to plan for peace and live by loving one another. ዘአትላንታ · pdf fileሥላሴም...

2
መልእክት ከብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ወደ ቀደመው ፍቅራችን እንመለስ! በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! «እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።»ኤፌ 4፤32 የተወደደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ ! ላለፉት 22 ዓመታት ክፉውንም ደጉንም አብረን ስናሳልፍ አደግን እንጂ አላነስንም ፣ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ሠራን እንጂ አላፈረስንም፣ ሰበሰብን እንጂ አልበተንም፣ ሞላን እንጂ አላጎደልንም፣ በሃይማኖት ጸናን እንጂ አልደከምንም። ስለሆነም ያሳለፍነውን የሰላም ጊዜ አስበን ጊዜ ያመጣውን ጸባችንን ትተን፤ተቻችለን ይቅር ተባብለን ወደ ቀደመው ፍቅራችን ተመልሰን አብረን እንኑር። በመለያየት እግዚአብሔር አይከበርም ። ይልቁንም እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ይቅር መባባላችንና መፋቀራችን ነው። “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”ማቴ 6፦14-15 ጌታ ዳግም ሲመጣ አንድ ሆነን እርስ በርሳችን ይቅር ተባብለን ተፋቅረን አንጂ ተለያይተን እንዳንገኝ፤ የቅዱሳን፣ የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎታቸው የመላእክት ጠባቂነታቸው የወላዲተ አምላክ ልመናዋ እና በረከቷ ከኛ ጋር ይሁን። የእግዚአብሔር አብ ጸጋ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን «ከሁሉ አስቀድመን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ።» (ሮሜ 1 ፥ 8) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳን ሐዋርያት ተያይዞ የመጣ ዶግማ ፥ ቀኖና ፥ ሥርዓት ያላት ጥንታዊት ዓለም አቀፋዊት መሆኗ ይታወቃል ። ሆኖም በዚህ ዘመን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን የጋራ ጠላት ሆነው በስፋት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የተሀድሶ መናፍቃን መንጋ እና ማኀበረ ቅዱሳን የሚባል አፍራሽ ቡድን ነው። ማኀበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎች መስለው በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን በማኅበር አደራጅተው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና ተገዢ ባለመሆን በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት ኃይል ተደግፈው በግፍ ተሰድደው በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር የሚገኙ አባቶችን ፥ የወንጌል መምህራንን፥ ዘማርያንን የሐሰት ስም በመስጠት ፣ በተለይም በኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎችና በኅትመት ውጤቶች በመታገዝ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ፥ በማን አለብኝነት የመከፋፈል ሥራ እየሠራ ይገኛል ። በተለይም በዕድሜና በእውቀት እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቱን ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ዕድሜ ጠገብ አባቶቻችንን በመድፈር የማይገባ ስም በመስጠት ማኅበሩ የሚፈጽመው ስም ማጥፋት ለምንወዳት ቤተክርስቲያን ታላቅ ሸክም ሆኖቧቷል። ስለሆነም እኛ የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ምእመናን የቅዱሳን እና የጻድቃን አማላጅነትን፣ የመላእክት ተራዳኢነትን እንዲሁም የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብሯን እና አማላጅነት የማይቀበሉትን የተሃድሶ መናፍቃንን እንቃወማለን። ትምህርተ ሃይማኖትን እየበረዙ የሐሰት ትምህርት በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የሚያስተምሩ የማኀበረ ቅዱሳን አባላት «እኛ ክርስቲያን አይደለንም ፤ጠላት ያወጣልን ስም ነው» «አዳም የተጠመቀ ክርስቲያን ነበር»እመቤታችን ከሌለች እግዚአብሔርም ሥላሴም የለምፍትሀ ነገስት በሰለሥቱ ምት ነው የተጻፈው»የሀዋርያት አመክንዮ በሰለስቱ ምት ነው የተጻፈውየሚሉና ሌሎችንም የፈጠራ ትምህርቶች የሚያስተምሩ ሐሳውያን መምህራንን እንቃወማለን። ቅዱሳን ቁርባን የሚቀርብበትን ወንጌል የሚሰበክበትን የተቀደሰውን አውደ ምህረት (የምህረት አደባባይ) በማርከስ ላይ ጥላቻን የሚዘሩ እና የሚሳደቡትን እናቃወማለን። በቅዱሳን ጸሎት በአበው ትምህርት በሰማዕታት ደም ጸንታ የኖረችው ኦርቶዶስሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንን የጽዋ ማኅበር አይተካትም። በጎበዝ አለቆችም አትመራም። ቤተክርስቲያናችን የምትመራው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሚመራው በህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው አራት ነጥብ። የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችንን ረድኤት አማላጅነት ከኛ ጋር ይሁን! በዚህ እትም ላይ መልእክት ከብጹእ አቡነ ያዕቆብ ርዕሰ አንቀጽ የሀሰት እና የክፍፍል አምራች ቅጥር መምህራን አሁንም እንደጎረፉ ነው! ብፁዓን አባቶቻችን ላይ ላነጣጠረው ዘለፋ እና መሰረት የለሽ ትችት መልስ ተሰጠ!! ፪ኛው አውነቱን እንታደግ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በከፍተኛ ስኬት ተጠናቀቀ ከሳሹ ወንድሜ ግጥም ሕገ ደምባችንን እወቁ Message to Children 1ኛ ዓመት ቁጥር 1 መጋቢት 2009 ዘአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እውነትን በሚታደጉ ምዕመናን እየተዘጋጀ የሚቀርብ ዜና መፅሄት ርዕሰ አንቀጽ "እኛስ የሐይማኖት ለዋጮችን ስራቸውን እንጸየፋለን፤ መለየታቸውንም ሁሉ ሕግ መለወጣቸውንም። እነርሱ በእኛ ዘንድ የረከሱ ናቸውና።." today is frustrating, we are however, wit- nessing a bright light at the end of the test- ing tunnel! The hard work is paying off and the committee of elders that has been work- ing hard to defend the truth about our cathe- dral, protect our holy father and fight the false and negative accusations directed against the Holy Synod is already witness- ing some good results. We also want you to know that our success thus far, is achieved not because it was easy. Instead, it was because God helps the truth to flourish! As it is written in the Psalm 119:160, “The sum of your word is truth, and every one of your righteous rules endures forever.” Yes, the truth endures forever! Therefore, we are proud of you in how you were passionate about defending the truth side by side with your parents and our holy father, Abune Yaekob. Again, your enthusiasm and pray- ers are something that made all of us proud and your all around contributions have been Dear Our Children, Greetings from Awde Mihret!!! Our Sealite Mihret Atlanta Saint Mary Cathedral has been our spiritual home for the past few decades. Our cathedral has indeed baptized, educated and raised most of you and continues to do so with our younger children that are following your footsteps. Given such a reality, we the editors of this newsletter as well as all your parents be- lieve that the events that have been transpiring in our church in the last seven or eight months were too disturbing for you. We know that the situation has affected you, our children than most of the community at large. Of course, this is something that made most of you react in your clear terms. And we completely agree with you and accept your frustration. Yes, our community in general and the members of our cathedral in particular have let us down in multiple occasions in the past. We, how- ever, hope and work that this situation will soon be history as God will prove the truth sooner rather than later. Dear Our Children: While the situation that you have been enduring in such times like really amazing. With that spirit, let’s invite you to read and discuss the following two quotes from the holy bible. These quotes teach us about peace, they discuss the importance of forgiveness and moving on and most of all, they teach us about why we need to plan for peace and live by loving one another. After all, we know that our savior, Jesus Christ came to this world because he loves us and he want- ed to inspire us to love one another. Please share this two quotes with your friends and discuss them amongst yourselves. We adore you and we pray that our God’s protection and our Holy Mother Saint Mary’s prayers and mediations protect you, the children of Sealite Mihret Saint Marry of Atlanta!! Quote one: “Proverbs 12: 20, Deceit is in the heart of those who devise evil, but those who plan peace have joy.” Quote Two: “Galatians 5:22, But the fruit of the Spirit is love, joy, peace, patience, kindness, goodness, faith- fulnessAwde Mihret’s Message to the Children of Sealite Mihret!! ይህ የውስጥ ደምብ የሚከተለውን ይደነግጋል። (ከቤተክርስቲያኒቱ ውስጠ ደምብ ገጽ 19 የተወሰደ) "የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር የደብሩ እልቅና ሃላፊነት ሲሰጥም ሆነ ተጨማሪ ካህን ቢያስፈልግና ቢያስመጣ በደብዳቤ ለሐገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ያሳውቃል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ደብዳቤ ሥርዓተ ኖላዊ ተደርሦ ይሾማል። በደብሩ አለቃና በአስተዳደር መሀከል ችግር ቢፈጠር መተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ከሐገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ጋር በመመካከር አስተደደሩ እርምጃ ይወስዳል፤ ችግሩ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስና በአስተዳደሩ መካከል ከሆነ ግን ጉዳዩ ለሲኖዶሱ ተላልፎ የማህበረ ምዕመናኑ ጉባኤና ሲኖዶሱ የሚወክላችው አባላት በጋራ እንዲያዩት ይደረጋል።ሁለቱ የሚሰጡት ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል።- የጠቅላላ ማኀበረ ምእመናን ጉባኤ ስልጣን ምእራፍ 3 አንቀጽ 3 ማኀበረ ምእመናን አጥብቆ ሊገነዘባቸው የሚገባ የቤተክርስቲያናችን ሕገ ደንብ ክፍሎች የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት ምእራፍ 3 አንቀጽ 19 ቤተክርስቲያናችን እዚህ ቀውስ ላይ ለመውደቅ አስሩ የቦርድ አባላት የጣሱት የህገ ደንብ ክፍል ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ለምን/እንዴት ተባረሩ? አስሩ የቦርድ አባላት፥ ቀኖና ቤተክርስቲያን እና ህገ ደንባችንን ጥሰው፤ የጂርጂያ ቀጣሪ እና ተቀጣሪ ሕግን ጠቅሰው ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ነው ያባረሩዋቸው። ይህን የኮርፖሬሽን ህግ የተሐቀሙት አንድ ቀጣሪ ተቀጣሪ ያለ ምንም ምክንያት አንድን ሠራተኛ ማባረር ስለሚፈቅድ ብቻ ነው። ምእራፍ 3 አንቀጽ 11 ምእራፍ 3 አንቀጽ 5

Upload: lamtruc

Post on 08-Feb-2018

326 views

Category:

Documents


94 download

TRANSCRIPT

Page 1: to plan for peace and live by loving one another. ዘአትላንታ · PDF fileሥላሴም የለም”፣ “ፍትሀ ነገስት በሰለሥቱ ምዕት ነው የተጻፈው»፣

መልእክት ከብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ወደ ቀደመው ፍቅራችን እንመለስ!

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

«እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር

እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።»ኤፌ 4፤32

የተወደደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ !

ላለፉት 22 ዓመታት ክፉውንም ደጉንም አብረን ስናሳልፍ አደግን እንጂ አላነስንም ፣ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ሠራን እንጂ አላፈረስንም፣ ሰበሰብን እንጂ አልበተንም፣ ሞላን እንጂ አላጎደልንም፣ በሃይማኖት ጸናን እንጂ አልደከምንም። ስለሆነም ያሳለፍነውን የሰላም ጊዜ አስበን ጊዜ ያመጣውን ጸባችንን ትተን፤ተቻችለን ይቅር ተባብለን ወደ ቀደመው ፍቅራችን ተመልሰን አብረን እንኑር። በመለያየት እግዚአብሔር አይከበርም ። ይልቁንም እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ይቅር መባባላችንና መፋቀራችን ነው። “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”ማቴ 6፦14-15 ጌታ ዳግም ሲመጣ አንድ ሆነን እርስ በርሳችን ይቅር ተባብለን ተፋቅረን አንጂ ተለያይተን እንዳንገኝ፤ የቅዱሳን፣ የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎታቸው የመላእክት ጠባቂነታቸው የወላዲተ አምላክ ልመናዋ እና በረከቷ ከኛ ጋር ይሁን።

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን

«ከሁሉ አስቀድመን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን

እናመሰግናለን ።» (ሮሜ 1 ፥ 8)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳን ሐዋርያት

ተያይዞ የመጣ ዶግማ ፥ ቀኖና ፥ ሥርዓት ያላት ጥንታዊት ዓለም አቀፋዊት

መሆኗ ይታወቃል ። ሆኖም በዚህ ዘመን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ላለችው

ቤተ ክርስቲያን የጋራ ጠላት ሆነው በስፋት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የተሀድሶ

መናፍቃን መንጋ እና ማኀበረ ቅዱሳን የሚባል አፍራሽ ቡድን ነው።

ማኀበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎች መስለው

በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን በማኅበር አደራጅተው ለቤተ ክርስቲያኒቱ

ዶግማና ቀኖና ተገዢ ባለመሆን በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት ኃይል

ተደግፈው በግፍ ተሰድደው በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር የሚገኙ አባቶችን

፥ የወንጌል መምህራንን፥ ዘማርያንን የሐሰት ስም በመስጠት ፣ በተለይም

በኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎችና በኅትመት ውጤቶች በመታገዝ የስም ማጥፋት

ዘመቻውን ፥ በማን አለብኝነት የመከፋፈል ሥራ እየሠራ ይገኛል ። በተለይም

በዕድሜና በእውቀት እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቱን ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ

ዕድሜ ጠገብ አባቶቻችንን በመድፈር የማይገባ ስም በመስጠት ማኅበሩ

የሚፈጽመው ስም ማጥፋት ለምንወዳት ቤተክርስቲያን ታላቅ ሸክም

ሆኖቧቷል።

ስለሆነም እኛ የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ምእመናን የቅዱሳን

እና የጻድቃን አማላጅነትን፣ የመላእክት ተራዳኢነትን እንዲሁም የቅድስት

ድንግል ማርያምን ክብሯን እና አማላጅነት የማይቀበሉትን የተሃድሶ

መናፍቃንን እንቃወማለን።

ትምህርተ ሃይማኖትን እየበረዙ የሐሰት ትምህርት

በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የሚያስተምሩ የማኀበረ

ቅዱሳን አባላት «እኛ ክርስቲያን አይደለንም ፤ጠላት ያወጣልን ስም ነው» ፣

«አዳም የተጠመቀ ክርስቲያን ነበር»፣ “እመቤታችን ከሌለች እግዚአብሔርም

ሥላሴም የለም”፣ “ፍትሀ ነገስት በሰለሥቱ ምዕት ነው የተጻፈው»፣

የሀዋርያት አመክንዮ በሰለስቱ ምዕት ነው የተጻፈው” የሚሉና ሌሎችንም

የፈጠራ ትምህርቶች የሚያስተምሩ ሐሳውያን መምህራንን እንቃወማለን።

ቅዱሳን ቁርባን የሚቀርብበትን ወንጌል የሚሰበክበትን የተቀደሰውን አውደ

ምህረት (የምህረት አደባባይ) በማርከስ ላይ ጥላቻን የሚዘሩ እና

የሚሳደቡትን እናቃወማለን።

በቅዱሳን ጸሎት በአበው ትምህርት በሰማዕታት ደም ጸንታ

የኖረችው ኦርቶዶስሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንን የጽዋ ማኅበር

አይተካትም። በጎበዝ አለቆችም አትመራም። ቤተክርስቲያናችን የምትመራው

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሚመራው በህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው አራት

ነጥብ። የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችንን ረድኤት አማላጅነት ከኛ ጋር

ይሁን!

በዚህ እትም ላይ

መልእክት ከብጹእ አቡነ ያዕቆብ

ርዕሰ አንቀጽ

የሀሰት እና የክፍፍል አምራች ቅጥር

መምህራን አሁንም እንደጎረፉ ነው!

ብፁዓን አባቶቻችን ላይ ላነጣጠረው

ዘለፋ እና መሰረት የለሽ ትችት መልስ ተሰጠ!!

፪ኛው አውነቱን እንታደግ የገቢ

ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በከፍተኛ ስኬት ተጠናቀቀ

ከሳሹ ወንድሜ ግጥም

ሕገ ደምባችንን እወቁ

Message to Children

1ኛ ዓመት ቁጥር 1 መጋቢት 2009

ዘአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እውነትን በሚታደጉ ምዕመናን እየተዘጋጀ የሚቀርብ ዜና መፅሄት

ርዕሰ አንቀጽ

"እኛስ የሐይማኖት ለዋጮችን ስራቸውን እንጸየፋለን፤ መለየታቸውንም ሁሉ ሕግ መለወጣቸውንም። እነርሱ በእኛ ዘንድ የረከሱ ናቸውና።."

today is frustrating, we are however, wit-

nessing a bright light at the end of the test-

ing tunnel! The hard work is paying off and

the committee of elders that has been work-

ing hard to defend the truth about our cathe-

dral, protect our holy father and fight the

false and negative accusations directed

against the Holy Synod is already witness-

ing some good results. We also want you to

know that our success thus far, is achieved

not because it was easy. Instead, it was

because God helps the truth to flourish! As

it is written in the Psalm 119:160, “The

sum of your word is truth, and every one of

your righteous rules endures forever.” Yes,

the truth endures forever! Therefore, we are

proud of you in how you were passionate

about defending the truth side by side with

your parents and our holy father, Abune

Yaekob.

Again, your enthusiasm and pray-

ers are something that made all of us proud

and your all around contributions have been

Dear Our Children, Greetings from Awde Mihret!!!

Our Sealite Mihret Atlanta Saint Mary

Cathedral has been our spiritual home for the past

few decades. Our cathedral has indeed baptized,

educated and raised most of you and continues to

do so with our younger children that are following

your footsteps. Given such a reality, we the editors

of this newsletter as well as all your parents be-

lieve that the events that have been transpiring in

our church in the last seven or eight months were

too disturbing for you. We know that the situation

has affected you, our children than most of the

community at large. Of course, this is something

that made most of you react in your clear terms.

And we completely agree with you and accept your

frustration. Yes, our community in general and the

members of our cathedral in particular have let us

down in multiple occasions in the past. We, how-

ever, hope and work that this situation will soon be

history as God will prove the truth sooner rather

than later.

Dear Our Children: While the situation

that you have been enduring in such times like

really amazing. With that spirit, let’s invite you to

read and discuss the following two quotes from the

holy bible. These quotes teach us about peace, they

discuss the importance of forgiveness and moving

on and most of all, they teach us about why we need

to plan for peace and live by loving one another.

After all, we know that our savior, Jesus Christ

came to this world because he loves us and he want-

ed to inspire us to love one another. Please share

this two quotes with your friends and discuss them

amongst yourselves. We adore you and we pray that

our God’s protection and our Holy Mother Saint

Mary’s prayers and mediations protect you, the

children of Sealite Mihret Saint Marry of Atlanta!!

Quote one: “Proverbs 12: 20, Deceit is in the heart of those who devise evil, but those who plan peace have joy.”

Quote Two: “Galatians 5:22, But the fruit of the Spirit

is love, joy, peace, patience, kindness, goodness, faith-

fulness”

Awde Mihret’s Message to the Children of Sealite Mihret!!

ይህ የውስጥ ደምብ የሚከተለውን ይደነግጋል። (ከቤተክርስቲያኒቱ ውስጠ ደምብ ገጽ 19 የተወሰደ) "የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር የደብሩ እልቅና ሃላፊነት ሲሰጥም ሆነ ተጨማሪ ካህን ቢያስፈልግና ቢያስመጣ በደብዳቤ ለሐገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ያሳውቃል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ደብዳቤ ሥርዓተ ኖላዊ ተደርሦ ይሾማል። በደብሩ አለቃና በአስተዳደር መሀከል ችግር ቢፈጠር መተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ከሐገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ጋር በመመካከር አስተደደሩ እርምጃ ይወስዳል፤ ችግሩ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስና በአስተዳደሩ መካከል ከሆነ ግን ጉዳዩ ለሲኖዶሱ ተላልፎ የማህበረ ምዕመናኑ ጉባኤና ሲኖዶሱ የሚወክላችው አባላት በጋራ እንዲያዩት ይደረጋል።ሁለቱ የሚሰጡት

ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል።” -

የጠቅላላ ማኀበረ ምእመናን ጉባኤ ስልጣን ምእራፍ 3 አንቀጽ 3

ማኀበረ ምእመናን አጥብቆ ሊገነዘባቸው የሚገባ የቤተክርስቲያናችን ሕገ ደንብ ክፍሎች

የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት ምእራፍ 3 አንቀጽ 19

ቤተክርስቲያናችን እዚህ ቀውስ ላይ ለመውደቅ አስሩ የቦርድ አባላት የጣሱት የህገ ደንብ ክፍል

ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ለምን/እንዴት ተባረሩ? አስሩ የቦርድ አባላት፥ ቀኖና ቤተክርስቲያን እና ህገ ደንባችንን ጥሰው፤ የጂርጂያ ቀጣሪ እና ተቀጣሪ ሕግን ጠቅሰው ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ነው ያባረሩዋቸው። ይህን የኮርፖሬሽን ህግ የተሐቀሙት አንድ ቀጣሪ ተቀጣሪ ያለ ምንም ምክንያት አንድን ሠራተኛ ማባረር ስለሚፈቅድ ብቻ ነው።

ምእራፍ 3 አንቀጽ 11

ምእራፍ 3 አንቀጽ 5

Page 2: to plan for peace and live by loving one another. ዘአትላንታ · PDF fileሥላሴም የለም”፣ “ፍትሀ ነገስት በሰለሥቱ ምዕት ነው የተጻፈው»፣

ሲኖዶሳዊ የፖለቲካ ዓላማንና ፍቅረ ንዋይን

መሰረት ያደረገውን ህልማቸውን እውን

ለማድረግም በመሃከላቸው የሚገኙት እና

የነገሩዋቸውን ሁሉ የሚያሳተጋቡላቸው

ካህናት ከሚያሳተላልፉት አሳዛኝ እና እኩይ

የሆነ መልዕክት ባሻገር ቅጥር ከፋፋዮች የሆኑ

ሃሰት መስካሪወች ከየቦታው እያመጡ

ምዕመናንን የማጭበርበር ሥራቸውን

እያጧጧፉ ይገኛሉ። ብዙ ሊጠቀሱ የሚችሉ

ተመሳሳይ ባህርያትን የተላበሱ መምህራን

ቢሆኑም ሁለት ጉዳዮች ግን ከምንም በላይ

እንድነታቸውን ያጎሉላቸዋል። ፩ኛው እኒህ

መምህራን ሁሉም በሚያስተምሩበት

አውደምህረት ላይ የሃሰትን ሸማ አሳምረው

ተከናንበው የሚመጡ መሆናቸው ሲሆን፤

፪ኛው ደግሞ ሁሉም መምህራን ስደተኛው እና

ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስን በተመለከተ ያነገቡት

የሃሰት እና የጥላቻ መልዕክት ነው።

ውድ የዚህ ኒውስ ሌተር አንባቢ ሆይ፥

በአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት

ማርያም ካቴድራል የተከሰተው፤ በዓለም ላይ

ተሰራጭተው በሚኖሩ የተዋህዶ እምነት ተከታይ

የሆኑ ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያን ዘንድ

እንደትንግርት የተወራለትና በአሳዛኝነቱ በእዝነ

ህሊናችን የማይጠፋው የወርሃ ጥቅምቱ ትእይንት

መዘዝ ምዕመናንን ከፋፍሎ እንደቀጥለ ነው። ይህ

የቤተክርስትያናችን ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ

አባታችን አቡነ ያዕቆብን በፖሊስ በር በማዘጋት

ቤተክርስትያን ገብተው እንዳይቀድሱ፥

እንዳይባርኩን እና ብቻ ባጠቃላይ እንዳይሳተፉ

ለማገድ ያወጡት ስርዓተ ቤተክርስትያንን የጣሰ

ኢፍትሃዊና አምባገነናዊ ውሳኔያቸው አብዛኛውን

ምዕመናን በማሳዘኑ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ

ገጥሞት በህዝቡ ዕዝነ ህሊና ሳይወሰን በዓለማዊ

ፍርድ ቤት ሳይቀር ሽንፈትን እየተከናነበ ይገኛል።

ይህ ሸፍጥን፥ ተንኮልን፥ ከፋፋይ መንፈስን፤ ፀረ

እነዚህ የሃሰት መልዕክተኞች የሆኑ መምህራን ታድያ

የቤተክርስትያን የውስጥ ችግርን አስመልክቶ የምዕመናን የአንድነት ጉባዔ ከተፈጠረ ጠንካራ ሚና ይህ የአንድነት ሃይል ሰላምን ሊያመጣ እንደሚችል መረዳታቸው ግልፅ ስለሆነ ስጋት ቢያድርባቸው ምኑ ይደንቃል? በመሆኑም ይህ የምእመናንን መከፋፈል እንዳለ መቆየት አለበት፤ ይህ ካልሆነ የሃሰት ግብረ ሃይላችን ሽንፈትን መቅመሱ ሊቀጥል ይችላል ብለው የሃሰት መስካሪወችን መጋበዝን ቀጥለውበታል። ስለዚህ ዶክትሬቱ ሳይኖራቸው ራሳቸውን ዶክተር ብለው የሚጠሩ እና የሚያስጠሩትን የዳላሱን ቀሲስ አንዱዓለም እና የናሸቪሉ ቀሲስ ንዋይ፥ እንዲሁም የይሉኝታ እና የሃፍረት ዓይነሞራው የተገለጠት ህዝቅያስ የተሰኘውን ግለሰብ በተደጋጋሚ መጋበዛቸው ይታወቃል። ይህም ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ሁለተኛ ዙር የሀሰት ጉባዔያቸውን እንደገና ህዝቅያስን በመጋበዝ ጀምረዋል። ውድ የካቴድራሏ አባላት እንዲሁም የተዋህዶ ልጆች የሆናችሁ ምዕመናን የሃሰት ወሬወችን መስማት ብቻ ሳይሆን የሃሰት መስካሪውን ማንነት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነው።

የሀሰት እና የክፍፍል አምራች ቅጥር መምህራን አሁንም እንደጎረፉ ነው! ከሳሹ ወዳጄ

ስምህ ክርስቲያን ነው ዘርህ ክርስትና ህይወትህ ፍቅር ነው ስራህ ትህትና ንጉሥህ ክርስቶስ ሰማዩን ያፀና አንተን በመፍጠሩ ሰይጣንን ያስቀና።

የተዋህዶ ልጅ እምነትህ ኦርቶዶክስ የሃይማኖት አጥርህ ቅዱሱ ሲኖዶስ በቅዱስ ፈቃድ መሪህ መንፈስ ቅዱስ።

ችኩል ትጉህ መስሎ ታጋሹ ሰው ሰነፍ ተው አይሉትም ወይ ልጅ አባቱን ሲዘልፍ ያለመሪ አይሆንም ቅኔ እንኳን ሱዘረፍ ከሳሹ ወዳጀ እባክህ አትለፍልፍ።

ፅድቅ በእምነት እንጅ መስቀል በመሸከም በጮሌነት ቢሆን ነግር በመከርከም ሰዎችን በመክሰስ አቁስሎ በማከም ሳጥናኤል ነበረ የመንግሥቱ ወራሽ ያለምንም ድካም።

አዳምን ከገነት፤ ሄዋንን ከገነት፣ በምክር ሲያስወጣ የቃኤልን ቀኝ እጅ ድንጋይ አስጨብጦ አቤልን ሲቀጣ ፈጣሪ ነኝ ብሎ መላዕክት ሲያስቆጣ ተሃድሶ እያለ ዛሬ በሶች አፍ ተመልሶ መጣ።

ፍፃሜው ምን ሆነ በመሰሪነቱ? እዮብን በመክሰስ እስኪያልቅ ትዕግስቱ አይሁድን ሲያባብል ለስቅለተ ሞቱ ከሶስት ቀን በኋላ ላይቀር መረታቱ ከሳሹ ወዳጀ አትድከም በከንቱ ፍቅር ስለሆነ የሰው ልጅ ጉልበቱ ያንተን ነብስ ጠብቅ እሱ አለ ለቤቱ።

ዝቅ በል ወዳጀ ከራስ ላይ አትዉጣ የአቡኑን ቆብ ቀደህ በነገር አራጣ መሸሸጊያ ጠፋ ሰው ሁሉ መላ አጣ። ከፍተኛው ስልጣን የሰው ልጅ ስጦታ ራስን መግዛት ነው በወንጌል እይታ።

በሰማይ መነፀር በቃሉ መርምሮ ሰላምን ማግኘት ነው እምነትን ጨምሮ ፅድቅ መቀበል ነው በሰጡት ተሰፍሮ።

እግዜር አይፈልግም የሚሳደብለት በርከክ....ጎንበስ ብሎ እግር ለሚያጥብለት ለክርስቲያን ልጁ ታይቷል ሲሞትለት።

ከሳሹ ወዳጀ ሰዎችን ተዉና እሱን ተከተለው እንደ ፈሪሳዉያን ዛሬም አትስቀለው። ከሰማየ ሰማይ መሬት የወረደ

በከብቶች ማደሪያ በረት ተወለደ፤ ግብፅ ተሰደደ አህያ ጋለበ በእግሩ ተራመደ ፅድቅን ለማስተማር በሰዉኛ ሄደ እዉነት ተናገረ.... ገዳዩን ማለደ...በፅድቅ ፈረደ ተቸንፎ...ሙቶ ማዳኑን ወደደ።

ፅድቅ እንዴት ይገኛል? ወዳጀ ከሳሹ? ፊትን አጨማዶ! አንገትን አንጋዶ! ከልብ እየዋሹ? ደግሞ ክህነት ይዞ! አዉደ ምህረቱ ላይ እስከነ ጭራሹ? እግዚኦ መሃረነ! እግዚአብሔር ታጋሹ!!!!

መምህራን የወንጌል ትምህርት ባበረከቱበት እና፥

የሰላምን መለከት ባሰሙበት አውደምህረት ላይ ይህ

የሀሰት ዝናብ መዝነብ ጀመረ። ይህ ወጣት ቄስም

አለ፤ “ቤተክርስትያን ላይ አደጋ ተጋርጧል!! ይህ

አደጋ ደግሞ እንደድሮው በሩቁ እየሰማን በሩቅ

እንመለከተው የነበረው በተሃድሶወች የተጋረጠብን

ችግር ሳይሆን ካጠገባችን ባሉ እና

ከቤተክርስትያናችን ውስጥ በማይጠፉ ሰወች

የተጋረጠብን ሃይማኖታችን ላይ አደጋ

እንዲያንዣብብ ያደረገ ክስተት መሆኑ ሊታወቅ

ይገባል” ሲል ተናገረ። ወጣቱ ቄስ ቀጠለ። የብፁዓን

አባቶችችን ምስሎች በፕሮጀክቶር በማሳየትም

ታላቁን አባት ብፁዕ አቡነ መልከፀዴቅን ሳይቀር

በተሃድሶነት ከሰሰ። በዚች ሰዓት ላይ

ለቤተክርስትያኗ የለፉትን እና እዚህ ያደረሷትን

አባት መዝለፍ በተለይም የሳቸውን ቡራኬ እና

ምርቃት ሊሻማ ከሚገባው አንድ ወጣት ቄስ

አንደበት መውጣቱ እጅግ አሳዛኝ ያደርገዋል።

ይህንን ትምህርት ሳይሆን የጥላቻ ንግግር (hate speech) ልንለው የምንችል ክስተት ግን

ሰምተው እውነታው ለቄስ ወይም “ውስጡ ለቄስ”

ነው ብለው ታዝበው የሚያልፉ ይኖራሉ። ከዛም

አልፎ ደግሞ በዋናነት በተዋህዶ እምነታችን

ሲቀጥልም ደግሞ በኛዋ የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት

ቅድስት ማርያም ካቴድራል የውስጥ ችግር እንዲህ

የወረደ አቋም ባላቸውና የመንፈሳዊ አባትነት

ጊዜው ዕለተ ሰንበት ጠዋት ነው (እኤአ

02/12/2017) በአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት

ማርያም ካቴድራል ቅዳሴውን ለማስቀደስ፥ በፀሎት

ከአምላካቸው ቅዱስ እግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት

ከዚያም አልፎ ከአንድ ሳምንት በሗላ የሚጀመረውን

ታላቁን የአብይ ፆም አስመልክቶ መልካም ትምህርት

ከምክር ጋር ለመቀበል ምዕመናን ተስፋ አድርገው

ተገኝተዋል። የዕለቱ የቅዳሴ መርሃ ግብር

እንደተጠናቀቀም የወንጌል ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ ላይ

ደረሰና የሁሉም ትኩረት ወደ መምህሩ ሆነ።። ወንጌልን

የተጠሙ፤ የእግዜርን ቃል የናፈቁ ምዕመናን ግን

ያጋጥማቸው ትዕይንት ሌላ ነበር። በተግባር የተመለከቱት

እና የታዘቡት ግን አንባቢ እንደሚገምተው እኛም ከላይ

እንደጠቀስነው ሳይሆን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ

በአሳፋሪነቱ ወደር የማይገኝለት እና አሳዛኝ የሆነ

የቤተክርስትያንን ስም እና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር

ነበር።

ነገሩ እንዲህ ነው። ህዝበ ክርስትያኑን ለረጅም ዘመናት

ሊያገለግል የሚገባው፤ ከስህተት በመማር የቅዱስ

ወንጌልን መልዕክቶች ሳያዛንፍ በማስተማር ምዕመናንን

ሊያንፅ የሚገባው፤ እኩያወቹ ለሚሆኑ ወጣቶች ምሳሌ

በመሆን ወደ ተዋህዶ ክርስትና እምነታቸው ሊያቀርባቸው

የሚገባው አንድ ወጣት ቄስ እጅግ በሚያሳፍር ብሎም

ማንንም የክርስቶስ ልጅ ሃዘን ውስጥ ሊከት በሚችል

ሁኔታ ብፁዓን አባቶቻችን መዝለፍን፥ ማዋረድን፥ ቃላት

በመሰነጣጠቅ መዋሸትን ተያያዘው። ብዙ ታላላቅ

ሳይሆን የግል እና የቡድን አመለካከታቸውን የፍቅር እና

የእውቀት ሊሆን በሚገባ አውደ ምህረት ላይ ሲያንፀባርቁ

ሲታዩ ፍፁም እሳዛኝ ያደርገዋል።

ይህን የሚመስል አሳዛኝ የውሽት ክስ

በቤተክርስትያን እና ብፁዓን አባቶቻችን ላይ ሲታወጅ

የመጀመርያ ሆኖና ፍፁም አስደንቆን አይደለም። ሆኖም

ግን ይህ የሀሰት ውንጀላ በስም ማጥፋት ክስ ተመስርቶ

በዛው በለመዱት የዓለማዊ ፍርድ ቤት ሊታይ ቢችልም

ለጊዜው ግን ህዝበ ክርስትያኑ እውነታውን ጠንቅቆ ይረዳ

ዘንድ፤ ተረድቶም ለሌሎች ወንድሞች እና እህቶች ያስረዳ

ዘንድ ግድ ይላል። ይህን ለማድረግ እና ተገቢውን

ትምህርት በመስጠት የቀረበውን የውንጀላ የሀስት ክስ

መሰረተ ቢስነት ደግሞ አግባብ ባለው ሁኔታ ለምዕመናን

የሚያስረዱ አባቶች እና ምዕመናን ደግሞ

ቤተክርስትያናችን ውስጥ ሞልተው ተርፈዋል። እነዚህ

ንፁህ አባቶች ታድያ ፍፁም በተንኮለኞች ሲገለሉ እና

መከራን ሲቀበሉ የቆዩ ሊቃውንት ናቸው። ለዚህ በእነ አቶ

አባተ እና መሰሎቹ የተደገሰውና የተቀነባበረው እንዲሁም

በዚህ ወጣት ቄስ እንደበት የተነገረውን ይህን የሃሰት ክስ

መጋቤ ሃዲስ መምህር ልዑለ ቃል አካሉ

በቤተክርስትያናችን ተገኝተው ይህንን አግባብ ያለው

መልስ ሰጥተዋል። እኛም ይህን ልዩ ትምህርታቸውን

በዩቱብ (YouTube) ቪዲዮዎች አማካኝነት መልስ

ያገኙላቸው ዘንድ eneweyay.com ከሚባለው

ድህረ ገጽ (website) እንዲሄዱ እንጋብዞታለን።

ብፁዓን አባቶቻችን ላይ ላነጣጠረው ዘለፋ እና መሰረት የለሽ ትችት መልስ ተሰጠ!!

በሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል

የተከሰተውን አሳዛኝ ቀውስ እና የብፁእ አባታችን አቡነ

ያዕቆብን ህገወጥ እገዳ አልፎም ብጹእነታቸው እና ስምንት

የቦርድ አባላትን በአለማዊ ፍርድ ቤት የተመሰረተባቸውን

ህገ ወጥ ክስ ለመከላከል ሲባል እንዲሁም ምዕመናኑ

እውነቱን ይረዱ እና የቤተ ክርስታያናችንን ትውፊት

የመጠበቅ አደራ ይወጡ ዘንድ እንዲሰራ የተቋቋመው

ግብረ ሃይል መልካም የተሰኙ እና ውጤታማ ጉዞዎችን

እያደረገ ይገኛል። የመጀመርያውን የገቢ ማሰባሰቢያ

ፕሮግራም በከፍተኛ ስኬት ያከናወነው ግብረሃይል

የተጠናከረ እንቅስቃሴውን ቀጥሎበት ሁለተኛውም የገቢ

ማሰባሰቢያ በዚሁ የስኬት መንገድ እንዲቀጥል ያላሰለሰ

ጥረት ተደርጓል። ውድ ወንድሞች እና እህቶች ሆይ፥

የእናንተ ከልብ የመነጨ እና የቤተክርስትያናችንን አደራ

የመጠበቅን እና እውነትን የመታደግ አገልግሎታችንን

ለመፈጸም በስኬት ይታጀብ ዘንድ ያሳያችሁት ልግስና

ታላቅ አርአያነት በተግባር ታይቷል። በቤተክርስቲያን የህግ

ሙያ በአገር አቀፍ ደረጃ የተመሰከረላቸውን እና

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ህግጋት

ጠንቅቀው የሚያውቁ የህግ ባለሙያዎችን

በመቅጠርም አባታችን ብፁእ አቡነ ያዕቆብ

በመኖሪያ ቤታቸው ቆይተው ካቴድራላችን ውስጥ

እንዲያገለግሉ እና እንዲባርኩን ምዕመናንም

ቤተክርስትያናችን ውስጥ በጠዋት ተገኝተውና

አስቀድሰው ልጆቻቸውን አቁርበውና ቆረበው ቅዳሴ

ጸበሉን ጠጥተው ከበረከቱ የሚሳተፉበትን መንገድ

እንዲመቻች እግዚአብሔር ረድቶናል።እግዚአብሔር

ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? (ሮሜ 8-31)

የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች ሆይ፥ ይህ ሁሉ

ስኬት ታድያ ፍፁም ሃያል የሆነው አምላክ ቅዱስ እግዚአብሄር ፈቃድ ነውና በፀሎት ተግታችሁ ፤ ከዕለት ጉርሳችሁ ቀንሳችሁ እውነት የሆነውን መንገድ በጋራ እንድታደግ ዘንድ ላሳያችሁት መንፈሳዊ ወኔ በአባቶቻችንን የቅዱሳን አምላክ ስም ምስጋናን አናቀርባለን።

፪ኛው “አውነቱን እንታደግ” የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በከፍተኛ ስኬት ተጠናቀቀ

የቅዱስ ሲኖዶስ የኀዘን መግለጫ