temsalet magazine 2 pages

36
1 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008 www.temsalet.com ትምህርት በጥርስ መካከል ምክንያትና ውጤቱ ማህበራዊ ድረ ገጾችና ትምህርታዊ ፋይዳ የሥነ ምግባር ጉዳይ

Upload: addis-tsegaye

Post on 15-Apr-2017

121 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

Page 1: Temsalet Magazine 2 Pages

1 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008 www.temsalet.com

ትምህርት በጥርስ መካከል

ምክንያትናውጤቱ

ማህበራዊድረ ገጾችናትምህርታዊፋይዳ

የሥነ ምግባርጉዳይ

Page 2: Temsalet Magazine 2 Pages

2 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

አገሬአገሬ ውበት ነው

ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት

ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።

አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ

እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ።

አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ

አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።

ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም

ክረምቱም አይበርድም፣

አይበርድም፣ አይበርድም።

አገሬ ጫካ ነው

እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት

በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።

እዚያ አለ ነጻነት።

በሃገር መመካት፣

በተወላጅነት፣

በባለቤትነት.....

(ሰዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)

Page 3: Temsalet Magazine 2 Pages

ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ክብርት ዶክተር ስንዱ ገብሩ

10 ጥያቄዎች ለትምህርት ቢሮ

10 ጥያቄዎች ለግል ት/ቤቶች ማሕበር

የነገዛሬዎች

የሃይገርወጎች

ትምህርትበጥርስመካከል

ምክንያትናውጤቱ

የሰው ልጅ አንጎልድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ

የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤበእጓለ ገብረዮሃንስ

ማህበራዊድረ ገጾችናትምህርታዊፋይዳ

ከአዕምሮ ውስጥየሚሸት ጣፋጭየዩኒቨርሲቲ ትዝታ

የሥነ ምግባርጉዳይ …

13

25

1416

19

23 289

1011

በዚህዕትም

www.temsalet.com

Page 4: Temsalet Magazine 2 Pages

ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

በአገራችን ትምህርትን አስመልክቶ የሚነሳ አባባል አለ ለወራት ችግር ጎመን፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ጤፍ ዝራ፤ ለአመታት ችግርህ ማንጎ፣ ቡና ዝራ፤ ለመቶ አመታት ችግርህ ዛፍ ዝራ፤ ለዕድሜ ልክ ችግርህ ትምህርት ዝራ፤ ይባላል፡፡ እነዚህ አባባሎች ከአባባል ባሻገር የሚሰጠው መልዕክት ትልቅ ነው።

ለዕድሜ ልክ ችግርህ መፍቻ የተጠቀሰው ትምህርት ምን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታል ብለን ያልን እንድሆን እንብዛም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ መንግስት ለትምህርት ቤቶች መስፋፋት እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ የሚበረታታ እና የሚደገፍ ሆኖ ሳለ ዛሬም ለትምህርት ጥራት እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች የሚደረገው ድጋፍ የሚያበረታታ አይደለም፡፡ Africa.com Blog ኢትዮጵያ በአምስት የተመረጡ ዘርፎች በኢንቨስትመንት ዓለምን የምትስብ ሀገር ናት ሲል ይገልፃል ፡፡ ከነዚህ ሳቢ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ትምህርት ነው ፡፡ መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለእርሻ ኢንዱስትሪ፣ ለኢንዱስትሪ ማስፋፋያ እና ለአይ ሲቲ ዘርፎች የሚደረግ የኢንቨስትመንት ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን እንደ ሆቴል እና አበባ ልማት የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶች ላይ ከታክስ እና ግብር ቅናሳ ጀምሮ ያለቀረጥ የሚገቡ መገልገያዎችን በነፃ እንዲገቡፈቅዷል ፡፡ ለትምህርት አገልግሎት ሲሆን እነዚህ ማበረታቻዎች ለምን ዝግ እና ቅድሚያ የሚሰጠው እንዳልሆነ ግልፅ አይደለም ፤ በተለይም ትምህርት በኢንቨስትመንት ሊታቀፍ የሚገባው ዋና የኢንቨስትመንት መስክ ነውና፡፡ የሆነው ሆኖ ለሁሉም ነገር መሰረት የሆነው ትምህርት ጠንካራ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል፡፡

የተምሳሌትአቋም

የተምሳሌትአቋም

በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር በየወሩ የሚታተም መጽሔት ነው ፡፡ ተምሳሌት መጽሔት በኢትዮጽያ

ብሮድካስት ባለሥልጣን ምዝገባ ቁጥር 279/2006 እና በንግድ ምዝገባ ቁጥር kik/AA/2/0003278/2007 ሐምሌ 15 ቀን

2006 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡

ዋና አዘጋጅንጉስ ይልማ

አድራሻ: ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09የቤት ቁጥር 1711

[email protected]

ማኔጂንግ ዳይሬክተርከድር አህመድ

[email protected]

ኤዲቶሪያል ቡድንደሳለኝ መኩሪያ [email protected]

አዲስ ፀጋዬ [email protected]በለጠ ጌታቸው [email protected]

ዓለማየሁ ስሜነህ [email protected]

አምደኞችወንድሙ ነጋሽ (ከሎንዶን)

ጽጌሬዳ ጎንፋመላኩ አላምረው (የእናት ልጅ)

ክቡር መተኪያ ሄኖክ ሰይድአየለ ተሰፋዬ

ዲዛይንበፀጋ ግርማ

ካርቱኒስትገነነው ውብሸት

የኮምፒዩተር ጽሁፍ አዜብ ዓለማየሁ [email protected]

ገበያ ስርጭት እና ክትትልዮርዳኖስ በቀለ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 3277 ዘርሽታ

ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 212 ስልክ ቁጥር 251 911225298 ፖ.ሳ.ቁ 54154

ኢ-ሜይል [email protected]

አሳታሚ ኤኬቢዲ የፕሬስ የማስታወቂያና የማማከርአገልግሎት

www.akbdmedia.com

Page 5: Temsalet Magazine 2 Pages

1 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ክብርት ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1952 ዓ.ም. ድረስ የመጀመሪያዋ የሴት የፓርላማ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ም/ሊቀመንበር ሆነው በማገልገላቸው ታሪክ “የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ አባል”

ብሎ መዝግቧቸዋል።

ትዉልድ እና እድገትከአጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ አጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ በከፍተኛ ሃላፊነት ያገለገሉት እና በወቅቱ ተራማጅ አስተሳሰብ ከነበራቸው ቀደምት ኢትዮጵያዊ ምሁራን መካከል የሚመደቡት እና የጎንደር ከተማ ከንቲባ የነበሩት ገብሩ ደስታ ወይም በብዙዎች ዘንድ በሚታወቁበት ስማቸው ጆቤው እና ወይዘሮ ካሳዬ ይሌምቱ ከወለዷቸው በርካታና ዝነኛ ልጆች መካከል ስንዱ ገብሩ የላቀ እዉቅናን የተጎናጸፉ ሴት ናቸው::እኚሁ ሰው በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሃገር በመናገሻ አዉራጃ በአዲስ አለም ከተማ በወረሃ ጥር በስድስተኛዉ ቀን በ1908 ዓ.ም ተወለዱ::የታላቅ ባላባት ልጅ እንደመሆናቸው መጠን በመኖሪያ ቤታቸው መምህር ተቀጥሮላቸው ሲማሩ ቆይተዋል:: ይህንን በወቅቱ እንደ ታላቅ ትምህርት ይቆጠር የነበረዉን የአብነት ትምህርት እና ዳዊት መቁጠር ከተማሩ በኋላ በወቅቱ በአቅራቢያቸው ይገኝ ከነበረው የስዊድን ወንጌላዊት ሚሲዮን ትምህርት ቤት በመግባት የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በሚገባ አጠናቀቁ::

ከተቀዳሚዎቹ የዉጪ ተማሪዎች አንዷከንቲባ ገብሩ ደስታ ዉጪ ሃገር ሄደው ከተማሩ ቀደምት እና ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ምሁራኖች መካከል የሚመደቡ ከመሆናቸው የተነሳ እንዲሁም እንደ እነ ስንዱ ገብሩ ያሉ ህጻናቶች ስለ አባታቸው የዉጭ ሃገር ቆይታ ብሎም የትምህርት አይነት አጥብቀው ይጠይቁ ስለነበር በወቅቱ እንደ ብርቅ ይታይ የነበረዉን የዉጭ ሃገር ከፍተኛ ትምህርት ለመቅሰም ስንዱ ገብሩከታናሽ እህታቸው ከየዉብዳር ገብሩ ጋር በአንድነት በመሆን በአባታቸው በከንቲባ ገብሩ ደስታ አጃቢነት ወደ ስዊዘርላንድ ሃገር አመሩ:: ከንቲባ ገብሩ ደስታ(ጆቤው) ከአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ጋር ከፍተኛ ቅርርብ ስለነበራቸው የልጆቻቸው የዉጭ ሃገር ትምህርት በቀላሉ እንዲሳካ ረድቷቸዋል፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ነው የጆቤው ልጆች ወደ ዉጭ ሃገር ሄደው እንዲማሩ የተወሰነው፤ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ከታናሽ እህታቸው የዉብዳር ገብሩ ለትምህርት ወደ አውሮፓ ተጉዘዋል፡፡

ወደ ስዊዘርላንድ ሃገር ለከፍተኛ ትምህርት በሄዱበት ወቅት የመነጋገሪያው ቋንቋ በርካታ ቢሆንም ስንዱ እና እህታቸው ባረፉበት ግዛት ይነገርበት

የነበረው ቋንቋ ጀርመንኛ ስለነበረ እና ቋንቋዉን ለመረዳት ከባድ ስለሆነባቸው ለስድስት ወር የነበራቸውን የስዊዘርላንድ ቆይታ በመተው ወደ ፈረንሳይ ሃገር አመሩ:: በጊዜው የገቡበት “ሞሚራይ” የተሰኘው ትምህርት ቤት እድሜያቸው ከአስራ አምስት አመት በላይ የሆናቸውን ልጃገረዶች ብቻ የሚቀበል የነበረ ተቋም ቢሆንም ከእሩቅ ሃገር ትምህርትን ብለው ለመጡት ለእነዚህ ህጻናቶች ሲባል ብቻ መምህር በግል ተመድቦላቸው ታላቅ እና ታናሽ እህትማማቾቹ ስንዱ እና የዉብ ዳር ገብሩ የቀለም ትምህርትን እንዲማሩ እና ጥሩ እዉቀትን እንዲያገኙ ተደረገ:: (የዉብዳር ገብሩ በኋልኛው ዘመን በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የረቂቅ ሙዚቃ ተጫዋች በመሆን በርካታ የሙዚቃ አልበምን ያሳተሙ ከጊዜያት በኋላ ደግሞ እድሜያቸውን በምንኩስና ህይወት ለመምራት የመረጡ የዉብዳር የተሰኘ የአለም ስማቸውን ትተው እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ በሚል ስማቸው የሚታወቁ ሌላ ስመጥር ኢትዮጵያዊ ናቸው)::በወቅቱም የቤት አስተዳደር የምግብ አዘገጃጀት የፒያኖ አጨዋወት የስፌት መኪና ትምህርት የአመት በጀት አያያዝን ጨምሮ በወቅቱ ለሃገራችን ብርቅ የሆኑ ትምህርቶችንበፈረንሳይ ሃገር ተምረው በዲፕሎማ ማዕረግ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ::

በበርካቶች ዘንድ የወይዘሮ ስንዱ ቀዳሚነት እሚጠቀስላቸው የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባል የመሆናቸው ጉዳይ ቢሆንም በኢትዮጵያ እምብዛም ያልተለመደውን የሴት መምህርነት እና የሴት ርዕሰ መምህርነት፣የሴት ጸሃፊ ተዉኔትነት፣የሴት ደራሲነት፣የሴት ገጣሚነት ወዘተ በመስራት ለብዙ ሰዎች አርአያ ለመሆን በቅተዋል::

ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ተቀጥረው ፈረንሳይኛ አማርኛ ጽሁፍ እና ስለ ጤና አጠባበቅ ለማስተማር ችለዋል::በዚህ ሁኔታ ለአንድ አመት ከቆዩ በኋላ ከአምባሳደር ብላታ ዶክተር ሎሬንዞ መብርሃቱ ጋር ጋብቻ ፈጸሙ፡፡ ወይዘሮ ስንዱ ባለቤታቸው ብላታ ሎሬንዞ በቀድሞ መጠሪያው የሃረርጌ ጠቅላይ ግዛት በአስተዳዳሪነት በመሾማቸው ከአዲስ አበባ ወደ ሃረርጌ አቀኑ::ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ደግሞ ባለቤታቸዉ ሎሬንዞ የፍርድ ቤት ሹምና የዜና ስርጭት ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ቻሉ::

የሴት አርበኝነትበአድዋ ድል በቀመሰው የሽንፈት ቂም ይዞ ለአርባ አመታት ገደማ ሲያደባ እና ጦር ሲያደራጅ የከረመው የፋሽት ኢጣልያ ወራሪ ጦር የአዉራዉን የሞሶሎኒ የሮም አደባባይ ድንፋታ ተከትሎ እና የመረብ ወንዝን ተሻግሮ የኢትዮጵያን ዋና ዋና ከተማዎች በተቆጣጠረበት ጊዜ ንጉሰ ነገስቱ አጼ

ክብርት ዶክተር ስንዱ ገብሩ

በ ክቡር መተኪያ

Page 6: Temsalet Magazine 2 Pages

2 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ሃይለስላሴ በስደት ወደ እንግሊዝ ሃገር ሲጓዙ አብረዋቸው እንዲጓዙ ከመረጧቸው የቅርብ ዘመዶች ልጆች እና ታላላቅ ሹማምንቶች መካከል ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ሲገኙበት ቆራጧ አርበኛ ስንዱ ገብሩ ግን እምቢኝ ላገሬ ብለው ሆለታ ከሚገኘው የአርበኛ ጦር እና ጎሬ ላይ ከተቋቋመው ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት ባላደራ አርበኞቹ ከእነ ራስ እምሩ ጦር ጋር ተቀላቀሉና ሃገራቸውን ከወራሪ ጦር የማስጣል ስራ ጀመሩ::በዚህ ጊዜም ለአርበኝነት ይረዳቸው ዘንድ ከወሰዱት ስልጠና ሁሉ የመትረየስ

አተኳኮስ ስልጠናው ቀዳሚ እና ተጠቃሽ ነው::

ወይዘሮ ስንዱ ተኩሰው ጠላትን ለመጣል የሚንተገተግ ወኔ የነበራቸው እና ለነብሳቸው ቅንጣት ታክል የማይሳሱ ጀግና አርበኛ የነበሩ ቢሆንም ቀደም ብለው በፈረንሳይ ሃገር በቀሰሙት እዉቀት ምክንያትነት እንዲሁም በጊዜው የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጥ ሰው ከአርበኞቹ መካከል እንደልብ ማግኘት ከባድ ስለነበር በወቅቱ የአርበኞቹን መሪ ልዑል ራስ እምሩ ሃይለስላሴን አማክረው አምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር በመቀበል የኢትዮጵያ

ቀይ መስቀል የህክምና እርዳታ መስጫ ጣቢያ አቋቋሙ:: ከዛም በጦር ሜዳ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በማከም ለአርበኞች ደጀን የመሆን ስራን ቀጥለው በርካታ የጦር ሜዳ ጉዳት የደረሰባቸውን ተዋጊዎች ቁስል በመጥረግ እና በመስፋት ወትሮ ሊያዩት የማይፈቅዱትን የሰው ልጅ ስቃይ ለሃገራቸው ብለው ጨክነው በማከም በዚህም አርበኛዉን ከሞት እና ከስቃይ በማትረፍ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጀግኖች አርበኞች መካከል በተሰገሰጉት ባንዳዎች ጠቋሚነት ከበርካታ የጥቁር አንበሳ ፋኖ ሰራዊት

ጋር የወራሪዉ የጣልያን ጦር ምርኮ ለመሆን ተገደዉ በግዞት ወደ አዲስ አበባ መጡ::

ቀድሞ ገነተ ልኡል ቤተ መንግስት ይባል የነበረው እና የኋላ ኋላ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ግቢ ፤የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ ፊልድ ማርሻል ግራዚያኒ ላይ አብረሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ወጣቶች የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ የስንዱ ገብሩ ወንድም መሸሻ ገብሩ ከሴራዉ ጋር ተነካክቷል በሚል ምክንያት ከተማዉ ዉስጥ በወራሪዉ ጦር በጥብቅ ሲፈለጉ ከነበሩ ሰዎች መካከል ስለነበር በግዞት ወደ አዲስ አበባ መጥተው የነበሩት ስንዱ ገብሩ ወንድማቸውን ለማዳን ሲያደርጉ የነበረዉን ጥረት እግር በእግር ሲከታተል ከነበረው የጣልያን ጦር እጅ ላይ በድጋሚ ወደቁ እና በቅድሚያ በገነተ ልኡል ቤተ መንግስት ከዛም አስመራ ከዛም ምጽዋ ተወስደው ታሰሩ:: አስከትለዉም ከሶስት መቶ ወንዶች መካከል ስምንት መቶ ሴቶች አብረው በመሆን ወደ ጣልያን ሃገር “አዚናራ” ወደተባለ ማጎሪያ እስር ቤት ተወስደው ለዘጠኝ ወር ከቆዩ በኋላ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ዳግመኛ በዚህ አይነት የአርበኛነት ተግባር ላይ እንዳይገኙ ማስፈራሪያ ቢደርሳቸውም እርሳቸው ግን አርበኞችን በግጥም፣በወኔ ቀስቃሽ ጽሁፍ፣በመረጃ ማቀበልና በመሳሪያ ማመላለስ ፍጹም ድፍረት የተመላ ስራን ለእናት ሃገራቸው ሲያከናዉኑ ቆይተው የጓጉለት ነጻነት በ1933 ዓ.ም እዉን ሊሆን ቻለ፡፡

Page 7: Temsalet Magazine 2 Pages

3 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

10

ጥያቄዎች ለትምህርት ቢሮ

አቶ ማስረሻ ዘሪሁን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆኑ ከተምሳሌት መጽሔት ጋር ከግል የትምህርት ተቋም አሰራር እና የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጥያቄዎች

አስመልክተው የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ይዘን ቀርበናል ፡፡

በመንግስት እና በግል ትምህርት ተቋማት መካከል አለ የሚባል መሰረታዊ ልዩነት አለ?

አቶ ማስረሻ ፡- የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በዋናነት ከሚሰራቸው አገልግሎት አንዱ ትምህርትን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ማድረግ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር መሰረታዊ መርህ (motto) የሆነው በተስማሚ ፕሮግራሞች ትምህርትን ለዜጎች ማዳረስ የሚል ነው ፡፡ በመሆኑም ቢሮው በት/ት ተቋማት መስራት የሚገባውን ሁሉ በመስራት ላይ መሆኑን ማረጋገጥ እንጂ በስያሜ በግልና በመንግስት ላይ መሰረት ያደረገ ልዩነት የለም፡፡ነገር ግን የግል ተቋማት አንዱ ያደረጃጀት እና የራሳቸው አወቃቀር ይለያቸዋል ፡፡ የመንግስት ት/ቤቶች በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ ሲሆኑ የግል ት/ቤቶች ደግሞ ሃብታቸውን በትምህርት ላይ ኢንቨስት አድርገው በሚሰሩ ልማታዊ ባለሃብቶች የተቋቋመ ት/ቤት መሆኑ ነው ፡፡

ለመንግስት ት/ቤቶች የሚበጀተው በጀት ምንን መሰረት ያደረገ ነው ? ለሁሉም ተመሳሳይ ነው ወይስ ይለያያል ?

አቶ ማስረሻ ፡- የመንግስት ት/ቤቶች በጀት የሚወሰነው በዋናነት ከተማሪዎች ቁጥር አንጻር ነው ፡፡ ስለሆነም እንደ ት/ቤቶች ተማሪዎች የመቀበል አቅም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሚይዘው እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ በመሆናቸው መጠነኛ ልዩነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ከአፀደ ህጻናት እስከ ስምንተኛ፣ ከዘጠነኛ እስከ መሰናዶ ት/ቤት ተብሎ የተከፈለ የበጀት አጠቃቀም ነው ያለው ፡፡ ምናልባት በቁጥር ደረጃ ለእያንዳንዱ ተማሪ (per head) በዓመት 1700-2700 እንደ ትምህርት ደረጃው ሊመደብ ይችላል ፡፡ ይህ የራሱ ስሌት ስላለው በዚህ አግባብ ይሰተናገዳል ፡፡

ለግል ት/ቤቶች የሚደረጉ የማበረታቻ ድጋፎች አሉ ? በመንግስት የሚደረግ

ድጋፍ ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ የማስተማሪያ ቦታ በሊዝ ኪራይ ማግኘትን፣ መጽሐፍቶችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ መፍቀድን፣ የቀረጥ ቅነሳ ማድረግን የመሳሰሉትን መንግስት ለግል ትምህርት ተቋማት የሰጠበት ሁኔታ አለ ?

አቶ ማስረሻ ፡- መንግስት ለት/ቤቶች በርካታ ድጋፎች ይደረጋል፡፡ በዋናነት ስርዓተ ትምህርቱን የተከተለ መጽሐፍ ለሁሉም የግል ት/ቤቶች ተደራሽ ማድረግ በጣም ትልቅ እና ስኬታማ የሆነ የት/ቢሮ ስራ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩት ዓመታት ተሞክሮ የትኛውም የግል ተቋም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ መሰናዶ ያለውን መጽሐፍ ከመንግስት አግኝቶ አያውቅም ፡፡ ከገበያው ላይ ወላጆች የሚገዙት በውድ ዋጋ በመሆኑ ለብዝበዛ ዳርጓቸው ቆይቷል ከዚህ አንጻር የከተማ አስተዳደሩ ለት/ቢሮ በሰጠው ከፍተኛ ድጋፍ የግል ት/ቤቶች መጽሐፍ ማግኘት የሚችሉበትን ስርዓት እገዛ በማድረግ በቅርብ አመታት ውስጥ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ፡፡ ነገር ግን ይህንን እገዛ ሁሉም ት/ቤቶች በአግባቡ እየተጠቀሙበት ነወይ ስንል አንዳንድ የግል ት/ቤቶች እየሰጡ ያሉትን ስርዓተ ትምህርት ተከትሎ የማስተማሪያ መጽሐፍ ወስደው ለተማሪዎቻቸው በማዳረስ ትክክለኛ ትምህርት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ውስንነት ይታይባቸዋል ፡፡ መጽሐፍቶችን በተማሪዎች ልክ አለመግዛት ከገዙም በኋላ ለተማሪዎች ከመስጠት ይልቅ ት/ቢሮው በማያውቀው መልኩ ራሳቸው የሚዘጋጁትን “አጋዥ መጽሐፍት” በሚል ለወላጆች ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቁ የሚሸጡ ት/ቤቶች ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም አሰራሩ ግን ትክክል አይደለም ብሎ ቢሮው ያምናል ፡፡ ይህም እንዲስተካከል የተለያዩ የክክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን፡፡

ሌሎች የድጋፍ ጥያቄዎችን በተመለከተ የግል ት/ቤቶች ህብረት በነዚህ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ በራሱ ተነሳስቶ ተወያይቷል ወይ የሚለው ጥያቄ ሊታይ ይገባል፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡት አካላት በእኔ በኩል ጉድለት አለ ወይ ብሎ ማየቱ መልካም ነው ፡፡ አንድ ግለሰብ ቦታ ሊጠይቅ ይችላል ህብረቱ ግን እንደ ህብረት በማስፋፊያ ቦታዎች ላይ የማስፋፊያ ጥያቄ በያቀርብ የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህንን ጥያቄ ሊያስተናግድ የሚችል አግባብ ያለው አካል አለ፡፡ በዚህ መልኩ ቀርቦ ከሆነ እኔ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ህብረቱ እንደገና ራሱን ቢፈትሽ ጥሩ ነው ፡፡ ከ1500 ባላይ የሚደርሱ ት/ቤቶች ህብረት ሆነው ጠንክረው እየሰሩ ነወይ ? አንድነት ኃይል ነው በሚል መሪ ቃል ስር ሆኖ ጥያቄያቸውን ማቅረብ የሚችሉበት አቅም ላይ ናቸው ወይ ? እነዚህ ነገሮች አብረው ጎን ለጎን መታየት አለባቸው፡፡ በተረፈ ችግሮች የሉም ማለት አይደለም ፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት መንግስት እምነቱም ቁርጠኝነቱም ስላለው በሂደት የሚሰሩ ስራዎች ማሳያ ናቸው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ለትምህርት ቢሮ ሊቀርብ የሚገባው አይደለም፡፡ማሕበሩ ቢያንስ እየተጠናከረ የሚሄድበትን አግባብ በማሳየት ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ፣ እየሰሩ ያሉትን ልማታዊ ስራ በማረጋገጥ ሪኮመንዴሽን ከመስጠት አንጻር የምንሰራቸው ስራዎች አሉ፡፡ ለአብነት ብንጠቅስ ግንቦት ወር ላይ ደንብና ህግን ተከትለው ህብረተሰቡን የማገልገል ዓላማ ይዘው የተነሱ 60 የግል ት/ቤቶች ተቋሞቹ ክ/ከተማና ወረዳ ተመርጠው በመምጣታቸው ት/ቢሮው እውቅና ሰጥቷቸዋል ፡፡ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም ፡፡ እንደነዚህ አይነት ተቋማትን ለማበራከት የት/ቢሮ እምነትም ፍላጎትም ነው ፡፡ ተቋማቱ በተበራከቱ መጠን የህብረተሰቡን ፍላጎት ማርካት ይቻላል ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ት/ቢሮው የግልንም ሆነ የመንግስት ተቋም ያለ ምንም ልዩነት ጥራት ባለው መልኩ ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ነገ አገር ተረካቢ ዜጎችን መፍጠር ነው ፡፡

Page 8: Temsalet Magazine 2 Pages

4 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

የግል ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ከወጣ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ 20 ዓመት ሆኖታል ፡፡ በደንቡ አንቀጽ 12(ለ) እንዲሁም አንቀጽ 23 ላይ ተደንግጓል ፡፡ መመሪያ አለው ? መመሪያ ከሌለው መመሪያው ሊሸፍናቸው የሚገቡ አሰራሮች በምን አግባብ ይሸፈናሉ ?

አቶ ማስረሻ ፡- የግል ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመመሪያ ቢታገዙ ጥሩ ነው ብለን ባሰብናቸው ነጥቦች ላይ ት/ቢሮ፣ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ባለሙያዎች የተሳተፉበት አንድ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ፡፡ ይህ ረቂቅ በግል ት/ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ አፈጻጸም ስርዓት መመሪያ በሚል የወጣ ነው ፡፡ ምናልባትም ከአሰራር አንጻር፣ ከሂደት አንጻር የሚታዩ

ችግሮችን ሊቀርፍ ይችላል የሚል እምነት አለን ፡፡ ት/ቤቶች ዋጋ ለመተመን የሄድንበት ርቀት አካሄዱ ፍትሃዊ ነው አይደለም ፤ አግባብነት አለው ወይስ የለውም በሚሉ ጥያቄዎች ላይ እገዛ የሚያደርግ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ የመመሪያ ረቂቅ በመጀመሪያ ዙር ረቂቁን በባለሙያዎች እና በራሱ በግል ባለሃብቶች እንዲተቹ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ፡፡ ረቂቁ ከዜሮ ጅምር ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ተወስደው የሁለተኛ ክለሳ ስራዎች በመሰራት

ላይ ነው ፡፡ ይህ ስራ እንዳበቃ የሚመለከተው አመራር አካል አጽድቆ መመሪያ መሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ካሰፈረ ወደ ተግባር የሚኬድበት አሰራር ይኖራል ፡፡

በግል ትምህርት ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ አንቀጽ 17 የግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ ሲያስቡ ከ3 ወር በፊት ለወላጅ ማሳወቅ አለባቸው ላል ፡፡ ነገር ግን በተግባር እንደሚታየው የወላጆች ማወቅ ብቻ ሳይሆን መስማማትም ይጠበቃል ፡፡ ይህ ከነጻ የገበያ መርህ አንጻር እንዴት ይታያል?

አቶ ማስረሻ ፡- በግል ት/ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 206/87 እንደተደነገገው ት/ቤቱ የአገልግሎት ክፍያ የመጨመር መብት

አለው የምትለዋን ዓ/ነገር ብቻ በማጉላት እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ የግል ትምህርት ተቋም ክፍያ መጨመር መብት አለው፤ ሆኖም ግን ይህንን ጭማሪውን ት/ቤቱ ከመከፈቱ ከ3ወር አስቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባው ተጠቅሷል፡፡ እዚህ ላይ ለማለት የተፈለገው መጨመር ለተፈለገው ጉዳይ ምክያታዊ (የኢኮኖሚ ምክንያት) ተብሎ የሚጠቀሱ ነገሮች አሉት ፡፡ ህብረተሰቡ በዚህ አግባብ ተረድቶ የመክፈል አቅሙን አገናዝቦ እንዲከፍል ነው ፡፡ ሌላ አማራጭ

ያለው አማራጩን እንዲፈልግ ወላጆች ት/ቤት ከማጣት እንዳይሰተጓጎሉ ለማድረግ ነው ፡፡ በሌላ በኩል ታሳቢ የሚደረገው የዋጋ መጨመር ጉዳይ የባለ ሃብቱ ቢሆንም ምክንያታዊነታቸው በገሃድ የወጡና ህብረተሰቡ የሚያውቃቸው ናቸው ወይ ብሎ ማየቱ ተገቢነት አለው ፡፡ ከዚህ አንጻር ተዛማጅነት የሌላቸው ከነጻ ገበያ መርህ ጋር የማይዛመዱ አንድ የሆነ አካል በፈለገ ጊዜ ብቻ ብር እየጨመረ ብትፈልግ ክፈል ከሚል ስሜት ሳይሆን ምንድነው የኢኮኖሚዟል፡፡ የውድድሩን ስርዓት ጤናማ ያደርገዋል ወይ፤ ራሱን የቻለ ስርዓት የለውም ወይ ነጻ ገበያ ስንል ፤ብሎ መፈተሸ አለበት ፡፡ ይህ አካሔድ ተገቢነት አለው ብለን እናምናለን ፡፡ በዚህም ት/ቢሮ በናሙና የተመረጡ ት/ቤቶችን የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ሞክሯል ፡፡ በዚህም ህበረተሰቡ እያቀረበ ያለው ቅሬታ መነሻ ምንድነው የሚለው ተለይቷል ፡፡ በተደረገው ጥናት የግል ት/ቤቶች ባለሃብቶችም፣ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ፣ የአስተዳደሩ ንግድ ቢሮ የተሳተፉበት ስራዎች ተሰርቷል ፡፡ የግል ት/ቤቶቹ የአከፋፈል ሁኔታ በአግባቡ ያልተኬደበት ሁኔታ አለ ፡፡ ወጥ የሆነ የክፍያ ስርዓት የለም ፡፡ በብሮሹር ይሄ ክፍያ ተወስኖብሃል፤ በሚቀጥለው ዓመት ልጅህን የምታስተምር ከሆነ ይህንን እንድትከፍል ወይም በስልክ በቴክስት መልዕክት በመላክ ወይም የትምህርት ማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ በምትደረግ ትንሽ ውይይት ላይ ያገኙትን ውጤት በመናገር ፣ የተሰሩትን ስራዎች በማስተዋወቅ ይህንን ት/ቤት የምትፈልጉ ከሆነ ይህንን ያህል ገንዘብ ያስጨምሯችኋል እንድታውቁት የሚል ነገር ነው ያለው ፡፡ነገር ግን ከሚልኩት ማስታወሻ ጋር ፈቃደኝነታቸውና ስምምነታቸው የሚረጋገጥበት የሁለትዮሽ ውይይት የለም ፡፡ ቢሮው ይህ አሰራር መስተካከል አለበት ብሎ ያምናል ፡፡ አጽንኦት ሰጥቶ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ፡፡

ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆን አማራጭ ት/ቤት ችግር ከሌለ፣ በመንግስትና በግል ት/ቤቶች መካከል ተመሳሳይ የማስተማሪያ ካሪኩለም እና መመዘኛ ካለ ይህንኑ ሁሉም ት/ቤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ ከግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የሚነሳው አለመግባባት ለምን ይከሰታል ?

አቶ ማስረሻ ፡- በት/ቤቶች መካከል ሊኖር የሚገባው ልዩነት ብዙ እና ትንሽ በማስከፈል ሳይሆን ተማሪዎች በእውቀት ፣ በክህሎት በአመለካከት ተለውጠዋል ወይ የሚለውን

Page 9: Temsalet Magazine 2 Pages

5 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ማሳየት ነው ፡፡ የትምህርት የመጨረሻው ግብ የባህሪይ ለውጥ ማምጣት ነው ስንል ደግሞ ምናልባትም እንደ ውጤት ሊሆን የሚችለው በስራ ዓለም ውስጥ ውጤታማ የሆነ ሰው መፍጠር መቻላችን ነው ፡፡ በት/ቤት ቆይታ ውስጥ በስነ- ምግባር እየተሸሻለ በአእምሮ የዳበረ፣ በዕውቀት ጎለበተ ልጅ መቅረጽ ማለት ነው ፡፡ ኃላፊነት የሚሰማው በምክንያት የሚያምን ሁለንተናዊ ስብዕና ያለው የተሟላ ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል ማለት ነው ፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ጥቂት ት/ቤቶች የውጪ ሃገር ዜጎችን የት/ቤት መግቢያ በር ላይ በማቆም የወላጆችን አስተሳሰብ በመቀየር ገንዘብ የመሰብሰቢያ አማራጭ የማድረግ ሁኔታ ይታያል ፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም ፡፡ የተሸለ ስራ እየሰሩ ያሉት ውጤታማ የሆኑ በሃገራችን የተለያዩ ሚዲያዎች የፕሮግራም ሽፋን የተሰጣቸው በገጠር ተወልደው እዚያው ተምረው የመጡ ዩኒቨርሲቲ በጥሩ ውጤት ያለፉ ራዕይ ያላቸው ተማሪዎች ማፍራታችን ልብ ሊባል ይገባል ፡፡ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ከህብረተሰቡ ጋር ጤናማ የንግድ ውድድር ይኖራቸዋል የሚል ስሜት የለኝም ፡፡ የሚመለከተው አካል በእርግጥ የንግዱን ስርዓት ይከታተላል ፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ ጤናማ እንዲሆን ከተፈለገ እውነታውን በማሳየት ወላጅ በአገልግሎቱ ረክቶ ከሆነ ቀድሞውንም ቅሬታ ያቀርባል የሚል እምነት የለኝም ፡፡ የትምህርት አገልግሎቱ እና እየከፈልኩት ያለው የትምህርት ክፍያ ተገቢ ነወይ በሚል ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል በአገልግሎት ፈላጊና በአገልግሎት ሰጪ የጋራ ውይይት መደረግ አለበት ፡፡ ግልጽነት ሊኖር ይገባል፡፡

በቅርቡ የተለያዩ ሚዲያዎች እንደተገለጸውም የፌዴራል ንግድ ውድድር እና ሸማቾች ባለስልጣን ጤናማ የሆነ ውድድር በማይፈጥሩ እና ህብረተሰቡን ባልተገባ መንገድ ክፍያ ያስከፍላሉ ብሎ የያዛቸው ቀላል የማይባሉ ወደ 190 አካባቢ የሚደርሱ ት/ቤቶች መረጃዎችን እስከ 3 ወር ከፈተሸ በኋላ ከት/ቢሮ ጋር በጋራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው ዋጋው ስለጨመረ ብቻ የተከሰሰ ት/ቤት አይደለም ፡፡ አማራጩን ህበረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀም ያላደረጉበት ሂደት ነው የተከሰተው ፡፡ ቆም ብለው እንዲያስቡ ከማለት አንጻር ነው ፡፡ ይሄ ከተስተካከለ አሁን በህብረተሰቡ እየተሰማ ያለው ቅሬታ በሂደት ሊከስም ይችላል ፡፡

የግል ት/ቤቶች በትምህርት ይዘታቸው ደረጃ

እንደሚወጣላቸው ይነገራል እውነት ነው? ይህ ከሆነ ደረጃው ምን መሰረት አድረጎ ነው የሚሰጠው? ደረጃው በት/ቤቶች መካከል አላስፈላጊ ውድድር አያመጣም?

አቶ ማስረሻ፡- ደረጃ የሚሰጣቸው ት/ቤቶች በይዘታቸው አይደለም የትምህርት ቤቶቹን ሰርተፊኬሽን ደረጃ ፍረጃ ወደ ተግባር የተገባው በ2005 ዓ.ም በኋላ ነው ከጥራት አንፃር የሚቀሩ ስራዎች ሲነሱ ይህንን የጥራት ችግር ለመቅረፍ ከሚያግዙ ስራዎች አንዱ ነው ተብሎ ታምኖበታል ፡፡ ውጤታማ እየሆነ ነውያለው ህብረተሰባችን የተሻለ ነገር የመጠየቅና የማወቅ ፍላጎት ስላለው የጥራት ጥያቄ ሁል ጊዜ ይነሳል፡፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንደ አገር አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በ1999 ተቀርጾ 6 መርሃ ግብሮችን ይዞ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ያለው፡፡ የኢኒስፔክሽን ስራ የሚያሳየው እነዚህ መርሃ ግብሮች መሬት ላይ ወርደው በምን አግባብ እየሄደ ነው፡፡ ት/ቤቶችስ ራሳቸውን እንዴት እያዩ ነው የሚሉትን ስራዎች በ26 ስታንዳርድ የመፈተሽ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ስለዚህ 26ቱ ስታንዳርድ ከግባዓት ከሂደት እና ከውጤት አንፃር ሲፈተሹ ደረጃ አንድ ላይና ደረጃ ሁለት ላይ የወደቁ ት/ቤቶች ተማሪዎቹን ት/ቤት በማቆየት ብቻ እንጂ ትምህርት እየሰጠ አይደለም ወደሚል ድምዳሜ ላይ ነው የሚያደርሰው፡፡ ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠር ያልቻለ ት/ቤት ብዙ ችግር አለበት መስተካከል አለበት ፡፡ ደረጃ3 እና ደረጃ4 ደግሞ ሞዴል መሆን የሚችሉ ት/ቤቶች ናቸው፡፡ ት/ቤቶቹ ከቲዩሪ ወይም ከንድፈ ሃሳብ በዘለለ የተግባር ትምህርት እየሰሩ መሆኑን ማወቅ የሚችሉበት መንገድ ያመቻችላቸዋል፡፡ ደረጃ ማለት ጉድለት እና ስኬት የሚያሳይ ማለት ነው፡፡ ደረጃ 1 እና 2 የሚገኙ ት/ቤቶች ያላሟሉት ነገር አላቸው ስለዚህ ማስጠንቀቂያ ነው የማንቂያ ደወል ነው፡፡ ደረጃ 3 ወደ ደረጃ 4 ለመሸጋገር የሚጎድልህ ነገር አለ የሚል ማንቂያ አለው፡፡ ደረጃ 4 ማለት ለሌሎች ሞዴል ተቋም ነው፡፡ ውድድር አይቆምም ሁል ጊዜ የተሻለ ስራ ውስጥ መግባት መቻል አለበት ከሚል እሳቤ ተነስቶ የተሰራ ስራ ነው፡፡ በተለይ አሁን የግል ት/ቤቶች በጭፍን ከመወዳደር ይልቅ ሳይንሳዊ በሆነ ፍተሻ እያለፉወይም ጤናማ እንዲያደርጉት አግዟቸዋል ብለን እናምናለን፡፡ ወላጆች ብዙ ብር በከፈሉ ቁጥር ጥራት ያለው ትምህርት ለልጆቻቸው እየተሰጠ ነው ብሎ መደምደም የለባቸውም፡፡ ደረጃና የዋጋ ተመን የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ ት/ቢሮ በዋጋ ተመን ስራ ላይ አይሰራም፡፡

በትምህርት ቤቶች ውስጥ ት/ቤት ከተዘጋ በኋላ የማሻሻያ ክረምት ትምህርት መሰጠት በት/ቢሮ አሰራር ይፈቀዳል? አጋዥ (ሪፈረንስ መጽሐፍቶች) በግል ት/ቤቶች ቢዘጋጅ ት/ቢሮው ይከለክላል ?

አቶ ማስረሻ፡-የማጠናከሪያ ትምህርት በጥሬ ቃሉ የወሰድነው እንደሆነ ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት እኩል የሆነ የመረዳት ግንዛቤ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ አንዳንዱ ተማሪ በሳይንስ ትምህርት ጥሩ ውጤት ሲያስመዘግብ ሌላውያልቻለውን ጥሩ አረዳድ እንዲኖረው ለማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉንም የትምህርት አይነቶች በመደዳው በመስጠት መሆን የለበትም ፡፡ ይህ ችግር በክረምት ብቻ ሳይሆን በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይም ይታያል፡፡ ወላጆችም ልጄ አልባሌ ቦታ ከሚውል ት/ቤት ቢውል እመርጣለሁ የሚሉት አግባብነት ይኖረዋል፡፡ ይህንን ስል በቀናነት ከት/ቤቶች ጋር ተግባብቶ የሚሰሩ ስራዎች የወላጆችን ቅሬታ አያመጣም ፡፡በግል ት/ቤቶች አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በሚል የመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም እያስተማሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ ስህተት ነው ት/ቤቶቹ የሚያደርጉት አንድ እና ሁለት ምዕራፍ በክረምት አስተምረው መስከረም ትምህርት መጀመሪያ ላይ ከምዕራፍ ሦስት የሚጀምሩ አሉ፡፡ ይሄ የተሳሳተ አሰራር ነው በት/ሚር የወረደው የትምህርት አካዳሚ የትምህርት ጊዜ ከመስከረም እስከ ሰኔ ያለው 10 ወራት ነውሁለቱ ወራቶች የእረፍት ጊዜያቶች ናቸው፡፡ ተማሪዎች፣ መምህራን ራሳቸውን በማሳረፍ ለቀጣይ ትምህርት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚደረግበት ጊዜ ነው፡፡ ሌላው ችግር ት/ቤቶቹ በክረምት አስተምረው ያልተማረውን ተማሪ በበጋው መማር አትችልም በማለት የመማር መብቱን የሚከለክሉበት አሰራር ነው፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ አሁን ምናወጣው መመሪያ ይህንን ሁሉ የሚያስተካክል ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡

ለመማር ማስተማር የሚጠቅሙ መጻሕፍት እና ማጣቀሻ ሪፈረንሶችን በጭራሽ አትስሩ ያልንበት ሁኔታ የለም ፡፡ ነገር ግን እንደ ት/ቢሮ እምነት ከትምህርት ጋር ያለ ህብረተሰብ ሁሌ ከማንበብ ጋር የተዛመደ እውቀትን በመፈለግ ላይ ያለ ነው ፡፡ ስለዚህ ጥሩ ነገሮች እንደሚፈጠሩ እናምናለን ፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች አድናቆትን ያተረፉ ስራዎች ከግል ት/ቤቶች ተቋማት እያገኘን ነው ፡፡ እነዚህ ማጣቀሻ

Page 10: Temsalet Magazine 2 Pages

6 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ተምሳሌት መፅሔት ከግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች የግል ት/ቤቶች ማህበር ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቶ ሰለሞን ገሰሰ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ይዘን ቀርበናል፡፡

የግል ት/ቤቶች ማህበር ሁሉንም ት/ቤቶች ተደራሽ ያደርጋል?

አቶ ሰለሞን ገሰሰ ፡- ከማንኛዉም የማህበሩ እንቅስቃሴና ዉጤት፤ ሁሉም የግል ትምህርት ሊባል በሚችል ተጠቃሚ ነው፡፡ነገር ግን ሁሉም የግል ት/ቤት የማህበሩ አባል አይደለም፡፡ ወደፊት በሂደት ሁሉም የግል ት/ቤት የማህበሩ አባል የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም ፡፡ የግድ መተባበር አለባቸዉ፡፡

የግል ት/ቤቶች ለአገሪቱ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ምንድን ነው ?

አቶ ሰለሞን፡- ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፡፡ ትምህርት ላይ በሃላፊነት ስሜት መስራት ሲቻል በየትኛውም መንገድ ለዉ ጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ የግል ት/ቤቶች ደግሞ ጥራት ላይ አድምተው የሚሰሩ ተቋማት ናቸው ፡፡ ከዚህ አንፃር ለሃገሪቱ ባለውለታዎች ናቸው ፡፡ ብዙ አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቀቁመዉ ተማሪዎቻቸዉን በጥሩ ሁኔታ እያነጹ ይገኛሉ ፡፡ ለምሳሌ በአገርአቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎች ተማሪዎቻቸዉን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል በማሳለፍ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ፡፡ ተማሪዎችን ከቀለም ትምህርት ባሻገር በስነ ምግባር በስራና በዘመናዊ ስተሳሰብ ኮትኩቶ በማሳደግ ነገ ኃላፊነትን ለመሸከም የሚችሉ ተማሪዎችን በማፍራት ረገድም የግል ት/ቤቶች ትልቅ አስተዋፅዎ አበርክተዋል ፡፡ ወደፊትም የተሻለ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በመንግስትና በግል ት/ቤቶች መካከል መሰረታዊ የሚባል ልዩነት አለ?

አቶ ሰለሞን፡- አኔ አለ ብዬ ነው የማምነው ፡፡ ከአንድነታቸው ብጀምር አንድ አይነት ስርዓተ ትምህርት ይተገብራሉ ፣ በአንድ ወጥ ፖሊሲም ይመራሉ፤

ነገር ግን በጥራት ላይ ስንመጣ የግል ት/ቤቶች የተሻለ የጥራት ደረጃ አላቸው ብዬ አምናለሁ ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ብዙ አመልካች መገለጫዎች አሉት :: የግልት /ቤቶች በአስተዳደር ረገድ ጊዜያቸውንና የሰው ኃይላቸውን በአግባቡ ይጠቀማሉ፡፡ ያ ደግሞ በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆነዉም የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ረድቷቸዋል ፡፡ ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ስራን እግር በእግር ተከታትሎ በመስራት ረገድ የግልት /ቤቶች የተለየ መገለጫቸው ነው ማለት ይቻላል ፡፡ ሌላው የግል ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በቅርበት ይሰራሉ ፡፡ ተማሪዎቻቸዉንም አግር በአግር ይከታተላሉ፡፡ትምህርት ቤቶችና ወላጆች አለት አለት ከመገናኘት ባሻገር በመደበኛ ፕሮግራም ቢያንስ በዓመት ለአራት ጊዜ ተገናኝተዉ በተሻለ የትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ የሚመክሩበት በደካማም ሆነ ጠንካራ ጎናቸዉ የሚወያዩበት

10

ጥያቄዎች ለግል ት/ቤቶች ማሕበር

መፅሐፎች በት/ቢሮ ሥ/ት/ዝ ባለሙያዎች ከስርዓተ ትምህርቱ ጋር ተዛማጅነት ስለመኖሩ ማረጋገጥ የግድ ነው፡፡

የግል ት/ቤቶች ያለ አንዳች የኢኮኖሚ መሰረት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም የሚል አስተያየት አላቸው ት/ቢሮ የት/ቤቶቹን የዋጋ ጭማሪ ያለ አግባብ ነው ብሎ ያምናል? በሌሎች ዘርፎችስ ከሚደረገው እርዳታ አንፃር ት/ቤቶቹ እርዳታ አግኝተዋል?

አቶ ማስረሻ፡-ቀደም ብሎ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በተደረገው የዳሰሳ ጥናት የግል ት/ቤቶች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ነበሩ እነዚህ ጥያቄዎች የት/ቤት ኪራይ አገልግሎት በየጊዜው መናር ሁለተኛ መምህራንን በክፍያ ለማቆየት የሚደረግ ነው ፡፡ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸው የስቴሽነሪ መገልገያዎች የመጨመር ሁኔታ አለ የሚሉ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ በእርግጥ አንዳድ አሰራሮች በሂደት ሊስተካከሉ የሚችሉ ይመስለኛል በግሌ ሳየው በተለይም ከአከራይ ተከራይ ውል ጋር የሚጨመርበት አግባብ ሊፈተሽ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ ሌላው የተቃረነ ነገር የምናየው ለመምህራን ስራቸውን እንዳይለቁ ማቆያ የሚከፈለውን ክፍያ በተመለከተ አንዳንድ መምህራኖች ት/ቢሮ ድረስ እየመጡ ሐምሌና ነሐሴን አናውቃቸውም ዞር በሉ እንባላለን በእኛ ስም ጭማሪ ተጨምሮ ነገር ግን ለእኛ የሚደርሰን

አናገኝም የሚሉ ብሶቶች ይሰማሉ፡፡እንግዲህ ሚዛናዊነቱ የቱ ላይ ነው ብሎ ማየቱ ጥሩ ነው፡፡በእርግጥ ይህ ሚዛን የደፋ ክስ አቤቱታ ነው ብሎ ለማስቀመጥ ሳይሆን ችግሩን ያመለክታል ስለዚህ ከህብረተሰቡ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መወያየቱ ተገቢነት ያለው ነው፡፡

እንደ ዜጋ ሁሉም በፈለገው ቦታና ት/ቤት ልጁን ማስተማር ይችላል፡፡ ነገር ግን በመንግስ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለስልጣኖች በአብዛኛው ማለት ይቻላል መንግስት ት/ቤት ልጁን ሲያስተምር አይታይም ለምን ይመስሎታል? እርሶዎ ልጅ ካልዎት ልጅዎ የት ይማራል?

አቶ ማስረሻ፡-ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች ያስተምራሉ ነገር ግን በዚህ ላይ በቂ መረጃ የለኝም እንግዲህ የግል አስተያየት ይመስለኛል እኛ የምናምነው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርት በፍታሃዊነት፣ በእኩልነት፣ ያለ አንዳች ልዩነት ማድረስ ነው፡፡ ከአቅርቦት አንፃር ሁሉንም ዜጎች ተደራሽ ማድረግ ነው የሚል ነው ፡፡ት/ቢሮ አሰራሩም ይሁንንመርህ የተከተለ ነው፡፡ ከዚህ ውጪየእገሌ ልጅ እዚህ ይማራል የእገሌ ልጅ እዛ የሚሉትን አስተያየቶች እኔ የግለሰቦች አስተያየት ነው ብዬ ነው የምወስደው፡፡

እናመሰግናለን ፡፡

Page 11: Temsalet Magazine 2 Pages

7 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

የግንኙነት መድረክ አላቸው ፡፡ በእነዚህ ቀናት ወላጅና ፣ መምህሩ ከተማሪዉ ጋር በመሆን ተማሪዉ በነበረዉ የትምህርት ትጋት አንዲሁም ስነምግባር ዙሪያ በግልጽ ይመክራሉ ፡፡ ለልጆቹም መለወጥ የተናጠል ሃላፊነታቸዉን ይወስዳሉ፡፡የግል ት/ቤቶች በያንዳንዱ ተማሪ መሻሻልና ለዉጥ ላይ ክትትል ያደርጋሉ፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በየቀኑ የሚገናኙበት የግንኙነት መስመር አላቸዉ፡፡ communication book የሚባል እለታዊ የመረጃ መለዋወጫ መፅሐፍ አላቸዉ ፡፡ ይህ በብዙ የግል ት/ቤቶች የተለመደ አሰራር ነው ፡፡ ሌላዉ የግል ት/ቤቶች ምናልባትም ከመንግስት ት/ቤቶች በተሻለ ስርዓተ-ትምህርቱን በየጊዜው ለማበልጸግ ቅርብ ናቸዉ፡፡ በክበባትና በቤተ ሙከራ እንቅስቃሴዎችም የግል ተቋማት የተሻለ የሚንቀሳቀሱ ይመስለኛል።

መንግስት ለግል ት/ቤቶች የሚያደርገው የተለየ ድጋፍ አለ ?

አቶ ሰለሞን ፡- ቴክኒካላዊ የሆኑ እገዛዎች አሉ ፡፡ መንግስት ያስቀመጠውን ስታንዳርድ ለሟሟላትና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የግል ት/ቤቶችን የሚያግዙ ፤ መንግስት ያሰማራቸው ሱፐርቫይዘሮች አሉ፡፡ እነዚህ ሱፐርቫይዘሮች ዋና ስራቸው ትምህርት ቤቶችን ማገዝና መርዳት ነው ፡፡ ሱፐርቫይዘሮች ተመድበው ት/ቤቶች ጥራትና ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ አግባብና ስርአት ባለው መልኩ ሲከናወን ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ ፡፡

ነገር ግን ከመሬት አቅርቦት፣ ከፋይናንስ አቅርቦትና ከቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚነት አንጻር ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ድጋፍ በአሁን ሰአት የለም ፡፡ አቅም ያደረጁ የግል ት/ቤቶች ቁጥራቸው ትንሽ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የግል ት/ቤቶች አቅማቸው ውስን ነው ፡፡ይሁንና በብዙ ችግሮች ውስጥ እያለፉም ባላቸው ውስን አቅም ድንቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መንግስት ተጨማሪ ድጋፍ እንደ ሌሎች ሴክተሮች ለግል ት/ቤቶች ቢያደርግላቸው ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ መገመት አያቅትም፡፡ በአጠቃላይ መንግስት ፊቱን ወደ ግል ት/ቤቶች በማዞር ከመሬት አቅርቦት፡ ከፋይናንስ አቅርቦት፡ ከቀረጥ ነጻ መብት መፍቀድና ሌሎች መሰረታዊ እገዛዎችን ሊያደርግላቸው ይገባል፡፡ ይህም የዋጋና የጥራት ተፎካካሪነትን ይጋብዛል፡፡ በዋና ከተሞች የተወሰነውም የግል ት/ቤቶች ስርጭት በክልሎች እንዲስፋፋ ትልቅና ታሪካዊ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡

ከዚህ በፊት ለግል ትምህርት ተቋማት ያልተሰጡ እንደ መጽሐፍ ማሳተም የመሳሰሉ ስራዎች በት/ቢሮ ድጋፍ እየተደረገላችሁ እንደሆነ ነው የሚገለጸው ፡፡ ማህበራችሁም ጠንካራ እንዳልሆነ ይገለፃል ፡፡ የተለያዩ ጥያቄዎችን ከማቅረብ አንፃር ማህበሩ ክፍተት ይታይበታል የሚል አስተያየት አለ፡፡ እርስዎ ይህንን እንዴት ያዩታል ?

አቶሰለሞን ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ስርዓተ ትምህርትን ስታስተገብር መጽሐፍ አሳትሞ ለመንግስትም ሆነ ለግል የትምህርት ተቋማት ማዳረስ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ በእኛ ሃገር

ስርአተ ትምህርትን የግል ተቋማት እንዲያወጡም ሆነ እንዲያሻሻሽሉ አይፈቀድም፡፡ ስርዓተ ትምህርት ይተግበር ብለህ ደግሞ መሳሪያው/የመማሪያ መጽሀፍ የለም ካልክ ሁለቱ አንድ ላይ አይሄዱም ፡፡ ያም ሆኖ ማህበራችን ትምህርት ቤቶችን አስቸግሮ የመማሪያ መፃሕፍትን ያሳተመበት ወቅትም ነበር፡፡ ከፍተኛ እጥረት በነበረበት በተለይም አንድ መፅሐፍ በ150 እና በ200 ብር በነጋዴ በሚሸጥበት ወቅት ገበያውን ሰብሮ ገብቶ መጽሃፍ በማሳተምና ለግል ት/ቤቶች በዋጋው በማሰራጨት ማህበሩ ዋጋን የማረጋጋት ስራ የሰራበት ጊዜም ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ማህበሩ መጠናከር አለበት ፤ አዎ መጠናከር አለበት፡፡ ተጠናክሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለመንግስት ማቅረብ አለበት ፡፡

ማህበሩ ከሰራቸው በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ ችግሮችን/ቀውሶችን ስርዓት ለማስያዝ ብዙ ጊዜ አጥፍቷል ፡፡ ይህም ሆኖ ደረጃ ማህበሩ ተጠናክሮና ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ ሊሰራ ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ የግል ት/ቤቶች በተሻለ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዲሁም ሃገርንና ህብረተሰብን ለመጥቀም ሁሉም የማህበሩ አባልና በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል፡፡ መንግስትም ማህበሩ እንዲጠናከር ማገዝ ያለበት ይመስለኛል፡፡

በቅርቡ ወደ ተከሰተው ጉዳይ ልምጣና የግል ትቤቶች በተጠቃሚው ላይ በተደጋጋሚ የክፍያ ዋጋ እየጨመሩ ነው በሚል የአ/አ ት/ቢሮ እና የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ አጥንተናል የሚሉት አንድ ጥናት ነበር ፡፡ የግል ት/ቤቶች ማህበሩም እንደተሳተፍበትም ይናገራሉ በዚህም መሰረት ከ194 በላይ ለሆኑ ት/ቤቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ይህንን ምን ያህል ታውቃላችሁ? አብራችሁ ሰርታችኋል ?

አቶ ሰለሞን፡- እንግዲህ አይነት ማስጠንቀቂያ ላይ እኛ የለንበትም:: በዚህ ረገድ የግል ት/ቤቶችን ማስጠንቀቂያ የሚያሰጣቸው ምንም አይነት ጥፋትም ሆነ ወንጀል ፈጽመዋል ብዬ ለመቀበል ይከብደኛል ፡፡ ነገር ግን ከወላጆች በኩል አንዳንድ ጥያቄዎች አሉ ከተባለ መምከሩ ተገቢ ነው ፡፡ ከዚህ አንፃር በዳሰሳ ጥናቱ ጅማሬ ላይ ተሳትፈን ፡፡ ነገር ግን ጥናቱ ብዙ ግድፈቶች ነበሩበት፡፡ አቀራረቡም ተገቢ አልነበረም፡፡ ሲጀመር ከ1500 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች ባሉበት ከተማ ውስጥ 16 ት/ቤቶችን ብቻ በናሙናነት መውሰድ ትክክለኛውን ምስል ለማየት ይገድባል፡፡ ይሔ በፐርሰንት ብታወጣው ምንያህል ነው? ሁለተኛ እነዚህ ት/ቤቶች ደግሞ የተሻለ ገቢ

Page 12: Temsalet Magazine 2 Pages

8 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ያለውን የህብረተሰብ ክፍል የሚያስተናግዱ ናቸው፡፡ ይህ ምን ያህል ገላጭ ነው ፡፡ ያም ሆኖ በአማካኝ የመጣው ከ70-150 ብር ወርሃዊ ጭማሪ ነው የተደረገው ፡፡ ለእኔ ግን መሰረታዊው ነገር በሃገራችን የትምህርት ክፍያ ጭማሬን የሚከለክል ወይም የሚገድብ ህግ አለ ወይ እስከማውቀው ድረስ የለም፡፡ It’s just a free market.

የግል ት/ቤቶች የቤት ኪራይ አለባቸው ፣ በየዓመቱ የደሞዝ ጭማሪ ለመምህራንና ሰራተኞች ያደርጋሉ፡፡ሲልም ሰራተኛ በሚለቅበት ሰአት በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ጭማሬ ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡ አስር ወር አስተምረውና ገንዘብ ሰብስበው አስራ ሁለት ወር ደሞዝ፤የቤት ኪራይና ሌሎች በርካታ ወጪዎችን መሸፈን ግዴታቸው ነው፡፡ መሰረታዊ የሆነው ነገር ት/ቤቶች አድመው ጭማሪ አድርገዋል ወይ የሚል ነው ፡፡ በዚህ ሁኔታ በአድማና በመመካከር በመወሰን፤ በማሴር ዋጋ የጨመሩ ሁለት ት/ቤቶች እንኳን ፈፅሞ ማግኘት አይቻልም፡፡ አንዱ ከአንዱ በማንኛውም ሁኔታ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ነው፡፡

በየዓመቱ ትምህርት ቤቶች ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖራቸው ይጨምራሉ ፡፡ ይሄ መቼ ይቆማል ሲሉም የሚጠይቁ አሉ በዚህ ጉዳይ ላይ እርስዎ ምን ይላሉ ?

አቶ ሰለሞን ፡- ይህ ጥያቄ ለእኔ መሰረታዊ አይመስለኝም:: ምክንያቱም መንግስት ለህብረተሰቡ ትምህርትን በነፃ አቅርቧል፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለም ቢባል እንኳን ማንኛውም ት/ቤት የራሱና በራሱ ልክ የተሰፋ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ምክኒያቶች አሉት፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የሉም ብሎ በዚህ ሰአት መናገርም የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ወላጅ ይህ አማራጭ በግልፅ ተቀምጦለታል ፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ የግል ት/ቤቶችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም ፡፡ የዋጋ ግሽበትን ጨምሮ በርካታ የኢኮኖሚ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል ፡፡ የኢኮኖሚ ምክንያት እኮ ባለሙያ ባልሆንም የተለያየ ነው፡፡ ለአንዱ የኢኮኖሚ ምክንያት የሆነው ለሌላው ላይሆን ይችላል ፡፡ ት/ቤቶቹ በራሳቸው የውስጥ አሰራር የኢኮኖሚ ምክንያት ይኖራቸዋል፡፡ አንድ ት/ቤት የዋጋ ጭማሪ በማያደርግበት አጋጣሚ እንኳን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖለት ነው ማለት አይደለም ፡፡ የሚገጥሙትን ችግሮች ተቋቁሞ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነት ትምህርት ቤቶችን የበለጠ ማበረታታት ያስፈልጋል ፡፡ በየዓመቱ የሚታየው ዋጋ ንረት ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ባሉበት የግል ት/ቤቶች ላይ ጣትን መቀሰር ተገቢ አይደለም፡፡ ያም ሆኖ የግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሬ ሲያደርጉ ከሞራል አኳያ የሚያስተምሩትን የህብረተሰብ ክፍል አቅም ከግንዛቤ ቢያስገቡ ከሃገራዊ ሃላፊነቶቻቸው አንዱን የመወጣት ያህል ይሰማኛል፡፡ ለዚህም ሞራላዊ ቅስቀሳና አስተምህሮ እንጂ ቁጣና ሃይለ ቃል ሊሆን በፍጹም አይገባም፡፡ ት/ቤቶች ተስፋ እንዲቆርጡ ሳይሆን የበለጠ ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ጠንክረው እንዲሰሩ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡

ለግል ት/ቤቶች ደረጃ የማውጣት አሰራር አለ የትምህርት ቤቶቹ ደረጃ በማህበረሰቡ መካከል የደረጃ ፍረጃ ልዩነት እንዲፈጠር ተፅዕኖ አያደርግም ?ከዚህ አንፃር ማህበሩ ያለው አቋም ምንድን ነው?

አቶ ሰለሞን፡- ደረጃ ማውጣቱ ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡ችግር ሊሆን የሚችለው ደረጃውን ተከትሎ አንድ ት/ቤት ይህንን ያህል ክፍያ ማስከፈል አለበት የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡የደረጃ ማውጣት ግቡ፤ ለህብረተሰቡ መረጃ ከማቅረብ የዘለለ መሆን የለበትም፡፡ ውሳኔ ሁልጊዜም ለወላጅ ሊተው ይገባል፡፡ነገር ግን በማህበር ደረጃ ተመክሮበት የተሰራ ስራ የለም

፡፡ ስታንዳርድ መውጣት አለበት በሚል የሄድንበት ነገር የለም ፡፡ የደረጃ ማውጣት ጉዳይ የወላጅ ቢሆን የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ ፡፡ ወላጅ ከፋሲሊቲ፤ ከሂደትና ከውጤት አንጻር የት/ቤቱ ታሪክና ወቅታዊ ሁኔታ ፈቲሾና የራሱን ደረጃ አውጥቶ ነው ወደ ት/ቤቶች ልጆቹን የሚልከው፡፡ ይበለጥ ግን መንግስት ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደነበረው ት/ቤቶችን በሱፐርቪዥን ፕሮግራሙ በማገዝ ት/ቤቶችን የማብቃት ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

ሌላው በአለም አቀፍ ተቋማት አማካኝነት ለመንግስት ት/ቤቶች የሚደረጉ የመጽሃፍት፤ የኮምፒውተሮችና ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፎች የግል ት/ቤቶችን በተወሰነ ደረጃ ቢያካትት ጥቅሙ ከግለሰብ ይልቅ ለሃገር ነው፡፡ የግልም ሆነ የመንግስት ት/ቤቶች የሚቀርጹትና የሚያወጡት አንድ አይነት ዜጋ ነው፡፡

ከክረምት ትምህርት ጋር የሚነሳ ጥያቄ አለ የግል ትምህርት ተቋሞች የመደበኛውን ትምህርት በክረምት ያስተምራሉ እንደውም አንድ እና ሁለት ቻፕተር ድረስ ያስተምራሉ፣ ክረምት ያልተማረ ተማሪ በበጋ አይማርም፣ ጎበዝ ተማሪ በክረምት እንዲማር ይደረጋል፣ ገንዘብ ለመሰብሰቢያ የሚጠቀሙበት ነው የሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ ይህንን እርስዎ እንዴት ያዩታል?

አቶ ሰለሞን ፡- በክረምት ትምህርት ሲጀምር ጎበዝ ሰነፍ፣ አጭር ረጅም ይማር ብሎ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም ፡፡ መሰረታዊ ሃሳቡ መማር የፈለገ ይማር ነው ፡፡ በክረምት የሚማሩ ተማሪዎች በየትኛውም ቦታ የሚማሩት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ነው ፡፡ ተማሪዎች በዚህ ሰዓት እቤታቸው ቢቀመጡ ምናልባትም በእንቅልፍ ነው የሚያሳልፉት ፡፡ ነገር ግን ንቁ ሆነው በጠዋት ሄደው ት/ቤት ቆይተው ቢመለሱ ያቺን አጭር ሰአት የተሻለ እውቀት ይገበያሉ ፡፡ በክረምት ፕሮግራም የሚሰጠው ትምህርት ከማጠናከሪያነቱ ባሻገር የማዝናናት ተፈጥሮ ያለው ነው፡፡ የተለያዩ የታቀዱ የሙዚቃ፤የስፖርት ውድድሮች፣ ጨዋታዎች ትምህርቱን ያጅባሉ፡፡ ትምህርቱም ቢሆን ልጆቹ ለቀጣይ ዓመት ትምህርታቸው እንዲዘጋጁ ያደርጋቸዋል ፡፡ ደከም ያሉበት ትምህርት ካለም እንዲያሻሽሉ እድሉን ያገኛሉ፡፡ ጎበዝ ተማሪ ለምን በክረምት ይማራል የሚለው አስተሳሰብ ግን አይገባኝም ፡፡ የክረምት ትምህርት ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶችን እንዲለማመዱ ይረዳል ፡፡ ጎበዝ ተማሪም ቢሆን እየተዝዝናና የተለያዩ ክህሎቶችን እየቀሰመ ለሚቀጥለው የትምህርት ጊዜ ቢዘጋጅ ምንም ችግር የለውም ፡፡ የክረምት ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎችን ያስገድዳሉ የሚባለው አነጋገር ስህተት ይመስለኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ወላጆች ትምህርት ቤት ከተዘጋ በኋላ ልጆቻቸውን ዘመድ ጋር ክ/ሀገርም ጭምር የሚልኩ አሉ እንዴት ተደርጎ ነው ት/ቤቶቹ ክረምት ካልተማረ ብለው የሚያስገድዱት፡፡ ይህ ተደርጎም ከሆነ ትክክል አይደለም ፡፡እንደዚሁ የመደበኛውን ትምህርት በክረምት ይጀምራሉ የሚባሉ ት/ቤቶች ካሉ ስህተት ሆኖ ይታየኛል ፡፡ ያም ሆኖ ከግንዛቤ ችግር ካልሆነ በክፋት አልወስደውም፡፡

ት/ቤቶች እርስ በርሳቸው ወይም ከመንግስት አካላት ጋር በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ማህበሩ ያለው ተሳትፎ ምን ያህል ነው ?

አቶ ሰለሞን ፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት በት/ቤቶች መካከልም ሆነ ከፍቃድ ሰጪ መ/ቤቶች ጋር የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ከማህበሩ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳና በክ/ከተማ ድረስ በመሄድ የማስማማትና የማግባባት ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

Page 13: Temsalet Magazine 2 Pages

9 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ጂቱ አለሙ ዲሪብሳ የቤተሰብ አካዳሚ ተማሪ ነች፡፡ ጂቱ አንድ ብሎ ሁለት ያለውን የትምህርት ቤት ዳዴዋን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በጥሩ ውጤት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ተቃርባለች፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ደጃፍ

ላይ ቆማ ብዙ ታስባለች፤ አብዝታም ትጥራለች ይህ ጥረቷ ታዲያ በተለይ በሳይንስ ትምህርቶች እጅጉን ውጤታማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ጂቱ ትላለች “የሳይንስ ትምህርቶችን ከልቤ እወዳለሁ በዚህኛው ዘመናዊ ዓለም ደግሞ ማንኛውም ነገር እውን የሚሆነው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው፡፡”ይህ የሳይንስ ትምህርት ፍቅሯ ዛሬ ላገኘችው እድል በር ከፋች ሆኗል፡፡ ሴቶችን በሳይንስ /Women in science/ ከመላው አፍሪካና አሜሪካ ለተገኙ በሳይንስ የትምህርት ዓይነቶች ጥሩ ውጤት ላላቸው ሴት ተማሪዎች በክረምት ወራት የሚሰጥ ስልጠና ነው ፡፡ የስልጠናው መጠሪያ በአጭሩ ዊስ ካምፕ (Wisci Camp) ይባላል ፡፡ ይህ ስልጠና ሴቶች በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ አቅማቸውን የሚያሳድግ ስልጠና ነው፡፡

ስልጠናው ለ25 ቀናት በሩዋንዳ በሚገኘው በጋሻራ የልጃገረዶች አካዳሚ ይሰጣል፡፡ ሴት ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በአርት፣ በዲዛይን እና በሒሳብ ዘርፎች ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ስልጠናው እድል ይሰጣል፡፡

ሴት ተማሪዎቹ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሸኛኘት

ሲደረግላቸው በስፍራው የተገኙት የአሜሪካ የዓለም አቀፍ አጋርነት ምክትል ልዩ ተወካይ ቶማስ ዲባስ ይህ በተለያዩ አካላት ትብብር የሚዘጋጀው ስልጠና ሴት ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች እውቀት እንዲጨብጡና ክህሎታቸውንም እንዲያሳድጉ እድል ይፈጥራል ፡፡ ከስልጠናው በኋላ ሴት ተማሪዎችም ለዓለም ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ቀላል አይሆንም ብለዋል፡፡

የዊስ ካምፕ ስልጠና በአሜሪካ መንግስት፣ በማይክሮ ሶፍት፣ በኢንቴል ኩባንያ፣ በአፍሪካ ሊደርሽፕ አካዳሚና ሌሎችም አካላት ትብብር የሚዘጋጅ ነው፡፡ ለሦስት ሳምንታት በሚቆየው ስልጠና የኮምፒውተር ሳይንስ፣ የሮቦት ቴክኖሎጂ፣ የዲዛይን፣ የአርት፣ የባህልና የፈጠራ ክህሎት የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎቹ በቡድን በመሆን ትናንሽ ፕሮጀክቶችን ይሰራሉ፤ በአመራር፣ የገበያ ጥናትና በተለያዩ አነቃቂ ስልጠናዎችን ያገኛሉ ተብሏል፡፡ ጂቱ ስልጠናውን ለመውሰድ ከአፍሪካ ሊደርሽፕ አካዳሚ ከኤስ ኦ ኤስና ከልደታ ካቶሊክ ከተገኙ ሌሎች 12 ሴት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር ወደ ሩዋንዳ ሄዳለች፡፡

በሩዋንዳው ጋሸራ የልጃገረዶች አካዳሚ ከጋና፣ ኬኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ዩጋንዳና አሜሪካ ከተገኙ ሌሎች ሴቶች ጋር ቁጥራቸው 120 ይደርሳሉ፡፡ ህሊና ታመነ እና በአምላክ ታደሰም ከጂቱ ጋር ከሩዋንዳ ስልጠና ሲመለሱ አገሪቱ በሳይንሱ ዘርፍ ለሰጠችው ትኩረት ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው እርግጠኛ ሆነው ይናገራሉ፡፡

የነገ ዛሬዎች

ፎቶ

አ.

አ አ

ሜሪካ

ኤም

ባሲ

Page 14: Temsalet Magazine 2 Pages

10 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ከፒያሳ የተነሣው ‘ሃይገር ባስ’ መገናኛ ተሳፋሪ ሊያወርድ ቁሟል። መገናኛ ላይ ለውዝ የሚያዞሩ ልጆች አሉ። ባትፈቅድም አስገድደውና ይሉኝታ(“ሼም”) አስይዘው ያስገዙኻል። ከአዟሪዎች አንዱ ወደ ተሳፈርንበት ‘ሃይገር’

ገብቶ ሦስትና አራት ፍሬ ለውዞች በየሰው እጅ እያስቀመጠ ሁሉንም አዳረሰ። እጅህ የሆነ ነገር ይዞ ልትቀበለው ካልቻልክ ለውዙን የሸሚዝ ኪስህ ውስጥ ጨምሮት ያልፋል። አጠገቤ የተቀመጠው ልጅ ለነገሩ እንግዳ ስለሆነ ተደናግሯል። አንዴ ለውዝ ሻጩን፣ ከዛም እጁ ላይ ያለውን ለውዝ፣ መጨረሻ እኔን አፈራርቆ ተመለከተ። ሻጩ ኋላ ደርሶ ሲመለስ ለቅምሻ እጃቸው ላይ ላስቀመጠላቸው ሁሉ በወረቀት የተጠቀለለ ለውዝ ጣል ጣል አደረገላቸው።“ምንድን ነው? ምን ላድርገው?” ከጎኔ የተቀመጠው ልጅ እንደተደናገረነው።

“የሃይገር ቁርስ ነው! እዚህ በቁርስ እየተንከባከቡ ነው የሚያደርሱህ” አልኩት ሳቄ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ።

“እንዴ!? እውነትክን ነው?” ልክ ቁርሱ መጥቶ ቡናው እንደዘገየበት ሱሰኛ ፊትና ኋላ ተገላምጦ ረከቦት የተዘረጋበትን ቦታ ማፈላለግ ጀመረ። ሳቅአፈነኝ። ሻጩ ‘ሃይገሯ’ን እንደታቦት ንግሥ ለሦስተኛ ጊዜ ዞራት። አሁን ገንዘቡን እየለቀመነው። ወንበር የተጋራኝ ልጅ በእጁ ጭብጥብጥ አድረጎ የያዛትን የመጓጓዣ ገንዘቡን ቆጠራት-አራት ብር።

“እህ!? ምን… ማለቴ…ምን ማለት ነው? እንዴት?” ሳልፈልግ… በሻጩ መገደዱ አሞታል።

“አልበላኸውም አይደል? መመለስ ትችላለህ እኮ!”

“አስገደዱኝ አይደል እንዴ? አስገደዱኝ እኮ!”

“አልፈልግም አታስገድዱኝ! በል እያልኩህ ነው ሰውዬ”

“አታይም!? ሰው ሁሉ ከፈለኮ!”

“አንተ ግን ካልፈለከው አለመክፈል ትችላለህ”

“ሼም ይሆንብኛላ!!”

“እንግዲህ ወይ ሼምህን ወይ ብርህን አትርፍ” አበሳጨኝና መጽሐፌን ገልጬ ለማንበብ ሞከርኩ።

“ይኼውልህ ወንድሜ… ቢኖረኝ እኮ…”

“ለምን ድምፅህን ለኔ ብቻ እንዲሰማ ትቀንሰዋለህ? ለቀቅ አድርገውና ሻጩ ሰምቶ ይራራልህ ይሆናል።” ልጁን ማንቃት ከበደኝ፡፡ ልክ ማይምነትን ለማስወገድ የዕድገት በሕብረት ዘመቻ የዘመትኩ ነው የመሰለኝ። ስንቱን

ፈርተን እንኖራለን? አንድ ወይም ሁለት ብር ከፍዬ ልላቀቀው ፈለኩግን እንዲህ ዓይነቱ ሰው ነገም ‘ሼም’ን ፈርቶ ሌላውን ማስቸገሩ አይቀርም። ኤጭ ምነው እቴ!?

“ለምን መብትህን ታስደፈጥጣለህ? አይሆንም አልከፍልም አትልም? ምን ይመጣብኻል?” አንድ ወደ ጎልማሳነት በመገሥገሥ ላይ ያለ ወጣት ንግግራችንን ሰምቶ ልጁን አደፋፈረው። ጎልማሳው በቲሸርት ላይሹራብ፣ በሹራብ ላይ ጠቆር ያለ ኮት ለብሷል። አውራ ጣቴን ቀስሬ ሐሳቡን “ላይክ” ማድረጌን አሳየሁት።

“ይገርምሃል እኔ አልከፍልም አልኩ። አዳሜ ግን ‘ምናላት አንድ ብር… ሁለት ብር ናት እኮ!’ ብለው::

አንድ ብር ለነሱ ቀላል ነገር መሆኗን ነገሩኝ። ሃቁ ግን ‘ሼም’ ይዟቸው ነው እንጂ ሁለት ብር ለነሱም ቀላል አይደለም። እንደኔ ተጋፍቶና ቁሞ እየሔደ አንድ ብር ምናላ ትይለኛል!” አጠገቡ ያሉትን ወረፋቸው። ሻጩ እንደ ጥሩ አዛኝ እጃችንን ፈልቅቆ በጣቶቻችን ልክቆጥሮ ያዘጋጀውን የለውዝ ፍሬ ያስጨብጠናል። ያልታሰበ ሲሳይ መጣልኝ ብሎ ወደ አፉ ከላከሰው ኪስ ሁለት ብር ፈልቅቆ ይወስዳል።

“…እንዴት ለሁለት ብር ብለህ አትጨቃጨቅ ትሉኛላችሁ? ሁለት ብር ቀላል ነገር ነው?...”

ሰውዬው በነካ አፌ ብሎ ነው መሰል ብሶቱን ቀጠለ።

“… አምና ከቤቴ ወጥቼ ከሻሼ ቁርስ ቤት አንድ ቆቆር(ፓስቲኒ) በሻይ አወራርጄ ነበር ሥራ የምገባው። አሁን ግን አልሆነም። ሻሼ ራሷ በአርከበ ሱቅ እየነገደች አንድ ፓስቲኒ ሦስት ብር ካልሆነ አልሸጥም አለች። ስለዚህ እሷጋ ስደርስ ፊቴን አዙሬ ባላየ ‘ሙድ’ አለፍኳት። ታዲያ ለምን ለምፈልገው ነገር ያላወጣሁትን እዚህ እንዳወጣ እገደዳለሁ?” ብሶቱን ሲዘረግፈው የብሶታቸው ድምፅ ማጉያ የሆነላቸው ሁሉ ፊታቸውን ኮስኩሰው(አጨፍግገው) ያዩታል። ሌሎች ደግሞ እነሱን የሚመለከት ጉዳይ ያነሣ አላስመሰሉትም። እንዲያውም “ምን ለአንድ ብር ያጨቃጭቀዋል?…” ይላሉ -በሹክሹክታ።

“…የኑሮ ውድነትና ገበያው በየምክንያቱ ደፍጥጠው ደፍጥጠው ረብየለሽ ያደረጉትን ኑሮዬን እንደዚህ ዓይነት ጥቃቅን መንግሥታት ደግሞ ይኼው በየምክንያቱ ይደፈጥጡታል። ባይሆን ትንንሽ መንግሥት የሆኑብንን ተውን እንበላቸው እንጂ ጎበዝ!?

አሁን ብዙዎቹ በድንጋጤ አፍጥጠው እየተመለከቱት ነው።

“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን!

ሆነ ነገር። አቦ ከፍ ብለህ ጩህ! ብትችል ቤተመንግሥት አካባቢ” ለውዝ ሻጩ ብሩን ይዞ እየወረደ የተናገረው።

የሃይገርወጎች

በ ወንድወሰን ውቤ

Page 15: Temsalet Magazine 2 Pages

11 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

መግቢያ‹‹ልጅ ያለው ሰው ሁሉ ልጁ ክፉንና በጎውን የሚለይበትን፣ንጉስና ፈጣሪውን የሚለይበትን እውቀትን ለማግኘት፤ የንባብንና የጽህፈትና ትምህርት ያላስተማረ መቀጫውን 50 ብር እየከፈለ የመቀጫውን ገንዘብም ወደ ቤተ እምነት እያገባ ለነዳያን ምግብና ልብስ ይሆናል ፡፡ የንስሀ አባትም የሆንክ የንስሀ ልጆችህ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ ምከር….ይህንን ሳትቀበል ሳታስተምር የቀረህ እንደሆነ ግን በሹመትህ ትቀጣለህ፡፡››

ይህ አዋጅ የዘመናዊ ትምህርት ጅማሮን ያበሰረ፣ የትኛውም ወላጅ ልጁን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልክ የሚመክር፣የሚገስጽ ካልሆነም የሚቀጣ ህግ የተቀመጠበት እ.አ.አ በ1921 ዓ.ም የወጣ አዋጅ ነበር ፡፡ አያሌው ሺበሺ /ማኅተመሥላሴ ወልደ መስቀል ዝክረ ነገር/ ብለው በጻፉት መጽሀፍ ላይ የተወሰደ ፡፡

ከሃይማኖት ንክኪ ነጻ የሆነና ዘመናዊውን ትምህርት በመላው ሀገሪቱ እንዲሰጥ ንግሥት ዘውዲቱ የአጤ ሚኒሊክን ፈር በመከተል የወጡት አዋጅም እንደሆነ ይነገራል፡፡ በ1908 እ.አ.አ አጤ ሚኒሊክ በስማቸው የተሰየመውን የመጀመሪያውን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በትብብር መክፈታቸውም ይታወሳል ፡፡

በመንግስት ትምህርት ቤት የተጀመረው የትምህርት ስርዓትና አካሄዳችን በዘመናት ቆይታው የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ከ1983 ወዲህ ደግሞ በርካታ የግል ትምህርት ቤቶችንና ተቋምትን ማፍራት ችሏል፡፡አሁንም በየአመቱ የትምህርት ቤቶቹ ቁጥር እያጨመረ መምጣቱን ማየት ይቻላል፡፡

ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ጎን ለጎን የግል ትምህርት ቤቶች እና ተቋማት ለሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት የኩላቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ የተምሳሌት የዝግጅት ክፍልም ትምህርት ዘርፍ በአገልግሎቱ መስክ ውስጥ ቢሆንም ከአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ወይም ከሸቀጥ ሸመታ በተለየ የሚታይበት መንገድ ባለመኖሩ የትምህርቱ ዘርፍ ተገቢው ድጋፍ

እየተደረገለት ነው ወይ ስትል ጥያቄ አንስታ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ አፈላልጋለች፡፡

ለትምህርቱ ዘርፍ የሚደረግ ድጋፍመንግስት በየዓመቱ የሚይዘውን የትምህርት በጀት ለመንግስት ትምህርት ቤቶች እንደየደረጃቸውና እንደየተማሪዎቻቸው ብዛት የሚያከፋፈል እንደሆነም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ይጠቁማል፡፡ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 41/4 መንግስት የጤና የትምህርት እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለህዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሃብት ይመድባል ይላል ፡፡ይሁን እንጂ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚታዩ የመጽሀፍት ፣ የቤተ ሙከራና የቁሳቁስ እጥረቶች እንዲሁም የመምህራን በጊዜው ያለመመደብ ክፍተቶች አሳሳቢ ችግሮች ሆነው ይታያሉ ፡፡ በተመሳሳይ ትምህርት ቢሮ ለግል ትምህርት ቤቶችም መጽሀፍት አሳትሞ እንደሚያከፋፍል ይገልጻል ፡፡ ሆኖም የግል ትምህርት

ትምህርት በጥርስ መካከል

በ አዲስ ፀጋዬ

Page 16: Temsalet Magazine 2 Pages

12 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ቤቶቹ መንግስት ከመጽሀፍ እደላው ባሻገር መንግስት መሰረታዊ የሚባሉ እገዛዎችን እያደረገ አይደለም የሚል ስሜት አላቸው ፡፡ ለአብነት ያህል

የመሬት አቅርቦት ፡- መንግስት መሰረታዊውን የመሬት አቅርቦት ለግል ትምህርት ቤቶቹ ለመስጠት ያሳየው ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ነገር የለም ይላሉ፡፡

የፋይናንስ ድጋፍ፡- መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረኩ ነው ሲል ቢደመጥም በተለይ ለግል ትምህርት ቤቶች የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትን መንገድ እንዲፈጥሩ የሚያደርገው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ነው ሲል የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር በበኩሉ ይጠቅሳል፡፡

የቀረጥ ነጻ መብት፡- በዚህ መብትም ተጠቃሚ ያለመሆናቸውን የግል ት/ቤቶች ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ድጋፎች አለመኖራቸው ደግሞ በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡

ትምህርት ኢንቨስትመንት ወይስ ሸመታ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በተለይም ብዙ ካፒታል በሚጠይቁ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡ በማኑፋክቸሪንግ ፣በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ሰፋፊ እርሻዎችና ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚዎች በሁለት መልኩ ማበረታቻ ይደረግላቸዋል ይላል ፡፡ የመጀመሪያው ማበረታቻ ከቀረጥ ነጻ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ /duty free/ ማድረግ ሲሆን በዚህ እድል ማሽነሪዎችን እስከ 100% ነጻ እንዲሁም የማሽኖቹን 15% የሚሆኑ መለዋወጫዎችን በነጻ ማስገባት ይችላሉ ፡፡ ሌላው የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜ /tax holiday/ መስጠት ሲሆን እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነትና እንደመገኛ ስፍራው ከሁለት እስከ አምስት አመት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ከነዚህ ዘርፎች በተጨማሪም መንግስት የአገልግሎት ዘርፉ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ይሸፈናል ብሎ ያምናል፡፡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚሳተፉ የውጭ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ሲገቡ የራሳቸውን ህንጻ እንዲገነቡ ይገደዳሉ ፤ ይህም በቀላሉ ኢንቨስትመንቱን ትተው እንዳይሄዱ የተወሰደ እርምጃ ነው ሲሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ይገልጻሉ ፡፡ እንደ ኮሚሽኑ ለትምህርት ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በዝቅተኛ ቀረጥ በማስገባት መንግስት የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ይገልጻል ፡፡ ነገር ግን ለትምህርት ቤቶች በተለይም ለግል ትምህርት ቤቶች

ተብሎ የተዘጋጀ የኢንቨስትመንት መሬትና የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜ አለመኖሩን ያስቀምጣል፡፡

በኢንቨስትመንቱ ያን ያህልም ተጠቃሚ ያልሆነው የትምህርቱ ዘርፍ ወላጆች አገልግሎትን በገንዘባቸው የሚገዙበት፤ ትምህርት ቤቶች ደግሞ የሚያቀርቡ ሆነው በሸማችና በሸመታው ዘርፍ የሚዳኙበት አግባብ እንዳለ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ይጠቁማል፡፡ በዚህ ዘርፍ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡት የትምህርት ሁኔታ ወይም ትምህርቱ ጥራትን ሳይሆን የክፍያ ዋጋ ላይ ብቻ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ብዙም ድጋፍ ያላገኘው የትምህርት ዘርፉ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ ወይም በሸመታው ዘርፍ የሚታይበትም አግባብ ተፈጥሯል ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሰሞነኛውን የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ጭማሪና ይህንን ተከትሎ የተነሳውን ውዝግብ ማንሳት ይቻላል፡፡

ነጻ ገበያና የክፍያ ተመንበነፃ ገቢያ የኢኮኖሚ ፅንሰ ሃሳብ የግል የንግድ ተቋሙና ሸማቹ በሚስማሙት መሰረት የሚከናወን የግብይት ስርዓት ነው፡፡ በዚህ ስርዓት መንግስት በንግድ ውድድርና ሸማቾች አዋጅ እንደነገገው ለነጻ ገበያ አመቺነት ያለው ስርዓት ከማስፈን እና የንግዱን ህብረተሰብ ከፀረ-ውድድርና ተገቢ ካልሆኑ ተግባራት ከመከላከል በዘለለ በአቅርቦቱ እና በፍላጎቱ መካከል ጣልቃ እንደማይገባ ተቀምጧል ፡፡ ነጻ ገበያ መሰረት የሚያደርገው ገበያውን ብቻ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በአቅራቢዎቹም መካከል የግል ድርድር በማድረግ ሸማቹ በሚገዛው ነገር ላይ ተመሳሳይ ዋጋ የማስተመን (Price setting) ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ይህ ሆኖ ሳለ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የግል ት/ቤቶች በክፍያው ላይ በየዓመቱ ጭማሪ እያደረጉ ነው ሲል ይከሳል ፡፡ የዋጋውን ተመን መሰረት በማድረግም ቅሬታ ያቀርባል ፡፡ በሌላ በኩል ዋጋውን መሰረት ያደረገ የዋጋ ተመን በግል ት/ቤቶቹ ላይ እንደማይጥል ያስታውቃል፡፡

የግል ት/ቤቶች ክፍያ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በስሩ የሚገኙትን የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ስርዓት ይቆጣጠራል፡፡ ከዚህ ባሻገር የግል ት/ቤቶቹ ክፍያ ላይ መንግስት እጁን ማስገባቱ ለምንድን ነው ሲሉ የሚጠይቁ አሉ ፡፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የት/ቤቶቹ የክፍያ ጭማሪ በየዓመቱ የሚደረግ እና የኢኮኖሚ ምክንያት የሌለው ነው ሲል 194 ለሚሆኑ የግል ት/ቤቶች ከት/ቢሮ ጋር በመሆን ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጧል ፡፡ ባለስልጣኑ የግል ት/ቤቶችን ጥራት ጉዳይ የሚከታተለው የአዲስ አበባ ት/ቢሮ መሆኑንም አያይዞ አስቀምጧል ፡፡ ታዲያ ይህ ተግባር የአንድ ት/ቤትን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ ደረጃና ብቃት ያገናዛባል ? በዋጋ ላይ ብቻ መሰረት ያደረገ ፍተሻ ማድረግስ ተገቢ ነው ?

የኢኮኖሚ ምክንያት የግል ት/ቤቶች ካለ በቂ ምክንያት በክፍያ ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርገዋል የሚሉ ሃሳቦች በተደጋጋሚ መነሳታቸውን እና ይህንንም አዲስ አበባ ት/ቢሮም ሆነ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን በጥናት ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢኮኖሚ ምክንያት ምንድነው? ብለን ስንነሳ በዋናነት የኢኮኖሚ ምክንያት በሀገሪቱ ካለው የእቃዎች ዋጋ መናርና ከዋጋ ግሽበት/ Inflation /ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችል ነው፡፡

በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት ተቋማት

ዓመት 2002 ዓ.ም

2003 ዓ.ም

2004 ዓ.ም

2005 ዓ.ም

2006 ዓ.ም

አማካይ አመታዊ እድገት

ትምህርት ቤቶች/ተቋማት/

መዋዕለ ህጻናት 3318 3418 3580 3688 4560 6.6

የመጀመሪያ ደረጃ 20251 28349 29643 30495 32048 3.5

ሁለተኛ ደረጃ 1335 1517 1710 1912 2333 11.8

የመምህራን ትምህርት 29 32 32 34 34 3.2

ቴክኒክና ሙያ 460 505 502 437 437 -1.0

ከፍተኛ ተቋማት 70 74 91 99 124 12.1

ድምር 32163 33895 35561 36665 39536 4.2

የትምህርት ሚንስቴር አመታዊ የትምህርት ስታትስቲክስ 2006 ዓ.ም 2013/14

Page 17: Temsalet Magazine 2 Pages

13 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ያናገርናቸው አንድ ምሁር እንደሚሉትም “Inflation is defined as a rise in the general price level. In other words, prices of many goods and services such as housing, apparel, food, transportation, and fuel must be increasing in order for inflation to occur in the overall economy. If prices of just a few types of goods or services are rising, there isn’t necessarily inflation.”ግሽበት የሚለካው በአጠቃላይ ዋጋ ጭማሪ መሰረት ነው ፡፡ በሌላ አነጋገር ብዙ የአገልግሎት እና የሸቀጥ ዋጋዎች ጭማሪ ሲታይባቸው ነው ፡፡ እነዚህም ቤቶች ፣ አልባሳት፣ ምግብ፣ ትራንስፖርት፣ እና ነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርግ ሲሆን ነው ፡፡ በጥቂት ግብይቶች ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ የዋጋ ግሽበትን አያስከትልም፡፡

በዚህ መረጃ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የዘንድሮ እና የዓምና ተመሳሳይ ወሮች ኢንዴክስ የችርቻሮ ዋጋ 11.9 % ጭማሪ ማሳየቱን ለመረዳት ተችሏል ፡፡ በሌላ በኩል ትራንስፖርት 4.8 % መገናኛ 0.6 % ትምህርት 0.9 % ቅናሽ አሳይቷል ፡፡ ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት የሚባለው ረዘም ያለ ጊዜ ሲንከባለል የመጣ የዋጋ ግሽበት ነው፡፡

ከዚህ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ሪፖርት መረዳት የሚቻለው ሁለት ነገር ነው ፡፡ የመጀመሪያው የት/ቤቶቹ የዋጋ ጭማሪ የኢኮኖሚ መሰረት የለውም የሚለው ክስ በዚህ መረጃ መሰረት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡ ሌላው በአገልግሎት ዘርፍ በተለይም በትራንስፖርት፣ በመገናኛና እንዲሁም

ከፍተኛ ጭማሪ እየታየበት ነው የሚባለው ትምህርት በአንጻራዊነት ቅናሽ የሚያሳይ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል ፡፡

የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን በግል ት/ቤቶች ውስጥ የተደረገው ጭማሪ ለ3 ተከታታይ ዓመታት መሆኑንና 97% ያህል የሚሆኑ ት/ቤቶች ጭማሪ ማድረጋቸውን ይህም በባለሥልጣኑ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች መረጋገጡን ይገልጻል ፡፡እነዚህ የማዕከላዊ ስታስቲክስና የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ሁለት መረጃዎች እርስ በእርሳቸው የተጣረሱና አንድ አይነት መደምደሚያ ላይ ለመድረስም አሻሚ ሆነዋል፡፡

ወላጆች ምን ይላሉ?ወላጅ 1

ወ/ሮ ስርጉት በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሴት ናቸው፡፡ ሁለት ልጆቻቸውን በግል ት/ቤት ውስጥ የሚያስተምሩ ሲሆን ወላጇ እንደሚሉት በየዓመቱ ለት/ቤት ከሚከፍሉት ዋጋ በተጨማሪ ለተለያዩ መገልገያዎች የሚያወጡት ወጪ እንዳስመረራቸው እና መንግስት ጣልቃ ገብቶ የዋጋ መረጋጋት ማድረግ እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡

ወላጅ 2ዶ/ር አብረሃም የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ናቸው ፡፡ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት በግል ት/ቤት ነው ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ት/ቤቶቹ በየዓመቱ ከሚጨምሩት ክፍያ ይልቅ ልጆቻቸው የተሻለ ትምህርት አግኝተዋል ወይ ብለው ይጠይቃሉ ፡፡ መንግስት የዋጋ ተመን ውስጥ ገብቶ ከሚሰራ ይልቅ በሀገሪቷ ላይ ያሉ ት/ቤቶች የግልም ሆነ የመንግስት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች የሚሰጥበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ባይ ናቸው፡፡ ዛሬ ልጄን በክፍያ መጨመር ምክንያት ወደ ት/ቤት ባልወስደው ሌላ አማራጭ አለኝ ወይ ሲሉም ይጠይቃሉ ፡፡ ራሳቸው ሲመልሱም የለኝም ፡፡ በርካታ ጥራት ያላቸው ት/ቤቶች የሚፈጠሩ ከሆነ ወላጅ ብዙ አማራጭ ይኖረዋል ፡፡ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረም ወላጅ ዋጋ ብቻ ሳይሆን ጥራትንም ማወዳደር ይጀምራል የሚል እምነት አላቸው፡፡

ማጠቃለያለቀጣይ የኢትዮጵያ እድገት ወሳኙ የሰው ሀይል መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡በተለይም የተማረ ራሱን ለእውቀት ያስገዛ ሀይል እጅጉን ትፈልጋለች፡፡ እናም እነዚህ ሀይሎች የሚፈራባቸው ተቋማት ሳሙናና ብረት ከምናገኝባቸው ፋብሪካዎች በተሻለ ወይም በበለጠ ድጋፍ ሊደርግላቸው ይገባል፡፡ መንግስት በስሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን አቅም በማጎልበት ተወዳዳሪነቱ ላይ በመስራት ለወላጆችና ለተማሪዎች አማራጭ መፍጠር ይኖርበታል፡፡ ለግል ትምህርት ቤቶች የሚደረገው ድጋፍም ቸል ሊባል አይገባም፡፡ የግል ትምህርት ተቋማቱም ከመንግስት የትምህርቱ አካላት ጋር በአዎንታዊ አመለካከት ተቀራርበው መስራት ቢችሉ በየጊዜው ለሚያነሷቸው የፋይናንስና የመሰረተ ልማት እጥረቶች መፍትሄ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ በትምህርቱ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አካላትም በትምህርት ተቋማቱ ላይ እርምጃ ከመውሰዳቸው አስቀድመው ህገ መንግስቱን ጨምሮ የሀገሪቱን ህጎች የሚጥስ ስላመሆኑ በእርምጃውም ወላጅና ማህበረሰቡ ተጎጂ ስላለመሆናቸው ሊያረጋግጡ ይገባል፡፡ የሀገሪቱ ከኢንቨስትመንቱም ከሸመታውም ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን ያልቻለው የትምህርቱ ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይልን እንዲያፈራ በትንንሽ ምክንያቶች ጫና ከማብዛት ይልቅ ቁጥጥሩንም ከድጋፉንም ማጠናከር ይገባል፡፡

የፌዴራል ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም ሪፖርቱም በሀገሪቱ ባሉ አብዛኞቹ ምርቶች ላይ ጭማሪ ማሳየቱንይገልጻል ፡፡ ግሽበትም መኖሩን ያሳያል፡፡

ጥናት የተደረገበት

ጊዜ

አገልግሎቶች ተንከባላይ የዋጋ

ግሽበት

አጠቃላይ ግሽበት

ምግብ ነክ ምግብ ነክ ያልሆኑ

2007 ዓ.ም 8.0% 8.0% 8.1 % 7.7 %

መረጃ ቁ. 29 2007 ዓ.ም

Page 18: Temsalet Magazine 2 Pages

14 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

የግል ት/ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ፤ ደንብ ቁጥር 206/1987 ከወጣ 20 ዓመታት ተቆጥረዋል ፡፡ ደንቡን ተከትለው የሚከናወኑ የአፈጻጸም ስራዎች የሚተገብረው መመሪያ ግን አልወጣም፡፡ በዚህ የተነሳ ከግል ት/ቤቶች ጋር የሚነሱ

አለመግባባቶች በልዩልዩ አካላት የተለያዩ ምላሾች ሲሰጣቸው ይስተዋላል ፡፡ ደንቡ ሳይሻሻል የቆየበት የራሱ ምክንያቶች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ደንቡ ባለመሻሻሉ የተፈጠሩ ክፍተቶች ምንድናቸው የሚለውን መመልከቱ አግባብ ነው ፡፡ ማሳያ 1፡- በደንቡ አንቀጽ 6 ላይ የግል ት/ቤቶች ፈቃድ ለማውጣት የሚቀርቡ ማመልከቻዎች በመመሪያው መሰረት እንደሚዘጋጁ ይደነግጋል ፡፡ ይሁንና በትምህርት ሚኒስትር መዘጋጀት የነበረበት መመሪያ አልተዘጋጀም ፡፡ መመሪያው በዝርዝር ሊሸፍናቸው የሚገቡ አሰራሮች ወጥነት በሌላቸው ህግን መሰረት ያላደረጉ አሰራሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በአ.አ.ዩ የህግ መምህሩ ይገልጻሉ ፡፡ መምህሩ አያይዘውም የህግ፣ የደንብ እና የመመሪያ አስፈላጊነት ህጉን ባወጣው አካል በራሱ ተከባሪ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል ይላሉ ፡፡ ት/ቢሮ ከግል ት/ቤቶችና ተቋማት ስታንዳርዱን የጠበቀ ትምህርት ቤት መኖሩን ለማረጋገጥ የመመሪያው አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም ፡፡ ይሁንና ት/ቢሮ የአንድን የግል ት/ቤት ፈቃድ ለመስጠት የሚያወጣው ስታንዳርድ የራሱ ቼክ ሊስት በማዘጋጀት እየሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡

ማሳያ 2፡- በደንቡ አንቀጽ 6/2 ላይ አንድ የግል ት/ቤት የሚያቋቁም የአገር ውስጥ ባለሃብት 250 ሺህ ብር ኢንቨስት የሚያደርግ ከሆነ ከሚያቀርበው ማመልከቻ ጋር የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማቅረብ እንዳለበት ይደነግጋል ፡፡ ድንጋጌው አስገዳጅ መሆኑ ብቻ አይደለም፤ በደንቡ ውስጥ የተጠቀሰው የኢንቨስትመንት አዋጅ 15/1984 ለአራት ጊዜ ያህል የተሻሻለ መሆኑን ልብ ይሏል ፡፡ በተሻሻለው ኢንቨስትመንት አዋጅ ለግል ት/ቤቶች የሚደረግ ማበረታቻ እንደሌለ የሚገልጹት የኢንቨስትመንት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ ትምህርት ከሁሉም በተሻለ መልኩ በመንግስት ትኩረት የተሰጠው የኢንቨስትመንት ሴክተር ቢሆንም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ቅድሚያ የሚሰጣቸው እንደ ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ እርሻ ኢንዱስትሪ፣ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ እና አይ ሲቲ ያሉ ዘርፎች ናቸው፡፡

ማሳያ 3፡- በደንቡ አንቀጽ 12 ላይ አንድ የግል ት/ቤት ስታንዳርድ ባለመጠበቁ ወይም ደንቡን ተከትሎ የሚወጡ መመሪያዎችን ባለማክበሩ ፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እርምጃ እንደሚወስድ

ይደነግጋል ፡፡ ይሁንና መመሪያው ባለመውጣቱ የተነሳ በአሁኑ ሰዓት በግል ት/ቤቶች ውስጥ ተከስቷል በተባለው ያለ አግባብ የዋጋ ተመን ጭማሪ ላይ ት/ቢሮ፣ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ፣ የግል ት/ቤቶች ማህበር እንዲሁም የከተማው ንግድ ቢሮ እያወያየ ይገኛል ፡፡

ማሳያ 4፡- በደንቡ አንቀጽ 13 ላይ አንድ የግል ት/ቤት ተቋም ፈቃዱ የተሰረዘበት ወይም ስራውን ያቋረጠ እንደሆነ ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎች በምን አግባብ ወደ ሌላ የትምህርት ተቋም እንደሚዘዋወሩ ወይም ከት/ቤቱ ጋር የሚነሱ አለመግባባቶች በምን መንገድ እንደሚፈቱ ያስቀመጠ የአፈጻጸም መመሪያ የለም ፡፡

ያለመግባባት ምንጮች ሕግና ደንብ መከበር አለበት የሚሉት የአዲስ አበባ ት/ቢሮ የትምህርት አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ሂደት ኢንስፔክሽን አስተባባሪ አቶ ማስረሻ ዘሪሁን የአዲስ አበባ ት/ቢሮ፣ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ፣ የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ባለሙያዎች ተውጣጥተው ያዘጋጁት ረቂቅ መመሪያ መኖሩንና መመሪያው የአገልግሎት አፈጻጸም ስርዓት መመሪያ በሚል የተዘጋጀ ሲሆን በወላጆች እና በግል ት/ቤቶች መካከል የተለያዩ ልዩነቶች ከስር ከመሰረታቸው ሊቀርፍ እንደሚችል ነው የገለፁት ፡፡ ይሁንና በረቂቅነት የተዘጋጀው ይህ መመሪያ በግል ት/ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ አንቀጽ 6 የተገለጸው የማስፈጸሚያ መመሪያ ይሁን አይሁን የሚታወቅ ነገር የለም ፡፡ መመሪያውን የማውጣት ስልጣን የት/ሚር መሆኑንም በዚሁ ደንብ ላይ ተገልፆአል ፡፡

የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን የምርመራና ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮሴፍ ጌታቸው ባለስልጣኑ የሚስተናገዱ ተዋናዮች ነጋዴውና ሸማቹ መሆናቸውን ገልጸው የሸመታ ጉዳይ ከንግድ ህጉ ጋር ያለውን ዝምድና እና ልዩነት ሲገልጹ የሸማቾች ህግ ከንግድ ህጉ ጋር የሚለየበት መሰረታዊ ባህሪይ የወንጀል ጉዳይን በዋናነት የሚመለከት ሲሆን ባለስልጣኑ የሚመለከተው የወንጀል ተግባር የተፈጸመበትን ሁኔታ መመርመርና ዳኝነት መስጠት ነው ይላሉ ፡፡ በሌላ በኩል ከንግድ ህጉ ላይ የሚነሱ አለመግባባቶች ከፍ/ብሄር ህግ ጋር በተያያዘ ጉዳያቸው እንደሚታይ ይገልጻሉ ፡፡ የትምህርት ጉዳይ በንግድ እና ሸማቾች አዋጅ ስር የሚስተናገድበት አግባብ አለ የሚሉት አቶ ዮሴፍ ትምህርት አንዱ የአገልግሎት ዘርፍ መሆኑንና በወላጆች እና በት/ቤቶች መካከል የሚካሄዱ ግንኙነቶች በንግድ አግባብ ስርዓትን ተከትሎ የሚሄድ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

Page 19: Temsalet Magazine 2 Pages

15 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ትምህርት እና ንግድበመንግስት ትምህርትን ለህብረተሰቡ በነጻ የመሰጠቱን ያህል ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ባለሃብቶች በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው እሰሩበት ይገኛሉ ፡፡ በትምህርት ለማትረፍ ጊዜ ይፈጃል የሚሉት ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ እርሳቸው በቦርድ የሚመሩት አንድ ኢንተርናሽናል ት/ቤት መስራች እና ባለቤት ናቸው ፡፡ እርሳቸው በተማሩበት በአሜሪካን ሀገር ትምህርት እጅግ ውድ ከሚባሉ አገልግሎቶች አንዱ መሆኑን ይገልጻሉ ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ ት/ቤቶች (ሁለተኛ ደረጃና ዩኒቨርሲቲ) ችግረኛ ለሆኑ ጎበዝ ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ስኮላርሺፕ ዕድል የሚሰጡ መሆናቸውን እርሳቸውም በዚህ ዕድል ተጠቅመው መማራቸውን ገልጸዋል ፡፡

በሀገራችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ጎበዝ ለሆኑ ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል ይሰጣሉ ; በተለይ የግል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፡፡ የዚህን ጥያቄ መልስ የሚሰጡት የአንድ የግል ት/ቤት ባለቤት ናቸው ፡፡ የእኔ ት/ቤት በዓመት ቢያንስ ለ 10-15 ችግረኛ ለሆኑና በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ውጤት ለሚያመጡ ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡ ነገር ግን ችግሩ እንደ ንግድ ተቋም በየዓመቱ የገቢዎች ባለስልጣን ኦዲት ሲያደርግ እንደነዚህ አይነት አገልግሎቶችን የሚያስተናግድበት አግባብ ዝግ መሆኑ ትልቁ ችግር ነው ይላሉ ፡፡ የነጻ ትምህርት አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ት/ቤታቸው ለተማሪዎች ወንበርና ጠረጴዛ ከገበያው ላይ በውድ ዋጋ ከመግዛት ይልቅ የግብዓት ዕቃዎችን በመግዛት ትምህርት ቤቱ ውስጥ በመሰራቱ ከወጪ በማዳኑ ት/ቤቱ የተጠቀመ ሲሆን ነገር ግን በገቢዎች ባለስልጣን ኢዲተር እነዚህ ወጪዎች የማይሰተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ትምህርት እንደ ንግድ፤ የንግድ ፈቃድ ወጥቶለት ምግብ ነክ ከሆኑና ምግብ ነክ ካልሆኑ ጎራዎች የተመደበ ቢሆንም የውስጥ አሰራሩና አመራሩ ከሌሎች የንግድ ዘርፎች ይለያል ፡፡ በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚወጡት አዋጆችና እና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎች የትምህርት ተቋሙን ማዕከል ያደረጉ ቢሆኑ፤ በተለይም የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት የሚያፈሩት ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑና ለአንድ ሃገር መሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ ሁሉም የትምህርት ቤተሰቦች የተሳተፉበት ህግ ቢወጣ በትምህርት ቤቶች ላይ የሚነሱ አለመግባባቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳሉ የሚል እምነት ይኖረናል ፡፡ የዕውቀት ሽግግሩም መልካም ይሆናል፡፡

ምክንያትና ውጤቱ

በ ከድር አህመድ

Page 20: Temsalet Magazine 2 Pages

16 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ክብደቱ በአማካይ አንድ ኪሎ ተኩል የሚሆን፣ የስፖንጅነት ጸባይ ያለው፣ መጠኑ በእጃቻችን መዳፍ ዉስጥ ልንይዘው የምንችለው፣በአጠቃላይ አእምሮኣችን አስተሳሰባችንን፣ ተስፋችንን፣ ህልማችንን እና ራዕያችንን ቅርጽ የሚያሲዝልን

ነው፡፡ በአጭሩ እኛን ሰው ያደረገ ለእኛ ብቻ ተፈጥሮ የሸለመን አንጎል ነው።የሰው ልጅ ያሰበውንና የፈለገውን መሆን የሚችለው የቢሊዬን ኒውሮኖች (የአንጎል ሴሎች) ክምችትና የነፍስ ጠንካራው ክፍል የሆነው አንጎል በትክክል ሲሰራ ነው። ደስታ፤ፍቅር፤መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት፤ ትዳር፣ እምነት፤ በስራም ሆነ በሌላውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን የአንጎላችን በትክክል መስራት ወሳኝነት አጠያያቂ አይደለም።

አአምሯችን የማናውቀው ፕላኔት ነው፡- ብዙ አስደናቂ ተግባራትን የሚከውነው ፋብሪካ ነው አይምሮ :: ይህንን ፋብሪካ አሰራሩን በቅጡ ሳናውቀው ከኖርን እንቸገራለን:: አእምሯችን እንዴት እንደሚሰራ ስንረዳ በአስቸጋሪ ወቅት እንዴት መግራት እንደምንችል ማወቅ እንጀምራለን::

እኔ ማነኝ? ሰብአዊ ፍጡር ማለት ምን ማለት ነው? ስናፈቅርም ሆነ ስንጠላ በአንጎላችን ውስጥ ምን አይነት ነገር ይፈጠራል? ሰዎች በቁማር፤

በአልኮልም ሆነ በኮኬይን ሱስ ሲያዙ በየትኛው የአንጎል ክፍላቸው ላይ ነው ችግር ያለው? የወንጀለኛ ሰዎች አንጎል ችግሩ ምንድነው? ወዘተ የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ዛሬ በቀላሉ አንጎል ውስጥ ጎራ ብሎ በቴክኖሎጂ እርዳታ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

በዓለም ዙሪያ የሚደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከአራት ሰዎች ውስጥ አንዱ በህይወት ዘመኑ የአእምሮ ህመም ሊያጋጥመው ይችላል። በጣም የሚያሳዝነው ግን እነሱ ፍቅርን በሚፈልጉበት ግዜ እኛ ፍቅር እንነሳቸዋል፡፡ የእኛን እርዳታ በሚፈልጉበት ግዜ መጥፎ መንፈስ አለባቸው ብለን እናርቃቸዋለን፡፡ እንደ ጥፋተኛም እንቆጥራቸዋለን፡፡ ከነርሱ ህመም ይልቅ የኛ ቤተሰብ መሆናቸው ያሸማቅቀናል፡፡ በዚህም የተነሳ እናገላቸዋለን ፡፡ይህንን ነው መቀየር ያለብን ።

የአእምሮ መታወክ ችግር በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገሮች ውስጥ ከምጣኔ ሀብት ቀውስና ሌሎች ማኅበራዊ ስንክሳሮች ጋር ተዳምሮ ስፋቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስደንጋጭ በሚባል ደረጃ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል:: ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ የአገራችን ጎዳናዎች ከፍተኛ ደረጃ በሚባለው የአእምሮ መታወክ በሚሰቃዩ ዜጎች ሊሞሉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው:: አሁን በአብዛኛዎቹ የክልል

የሰው ልጅ አንጎል

ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ

በ ወንድሙ ነጋሽ (ከለንደን)

Page 21: Temsalet Magazine 2 Pages

17 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ከተሞች የምናያቸው ምልክቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው::

የአእምሮ ህመም ሁልጊዜ ራቁትን ከመሄድ፣ በመንገድ ከመለፈለፍ እና ጮክ ብሎ ከመበጥበጥ ጋር የተያያዘ ነው ።ይህ ብቻ አይደለም፤ ህመሙ ከመንፈሳዊና እርኩስ በሽታዎች ጋር በብዛት ይያያዛል፤ የሰይጣን በሽታ ነውም ተብሎ ይታመናል። የአእምሮ ህመምተኞችን እንደተተናኳይ እና መቼም ለውጥ የማያመጡ አይነት ተደርገን እንስላለን ፡፡ በዚህም ምክንያት የችግሩ ተጠቂዎች በህብረተሰቡ መገለል እና መድሎ ይደርስባቸዋል።

በሀገሪቱ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የአእምሮ ህመም ያለባቸው፣ እፆችንና አልኮል ተጠቃሚዎች፣ ህፃናት እና ወጣቶች እንዲሁም በስደት ህይወት የሚኖሩ ሰዎች እና በእድሜ የገፉ አረጋውያን ለአእምሮ ጤና ችግር ከፍተኛ ተጋላጭነት ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሰዎች እና የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች ለአእምሮ ጤና ችግር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ በአእምሮ ጤና ችግር ከተጠቁ አስር ሰዎች መካከል ተገቢውን ህክምና የሚያገኘው ቢበዛ አንድ ሰው ብቻ ነው። ከሀገሪቱ ህዝብ አንድ በመቶ የሚሆነው የሚጥል በሽታ ተጠቂ ቢሆንም ተገቢውን ህክምና የሚያገኙት ግን ከአምስት በመቶ በታች የሚሆኑት ናቸው፡፡

በከፍተኛ የአእምሮ ህመም (Schizophrenia) በከፍተኛ የአዕምሮ ህመም የሚጠቁ ሰዎች በቂ ህክምና አያግኙም በተለያየ ግዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቤት አልባ የሆኑከ 30 እስከ 50 % የሚሆኑት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በከባድ የአእምሮ ህመም ይጠቃሉ። በአብዛኛው ወደ አረብ ሃገራት የሚጎርፉት ወጣት ኢትዮያዊያን ሴቶች አእምሯቸው በከፍተኛ ሁኔታ ታውኮ ይመለሳሉ፡፡

ማኅበረሰባችን የአእምሮ መታወክ ለደረሰባቸው ሰዎች የሚያሳየው አመለካከት ችግሩን ያባብሰዋል:: በየዋህነት በሁሉም አካባቢና ሁኔታ በአእምሮ መጠነኛ መረበሽ የሚታይባቸውን ሰዎች ‹‹እብድ›› እያሉ ለመጥራት ጊዜ አይወስድብንም:: “እከሌ እኮ አበደ…”፣ “የነእንትና ቤት ልጅ ጨርቁን ጣለ…”፣“የእንትና ወንድም ቀወሰ” በሚል ሁኔታውን እንገልጸዋለን:: ‹‹አበደ››፣ ‹‹ቀወሰ›› እና ‹‹ጨርቁንጣለ›› መልካም ስሜትን የሚፈጥሩ ገለጻዎች አይደሉም:: በተለይም መጠነኛ የአእምሮ መታወክ የደረሰበት ሰው ድንገት በነዚህ ቃላት ሲወከል ህመሙ ይቀልለታል ተብሎ አይጠበቅም::

በሌላ መልኩ ማኅበረሰባችን በአመዛኙ የአእምሮ መረበሽ የደረሰባቸውን ግለሰቦች ለማከም የሚሞክረው ከንፈር በመምጠጥ ነው:: ይህ ሁኔታ ‹‹የከንፈርቫይረስ›› ነው:: በዚህ “ቫይረስ” የተጎዱ፣ የቆሰሉ፣ የሞቱትን ቤት ይቁጠራቸው :: በቅን አመለካከት የምንመጠው ከንፈር ለሌሎች “ክፉ ቫይረስ” ሆኖ ሞታቸውን እንደሚያፋጥን የምንረዳውስ ስንቶቻችን እንሆን?

የአእምሮ መታወክም ሆነ በሌላ ህመም የሚሰቃይ ሰው ሌሎች እንደ አንዳች ጉድ የሚመለከቱት እንደሆነ ተስፋ በሚያስቆርጥ ስሜት ይበልጡኑ ይታመማል:: ሰው ተስፋን ማየት ሲያቆም ደግሞ ወደ ሞት አፋፍ መንሸራተት ይጀምራል፡፡

በተለያየ ደረጃ የሚገኝ የአእምሮ ህመም ከ 20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን አጥቅቷል። በዛሬው ቀን 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአእምሮ ህሙማን ወገኖቻችን ዕርዳታ ይፈልጋሉ።

በተከታታይ በተምሳሌት መጽሔት ይጠብቁ

የሰው ልጅ አንጎል

ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ

በ ወንድሙ ነጋሽ (ከለንደን)

Page 22: Temsalet Magazine 2 Pages

18 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ልጆች ያደጉበትን ነው የሚኖሩት

» ልጆች በትችት ካደጉ ተከላካይ ይሆናሉ

» በጥላቻ ካደጉ ተደባዳቢ ይሆናሉ

» በፍርሃት ካደጉ ተጠራጣሪ ይሆናሉ

» በባዶነት ካደጉ በራሳቸው የሚያዝኑ ይሆናሉ

» በማንኳሰስ ካደጉ አይናፋር ይሆናሉ

» በምቀኝነት ካደጉ ስግብግብ ይሆናሉ

» በማሸማቀቅ ካደጉ የወንጀለኛነት ስሜት ያድርባቸዋል፡፡

ነገር ግን

» ልጆች በመቻቻል ካደጉ ፅናት ይማራሉ

» በማበረታታት ካደጉ በራሳቸው መተማመንን ያዳብራሉ

» በማመስገን ካደጉ ማድነቅን ይማራሉ

» በእውነት ካደጉ ሌላውን ይወዳሉ

» በመቀበል ካደጉ በመቀበል እና በመዋደድ ያምናሉ

» በማካፈል ካደጉ ቸር ይሆናሉ

» በፍትህና ሁሉንም በእኩል ዓይን በማይት ካደጉ እውነተኛ እና በፍትህ የሚያምኑ ይሆናሉ

» ዋስትና ባለው ህይወት ካደጉ በአካባቢያቸው ላይ እምነት ይኖራቸዋል

» በጓደኝነት መንፈስ ካደጉ ዓለም ሰላም የሰፈነባት ለመኖሪያ ምቹ መሆኗን ይረዳሉ፡፡

ልጆችዎን እንዴት እያሳደጉ ነው?

» ቃል የአንድ ጀንበር ሳይሆን ያልተከፈለ የዝንተ አለም እዳ ነው፡፡

ጄ ኬ ቼስትሪ

» ከቀኖች ሁሉ በከንቱ የሚባክነው ሳንስቅ የምናሳልፈው ነው፡፡

ኒኮላስ ፓምሮድት

» ንፋስና ወደ ላጤ አንድ ናቸው፡፡ሁለቱም መጨረሻቸው አይታወቅም፡፡

ከወገግታ መፅሀፍ

የሀገራትአባባሎች

» ጨዋ አፍ የተዘጉ በሮችን ይከፍታል፡፡ /ደቡብአፍሪቃውያን/

» እንደሞት ሚዛናዊ ዳኛ የለም፡፡ /ደቡብ አፍሪቃውያን/

» ራሷን ከፍ ከፍ የምታደርግ ማሽላ አንድም ለሰው አንድም ለወፍ፤

/ኢትዮጵያውያን/

» የላሳደከው ውሻ ብትጠራው አይመጣም፡፡ /ኮንጓውያን/

» በድን አልበሰብስም አይልም፡፡ /ደቡብአፍሪካውያን/

» ድርጊት ከቃላት ይጮሀል፡፡ /እንግሊዛውያን/

» የዝሆን ኩምቢ የውሻ አፍ ላይ አይበቅልም፡፡ /ጃፓናውያን/

» ዶሮዋን ከያዝክ ጫጩቶቿን መሰብሰብ ትችላለህ፡፡ /ጋናውያን/

በኢትዮጵያ የደቡብ ክልል ህዝቦች አባባሎች

» መብላት እንደምታውቅ ሁሉ መስራትም እወቅ፡፡ /ጌድኦ/

» የአዋቂ ውሸታምና የሀብታም አስቀያሚ የለውም፡፡ /ሐድያ/

» ወገቡ እስኪጎብጥ የሰራ አንጀቱ እስኪርስ ይበላል፡፡ /ወላይታ/

» ተው ቢሉት እምቢ ያለ መካሪ ያጣል፡፡ /ጋሞ/

» ቀጠሮ የሌለው እረኛ መስቀልን ይናፍቃል፡፡ /የም/

‹‹ ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም

ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም ››

አብዬ መንግስቱ ለማ

ሒስና ሐያሲ

» ወጣት ሐያሲ ጠመንጃ እንደያዘ ልጅ ነው፡፡ህይወት ኖሮት የሚንቀሳቀስ ነገር

ከተመለከተ ይተኩሳል፡፡

» ሐያሲ ሩጫ የሚያስተምር እግር የሌለው ሰው ነው፡፡

» ሒስን ለማስወገድ ከፈለክ ምንም አታድርግ፣ምንምአትበል፣ምንምአትሁን፡፡

Page 23: Temsalet Magazine 2 Pages

19 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

እጓለ ገብረዮሃንስን ለማታውቁ ጥቂት ስለሰውዬው ዶ/ር እጓለ ገ/ዮሃንስ በ1950ዎቹ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ወደ አውሮፓ ተልከው በአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው ከተመለሱ ምሁራን አንዱ ናቸው፡፡ እኚህ ሰው በ1924 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ አከባቢ ተወልደው ያደጉ አዲስ አበቤ ናቸው፡፡ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ከተማሩ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ተልከው በዚያ ሥነ-መለኮት (theology)እና ፍልስፍና ተምረዋል ፡፡ይህንኑ የፍልስፍና ትምህርታቸውን ወደ ጀርመን እና እንግሊዝ አገር ጭምር ዘልቀው ተምረው ሲያበቁ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ፒኤችዲ ድግሪ ነበራቸው፡፡

የአውሮፓን ፍልስፍና ዘልቀው መማራቸው ግን ከፒኤችዲ ዲግሪና ዲግሪው ከሚሰጠው ክብርና ጥቅም ይልቅ ያስተሳሰብ አድማሳቸውን እንደቃኘላቸውና እንዳሰፋላቸው ከዚያ ከተመለሱ በኋላ የከፍተኛ ትምህርት በኢትዮጵያ ምን ዓላማን ይዞ መቀረጽ እንዳለበት የመጨረሻ ግቡስ ምን ሊሆን እንደሚገባ እየጻፉ በሬዲዮ በንባብ ያስተላልፉዋቸው የነበሩ የሬዲዮ ዲስኩሮቻቸው ይመሰክራሉ፡፡

ጥቂት ቆይተው እነዚህን የሬዲዮ ዲስኩሮች በሥርዓት አደራጅተው ሲያበቁ “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” በሚል ርዕስ በ1956ዓም አሳተሟቸው፡፡ ዛሬ በዚህ መድረክ ላስተዋውቃችሁ የምሞክረው በዚያን ዘመን ተጽፈው ከታተሙ መጻህፍት በይዘትና በቅርጹ ለብቻው ተነጥሎ የሚታየውን የዚህን መጽሃፍ የወፍ በረር ዳሰሳ ነው፡፡

እጓለ ገብረዮሃንስ በነዚህ የሬዲዮ ዲስኩሮቻቸው ትምህርት በተለይም ከፍተኛ ትምህርት ለምዕራቡ ዓለም ሥልጣኔ እንደምን ያለ ፋይዳ እንደነበረው በሰፊው ይተነትናሉ፡፡

ከጥንታዊት ግሪክ ፍልስፍና አንስተው በዚያን ዘመንና ከዚያን ቀደም የአውሮፓን የአስተሳሰብ አቅጣጫ በመቃኘት ከፍ ያለ ጉልበት የነበረውን የጀርመን ፍልስፍና ጭምር አንብበው ከዚሁ አውሮፓዊ የጥበብ ወይን ጠጅ ተጎንጭተው የተመለሱት እኚህ ኢትዮጵያዊ ምሁር ወደ አገራቸው ሲመለሱ የጠበቃቸውና ወትሮም የሚያውቁት ንጉሳዊ ሥርዓት ከአውሮፓ ይዘውት የተመለሱትን እውቀት ለፍሬ ለማብቃት እድል የሚሰጥ አልነበረም፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ በእጓለ ገብረዮሃንስ

በ ሚካኤል ሽፈራው

Page 24: Temsalet Magazine 2 Pages

20 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ይሁንና በቀጥታ ሥርዓቱንና ሥርዓቱን ተከትሎ በሥራ ላይ የነበረውን የትምህርት ዓላማና ቅኝት በቀጥታ ከመቃወም ይልቅ ምዕራባዊውን ዓለም ወዳለበት የሥልጣኔ ማማ ከፍ ያደረገውን የትምህርተ ዘይቤ ማንም ተራ ሰው ሊገባው በሚችል ቋንቋ አጉልቶ በማሳየት ያገራችን የትምህርት ዘይቤ የነበረውን ጉድለት ባግድመት ለማሳየት ሞክረዋል፡፡

ዘመኑ ባንድ በኩል በግራ ዘመም ፍልስፍና በተቃኙ በሌላ በኩል ባጠቃላይ ንጉሣዊ ሥርዓቱን ከሥረ መሰረቱ ሳይነኩ የትምህርትን ዘይቤ ብቻውን ለማደስም ሆነ ለመለወጥ መሞከር የችግሩን ምክንያት ማድበስበስ ነው የሚል አስተሳሰብ ጥንስስ ውስጥ ውስጡን ይፈላ የነበረበት ዘመን ነበርና ተቺዎቻቸው የሰውዬው ጽሁፎች አሮጌውን ሥርዓት ከስሩ የሚነቀንቁ ባለመሆናቸው ሥር ነቀልነት ይጎድላቸዋል የሚል ትችት ይሰነዝሩባቸው ነበር፡፡

እንዲህ ያለ ወቀሳ ይሰነዘርባቸው እንደነበረ የምንሰማው ከሳቸው ከራሳቸው ነው፡፡ ይሁንና እኚህ ሰው በነበሩበት ዘመን ሃሳብን በነጻነት በማንሸራሸር ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ ደህና አድርገው የሚያውቁ ነበሩና እንዲህ ላለው ትችት ጥበብ የተሞላው በሁለት ወገን የተሳለ ምላሽ ነበራቸው፡፡

በዚህም የተነሳ ተቺዎቻቸው ሥርዓቱን ከመሰረቱ ከመተቸት ወደኋላ እንዳላሉ እንዲረዱላቸው የሥርዓቱም ባለቤቶች እንደ አመጸኛ ቆጥረው እንዳይተናኮሏቸው ወደ ፈንጂ ወረዳ ሳይገቡ ሃሳባቸውን በጥበብ ለማስተላለፍ ይሞክራሉ፡፡ ይህን አካሄድ የመረጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ ያንድ አገር ያስተሳስብ አድማስ የሚሰፋው በሁለት መንገድ ነው ይላሉ፡፡አንዳንድ ሰው አሮጌውን ቤት እርጅናውን አጉልቶ በማሳየት ከመሰረቱ ለማፍረስ ይተጋል ፤ሁለተኛው ደግሞ አሮጌውን ከማፍረስ ይልቅ የማፍረሱን ተግባር ለሌላው ትቶ በገዛ ሃሳቡ መሰረት ከአሮጌው አጠገብ አዲስ ቤት ለመገንባት ይሰለፋል ፡፡ የተሻለው ዘዴ ከአሮጌው አጠገብ አዲስ ቤት ሰርቶ በማሳየት አሮጌው ያረጀና የደከመ አዲሱም የተሻለ መሆኑን ማሳየት ነው ይላሉ፡፡አዲሱ ቤት ስለራሱም አዲስነት ሆነ ስለ አሮጌው ቤት እርጅና ምስክር ነው ብዬ ስለማምን ይህንን መንገድ ተከትያለሁ ሲሉ በኢትዮጵያዊ ብልህነት ከሥርዓቱ የማያጋጫቸውን ምላሽ ለተቺዎቻቸው ሲሰጡ እንሰማቸዋለን፡፡ በእርግጥም ሰውዬው ብልህ ነበሩ፡፡ወቃሾቻቸው ሊረዱት አልወደዱም እንደሁ እንጂ ሰውዬው በዚያን ዘመን በቀጥታ

ከሥርዓቱ ጋር መጋጨት ውጤት የሌለው ዋጋን የሚያስከፍል መሆኑን ባግድመት ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ፋይዳው ምንድነውበእኔ መረዳት ምናልባትም በሁላችንም መረዳት ሳይንስ መሳሪያ /tool/ ነው፡፡ማለትም ሳይንስ እንደ ማረሻ፣ ሞፎር ቀንበርና ድግር ሊቆጠር የሚችል በመሬት ላይ ያለውን እውነት የምንቀይርበት መሳሪያ ነው፡፡ እጓለ ገብረ ዮሃንስም የትምህርትን utilitarian የጥቅም ሰጪነት ግብ አስመልክተው ከጥንታዊት ግሪክ ፍልስፍና እየጠቀሱ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ይሁንና ያገራችን ከፍተኛ ትምህርት ለፋይዳ በመዋል ረገድ በዚያን ዘመንም ሆነ ከዚያን ዘመን በኋላ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እጅግ ብዙ ይቀረው ነበር፡፡

የትምህርት ዓላማው ምንድነው? ምን እናስተምራለን?ዶ/ር እጓለ ገ/ዮሃንስ ስለ ትምህርት ያላቸውን አስተያየት በመጽሐፋቸው መግቢያ ላይ ሲገልፁ ስለ ትምህርት ያለን አስተያየት ትክክለኛ ከሆነ ማንኛውንም የህይወት ችግር ሊፈታ ይችላል ፡፡ እጓለ ገብረዮሃንስ በዚህ ጽሁፍ ሊያስረዱዋቸው ካሰቧቸው በርካታና ጥልቅ ሃሳቦች አንኳር ሊባሉ የሚችሉትን ሁለት ፍሬ ነገሮች ብቻ ማንሳት ለዚህ አጭር ዳሰሳ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በዚህች አጭር ጽሁፍ መነሻ መጽሐፉን የማንበብ ፍላጎት የተቀሰቀሰበት አንባቢ ቀሪውን ራሱ ከመጽሃፉ ያገኘዋል፡፡

እውቀትና ሠናይትበእጓለ ገብረ ዮሃንስ አስተሳሰብ የከፍተኛ ትምህርት ሁለት ዋና ዋና ግቦች እውቀትና ሠናይት ወይም knowledge and virtue ናቸው፡፡ ይህም ማለት ትምህርት የተማሪውን አእምሮ በእውቀት ስታበለጽግ በሌላ በኩል ደግሞ ከሰውነት ማዕረግ በሚያደርሱት የስብዕና እሴቶች ወይም values ታንጾና ተቀርጾ ትልቅ ሰው ሆኖ እንዲወጣ ታደርጋለች ፡፡ ወይም ደግሞ መልካም ባህሪይ ያለው፣ትሁት ሚዛናዊ ፍርድን የሚያውቅና ስለአገሩና ስለሌሎች ግድ የሚለው ሙሉ ሰው አድርጋ ትቀርጸዋለች እንደማለት ነው፡፡

በእጓለ ገብረ ዮሃንስ አባባል ሰው ከሙሉ የሰውነት ደረጃ የሚደርሰው በትምህርት ነው፡፡ ይህን ሃሳባቸውን ለማብራራት ታላቁን የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ፕላቶን ጠቅሰው እንዲህ ይላሉ

“የሰው ልጅ ትክክለኛ ትምህርት ያገኘ እንደሆነ ለስላሳና (ኖብል) እግዚአብሄርን የሚመስል ድንቅና ውብ ፍጥረት ነው ፡፡ በትምህርት ባልተገራ ጊዜ ግን በምድር ላይ ካሉት አራዊት ሁሉ ዝቅ የሚያደርጉትን ባህሪያት በውስጡ ተሸክሞ የሚኖር እጅግ የሚያስፈራ ፍጡርም ጭምር ነው፡፡” ስለዚህ በከፍተኛ ትምህርት የሚያልፈው ምሁር በዚህ ባለ ሁለት አምድ የትምህርት ዓላማ መቀረጽ ይገባዋል፡፡

በእርግጥም የትምህርት ዓላማ እርሳቸው እንደሚሉት እውቀትና ሠናይት መሆናቸው እውነት ቢሆንም ከፍተኛ ትምህርት በግልና በሃገር ደረጃ ትርጉምና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ ትምህርትን ከማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሂደቱ ውጪ ብቻውን መተቸትም ይሁን መቃኘት የማይቻል መሆኑን በወቅቱ ተቺዎቻቸው የሰነዘሩት ወቀሳ ባዶ አልነበረም ፡፡ ምክንያቱም ትምህርት አንድን አገር በኢኮኖሚያዊም ሆነ በማህበራዊ ህይወቷ ካንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት መሳሪያ ወይም tool ነውና ነው፡፡ ይህን ሳይንሳዊ መሳሪያ በሥራ ላይ ለማዋል ደግሞ ሥርዓቱ ይህን የሚፈቅድ ይሆን ዘንድ አፍርሶ እንደገና ማዋቀርን መጠየቁ የግድ ነበር፡፡

ምዕራባዊው ዓለም በኢኮኖሚ ከፍ ወዳለ አምባ ለመዝለቅ ሳይንስና ቴክኖሎጂን እንደመሳሪያ መጠቀም ነበረበት፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሊዳብሩ የቻሉት በየጊዜው በዩኒቨርሲቲዎቻቸው በሚደረጉ ፈጠራዎችና የምርምር ውጤቶች ነበር ፡፡ እነዚህ የምርምር ውጤቶች በዩኒቨርሲቲዎቻቸው በስፋት ሊያብቡ የቻሉት ደግሞ በገበያ ውድድር ይመራ የነበረው የካፒታሊዝም ሥርዓት እነዚህን ምርምሮች ለፍሬ ማብቃት የሚያስችል መሠረት ስለነበረው ነው፡፡ በአውሮፓ በዩኒቨርሲቲዎቻቸው የሚደረጉትን ምርምሮች በገንዘብ ከመደገፍ አንስቶ ተቀብሎ ለፍሬ በማብቃት ኢንዲስትሪያሊስቶቹ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው፡፡ በሳይንሳዊ ምርምር በስሎ የሚወጣው ምሁርም ከትምህርቱ መጨረሻ ማረፊያው በስፋት የተዘረጋው የእውቀትና የምርምር ገበያ ነበር፡፡

እጓለ ገብረ ዮሃንስ ይህን ጽሁፍ በጻፉበት ዘመን ግን የከፍተኛ ትምህርትም ሆነ ከዚያ በመለስ ያለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በቢሮክራሲ ውስጥ የሚያስፈልገውን የተማረ ሃይል በማሰልጠን ቢሮክራሲውን በዘመናዊ መልክ ከማደራጀት ያለፈ ግብ የነበረው አልነበረም፡፡ ሳይንስ በአውሮፓ ሃገራትን ወደ ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብሎም ወደ

Page 25: Temsalet Magazine 2 Pages

21 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ የበላይነት ሲያሸጋግር በየሃገራቱ በመካከለኛው ዘመን የነበረውን ፊውዳላዊ ሥርዓት ከስሩ የሚያናጋ የሥርዓት ለውጥን ፈልጎ ነበር፡፡ የእጓለ ገብረ ዮሃንስ ተቺዎች ወይም የወቅቱ አብዮታዊያን ትችት ሥረ ነገር በዚህ ላይ ያጠነጠነ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

አውሮፓዊ ሥልጣኔ እጓለ ገብረ ዮሃንስ አውሮፓዊውን ሥልጣኔ ፋውስታዊ ሥልጣኔ ነው ይሉታል፡፡ ፋውስት በጀርመናዊው ባለቅኔ በዎልፍጋንግ ቮን ጎይተ በተጻፈ ተውኔት ላይ የእውነትን ምንነት ለመመርመር ሲል ከዲያቢሎስ ጋር ኮንትራት የሚገባ የጀርመናዊ ሊቅ ገጸ ባህሪይ ነው፡፡ እጓለ ገብረ ዮሃንስ ይህን ገጻ ባህሪይ ለአውሮፓዊ ጥበብ እንደ ተምሳሌት ሲወስዱ ለማለት የፈለጉት አውሮፓዊው አለም ስለጥበብ ሲል ቀድሞ ከነበረው መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ ራሱን ማላቀቅ ነበረበት በዚህም አስቀድሞ ለእግዚአብሄር አሳልፎ የሰጠውን የሁሉን አወቅነትና የሁሉን ተጠየቅነት ሥልጣን መልሶ ከአምላኩ ተረክቦ የገዛ ዕጣ ፈንታው ባለቤት ለመሆን የወጣ ሥልጣኔ ነበር ማለታቸው ነው፡፡

በሌላ በኩል እጓለ ገብረዮሃንስ አውሮፓዊውን የሥልጣኔ መንገድ በጥንታዊት ግሪክ ሚቶሎጂ ከአማልክቱ እሳትን ሰርቆ ለሰው ልጆች በሰጠው በዚህም ዘለዓለማዊ ሥቃይን እንዲሰቀይ በተፈረደበት ፕሮሚቲየስ በተባለው የሚቶሎጂ ገጸ ባህሪይ ይወክሉታል፡፡ ይህም አስተሳሰብ ያው ከላይ በጎይተ ፋውስት ተምሳሌትነት ከቀረበው የጥበብ ረሃብ በዚህም ረሃብ ከአማልክቱ ጋር ከተቆራረጠው የሰው ልጅ ሥልጣኔ ጋር የሚነጻጸር ነው፡፡ ፕሮሜቲየስም ሆኑ ፋውስት ክፉና ደጉን ከምታሳውቀው በርሷም ሞትን ደብቃ ከያዘችው ዛፍ እንደበላው እንደ አባታችን እንደ አዳም የሚቆጠሩ የአምላክነትን ክብር ለመቀናቀን ሲል ከክብሩ የወደቀውን የሰው ልጅ የሚወክሉ አውሮፓውያን ገጸባህሪያት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊ ሥልጣኔ አውሮፓዊውን ሥልጣኔ በዚህ መልክ ከገለጹት በኋላ ማንነታችንን ይወክላል ያሉትን ኢትዮጵያዊውን ሥልጣኔ በኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ይወክሉታል፡፡ እንደ እጓለ ገብረ ዮሃንስ ትንተና ኢትዮጵያዊው ሥልጣኔ የመጨረሻ ግቡ የፈጠረውን አምላክ ማወቅና ከፈጠረው አምላክ ፊት በሞገስ ቆሞ የክብሩ ተካፋይ መሆን ነው፡፡ በዚህ ትንተናቸው ኢትዮጵያዊ ትምህርት ከፊደል ገበታ አንስቶ እስከ

መጻሕፍት አንድምታና ሃተታ ቅኔ መወድሱና ዜማው ሁሉ የመጨረሻ ግባቸው ተማሪውን በመንፈስና በጥበብ ከፍ አድርገው የአምላኩ ክብር ተካፋይ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ዓለማዊ የሆነው አውሮፓዊ ሳይንስ ካፈራቸው ፍሬዎች ሳንቋደስ ባለማወቅ ጨለማ የኖርንበት ዘመን አብቅቶ አውሮፓዊውን ሳይንስ ዘልቀን አውቀን ከፍሬው መካፈል ይኖርብናል የሚል እንደምታ ያለው ትንተና ያቀርባሉ፡፡

የአውሮፓዊና የኢትዮጵያዊ ሥልጣኔ ውህደት እዚህ ላይ ነው እጓለ ገብረ ዮሃንስ በተዋህዶ ከበረ የሚለውን ሁለተኛ ሃሳብ የሚያነሱት፡፡ ይህንኑ ሃሳባቸውን ሲያብራሩም የትምህርት ዓላማው ባንድ በኩል እውቀትና ሰናይት ናቸው ስንል በከፍተኛ ትምህርት በአውሮፓዊው ሳይንሳዊ እውቀት ታንጾ የሚወጣው ምሁር በአገራዊው መንፈሳዊ ጥበብ ተቃኝቶ በእውቀት የበለጸገ በስብዕናውም ከፍ ያለና እግዚአብሄርን የሚመስል ሊሆን ይገባዋል የሚል ከፍተኛ ህልም ያልማሉ፡፡ ይህን ሃሳባቸውን ሲያብራሩ አውሮፓዊውን ሳይንስ ከኢትዮጵያዊው የነገረ መለኮት ጥበባችን ጋር በማዋሃድ ኢትዮጵያዊነቱን ያልሳተ የአውሮፓውያኑን ጥበብ የራሱ ያደረገ የትምህርት ዓላማና ግብ ሊኖረን ይገባናል ይላሉ፡፡

ጽሁፉ የተጻፈበት ዘመንእዚህ ላይ እጓለ ገብረ ዮሃንስ ይህን መጽሐፍ የጻፉበትን ዘመንና ምክንያት መልሶ ማስታወስ ይገባል፡፡ ሰውዬው አውሮፓዊ ፍልስፍናን አጥንተው ያስተሳሰብ አድማሳቸውን አስፍተው የተመለሱት የ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ተሞክሮ በከሸፈ ማግስት ነው፡፡ የመፈንቅለ መንግስቱ ተዋናዮች በወቅቱ የሥርዓቱ ዋነኞች ናቸው ያሏቸውን ሹማምንት በጅምላ የገደሉዋቸው በዚያን ዘመን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት በነበረው በዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ግቢ ነው፡፡ ንጉሱ ተቀናቃኞቻቸውን አስወግደው የስልጣን መንበራቸውን ካደላደሉ በኋላ ይህን የሹማምንቶቻቸው ደም የፈሰሰበትን ግቢ ለከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት ይውል ዘንድ በፈቃዳቸው አሳልፈው ሰጥተው እሳቸው ወደታችኛው ቤተ መንግስት መንበረ መንግስታቸውን ያዞሩበትም ዘመን ነበር፡፡

ይህ ዘመን ከዚያን ቀደም ባመዛኙ በውጭ አገር እየተላኩ ይማሩ የነበሩትን የከፍተኛ ትምህርት

ምሁራን ባገር ውስጥ ለማፍራት መሰረት የሚጣልበት ዘመን ነበር፡፡ በውጭ አገር ትምህርት ያገሪቱን ምሁራን ማሰልጠንና አንዲት አገር ከራሷ ተጨባጭ እውነታ ላይ ተነስታ የራሷን የወደፊት እድል የሚወስን የትምህርት ሥርዓት ተመስርቶ ያገር ውስጥ ምሁራንን ማፍራት መጀመር ከፍተኛ ልዩነት ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ባገር ውስጥ ምሁራንን የማፍራቱ ሥራ እንደዋዛ የሚቆጠር ጉዳይ አለመሆኑን የተረዱት እጓለ ገብረ ዮሃንስ ለዚህ ነበር ኢትዮጵያዊውን የከፍተኛ ትምህትር ዘይቤ ልብ ሊላቸው ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች ለማስረዳት ይደክሙ የነበሩት፡፡

የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓታችን ሌላው እኚህ ኢትዮጵያዊ ምሁር በዚህ መጽሃፋቸው ሊያነሱት የሞከሩት ፍሬ ሃሳብ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴን ወይም (Methedology)ን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ የሃሳባቸው ምዕራፍ የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓታችን በጥንታዊት ግሪክ ይታወቅ የነበረውን የፕላቶናዊ የተጠየቅ መንገድ (pelatonic dialogue)አካሄድ ሊከተል እንደሚገባው ሊያስረዱ ይሞክራሉ፡፡ ይህን ፕላቶናዊ ዲያሎግ የምንማረው በጥንታዊት ግሪክ ፍልስፍና ውስጥ ነው አካሄዱ መምህሩ ወይም የተጠየቁ መሪ ሁሉም ነገር ያውቃል ተማሪው ወይም የተጠየቁ ተከታይ ምንም አያውቅም ከሚል የተሳሳተ መነሻ አይነሳም፡፡ የሚታወቀውም ነገር አስቀድሞ የታወቀ ሳይሆን የተጠየቁ መሪና ተከታዩ በምልልሳቸው ውስጥ በምክንያታዊነት ላይ ተመስርተው የሚደርሱበት አዲስ እውነት ነው፡፡

እጓለ ገብረ ዮሃንስ በግሪክ ስነ መለኮትንና ፍልስፍናን ተምረው የመጡ እንደመሆናቸው መጠን ይህን የእውቀትና የእውነት ማፈላለጊያ የትምህርት ሥርዓት ደህና አድርገው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓታችን ይህን አካሄድ ተከትሎ መምህሩ ተማሪውን እየመራ በመረጃዎች የተሞላና የመረጃ ቋት ሳይሆን በገዛ ራሱ አስቦና ተመራምሮ ከእውነቱ መድረስ የሚችል ወይም ማሰብ የሚችል ምሁር መፍጠር መቻል እንዳለበት ለመጠቆም ይሞክራሉ፡፡

እኒህ ኢትዮጵያዊ ምሁር ከፍተኛ ትምህርትን አስመልክተው ያነሷቸው ሃሳቦች እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡ ይሁንና በዚህች ውሱን ጽሁፍ ሁሉን መዳሰስ ስለማይቻል ከላይ እንዳወሳሁት የማነሳው የመጽሐፉን ዋና ፍሬ ሃሳቦች ብቻ ነው፡፡ ከነዚህም ከላይ ከጠቀስኳቸው ፍሬ ሃሳቦች ተነስቼ ከዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ እጓለ ገብረ

Page 26: Temsalet Magazine 2 Pages

22 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ዮሃንስ በዚያን ዘመን ያነሷቸውን ሶስት ፍሬ ሃሳቦች ባገራችን የትምህርት ሥርዓት ላይ የነበራቸውን ፋይዳ ወይም ውጤቱን ባጭሩ ያየሁትን ያህል ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡

እውቀትና ሠናይት እምን ደረሱበዚህ ረገድ ባለፉት ሃምሳ ወይም ከዚያ በላይ ለሚሆኑ ዓመታት በተለይም ከደርግ ውድቀት በፊት በነበረው ዘመን ላይ አተኩረን በእርግጥም ያገራችን ከፍተኛ ትምህርት ባሃገርና በግለሰብ ደረጃ በምሁሩም ሆነ ባገር ህልውና ላይ ትርጉም ያለው እውቀትን ጨምሮ ነበር ወይ የሚለውን ጥያቄ ያነሳን እንደሆነ ከላይ ወዳነሳነው ጉዳይ ይመልሰናል፡፡ ትምህርት እውነተኛ ትርጉም ይኖረው ዘንድ አገርና አገሬውን በትምህርት ቃኝቶና ቀርጾ ለምን ግብ ለማድረስ እንደሚፈልግ የሚያውቅ ሥርዓትን የሚጠይቅ ነበርና እርሳቸው ለትምህርት ያስቀመጡትን የእውቀት ግብ ያገራችን ከፍተኛ ትምህርት ደርሶበታል ለማለት ያስቸግራል፡፡ እውነትም ትምህርት ለፍሬ ይበቃ ዘንድ የአንዲት አገርና ህዝብን እድል ፈንታ መወሰኛ መሳሪያ የሆነውን ሳይንስን ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የማህበረ ኢኮኖሚ ስርዓት አልነበረምና ሳይንስን እንደ መሳሪያ ተጠቅመን ልናፈራበት አልቻልንም፡፡ እንደምሳሌ ለማንሳት ከተፈጥሮ ሳይንስ እንደ ፊዚክስ ያሉ የሳይንስ ዘርፎች ባገራችን ከሃምሳ ዓመታት በላይ በትምህርት ቢሰጡም የፊዚክስ የሳይንስ ዘርፍ አውሮፓዊውን ዓለም በኢንዲስትሪ ልማት በስነ ጠፈር ምርምርና በሌላውም የፊዚካል ሳይንስ በሚዳስሳቸው የዓለማችን ምስጢራትና ከትሩፋቶቻቸው ተካፋይ ለመሆን የሚያስችለን ነባራዊና መንፈሳዊ ሁኔታ ያልነበረ በመሆኑ ሳይንሱን ራሱን በትክክል ልንጨብጠው አልቻልንም፡፡

ሁለተኛው የትምህርት ግብ አድርገው ያስቀመጡትን ሠናይት ወይንም virtue የተመለከትን እንደሆን ያገራችን ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ቅርብ ድረስ ያፈሯቸውን ምሁራን መንፈስና ስነልቡና ወደ መቃኘት ያስገባናል፡፡ በእርግጥም ይህ ተግባር ከፍ ያለ ጥናትን የሚጠይቅ ሊሆን እንደሚችል ብገምትም በዚህ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያለፈውን ልሂቅ ስንመለከት በተለይም በቀደመው ዘመን የነበረው ልሂቅ በስነልቡናው እርሳቸው ወዳለሙለት እግዚአብሄርን ወደሚመስል ባህሪው የተጠጋ ነበር ለማለት ያስቸግረናል፡፡ ለዚህ ምስክሩ ያለፍንባቸው ዘመናትና ዛሬም ድረስ በልሂቃኑ መካከል የምናየውና የምንሰማው በሁሉን አወቅነት ከፍታ ላይ ተቀምጦና ተዘግቶ ያለመደማመጥ ልክፍት ነው፡፡

ያም ሆኖ ይሄኛው ወይም እጓለ ገብረ ዮሃንስ ሠናይት ሲሉ ያስቀመጡት የትምህርት ግብ በተጨባጭ ሳይንሳዊ መንገድ ለክቶና ሰፍሮ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል ለማለት አስቸጋሪ ስለሆነ ቀሪውን ላንባቢ መተው እመርጣለሁ፡፡

በተዋህዶ ከበረ ሁለተኛው ፍሬ ሃሳብ ኢትዮጵያዊውን ወይም ያሬዳዊውን ስነ መለኮታዊ ጥበብ ከአውሮፓዊው ወይንም ፋውስታዊው ሳይንሳዊ ጥበብ ጋር አዋህዶ በመንፈስ ከፍ የሚያደርግ በእውቀትም ጥልቅና ሰፊ ወደሚያደርግ የትምህርት ሥርዓት መግባት ይኖርብናል የሚለው ሃሳባቸው ለፍሬ አልበቃም ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ይልቁንም ያሬዳዊው ጥበባችን በቤተ ክህነትና በካህናት ተወስኖ ሲቀር ሳይንሳዊ እውቀታችንም ለፍሬ በማይሆን መንገድ አውሮፓውያኑ አገራቸውን ሲገነቡ በምርምር የደረሱባቸውን ሳይንሳዊ መርሆች ድምዳሜዎችና ፎርሙላዎች በማነብነብና

በማስታወስ ላይ የተመሰረተ ነበር ማለት እንችላለን፡፡

ፕላቶኒክ ዲያሎግእጓለ ገብረ ዮሃንስ የትምህርት አሰጣጥ ዘይቤያችንን በሚመለከት ጠያቂ ተመራማሪና ራሱ አስቦ ነገርን መፍታት የሚችል ምሁርን የማፍራት ህልማቸውም እንዲሁ በህልምነት የቀረ ነበር ማለት እንችላለን፡፡ በቄስ ትምህርት ቤት ሳለን የኔታ የፊደል ገበታን በቃላችን ደጋግመን በማነብነብ እንድንይዝ ያደርጉን ነበር፡፡ ብዙዎቻችን በልጅነታችን በምናነበንበው የፊደል ገበታ ላይ የሐዋሪያው የዮሃንስ መልዕክት እንደነበረ ያወቅነው አድገን ለቁም ነገር ከበቃን በኋላ ነው፡፡ የመልዕክቱን መንፈሳዊ ይዘትና ለህይወታችን የሚሰጠንን ትርጉም የኔታም አልነገሩንም እኛም ግዳችን አልነበረም፡፡ በዚህ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ቁም ነገሩ ያ መልዕክት የተጻፈባቸውን ፊደላት ለይቶ ማወቅ ብቻ የነበረ ይመስላል፡፡

የቄስ ትምህርት ቤት አጠናቅቀን የምንመረቀው የዳዊትን መዝሙር በግዕዝ በቃላችን ማንበልበል ስንችል ነበር ፡፡በዚህ መጽሐፍ ንጉስ ዳዊት በሃዘኑና በትካዜው በጭንቀቱና በድሉ ጊዜያት ያዜማቸው መዝሙሮች መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ፍቺና ትርጉም ግን የኛም ሆነ የየኔታ ጉዳይ አልነበሩም፡፡ ዳዊት የሚያንበለብለው ልጅ ንባብን እንደልቡ ማንበብ መቻሉ ብቻ በቂ ነበር፡፡

መድረሳ በሚባሉቱ የእስልምና የቁርዓን ትምህርት ቤቶችም ቁርዓን የሚቀራው ተማሪ አረብኛ ቋንቋ ተምሮ በቁርዓኑ የሰፈረውን መልዕክት መረዳት አይጠበቅበትም፡፡

ይህ የትምህርት ዘዬ በሁለተኛ ደረጃም ሆነ በከፍተኛ ትምህርት ሳለን ይህንኑ ተከትሎ የሄደ ነበር ብለን ብንናገር እንደ ድፍረት አይቆጠርብንም ፡፡ በተለይም ደግሞ (Applied Scinece) ከሚባሉት እንደ ህክምና ግብርናና ምህንድስና ውጪ ባሉት የከፍተኛ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓቱም ሆነ ካሪኩለሙ ከየኔታ መልዕከተ ዮሃንስና የዳዊት ድግምት እጅግም የሚሻል ነበር ማለት አይቻልም፡፡

በነዚህ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ ለመመረቅ የዩኒቨርሲቲው የኔታ የሚያስደግሙትን ድግምት በጥንቃቄ አነብንቦና በአእምሮው ሰሌዳ አትሞ በተጠየቀ ጊዜ እንደ ዳዊት ደጋሚው ማንበልበል መቻል ያስፈልጋል፡፡ በኛ ዩኒቨርሲቲዎች መጠየቅ ለመመራመር መሞከር በተለይም ደግሞ በሊቃውንት ተደንግገው በመጻሕፍት የሰፈሩ ድንጋጌዎችን መጠራጠርም ሆነ መምህሩ የተናገረውን ለማብራራትም ሆነ ለመፈተን መሞከር በጽኑ የሚያስቀጣ ከፍተኛ መተላለፍ ነበር፡፡ ዛሬ ይህ ባህል ምን ያህል እንደተለወጠ ወይም እየተሻሻለ እንደሆነ ባላውቅም በቀላሉ ከስሩ ሊገለበጥና ሊለወጥ የሚችል አለመሆኑንና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን ግን እረዳለሁ፡፡

በዚህ ምክንያት እጓለ ገብረ ዮሃንስ በዚህም ረገድ ህልማቸው ተፈትቷል ማለት ባይቻልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የትምህርትን ትክክለኛ ፋይዳ ለመረዳት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለመግባት እየሞከርን ያለን ሆኖ ይሰማኛል፡፡ ያዲሱ ዘመን የትምህርት አቅጣጫ ውጤቶቹና ጉድለቶቹ ራሱን የቻለ ሰፊ ዳሰሰ የሚጠይቅ በመሆኑ ከዚህ ጽሁፍ አድማስ ውጪ በመሆኑ ገብቼበት ላልከሰክሰው ስለማልፈቅድ ሃሳቤን በዚሁ ልግታ፡፡

የእጓለ ገብረ ዮሃንስ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ ግን ጥልቅ የፍልስፍና ሃሳቦች የተነሱበት ምናልባትም ከዚያን ቀደም ተሞክሮ በማያውቅ መንገድ የትምህርት ፍልስፍና ውብ በሆነ ቋንቋና አቀራረብ የተተነተነበት መጽሃፍ መሆኑ ግን ዘመን የማይሽረው እውነት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡

Page 27: Temsalet Magazine 2 Pages

23 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

አገራችን በዓለም ላይ ከሚገኙ ዝቅተኛ የኢንተርኔት(የበይነ መረብ) ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበይነ መረብ ፍጥነትና ተደራሽነት ከምንግዜውም በተሻለ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ

እያለ የበይነ መረብ ክፍሎች የሆኑት ማህበራዊ ድረ-ገጽ /social media/ና የመወያያ መድረክ /chat forum/ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቀሜታ እጅግ ብዙ እና ዘርዝረን የማንጨርሰው ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳንዶች ዘንድ ለግል ወሬ እና ለመዝናኛ አገልግሎት ብቻ የዋለ መድረክ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተደረጉ ያሉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቀሜታቸው ሰፊ ነው፤ከዚህም ባሻገር ለታላላቅ ተግባሮች መሳሪያ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በሰለጠነው ዓለምም የፕሬስን ሚና እስከ መጫወት እንደደረሱ በግልፅ የምናየው ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹን በተመለከተም በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ በፈረንጆቹ በታህሳስ 2014 የተደረገ አንድ ጥናት ይጠቁማል፡፡

በዓለም ላይ ከሚገኙ የበይነ መረብ ተገልጋዮች ውስጥ 72 በመቶ የሚሆኑት ማህበራዊ ድረ-ገጾችን እንደሚጠቀሙ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ፌስቡክን (facebook) ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር 1 ነጥብ 15 ቢሊዮን እንደሆነ ታውቋል፡፡

በአገራችንም ያለውን ገፅታ በቁጥር ለማስቀመጥ ጥናት ቢያስፈልግም የበይነ መረብ ተደራሽነት ግን ከምንግዜውም በተሻለ ፍጥነትና ጥራት እያደገና የህይወታችን አንዱ ገፅታ እንደሆነም መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡

እንግዲህ ከበዛው የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጥቅምና አገልግሎት ውስጥ በዚህ ፅሁፍ ላይ ትኩረት የተደረገበት ጉዳይ ትምህርታዊ ፋይዳውን ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ ማህበራዊ ድረ-ገጾች በሰለጠነው ዓለም በትምህርት ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በተለይም ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቶች ብዙ ጥቅምን ሲሰጡ ይታያሉ፡፡

በአሁኑ ወቅትም በአገራችን በተለይም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ ስሙ የማይገኛ ተማሪ ቢኖር በይነ መረብ (Internet) ባልደረሰበት ስፍራ የሚኖር ወይም በግል ምክንያትን እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ከዚህ የቴክኖሎጂ ውጤት ተማሪዎችም ሆኑ ትምህርት ቤቶች ምን ጥቅም ያገኛሉ የሚል ጥያቄ እዚህ ጋር ሊነሳ ይችላል፡፡ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለመማርና ሀሳብን ለመለዋወጥ ብዙ እድሎችን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ ተማሪዎች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በመገኘት በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ ሰው ጋር መወያየትና መረጃን በተለያየ መልክ መለዋወጥ ይችላሉ ፡፡ እንግዲህ በነዚህ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ድርጅቶች

የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች በእድሜ ክልል

89%

18-29 ዓመት

72%

30-45 ዓመት

48%

50-60 ዓመት

43%

65> ዓመት

89%

18-29 ዓመት

72%

30-45 ዓመት

48%

50-60 ዓመት

43%

65> ዓመት

የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች በእድሜ ክልል

89%

18-29 ዓመት

72%

30-45 ዓመት

48%

50-60 ዓመት

43%

65> ዓመት

ማህበራዊ ድረ ገጾችና ትምህርታዊ

ፋይዳ በ ዓለማየሁ ስሜነህ

Page 28: Temsalet Magazine 2 Pages

24 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ስለሚገኙ፤ አንድ የተፈለገን መረጃ ከሚመለከተው አካል ለማግኘት ከድርጅቱን ወይም ከግለሰቡን ገጽ ጋር በማገናኝትና ወጃጅ በመሆን (Like) በማድረግ ጓደኝነትን እንዲሁም ግንኙነትን በመፍጠር ግለሰቡ ወይም ድርጅቱ የሚያስተላልፈውን መረጃና መልዕክት በቀላሉ ማግኘት ይችላል፡፡

እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም በቀላሉ ከተማሪዎች እንዲሁም ከወላጆች ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግ ይቻላሉ፡፡ በዚህም ወላጆች በሚመቻቸው ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ እንዲመዘገቡ ወይም Account እንዲኖራቸው ማድረግ ከዚያም ትምህርት ቤቱ የሚፈለገውን መልዕክት ማስተላለፍ፤ ከወላጆችም ጥያቄ ወይም አስተያየትን በቀላሉ መቀበል ይችላል፡፡ ይህም ደብዳቤ ከመፃፃፍ ለወላጅም በአካል ትምህርት ቤቱ ድረስ ከመሄድ በፍጥነቱ በቀላልነቱ እንዲሁም በርካሽነቱ የተሻለ ያደርገዋል፡፡

በተለያዩ አገራት የሚገኙ መምህራንም በሚያስተምሩት ትምህርት ዓይነት ማህበራዊ ድረ-ገጽ በመክፈት የቤት ስራን ለመስጠትና ለወይይት

ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ ይህም ተማሪዎች ከትምህርት ሰዓት በተጨማሪ ትምህርታዊ ጉዳዮችን ከመምህራኖቻቸው ጋር ለመነጋገር ያልገባቸውን ለመጠየቅ ሌላኛው መንገድ ይሆናል፡፡

ማህበራዊ ድረ-ገፆችን በመጠቀም የፅሁፍ ክህሎትንም ማዳበር እንደሚቻል ጥናቶቹ አመላክተዋል፡፡ ባደጉት አገራት ት/ቤቶች ስማቸውንና የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲሁም የት/ቤቱን አላማ፣ ተልዕኮና ጉዞ ለማስተዋወቅ ማህበራዊ ድረ-ገጽን ከዋናው የት/ቤቱ ድረ-ገጽ ጋር በማገናኘት ይጠቀማሉ፡

፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከላይ የጠቀስነው ጥናት እንደሚጠቁመን ወደ 75 በመቶ የሚጠጉት የዋናው ድረ-ገጽ ጉብኝቶች የተደረጉት ማህበራዊ ድረ-ገጾቹን በመጠቀም ነው፡፡ ስለሆነም ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለሌሎች ገጾች መጎብኝት ትልቅ ሚና እንዳላቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቶች ማህበራዊ ድረ-ገጽ እንዲኖራቸው በማድረግና በሚገባ በማንቀሳቀስ የተለያዩ መልካም ስራዎችን ማበረታታትና ስለ እያንዳንዱም አገልግሎታቸው አስተያየትን ከሚመለከታቸው ወገኖች ለማግኘት ያስችላል፡፡

በርግጥ እዚህ ላይ አንድ ነገር ሊነሳ ይችላል፡፡ ይህም በማህበራዊ ድረ ገጾች ይዘታቸውንና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መረጃዎች ከየትኛው ወገን ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ለነዚህ እንደ መፍትሄ ሊወሰድ የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖውን ብቻ በማሰብ ፋይዳውን ሙሉ ለሙሉ ከማጣት ይልቅ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ የአጠቃቀም ፖሊሲና ዕውቀትን ከባለሙያ ጋር በማቀናጀት በቀላሉ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡

እንግዲህ ዘመኑ የኢንተርኔት እንደመሆኑና ወጣቱም በመረጃ ምንጭነት እየተገለገለበት ስለሚገኝም በዚሁ ሚዲያ ተጠቅሞ ወጣቱን ማግኘትና ወደሚፈለገው የእድገት ደረጃና አቅጣጫ መምራትና ማስተማር ተመራጭ መንገድ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎ የሚጋሩት ሃሳብ ነው፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ሊያሳድሩ የሚችሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ ስጋት በመጋራት በአግባቡ የመጠቀም ባህሪ ማዳበር ቅድሚያ ለሚሰጠው ተግባር ነው፡፡

Page 29: Temsalet Magazine 2 Pages

25 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ምንአልባት አንባቢዬ ይህንን ርዕስ ሲመለከቱ ደግሞ ትዝታ ይሸታል እንዴ ብለው ይጠይቁ ይሆናል፡፡ አዎን በተለይ ጥሩ ትዝታ ይሸታል ልክ እንደትኩስ አበባ እንደ ጥሩ ሽቶ እንደሚያውድ ምግብ ከወራት በፊት በአንዱ ቀን በአንዱ

ዪኒቨርሲቲ ውስጥ (አ.አ.ዩስድስት ኪሎ ካምፓስ) ከማውቀው ጓደኛዬ ጋር ስለቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ህይወት ትዝታችንን እየተጨዋወትን ነበር፡፡ ይህ ጓደኛዬ የትዝታውን ጥልቀት የገለጸው ‹‹በተለይ የተማርንባቸውንክፍሎች ሳይ፣ ከክፍል ጓደኞቻችን ጋር የተቀመጥንባቸውን ያጠናንባቸውን ቦታዎች ሳይ ትዝታው ከአይምሮዬ ውስጥ ይሸተኛል፡፡›› አለኝ አገላለጹን ወደድኩለት እናም ተዋስኩት መቼም በትምህርት ዓለም ውስጥ ላለፈ ሰው የትምህርት ቤት ቆይታ የራሱ ጣፋጭ አንዳዴም መጥፎ ትዝታ እንዳለው ይረዳል፡፡ ይችን ፅሑፍ ስፅፍ እኔ የተሰማኝ ወይም ያሳለፍኩትን ነገር ከማጋራት ባለፈ ሌሎች ብዙዎች መሰል ትዝታዎቻቸውን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በማንሳት እንዲሳተፉ ለመጋበዝም ነው፡፡ለማንኛውም ወደ ፅሁፌ ልግባ፡፡

ሌላ አዲስ ምዕራፍከዛሬ አስራስድስት ዓመት በፊት በቀድሞው አሰራር የአስራሁለተኛ ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን አልፈን አ.አ.ዩ /አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ/ ገባን፡፡ ገና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሳለን ዝናውን ወደ ሰማንለት ዩኒቨርሲቲ መግባት መቻል በራሱ ምን ያህል አስደሳች እንደነበር ያኔ በዚያ ጊዜም፣ ከዛ በፊትም ሆነ በኋላ ዩኒቨርሲቲ የገባ ተማሪ ያስታውሰዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ ነገር ዛሬ ዛሬ ምን ያህል ስሜት እንደሚሰጥ አላውቅም፡፡ ለማንኛውም ዩኒቨርሲቲ መግባት ከመጨረሻ ውጤቱ ሳይሆን በሂደቱ ውስጥ ከነበረው ጥናትና ውጤታማ የመሆን ፍላጎት አንፃር ካየነው ፋይዳውን እንረዳለን፡፡ ለተማሪው በትምህርት ውጤታማ መሆን ከመቻል የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር አለና? ብቻ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርትም ሆነ ለግቢው ያለን አዲስነትና ጉጉት ፊታችን ላይ በግልፅ ይነበብ ነበር፡፡ ‹‹ፍሬሽ››ተማሪ

ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚመጣው ተማሪ ልብሱን እና ጫማውን፣ አንሶላና ብርድልብሱ በሻንጣ ብቻ ሳይሆን በትምህርት ህይወቱ የመለወጥና የማሻሻል ህልሙንም በልቡ ሰንቆ ዩኒቨርሲቲውን

ተቀላቅሏል፡፡

ከመጀመሪያ ዓመት ተማሪነት ጋር የገና ማዕበል የማለፍ ጉዳይ በሁሉም አዕምሮ ውስጥ መጠኑ ቢለያይም ስጋቱ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ይህን ስል ግን በራስ የመተማመን ስሜትም መኖሩን ሳልዘነጋ ነው፡፡ ትምህርት በተለይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ፈተናን ከመውደቅ እና ማለፍ ባሻገር ልናጣጥመው የሚገባ ነገርም አለው፡፡ በዚያ ላይ ትልቅ አቅም ኖሯቸው በጥቃቅን ችግሮች ለምሳሌ በአጠናን መንገድ፣ በስነልቦናዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ፈተናውን ማለፍ ሳችሉ የቀሩ ተማሪዎችን ጉዳይ ሳስብ ህመሙ ጠልቆ ይሰማኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስጋቱ ከራስ የትምህርት ጉዞ መሰናክል አንፃር ብቻ ሳይሆን የወላጆች፣ የቤተሰብ እና ጓደኛን ወዘተ ተስፋና እምነት ገደል ላለመክተት ማሰቡ የራሱ ስነልቦናዊ ተፅእኖ እንዳለው ይሰማኛል፡፡ ማዕበሉን አልፎ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለውን ቆይታ አራዝሞ ‘ሲኒየር’ ተማሪ ለመባል እና ፍሬሽጦጣው የሚለውን ቅጥያ ለመግፈፍ በሚደረግ ጥረትና ፍላጎት ውስጥ የተሸፈነ መልካም ነገር አለ፡፡ በ’ርግጥ ከዚህ ጋር የተያያዙ ከመጠን ያለፉ ብሽሽቆሽ እንደነበሩም አልዘነጋም ፡፡

ዩኒቨርሲቲ መማር የሚጀመርበት ዩኒቨርሲቲ ማለት የትምህርት መጨረሻ አይደለም ይልቅ ሰፊው የመማር ጉዞ የሚጀመርበት ነው፡፡ የሚለውን አባባል እቀበለዋለሁ ፡፡ የዓለምን ማለትም የእውቀትን ሰፊነት አንድ ሰው ይበልጥ የሚረዳው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ነው ፡፡ አንድ ተማሪ ራሱንና የእውቀት አቅሙን በሆነ መልኩም ቢሆን የሚለካበ፣ ደረጃውንም የሚያውቅበት ስፍራ ነው፤ ዩኒቨርሲቲ ፡፡ ከክፍል ጓደኞቹ፣ ከመምህራኑ ወዘተ.. ብዙ ነገር ይማራል፡፡ ፡፡ በትምህርት ዘመን ቆይታውምእንደዚያው ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የትምህርት ባህላችን ላይ የተሰጠንን የትምህርት ይዘት አጥንቶ ተፈትኖ ከማለፍ የዘለለ የምርምር ሃሳቦችን የማንጸባረቅ /Reflective Learning/ ያለመዳበሩ ሁኔታ አንዱ በክፍተት የሚነሳ ጉዳይ እንደሆነ አምናለሁ ፡፡ ግን ደግሞ ችግሩ ከተማሪው በኩል ብቻ ሳይሆን ከመምህራኑ የማስተማር ዘዴ፤ በሃገሪቷ ውስጥ በነበረው ምናልባትም አሁንም ካለው የትምህርት አሰጣጥ የመነጨ ነው የሚል አመለካከት አለኝ ፡፡ ዛሬስ ይህ ነገር በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን ጥያቄ በዚህ አጋጣሚ አንስቼ ባልፍ ፡፡

ከአዕምሮ ውስጥየሚሸት ጣፋጭየዩኒቨርሲቲ ትዝታ

በ ዳግም ትንሳኤ

Page 30: Temsalet Magazine 2 Pages

26 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ሌላውበዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተማርነው ነገር ማህበራዊ ህይወትን ነው ፡፡ ከአዲስ አበባ ት/ቤቶች ለመጡ ተማሪዎች የመኝታ አገልግሎት ያኔም ቢሆን የሚሰጠው በአብዛኛው በሁለተኛ ሴሚስተር የትምህርት ወቅት ነበር ፡፡ ብቻ በዚህ አጋጣሚ “የዶርም” ሕይወትን የማጣጣም እድል ነበረኝና ከተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች ከመጡ ተማሪዎች ጋር ማህበራዊ ህይወትን አሳልፌያለሁ ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ መግባባትና ተቻችሎ መኖር እንዳለ ሁሉ አለመግባባት እና ግጭት ይኖራል ፡፡ ይህ ደግሞ አንድ የማህበራዊ ህይወት አካል ነው፡፡ በሰፊው የጋራ መስተጋብር በግብዓትነት የሚያገለግል ብዙ ስንቅ አግኝተናል ፡፡ በዚህ የጋራ ቆይታችን ውስጥ ስለብዙ አይነት ጉዳዮች ተጨዋውተናል ፤ በጋራአጥንተናል ፡፡ ስለ ሃገራችን ብቻ ሳይሆን ስለ አለምአቀፍ ጉዳዮች አንስተን ተከራክረናል ፣ አንዳችን ስለ ሌላኛችን የትምህርት ውጤት ማማር

ተጨንቀናል ፣ ደስታን ብቻም አይደል ጭንቀት እና ቁዘማን ተካፍለናል ፣ እንደተማሪነታችን የየራሳችን ጀብዱ ለመስራት እድሜያችን ወይም ተማሪነታችን ገፋፍቶናል ፡፡ በተለያዩ ጊዜያቶች ውጤትንም ሆነ ውድቀትን አስተናግደናል ፡፡ አይነቱና መጠኑ ቢለያይም ቅሉ ፡፡

ይህ በዩኒቨርሲቲው የመኝታ ክፍሎችም ሆነ በሌሎች ስፍራዎች ለምሳሌ በመመገቢያ አዳራሾች እና ካፍቴሪያ ማህበራዊ ህይወት መቻቻልና መከባበር ዛሬ፤ ዛሬ በዚህ ብቻ ሳይሆን በሌሎች በሃገሪቷ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ውስጥ እንደሚከሰቱ ከምንሰማቸው አሉታዊ ነገሮች አንጻር ስናየው ያለውን አስተዋጽዎ እንገነዘባለን ብዬ አስባለሁ፡፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ ሃገር በትንሹ የሚወከልባቸው ስፍራዎች ናቸው ፡፡ ስለሆነም በነሱ ውስጥ የሚገኙ በጎ እሴቶች ወይም አሉታዊ ነገሮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

Page 31: Temsalet Magazine 2 Pages

27 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

አቶ ረዲ ሽፋ በአገር አቀፍ ትምህርት ፈተናዎች ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው ፡፡

በ 2008 ዓ.ም ወደ የኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

» በ2008 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ ምደባ ከተከናወነ በኋላ ከአንዱ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ለመቀየር የሚችለው የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው ፡፡ የቅያሪ ጥያቄ በትምህርት ሚ/ር ወይም በአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ አይስተናገድም ፡፡

» በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ተምረው ከአንዱ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ወይም በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንት ለመቀየር ጥያቄውን ማቅረብ የሚቻለው እየተማሩ ባሉበት ዩኒቨርሲቲ ነው ፡፡

» በፈተና ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፈተና ለማስመርመር ከፈለጉ በአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረ-ገጽ www.nae.gov.et በመጠቀም student የሚለውን በመምረጥ ቅሬታ/ complain ማቅረብ ይችላሉ ፡፡ ቅሬታው በ3 ቀን ምላሽ ያገኛል ፡፡

» ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ አቀባበል እና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኙት ከተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ነው ፡፡

» ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ከመሄዳቸው በፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉትን መልዕክት በጥሞና መከታተል አለባቸው ፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን ከጠሩበት ጊዜ በፊት እና በኋላ እንዳይሄዱ ፡፡

» በሁሉም የትምህርት መስክ በመንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው ዲግሪ ተመሳሳይ እና አንዱ ከሌላው የማይበላለጥ ነው ፡፡

መልካም ዕድል!

ልዩነቱን ያውጡ ያሽልማል!

ጠቃሚ መረጃወደ ዩኒቨርሲቲ

ለተመደቡ!

Page 32: Temsalet Magazine 2 Pages

28 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ከ2 ዓመታት በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ አንድ አስገራሚም፣ አስደንጋጭም፣ አሳዛኝም ዘገባ ማንበቤን አስታውሳለሁ። በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የተፈፀመ አስነዋሪ ተግባር።

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሰባት ተማሪዎች (3 ወንድና 4 ሴት) የማጠናከሪያ ትምህርትና ጥናት አለን በማለት በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ ያመሻሉ። ከዚያም (ከጥበቃዎች ጋር በመስማማት ይመስላል) ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአንድ ክፍል ውስጥ በቦርሳቸው ደብቀው ያስገቡትን ሁለት ጠርሙስ ውስኪ እየጠጡ ጭፈራ ይጀምራሉ። ይጠጣሉ፣ ይጨፍራሉ፣ ይጮሀሉ… ድምፁ በጣም እየተሰማ ተው የሚል ግን አልነበረም። እስከ ምሽቱ 7 ሰዓት አስረሽ ምችው ከጨፈሩ በኋላ ድምፃቸው ይጠፋል።

በማግስቱ ጠዋት ተማሪዎች ወደ ክፍል ሲገቡ የታየው ነገር አስደንጋጭ ነበር። ሴቶችም ወንዶችም እርቃናቸውን በወንበሩም በወለሉም ላይ ተረፍርፈዋል። ክፍሉ በትውኪያና ሽንት ተጥለቅልቋል። ሁለት የውስኪና ሦስት የአምቦ ውሃ ጠርሙሶች በየቦታው ወድቀዋል። የምግብ ፍርፋሪም በክፍሉ ይታያል። በጣም የሚገርመው ደግሞ በ’ላፕቶፓቸው’ ሲመለከቱት (ምንአልባት ያንኑ ሲለማመዱት) የነበረው አስፀያፊ የ“ኦንላይን” ልቅ የወሲብ ፊልም አልተዘጋም ነበር። አገር ሰላም ያሉት ቀበጦቹ ተማሪዎች ግን እንቅልፍ ላይ ነበሩ።

እኔን በጣም የገረመኝ ነገር በሌሊት ክፍል ውስጥ ሲጨፈር ድምፁ እየተሰማ ጥበቃዎች ተው አለማለታቸውና ወላጆችም ልጆቻችን የት ቀሩ ብለው አለመጠየቃቸው ነበር። ለማንኛውም ይህ በአገራችን በተለይም በመዲናችን እየተፈጠረ ላለው አዲስ የወጣቶች መንፈስ እንደ ማሳያ ይሆናል ብዬ እንጂ ሌላም እጅግ ብዙ አሳዛኝና ዘግናኝ ነገሮች እየተፈፀሙ መሆኑን በየጊዜው እየሰማን ነው።

የአባቶች ውብ ባህል ወደ ልጆች እየተሻገረ አይደለም። የሥነ ምግባር መበላሸቱ ብቻ ሳይሆን ሀገርን እንደ ሀገር አለማየቱ እየበዛ ነው። ቋንቋችንን መናገር አሳፋሪ ነገር እየሆነ መጥቷል። ገና በ’ሃይስኩል’ና ከዚያ በታች በሆኑ የትምህርት ደረጃዎች የሚጀመረው ከአገር ወግና ባህል ማፈንገጥ ነው አድጐ ነገ ሀገር የሚያጠፋው። በሥነ-ምግባር ያለታነፀ ትውልድ ለአገር ይጠቅማል የሚል እምነት የለኝም። ጥያቄው ግን ሥነ ምግባርን ማን ያስተምር የሚለው ነው። ወላጆች? ጓደኞች? ትምህርት ቤቶች? ወይስ የምዕራባውያን ፊልሞች? የእያንዳንዳቸው ድርሻስ በምን መልኩ መሆን አለበት?ሁሉም ድርሻ አላቸው (መጥፎም ጥሩም ለማድረግ)። የአንዱ ግን ከሌላው ይለያል። ትልቁን ድርሻ መውሰድ ያለበት እና ለዚህም ጠንክሮ መስራት ያለበት ግን ከትምህርት ቤቶች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው አካል

ይመስለኛል። ምክንያቱም ትውልዱን በእውቀትና በሥነ ምግባር አርሞና ኮትኩቶ የማሳደግ ድርሻው በአብዛኛው በትምህርት ቤቶች ላይ የወደቀ ነውና፡፡ የትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ ሁኔታ መፈተሽ ያስፈልጋል። የሥነ ምግባር ትምህርቶች ውጤታማነት መታየት አለበት። ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ የትምህርት ስልት ማስተማር አለማስተማራቸው ሁሉ ሊጠናና የተጣመመው ሊቃጠጥ ግድ ነው፡፡

የተደበላለቀ ዓይነት ትውልድ የሚፈጠረው ወጥ ባልሆነ ሥርዓተ ትምህርት ነው። ዛሬ አገራችንን ደም እያስለቀሰና ታላቅ ዋጋ እያስከፈለ ያለው ሙስና መነሻው ትምህርት ቤት ነው። የሥነ ምግባር አስተምህሮታችን ውጤት ነው ሙስና። ሙስናን የሚጠየፍ ትውልድ በአንድ ጀምበር አይፈጠርም። ትምህርት ቤቶች ላይ ብዙ መድከምን ይጠይቃል። ልጆች ሥነ ምግባርን መማር ብቻ ሳይሆን የሕይወት መርህ ማድረግ መቻል አለባቸው።

እንዲህ የሚባል ተረት አለ። “በእንግሊዝ አገር አንድ ገበሬ ነበር አሉ። ከእርሻ ሥራው ጐን ለጐን ድመቶችን በማሰልጠን የገቢ ማስገኛ ሥራ ይሰራባቸው ነበር። ገበሬው በልደት፣ በሠርግ፣ በምርቃትና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ የደስታ ቀናት /በዓላት ላይ ስልጡን ድመቶቹን በመደዳ ያሰልፋቸውና በሁለቱ የኋላ እግሮቻቸው ቆመው በሁለቱ የፊት እግሮቻቸው ደግሞ የተለኮሰ ሻማ ይዘው እንዲታዩ በማድረግ ነበር ገቢ የሚያገኝባቸው። ከዕለታት በአንዱ ቀን ታዲያ ገበሬው በአንድ ልዑል ሠርግ ተገኝቶ የተለመደውን ትርዒት እንዲያሳይ ይጋበዛል። ከ20 በላይ የሆኑት ድመቶችንም ግራና ቀኝ ተሰልፈው ሻማ እንዲያበሩና ሙሽሮቹ በመካከል እየተጀነኑ እንዲያልፉ በማድረግ ልዩና ዘና የሚያደርገውን ትዕይንት በማሳየት ላይ እያለ አንድ አሳፋሪ ክስተት ተከሰተ።

ነገሩ እንዲህ ነው። ድመቶቹ በሚያሳዩት ልዩና ቀልብ የሚስብ ትዕይንት ሰው ሁሉ ማጨብጨቡን ትቶ ፈዞ በመመልከት ላይ ነው። የሙሽሮቹ ደስታ እጥፍ ድርብ እየሆነ ነው። ሁሉም ቀልቡ በትርዒቱ ተስቦ በአግራሞትና በአድናቆት ሲከታተል ከየት እንደመጣ ያልታወቀ አንድ የደነበረ ወደል አይጥ በድንገት ዘው ብሎ አዳራሹ ውስጥ ይገባል። “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” ሆነና የገበሬው ድመቶች ያን ወደል አይጥ ባዩ ጊዜ የተሰጣቸውን በልዑል ሠርግ ፊት እየተደረገ ያለ እጅግ ታላቅ ኃላፊነት ከምንም ሳይቆጥሩ ሻማቸውን እያሽቀነጠሩ በመጣል አይጡን ማባረሩን ተያያዙት። አዳራሹም በቅፅበት በትርምስና በሁከት ተሞላ። ገበሬው ታላቅ ሐፍረት ተሰማው። አንድ ነገር ግን ትዝ አለው። ድመቶቹን ስለ ሻማ አያያዝና አሰላለፍ ለማስተማር ያን ያህል ጊዜ ሲደክም ቢያንስ እንደዚህ ባለ የተከበረ ትርዒት ወቅት አይጥን አይቶ እንዴት ማለፍ እንደሚቻል አላስተማራቸውም ነበር።” (ምንጭ፤ ምጥን ቅመም መጽሐፍ)

የሥነ ምግባር ጉዳይ … በ መላኩ አላምረው

Page 33: Temsalet Magazine 2 Pages

29 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

ከታሰበበትና ከልብ ከተደከመበት ሰውን አይደለም እንስሳትን አሰልጥኖ ልዩ ተአምር መፍጠር ይቻላል። የሰው ልጅ በባህርይው ባስተማሩትና በደከመበት ልክ የማወቅ ፀጋ አለው። መጥፎ ነገር ላይ ካተኮረ መጥፎን ይማራል። ጥሩን ካዘወተረም ጥሩውን ነገር የህይወቱ አካል ያደርጋል። ያልተማረውን መልካም ነገር ከየትም ሊያመጣው አይችልም። ትውልዳችንን ምን አልባት ፊደል እያስቆጠርነውና ሳይንስን እያስተማርነው ይሆናል። ለዲፕሎማ፣ ለዲግሪ፣ ለዶክትሬት… የሚያበቃውን እውቀትና ክህሎትም ሰጥተነው ሊሆን ይችላል። ይህ ሁሉ ግን ሥነ ምግባር ከጐደለው ከንቱ ነው። በትምህርት ውጤት አራት ነጥብ (4.00) ሊኖረን ይችላል። በክህሎትም ምስጉኖች ልንሆንና ሰው ሁሉ የእኛን ጥበብ የሚመኘው ሊሆን ይችላል። ሥነ ምግባር ከሌለን ግን ይህ በሰው ልጅ ሕይወት ላይ ሊተገበር አይችልም።

ሥራን እንዴት መሥራት እንደሚቻል ማስተማር አንድ ነገር ነው። በሥራ ሂደት የሚመጡ መሰናክሎችን ሁሉ አልፎ ከሚፈለገው ግብ ላይ መድረስ እንዴት እንደሚቻል ማሳወቅ ደግሞ ሌላ። ሥራን በልዩ ፍጥነትና ክህሎት እንድንሰራ ብቻ ሳይሆን ለማን እንደምንሰራና ለምን እንደምንሰራ ሁሉ ማወቅ አለብን። ሥራችን እየተደነቀ ባለበትና ልዩ ተስፋ በተጣለብን ወቅት ወፍራም ብር ሲመጣ ቃላችንን የምናጥፈውና ህዝብን ሳይሆን ግለሰብን0 የምናገለግለው እኮ እንዴት መስራት እንዳለብን እንጂ ወፍራም ብርን እንዴት ማለፍ እንዳለብን ስላልተማርን ነው። እነዚያ ድምቶች እኮ ገበሬውን ያዋረዱት አይጥ የማሳደድ ተፈጥሮ ስላላቸው ብቻ አይደለም።

አይጥ መቼና የት ማባረር እንዳለባቸው እና መቼ እንደሌለባቸው አልተማሩም። በትርዒት ወቅት አይደለም አንድ አይጥ ሺህ አይጥ ቢመጣ አቋርጦ መሄድ እንደማይቻልና ይህንን የማለፍ ጥበቡና ሥርዓቱ (ምግባሩ) እንዴት እንደሆነ አልተማሩም። ለዚህም ነው ገበሬውን ያዋረዱትና ሠርጉን የረበሹት።

እኛም እኮ ዛሬ ገንዘብ የመውደድ ባሕርይ ስላለን ብቻ አይደለም ሙስና የምንበላው። ገንዘብን ከወደድን እንዴት ሠርተን ማግኘት እንደምንችል፣ ካሰብን እና ከጣርን ማግኘት እንደምንችል እንጂ የህዝብን ተስፋ ገድለን ኪሳችንን ማሳበጥ ፍፁም ቆሻሻና ወራዳ ሥራ እንደሆነ አላወቅንም። እንዲሁ ሰማነው እንጂ አልተዋሃደንም። በወሬ እንጂ በተግባር ያሳየን የለም። የሚያስተምሩንም እራሳቸው ሲዘርፉ እያየን ይሆናል። በልጅ አዕምሮአችን ያልተማርነውን የት እናምጣው። ሙስና ወንጀል ነው ተባልን እንጂ ሙሰኛው በተጨባጭ ሲወነጀልና ሲቀጣ አላየንም/አልተማርንበትም። ሙሰኛው ሲቀጣ በተግባር አሳይቶን የሚያውቅ መምህርም የለም። ታዲያ ሙስና እንደሚያስቀጣ እንዴት እንመን? ሥነ ምግባር የሚያስተምረንን ነገር ግን በተግባር የማያሳየንን መምህር እንዴት እኛ በተግባር እናሳየው? የምንማረው ሁሉ እንደሚሆን እንጂ እንዴት እንደሚሆን ካላየን እንዴት እንፈፅም? ይህ ሁሉ የትምህርትን ጉዳይ ጉዳየ ነው ባለው አካል ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል። ወላጆችም ሆንን መምህራን ትውልድን ብሎም ሀገርን የመገንባት ድርሻው የእኛ ነውና የሥነ ምግባሩን ጉዳይ አንዘናጋበት!

Page 34: Temsalet Magazine 2 Pages

30 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

Page 35: Temsalet Magazine 2 Pages

31 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008

Page 36: Temsalet Magazine 2 Pages

32 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም 2008