ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “...

80
Chris Oyakhilome ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Upload: others

Post on 19-Oct-2020

45 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Chris Oyakhilome

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Page 2: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

All rights reserved under International Copyright Law. Contents and/or cover may not be reproduced in whole or in part in any form without the express written permission of LoveWorld Publishing.

www.rhapsodyofrealities.orgemail: [email protected]

NIGERIA:Plot 97, Durumi District, Abuja, Nigeria.

51/53 Kudirat Abiola Way, OregunP.O. Box 13563 Ikeja, LagosTel.: 01-8888186

UNITED KINGDOM: Unit C2, Thames View Business Centre, Barlow Way Rainham-Essex, RM13 8BT. Tel.: +44 (0)1708 556 604 +44 (0)08001310604

CANADA:Christ Embassy Int’l Office, 4101 Steeles Ave. West. Suite 201. Toronto M3NIV7. VaughanTel.:+1 647-341-9091

USA:Christ Embassy Houston,8623 Hemlock Hill DriveHouston, Texas. 77083 Tel.: +1-281-759-5111

SOUTH AFRICA:303 Pretoria AvenueCnr. Harley and Braam Fischer, Randburg, Gauteng 2194South Africa.Tel.:+27 11 326 0971

KuKÖ S[Í“ }ÚT] KT²´:

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...ዕለታዊ የመንፈሳዊ ጥናት መጽሃፍISSN 1596-6984ነሐሴ 2011 editionCopyright © 2011 by LoveWorld Publishing

u}K¾ G<’@� “M}Ökc ue}k` G<KU Øpf‹ ŸSÅu—¨< ¾SêNõ pÆe ¾}¨cÆ “†¨<::

Page 3: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

የ 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ እርምጃና እድገት ለማሳደግ በተለየና ባማረ ሁኔታ ለተሻለ ነገር በሚያነሳሳ

መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመረጃና በመገለጥ ከተሞሉ ፁሁፎች በተጨማሪ የዚህ ወር ዕትም በየዕለቱ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ መገኘት ለማወቅ በምታደርገው ጉዞ እምነትህን በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንድታሳድግ በተመቻቸ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ቀርቦልኃል፡፡ በየቀኑ ባጠናኽው፣ ባሰላሰልከውና በአፍህ በተናገርከው ወይም ደግሞ ባወጅከው መጠን እየታደስክ ትሄዳለህ፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ በወሰድን ጊዜ የእግዚአብሔርን የክብር መገኘትና ድል ዓመቱን በሙሉ እንዲደሰቱበት ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በጣም እንወዳችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

- ይህንን መነቃቅያ እንዴት በበለጠ መጠቀም ይቻላል -

መግቢያ

-ፓስተር ክሪስና ኦያኪሎሜ

ይህን ጽሁፍ አንብብና በጥንቃቄ አሰላስል፡፡ ፀሎቶቹንና የአፍ ምስክርነት ቃሉን

በየቀኑ ለራስህ ድምጽህን ጎላ አድርገህ መናገርህ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወትህ

እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በአዲሱ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ

ቅዱስ ጥናት በሚገባ አንብቡ

የዕለታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን በጠዋትና በማታ ከፍለህ ማንበብ ትችላለህ

መነቃቅያውን በጸሎት ተጠቀሙበትና በእያንዳንዱ ወራት ያላችሁን ግብ ጻፉና

ከአንዱ ግብ ወደ ሌላው ግብ ያላችሁን ስኬት በሚገባ ለኩ

Page 4: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

eU

݃^h

eM¡

¾ÓM S[Í

Page 5: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

www.rhapsodyofrealities.org

...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Page 6: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

በሮሜ 6:14 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ “ኃጢአት አይገዛችሁምና. . . “ይላል:: የኃጢያት ችግር ተወግዶአል:: በብሉይ ኪዳን

ነቢዩ ኢሳይያስ “ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል” እያለ አለቀሰ (ኢሳይያስ 59:2):: ነገር ግን በክርስቶስ የመታደግ ስራ ከዚህ በኃላ እንደዚህ አይሆንም፤ እርሱ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለ ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር:: ከክርስቶስ የተነሳ እግዚአብሔር ኃጢያትን አይቆጥርባችሁም፥ ኃጢያታችን በሙሉ በእርሱ ላይ ሆኗል:: ዛሬ ማንም ስለኃጢያቱ ቅጣትን ሊቀበል አይገባም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ለኃጢያታችን ሙሉ የሆነን ክፍያ አስቀድሞ ከፍሎአል:: ስለ እኛ ተፈረደበት (ኢሳይያስ 53:5)::

ለእኛ ከከፈለው ታላቅ መስዋትነት ባሻገር፣ እርሱ በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ሰላም እንዲሆን እና እንዲጸና አደረገ፤ እርሱ የሰውን ዘር ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ:: ሰው በአዳም አለመታዘዝ ከእግዚአብሔር ህይወት ርቆ ነበር፤ ነገር ግን ኢየሱስ በስጋው ሞት ከአብ ጋር አስታረቀን፡፡

ቆላስይስ 1:21-22 እንዲህ ይላል፡- “እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።” የዚህ ጥቅስ የመጀመሪያው ክፍል የማስታረቁን ምክንያት በግልጽ ያሳያል “እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ. . . “ አሁን እናንተ ያለምንም

ክርስቶስ አስታራቂያችን

አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። (1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5)

ሐሙስ 1

Page 7: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 6:1-14 & መዝሙረ ዳዊት 56-59

የሉቃስ ወንጌል 12:22-34 & መጽሀፈ መሳፍንት 7

ሮሜ 5:10; ሮሜ 8:31-34; ዕብራውያን 7:25

የበታችነት፥ የጥፋተኝነት ወይም የኩነኔ ስሜት፣ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ለመኖር ብቁ ናችሁ፤ እናንተ በጸጋው ጸድቃችሁ ከማንኛውም ክስ ነጻ ናችሁ:: እግዚአብሔር ይባረክ!

ወንጌል ይህ ነው! በአብ ፊት ቅዱስ፥ ነጻ እና ጻድቅ ሆናችሁ የመታየታችሁ ምክንያት እናንተ የሰራችሁት ወይም ያልሰራችሁት ነገር አይደለም፤ ምክንያቱ ኢየሱስ የሰራው ስራ ነው:: የእርሱ ሞት፥ መቀበር እና መነሳት ከአብ ጋር እንድትታረቁ አደረጋችሁ፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ወደ አንድነት እና ህብረት አደረሳችሁ:: ሃሌሉያ!

እኔ የአብን ጽድቅ እያሳየሁ የእርሱን ክብር እና ልቀት ለመግለጥ ተጠርቻለሁ:: እርሱ ብርሃን እንደሆነ እኔም በቃሉ እና በእርሱ ጽድቅ ብርሃን እኖራለሁ፣ እመላለሳለሁም:: ስለዚህ እኔ ከበሽታ፥ ከህመም፥ ከድህነት፥ ከጨለማ እና ከዚህ ዓለም ሁኔታ የበላይ በመሆን በዚህ ህይወት እገዛለሁ:: ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

የእምነት አዋጅ

Page 8: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

አንዳንድ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ እንዳሉ አይገነዘቡም:: በዓለም እንዳሉ እንዲሁ ይመላለሳሉ:: እነርሱ

ተግባር እና ድርጊታቸው፥ ሀሳባቸው፥ ንግግራቸው እና ምላሻቸው በዓለም ላይ እንዳሉ ሰዎች ነው:: በእምነት ከመመላለስ በስሜታቸው ይራመዳሉ፤ ህይወታቸውን የሚመሩት በአካላቸው በሚመለከቱት ብቻ ነው:: ነገር ግን የክርስትና ህይወት ይህ አይደለም፤ የምንኖረው እምነት መመሪያችን በሆነ በመንፈሳዊ መንግስት ውስጥ ነው::

እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም በላይ ሆናችሁ እንድትኖሩ ይጠብቃል፤ ምክንያቱም እናንተ ከዚህ ዓለም አይደላችሁም:: ኢየሱስ በዮሐንስ 15:19 ላይ እንዲህ አለ ፡-”ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ . . .”፡፡ መንፈስ በሐዋሪያው ጳውሎስ በኩል እንዲህ ማለቱ አያስገርምም፡- “በክርስቶስ እና በመንፈስ እየኖራችሁ ለምን እስካሁን በዓለም እንዳላችሁ ስለ ምን ትኖራላችሁ?” ቀጥሎም በገላትያ 5:25 ላይ በመንፈስ እንድንመላለስ ይነግረናል፤ ምክንያቱም እኛ የምንኖረው በመንፈስ ነው::

አሁን ዳግም ከተወለዳችሁ በተመሳሳይ ጊዜ በሁለት ዓለም ውስጥ ትኖራላችሁ - ግዑዙ ዓለም እና መንፈሳዊው ዓለም ውስጥ:: ለተወለዳችሁበትን እና ለምትሰሩበትን መንፈሳዊ ዓለም እውቅና ልትሰጡ ይገባል:: እናንተ የሰማያዊ ዜጋ ናችሁ፤ ስለዚህ በምድር ላይ በሰማያዊ ሕይወት ኑሩ:: አስተሳሰባችሁ፥ ለሁኔታዎች የምትሰጡት ምላሽ እና ለህይወት ያላችሁ አመለካከት ከሰማያዊ አስተሳሰብ፥ ከቃሉ እይታ አንጻር መሆን

ከዚህ ዓለም ያልሆነ

ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥

አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ። (ቆላስይስ 2:20)

አርብ 2

Page 9: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 6:15-7:1-6 & መዝሙረ ዳዊት 60-63

የሉቃስ ወንጌል 12:35-48 & መጽሀፈ መሳፍንት 8

2 ኛ ቆሮንጦስ 5:7; ቆላስያስ 1:12-13; ቆላስያስ 3:1-3

አለበት:: አስተሳሰባችሁ ከተፈጥሮአዊው ሰው የተለየ መሆን መቻል አለበት::እናንተ የምትኖሩት በመንፈሳዊ መንግስት በመንፈሳዊ መርሆዎች

ነው:: ይህ መረዳት ሊኖራችሁ ይገባል:: ይህንን ስትረዱ ችግር እና ተግዳሮት ሲገጥማችሁ ትደሰታላችሁ፣ ምክንያቱም ነገሩ ለመልካም እንደሚለወጥ እርግጠኞች ናችሁ:: በመንግስታችን ማሸነፍ እና ከክብር ወደ ክብር ማደግ ብቻ የምናውቀውም ለዚህ ነው:: ይህን ግዑዝ ዓለም በሰማያዊ መንግስት መርሆዎች እንገዛዋለን:: ሃሌሉያ!

ከጨለማው መንግስት ወደ ልጁ የፍቅር መንግስት ላፈለሰኝ እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን:: በእርሱ እኖራለሁ፥ እመላለሳለሁ፤ እንዲሁም ማንነቴ በእርሱ ነው! እርሱ ስፍራዬ ነው፤ - የእረፍት፥ የጤንነት፥ የሀብት፥ የደህነት እና ብልጽግና ያለው የሰላም ስፍራዬ ነው:: በምኖርበት በዓለሜ ላይ በከበረ በእግዚአብሔር መንግስት ተጽዕኖ አደርጋለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

የእምነት አዋጅ

Page 10: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

በኤፌሶን 5:1 ላይ እንደ ተወደዱ ልጆች “እግዚአብሔርን እንድንከተል” ይነግረናል:: የእርሱ ህይወት እና ተፈጥሮ በእኛ

ውስጥ ስላለ ይህ ይቻላል:: ስለዚህ ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ እንደነበረው ልክ እንደ እርሱ ማውራት፥ መውደድ እናም በፍጹም ድል እና መግዛት መመላለስ እንችላለን:: እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና (ዮሐንስ 4:17)።

ዳግም ስትወለዱ ሁለተኛው አዳም ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዳችኋል፤ እናንተ ከእርሱ ጽድቅ እና እውነተኛ ቅድስና ተወልዳችኋል:: 2ኛ ቆሮንቶስ 5:17 ላይ “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው . . .” ይላል:: ይህ አዲስ ፍጥረት ከእግዚአብሔር መልክ ተወልዶአል (ቆላስይስ 3:10):: ስለዚህ እናንተ ከእግዚአብሔር የተፈጠራችሁ አዲስ ፍጥረት ናችሁ:: ለዚህ ነው ክርስቶስን መምሰል የምትችሉት:: ምንም ያህል አንድን ዝንጀሮ ወይም የዝንጀሮ ዘር እንደ ሰው እንዲሆን ብታሰለጥኑት ሰው ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ዝንጀሮ የሰው ተፈጥሮ የለውም:: ሰው ለመሆን ሰው ሆናችሁ መፈጠር አለባችሁ::

ዳግም ሳይወለዱ አጋንንትን በማስወጣት ጳውሎስን ለመምሰል የሞከሩትን ሰባቱ የአስቄዋ ልጆች አስታውሱ:: የክርስቶስ ሕይወት በእነርሱ ውስጥ አልነበረም:: መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “. . .ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም” (የሐዋርያት ሥራ 19:13-16)።

በኢየሱስ ስም አጋንንትን ለማስወጣት መብት እና ስልጣን ያላቸው ዳግም የተወለዱ እና የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ያላቸው ናቸው:: ኢየሱስ አጋንትን አወጣ:: በእርሱ ስም ለእኛ ስልጣንን ሰጠን:: በዮሐንስ 14:12 ላይ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል” አለ::

በተጨማሪም በፍቅር በመመላለስ እርሱን ልትመስሉ ይገባል:: ኤፌሶን

እርሱን በመምሰል

ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። (ኤፌሶን 4:24)

ቅዳሜ 3

Page 11: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 7:7-25 & መዝሙረ ዳዊት 64-67

የሉቃስ ወንጌል 12:49-59 & መጽሀፈ መሳፍንት 9

2 ኛ ቆሮንጦስ 5:17; ኤፌሶን 5:1; 1 የዮሐንስ ወንጌል 4:17

5: 2 እንዲህ ይላል፡- “ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።”

የእናንተ ፍቅር የሚገባቸውም የማይገባቸውም ሰዎች ቢሆኑ እንኳን፣ ዓለማችሁ ውስጥ ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ ፍቅርን አሳዩ:: ያንን ማድረግ የሰማይ አባታችሁን መምሰል ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ . . . እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና” (ማቴዎስ 5:45)። ሃሌሉያ!

ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ ከመለኮታዊ ባህሪይ ተካፋይ እንድሆን ስላደረግከኝ አመሰግንሃለሁ:: መለኮታዊ ባህሪዬ ነገሮችን እንዳንተ እንዳደርግ፥ እንዳንተ እንዳወራ እና እንዳንተ እንዳስብ ያደርገኛል፤ በእኔ ውስጥ የኢየሱስ ውበት እና ርህራሄ ይታያል፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን።

ጸሎት

Page 12: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

አንዳንድ ሰዎች መልካም ያልሆነን ልማድ ማቆም ይከብዳቸዋል፤ ለምሳሌ ውሸትን መናገር:: ነገር ግን ዳግም ስትወለዱ እናንተ

የተለየ ተፈጥሮ አላችሁ፤ እናንተ በኃጢያት ወይም በሰይጣን ስር አይደላችሁም፤ ምክንያቱም ከሞት እና ከኃጢያት ሕግ ነጻ ተደርጋችኋል:: ሰዎችን ኃጢያት እንዲሰሩ የሚያደርጋቸው ነገር ከሕይወታችሁ ተወግዶአል::

ስለዚህ መጥፎ ልምምድን “አይ” ማለት ትችላላችሁ፤ እናም ያ ማብቂያ ይሆናል:: የሚያስፈልገው ነገር የእናንተ ውሳኔ እና ከቃሉ ጋር የመጣበቅ ባህሪይ ብቻ ነው:: ቃሉ “ሐሰት መናገርን አስወግዱ”፤ ስለዚህ ለእራሳችሁ እንዲህ በሉ፡- “ሁልጊዜ በማንኛውም ሁኔታ እኔ እውነትን ብቻ እናገራለሁ!”

ስህተት እንደሆነ የምታውቁትና ግን የምታደርጉት ነገር ቢኖር ማቆም ትችላላችሁ፤ አእምሮአችሁን ማሳመን ብቻ ይጠበቅባችኋል:: ሮሜ 6:14 እንዲህ ያላል፡- “ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።” ኃጢያት ከእንግዲህ አይገዛችሁም፤ ከዚህ በኃላ የማትፈልጉትን ነገር እንድታደርጉ ሊያስደርጋችሁ አይችልም፤ ምክንያቱም እናንተ የእግዚአብሔር ባህሪይ ያላችሁ አዲስ ፍጥረት ናችሁ::

በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ጌታ ከሚጠላቸው ነገሮች ውስጥ በሐሰት መናገር እና ሐሰተኛ ምስክር መሆን ተጠቅሰዋል:: ስለዚህ ሐሰት መናገርን አስወግዱ፤ ሐሰት መናገር በክርስቶስ ያላችሁ አዲሱ ተፈጥሮ አካል አይደለም:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና

ሁልጊዜ እውነቱን ተናገሩ

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች ትዕቢተኛ ዓይን፥

ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት

የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ። (ምሳሌ 6:16-19)

እሁድ 4

Page 13: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 8:1-17 & መዝሙረ ዳዊት 68-69

የሉቃስ ወንጌል 13:1-9 & መጽሀፈ መሳፍንት 10

ትንቢተ ዘካርያስ 8:16; ቆላስያስ 3:8-10; ኤፌሶን 4:25

ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ” (ኤፌሶን 4:24)። አሁን በክርስቶስ ሆናችሁ አዲሱን ሰው ለብሳችኋል፤ እናንተ የተለያችሁ ናችሁ:: እንደዛው ተመላለሱ:: ሁልጊዜ እውነትን ተናገሩ::

ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ በክርስቶስ ስለሰጠኸኝ አዲስ ሕይወት አመሰግናለሁ:: በጽድቅ እና በፍጹም ቅድስና የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ለብሻለሁ:: የስጋን ስራ አስወግጃለሁ፤ እናም በእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ብቻ እኖራለሁ:: በአዲሱ ሕይወቴ ባለው ክብር እና የክርስቶስ ተፈጥሮ ወደ መንፈስ ነጻነት ስላመጣኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 14: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ሮሜ 8:16-17 የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን፣ የእግዚአብሔር ወራሾች እና ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች

እንደሆንን ያሳየናል:: የመክፈቻ ጥቅሳችንን በድጋሚ አንብቡ፤ እንዲህ ይላል፡- “እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ”፡፡ በደስታ ሳትጮሁ ይህንን ማንበብ አትችሉም፤ ምክንያቱም ይህ ማለት ዓለም ሁሉ የእናንተ ነው:: እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ለአብርሃም እና ለዘሩ ሰጠ:: ያ ዘር ክርስቶስ ነው፤ እናም እናንተ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ ስለዚህም እንደ ተስፋው ቃል ወራሾች ናችሁ::

መጽሐፍ ቅዱስ በ(ኤፌሶን 4:28) ላይ “የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም”” ለምን እንዳለ የበለጠ መረዳት ትችላላችሁ:: ዓለም ሁሉ የእናንተ ከሆነ እንዴት ልትሰርቁ ትችላላችሁ? ለመሬት ወይም ለይዞታ ከሚጣሉት መሃል አትሁኑ፥ ዓለም የእናንተ ነው! የዚህም ማረጋገጫው የእግዚአብሔር ቃል ነው::

1ኛ ቆሮንቶስ 3:21-23 እንዲህ ይላል፡- “. . . ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው”:: ይህ መረዳት ይኑራችሁ:: በተደጋጋሚም በሙሉ ልብ “ዓለም የእኔ ናት፥ ሁሉ ነገር የእኔ ነው!” ብላችሁ አውጁ:: ይህን የሚያሳይ ሕጋዊ መረጃ አላችሁ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው:: ስለዚህ ማንም ቢያስቸግራችሁ ወይም ቢያሾፍባችሁ ለውጥ አያመጣም፥ አሁንም እናንተ የዓለም ባለቤት ናችሁ::

በእርግጥ በመትረፍረፍ ውስጥ ትኖራላችሁ:: “ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም

ዓለም የእናንተ ነው

እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ (ገላትያ 3:29)።

ሰኞ 5

Page 15: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 8:18-39 & መዝሙረ ዳዊት 70-73

የሉቃስ ወንጌል 13:10-21 & መጽሀፈ መሳፍንት 11

መዝሙረ ዳዊት 23:1; መዝሙረ ዳዊት 24:1; 2 ኛ ጴጥሮስ 1:3-4

የእኔ ነው. . . “(ሐጌ 2:8) “የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና።” (መዝሙር 50:10) ብሎ ከተናገረው ለእናንተ የተሰጠ ውርስ አለ:: እርሱ የዓለም ባለቤት ነው፤ እናንተም የእርሱ ወራሾች ናችሁ::

በዚህ ዓለም ያለው ሀብት ሁሉ፣ የከበሩ ድንጋዮች፥ ማዕድናት፥ ዘይት እና ሰዎች የእኛ ናቸው ብለው የሚያምኑአቸው ነገሮች ሁሉ የጌታ ናቸው፥ በእርሱ እናንተ አብሮ ወራሽ ናችሁ:: ስለዚህ ሀብታችሁ ገደብ የለሽ፥ የማይገመት እና የማይቆጠር ነው:: በየቀኑ ሀብታም እንደሆናችሁ እና ከመጠን በላይ እንደተባረካችሁ አውጁ:: ሃሌሉያ!

ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሽ መሆን እንዴት ታላቅ በረከት ነው! ዓለም የእኔ ነው:: ምንም ነገር አላጣም፤ ምክንያቱም አንተ እረኛዬ ነህ:: ሀብቴ ገደብ የሌለው፥ የማይገመት እና የማይቆጠር ነው፤ ብልጽግናዬ ከመንፈስ ነው፤ ስለዚህ የማያልቅ ነው:: እግዚአብሔር ይባረክ!

የእምነት አዋጅ

Page 16: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ማክሰኞ 6

የተበላሸ ንግግር የማይጠቅም እና መጥፎ ንግግር ነው፤ ለጌታ የማይገባ ንግግር ነው:: ፈጽሞ መጥፎ ወይም ጎጂ ንግግሮችን፥

ክፋት የሆኑ እና ተገቢ ያልሆኑ ንግግሮች ወደ እናንተ እንዲገቡ አትፍቀዱ:: እኔ በንግግሬ መልካም እና ጸጋ የተሞላሁ፥ ትክክለኛ ቃልን ለመናገር ብቻ ከረጅም ጊዜ በፊት አዕምሮዬን አሳምኛለሁ::

መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ምንጭ የሚጣፍጥንና የሚመር ውኃ አይወጣም ይላል (ያዕቆብ 3:11):: ዳግም ስትወለዱ ሌሎችን ለመባረክ ተወልዳችኋል:: ንግግራችሁ ሌሎችን ወደታች ማድረግ ሳይሆን ሌሎችን ወደላይ ማንሳት፥ ከፍ ማድረግ እና ማነጽ ይገባዋል:: ቀልድ በሚመስሉ ንግግሮች እንኳን ከአንደበታችሁ ትክክለኛ ቃል ብቻ እንዲወጣ ወስኑ:: ከጽድቅ ተፈጥሮአችሁ ጋር የሚመሳሰል ንግግርን ተናገሩ::

ሁሌም ንግግራችሁ በክብር እንዲሞላ ውጤታማ የሆነው መንገድ ልባችሁን እና አዕምሮአችሁን በቃሉ መሙላት ነው፤ ከሙላት ትናገራላችሁ:: ለቃሉ ታላቅ የሆነን ትኩረት ስጡ እናም አስፈላጊ ጊዜ ሲመጣ፥ በችግር እና በፈተና ጊዜ፥ የጥበብ፥ የመፍትሄ፥ የበረከት እና የፍቅር ቃል ብቻ ከእናንተ ይወጣል::

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል” (ሉቃስ 6:45)። በእናንተ ውስጥ ምንም አይነት ሞኝነት ከሌለ ከአንደበታችሁ አይወጣም:: ጥላቻ፥ መራርነት፥ ንዴት ወይም ትዕቢት በውስጣችሁ ከሌለ ከአንደበታችሁ አይወጣም::

በንግግራችሁ መልካም ሁኑ:: ከምትናገሩት የጥበብ እና የጸጋ ቃል

በቃላችሁ ጸጋን አካፍሉ

ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ

ከቶ አይውጣ (ኤፌሶን 4:29)።

Page 17: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 9:1-29 & መዝሙረ ዳዊት 74-77

የሉቃስ ወንጌል 13:22-30 & መጽሀፈ መሳፍንት 12

መዝሙረ ዳዊት 19:14; መጽሀፈ ምሳሌ 8:7-8; ቆላስያስ 4:6

የተነሳ ሰዎች ከእናንተ ጋር መሆን እና እናንተን መስማት ደስ ሊላቸው ይገባል:: ሃሌሉያ!

ቃሌ በጸጋ የተሞላ ነው እናም የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንዲያፈሩ ለሚሰሙትም ጸጋን ያስተላልፋል:: ከልቤ ከሞላው ሕይወትን፥ ደህንነትን፥ ጤንነትን፥ ብልጽግናን እና በረከትን ብቻ እናገራለሁ:: በኢየሱስ ስም:: አሜን::

የእምነት አዋጅ

Page 18: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ወደ ቤተ ክርስትያን ለህብረት ፀሎት በምንመጣበት ጊዜ ሁሉ፤ ተራ ስብሰባ እያደረግን አይደለም፤ የእግዚአብሔር አምሳሎች

የህብረት ስብስብ ነው፤ የቤተሰብ ህብረት ነው፡፡ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸው የብዙ ሰዎች ህብረት አይደለም፥ በጭራሽ! በመንፈስ አንድ ሆነናል፤ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ፊት አንድ አእምሮ አለን፡፡

የእናንተን ባላውቅም፤ ለእኔ ከሁሉም የሚበልጥ እጅግ በጣም ውብ የሆነ ህብረት ነው፡፡ ከምንም ዓይነት የፖለቲካ፣ የስፖርት፣ የመዝናኛ ወይም ሌላ ማህበራዊ ህብረት ይበልጣል፡፡ በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ዳዊት የእግዚአብሔር ልጆች ህብረት እንዴት ብሩክ እንደሆነ የተረዳበትና የገለጸበት መንገድ ጥልቅ ነው፡፡ በዚያ እግዚአብሔር በረከትንና ሕይወትን ለዘላለም አዝዞአል ይላል፡፡

ሰው ይህንን ካነበበ በኋላ እንዴት ነው ከቤተ ክርስትያን የሚቀረው? የክርስቶስን አካል ስላላወቀ ነው፤ በኀብረት ስንሆን የሚለቀቀውን ሀይል ስላልተረዳን ነው፡፡ ለአምልኮ ወደ ቤተ ክርስትያን በመጣችሁ ቁጥር ወደ በረከት ስፍራ መምጣታችሁን እወቁ፡፡ ጳውሎስ በመንፈስ ሆኖ የበኩሮች አጠቃላይ ጉባኤና ቤተ ክርስትያን ይለዋል (ዕብራውያን 12:23)፡፡ ከተባበሩት መንግስታት አጠቃላይ ጉባኤ ጋር ሲወዳደር ከምታስቡት በላይ ፈፅሞ የበለጠና እጅግ የከበረ ነው፡፡

ምንም እንኳን የተጣበበ ፕሮግራም ቢኖራችሁ ቤተ ክርስትያን የመሄድን ልምድ አዳብሩ፡፡ እያንዳንዱ አገልግሎት የሚታቀደው በልዩ ሁኔታ እናንተን ታሳቢ አድርጎ ነው፡፡ ልዩ የሆኑ የኀብረት፣ የመማር፣ የመንጻት፣ የመታነጽና የክብር ጊዜዎች ናቸው፡፡

የእግዚአብሔር አምሳሎች ህብረት

ወንድሞች በኀብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም ያማረ ነው፡፡ . . . በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን

ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና፡፡ (መዝሙር 133:13)

ረቡዕ 7

Page 19: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 9:30-10:1-21 & መዝሙረ ዳዊት 78

የሉቃስ ወንጌል 13:31-35 & መጽሀፈ መሳፍንት 13-14

1 ኛ ቆሮንጦስ 1:2; የሐዋርያት ስራ 9:31; የሐዋርያት ስራ 11:26

ዕብራውያን 10:25 እንዲህ ይላል፡- “በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደሆነው መሰብሰባችንን አንተው. . .” እንደ ዳዊት ሁኑ፡፡ እንዲህ እንዳለው፡- “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡” (መዝሙር 122:1) እግዚአብሔር በልዩ ሁኔታ ሊባርካችሁና ሕይወታችሁን ሊነካ እናንተን የቀጠረበት ስፍራ ስለሆነ ወደ ቤተ ክርስትያን ለመሄድ የምትጓጉ ሁኑ፡፡

ግርማ ሞገስን የተላበስከው አባት ሆይ፣ የእውነት አምድና መሠረት ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አመሰግንሃለሁ፡፡ በዓለም ዙሪያ ስላሉት አብያተ ክርስትያናት እጸልያለሁ፤ ሙሉ ሰው ወደ መሆንና ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እንክንደርስ ድርስ፥ እምነትንና የእግዚአብሔርን ልጅ ዕውቀት በማግኘት፡ አንድነት፣ ፅናትና እድገት፡ ይሆኑልናል፤ በኢየሱስ ስም አሜን፡፡

ጸሎት

Page 20: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

የልብ መለወጥ

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስን እስካገኝ ድረስ፣ ግትር መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ ሁልጊዜም ነገሮችን በራሴ መንገድ የማደርግና የህይወቴ ዓለቃ ነበርኩ፡፡ ያደግኩት ክርስቲያን ከሆነች ከሴት አያቴ ጋር ቢሆንም ክርስትና ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ እንዳልተረዳሁ ይሰማኝ ነበር፤ ስለሆነም፣ የተለየ መንገድን ተከተልኩ፡፡ በትዳሬ ባሌን በተለይ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በተመለከተ ያን ያህል አላከብረውም ነበር፡፡ ህይወቴን ራሴ በመቆጣጠሬ ጥሩ ስሜት የሰጠኝ ቢመስለኝም እንኳን፣ ሁልጊዜ ደስታ የሌለኝና አብዛኛውን ጊዜ ብዙ ፍርሃቶች ነበሩብኝ፡፡

እምብዛም ሳይቆይ፣ በህይወቴ ያሉ ነገሮች፣ ሥራዬ፣ ገንዘቤ፣ እና ግንኙነቶቼ ወደማይሆን አቅጣጫ ተመሩ፡፡ እኔ ልቆጣጠራቸው ስለማልችላቸው ስለ የወደፊት ዕጣዬ፣ ጤናዬ እና ሌሎች ነገሮች መጨነቅ ጀመርኩኝ፡፡ በዚያ ሁኔታ ሳለሁ ነበር፤ ሰዎች አግኝተውኝ ወንጌሉን ሰብከውልኝ የራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስን ቅጂ የሰጡኝ፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ስከፍተው መልእክቱ ውስጤን ነካው፡፡ ከዚህ አስቀድሞ ሰምቼው በማላውቀው ሁኔታ የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ ከዚያ በኋላ ነበር እንዴት እስከአሁን ድረስ በግትርነት ህይወቴን በተሳሳተ አቅጣጫ እየመራሁ እንደሆነ የተገነዘብከት፡፡

የደህንነትን ጸሎት ጸለይኩና ወዲያውኑ ልቤ ተለወጠ፡፡ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የቃሉ ረሃብ ያዘኝና ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስን መመገብ ጀመርኩኝ፡፡ ብዙም ሳይቆይ፣ ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙነት መሻሻል ጀመረ፡፡ ባሌን ማክበር እና ለወላጆቼ የበለጠ ትዕግስተኛ ሆንኩኝ፡፡ እነርሱም በእኔ መልካም ለውጥ በመነሳሳት የእኔን እምነት ተቀብለውና ድነው ተቀላቀሉ!

ብዙ የተለያዩ ኮርሶችን ተምሬያለሁ፤ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ገብቻለሁ፤ ነገር ግን፣ የትኞቹም ባህርዬን ለመቀየር አልረዱኝም፡፡ ሊቀይረኝ የቻለው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፤ በራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲሰ ውስጥም ይህን ስላገኘሁ ተደስቻለሁ

በቃሉ የመለወጥ የኤሊሳ ምስክርነት

Page 21: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 22: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ሁሉም ክርስትያን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትን፡ ሀይልና፡ እጅግ አስፈላጊነት እንዲረዳ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ። እርሱ

የተላከው በሕይወታችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ ነው፡፡ ረዳታችሁ ነው፥ ዕርዳታውም ገደብ የሌለው ነው፤ በሁሉ ነገር ይረዳችኋል፡፡ ለመጎዳት ስፍራ የሌላችሁ ለዛ ነው ፡፡

ችላ አትበሉት፡፡ ምንም እንኳን እንደ ግለሰብ ችግር ያጥለቀለቃችሁ እንኳን ቢመስል ከጎናችሁ ለመራመድ የተጠራው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡ ለብቻችሁ አይደላችሁም፡፡ ብታዳምጡት የሚያስፈልጋችሁን ጥበብ ይለግሳችኋል፡፡ በእርሱ ብትታመኑ፡ ምንጩ ምን ይሁን ምን ከችግር ሁሉ ነፃ ያወጣችኋል፡፡

የሚያስፈልጋችሁ በእርሱ መታመንና ከዚያም ድምፁን ለመለየትና ለማዳመጥ መንፈሳችሁን ማሰልጠን ነው፡፡ በቃሉ ውስጥ ነው የሚመራችሁ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሌም ያመጣላችኋል፡፡ በልሳን በመናገር መንፈሳችሁን ቀስቅሱት፡፡ የዛኔ ስለ ጥሪውና እንድትሰሩት ስለፈለገው ነገር መንፈሳችሁ በውስጣችሁ ንቁ ይሆናል፡፡

መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ የበለጠ ስኬታችሁን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ትብብራችሁን ያስፈልገዋል፡፡ አሞጽ 3:3 ላይ እንዲህ ብሏል፡- “በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?” አዎ እንድታሸንፉ፣ ስኬታማ እንድትሆኑና፡ በሕይወት ድል አድራጊዎች እንድትሆኑ ሊረዳችሁ ነው የመጣው፤ አገልግሎቱን በሕይወታችሁ ለመፈጸም የእናንተ ትብብር የግድ ያስፈልገዋል፡፡ ያለናንተ በውስጣችሁ ሊሰራ አይችልም፡፡ ለእርሱ ሃሳብና ተጽዕኖ ራሳችሁን የመስጠት ሚና አለባችሁ፡፡

በሕይወታችሁ ስራውና አገልግሎቱ የሚገለጠው በፈቀደላችሁለት

እንድታሸንፉ ሊረዳችሁ መጣ

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም . . . (ዮሐንስ 14:26)

ሐሙስ 8

Page 23: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 11:1-24 & መዝሙረ ዳዊት 79-81

የሉቃስ ወንጌል 14:1-14 & መጽሀፈ መሳፍንት 15-16

ትንቢተ ኢሳያስ 1:19; የዮሐንስ ወንጌል 14:16; ሮሜ 8:14

መጠን ነው፡፡ ይበልጥ በሕይወታችሁ ስራውን ስትተባበሩና ስታበረታቱ፡ ይበልጥ በውስጣችሁና በእናንተ በኩል ራሱን ይገልጣል፡፡ የሚያስፈልጋችሁ ጥበብና ጥንካሬ እርሱ ነው፡፡ 1ኛ ሳሙኤል 2:9 እንዲህ ይላል፡- “. . . ሰው በኃይሉ አይበረታምና፡፡”

ፈፅሞ መቼም ቢሆን በራሳችሁ ችሎታ አትደገፉ፡፡ የምታደርጉትን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታና ሀይል አድርጉ፥ የዛኔ ሁሌም ታሸንፋላችሁ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በውስጤ ስለሚኖር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ዕውቀት፡ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ መረዳት ተሞልቻለሁ፡፡ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ማእከል ነኝ፤ እድሜ ልኬን በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖና ምሪት ቁጥጥር ስር ነኝ፥ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 24: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ከግል ሕይወታችሁ ውስጥ ማስወገድ ከሚገባችሁ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሰበብ መስጠትን ነው፡፡ ማድረግ የሚገባችሁን ነገርና፡

መናገር ያለባችሁን ነገር፡ በትክክለኛው ጊዜና በትክክለኛው መንገድ አድርጉት፡፡ የክብር፣ የሀይል፣ የስኬትና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሕይወትን መምራት ከፈለጋችሁ ተራ መሆንንና ሰበብ መስጠትን አስወግዱ፡፡

አንድን ነገር ላለማድረግ ሰበብ ማቅረብን እስካላቆማችሁ ድረስ የላቃችሁ አትሆኑም፡፡ በክርስቶስ የተጠራችሁት ለዛ ስለሆነ፡ የምትታወቁት በልቀትና በክብር ይሁን፡፡ ድንቅ ስራውን፣ ፀጋውን፣ በጎነቱን፣ ፍፅምነቱን፣ ልቀቱንና ጥበቡን እንድታሳዩ ነው የጠራችሁ፡፡ “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉስ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” (1 ጴጥሮስ 2:9)

መንፈስ ቅዱስ በልባችሁ ያስቀመጠው ራዕይ፡ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ምን አከናውናችሁ እንድትጨርሱ ነው? ያለውን ሁኔታ ገምግሙና ምንም ዓይነት ሰበብ ላለማቅረብ ወስኑ፡፡ ትኩረትና ዲሲፕሊን ያላችሁ ሁኑ፤ ከፍተኛ የሆነ የጥራት ደረጃ ካለው ነገር በታች፡ ምንም ነገር እንደማታደርጉ ለራሳችሁ ንገሩት፡፡ በላቀ ሁኔታ መጨረስን በደስታ በመጠባበቅ፣ ራሳችሁን ስራው የሚጠይቀውን ተግዳሮት ለመጋፈጥ፣ እና ለመነሳሳት ወስኑ፡፡

ብዙዎች ዛሬ ነገ እያሉ ዝቅ ላለውና ውጤታማ ላልሆነው ስራቸው ሰበብ ይሰጣሉ፡፡ ለማሸነፍና ስኬታማ ለመሆን ምረጡ፡፡ ስኬት የሚለካው በተለያየ ደረጃዎች ነው፡፡ ስለዚህ የተቻላችሁን ሁሉ አሁን አድርጉ፥ ከዛም ወደሚቀጥለው ደረጃ እለፉ፡፡ ለስኬታማነት ጥልቅ ፍላጎት ካላችሁ ለሰበብ

ምንም ሰበብ አያስፈልግም

እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፡- አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።

(ዕንባቆም 2:2)

አርብ 9

Page 25: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 11:25-36 & መዝሙረ ዳዊት 82-84

የሉቃስ ወንጌል 14:15-24 & መጽሀፈ መሳፍንት 17

መጽሀፈ ምሳሌ 22:29; የዮሐንስ ወንጌል 9:4; 2 ኛ ቆሮንጦስ 3:5

ቦታ አትሰጡም፡፡ለትክክለኛው ዓላማ፣ ትክክለኛውን ነገር፣ በትክክለኛው ጊዜ አድርጉ።

ይህንንም በቀጣይነት ሁልጊዜ ፈጽሙ፡፡ ታታሪ ሁኑ፡፡ ሁልጊዜ ነገሮችን ጀምሮ መቼም እንደማይጨርሰው ሰው አትሁኑ፡፡ ራዕያችሁን ወደ እውነታ ለማምጣት ተግታችሁ ስሩ፡፡ በክርስቶስ ብቃት ውስጥ ብቃት አላችሁ (2 ቆሮንቶስ 3:5)፡፡ በእርሱ ማናቸውንም ስራ ማከናወን ትችላላችሁ፤ ኃይልን በሚሰጣችሁ በክርስቶስ ሁሉን ትችላላችሁ (ፊልጵስዩስ 4:13)፡፡

የክርስቶስን በጎነት፣ ፍጽምና፣ ልቀትና ጥበብ እያሳየሁ፣ የክብር፣ የሀይልና፡ የተፅእኖ ፈጣሪነትን ሕይወት እኖራለሁ፡፡ ጥንቃቄን፣ ታታሪነትንና ቁርጥ ውሳኔን በማድረግ፣ ቃሌን በማክበር ራዕዬ እውን እስኪሆን ድረስ እተጋለሁ። ውጤታማና ምርታማ በመሆን፡ ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድሎች እየቀየርኩኝ፡ ወደ ታላቅነት እመጥቃለሁ፡፡ ሀሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 26: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ቅዳሜ 10

ደስተኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ውስጣቸው መራርነት አለ፡፡ የበደልዋቸውን ወይም የጎድዋቸውን ሰዎች ይቅር እንዲሉ

ሲመከሩ እንኳን፣ ይቅር ለማለት ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ይቅር ብያለሁ ብለው ቢናገሩም ፀሎታቸውና ውሳኔያቸው የተመሰረተው፡ መጎዳታቸው፣ መበደላቸውና ምሬታቸው ላይ ነው፡፡

ቂምን በውስጣችሁ ለማስተናገድ እምቢ በሉ፡፡ አንድ ሰው ርህራሄ የሌለው ድርጊት ቢፈጽምባችሁ ለውጥ አያመጣም፤ የዛን ገጠመኝ ህመምና ቂም መያዝ፣ ጤናችሁን በሚጎዳ መልኩ ስሜታችሁን ያቆስላል እንጂ ሌላ ትርፍ የለውም፡፡

ይቅር አለማለት በሕይወታችሁ ውስጥ ያለውን ደስታ፣ ሁኔታዎች እንዲሰርቋችሁ መፍቀድ ማለት ነው፡፡ ይቅር ማለት በይበልጥ የሚመለከተው የበደላችሁን ሰው አይደለም፤ የሚመለከተው እናንተን ነው፣ ጥቅሙም የእናንተው ነው፡፡

የበደልዋችሁ ላይ ቂም እስከያዛችሁ ድረስ ነፃ አይደላችሁም፤ ከተናደዳችሁበት ሰው የበለጠ እናንተ ችግር ውስጥ ናችሁ፡፡ ነገር ግን ይቅር ባይ ልብ ሲኖራችሁ፣ ደስ የሚል ሕይወት መኖር ብቻ ሳይሆን፣ በሰዎች ለዛ ያለው አቀራረብና አነጋገር ደስ ትሰኛላችሁ፡፡ ሰዎችን ስትፈቱ፣ እናንተም ትፈታላችሁ፡፡

አዎ፣ በመፅሐፍ ቅዱስ መሠረት ጥቃት ይመጣል፡፡ ሰዎች የሚጎዳችሁንና የሚያስቀይማችሁን ነገሮች ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ቢሆንም ግን ንዴት ትክክል ባልሆነ መልኩ ምላሽ እንድትሰጡ እንዲያደርጋችሁ

ምንም ቁራጭ ነገር በትከሻችሁ ላይ አይኑር

መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ፡፡ እርስ

በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ፡፡

(ኤፌሶን 4:31-32)

Page 27: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 12:1-16 & መዝሙረ ዳዊት 85-88

የሉቃስ ወንጌል 14:25-35 & መጽሀፈ መሳፍንት 18

ኤፌሶን 4:26; ቆላስያስ 3:13; የማቴዎስ ወንጌል 18:21-22

አትፍቀዱለት፡፡ ኢየሱስ ያለውን አስታውሱ፡- “እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤” (ማቴዎስ 5:44) ቃሉን በማድረግ በፍቅር ተመላለሱ፡፡ ይቅርታ ባይጠይቋችሁ እንኳን የበደሉዋችሁን ይቅር በሉ፡፡ በሕይወታችሁ የሚያንቀሳቅሳችሁ የእግዚአብሔር ፍቅር ይሁን፡፡ በቀላሉ ይቅር በሉ፡፡ ቂም አትያዙ፡፡ ትሁትና ደግ በመሆን፡ በቀላሉ የማትቀየሙ ሁኑ፡፡ ከሰዎች ጋር በፍቅር እንድትመላለሱ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ ወንዝ በውስጣችሁ እንዲፈስ ፍቀዱለት፡፡

አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ውበት በተግባር መዋል መቻሉ ነው፤ መክፈቻ ጥቅሳችን “መራርነትና ንዴት ቁጣም . . . ከእናንተ ዘንድ ይወገድ” ሲል ተግባራዊ ማድረግ እንደምንችል ለማሳየት ነው፡፡ ይህን ከመሳሰሉና ከሌሎች አሉታዊ ስሜቶች እንድትወጡ ቃሉን ተጠቀሙ፡፡ ቂም የያዛችሁበት ወይም ቂም የያዘባችሁ ሰው ካለ፣ ጥፋቱ የማን ይሁን የማን፡ እናንተን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ስለሆነ፡ ሰላምን ለመፍጠር የድፍረት እርምጃን ተራመዱ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልቤ ፈሷል፡፡ ትሁት፣ ደግና ታጋሽ ሊያደርገኝ የእግዚአብሔር ፍቅር ሙሉ በሙሉ በእኔ ስለተገለጠ፣ ይቅር ባይ ልብ አለኝ፡፡ በሰዎች ውስጥ ባለው ደስ የሚል ባህሪይ በቀጣይነት ደስ እየተሰኘሁ ደስ የሚልና አጓጊ ሕይወትን እኖራለሁ። ሀሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 28: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ይበልጥ ቃሉን ስታጠኑ፣ በይበልጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ታውቃላችሁ፤

ይህም ከቃሉ ደራሲ ጋር ይበልጥ ስለምትተዋወቁ ነው፡፡ በቃሉ በኩል ፈቃዱን ካወቃችሁ፥ ጥቃቅን ዝርዝር ጉዳዮቻችሁንም ጨምሮ፥ በሁሉም ነገር ውስጥ ፈቃዱን ታውቃላችሁ፡፡

ሰዎች አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ ውጥረት ውስጥ የሚገቡት የአብን ፈቃድ ስለማያውቁ ነው፡፡ ለምሳሌ ስራችሁን ወይም ንግዳችሁን ስታጡ “እግዚአብሔር ሆይ ለምን? ይህ እንዴት በእኔ ላይ ይደርሳል?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፡፡ ይህ ምላሽ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በተመለከተ ስፍራችሁን በእርግጠኝነት አለማወቃችሁን ያሳያል። በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እንደሆናችሁ እርግጠኞች ከሆናችሁ አትናወጡ፡፡

በክርስቶስ ውስጥ በአሸናፊነት ለመኖርና እንደ ንጉስ ለመግዛት በእግዚአብሔር ተሾመናል፡፡ ብዙዎች የዚህ ዓይነት ውጤትን የማይለማመዱት፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ እውቀት ውስጥ መራመድን ስላልተማሩ ነው፡፡ ሮሜ 12:2 ላይ በጎ፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም ስለሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ይነግረናል፡፡ የመጨረሻው ግብ በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ መመላለስ ነው፡፡ ይህም ውጤት የሚመጣው ከጌታና ከቃሉ ጋር በሚኖረን ኅብረት ብቻ ነው፡፡

በጸሎት፣ ቃሉን በማጥናትና በማሰላሰል ከጌታ ጋር ኅብረትን ስታደርጉ ፍጹም ፈቃዱን፣ ዕቅዱንና አላማውን ታውቃላችሁ፡፡ በዛ ቅርርብ ውስጥ በሃሳብና በባህሪይ አንድ በመሆን እርሱን ትመስላላችሁ። በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ትረዳላችሁ፤ ጉልበታችሁንና

ፈቃዱን ስታውቁ

ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ፡፡ (ኤፌሶን 5:17)

እሁድ 11

Page 29: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 12:17-13:1-14 & መዝሙረ ዳዊት 89

የሉቃስ ወንጌል 15:1-10 & መጽሀፈ መሳፍንት 19

ትንቢተ ኤርምያስ 29:11; ቆላስያስ 1:9-10

አቅርቦታችሁን ለትክክለኛው ውጤት፡ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ታፈሳላችሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስታውቁ በመለኮታዊ ጥበብ ትሞላላችሁ፤ የመንግስቱን ሚስጢራት ለማወቅ የእግዚአብሔርን አእምሮ ትረዳላችሁ፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መኖራችሁን ማወቅ ሁሉን ማድረግ የመቻልና የመግዛት ስሜትን ይሰጣችኋል፡፡ ቃሉ መልህቃችሁ ስለሆነ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ብታልፉ እንኳን አትናወጡም፡፡ ምንም ዓይነት መከራ ወይም ጨለማ ቢመጣ ደስተኞች ናችሁ፥ ምክንያቱም በምንም ነገር ውስጥ ብታልፉ አላፊ መሆኑን ታውቃላችሁ! መጨረሻ ላይ ታላላቅ ድሎች ይጠብቋችኋል፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ በቃልህ በኩል ወደ መንፈሴ ስለመጣው መገለጥ አመሰግንሃለሁ፡፡ ቃልህን ባሰላሰልኩኝ መጠን ፈቃድህና አላማህ ስለተገለጡልኝ አመሰግንሃለሁ፤ እመላለስበት ዘንድ አስቀድመህ ባዘጋጀኸው መንገድ ላይ ለመሄድ በጥበብህ በመመራት፡ በክርስቶስ የተጠራሁበትን ክቡር ጥሪ ለስምህ ክብር እፈጽማለሁ፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 30: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የመክፈቻ ጥቅሳችን፣ በየዕለቱ ሃያ አራት ሰዓት፣ በቀጣይነት በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላና በእርሱ ተፅዕኖ ስር ሆነን

እንድንንቀሳቀስ ይነግረናል፡፡ ያ ነው መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ያለው ጥልቅ ፍላጎት፥ በቀጣይ ቁጥሮች ላይ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ያሳየናል፡፡

“በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤” ፡፡ አንደኛው ያለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት መንገድ ይህ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ መዝሙሮችን በአምልኮ ትዘምራላችሁ፡፡ የምስጋናና የአምልኮ መዝሙሮችን ትዘምሩለታላችሁ፤ እነዚህ አብዛኛውን ጊዜ ከመንፈሳዊው ዓለም የምትቀበሏቸው ትንቢታዊ መዝሙሮች ናቸው፥ የሚመጡላችሁ በልሳን ስትጸልዩ ሊሆን ይችላል፡፡

ደግሞም “. . . ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤” ይላል፡፡ እነዚህ ከልባችሁ ለጌታ የምታቀርቧቸው የምስጋና፣ የአምልኮ፣ የማነጽና የደስታ ዝማሬዎች ናቸው፤ በልሳን ወይም በአእምሮ የምቀርቡ ናቸው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን አስባችሁት በየዕለቱ የምታደርጉት ነገር ይሁን፡፡

ያኔ መንፈሳችሁ ያለማቋረጥ ለድልና ለስኬት ይነሣሣል፡፡ ሁልጊዜም በመንፈሳችሁ ከፍታን ያዙ፡፡ መንፈስ ቅዱስን ለመሞላት ቤተ ክርስትያን እስክትሄዱ ድረስ አትጠብቁ፤ በየትኛውም ጊዜና ቦታ በመንፈስ መሞላት ትችላላችሁ፤ የሚወሰነው በእናንተ ነው፡፡

ከምታውቁት ጀምሩና ወደማታውቁት ሂዱ፡፡ በሌላ አነጋገር ከተጻፉት የመዝሙረ ዳዊት ጥቅሶች፥ ለምሳሌ መዝሙር 23ን ፣ 27ንና የመሳሰሉትን ጮህ ብላችሁ በማንበብ ጀምሩ፡፡ አንብባችሁ ስትጨርሱ

የማያቋርጥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ማባከን ነውና፤ (ኤፌሶን 5:18)

ሰኞ 12

Page 31: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 14-15:1-4 & መዝሙረ ዳዊት 90-93

የሉቃስ ወንጌል 15:11-19 & መጽሀፈ መሳፍንት 20

መዝሙረ ዳዊት 23:1-4; መዝሙረ ዳዊት 48:1-2; የያዕቆብ መልእክት 1:20

በሀይል ተሞልታችሁና ተነሳስታችህ የእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጣችሁን መዝሙር ትዘምራላችሁ፡፡ በሕይወታችሁ ይህንን በቀጣይነት አድርጉ፡፡ ሀሌሉያ!

ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከአንተ ጋር ኅብረት የማድረግ ዕድልን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ መንፈስህ ሙሉ በሙሉ እየሞላኝ፣ ከዚህ ዓለም የተበላሸ ተጽዕኖ በላይ ሆኜ መንፈሳዊ ህንፃ ለመሆን ተሰርቻለሁ፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

የእምነት አዋጅ

Page 32: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ማክሰኞ 13

አንዳንድ ክርስቲያኖች እምነታቸውን የሚሸረሽርና አዲሱን ማንነታቸውን የማይገልጽ መዝሙር ይዘምራሉ፡፡ ለምሳሌ

አንድ ሰው እንደዚህ ብሎ ሊዘምር ይችላል፡- “ኢየሱስ ይወደኛል፤ እኔም እወደዋለሁ፣ ምክንያቱም ሁልጊዜ ስሰናከል እርሱ ያነሳኛል”፡፡ ይሄ ከላይ ሲታይ ግሩም የሆነ መዝሙር ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ በክርስቶስ ያለንን ስፍራና ርስትም አያመለክትም፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ በወደቅን ቁጥር ያነሳናል አይልም፤ ይልቁኑ የሚለው እንዳንወድቅ ሊጠብቀን ይችላል ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በጣም የከበረና የተሻለ ነው፡፡ ሁልጊዜ ስወድቅ እርሱ ያነሳኛል በሚል አስተሳሰብ ውስጥ ሆናችሁ የምትመላለሱ ከሆነ ያለማቋረጥ እየወደቃችሁ እርሱ እንዲያነሳችሁ ትጠብቃላችሁ ማለት ነው፤ ይሄ ደግሞ የእርሱ አገልግሎት አይደለም። የእርሱ አገልግሎት እንዳትወድቁ መጠበቅ ነው፡፡ እምነታችሁ እርሱ ከውድቀት ሊጠብቃችሁ እንደሚችል ከሆነ መጀመሪያውኑም ልትወድቁ አትችሉም፡፡ ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን፡፡

እርሱ አጥብቆ የሚያጸናችሁና የሚይዛችሁ አለት እንደሆነ እመኑ፤ ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት “በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ” ነው፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ! ስለዚህ ሁልጊዜ እንደዚህ እያላችሁ አውጁ፡- “ጌታ እንዳልወድቅ ሊጠብቀኝ ይችላል”። ይሄ ፍጹምና ዘላለማዊ በሆነው በመቤዠቱ ስራ ላይ ያላችሁን እምነት የምትገልጹበት የእምነት ንግግር ነው፡፡

በሌላ ስፍራ ላይ መንፈስ በሀዋርያው ጴጥሮስ አማካይነት ተመሳሳይ ሀሳብን የሚገልጽበት ክፍል አለ፡፡ 2ኛ ጴጥ 1፡1-10 ላይ መንፈስ ቅዱስ

ጌታ እንዳትሰናከሉ ይጠብቃችኋል

ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው

ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ

ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። (ይሁዳ1፡24-25)

Page 33: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 15:5-13 & መዝሙረ ዳዊት 94-98

የሉቃስ ወንጌል 15:20-32 & መጽሀፈ መሳፍንት 21

ትንቢተ ኢሳያስ 30:21; ቆላስያስ 1:21-23; 2 ኛ ጴጥሮስ 1:5-10

ለክርስቲያኖች ውጤታማ መንፈሳዊ ህይወት የሚጠቅሙ ባህሪያትንና ሁኔታዎችን ያሳያል፡፡ የተጠቀሰውን ክፍል በሙሉ አንብቡት፤ ቁጥር 10 ላይ እንደዚህ ይላል “…እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም “፡፡ ምንኛ የሚያጽናና፤ ምንኛ የሚያረጋጋ ምክር ነው!

እኛ እየወደቁ ከሚነሱት ውስጥ ሳንሆን ለዘላለም ጸንተን የምንቆም ነን። ኤፌ 6፡14 “እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ ቁሙ፤” ይላል። በእምነት ጉዟችሁ ውስጥ ሁልጊዜ ጸንታችሁ እንደምትቆሙና ለወንጌል ብርቱዎች እንደሆናችሁ መረዳት ይኑራችሁ፡፡ ጌታ አለትና መከታችሁ ስለሆነ እግራችሁ አይሰናከልም፡፡ በቃሉ አማካይነት እርሱ ይጠብቃችኋል፤ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስም ከውድቀት ይጠብቃችኋል፡፡ ሀሌሉያ!

ውድ አባት ሆይ እኔን ስለወደድክበት ታላቅ መውደድ አመሰግንሀለሁ፤ እንዳልንገዳገድና እንዳልወድቅ በቀኝህ ስለደገፍከኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ በቃልህና በመንፈስህ ምሪት ስለምመላለስ እርምጃዎቼ አይሰናከሉም፤ በኢየሱስ ስም አሜን፡፡

ጸሎት

Page 34: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ከላይ ያነበብበነው ጥቅስ የተጻፈው ለክርስቲያኖች ስለሆነ የሚያወራው ስለእናንተ ነው ማለት ነው፡፡ በእናንተ ውስጥ

መዝገብ አለ፤ መለኮታዊ ባህሪውንም ተሸክማችኋል፡፡ ተራ ሰዎች አይደላችሁም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ በፊልሞና 1፡6 ላይ “የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤ ስለሚል ይህንን እውነት ልትቀበሉት ይገባል። የመለኮታዊ ስርአትና የመለኮታዊ ህልውናው ተሸካሚ መሆናችሁን ከዚህም የተነሳ የሀይሉ ታላቅነት በእናንተ ተገልጦ የምትሰሩትን ሁሉ እንደሚያከናውንላችሁ ልታምኑ ይገባል፤ ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ የክርስትናችሁ ሚስጥርና ክብር ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ መሆኑ ነው ይላል፡፡ (ቆላ 1፡27) ህይወታችሁ ባዶ አይደለም፡፡ በውስጣችሁ መዝገብ አለ፡፡ የሀይል መዝገብ፤ የፍቅር መዝገብ፤ የብርሀን መዝገብ፤ እንዲሁም የመለኮታዊ ፍጽምና መዝገብ አለ፡፡ ስጋችሁ የተሰራው ከምድራዊ ሸክላ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሄር ክብር ያለው በመንፈሳችሁ ውስጥ ነው፤ ያ ክብርም ስጋዊ አካላችሁን በመሸፈን ፍጹም ያደርገዋል፡፡

ሁልጊዜ የእግዚአብሄር ብርሀን፤ የእርሱ ክብር፤ ሀይልና ጸጋ በእናንተ በኩል ለአለማችሁ እንደሚገለጥ አውጁ፡፡ እንደዚህ አይነት አዋጆችን በተደጋጋሚ አድርጉ፡፡ ምክንያቱም በህይወታችሁ ቃሉ ውጤታማ የሚሆነው ለእግዚአብሄር ቃል በምትሰጡት ምላሽ መሰረት ነው፡፡

የመክፈቻውን ጥቅስ በተመለከተ ምላሻችን መሆን ያለበት “እኔ የእግዚአብሄር ተሸካሚ ነኝ፤ የመለኮታዊ በረከትና ሀብት መያዣ ነኝ” በሉ። ሀሌሉያ!

በእናንተ ውስጥ መዝገብ አለ

ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤

(2 ኛ ቆሮንቶስ 4፡7)

ረቡዕ 14

Page 35: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 15:14-33 & መዝሙረ ዳዊት 99-101

የሉቃስ ወንጌል 16:1-12 & መጽሀፈ ሩት 1-2

የሉቃስ ወንጌል 6:45; ቆላስያስ 1:27; 1 የዮሐንስ ወንጌል 4:4

ክርስቶስ በእኔ ውስጥ አለ፤ ፍጽምናው በመንፈሴ ውስጥ አለ፡፡ የእግዚአብሄር ህይወትና ክብር በእኔ ውስጥና በእኔ አማካይነት ተገልጧል፡፡ በቃሉ አማካይነት በመንፈሴ ውስጥ መዝገብ እንዳለ አምናለሁ፡፡ በእምነት ንግግርም እውን አደርገዋለሁ፡፡ በማደርገው ሁሉ ልቀትን፤ ፍጽምናንና ማስተዋልን እገልጣለሁ፡፡ በፍቅር የተሞላሁ ነኝ፤ አለሜን በእግዚአብሄር መልካምነት፤ ውበትና ጸጋ አጥለቀልቃለሁ፡፡ ሀሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 36: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 37: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 38: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የመክፈቻ ጥቅሳችን “መሬታዊ” የሚላቸው ዳግም ያልተወለዱ ሰዎችን ነው፤ ይሄ ማለት ከዚህ አለም ናቸው ማለት ነው፡፡

የሚያውቁት ይሄንኛውን አለም ብቻ ነው፤ ህይወታቸው እንደዛ ነው፡፡ ለሰው ውድቀት ምክንያቱም ይሄው ነው፤ ከአዳም ውድቀት ጀምሮ ሁኔታው እንደዚሁ ነው፡፡ ኢየሱስ “ዳግም ልትወለዱ ይገባችኋል” ያለውም ለዚህ ነው (ዮሀንስ 3፡7)፡፡

ሰው በወላጆቹ አማካይነት ወደዚህ አለም በመጣበት በዛው ህይወት ከቀጠለ፤ ምንም ያህል ጥረት ቢያደርግ አይሳካለትም፡፡ በእርግጥ አናዳንድ ሰዎች በሙያቸው የስኬት ጥግ ላይ ደርሰዋል፤ ባለብዙ አቅምና ተጽእኖ ፈጣሪዎችም ሆነዋል፤ ይሁን እንጂ በህይወታቸው አንድ ወቅት፣ ህይወት ማለት ይሄ ብቻ እንዳልሆነ ይገነዘባሉ፡፡

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በማርቆስ 8፡36 ላይ “ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በዚህ አለም ላይ ላለማድረግ እንዲጠነቀቁ እየመከራቸው ነበር፡፡ ይሄ አለም ሁሉንም ነገር ሊሰጣችሁ ይችላል፤ ነገር ግን በቂ አይደለም፡፡ የሚያስፈልጋችሁን ከሁሉም የሚሻለውም እግዚአብሄር የሚሰጣችሁ ነው፡፡

1ኛ ዮሀ 2፡15 እንደዚህ ይላል፡- “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።” የሚያሳዝነው ግን ክርስቲያኖች ከሆኑ በኋላ እንኳን አለምንና በአለም ያለውን የሚወዱ አሉ፡፡

ለምሳሌ 2ኛ ጢሞ 4፡10 ላይ ስለዴማስ የተጻፈውን እንመለከታለን። እርሱ ከሀዋርያው ጳውሎስ ጋር አብሮ ለወንጌል የሚተጋ ነበር፤ ነገር ግን

አለምን አትውደዱ

መሬታዊው እንደ ሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው (1ኛ ቆሮንቶስ 15:48)

ሐሙስ 15

Page 39: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 16:1-27 & መዝሙረ ዳዊት 102-103

የሉቃስ ወንጌል 16:13-18 & መጽሀፈ ሩት 3-4

የማቴዎስ ወንጌል 6:33; ያዕቆብ 4:4

ፍጻሜው እንዴት አሳዛኝ እንደሆነ ከጳውሎስ ንግግር እንመልከት፡- “ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤…”፡፡

ዴማስ ከጳውሎስ ጋር ሲሰራ መንፈስ ቅዱስ በጳውሎስ አማካይነት ታላላቅ ተአምራቶችን ሲያደርግ አይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ቆይቶ ከአለም ጋር ማመቻመች ጀምሯል፡፡ አለምን ስለወደደ ከመንፈስ ቅዱስ መንገድና ህይወት ስቶ ወጥቷል፡፡ ዛሬም በብዙ ሰዎች ህይወት ውስጥ ይህንኑ እንመለከታለን። ሀዋርያው ጳውሎስ ግን እንደዚህ ብሏል፡- “አለም ለእኔ እኔም ለአለም ተሰቅያለሁ” (ገላቲያ 6፡14)፡፡ የእናንተም መሻትና ሀሳባችሁ እንደዚህ መሆን አለበት፡፡

በህይወታችሁ፤ በመንፈሳዊ እድገታችሁ የምትመኙት ሁሉ የመንግስቱን መስፋት፤ የክርስቶስን ፍቅርና ዳግም ምጽአቱን ብቻ የሚሆንበት ደረጃ ላይ ድረሱ፡፡ ምኞታችሁም ሆነ የህይወት አላማችሁ ይሄ ብቻ ይሁን፡፡

እኔ ለአለም ተሰቅያለሁ፤ አለምም ለእኔ ተሰቅሏል፤ የምኖረው ለክርስቶስና ለወንጌሉ መስፋት ብቻ ነው፤ ወንጌሉ ለሚያምኑ ሁሉ ለማዳን የሆነ የእግዚአብሄር ሀይል ነውና፡፡ እኔ ሰማይንና ጽድቅን በሰዎች ልብ ውስጥ ለማጽናት የተጠራሁ የክርስቶስ አምባሳደር ነኝ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

የእምነት አዋጅ

Page 40: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

1ኛ ቆሮንቶስ 1፡30 ክርስቶስ ለእኛ ጥበባችን መሆኑን ይናገራል፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ አማካይነት እውቀትን መረዳት እንድንችል

ማስተዋል ተሰጥቶናል፡፡ መክፈቻ ጥቅሱ “ማስተዋልን አትርፍ” ይላል፡፡ ይሄ የእውቀት ማስተዋል ነው፡፡ ይሄ ማስተዋል የምትሰሟቸውን የተለያዩ ድምጾች እንዴት መለየት እንደምትችሉና ከእግዚአብሄር ቃል መመሪያ ጋር በአንድ ላይ በማድረግ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለባችሁ ለማወቅ ይረዳችኋል፡፡

በዚህ መለኮታዊ ጥበብ ስራችሁ ወይንም የሙያ መስካችሁ ምንም ይሁን ምን ሁልጊዜም ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡ ሁልጊዜም በማንኛውም ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ ስለምታውቁ ያላችሁበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳታስገቡ የምትናገሩት፤ የምታደርጉትና የምትኖሩት ከምታዩት በላይ ይሆናል፡፡

የነቢያት ልጆች ኤልሳዕን አብሯቸው ወደዮርዳኖስ እንዲሄድና ምሶሶ እንዲያመጡ ሲጠይቁት አጣብቂኝ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ እንጨት ሲቆርጥ የመጥረቢያው ብረት ወንዙ ውስጥ ገብቶ ጠፋበት፡፡ ወደኤልሳእም በመጮህ “ጌታዬ ሆይ ወዮ ወዮ የተዋስኩት ነበር” (2 ነገስት 6፡5) አለ፡፡ ኤልሳዕም ወዴት ነው የወደቀው ብሎ ጠየቀ፤ እነርሱም ብረቱ የሰመጠበትን ትክክለኛ ቦታ አሳዩት፡፡

ኤልሳዕ ወዲያውኑ አንድ ያልተለመደና ያልተጠበቀ ነገር አደረገ። እንጨት ቆረጠና የመጥረቢያው ብረት የወደቀበት ቦታ ላይ ጣለው፤ ብረቱም ወደላይ ተንሳፈፈ፡፡ ጥያቄው ብረቱን ለማውጣት ምን ማድረግ እንዳለበት ኤልሳዕ በምን አወቀ?

እርሱ የማስተዋል እውቀትና መንፈሳዊ ማስተዋል ስለነበረው ነው፡

መለኮታዊ ጥበብ

ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። (ምሳሌ 4፡7)፡፡

አርብ 16

Page 41: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 1 & መዝሙረ ዳዊት 104-106

የሉቃስ ወንጌል 16:19-31 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1

ኤፌሶን 1:17-18; 1 ኛ ቆሮንጦስ 2:6-7; ትንቢተ ኢሳያስ 11:2

፡ ሁላችንም በእንደዚህ አይነት መለኮታዊ ማስተዋል እንድንመላለስ የእግዚአብሄር ፍቃድ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላብን መጸለዩ አያስገርምም (ቆላስይስ 1፡9)፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ በክርስቶስ ስለሆንኩና ከተለመደው ያለፈ መረዳት፤ ላቅ ያለ አይምሮ እንዲሁም በምሰራው ሁሉ፤ በንግዴ፤ በስራዬ፤ በትምህርቴ፤ በአገልግሎቴ ሁሉ ለልቀት የሚሆን ልእለ ተፈጥሯዊ ብርታት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ አስተሳሰቤ ላቅ ያለ ነው፡፡ የፈጠራ ብቃቴ፤ መረዳቴ፤ ማስተዋሌ ከሰው አይምሮ በላይ ናቸው፡፡ በኢየሱስ ስም አሜን፡፡

ጸሎት

Page 42: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ቅዳሜ 17

የንግግር ችሎታ ወይንም የቃል እውቀት አላችሁ ማለት ሀጢያተኞች እንዲድኑ ወይንም ወደጸድቅ እንዲመለሱ ማሳመን

ትችላላችሁ ማለት አይደለም፡፡ ከአንድ ሰው አእምሯዊ ልዩ ችሎታ፣ ግርማ ሞገስ ወይም ሌሎችን ለማሳመን አነቃቂ ንግሮችን የማድረግ ችሎታ ባለፈ፣ የአገልግሎትን መንፈሳዊነት ልንረዳ ይገባል፡፡

ውጤታማ ክርስቲያን ወይንም የወንጌል ሰራተኛ መሆን ከሰው ተፈጥሯዊ ብቃታችሁ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ ብቃታችሁና ችሎታችሁ በመንፈስ ቅዱስ መሆን አለበት፡፡ በ2ኛ ቆሮንቶስ 3፡5-6 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ጉዳይ ግልጽ አድርጎ ያስቀምጥልናል፡-“ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።”

በመንግስቱ ውስጥ ያለን ህይወትና ለእግዚአብሄር የምንሰጠው አገልግሎት መሆን ያለበት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በእምነት ነው። ለዚህ ነው በአለም ላይ ምርጥ የሚባሉ ስብከቶች የማንንም ህይወት ሊለውጡ የማይችሉት፡፡ ብልሀት የተሞሉ ቃላት የጠነከሩ ልቦችን አይለውጡም። ታላቅ የተባለ የንግግር ሊቅ ምንም ያህል ምርጥ ጥበብ የተላበሰ ንግግር ቢያደርግ፤ ምንም ያህል የቃላት ምርጫው ላይ የተካነ ቢሆን ጥልቅ ወደሆነው ወደሰው ተፈጥሮ ሊደርስ አይችልም፡፡ ካለመንፈስ ቅዱስ ሁሉም ህይወት አልባ ነው፡፡

ህይወትን የሚሰጠው መንፈስ ነው፤ ዘካርያስ 4፡6 እንደዚህ ይላል፡

ከሰው ችሎታዎች ያለፈ

እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና

ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። (1ኛ ቆሮንቶስ 2፡4)

Page 43: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 2 & መዝሙረ ዳዊት 107-108

የሉቃስ ወንጌል 17:1-10 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2

2 ኛ ቆሮንጦስ 3:5-6; ፈልጵሱዮስ 4:13

- “በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦” ሀሌሉያ! 1ኛ ቆሮ 4፡20 ደግሞ እንደዚህ ይላል፡- “የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና።” በሀይል የሚለው የመንፈስ ቅዱስን ሀይል ነው፡፡

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረት ለማድረግና ቃሉን ለማሰላሰል ቅድሚያ ስጡ፤ ከእርሱ ጋር ይበልጥ ልትተዋወቁ፤ ቃሉን ልታውቁና በሀይል ልትመላለሱ እንዲሁም ውጤታማ የጌታ ምስክር ልትሆኑ የምትችሉት እዛጋ ነው፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ ለክርስቶስ ውጤታማ ምስክር ስላደረግከኝ አመሰግንሀለሁ፤ ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ብልጥግና እንድሰብክ ብቃት የሆንክልኝ አንተ ነህ፡፡ የምናገረው ቃል የሚሰራ፤ ፍሬያማ፤ የጸጋውን ሀይል የተሞላና በሀጢያተኞች ልብ ውስጥ የጽድቅን ፍሬ የሚያፈራና ወደ እውነተኛና ትክክለኛው ፍቅርህ የሚያመጣ ነው፡፡

ጸሎት

Page 44: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የታሰበበት የክፋት ስራ፣ አመጻ፣ ሽብር፣ በወገን ላይ የሚደረግ ተንኮልና ሰብአዊነት የጎደለው ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ

ነው። ስታትስቲካዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አለም ክፋትን እየጨመረችና ተስፋ የምታስቆርጥ መሆኗ ብቻ ሳይሆን የህይወት ጫናም ከምን ጊዜውም ይበልጥ እየጨመረ ሄዷል፡፡

ይሄ ደግሞ የሚያመለክተው ኢየሱስ አስቀድሞ በተናገራቸው በመጨረሻዎቹ ቀኖች ላይ መሆናችንን ነው፡፡ የአለም መሪዎች እነዚህን በርካታ ችግሮች እንዴት መፍታት እንዳለባቸው ስለማያውቁ ግራ ተጋብተዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ግን መፍትሄ ከእነርሱ ለማግኘት የሚፈልጉት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱና እነርሱ ደግሞ ምንም መፍትሄ ለመስጠት አለመቻላቸው ነው፡፡ መልሱ ያለው እኛጋ ነው፤ መፍትሄው ክርስቶስና የክብሩ ወንጌል ነው፡፡

ኢየሱስ በማቴ 24፡14 ላይ ሲናገር “ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” ብሏል፡፡ ሁሉም ሰው ይድናል ብሎ አልነገረንም ፤ ይሁንና ለሁሉም ሰው የመንገር ግዴታ አለብን፡፡ እጃችን ውስጥ ላለው መረጃ ሀላፊነቱ የእኛ ነው፡፡

ስለሆነም ገደብ በሌለው የመንፈስ ቅዱስ ፍጥነት ወንጌልን ለአለም ሁሉ ስበኩ፤ የምድር የጨለማ ስፍራዎች ሁሉ በክፋት ተሞልተዋል፤ እኛ ግን ለጨለማው አለም ብርሀናት ነን፡፡ የወንጌሉን ብርሀን እናበራለን፡፡

በማቴ 5፡16 ላይ ኢየሱስ ሲናገር “መልካሙን ሥራችሁን አይተው

ጊዜው አጭር ነው

በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ

የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት

ኃይላት ይናወጣሉና ፡፡ (ሉቃስ 21፡25-26)

እሁድ 18

Page 45: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 3 &መዝሙረ ዳዊት 109-112

የሉቃስ ወንጌል 17:11-19 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 3

መዝሙረ ዳዊት 67:2; የማርቆስ ወንጌል 16:15-16; 2 ኛ ጢሞቴዎስ 4:2

በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ብሏል፡፡ በተጨማሪም ማርቆስ 16፡15 ላይ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ብሏል፡፡ ይሄንን ሀላፊነት አጥብቃችሁ ልታስቡበት ያስፈልጋል፡፡

ህልማችሁ ከእራሳችሁ ያለፈ ሊሆን ይገባዋል፤ የወንጌልን አርማ አንሱ፤ ሀብታችሁን፣ ጊዜያችሁን፣ ጉልበታችሁን በመስጠት በአለም ዳርቻ እስኪደርስ ድረስ በፍጥነት ስበኩ!

ውድ አባት ሆይ፣ ለሚያምኑ ሁሉ ለማዳን የሆነውን ወንጌል ለመስበክ ስለሰጠኸኝ እድል አመሰግንሀለሁ፤ ወንጌል ከምን ጊዜውም ይበልጥ እየሰፋ፤ በየቤቱ፣ በየትምህርት ቤቱ፣ በየመስሪያ ቤቱ እየተዳረሰና ብዙዎችን ስለሀጢያት እየወቀሰ ወደጸድቅም እየመለሰ እንደሆነ አውጃለሁ፤ በኢየሱስ ስም አሜን!

ጸሎት

Page 46: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

በክርስቶስ እኛ ለእግዚሃብሄር ንጉስና ካህን ተደርገናል (ራዕይ 1፡6)፡፡ በክርስቶስ እንደ እግዚሃብሄር ንጉስ-ካህን አገልግሎት

አለን፡፡ በመግቢያ ጥቅሳችን እንዳነበብነው የካህኑ ከንፈር እውቀትን መጠበቅ አለባት፡፡ ይህ ማለት ለሌሎች የመንግስቱን መንገድ እና ህይወት ለማስተማር ከንፈሮቻችሁ በእግዚሃብሄር እውቀት መፍሰስ አለባቸው፡፡

የሊቪንግ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ውብ በሆነ መንገድ የመክፈቻ ጥቅሱን ሁለተኛ ክፍል ይገልጸዋል፡፡ እንዲህ ይላል፡- “ካህናት የኃያሉ ጌታ መልእክተኞች ናቸው፣ ሰዎች ወደ እነሱ ለምሪት መምጣት አለባቸው፡፡” በ1ኛ ጴጥሮስ 4፡11 ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጻፈ “ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።”

ማንም ሰው ስለ እግዚሃብሄር የተወሰነ ነገር ማወቅ ቢፈልግ፣ ወደ እናንተ መምጣት አለበት፡፡ የእግዚሃብሄርን ቃል እና የጌታን እውቀት ከአፋችሁ ማግኘት አለባቸው፡፡ የመለኮት እውቀት እና የመንግስቱ መረጃ ጠባቂዎች ናችሁ፡፡

2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 እንዲህ ይላል፡- “ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፡፡” እግዚሃብሄር ውብ የሆነውንና አስደሳቹን የእውቀቱን መአዛ በሁሉም ስፍራ በእኛ አሰራጭቷል፡፡ ቃሉ በአለም እንዲታወቅ ማድረግ አገልግሎታችሁ፣ ጥሪያችሁና ኃላፊነታችሁ ነው፡፡

ቃሉ እንዲታወቅ አድርጉ

ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል። (ሚልኪያስ 2፡7)

ሰኞ 19

Page 47: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 4 & መዝሙረ ዳዊት 113-116

የሉቃስ ወንጌል 17:20-30 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 4

የማቴዎስ ወንጌል 28:18-20; 2 ኛ ጢሞቴዎስ 4:2

ስለሆነም በገበያ ስፍራ፣ በጎረቤት፣ በምትኖሩበት ሰፈር፣ በስራ ቦታችሁ እንዲሁም በሁሉም ስፍራ ቃሉን ስበኩ፤ አስተምሩም፡፡ እናንተ የምትደርሷቸውን ተማሪዎቻችሁ አድርጉዋቸው፤ ስለእግዚሃብሄር እና ስለ መንግስቱ ህይወት አስተምሩአቸው፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ የማስታረቅ አገልጋይ ስላደረከኝ አመሰግናለሁ፡፡ የክርስቶስን ማዳን መልእክት ለምኖርበት አለም አሳውቃለሁ፡፡ የከበረውን መንግስትህን ምስጢር አሳውቃለሁ፣ በባርነት እና በጨለማ የተጨቆኑትን ወደ እግዚአብሔር ልጆች ወደ ከበረው ነፃነት እንዲወጡ አደርጋለሁ፣ በኢየሱስ ስም ! አሜን፡፡

ጸሎት

Page 48: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ክርስትና አስደሳች ህይወት ነው፡- በቃሉ የማሸነፍ ህይወት፡፡ በእውነተኛው ክርስትና እግዚሃብሄርን ለማስደሰት መታገል

አይጠበቅባችሁም፣ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ እርሱን የሚያስደስተውን የእምነት ህይወት እንድትኖሩ ይረዳችኋል፡፡ ማድረግ ያለባችሁ በቃሉ ለእርሱ ትኩረት መስጠት ነው፡፡ በቃሉ እና በቃሉ ውስጥ ኑሩ፡፡

እንደ እግዚሃብሄር ቃል ስትኖሩ፣ እግዚሃብሄርን እያስደሰትኩ ነው ወይስ አይደለም ብላችሁ ህይወታችሁን መጠበቅ የለባችሁም፡፡ እርሱን ለማስደሰት እምነት ያስፈልጋል (ዕብራዊያን 11፡6)፣ እምነት ደግሞ ቃሉን ማድረግ ነው፡፡

ጌታ ኢየሱስ በእግዚሃብሄር ቃል ላይ የተራመደን የአንድ ሰው እውቀት እና ጥበብ ይነግረናል፡፡ ጌታ እንዲህ አለ፡- “ቤት ሲሠራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሠረተ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም” (ሉቃስ 6፡48)፡፡

ይህ በያዕቆብ 1፡22-25 ላይ ካነበብነው ጋር ይዛመዳል፡- “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል። ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።”

ህይወታችሁ በቃሉ ላይ ሲመሰረት፣ ሁልጊዜም በከፋ ወጀብ ውስጥ እንኳን ቢሆን ጎልታችሁ በጥንካሬ ትቆማላችሁ፡፡ የእግዚሃብሄር ቃል

ህይወታችሁን በቃሉ ገንቡ

ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል

ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ (1ኛ ጴጥሮስ 1፡23)

ማክሰኞ 20

Page 49: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 5 & መዝሙረ ዳዊት 117-118

የሉቃስ ወንጌል 17:31-37 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 5-6

1 ኛ ጴጥሮስ 1:25; የሐዋርያት ስራ 20:32; የሉቃስ ወንጌል 6:48-49

እናንተ ሳትታገሉ እርሱ እንድትሆኑ የፈለገውን ያደርጋችኋል፡፡ በማቴዎስ 4፡19 ላይ የኢየሱስን ቃል አስታውሱ፡- “ተከተለኝ እና ሰዎችን የምታጠምድ አደርግሃለሁ፡፡”

ማድረግ የነበረባቸው መከተል ብቻ ነበር፡፡ ስኬታማ ያደርጋቸዋል፡፡ ቃሉ በጤና በጥንካሬ፣ በአሸናፊነት ይጠብቃችኋል፣ በህይወታችሁ ሰላምን፣ ብልጽግናን እና ያልተጠበቀ እድገትን ትጎናጸፋላችሁ፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ ሞገስ ስላለው፣ ስለሚያበራው፣ ስለሚያነቃቃው ቃልህ አመሰግንሃለሁ፣ አለማቋረጥም ወደ ከፍታ ይገፋኛል፡፡ በማጥናት እና በማሰላሰል ለቃሉ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተሰጥቻለሁ፡፡ ስለሆነም በጤና፣ በጥንካሬ እናም በአሸናፊነት፣ በሰላምና በብልጽግና እራመዳለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 50: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ሐዋሪያው ጳውሎስ በመክፈቻ ጥቅሳችን ክርስቶስ ስለ እኛ ስላለው ፍቅር አይደለም የሚያወራመው፣ ነገር ግን እኛ ለእርሱ

ስላለን ነው፣ ይህም ፍቅር ከወንጌል እውነታ ጋር- በምንም አይነት ተቃውሞ ውስጥ- ጸንተን እንድንቆም ያደርገናል፡፡ ጳውሎስ ለክርስቶስ ያለው ፍቅር ወንጌልን ለመስበክ ላለው ጉጉት እንዲሁም የወንጌልን እውነት እንዲጠብቅ ከበስተጀርባው ጉልበት ሆኖታል፡፡

ገላቲያ 2፡11-21ን አንብቡ ምን ያክል ጴጥሮስ የወንጌልን እውቀት እንደጠበቀ ያሳየናል፡- ለጴጥሮስ እንኳን አልራራለትም፤ እንዲህ ብሏል፡- “ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና። አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ። የቀሩትም አይሁድ ደግሞ፥ በርናባስ ስንኳ በግብዝነታቸው እስከ ተሳበ ድረስ፥ ከእርሱ ጋር አብረው ግብዞች ሆኑ።” (እስከ ቁጥር 19 ድረስ ያለውን አንብቡት)፡፡

በቁጥር 20 ላይ ራሱን መስጠቱን እንዲህ ብሎ አብራራ፡- “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” ምን አይነት መሰጠት ነው፣ ጉዳያችሁ ስለ እርሱ ስላላችሁ ፍቅር ነው፡፡

ይህ ፍቅር የሚቆጣጠር አስተሳሰብ፣ የህይወታችሁ መመሪያ መሆን አለበት፤ ተቃውሞው ምንም ያክል የበረታ ቢሆን ግድ ሊል አይገባም፣ አለምንም መጠራጠር የክርስቶስን ወንጌል ለመጠበቅ መቆም አለባችሁ!

ምን ያክል ታፈቅሩታላችሁ? በልባችሁ ይህ ፍቅሩ ጠንካራ አይደለም ብላችሁ ካሰባችሁ፣ ማድረግ ያለባችሁ ቀላል ነው፤ ልባችሁን በጸሎት ለእርሱ ክፈቱ፣ እናም ንገሩት “ጌታ ኢየሱስ፣ አፈቅርሃለሁ፣ በእርግጥ አፈቅርሃለሁ፣

እናንተ ስለ እርሱ ስላላችሁ ፍቅር ነው

ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ። (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14)

ረቡዕ 21

Page 51: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 6 & መዝሙረ ዳዊት 119:1-112

የሉቃስ ወንጌል 18:1-8 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 7-8

የማርቆስ ወንጌል 12:30; 1 የዮሐንስ ወንጌል 5:3; የዮሐንስ ወንጌል 14:15-21

በሙሉ ልቤ እናም ለዘላለም ማድረግ የምፈልገው ይህንን ነው፡- አንተን ማፍቀር እና ቃልህን ማድረግ፡፡”

ይህንን የፍቅር አዋጅ ለእርሱ ስታደርጉለት፣ ታላቅ መነሳሳት ይሆንላችኋል፣ ለወንጌል ያላችሁ መሰጠት ይጨምራል፡፡ ምንም ነገር ከምትሰጡት ይልቅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁ ፍቅር ለእግዚሃብሄር ብዙ ነው፡፡ ስለሆነም በሙሉ ልባችሁ አፍቅሩት፣ ቃሉንም በመጠበቅ አረጋግጡለት፡፡ ሃሌሉያ! (ዮሐንስ 14፣15፣21ን ተመልከቱ)፡፡

በሰማይ የምትኖር አባት ሆይ፣ የክርስቶስ ፍቅር ስለ ወንጌል ስላለኝ መሰጠት ታላቅ አነሳሽ ኃይል ስለሆነ አመሰግንሃለሁ፡፡ ወንጌልን እንድሰብክ ያ ፍቅር ግድ ይለኛል፡፡ አለም በሙሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለህን ፍቅር እንዲያቅ በታላቅ መጣደፍ ወንጌልን አሰራጫለሁ፡፡ አሜን፡፡

የእምነት አዋጅ

Page 52: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 53: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 54: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

በዮሐንስ 5፡26 ላይ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት

እንዲኖረው ሰጥቶታልና፡፡” በመግቢያ ጥቅሳችን እግዚሃብሄር ዘላለማዊ ህይወት እንደሰጠን አንብበናል፡፡ ብዙዎች ዘላለማዊ ህይወት እግዚሃብሄር ቃል የገባልን ይመስላቸዋል፤ እንደዚያ አይደለም፤ በክርስቶስ የአሁኑ ሰአት ይዞታችሁ ነው፡፡ አሁን ዘላለማዊ ህይወት አላችሁ፡፡

ዳግም ስትወለዱ የእግዚሃብሄርን ህይወት እና ባህሪይ በመንፈሳችሁ ተቀብላችኋል፤ ይህ በተጨባጭ ሆኗል፡፡ ይህም የዘላለማዊ ህይወት ማለትም የእግዚሃብሄርን ህይወት እና ባህሪይ፣ በሰውነታችሁ ላይ ተጽእኖ ማምጣት አለበት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው እንደዚህ ነው፡- “ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል” (ሮሜ 8፡11)

ክርስቶስ መኖሪያውን በእናንተ ውስጥ ሲያደርግ፣ ከላይ የተቀመጠው ቃል በእናንተ ውስጥ እውን ይሆናል፡፡ ስለሆነም ሞት የማይቀርለት ሟች የሆነው ሰውነታችሁ ህይወት ያገኛል፡፡ አቤት! ቤተ-ክርስቲያን በዚህ እውነታ ላይ ትኩረቷን ብታደርግ! ስለዚህ ነገር እናንተ ሁልጊዜ ይህ ንቃተ ህሊና ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐንስ 5፡13 ላይ ጽፎታል፡- “የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ ዘላለማዊ ህይወት በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ለሚያምን በሙሉ

አስቀድሞ ዘላለማዊ ህይወትን ተቀብላችኋል

እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው

ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም (1ኛ ዮሀንስ 5፡11-12)

ሐሙስ 22

Page 55: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 7 & መዝሙረ ዳዊት 119:113-176

የሉቃስ ወንጌል 18:9-17 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 9

የዮሐንስ ወንጌል 17:1-3; 1 የዮሐንስ ወንጌል 5:11-13

የሰጠው ህይወት ነው፡፡” አንዳንድ ሰዎች ጤና በማጣት የሚታገሉት፣ የዘላለማዊ ህይወትን

ካለመረዳት እና የዚህ ንቃተ ህሊና ስለሌላቸው ነው፡፡ ዘላለማዊ ህይወት አይታመምም፤ ሞት እና ህመም አያጠቃውም፡፡ ሰውነታችሁ የህያው አምላክ ህያው መኖሪያ ሆኗል፡፡ ምን ማለት እንደሆነ ገብቷችኋል?

ቃሉ እንደሚያውጀው፣ እርስቶስ በእናንተ ቢሆን፣ ሰውነታችሁ በሃጢያት ቢሞትም፣ መንፈስ በጽድቅ ህይወትን ይሰጠዋል (ሮሜ 8፡10)፡፡ በቆላስያስ 1፡27 ላይ ጳውሎስ ይህንን አወጀ፡- “የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው”፡፡

እግዚሃብሄር ይባረክ! ክርስቶስ በእኔ ይኖራል! የእርሱ መለኮታዊ ኃይል መለኮታዊ እና አሸናፊ ህይወት እንድኖር የእርሱን መለኮታዊ አላማ እንዳሟላ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች በሙሉ ሰጥቶኛል፡፡ እኔ በመለኮት ክብር እና ከፍታ የተሞላሁ የእግዚሃብሄር ሰው ነኝ፡፡ ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 56: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የሜሴጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የመግቢያ ጥቅሳችንን ባማረ ሁኔታ ይገልጸዋል፡፡ እንዲህ ይላል፡- “በእምነት የጠነከራችሁ

እንደሆናችሁ ራሳችሁን ፈትኑ፡፡ ሁሉንም ነገር እንዳመጣጡ ብቻ የምትቀበሉ አትሁኑ፡፡ ሁልጊዜ ራሳችሁን ፈትሹ…”፡፡ እንደ ክርስቲያን ለራሳችሁ ማድረግ ያለባችሁ ይህንን ነው፤ በእምነት ስራችሁ ምን ያህል እያደጋችሁ እንደሆነ ሀቀኛ የሆነ ግምገማ ማድረግ አለባችሁ፡፡

ለምሳሌ ነፍስ የማዳን ስራችሁን መገምገም አለባችሁ፡፡ ይህንን ሁልጊዜ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡ ስለ ወንጌል ያላችሁን መሰጠት ገምግሙ። ለረጅም ጊዜ ክርስቲያኖች ከሆናችሁ፣ ቃሉን እየተቀበላችሁ ከነበረ፣ በማያቋርጥ ሁኔታ ለክርስቶስ ነፍስ እንድታድኑ መለመን ወይም መባበል የለባችሁም፡፡ በመንፈስ እራሳችሁን ማነሳሳት አለባችሁ፡፡

አስተውሉ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዛሬ ለአለም ብቸኛው ተስፋ ነው፡፡ ለዚህ መንገድ ምንም አይነት መስዋእትነት የበዛ አይደለም፡፡ ጳውሎስ እንዲሀ አለ፡- “ወንጌልን ባልሰብክ ወየውልኝ” (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡16)፡፡ ስለሆነም በነፍስ ማዳን ስራ ላይ የእናንተን አስተዋጽዖ በእውነት ገምግሙ፡፡ “ይህ ለፓስተሮች እና ለቤተ-ክርስቲያን መሪዎች የተለየ ስራ ነው” አትበሉ፤ አይደለም! የእያንዳንዱ ክርስቲያን የግል ኃላፊነት ነው፡፡

ለክርስቶስ ለምታድኑት ነፍስ ግላዊ ግብ አስቀምጡ፤ እናም አድርጉት። በዘር ዘሪው ምሳሌ ላይ እንዳነበብነው ነው፤ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ” (ማቴዎስ 13፡3)፡፡ በመልካም መሬት ላይ የተዘራው ዘር፣ ጥሩ ፍሬን አፈራ፡- “አንዳንዱ መቶ እጥፍ፣ አንዳንዱ ስልሳ እጥፍ፣ እንዲሁም ሰላሳ እጥፍ” (ማቴዎስ 13፡8)፡፡ የተዘራው ቃል “ውጤትን” ያመጣል። ጥያቄው ግን “በየትኛው ደረጃ ነው ውጤትን የምታመጡት ወይንም ለመንግስቱ ነፍሳትን የምትጨምሩት?”

እናንተ እስካሁን ድረስ ልክ ነፍሳችሁን ለክርስቶስ በሰጣችሁት ጊዜ

ነፍስ የማዳን ስራችሁን አሳድጉ

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ

በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? (2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5)

አርብ 23

Page 57: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 8 & መዝሙረ ዳዊት 120-127

የሉቃስ ወንጌል 18:18-27 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 10

ሮሜ 1:16; 1 ኛ ቆሮንጦስ 9:16; መጽሀፈ ምሳሌ 11:30

“በሰላሳ እጥፍ” ደረጃ ላይ ናችሁ? ወደ መቶ እጥፍ ደረጃ ማደግ አለባችሁ? በሌላ አነጋገር ሙሉ በሙሉ አለም እናንተን ብቻ እየጠበቀ እስኪመስል ድረስ ለወንጌል ውጡ፡፡ ለወንጌል ሊኖራችሁ የሚገባው ትክክለኛው ባህሪይ ይህ ነው፡፡

ገምግሙና ለወንጌል ያላችሁን መሰጠት ጨምሩ፤ መሰጠታችሁን ስትጨምሩ፣ ጌታ ደግሞ ለክርስቶስ የበለጠ ነፍሳትን እንድታድኑ ለበለጠ ውጤትና ብቃት ጸጋውን ይሰጣችኋል፡፡ ሃሌሉያ!

ውድ አባት ሆይ፣ ታማኝ አድርገህ ስለቆጠርከኝ፣ በጨለማ ውስጥ የታሰሩትን ወደ እግዚሃብሄር ልጅ ነጻነት እንዳመጣቸው አገልግሎት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በጸጋህ ለእግዚሃብሄር መንግስት ብዙ መኸርን ለማምጣት ከምን ጊዜውም በላይ ለነፍስ ማዳን ተሰጥቻለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 58: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የእግዚሃብሄር ቃል፣ የእግዚሃብሄርን መንግስት ለነፍሳችሁ የሚገልጥ ኃይል አለው፤ ያበራል፡፡ ቃሉን ስታጠኑ እና

ስታሰላስሉ፣ በእናንተ መንፈስ እና በእግዚሃብሄር መንፈስ መካከል መናበብ ይፈጠራል፡፡

በመንፈሳችሁ የእግዚሃብሄር ቃል በበዛ ቁጥር፣ የእግዚሃብሄር መንግስትን በበለጠ ትረዳላችሁ፣ መንግስቱ ደግሞ ለእናንተ በበለጠ እውነታ ይሆንላችኋል፣ የመንግስቱ ንቃተ ህሊና ይኖራችኋል፡፡ አሁን የመንግስቱን ህይወት ትኖሩታላችሁ፤ ትራመዱታላችሁ፡፡ በመንፈሳችሁ ውስጥ በተጠራቀመው እውቀት፣ በመንግስቱ መርሆ ትሰራላችሁ፣ እነዛን መርሆዎች ደግሞ በዚህ አለም ላይ እና በማንኛውም ሁኔታዎች ላይ ትተረጉሟቸዋላችሁ፡፡

ሁልጊዜም የቃሉን አገልግሎት በቁም ነገር ውሰዱት፣ ሆን ብላችሁ ሰአታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ሃብታችሁን፣ መንፈሳችሁን በማስተማር እና በማሰልጠን ላይ አውሉ፡፡ መንፈሳችሁን ለማንጻት እና ለማሳደግ በእኛ አገልግሎት እምነትን የሚገነቡ አስተምህሮቶች ክምችት አለን። በብዙ መልኩ ያሉትን እነዚህን ክምችቶች እዘዙ፡፡ የፓስተር ክሪስን ዲጂታል ላይብረሪ ሰብስክራይብ አድርጉ እናም የመንግስቱ ንቃተ-ህሊና እንዲኖራችሁ አድርገው ህይወታችሁን የሚቀይሩ የድምጽ እና የምስል መልእክቶችን አግኙ፤ ሁሌም አሸናፊ የሆነ ድል አድራጊ ህይወት እንዲኖራችሁ ይረዱአችኋል፡፡

ይህም በቂ አይደለም! በእናንተ አለም ያሉ የጠፉት ወደዚህ መለኮታዊ የሆነ ልምምድ ማለትም ወደ አሸናፊ የሆነው የመንግስቱ ህይወት እንዲመጡ፣ እናንተም እነርሱን መርዳትና ድጋፋችሁን መቀጠል አለባችሁ።

በቃሉ ያለ የመንግስቱ ህይወት

የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና (1ኛ ቆሮንቶስ 4፡20)

ቅዳሜ 24

Page 59: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 9 & መዝሙረ ዳዊት 128-134

የሉቃስ ወንጌል 18:28-34 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 11-12

መጽሀፈ ኢያሱ ወልደነዌ 1:8; 1 ኛ ጢሞቴዎስ 4:15; 2 ኛ ጢሞቴዎስ 3:16-17

ይህ መልእክት ወደ አለም ሁሉ እንዲስፋፋ ሁላችንም ኃላፊነት አለብን፡፡ የተጠራነው፣ ሰዎችን ከጨለማ ለማውጣት እና ወደ ብርሃኑ መንግስት

እንዲገቡ ለማድረግ ነው፤ ኢየሱስም የመጣው ለዚህ ነው፤ “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና” (ሉቃስ 19፡10)፡፡ ዛሬ የእርሱን ህልም ፍሬያማ የምናደርገው እኛ ነን፡፡ ሃሌሉያ!

ውድ አባት ሆይ፣ ብርሃንና እድገትን ወደ እኔ ስላመጣው፣ በመንፈሴ ስላስቀመጥከው ቃልህ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለመንግስቱ ህይወት በቃልህ ተነቃቅቼአለሁ፣ ተምሬአለሁ፣ ሰልጥኜአለሁ፣ አድጌአለሁ እንዲሁም ጠንክሬአለሁ፡፡ በቃልህ ኃይልና ውጤታማ ስራ ለታላቅነት፣ በአሸናፊነት ለመኖር፣ የባለጸጋ ህይወት እንዲኖረኝ ተሰርቻለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 60: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

አንዳንድ ጊዜ፣ ምናልባትም በህብረት ስብሰባ ላይ፣ የትንቢት ቃል፣ ራእይ ወይም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለማየት በመጠባበቅ፤

አንዳንዶች እንደነኛ ዓይነት ነገሮች ስላልተለማመዱ ይደናገራሉ፡፡ነገር ግን፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡32 በኤን ኤል ቲ ትርጉም አንዳንድ ጊዜ

ሁኔታው ምን እንደሚመስል ፍንጭ ይሰጠናል፤ እንዲህ ሲል፡- “ትንቢትን የሚናገሩ ሰዎች ተራቸውን በመጠበቅ ለመናገር መንፈሳቸውን መቆጣጠር ይችላሉ፤” ይላል፡፡ እናንተ ወይም አንድ ሌላ ሰው የትንቢት ቃል ኖሮት ሊናገር ባይፈቅድ፣ እግዚአብሄርን የሚመለከተው ምንም ነገር የለም፤ እርሱ ሊወቀስ አይችልም፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች “የትንቢት ቃልን እግዚአብሄር ከሰጠኝ፤ ንግግሬን እርሱ ተቆጣጥሮ እንድናገር ያደርገኛል!” ብለው ያስባሉ፡፡ የሚሰራው በዚህ መንገድ አይደለም፤ እናንተ መጫወት ያለባችሁ ሚና አለ፡፡ ሌሎችን ለመምከር፣ ለማነጽ እና ለማጽናናት የሚሆን የትንቢት ቃል፤ ለመናገር ወይም ላለመናገር እናንተ ካላችሁ ፈቃድ ጋር አይጣረስም፡፡

እኛ የእግዚአብሄርን ምልክቶች በማስተዋል እርሱ የሰጠንን ለመናገር በመንፈስ ጠንካራና ጥበበኛ ልንሆን ይገባል፡፡ እርሱ ሁልጊዜም እየተናገረ ነው፤ እናንተም እርሱ የሚናገረውን ነገር ለመስማት መንፈሳችሁን ማሰልጠን አለባችሁ፡፡ በዚህ መንገድ፣ እርሱ ሲናገር በቀላሉ መልእክቶቹን ለመያዝና ያንኑ በትንቢት ለመናገር ፈቃድ ይኖራችኋል፡፡

በልባችሁ እርሱን እንዴት መስማት እንደምትችሉ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም፤ የትንቢት ቃሎችን እንዴት መናገር እንዳለባችሁም መማር አለባችሁ፡፡

ስለዚህ፣ በውስጣችሁ የሚንፈቀፈቅ የትንቢት ቃል ሲኖራችሁ፣ ዝም

እርሱ ሁልጊዜ እየተናገረ ነው

እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር

እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። (የዮሐንስራእይ 3፡20)

እሁድ 25

Page 61: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 10:1-13 & መዝሙረ ዳዊት 135-138

የሉቃስ ወንጌል 18:35-43 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 13

1 ኛ ቆሮንጦስ 14:26-32; የዮሐንስ ወንጌል 10:27

አትበሉ ወይንም ከመውጣት አትግቱት፡፡ ሁኔታው በአጠቃላይ ስብሰባ ላይ ሲሆን ተገቢውን ጊዜ ጠብቃችሁ ቃል እንዳላችሁ አስታውቁ ወይንም የትንቢት ቃል ያለው ሰው ካለ ጥሪ ሲደረግ፤ እናንተ እንዳላችሁ ለማስታወቅ ደፋሮች ሁኑ፡፡ እንድትጽፉት ልትጠየቁ ትችላላችሁ፡፡ በየትኛውም ሁኔታ በጉባኤው መሪዎች የሚሰጣችሁን ትእዛዝ አክብሩ፡፡

ከጌታ ጋር ህብረት ስታደርጉ፣ እርሱ በእርግጠኝነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር የሚጣጣሙ ቃላትን ለእናንተ መልሶ እንደሚያገለግላችሁ ሁልጊዜም አስታውሱ፤ ነገር ግን እናንተም እርሱ በልባችሁ ያስቀመጠውን ቃላት በእምነት መናገር አለባችሁ (ሮሜ 12ን ተመልከቱ)፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ ለህይወቴና እኔ እንድንከባከባቸው የሰጠኸን ሰዎች በሚመለከት የአንተን መለኮታዊ ምክር እና ምሪትን ለመቀበል ንቁ ነኝ፡፡ ለአንተ ክብርና ለስምህ ምስጋናን ለማምጣት የክርስቶስን አካል ለማነጽ፣ ለመገሰጽና ለማጽናናት፣ የአንተን ቃል ለመናገር ደፋር ነኝ፡፡ ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 62: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

በሉቃስ 8፡5 ኢየሱስ ክርስቶስ የዘሪን ምሳሌ ተናገረ፤ እንዲህ ሲል፡- “ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ…” (ሉቃስ 8፡5)፡፡ ከዚያም አስራ አንደኛው

ቁጥር ላይ ዘሪው የዘራው ዘር የእግዚአብሄር ቃል መሆኑንን አስረዳ፡፡ ነገር ግን፣ አንድ ልናስተውለው የሚገባ ነገር ቢኖር “ዘርን ሊዘራ ገባ” እንዳላለ ነው:: ይልቁኑ፤ ቃሉን ለመዝራት ወጣ! ይለናል፡፡ ስለዚህ ቃሉን ውጪ ላሉት የማገልገል ሃላፊነት አለብን፤ ቃሉን ለመዝራት መውጣት አለብን፡፡

በማርቆስ 16፡15 ላይ ያለውን ታላቁን ጉዞ ማለትም ታላቁን ተልእኮ ያስታውሰናል፡፡ ጌታ እንዲህ አለ፡- “…ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ከዚያም በሃያኛው ቁጥር ላይ እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር። “ ይላል፡፡ ቃሉን ለመዝራት ማለትም ለመስበክ ወጡ፡፡

ኃጥያተኞች ያሉት ከውጪ በዓለም ነው፤ የእኛ ተልእኮ መስክ እዚያ ነው፤ በየጉራንጉሩ የተሰበረ የሰው ልጅ ባለበት፣ በህይወት በተሰናከለው መካከል ነው፡፡ የእኛ ስራ ወንጌልን ወደ እነርሱ መውሰድ ነው፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ የእግዚአብሄር የማዳን ኃይል ነውና፡፡

ስለዚህ በምንም ስራ ላይ ብትሆኑ ቃሉን ዝሩ፣ ቃሉን ስበኩ፡፡ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነፍሳትን አድኑ፤ ምክንያቱም ጊዜው አጭር ነው። የማይሸበርና ነፍሳትን ለማዳን በምታደርጉት ጥረት ቁርጠኛ ሁኑ፡፡ ለጠፉ ነፍሳት ያላችሁ ጥልቅ ስሜት አይሸርሸር፡፡

ባይሰሙኝስ? ልትሉ ትችላላችሁ፤ ስለዛ አትጨነቁ፡፡ ኢየሱስ አስቀድሞ የዘሪን ምሳሌ ሲነግረን ስለምናገኛቸው የተለያዩ ምላሾች ነግሮናል (ማርቆስ 4፡4-8ን ያንብቡ)፡፡ በእርግጠኝነት የሚሰሟችሁና ቃሉ የጽድቅን ፍሬ የሚያፈራላቸው አሉ፡፡ የእኛ ደስታና ትኩረት ይህ መሆን ይገባዋል፡፡

የምነጋገኛቸው ምላሾች ምንም ይሁኑ ምን፣ ቃሉን መዝራት፣ በመቀጠልም መዝራት ኃላፊነታችን ነው፡፡ ጌታ የዘር ከረጢትን ሰጥቷችኋል፤ ያ ማለት በመንፈሳችሁ ውስጥ ቃሉን ሰጥቷችኋል፤ ለራሳችሁ ይዛችሁ አታስቀሯቸው፡፡ የጠፉትን አሳምኑ፤ በወንጌሉ አማካኝነት እግዚአብሄር

ቃሉን መዝራት

ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ…(ሉቃስ 8፡5)

ሰኞ 26

Page 63: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 10:14-11:1 & መዝሙረ ዳዊት 139-141

የሉቃስ ወንጌል 19:1-10 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 14

1 ኛ ቆሮንጦስ 9:16; 2 ኛ ቆሮንጦስ 5:18-20

እንዴት ያለውን ታላቅ ፍቅሩን እንደሰጣቸው ንገሯቸው፡፡2ኛ ቆሮንቶስ 5፡11 እንዲህ ይላል፡- “እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን

ሰዎችን እናስረዳለን፡፡” እናንተ ለድነት ማለትም ኃጥያተኞችን ከጨለማ ወደ ብርሃን እና ከሰይጣን ኃይል ወደ እግዚአብሄር ለማምጣት ተቀብታችሁ፣ የእግዚአብሄር ወኪሎች ማለትም ከሰራተኞቹ በተለየ ሁኔታ የተመዘገባችሁ ናችሁ፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ አስደናቂውን የክርስቶስን ወንጌል ታጥቄ የመጨረሻው ዘመን ነፍሳትን አዳኝ አድርገህ ስለመዘገብከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በእኔ ውስጥ በሚሰራው ጸጋህና ኃይልህ፣ ብዙዎችን ወደጽድቅ እየመራሁ፣ በዓለም ዙርያ ወንጌሉን በፍጥነት ለማሰራጨት እተጋለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 64: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ዮሐንስ ምዕራፍ 6 ኢየሱስ የሰራውን አስደናቂ ተአምር መዝግቧል፡፡ ወደ አምስት ሺህ ሰዎችን አስተምሮ እንደጨረሰ

ነበር (ሴቶችንና ህጻናትን ሳይጨምር)፡፡ ህዝቡ ለረዥም ሰዓታት በዚያ እንደነበሩ ተገንዝበው፣ ከደቀመዛሙርቱ አንዳንዶቹ ለራሳቸው ምግብ ያገኙ ዘንድ እንዲሄዱ ጠየቁት፡፡

ነገር ግን፣ ኢየሱስ “በእጃችሁ ምን አለ?” በማለት ጠየቀ፡፡ እንድርያስም “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ያ ግን ለዚህ ቁጥር ህዝብ በባልዲ ውስጥ ያለ አንድ ጠብታ እንደማለት ነው፡፡” ብሎ መለሰለት (ዮሐንስ 6፡9 የኤም ኤስ ጂ ትርጉም)፡፡ ኢየሱስ ጥርጣሬያቸውን ችላ በማለት ደቀ መዛሙርቶቹ ህዝቡ ለመመገብ እንዲቀመጡ እንዲነግሯቸው አደረገ፡፡

ኢየሱስ በዛ ግርግር ውስጥ አንድ ነገር ማድረግ ነበረበት፤ ስርዓት እንዲኖር ጠየቀ፡፡ እንዲህ አለ፡-“ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ ቍጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር” (ዮሐንስ 6፡10)፡፡ በህይወታችሁ ስርዓት ለመጠበቅን ተማሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በተቃወሰ ሁኔታ ውስጥ መስራት አይችልም፡፡ በመንፈሳችሁ ውስጥ ስርዓት አልባነት እስካለ ድረስ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ውጤታማ የሆነ መመላለስ ሊኖራችሁ አይችልም፡፡ እርሱ ግራ መጋባትን የሚያመጣ አይደለም (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡33)፡፡

ተአምር እንዲሆንላችሁ ከፈለጋችሁ፣ ስርዓት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል። በብዙዎች ህይወት ውስጥ የሌለው ይህ ነው፤ ከዛ ተአምራት የማይሆንላቸው ለምን እንደሆነ ግራ ይጋባሉ፡፡ በእንድ ወይም በሌላ መልኩ፣ ራሳችሁን መቼም ቢሆን ከስርዓት ውጪ ሆኖ እንዳታገኙት፤ ያም ማለት ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ተቃራኒ የሆነ ዓላማ አይኑራችሁ፡፡ ለነገሮች የተቀመጡትን ስርዓቶች ማለትም ቃሉን ተከተሉ፡፡ መለኮታዊ ውጤቶችን ከፈለጋችሁ፣ በቃሉ

ስርዓትን መጠበቅ

ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን። (1ኛቆሮንቶስ 14:40)

ማክሰኞ 27

Page 65: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 11:2-34 & መዝሙረ ዳዊት 142-145

የሉቃስ ወንጌል 19:11-19 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15

1 ኛ ቆሮንጦስ 14:40; ዕብራውያን 8:5

መሰረት ነገሮችን አከናውኑ፡፡ ሙሴ ድንኳኒቷን ሊሰራ ሲል፣ ጌታ በታዘዘው ስርዓት መሰረት

እንዲሰራ እንዳስጠነቀቀው አስተውሉ (ዕብራውያን 8፡5)፡፡ ነገሮችን በራሳችሁ “መንገድ” ልትሰሩ ትችላላችሁ፤ የእግዚአብሄር ነገሮች ደግሞ በእግዚአብሄር መንገድ መሰራት ይገባቸዋል፡፡ እናንተ ስርዓት አልባ ከሆናችሁ አያከብራችሁም፡፡

ስርዓት ጠብቁና፣ ነገሮች ወደፊት ሲሄዱ ተመልከቱ፡፡ ለምንም ነገር ወይም ነገሮች እንደከናወኑ መታገል አያስፈልጋችሁም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ብርሃን ማለትም በእርሱ የአሰራር ስርዓቶች እስከተመላለሳችሁ ድረስ፣ ሁልጊዜም የእርሱ ክብርና ጸጋ ይኖራችኋል፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ እኔ ለቃለህ ሙሉ በሙሉ ተገዝቻለሁ፤ ስርዓታዊ በሆነ መልኩ በአንተ መለኮታዊ ትዕዛዛት መሰረት እመላለሳለሁ፡፡ ስርዓት አልባ፣ ከቁጥጥር ውጪ፣ ስነ ምግባር የሌለው ወይም የማይታዘዝ መሆንን አሻፈረኝ እላለሁ፡፡ ካለምንም ማወላወል ትዕዛዛትህን በፍጥነት እፈጽማለሁ፡፡ ስለሆነም በየዕለቱ የተአምራት ህይወትን እኖራለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 66: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ሐዋርያው ጳውሎስ በአገልግሎቱ ጊዜ ብዙ መከራን ተቀብሏል። እጅግ በብርቱ ተሰዷል፡፡ የመክፈቻ ጥቅሳችንን በድጋሚ

አንብቡ፡፡ በተለያየ ጊዜ ከሞት ጋር ተፋጧል፤ በአንድ ወቅት በእስር እያለ በጓደኞቹ ሁሉ ተከድቶ ነበር (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15)፡፡

ምንም እንኳን ለወንጌሉ ሲል ስቃይ ቢቀበልም በሮሜ 5፡3 ያለውን የሚነሳሳ ቃላት ጽፏል፡፡ ከፊሉ እንዲህ ይላል፡- “…በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤”፡፡ የተባረከ አስተሳሰብ! ይህም ማለት አስቸጋሪ ጊዜዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ለእኛ ክብር ናቸው፤ በመከራ እንመካለን፡፡ ሃሌሉያ!

ያዕቆብ፣ በያዕቆብ 1፡2 ላይ የተናገረው ይህንኑ የሚደግም ነው፡- “የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፡፡” ችግሩ ወይም የተጋረጠባችሁ መከራ ምንም ይሁን ምን፣ ደስ ይበላችሁ፡፡ ዛሬ የተጋረጠባችሁ ተግዳሮት ምንም ዐይነት ቢሆን፣ በእናንተ ልክ የተሰፋ ነው፤ ለእድገታችሁና ለክብራችሁ ነው፡፡

ስለዚህ፣ ልባችሁ አይታወክ፡፡ ዛሬ ነገሮች ከባድና አስቸጋሪ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ከውጪ ሁኔታዎች ሲታዩ፣ ቃሉን ማወጃችሁና ለወንጌሉ መሰጠታችሁ ውጤት አልባ ሊመስል ይችላል፡፡ ሳትናወጡ እዚያው ቆዩ! በክርስቶስና በዘላለማዊ ቃሉ ላይ ትኩረታችሁን ቀጥሉ፡፡

2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16 ላይ ጳውሎስ በሚያነሳሳ መንገድ ያስቀመጠውን እወደዋለሁ፡፡ እንዲህ አለ፡- “ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።” እኛ የምንጠፋ አይደለንም፡፡ እርሱ በቁጥር 17 እና 18 እንዲህ ሲል ቀጠለ፡- “የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤

በመከራ መመካት

እንደ እብድ ሰው እላለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ በድካም አብዝቼ፥ በመገረፍ አብዝቼ፥ በመታሰር አትርፌ፥ በመሞት

ብዙ ጊዜ ሆንሁ። አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ። ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ

ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤… (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡23-25)

ረቡዕ 28

Page 67: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 12 & መዝሙረ ዳዊት 146-150

የሉቃስ ወንጌል 19:20-27 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16

የማቴዎስ ወንጌል 5:10-12; የሐዋርያት ስራ 20:22-24

የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።” ቃሉን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ልክ እንደ አብርሃም፣ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ

ተስፋ ይዞ አመነ (ሮሜ 4፡18)፡፡ ሮሜ 12፡12 በተስፋ ደስ እንዲለንና በመከራ እንድንታገስ ይነግረናል፡፡ ምሽቱ ድቅድቅ ጨለማና ረዥም ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ንጋት ላይ ደስታ እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር ይሁን!

ተስፋዬ በጌታዬ በክርስቶስ ነው፤ በመንገዴ ፈተናዎችና መከራዎች ቢመጡም እንኳን፣ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለእኔ በተዘጋጀልኝ በደማቁ የክብር አክሊል ላይ ባለኝ እርግጠኛ ማስተማመኛ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ወዳለኝ ታላቅ የጥሪ ሽልማት እያቀናሁ፣ በእምነት ወደፊት እጓዛለሁ፡፡ ለእግዚአብሀር ክብር ይሁን!

የእምነት አዋጅ

Page 68: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 69: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 70: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

ዳንኤል 12፡3 እንዲህ ይላል፡- “ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ …እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።” “ይደምቃሉ” የሚለው

ቃል “ዛሃር” ከሚለው ከእብራይስጥ ቋንቋ የተተረጎመ ሲሆን፣ ካሉት ከሌሎቹ ትርጉሞቹ በተጨማሪ ማነሳሳት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እናንተ የተጠራችሁት ሌሎችን ለማነሳሳት እና ለመምራት ነው፡፡ እናንተ ምሳሌ ናችሁ፡፡

እርሱ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ “(ማቴዎስ 5፡14) ሲል ይህንን ማለቱ ሲሆን አስቀድሞ እንደተገለጸው ብርሃን መሪነትን ይሰጣል፡፡ ይህ እንደ ክርስቲያን ያላችሁን ጥሪ ያሳውቃችኋል፡፡ ነገር ግን ጥያቄው እናንተ ሌሎችን እንዴት እያነሳሳችሁ ነው?

ይህ መንፈሳዊ ነው፡፡ ጉዳዩ ስንቶች እንደ እናንተ ሊለብሱ እና ጸጉራቸውን ሊፈሸኑ ስለመፈለጋቸው አይደለም፡፡ ስለእናንተ የሚያነሳሳው ነገር ያ ብቻ ከሆነ በቂ አይደለም፤ ምክንያቱም እነኛ ነገሮች ሥጋዊ ነገሮች ናቸውና፡፡ ሰዎች በህይወታችሁ ባለው የመንፈስ ቅዱስ ስራ እንዲነሳሱ አድርጉ፡፡ በዙርያችሁ ላሉ ሰዎች በእናንተ ውስጥ ያለው የእግዚአብሄር ብርሃንና ጥበብ ከመታየቱ የተነሳ ስትናገሩ ከእናንተ ጥበብ እየወጣ ሌሎች ሰዎችን እስኪባርክ ድረስ ይሁን፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ በመክፈቻ ጥቅሳችን ያነበብነውን ጥልቅና ደፋር ንግግር ተናገረ፡፡ እናንተስ በዙርያችሁ ላሉ ያን የመሰለ ንግግር መናገር ትችላላችሁ? ህይወታችሁን በእግዚአብሄር ሞዴል አድርጉት ሳይሆን ያለው፣ ምንም እንኳን በውስጡ ያ እንድምታ ቢኖረውም፣ ይልቁኑ እርሱ ያለው

እናንተ ምሳሌ ናችሁ

ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን

ተመልከቱ። (ፊልጵስዮስ 3፡17)

ሐሙስ 29

Page 71: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 13 & መጽሀፈ ምሳሌ 1-2

የሉቃስ ወንጌል 19:28-40 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 17

1 ኛ ተሰሎንቄ 1:4-7; የማቴዎስ ወንጌል 5:14-16

የእኔን ምሳሌ ተከተሉ ነው፡፡ተመሳሳይ አስተሳሰብ ይኑራችሁ፤ ምክንያቱም እናንተ እግዚአብሄርን

የሚመስል ሰዎች ማለትም በዓለማችሁ ውስጥ ክርስቶስን የሆናችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡ እናንተ በጨለማው ዓለም ብርሃን ናችሁ፤ ስለሆነም ከምንጊዜውም በላይ አብሩ፡፡ ዓለማችሁን አነሳሱ፡፡ ለዛ ኃይልን አግኝታችኋል፡፡ የጌታን መንገድ አሰልጥኑ፤ ሌሎችን አነሳሱ፤ ለሌሎች አሰልጣኝና ምሳሌ ሁኑ፡፡ ሰዎች መልካም ስራችሁን አይተው ጌታን ያክብሩ፡፡

ዓለሜን ላበራ የተላክሁ፤ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፡፡ ይህ በህይወት ያለኝ ጥሪዬ ነው፡፡ በሄድኩበት ሁሉ ምሳሌ ነኝ፤ ሴቶች እና ወንዶን ልጆችን ወደ ጽድቅ እያመጣሁ፣ ልክ እንደ ሰማያት ብርሀን አበራለሁ፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር ይሁን!

የእምነት አዋጅ

Page 72: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

አሁን ባለንበት ዓለም፣ የትዕግስት ማጣት ንፋስ በኃይል እየነፈሰ ነው፡፡ ቁጣቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ሰዎችን ማግኘት

የተለመደ ነው፡፡ ትናንሽ ነገሮች ያናድዷቸዋል፤ እናም ከክርስቲያኖች የማይጠበቅ ንዴትን ያሳያሉ፡፡ “ያንን ወንድም ወይም ያቺን እህት ማየትም አልፈልግም” የሚሉ ንግሮችን ሲናገሩ ይስተዋላሉ፡፡“ ስለቤተክርስቲያናቸው እንኳን የማያቋርጥ ማጉረምረም እና ንጭንጭ አላቸው፡- “ይህ ስፍራ ያስጠላኛል፤ በአግባቡ አልተያዘም፤ ወደዚህ ቤተክርስቲያን በቀጣይነት የምመጣ አይመስለኝም፡፡ “መቋቋም የማይችሏቸው ሰዎች፣ ቦታዎች እና ነገሮች አሏቸው፡፡ እንደዚያ አትሁኑ!

ነገር ግን እስቲ አስቡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “በመንፈሱ (በእግዚአብሄር) ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች።” (ኢዮብ 16፡13) መንፈስ ቅዱስ አለምን በሙሉ ፈጥሯል፤ ሰመያትን አስውቧል፤ እንደዚያ ሆኖ ግን በእናንተ ውስጥ እስኪኖር ድረስ ትሁትና ቸር ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ታላቅነቱና ዕጹብ ድንቅነቱ፣ እናንተ የእርሱ መኖርያና ህያው ማደሪያ እንድትሆኑ ብቁ አድርጎ ቆጥሯችኋል፡፡ ፍጹም ባልሆነው ባህርያችሁ እንኳን ይንህን/ ያቺን አልፈልገውም/አልፈልጋትም አይላችሁም፡፡

ታዲያ በምንም ምክንያት ይሁን አንድን ሰው መቋቋም አልችልም ወይም አልወደውም ለምን ትላላችሁ? ለምን አንድን ሰው ትጠላላችሁ ወይም ትሸሻላችሁ? በእናንተ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ሊኖር ከመጣ፤ ትሁታን ሁኑ፡፡ እርሱን ምሰሉ፤ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል¬፡- “እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ

ከፍቅር ጋር ግንኙነት ይኑራችሁ

እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ

ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ። (ቆላስይስ 3፡13)

አርብ 30

Page 73: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኛ ቆሮንጦስ 14 & መጽሀፈ ምሳሌ 3-4

የሉቃስ ወንጌል 19:41-48 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 18

ኤፌሶን 4:2; 1 ኛ ጴጥሮስ 4:8; 1 ኛ ተሰሎንቄ 4:9

ወደዳችሁ … “ (ኤፌሶን 5፡1-2):: ትኩረታችሁ እርሱ ይሁን፤ ኢየሱስን ከወደዳችሁት ከሌሎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ይታያል፡፡

የመክፈቻ ጥቅሳችን “እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥…” ይላል፡፡ በክርስቶስ ወንድሞቻችሁና እህቶቸችሁ የሆኑ ሰዎችን ለማቅረብና ለመታገስ ትሁት ሁኑ፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ሲናገር “…ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ…” (ሮሜ 12፡3) ይላል፡፡ እግዚአብሄር ስለራሳችሁ ከፍ ያለ አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ይጠብቃል፤ ነገር ግን፣ ራሳችሁን ከሌሎች የበለጠ አድርጋችሁ በትዕቢት ማሰብ የለባችሁም፡፡

የጥላቻና የትእግስት ማጣት ባህርይን ስታሳዩ ራሳችሁን ካገኛችሁት፣ ሆን ብላችሁ በቃሉ ባህርያችሁን ለውጡ፡፡ በህይወታችሁ ያለውን የእግዚአብሄር ፍቅር ብቻ ማሳየታችሁን አረጋግጡ፡፡

በሙሉ ትህትና፣ረጋ ባለና በትእግስት ሁሉ፣ ለዓለሜ የእግዚአብሄርን ፍቅር በሙላት እየገለጥኩ፣ ከሌሎች ጋር ያለኝ ግንኙነት በፍቅር ነው፡፡ ፍጽም ያለመሆናቸውን እና ጉድለታቸውን በመረዳት፣ ለሌሎች ታጋሽ፣ ደግ እና ርህሩህ ነኝ፤ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር ፍቅር በልቤ ውስጥ ፈሷልና፡፡

የእምነት አዋጅ

Page 74: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

amharic

የክርስቶስን ቤተክርስቲያን መገንባት

እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።

(ማቴዎስ 16፡8)

ቅዳሜ 31

ቤተክርስቲያን ለኢየሱስ ክርስቶስ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ኤፌሶን 5፡ 29-30 እንዲህ ይላል- “…ነገር ግን የአካሉ ብልቶች

ስለሆንን፥… “:: ቤተክርሰቲያን የእርሱ አካል ናት፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኔን እሰራለሁ ሲል፣ እየተናገረ የነበረው ስለክርስቶስ አካል ነው፤ ያ ደግሞ እናንተ እና እኔ ነን፤ በዓለም ዙርያ ያሉ የእኛ እህቶችና ወንድሞች ናቸው፡፡ ነገር ግን ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላ እንዴት ቤተክርስቲያኑን ሊገነባ ይችላል?

መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤…ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥…ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።” (4፡11-12)፡፡ በዚህ ላይ “ሕንጻ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “መገንባት”ን ሲሆን የክርስቶስ አካልን ከመገንባት ጋር የተያያዘ ተመሳሳይ ቃል ነው፡፡ ስለዚህ የአምስቱ የአገልግሎት ስጦታዎች ዓላማ የክርስቶስን አካል መገንባት ነው፡፡ እርሱ አካሉን በእኛ አማካኝነት እየገነባ ነው፡፡

ባሉን ግንኙነቶች ወንዶችና ሴቶችን ወደ ክርስቶስ እየመራን እኛ ሁላችን ነፍሳትን ለማዳን ስንሰጥ፤ ኃያሉን የእግዚአብሄርን ገናና መዋቅር እየገነባን ነው! አስታውሱ፣ ሰለሞን ለእግዚአብሄር ቤትን ሲገነባ ለኪራም መልእክትን ልኮ እንዲህ አለው፡- “እባክህ የሚያስፈልጉኝን ቁሳቁሶች ላክልኝ፡፡ ለእግዚአብሄር ልሰራው የምፈልገው ቤት ዕጹብ ድንቅ የሆነ ህንጻ ነው፡፡” አለው (1ኛ ነገስት ምዕራፍ 5ን ያንብቡ)፡፡

ዛሬ የክርስቶስ አካል ከዚያ የበለጠ ዕጹብ ድብቅ ነው፡፡ ሃሌሉያ!

Page 75: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

እኔ የአካሉ ብልት የሆንኩ አባል ነኝ፡፡ የህይወትን ጠላቶች በሚቃወም እምነት እየጠነከርኩ ነው፤ ዛሬና ሁሌም በአስደናቂ ሁኔታ አሸንፋለሁ፡፡ ጌታ አካሉን በእኔ አማካኝነት ማለትም በእኔ ጠቃሚ የወንጌል ስርጭት ተሳትፎ እየገነባ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን!

የእምነት አዋጅ

1 ኛ ቆሮንጦስ 15:1-34 & መጽሀፈ ምሳሌ 5-7

የሉቃስ ወንጌል 20:1-8 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 19

1 ኛ ቆሮንጦስ 12:27; ኤፌሶን 1:22-23

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ እንደማናርፍ ይናገራል (ኢሳያስ 62፡7)፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ በምድር ገጽ ላይ ካሉ ህያው ነገሮች ሁሉ በበለጠ የተዋበች እስክትሆን ድረስ አናርፍም ማለት ነው፡፡ ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን!

በተጨማሪም የዛ አካል አባላት እንደመሆናችሁ መጠን፣ በየትኛውም ሥፍራ ላይ የነበራችሁ ቢሆን ግድ አይልም፤ በጥንካሬ እየተገነባችሁ ነው፤ እምነታችሁ እያደገ ነው፤ በየዕለቱ እየጠነከራችሁ ነው! በሐዋርያት ሥራ 20፡32 ላይ እንዲህ ብሏል፡- “አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።”

Page 76: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

በዚህ መጸሐፍ እንደተባረካችሁ እናምናለን፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን በሕይወታችሁ ጌታ እንድታደርጉ እንጋብዛችኋለን፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ኢሱስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፤ በሙሉ ልቤ አምነለሁ ፡፡ ለእኔ ሲል እንደሞተ እና እግዚአብሔርም ከሞት እንዳስነሳው አምናለሁ፡፡ ዛሬ ሕው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ኢየሲስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ እንደሆነ በአፌ አውጃለሁ፡፡ በእርሱ በኩል እና በስሙ ዘላለማዊ ሕይወት አለኝ፡፡ዳግም ተወልጃለሁ፡፡ ጌታሆይ ነብሴን ስላዳንካት አመሰግንሀለሁ! አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡፡ ሀሌሉያ!

እንኳን ደስ ያልዎት፤ አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ኖት፡፡ እንደክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወትዎ እንዲያድጉ ከኋላ በተጻፈውን ስልክ ቁጥር ይደውሉ፡፡

የደህንነት ጸሎት

amharic

united kingdom: +44 (0)1708 556 604+44 (0)08001310604

nigeria:01-8888186

canada:+1-647-341-9091

usa:+1 (0) 980-219-5150+1-281-759-5111

south africa: +27 11 326 0971

Page 77: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Pastor Chris Oyakhilome, the President of Believers’ LoveWorld Inc., a dynamic, multifaceted, global

ministry, is the author of Rhapsody of Realities, the world’s #1 daily devotional, and more than 30 other books. He’s a dedicated minister of God’s Word whose message has brought the reality of the divine life to the hearts of many.

Millions have been affected by his television broadcast, “Atmosphere For Miracles,” which brings God’s divine presence right into people’s homes. The scope of his television ministry extends throughout the world with LoveWorld satellite television networks, delivering qualitative Christian programming to a global audience.

A t the wor ld - renowned Hea l ing Schoo l , he manifests the heal ing works of Jesus Christ and has helped many receive healing through the operation of the gifts of the Spirit.

Pastor Chris has a passion to reach the peoples of the world with God’s presence—a divine commission he’s fulfilled for more than 30 years through various outreaches, crusades, as well as several other platforms that have helped millions experience a victorious and purposeful life in God’s Word.

ABOUT THE AUTHOR

Page 78: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 79: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 80: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - cedmvas.org€¦ · 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic