በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 ·...

14
2010 .አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የሁሉም አራተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የተጠቃለለ የሱፐርቪዥን ሪፖርት /ሚኒስቴር ግንቦት/2010

Upload: others

Post on 12-Mar-2020

26 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የሁሉም አራተኛ

ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የተጠቃለለ

የሱፐርቪዥን ሪፖርት

ት/ሚኒስቴር

ግንቦት/2010

Page 2: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

1

1. ቁልፍ ተግባርን በተመለከተ

1.1 የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት አደረጃጀትና አሠራር

በጥንካሬ የታዩ

የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት በመምህራንና በአስተዳደር ሰራተኞች በአብዛኛው

በመመሪያው መሰረት በማደራጀት የግንኙነት አግባብ ተዘርግቶ ጅምር እንቅስቃሴ መኖሩና፡

የተቋማቱ አደረጃጀቶች ለትምህርት ጥራት አልሞ እንዲሰሩ በማድረግ አደረጃጀቶችን ወደ

ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡

በራያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችየትምህርትናየቴክኖሎጂልማትሠራዊትበ1ለ5 ቡድን የተደራጁ

ሲሆን ለሌሎች ተቋማት በአርአያነት ሊጠቀስ በሚችል ሁኔታ ተከታታይ ውይይት በማድረግ

እርስ በርስ እንዲረዳዱ በሚያስችል ሁኔታ በተጨባጭ እየተከናወነ መሆኑ፤

በአንዳንድ ወቅታዊ ያለመረጋጋት ችግር ተከስቶባቸው በነ በሩ ተቋማት (እንደ አርሲ

ዩኒቨርሲቲ)የህዝብክንፉንለይቶ በጋራእቅድወደሥራበመገባቱ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ጤናማ በማድረግ

ሐብትና ንብረት ከብክነ ትና ከጥፋት ከመታደጉ ባሻገር በየደረጃው ያለው የአደረጃጀት የከፍተኛ

አመራር፣ የመካከለኛ አመራር፣ የታችኛው አመራር፣ የመምህራን፣ የአስተዳደር የሰራተኞችና የተማሪዎች

አደረጃጀቶችን ጭምር በመጠቀም የነ በረውን ወቅታዊ ሁኔታ በመቋቋም የትምህርት ብክነ ት ሳይከሰት ጠንከራ

በሆነ ህብረትና አንድነ ት መወጣት መቻሉ፣

በክፍተት የታዩ፡ -

በአብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች በተከሰተው ወቅታዊ ችግር ምክንያት (በተወሰኑ ተቋማት) እና

ተቋማት አዲስ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች በመኖራቸው

የተነሳ የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት ግንባታ በአዲሱ የአደረጃጀት መመሪያ መሰረት

በእቅድ እየተመሩ ፣ ተከታታይነት ያለዉ ዉይይት በማድረግ ሁሉም የተቋሙ አደረጃጀቶች

ያሉባቸዉን ዉስንነቶች እየፈቱ ወደ ተቀራረበ የመፈጸም ደረጃ ለመምጣት አልሞ በመሰራት

ላይ ውስንነቶች በስፋት መታየታቸው፣

ተማሪዎች በአደረጃጀታቸው አማካይነት ተቀራርበው በመረዳዳት ወደ ተሻለ ብቃት ደረጃ

መድረስ ሲገባቸው ለአሳይመንት እና ለቡድን የቤት ስራ መስሪያ ብቻ አድርገው መጠቀማቸው

ከተቀመጠለት ዓላማ አንጻር የሚፈለገው ውጤት መጥቷል ለማለት የማይቻል መሆኑ

Page 3: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

2

1.2 የመልካም አስተዳደር ስራዎች በተመለከተ፡ -

በጥንካሬ የታዩ፡ -

በአንዳንድ 4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎ የአገልግሎት አሰጣጥ የእርካታ ደረጃ ዳሰሳ ጥናት በተለይ በተማሪዎች

አገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ የተማሪዎች አገልግሎት እርካታ

የተለካ መሆኑና ለዩኒቨርሰቲዎች አመራር አቅጣጫ ወይም ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል እንደግብዓት ሊያገልግል

የሚችል ግብዓት መገኘቱ፤

አብዛኞቹ ተቋማት ለመምህራንና ለአሰስተዳደር ሰራተኞች ፍትሃዊ የትምህርትና የስልጠናእድል አሰጣጥ ግልፀኝነ ት

አሰራርን የተከተለ መሆኑና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሊያስነ ሳ ማይችል አሰራር መፈጠሩና በየደረጃዉ ያለው

አመራር ብቃትንና ተጠያቂነ ትን መሰረት ያደረገ ፍትሃዊ የውድድርና አመዳደብ እንዲሁም የሥልጣን አጠቃቀም

ስርዓት የተዘረጋ መሆኑ፣

ተማሪዎች ቅሬታ ወይም አቤቱታ ሲኖራቸዉ በነ ጻነ ት በማቅረብ መፍትሄ የሚያገኙበት ስርዓት መዘርጋቱ፤ እንደ

ማሳያ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ.) መምህራኖች ተማሪዎቻቸዉን “የበኩር ልጅ” በሚል አስተሳሰብ በመካከላቸዉ ጠንካራ

ግንኙነ ት እንዲኖር ማድረጋቸው (

እንደ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሀሰት የትምህርት ማስረጃ የሚጠቀሙ ማህብረሰብን ዜሮ ለማድረስ

የአመራሩን፣ የመምህራን፣ የሰራተኞችንና የምሩቃን ትምህርት ማስረጃ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ

መጀመሩ፤

እንደ ቀብሪዳህር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከተቋሙ ወደ ከተማ፣ ከከተማ ወደ ተቋሙ

በሚጓጓዙበት ጊዜ ቀብሪደሀር ከተማ አስተዳደር የህዝብ ትራንስፖርት በተማጣጣኝ ዋጋ

ተማሪዎች መታወቂ አሳይተው የሰርቪስ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ፤

በክፍተት የታዩ

የውሃና የመብራት ችግር ለመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት እየሆነ መምጣቱ፣ለሰለማዊ

የመማር ማስተማር ስራም ሆነ አስተዳደራዊ ስራውን ከማወኩ ባሻገር ዩኒቨርስቲዎችን

ለተጨማሪ ወጭ እየዳረገ መሆኑው ይገኛል፡፡

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ችግርን ለመቅረፍ ያደረገው ስራ የሚደነቅ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው

የውሃ ችግር በዘላቂነት መፈታት አለበት፡፡ የንፁህ ውሃ ችግር ተማሪዎች ለህመም( ለበሽታ

መነሻ) ምክንያት እየሆነ መምጣቱን እና በጣም ከፍተኛ የሆነ የመብራት መቆራረረጥ መኖሩን

ተማሪዎች በምሬት ያነሱት በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ነው

ዩኒቨርስቲው በሚያሰራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የአካባቢው ስራ አጥ ወጣቶች

ተደራጅተው የስራ እድል የሚፈጠርላቸው ሁኔታ ላይ ዩኒቨርስቲው እየሰራ አይደለም የሚሉ

ቅሬታዎች ተነስተዋል፣( ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ)

Page 4: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

3

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት በቂ እንዳልሆነ

በመምህራን መድረክ በስፋት ተነስቷል ለዚህም አማራጮችን መጠቀም ቢቻል / ሰራተኞች

በግቢው ምግብ አገልግሎት እንዲገኙ ቢደረግ እና፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱን አሰጣጥ

መፈተሽና ማስተካከል አለበት፡፡

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የየትኛው ጀነሬሽን አካል እንደሆነ ተለይቶ አለመታወቁ!

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሌሎች የአካበቢው ያሉ መስሪያ ቤቶች የሚከፍሉትን የበረሃ

አበል (hardship allowance) ለእነርሱ ባለመከፈሉ ቅሬታ መፍጠሩ፤

በቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲ የጽዳት ሰራተኞችን ቁጥር በፐብሊክ ሰርቪስ ሚኒስቴር ተቀንሶ

እንደተላከና አሁን ባለው ሁኔታ የተላከው የሰው ሀይል ለተቋሙ ስራ በቂ አለመሆኑን

መገለፁ፣

በአብዛኛው ተቋማት የተሽከርካሪ ችግር መኖሩ የተገለፀ በመሆኑ በትኩረት ቢሰራበት

የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ልጠናዎችን በማዘጋጀት ለቤተ መጽሀፍት፣ ሪጀስተራር፣ ንብረት

ክፍል ሰራተኞች ከስራቸው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎችንና የልምድ ልውውጦች

ቢደረጉ የአሰራር ክፍተት የሚቀንስ መሆኑ ግንዛቤ ተወስዶ ቢሰራ

1.3 ተቋማዊ የለዉጥ ስራዎች ትግበራና አፈጻጸም

እንደ አጠቃላይ በለውጥ መሳሪያዎች (BSC፣ BPR፣ Kaizen) አተገባበር ዙሪያ በተወሰኑት

ተቋማት የተወሰኑ ሙከራዎች ቢኖሩም በአብዛኛው የ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ ክፍተቶች

በመኖራቸው በቀጣይ በትኩረት ቢሰራበት፡ ፡

2. አብይ ተግባርን በተመለከተ

2.1 የትምህርት ጥራትንና አግባብነትን ማረጋገጥ

ሀ. የመምህራን ልማት

በጥንካሬ የታዩ

በ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የመምህራንን የት/ት ደረጃ ስብጥር የ70፡ 30 ግብ ካሁኑየማይጠበቅ ቢሆንም

ከተወሰኑት ተቋማት በስተቀር ከመጀመሪያውም የቀጠሯቸው መምህራን 2ኛ ዲግሪ ያላቸው መሆኑ ግቡን ከማሳካት

አኳያ አበረታች መሆኑን ለማየት ተችሏል

Page 5: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

4

በብዙዎቹ በ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የመምህር ተማሪ ጥምርታ በስታንዳርዱ መሰረት እና በአማካኝ (1:19)

ለማድረስ የመምህራን ቅጥርን ለመጨመር ያለው ጥረት የሚያበረታታ መሆኑና የመምህራን የክፍለ ጊዜ ድልድል ወደ

ስታንዳርዱ ለማስጠጋት እና ለመምህራን ኦቨርሎድ ለመቀነ ስ የሚደረገው ጥረት አበረታች መሆኑ

በአንዳንድ ተቋማት ከወዲሁ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ማዕከልን በማቋቋም የመምህራንን

የማስተማር አቅም ለማጎልበት ለአዲስ መምህራን የሙያ ትውውቅ ሥልጠና እና ለሌሎች

መምህራን የHDP ሥልጠና መሰጠቱ እና ELIP ተግባራዊ መደረጉ፤

እንደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን የመልቀቅ ምጣኔ ለመቀነ ስ ለመምህራን የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበትንና አሰራር

በመፍጠር የሚደረገው ጥርት ጥሩ ጅማሬ መሆኑ፣ በጂንካ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ አዲስ ተቋም ቢሆንም መምህራን

ተመችቷቸዉና ተረጋግተዉ መስራት ይችሉ ዘንድ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ማግኘታቸዉ

እንደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሙያ መተዋወቂያ ስልጠና (Induction training) ከአርባ ምንጭ

ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኝ መምህራን ሰልጠና እንዲያገኙ መደረጉ

በክፍተት የታዩ

እንደ ራያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር አዳዲስ መምህራንን ምደባ በሚያደርግበት ወቅት

የተቋሙን ፍላጎት ያገናዘበ ባለመሆኑ በፊዚካል ጂኦግራፊ፤ ባዮሎጂና ፊዝክስ ትምህርቶች ላይ

በትርፍነት የተመደቡ እንዲሁም በተቋሙ ባልተከፈተ ፕሮግራም ለምሳሌ ላንድ ሪሶርስ

ማኔጅመንት ላይ የተመደቡ መምህራን በመኖራቸው መፍትሄ ቢፈለግ፤

እንደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮመን ኮርስ መምህራን እጥረት በመኖሩ ለማሟላት ጥረት

ቢደረግ፤

ለ.ብቁየአካዳሚክፕሮግራሞችንናስርዓተትምህርቶችንመተግበር

በጥንካሬ የታዩ

ለፕሮግራሞች አከፋፈት የሚረዳ መመሪያ በማዘጋጀትና ተግባራዊ ለማድረግ፤ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በገበያው

ተፈላጊና የአገሪቱን የልማት አቅጣጫ የተከተሉ እንድሆኑ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካለት ጋር በመወያየት

ከፍላጎት ዳሳሳ አስከ መመሪያዉን ማስፅደቅ ደረስ ተሰርቶ በብዙዎቹ ተቋማት አደዲስ ፕሮግራሞችን ለማከፍት

በዝግጅት ላይ መሆናቸው፡

በክፍተት የታዩ

ተቋሙ በስርዓተ ትምህርት አተገባበር ላይ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በየጊዜው ግብረ መልስ

በመሰጠትና በተሰጠው ግብረ መልስ አማካኝነት በትምህርት ክፍሎችና በኮሌጆች

መስተካከሉን በቅርበት መከታተል የሚቻልበትን ስልት በመቀየስ ቢሰራበት፤

ሐ. የመማር ማስተማር

Page 6: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

5

በጥንካሬ የታዩ

በሁሉም ተቋማት መምህራን ለመማር ማስተማሩ ስራ አስፈላጊ የሆኑ course outline, Teaching

materials, modules አዘጋጅተዉ ለተማሪዎች በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ በኩል በተማሪዎች ዘንድ ይህ

ነው የሚባል ቅሬታ አለመቅረቡ፤

ትምህርት ዘግይቶ ቢጀመርም ከተጀመረ በኋላ ኮርሶች ባለተቆራረጠ ሁኔታ እየተሰጡ መሆኑን ለማየት ተችሏል፣

እንደ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የክፍለ ጊዜ ብክነትን ለመቀነስ ስልት በመቀየስ መምህራንን

ለመቆጣጠር class audit ሪፖርት ተሰርቶ ለየትምህርት ክፍሎች እንዲቀርብ መደረጉን

በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት መታየቱ፤

እንደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በአንዳንድ የትምህርት ክፍሎች የተከታታይ ምዘና እና Course

progress መከታተያ ቅጽ በማዘጋጀት ክትትል እየተደረገ ለመምህራን ግብረ መልስ እየተሰጠ

መሆኑ

በሁሉም ተቋማት በተለያየ ደረጃ ቢሆንም በትምህርት አቀባበላቸዉ ዝቅተኛ ለሆኑ፣ ለሴቶች

በቱቶሪያል ክላስ እገዛ እየተደረገ መሆኑ

በክፍተት የታዩ

ቱቶሪያልን በተመለከተ ልዩ ድጋፍ ከሚሹ ክልሎች የመጡ ተማሪዎችን ከመደገፍ አንጻር በተወሰነ ደረጃ ክፍተት

መኖሩ

መ.የተከታታይ ምዘና፣ ማብቃትና የፈተና አስተዳደር ሥርዓትን በተመለከተ፡

በጥንካሬ የታዩ

እንደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ በመምህሩ የተማሪውን ውጤት በonለine ከማስገባቱ በፊት ተከታታይ ምዘናውንና

የማጠቃለያ ፈተናውን ውጤት ከተማሪ ጋር በመተማመን የሚፈጸምበት ተቋማዊ አስገዳጅ ሥርዓት የተዘረጋ መሆኑ፣

በታካታታይ ምዘና ዝቅተኛ ውጤታቸው ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመለየት ዉጤት በቲቶሪያል እገዛ ከማድረግ በሻገር

በትምህርት ወጤታቸው የተሸሉ ተማሪዎች ሌሎችን እንዲያሰጠኑና እርስ እንዲዩረዳዱ በማድረግ ፕሮግራም ተዘርግቶ

የክትትል ስራም በተወሰኑ ተቋማት መጀመሩ፤ ፡

በትምህርት ክፍል ደረጃ የተማሪዎችን ውጤት በመጀመሪው ሲሚስተር የፈተና ውጤት ትንተና / Analysis /

የተሰራና በታዩ ውጤቶችና ክፍተቶች ላይ አቅጣጫዎች የሚወሰዱ መሆኑ፣ (አርሲ ዩኒቨርሲቲ.)

በክፍተት የታዩ

Page 7: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

6

የFX አተገባበር ላይ በመምህራንና ተማሪዎች ላይ በቅድሚያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ

በመስራት ህጉንና መመሪያውን ተከትለው እንዲሰሩ ተከታታይነት ያለው ክትትል ድጋፍ

ከማድረግ አኳያ በአንዳንድ ተቋማት ላይ ክፍተት በመኖሩ መታየት ይኖርበታል፤

ከመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የሚነሱና ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች መመሪያ ወጥቶላቸው ግንዛቤው

ቢፈጠር ፤

በተለይ ቀደም ብለው ተማሪ ተቀብለው የሚያስተምሩ የ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎችበ2011

ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና / Exit Exam / የሚሰጥ መሆኑን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ቢሰራ፤

እንደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ምዘና ስርዓት እየተተገበረ ቢሆንም እንደ ሀገር የተዋደደዉ

ስርዓተ ትምህርት ከሚያዘዉ ዉጪ ተገቢዉ ምክክርና ዉይይ ሳይደረግበት 60፡40 በሆነ

ምጥጥን እንዲተገበር መደረጉ ቢታይ፤

በተለይ በ2010ዓ.ም ወደስራ የገቡ ተቋማት ካለው አደረጃጀት፣ የግብአት አቅርቦት እና ከትምህርት ጊዜ

እጥረት ጋር ተያይዞ የመማር ማስተማር፣ የምዘና ስርዓቱ ተማሪዎችን ከአቅም በላይ ከማጨናነ ቁ የተነ ሳ

በተከታታይ ምዘና ውጤት ዝቅተኛ የሆኑ ተማሪዎች ለማስቀጠል ተገቢው መረጋጋት ስራ ቢሰራ፤

ሠ. የትምህርት ግብአትና ፋሲሊቲ አቅርቦትን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ

በአጠቃላይ የ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ከአጎራባች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመስራት እንደ መፃህፍት እና ሌሎች

ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር እና በስልጠና በኩል የሚደረግ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚገባው መሆኑ ፤

በአብዛኛወ ከተማሪዎች ቁጥር ጋር የተጣጣሙ፤ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ምቹ የሆኑ የመመገቢያ አደራሾች እና

ቤተ መፅሀፍት መኖራቸውና በአብዛኛው በአግባቡ የሚሰተናገዱበት ሁኔታ መፈጠሩ፡ ፡

በክፍተት የታዩ

በየትምህርት ክፍሉ ያሉ የአጋዥ መጽሀፍት እጥረት በመለየት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም እንዲሟሉ በግዥ፣

በትውስት፣ ኮፒ በማድረግና በመሳሰሉት/ በተጨማሪም ቤተ-መጽሀፍቱ አገልግሎት የሚሰጡበትን ሰዓት ማራዘም

ቢቻል፤

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በስታንዳርዱ መሰረት 4 ተማሪዎችን መያዝ የሚገበው አንድ የተማሪዎች መኝታ ግንባታዎች

ባለመጠናቃቀቸው ምክንያት 6 ተማሪዎች በአንድ ክፍል ዉስጥ እንዲኖሩ መደረጉ

ቤተ መፃህፍት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የመፃህፍት እጥረት እንዳለ በተማሪዎች ተነ ስቷል፣ (እንጅባራ ዩ.)

ከትምህርት ሚኒስቴር መቅረብ የሚገባው የቤተ ሙከራና ወርክሾፕ ቁሳቁሶች ፣ የምግብ

ማብሰያ ማሽኖች፣ ጄኔሬተር፣ ተሽከርካሪ ወዘተ ባለመድረሱ አገልግሎት መስጠት ያልተቻለ

በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ ቢፈለግ፤

Page 8: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

7

በብዙወቹ ተቋማት ለተማሪዎች ተጨማሪ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ የፎቶኮፒ ቤቶች ሱቆች ፣ ጸጉር ቤቶች፣ ምግብ

ቤቶች…እንዲደራጁና የተማሪዎችን አቅም በአገናዘበ ሁኔታ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ቢደረግ፤

በተወሰኑ ተቋማት ለምግብ ቤት ሰራተኞች ተከታታይነት ያለዉ የጤና ምርመራና ክትትል በማድረግ የተማሪዎችን ጤና

በመጠበቅ በኩል ክፍተት መኖሩ፤

እንደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ የግንባታ ፕሮጀክቶች አጀማመር እየዘገየ ስለሆነ ቢታይ፣

በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የIOT ወርክ ሾፕ Hydraulic laboratory ውስጥ ያለተገጣጡሙ

ማሽኖች መኖራቸው፣ Solil Mechanicanics laboratory የለሌ መሆኑ እና Hydraulic

laboratory I የተሟላ አለመሆኑ ተማሪዎች የሚፈለገውን የተግባር ትምህርት በወርክ ሾፕ

እያገኙ አለመሆኑ፣

በማዕቀፍ ግዥ ምክንያት የግብዓት ፍላጎት መጓተት በዕቅድ አፈጻጸም ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ

በመሆኑ መፍትሔ ቢፈለግ፤

በተቋማቱ ያለው የተሽከርካሪ እጥረት ትኩረት ተሰጥቶበት መፍትሔ ቢያገኝ

ረ. ተቋማዊፋይዳውየጎለበተየ ICT አገልግሎትንማጠናከር

በጥንካሬ የታዩ

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ አይሲቲ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስቲሪ ትስስርን ለማጠናከር ከት/ሚር ስምምነት ተደርጎባቸዉ

ስልጠናና ግብአቶች በመስጠት ለአፈጻጸም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ከወረዱት ውስጥ Huawei, ተማሪዎች ተመድበው

ትምህርት መጀመራቸው፣ Cisco ስልጠናውን ለመስጠት የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱና Microsoft

ለተማሪዎች፣ ለመምህራንና ለሰራተኞች office application አንዲጠቀሙ ድጋፍ መደረጉ፣ ዩኒቨርሲቲው

ደረጃዉን የጠበቀ የካምፓስ ኔትዎርክ መዘርጋቱንና ዳታ ማእከል፣ ሁሉም ህንጻዎች፣ ኦፊሶች፣ተደረሸ ለማድረግ

ጥረት እየተደረገ መሆኑ፣

በተጨማሪም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ አቅም ግንባታ ስልጠና ለተቋሙ ማህበረሰብ አመራሮች የአይሲቲ

ባለሙያዎችና በየደረጃው ላሉ ተጠቃሚዎች ስልጠና የተሰጠ መምህራን የተማሪዎችን ውጤት በonline

እንዲጠቀሙና ተማሪዎችም online ላይ ገብተው ውጤታቸውን እንዲያዩ መደረጉ ሰራተኞችም መረጃዎቸን አውቶሜት

በማድረግ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት እንዲጀመር መደረጉ፣

በክፍተት የታዩ

በአብዛኛው ተቋማት ውስን ቁጥር ባላቸው ኮምፒዩተሮች ላብራቶሪ በማቋቋም ተማሪዎች

በተወሰነ ደረጃ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረግ ውጪ የICT አገልግሎት ጠንካራ አለመሆኑ

ታይቷል

ከኢንተርኔት ጋር በተያያዘ ፕሮጀክቶች መፍጠን እንዳለባቸው በክፍተት ተነስቷል፣

Page 9: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

8

ሰ. ሰላማዊመማርማስተማርንበዩኒቨርስቲዎችስለማስፈን

በጥንካሬ የታዩ

በኦዳቡልቱም ዩኒቨርስቲ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን በሀገራዊ ችግር ምክንያት ወደ

ቤተሰብ የተመለሱ ተማሪዎችን እስከ ቤተሰብ መኖሪያ ክልል እና አካባቢ በመሄድ ተማሪዎችን

የማስመለስ ስራ በመስራቱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታታሉ ተደርጎ በችግሩ ምክንያት

የባከነ ክፍለ ጊዜ በአካዳሚክ ዳይሬክቶሬት በኩል ተቆጥሮና በመረጃ ተይዞ ለተማሪዎች

ቅዳሜ እና እሁድ ጭምር የማካካሻ ትምህርት እየተሰጣቸው መሆኑ እና ክትትሉም በመረጃ

የተደገፈ መሆኑ ፤

እንደ ቀብሪዳህር ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ መላ ሰራተኞች ለመማር ማስተማሩ ትኩረት በመስጠት

ተማሪዎች አካባቢውን እንዲለምዱና በትምህርታቸው የላቀ ውጤት አንዲያስመዘግቡ ርብርብ

እያደረጉ መሆኑ፣

የዶርሚተሪ አገልግሎት ህብረ ብሄራዊነ ትን ፣ አብሮነ ትና መቻቻልን በሚያጎለብት መልኩ በአብዛኛው ዶርሞች

ተማሪዎች ከተለያየ ክልል በመጡ ተማሪዎች ስብጥር የተደራጀ መሆኑ፣

በክፍተት የታዩ

እንደ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚመደቡበት ጊዜ ከአንድ አካባቢ ( አንድ አንድ ጊዜ

ከአንድ ዞን ከአንድ ወረዳ) የመጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ላይ የመከማቸት ነ ገር ይታያል

፡ ፡ ይህ ነ ገር ከሰላማዊ መማር ጋር በተያያዘ ችግር ስለሚኖረው አመዳደደብላይ ይህ ነ ገር ቢታይ፡ ፡

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ህብረትን የሀገር አቀፉን መመሪያ መነሻ በማድረግ እንዲደራጅ ቢደረግና

እየታዩ ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ውስንነ ቶችን በመቅረፍ በኩል የበኩላቸውን እንዲወጡ እድሉ ቢመቻች፤

2.2የጥናትናምርምርአተገባበርንበተመለከተ

ጥንካሬ የታዩ

በአብዛኛው ተቋማት የጥናትና ምርምር መስኮች /thematic areas/ የመለየት ጅምር ሥራዎች

መኖራቸው፤

እንደ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በ2010ዓ.ም 92 ፕሮፖዛሎች ቀርበው ከነዚህም ውስጥ 64

የሚሆኑት እንደጸደቁና ፈንድ አግኝትው ስራ መጀመራቸው፣

Page 10: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

9

እንደ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሴቶች የምርምር አቅም ለማጎልበትና ለመገንባት ከስርዓተ

ጾታ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለሴት ተመራማሪዎች ብቻ በምርምር ስነዘዴ፣ በዳታ

ትንተና ሶፍትዌሮች ወዘተ… ስልጠና መሰጠቱ፣

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱን የልማት አጀንዳዎች መሰረት በማድረግ ከሌሎች የምርምር ተቋማት በመተባበር

በአገር ውስጥ ከMost (ሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤት) ጋር የአሳና የደሮ እርባታ በጥምረት

በመስራትና የአዓሳና የድሮው ኩሱን ለአትክልት በግብዓት በመጠቀም በአንድ ቅንጃታዊ አሰራር የተለያዩ

ምርቶችን ማምረት የሚቻልበትን ምርምር በመፍጠርና ከውጭ ሀገር ከኮሪያ አንድ ድርጅት ጋር የእናቶችና

የህፃናት ጤና ላይ በ1.8 ሚሊዮን ብር እየተሰራ ያለው ስራ በአርአያነ ት የሚጠቀስ መሆኑ፤

በክፍተት የታዩ

እንደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለጥናትና ምርምር ሥራው በጀትና ግብዓት ማሟላትና ማሳደግ እንዲሁም ስለአጠቃቀምና

አያያዝ ዙሪያ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ግንዛቤ መሰጠቱን በተመለከተ እና ለተመራማሪዎችን ለማነ ሳሳትና

ውጤታማ ለማድረግ የማትጊያ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሠራበት አለመሆኑ፣

እንደ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለጥናትና ምርምር ሥራው በጀትና ግብዓት ለማሟላትና ለማሳደግ

እንዲሁም ስለበጀት አጠቃቀምና አያያዝ ዙሪያ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብና ለተመራማሪዎች

በዚህ ዓመት ግንዛቤ አለመፈጠሩ፣ የአመቱ የምርምር በጀት አለመለቀቁእናአ የሚጸድቁ

ፕሮፖዛሎች ከትምህርት ክፍል እስከ ፋኩሊቲ ዲን ድረስ በኮሚቴ እየታየ መሆኑ በአመራሩ

ቢገለጽም በመምህራን ዘንድ የአሰራሩ ግልጸኝነት የለም የሚል ቅሬታ ማሳደሩ፤

እንደ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስት ትስስርየተሰሩ

ስራዎችን መረጃ ሊሰጥ የሚችል የስራ ክፍል ሃላፊ ባለመገኝቱ በጥንካሬም ሆነ በክፍተት ግብረ

መልስ / ሪፖርት / ማቅረብ ያልተቻለ በመሆኑ ተቋሙ የስራ ክፍል ሀላፊዎች በስራ ገበታቸው

ተገኝተው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ክትትል ማደረግ ያስፈልጋል፤

2.3 የማህበረሰብ አገልግሎትን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ

በክህምናው ዘርፍ ያይን ብርሃናቸው ላጡ ወገኖች የተለያዩ ኦፕራሴዮኖችን በማካሄድ ከጭለማ ወደ ብርሃን

ዓለም እንዲቀላቀሉና ዩኒቨርሲቲው ታላቅ ተግባር ከመፈፀሙ ሌላ ለHIV/AIDS በሸተኞች እንዲሁም ትዳርን

በመፍታት በወንዶች የበላይነ ት ሀብትና ንብረታቸውን የሚያጡ ሴት እህቶቻችንን ነ ፃ የህግ አገልግሎት በመስጠት

መብታቸውና ንብረቶቻቸውን እንዲያስከብሩ በማድረግ ወደ ድህነ ት ማጥ እንዳይገቡ ዩኒቨርቲው ቀድሞ በታደግ

ህብረተሰቡና ዩኒቨርሲቲው ያለውን ጥብቅ ቁርኝነ የበለጠ እንዲጠናክር ማድረግ የቻለበት የማህበረሰብ

አገልግሎት በጥሩ ተሞክሮነ ት የሚወሰድ መሆኑ፣ (አርሲ ዩኒቨርሲቲ)

Page 11: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

10

ከኦሮሚያ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም ችግሮችን ለይተው እንዲመጡ ተደርጎ በተለዩ ከፍተቶች

ዙሪያ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም አመራሮች አቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሰጠቱ፣ በነዚሁ

በተለዩ ችግሮች ላይ ምርምር በመሰራትላይ መሆኑ፣(ኦዳ ቡለቱም ዩኒቨርሲቲ)

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚገኙ ለ58 ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የአቅም ግንባታና የቁሳቁስ

ድጋፍ እየተደረገ ነዉ፡፡ እንዲሁም የኒቨርሲቲዉ በዞኑ ለሚገኙ ለ58ቱም ት/ቤቶች

ለእያንዳንዳቸው 25 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ድጋፍ ከማድረግ በሻገር በአጠቃቀሙ ላይ

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲዉ መምህራን በአከባቢው የሚገኙ

ትምህርት ቤቶችን ከመደገፍ አኳያ ቢሸው ዮሐንስ ፕሪፓራቶሪና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች

ቅዳሜና እሁድ ለ10ኛእና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትቶሪያል አገልግሎት እየተሰጠ የሚገኝ

መሆኑ አበረታች ጅምር ያለ መሆኑን ያሳያል

በክፍተት የታዩ

እንደ 4ኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች በሁሉም ተቋማት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በጀት

ቢመደብ

2.4 የዩኒቨርሲቲኢንዱስትሪትስስር

በጥንካሬ የታዩ

በቦንጋዩኒቨርሲቲ የህዋ ሳይንስ ቅርንጫፍ ማዕከል ለመክፍት እንዲቻል ከፌዴራል ህዋ ሳይንስ የሚመለከታቸው

ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት ኮንፍረንስ የ1 ቀን ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል፡ ፤ .

በክፍተት የታዩ

እንደ አጠቃላይ በ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር በተመለከተ ይህ ነው የሚባል በተቋማቱ የተሰራ ስራ

አለመኖሩ

2.5 የሀብት አጠቃቀምና ንብረት አስተዳደር በተመለከተ

በክፍተትየታዩ

በአብዛኛው ተቋማት የንብረት አገባብና አወጣጥ ስርዓቱን በጠበቀ መንገድ ህግና ደምብን ተከትሎ እነዲፈፀም ለሰራተኞች የስራው ሁኔታያገናዘበ ስልጠና አለመሰጠቱ፤

ከሀብት አጠቃቀም አንፃር በቀብሪዳህር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጡ ንብረቶችና

የግንባታ ግብአቶች፣ የተማሪዎች ወንበሮች፣ አልጋዎችና ሎከሮች ወዘተ…በግቢው ውስጥ

Page 12: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

11

በጸሀይና በዝናብ እየተጎዱ ስለሆነ ለንብረቶቹ ተገቢውን ጥንቃቄ በማደረግ ከብልሽትና ብክነት

በመታደግ ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረግ ይገባዋል፣

3. ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች

3.1 በሴቶችና ወንዶች መካከል ያሉ የተሳታፊነትና የተጠቃሚነት ልዩነትን

ለማጥበብየሚከናወኑተግባራት

በጥንካሬ የታዩ

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሴት መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፎ እንዲጨምር ልዩ ድጋፍ በማድረግ የሴት

መምህራን ተሳትፎ 33%ና 51% ሴት የአስተደደር ሰራተኞች በተቋሙ ተቀጥረው እየሰሩ ይመገኘታቸው፤

በአርሲ ዩኒቨርሲቲየሴቶች የመመረቅ ምጣኔ ለማሳደግ ጥሩ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች ከሰርተፍኬት እስከ ታብሌት

የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት የተማሪዎችን ተነ ሳሸነ ት መፍጠር መቻሉ፣

በክፍተት የታዩ

ሴቶችን በአካዳሚክና በአስተዳደር ዘርፍ በዝቅተኛ፣ በመካካለኛና በከፍተኛ የአመራርነት

ተሳትፎ ከማጎልበት አንጻር የተሰሩ ስራዎች በአብዛኛው አጥጋቢ አለመሆናቸው ታይቷል፤

3.2 ልዩድጋፍለሚሹእናለታዳጊክልልተማሪዎችስለሚደረግድጋፍ

በጥንካሬ የታዩ

በአብዛኛው የአካል ጉዳተኞች በመረጡትና አቅማቸዉ በሚፈቅደዉ የትምህርት ዘርፍ

እንዲመደቡ በማድረግ የመዝለቅ አቅማቸው እንዲያድግ ድጋፍ መደረጉ፣

ልዩ ድጋፍ ከሚሹ ክልሎች ለመጡ ተማሪዎች የቱቶሪያል እገዛ በአብዛኛው ተቋማትእየተደረገ

መሆኑ

በክፍተት የታዩ

ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎች ከመደገፍ አንፃር በጂንካ ዩኒቨርሲቲ መናገር የማይችል ተማሪ

የትምህርት ከፊዚክስ ትምህርት ክፍል ወደ ሌላ መቀየር ፈልጎ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ

አለማግኘቱ፤

3.3 አከባቢጥበቃ፣ኤች.አይ.ቪእናአደንዛዥዕጽንበተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ በተወሰኑ ተቋማት ሱስ አምጪ ዕፆችንና ነ ገሮችን ለመከላከል መመሪያ በማዘጋጀት የተቋሙን ማህበረሰብ አፍራሽ

ለሆኑ እፆች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ግንዛቤ መሰጠቱ፣

Page 13: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

12

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሱስ አምጪ ዕፆችን ለመከላከል መመሪያ በማዘጋጀት የተቋሙን ማህበረሰብ

አፍራሽ ለሆኑ እፆች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ልዩ ልዩ እርምጃዎች ተወስዷል፡፡ለምሳሌ፡-

በዩኒቨርሲቲዉ አከባቢ የነበረዉ የጫት ገቢያ በከተማ መስተደደር ጋር በመሆን እንድወገድ

መደረጉ

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ HIV/AIDS ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ላለባቸው የዩኒቨርስቲው ሰራተኞችና ተማሪዎች ቋሚ

ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር እንዲቻል ከሰራተኞች የሚዋጣ ወርሐዊ ገቢ የፀረኤድስ ፈንድ ለማቋቋም

የሚያስችል በውይይት የዳበረ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለዩኒቨርስቲው የበላይ አመራር መቅረቡ፣

በክፍተት የታዩ

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትምህርት ተቋሙ ርቀዉ ተገቢ ወዳልሆነ ህይወት ዉስጥ እንዳይወድቁ አስፈላጊዉን

ቁጥጥር ለማድረግ ያመች ዘንድ በተማሪዎች ማደሪያ የመኝታ ቤት ተወካይ፣ ፍሎር ማስተር፣ በሎክ ማስተር እና

መሰል አደረጃጀቶችን በመፍጠር ተገቢዉ ክትትልና እርማት ቢደረግ

በኤች.አይ.ቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ በሱስ አምጪ ዕፆችን ለመከላከል መመሪያ በማዘጋጀት

ቅንጅታዊ አሰራር በመቀየስ የኤች.አይቪንና ሌሎች የአባለዘር በሽታዎችን ለመከላከል

እየተሰራ ያለው ስራ በቂ አለመሆኑ

ለተማሪዎች ምግብ ቤት ሰራተኞች ተከታታይነት ያለዉ የጤና ምርመራና ክትትል በማድረግ የተማሪዎችን ጤና

በመጠበቅ በኩል ክፍተት በመኖሩ ቢሰተካከል፤

3.4 ክትትልና ድጋፍን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ

በብዙዎቹ ተቋማት ክትትልና ድጋፍን በተመለከተ ከላይ እስከ ታች በየደረጃው ያለው አመራር በየወቅቱ ክትትልና

ድጋፍ የሚደርግበት ሁኔታ ጅምሩ አበረታች እንደሆነ ለማየት ተችሏል፣

በክፍተት የታዩ

በመልካም ተሞክሮዎች ሊወሰዱ የሚችሉ ተሞክሮዎች ቢሆንም ተሞክሮዎችን ለመቀመርና ለማስፋት የሚረዳ ሥርዓት

የተዘረጋ አለመሆኑ፣ (አርሲ ዩ.)

በየደረጃው ያለው አመራር ተቋማቱ ለትምህርት ዘመኑ ይሰራሉ ብሎ ያወረዳቸው ተግባራትና

ስታራቴጅካዊ ጉዳዮች በተቀመጠው መጠን ጥራት ወጭ የጊዜ ገደብ መሰረት እየተፈጸሙ

መሆን በክትትልና ድጋፍ የማየት የመጠየቅ ጠንካራና ክፍተት ያለባቸውን አፈፃጸሞችንም ሆነ

ፈፃሚና አመራር የመለየትና አቅጣጫ የማስቀመጥ ሁኔታ ላይ ቢታይ፤

እንደ ቀብሪዳህር ዩኒቨርሲቲ በሚዛናዊ ውጤት ተኮር /BSC/ ስርዓት መሰረት የታቀደ እቅድ

ተዘጋጅቶ የእይታ መስኮች፣ ስትራቴጂክ ግቦች ለግቦች የተሰጠ ክብድት፣ ነባራዊ መነሻ፣ ኢላማ

እና መለኪያ የያዘ ሆኖ ወደ ኮሌጆች፣ ፋኩልቲዎች፣ የሥራ ክፍሎችናግለሰቦች ወርዶ

Page 14: በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከፍተኛ ... · 2020-01-06 · በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተከፈቱ 11 የመንግስት ከተኛ ትምህርት

13

እቅድአዘጋጅተው ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች የሚገመግሙትና ተቆጥሮ

እንዲሰጣቸው ቢደረግ፤