ጋዜጣው፡- (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡...

16
ጋዜጣው፡- • መንግሥት የተመሠረተበትን ሕዝብ፣ • እግዚአብሔር የተገለጠበትን ወገን፣ • ከተማይቱን — የተፈጸመውን ሕዝብ፣ • እግዚአብሔር ሰውን — ራስንና አካልን፤ • ልጅነትን—እግዚአብሔርን መኖር፣ • የልጅነት መገለጥ — የሁሉ መዳንን፣ • የሰው(ነት) መጥፋት፣ • በሕይወት ጋልቦ ስለሚሞተው ሞት፣ .... ይገልጣል <<መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች>> (መዝ.103.19) ‹‹እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው›› (1ጢሞ. 3፡16) (ምዕራፍ1 ቁ.10) ኅዳር 2006 የምሕረት ዓመት፡፡ ልጅነት ማንነት ነው - ባሕሪይ፡፡ ልጅነት ይተረጎማል - በሕይወት፡፡ ልጅነት አባትን በራስ ላይ ከማንም በላይ ያተልቃል - የሕልውናውና የእንቅስቃሴው ሕግ ያደርጋል፡፡ ልጅነት ሁል ጊዜ - የትም - በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ይሰጣል፡፡ ልጅ ‹‹የራሱ ፈቃድ›› የለውምና! ልጅነት ለእግዚአብሔር ሕያውና ደስታው ለሆነው ፈቃዱ ተወልዶ ይኖራል፤ በዚህ ሁኔታ ለኃጢአት ሞቶ ወደ አባትነት ይገባል፡፡ ልጅነት ማትረፊያ ወይም የነፍስ ራዕይ ማስፈጸሚያ አይደለም፡፡ የልጅነት ‹‹አገልግሎት›› የታናሽነት፣ የትኅትና አገልግሎት ነው፡፡ ልጅ ባገለገለ መጠን ወደ ሞት ይመጣል - ለመሰቀል ያገለግላል፡፡ ልጅነት የሚቃጠልበትን እንጨትና የሚሰቀልበትን መስቀል እስኪሸከም ለአብ ፈቃድ የሞተ ነው - ይሄ ማንነት በዚያው ላይ አልቆ ወደ አባቱ ይጨሳል፡፡ ልጅነት ሲጨስ የአብ መቅደስ የክብሩ ጢስ ይሞላበታል፡፡ ልጅ… በተአምር አይኖርም፡፡ እግዚአብሔር ግን በእርሱ ይኖራል፡፡ ልጅነት የነፍስን ጉልበት የጨረሰ አይደለምን? በልጅነት አትነግሡም ታገለግላላችሁ እንጂ፡፡ ልጅነት አብ በሁሉ እስኪሞላ የአብን ሥራ ብቻ ይሠራል፡፡ (ካለፈው የቀጠለ) ልዩ ዕትማችን - ከመጽሔቱ በኋላ እንደ ገና በዚህ ጋዜጣ ተገናኝተናል፡፡ የመጽሔቱ አስተያየታችሁን ግን አልሰማንም መጽሔቱ ስናዘጋጅ የመጀመሪያ እንደ መሆኑ አስተያየታችሁን ጠብቀን ነበር፡፡ … እንግዲህ በተዋወቅንበት በዚሁ ጋዜጣ እንቀጥል፡፡ ‹‹መጽሐፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው…›› (ራእ.20÷12)፡፡ በአንድ በኩል (ብዙ) መጻሕፍት ተከፈቱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ (አንድ) መጽሐፍ ተከፈተ፡፡ መጽሐፍት በተከፈቱ ጊዜ የተነበበው ‹‹የሙታን ሥራ›› ነው፡፡ መጽሐፍ ሲከፈት ግን ሕይወት ነው የተነበበው፤ እርሱ የሕይወት መጽሐፍ ነውና፡፡ በዚህም መጽሐፍ ነው እነዚያ መጻሕፍት የተከፈቱትና የተነበቡት፡፡ መጽሐፍ የሰው ሕይወት ነው፡፡ የሰው ሕይወትም በመጽሐፍ ነው፡፡ ማንም ሕይወቱን ‹‹ሌላ መጽሐፍም›› በተባለው ያነበዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ የተዘጋበት ግን ማንነቱን ማንበብ አይችልም፡፡ በዚህም መጽሐፍ የተነበበው - የተገለጠው የሙታን ሥራ በእሳት ባሕር ሊጣራ ይጣላልል፡፡ የተከፈቱት የመጽሐፍትም ሆኑ የተከፈተው ሌላ መጽሐፍ ከሕይወት - ከአካሄድ - ከዘመን ሌላ አይደሉም፡፡ ‹‹ሌላ መጽሐፍ›› ዓለም ያላወቀው የእውነት መንፈስ ነው፡፡ እርሱ የሰውን ሁለንተና ያነባል፡፡ ይመረምራል፡፡ ይወቅሳል፡ ፡ ወደ እውነትም ይመራል፡፡ ሕይወታችን ያ የተከፈተው ‹‹ሌላ መጽሐፍ›› ይሆን ዘንድ በሰማይ ያለ የአብ ፈቃድ ነው፡፡ የሙታንን ሥራ እንገልጣለን፡፡ እነርሱም መጽሐፋቸውን (ሕይወታቸውን) ለመመለስና ለመታደስ ያነቡታል፡፡ ተወቅሰውና ተጸጸተው ይመለሳሉ፡፡ ሕይወታችን - የሕይወት መንፈስ ሕጋችን - መጽሐፋችን በተከፈተና በተነበበ ጊዜ የሚመላለሱበት የሕይወት ብርሃን ይሆንላቸዋል፡፡ በባለፈው ዕትማችን(ቁ.9) ላይ፡- ‹‹የተናገርንበትና የጻፍንበት ዘመን ያልፍና የተናገርነውና የጻፍነው ሁሉ በአብ ሕይወት ኃይል የምናሳይ እንሆናለን፡፡›› ብለናችሁ ነበር፡፡ የደረስንበት ሰማያዊ ስፍራ የሕይወት መንፈስ ሕግ ነው፡፡ እርሱን ስናብለጨልጭ ምድር ሁሉ በብርሃናችን ይመላለሳል፡፡ በሰማያት (ጠፈር) ያሉት ብርሃናት በምድር ላሉት ሁሉ ለምልክቶች - ለዘመኖች - ለዕለታት - ለዓመታት… ይሆናሉ፡፡ ይህንን ሕይወት - ይህንን መጽሐፍ ለመተርጎም አብ ልጆችን ተናጣቂና ኃይለኞች አድርጓቸዋል፡፡ ከእንግዲህ የምንኖረው ኑሮ በግብፅ እንደኖርነው ኑሮ አይደለም፡፡ አሁን የወረስናት ምድር ሁሌም በሰማይና በሰማያዊ ነገር የምትጎበኝ ናት፡፡ የግብፅ ምድር ሜዳ ነው፡፡ ማንም ሊኖርባት ይችላል፡ ይህች ግብፅ ጌታቸው የተሰቀለባት ሶዶም ናት፡ ፡ ሶዶምም በግብፅ ምድር አምሳልናትና (ዘፍ.13÷10)፡፡ በግብፅ ሕይወት (ኑሮ) ቀላል ናት፡፡ ከነዓን (ወተትና ማር የምታፈስሰው ምድር) ግን ሸለቆና ኮረብታማ የበዛባት ሀገር ናት፡፡ በጦርነት - በትግል - በመከራ - በስቃይ… እንጂ በቅምጥልነት አትወረስም፡፡ ለታካቾችና ለሰነፎች - ጌታን ለማይገልጡና ለማያወጡ ለልበ ስውራን የተስፋይቱ ምድር ጨለማ ናት (ዘዳ.11÷10-12)፡፡ መልእክታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰዎች ቢሆንም - ራሳቸውን ‹‹ክርስቲያኖች›› ብለው ለሚጠሩት ቢሆንም የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10

Upload: others

Post on 01-Apr-2020

10 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ጋዜጣው፡-• መንግሥት የተመሠረተበትን ሕዝብ፣

• እግዚአብሔር የተገለጠበትን ወገን፣

• ከተማይቱን — የተፈጸመውን ሕዝብ፣

• እግዚአብሔር ሰውን — ራስንና አካልን፤

• ልጅነትን—እግዚአብሔርን መኖር፣

• የልጅነት መገለጥ — የሁሉ መዳንን፣

• የሰው(ነት) መጥፋት፣

• በሕይወት ጋልቦ ስለሚሞተው ሞት፣

.... ይገልጣል

<<መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች>> (መዝ.103.19)

‹‹እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው›› (1ጢሞ. 3፡16)

(ምዕራፍ1 ቁ.10) ኅዳር 2006 የምሕረት ዓመት፡፡

የልጅነት አካሄድ የከፍታውም ማለቂያ ልጅነት ማንነት ነው - ባሕሪይ፡፡ ልጅነት ይተረጎማል - በሕይወት፡፡ ልጅነት አባትን በራስ ላይ ከማንም በላይ ያተልቃል - የሕልውናውና የእንቅስቃሴው ሕግ ያደርጋል፡፡ ልጅነት ሁል ጊዜ - የትም - በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ይሰጣል፡፡ ልጅ ‹‹የራሱ ፈቃድ›› የለውምና! ልጅነት ለእግዚአብሔር ሕያውና ደስታው ለሆነው ፈቃዱ ተወልዶ ይኖራል፤ በዚህ ሁኔታ ለኃጢአት ሞቶ ወደ አባትነት ይገባል፡፡ ልጅነት ማትረፊያ ወይም የነፍስ ራዕይ ማስፈጸሚያ አይደለም፡፡ የልጅነት ‹‹አገልግሎት›› የታናሽነት፣ የትኅትና አገልግሎት ነው፡፡ ልጅ ባገለገለ መጠን ወደ ሞት ይመጣል - ለመሰቀል ያገለግላል፡፡ ልጅነት የሚቃጠልበትን እንጨትና የሚሰቀልበትን መስቀል እስኪሸከም ለአብ ፈቃድ የሞተ ነው - ይሄ ማንነት በዚያው ላይ አልቆ ወደ አባቱ ይጨሳል፡፡ ልጅነት ሲጨስ የአብ መቅደስ የክብሩ ጢስ ይሞላበታል፡፡ ልጅ… በተአምር አይኖርም፡፡ እግዚአብሔር ግን በእርሱ ይኖራል፡፡ ልጅነት የነፍስን ጉልበት የጨረሰ አይደለምን? በልጅነት አትነግሡም ታገለግላላችሁ እንጂ፡፡ ልጅነት አብ በሁሉ እስኪሞላ የአብን ሥራ ብቻ ይሠራል፡፡

(ካለፈው የቀጠለ)

ከ ልዩ ዕትማችን - ከመጽሔቱ በኋላ እንደ ገና በዚህ ጋዜጣ ተገናኝተናል፡፡ የመጽሔቱ አስተያየታችሁን ግን አልሰማንም መጽሔቱ ስናዘጋጅ የመጀመሪያ

እንደ መሆኑ አስተያየታችሁን ጠብቀን ነበር፡፡ … እንግዲህ በተዋወቅንበት በዚሁ ጋዜጣ እንቀጥል፡፡

‹‹መጽሐፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው…›› (ራእ.20÷12)፡፡

በአንድ በኩል (ብዙ) መጻሕፍት ተከፈቱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ (አንድ) መጽሐፍ ተከፈተ፡፡ መጽሐፍት በተከፈቱ ጊዜ የተነበበው ‹‹የሙታን ሥራ›› ነው፡፡ መጽሐፍ ሲከፈት ግን ሕይወት ነው የተነበበው፤ እርሱ የሕይወት መጽሐፍ ነውና፡፡ በዚህም መጽሐፍ ነው እነዚያ መጻሕፍት የተከፈቱትና የተነበቡት፡፡ መጽሐፍ የሰው ሕይወት ነው፡፡ የሰው ሕይወትም በመጽሐፍ ነው፡፡ ማንም ሕይወቱን ‹‹ሌላ መጽሐፍም›› በተባለው ያነበዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ የተዘጋበት ግን ማንነቱን ማንበብ አይችልም፡፡ በዚህም መጽሐፍ የተነበበው - የተገለጠው የሙታን ሥራ በእሳት ባሕር ሊጣራ ይጣላልል፡፡ የተከፈቱት የመጽሐፍትም ሆኑ የተከፈተው ሌላ መጽሐፍ ከሕይወት - ከአካሄድ - ከዘመን ሌላ አይደሉም፡፡ ‹‹ሌላ መጽሐፍ›› ዓለም ያላወቀው የእውነት መንፈስ ነው፡፡ እርሱ የሰውን ሁለንተና ያነባል፡፡ ይመረምራል፡፡ ይወቅሳል፡፡ ወደ እውነትም ይመራል፡፡

ሕይወታችን ያ የተከፈተው ‹‹ሌላ መጽሐፍ›› ይሆን ዘንድ በሰማይ ያለ የአብ ፈቃድ ነው፡፡ የሙታንን ሥራ

እንገልጣለን፡፡ እነርሱም መጽሐፋቸውን (ሕይወታቸውን) ለመመለስና ለመታደስ ያነቡታል፡፡ ተወቅሰውና ተጸጸተው ይመለሳሉ፡፡ ሕይወታችን - የሕይወት መንፈስ ሕጋችን - መጽሐፋችን በተከፈተና በተነበበ ጊዜ የሚመላለሱበት የሕይወት ብርሃን ይሆንላቸዋል፡፡ በባለፈው ዕትማችን(ቁ.9) ላይ፡- ‹‹የተናገርንበትና የጻፍንበት ዘመን ያልፍና የተናገርነውና የጻፍነው ሁሉ በአብ ሕይወት ኃይል የምናሳይ እንሆናለን፡፡›› ብለናችሁ ነበር፡፡ የደረስንበት ሰማያዊ ስፍራ የሕይወት መንፈስ ሕግ ነው፡፡ እርሱን ስናብለጨልጭ ምድር ሁሉ በብርሃናችን ይመላለሳል፡፡ በሰማያት (ጠፈር) ያሉት ብርሃናት በምድር ላሉት ሁሉ ለምልክቶች - ለዘመኖች - ለዕለታት - ለዓመታት… ይሆናሉ፡፡ ይህንን ሕይወት - ይህንን መጽሐፍ ለመተርጎም አብ ልጆችን ተናጣቂና ኃይለኞች አድርጓቸዋል፡፡ ከእንግዲህ የምንኖረው ኑሮ በግብፅ እንደኖርነው ኑሮ አይደለም፡፡ አሁን የወረስናት ምድር ሁሌም በሰማይና በሰማያዊ ነገር የምትጎበኝ ናት፡፡

የግብፅ ምድር ሜዳ ነው፡፡ ማንም ሊኖርባት ይችላል፡፡ ይህች ግብፅ ጌታቸው የተሰቀለባት ሶዶም ናት፡፡ ሶዶምም በግብፅ ምድር አምሳልናትና (ዘፍ.13÷10)፡፡ በግብፅ ሕይወት (ኑሮ) ቀላል ናት፡፡ ከነዓን (ወተትና ማር የምታፈስሰው ምድር) ግን ሸለቆና ኮረብታማ የበዛባት ሀገር ናት፡፡ በጦርነት - በትግል - በመከራ - በስቃይ… እንጂ በቅምጥልነት አትወረስም፡፡ ለታካቾችና ለሰነፎች - ጌታን ለማይገልጡና ለማያወጡ ለልበ ስውራን የተስፋይቱ ምድር ጨለማ ናት (ዘዳ.11÷10-12)፡፡

መልእክታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰዎች ቢሆንም - ራሳቸውን ‹‹ክርስቲያኖች›› ብለው ለሚጠሩት ቢሆንም

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10

Page 2: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

የምንጽፍበት ይዘት ግን ክርስትና ሳይሆን የእግዚአብሔር መንግሥት ነው፡፡ ክርስትና ሕይወትን አቅልሎታል፡፡ ትውልዱ ጣፋጭ ጣፋጩን የሚልስበት ባቡር ላይ ነው የተሳፈረው፡፡ በእንቅልፋቸውም የሚበሉ ብዙ ናቸው፡፡ የዘመናችን መጋቢዎችና አገልጋዮች አንቀልባ እነዚህን ተሸክሟል፡፡ …መንግሥቱ ግን የተፈተነ - አሸናፊ - የሚነጥቅ - ኃይለኛ - በብዙ መከራ የማይበገር ስብዕና የተላበሰ ነው፡፡ ክርስትናን አንሰብክም አንጽፍምም፡፡ የእርሱ ሙያተኞች ብዙ ናቸውና ስለ እርሱ እኛ አንደክምም፡፡ ከምናየውም የክርስትና ሕይወት ተነሥተን ዛሬ እግዚአብሔር ከክርስትና ጋር ይወግናል ከእርሱም ጋር ነው ለማለት ‹‹እምነት›› ጠፍቶብናል፡፡ ያለ እግዚአብሔር ብዙ ተቋማት እንደ ሆኑት እርሱም ሆኖብናል፡፡

ማንም ራሱን እንዲህ ይይ፡- ወደ እኛ የሚመጡት ከእኛ ምን ያነባሉ? የማኅበረ ሰብ መራርነት በጨዋችን ካላወጣነው የእኛ ጨው አልጫ (tasteless) ነው፡፡ ወደ ከርስቶስ ተልከው (ሊይዙት የመጡት ምን አነበቡ? ‹‹… እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም ብለው›› ለላኩዋቸው መለሱ(ዮሐ.7÷46)፡፡ ከዚያ፣ ከእግዚአብሔር አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ሕገ - መንፈስ ይወጣ ነበር፡፡ የሕይወትን ቃል እያቀረብን እንደ ብርሃን ልጆች (ብርሃናት) ሁነን ካልተገለጥን ብርሃን - ምልልስ - ኑሮ - ምሳሌ… ያጣብን ትውልድ ከእኛ ቀድሞ መንግሥተ ሰማያት ይገባል፡፡ ቀራጮችና ጋለሞታዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት የሚቀድሙትን (ግብዝ) መንፈሳዊ ማኅበር የምንሠራው ስለ ምንድር ነው?

የሚድንበትን - ወደ አምላኩና አባቱ የሚመለስበትን መልእክት ከእኛ ያጣው ‹‹አልዳነም - ጌታን አልተቀበለም›› የምትሉት ወገን ‹‹ቢጠፋ›› የሁሉ ዳኛ ደሙን ከእኛ አይሻውምን?

‹‹እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ…በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው፡፡›› ለማን? ለሚያነብቡን ሁሉ፡፡ ይሄ የሕይወት ልክ (standard) ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ነው የሃይማኖት መልክ - አስመሳይነት - ግብዝነት - ለሰው ለመታየት ሥራን ሁሉ መሥራት፡፡

መጽሐፉ የተተረተረው - የተነበበው በጌታ ዓመት አይደለምን? መጽሐፉ የተዘጋው ማኅተሙም የታተመው ግን በሰው ዘመን ነው፡፡ እናነበውና ያነቡን ዘንድ በጌታ ዓመት ከሚከፈተው መጽሐፍ በሚሰሙት ጆሮ የሚፈጸም ቃል ነው፡፡ የተፈጸመና የሚፈጸም ቃል እናነባለን፡፡ በሕይወትም የተፈጸመው ቃል የሚያዩንና የሚሰሙን ሁሉ ያነቡታል፡፡ በቃሉ የሚኖሩ በእርሱም የተፈተኑ ከአፋቸው የሚወጣው የጸጋው ቃል ከቶ ሊወድቅ አይችልም፡፡ … የተወደዳችሁ ሆይ÷ ወደዚህ ከፍታ ትደርሱ ዘንድ በመንፈስ በተቀባው ብዕሬ እናንተን አነሣሣለሁ፡፡ ይሄ የምታነቡበትና የምትነበቡበት የጌታ ዓመት ነው፡፡ ከዚህ የጎደለ ነገር ቢሆንባችሁ ወይም

ቢታይባችሁ ፈልጋችሁት እንዳልሆነ ጸሐፊውም የሕይወት ምስክርነት አለው፡፡ አንድ ነገር አውቃለሁ፡፡ እኔ በፊቴና በኋላዬ ባለው ነገር መካከል ነኝ፡፡ እንደ ወንድሜም አንድ ነገር አደርጋለሁ፡፡ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውነ ለመያዝ እዘረጋለሁ፡፡

በልባችሁ ውስጥ ደግሜ አንድ ነገር እንድጽፍ ፍቀዱልኝ የጌታ ምርጦች ሆይ÷ ‹‹ሰዎች አንዳች የጌታ ፊት - የማንፀባረቁም ክብር ሊያነቡ ወደ እናንተ ይመጣሉ›› ብዬ፡፡ አዲስ ኪዳን የተጻፈባችሁ የኪዳኑ መጽሐፍ እናንተ አይደላችሁምን?... አብ አባት የልጁን መልክ የጻፈው - የሳለው በእናንተ ላይ እንደ ሆነ መጽሐፉና መንፈሱ ይመሰክራሉ፡፡

እናንተ የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፡፡ በዚህ እርሻ ውስጥ የተሰወረው መዝገብ አለ፡፡ እርሱ የእግዚአብሔር የክብሩ እውቀት ብርሃን ነውና ሰዎች ይመላለሱበት ዘንድ ሽክላችንን ሰብረን - እርሻችንን አርሰን - ያለንን ሁሉ ሸጠን እናወጣላቸው ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነ ጥሪ፣ መርጫና ቅባት አለን፡፡ በመንፈስ ያየነውና የተረዳነው እስካሁን ያለው አሳዛኝ ነገር ግን ብዙዎች በራሳቸው ውስጥ ያለውን መዝገብ ሳያነቡና ሳይገልጡት በውጭ ያለ መዝገብ ያልሆነ መዝገብ መጽሐፍ ያልሆነ መጽሐፍ ማንበባቸው ነው፡፡ በውጭ ያለ ስለ አዲሱ ሰው - ስለ ተሰወረው ሰው ምንም ያልተጻፈበት ባዶ ጥራዝ (መጽሐፍ) ትውልዱ ተሰልፎ አንዳች ሳይሸጥ እየገዛው መሆኑን ስናስተውል መንፈሳችን ይበሳጫል፡፡ ቅዱስ ቅናትም ይበላናል፡፡ ፍርድም ይሆን ዘንድ ብዙ ጊዜ እንጸልያለን፡፡

በእናንተ ያለው እናንተ ካላነበባችሁት ማን ያነብላችኋል?... ሥጋ - የውጭ ሰውነት አፈር - አቧራ የለበሰው የውስጥ ሰውነት መጽሐፋችሁን (አዲስ ኪዳን) ሳታነቡ በውጭ ያለውን የባቢሎንን ምሥጢር - የነፍስ ጥበብና እውቀት ያነበባችሁበት ዘመን እጅግ በዛላችሁ፡፡ አሳዛኝ ውድቀት! በውስጣችሁ የተጻፈውን ሳታነቡ ከሰው ትማራላችሁን?... ኢየሱስ ክርስቶስ ከገለጠላችሁ ወንጌል ሌላ እንደ ሰው በመስማታችሁና በማንበባችሁ ነው የሚነበብ መልእክት ከእናንተ እንዲጠፋ ምክንያት የሆነው፡፡ መንፈስ የጻፈውና መንፈስ ለአብያተ ክርስቲ ያናት የሚለውን ማንበብ ያቃተው ‹‹አማኝ›› የውጭ መጽሐፍ - ፊደል በማንበብ ራሱን የሚያጠፋ ነው፡፡ የነፍሳት ጥፋት በእምነት ቤቶች እየተካሄደ ያለው በዚህ ዓይነት ‹‹አገልግሎት›› ነው፡፡ … የሩዋንዳውን የዘመናችን እልቂት ዓለም አውግዞታል፡፡ ከውጭ የተጻፈውን በማንበብና በማስነበብ የሆነው መንፈሳዊ እልቂተ ግን ማንም አላስተዋለውም፡፡

ሁሌም ከውጭ ትሰማላችሁ - በየፕሮግራሙና በየዲሹ፡ መቼ ነው ከውስጥ - መንፈስ የሚለውን የምትሰሙት; ሁሌም መጻሕፍትን ያሳይዋችኋል፡፡ ትንሹን መጽሐፍ ግን ለምን አልከፈታችሁትም?... ዘመን የተሰጣቸው ግን አብ ከሰው - ከሰፈር ውጭ የጻፈውን ያነባሉ፡፡ መጋቢው በውጭ በተጻፈው ቃል አፉን የሚከፍተው እንድታጎርሱት ነው፡፡የሚያሳዝነው ግን መልካም ያደረጋችሁ እየመሰላችሁ በምትሰሙት የውጭ መጽሐፍ ለዲያብሎስ ሕያዋን ሁናችሁ መያዛችሁና መጠመዳችሁ ነው - እያዘንኩ እጽፋለሁ፡፡ የትኛውም መጋቢ፣ የትኛውም ሐዋርያ የእናንተን የውስጥ መጽሐፍ ሊያነብ አይችልም፤ እንድታነቡ ይነግራችሁ እንደ ሆነ እንጂ፡፡ እኛም እየገሠፅን የምንጽፈው እስከዚህ እንድትደርሱ ነው፡፡ ብዙ የስብከት ሞግዚቶች እንዳሏችሁ እኛ ግን ለእናንተ የመልእክት ሞግዚቶች አይደለንም፡፡ መጽሐፋችሁ የት እንዳለ እየነገርናችሁ ነው፡፡ መንግሥተ ሰማያት በእርሻችሁ ውስጥ የተሰወረ መዝገብ ነው፡፡ ከእርሱም አዲሱንና አሮጌውን

በባዚሊያ ማለዳ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚታተም መንፈሳዊ ጋዜጣ

በ0911404275 (ካሣ ኬራጋ) ወይም በ 1183 ወይም በ www.bazilia.org

እንገናኝ፡፡አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ጋዜጣችን በቂርቆስ ገበያ ማዕከል በቢሮ ቁ. 239 ማግኘት የምትችሉ ሲሆን በፖስታ ቤት ልንልክላችሁ የምትፈልጉ ግልጽ አድራሻችሁን ጻፉልን፡፡(የማይሸጥ)

ገጽ 2 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 3: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

የምታወጡ ባለቤት እንድትሆኑ እግዚአብሔር ይርዳችሁ (ማቴ.13÷44-53)፡፡ የዚህን መጽሐፍ ምሳሌ ከፊታችሁት እርሱ ሕይወታችሁ ነው - ይሁን!

አሁን ሥጋ የሚለውን አይደለም፡፡ አሁን የውጭ ሰውነት የሚለውን አይደለም፡፡ አሁን ከሥርዓት - ከፕሮግራም - ከሕግ - ከአባቶች ወግ - ከየጉባኤዎች ከተላለፈው ውሳኔዎች፣ ድንጋጌዎችና ጥናታዊ ጽሑፎች መስማት አይደለም፡፡ አሁን መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ነው መስማት የተገባን፡፡ ይህ የክርስቶስ መገለጥ ነው፡፡ ለዚህ ጆሮ ያለው ማን ነው - የመንፈስ ጆሮ?... እግዚአብሔር ያለ ጩኸት - በፀጥታ - ያለ መወራጨት - ያለ ሥጋ ሥራ ለመንፈሳችን ራሱን የሚገልጥበትና የሚያስረዳበት ስፍራ እንምጣ፡፡ ላስረዳንም ነገር እምቢ እንዳንል መጠንቀቅ እንዳለብን ተነግሮናል፡፡ ትውልዳችን ግን ያለፈውን ዘመን ታሪክ እንደ ደገመው በመንፈስ አይቻለሁ፡፡ ስለ ሰማዊው ነገር ቀርቶ ስለ ምድራዊም ነገር ቢነገረው ማስተዋል ያልቻለ ትውልድ አለ፡፡ መወለድ እንኳ በቅጡ አልገባውም እንኳን መገለጥ፡፡ የጥንቶቹ ‹‹በምድር ላስረዳቸው›› ነገር ነው እምቢ ያሉት፡፡ ዛሬ ከሰማይ ለወጣው ራሱ ሰማይ ካልሆነ እንዴትና ማን ያስተውለዋል? የአሁኑ መልእክት ከሰማይ ነው - ከመንፈሳችሁ ከፍታ የተወደዳችሁ ሆይ፡፡ የውጩን መጽሐፍ ዝጉት፡፡ ጆሮዎቻችሁንም ከልክሉ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህንን አድርጉ፡፡ በዚያ አዚም - በዚያ ሟርት - በዚያ ድግምት ሌላ መጽሐፍ መጻፉን አትርሱ፡ ሌላ መጽሐፍ - ሌላ ወንጌል በዚህን ያህል ዘመን እስከ ዛሬ አለ፡፡ በጣም ሥር ሰድዶአል፡፡ ‹‹እስረኛ ሲቆይ ባለርስት ይሆናል›› እንዲሉ ሐሰት ብዙ በመኖሩ እውነት እየመሰለ አሳስቷልና ብዙዎችን ወረሰ፡፡ አያሌዎች ለዚህ ሐሰት ዘብ ውለው አድረዋል፡

‹‹ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቁራሽ ይሻላል›› (ምሳ.17÷1)፡፡

ይሄን የመጽሐፍ ክፍል የብልጽግና ወንጌል መሐንዲሶች ‹‹የድህነት ጥቅስ›› ይሉት ይሆናል፡ እኛም ስንጠቅሰው በእነርሱ ዘንድ ወዮልን፡፡ ንቀታቸ ውና ማንጓጠጣቸው የማን ትከሻ ይችለዋል? በእርግጥ ሀብታም ናቸው በልጽገዋልም፡፡ በውስጣቸው ግን ለእግዚአብሔር ነገር የተራቆቱ እንደ ሆነ እኛ እንነ ግራቸዋለን፡፡ ጥቅሶችን ማወቅና በውጫዊነት መተርጎም መገለጥ አይደለምና መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር እንጂ ጥልቅ አይደለም፡፡

እርድ የሞላበት ቤት የጥል - የመለያየት - የባዶነት… ቢሆን ምን ረብ አለው? የጸጥታ ቤት ግን የት ነው? ይሄ ከውስጣችን ሰላም፣ እረፍትና መጽናት ሌላ ይሆናልን?... የሰው ሁከት ከውስጡ ሊሆን እጅግ ከባድ ነው፡፡ ውስጥ ሰላም ገዝቶ ውጭ ቢረበሽ አትናወጡም፡፡ ከባድ ነፋስ በሚያናውጠውና በሚያንቀሳቅሰው ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ያለች አንዲት ትንሽ ወፍ ስለ ዛፉ መንቀሳቀስና መናወጥ መነቀልስ ቢሆን ትናወጣለችን? በጭራሽ፡፡ ምክንያቱም ከክንፍ ጋር ተፈጥራለችና የዛፉ ዕጣ ፈንታ (መውደቅ ወይም መነቀል ወይም መሰበር) ቢሆን ጉዳይዋ አይደለም፡፡ ትበርራለችና!

ትንሽ ቁራሽ ያለበት ያ የጸጥታ ስፍራ እግዚአብሔር በጸጥታ - ያለ ጩኸት ፈቃዱን ለመን ፈሳችሁ የሚያስረዳበት ቦታ (መንፈሳዊ ስፍራ) ነው፡፡ ይሄ ቁራሽ ግን ድህነት ሳይሆን የጌዴዎንን እንጎቻ - እጅ የምታህለውን ደመና - የዳዊትን ጠጠር ያስታውሰናል፡

የሐሳብ፣ የአስተሳሰብ፣ የመረዳት፣ የጥቅስ፣ የአመለካከት፣ የትምህርት ጠብ ካለበት ደረቁን ቁራሽ የጥበብ መንፈስ ስለ እኛ መርጦታል፡፡ ክርስቶስ ራሱ ‹‹ከደረቅ መሬት›› አይደለምን(ኢሳ.53÷2)? ወደ ውስጣችሁ ድምፅ

ተመለሱ፡፡ ጠብ፣ ወከባ፣ ግርግር፣ ስሜታዊነት፣ ጩኸት፣ ረብሻ፣ ድካም፣ ትግልሸሚዝ እስኪረጥብና እስኪጨመቅ ማምለክ… (እነዚህ ሁሉ በቤተ ክርስቲያንና በሚኒስቲሪዎች ዘንድ በአምልኮ ስም የሚስተዋሉ ናቸው) የመንፈስ ድርቀት - የውስጥባዶነት ማሳያ ናቸው፡፡

በውስጣችሁ የመጣውንና የተመሠረተውን መንግሥት በእምነት እንጂ በውጭ በምታደርጓቸው ልዩ ልዩ ሥርዓቶች ማረጋገጥ አትችሉም፡፡ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔዴር ያለውን ማን ሊያውቅ ይችላል? ከእግዚአብሔር የሆነውን - የተደረገውን ለማወቅ የእግዚአብሔር መንፈስ የተቀበለ እርሱ ተመሰገነ፡፡ በውጭም አገልግሎቶችና ስጦታዎች በው ስጥ ያለውን ማጽናት አልተቻለም፡፡ ይልቅስ እነዚህ ብዙዎችን በውጭ ያስቀሩ የዲያቢሎስ ናቸው፡፡ ጥልቁን በጥልቀት ነው የምንወርደው፡፡ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ እንላለን፡፡ አንጠልቃለን፡፡ ጥልቁንም እንጠልቀዋለን፡፡ በመንፈሳዊነት ስም ግን ሸርተቴ የሚጫወቱ ወዮላቸው፡ ባደግሁበት አካባቢ (አሁን መኖሩን ግን አላውቅም) በወርሃ ቡሄ ሕፃናት የጭቃ ሸርተቴ (ከዳገት ወደ ቁልቁለት) ሲጫወቱ አይቻለሁ፡፡ ተጫውቻለሁም፡፡ ያኛው ደስ ይላል፤ መዝናኛ ነውና፡፡ የአሁኑ መንፈሳዊ የጭቃ ሸርተቴ ግን እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ብዙዎች በሸርተቴው ከወረዱበት አልወጡም - አይችሉምና፡፡ ሎጥ ለመውረድ አልተቸገረም፡፡ ለመውጣት ግን ሁለቱ መላእክት ናቸው እጃቸውን የዘረጉለት፡፡

በእናንተ ውስጥ ተመሠረተው መንግሥተ ሰማያት ጽድቅን፣ ኃይልን፣ ክብርን፣ በረከትን፣ አለመጥፋትን… ከውስጣችሁ - ከምንጫችሁ እንድትቀዱ ያደርጋል፡፡ እነዚህን ሁሉ ከውጭ አትፈልጉም፡ የሙላቱ ቤት እናንተ ናችሁና፡፡ ከወጫዊነት ተለይታችሁ ከውስጣችሁ ወደ ውስጣችሁ ማለት ወደ ቅድስተ ቅዱሳናችሁ ከገባችሁ ስለ እግዚአብሔር ማስረጃ የሚሰጣችሁ የውጭ ምስክር አያስፈልጋችሁም፡፡ ከምንጫችሁ በሚወጣ የሕይወት ውኃ ወንዝ ምክንያት ራሳችሁ ሕያዋን ምስክሮች ናችሁ - የገዛ ዘመናችሁ ሰማዕታት!

ይህ ውድ በቆነጃጅትና በልጆች መካከል ነው (መኃ.መኃ.2÷1-4) እርሱም ሕያው ፍሬውን ይሰጣል፡ ከሚኖርበት ይወጣልና እርሱ የሚደርስበት ሰፊ ሁሉ ለምለም ነው፡፡ በጸጥታ የሚኖረው ‹‹ቁራሽ›› (ይህ ግን ለሰው ዓይን ነው - ቁራሽነቱ) ሁሉን ያጠግባል - ሃሌ ሉያ!

ነፍስ ፍጻሜ በሌለው - ወሰኑም በማይታወቅ በሕያው እግዚአብሔር (reality) ሕልውና - መገኘትና መገለጥ - በእግዚአብሔር ሕይወት ሙላት ብትገኝ - በእርሱም ፊት ብትሆን አቤት ድንቅ፡፡ በመገረም የምናመልከው ያኔ ሆኗል፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው ስፍራ (realm) ግን የእርድ ስፍራ ይምሰል እንጂ የሙታን አጥንት የሞላበት መቃብር ብቻ ነው፡፡ ነፍስንም ከዚህ ውጭ ማገልገል የበኣል ነቢያት ምሥጢር ፍጻሜ መሆኑ የታወቀ ይሁን፡፡ የበኣል ነቢያት የነፍስን ፈቃድ ያገለግሉ ነበሩና፡፡

የመንገድ ዳር ቤት አገልግሎትና ስጦታዎች የሚፈለግ፣ ውድ፣ የከበረና ሁሉን ያማለለ ይምሰል እንጂ የጌታን ድምፅ በውስጣችን እንዳንሰማ ያጠፋብን የሌባው ሥራ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ ነው፡ መንፈሳዊ ኃይላችን፣ የውስጥ ጥንካሬአችን፣ የውስጣችን መጽናትና መጽናናት፣ እምነትና ድፍረት… ከአብ ጋር ያለን ኅብረትና አንድነት ነው፡፡ ድምፁ በውስጣችን በውጭ ከምንሰማው ይልቅ እርግጠኛ ነው፡፡ ለእርሱም የነፍስ ፈቃድ በሌለበት እንገዛለን፡፡ ነፍሳችን ፈቃድዋን የምትጠየቀው በውጭ ላለ ድምፅ አይደለምን? ያለ ጩኸት (ምናልባትም) ያለ ሰው መግባቢያ ቋንቋ የምንሰማው የውስጥ ድምፅ (የእርሱ ድምፅ) እጅግ ግልጽ ነው፡፡ ኤልያስን

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 3

Page 4: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ወደ አብ ፈቃድ ያዞረና የመለሰ ድምፅ ‹‹ትንሽ የዝምታ ድምፅ›› ነበር፡፡ ዝምታ ድምፅ አለውን?... የተለማመዱት ብቻ ያውቁታል፡፡

‹‹… ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ›› (ራእ.2÷7)፡፡የፊተኛው ሰው እንኳ ከገነቱ የሕይወትን ዛፍ እንዲበላ አልተከለከለም ነበር፡፡ በእርሱም ገነት መካከል ሁለት ዛፎች ነበሩ (ዘፍ.2÷8-9)፡፡ እነዚህ ዛፎች የሚገልጡትና የሚወክሉትም ነገር ሁለት ነበር፡፡ በምሥራቅ በኤደን (አሁን የዚህን ስፍራ አቅጣጫ ማንም ሊያውቅ አይችልም) የነበረው ገነትና ያበቀላቸው ሁለት ዛፎች (?) ማንነት ለማወቅና እነርሱን ለመግለጥ ላያስጨንቀን ይችላል፡፡ በሰው (ውስጥ) ያለው ገነት ያበቀላቸውና ፍሬ እንዲያፈሩ ያደረጋቸውን ሁለቱን ዛፎች አለማወቅና ለማወቅ አለመፈለግ ግን አይቻልም፡፡ ዋጋ ያስከፍላልና፡፡

‹‹ተመልከት፤ ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን÷ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ›› (ዘዳ.30÷14)፡፡ አነበባችሁትን? አስተዋላችሁትን? … እነዚህ በሰው ፊት - በሰው ሕይወት ናቸው፡፡ በዚያኛወም ገነት ‹‹መልካምንና ክፉን የሚያስታውቅ ዛፍ(ፍሬ›› ነበረ፡፡ አሁን በምድረበዳውም ገነት (ማኅበር) ሁለት ዓይነት ነገር በፊቱ (በሕይወቱ) ተቀምጧል፡፡ ይሄ ሁሉ የፊተኛው ሰው ማንነት እንደ ሆነ እናውቃለን፡፡ ያለ ክርስቶስ በአሮጌው ሰው - በአሮጌው ኪዳን ሕይወትና መልካምነት፤ ሞትና ክፋት የዛፉ ዋጋ ናቸው፡፡ በሁለተኛው ሰው ግን ሁለት ዓይነት ዛፍ የለም፡፡ በእርሱ የሕይወት ዛፍ ብቻ ነው፡፡ በራሱ በፈጠረው አንድ አዲስ ሰው ውስጥ - በእግዚአብሔር ሕያው ገነት - በጉና አብ በሞሉበት ገነት የሕይወት ዛፍ ብቻ አለ፡፡ግን ግን ምን ዓይነት ገነት ነው ሁለት ዓይነት ዛፍ የሚያበቅለው?... ከሰው ልብ የሰፋ፣ የከፋ፣ የማይታወቅ፣ ሌላ ስውር ገነት አለን? ሥረ - መራራ፣ ውጩ እሾህና አሜከላ፣ ያልተገረዘ ዛፍ፣ ፍሬው ሆምጣቴ… ያበቀለና ያፈራ - ታላቅም ዱር ሁኖ የአውሬ መኖሪያ የሆነው የሰው ልብ ነው፡፡ ‹‹እጅግ ክፉ ማንስ ያውቀዋል?›› የተባለው ፍጡር እርሱ አይደለምን?... ልባችን፣ ሐሳባችን፣ ትምህርታችን፣ መረዳታችን፣ ውስጣችን በሚያበቅለውና በሚያፈራው የተወሰንን ነን፡፡ በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ ይሁን ወይም በቀለም (በፊደል) የተገለገለ ቃል የሕይወት እና/ወይም የሞት ዛፍ መሆኑ በልባችንና በተሰጠን ዘመን ልክ ይወሰናል፡፡

መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ታነባላችሁን? ማንም ለሕይወት ወይም ለሞት ያነበዋል - እንደ ሆነለት መንፈስ፡፡ ዲያብሎስም ክርስቶስም መጻሕፍትን እኩል ጠቅሰዋል - ከልባቸው ልክና መንፈስ፡፡ ስለዚህ መጻሕፍትን ለሞትና ለሕይወት የሚያነቡ ዲያቢሎስሳውያንና ኢየሱሳውያን ዛሬም አሉ፡፡ መጽሐፍት የውስጣችሁ ዛፍ ማዳበሪያ ነው፡፡ ፊደል - ቀለም ቢሆን ሞትን ታፈራላችሁ፡፡ የሕያው እግዚአብሔር መንፈስ ቢሆን ሕይወትን ታፈራላችሁ፡፡ በገነታችሁ ውስጥ ዛፍ አለ፡፡ ዛፎቹም መጽሐፍትን እየነኩ - እየጠቀሱ እየተማሩ በእርሱም እየተመረቁ… ያድጋሉ - ያፈራሉ፡፡ … ከአብ ከመንፈሱም የምትማሩት ብቻ የገነታችሁ (የሕይወት) ዛፍ ሕይወትን እንዲያፈራ ያደርገዋል፡፡

አብ የላከው ወደ ልጅ(ነት) ይመጣልና በመጨረሻው ዘመን በዓለም፣ በሥጋና በሰይጣን ላይ ከፍ ከፍ ለማለት ይነሣል፡፡ ከአብም የሰማና የተማረ ብቻ ነው ወደ ክርስቶስ ሊመጣ የሚችል፡፡ በዚህ ምክንያት ክርስቶስ ከሰማይ የወረደ መብልና መጠጥ ነው፡፡ የሚበላውም የሚጠጣውም ለዘላለም ይኖራል፡፡ እንዴት?... ‹‹እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው›› ተብሎ እንደተጻፈ(ዮሐ.6÷63)፡፡ በመስማትና በመማር (ከአብ በመንፈስ) ነው በሕይት

መንገሥ፡፡ ከዚህ በቀር ሌላ መንገድ አልታወቀም እንደ እግዚአብሔር ልብ፡፡

የልባችሁ ዛፍ - በገነታችሁ ያሉት ዛፎች ከውጭ ወይም ከውስጥ ሰምተው ሞትን ወይም ሕይወትን ያፈራሉ፡፡ በገነታችሁ ውስጥ (መካከል) ዛፎች አሉ፡፡ የሕይወትና የሞት ዛፍ፡፡ የደኅንነትና የጥፋት ዛፍ፡፡ መጻሕፍትም ከእነዚህ ዛፎች አንዱን ይመግባሉ - ያሳድጋሉም፡፡ በአዳም ገነት የነበሩት ሁለት ዓይነት ዛፎች በእርግጥ ምንም ማለት አይደሉም ከውጭ ወይም ከውስጥ ከሚሰሙት ድምፅ በቀር፡፡ የሁለቱን ዛፎች ማንነት በሰውነት ሊገልጠው የሚችለው ወዲዚያ የሚመጣው ድምፅ ነው፡፡ የእባቡና የእግዚአብሔር ድምፅ የዛፉን ፍሬ ይወስናል፡፡ ለዚህ ነው ክርስቶስ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ ያለው፡፡ ድምፆቹ ልዩነት አላቸው፡፡ ሕይወትን የሚያፈራ - የሚገልጥ ድምፅ ከውስጥ - ከመንፈስ ነው፡፡ መጻሕፍትም ስለዚህ ይመሰክራሉ፡፡ ሞትን የሚገልጥ - የሚያመጣ ድምፅ ከውጭ - ከሥጋ ሰውነት ነው፡፡ መጽሐፍ ሁለቱን የሞትና የመንፈስ አገልግሎት ብሎ በግልፅ ለይቷቸዋል(2ቆሮ.3÷7-8)፡፡ የመጀመሪያው አገልግሎት የሞት የተባለው በተጻፈው ላይ መጋረጃ አኑሮ ስለነበር ነው ማለትም በፊደልና በቀለም ‹‹በመንፈስ›› ነበርና ነው፡፡ እርሱ ሲነበብ ሁሌም መጋረጃው አለና ለሞት ይነበባል፡፡ የውስጡም ዛፍ ድምፅ ከመጣበት ስፍራ ጀምሮ ሞትን ያፈራል፡፡ ኋለኛው አገልግሎት ሕይወት የተባለውና መጋረጃው የተወሰደለት የመንፈስ አገልግሎት ነው፡፡ እርሱም ወደ ጌታ ዞር ያለና የመንፈስ ብርሃን በመውረስ መጻሕፍትን በምሳሌነቱ እያነበበ አካሉን ያገኘ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ፡፡

የአገልግሎቶቹ - የድምፆቹ - የመጻሕፍቶቹ… ጉዳይ የሞትና የሕይወት፣ የጸጋና የሕግ፣ የሙሴና የክርስቶስ፣ የሥጋና የመንፈስ የመሻርና ጸንቶ የመኖር… ጉዳይ አይደለምን?... ዛሬ በፊደል ማገልገልና መኖር ምን ማለት እንደ ሆነ ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡ ፊደልን እየኖሩበትና እያገለገሉበት ይቃወሙታል፡፡ ሐሰት ራሱን ይክዳልና እርሱን የካዱት እየመሰላቸው ይመስሉታል፡፡ ይህ የተሰወረ - የቅብብሎሽ - የጥንት ጉባኤዎች ትምህርት ቀኖና ግትርም አስተሳሰብ በዘመናት ሁሉ እየተራመደ ዛሬም ድረስ ደርሶ መገዳደሩ ግልጽነቱ ለጥቂቶች ብቻ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የሰረቀ የአጋንንት ትምህርት ቅሬታዎች በየዘመናቱ በመገለጡ ክብር አጋልጠውት አልፈዋል፡፡ ዛሬም በእኛ ዘመን የክርስቶስን መገለጥ የሚገዳደረውን ይህን ትምህርት (የውጭን ሰው- የአውሬውን ድምፅ) የሚያጋልጠውን መገለጥ ይዘው በተገለጡት ዘንድ ልዩነት መኖሩ ግልፅ እየሆነ ነው፡፡ የነበረውን ‹‹መንፈሳዊነት›› ባዶ ያደረገና አይረቤ መሆኑን ያጋለጠው የልጅነት መንፈስ በሁሉ ሰማይ ላይ መብረሩን የተመለከትንበት ራእይ የተባረከ ይሁን፡፡

በተዘረጋውና በተከፈተው በእግዚአብሔር መቅደስ መካከል ልዩነት መኖሩ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ሕይወታችንም ይመሰክራል፡፡ የብሉይ - ኪዳን - ዘመን - መጽሐፍ - ዛፍ… መቅደስ የተዘጋ ነበር፡፡ ግን እግዚአብሔርን ሳይዝ ነውን? አይደለም፡፡ ነገር ግን ሐሳባቸው ደነዘዘ፡፡ የአዲስ ኪዳን - የጌታ ዓመት - መጽሐፍ … መቅደስ ግን የተከፈተ ነው፡፡ ምስክሩ - የኪዳኑ ታቦት የታየው በዚህ በተከፈተው በአዲሱ (ሰው) መቅደስ ነው (ራእ.11÷19፤ ሕዝ.44÷1-2)፡፡ ያ ኪዳን መቅደሱን ዘግቶታል፡፡ እግዚአብሔር አልወጣም - አልመጣም- አልተገለጠም - አልታየም፡፡ ይሄኛው ኪዳን ግን መቅደሱን ከፈተው፡፡ ጌታንም አመጣው - ተረከው - ገለጠው፡፡ የመለኮት ሙላት በሰውነት ተገልጦ ኖረ - እየኖረም ነው፡፡

ለዚህ ዓለም ለውጫዊነትም ካበድንበትና ከሳትንበት እየጮህን እንዲህ እንላለን፡፡ የተወደደው የጌታ ዓመት በእናንተ እርግጠኛና ጽኑ የሚሆነው በትምህርታችሁ

ገጽ 4 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 5: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ሳይሆን በጌታ መገለጥ ነው፡፡ ከሰው ያልተማራችሁትና ኢየሱስ ክርስቶስ የገለጠላችሁ ከሆነ እናንተ በጌታ ቀን በመንፈስ ናችሁና ዛፋችሁ ሕይወትን ያፈራልና በዓለም ያለውን ሞት ሊውጥ ራሱን ያዘጋጃል፡፡ ሞት ሕይወትን ይፈልገዋል - ይከተለዋል - በእርሱ ይዋጥ ዘንድ፡፡ ሞት የሚኖረው ሕይወት ባለበት ነው፡፡ ሞት በሕይወት ላይ መጋለቡስ ምሥጢር አይደለምን?... ልጅነት ባለበት ፈታኙ አለና በጌታ የተወደዳችሁ ሆይ÷ የጌታ መገለጥ (በእናንተ) ውኃችሁን እንደ ውሻ ተንበርክካችሁ ትጠጡ ዘንድ ሳይሆን እያያችሁ ትናጠቁ ዘንድ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ዛሬ እንዲህ ይመሰክራል፡፡

ከእኛ ውጭ ባለው ፍጥረታዊ ሰማይ ጌታ ሲገለጥ ሊሆን ያለውን ብዙ እጅግ በጣም ብዙ ዓይነት ሁኔታዎች እንዳሉ ሰምተናል፣ አንብበናል፣ ተምረናል፣ በፊልሞችም አይተናል፡፡ በመቅረዞች ዘመን ያልተባለ ነገር የለም፡፡ አሁን ግን ከዙፋኑ የምንሰማበት ዘመን ነውና ምሳሌ አናወራም፡፡ የጌታን ነገር ከራሳችን አርቀን ፍጥረታዊ ማድረግ ከእንግዲህ አይገባንም፡፡ ጌታ በቅዱሳኑ ሊከብርና ሊገረም ሲመጣ - ሲገለጥ በሥጋዊነት ላይ፣ በፍጥረታዊ ላይ፣ በውጫዊነት ላይ፣ በመነፈሳዊ ሕፃንነት ላይ፣… የሚሆነውን ማወቁ ነው የበለጠ የሚጠቅመን፡፡

ጌታ ሲመጣ - በመንፈሳችን (ሰማያት) ሲገለጥ እስከዛሬ ድረስ ያልሆነ ወደፊትም የማይሆን መከራ ይሆናል፡፡ መከራም ለሚያምኑት እንጂ ለማያምኑት አይደለም፡፡ የያዕቆብ መከራ ከኤሳው መከራ ፈጽሞ ይለያል፡፡ የይስሐቅና የእስማኤል መከራ አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ በጌታ መገለጥ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፡፡ ከዋክብት ይወድቃሉ፡፡ ‹‹እነዚህ ለምልክቶች፣ ለዘመኖች፣ ለዕለታት ለዓመታትም›› አይደሉምን?... በእኛ ጌታንና ብርሃኑን ደብቀው እነርሱ ያበሩበት (ያገለገሉበት) የአገልጋዮች ዘመን ይጨልማል፡፡ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ (በመንፈሳችን) ላይ እነዚህን ሁሉ ያስወግዳል፡፡ ታላቁ መከራ የዚህ ምክንያት ነው - ሃሌሉያ!

ጌታ እንደ ሰው ሳይፈተን አልተገለጠም፡፡ የልጅነት መልክ የሚገለጠው በእሳት ነው፡፡ ዲያብሎስ ኢየሱስን ከፈተነው በኋላ በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ (ሉቃ.4÷1-4,14)፡፡ ባሕር ዳሩ ያሉ አሦች ያላደጉ አሦች አሊያም ትሎች ናቸው፡፡ በመንፈስ ሕፃናት የሆኑ ለመከራም ለፈተናም የተጋለጠው አይደሉም፡፡ ዛሬም ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ የማይጠቀሱት ጥቅስ የለም ልክ እንደ ወዳጃቸው ዲያቢሎስ፡፡ ክርስትናና ሚኒስትሪዎች ችግር ማስወገጃ - መከራ መቃወሚያ ተቋማት እየሆኑ ነው፡፡ ክርስቶስ ግን ጠቅሶ አልሸሸም፤ በሕይወቱ የተጻፈውን በመጥቀስ አሸነፈ እንጂ፡፡ ለእናንተ ለምትሰሙና ጆሮ ላላችሁ ደግሜ እላለሁ፡- ልጅነት ባለበት ፈታኙ አለ፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ሲመጡ - ሲወጡ ነው ሰይጣንም የሚወጣው - ጻድቁን ኢዮብን ለማጥፋት - ጌታ ሆይ÷ አከብርሃለሁ!

በኢዮብ ውስጥ የነበረውን ኢዮብን የገለጠው የተላከው ሰይጣን አይደለምን? … የእግዚአብሔር ልጆች ባሉበት በእርግጥ ሰይጣን አለ፡፡ የልጅነት መልካቸው ተፈትኖ ይወጣ ዘንድ፡፡ ይህ ግን ዛሬ ምድሪቱን ለሞሉ አገልጋዮችና በከንቱ ተስፋ ለሚነዱ ምዕመናን የሚነገር ወንጌል አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለእኛም የወሰናት ክብር ትገለጥ ዘንድ ፈታኙ እንደ ሚሠራ ግን እናውጃለን፡፡ ‹‹የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር›› ነው የነገረን (1ጴጥ.1÷11)፡፡ የዚህ ወንጌል ማኅበርተኛ ነን፡፡ ከዚህ ውጭ ከሚያታልሉት ጋር ኅብረት ከሚኖረን መካድን እንመርጣለን፡፡ ከአታላይቱ ይልቅ ከዳተኛይቱ ትጸድቃለችና፡፡

በፈተናና በመከራ ማን ምን እንደ ሆነ ይገለጣል፡፡ መጀመሪያ ጥቅስ በመጥቀስ የተገለጠው ፈታኙ በፈተናው አልቆመምና ቀድሞ ተለየ፡፡ ክርስቶስ ግን በመንፈስ ተሞልቶ ተመለሰ፡፡ ስለልጅነቱም በእግዚአብሔር ተመሰከረለት፡፡ ዲያብሎስ አሁንም ጊዜ አለው፡፡ አገልግሎት ተሰጥቶታል፡፡ እኛን ሊፈትን፡፡ ልጅነታችን ሊገለጥ፡፡ ጥቅሶች - የሰው ትምህርት - በገዛ ፈቃድ መጻሕፍትን መተርጎም.. ከእንግዲህ መሸሸጊያ አይሆኑም፡፡ እንደ ሰንሰለት ተያይዞ አንዱ በአንዱ ላይ እንደሚወርድ (የሚገለጥ) በረዶ የሐሰት መሸሸጊያችንን ይጠርጋል፡፡ ዲያብሎስ ከውጭ (ከመጽሐፍ) በራሱ የሌለውን ጠቀሰ፡፡ ክርስቶስ ግን ከማንነቱ ጠቀሰ፡፡ ዛፉም ፍሬውን ገለጠ፡፡ ዛፉ የተጠቀለለት ጥቅስ ያስተላለፈውን (ያፈራውን) ልብ ፈትኖ ሊያስተውለው ውድቅ አደረገው፡፡ ከዲያብሎስ (ከውጭ) የሚመጣው ከመጻሕፍት ቢሆን እንኳ በእርሱ ዘንድ ዋጋ አልነበረውም፡፡ ዛሬም የልጅነት ዛፍ (ፍሬ) ከውጭ - ከሰው የሚሰጠው (መርዛማ) ጥቅስ (አዎን÷ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ) - ፊደል - ቀለም በፍጹም አይቀበለም፡፡ ለዚህ ነው ውስጣችን ሰውን ለመስማት እምቢ ያለን፡፡ መንፈሳዊ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ መጽሔቶች፣ መጻሕፍት፣ ካሴቶችና በእነርሱ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች፣ ትምህርቶች፣ መልእክቶች፣ ጽሑፎች… ውስጣችን በፍጹም ጠላቸው፡፡

መከራ መጽሐፋችንን እንደሚገባን እንድናነብ ከውስጥም መገለጥ መሆን እንዳለበት ይነግረናል፡፡ ወርቅ ከአፈር ውስጥ ይወጣል፡፡ ወርቅ ከመሬት ጋር የተደባለቀ ነው፡፡ የወርቅ ማብለጭለጭ የመጽሐፉም መነበብ ከብዙ መከራ በኋላ መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ቢያጣም እውነት ነው፡፡ አፈር የደበቀውን ወርቅ የአንጥረኛው እሳት ይገልጠዋል፡፡ አቧራም የለበሰው መጽሐፍ በእግዚአብሔር ንፋስ ይነፃል፡፡

የሚጠበቀውን ጌታ ድንገት ወደ መቅደሱ የሚመጣው እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነው፡፡ እርሱ ሊያጠራ ይመጣል ይቀመጣልም (ሚል.3÷1-3)፡፡ ዲያቢሎስ፣ መከራ፣ መስቀል፣ ስቃይ… የአንጥረኛው እሳትና የአጣቢው እሳት ቢሆኑስ? … የእነዚህ አገልግሎት (በእኛ) በተፈጸመ ጊዜ እንደ ሙሉ ደስታ መቁጠሩን ክደንና ተቃውመን እየሰበክነው ያለው የዛሬው ‹‹መከራ የሌለበትና የመከናወን ወንጌል›› የት ድረስ ያደርስና ይደርስ ይሆን?

በአንድ ዘመን በእስራኤል መንግሥት ለንጉሥነት የተቀቡ ሁለት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሳኦልና ዳዊት፡፡ ሳኦል በሰው ጥያቄ፣ በሰው ልክ፣ በሰው ልብ፣ በአሕዛብ ዓይነት፣ እንደ ሰው ፈቃድ ተመረጠ - ተቀባ፡፡ሰውነቱን እየገለጠ - የሥጋ ሥራ (እያፈራ) እየገለጠ አርባ ዓመት ነገሠ፡፡ ዳዊት ግን በእግዚአብሔር ሐሳብ፣ በእግዚአብሔር ልክና ልብ ተገለጠ፡፡ የእግዚአብሔርንም ሐሳብ እየገለጠ አርባን (የፈተናና የመከራ ዓመት) የገዛ ዘመኑ አድርጎ እግዚአብሔርን አገለገለበት - የእግዚአብሔርንም ፍቅር ለሕዝቡ ገለጠ፡፡ ዛፎቻችን ዛሬም ዳዊትን ወይም ሳኦልን በገዛ ዘመናችን ማፍራታቸው አይቀርምና እንዴት እንደምንሰማ፣ እንደምናነብ እንጠንቀቅ፡፡

ትውልዱ መጽሐፎቻቸው የተገለጠላቸውን ከማኅበራቸው - ከከተማቸው አስወጥቷል፡፡ ክርስቶስን ወደ ውጭ ያስወጡት የሃይማኖት - የእምነት ቤተ ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱም ለራሳቸው ምስክርነትን ያገኙት - በራሳቸው ላይ ራሳቸው የመሰከሩት ያኔ ነው፡፡ ጥቂቶች ነቀፌታውን ዛሬም ድረስ ይሸከሙታል፡፡ ትውልዱም (የዛሬው) እነዚህን ወደ ውጭ ባስወጣና በጣለ መጠን የትውልዱ ምልክት መሆናቸው አልቀረም፡፡ ይህም ትውልድ ቢሆን በራሱ ላይ መስክሯልና ቤቱ የተፈታ ሁኖ ቀርቷል፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 5

Page 6: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ነቀፌታውን የተሸከመው ልጅነት ግን በገዛ ወገኖቹ የሚደርስበት መከራ ልጅነቱን የበለጠ ሠርቶ ይፈጽመዋል፡፡ መርኮክዮስን ወደ ንጉሥ በቅሎ ያመጣው ‹‹የመከናወን ወንጌል›› አይደለም በእርግጥ፡፡ የተገፋ - የተረሳ - የተሰደደ - የሐማ ሴራ ያሰቃየው አይሁዳዊ ሰው ነበር መርዶክዮስ፡፡ የአይሁድ ምሕረትና መታወቅ ያለፈው በሞት አዋጅ ነው፡፡ በመስቀሉ ልጅነትን ይገልጠዋል፡፤ ልጅነትም በመከራ ይጎላል አይከሰስም፡፡ መስቀሉ የሚያናውጠው

ነገር አለ፡፡ የሚለውጠው ነገር አለ፡፡ በዚህ ነውጥና ለውጥ ነው ‹‹የመቶ አለቃው ከእርሱ ጋር የነበሩት መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው ይህ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ›› ያሉት(ማቴ.27÷54)፡፡ መጽሐፋችሁን የምታነቡት፣ የምትተረጉሙትና ሌሎች የሚያነቡት እንዲህ ነው፡፡ (የሚቀጥል)

በዚሀ ዓምድ ሥር የሃይማኖት ማንነት (ምንነት አይደለም ማንነት) ስንጽፍ ማንም ስለ ምዕራባውያንና ምሥራቃውያን የሃይማኖቶችና የእምነት አይነቶች እንደምንጽፍ አያስብ፡፡ ሃይማኖት ከእነዚያ በጣም የጠለቀ ‹‹ሃይማኖት የለሽ›› የሚባሉት ሳይቀር በሥሩ የሚያኖር ሲሆን በሰው ልጆች ሁሉ የኖረ፤ ሁሉን ከአንዱ ከእግዚአብሔር ያራቀ የሰው የራሱ ከፍታና የጥበቡ መገለጥ ነው፡፡ ሰውና ሃይማኖት አንድም ሁለትም ናቸው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ ሰዎች ‹‹የእኔ›› የሚሏቸው ሃይማኖቶች እኛ ከምንለውና እግዚአብሔር ክፋቱን ካሳየን ከዚህ ሃይማኖት ቢቀዱ (ማስመሰያ ቢሆኑ) እንጂ በዚህ ዓምድ የምንጽፍበት አይደሉም፡፡ ሃይማኖት በዓለም ሃይማኖቶች ቢሠራ እንጂ በዓለም ካሉ ሃይማኖቶች ስለ አንዱ እንኳ አንልም፡፡ ሃይማኖት አንዳንዴ የሰው የስብዕናው መቀመጫ፣ አንዳንዴ ፍልስፍናው፣ አንዳንዴ ፈጣሪውን የሚያመልክበት የአምልኮ ሥርዓት፣ አንዳንዴ መንፈሳዊ ተቋም፣ አንዳንዴ ሰው በፈቃዱ የሚጥለውና የሚያነሣው በማንም ላይ ተጽዕኖ የማያደርግ ይመስላል፡፡ ሃይማኖት ብዙ ፊቶችና ራሶች ስላሉት ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡

ሃይማኖት የሰው(ነት) ሁሉ ራስ - የ’ኔነት ማማ

(ካለፈው የቀጠለ)

ከሃይማኖት መልእክተኛና ከዚህ ዓለም መንፈስ ነጽተን በመንፈስና በእውነት ወደምናመልክበት ስፍራ መምጣት ካለብን ጊዜው በእውነት አሁን ነው፡

፡ ‹‹ቤተ ክርስቲያን›› ላለፉት ሁሉ ሺህ ዓመታት በሰው ነገር ረክሳለች፡፡ ሰው ነፍሱ (Carnal mind) የፈጠረለትን ትምህርት፣ ጥበብ፣ ፕሮግራም፣ ሥርዓት፣ ቀኖና፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከትና ፍልስፍና ወደ ሃይማኖት መንዝሮ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ከሆነው ክርስቶስ አፈነገጠ፡፡ የሰው የነፍሱ በለዓማዊነት፣ ኒቆላዊነትና ኤልዛቤላዊነት… ሃይማኖት የሚያህል ግዙፍ አውሬ ፈጥሮለት ባሪያ በሆነበት ነገር ነፃ የሚያወጣውን መፈለግ ተሳነው፡፡ የበለዓም መንገድ፣ ስሕተት፣ ትምህርትና ደመወዝ እንዲሁም የኒቆላውያን ‹‹መንፈሳዊ ሹመት›› በእምነት ሥርዓት የበላይና የበታች መሆን (በአገልግሎት - በቅባት - በስጦታ - በሹመት ስም) … ቤተ ክርስቲያንን አርክሰዋል አስነውረዋልም፡፡

አባት ግን በዚህ ጊዜ የመረጣቸውን ከዚህ ዕድፍ - ርኩሰት ሊያጠራ በቃሉ መንፈስ እየጠራ አይደለምን? ከባቢሎን የወጣና ባቢሎን የወጣለት (ያስመለውሰ) ወገን በእርግጥ ያስፈልጋል፡፡ ጌታ እግዚአብሔር በመስቀሉና በመንፈሱ አሠራር በሕይወታችን ጥልቅ የሆነ የመቀደስና የማጥራት ሥራ እየሠራ ለመሆኑ ምስክሮች አሉ፡፡ የእርሱ ካልሆኑ እርሱም ከማያውቃቸው ብዙ የሰው፣ የዓለም፣ የሰይጣን ነገሮች ነፃ እያወጣን ነው በመንፈስ እየሰማነው ባለው ሕያው የእግዚአብሔር ቃል፡፡ ብዙ የቀደሙ - በመጀመሪያ የሰማናቸው፣ የኖርንባቸው፣ የበላናቸውና የተለማመድናቸው ነገሮችን እያስታወክን (ለቃሉ ይቅርታ!) ነው፡፡ የሰውና ‹‹የቤተ ክርስቲያን ነገር›› እየወጣልን አርነት እየወጣን ነው - የድንቆች ድንቅ!

እንደ ለማኝ እንጀራ ከብዙ ነገር ጋር የተደባለቀው ሃይማኖት - የሰው ነፍስ ሥራና እዚያና እዚህ የምንረግጥለት አቋም የለሽ ያደረገን አስተምህሮው ሁሉ በመጸየፍና በሰማያት ኃይል ክእርሱነቱ ሁለንተና ሙሉ በሙሉ ነፃ በመውጣት እርሱንም ፈጽመን በመተው በሰማያት ወደ ተዘጋጀልን ከፍታና ድል መንሣት ልናርግ ተገብቶናል፡፡ ሁል ጊዜ በነገር ሁሉ ጌታንና ጌታን ብቻ አምነንና በእምነታችን ኖረን መጽናት፣ መጽናናትና መንጻት ጥረአችን ይሁን፡

፡ ጌታ በአፉ ሰይፍ የሚያጠፋቸው (ራእ.2÷16) በለዓም፣ ኒቆላውያና ኤልዛቤል የተገለጡባቸው ሃይማኖታዊ ሰርኮችና የሚያመልኩባቸው ከፍጻሜ ከመድረሳቸውና ከመቀጣታቸው በፊት ንስሐ - መመለስ ከእኛ መንቃት ይጠበቃል - እንደ ልጆች!

ለልጅነት የተጠራን ሁላችን ከበለዓም መንገድ፣ ከበለዓም ስሕተት፣ ከበለዓም ትምህርት፣ ከኒቆላውያን መንፈሳዊ እልቅና፣ ዘውገኝነትና የበላይነት እንዲሁም ከኤልሣቤል ሴሰኝነት፣ አመንዝራነት፣ የሥልጣን ብልግና፣ የመንፈሳዊ አገዛዝ ቁማር… ንስሐ ልንገባና ልንመለስ መንፈስ ቅዱስ ግድ እያለን ነው፡፡

ትውልድ ሆይ÷ ለጣዖት የተሠዋውን በልተሃል

‹‹ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴሲኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባለቅን ያስተማረ የበለዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ÷ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ›› (ራዕ.2÷14)፡፡

የበለዓም ትምህርት የእግዚአብሔር ለጣኦት የተሠዋውን እንዲበላ ያታለለና ያሰናከለ ነበር፡፡ በለዓም ባለቅን ያስተማረው ዋና ነገር ይሄ ነበር፡፡ እስራኤል ሁለት ነገር በማድረግ አምላኩን እንዲበድልና እንዲጣላው በለዓም ባለቅን አስተማረው፡፡ እነዚህም ሁለት ነገሮች መብላትና ማመንዘር ናቸው፡፡ ‹‹የሰው ሁለቱ ኃይለኛ ፍላጎቶች (the two most powerful human passions) እነዚህ ናቸው፡፡ መብላት በመንፈሳዊ ትርጉም ምንን ያሳያል?... መብላት እንደ መጽሐፉ መንፈስ የምንበላው የምናስገባው ማንኛውም ዓይነት አስተሳሰብ … ምሳሌ ነው›› ይላል የተወደደው ወንድም፡፡ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ መንግሥተ ሰማያት፣ ስለ ዘላለም ፍርድ፣ ስለ ሲኦል፣ ስለ አውሬው፣ ስለ ምጽአት፣ ስለ መጨረሻው ዘመን፣ ስለ… ወዘተርፈ ወደ ውስጣችን ያስገባናቸው ትምህርቶች፣ አስተሳሰቦች፣ መረዳቶች፣ ትርጉሞች…. እንደየ ባለ ራእዩ… ዓይነት እጅግ በመብዛቱና በመለያየቱ ለመንፈሳዊ ነገር በተለይም ስለ እግዚአብሔር ዓላማ፣ ፈቃድ፣ ፕሮግራም፣ መንፈስ፣ ግብና መጨረሻ… የሰጠነው ትርጓሜና መረዳት ትምህርት ሃይማኖታዊ ጣዖት ፈጥሮብናል፡፡ እግዚአብሔርን እንኳ በምናባችን የሳልንበት

ገጽ 6 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 7: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

(የትምህርታችን ውጤት የሆነው) መረዳት ከጣዖት ወይም ከአንድ የአሕዛብ ጨካኝ አምባገነን ወይም ደግ መሪ በላይ ሊያሳየን አለመቻሉ ያሳዝናል፡፡ ከሁሉም የከፋው ግን በሥጋዊ አእምሮአችን ለእግዚአብሔር የሰጠነው ሐሰተኛ ምስል - የሃይማኖት ጣዖት ነው፡፡ በግድግዳ ላይ የተሳለው ‹‹የእግዚአብሔር ምስልና›› በልባችን ስለ እግዚአብሔር ያለው ‹‹አካላዊ ምስል›› ልዩነት የሌላቸው ጣዖታት ናቸው፡፡

እውነትን አብዝቶ - ቀንሶ - ጨምሮ መቀበል፣ እውነትን ማደብዘዝ፣ እውነትን መሸቀጥና ከሐሰት ጋር መቀላቀል፣ እግዚአብሔርን በፈጠረው መምሰለ፣ ማስተያየትና መሳል… ሃይማኖታዊ ቅርጽ (Image –idol) መስጠትና የመሳሰሉትን በትምህርት መቀበል በተበከለ መረዳት መንፈስን ማርከስ ነው፡፡ ለጣዖት የተሠዋውን መብላት ይህንን ይመስላል፡፡ እንዲህም ይፈረጃል፡፡ ስለ እግዚአብሔር በተፈጠረ የሰው ሐሳብ ምክንያት የሚቀርብና የሚበላ ትምህርት ሁሉ ርኩሰት ነው፡፡ ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ (ቃል) ነውና፡፡ ዛሬ ምን እንደምናንብና ምን እንደምንሰማ መጠበቅ/መጠንቀቅ አለብን፡፡ እንደ አቴና ሰዎች በሰው ሐሳብ ለተፈጠረና ለፈጠርነው አምላክ ስለ እርሱም የምንማረው ትምህርት ነው ለጣዖት የተሠዋ መብል የሆነብን፡፡ ይህም የእያንዳንዳችን የነፍስ/የባቢሎን ትምህርት፣ አገልግሎት፣ ፕሮግራምና እምነት ነው፡፡ ‹‹… በለዓምንና ያስተማረውን፤ ለጣዖት የተሠዋውን መብላትና በትምህርት መዳራት - ማመንዘር ከራሳችሁ (ከነፍሳችሁ) ውጭ የትም - ከየትኛውም ድርጅት እንዳትፈልጉት፡፡ አገልጋይ ይሁን ምዕመን… ይሁን አንተ ውስጥ አሉ፡፡›› (አቤ ፕሪስተን)፡፡

ዛሬ በቃሉ መንፈስ ትነፃ ዘንድ ብትወድድ፣ ትምህርትህን፣ መረዳትህን፣ እምነትህን፣ መንፈስህን…. መርምር፡፡ በከንቱ አትመካ፡፡ ለጣዖት የተሠዋውን የምትበላና የምታበላ ጳጳስ፣ ሐዋርያ፣ ነቢይ፣ መጋቢ፣ ቄስ፣ ካህን፣ ኤፒስቆጶስ፣ ምዕመን… አንተው ልትሆን ትችላለህና ራስህን አንፃ፡፡ ሐሰተኛው ሃይማኖታዊ ሥርዓት፣ አሠራርና ፕሮግራም የአባታችንን እውነትና መንፈስ ተክቶና አጥፍቶ አረም ዘርቶብንና አብቅሎብን ቢሆን ምን ያህል እርግጠኞች ነን?... ይህም ሁሉ የሆነውና እየሆነ ያለው እያስኬድነውና እያገለገልንበት ባለ ራእይ፣ አገልግሎትና ተልዕኮ ቢሆንስ?! እግዚአብሔር ከመንፈሳችን ጋር ይመስክር - ይሁን!

ለጣዖት የተሠዋውን ከመብላት ቀጥሎ የሚመጣው በለዓም ያስተማረው ማመንዘር ምንድር ነው? በዚህ በራእይ (2÷14) መጽሐፍ መንፈስ ደረጃ ማመንዘር የሚባለው በሥጋ ማመንዘር ሳይሆን መንፈሳዊ ማመንዘር ነው፡፡ መንፈሳዊ ማመንዘር ምንድር ነው? … ዛሬ እንደ መንፈሳውያንና እንደ መንፈሳዊ ተቋም ከጋብቻ ውጭ ከተቃራኒ ፆታ ጋር የሚደረግ ወሲብን ጨምሮ ሰዶማዊነትን - ሴት ከሴት ጋር፣ ወንድ ከወንድ ጋር የሚደረግን ዝሙት በቃለ መጠይቆቻችን፣ በጽሑፎቻችን፣ በስብከቶቻችን፣ በፓናል ውይይቶቻችን፣ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በማኪያቶና በቡና ሲኒዎች ዙሪያ… አውግዘናል፡፡ የመሰለንን ብለናል፡፡ ፈርደናል፡፡ በጉዳዩም ላይ ከደሙ እንደ ነፃን እጃችንን የታጠብንም እንኖራለን፡፡ ግን እያንዳንዳችን በራሳችን ራሳችን እንደምናመነዝር አናውቅ ይሆን? ሥጋዊ/ፍጥረታዊ ሰዶማዊነት በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰዶማዊነት ግን እጅግ በጣም የተጠላ ነው፡፡ በመንፈስ ያመነዘሩ በሥጋ ካመነዘሩት እኩል አይፈረድባቸውም፡፡ በሥጋ ያመነዘሩ ቁስል፣ በሽታ፣ ደዌ… አያጣቸውም፡፡ በመንፈስ ያመነዘሩት ግን ሲዖል አያነጻቸውም፡፡ እንደ መንፈሳውያን በዚህኛው ሰዶማዊነት ላይ መቼ ሰላማዊ ሰልፍ እንደምንጠራና እንደምንሰበሰብ ግን አላውቅም፡፡

‹‹ከታጨንለት አንድ ወንድ…›› (2ቆሮ.11÷2) አፈንግጠን የማገጥነው‹ የባለግነው፣ ያመነዘርነው…

ስንት ጊዜ ነው በየትምህርቱና መረዳቱ?! በየሚኒስትሪው መድረኮች፣ የ‹‹መንፈሳዊ ቴሌቪዥን›› በሚሰጡ ትምህርቶች ምክንያት በመንፈስ የጀመርነውን የለቀቅነውና ለሰው ስሜት የተጋደምነው ስንት ጊዜ ነው? … በጌታ ማደግና ማፍራት ሲገባን ዛሬም ከዚህን ያህል ዘመን በኋላ የፕሮግራሞች ጥገኛ የሆንበት ምክንያት የእነዚህ የማምለኪያ አጸዶች (መድረኮች፣ ጣቢያዎች፣ አዳራሾች…) አመንዝሮች ስለሆንን አይደለምን? በነፍስ ስፍራ - ክበብ (realm) የሚፈጸሙ መንፈሳዊ የሚመስሉ እንቅስቃሴዎች፣ አገልግሎቶች፣ ቅባቶች፣ ሹመቶች፣ በረከቶች የዘመኑ በለዓማውያን የሰጡንና ያመነዘርንባቸው ትምህርቶች ቢሆኑስ?

ክርስቶስ ጌታ የዘራብንን ዘር፣ ክርስቶስ የሆነው መንፈሳዊ ሕይወታችን በሰው ሠራሽና ፈጠራ (ሃይማኖታዊ) ሥርዓትና ፕሮግራም ያበላሸነውና የክርስቶስ ሕያውነት ከሰው በተቀበልነው ‹‹አትያዝና አትቅመስ›› ሕግና ደንብ፣ ወግና ባሕል ጋር ያደባለቅነው የማይጠራም ያደረግነው… ስንት ጊዜ ነው? ይሄ ነው መንፈሳዊ ምንዝርና፡፡ ይሄ መልእክታችን ብዙዎችን የሚያስቆጣ ይሁን እንጂ እውነት አይደለምን? … ስንትስ ጊዜ ነው ራሳችንን በሥጋዊ ሥርዓት፣ በሰውነት መንገድ፣ ዘዴ፣ ጥበብ፣ ፕሮሞሽን፣ ዓለማዊነት በዋጠወ ሃይማኖታዊ ወግ የነፍሳችንን ፍትወትና ፍላጎት በሃይማኖት መንፈስ ሳለን ‹‹በጌታ ስም›› ልናረካ የተጋነው?... ይህ ነው መንፈሳዊ ምንዝርና፡፡

ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ነበር፡-‹‹በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ትፈጽማላችሁን?›› (ገላ.3÷3)፡፡ ይሄ ነው ተወዳዳሪ ያልተገኘለት መንፈሳዊ ማመንዘር፡፡ በለዓማዊነት ያስተማረው ማመንዘር በዘመናችን ከፍ ከፍ ያለ መንፈስ ይሄ ነው የተወደዳችሁ ሆይ፡፡

መንፈሳዊ ምንዝርና ከነፍስ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለ ነፍስ ክፋት ነው በበለዓም፣ በኒቆላውያንና በኤልዛቤል መንፈስ ጠልቀን የምናየው፡፡ የነፍስም ትልቁ ችግር (በሥጋ) ኃጢአት መሥራቷ አይደለም፡፡ ነገር ግን ያለ መንፈስ - ለነፍሳችን ሳትገዛ ጌታን ለማገልገል ራስዋን መሾሟና መቀባቷ ነው፡፡ ይህ ነው የዘመናችን አገልጋዮችና አገልግሎቶች መንፈስ - ጸጋ - ትጋት - ራእይ - ተልዕኮ፡፡ ማንም ከዚህ መልእክት ራሱን ቢያነጻ ምስጉን ነው፡፡ ነፍስ በመንፈስ መመራትን አይወድም፡፡ ያመልካል - ያገለግላል - ይሰግዳል - ይጾማል - ይሰጣል… ሥርዓትን ሁሉ ይፈጽማል፡፡ ግን እያታለለንና እያረደን ነው፡፡ ነፍሳችን ሞቷን ጠልታ፣ መከራን አውግዛና ንቃ፣ ለክርስቶስ መስቀል ጠላት ሁና… በመከናወን፣ በድል፣ በብልጽግና፣ በመግዛት… ‹‹ወንጌል›› ልታገለግል መሻቷ ስፍራን መተውና እንግዳን ሥጋ መከተል ነው - ማመንዘር! በዚህ ዓይነት ነፍስ ለሚኖርና ለሚያገለግል ሰው (አገልጋይ) ለራሱ ከሰይጣን መቶ እጥፍ የከፋ ጠላቱ ነፍሱ ነው፡፡ ‹‹መንፈስን የሚያጠፋ የመንፈስ እንቅፋት የነፍስ አምልኮና አገልግሎት ነው፡፡ አስቀድሜ እንዳልኩ ‹‹ይህ እጅግ አደገኛ አሳች ሥጋችን (የነፍስ መገለጥ) በመንፈስ የተጀመረውን በሥጋ ሊጨረስ የጣረ ያደረገውም አጥፊ ነው - የጥፋት ልጅ! ‹‹ነፍሳችን ሙሉ በሙሉ ለመንፈሳችን ካልተዋረደ - ካልተገዛ፤ ሙሽራይቱ ለሙሽራው እንደምትገዛ ሙሉ በሙሉም እንደምትማረክ ካልተማረከ - ሙሽራይቱ ነፍስ ለሙሽራው መንፈስ በመገዛት ካልተጋባች (እንደ በጉ ሠርግ ሥርዓት) ነው በመንፈስ ጀምሮ በነፍስ (በሥጋ) መጨረስ›› (willam Law)፡፡

በራእይ(በዮሐንስ) መልእክት የተጠቀሱት ሦስት፡- በለዓም፣ ኒቆላውያንና ኤልዛቤል እንደ ቅደም ተከተላቸው ልንረሳቸው አይገባም፡፡ እነዚህ በእያንዳንዳችን ያሉና የሠሩ በመሆናቸው ድል ልንነሣቸው ይገባናል፡፡ የበለዓም ትምህርት፣ መንገድ፣ ስሕተትና ደመወዝ ብዙ አስተምረውናል፡፡ በለዓም እስራኤላውያን ይሰናከሉና በመሰናከላቸው እግዚአብሔር

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 7

Page 8: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ይጣላቸው ዘንድ ያንንም ባላቅ ያደረገው ዘንድ ባላቅን አስተማረ፡፡ እስራኤላውያን ይረክሱና ከእግዚአብሔር መንገድ ተሰናክለው ይወድቁ ዘንድ በለዓም ባላቅን ያስተማረው ካስተማረው ለሚሻቸው ክብር፣ ሽልማት፣ ገንዘብ፣ ስምና ዝና ነበር፡፡ በሁሉም ባይሆን በብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ዘንድ ሁሌም ያለው የገንዘብ ቅጥረኝነትና የሃይማኖት ቁማርተኞች ጉዳይ የበለዓም መንገድ፣ ስሕተት፣ ትምህርትና ደመወዝ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ‹‹በሀብት፣ በዝና፣ በመንፈሳዊ ጨዋታ፣ በሰው አፍ… ትልቅ ስፍራና ስም የያዙ የመድረክና የቴሌቪዥን ሰባኪዎችና ፈዋሾች ካለፉት ሰባ ዓመታት ጀምሮ በበለዓም መንገድ ያከማቹት ከብርና ሀብት ልክ የለውም፡፡›› መንግሥታት በየሀገራቸው ስለ ሙስና ሲያወሩና እርምጃ ሲወስዱ ከባለ ሥልጣኖቻቸውና ከሚመሳጠሯቸው ነጋዴዎች ውጭ አያወሩም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና በሚስትሪዎች አካባቢ የተሰበሰበው የ®Sí ሀብት መንግሥታት አንዳች አለማለታቸው ምክንያቱ ይሆን?

በዮሐንስ ራእይ (መልእክት) የተጠቀሱት ሦስቱ የጥፋት አካሄዶች ማለት በለዓም፣ ኒቆላውያንና ኤልዛቤል ፈጽሞ ልንረሳቸው አይገባም፡፡ ይሄ በእያንዳንዳችን ያሉ - የሠራና እየሠሩ ያሉ በመሆናቸው ድል ልንነሣቸው ተገባን፡፡ ኒቆላዊነት መንፈሳዊ ሹመኝነት ነው ብለናችሁ ነበር ባለፋት ብዙ ዕትሞቻችን፡፡ የኒቆላውያን ትምህርቶች ሁል ጊዜ አንዱን የበታች ሌላውን የበላይ (አለቀና ምንዝር - ጌታና ሌሎ - ካህንና ምዕመን - እረኛና በጎች) በማድረግ የሚሠራ ነው፡፡ ይህንንም አሠራሩ ሕዝቡን ለማሳደግ ሳይሆን ለሁል ጊዜም የሚገዛበትና የሚያስተዳድርበት ሙያው ነው፡፡ ራስ በሆነው በክርስቶስ የአንድ አብ ልጆችና ቤተ ሰብ የሆንበት መንፈስ በሹመት መንፈስ በማዘናጋት ያስረሳል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት ምሩቁን በመሆናቸው፣ በማዕረጋቸው፣ በስማቸው ፊት ለፊት በለጠፉት ሹመት/ ማዕረግ፣ አገዛዝ፣ ቅባት፣ ዝና፣ ስም፣ ሕግና ሥልጣን ትዕዛዝም ሕዝቡን ይገዛሉ፡፡ በትህትና መንፈስ ከማገልገል ይልቅ በተጠቀሱት በአነዚህ ሁኔታዎች ሕዝቡን ሲመሩና በሕዝቡ ሲገለገሉ ይታያሉ፡፡ ይሄ የኒቆላውያን መገለጥና መንፈስ ዛሬ እስከ የት እንደደረሰ ከማኅበራችን ውጭ የትም ማየት የለብንም፡፡ ነፍስ በልዩ ልዩ ‹‹መንፈሳዊነት›› እና አታላይነት (sebtle way) የሄደበት እርቀት በመንፈስ መገለጥ በቀር ማየት አይቻልም፡፡

ራስን የተቀባና የበላይ ሌላውን ግን ታናሽ አድርጎ የማየት መንፈስ በእነዚህ በኒቆላውያን ዘንድ አለ፡፡ ይህም መንፈስ በምዕራባውያን ካቶሊኮች ዘንድ ተመሥርቶና ደርጅቶ ሲያበቃ መንፈዊ እልቅናን የምሥራቆቱ ኦርቶዶክሶች ተቀብለው አጠኑት፡፡ ከማን አንሼ ፕሮቴስታንቶችም እስከ ካሪዝማቲክ ዘመናቸው ድረስ ናኙበት፡፡ ለሁሉም ከልካይ አልነበረባቸውም፡፡ ኒቆላዊነትን እግዚአብሔር ይጠላዋል፡፡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የገባ የአገልግሎት ሥርዓት ነው መንፈሳዊ እልቅና፡፡ መንፈሳዊ ሹመትም የምናገለግልበት መሆኑ ቀርቶ የምንፈራበትና የምንከበርበት ሆነ፡፡

አስተዋላችሁን!? የመጀመሪያውና በለዓማዊነት በአገልግሎት - በማዕረግና በገንዘብ ቅጥረኝነት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከሥጋና ከዓለም ጋር በማጋባት የእግዚአብሔር ሥራ በውስጣቸው እንዲረክስ አደረጉ ብዙዎች፡፡ ሁለተኛውና ኒቆላዊነት በውጫዊ አገዛዝ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሥልጣን ገዝተውታል በቅንነትም ያለቅንነትም፡፡ ከግብፅ የወጣውን ሕዝብ በመግዛትና በመምራት ‹‹የተጠቀሙ››፣ ‹‹ያተረፉ›› እና እነርሱ እንደሚሉት ‹‹የተባረኩ›› አሉ ግብፅ ግን ከውስጡ ያልወጣለትን ሕዝብ በመምራት…፡፡ እግዚአብሔር ግን ከግብፅ ያወጣውን ሕዝብ ግብፅ ከውስጡ እሰኪወጣ በምድረ በዳ የመራውን፣ የተሸከመውን፣ ውግያ ያስተማረውንና በመከራ የፈተነውን ሕዝብ አስቡ፡፡ በሁሉ ነገር እኛን ድል በመንሣት ሊያዞረንና ወደ ዙፋኑ ሊወስደን

ከበለዓማዊነት፣ ከኒቆላዊነትና ቆይተን ከምንነጋገርበት ከኤልዛቤል ድል መንሣት ሊኖርብን ነው፡፡

ኤልዛቤል

ከእነዚህ ሁለቱ በተጨማሪ በሦስተኝነቱ በዚሁ በራእይ መጽሐፍ ኤልዛቤል ትገለጣለች፡፡ ኤልዛቤል ራስዋን ነብይት ብላ ጠርታለች፡፡ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ ታስተምራለች ታስታለችም፡፡ የምታስተው ደግሞ ባሪያዎችን ነው - የጌታ ባሪያዎች - ልብ አድርጉ፤ ለምንም ባሪያ ሳይሆኑ ለጌታ ባሪያ የሆኑትን - አስደናቂ ነው!

በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ - እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፡-ሥራህንና ፍቅርህን፣ እምነትህንም፣ አገልግሎትህንም፣ ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ፡፡ (ራዕ.2÷18-20)፡፡

ኤልዛቤል÷ ስምዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ የታወቀና ዝነኛ ቢሆንም አንድ ወንድም እንዳለው የትኛውም ወላጅ ለሴት ልጁ የሚመርጠው ስም አይደለም፡፡ ከትርጉም ሆነ ከሚገልጸው ባሕሪ ፈጽሞ ለአንድ ጨዋና ለከበረ ቤተ ሰብ (ትዳር) የሚመርጥ ስም አልሆነም፡፡ ኤልዛቤል የኤት በኣል ልጅ ነበረች ይለናል መጽሐፍ(1ነገ.16÷31)፡፡ ኤት በኣል የሲዶና አገር ገዥ እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን የአስታሮት (የሴት አምላክ) ካህንም እንደ ነበረ መጽሐፍ በድጋሚ ያስታውሳል፡፡ የዚህ ሰው የስሙ ትርጉምም ‹‹ከበኣል ጋር›› ማለት ነው፡፡ ይህ(ች) ጣዖት የፍትፈወት፣ የወሲብ ስሜት … አምላክ - ሴት አምላክ (goddess) ነበረች፡፡ ኤልዛቤል ገና ከሕፃንነቷ ጀምሮ የሐሰት ሃይማኖትና በውሸት ላይ የተመሠረተ አገዛዝ ቤተ ሰብ ተመልካችና ተለማማጅ ሁና አድጋ እንደ ነበረ አያሌ ጻፍት ይስማማሉ፡፡ ኤልዛቤል ብዙ አክብሮት፣ መፈራት፣ ለባለ ማዕረግ መስገድና ማጎብደድ በሞላበት፣ ክብርና ሥልጣን… ከሰው በላይ በገነኑበት ቤት፣ ሁኔታ፣ ከባቢ… እንዳደገችም ይታመናል፡፡ ‹‹በፖለቲካ የማጭበርበር አርት፣ ሽፍጥ በማያጣው የፖለቲካ ጥበብ ባለበት ያንንም እንደሚገባ ጠጥታ የምታድግበት ስፍራ ላይ ነበረች›› ይላል አንድ መንፈሳዊ አባት፡፡ በጥልቀትም የጠጣችው ይህንኑ ነው የኋለኛው ሕይወቷ ሲጠና፡፡

ከላይ የጠቀስኩት መንፈሳዊ አባት፡- ‹‹ኤልዛቤል የሚለው ስም በኣል ከፍ ከፍ አለ - በኣል ከበረ የሚት ትርጉም ያለው ሲሆን ያልተገራ - ባለጌ - ያልተቀጣ - ልቅ የሚል ስሜትም ያለው ትርጉም ይለናል፡፡ በሌላ አባባል የረከሰች - ወሲብን ባልተገራ መንገድ የምታለማምድ - ከልብ (ከውስጥ) የሚፈስስ ምንዝርነት ሁሉ… ጋር የሚተካከል ትርጉም አለው፡፡ የኤልዛቤል ስም የባሕሪይዋ አመልካች ብቻ ሳይሆን ሕይወቷ ወደፊት የሚመስለውንም ይተነብያል፡፡ እርስዋ የእርኩሰት፣ የብልግና፣ የመዳራት የፀረ - ጨዋነት፣ የልቅነት… ምሳሌና አራቢ እንደ መሆኗ በዘመናት ሁሉ እርስዋን በመምሰል ከሰው(ነት) የወጠና የወረዱ እንስት እንስሳቶች (ሴቶች) ብዙ ነበሩ፡፡ እነዚህ ሴቶች ሁሌም አልዜቤልን መስለውና ገልጠው ኖረዋል፡፡›› (የጥቅሱ መጨረሻ ) (ይቀጥላል)

ገጽ 8 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 9: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

መሆኔን ከልክለውወዬው! - ጉድ - አስብሎ - ወዲያው የሚረሳ

መሆኔን ከልክለው - የስዕል አንበሳ

መዓዛው ማያውድ - የስዕል ላይ - ሽቱ

መሆኔን ከልክለው - የወረቀት ፎቶ

ቁጣው! - ማያሸብር - የስዕል ግስላ

መሆኔን ክልክለው - የወረቀት ቢላ

ዓውሎ ንፋስ አጫጅ - ትጉህ! ንፋስ ዘሪ

መሆኔን ከልክለው - ወሬ - ኩሎ - ዳሪ

ሙክት - ሰንጋ ሚጥል! - የወሬ ፍሪዳ

መሆኔን ከልክለው - አፍቃሪ ቀዳዳ!

መድረሻው - ግብ አልባ - ወደ- የትም ተጓዥ

መሆኔን ከልክለው - ሕያዋንን ገናዥ

መክሊት የሚታቀፍ - ማይዘራ ገበሬ

መሆኔን ከልክለው፡ - ተግባረ ፍካሬ!

የመቃብር ኖራ - ውበት - ላይ - ላይ

መሆኔን ከልክለው፡ - አፈ ወንጌላዊ

ቆፈን የሚንቀው - የወረቀት ላይ - ፍም! መሆኔን ከልክለው፡ - ታፔላ! ባለስም

ዕፎይ! - ማይሉበት - የስዕል ላይ ፍራሽ

መሆኔን ከልክለው - አፅኚ ሊባል - አድራሽ

ላም አለኝ - በስዕል - ናፍቆቶችን

ምኞቶችን - አርቢ

ጉጉቶችን

መሆኔን ከልክለው - ቃል የለሽ - መጋቢ

ማንንም ማያግድ - የስዕል እረኛ

መሆኔን ከልክለው - አልባል- ‹መናኛ!፡፡›

(አቤ ነኝ)

ቀን ነውና አሁንም እንተያይ፤ በቀን ጨለማ ቀርቶ የጨለማ ቁራጭ የለምና፡፡ እንደ አምላክና እንደ አባታችን ፈቃድ ከተሰወርንበት መገለጥን ለሚያደርግ ለአባታችንና ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!!

እንዲህ ናት እንዲያ ናት የማይባልለት በመካከላችን ያለች የአምላካችን ፈቃድ በእኛ ናት እኮ ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን!!

ወንድምና አምላካችን ክርስቶስ ጌታ በፀጋው ባለፀግነት ከተደረግንበት ለፍጥረት ሁሉ ሊለቀን ዘርን በእኛ ያደረገው ለመከሩም የታመነ ነው፡፡ ያለታመነ እንደሆነ ትዋልላላችሁ እንዴ? ይህ የሮቤል እንደሁ እንጂ የክርስቶስ ልብ አይደለም፤ ግን ሮቤል አይሙት በሕይወት ይኑር ተብሎ ተጽፎዋልና፤ እርሱም ተስፋ አለው፡፡

እንግዲህ አሁን በእኔ አሜን የሆነው በእናንተም አሜን ነውና በእርሱ ዘንድ መለወጥ የለምና የወሰነው እርሱ የድፍረት እንጂ የፍርሃት መንፈስ ስላልሰጠን ለእርሱ ክብርን እናበዛለን! ሃሌሉያ!

የዓለም ብርሃን ናችሁ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ፍለጋውን አሳይቶናልና የአባቴ ብሩካኖች ሆይ! እነሆ! ክረምቱ አልፎ ዝናቡም አባርቶ አበቃ አበቦች በምድር ላይ ታዩ የዝማሬ ወቅት መጥቷል የርግቦች ድምፅ በምድራችን ተሰማሩ፡፡ መኃ.2÷11-12፤ 14… ፊትሽን አሳይኝ ድምፅሽንም አሰሚኝ ድምፅም ውብ ነውና፡፡ ተነሽ! እህቴ እንተያይ!

ጎኑን ሲመታ የማይነሳ በድን እንጂ በእኛ የተነሳው ክርስቶስ እንዲህ አይደለም፡፡ ለእኛ እርሱ ትንሳኤም ነውና በተደረግንበት እንተያይ እንጂ? መቸስ እኛ እንደገና ለባርነት መጋረጃ አንጥል ያልተጣለብንን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ጠርቆ ያስወገደውን (የገፈፈውን) ትለብሱ ዘንድ ማን አዚም ጣለባችሁ? … ውሾች በተገኙበት ማዕድ መገኘት ላልሆነላችሁ እጽፍ ዘንድ እኔም ከደሴ መንፈስ ቀሰቀሰኝ ነው የምላችሁ አሜን በሉ እጅ - አሜን ነው!?

በርግጥ የሀገራችን ሰዎች ሲተርቱ ‹‹ውሻ በበላበት ይጮሀል›› ለፍራፍሪው ማለት ነው መብሉም እሱም እንደሚጠፉ ትዕዛዝ እንደወጣ መንፈስ ሹክ አላላችሁምን? ለውሻ የተሰጠው ያውም ጩኸቱ ነው፡፡

ወደ ገጽ 13 ዞሯል

ባልንጀሮች እንተያይ!!

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 9

Page 10: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

የእግዚአብሔር ምሕረትና እውነት በተገለጠበት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተዋጁትና ዳግመኛ የተወለዱት ቅዱሳን በአንድ ዘመን በአንድ ስፍራ ከኖሩት ሕይወት የተነሣ ‹‹ክርስቲያን›› ተባሉ፡፡ የእነርሱም ሕያውና እውነተኛ ኅብረት ቤት - ክርስቲያን የሚል ማንነት አገኘ፡፡ ይህ የጌታ አካል በዓለም በመሆኑ ለዓለም ጨው ሆነ፡፡ ይህም የጌታ አካል በልጅነት ሲፈጸም የፍጥረት ናፍቆት የሆነው የእግዚአብሔር ልጆች ክብር መገለጥ ነው፡፡ ይህ ጨው ሆነ፡፡ ይህ ጨው የሆነው የጌታ ስብስብ በሁሉ ፊት እንዴት መመላለስ አለበት?... ቤተ ክርስቲያን ከእርሷ ያለፈ በውጭ ላሉት የምታሳየው ሕይወት ሊኖራት ይገባል፡፡ ቤተክርስቲያን ከቃልና ከስብከት ባለፈ በሕይወትና በምልልስ እግዚአብሔርን ለዓለም መተርጎም አለባት፡፡ ክርስቶስን (እርሱ ሕይወት ነው፡፡) በኑሮ ሁሉ ወደ ዓለም ካላወረድነው - ካልመነዘርነው ‹‹ክርስቶሳችን›› በዓለም ከተነሡት ከአንድ የሃይማኖት መሥራችና መሪ የተለየ አይደለም፡፡ … ይህ ጨው አልጫ ቢሆን ግን ዋጋው ምን ያህል ነው?

በዚህ ዐምድ ሥራ የኃላፊነታችንን ልክ፣ የተጠያቂነታችንን ብዛት፣ የነፃነታችንን ዕዳና የልጅነታችንን ክቡር መሥዋዕትነት… ይጽፋሉ፡፡ ጌታ ለስሙ የሚሆን ወገን ከዓለም የወሰደው ለዚያው ለዓለም ነው፡፡ እግዚአብሔር የጠራን ምንጭ ከባሕር ከቀዳ በኋላ ያንኑ ምንጭ (ወንዝ) ወደ ባሕር ይፈስስ ዘንድ ይመልሰዋል፡፡ ባሕሩም ይፈወሳል፤ዓለም እየበሰበሰች ነው፡፡ በሌላ ወገን ከዚህ ከመበስበስ ባርነት ነፃ የሚያወጡ እየተሰናዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር የታመነ ነው፡፡

የማኅበረ ሰብ ጨው

ባለፉት ጥቂት እትሞች በዚህ ዓምድ ሥር የተጻፉት ማስታወሻዎች በቀጥታ የጌታን ቤተ ሰቦች ማለት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን የተመለከቱ

ነበሩ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ላለችበት ማኅበረ ሰብ ጨው መሆን አንዳለባት ጽፈን ነበር፡፡ ዛሬ ግን በተለየ መልኩ መንግሥት ወይም መሪዎች ለሚመሩት ሕዝብ እግዚአብሔርን ወክለው ምሳሌ በመሆን የጨውነታቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ልንላቸው የተቀባውን ብዕራችንን አንሥተናል፡፡ በእርግጥ ለይቶ በአንድ ወገን ላይ ይጻፍ እንጂ (አስቀድሞ እንዳደረግነውና ዛሬም እንደምናደርገው) ማንም የሚጠቅመውን ለገዛ ራስ ወስዶ እነደሚማርበት እኛ እናምናለን፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን በተጻፈው ግለ ሰቦች፣ ቤተ ሰብና መንግሥት ይማራል ይመለስማል፡፡ ስለ መንግሥት ደግሞ ቢጻፍ እንዲሁ በተመሳሳይ ሌሎች ለትምህርታቸው በመውሰድ ይጠቀሙበታል፡፡

በአንድ ሀገር ወይም በአንድ ማኅበረ ሰብ መካከል ግለ ሰቦች፣ ቤተ ሰብ፣ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ሰብ ጨው ሊሆኑ፤ ይህንንም ኃላፊነት ሊወጡ የተጠሩበት የእግዚአብሔር ጥሪና ክቡር ፈቃድ እጅግ ታላቅና ውድ ነው፡፡ ማንም ይህንን በደስታ ቢፈጽመው ፍጻሜው በረከት፣ ክብር፣ ድል… ሲሆን ይህንን ባያደርግ ግን በዚህም ሆነ በሚመጣው ዓለም የነዚህ ተቃራኒ እንደሚወርስ የመጻሕፍት ብቻ ሳይሆን የታሪክም ማስረጃ አለ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት አራቱ አንደየ ጥሪአቸው ብዙ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከአራቱም የሚፈለገው አርያአያነት በበጎ ፈቃዳቸው ላይ የተመሠረተ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር በተፈጠሩበት፣ ለመኖር ዕድል ባገኙበትና በተላኩበት ተልዕኮ ላይ የሚወሰን ነው፡፡ የመፈጠራችንና የመኖራችን ነፃነት ደምቀቱ በተቀበልነው ግዴታ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ላይ ያረፈ ነው፡፡ ‹‹… ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካልና፡፡›› ፈጣሪም ሁሉን ከአንድ ፈጥሯልና አንዱ ከአንዱ ይማራል፡፡ ሁሉም ተደጋጋፊ ናቸው፡፡ እውነት ነው፤ እግዚአብሔር በአንድ እንጂ በግሩፕ አልጀመረም፡፡ የግሩፕ - የማኅበረ ሰብ መሠረቱ አንድ ነው፡፡ የዚህ ምንጭ መጥራት ወይም መደፍረስ የወንዙን (የግሩፕን - የማኅበረ ሰብን) ዕልድ ይወስናል፡፡ ቡድን የግለ ሰብ መሠረት አይደለም፡፡ ግለ ሰብ የቡድን መሠረት እንጂ፡፡ ቡድን የአንድ ወይም የግለ ሰቦች ስብስብ ነው፡፡ እግዚአብሔር በመንግሥት ወይም በቤተ ክርስቲያን አልጀመረም፡፡ የእግዚአብሔር መጀመሪያ አንድ ሰውና ቤተ ሰብ ነው፡፡ ቤተ ሰብም (ባልና ሚስት) አንድ እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ መንግሥትን ለማኅበረ ሰቡ እንደ አንድ ተቋም

(ግለ ሰብ) እና ቤተ ክርስቲያንን ለማኅበረ ሰብዋ እንደ አንድ የጌታ አካለ አድርገን ስንማርባቸው ምሳሌነታቸው በፍጹም ወደር የለውም፡፡ ጌታም የጀመረበትን ተቋም መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን አድርጎ በማሳደግ ለማኅበረሰባቸው - ለሀገራቸው እንዲሁም ለሚመጣውም ትውልድ አለፍ ሲልም ለዓለም ሕዝቦች የጨው ማንነት ይኖራቸው ዘንድ ተፈለገ፡፡

ብዙ ጊዜ ብዙ መንግሥታትና መሪዎች መንግሥት ፈጽሞ ዓለማዊ እንደ ሆነና እግዚአብሔርም እንደማያውቃቸው ጣልቃም እንደማይገባባቸው፤ እግዚአብሔር የመንፈሳዊ ዓለም (የማይታየው ዓለም) ገዢ እንጂ በዚህ ነባራዊ ዓለም፣ በሰዎች ተፈጥሮ፣ ኑሮ፣ ፖለቲካ፣ ሀገር፣ አመራር… ላይ ደንታ እንደ ሌለው፤ ፊቱን የመለሰ፣ አንዳችም የማያገባው እንደ ሆነ ይደሰኩራሉ፡፡ መጽሐፍ ግን በግልጽ፡-‹‹ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሸሙ ናቸው፡፡››

‹‹ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሰለጥን ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ›› (ሮሜ.13÷2፤ ዳን.4÷30) ይላል መጽሐፍ፡፡ የሆነ ሆኖ መንግሥት ከእግዚአብሔር እንደ ሚሰጥ ቢታወቅም (ፈጣሪውን ቢያምንም ባያምንም)፤ አሁን ያለው ዓለማዊ መንግሥት ፈጽሞ ከእግዚአብሔር በመራቁ ዲያቢሎስ በኩራት፡- ‹‹የዓለም መንግሥት ሥልጣንና ክብር ለእኔ ተሰጥቷል›› ቢልም … መንግሥት መቼም ቢሆን የእግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ለማኅበረ ሰብ ጥቅም፤ ክብርና በረከት አድረጎ ሰጥቶታል፡፡ መንግሥታት ይህንን ስጦታ - ተልዕኮ ከእግዚአብሔር ተቀበሉት፡፡ አሁን ካለው የዓለም መንግሥት ማንነት አንፃር ግን እግዚአብሔር ምሳሌነትንና የማኅበረ ሰብ ጨውነትነት አይጠብቅም፡፡ ታድያን እኛ ለምን እንጽፋለን? … የመመለስ ጊዜ አልተዘጋም፡፡ መንግሥታት - መሪዎች ራሳቸውን አዋርደው የእግዚአብሔርን ፊት ቢፈልጉ የተላኩበትን ለመፈጸም ዕድሉ ገና አለ፡፡ እግዚአብሔርም ይረዳቸዋል፡፡ መንግሥት ማኅበረ ሰብን ወደ ጽድቅ ሊመራ ትልቅ ዕልድ ጥሪም አለው፡፡

‘‘ከግብጽ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክት በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል፡፡ አሁንም ቃላቸውን ስማ ነገር ግን ጽኑ ምስክር መስክርባቸው÷ በእነርሱም ላይ የሚነግሠውን የንጉሡን ወግ ንገራቸው፡፡

ገጽ 10 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 11: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

‘‘ሳሙኤልም የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ንጉሥን ለፈለጉ ሕዝብ ነገራቸው፡፡ እንዲህም አለ፡- በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ወግ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል÷ በሰረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ፣ ራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋቸዋል÷ እርሻውንም የሚያርሱ እህሉንም የሚያጭዱ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ይሆናሉ፡፡ ሴቶች ልጆቻችሁንም ወስዶ ሽቶ ቀሚሚዎችና ወጥ ቤቶች አበዛዎችም ያደርጋቸዋል፡፡ ከእርሻችሁ ከወይናችሁም መልካም መልካሙን ወስዶ ለሎሌዎቹ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዘራችሁና ከወይናችም አሥራት ወስዶ ለጃንደረቦቹና ለሎሌዎቻችንና ገረዶቻችሁን÷ ከከብቶቻችሁና ከአህዮቻችሁም መልካም መልካሞቹን ወስዶ ያሠራቸዋል፡፡ ከበጎቻችሁና ከፍዮቻችሁ አሥራት ይወስዳል እናንተም ባሪያዎች ትሆኑለታላችሁ፡፡ በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አልሰማችሁም፡፡

‘‘ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰማ ዘንድ እንቢ አለ፡- እንዲህ አይሁን÷ ነገር ግን ንጉሥ ይሁንልን÷ እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን ንጉሣችንም ይፈርድልናል÷ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል አሉት፡፡ ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ÷ ለእግዚአብሔርም ተናገረ፡፡ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፡- ቃላቸውን ስማ÷ ንጉሥም አንግሥላቸው አለው፡፡ ሳሙኤልም የእስራኤልን ሰዎች፡- እያንዳንዳችሁ ወደ ከተማች ሂዱ አላቸው፡፡’’ (1ሳሙ.8÷8-22)፡፡

እስራኤላውያን ከሚገዛቸው ከፍቅር ገዢአቸው ከእግዚአብሔር ሌላ የአሕዛብ ዓይነት መንግሥት በጠየቁት ጊዜ የአሕዛቦች መንግሥት ወግ ይህ ነው አላቸው፡፡ የአሕዛብ መሪዎች የወገኖቻቸው ገዢ ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔርም ‘‘ይህ ወግ ለእኛም ይሁን’’ አሉት እስራኤላውያን፡፡ እርግጥ ነው፤ ዘመናዊው መንግሥት፡- ‹‹መንግሥት የሕዝብ አገልጋይ ነው፡፡›› ይበል እንጂ በግብር ግን ሲታይ ይህ ከእውነታው እጅግ የራቀ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ፡- መንግሥት ገና ከመነሻው ራሱን የሚያገለግል፣ ለሥልጣኑ ክብርና ልዕልና ዘብ የሚቆም፣ ለፖለቲካ አመለካከቱ፣ ለፈጠረው የመንግሥት ቅርጽ ብቻ የሚጋደል፣ ያለፈውና ሊመጣ ያለውን ማንኛውም ዓይነት የመንግሥት ዓይነት የሚኮንን፤ ራሱን ፍጹም አድርጎ የሚያቀርብ መሆኑና ‹‹ለራሱ›› የመኖር ዋስትና ብቻ የሚሰጥ መሆኑን ከፍ ብለን የጠቀስነው የመጽሐፍ ክፍል ያሳብቃል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ግን መንግሥት ሕዝብን ማስተዳደሪያ እንጂ ሕዝብን መግዣ አይደለም፡፡ መንግሥት ግን ሕዝብን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከማስተዳደር ሲወድቅ ሕዝቡን ወደ ራሱ ፈቃድ የመንዳትና የመግዛት ክፋት ላይ ይወድቃል፡፡ እንዲህ ዓይነት መንግሥት ወይም መሪ ሕዝቡን እንዲያ አድርጎ ይንዳው እንጂ የሕዝቡ ልብ በእውነት ተገዝቶለት አይደለም፡፡ ሕዝብ ዕልድ ካገኘ በዚህ ዓይነት መንግሥት ላይ ክፉኛ ይነሣል፡፡ ያለ ጥርጥር በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የወደቀውን መንግሥት፡- ‹‹የእግዚአብሔርን መንገድ ማስተማር፣ ለማኅበረ ሰብህ ጨው ልትሆን የተጠራህ ተቋም ነህ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ለምትመራው ሕዝብ አርአያ መሆን ይገባሃል…›› ማለት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ለእርሱ ሥልጣኑ አምላኩ ነው፡፡ ፖሊሲውም ‹‹ቅዱስ መጽሐፉ›› ነው፡፡ ማንንም አይሰማም፡፡

ዳሩ ግን መንግሥት ለመንግሥት የበቃበት ትልቁ ቁም ነገርና ስጦታ የሀገር - የማኅበረ ሰብ ብርሃን እንዲሆን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ብርሃንም ለጨለማ፣ ለመሰናክል፣ ለመደናበር… የተሰጠ ፈውስ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ያገኘው የአመራር ብሩህነት ለትውልድ መሻገሩ ይታመናል፡፡ መንግሥት ማስተዋል ከሆነለት ሕዝቡን ለጽድቅና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚያበረታታ፣ የአምላኩን ፊት እንዲፈልግና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲኖረው የሚያስተምር

(እንደ ቤተ ክርስቲያንም ባይሆን) ምሳሌ መሆን አለበት ብለን እናምናለን፡፡ ዙፋን (ሥልጣን) በጽድቅ ብቻ ነውና የሚጸናው፡፡

መንግሥታት እርግጥ ነው ይህንን ከሚያደርጉበትና ኃላፊነታቸውን ከሚወጡበት ከፍታ ተንሸራትተው ወድቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም የማኅበረ ሰባቸው ጨው የሚሆኑበት ዕድል በእጃቸው እንደ ሆነና እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እንዳልጣላቸው ሊነገራቸው ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የመርሳት ክፉ ፍሬ እንዳናጭድ ልንፈራ ይገባናልና፡፡

በሀገራችንም አያሌ የመንግሥት ዓይነቶች መጥተው ሄደዋል እስከ ዛሬ ባለው ታሪካችን፡፡ ነገር ግን የትኛውም የመንግሥት ቅርጽ (ዓይነት) ከሁለት አሐዝ በላይ ያሳለፈ መንግሥት በታሪካችን አልተፈጠረም፡፡ የመንግሥታቱ (ቅርጽ) ዕድሜም በንጉሡ ወይም በመሪው ዕድሜ ልክ ብቻ መሰፈሩ አሳዛኝ ነው፡፡ ‹‹መንግሥት - ዙፋን - ሥልጣን በጽድቅ ይጸናል›› ሲባል ለመሪው ረዥም ዕድሜ ይሆናል፤ መንግሥቱንም ለልጅ ልጁ ያወርሳል ማለት ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የዚያ መንግሥት ምሳሌነት፣ መልካምነት፣ የሕዝብና የሀገር አገልጋይነት፣ ታሪክ ተሸጋሪና አሻጋሪነት፣ ትውልድ የሚያሻሽለው እንጂ የማይሽረው ጽኑነት ይኖረዋል … ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለትውልድ የቀጠለ ወይም የተላለፈ የመንግሥት ቅርጽ አልተፈጠረባትም፡፡ አሁንም በሥራ ላይ ያለው የመንግሥት ቅርጽ ለምን ያህል ትውልድ እንደሚቀጥል በሂደት ብቻ የሚታይ ይሆናል፡፡

አንድ ምሳሌ ግን እናንሣ፡፡ የቅርቦቹን ሦስት መንግሥታት በመጥቀስ፡፡ ምሳሌአችን ባንዲራችንን ይመለከቷል፡፡ የቀዳማዊ ኃ. ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የመንግሥት ቅርጽ በባንዲራው ላይ የራሱን አርማ፣ አመለካከት፣ ዓላማ፣ ራእይ፣ ተልዕኮ… ለጥፎበት ነበር፡፡ ጊዝያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ጊዜውን ሲረከብ ያንን የመንግሥት ቅርጽ በማክሰም ባንዲራውን ሲቀበል የነበረውን አጥፍቶ የራሱን አርማ፣ አመለካከት፣ ዓላማ፣ ራእይ፣ ተልዕኮ… የሚያንጸባርቀውን ምልክት ሰፋበት፡፡ የዘውድ መንግሥት ባንዲራ አልተሻገረም፡፡ ቀጣይ ትውልድ አልወረሰውም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መጥቶ መንግሥት ሲመሠረት ታሪክን በመድገም ባንዲራውን ላይ የነበረው የደርግ አርማ በመፋቅ አሁን ያለውን የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት፣ ፖሊሲ፣ አመራር፣ የፌዴራሊዝም አወቃቀር፣ ራእይ… በሚያመላክት መልኩ ባንዲራው ላይ አደረገበት፡፡ የደረግ መንግሥት ባንዲራ ከደርግ አልፎ አልተሻገረም፡፡ ትውልድም አልወረሰውም፡፡ ጥያቄው ግን አሁን ያለው የመንግሥት ቅርጽ (ዓይነትና) ባንዲራው በቀጣይነት ምን ያህል ትውልድ ይረከበዋል ነው? መልእክታችን ይህ ነው፡- ያለ እግዚአብሔር አታቅዱ፡፡ ያለ እግዚአብሔር አትሥሩ፡፡ ለዕድሜአችሁ ልክ ብቻ ነው የምትደክሙት ሌላው ትውልድ አይከተላችሁም፡፡

ለምንለው ነገር እንዲሁም ላለንበት ሁኔታ አንድ ምሳሌ በማንሣት ሐሳባችንን እናስፋው፡፡ ጄ.ኤ.ስፐንሰር በጁላይ 1987 ዓ.ም በፊልደልፊያ ግዛት በተካሄደ ፌደራላዊ ስብሰባ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹… የምንፈልገውን የመንግሥት ምሳሌ (ሞዴል) ለማግኘት ብለን ወደ ጥንታዊ ታሪክ በመመለስ ገና ከመጀመሪያው ሲመሠረቱ በሚከስሙበት አኳሀን በመሆኑ በአሁን ጊዜ ሕልውናቸው የጠፋ ልዩ ልዩ ሪፐብሊኮችን መርምረናል፡፡ እንዲሁም በያዝነው ዘመን በመላው አውሮጳ የሚገኙ መንግሥታትን አይተናል፡፡ ዳሩ ግን ከሕገ መንግሥታቸው አንዱም ለሁኔታችን ተስማሚ ሁኖ አላገኘነውም፡፡›› ከዚህ በኋላ ነበር ያ ጉባኤ ለሚመሠረተው የመንግሥት ዓይነት ተሰብሳቢው በሙሉ ጠዋት ጠዋት የእግዚአብሔርን ዕርዳታና ምሪት ለመጠየቅ ይጸልይ ዘንድ የተደረገው፣ ይህንም በዩናይትድስቴትስ ታሪክ ቅጽ ሁለት

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 11

Page 12: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ገጽ መቶ ሃያ ሁለት ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ … ለዚህም ይሆናል የዚያች ሀገር የመንግሥት ቅርጽ (ሞዴል) እስከ ዛሬ ጸንቶ የኖረው፡፡ ይህ የመንግሥት ሞዴል በየጊዜው በዳበሩና በሠለጠኑ አስተሳሰቦችና መሻሻል ባያጣውም መሠረቱን ሳይለቅ ጸንቶ መኖሩና እርሱን ብዙ ሀገሮች ለሞዴልነት መገልበጣቸው አስተማሪነት አለው፡፡ አስተማሪነቱም የእግዚአብሔርን ፊት በመፈለግ፣ ለምናደርገው ነገር እርሱን መጀመሪያ ማድረግ… ነገሮች ምን ያህል ጽኑ፣ የተባረኩ፣ ትውልድ የሚፈልጋቸው መሆኑን ያስተምረናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ምሳሌዎች ለሀገራችን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ስላለንበት ሁኔታ፣ ስለ ገጠመን ማንኛውም ነገር… ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛቦችም ታሪክ ሎጂካዊ መግለጫ ልናገኝ እንችላለንና በአሜሪካውያኖች ሁኔታ ልንማር እንችላለን፡፡ ለምንጥለው ትውልድ ተሻጋሪ መሠረት የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ እንዴት የከበረ ነገር ነው! መንግሥት በዚህ ረገድ ምሳሌ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በሀገራችን (ውስጥ) በእውነተኛ አምልኮ ላይ የተመሠረተ እምነትና ጸሎት፣ ምሪት የእግዚአብሔርን ፊት በመፈለግ የተመሠረተ የመንግሥት ዓይነት ወይም ዘመን ተሻጋሪ ሥራ አልታየም፡፡ ለዚህም ይሆናል ከጅምራቸው የከሰሙት፡፡ አሁን ያለው ይህ መንግሥት ‹‹ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ነፃነት›› እንደ መፍቀዱ በዚህ ነፃነት ለእርሱና ለሁሉም የሚጠቅማቸውን እንደ እግዚአብሔር ቃል መጻፍ አግባብ ነው፡፡ መንግሥት ለማኅበረ ሰቡ ጨው መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ አልጫ ይሆናል፡፡ ትውልዱም ታሪክም ይረግጠዋል፡፡ መንግሥት ሕዝብን የሚያገለግል በመሆን ለሀገር ሰላም፣ ፍቅር፣ መተሳሰብና አንድነት… ጽኑ መሠረት ኖሮት መሠረቱ ለትውልድ ይሻገር ዘንድ በጽድቅ፣ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ የተቀበለው ሕዝብን የማስተዳደር አደራ በቅንነት በማገልገል እንዲፈጽመው ሊተከል፣ ሊከተኮትና፣ ሊታረም ይገባዋል ብለን አምንን እንጽፋለን፡፡

በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ የምንለው ነገር በግልጽ እንደ ተደረገ ምስክርነት ማግኘት ይቻላልን?... እኛም ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ከመምከርና ከማስጠንቀቅ ቸል አላልንም፡፡ በእርግጥ መልእክቶቻችን ወደ መንግሥት ደጀች ለመድረሳቸው እርግጠኛ አይደለንም፡፡ መንግሥትም ከፖለቲካ ጋዜጦችና መጽሔቶች ውጭ መንፈሳዊ የሆኑትን ያነብ እንደ ሆነ እንዲሁ እርግጠኛ አይደለንም፡፡ እውነቱን ለመናገር መንግሥት ከቤተ ክርስቲያን ድምፅና መልእክት ይበልጥ የተቃዋሚዎቹን ሚድያ መከታተሉ ይገርማል፡፡ ከቤተ ክርሰቲያን የሚጠቅመኝ ነገር የለም ብሎ ከሆነ ግን ተሳስቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያንና መልእክተኞችዋ የሌሏት ሀገርና መንግሥት ወዮላቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን በተቃራኒው መልእክትም መልእክተኛም ከሌላት ወዮላት፡፡‹‹ጻድቃን በበዙ (በሠለጠኑ) ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥአን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል›› (ምሳ.29÷2)፡፡

‹‹መኮንን (ገዥ) ሐሰተኛ ነገርን ቢያደምጥ÷ ከእርሱ በታች (አገልጋዮቹ) ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ›› (ምሳ.29÷12)፡፡

‹‹ራእይ ባይኖር ሕዝብ (ይጠፋል) መረን ይሆናል›› (ቁ.18)

እነዚህ የመጽሐፍ ክፍሎች ውድ ሀገሩን በሰላም ከገዛው ከንጉሥ ሰለሞን የተቀዱ ምሳሌዎች አይደሉምን? የሰላምን መንግሥት በእርግጥ ሰላም ገዝቶት ነበር፡፡ ሰላም ከጽድቅ ጋር ይወዳጃል፡፡ ጽድቅና ሰላምም የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጥ ናቸው፡፡ ጽድቅ ማለት ‹‹ትክክል›› ማለት ነው፡፡ በተጻፈው በእግዚአብሔር ሕግ ወይም በሕሊና ሕግ ትክክል - ልክ ልንሆን ይገባናል እንደየ ስፍራችንና

ጥሪአችን፡፡ መንግሥት ይህንን በማድረግና በማስተማር ለራሱም በመሆን ለሚመራው ሕዝብ ምሳሌ መሆን አለበት ስንል የማኅበረ ሰብ ጨውነቱን ኖሮ በማሳየት መግለጡ ነው፡፡ መሪዎች በግላቸው ይሁን በቡድን በእምነት፣ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በጽድቅና በእውነት በቅንነትም ለሕዝባቸው ምሳሌ መሆን አለባቸው፡፡

ሰው በኃይሉ ቢበረታ እስከ እድሜው ልክ ድረስ(?) ነውና ከዚያ በኋላ ሥራውን ሁሉ ሌላው ያዋርድበታል፡፡ የሕዝብ ደስታ እንዲሁም የሕዝብ ብዛት የሰወረው መሪ ጽድቅ እንደ ጎደለው መሪ ሊሆን አይችልም፡፡ በእግዚአብሔር የሚታመን - ሕዝብንም የማገልገል ጥሪ ያለውና ያንኑ የሚያደርግ መሪ - መንግሥት የሕዝብ ልብ አይሸሸውም አያሳድደውምም፡፡ በዚህ ዘመን ከሕዝብ ፊት በብዙ የሚደበቁ መሪዎች - መንግሥታት የሕዝብ ልብ ስለሌላቸውና እነርሱን ስለካደ አይደለምን?... እግዚአብሔርን የሚፈራ ግን እንደ አንበሳ በመንጋው - በሚመራው፣ በሚወድደው፣ በሚያገለግለው፣ በሚሠዋለት… ሕዝብ መካከል በሞገስ፣ በምስጋናና በክብር ይመላለሳል፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ዓይነት መሪ ላይ ተቃዋሚዎች /ጠላቶች የሉበትም ማለት አይደለም፡፡ በአንድ ሀገር መልካምን፣ ዕድገትን፣ ልማትን፣ መከናወንን የማይወዱ፣ በከንቱ የሚጠሉና የሚቀኑ፣ እነርሱ በቀር ሌላ መሪ ያለ የማይመስላቸው ትምክህተኞችና ክፉ ሰዎች የሉም ማለት ያስቸግራል፡፡ እንደነዚህም ዓይነት ሰዎች ያንን መሪ ለማጥፋት አያሴሩም አይባልም፡፡ የእነርሱን ጠጠር ለመመሽ ግን ሙሉ በሙሉ መደበቅ አያስፈልገውም ለደግ መሪ - ጠጠራቸውን የሚጥሉት በሕዝብ ላይና መካከል ነውና፡፡ እግዚአብሔርም ለእንደነዚህ ዓይነት ምናምንቴዎች አሳልፎ አይሰጠውም፤ በጽድቅ፣ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ ሕዝብን በመውደድና በማገልገል… ይታወቃልና፡፡

መንግሥት ለሚያደርገው፣ ላሰበው፣ ለወጠነው፣ ለሚመሠርተው… ማንኛውም ታላቅም ይሁን ታናሽ ነገር… በአጠቃላይ ለሀገራዊ ጉዳዮች ሕዝቡ እንደ የእምነቱ ወደ ፈጣሪው እንዲጸልይ፣ ሀገራዊ ምሪት ለመቀበል የእምነት ቤቶች ለመንግሥት (ለመሪ) እንዲማልዱ… ያለፉት መሪዎቻችን አንዳቸውም ይህንን እንዳደረጉ (ሕዝቡን እንደለመኑ) ምስክር የላቸውም፡፡ የግል እምነት አልነበራቸውም ለማለት ግን ማንም አይደፍርም፡፡ ይህ የግል እምነታቸው ግን በቤት (በሀገር) ላሉ ሁሉ ቢያበሩት መልካም ነበር ነው መልእክታችን፡፡ አሁን ያለፉቱ በሌሉበት ይህ ለማለት የተፈለገበት ምክንያት እነርሱን ለመውቀስ አይደለም፡፡ አይጠቅምምና፡፡ ነገር ግን አሁን ያሉት መሪአችንም ሆኑ መንግሥታቸው ለትውልድ የሚሻገር፣ ሞዴል የሚሆን… የመንግሥት ዓይነት፣ ልማት፣ ሕዝባዊነት፣ አገልጋይነት… በመፍጠር ለሕዝባቸው ጨው ይሁኑ የሚለው መልእክታችን ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ለዚህች ምድር የጻድቃን ብዛትና ሥልጣን ፈጣሪ ይስጠን፡፡ የዚህ ዓመድ ጸሐፊ ‹‹ጻድቃን›› ሲል እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወድድ ባልንጀራውንም (ሕዝቡን) እንደ ራሱ የሚወድድ ማለቱ ነው፡፡ የግድ ክርስቲያን ወይም ሙስሊም መሪ መሆን አለበት ብሎም አያምንም፡፡ የሕሊናውን ሕግ የማያከብር ወንድሙንም የማይወድድ የማያየውን እግዚአብሔርንና ሕጉን ያከብራል ይወድድማል ብሎ ማመን ሞኝነት ነው፡፡ በእርግጥ ለማኅበራዊ ሳይንስ የእምነት ወይም የእግዚአብሔር ነገር ሞኝነት ሊሆን ይችላል፤ ነውም፡፡ ዳሩ ግን ማኅበራዊ ሳይንስ ብቻውን ሰውን ካለበት ውስጣዊ ባዶነት፣ ከንቱነት፣ አለመርካት፣ ደስታ ማጣት… ነፃ በመውጣት የተመሠረተና የተደላደለ ሰላም ሲሰጥ እስከ ዛሬ አልታየም፡፡

እግዚአብሔርንና ባልንጀራን (የሰውን ልጅ ሁሉ) መውደድ የሚነጣጠሉ አይደሉም፡፡ ማንም የተፈጠረውና በዚህ ዓለም የሚኖርና ለመኖር ዕድል የተሰጠው እግዚአብሔርንና ባልንጀራውን ለማፍቀር (ለመውደድ) ነው፡፡ የወደድነውም እናገለግለዋለን፡፡ መንግሥት የተፈጠረውና ለመኖር ዕድል

ገጽ 12 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 13: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

የተሰጠው ከዚህ ከእግዚአብሔር መርህ ውጭ ሊገኝ አይደለም፡፡ሕዝብን የሚወክል መሪ ወይም መንግሥት ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረው ግንኙት ስለ ሕዝቡ፣ ስለ ሀገሩ፣ ስለቀጣይ ታሪካቸው… ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ አንድ ጊዜ ሕዝባቸውን (ነገዳቸውን) ወክለው ምድሪቱን የሰለሉ የእስራኤል መሪዎች ባመጡት ወሬና አቋማቸው ምክንያት እነርሱም የወከሉትም ሕዝብ ነው ከእግዚአብሔር በረከት ጋር ሳይገናኝ የቀረው፡፡ መሪዎች የሕዝብ በረከትም መርገምም፤ ክብርም ውርደትም፤ መጽናትም መውደቅም… ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

‹‹እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ÷ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል›› (መዝ.127÷1) የተባለውን የእግዚአብሔርን ቃል ዘወትር ማሰብ ይገባናል፡፡ ይህ በግልም ሆነ በቡድን ለምንሠራው ሥራ የሚጠቅም ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ግን መንግሥት ለሚወጥነው ታላቅም ሆነ ታናሽ ነገር፤ በፊቱም ከባድ መስሎ ለሚታየው ማንኛውም ነገር አምላክን ለምሪት መጠየቅ ወይም ሕዝቡ ሁሉ በዚህ ነገር ልቡን ወደ ፈጣሪው እንዲመልስና እንዲማፀን ማድረግ (መጠየቅ) ይጠበቅበታል፡፡ ይከናወናል፡፡ እስከምናውቀው በዚህች ሀገር በጠላት ወረራና በድንበሯ መደፈር፣ ለትላልቅ ልማቶች - አንደ ሕዳሴው ግድብ ዓይነቶች… ብራችንን እንጂ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት፣ ጸሎታችንን፣ የእግዚአብሔርን ፊት (ለምሪት) መፈለግ… ስናዋጣ አልተገኘንም፡፡ መንግሥትም እንደዚህ ጠይቆ አያውቅም፡፡ ነገር ግን መንግሥት ከብራችን በፊት ይህንን እንድናደርግ ቢጠይቅ እንዴት የከበረ አርአያነት ነበር?!

መንግሥት እንደየእምነታችን ‹‹ጸሎታችሁን፣ እምነታችሁን፣ የፈጣሪን ፊት መፈለጋችሁን አስቀድማችሁ አዋጡ፡፡ ከዚያም ያላችሁን ማንኛውም ነገራችሁን ስጡ›› ቢል እንዴት ያምርበት ነበር?! ‹‹ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፡፡ እንዲህም ነው የማኅበረ ሰብ ጨው መሆን የሚቻለው - እንደ መንግሥት፡፡

መንግሥት በአባት ይመሰላል፡፡ አባት ማን ነው?... አባት ለቤቱ ሰዎች ሁሉ ምሳሌ ነው፡፡ በመልካም አስተዳደር ምሳሌ ነው፡፡ ሐሰተኛ ነገርን ባለማድመጥ፣ ባለመከተል፣ ባለማድረግ ምሳሌ ነው፡፡ መልካምን እያደረገ በትጋት በመሥራት ምሳሌ ነው፡፡ የቤቱን ሰዎች በማሠልጠን፣ በማስተማር፣ በማሳደግ፣ በመግራት፣ በመቅጣት፣ አባታዊ ባሕሪውን በምሕረትና በእውነት በማካፈል … ምሳሌ የሚሆን አባት ነው፡፡ አባት ቤቱን በመመገብ፣ በማጥገብ፣ በማሳደግና በማበልጸግ (Becaise he is provider.)ምሳሌ ነው፡፡ አባት የቤቱም ካህን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ ለቤተ ሰቡ እግዚአብሔርን የማሳየት፣ የመግለጥ፣ ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መፍራትና በነገር ሁሉ ፊቱን መፈለግን… የሚያሳይ በመሆን ምሳሌ ነው፡፡ አባት መጪውን ዘመን አስቀድሞ በማየት (ባለ ራእይ ነውና!) ለቤተ ሰቦቹ እንደየ ተፈጥሮአቸው፣ ስጦታቸውና ዝንባሌአቸው ሰፊ ነገር በማደራጀትና በማዘጋጀት ሁኔታዎችን ያስረዳል፡፡ አባትም ከቤተ ሰዎች መካከል ዓመፀኛ፣ የማይታዘዝ፣ ለፈቃዱም የማይገዛ፣ ወገን ቢኖር በፍቅርና በርኅራኄ ይቀጣዋል፡፡ ተመልሶም ከቤተ ሰቡ ጋር እንዲኖር ሰፊ ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ልቡ ሰፊ ነውና፡፡… በዚህ ሁሉ ታላቅ ዋጋ በመክፈል ምናልባት እርሱ ሞቶ፣ ደግሞ፣ መሥዋዕት ሁኖ… ቤተ ሰቡን በማኖር ምሳሌ ይሆናል፡፡ በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ሆይ፣ እኛ ይህንን የአባትነት ምሳሌ ለመንግሥታት (በተለይም ለኢትዮጵያ መንግሥት) ይፈጽሙት ዘንድ እንደሚገባቸው በማመን መስለነዋል፡፡ በዚህም የማኅበረ ሰባቸው ጨው ናቸው፡፡ በጨውነታቸውም የማኅበረ ሰባቸውን የድህነት፣ የክፋት፣ የስንፍና፣ የጥላቻ፣ የመለያየት… መራርነት ሊያስወግዱ

ይችላሉ፡፡ አባት የሚሆን መሪ ግን እግዚአብሔር ይስጠን፡፡ የአባትነትንም መንፈስ በመንግሥታችን ላይ ያሳድር፡፡ (የሚቀጥል)

ከገጽ 9 የዞረ

ቢያስፈልግ እኮ ስለ ተሰጠው እንጂ ለንጹሀኖች ስላልታዘዘ ጌታው ያስረው ዘንድ ግድ ይለዋል፡፡ፍጥረታዊ ውሻ እንኳ ሰውን ሲያውክ ጌታው ቢያገኘው ጎረቤት እንዳይነክስበትና በሕግም እንዳይጠየቅ በሰንሰለት በግቢው መታሰሩን ተፈጥሮ አላስተማራችሁም? ውሻው እንኳ እንቢ ብሎ ወፈፌና በሽተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ሰውን ሁሉ ከበሽታው እንደያጋባና ጌታው እንዳይጠየቅ በመንግሥት ይገደል ዘንድ ትዕዛዝ እንደሚወጣ አታውቁምን? በሽተኛ ውሻ ይገደል ዘንድ ጤነኛና በጥባጭ ውሻም ይታሰር ዘንድ ተፈጥሮ አስተምሮናል፡፡ ወንድሞች ሆይ! ውጡ? ታዩ! ተገለጡ! ፍጥረት በመቃተት ላይ ነው፡፡

አባት ሆይ! አስቀድመህ የወሰንከውንና በመንፈስ ክበብ ሰርተህ ጨርሰህ እንዳረፍክ እኛም ባረፍክበት እረፍት እናርፍ ዘንድ አካልን መዳሰስና መንካትና መታየትን መቅመስን ስጠው?በነገር ሁሉ መሆንና መደረግን በዘመናችን በእግዚአብሔር ለእኛ ማፍጠን ይሁን! ወንድማች ሰለሞን ሽፈራው ነኝ (ደሴ)

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 13

አሁን ሥጋ የሚለውን አይደለም፡፡ አሁን የውጭ ሰውነት የሚለውን አይደለም፡፡ አሁን ከሥርዓት - ከፕሮግራም - ከሕግ - ከአባቶች ወግ - ከየጉባኤዎች ከተላለፈው ውሳኔዎች፣ ድንጋጌዎችና ጥናታዊ ጽሑፎች መስማት አይደለም፡፡ አሁን መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ነው መስማት የተገባን፡፡ ይህ የክርስቶስ መገለጥ ነው፡፡ ለዚህ ጆሮ ያለው ማን ነው - የመንፈስ ጆሮ?... እግዚአብሔር ያለ ጩኸት - በፀጥታ - ያለ መወራጨት - ያለ ሥጋ ሥራ ለመንፈሳችን ራሱን የሚገልጥበትና የሚያስረዳበት ስፍራ እንምጣ፡፡ ላስረዳንም ነገር እምቢ እንዳንል መጠንቀቅ እንዳለብን ተነግሮናል፡፡ ትውልዳችን ግን ያለፈውን ዘመን ታሪክ እንደ ደገመው በመንፈስ አይቻለሁ፡፡ ስለ ሰማዊው ነገር ቀርቶ ስለ ምድራዊም ነገር ቢነገረው ማስተዋል ያልቻለ ትውልድ አለ፡፡ መወለድ እንኳ በቅጡ አልገባውም እንኳን መገለጥ፡፡ የጥንቶቹ ‹‹በምድር ላስረዳቸው›› ነገር ነው እምቢ ያሉት፡፡ ዛሬ ከሰማይ ለወጣው ራሱ ሰማይ ካልሆነ እንዴትና ማን ያስተውለዋል? የአሁኑ መልእክት ከሰማይ ነው - ከመንፈሳችሁ ከፍታ የተወደዳችሁ ሆይ፡፡ የውጩን መጽሐፍ ዝጉት፡፡ ጆሮዎቻችሁንም ከልክሉ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህንን አድርጉ፡፡ በዚያ አዚም - በዚያ ሟርት - በዚያ ድግምት ሌላ መጽሐፍ መጻፉን አትርሱ፡ ሌላ መጽሐፍ - ሌላ ወንጌል በዚህን ያህል ዘመን እስከ ዛሬ አለ፡፡ በጣም ሥር ሰድዶአል፡፡ ‹‹እስረኛ ሲቆይ ባለርስት ይሆናል›› እንዲሉ ሐሰት ብዙ በመኖሩ እውነት እየመሰለ አሳስቷልና ብዙዎችን ወረሰ፡፡ አያሌዎች ለዚህ ሐሰት ዘብ ውለው አድረዋል፡ ••••••••

Page 14: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

(ካለፈው የቀጠለ)

እምነት ከመስማት እንደ ሆነ አለማመንም ከመስማት ነው፡፡ አለማመንም ያለማወቅ በኩር ልጅ ነው፡፡ ብዙዎች በሰሙት በሰው ትምህርት (በአሮጌው የሰው አስተሳሰብ) U¡”Áƒ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ከተገለጠውም ፈቃዱ ራቁ፡፡ እግዚአብሔርም ሰው በገዛ መንገዱ ይሄድ ዘንድ በተወበት ዘመን ከገዛ ልቡ እያወጣ ነው ለባልንጀራው ትምህርት ብሎ ያስተማረው፡፡ የውድቀትን መስመር እግዚአብሔር በሰው ሕይወት እንዳላሰመረው ሰው ከወንድሙ÷ ከሰው ተማረው፡፡ ሰው እንዳይወድቅ ተደርጎ ተፈጥሮ እንደ ነበረና ክርስቶስም ዓለም ሳይፈጠር - ውድቀት ሳይኖር ለዚህ ያልተዘጋጀ እንደ ሆነ ‹‹የሰው ነፃ ፈቃድ›› የፈጠረው ይሄ ሁሉ ጣጣ በእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት፣ ሁሉን ቻይነት… ላይ ጥያቄ እንደ ፈጠረ በቀደሙት ዕትሞች የተማመንበት የድንቁርና አስተሳሰብ እንደ ነበር አይተናል፡፡

‹‹አዳም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ አድርጓልና ከዚህ አዳም ካደረገውም በመነሣት እግዚአብሔር ስለ አዳምና ፍጥረት ማሰብና ማቀድ መጀረ፡፡ ስለዚህም ልጁን ላከ፡፡›› ‹‹አዳም በእግዚአብሔር የተፈጸመ ፍጡር የእግዚአብሔርም ያለቀ ሥራ ነበር፤ ነገር ግን ባልታሰበ ሁኔታ ስለ ወደቀ›› እግዚአብሔር የሚለው ፍጹም ሰውና ያለቀ ሥራ ሊሳሳት - ሊወድቅ የሚችል በመሆኑ ነገሩ ጥያቄ ላይ ይወድቃል፡፡

እንዲህ ከሚሉት፣ ከሚያምኑትና ከሚጽፉት ጋር መሟገት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ዳሩ ግን የሕሊና ሙግት ከሁሉ የበለጠ ተፋላሚ ነው፡፡ እነዚህ ከፍ ብለው የተጠቀሱ ሐሳቦች ብዙዎች በሰው መርዛማ ትምህርት ሕሊናቸውን አደንዝዘው የሚሰነዝሯቸው ከሆኑ እንጂ በጎ ሕሊና ያላቸው ለሕሊናቸው ሙግት መልሳቸውን ሊያገኙ መንፈስ ቅዱስን ይማጸናሉ፡፡ የሆነ ሆኖ ለባለ በጎ ሕሊናዎችም ሆነ ሕሊናቸውን ማደንዘዣ ለወጉ መንፈስ ቅዱስ በዘመናት ሁሉ ሕይው ምስክሮችን ይሰጣል፡፡ አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ከፍ ከፍ ባለ በእግዚአብሔር ሐሳብ የሚገለጡ የእግዚአብሔር ልጆች አሁን አሉ፡፡

ውድቀት በሰው ሁሉ ሕይወት እንዲገለጥ በእግዚአብሔር የተሰመረ - የተሠራ - የታሰበ - የታወቀ - የተፈቀደ - በጊዜው አካል የሚያገኝ የከበረ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር (አራት ነጥብ)፡፡

ውድቀት ደኅንነትን የምጠራበት ከሆነና

ከውድቀት በኋላ ደኅንነት አብዝቶ የተገለጠ ከሆነ ሰው በውድቀት መጀመሩ መልካም ነው እላለሁ፡፡ ለደኅንነት የተዘጋጀው ፀጋ ከመጠን የበለጠ ከሆነ (ሮሜ.5÷21) ‹‹ውድቀት ባይሆን ኖሮ…›› የሚለውን ተረት ለመድገም በሆዴ መሳብ የለብኝም፡፡ ይሄ የእባብ ልጅነት ነው፡፡

ዓመፃዬ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ (ሮሜ.3÷5) ውድቀቴ ደኅንነቴን ከማስከተሉ በቀር ምን አረገኝ?... ለእኔ ‹‹ውድቀት መልካም ነው›› የተባለበት ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ያለ ውድቀት ደኅንነት ያልተሰጠ - ያልተዘጋጀም ከሆነ ውድቀት መሆኑና መፈቀዱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም፡፡

‹‹በአዳም ሞት - ውድቀት የክርስቶስ መምጣትና የሕይወት መገለጥ እንደ ሆነ ልብ በሉ፡፡ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ሰው ወደ እግዚአብሔር ተነሣ፡፡ ከሕያው ነፍስ ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ከላቀ ሕያው ነፍስ የተባለው ሰው ባይወድቅ ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ እንዴት ይለቀቃል?... የእግዚአብሔር ሕይወት ወደ ሁሉም የጎረፈው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ከሆነ ሞት ሕይወትን አገልግሏል፡፡›› ከቀደሙት ዕትሞች፡፡

ውድቀት በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተሰመረና የተወሰነም ስለ ሆነ ነው እግዚአብሔር ለመሥዋዕትነት ሊዘጋጅ የሰውን ፈቃድ፣ ትብብርና ‹‹ነፃ ፈቃድ›› ያልጠየቀው፡፡ የሰው ነፃ ፈቃድ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድ ላይ አንዳችም ድርሻ የለውም፡፡

ስለ ተዘጋጀው መሥዋዕት ማንም አይመካም፡፡ ውድቀት ያለ ሰው እንደ ነበር (በሰው ቢገለጥም) ደኅንነትም ያለ ሰው ነው የተፈጸመው፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሁኖ ራሱን ከዓለም ጋር ሲያስታርቅ የማን ሥራ የማንስ እምነት ተጠየቀ? የማን ነፃ ፈቃድስ እግዚአብሔርን አገዘ? በዳዩ ሳይሆን የተበደለው ነው የታረቀው፡፡ የተበደለውም እርቅ አልተጠየቀም፡፡ ራሱን ከዓለም ጋር ነው ያስታረቀው፡፡ ይሄ ያለቀ ሥራ ነው፡፡ መታረቁንም በእያንዳንዳችን በጊዜ እየገለጠው ነው - በራሳችን ተራ፡፡ ከዓለም ጋር ያለው እርቅ ተፈጽሟል፡፡ ይሄ በሁሉም ይገለጥ እንደ ሆነ እንጂ እንደ ገና የሚሠራ እርቅ የለም፡፡ እግዚአብሔር ውድቀትን በሁሉም እንዲገለጥ ወስኖት ነበር፡፡ ደኅንነትም (በውድቀት ልክ ባይሆንም) ከመጠን ይልቅ አስበልጦ አዘጋጀው፡፡ ምሕረቱ ፍርድን ፍቅሩም ቁጣን ማለፉን አስተውሉ፡፡ ፍርዱ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ ነው፡፡ ምሕረቱስ? እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ፡፡ ፍርዱ ሁሉንም እንዳገኘ (በሦስትና በአራት ትውልድ የጊዜ ዘመን) ምሕረቱም ሁሉን ያገኛል፡፡ ምሕረቱም ከፍርድ በኋላ በመሆኑ ውድቀት፣ ኩነኔ፣

የዘላለም አምላክ ዋነኛ አጀንዳ ፍጻሜ ያገኘው በውድቀት ምክንያት እንደሆነ በጥልቀት የምናስተውለው ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ሐሳብና ሥራ ትልቁ ጉዳይ የሰው ውድቀት ነው፡፡ ሥራው ሁሉ - ሰውን ሁሉ ከውድቀት መልሶ ወደ ቀደመው (ስለ ሰው) ሐሳቡ መመለስ እንደሆነ ሥራው ያሳየናል፡፡ ውድቀት ባይኖር በክርስቶስ ያወቅነው፣ የተባበርነውና የተሠራው ሁሉ በምንና እንዴት ይገለጥ እንደ ነበረ አሁን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ ውድቀትም መቤዠትም በእግዚአብሔር በቀደመው እውቀቱ ውስጥ አለ፡፡ ውድቀት ለደኀንነት መገለጥ መጀመሪያ ነበረ፡፡ ውድቀት ሁሉን እንዳገኘ ደኅንነትም የሚያጣው አንድም ነፍስ የለም፡፡ ሁለቱም የተገለጡት በሰው ነውና፡፡ ሰውም የእግዚአብሔር መገለጫ ነው - በፊተኛውም በኋለኛውም፡፡ ሰው በአዳም ውድቀት እግዚአብሔዴር አባት ሁሉን እንዳጣ እንዲሁ በክርስቶስ የደም - የሕይወት መሥዋዕት ሁሉን ያድናል፡፡ ሞት ማንንም አይገድልም፡፡ ሲኦል ባዶ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆናል፡፡

ሥጋን ያገኘ የእግዚአብሔር የቀደመው ሐሳብ

ገጽ 14 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት

Page 15: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

ፍርድ የማይገኙበት የአዲስ ዓለም ሥርዓት በፍጥረት ላይ ይነጋል፡፡

‹‹ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና›› (ዮሐ.3÷17)፡፡ ልጁ የዓለምን ፍርድ በራሱ ላይ ተቀበለ እንጂ በዓለም ሊፈርድ አልተላከም፡፡ እርሱ÷ በዓለም የነበረውና ወደ ዓለም የገባው ዓለምን ለማዳን ነው፡፡ ሆኖም ‹‹የሰው ልጅ ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ቢሰጠውም›› - በዓለም ቢፈርድም (ለማረምና - ለማስተካከል - ጽድቅን ለማካፈል) ለዓለም የሠራውንና ያዘጋጀውን ማዳን ረስቶና ወድያ ጥሎ እንዳይደለ ማወቅ ይገባናል፡፡ ምሕረቱ ፍርዱን ማለፉና መብለጡ ግን እውነት ይሁን፡፡

ውድቀት በሰው በኩል እንደ ሆነ ማለት ውድቀተ በሰው በኩል እንደ ተገለጠ እንዲሁ ደኅንነትም በሰው በኩል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ሰው የሆነው፡፡ ቃል የነበረው እግዚአብሔር በሰው ምሳሌ የተገለጠው ሰውን እንደ ገና ወደ ክብሩ ለመመለስ መሆኑ ክርክር የለበትም፡፡ ሰው ለሚቀበለው የእግዚአብሔር ፍርድ ምትክ - ቤዛ ያገኝ ዘንድ እግዚአብሔር ራሱን በሰው ምሳሌ - በባሪያ መልክ አደረገ፡፡ ሰው በሰው(ነቱ) ቢፈረድበት ዕዳውን ይከፍል ዘንድ በቂ(ዋጋ) አልነበረም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰውን ሙሉ ዋጋ በራሱ ከፈለ፡፡

በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረና እግዚአብሔር የነበረ ቃል ነበረ፡፡ ቃል የተገለጠው እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ ሥጋ ሆነና የማይታየውን ባሕሪይ ተረከው - ገለጠው - አወጣው - አወረደው - አመጣው - እንዲታይና እንዲታወቅ አደረገው፡፡ ሥጋ የሆነውና የተገለጠው እግዚአብሔር በደኅንነት የተዘጋጀው - የሚሠዋው በግ ነው፡፡ በጉ በመጀመሪያ ነበረ፡፡ በጉም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ በጉም እግዚአብሔር ነበር፡፡ በግም በግ (ሥጋ) ሆነ፡፡ ዮሐንስ፡- ‹‹እነሆ÷ የእግዚአብሔር በግ›› ያለው እርሱን ነው፡፡ የዚህ መሥዋዕት የማይጠቀልለው ነፍስ አንድም የለም፡፡ ይህንን የማያምኑ ቢኖሩ ግን የእግዚአብሔርን ታማኝነት አያስቀርም፡፡

ክርስቶስ አብን የገለጠ የእግዚአብሔር ጥበብ፣ የእግዚአብሔር ክብር፣ የእግዚአብሔር መልክ፣ ኃይል፣ የባሕሪው ምሳሌ የክብሩም መንፀባረቅ… ነው፡፡ በዚህ ሁሉ የሰውን ዋጋ ትልቅነት አያለሁ፡፡ እግዚአብሔር - ሰው ለሰው የተከፈለ ዋጋ አይደለምን? ዋጋውም የተከፈለው ለተለዩት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ነው፡፡ ወደዚህ ዋጋ ክብርና ደኅንነት ሁሉም መጠቅለላቸው በክርስቶስ የተሠራ ተአምር ነው፡፡ በኩራት ሁነን አስቀድመን ያመንነው ይህንን ለማወጅ ነው፡፡ ብልጫችን መቅደማችን ነውና በሁሉ መዳን የእግዚአብሔር ፍጹም ክብር ይሆናል - ተደነቁ!

የማይታይ አምላክ ምሳሌ እርሱ እግዚአብሔር ወደ ሰው የመጣበት - የተገለጠበት - የወረደበትና ሰውም ወደ እግዚአብሔር ያረገበት የራሱ የእግዚአብሔር ምሥጢር ወይም አሠራር ወይም ሥርዓት - መንገድ ነው፡፡ ዓለም ሳይፈጠር (ዮሐ.17÷5) ስለ ነበረውና በመጨረሻ ዘመን በሥጋ ወደ ዓለም ስለገባው አዳኝ - የዘላለምና ፍጹም አዳኝ እናወራላችኋለን፡፡ በገሊላና በናዝሬት ጎዳናዎች በሥጋ የተመላለሰው ከአብርሃም በፊት ያለ (ዮሐ.8÷58) በአብርሃም ምሳሌ - የአብርሃምን ዘር የዞ (ዕብ.2÷16)

የወረደ - የመጣ እርሱ የዘላለም አባት - ኃያል አምላክ ነው፡፡ ሁሉን የገደለው ሞት በሞቱ ይሽረው ዘንድ እርሱ በሥጋና በደም ተካፈለ፡፡ ሞት በሞት ተሸሯል፡፡ የሲኦልም ቁልፍ ሞት በነበረውና አሁን ሕያው በሆነው በክርስቶስ እጅ ነው (ራእ.1÷17-18)፡፡ ሲኦል ተቆልፎበታል፡፡ ቢከፍተው ወይም ቢዘጋው ሥልጣኑ በሞተውና በሚኖረው ነው፡፡ ሌላ ሥልጣን ያለው የለም፡፡ የሞተውና የሚኖረው ይበቀል ዘንድ ሳይሆን ይቀጣ ዘንድ ቢከፍተው ምክንያቱ የሞቱን ዋጋ ያደምቃል፡፡ ዋጋ የከፈለላቸው እርሱ ዳግመኛ ከዚያ ላይወጡ የሚዘጋባቸው ከሆነ ግን ስለ እነርሱ የከፈለው ዋጋ ክብርና ምላሽ የት አለ?‹‹…God was manfest in the flesh››. (K.J.V)‹‹He (God) was made visible in human flesh.››(AMP)‹‹He who was revealed in the flesh…››(NASV)‹‹He appeard in a body››(NIV)

ይሄ እግዚአብሔር ከገለጠላቸው በቀር ማንም የሚረዳው አይደለም፡፡ እርሱን ሰው ሊሰማውም ሊናገረውም አይችልም፡፡ ምሥጢር ነው - የተገለጠ ምሥጢር! ለዚህም ነው ለእምነት ቤቶችም ሆነ ለብዙ ሃይማኖቶች ይህ ምሥጢር የልዩነት ምክንያት የሆነው፡፡ የተገለጠው እግዚአብሔርን - ክርስቶስን ሰውም አናጢዎችም ጥለውታል፡፡ እርሱ የተመረጠና የማዕዘን ራስ ድንጋይ ጭምር ነው፡፡ የተላከውን የናቃችሁ እናንተ ሆይ÷ በሥጋ የመጣውን እግዚአብሔርን ያላወቃችሁና ያላመናችሁ እናንተ ሆይ÷ በእርሱ ላይ ብትወድቁ ትቀጠቀጣላችሁ፤ እርሱ ደግሞ ቢወድቅባችሁ ትቢያ ወይም ዱቄት ትሆኑ ዘንድ ይፈጫችኋል - አብ በማያምኑትም በሚያምኑትም ላይ ቃሉን ያድርግ - አዎን፡፡

የምንደኛው ደመወዝ የምንደኛው ሙሉ ዋጋ አይሆንም፡፡ የሞያተኛው ደመወዝ የሞያተኛው ሙሉ ዋጋ ሊሆን አይችልም፡፡ ሠራተኛው የሚያገኘው ደመወዝ ሙሉ ዋጋ ሆኖ ሠራተኛውን ሊገዛ - ሊቤዥ አይችልም፡፡ የኃጢአትም ደሞዝ የሆነው ሞት ኃጢአተኛውን ከኃጢአት ዕዳ ሙሉ በሙሉ ነፃ አያወጣውም፡፡ ይሁን እንጂ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ ሰው በኃጢአቱ ስለ ሞተ (በሥጋውም በመንፈሱም ስለ ሞተ) የኃጢአትን ዋጋ (ዕዳ) ሊከፍል አልቻለም፡፡

ስለዚህ ለሰው ሌላ ሙሉ ዋጋ ሊከፍልለት የሚችል ምትክ አስፈለገው:፡ ከመላእክት አንዱ ምትክ አልሆነም፡፡ ከቅዱሳን አንዱ ዋጋ አልከፈለም፡፡ ለዚህ ሙሉ፤ ፍጹምና በቂ የሆነው እግዚአብሔር በሥጋ ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ በግልጽ፡- ‹‹ኑዛዜ ያለ እንደ ሆነ የተናዛዡን ሞት ማርዳት የግድ ነውና ሰው ሲሞት ኑዛዜው ይጸናልና ተናዛዡ በሕይወት ሲኖር ግን ከቶ አይጠቅምም›› ይላል፡፡ ይሄ ምን ማለት ነው?... እግዚአብሔር በሲናይ ምድረ በዳ - በኮሬብ ተራራ ስለ ተናዘዘው ኪዳን ደም አስፈለገው፡፡ ያለ ደም አልተመረቀም፡፡ ብሉይ በደም ተመረቀ - ጸና፡፡ እግዚአብሔር ግን አዲስን ኪዳን ተናግሮ ነበርና - ኑዛዜው ነበርና ይህ ኑዛዜ ይጸና ዘንድ ሌላ የእንስሳ ደም አላስፈለገውም፡፡ እራሱን (ተናዛዡ) ግን ለመሥዋዕት አቀረበ፡፡ ምን ማለት ነው? .. ተናዛዡ - ተስፋ የሰጠው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር በእግዚአብሔርነቱ - አምላክ በአምላክነቱ ግን መሞት አይችልም፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ነውና መንፈስ አይሞትም፡፡ … ስለዚህም ሰው እንኳን ሊያውቀውና ሊተባበረው ቀርቶ ሊያስበው እንኳ ጭንቅ የሚሆንበት ከቶም የማይችለው ነገር እግዚአብሔር ቻለ - ሆነ፡፡ ሰውም ሊያውቀውና ሊያምነው የተናነቀውና የሚተናነቀው ተአምር - ድንቅ

የእግዚአብሔር መንግሥት ምዕ.1 ቁ.10 ገጽ 15

Page 16: ጋዜጣው፡-  (መዝ.103.19) · መንፈስንና ኃይልን አይገልጡም፡፡ ቃላቸው ጭንቁር

- የድንቆች ድንቅ ይሄ አይደለምን?... እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡ ሥጋና ደም ተካፈለ፡፡ የአብርሃምን ዘር ያዘ፡፡ እግዚአብሔር በሰው ሥጋ - በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ መጣ፡፡ በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ሁሉን ማድረግ ሁሉን መሆን የሚችል መንፈስ የሆነው እግዚአብሔር ሥጋ ሆነ፡፡ እግዚአብሔር ሥጋ ሲሆን መንፈስ መሆኑን ትቶ አልነበረም፡፡ ‹‹ከሰማይ የመጣው›› በመጣበት ጊዜ - ዘመን - ዘላለም ሁሉ ‹‹በሰማይ የሚኖረው›› እርሱ ነበር (ዮሐ.3÷13,31)፡፡

መንፈስ ሆኖ ሥጋ ሆነ፡፡ እርሱ በሥጋም በመንፈስም ያለ ልዩነት ነው፡፡ ለመንፈስ(ነቱ) መታየትን ለመስጠት መጥቶ ዕዳ ለመክፈል ሥጋ ሆነ - በሥጋ (in the flesh) ተገለጠ፡፡ የተገለጠበትም ሥጋ ለአንድ ጊዜና ለሁሌም ዋጋ ሊከፍልበት ነው፡፡ ያም የኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ እንደ ገና እንፈልገው ዘንድ በየትኛውም ስፍራ የለም፡፡ ጌታ (ግን) መንፈስ ነው፡፡ ወደ ወጣበት ተመልሶ ገብቷል፡፡ በገባበት በአብ የአብ መንፈስ ሆኖ ፈሰሰ - እርሱ የእውነት መንፈስ ነው፡፡ ‹‹… ከእናንተ ዘንድ (በሥጋ - ከደቀ መዛሙርት ጋር) ስለሚኖር በውስጣችሁም (መንፈስ ሆኖ) ስለሚሆን (አንዱ ክርስቶስ) እናንተ ታውቃላችሁ›› (ዮሐ.14÷17)፡፡‹‹… ድንግል ተፀንሻለሽ÷ ወንድ ልጅም ትወልዳለች÷ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› (ኢሳ.7÷14)፡፡‹‹ሕፃን ተልዶልናልና÷ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና÷ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል÷ ስሙም ድንቅ መካር÷ ኃያል አምላክ የዘላለም አባት÷ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል›› (ኢሳ.9÷6)፡፡

ዓመፃዬ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ (ሮሜ.3÷5) ውድቀቴ ደኅንነቴን ከማስከተሉ በቀር ምን አረገኝ?... ለእኔ ‹‹ውድቀት መልካም ነው›› የተባለበት ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ያለ ውድቀት ደኅንነት ያልተሰጠ - ያልተዘጋጀም ከሆነ ውድቀት መሆኑና መፈቀዱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም፡፡

በአዳም ሞት - ውድቀት የክርስቶስ መምጣትና የሕይወት መገለጥ እንደ ሆነ ልብ በሉ፡፡ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ሰው ወደ እግዚአብሔር ተነሣ፡፡ ከሕያው ነፍስ ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ከላቀ ሕያው ነፍስ የተባለው ሰው ባይወድቅ ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ እንዴት ይለቀቃል?... የእግዚአብሔር ሕይወት ወደ ሁሉም የጎረፈው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ከሆነ ሞት ሕይወትን አገልግሏል፡፡

እነዚህ የመጽሐፍ ክፍሎች ወላዲትን ሳይሆን የተወለደውን ይሰብካሉ ታላቅም ያደርጋሉ፡፡ በእነዚህም ጥቅሶች ወላዲቱንና የተወለደውን ማወዳደር ፈጽሞ ያስቸግራል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር የተጠቀመባት ይህች ሴት እንዴት የተባረከችና ብፅዕት ናት!! ‹‹የወለደችው›› የተባለውን ወደ ዓለም ሲያገባው ሥጋን ሊያዘጋጅበት ግን ማኅፀንዋን እግዚአብሔር ተውሷል፡፡ አስገራሚ ነው! እግዚአብሔር በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ ለመጣበት አሠራር ማርያም ‹‹እናት›› ተባለች፡፡ ሰለ ማሪያምም የተባሉ ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አስደናቂ ናቸው (ማቴ.1÷18-25)፡፡ የወንጌል ጸሐፊዎችም ማሪያምን ‹‹የኢየሱስ እናት›› ብለው ጽፈዋል፡፡ እርስዋ በገዛ ዘመኗ እንደዚያ ተገልጣዋለችና፡፡ ዳሩ ግን ምሥጢር የሚሆነውና መገለጥ የሚያሻው ጉዳይ በወንጌሎች አንድም ጊዜ ኢየሱስ፡ ‹‹እናቴ›› ብሎ አለ መጥራቱ ነው፡፡

‹‹አማላጅነቷ›› በሚወደስበትና ብዙ በሚነገርበት የመጽሐፍ ክፍል (ዮሐ.2÷1-5) ኢየሱስ፡- ‹‹አንቺ ሴት›› እንጂ ‹‹እናቴ›› አላላትም፡፡ ወንጌላውያን ዛሬም

ብዙዎቻችን ማርያምን፡- ‹‹የኢየሱስ እናት›› እንላታለን፡፡ ኢየሱስ ግን አንድም ጊዜ ‹‹እናቴ›› ብሎ ያልጠራት ለምን ይሆን?

እርሱ ከማሪያም በፊት ነው፡፡ ራሱንም በሥጋ አያውቅም አይቆጥርም፡፡ ‹‹እንደ መሰላቸው የዮሴፍ ልጅ… የአዳም ልጅ…›› አሉት እንጂ እርሱ ራሱ ‹‹የዘላለም አባት›› ነው፡፡ አባትም እናትም የሌለው አባት፡፡ አባት ማለት የሚያስገኝ - የመጀመሪያ ማለት አይደለምን? … በሥጋ አምሳል (ምሳሌ) እንጂ በመንፈስ እርሱ አባትና እናት የሉትም፡፡ ራሱን እንዲህ ያገኘው ‹‹የዘላለም አባት›› ሰውን አባቴ ወይም እናቴ ብሎ ሊጠራ አይመጥነውም፡፡ ክርስቶስን እንኳ በሥጋ እንዳናውቀው ሐዋርያው ጳውሎስ ግድ የሚለን ከሆነ (2ቆሮ.5÷16) በሥጋ የወለደችውን እናት እንድናውቅ የሚያስተምረን ሃይማኖት እንጂ መጽሐፍ አይደለም፡፡እግዚአብሔር በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሻር ለማድረግ ማርያምን የክብር ዕቃ አድርጎ ተጠቅሞባታል፡፡ ይህን ታላቅ የማዳን ሥራ ባሰብን ጊዜ ወደ ኋላ ሄደን ብፅዕትን እናስባለን፡፡

ማርያም ዮሴፍ ከተባለ አንድ ሰው የታጨች ተራ ሰው ነበረች እንደ ሰው ልኬት፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ስለ እርሷ አንድ ታላቅ ነገር ታስቧል፡፡ ይህ ታላቅ ሐሳብ ግን ትውልዱ የሚቀበለው አልነበረም፡፡ ነገሩም በሆነ ጊዜ ‹‹ዮሴፍ (እንኳ) በስውር ሊተዋት›› አስቦ እንደ ነበር መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ ለፈጸመው ለእግዚአብሔር ድንቅ ለዮሴፍ ግን እንግዳ ነው፡፡ እርሱ ከተዋት ግን ማኅበረ ሰቡም እንደሚተዋት ይታመናል፡፡ በእርሷ የተፈጸመው

(ድንግል መጸነስዋ) ያልሆነ ሊሆንም የማይችል ነውና፡፡ ለዚህ እንግዳ ታሪክ - በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ድንቅ ለነበረ - ዓለም ለሚድንበት የከበረ ሥራው ማሪያም፡- ‹‹እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› ያለች ብቸ— መንፈሳዊ ጀግና ነበረች፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት ለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ስለማሪያም የሚሟገቱ - የሚጣሉ ብዙ አማኞች ለእርሷ እንደ ሆነው ዓይነቱም ባይሆን እግዚአብሔር አዲስ ነገር ቢገልጥባቸው በታሪክ ያልታየና ያልተሰማ ነገር ቢናገራቸው ወይም ቢያደርግባቸው እንደ እርሷ፡- ‹‹እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› የሚሉ አባቶቻቸውና የዚህች እናት (የእመቤታችን) ዓይነት ጀግኖች ይሆኑ ይሆን?... እርሷን የምንወድደው እንደ እርሷ የእግዚአብሔርን ቃል በእምነት ተቀብለን በመጠበቅ - ዋጋም ቢያስከፈል በመታገሥ እንጂ ስለ እርሷ በመጣላትና በከንቱ በመቅናት አይደለም፡ ስለ ማታውቁት ሰው አትዋሹ ጠበቃም አትሁኑ፡፡ እርሷን ግን የሚያድናትንና የሚያድነንን አዳኝ ወለደችው - ገለጠችው - የተባረከች ናት፡፡ (የሚቀጥል)

••••

ገጽ 16 ምዕ.1 ቁ.10 የእግዚአብሔር መንግሥት