማን የደም ግፊት መጠናቸውን መቆጣጠር ስለሚገባቸው ሲጋራን ከማጨስ በመቆጠብና ተገቢውን አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የአኗኗር ዘይቤያቸውን ማስተካከል ይኖርባቸዋል።

የማስታወስ ችግሮችን የመከላከሉ ሁኔታ የተገደበ መሆኑ ይገለፃል። ድንገተኛ የመርሳት ችግር ከዕድሜ መግፋት ጋር የመጣ ከሆነ የግለሰቡን የአንጎል ሕዋሳት ጤናማነትና ንቃት ለመጠበቅ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግና ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገብ ይመከራል። ይሁንና የተወሰኑ የአመጋገብ ምርጫዎች እና የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ችግሩን ለመቅረፍ በመፍትሄነት ቢቀርቡም፣ እነዚህ ሰዎች ለችግሩ ያላቸውን ተጋላጭነት በምን ያህል መጠን እንደሚቀንሱት በጥናት እስከአሁን ድረስ አልተረጋገጠም፤ በተለይ በዕድሜ ለገፉ ሰዎች።

የተወሰኑ ሳይንቲስቶችም በሰውነት ውስጥ ያለው የውሃ መጠን የተሻለ እንዲሆን ሕሙማን ውሃ አብዝተው እንዲጠጡ ይመክራሉ። ከላይ እንደተገለፀውም በቂ እንቅልፍ አለማግኘትና ጫና በአንጎል ውስጥ የሚገኙ ሕዋሳት ተገቢ ሥራቸውን እንዳይሰሩ ተፅዕኖ ይፈጥርባቸዋል። በመሆኑም ሰዎች ተገቢውን ዕረፍት በመውሰድ ጫናዎችን ማስወገድ አለባቸው።

ይረሳሉ!?እንዲሁም ማሕበራዊ ሕይወት

ችግሩ ላለባቸው ሰዎች ጠቀሜታ አለው። የተወሰኑ ተጨማሪ ምግቦችም ችግሩን ለመቅረፍ ስለሚረዱ በዘርፉ ባለሙያዎች አማካኝነት ለሕሙማን የሚታዘዙ ሲሆን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የአንጎል ሕዋሳት ጤናማነታቸው በጥሩ ሁኔታ ተጠብቆ እንዲቆይ ጥቅም ይሰጣሉ። ከእነዚህም ውስጥ መልቲ ቫይታሚኖች፣ የማዕድን ውህዶች፣ ቦሮን፣ ሌሲቲን (በዕፅዋትና እንስሳት ውስጥ የሚገኝ የሕብረ ሕዋስ ንጥረ ነገር ሲሆን፣ የተለያዩ ክፍል የምግብ ውጤቶች እንዲጣበቁ ይረዳል)፣ ዥንጅብል፣ ቫይታሚን ‹‹ቢ›› ኮምፕሌክስና ‹‹ሲ››፣ ዚንክ፣ መዳብ፣ አሲታይልኮላይን፣ እና ባዮፍላቮኖይድ ተጠቃሽ ናቸው። በቫይታሚን ‹‹ኢ›› የበለፀገ የስንዴ ጀርም በእርጅና ምክንያት የሚከሰተውን የመርሳት ችግር ይፈታል። እንጆሪ፣ ካሮት፣ እንቁላል፣ ኦክራና አፕሪኮት መጠናቸው በዝቶ ከተወሰዱ ደግሞ የማስታወስ ብቃትን ይጨምራሉ። አረንጓዴና የመድሃኒትነት ጠቀሜታ ያለውን ሻይ እና አዝመሪንን መጠቀም ደካማ አዕምሮን ሲያጠነክሩ፣ ቡናና ሻይን መጠጣት ደግሞ የአዕምሮን ተግባር አነቃቅተው ያሻሽላሉ። በተጨማሪም አዕምሮን የሚፈታተኑ እንቆቅልሻዊ ፅሁፎችን ማንበብ፣ ውስብስብ የሆኑ የቃላት ጨዋታዎችን ማከናወን እና ወሳኝ የሆኑ ዕቃዎችን በተደጋጋሚ በተመሳሳይ ቦታዎች ላይ ማስቀመጥ ነገሮችን በቀላሉና በፍጥነት ለማስታወስ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው። በተመስጦ ማሰላሰል (ሜዲቴሽን) እና አዕምሮን ዘና የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጫናን በማስወገድ የመርሳት ችግር ሂደትን ይቀንሳሉ፤ ብሎም ይቀርፋሉ።

በኤልያስ ገብሩ[email protected]

ባለስልጣን ሆኜ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት ስለገፈፍኩ አይደለም። አቶ ስዩም መስፍን ሥራ ፈትቶ አብዱልመጂድ ሑሴንን በማስከተል በአካል ዴንማርክ ድረስ መጥቶ በጽሁፍ ለዴንማርክ መንግስት ክስ ሲያቀርብ ሥርዓቱ በእኔ እጀግ ስጋት ገብቶት ነበር ማለት ነው። ስለዚህ አሁንም በግንቦት-7፣ በአንድነት ፓርቲና በሌሎች ኃይሎች ላይ በተደጋጋሚ ክሶች ሲደረደርና የድርጅቶቹ አባላትና ደጋፊዎች ሲያሳድድ መመልከት ያለብን የድርጅቶቹ ክብደት ብቻ ነው።

አሳዛኙ የወ/ሪት

ብርቱካን ዳግም እስርወ/ት ብርቱካንና ፓርቲዋ

ካገኙት የሕዝብ ተቀባይነትና በሥርዓቱ ላይ በፈጠሩት ስጋት ምክንያት ወ/ሪት ብርቱካን የሥርዓቱ ሰላባ የመሆኗ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከሥርዓቱ በተጨማሪ ደግሞ ተበለጥን ብለው ከሚቆጩ ክፍሎች በኩል አራት ችግሮች ነበሯት። አንደኛ፣ ወ/ሪት ብርቱካን በነ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል አምባገነናዊ አያያዝ በቅንጅቱ ወስጥ ከተለኮሰው የትርምስ እሳት ተፈልቅቃ የወጣች ወርቅ ናት። ስለዚህ በአንድ በኩል ቀደም ሲል በቅንጅቱ ጎልቶ መውጣት አንጀታቸው ያረረ (ከቅንጅቱ ውጪ ያሉ ኃይሎች) በቅንጅቱ መሰባበር የጀመሩት የዳንኪራ መድረክ መጋረጃው ሳይዘጋ

ብርቱካን አንጸባራቂ ኮከብ ሆና ብቅ ማለቷ አበሳጭቷቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የወ/ሪት ብርቱካን ዝነኛ ሆኖ መውጣት ለመኢአድ ሰዎችና ጋሻ ዣግሬዎቻቸው ምን ያህል አስደንጋጭ ዜና እንደሆነ ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችል ግልጽ ጉዳይ ነው።

ሁለተኛ፣ ወ/ሪት ብርቱካን ወደ ሰሜን አሜሪካ የሄደውን የቅንጅት የልዑካን ቡድን መርታ ሜኒሶታ ላይ በተጠራ ሰፊ ስብሰባ ላይ ታሪካዊ ሥራ አከናውናለች። ይኸውም፣ አስተዋይዋ መሪ፣ በቅንጅት ድረ-ገጽ አማካኝነት በትግራይ ሕዝብ ላይ በጅምላ ሲሰነዘሩ የነበሩ አሳፋሪ ስድቦችና ውንጀላዎች በጥብቅ ኮንና በቅንጅቱ ስም ይቅርታ መጠየቋ ነው። ይህ እርምጃዋ በትግራይ ተወላጆች ዘንድ ተጨማሪ ከበሬታ ሲያጎናጽፋት፣ በአንጻሩ ደግሞ በጥላቻ የታወሩ የጭፍን ፖለቲካ አራማጆች ጥርስ ውስጥ አስገብቷታል።

ሦስተኛ፤ ባለፉት ዘመናት በቅርብ የታዘብኩት አሳዛኝ ነገር ትግሉን እንደ ማንኛውም ተራ ንግድ የመጠቀሚያ ቋሚ ሥራ አድርገው የሚጠቀሙበት ብዙ ስደተኞች መኖራቸውን ነው። እነዚህ የፖለቲካ ነጋዴዎች ለ30 እና 40 ዓመታት ያህል ያካበቱት ልምድ ስላላቸው ተፎካካሪዎቻቸውን ከገበያ ለማስወጣት ያላቸው የአፍራሽነት ብቃት የሚናቅ አይደለም። ንግድ ደግሞ ውድድርና ፉክክርን ስለሚጠይቅ የራስን ደንበኞች ላለማስነጠቅና የሌላውን ደንበኛ ለመንጠቅ በሚደረግ

ትርምስ የተጨማለቀ ነው። የወ/ሪት ብርቱካን ተክለሰውነትና ማንነት ለዚህ የተጨማለቀ የገበያ ውድድር ጠንቅና አስጊ ነው። ይህንን ለመገንዘብ የሚያስችሉን አንዳንድ አብነቶች ልጥቀስ።

ብርቱኳን ሴት ናት። እንደ ብርቱካን ያለች ታታሪ የሴት መሪ ገናና ሆኖ መውጣት ከቁጥራቸው ብዛት አንጻር ይህ ነው የሚባል ተሳትፎ የማይታይባቸው የኢትዮጵያ ሴቶች በወንዶች ሞኖፖሊ የተጨናነቀውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ሚዛን መለወጡ አይቀሬ ነው። ይህ ቁልፍ የሆነ ጉዳይ ፖለቲካን እንደ ንግድና መተዳደሪያ አድርገው በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ነባርና አዳዲስ ደንበኞችን በመንጠቅ ረገድ ጉዳቱ ቀላል አይደለም። ብርቱካን ወጣት ናት። ይህ ደግሞ በጣም አሳሳቢ ጎኗ ነው። ወጣቱ ትኩስ ትውልድም ምን ዓይነት ተዓምር እንደሚሰራ ትንተና አያስፈልገውም። አስቀጣይ መሪና አስተባባሪ በማጣቱ ሜዳ ላይ ቀረ እንጂ በ1997 ምርጫ ሂደትና በዋዜማው የተደረገው ታላቁ ሰልፍ የወጣቶቻችን ማንነት በሚገባ ያስመሰከረ አስገራሚ ክንዋኔ ነው። ወ/ሪት ብርቱኳን የሰላም ትግሉን ስለመረጠች ደግሞ በአገር ቤት ያለው ወጣት ከጎኗ እንደሚሰለፍ የሚያጠራጥር አይደለም። የወጣቱ ትውልድ ጎራ ደግሞ ሁለቱንም ጾታ ስለሚያካትት የኔ ቢጤ አዛውንቶች ለሚያንቀሳቅሷቸው ድርጅቶች በጥራትም ሆነ በብዛት ወሳኝ የሆነን ደንበኛ የሚያስነጥቅ ነው።

አራተኛ፣ ብርቱካን የኦሮሞ

ሕዝብ ልጅ ናት። የብርቱካን ኦሮሞነት ደግሞ በሁሉም መስፈርቶች ሰፊ የሆነውን የኦሮሞ ሕዝባችንን የመማረክ ኃይል ስላለው በሁለት ጎራ በኩል ያሉ ተቃዋሚ ኃይሎችን ያስደነብራል። በአንድ በኩል የህብረ-ብሔር ድርጅቶች ነን በሚሉትና በተጨባጭ ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ ቦታ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ በከፍተኛ አመራር የማያሳትፉትን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅቶች በሆኑት ዘንድ ደጋፊ የመንጠቅ ኃይል አለው ማለት ነው።

እንግዲህ ወ/ሪት ብርቱካን እነዚህን “ዕዳዎች” ተሸክማ ነው በአንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ ስቶክሆልም፣ ስዊድን የተጓዘችው። ለወ/ሪት ብርቱካን ዳግም እስር ሰበብ የሆነው ምክንያትም የሚመነጨው በስቶክሆልም ከተካሄደው ስብሰባ ይጀምራል። በዚያ ስብሰባ አንድ የስብሰባው ታዳሚ ለወ/ት ብርቱኳን ባቀረበው ጥያቄ ላይ ተመርኩዛ ወ/ሪት ብርቱካን ሰጠች የተባለው መልስ ነበር ለችግሩ መንስኤ የሆነው።

ለወ/ሪት ብርቱካን የቀረበላት ጥያቄ “ወንጀለኛ ነኝ ብለሽ ፈርመሽ ነው ከወህኒ ቤት የወጣሽው” የሚል የትንኮሳ ይዘት ያካተተ ‹‹ጥያቄ›› ነበር። እንግዲህ ጠያቂውን መልሰን መጠየቅ ያለብን፣ ይህንን ትንኮሳ ለመሰንዘር ለምን አስፈለገህ? ብለን መሆን አለበት። ወ/ሪት ብርቱካንም ሆነች ሌሎች ሰዎች የታሰሩበትና የተፈቱበት ሆኔታ እንኳንስ ዘመናዊ የመገናኛ መስመሮች በተትረፈረፈባት ስዊድን ለሚኖር ሰው ቀርቶ ይህን ዕድል ለሌላቸው ሰዎችም የተደበቀ ምስጢር አይደለም። ስለዚህ የወ/ሪት ብርቱኳን ለዳግም እስር መዳረግ ምክንያት ለመመርመር ከተፈለገ ዋናው ፍተሻ መጀመር ያለበት፣ ቀደም ሲል ያስቀመጥኳቸውን አራት ጉዳዩች ግምት ውስጥ በማስገባት ጭምር፣ የዚያን ጠያቂ ሰው ማንነት

መንጥሮ በማውጣት መሆን አለበት። ጠያቂው የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ አለመሆኑን የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች ስላሉ፣ ከዚያ በመለስ ሰውየው የየትኛው ጎራ አባል ወይም መልዕክተኛ እንደሆነ ተለይቶ ሲታወቅ የትንኮሳው መንስኤና ግብ ለመረዳት አያስቸግርም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ ወ/ሪት ብርቱካን ለዳግም እስር የተዳረገችው ግን ሆን ተብሎ በተንኮል በተሸረበ ወጥመድ ምክንያት እንደሆነ አጠያያቂ መስሎ አይታየኝም። ወ/ሪት ብርቱካን ከዳግም እስር የተለቀቀችበት ሁኔታ ቀደም ሲል ሁሉም የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞቻችን ከተፈቱበት ሆኔታ የተለየ አይደለም። በመሰረቱ የታሰረችው ወ/ሪት ብርቱካን ሳትሆን ሥርዓቱ ነበር ማለት ይቻላል። ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ቀደም ሲል ታስረው የነበሩትም ሆኑ በድጋሚ ወደ ወህኒ የተወረወረችው ወ/ት ብርቱካን ወንጀል ሰርተው ሳይሆን ሥርዓቱ ካለበት የመንፈስ ጭንቀት የተነሳ እነሱን በማሰር ሌሎች ታጋዮችን ለማስበርገግና መቀጣጫ ለማድረግ ነበር። ሥርዓቱ ሰዎቹን ለረጅም ጊዜ አስሮ ማስቀመጥ ደግሞ ከተለያዩ ወገኖች በተለይ ከለጋሽ መንግስታት ነጋ ጠባ ጥያቄ እያስነሳ ስለሚረብሸው ለሽማግሌዎቹ ምስጋና ይግባቸውና ሥርዓቱ እነሱን ተጠቅሞ እስረኞቹን መልቀቁ የግድ ነበር።

እዚህ ላይ ማስታወስ የምፈልገው ነገር አለ። ይኸውም፣ አንዳንድ ወገኖች በሽማግሌዎቹ ላይ ያላቸው ቅሬታ ትክክል ያለመሆኑ ነው። ሽማግሌዎቹ ከዚያ በላይ ሊያደርጉት የሚችሉት ምንም ነገር አልነበረም፤ አሁንም የለም። ሌላ ማድረግ የሚችሉት ነገር ቢኖር ምንም ያለማድረግ ብቻ ነው የሚሆነው። ምንም ያለማድረግ ደግሞ በድንጋጤ የተወጠረው ሥርዓት ወገኖቻችንን በእስር እያማቀቀ እንዲቀጥል

የብርቱካን የመኸር...

የማስታወስ ችግሮችን የመከላከሉ ሁኔታ የተገደበ መሆኑ ይገለፃል። ድንገተኛ

የመርሳት ችግር ከዕድሜ መግፋት ጋር የመጣ

ከሆነ የግለሰቡን የአንጎል ሕዋሳት ጤናማነትና

ንቃት ለመጠበቅ የተለያዩ የአካል ብቃት

እንቅስቃሴዎችን ማድረግና ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገብ

ይመከራል።

Page 20: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

21

መ/ቤቱ ኦዲት ባከናወነባቸው የመንግስት መ/ቤቶች የሒሳብ አያያዝ ግድፈቶች

እና የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች፣ እንዲሁም አፈፃፀማቸው ከደንብና መመሪያ ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች እንዳጋጠሙት ሪፖርት ያቀረበው የኢፌዴሪ ፓርላማ ባከናወነው 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን፣ ‹‹የምክር ቤቱን ትኩረት ሊያገኙ ይገባል›› ብሎ ያመነባቸውን አንኳር አንኳር ግኝቶች ዘርዝሯል።

በኦዲት ሪፖርቱ መሠረት የዕቃ ግዥ እና ንብረት አስተዳደርን በተመለከተ ከፍተኛ ችግር ከተስተዋለባቸው መ/ቤቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን አንዱ ነው፡፡ ለኃይል ማመንጫነት ከሚውሉ ጀነሬተሮች ውስጥ በኦዲተሮች በናሙና ተመርጠው ከታዩት ሶስት የኃይል ማመንጫ ጀነሬተሮች፤ ቃሊቲ የሚገኘው የዲዝል ኃይል ማመንጫ 14.0 ሜጋዋት ማመንጨት ሲገባው የሚያመነጨው 3.5 ሜጋ ዋት ብቻ መሆኑ፣ አዋሽ 7 ኪሎ የሚገኘው 35 ሜጋ ዋት ማመንጨት ሲገባው በ21 ሜጋ ዋት መወሰኑና 38 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የድሬ ዳዋው ጀነሬተር ያለአገልግሎት መቀመጡ ተገልጸDል፡፡

እንዲሁም ያለውን የኃይል እጥረት እንዲያቃልሉ በሚል ምክንያት ኮርፖሬሽኑ 60 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ ጀነሬተሮች ተከራይቶ ለኪራይ 10 ሚሊዮን 368 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ አድርጓል። ነገር ግን ኮርፖሬሽኑ የራሱ ንብረት የሆኑትን ጀነሬተሮች በሙሉ አቅማቸው ቢጠቀምባቸው ኖሮ 62 ሜጋዋት ማመንጨት ይችሉ እንደነበርና ለኪራይ የወጣውን የውጪ ምንዛሪ ሊያስቀር ይቻል እንደነበር ሪፖርቱ አመልክቷል።

‹‹ኮርፖሬሽኑ የግዥ

ሥርዓቱንና ንብረት አስተዳደሩን ዘመናዊ በማድረግ ውጤታማ ሥራ ሊያከናውን ይገባል›› የሚለው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት የኢ.ኤ.ኃ.ኮ ሌሎች ድክመቶችን ዘርዝሯል።

ከድክመቶቹ ውስጥም፡- - የኮርፖሬሽኑ ቋሚ

ንብረቶች አስፈላጊው የመድኅን ዋስትና ሽፋን በተሟላ ሁኔታ የተገባላቸው አለመሆኑ እና የመድኅን ዋስትና የተገባላቸውም የንብረቶችን ዋጋ ያላገናዘበ ወይንም በጥናት ያልተደገፈ መሆኑ፣

- በጎፋ፣ በድሬ ዳዋ፣ በሻሸመኔና በሐዋሳ በሚገኙ ዕቃ ግምጃ ቤቶች በመጋዘን ውስጥ ሊቀመጡ የማይችሉ ንብረቶች ለፀሐይና ለዝናብ ተጋልጠው እና በግቢው ውስጥ ቢጠፉ እንኳን በማይታወቅበት ሁኔታ ተዝረክርከው ሳር በቅሎባቸውና አቧራ ለብሰው ተቀምጠው መገኘታቸው፣ እንዲሁም

- በናሙና ተመርጠው ከታዩ 14 ግዥዎች ውስጥ በሁሉም ግዥው ከመፈፀሙ በፊት የዕቃዎቹን ጥራት ለማረጋገጥ ለሙከራ ምስክርነት ወደተለያዩ አገራት የሚሄዱ ሠራተኞች ዕቃዎቹ ተገዝተው ንብረት ክፍል ገቢ በሚሆኑበት ወቅት በታየው ስታንዳርድ መሠረት ገቢ መሆናቸውን አለማረጋገጣቸው ዋንኞቹ ናቸው።

የኦዲት ሪፖርቱ ካካተታቸው የገቢ አሰባሰብና የአሰራር ድክመቶች ውስጥ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሕገ-ወጥ መንገድ ሒሳብ ሲሰበስብ መቆየቱ የም/ቤቱን አባላት ትኩረት የሳበ ነበር። በሪፖርቱ መሠረት፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሠረት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርን ሳያሳውቅና ፈቃድ ሳያገኝ ብዛቱ አምስት ሺህ የሚሆን ጥራዝ የውስጥ ገቢ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ አሳትሞ ሲጠቀም ተገኝቷል።

ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት በፍሪላንስ ዜና አንባቢነትና ዘጋቢነት በኮንትራት ቅጥር ከሚያሰራቸው ሠራተኞች

የሚቀንሰው የሥራ ግብር በኮንትራት ውሉ መሠረት ድርጅቱ በሚከፍላቸው ደመወዝ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ በሕጉ መሠረት ሊሰበሰብ የሚገባው የሥራ ግብር አልተሰበሰበም።

የገቢ ሰብሳቢ ጽ/ቤቶች በአዋጅ በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት የመንግስትን ገቢ በአግባቡ መሰብሰባቸውንና ተገቢ የሆኑ የቁጥጥር ሥርዓት የዘረጉ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ ድክመት ከተገኘባቸው መ/ቤቶች ውስጥ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ይገኝበታል።

በባለስልጣኑ ሥር ባሉ ሦስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በሌሎች ሶስት መ/ቤቶች በድምሩ 58 ነጥብ 64 ሚሊዮን ብር የገቢ ደረሰኝ እና የግብር ማሳወቂያ በፋይሉ ውስጥ ተያይዞ ባለመገኘቱ ምክንያት ገቢው ከማን እንደተሰበሰበ ሳይገለፅ በኮድ በመሰብሰቡ ገቢው መሰብሰብ በሚገባው ልክ መሆኑን ለማረጋገጥ አልተቻለም።

ከጉምሩክ ሌላ ስማቸው ያልተዘረዘረ ዘጠኝ የመንግስት መ/ቤቶች ከውስጥ ገቢ የሰበሰቡት ብር 543 ነጥብ 29 ሚሊዮን፣ መ/ቤቶቹ ባቀረቡት ዓመታዊ የገቢ ሒሳብ ሪፖርት ውስጥ ሳይካተት ተገኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስር ባሉ ስድስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በድምሩ 285 ነጥብ 38 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ያልተሰበሰበ ውዝፍ ገቢ መገኘቱ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ኤ ች . አ ይ . ቪ / ኤ ድ ስ ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተመደበውን ሀብት አጠቃቀምን በተመለከተም የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት መልካም ክንዋኔ አለመኖሩን ነው የሚያሳየው። የሀገር አቀፉን የማስተባበሪያ ዘዴ ቢሮ ፈቃድ ሳያገኝ በአጠቃላይ 201 ሚሊዮን 449 ሺህ 630 የኢትዮጵያ ብር እና አንድ ሚሊዮን 623 ሺህ 466 የአሜሪካ ዶላር በተለያዩ መ/ቤቶችና በክልል ጽ/ቤቶች ከተፈቀደለት ተግባር ውጭ ወደሌላ እንዲተላለፍ ተደርጓል።

የተለያዩ የመንግስት

ሴክተሮችና አስፈፃሚ አካላት ለፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተግባራት የተላከላቸውን ገንዘብ በወቅቱ እንማይጠቀሙ፣ ተገቢውን ክትትል እንደማያደርጉና የማወራረጃ ጊዜ ገደብ ሲቃረብ ብቻ በመሯሯጥ ገንዘብ ለመጠቀም ጥረት ስለሚያደርጉ አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ መሆኑ ሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።

ደንብና መመሪያን ሳይከተሉ የተፈፀሙ ግዢዎችና ያለአግባብ የተፈፀሙ ክፍያዎችም በሪፖርቱ ውስጥ ተካተዋል። የዕቃና አገልግሎት ግዢ በመንግስት ደንብና መመሪያ መሠረት የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በ32 መ/ቤቶች 83 ነጥብ 34 ሚሊዮን ብር የመንግስትን የግዢ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዢ ተፈፅሞ ተገኝቷል። እንዲሁም ኦዲት በተደረጉት መ/ቤቶች ደንብና መመሪያ ተጠብቆ ክፍያ መፈፀሙ ሲጣራ በ22 መ/ቤቶች 584 ነጥብ 61 ሚሊዮን ብር ከደንብና መመሪያ ውጭ የተከፈለ ሲሆን፣ የትምህርት ሚኒስቴር 13 ዩኒቨርሲቲዎችን ለማስገንባት በተገባው ውልና በተፈፀመው ክፍያ መካከል 441 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ከውሉ በላይ በመፈፀም በመጀመሪያው ተርታ ላይ ይገኛል።

በሌላ በኩል ይኸው ሚኒስቴር መ/ቤት ዝርዝር ሥራ በሚያሳይ ማስረጃ ሳይደገፍ በቀረበለት የክፍያ ጥያቄ ብቻ ለጂ.ቲ.ዜድ 1 ነጥብ 42 ቢሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል። ሌሎች ሚኒስቴር መ/ቤቶችም በርካታ ሚሊዮን ብሮችን በስምምነት ከተቀመጠው ዋጋ በማስበለጥ ክፍያ ፈጽመዋል፡፡

በ39 ገጾች የተጠናቀረው የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2002 በጀት ዓመት ሪፖርት 20 የመንግስት ተቋማት በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ ይዘው መገኘታቸውን ያሳያል። መ/ቤቶቹ በአጠቃላይ ያለባቸው ተከፋይ ሒሳብ 247 ነጥብ 20 ሚሊዮን ብር ሲሆን ከእነሱም ውስጥ፤ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 117 ነጥብ 31 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሒሳብ በማሳየት

ቀዳሚው ነው። ዋና ኦዲተሩ ባከናወነው

ኦዲት ካገኛቸው የሒሳብ አያያዝ ግድፈቶች እና የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች ውስጥ አብዛኞቹን በማስመዝገብ ቀዳሚ የሆነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር፣ በከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ዙሪያ በአዋጁ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ አለመሆኑ ተገልጿል።

ከትምህርት ሚኒስቴር በተጨማሪ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንም የወጪ መጋራት ክፍያን እየፈፀሙ ያሉ ተጠቃሚዎችን፣ የአሰሪ ድርጅቶች እንዲሁም የተመራቂዎችን ዝርዝር መረጃ በተሟላ ሁኔታ ባለመያዙ ተተችቷል።

የመ/ቤታቸውን ሪፖርት ለፓርላማው በንባብ ያቀረቡት ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ፣ ሪፖርታቸውን ሲያጠናቅቁ በኦዲት ሂደት የተገኙት ዋና ዋና ግድፈቶች በአፋጣኝ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አፅንኦት የሰጡ ሲሆን፣ ‹‹በተለይ እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ እርምጃ ሳይወሰድባቸው ከዓመት ወደ ዓመት የሚተላለፉ የሰነድ ሒሳቦችና ደንብና መመሪያን ሳይጠብቁ የሚፈፀሙ ግዥዎች ልዩ ትኩረት አግኝተውና መርኃ-ግብር ወጥቶላቸው እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው›› ብለዋል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተርን የሚቆጣጠረው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ በሪፖርቱ ላይ ያላቸውን አስተያየት ለአውራምባ ታይምስ አካፍለዋል። ‹‹ሪፖርቱ በአጠቃላይ ሲታይ ጥሩ ነው›› ያሉት አቶ ግርማ የሪፖርቱን ደካማ ጎኖች ዘርዝረዋል።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁሉም ፌዴራል መ/ቤቶች እና ለክልሎች ተፈቅዶ የነበረው በጀት አጠቃቀም ላይ የተደረገው ኦዲት

በሪፖርቱ ውስጥ አለመካተቱና ሪፖርቱ ከቀረበበት ጊዜ አኳያ ለቀጣዩ ዓመት በጀት እንደ ግብዓት ሊያገለግል አለመቻሉ በአቶ ግርማ የተጠቀሱ ዋና ዋና ድክመቶች ናቸው።

የአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍልም በእነዚህ ድክመት ተብለው በተጠቀሱት ነጥቦች ዙሪያ ለዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ አቶ ገመቹም የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አጠቃላይ የሀገሪቱን በጀት አጠቃቀም የኦዲት ውጤት በሪፖርቱ ውስጥ ያልተካተተው ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር የመውጫ ስብሰባ ባለመደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‹‹የመውጫ ስብሰባ ለምን አልተደረገም?›› ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ስብሰባው ከመካሄዱ በፊት በኦዲተሮች ‹‹ግኝት›› ተብለው የተለዩ ጉዳዮች ላይ በቂ ማብራሪያ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እንዲያቀርብ ዕድል መስጠት ስላስፈለገ መሆኑን በመግለፅ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሥራው እንደሚጠናቀቅ አስረድተዋል።

ከሪፖርቱ መዘግየት ጋር የተነሳውን ጥያቄ ‹‹እኛ ሪፖርት የምናቀርበው ም/ቤቱ በሚያወጣው መርኃ-ግብር መሠረት ነው። ቀደም ብለው ቢጠይቁ ኖሮ ሚያዚያ ላይም ማቅረብ እንችል ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ሪፖርቱ ለቀጣዩ ዓመት በጀት ግብዓት መሆንም ይችላል፤ ምክንያቱም በጀቱ ገና ስላልፀደቀ›› በሚል መልሰውታል።

በኦዲት ሪፖርቱ ላይ የተገለፀው የፌደራል መ/ቤቶች የገንዘብ ብክነት እጅግ ከፍተኛ እና የአገሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ እንደሚጎዳ ያስገነዘቡት አቶ ግርማ ሰይፉ ‹‹እንዲህ ዓይነት የሒሳብ ጉድለቶች የተመዘገቡት በሌሎች አገራት ቢሆን ኖሮ ሚኒስትሮቹ ከቦታቸው ይነሱ ነበር›› ያሉ ሲሆን መ/ቤቶቹን የሚቆጣጠሩ የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከማድረግ ውጪ ሌላ ፋይዳ የለውም። ስለሆነም ሽማግሌዎቹ ያደረጉት ማድረግ የሚችሉትን ብቻ መሆኑን ተረድተን ልናመሰግናቸውና ልናከብራቸው ይገባል። በዚህ ረገድ በህይወት ያሉትም ሆኑ በሞት የተለዩን ሁሉም ያገር ሽማግሌዎቻችን እጅግ የሚመሰገኑ ሲሆኑ ታላላቆቹ ዜጎቻችን ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የአንበሳውን ድርሻ ይሰጣቸዋል። ወ/ሪት ብርቱካን አቶ መለስ ዜናዊ በእጁ ያረቀቀውን አስቂኝ ሃተታ ፈርማ መውጣቷም በእጅጉ አስደስቶኛል። ሥርዓቱ ወ/ሪት ብርቱካንን በማሰቃየቱ ትርፍ አግኝቸበታለሁ ብሎ የሚያምን ከሆነ ግን በጣም ተሳስቷል ባይ ነኝ። ሥርዓቱ እሷን በማሰቃየቱ አንዲት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ሴት በአገሯ ካገኘችው እውቅና በተጨማሪ በዓለም ህብረተሰብና መንግስታት ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታና ተደማጭነት እንድትጎናጸፍ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህንን ታላቅ ግኝት ፓርቲዋና የዚህ ሥርዓት ተቃዋሚ ነን የምንል ዜጎች እንዴት እንደምንጠቀምበት የሁላችንም የቤት ሥራ ይሆናል።

“ወ/ሪት ብርቱካን አሁን ስለያዘችው ግልጽ ያልሆነ አቋም” በሚል የሚሰነዘር ሀሳብ እኔ አልስማማበትም። በኔ እምነት ወ/ሪት ብርቱካን ከዳግም እስር ወጥታ እስካሁን ድረስ የተከተለችው መንገድ ትክክለኛ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚም ነው። በፓርቲዋ ውስጥ የተከሰተው አላስፈላጊ ትርምስና በመታሰሯ ምክንያት በራሷ፣ በሕፃን ልጇና በእድሜ የገፉ ወላጅ እናቷ ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ስቃይ ግምት ውስጥ በማስገባት በአሁኑ ወቅት ከወ/ሪት ብርቱካን የምንጠብቀው ነገር ቢኖር ዲስኩርና ስብሰባ ሳይሆን ጤንነቷን በመጠበቅና መንፈሷን በማረጋጋት ሰውነቷን በሚገባ ማጠናከርና መገንባት ያለባት

መሆኑን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ የሷ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ዕዳ ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ወ/ሪት ብርቱካን ከፖለቲካው ዓለም ትሰወራለች ብሎ የሚያስብ ካለ ግን የሴትየዋን ማንነት በሚገባ ያላወቀና የወጣቱ ትውልድ ንቃተ-ህሊና ጊዜ ካለፈባቸው ከኔ ቢጤዎቹ አዛውንቶች በላይ መጥቆ የሄደ መሆኑን ያልተገነዘበ ሰው ብቻ መሆን አለበት።

በኢትዮጵያ አንዲት መልካም ፍሬ የምታፈራ የምታምር ድንቅ ዛፍ ተተክላ በጥሩ ሁኔታ በቅላለች። ብዙ ውሽንፍርና ውርጭ ተቋቁማ ፍክት ብላ አብባለች። ያበበ ነገር በሚገባ እንዲያፈራ ደግሞ ተስማሚ አየር የግድ ይላል። ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጥሮ መልካም ወይም መጥፎ አየር የሚኖረው ደግሞ በዋናነት ከቀይ ባህርና ከሜዲተራኒያን ባህር በኩል በሚነፍስ ጥሩ አየር ላይ የተመሰረተ ነው። በአሁኑ ጊዜ ከዚያ በኩል የሚነፍሰው አየር ለሰውና ለአዝርእት እጅግ ተስማሚ ነው። ይህ ለወ/ሪት ብርቱካን የጥሩ አየር ጥሩ ዜና እንደሆነ መጠርጠር አይቻልም። ይህ ጊዜ የመኸር ጊዜ ነው። እናም በፍሬው ለቀማ ላይ ወ/ሪት ብርቱኳን ቅርጫቷን ይዛ ብቅ አትልም ብሎ መጠርጠር የማይታሰብ ነው። እልፍ አእላፍ ዜጎቿም ቅርጫቶቻቸውን አንግበው አብረዋት በምርት አሰባሰቡ ሥራ ላይ ሊረባረቡ ከጎኗ ቆመዋል፤ ቆመናል!

የብርቱካን

የእስር ቤት አያያዝወ/ሪት ብርቱካን በእስር

በነበረችበት ጊዜ የነበረው አሰቃቂ አያያዝ በተለያየ መንገድ ተከታትየዋለሁ። እናም አስቀያሚ መሆኑ አያጠያይቅም። በጨለማ ቤት ለብቻዋ ዘግቶ ከማሰቃየት ጀምሮ ሰው እንዳይጠይቃት እስከመከልከል የደረሰ የሰብዓዊ መብት ገፈፋ ተፈጽሞባታል። በእርግጠኝነት

መናገር የሚቻለው ሥርዓቱ ወ/ሪት ብርቱካንን እንደገና ለማሰርና ለማሰቃየት የፈለገበት በሁለት ምክንያት ነው። አንዱ ምክንያት ሥርዓቱ ካደረበት ድንጋጤ የተነሳ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በሷ መንገላታት መልዕክት ለማስተላለፍ ስለተፈለገ ነው። የድንጋጤው መሰረት ቅንጅት ተፈረካክሶ አብቅቶለታል በሚል ትንሽ እፎይታ አግኝቶ የነበረው ሥርዓት በቅንጅቱ አንጸባራቂ ኮከብ ከነበሩ ብዙ ሰዎች መካከል ገሚሶቹ የግንቦት-7 ንቅናቄ፣ ሌሎቹ ደግሞ የአንድነት ፓርቲ መስርተው ቀዝቅዞ የነበረውን የትግል መንፈስ እንደገና ነፍስ ዘርቶ እንዲያንሰራራ በማድረጋቸው ነው።

የወ/ሪት ብርቱካንን በተለየ ሁኔታ አስደንጋጭ የሚያደርገው መሪዋ ወጣትና የተማረች ሴት እንደመሆኗ መጠን በሁለቱም ጾታዎች ተከታይ የማፍራት አቅሟ ከፍተኛ ከመሆኑ ሌላ፣ በሴትነቷ ለትግሉ እጅግ ወሳኝ የሆነውና በአሁኑ ጊዜ በሚገባ ጥቅም ላይ ያልዋለውን የሴቶች ተሳትፎ በመማረክና በማጎልበት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራት ሥርዓቱ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው። በትግል ሂደት የሴቶች ተሳትፎ ያለው ብልጫና ጠቀሜታ ደግሞ በኢትዮጵያ መሬት ከሥርዓቱ መሪዎች የበለጠ ተሞክሮ ያለው ኃይል ያለ አይመስለኝም።

ይህ የሥርዓቱን ድንጋጤ መሰረት በተመለከተ ነው። ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት በተመለከተ ደግሞ፣ ማንም ሰው ከነዚህ ሁለት ኃይሎች ጋር የሆነ ንኪኪ ከተገኘበት የሚከተለው እንግልት ከባድ እንደሚሆን ለማሳየት ተብሎ ነው። ከዚህ የተነሳ ሥርዓቱ ያለበትን ድንጋጤ ለማስታገስ በሁለቱም ኃይሎች ላይ አሳፋሪ እርምጃ ወስዷል። በአንድ በኩል እጃቸውን ለመያዝ ያልቻላቸውን የግንቦት-7 ንቅናቄ መሪዎች፣ ሰዎቹ

በሌሉበት የሞት ቅጣት በማስወሰን የማስጠንቀቂያውን መልዕክት ለማስተላለፍ ተሞክሯል። በሌላ በኩል ደግሞ በቀላሉ ሊያጠምዳት የቻለውን እርግብ እጇን ጠፍሮ ወደ እስር ቤት ወርውሮ በማንገላታት የሚፈልገውን መልእክት ለማስተላፍ ተፍጨርጭሯል። ይህ በጭንቀት አዘቅት የተዘፈቀውን ሥርዓት ተግባር የታቀደለትን ያህል በፖለቲካው ትግል ተጽእኖ አሳድሯል ብዬ አላምንም።

በአጠቃላይ ሥርዓቱ በተቃዋሚው ላይ የራሱን ተጽእኖ የመፍጠር የሞራል ብቃት የለውም። በኔ እምነት በኢትዮጵያ ከታዩ ሥርዓቶች ውስጥ ይህንን ሥርዓት በቀላሉ ማሸነፍ ይቻላል። መቶ በመቶ አስረግጬና በድፍረት ለመናገር የምችለው ነገር ቢኖር የኢህአዴግ ብቃትና አቅም የተመሰረተው በራሱ በሥርዓቱ ውስጥ ባለ ምክንያት ሳይሆን በተቃዋሚዎቹ ድክመት፣ ክፋትና ሕብረት ማጣት ብቻ መሆኑን ነው። በትክክል ሊሰመርበትና ሕዝቡም፣ በተለይ የጉዳዩ ዋና ባለቤት የሆነው ወጣቱ ትውልድ፣ በሚገባ ሊረዳውና ተጽእኖ ሊያደርግበት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ይህ የተቃዋሚዎች ትርምስ መቆም ያለበት መሆኑን ነው።

የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎበዚህ አጋጣሚ ስለ አገራችን

ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ጥቂት ነገር መናገር እሻለሁ። የኢትዮጵያ ሴቶች በኢትዮጵያ ህልውና ላይ በሁሉም መስክ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም ትግሉ በተጠናቀቀ ማግስት ተመልሰው ወደ ማጀት እየተወረወሩ የወንዶች አገልጋይና ባሪያ ከመሆን አልተገላገሉም። ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ተፈጥሮ የጫነችባቸውን ዕዳ ተቋቁመው በጠመንጃ ጭምር ጠላትን የመከቱ እናቶቻችን ድል ከተገኘ በኋላ ድሉ

በወንዶች ብቻ የተገኘ ይመስል ሴቶቹ ተረስተው በለመዱት የሰቆቃ ህይወት መቀጠላቸው የትናንት ትውስታችን ነው።

በተመሳሳይ መንገድ ከህወሓት ጋር ተሰልፈው በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ጀግንነት የፈጸሙ ታጋይ ሴቶች (የታገሉለት ዓላማ ውሃ በልቶት መቅረቱ ቢያሳዝንም) ዛሬ የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እናውቀዋለን። በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ ውስጥ ስንት ሴቶች አሉ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ምንም የሚል ሆኖ እናገኘዋለን። ወ/ሮ አዜብ መስፍን የአቶ መለስ ባለቤት በመሆናቸው ብቻ ካልሆነ የተለየ ጀግንነት ኖሯቸው እንደመጠቁ የህወሓት ታጋይ ሴቶች ራሳቸው በሚገባ የሚያውቁት ግልጽ ነገር ስለሆነ ልዩ ትችት አያስፈልገውም። ይህ እጅግ የሚያስቆጭና በቀጣዩም የኢትዮጵያ ሴቶችን ተሳትፎ የሚያቀጭጭ ክስተት ነው።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ችግሩ በወንዶች ስግብግብነት ብቻ የተከሰተ ሳይሆን ራሳቸው ሴቶቹም ቢሆኑ የችግሩ አካል ስለሆኑ ነው። ለሴቶች መብትና ክብር መጠበቅ በመጀመሪያ መታገል ያለባቸው ራሳቸው ሴቶች መሆን አለባቸው። እዚህ እኔ ከምኖርበት አገር ያሉ ሴቶች የደረሱበት ደረጃ ስመለከት እጅግ እቀናለሁ። ያገሬ ሴቶች ወገኖቼ የሚገኙበትን ሁኔታ እያስታወስኩም እተክዛለሁ። የዴንማርክ ሴቶች ያሉበትን ደረጃ ለማመልከት የዚህ አገር ወንዶች የሚናገሩት ቀልድ መሰል ቁምነገር አለ። ወንዶቹ ሲቀልዱ፣ “ዴንማርክ፣ በመጀመሪያ ለሕፃናት/ለልጆች፣ ከዚያ ቀጥሎ ለሴቶች፣ ቀጥሎ ለሽማግሌዎች፣ ቀጥሎ ለውሾች፣ ከውሾች ቀጥሎ ደግሞ ለወንዶች የተፈጠረ አገር ነው” ሲሉ ይተርካሉ። እዚህ አገር ለልጆችና ለሴቶች የሚሰጠው ክብርና እንክብካቤ ግን እንዲሁ በምጽዋት

የተሰጠ ሳይሆን ሴቶች ሽንጣቸውን ገትረው ታግለው ያገኙትና ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበት ለመሆኑ የገድላቸው ታሪክ ይመሰክራል።

ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን ሴቶቻችን ለመብታቸው መከበር ከሁሉ በላይ ራሳቸው መታገል አለባቸው። በተለይ የተማሩት ሴቶች እናቶቻቸው፣ እህቶቻቸውና ልጆቻቸው በስስታም ወንዶችና ሥርዓቶች ሲሰቃዩ እያዩ እጅና እግራቸውን አጣጥፈው መቀመጥ አይገባቸውም። እነሱ ራሳቸው በትግሉ ተሳትፈው መብታቸውን ካላስከበሩ ደግሞ ማንም ሰው፣ በተለይ ወንዶቹ እንዲያስከብሩላቸው መጠበቅ የዋህነት ነው። ሴቶች ድግስ አሳማሪዎችና ቡና አቅራቢዎች መሆናቸው ማብቃት ካለበት ከዚች ደቂቃ ጀምሮ ከራስ ጋር መታገል ይጠበቅባቸዋል።

ስለዚህ፣ ሴቶች የወ/ሪት ብርቱካንና የመሰሎቿን ፈለግ ተከትለው ራሳቸውን ነፃ ከማውጣት ባሻገር ለሕዝባቸው መብት መከበር የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ የማበርከት ድርብ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ሌሎች እስኪነግሯቸው ድረስ መጠበቅ አይኖርባቸውም። እንደ ብርቱካንና መሰሎቿ ሳይደራጁና በፖለቲካው ትግል በሚገባ ሳይሳተፉ በመፈክርና በግጥም ብቻ መብታቸውን ያስከብራሉ ብሎ ማሰብ ደግሞ ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም። በጨለማው ዘመን ቀደምቶቹ እነ ጣይቱ ብጡል፣ ሸዋረገድ ገድሌ፣ ከበደች ስዩም፣ ስንዱ ገብሩ፣ ወዘተ. (ስንቶቹን ቆጥሮ መጨረስ ይቻላል?) ያበቀለ መሬት ዛሬ እንዲህ መክኖ ሲቀር እኛን ወንዶቹን ካስቆጨ ሴቶቻችንን ለምን ሊያነሳሳና ሊያስቆጭ እንዳልቻለ ለኔ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።

የመንግስት ተቋማትን ገመና ያጋለጠው ሪፖርት‹‹እንደዚህ ዓይነት የሒሳብ ጉድለት የተመዘገበው በሌሎች አገራት ቢሆን ኖሮ ሚኒስትሮቹ ከቦታቸው ይነሱ ነበር››

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ

ምክር ቤቱ

በሱራፍኤል ግርማ

Page 21: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003ስ ፖ ር ት22

በአቤል ዓለማየሁ[email protected]

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን‹‹ለችግሮች ተገቢውን መፍትሔ የማይሰጥና ወጥ

አሰራርን የማይከተል›› ተብሎ ተተቸ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2002 ዓ.ም. የበጀት ዓመት፣ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ከትላንት በስቲያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን የክዋኔ ኦዲት አስመልክቶ የተለያዩ ችግሮችን ዘርዝሯል፣ ማሳሰቢያም አቅርቧል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር የሆኑት አቶ ገመቹ ዱቢሶ በሪፖርታቸው ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ብሎም አገሪቱን ወክለው በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና በአህጉር ደረጃ በሚዘጋጁ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የሚወዳዳሩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሁሉም ክልሎች ከቀበሌ እና ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶት ስፖርቱን ለማስፋፋት የሚያስችል አደረጃጀት ባለማዋቀሩ በስፖርቱ ዙሪያ ለሚከሰቱ ችግሮች ተገቢውን ወቅታዊ መፍትሔ የመስጠት ድክመት እንዳለበት አስረድተዋል።

ዋና ኦዲተሩ ጨምረውም የታዳጊ እና ወጣቶች ፕሮጀክት ስልጠና፣ ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርጉ የባለድርሻ አባላት አደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት በግልፅ ያልተቀመጠ በመሆኑ ስፖርቱን በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲዘወተር እና እንዲስፋፋ ለማድረግ የተቀናጀና ወጥ አሰራርን የተከተለ የአተገባበር ስራ በፌዴሬሽኑ ውስጥ አለመቀየሱን ገልፀው ፌዴሬሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ወቅታዊ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ በመለዋወጥና፤ በመተግበር የተጠቀሱትን ችግሮች በማስወገድ አገሪቷ በዘርፉ ልታገኝ የሚገባትን ውጤት ለማሳካት ጥረት ሊያደርግ እንደሚገባ በሪፖርታቸው ላይ አሳስበዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስፖንሰሩን አስታወቀየተሳታፊዎች ቁጥር ይጨምራል •

በቀጣዩ ዓመት ለ11ኛ ጊዜ የሚካሄደው ዓለም አቀፋዊው የታላቁ ሩጫ ውድድርን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ስፖንሰር መሆኑ ታወቀ።

ከትላንት በስቲያ በቬልቬት ሬስቶራንት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ ዳይሬክተር ኃይሌ ገ/ሥላሴ እንደገለፀው በአሁን ሰዓት በዓለም ላይ መሮጥ ካለባቸው አስር የሩጫ ውድድሮች እየተባለ በዓለም መገናኛ ብዙሐን እየተነገረለት ያለው ይህ ኢቬንት ስኬታማ የሆነው በሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ መሆኑን ገልጾ ‹‹ማንኛውም ስራ እንደ ታላቁ ሩጫ ርብርብ ከተደረገበት ሁሉም ነገር ይቻላል›› የሚል መልዕክት አስተላልፏል። ውድድሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖንሰር በማድጉም ምስጋናውን አቅርቧል፤ ታላቁ ሩጫን ስፖንሰር ማድረግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በማስመር።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰው ኃይል አስተዳዳር ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሰይፉ ቦጋለ ይህን የብዙዎች ትኩረት የሳበ የስፖርት መድረክ ስፖንሰር በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ ‹‹ታላቁ ባንክ፣ ታላቁ ሩጫን ይደግፋል›› ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን ብር ቦንድ ከወለድ ነፃ በእለቱ የገዛ ሲሆን የ100 ሺህ የገንዘብ ስጦታ ማበርከቱም ተገልጿል። የታላቁ ሩጫ የተሳታፊዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት 35 ሺህ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ርግጠኛ መጠኑ ለጊዜው ባይገለፅም ቁጥሩ እንደሚጨምር ታውቋል።

ኮፓ ኮካ ኮላ ወደ ሩብ ፍፃሜ ተሸጋገረበሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች

መሀከል የሚካሄደው የኮፓ ኮካ ኮላ የእግር ኳስ ውድድር ወደ ሩብ ፍፃሜ ተሸጋገረ። ዛሬ እና ነገ ወሳኝ ጨዋታዎች ያደርጋሉ።

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ በጣምራ ያዘጋጁት አራተኛው የኮፓ ኮካ ኮላ ውድድር በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን የድሬዳዋው ነገ ድሬዳዋ አጠቃላይ እና ሳቢያን በሚያደርጉት የዋንጫ ጨዋታ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን ሰኔ 12 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የአዲስ አበባ ውድድር ደግሞ ወሳኝ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። በዚህ መሠረት ዛሬ እንጦጦ አምባ ከቦሌ መሰናዶ፣ ከፍተኛ 23 ከዳግማዊ ሚኒልክ፣ አዲስ ከተማ ከሚሊኒየም እንዲሁም ነገ ደጃዝማች ባልቻ ከአድቬንቲስት ጋር ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመግባት ይጫወታሉ። የሴቶች ውድድር ወደ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግሯል።

አራተኛው የኮፓ ኮኮ ኮላ ውድድር ሰኔ 19/2003 ዓ.ም. የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አሸናፊ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚያደርጉት የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ይጠናቀቃል።

ለተለያዩ አካላት እና ግለሰቦች እንዲደርሱ በህትመት መገናኛ ብዙሐን በኩል የሚላኩ ጦማሮችን ሳነብ ኖሬያለሁ እንጂ ይህን መሰል ጦማር ለመስደድ ብዕር እና ወረቀት ሳገናኝ የመጀመሪያዬ ነው። እንደ አጋጣሚም የመጀመሪው ለእርስዎ ሆነ፤ እንደምን አሉ አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ? ጠፉብን እኮ!

መቼም እርስዎን ለማግኘት በመደበኛነት በሚሰሩበት ኮተቤ ኮሌጅ እና ተመርጠው በፕሬዝዳንትነት በሚመሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቢሮ (አዲስ አበባ ስታዲየም) ከመምጣት ይልቅ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ቆሞ መጠበቅ የተሻለ ነው እየተባለ እየተዜመ ያለውን ዜማ ከጆሮዎ ሳይደርስ ይቀራል ብዬ አልገምትም። ከሚመሩት እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ በማስቀደም በኮሚሽነርነት እየተመደቡ ተደጋጋሚ ጉዞ ማድረግዎ የትችቱ የመጀመሪያ ሀረግ እንደሆነም ይጠፋዎታል ማለት ፊትን ጀርባ ብሎ የመግለፅ ያህል ቀልድ ነው። ሬዲዮውም፣ ጋዜጣውም የእርስዎን ነገር እያነሳሳ ቃላት እየወረወረ ነው፤ እኔም ይሄው እዚህ ቁጥር ውስጥ ተደመርኩ።

ከሁለት ዓመት በፊት፤ ግንቦት 8/2001 ዓ.ም. በሂልተን ሆቴል በዶ/ር አሸብር የሚመራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የፊፋ ልዑክ መሪና የሳይፕረስ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሚስተር ኮስታኪስ ኮትስኩምኒስን ጨምሮ ሌሎች የልዑክ ቡድኑ አካላት በተገኙበት አራት ንዑስ አንቀጾች የተካተቱበት የዶክተር አሸብርን አመራር የሚቃወም ፅሁፍ ማንበብዎን [በወቅቱ የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ነበሩ] ጉባዔውን የታደምን የምንዘነጋው አይደለም። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ራዕይ የሌላቸው፣ የውድድር ካላንደር በተገቢው ሁኔታ የማያከብሩና ተፈፃሚ የማያደርጉ፣ የክለቦችን አቤቱታ የማይሰሙና የማይቀበሉ መሆናቸውን፣ ለአዳጊና ለወጣት ፕሮጀክቶች የሚሰጡት ትኩረት አለመኖሩንና ከ14,850 በላይ አዳጊዎች የተካተቱባቸው ፕሮጀክቶች እንደተዘጉ፣ በዶክተሩ የሚመራው ፌዴሬሽን በአንድ አመት ውስጥ 12 የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች እንደቀያየሩ፣ ሰውዬው አምባገነን መሪ እንደሆኑና ተጨማሪ መረጃዎችን ሲዘረዝሩ ከቤቱ ሞቅ ያለ ጭብጨባ አግኝተዋል፤ ጉባዔተኛውንም በደስታ አፍነክንከዋል። በወቅቱ ከዘረዘሯቸው ውስጥ ብዙዎቹን እኔም የማምንባቸው በመሆኑ ያነበቡትን ሰነድ ቅጂ ከእጅዎ ስቀበልዎት አልንገርዎ እንጂ በሆዴ ‹‹ክብር ለእርስዎ›› ብዬ ነበር።

ይህን ሁሉ ችግር የደረደረ (ወይም እንዲደረደር እድሉ የተሰጠው ሰው) መልሶ ይህን ችግር ሲደግም አነጋጋሪም፣ አስገራሚም ይሆናል። እስቲ በቅንነት ያስቡትና ራስዎን ይጠይቁ ‹‹ከዘረዘርኩት ውስጥ እኔ ምን ያህሉን ቀርፌያለሁ?›› ብለው።

የውድድር ካላንደር በተገቢው ሁኔታ አለመከበር

ዛሬም ድረስ የሚመሩት ቤት ዋና ችግር ነው። ከሊጉ አቅም፣ ከአገራችን የኢኮኖሚም ሆነ የእግር ኳስ ደረጃ አንፃር በማይመጣጠን መልኩ በ16 ቡድኖች የሊግ ውድድር በማድረግ ‹‹ክለቦች›› በውድድር ማራቶን ይኸው እየዳከሩ ነው። የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና ሳይደረግ ተጨዋቾች ከክለባቸው ጋር ያላቸው የውል ዘመን መጠናቀቂያ፤ ሰኔ 30 ተቃርቧል። ሊጉንም ቢሆን ቶሎ ለማጠናቀቅ ሲባል ታላቆቹ የአውሮፓ ቡድኖች እንኳን የማያደርጉትን ሃያ ቀን በማይሞላ ጊዜ አምስት ጨዋታ ለማድረግ ይገደዳሉ፤ ከሰኔ 1-19 ድረስ።

የአዳጊና ወጣቶች ፕሮጀክትስ ቢሆን 24 ጣቢያዎች ከማቋቋም ባለፈ የእርስዎ ካቢኔ ምን ሰራ? ዛሬም ችግሩ እንዳለ ነው። የቀያየሩት የብሔራዊ ቡድን ቁጥር እንደቀድሞው ፌዴሬሽን ደርዘን ባይሞላም ግልፅ ባልሆነ ምክንያት መቀያየሩና መቅጠሩ በእርስዎ ዘመንስ ተቀረፈ? የአፍሪካ እግር ኳስ ስነ ልቦና የማያውቁት፣ በአሰልጣኝነት ይሄ ነው የሚባል ስራ ያልሰሩት ስኮትላንዳዊው ኢፊ ኦኑራ ያለ ባለሙያ መረጣ የተቀጠሩትና ‹‹ይሄ ነው›› ተብሎ ባልተገለፀ ምክንያት የተባረሩት ይሄው በእርስዎ ዘመን አይደለም እንዴ? ለአምባገነንነትስ መች መስፈርቱን ሳያሟሉ ቀሩና? ጋዜጠኞች ሊያናግርዎት ሲደውልሎት ጆሯቸው ላይ መዝጋትዎን እርስዎ ባሉበት ሲናገሩ ሰምቻለሁ። የአዲሱ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ (ቶም ሴንትፌት) ቅጥርን ከስራ አስፈፃሚ አባላት ውስጥ ብዙዎቹ ሳያውቁ መፈፀሙን በርግጠኝነት አውቃለሁና ውሳኔዎችዎ አምባገነናዊ እንደሆኑ አያሳዩም ታዲያ? ነው ወይስ ጊዜዎ በጉዞ ስለተጣበበ ለዚህ ማሰቢያ ጊዜ የለዎት ይሆን?

የጉዞው ነገር‹‹ባለፈው እሁድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች በሚጫወቱ ተጨዋቾች ከተጥለቀለቀው የናይጄሪያ አቻው ጋር በአዲሰ አበባ ስታዲየም ተጫውቶ በመጨረሻ ደቂቃ በተፈጠረ የእኛው ግብ ጠባቂ የጊዜ አጠባበቅ ስህተት ሁለት እኩል በተለያየንበት ጨዋታ ላይ በስታዲየሙ የተፈጠረውን እንባ ኩልል የሚያደርግ አገራዊ ስሜት እንዴት አዩት?›› ብዬ ጥያቄ እንዳላቀርብልዎ በወቅቱ እርስዎ መቼ በስታዲየሙም ሆነ በአዲስ አበባ አልነበሩም። በተለይ የናይጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የቡድናቸውን አባላት መርተው አዲስ አበባ ሲገኙና የአቻቸው ወንበር ስናይ ባዶ መሆኑ አስደንግጦናል። እስቲ ያስቡት ሰውዬው ‹‹አቻዬ የት ሄዱ?›› ብለው ሲጠይቁ ‹‹ለጨዋታ ኮሚሽነር ሆነው ታንዛኒያ ሄደዋል›› ማለት ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ።

አስቀድመው ትልቅ ድግስ አለብኝ ብለው መቅረት አሊያም ሌላ ኢትዮጵያዊ ሰው መመደብ እየቻሉ በውሳኔዎ መፅናትዎ ያስገርማል። እኛ ኃጢያታቸውን የዘረዘሩት ዶክተር አሸብር አንድ ቀን በኮሚሽነርነት ሄዱ ሲባል ሰምቼ አላውቅም። እድሉን ያኔ ‹‹በኃጢያቱ›› ዘመን በፌዴሬሽኑ ውስጥ ለነበሩት እና ዛሬ የእርሰዎ ፌዴሬሽን የፅህፈት ቤት ኃላፊ አድርገው ለሾሟቸው አቶ አሸናፊ እጅጉና ሌሎች ይጠቀሙበት ነበር። ከ80 ሚሊየን ህዝብ በላይ የወከለ የአንድ አገር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አገራዊ ኃላፊነቱን ጥሎ እንግዳ ለማስተዋወቅ ደረጃ በመውጣትና በመውረድ ስራ

ላይ ተጠምዶ በአገር የለም ሲባል ያሳፍራል። ክስተቱ እርስዎ እግር ኳስን ለመጥቀም ሳይሆን በእግር ኳሱ ለመጠቀም እንደመጡ ፍንጭ የሚሰጥም ይሆናል።

በእርግጥ እያንዳንዱ የውጪ ጉዞዎ ቀላል የማይባል ዶላር የሚዛቅበት መሆኑ እሙን ነው። በአንድ ጉዞ ከ800 ዶላር በላይ ኪሶ ይገባል። ይህ ማለት እስካሁን ድረስ አድርገዋቸዋል ተብሎ በሚገመተው 20 በላይ ጉዞዎች ከሦስት መቶ ሺህ ብር በላይ ኪስዎ ገብቷል ማለት ነው። ይህን ያህል ገንዘብ በሁለት ዓመት ውስጥ የሚያገኝ የመንግስት ተቀጣሪ ኢትዮጵያዊ የለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ደሞዜ 6,400 ብር ነው›› ካሉ በዲንነት በሚመሩት ኮተቤ ኮሌጅ ለእርስዎ ይህንን ያህል እንደማይከፍልዎ እገምታሁ። የተጠቀሰው ገንዘብ (የካፍ የአበል ክፍያ) ከፍተኛ መሆን ሊያጓጓዎ ቢችልም አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሰውን ያወገዘ ሰው በእርስዎ እንዳይደርስ ጥንቃቄ ሊወስዱ በተገባዎት ነበር። እያደረጉት ያለው ክስተት ግን ከዚህ ተቃራኒ መስሎኛል። የገንዘብ ጉጉ እንዳይሆን ገንዘባዊ አቅሙ ጠንካራ የሆነ ሰው ወደ ፌዴሬሽኑ ሊመጣ እንደሚገባው ሊታሰብበት የሚገባ አንኳር ጉዳይ ይመስለኛል። ይህን ስል እንደ ቀድሞ አቻዎ ዶክተር አሸብር አይነቱ ገንዘብ ስላለው ብቻ ይምጣ ማለቴም አይደለም፤ ገንዘብ ሲደመር እግር ኳሳዊ ፍላጎትና እውቀት ይታከልበት ማለቴ ነው። እርስዎ ከዚህ ውስጥ ምን ያህሉን እንደሚያሟሉ እኔ እንጃ!

ተዳፍኖ የቆየው ተግባርዎ በትልቁ ድግስ እለት (የናይጄሪያ ጨዋታ ላይ) ገኖ ወጣ እንጂ የጉዞ ውጥረት ውስጥ ከገቡ እንደሰነበቱ ሳናውቅ ቀርተን አይደለም። በእለቱ ሰንደቅ ዓላማውን አንግቦ ከስፖርታዊ ጨዋነት ዘጠና ደቂቃ ድጋፍ የሰጠ ህዝብ በሳምንቱ አጋማሽ በአዲስ አበባ በተካሄዱ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ለአገሩ በዘመረበት አንደበቱ፣ በእርስዎ ላይ የተቃውሞ ድምፅ ሲያሰማ ነበር። መገናኛ ብዙሐንም ‹‹አንደኛቸውን ጠቅልለው ካፍ ይግቡ›› ሲሉ እስከ መተቸት ያደረሳቸው

የእርስዎ ደጋግሞ አየር ላይ መንሳፈፍ የአገርን እግር ኳስ ከመጥቀም ይልቅ ኪስዎን እንደጠቀመ በማሰብ ነው። ህዝቡ ዝናም ‹‹እየቀጠቀጠው›› ለአገሩ ብዙ ሲያዋጣ፣ የድግሱ መሪ ግን የራስዎን ገፍተው በሰው ድግስ ላይ ሲያስተናብሩ መዋል በርካታ ባለድርሻ አካላትን አሸማቋል፡፡ እርስዎን ‹‹ምሩኝ›› ብሎ ያስቀመጥዎት ክለቦች፣ የክልል መስተዳድር ፌዴሬሽኖች እና የሌሎች በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምፅ ያላቸው አካላት ዝምታም አስገርሞናል። ዝምታቸው እርስዎንስ አላስገረምዎትም?

ከክስ፤ ኃላፊነትን መወጣት ይቅደም!

በፌዴሬሽን ውስጥ ያላችሁ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እያንዳንዳችሁ በስራችሁ የምትመሩት ኮሚቴ አለ። እርስዎም የህክምና ኮሚቴ ሰብሳቢ መሆንዎ ይታወቃል። ይህ ‹‹ኮሚቴ›› ግን ደካማና አለ ለማለት አስቸጋሪ እንደሆነ በዙሪያዎ ያሉ ይገልፃሉ፡፡ ኮሚቴውንም በአግባቡ መሰብሰብ አለመቻልዎን ሰምቻለሁ፤ በተጨባጭም ታይቷል።

ባለፈው ወር ሙገርና ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ላይ የሙገሩ ተከላካይ ዳንዔል መኮንን በግጭት ጉዳት ደርሶበት፣ ምላሱን ውጦ ህይወቱ ሊያልፍ ሲል አንድም እርስዎ የሚመሩት የህክምና ቡድን አባል በስታዲየሙ ተገኝቶ ሊረዳው አልቻለም። የዚህ ልጅ ህይወት አልፎ ቢሆን ኖሮ የህክምና ባለሙያና ረጂ መሳሪያዎችን ማቅረብ ያልቻለው ለስም ብቻ ያለው የህክምና ኮሚቴና [በዋናነትም] እርስዎ ተጠያቂ ይሆኑ እንደነበር ያውቁታል? አሁንስ ይህ ጉዳይ አሳስቦት ከውጪ ጉዞዎ ላይ ቀንሰው ጊዜ ሰጥተውት እያሰቡበት ነው?

በባህር ዳሩ የጠቅላላ ጉባኤ ላይ አድንቀዋቸው ‹‹ቤቱ አላሰራ አለኝ›› ብለው መልቂያ ካስገቡ በኋላ ፌዴሬሽኑ በቸርቸል ቪው ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ግን ምንም እንዳልሰራ የተቹትን የቀድሞውን የፌዴሬሽኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር (አቶ ዮሐንስ ሳህሌ) የፌዴሬሽኑን ችግሮች አስመልክቶ በፋና ብሮድካስት ግንቦት 8/2003 ዓ.ም. በሰጡት አስተያየት ሳቢያ ባለፈው ማክሰኞ የፌዴሬሽኑ ዲስፕሊን ኮሚቴ ጠርቶ አነጋግሯቸዋል። የክሱ ጠንሳሽ እርስዎ ስለመሆንዎ መረጃ ሰብስቤያለሁ። ትክክል ነው /አይደለም ለማለት ባልፈልግም በእለቱ የአቶ ዮሐንስን ገንቢ ትችት ተከታትየዋለሁ። በተለይ ፌዴሬሽኑ በባለሙያዎች

መመራት እንዳለበት ደጋግመው ሲያስገነዝቡ ነበር። ማንም ሰው ደግሞ አመለካከቱን እና ሀሳቡን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት እንዳለው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 29 ላይ የሰፈረ ነው። በዚህ አንቀጽ ‹‹ለ›› ላይ ‹‹ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት … በመረጠው ማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ፣ ሙያዊ አስተያየት የመሰብሰብ፣ የመቀበል፣ የማሰራጨት ነፃነቶች መብት ይኖረዋል›› ይላል። ይህ አንቀፅ ተማምነን ነው እኔና ሌሎች የሙያ ጓደኞቼ ሀሳባችንን እንድንገልፅ የሚያደርገን። እናስ እርስዎ እና ፌዴሬሽንዎ ይሄን ተገንዝባችሁ ጠቃሚውን ሀሳብ ወስዳችሁ የማይጠቅመውን መጣል ሲገባችሁ ለክስ መፍጠናችሁ አስገረሞኛል። ምነው ይሄን ፍጥነት እግር ኳሱን ለመርዳት ብታውሉት አስብሎኛል።

አቶ ዮሐንስን መክሰስ የሚያስተላልፈው መልዕክት እንደ አገርም ጎጂ መሆኑን እንዲያጤኑት ከሰሙኝ ወንድማዊ ምክሬን ባካፍሎት ደስተኛ ነኝ። እንደሚያውቁት እኚህ ባለሙያ መኖሪያቸውን ባደረጉበት አሜሪካ እና በተለያዩ አገሮች ተንቀሳቅሰው ያካበቱት ልምድ ከኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቁመት በላይ ነው። አገራቸውን ለመርዳት ወይም በአገራቸው ላይ ለመስራት መጥተው እሳቸው እንደገለፁት አመቺ የስራ ክበብ በፌዴሬሽኑ አልገጠማቸውም። አሁን ደግሞ ‹‹ሰጡት›› በተባለው አስተያየት ክስ መሰናዳቱ ሌሎች በውጪ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ገብቶ መስራት ያለውን ተግዳሮት ጉልህ ማመላከቻ ስለሚሆን አገራቸው ገብተው መስራት ይፈራሉ። ‹‹በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ባላቸው አቅም አገራቸውን የሚረዱበት አቅም ተመቻችቷል›› እየተባለ በሚደሰኮርበት ወቅት ይህ እርስዎ የመሩት ክስ የሚባለው ሁሉ ውሸት መሆኑን ስለሚገልፅ ለአገር ያለውን ጉዳት ሊያጤኑት ይገባል። [ይህ ማለቴ ግን ያጠፋ አይገሰፅ ማለቴ አይደለም] ለክስ ከመትጋትዎ በፊት ኃላፊነትዎን በአግባቡ መወጣትም ላይ ትኩረት ይስጡ።

ከስንብቴ በፊት…የኢትዮጵያ እግር

ኳስ እንደሚያውቁት በችግር የተተበተበ ነው። ችግሮቹ ሁሉ ለቅሞ ጥሎ የሚጨርስ ባለሙያ ማግኘት ቀርቶ እንኳን ችግሩን የሚያቀል ሰው ፍለጋ ላይ በሚዳክርበት ወቅት ጥሩ ፕሬዝዳንት እንዳላገኘ የዘረዘርኳቸው ምሳሌዎች ጥሩ ማረጋገጫዎች ናቸው፤ ይህን እየቆመጠጥዎትም ቢሆን ሊጎነጩትና ሊያምኑት ይገባል ብዬ አምናለሁ። ተቃውሞ ከሁሉም ቦታ በርክቶቦታል። ይህ የጭለማ ጊዜ አልፎ ጭላንጭል ብርሃን ለመመልከት በብርሃን ፍጥነት በመንቃት ስህተትዎን ለማረም ተግተው ካልሰሩ በአስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ ላይ ምስክርነት ያነበቡት ሰነድ በእርስዎ የሚነበብበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አምናለሁ።

በቅርብ የሚያውቆት ጥሩ አስተማሪ እንደሆኑ፣ የታመቀ የመስራት አቅምና መጥፎ የማይባል ግለሰባዊ ባህሪ እንዳለዎ ይገልፃሉና ይህን ዙሪያ ገባውን ቃኝተው ‹‹ምን እየሰራሁ ነው?›› ብለው በመጠየቅ ለመንቃት ይጠቀሙበት፡፡ ትችታዊ ጦማሬን በበጎ እና በቅንነት ይውሰዱት። መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልዎ።

ይድረስ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

ወደ ፌዴሬሽኑ የመጡት ራስዎን ወይስ እግር ኳሱን ሊጠቅሙ?

የዚህ ልጅ ህይወት አልፎ

ቢሆን ኖሮ የህክምና ባለሙያና ረጂ

መሳሪያዎችን ማቅረብ ያልቻለው ለስም

ብቻ ያለው የህክምና ኮሚቴና [በዋናነትም] እርስዎ ተጠያቂ ይሆኑ እንደነበር ያውቁታል?

አሁንስ ይህ ጉዳይ አሳስቦት ከውጪ ጉዞዎ

ላይ ቀንሰው ጊዜ ሰጥተውት እያሰቡበት

ነው?

Page 22: Awramba Times Issue 171

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ �n ዎ ‹ SgÝ“ �”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–<�M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ሰፋ ብሎ ውሃየሚያወርድ

ምቾት እናጥራት ያለው

ከበቂ መለዋወጫ ጋር

ለጥንቃቄዎ የተመሳሰሉትን

ይለዩ

ምን እየተሰራ ነው? ባህላዊ የትምህርት

አሰጣጦችን በዘመናዊ ለመተካት ጥንታዊ አሰራሮችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር ጊዜ ቆጣቢ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ምን ጥረት እየተደረገ ነው?

ነገሮች አሁን ባላው መልኩ ከቀጠሉ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ የራሷ ስለሆነው ፊደልመ፣ ያሬዳዊ ዜማ፣ ፅናፅል፣ ከበሮ ወዘተ የማውራት አቅሟን እንደምታጣ አጥታችሁት ነውን?

ለዚች አገር እንደቤተመጽሐፍት የሚቆጠሩ ግለሰቦች አንድ ባንድ በእርጅና በእረፍት እስኪለዩን የምንጠብቀው ለምንድን ነው? በግራም ነፈሰ በቀኝ የነሱ ዕውቀት እና ችሎታ ለዚች ሀገር ሥልጣኔ የራሱ የሆነ አስተዋጸኦ ይኖረዋል። ይህንንም ከትናንት ይበልጥ ዛሬ ከዛሬም ይበልጥ ነገ ማስመስከር መቻል የአገርን ግዴታ መወጣት ነው።

በሀገሪቱ በዓለማዊ ትምህርት ውስጥ የማይገኙ ባህረ-ሐሳብን (የቀን አቆጣጠር ትምህርት) የመሳሰሉ ትምህርቶችና ቀመሮች ለዚች አገር ተጠብቀው መቆየት የለባቸውም ወይ?

ይህንን ያስተዋሉ አንድ የቤተክርስቲያኗ ሰባኪ በአንድ ወቅት በየገጠሩ እየተንከራተቱ ብዙ ቀለም የቀሰሙ ምሁራን የሳንቲም መሰብሰቢያ ሳጥናቸውን አውርደው በማዕከላት ውስጥ የሚያገለግሉበት አሰራር ይፈጠር ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተው ነበር።

እኔም በግሌ የኢትዮጵያ ኃብቶች እየተባሉ የሚጠሩ ነገሮች መሠረታቸው ይችው ቤተክርስቲያን ስለሆነች በየጊዜው አዳዲስና ቀልጣፋ የማስተማሪያ ሥነ-ዘዴዎችና መዋቅሮችን ተቋማትንና ቴክኖሎጂን መጠቀም ተገቢ ይመስለኛል።

ረመሪዎች /መምህራን/

ፍፁም አንዲሆኑ እንኳ ባይጠበቅ ምሉዕ ሊሆኑ ግድ ነው። በቤተክርስቲያኗ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ፣ በሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሰላም አባት ተብላችሁ የምትጠቀሱ አባቶች እውን የሰላም አባት ነን ብላችሁ ታስባላችሁ? ካሰባችሁስ እንደሆናችሁ እርግጠኛ ናችሁ?

ለዚህ ህዝብ ምንድንነው የምናስትምረው? ምንን እየተናገርን ምንን እየኖርን ነው አርአያ የምንሆነው? ጥለነው ወጥተናል በምንኩስና ተለይተናል ከምንለው ዓለም መራቃችንን ዘወትር በጭቅጭቅ በግብግብ በንዝንዝ በኩርፊያ ነው እንዴ የምንገልፀው?

ከዓመትና ከኹለት ዓመት ወዲህ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሲቃረብ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ይመስል ደግሞ ዛሬ ምን ይመጣ ይሆን እየተባለ ይጠበቃል። ይሄ በመንፈሳዊ ቤት ይሄ የሀገርን አደራ በተሸከሙ አባቶች ዘንድ የሚጠበቅ ነበር?

እርስ በርሳችሁ እየተተረማመሳችሁ መደማመጥ እየተሳናችሁ እያየን በሚዲያ ስለፍቅር ብትሰብኩን ሊገባን ይችላል? በዓለማዊ መንግስት ውስጥ የታከቱንን አሰራሮችና ሸፍጦች ሰርተሃል አልሰራሁም እያላችሁ አተካሮ ስትገጥሙ እየተመለከትን ስለቅንነት ብትናገሩን እንዴት ብለን እንረዳለን?

ዋጋን የሚወስነው የዓለም የገበያ ዋጋ ነው። ነገር ግን የሥነ-ፅሁፍ ሙያን ለማበረታታት መንግስት ሊወስዳቸው የሚችሉ አንዳንድ እርምጃዎች ይጠፋሉ ለማለት ግን ይቸግራል። ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን ሕገመንግስቱ ለሕዝቡ የሰጣቸው በርካታ የባህል መብቶች ከቶም ሊተገበሩ አይችሉም። በመንግስት የሚተዳደሩት የመገናኛ ብዙሃን እንኳ ለሥነ-ፅሁፍ በአጠቃላይም ለሥነ-ጥበብ ያላቸው ትኩረት እጅግ አናሳ ነው።

በመድረኩ ላይ ከተነሱት ጥያቄዎች አንዱ ለሥነ-ጥበቡ ክብር የሚሆን አንድ ዓመታዊ ቀን እንዲሰየም ነበር። ይህ መልካም ሀሳብ ሲሆን ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተባለው የመታሰቢያ ቀን በዚሁ መድረክ ላይ እውቅና እንዲሰጡ በጭብጨባ ጫና ማስገደዱ ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው። ለጥያቄው በተሰጠው ምላሽም ጉዳዩ በዚህ መልክ የሚወሰን እንዳልሆነ ተገልጿል። በእኔ አመለካከት የሥነ-ጥበብ

መፈረጅንና መጠቆርን ሳንሰጋ በቅንነት የሚሰማንን ተነጋግረን መግባባት ላይ የምንደርስበት፣ የሚለያዩ የጓዳና የአደባባይ ማንነቶች ማበጀት የማያስፈልግበት ዘመን የሚመጣው መቼ ነው?›› ብሎ መጠየቅ የዋህ ያስብለን ይሆን?

መ ረ ዳ ታ ች ን የፈቀደልንን ያህል ስንገነዘበው አንድን ሁነት ተከትለው የሚያጎነቁሉ ሁሉንም አይነት አፀፋዎች አንደማስተናገድና ለመመርመር እንደመትጋት የተመረጡ የተወሰኑትን ይዞ፣ ለቀሩት ቦታና እድል ነፍጎ የቆመ አሰራር ህዝብን ያማከለና የሚያነቃንቅ ሊሆን አይችልም። ምናልባት ሁሌም የሚገባንን (‹‹ገ›› ጠብቆ ይነበብ) የሚመርጡልን አካላት ተገቢ ነው ብለው ያመኑበትን ሀሳብ ሁላችንም እንድናምንበት እስክንደነቁር ድረስ በማስጮህ ሌሎች እሳቤዎችን ጨፍልቆ ለማስቀረት አሊያም ከትኩረት እንዲሰወሩ ለማድረገ

ያስችል ይሆናል። ግን ነገሩ ‹‹ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ›› ነውና በኋላ አፋችንን ሞልተን አንድ ላይ ሆነን ይሄን አደረግን›› ለማለት እንቸገራለን።

እነኚህን መሰል ሰፊ ተሳትፎ የሚጠይቁ ታላላቅ አጋጣሚዎችን ታክከው የሚደመጡ ተዳፍነው የከረሙበትን አመድ አራግፈው ያልጨረሱ ሆድ ብሶቶች አሉ። ‹‹ተዘንግተን የኖርን ሰዎች ዛሬ እንደምን ታወስን?›› አንዱ ነው። እፍ ያለ ፍቅራቸውን አሟጠው ብው ያለ ጠብ ውስጥ የተገኙት ኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት በደራበት ወቅት በተደረጉ ውይይቶች/ስብሰባዎች ደጋግሞ ተነስቷል። ሥራ-አጦች ‹‹ኑሮን መጋፈጥ ከብዶን የምንሆነው ስናጣ ችግራችንን ሳትቀርፉ የተገኘውን ሥራ ሁሉ ለካድሬዎቻችሁ ስትነዙ ቆይታችሁ ትዝ ያልናችሁ የሚጠበቅብን ሲኖር ብቻ ነው?›› ብለዋል። ከገበሬ ወላጆች የተገኙ ተማሪዎች ወላጆቻቸውን በሚያገል መንፈስ ሲበግኑ መንግስት የት

እንደነበር አፋጠዋል። መንግስትን ወክለው የሚያወያዩ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው ምላሽ ዜጎቿን አበላልጣ የምትመዝን አገር መኖር እንደማይገባት የሚያሰረግጥ፣ ስህተት ካለም መታረሙ እንደማይቀር ተስፋ የሚሰጥ ጥሪ ነው። ይሄው ዛሬ ደግሞ አባይ ሆድ ብሶቶቹን ደግሞ ለፀሀይ አብቅቷቸዋል።

ሰዎች ዜግነታቸው እውቅና የሚሰጠው የሚፈለግባቸው ነገር ሲኖር ብቻ መሆን የለበትም። ዘመን ሞቶ ሌላ ዘመን በተወለደ፣ ትኩሳት በርዶ ሌላ ግለት መሟሟቅ በጀመረ ቁጥር የማይቀር ጉንጭ-አልፋ ንትርክ ካለ ያልተሰራ ሥራን አመላካች ነው። እስከመቼ ቀጣይነት እንደሚኖረው መገመት ይከብዳል። ብቻ ሁሉም በሮች ያለአድልኦ እኩል ተከፍተው እንደችሎታችንና ፍላጎታችን የምንገባ የምንወጣበት እለት ቶሎ እንዲመጣ እንመኛለን። ለልማትም ሆነ ለሌላ ሀገራዊ ጥሪ ሆ ብሎ መነሳት ያኔ ይቀለናል።

ሙያተኛው ‹‹ክብር ለጥበብ›› የተባለውን እለት በራሱ ሰይሞና በተለያዩ ትዕይንቶች ማክበር ጀምሮ የመንግስትን ይፋዊ እውቅ መጠየቅ የሚቻል ነው። ይህ ሥራ ከራሱ ከጥበብ ቤተሰቡ መጀመር ያለበት ነው። አባቶች ሲተርቱ ‹‹ባለቤቱ ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም›› እንዲሉ።

በመድረኩ ላይ አብላጫዎቹ ጥያቄዎች የቀረቡት ከኪነ-ጥበብ ሙያተኛው የእለት ከእለት ችግሮችና ወቅታዊ ተግዳሮቶች አኳያ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ምላሽ ግን አሁን ያሉትን የእለት ችግሮች የተመለከተ ሳይሆን የመንግስትን አጠቃላይ ፖሊሲ፣ ለመጪው ዘመን የሥነ-ጥበብ እድገት የሚያስፈልጉትን መሰረተ ልማቶች የተመለከቱ ሀሳቦች ላይ ነበር። ‹‹መንግስት የልማት አጀንዳውን ለማስፈፀም የሥነ-ጥበብ ሚናን ይፈልገዋል›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራውን ቅደም ተከተል በማውጣት መንግስት ባለው ውስን የሰው ኃይልና የፋይናንስ አቅም በጋራ ለመስራት የሚችል መሆኑን ገልፀዋል። እንዳሉትም

መንግስት በሥነ-ጥበብ ይገለገላል። ሥነ-ጥበብን የሚገለገል ከሆነ ደግሞ የሥነ-ጥበብ ህመሟን፣ ችግርና ጉዳቷን አብሮ ሊጋራው ይገባል። የአገሪቱ ከያንያን ሥራና ሕይወት እንደፕላስቲክ መጠጫ ‹‹use and throw›› ሆኖ መቀጠል አይገባውም።

በአንድ በኩል እራሱ የሥነ-ጥበብ ሙያተኛው መራመድ የሚችለውን ያህል አልተጓዘም። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በሥነ-ጥበብ ላይ ያለውን የቤት ሥራ በአግባቡ አልተወጣም። የመንግስት አስተዳደር ሊኮራ የሚገባው በከተማ ውስጥ በተገነቡ ፎቆች ብዛት ወይም በገጠር በዘረጋቸው መንገዶች ብቻ አይደም። መንግስት ለአገሩ የሥነ-ጥበብ እድገት ምን አስተዋጽኦ አበርክቷል? ባህል ነክ ዓላማዎችን በሕገመንግሰቱ ከማስፈር በተጨማሪ መብቶቹን በተግባር ለመተርጎም ምን ያህል እየሰራ ነው? የጥበብ ቤተሰቦች ሕይወት እንዴት ያለ ነው? የሚሉ መለኪያዎችም አብረው ይነሳሉ። በድራማው ላይ እንደታየው የሥነ-ጥበብ ሙያተኞች መራብ፣ መጠማት፣ መዘረፍና ከሀገር መሰደድ መንግስትን በእጅጉ ሊያሳስበውና ሊያነቃው ይገባል። ፈላስፋው ኦሻ እንደሚለው ደግሞ ‹‹ከልብ ካዳመጣችሁት የውሻ ጩኸትም የቡድሀ ጥሪ ሊሆን ይችላል። ከልብ ካላደመጣችሁ ግን የቡድሀ ጥሪም የውሻ ጩኸት ነው።››

መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የአምላካችንን ሕግ አድምጡ። የመስዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል? ይላል እግዚአብሔር … ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንፁ የሥራችሁንም ክፋት ከዐይኔ ፊት አስወግዱ። ክፉ ማድረግን ተዉ። መልካም መሥራትንም ተማሩ። ፍርድን ፈልጉ የተገፋውን አድኑ ለደሃ አደጉ ፍረዱለት ስለመበለቲቱም ተሟገቱ››

ት. ኢሳይያስ 1፤10 -18እናንተ ግን በተቃራኒው

እንደሆናችሁ ሚዲያዎች ያወራሉ። የደነደነ ልብ ይዛችሁ ስለምትመሩት ህዝብ ሳትጨነቁ በእግዚአብሔር ቤት ትፎካከራላችሁ።

እኛ’ኮ ከእናንተ የምንጠብቀው ይህንን አይደለም። ዓለማዊ መንግስታችን ሲበድለን፣ ሲጨቁነን፣ ሲያንገላታን መክራችሁና ያገባናል ብላችሁ የልጆቻችንን ለቅሶ ይሰማናል ብላችሁ እንድትቆሙልን፣ መአት ቢመጣ እንድትፀልዮልን በሽታ ቢመጣ እንድታማልዱን እንጅ በየጉባኤው እየተኮራረፋችሁ የሚዲያ ሲሳይ እንድትሆኑ አልነበረም።

ሰየኢትዮጵያ ህዝብ

የውስጡን ችግር የሚፈታለት የሚያስተባብረው አካል እስካገኘ ድረስ ለመተባበር የቆረጠ እንደሆነ በተለያየ አጋጣሚ አስመስክሯል። ይህንን ቢያንስ አሁን እየተባበረበት ባለው የአባይ ግድብ ግንባታ ማየት ይቻላል።

ማስተባበርም ሲባል ቀዳሚውንና ተከታዩን ለይቶ የሚጠቅመውንና ፈጣኑን ዘዴ መስርቶ ‹እባክህ› በማለት ማነሳሳት ነው። የቤትክርስቲያኗ አባቶች በዚህ በኩል እንዴት ናችሁ? በየቤተክርስቲያኑ አጥር የወደቁ ተመፅዋቾችን አንስቶ በማቋቋም፣ የታመሙትን በመርዳት፣ ያዘኑትን በማፅናናት ምን እየተደረገ ነው?

ቤተክርስቲያኗ እንደሀገር መስራት ያለባት ይመስለኛል። አባቶች የሰማኒያ ሚሊየን ህዝብ ኃላፊነት በላያችሁ አለ። የህፃናት መረጃ ያረጋዊያን ማቋቋሚያ እየተባለ ስም ከሚለጠፍላቸው ማኅበራት በዘለለና በገዘፈ መልኩ መንቀሳቀስ ያለበት ይመስለኛል።

አንዳንዶችን የሚያስቆጣ፣ አንዳንዶችን የሚያስደስት፣ ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ፎቶግራፍ ከመስቀልና ሐውልት ከማቆም በፊት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ።

እርግጥ እያነሳኋቸው ያሉ ጉዳዮችን የቤተክርስቲያኗ ኃላፊነቶች አይደሉም የሚል ተራ መከራከሪያ ሊነሳ ይችላል። እንዲሁም በግርድፉ ስናየው የመንግስት ብቻ ኃላፊነቶች ይመስሉ ይሆናል። እኔ ግን እላለሁ ያነሳኋቸው ነገሮች ከማንም በፊት የቤተክርስቲያን ኃላፊነቶች ናቸው። አዎ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ኃላፊነት!

ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ኗ የምታስተምረው ‹‹ተርቤ ነበር አበላችሁኝን ተጠምቼ ነበር አጠጣችሁኝን ታስሬ ነበር ጎበኛችሁኝን (ማቴ 25 - 15) ትምህርቶች ሁሉ ቃላዊ ሆነው የትም እናገኛቸዋለን። ተግባራዊ ሆነው ግን በዚች ቤተክርስቲያን ማግኘት አለብን።

ትናንትና አንድ የራበው የኔቢጤ የቤተክርስቲያን አጥር ተደግፎ ሲያንቀላፋ ስላላስተዋልነው

ዛሬ ዛሬ በየቤተክርስቲያኑ የኔ ቢጤዎች ሲርመሰመሱ ብናይ አልገርመን አለ። ትናንትና ምዕመናን ስለሚያቀርቡት መክለፍት እና መሀራ ግልጥ ያለ ደንብ ስላላወጣን ጠላና አረቂ ብሎም ቢራ (አሁን አሁን ደግሞ እንደምንሰማው ጉቦ) መጠየቅ ሲታይ አላስደነግጠን አለ።

የነፍስ አባት ለመሆን የምዕመኑን የገቢ መጠን የሚያጣሩ ካህናት እንዳሉ ሰምተን አናውቅምን? በመንግስት መስሪያ ቤት አካባቢ እያየነው የሚቀፈን የብሔር ጉዳይ የሚያነሱ እንዳሉ አልሰማንምን?

እኒህና እኒህን የመሰሉ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ሲገባ ተቀጥላ ለሆኑ ተግባራት ቅድሚያ ሲሰጥ ማየት ደስታ አያጭርም።

ሀገራዊ ማንነትንና አንድነትን ብሎም የጋራ መገለጫን መገንባት የሚቻለው በእምነትና በእውነት ነው። እምነትም እውነትም የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮዎች ናቸው። ከእነዚህ ትምህርቶች የሚጣረሱ ተግባራት ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ በቅለው ሲገኙ ያስቆጫል። ማንነትን አስመልክቶ ቅርሶች ነዋየ ቅዱሳት ጠፉ፣ ተሸጡ፣ ተመዘበሩ ወዘተ ይባላል። ከእነዚህ ችግሮች ፊት ግን የቤተክርስቲያኗን ምስጢር የሚያውቁ አገልጋይ ካህናት ይገኛሉ። እርግጥ ነው ሰው ናቸውና የስጋ ፍላጎት ያሸንፋቸው ይሆናል። እንዲህ ዓይነት ነገር ሲደጋገም ግን አዳዲስ ዘዴዎችን እየቀየሱ መቆጣጠር መልካም ነው። ቅርስ ከተሸጠ በኋላ የዘራፊው በእስር መቀጣት ቅርሱን እንደገና አይፈጥረውም። ቅርስን ሊያስጠብቅ የሚችል አሰራርና ሥነ-ምግባር መገንባት ጥሩ ነው እላለሁ።

አንድነትን አስመልክቶ አሁን አሁን አዲስ ፈሊጥ ይመስል የዜጎችን ጆሮ የሚያደነቁሩ ከህግም ከእምነትም የወጡ ነጋዴዎች የቤተክርስቲያኗን መዝሙርና ስብከቶች አስፓልት ላይ እያስጮኹ ይሸጣሉ። ይህ የተጧጧፈ ንግድ በብዙ መልኩ ፀያፍ እንደመሆኑ ቤተክርስቲያኗ ቁርጥ ያለና የመረረ ውሳኔ መወሰን አለባት። ያን ጊዜ የከተማ ፖሊሶችም እንዳሁኑ ቸል የሚሏቸው አይመስለኝም። ዳሩ ከቤተክርስቲያን ጠንካራ ተቃውሞ ስላልገጠማቸው የህግ ሰዎችም አልተቃወሟቸውም።

አሁንም፡- በየቦታው የጉዞና የጉብኝት ማስታወቂያዎች ይሰጣሉ። እነዚህን መርሀ-ግብሮች የሚያዘጋጇቸው ደግሞ መንፈሳዊ የሚመስሉ የንግድ ማኀበራት ናቸው። እነዚህን ለመቆጣጠር ምን እየተደረገ ነው? የፈለገ አካል በመንፈሳዊ ማኅበር ስም በአገልጋይ ስም እየተደራጀ ህጋዊ የሚመስል ሸማ እየለበሰ ሲኖር የአባቶች ቁጥጥር ምን ይመስላል? ቤተክርስቲያኗን ብሎም ህዝቡን ችግር ላይ የሚጥል ጥገኛ ማኅበር እንዳልሆነስ በምን ክትትል አየተደረገ ነው?

እንግዲህ ከዚህ በላይ የዘረዘርኳቸው በሙሉ ለአባቶች ያነሳኋቸው ጥያቄዎች ናቸው። ለሁሉም አዎንታዊና ተግባራዊ ምላሽ ቢሰጥ እወዳለሁ።

የተነሳሁበትን ሐሳብ ስደግመው፡- ቤተክርስቲያኗና አባቶች የዚህ ህዝብ ባለአደራዎች ናቸው። ምዕመናንና ህዝቦች ደግሞ ለቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት አለባቸውና ይህንን ሁሉ ፃፍኩ። ግና ስለመደመጤና አለመደመጤ አሁንም እሰጋለሁ።

‹‹እየተደረበ ሁለት ሰው ባንድ አካል

አንደበቱ ሲምል ልቦናው ይከዳል።››

ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ቸር ያሰንብተን!

‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄዎች...

ምክክር ለሥነ-ጥበብ...

ጥያቄዎች ...