more final aids day report

23
የየየየየየየ የየየ የየ የ / የየየ / የየ የየ የየየየየ የየ የየየየየ የየ የየየየየ የየየየ የየ የየ የ የየየየ የየ የየየየ የየየ የየየየ የየየየየየየ የየየየየ የየየ የየየየ የየ የየየየ የየየየየ የየ የየ የየ የየየየ የየየየየየየ የየየየየየ የየየየየየ የየየ የየየየየ የየየ የየ የየየ የየየየ የየየየየ የየየየየየየየ የየየ የየየየ የየየየየየየየ የየ የየ የ /የየየ የየየየየ የየ የየየየየየየየየ የየየ የየ የየየየየ የየየየየየ የየየየ የየየ የየየየየ የየየ የየ የ የየየ የየየየየ የየየ የየ የየየየየ የየየየ የየየየየ የየየየ የየየ የየ የየየየየ የየየየየ የየ የየ የየ /የየየ የየየየየ የ የየየየየ የየ የየየየየየ የየየ የየየየ የየየየየየየ የየየ የየየየየ የየየየ የየየየየየ የየየየየየ የየየየየ የ 1998 .የ የየየ የየየ የየየየየ የየ የየየየየየ የየየየየ የየየየ የየየ የየየ የየየየ የየ የየ የየየየ

Upload: gudetakuma

Post on 15-Oct-2014

69 views

Category:

Documents


26 download

TRANSCRIPT

Page 1: More Final Aids Day Report

የኮርፖሬሽኑ የኤች አይ ቪ / ኤድስ / ሥራ ቦታ መከታተል እና መቆጣጠር ሥራ አጠቃላይ ሪፖርት

ኤች አይ ቪ በአለም እና በሀገር ደረጃ በልማት እንቅፋትነቱ ተረጋግጦ ሁሉም ሀገሮች እና

የልማት ድርጅቶች ኤች አይ ቪን የልማት እንቅፋታቸው እንዳይሆን ተቀነኝተዉ በጋ ራ መከላከል

ይህው ዛሬ ሶስት አስርት አመቶቸን አስቆጥሯል፡፡ በዚሁ መሠረት ኮርፖሬሽናችን ኤች አይ ቪ /ኤድስ

የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ለይ እንቅፋት እንዳይሆን በሀገር ደረጃ የወጣውን የኤች አይ ቪ

ኤድስ መከላከል ፖሊሲ እና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ የራሱን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመንደፍ

ኤች አይ ቪን / ኤድስ መከላከል ና መቆጣጠር ስራ በተጠናከረ መልኩ በሁሉም የኮርፖሬሽኑ የሥራ

ቦታዎችና የልማት ፕሮጀክቶቹ ሚንስትሪም ለማድረግ ከ 1998 ዓ. ም ጀምሮ ጥረቱ በማድረግ ላይ

ይገኛል፡፡ ከነዚህም ጥረቶች

እስከ አሁን የተሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች

ኮርፖሬሽኑ በሥራ ቦታ ኤች አይ ቪ/ ኤድስን የመከላከል ሥራን የጀመረው በ 1998 ዓ.ም

ከፌደራል HAPCO ባገኘው የ 6 ወር ፈንድ ሲሆን ሥራዉ ም አንድ የመከላከል ፕሮግራም

ሥራ ብቻ ነበር፡፡

ከ1999 በጀት ዓመት ጀምሮ ኮርፖሬሽኑኤች አይ ቪ/ ኤድስን የመከላከል ሥራን በቀሚነት

የበለጠ ለመጠነከር

የኤች አይ ቪ / ኤድስ የኮርፖሬሽኑ ስትራተጂክ ፕላን ውስጥ በመካተት፣ ፕሮግራሙም

3 ቱን ፒለሮች ማለት መከላከል ፣ ማከም፣ እርዳታና መንከባከብ ፕሮግራሞችን በማቀፍ

ሁሉም በጋራ እንዲካሂዱ ተደረገ፡፡

ኮርፖሬሽኑ የ ሥራ ቦታ የኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከልና ማቆጠጠሪያ ፕሮግራም በጽ/ቤት

ደረጃ የሰው ኃይልና በጀት ተመድቦለት ተቋቋመ፡፡

የ ሥራ ቦታ የኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከልና ማቆጠጠሪያ በጽ/ ቤት የኮርፖሬሽኑየኤች አይ

ቪ/ ኤድስ ፖሊሲና የኤድስ ፈንድ መቋቋሚያና አጠቃቀም መመሪያ ሁሉንም ሠራተኛና

ማኔጅመንትን ባሳተፈ መልኩ አዘጋጅቶ በማደደቅ ተግባር ላይ አውሏል፡፡

በዋና መ/ ቤት ፀረ ኤች አይ ቪ /ኤድስ/ ግብሀይል እና በሪጅን ጽ/ ቤቶች ፀረ ኤች አይ ቪ

/ኤድስ/ ኮሚቴ ተመሥርቷል፡፡

ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች አስፈላጊና ወቅታዊ የኤች አይ ቪ / ኤድስ መረጃ የሚያገኙበ ት አንድ

የኤድስ መረጃ ማዕከል /AIDS Resource Center/ በኮርፖሬሽኑ ደረጃ በሜክሲኮ

ተቋቁሞ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ማዕከሉን በ ብሮድ ባንድ እንተርኔትና

መድሓፍት ቤት ጭምር የበለጠ ለመጠናከር ቅድመ ሁኔታዎች ተጠናቋል፡፡

በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የምክርና ደም ምርመራ ማዕከል በኮርፖሬሽኑ ክሊኒክ ውስጥ

ተከፍቶ አገልግሎት ከ መስጠት ጎን ለጎን በተለያዩ ኮርፖሬሽኑሪጅንና ፐሮጅክተ ጽ/ቤቶች

Page 2: More Final Aids Day Report

በዘመቻ መልክ ተን ቀስቃሽ VCT መመርያ መኪናና የጤና በለሙያዎችን በመዉስድ፡

በዘመቸ መልክ የአቻ ለአቻ አስተማሪዎች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን

በአርአያነት/ ሞዴልነት በይፋ እንዲመረመሩ ከ መጠቀም በተጨማሪ ሁለት ኮፒ ያለውን ልዩ

ካርዶች በማዘጋጀትና ለ ሠራተኛው ካርዱን በመሰረጨት ኮርፖሬሽኑ የዱቤ ሕክምና

ኮንትራት አብሮ ከተፈራረማቸው የግልና የመንግስት የህክምና ድርጅቶች ወደ ሚቀርበው

ጤና ተቋም ሄደው አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታውን በማመቻቸት በአዲስ አበበ ከ 1200

በአጠቃላይ ከ 3000 በለይ ሰራተኞች እስከሁን የVCT ተጠቃሚ ሆኖዋል

II. የኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከልና መቆጠጠር ሥራ ባልተማከለ ሁኔታ በሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሥራ

ቦታዎችና የልማት ፕሮጄክቶች ዉስጥ ሜኒስትሪም በማድረግ በተጠናከረ መልኩ መምራት እንዲችሉ

ከ 120 በለይ ለሚሆኑ የማንጅመንት አባላትና የሥራ ኃላፊዎች በኤች አይ ቪ/ኤድስ

ሜኒስትሪሚንግ ክትትልና ግምገማ ላይ ሥልጠና ተሰጥቷል፡

ከሁሉም የኮርፖሬሽኑ የስራ ክፍሎ ለተመረጡ ከ 750 በላይ ለሚሆኑ ች የኤች አይ ቪ/ኤድስ

የአቻ ለአቻ አስተማሪዎች ስልጠና በማሰጠት አንድ ሠልጣኝ ለ 20 ሠራተኞች በየወሩ ለአንድ

ቀን ለአንድ የሥራ ሰዓት እንዲያስተምር ተደርጓል፡፡

በኮርፖሬሽን ደረጃ የሚሠጠውን የአቻ ትምህርት ወጥነት እንዲኖረው ለ ማድረግ የማስተማሪያ

መፅሀፍት እና በፍሊፕ ቻርት ላይ የዓመት ትምህርት ርዕሶችን በማዘጋጀት ለአቻ አስተማሪዎች

እና ሥራ ክፍሎች ታድሏል

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በሥራ አካባቢያቸው በቀላሉ የኤች አይ ቪ/ ኤድስ ትትምህር እንድያገኙ

አስራ አንድ ባለ 28 ኢንች ቴሌቪዢን እና ዴኮች ተገዝተው ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ ክበቦችና

ክሊኒክ ለሠራተኛ ማስተማሪያነት እንዲጠቀሙ ተሠራጭቷል፡፡ የሚሰጠዉን ትምህርት አዝነኝና

ሳቢ ለማድረግ ድራማዎችና መረጃዎች በቪዲዮ ካሴቶች ተዘጋጅቶ ይሠራጫል፡፡

የተለያዩ ከ 20 ዓይነት በለይ የ IEC/BCC የትምህርትና ባህሪ የግንኙነት ቁሳቁሶች

… በራሪ ወረቀቶች መጽሔቶች፣ ፖስቸሮች፣ የመኪና ስኒከሮች ወዘተ በኮርፖሬሽን ደረጃ

ተዘጋጅቶ ለሁሉም የሥራ ቦታዎች 500፣000 ኮፒዎች ተሰራጭቷል፡፡ከ 50 የሚበልጡ

ቋሚ ባነሮች በተለያዩ የኮርፖሬሽኑ ሥራ ቦታዎች ተሰቅሎዋል

ኮንዶም በሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሥራ ቦታዎች በቋሚነት የምቀርብ ሲሆን፣ በአጠቀለይ ከ

3ሚሊዮን ኮንዶም በለይ ተሰረጭተዋል ፡፡ አቅርቦቱንና ሲርጥቱን የበለጠ ለማጠናከር

ከዲኬቲ ኢትዮጵያ ጋር ለሁሉም ሪጅንና ፕሮጄክት ጽ/ ቤቶች በሚፈልጉት መጠን እና

ግዜ እንዲያቀርብ ኮንትራት ተፈራርመን እያቀረበ ሲሆን ፡፡ በሚሰራጭበት ቦታም

ጥራቱንና ውበቱን ለመጠበቅ አዲስ 150 የ ኮንዶም መሰራጫ ሣጥን አሰርተን

ለሁሉም ሥራ ክፍሎች አሰረጭተነል ፡፡

V. ዕርዳታና እንክብካቤን በተመለከተ

Page 3: More Final Aids Day Report

በአሁኑ ወቅት ወደ 200 የሚጠጉ በኤች አይ ቪ በደማቸዉ ዉሰጥ የሚገኝ

ሠራተኞች፣ ቤተሰቦቻቸዉና በበሽታው ምክንያት ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆች ከኤድስ

ፈንድ ዕርዳታ እያገኙ ነዉ፡፡

የኮርፖሬሽኑ የኤድስ ፈንድ ለዕርዳታ እና ለዕንክብካቤ ሥራ ብቻ የሚዉል በመሆኑ

ከሌሎች መሠል ድርጅቶች ኤድስ ፈንድ የተለየ የሚያደርገዋል፣፣

በፕሮጅክት አከባቢ የተሰሩ ኤች አይ ቪ ሚንስትሪሚንግ

ኮርፖሬሽኑ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ከ ወርልድ ለርኒን ኢትዮጴያ ከሚባል መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት

ጋር ከ 2001 ዓ. ም ጀምሮ በአምስት ትላልቅ የሀይድሮ ኤሌትሪክ ግንባታ ፕሮጀክቶች ባለትም ተከዜ,

በለስ , ፊንጫ , ግልገል ጊቤ 2 እና 3 በጥናቱ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ኤች አይ ቪ/ኤድስ/

መከላከል ሥራ በ 6334 የኮንትራት ሠራተኞች ለ 22667 የአካባቢ ህብረተሰብ ነዋሪዎች፣እና 540

በንግዱ ምክንያት የሚሳቡ ወጠት ሴቶች ያቀፈ እየሠራን እንገኛለን፡፡በ 3 ፕሮጀክቶች ለ አይ ቪ/ኤድስ

የተገለጡ ወጠት ሴቶች ማለት በ ፊንጫ ሀመርቲ ነሼ 15ሴቶች ለ አይ ቪ/ ኤድስ የተገለጡ ወጠት

ሴቶች ፡ በለስ 15ሴቶች እና በ ጊቤ ሦስት 10ወጠት ሴቶች/ቄሮዎችን በመደረጀት በዘለቂነት

መቀቀሚያ እነድሆነቸዉ ለየአንደነደቸዉ 5000ብር በአጠቃለይ 200000ብር ተሰጥቸዋል፣፣

VI.

የኤች አይ ቪ / ኤድስ ጥ ና ቶች

ከሁሉም በላይ የኮርፖሬሽኑ ጠንካራ ጎን ማንኛውም አዲስ ሥራ ለመጀመርም ሆነ ነባርን ለማሻሻል

ጥናትን መሠረት ያደርጋል ፡፡ በመሆኑም

በኮርፖሬሽኑ ውስጥ ኤች አይ ቪ ኤድስን አስመልክቶ በአጠቃላይ 6 የተለያዩ

ጥናቶች የተካሄደ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4 ቅድመ ኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከል

ስራን በተመለከተ የተጠኑ ሲሆኑ

አንዱ ጥናት ደግሞ በ አለም ሥራ ድርጅት የ 2 ዓመት የሥረ አፈጻጸም

ውጤት ለመገምገም በ 2001 ዓ. ም የተ ጥና ኤች አይ ቪ ኤድስ ፕሮጄክት

ሥራ አጠቀለይ/የመጨረሻ ገመገመ ስሆን ፣፣ በወጣው አጠቃላይ በጥናት

ሪፖርቱ ላይ ድርጅቶ አብሮ ከሚሠራቸው 14 ድርጅቶች ውስጥ ኤች አይ

ቪን ሚንስትሪም በማድረጉ ረገድ ኮርፖሬሽኑ አንደኛ አድርገዋል፣፣

ሌላ ዉ ደግሞ የኤች አይ ቪ ኤድስ በተመለከተ የ ሠራተኞ ች ያላቸውን የግንዛቤ

መጠን የአመለካከትና አተገባበር ጥናት/KAP SERVAY/ በ 2002 ዓገዋል.ም

መጨረሻ በኮርፖሬሽኑ የተከሄደ ነበር፡፡

Page 4: More Final Aids Day Report

በዚህ የጥናት ውጤት መሠረት በጥናቱ በተካተቱ ርዕሶች ሁሉ የኮርፖሬሽኑ ሥራ

ካሀገር አቀፍ ማዕከላዊ ውጤት የተሻለ መሆኑንብያሰይም፣ የኮርፖሬሽኑትከረት

የሚሹ

ክፍታቶች ተይቶዋል ፡፡ እነዚህም፣

52% የተዘበ ግንዛቤ በየኤች አይ ቪ ኤድስ መተላለፊያና መከላከያ መንገድ

አለቸው፣

48% በኤች አይ ቪ ኤድስ ለይ አጠቀለይ/የተስተከከለ እዉቀት አለቸው፣

42.7 % ሠራተኞች ብቻ የተስተከከለ አመለከከት ስለ ኤች አይ ቪ/ኤድስ አለቸው፣፣

የኤች አይ ቪ ኤድስ ሥራ በአንድ ስራ ኃላፊዎች ዘንድ እንደተጨማሪ ሥራ መታየቱ፣

በ 2003 ዕቅድ እነዚህንየታዩ ክፍተቶች ለመሙላትና ሥራዉን የበለጠ ለመጠነከር

የሚከተሉት ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ እነዚህም፡-

የኤችአይቪ/ኤድስ ጥናት ውጤቶችን እና አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል ሥራ

ወደፊት የሚጠናከርበት ሁኔታ ለይ ከሪጅንና ከፕሮጀክት ጽ/ቤቶች የሰው ኃይል አስተዳደር ኦፊሰሮችንና

የፕሮጀክት ኃላፊዎችን እንዲሁም ሌሎችም ሁኔታዉ የሚመለከታቸውን አካላት ያሰተፈ ሁለት አውደ

ጥናቶችን በማከሄድ በጋራ ውይይትና ስምምነት የሚከተሉት ስራዎች ተሰርቶአል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የ 3 ዓመት እስትራቴጂክ

ዕቅድ ተዘጋጅቶአል፡፡

በእስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በመመስረት የሪጅን ጽ/ቤቶችና ሌሎች ዋና የስራ ክፍሎች ወደ ስራ

ቦታቸው ሲመለሱ የስራዉን የበለጠ ለመጠነከር የሚያስችላቸውን እስትራቴጂ፣ አመታዊ

የስራ እቅድና በጀት እንዲያዘጋጁና ሥራውን በባለቤት የሚመራ አንድ የኤችአይቪ/ኤድስ ፎካል

ሠራተኛ እንዲመደቡ ተደርጎአል፡፡

ከሁሉም ሪጅኖችና ከፕሮጀክቶች ጽ/ቤቶች ለተወጠጡ 148 አቻ ለአቻ አስተማሪዎችና

ሠራተኞችን በየፋ ለማስተማር ፍቃደኛ ለሆነ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ሰራተኞች

የአቻ ለአቻ አስተማሪዎች መጠነከሪያ ስልጠና ሰጥተናል፡፡

ከሁሉም ሪጅኖችና ፕሮጀክት ጽ/ቤቶች ለተመረጡ 20 ሠራተኞች የአቻ ለአቻ የአሰልጣኞች

ስልጠና ተሰጥቶአል፡፡

Page 5: More Final Aids Day Report

ለ 51 የሪጅንና የፕሮጀክት ጽ/ቤቶች የሰው ኃይል ኦፊሰሮችና የስራ ኃላፊዎች የመጠነከሪያ

ስልጠና በኤችአይቪ/ ኤድስ ሜይኒስትሪሚንግ የከትትልና ግምገመ ለይ ሰጥተናል፡፡

በDKT ለሁሉም የኮርፖሬሽኑ ዋናዋና የስራ ቦታዎች እንዲያደርስ በተደረገው ስምምነት

መሰረት 550,000 ኮንዶም ተገዝቶ ለሁሉም ቢሮዎች ተሰራጭቶአል፡፡

በቅርቡም የሪጅን ቢሮዎችን የአሰራር ሁኔታ ክትትል አድርጎ በመገምገም በተሻለና በተጠናከረ

ሁኔታ የአቻ ለአቻ ትምህርትን በዘመቻ መልክ የዓመቱን ትምህርት በ 6 ወር ቫይረሱ

በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ፍቃደኛ ሠራተኞችንና ሌሎችን ጠንካራ የአቻ አስተማሪዎችን

በማሳተፍ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በአራት የአዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤቶች በሙከራ

ደረጃ የተሰራ ሲሆን ይህንን ውጤታማ ስራ በቀጣይነት በሁሉም የስራ ክፍሎች ፕሮግራሙን

ለማካሄድ ዝግጅት እተደረገ ነው፡፡

የታዩ ለውጦች / መሻሻሎች

አንድ ፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ሥራ ውጤት ለመለካት ብዙ ጊዜ የሚወስድና የተገኘ

የሥራ ውጤቱም ብሆን የብዙ ድርጅቶች የሥራ ድርሸ የለበት በመሆኑ በትክክል

ለመለካት ችግር ያለባቸው መሆኑ እርግጥ ቢሆንም

የኮርፖሬሽኑ ኤች አይ ቪ ኤድስ የሥራ ቦታ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም ጥሩ

ዉጤት እያስመዘገበ መሆኑን ወይም ጥሩ የባህሪ ለውጥ በኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች

በኩል መታየቱን ከሚከተለው ሁኔታ ማየት ይቻላል፡፡

1. የኮንዶም ስርጭት መጨመር ለኮንዶም በይፋ ጥያቄ መቅረብ የሀላፊ

ጠረጴዛ ላይ ለማስቀመጥ ፍቃደኛ መሆን

2. በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የምክርና የደም ምርመራ አገልግሎት በሞባል

የቪሲቲ መኪና ሲሰጥ ሠራተኛው በረጅሙ ተሰልፎ ተራውን ጠብቆ በትዕግስት መቆሙ

Page 6: More Final Aids Day Report

3. ሠራተኛው ራሱ ከተመረመረ በኃላ ቤተሰቡ ሳይመረመር የምርመራ መኪና

እንዳይወጣብን ብሎ መኪና ፊት ቆሞመኪናውን መከልከል በተለይ በአዲስ አበባ

ኮተቤ ጋራጅ ዘንድ ታይቷል

4. ለኤች አይ ቪ ኤድስ በጎ ሥራ ወይም በሽተኛን በነፃ ለመገልገል በፈቃደኝነት

ጠይቆ ለማገልገል መዝግቡኝ ብሎ መጠየቅ

5. በኤድስ ምክንያት ወላጅ አልባ ልጆችና በሽተኞች የራሳቸውን ገንዘብ

በፍቃደኝነት ሰብስበው በጉሩብ ሄዶ መጠየቅ

6. ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ሠራተኞች በኛ ይብቃ ትውልድ

ይዳን ብለው በይፋ ወጥተው ሠራተኛን ለማስተማር

ፍቃደኛ መሆናቸው ከብዙዎቹ መለኪያዎች ጥቂቶቹ ከላይ በተገለጸው መልክ መታየቱ

የሥራችን ዉጤት ፍሬ እያፈራ መሆኑን ያሳያል፡፡

7.በ 2002 ዓ. ም የአለም ሥራ ድርጅት የ 2 ዓመት የሥረ አፈጻጸም የጥናት

ውጤት ላይ ተመሥርቶ በወጣው አጠቃላይ በጥናት ሪፖርቱ ላይ ድርጅቶ አብሮ

ከሚሠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ኤች አይ ቪን ሚንስትሪም በማድረጉ ረገድ ኮርፖሬሽኑ

አንደኛ አድርጓል

8. የኢትዮጴያ የንግድ ድርጅቶች ጥምረት ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር

ባዘጋጀው ዓመታ የልምድ ልውውጥ ላይ በመሳተፍ በ 2002 ዓ. ም ከ 53 ንግስታዊ እና

መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተወዳድረን በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነናል፡፡

9.በ 2003 ዓ. ም በኤች አይ ቪ በስራ ቦታ ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ድርጅቶች

ውስጥ ፌደራል ኤች አይ ቪ /ኤድስ/መ/መ/ፅ/ ቤት በጥሩ የስራ ልምዳቸውን ለሌሎች

ድርጅቶች በሚዲያ መተላለፍ አለባቸው ብሎ በመምረጥ ሥራቸዉ በሚዲያእያተለለፈ

ከአለዉ አራት ድርጅቶች መካከ ል አንዱ መሆን ችለናል፣፣

እነዚህን ለውጦች ስናስመዘግብ ግን ብቻችንን አይደለም የተለያዩ አጋር ድርጅቶች

በተለያየ ጊዜና መጠን የበኩላቸውን ዕርዳታ አድርገውልናል ከነዚህ ውስጥ

ፌደራል ኤች አይ ቪ መ/መ/ጽ/ ቤት የአንበሳውን ድርሻ ሲወስድ ሌሎቹ ደግሞ

የአለም ሥራ ድርጅት፣ ወርልድ ለርኒንግ ኢትዮጴያ፣ ሀብት አሶሴሽን፣ አዲስ አበባ ሀብኮ፣

ኦሳ፣ የኢትዮጴያ ማህበር ኮንፌዴሬሽን፣ ሲዲሲ ኢትዮጴያ እና ሌሎችም

Page 7: More Final Aids Day Report

የዋና ሥራ አስፈጻሚው ንግግር

ኤችአይቪ/ኤድስ በአለም አቀፍ ደረጃ በሰለጠኑትንና የሥራ ልምድ የካበቱ አምራች ኃይልን በከፍተኛ

ደረጃ በመጉዳት እያደረሰ ያለው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ሁሉንም

ሀገሮችና ድርጅቶች በአንድነት የተቀነጃ ዘርፈ ብዙ ምላሽ በመስጠት ወረርሽኙን በጋራ በመመከት

ላይ ይገኛሉ፡፡

ሀገራችንም የህብረቱ አበል በመሆን ለዓለም አቀፉ ኤችአይቪ/ ኤድስ ጥቀት ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዉስጥ

ተ የበኩለዋን ጉልህ ድርሸ በመበርከት ሲሆን በተለይ በለፉት አስርት ዓመት ውስጥ ስር ነቀል በሆነ

ሁኔታ ሁሉንም መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሃይማኖትና ህዝባዊ ድርጅቶችን

በአጠቃላይ ሁሉንም ዜጎች ባሳተፈና ባስተባበረ መልኩ የተቀናጀ ዘርፈ ብዙ ምላሽ በመተግበር

በዓለም ደረጃ አመርቂነቱ የተመሰከረበት ውጤት በኤችአይቪ/ ኤድስ ለይ ማስመዝገብ ችለሌች፡፡

በዚህ የተቀናጀ አገር አቀፍ ፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ ውስጥ ኮርፖሬሽናችንም ከዛሬ 6 ዓመት

(1998) ጀምሮ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት በማቋቋም ሁሉን አቀፍ

(Comprehensive) የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ሥራ በሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሥራ

ቦታዎች በማተግበር በብሔራዊ ደረጃ ሀገራችን በዘርፉ ላስቀመጠችው ግብ መሳካት የበኩሉን ሁሉ

ለማበርከት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የሥራ ቦታ ሁለንተናዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ሥራ እያተገበረ ያለው

በሁለት የተያያዙና የማይነጣጠሉ ዓላማዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን፡፡ እነሱም፡-

1. የኮርፖሬሽኑን የሰው ኃይል ከኤችአይቪ/ኤድስ ጥቃትና ተጽእኖ ነፃ በማድረግ

2. ኮርፖሬሽኑ እያካሄደ ለአለው ፈጣንና ዘላቂ የልማት ግቦች ለይ ከኤችአይቪ/ኤድስ እንቅፈት

እንዳይሆን መጠበቅ ናቸዉ፡፡

እነዚህን ሁለት ዓላማዎች ለማሳካት ኮርፖሬሽኑ ኤችአይቪ/ኤድስን እንደ አንድ ዋና የልማት ስራ

በኮርፖሬሽኑ የልማት አጀንዳ ውስጥ በማቀፍ ከ ልማቱ ጋር በጣምራ መተግበር አለበት፡፡ በመሆኑም

ኤችአይቪ/ ኤድስን ኮርፖሬሽኑ በእስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ በማካተት በጀትና የሰው ኃይል መድቦለት

እንደማንኛውም የኮርፖሬሽኑ መደበኛ ሥራ የሪፖርትና የግምገማ ሲስተም ውስጥ እንዲታቀፍ የተደርገ

ቢሆንም ይህ ሁኔታ ግን በሁሉም የኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍሎችና የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ

በተፈለገው መጠን ያልተጠናከረ ስለሆነ ለወደፊቱ በሚገባ የሚጠናከርበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

Page 8: More Final Aids Day Report

ኤችአይቪ/ኤድስን በሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሥራ ቦታዎችና የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ በሚገባ

ሜኒስትሪም የማድረጉ ጉዳይ በዘሬዉ እያከበርነው ከለው የዓለም ኤድስ ቀን በዓል መሪ ቃል

(መፈክር) ማለትም፡-

"አንድም ሰው በኤችአይቪ እንዳይያዝ ኃላፊነታችንን እንወጣ" ከሚለዉ ጋር

ከዚህ በተጨማሪም በቅርቡ ሀገራችን ያስተናገደችው የ ICASA 16 ኛ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት

በኤችአይቪ/ኤድስ፣ በሳንባ ነቀርሳና አባላዘር በሽታዎች ላይ ሲሆን፣፣ ዋና ዓላማውም "አፍሪካ

የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራምን በባለቤትነት ትምራ፣ ሥራውን ታስፋፋ/ ታሳድግ፣ የፕሮግራሙን

ዘላቂነትም ታረጋግጥ የሚል ነው፡፡"

ስለዚህ እነዚህ ማሪ ቃሎች ያዘሉት ቁም ነገሮች ለአፍሪካ፣ ለኢትዮጵያና ለኮርፖሬሽናችንም ቢሆን

የወደፊት የኤችአይቪ/ኤድስ ስራን በባለቤትነት ከመደበኛ ሥራ እኩል ተገቢ ትኩረት ሰጥተነው

ዘላቂነት ባለው መልኩ መስራት እንዳለብን በማያሻማ ሁኔታ ኃላፊነት የጣለብን መሆኑን መረዳት

ይቻላል፡፡

በአጠቃለይ አገራችን ብሎም ኮርፖሬሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ የኤችአይቪ/ኤድስ

ግቦችን ማለትም እ.ኤ.አ. በ 2025:-

በኤችአይቪ/ኤድስ የመያዝ ዕጣ ዜሮ ማድረግ፣

አድሎና ማግለልን ዜሮ ማድረግ /ማጥፋት፣

በኤችአይቪ/ ኤድስ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚከሰት ሞትን ዜሮ በማድረግ

በአጠቃለይ በዓለም አቀፍ ደረጀ እቅዱን ለማሳካት የሚደረግ ዘመቻም ሆና በተለይም በሀገራችን

ደረጃ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ኮርፖሬሽኑ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ጠንክሮ ይሰራል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ኤችአይቪን በሁሉም የኮርፖሬሽኑ የሥራ ቦታዎችና የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ

በሚገባ ሜኒስትሪም በማድረግና የተቀናጀ ሥራ ሰርተን አንድም ሰው በኤችአይቪ እንዳይያዝ

ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ሁሉንም የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራሮች በድጋሚ እጠይቃለሁ፡፡

አመሰግናለሁ

Page 9: More Final Aids Day Report

የ2004/2011 የአለም ኤድስ ቀን በአል

አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ቦታ ኤች አይ ቪ /ኤድስ/ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ጽ/ ቤት ሪፖርት

አቅራቢ ፡- አቶ አህመድ በዳሶ

ታህሳስ2003 ዓ.ም/2011/