ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና...

33

Upload: others

Post on 04-Sep-2019

14 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ
Page 2: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

ውይይት 1ኛ ዓመት ቁጥር 4 ሰኔ 4 /2008

ሐተታ ውይይት

21-22

9-11

ዋና አዘጋጅበፍቃዱ ኃይሉአድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 01፣ የቤት ቁጥር 255ኢሜይል፡- [email protected]

ማኔጂንግ ኤዲተርሞላ ዘገዬኢሜይል፡- [email protected]ተባባሪ ማኔጂንግ ኤዲተርአበበ በየነ

አምባሳደር ተስፋዬ ሐቢሶዶ/ር ዳንኤል ክንዴ

ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያምመብራቱ በላቸው

ሔኖክ አክሊሉተሾመ ተስፋዬ

ቴዎድሮስ አጥላው

ም/ዋና አዘጋጅዘላለም ክብረትኢሜይል፡- [email protected]

አዘጋጅበሪሁን አዳነኢሜይል፡- [email protected]

ዲዛይን ካርቱንሀብ ዲዛይን0941 39 84 46

አታሚ፡ ናታን ማተሚያ ቤትአድራሻ፡ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁ.1062ስልክ 0911 16 79 86

ሞላ ዘገየ እና ቤተሰቦቹ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር እየታተመ በየ15 ቀኑ የሚወጣ መጽሔትሚያዝያ 22፣ 2008 ተጀመረ!አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 283ፖ.ሳ.ቁ. 3845አዲስ አበባስልክ ቁጥር፡- +251118688992ኢሜይል፡- [email protected]ድረገጽ፡- www.weyeyetmagazine.com

አምደኞች

4

አንድ ሰው

ከዳግም አገርዐቀፍ ቅሌት ለመዳን ምን ይደረግ?

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምተፅዕኖ አድራሽ ወይስ ዴሞክራሲ ደምሳሽ?

የፌደራሊዝም ፖለቲካ በኢትዮጵያ

ብዝኃ-ዕይታ የሚፈትነው ‘የኢትዮጵያ ታሪክ’

ታሪክ እና አተራረኩ በኢትዮጵያ ልኂቃን ዘንድ የጋለ ሙግት ከሚቀሰቅሱ ርዕሰ-ጉዳዮች ውስጥ ይመደባሉ። ከዚያም በላይ የፖለቲካ ዝማሜዎች መሠረታዊ መነሻም ነው። ዘላለም ክብረት፣ ርዕሰ-ጉዳዩን በመምዘዝ፣ ከጥናቶች እና ምሁራን አንደበት ታሪክ እና አተራረኩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ለገጠማት ፈተና መፍትሔ ይፈለግለት ዘንድ የሐተታ ውይይት ርዕስ አድርጎ አቅርቦታል።

30-32

የፌዴራሊዝም ስርዓት ጉዳይ በኢትዮጵያ አነጋጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥትን ፈርመው ያፀደቁት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገ መንግሥቱ የፀደቀበትን ሒደት ከተነተኑ በኋላ፣ ሕገ መንግሥቱ የተሻለ ሕዝባዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ይደረግ የሚለውን የመፍትሔ ሐሳብ ይጠቁማሉ።

Page 3: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

2 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

12-13 14-15

16-17

5-6 7-8

የፈተና “ስርቆቱ” ስንክሳር ፍልሰት ወደ ከተማ፤ችላ የተባለ አሳሳቢ ጉዳይ?

የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ እና የዴሞክራሲ ሽግግር አገራዊ እሴት አልባ

የሕግ ንቅለ-ተከላዎች እና ፍትሕ

ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ዳንኤል ኦርቴጋን ፍለጋ

21-23

ለምን ባለቅኔው

ከግንቦት 22 እስከ 25፣ 2008 ድረስ በመላው የአገሪቱ ክፍሎች ሊሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ

መልቀቂያ ፈተና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቀድሞ በመለቀቁ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል። “የፈተናው

‹ተሰርቆ› በአደባባይ መለቀቅ መንግሥት ለመማር ከፈለገ ትምህርት ሰጪ ነው” በማለት መስከረም አበራ ጠቅላላ

ሁኔታውን በሚከተለው መጣጥፏ ዳስሳዋለች።

ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ጥሩ ፖሊሲ አልተቀረፀለትም፤ ይሁን እንጂ በተለይ በአዲስ አበባ ለሕዝብ ቁጥር መጨመር ከፍተኛ ድርሻ አለው፤ በዚህም ምክንያት ኑሮ በአዲስ አበባ ለስደተኞቹም ለነባሮቹም አስቸጋሪ እየሆነ ነው በማለት የጻፈው በፍቃዱ ኃይሉ መንግሥት ጉዳዩን የሚገባውን ያክል ትኩረት እንዲሰጠው ይጠይቃል።

አቶ ሞላ ዘገዬ በዚሁ አምድ ላይ ባለፉት ሦስት ተከታታይ እትሞች “የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ ወቅታዊነት” በሚል

ርዕስ ለዘላቂ ሠላም እና ሕገ መንግሥታዊነት የሚበጅ ያሉትን ምክረ ሐሳባቸውን ሲያካፍሉን ነበር። ኢዮብ ሲሳይ

በአቶ ሞላ ሐሳብ ላይ የጎደለ የመሰላቸውን ማጠናከሪያ ሐሳብ እንደሚከተለው አስፍረውታል።

18-20 26-29

አሌክስ አብርሃም ታይታን የሚያደበዝዝ ስውር ደራሲ‘የዶክተር አሸብር’ እና ‘ዙቤይዳ’ ንባብ

ሕጎች የአገራዊ እሴቶችን ከግምት ውስጥ አስገብተው ካልተቀረፁ ለተፈፃሚነት ያስቸግራሉ በሚል የሚከራከረው ተሾመ ተስፋዬ ‹የኢትዮጵያ ሕጎች እና ሕገ መንግሥቶች አገራዊ እሴቶችን አቅፈዋልን? ካልሆነስ፣ ማቀፍ ይቻላቸው ይሆን?› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሕግ ተከላ እና ንቅለ-ተከላ ታሪካችንን ዳስሷል።

የብሔራዊ እርቅን አጀንዳ ማነው የዘጋው?

Page 4: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

3ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

በውይይት መጽሔት ላይ የመጽሔቱ አቋም የሚንፀባረቀው

በ‹ርዕሰ አንቀፁ› ላይ ብቻ ነው።

መንግሥት ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ለመስማት ዳተኝነት ባሳየ ቁጥር፣ ዜጎች በሕጋዊ ስርዓት ሊያገኙት ይገባቸው የነበረውን ነገር በሕገ ወጥ መንገድ ለማግኘት መሞከራቸው የማይቀር ነገር ነው። ገዢው ፓርቲ “ሥር የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግር” እንዳለበት አምኗል። ይሁን እንጂ ይህ ሥር የሰደደው የመልካም አስተዳደር እጦት በነባሩ አሠራር እና የፖለቲካ ባሕል አይቀረፍም። ገዢው መንግሥት የአሠራር እና የፖለቲካ ባሕሉን ለመቀየር ይህ ነው የሚባል ጥረት እያደረገ አይደለም። ይህም አገሪቱ አሁን ለደረሰችበት የዕለት ተዕለት ፈታኝ ሁኔታ ዳርጓታል።

ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ በተቆጣጠራቸው የፌዴራል፣ የክልል እና የወረዳ ምክር ቤቶች፣ በፖለቲካ ሰነዱ ላይ የሰፈሩትን ፕሮግራሞቹን በቀጥታ የማስፈፀም ፖለቲካዊ አቅሙ አለው። ነገር ግን እነዚህ ፕሮግራሞቹን ሕዝብ አውቆ እና ፈቅዶ የሚያስፈፅምበት ስርዓት የለውም። እንደ እኛ አገር ነጻ ሚዲያ በሌለበት እና ሲቪል ማኅበረሰቡ በጫጨበት የፖለቲካ ምኅዳር በማንአለብኝነት ገዢው ፓርቲ የመሰሉትን ፕሮግራሞች በሙሉ በሕዝቡ ላይ ለመጫን የሚያደርገው ጥረት የሕዝቡን የትዕግስት ጫንቃ የሚሰብርበት ቀን ሩቅ አይመስልም።

በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ሕግጋት እና መመሪያዎች የሚወጡት የሚመለከታቸው አካላት ሳይመክሩበት፣ ሳያውቁት እና ሳይፈቅዱት ነው። “የሚመለከታቸው አካላትን ማሳተፍ” በሚል ሰበብ የሚደረጉ የይስሙላ ጉባኤዎችም ቢሆኑ፣ የወጡትን ሕግጋት እና መመሪያዎች እንዲቀበሉ ማግባቢያ ከማድረግ ያለፈ ሚና የላቸውም። በቅርብ ጊዜ እንኳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት ለሕልፈት የዳረገው የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃውሞ የተቀሰቀሰው የሚመለከታቸው አካላት ሳይመክሩበት በወጣው ‹የማስተር ፕላን› ሳቢያ ነው።

እንደዚህ ዓይነቶቹ በማን አለብኝነት ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ፖሊሲ እና ፕሮግራሞች ለመጫን የሚደረጉ ጥረቶች ሠላምና መረጋጋትን ከመቀማታቸውም በተጨማሪ፣ ዜጎች በገዛ አገራቸው የባይተዋርነት ስሜት እንዲያዳብሩ ያስገድዳቸዋል፤ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የመወጣት ተነሳሽነታቸውን ያቆረቁዘዋል። በውጤቱም አገሪቱ ወደማይታወቅ አቅጣጫ እንድታመራ ትገፋለች። ይህ ጉዳይ ምናባዊ ግምት ሳይሆን አሁን በአገራችን መታየት የጀመረ ጉዳይ ነው።

መንግሥት ችግሮች በተፈጠሩ ቁጥር ጣቱን የተለያዩ አካላት ላይ እየቀሰረ መቀጠል አይችልም። በእርግጥ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች የተለያየ የፖለቲካ አጀንዳ ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህን አጀንዳዎቻቸውን ለማስፈፀምም የተለያዩ አጋጣሚዎችን መጠቀማቸው አይቀርም። ገዢው ፓርቲም ቢሆን የሚያደርገው ይህንኑ ነው። ነገር ግን ሕዝቦች የፖለቲካ አጀንዳ የላቸውም። ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ወይም ማኅበራዊ ኢፍትሓዊነት ካልተፈፀመባቸው በስተቀር አያምፁም፤ በራሳቸው ጉዳይ ቸልተኛ ሊሆኑም አይችሉም። ስለሆነም የመንግሥት ሰበብ አስባቦች በሙሉ ለችግሮች መፍትሔ መስጠት አልቻሉም።

ገዢው ፓርቲ ችግሮችን ለመፍታት “አጥፊ” የሚላቸውን ተቃዋሚዎቹን እየሰበሰበ በማሰር እና በመቅጣት መፍትሔ በመፈለግ ፈንታ ችግሮችን ለማዳፈን የሚጥርበት አሠራር የማይወጣው ቅርቃር (dead end) ውስጥ ከቶታል። የእስከዛሬው ‹የእኔ አውቅልሃለሁ› የፖሊሲ አወጣጥ እና አፈፃፀም ስልት ወዴትም ማድረስ የማይችል እንደነበር በ25 ዓመታት የተግባር ሙከራ ተረጋግጧል። መንግሥት ከተራ የግለሰቦች እልኸኝነት በዘለለ መልኩ ድክመቶቹን አውቆ ሙሉ አሠራሩን ለመቀየር ቁርጠኝነት ማሳየት አለበት። ይህ ቁርጠኝነት የሚረጋገጠው ሕዝቦች ከፖሊሲ እስከ አፈፃፀም ባሉ ሒደቶች ላይ ቀጥተኛ እና የበላይ ተሳትፎ ማድረግ የሚፈቀድላቸው አሠራር ከተዘረጋ ብቻ ነው።

የመንግሥት ኃላፊዎች እና መሥሪያ ቤቶች ከተለመደው የመነባንብ ‹ግልጽነት› እና ‹ተጠያቂነት› ዲስኩር ተላቅቀው እውነተኛ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ካላዳበሩ ደግሞ ሕዝብ አሳታፊ የሆነ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ዕድል አይኖርም። ስለሆነም፤ አሁንም እንደምንግዜውም ገዢው ፓርቲን ለማሳሰብ የምንወደው ነገር ቢኖር የሕዝብ ቅሬታ፣ የተቃዋሚዎች አቤቱታ ይደመጥ፤ ዜጎች ኑሯቸውን እና ሥራቸውን በሚመለከቱ የፖሊሲ እና የመመሪያ ጉዳዮች ላይ ያለመሸማቀቅ እና ያለፍርሐት ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይፈቀድ፤ ዜጎች ያላወቁት፣ ያልመከሩበት፣ እንዲሁም ያላፀደቁት ምንም ዓይነት ውሳኔ በሥማቸው አይተላለፍ።

የመንግሥት “አልሰማም” ባይነት አገሪቱን ወዳልታወቀ አቅጣጫ እየወሰዳት ነው

ርዕስ አንቀፅ

Page 5: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

4 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ከግንቦት 22 እስከ 25፣ 2008 ድረስ ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ሾልኮ (leak) ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በይፋ በመለቀቁ ምክንያት፣ ተማሪዎች ለፈተና ከተቀመጡ በኋላ ረፋዱ ላይ መሠረዙ ይታወቃል። ይህ ከሆነ ከሁለት ቀናት በኋላ ትምህርት ሚኒስትር ተለዋጭ የፈተናው ጊዜ ከሰኔ 27 እስከ 30 እንዲሆን መወሰኑ ተነግሯል። ፈተናው በይፋ ለምን ተለቀቀ? ማነው ተጠያቂው? ወደፊት እንዲህ ያለው ቅሌት እንዳይደገምስ ምን መደረግ አለበት? የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደተራ ስርቆት እና ወንጀል ሲያጣጥሉት እና ሲያጥላሉት የነበረው ይህ ክስተት እውን ተራ የስርቆት ወንጀል ነውን? እኒህና መሰል ጥያቄዎችን ሰፊ ጉዳይን የሚመዙ ናቸው።

አገርዐቀፍ ፈተናው መሰረዙ ከመነገሩ ቀደም ብሎ፣ እሁድ (ግንቦት 21፣ 2008) ማታ እና በማግስቱ ሰኞ ማለዳ የመንግሥት ብዙኃን መገናኛዎች የትምህርት ሚኒስቴሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በማቅረብ “ፈተናው ተሰርቋል የሚባለው ውሸት ነው፤” በማለት ሲያስተባብሉ ነበር። ይሁን እንጂ እነዚህ ዜናዎች እየተተላለፉ በነበሩባቸው ሰዓታት ማኅበራዊ ሚዲያዎች (በተለይም ፌስቡክ) ተጠቃሚዎች፣ የተለያዩ ኮድ ያሏቸውን የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እያተሙ ነበር። የመጀመሪያዎቹን ቅጂዎች በይፋ ያሰራጫቸው ጃዋር መሐመድ የተባለ ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገ “የኦሮሞ ሕዝብ ሲቪል መብቶች አቀንቃኝ” ነው። ጃዋር ፈተናዎቹን በይፋ የለቀቃቸው መንግሥት የፈተናውን ጊዜ እንዲያራዝም ለማስገደድ መሆኑን ተናግሯል።

ፈተናው ለምን “በይፋ ተለቀቀ”?ፈተናዎቹን ከነመልሶቹ ፌስቡክ ላይ

ያተማቸው ጃዋር መሐመድ ግንቦት 23፣ 2008 በኦፊሴላዊው የፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን ማስታወሻ አስፍሯል። “…በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ፈተና 'ተሰረቀ' የሚለው አባባል ሊስተካከል ይገባል። መስረቅ ማለት አንድን የግለሰብ ወይንም የሕዝብ ንብረት በድብቅ ወስዶ በድብቅ መጠቀም ማለት ነው። እንዲሁም አንድ ፈተናን ወይም መልሱን በድብቅ ከቀኑ አስቀድሞ ለተወሰኑ ግለሰቦች በማድረስ ያለ አግባብ ተጠቃሚ (unfair advantage) ማድረግ ነው። በዚህ ፈተና ላይ የተወሰደው እርምጃ ግን ስርቆት ሳይሆን ግልጽ ፖሊቲካዊ እርምጃ ነው። ፈተናውን አስቀድሞ በማውጣት ለአንድ ቡድን የማከፋፈል ሥራ አልተሠራም። ለሰፊው ሕዝብ ነው በግልጽ የተሰራጨው። ይህ እርምጃ ጣልቃገብነት የሚባል የሠላማዊ የመብት ትግል ስልት ነው (nonviolent direct interven-

tion)። ይህ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ቀለል ያሉ (less aggressive) ስልቶች ተሞክረዋል። ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአገር ሽማግሌውች ተማፅነዋል። ያ ሰሚ ሲያጣ፣ ዓለምዐቀፍ የስልክ መደወል ዘመቻ ተካሂዶ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉ የትምህርት ዘርፍ ባለሥልጣኖች ተለምነዋል። ከዚያ ሁሉ የማግባባት (per-suasion) ጥረት በኋላ ነው ወደ ጣልቃ ገብነት የተሸጋገርነው። ይህም ስልት ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ይሄም ከፈተናው ቀን አንድ ሳምንት አስቀድሞ እንደመጨረሻ እርምጃ ፈተናው ወጥቶ ለሕዝብ በመበተን አስገድዶ የመሰረዝ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናችንን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነበር። በዚህም አልበቃ ብሎ በፈተናው ዋዜማ የወጣው የፈተና ኮፒ ለትምህርት ሚኒስቴር ተልኮ በኦሮሚያ ፈተናውን ከሰረዛችሁ ለሕዝብ አናሰራጭም የሚል የመጨረሻ መጨረሻ ዕድል ተሰጥቷቸው ነበር። ሰሚ ታጣ እንጂ።…”

ይህንን ለማረጋገጥ ወደ አገርዐቀፍ ፈተናዎች ድርጅትና ወደ ትምህርት ሚኒስትር የተለያዩ ቢሮዎች በተደጋጋሚ ደውለን መልስ የሚሰጠን ሰው ማግኘት አልቻልንም።

ትምህርት ለምን ያህል ጊዜ ተቋርጦ ነበር?

በመደበኛ ሥሙ ‹የአዲስ አበባ እና ፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ የልማት ዕቅድ› (ማስተር ፕላን) በ2006 ይፋ ከሆነ ጀምሮ ኦሮሚያ ክልል የነበረውን አንጻራዊ ሠላም አጥቷል። በሕዳር 2008 ዳግም የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ግን ከሁሉም የከፋ እና የተለየ ነበር። የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ፕሮጀክት የተቃውሞው የመጀመሪያ መቶ ቀናት ላይ ተመሥርቶ ባወጣው ሪፖርት፣ ሕዝባዊ ተቃውሞዎቹ በሁሉም፣ ማለትም በ18ቱም የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የተካሄዱ ሲሆን በየዞኖቹ ውስጥ ባሉ ከተሞች እና ትናንሽ የገጠር ቀበሌዎች የተወጡ የተቃውሞ ሰልፎች ብዛት 227 እንደነበር በዝርዝር አስቀምጧል። የተቃውሞዎቹ ተሳታፊዎችም ከተማሪዎች እስከ ገበሬዎች ሁሉም ዓይነት ሰዎች ነበሩ።

በዚህ ሪፖርት መሠረት እንኳን (በተለይም በምዕራብ ሸዋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ በምስራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች) ቢያንስ ለሦስት ወራት በክልሉ ትምህርት ተስተጓጉሎ እንደነበር መረዳት ይቻላል። መንግሥት ለወራት ትምህርት የተስተጓጎለባቸውን ተማሪዎች ፈተና ከሌሎቹ ትምህርት ካልተስተጓጎለባቸው ተማሪዎች አቻዎቻቸው ጋር እንዲቀመጡ መወሰኑ አግባብ አልነበረም። ከመንግሥት

በኩል በቂ ማብራሪያ ማግኘት ባይቻልም፣ በጥቂት የኦሮሚያ ትምህርት ቤቶች ፈተናው እንዲራዘም ታቅዶ እንደነበር ተወርቷል። ይሁንና ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በኦሮሚያ ትምህርት የተስተጓጎጎለው በሁሉም አካባቢ ነው። ባልተስተጓጎለባቸው ጥቂት አካባቢዎችም የሥነ ልቦና ጫናው ቀላል አልነበረም።

መንግሥት ምንም እንኳን በኦሮሚያ ተከስቶ የነበረውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ስህተት መሆኑን አምኖ ይቅርታ ጠይቆ ‹ማስተር ፕላኑን› ቢሰርዝም ጥያቄው ፖለቲካዊ መሆኑን አድበስብሶ አልፎታል። አሁንም የፈተናው ይፋ መለቀቅ ተራ ስርቆት እንደሆነ ብቻ ለማስመሰል እና ለማሳመን በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን እየተናገረ ነው።

ምን ይሻላል?ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል አገርዐቀፍ ፈተና

ላይ ከ253 ሺሕ በላይ ተፈታኞች ይቀመጡ ነበር፤ ለፈተናው ዝግጅት የወጣው ገንዘብም ከ215 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል። ፈተናው አለመካሄዱ (ጊዜው መራዘሙ) ትምህርት ተቋርጦባቸው ለነበሩት እፎይታ ቢሰጥም፤ ለፈተናው ተዘጋጅተው የነበሩት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ሊኖር ይችላል።

ጥያቄቹ እና መልሶቹ በይፋ በመለቀቃቸው ምክንያት የተራዘመው የፈተና መርሐ-ግብር አዲስ የተያዘለት ቀነ ቀጠሮ (ከሰኔ 27 እስከ 30፣ 2008) ደግሞ የሙስሊሞች የፆም ወር ረመዳን ፍቺ (ኢድ አል ፈጥር) የሚውልበት ቀን ላይ ያርፋል። የመንግሥት ኃላፊዎች ‹የሙስሊሞቹ በዓል እና አዲሱ የፈተና ቀን ቢገጣጠምም በዓሉ ይዘለላል› የሚል ማስተባበያ እየሰጡ ነው። ይሁን እንጂ ወትሮም በሙስሊሙ ጉዳይ እና በመንግሥት መካከል ለተነሳው ቅሬታ ‹መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› ተብለው የተሰየሙት ሰዎች ከታሰሩ ወዲህ ሙስሊም የመብት አራማጆች ‹ፈተናው ትልቅ ሱባዔ በሚጠይቀው በፆሙ ማብቂያ አካባቢ መደረጉ እኛን ለማጥቃት የተደረገ ሴራ ነው› በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የመጀሪያውን ፈተና ቀድመው ይፋ ያደረጉት እነ ጃዋር መሐመድም ፍትሐዊ የፈተና መርሐ ግብር እንዲወጣ በማለት 6 ነጥቦች የያዘ ምክር ሐሳብ በቅድመ ሁኔታነት ለትምህርት ሚኒስቴሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ላይ አስቀምጠዋል። ይህ መጽሔት ለሕትመት እስከተላከበት ጊዜ ድረስ መንግሥት የፈተና ቀነ ቀጠሮውን አስመልክቶ የሰጠው ምንም ምላሽ የለም።

የመንግሥት ኃላፊዎች በአላስፈላጊ እልህ መጋባት እና በማንአለብኝነት ከጊዜ ወደጊዜ የሕዝብን ጥያቄ ለመስማት እና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ባለመፍቀዳቸው ያለፈው ቅሌት ተከስቷል። አሁንም ሆነ ወደፊት የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ የተቀመጡ ግለሰቦች የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን አቤቱታ የማያዳምጡ እና ለጥፋታቸው ተጠያቂ የማይሆኑ ከሆነ ተመሳሳይ አገርዐቀፍ ቅሌቶች መከሰታቸው አይቀርም።

ከዳግም አገርዐቀፍ ቅሌት ለመዳን ምን ይደረግ?

Page 6: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

5ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ሐሳብ

ወደሚቀጥለው ገጽ

ሐረግ ስቦ ለሚያሳስበን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ምስጋና ይግባውና ዘውግ ሳንቆጥር፣ ጎጥ ሳንለይ ሐሳብን እንደሐሳብ የምናስተናግድበትን ትልቅ ሰውኛ ፀጋችንን ተነጥቀናል። አንድ ሐሳብ ከአንድ ዜጋ ሲነሳ ሐሳቡን ከሰውየው ዘውግ ጋር ማጋመድ 25 ዓመት ከገዛን ፓርቲ ሳናውቀው ወደ እኛ የተላለፈ በሽታችን እየሆነ ነው። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. እንደሆነ ሐሳብን ቀርቶ ሐይማኖትን ለአንድ ዘውግ ‹ከመሸለም› ወደ ኋላ የማይል ነው። ተፀንሶ ያደገበት ነውና አሁን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን በዘውገኝነት ለመክሰስ አይዳዳኝም። ይልቅስ የእኛ መባስ ያሳስበኛል። ነገራችን ሁሉ ዘውገኝነትን የተመረኮዘ መሆኑ አሳዛኝ ነው። የሰሞኑ የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናዎች ከፈተናው ቀን በፊት በማኅበራዊ ሚዲያ በይፋ የመለቀቁ ነገርም በዚሁ በዘውግ ከረጢታችን ገብተን እንነታረክ ዘንድ ‹ጥሩ› አጀንዳ ሆኖልናል። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን በዘውገኝነት የሚከሰው ሁሉ በኦሮሞ እና ሌላ ዘር ተከፍሎ ነው የድርጊቱን ክፉ ደግነት የሚመረምረው። በዘውገኝነቱ ውስጥ ደግሞ ፍረጃ አድፍጧል።

‹የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናውን ‹መሰረቅ› የተቃወመ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ነው፤ የፈተናውን ‹መሰረቅ› ያልተቃወመ ደግሞ የተቀሩት ሕዝቦች መጉላላት የማይታየው ከሃዲ ነው› በሚሉ ግራ ገብ ፍረጃዎች ስንንገላታ ነው የሰነበትነው። በዚህ መሐል ምክንያታዊ ትችቶችን ለማቅረብ፣ የግራቀኙን ክፉ እና በጎ ጎን ለማሳየት ፋታ የለም፤ እንዲሁ ለመፈረጅ መቻኮል ብቻ! ከፍረጃ ችኮላ እና ከዘውገኝነት ተፅዕኖ ለመላቀቅ ግን ሁሉንም ተፈታኞች በኢትዮጵያዊነት መነፅር መመልከቱ አስፈላጊ ነው። ይህ ቢቀር እንኳን ተፈታኞቹ የነገ ሕይወታቸውን አቅጣጫ በሚወሰን ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ እንዳሉ የሰው ፍጡራን

የፈተና “ስርቆቱ” ስንክሳርከግንቦት 22 እስከ 25፣ 2008 ድረስ በመላው የአገሪቱ ክፍሎች ሊሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቀድሞ በመለቀቁ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል። “የፈተናው ‹ተሰርቆ› በአደባባይ መለቀቅ መንግሥት ለመማር ከፈለገ ትምህርት ሰጪ ነው” በማለት መስከረም አበራ ጠቅላላ ሁኔታውን በሚከተለው መጣጥፏ ዳስሳዋለች።

ማየት ቢቻል ደግ ነው። ይህ ነው ሚዛንን ከሚያስቱ የዘውገኝነት እና የፍረጃ አባዜ ወጣ ብሎ እንደ ባለአእምሮ ለማሰብ የሚያስችለን።

ሥረ ነገር‹የፈተናው ቀድሞ መውጣት እና

ተከታይ መስተጓጎሎቹ ሁሉ መሠረታቸው ምንድን ነው?› ብሎ መጠየቁ ለመፍረድም ሆነ ለመፈረጅ ከመቻኮሉ መቅደም ያለበት ምክንያታዊ ጥያቄ ነው። የዚህ ጥያቄ መልስ ነው ለነገሩ መከሰት ትክክለኛውን ተጠያቂ የሚነግረን። እንደሚታወቀው ‹አዲስ አበባን ከአጎራባች ከተሞች ጋር አቀናጅቶ ለማልማት ያለመ ነው› ሲል ገዥው ፓርቲ የተለመውን እቅድ በመቃወም በኦሮሚያ ከፍተኛ የሆነ ነፍስ የመዋደቅ ትግል ተደርጎ ነበር። ይህ ትግል የኦሮሞ ሕዝብ ከፍተኛ ፅናት የታየበት እና ገታራውን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ለመጀመሪያ ጊዜ ይቅርታ ያስጠየቀ፣ ገዥው ግንባር አድርጎት የማያውቀውን ውሳኔውን የመከለስ አጣብቂኝ ውስጥ ያስገባ ባለግርማ ሆኖ አልፏል። ትግሉ የሕዝብ ክንድ ምን ያህል ውጅግራ ከታጠቀ ፋኖ ደንዳና ልብ የበረታ እንደሆነ ያስመሰከረ ነው። ነገሩ ልብ ያለው ልብ እንዲያደርግ በብዙ መንገድ ታላቅ ትምህርት ያዘለ ነው ።

በሌላ በኩል ትግሉ ፖለቲካዊ መረጋጋትን አጥብቆ የሚሻውን የመማር ማስተማር ሒደት ጎድቶ ሰንብቷል። መጠኑ ቢለያይም በሰፊው የኦሮሚያ ክልል የመማር ማስተማሩ ሒደት ያልተስተጓጎለበት ጥግ ማግኘት አይቻልም። በአንዳንድ ቦታዎች እንደውም እስከ ቅርብ ጊዜ የመማር ማስተማሩ ሒደት ወደነበረበት እንዳልተመለሰ የዓይን ምስክሮች የሚገልፁት ነው። ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ኦሮሚያ ወዲያውኑ እንደ ገነት በሆነ ሠላም ውስጥ መሆኗን፤ መማር ማስተማሩም

በተገቢው ሁኔታ መቀጠሉን፤ በትግሉ ሳቢያ የተስተጓጎሉ ጥቂት የትምህርት ቀናት ወዲያው ተካክሰው ነገሮች በቦታቸው እንደተመለሱ መለፈፉን ተያያዙት። ዛሬ የመጣው አገራዊ ውርደት ሥሩን የተከለው በዚህ የመንግሥት ግብዝነት አፈር ላይ ነው።

የአገራችን መንግሥት ከእውነታ ይልቅ በፕሮፖጋንዳ ፍቅር የወደቀ በመሆኑ ሐቁን ወደ ጎን ብሎ ‹ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ችግር ተፈትቷል፣ በክልሉም ሠላም ወርዷል› እያለ እራሱን ሲያታልል ከረመ፤ እውነታው ግን ሌላ ነው። እውነቱ ሲገለጥ ታዲያ ለመንግሥት ውርደትን ያዘለ ትምህርት ሰጭ ነገር ይዞ መጣ - በጥብቅ ሚስጥራዊነት መጠበቅ የሚገባው ብሔራዊ ፈተና ጥያቄ እና መልስ ባሕር ተሻግሮ ተመልሶ ደረሳቸው። ይህ እንዳይሆን መንግሥት መሥራት የነበረበት ቀላል ሥራ የኦሮሚያ ተማሪዎችን የቀደሙ ወራት ቆይታ ሳይነገረው አጢኖ እንደ አካዳሚያዊ እና የሥነ ልቦና ዝግታቸው ሁኔታ የሚፈተኑበትን መንገድ መፈለግ፤ የሌላውን ክልል ተማሪ ደግሞ በወጣው መረሐ-ግብር መፈተን። ቀላሉ መንገድ ይህ ነበር! መንግሥት ግን ይህን ካደረገ በፊት ካወራው አጉል ፕሮፖጋንዳ ጋር የሚጋጭ ስለሆነ፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. እይታ ደግሞ ከሁሉ በፊት ፕሮፖጋንዳ በክብር ሰገነቱ ላይ ከነሞገሱ መቀመጥ ስላለበት ይህን አዋጭ መንገድ ትቶ ካፈርኩ አይመልሰኝ ጉዞውን ተያያዘው። ስንት ወር ስትታመስ የነበረችዋን ኦሮሚያ እንደተረጋጋች ሲያወራ ስለባጀ ለዚች ክልል ልዩ ፕሮግራም ማውጣቱ የሚጠነቀቅለትን ፕሮፖጋንዳውን ክብር መንካት መሰለው። ስለዚህ በተማሪዎቹ ዕጣፋንታ ላይ ፍርደ ገምድል ውሳኔ መወሰኑን መረጠ፤ ውጤቱንም አየው።

የብሔራዊ ፈተናው መውጣት የሚማር ከሆነ ለመንግሥት የሚያስተምረው ብዙ ነው። ጠመንጃ እና ፕሮፖጋንዳ የሁሉ ጥያቄ የመልስ ሳጥን እንዳልሆኑ የሚነግር አንድ አጋጣሚ ነው - ክስተቱ። ጠመንጃ እና ፕሮፖጋንዳ ሕ.ወ.ሓ.ት./ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ደርግን ገንድሶ ከደደቢት አዲስ አበባ እንዲዘልቅና አለቅነት በጫንቃው ላይ እንዲያደርግ ማስቻሉ እውነት ነው። ይህ ማለት ግን አዲስ አበባ ከገቡ በኋላም ሁሉ ነገር በብረት እና በፕሮፖጋንዳ ይመለሳል ማለት አይደለም። ይልቅስ ብረትን አውርዶ ከተማን እንደ ከተሜ የመያዝን ብልሐት እና

Page 7: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

6 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

እንደ መኖራችን ውግዘቱ በትክክለኛ የችግሩ ፈጣሪ በመንግሥት ላይ እንደሚበረታ አሳምረን እናውቃለን። የሆነ ሆኖ የመንግሥት ኃላፊነትን የመውሰድ ሽሽት እውነትን ወደ መካድ ሌላ ጥፋት መርቶታል። ይህ ደግሞ የይቅርታውን ቅንነት እንድንጠራጠር ያደርገናል።

መንግሥት ሌላ ፈተና ለማውጣትና ፈተናውን ለማስቀጠል ያቀደው ዕቅድ እና የሚናገረው ንግግር ተደናግሮ የሚያደናግር ነው። በመጀመሪያው ቀን ማታ ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ‹የወጣውን ፈተና ስናዘጋጅ ሌላ ተመጣጣኝ ፈተና አዘጋጅተን ስለነበር የፈተናውን ነገር እዳው ገብስ ነውና በእኛ ተዉት’ ዓይነት ነገር ተናግረው ነበር። አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ደግሞ ፈተናውን የማውጣቱን ኃላፊነት ‹የሚፈተን ልጅ ውላጅ፣ ዘመድ አዝማድ የሌለውን የዩኒቨርሲቲ መምህር ፈልገን እናስወጣለን› ሲሉ ቀልድ አይሉት ቁምነገር ነገር ተናገሩ። የዚህን አነጋገር ጨቅላነት አንባቢ አይረዳም ብየ ስለማላስብ ወደ ዝርዝር አልገባም። ሳልናገር የማላልፈው ነገር ግን የሰውየው ንግግር የሙያ ሥነ ምግባር እና ኃላፊነት የሚባል ነገር በምድር ላይ የሌለ የሚያስመስል ነገር መሆኑን ነው። እዚህ ላይ የአቶ ሽፈራውን የሥነ ትምህርት ሙያ ዕውቀት ደረጃ እንድንለካ፤ ትምህርት ሚኒስትርም ከነማን እጅ ወጥቶ በነማን እጅ እንደገባ አስበን እንድንቆዝም እንገደዳለን። (ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ፣ ዶ/ር ያየህ ይራድ ቅጣው፣ ዶ/ር ኃ/ገብርኤል ዳኜ፣ አቶ ኢብሳ ጉተማን የመሰሉ ዓለምዐቀፍ ምሁራን በአንድ ወቅት የአገራችንን የትምህርት ሚኒስትር እንደመሩ ልብ ይሏል)።

እንዴትም ሆኖ ይውጣ ‹በቀጣይ ቀናት ወጥቶ ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል› የተባለው ፈተና የቀድሞው ፈተና ከተሰረዘ አንስቶ የአንድ ወር ጊዜ የተሰጠው ነው። ትልቁ ጥያቄ ግን ይህ አንድ ወር ‹ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ለሆኑት የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች በቂ ነው ወይ?› የሚለው ነው። ‹ተማሪዎቹ በተነሳው አለመረጋጋት ሳቢያ ለወራት ከትምህርት ገበታቸው ተለይተው እንደመቆየታቸው አንድ ወር ቤታቸው መቀመጣቸው በክፍል ውስጥ ባለመማራቸው ያጡትን የሚያካክስ ነው ወይ? ይሄ ዋና ጉዳይ ባልተሟላበት ሁኔታ የሁለተኛው ፈተና ስኬታማነት ያስተማምናል ወይ?› የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መንግሥት በቅጡ ያሰበባቸው አይመስልም። ይህ ደግሞ መንግሥት ከመጀመሪያው የችግሩን ሥረ ምክንያት ላለመመርመር ከመፈለጉ አውቆ መተኛት ይመነጫል። መንግሥት የችግሩን ሥረ ምክንያት መመርመር የማይፈልገው ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው የችግሩ ፈጣሪ ራሱ ሆኖ ሳለ ይህን እውነት መቀበል ስለማይፈልግ ነው። በዚህ መንገድ የችግሩን ሥረ ነገር አለባብሶ ለመፍትሔ መገስገሱ ምን ያህል እንደሚያስኬድ የምናየው ይሆናል።

መስከረም አበራ በኢሜይል አድራሻዋ

[email protected] ሊያገኟት ይችላሉ፡፡

ሐሳብ

ዕውቀት ገንዘብ ማድረግ ግድ ነው። ካልሆነ የቸገረው ሕዝብ እንዲህ እንዳሁኑ (የፈተና “ስርቆት”) ድል መንሳት ሁሉ ከጠብመንጃ ብቻ እንደማይቀዳ በተግባር ያሳያል።

ሁለተኛው ክስተቱ ያስተማረው ትምህርት በአንድ አገር ያሉ ሕዝቦችን የሁለት ዓለም ሰው አድርጎ ከፋፍሎ መግዛቱ ሁሌ እንደማይሳካ ነው። በሌላ አባባል የተከፋፈለ የመሰለን ሕዝብ በደል አንድ እንደሚያደርግ ግፈኞች ልብ ካላቸው ልብ የሚሉበት አጋጣሚ ነው፤ ይህ የፈተናው መውጣት ጉዳይ። ከዚህ ቀደም ‹ወላይቶች ስለአኵስም ሐውልት ምን ተዳችሁ? ኦሮሞዎች ስለ አማራ መፈናቀል ምን ዶላችሁ? አማሮችስ ስለ ደቡብ ኦሞዎች በገመድ መጠፈር በየት ዞሮ ያስጨንቃኋል?› እየተባለ ሲነገረን እኛም እየተስማማን ኖረናል:: አሁንም ኦሮሞዎች ‹መሬታችንን አስረክበን በመሬታችን ላይ በሚሠራው የባለጊዜዎች ሕንፃ ዘበኛ አንሆንም› ብለው ሲሞቱ፤ ሌሎቻችን ዝም ብለን ነበር። የዚህ ጥያቄ መዘዝ ተማዞ ተጠማዞ የእኛንም ልጆች ፈተና እስከማሰረዝ ደረሰ። ሲያስገድላቸው እያየን ችላ ያልነው የወገኖቻችን ብሶት ውጤቱ በዘወርዋራው ቤታችንን አንኳኳ። ይሄኔ መጯጯህ ጀመርን። ከዚህ የምንገነዘበው በሰበብ አስባቡ እየተከፋፈልን የአምባገነኖች በደል እንዲጎለምስ ጊዜ በሰጠነው ቁጥር ሁላችንንም የማጥቃት ጉልበት እንደሚያበጅ ነው። በደልን የሚያጎለምሰው የእኛ ቸልታ ደግሞ መሠረቱ የተጣባን የዘረኝነት ልክፍት ነው።

በዘውገኝነት ትንሽ ከረጢት ውስጥ ስንገባ የሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ለቅሶ የሠርግ ቤት ድለቃ ይመስለናል፤ ሁሉን አይቶ እንዳላየ እናልፋለን። ይህ አርቆ ለማያየው መንግሥት ሠርግና መልስ ነው። የተረሳው ነገር ግን በዘውገኝነት ጎሬ ውስጥ ብንሆንም በአንድ አገር ጥላ ሥር የመሆናችን እውነታ ነው። የረሳነው የኢትዮጵያዊነት ሰፊ ማዕቀፍ ቢያንስ በትልልቅ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ አንድ ያደርገናል። የሰሞኑ የፈተና ስርቆት ይህን በማስታወሱ ረገድ የሚወዳደረው የለም። እዚህ እስከሚደርሱ ድረስ የሚያስተሳስራቸው ጉዳይ እምብዛም እንደሌለ እንዲያስቡ ተደርገው ያደጉት የዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ዛሬ በአንድ ጉዳይ ላይ ዕኩል በመንግሥት ላይ መቆጣታቸው ለመንግሥት ሁሌ መከፋፈል እንደማይሳካ ያመላከተ ነው፤ እኛ ዜጎችም ወደን ለመስማማቱ ማስተዋል ቢያጥረን በደል በግድ አንድ እንደሚያደርገን ጠቁሞናል። ማስተዋሉን ከሰጠን በደል ለማጉረምረም አንድ ከሚያደርገን ይልቅ ቀድመን በኅብረት ብንቆም ግፍን በአጭር መቅጨት እንደምንችል ይገባናል።

የመንግሥት ‹ተደናጊረ› የማንኛውም ፈተና ውጤታማነት ሙሉ

በሙሉ በምሥጢራዊነቱ ላይ የሚመሠረት ነው። ፈተና ምሥጢራዊነቱ ሲያበቃ ፈተናነቱም ያበቃል። መንግሥትም የደሀን አገር ብዙ ገንዘብ አፍስሶ ፈተና ከማዘጋጀቱ

በፊት ፈተናው የሚዘጋጅላቸውን ተማሪዎች ዝግጁነት ማጤን የፈተናውን ምሥጥራዊነት ለማስተማመን ያግዘው ነበር። የእኛ አገር መንግሥት ግን እንኳን በራሱ ተነሳሽነት ይህን ሊያደርግ ቀርቶ ጉዳዩ ያስጨነቃቸው አካላት ስለ ኦሮሚያ ልዩ ሁኔታ እንዲያስብበትና መላ እንዲያበጅ ደጋግመው ቢያሳስቡትም ‹የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ› እንዳለ ነው በሰፊው እየተነገረ ያለው። ሌላ ድምፅ ያለ መስማት አባዜው ቢገልጸውም ባይገልጸውም መንግሥትን የሚያሳፍር ውርደት ውስጥ እንደከተተው ግልጽ ነው። የሚብሰው ደግሞ ፈተናው ከወጣ በኋላ መንግሥት እየሰጠ ያለው መልስ ነው።

መንግሥት ፈተናው ወጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ እየተናገረ ያለው ነገር የተቀመጠበትን ወንበር የሚመጥን አይደለም። በእርግጥ ለተፈጠረውን መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቋል። ይህ በጎ ነገር ቢሆንም ይቅርታው የተጠየቀው ለየትኛው ስህተት እንደሆነ ግልጽ መሆን ነበረበት። ይቅርታ የተጠየቀው ‹መንግሥት የኦሮሚያን ልዩ ሁኔታ ያላገናዘበ የፈተና መርሐ-ግብር በማውጣቱ ነው፤ ወይስ ፈተናውን ሚሥጥራዊነት ማስጠበቅ ለተሳነው ዝርክርክነቱ?› በበኩሌ ይቅርታው መሆን ያለበት ለመጀመሪያው ጉዳይ ነው (ሁለተኛው የአንደኛው ውጤት ነውና)። መንግሥት ግልጽ ባያደርግም ይቅርታ የጠየቀው ለሁለተኛው ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም። ፈተናውን አወጡ የተባሉ ሰዎችን ረግሞ ሕዝብም እየረገማቸው እንደሆነ ለማስመሰል የፕሮፓጋዳ ከበሮውን ማንሳቱ ይህን ያመላክታል። እኛ ደግሞ በሕዝብ መሐል

የአገራችን መንግሥት ከእውነታ ይልቅ

በፕሮፖጋንዳ ፍቅር የወደቀ በመሆኑ ሐቁን ወደ ጎን ብሎ ‹ኦሮሚያ

ውስጥ ያለው ችግር ተፈትቷል፣ በክልሉም ሠላም ወርዷል› እያለ

እራሱን ሲያታልል ከረመ፤ እውነታው ግን

ሌላ ነው

Page 8: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

7ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ሐተታ

ወደሚቀጥለው ገጽ

በአዲስ አበባ ከተማ በጫማ ጠረጋ፤ እንደ ማስቲካ፣ ሲጋራ፣ ሶፍት፣ የሞባይል ስልክ ካርድ የመሳሰሉት ትንንሽ ሸቀጣ ሸቀጦች

ሽያጭ፤ የግንባታ እና የቀን ሥራዎች ላይ የተሰማሩት አብዛኛዎቹ ሰዎች ወደአዲስ አበባ ከመጡ ብዙ ዓመታት ያላስቆጠሩ የደቡብ ክልል ወጣቶች ናቸው። በቤት ሠራተኝነት እና በሴተኛ አዳሪነት የተሰማሩት ደግሞ ባብዛኛው ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እና ከኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ሴቶች ናቸው። አብዛኛዎቹ ከገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ አቅራቢያቸው ከተሞች፣ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ፍልሰት በመዲናይቱ አይቆምም፤ ብዙዎቹ እንደመሸጋገሪያ ነው የሚቆጥሩት። ወንዶቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያልሙ፣ ሴቶቹ ደግሞ ወደ አረብ አገራት መሄድን በዕቅድ ይይዛሉ። እዚህ የሚሠሩትንም ሥራ ለመሸጋገሪያ ገንዘብ ለማግኘት ነው የሚጠቀሙበት።

የከተማ ስደተኞቹ በብዛት ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ቀድሞ የመጣ ጓደኛ ወይም ዘመዳቸውን ተከትለው ሲሆን፣ የሚኖሩት በጋራ በተከራዩት ቤት ወይም ደግሞ በየዕለቱ ጥቂት ብር ብቻ በሚያስከፍሉ የጋራ አልቤርጎዎች ውስጥ ነው። ምንም ወዳጅ እና ዕውቀት የሌላቸው ጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው። ስደተኞቹ፣ የቋንቋ እና የባሕል ልዩነታቸው ከነባሩ የአዲስ አበቤ ጋር እንዲቀላቀሉ ስለማያበረታታቸው፣ ዙሪያቸው ከቀያቸው በመጡ ሰዎች የተከበበ ነው። የሚሠሩት ሥራም እንዲሁ ተመሳሳይ ሲሆን፣ ባብዛኛው በጉልበት ላይ የተመሠረተ ነው። ብዙዎቹ በጋራ መኖሩ እና መሥራቱ በተለይ በኢኮኖሚ መቋቋም እንዲችሉ እንዳደረጋቸው ይናገራሉ።

ለመሆኑ የወደ ከተማ ፍልሰት መንስኤው እና ውጤቱ ምንድን ነው?

የከተማ ስደት በኢትዮጵያአሉላ ፓንክረስት እና ፈለቀ ታደለ በጋራ

በሠሩት ጥናት (Migration and Well Being in Ethiopia) የከተማ ስደት ታሪክን በኢትዮጵያ ከዳግማዊ ምኒልክ የደቡብ ወረራ (Conquest) እና አገር ግንባታ (nation building) እንቅስቃሴ

ጋር ነው አያይዘው የሚያስጀምሩት። በወቅቱ አዳዲስ ከተሞች የሚመሠረቱበት ጊዜ ስለነበር፣ የግንባታ ሥራዎች ላይ በጉልበት ሠራተኝነት እና በሌሎችም የአገልግሎት ሠራተኝነት ለመቀጠር ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰቶች ተከስተዋል። ከዚያ በኋላ የጅቡቲ አዲስ አበባ የባቡር መሥመር መዘርጋት የከተሞችን መፍላት እና የገጠሬ ወደ ከተሜው መፍለስንም ባሕል አሳድጎታል። በመቀጠል በአምስት ዓመቱ የኢጣልያ ወረራ ወቅት፣ ከተሜነት መስፋፋቱ እና የሥራ ክፍፍልና ልዩነት (labor divi-sion and specialization) መፈጠሩ ለከተማ ፍልሰት ሌላ የወቅቱ አዲስ መንስኤ ሆኗል። በደርግ ዘመነ መንግሥት ለገጠሬው ወደከተማ መፍለስ በርካታ ምክንያቶች ነበሩ፤ የባላባቶች መሬት መነጠቅ፣ የንግድ እርሻዎች መዘጋት እና አዳዲስ ኬላዎች መከፈት ጥቂቶቹ ናቸው።

በዘመነ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.፣ በአሉላ እና ታደለ ጥናት መሠረት ዘውግ ላይ የተመሠረተው አከላለል በክልሎች መካከል ያለውን የፍልሰት ልምድ ሲገድበው፣ መሬት በመንግሥት ይዞታ ስር እንዲሆን መደንገጉ ደግሞ ወደ አቅራቢያ የገጠር ከተሞች ያለውን ፍልሰት እንደገደበው ቢነገርም፣ ለዘለቄታውም ይሁን ለአጭር ጊዜ የሚደረገው ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት መጨመሩን ግን እንዳላገደው ጠቁመዋል።

ፍልሰት መር የአዲስ አበባ ሕዝብ ዕድገት

የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በ2000 ባሠራው ጥናት መሠረት በ1950ዎቹ በአዲስ አበባ ይኖር የነበረው ከተሜ ብዛት 46 በመቶ ብቻ ነበር። ቀሪው በፍልሰት ወደ ከተማዋ የገባ እና ከተማዋ ዳርቻ ላይ በእርሻ የሚተዳደር የገጠር ሰው ነበር። በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የአዲስ አበባ ሕዝብ ብዛት ዕድገት ዋነኛ ምንጭ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ሆኖ ተመዝግቧል።

ጥናቱ በተደረገበት ወቅት ከኢትዮጵያ የከተማ ነዋሪዎች መካከል ብዙዎቹ (23 በመቶ ያህሉ) በአዲስ አበባ ብቻ ነበር የሚኖሩት።

በዚሁ ጥናት መሠረት፣ 1990ዎቹ አጋማሽ ድረስ የአዲስ አበባ ሕዝብ ዕድገት 58 በመቶ የሚሆነው ምንጩ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት ነበር። በ1996፣ 1.3 በመቶ የሚሆነው የከተማዋ የሕዝብ ዕድገት መንስኤው ከገጠር ወደ ከተማ የነበረው ፍልሰት ሲሆን፣ በውልደት የነበረው የአዲስ አበባ ሕዝብ ዕድገት 1.5 የነበረ በመሆኑ የከተማ ፍልሰት ለአዲስ አበባ ሕዝብ መጨመር ተመጣጣኝ ሚና ያለው መሆኑ የፖሊሲ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጥናቱ አመልክቷል።

በወቅቱ ወደ አዲስ አበባ ይፈልሱ የነበሩት በተለይ ሴቶች ነበሩ። ለዚህ በምክንያትነት የተቀመጠው ሴቶች ከወንዶች የተሻለ የቤት ሠራተኝነት፣ የችርቻሮ ንግድ እና ሌሎችም ሕገወጥ ንግዶች ላይ የመሠማራት ሰፊ ዕድሎች ስለነበሯቸው ነው። የሴቶች ፍልሰት አሁንም ከወንዶች የበለጠ ነው።

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚጠቁመው በ1986 ብቻ አገር ውስጥ ከአንዱ ቦታ ወደሌላው የሚደረጉ ፍልሰቶች 6.91 ሚሊዮን ሰዎች ተሳትፈዋል። ይህ እንግዲህ ከጠቅላላው ሕዝብ 14.1 በመቶ ያክሉ ከቀያቸው እንደፈለሱ ያሳያል። የአገር ውስጥ ፍልሰት ቁጥሩ በ1999 በእጥፍ አድጎ ወደ 12.2 ሚሊዮን (16.6 በመቶ ሕዝብ) ደርሷል። በሁለቱም ጊዜያት ውስጥ የሴት ስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ነበር።

አብዛኛዎቹ (በ1986፣ 46.6 በመቶዎቹ እና በ1999፣ 47.6 በመቶዎቹ) ስደተኞች የፈለሱት ወደአዲስ አበባ እንደሆነም ተመዝግቧል።

ወዲህ ጎታች እና ከዚያ ገፊ ምክንያቶች

ብርሃን አስማሜ ምሕረቱ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረጉ ፍልሰቶች መንስኤ እና ውጤት ላይ ለሁለተኛ ዲግሪያቸው ማሟያ በሠሩት ጥናት ላይ፣ ፍልሰትን የሚያስከትሉ ወደ ከተሞች ጎታች እና ከገጠር ገፊ የሆኑ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል። የገጠሩን ነዋሪ ለፍልሰት የሚዳርጉት ገፊ ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ድርቅ እና ረኀብ፣ ለትምህርትና ጤና አገልግሎት ያልተመቻቸ የኑሮ ሁኔታ፣ የግብርና ምርት ማሽቆልቆል እና የሥራ ዕድል መጥበብ ሲሆኑ፤ ወደከተማ እንዲፈልሱ የሚያስገድዷቸው ምክንያቶች ደግሞ የተሻለ የሥራ ዕድል በከተሞች መኖሩ፣ ከፍ ያለ ገቢ፣ የተሻለ የጤና እና የትምህርት ተዳራሽነት፣ እንዲሁም የተሟላ የከተማ መሠረተ ልማት፣ የተሻለ የኑሮ ዘዬ እና ወዘተ. ናቸው። በሌላ

ፍልሰት ወደ ከተማ፤ችላ የተባለ አሳሳቢ ጉዳይ?

ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ጥሩ ፖሊሲ አልተቀረፀለትም፤ ይሁን እንጂ በተለይ በአዲስ አበባ ለሕዝብ ቁጥር መጨመር ከፍተኛ ድርሻ አለው፤ በዚህም ምክንያት ኑሮ በአዲስ አበባ ለስደተኞቹም ለነባሮቹም አስቸጋሪ እየሆነ ነው በማለት የጻፈው በፍቃዱ ኃይሉ መንግሥት ጉዳዩን የሚገባውን ያክል ትኩረት እንዲሰጠው ይጠይቃል።

Page 9: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

8 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ጥናት እንደተመለከተው፣ ትምህርት ወይም ሥራ (ከሁለት አንዱን) ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ የሚፈልሱት ዜጎች ቁጥር ከጠቅላላው ስደተኞች 77 በመቶ ይደርሳል።

የዓለም ባንክ በ2000 ባሠራው የከተማ ስደትን የተመለከተ ጥናት ላይ፣ በወቅቱ 2.6 በመቶ ያድግ የነበረው የሕዝብ ብዛት ገጠሬው የእርሻ መሬት እንዲጠበው ስላደረገው ለስደት እንደተዳረገ ጠቅሷል። በገጠር፣ መሬት ዋነኛው ሀብት እንደመሆኑ እና ከአባት ወደ ልጆች ሲተላለፍ እየተሸነሸነ በመምጣቱ በቂ ምርት መስጠት የማይችል መሬታቸውን እየተዉ ወደ ከተማ የሚሰደዱት ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ችሏል። ይሁን እንጂ፣ የዓለም ባንክ እንደሚለው፣ የመንግሥት ፖሊሲዎች ይህንን ችግር ከቁብ አልጣፉትም።

በተጨማሪም ከ7 ዓመት ያልበለጡ ሕፃናት በተለይ ከጋሞ አካባቢ ወደ ኮልፌ እና ሽሮሜዳ አካባቢዎች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ይመጡና በሽመና ሥራ እንዲሰማሩ እንደሚደረግ የነአሉላ ፓንክረስት ጥናት ያመለክታል። በተመሳሳይ የከተሜ ቤተሰቦች የገጠር ልጆችን እናስተምራለን በሚል ሰበብ ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው ያስመጡና ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ፈንታ በጉልበት ብዝበዛ ሊፈረጅ ወደሚያስችል ሥራ ያሰማሯቸዋል።

ትልልቅ ተስፋ አዝለው ከገጠር የሚፈልሱት ብዙዎቹ ዜጎች የተመቻቸ ሁኔታ በሚፈልሱበት ከተማ አይጠብቃቸውም። ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሱ ዜጎች ውሱን የሥራ ዕድሎች ላይ ብቻ ነው የመቀጠር ዕድል ያላቸው። ይኸውም አብዛኛው ከተሜ በማይሠራቸው (ወይም በሚንቃቸው)፣ እንደ ጫማ ጠራጊነት፣ ሱቅ በደረቴ እና የቤት ሠራተኝነት በመሳሰሉት የሥራ ዕድሎች ላይ የተወሰነ ነው። በተጨማሪም፣ ከድህነት እና ጣሪያ ከነካ የኑሮ ውድነት ጋር በጥቂት ገቢ እንዲፋጠጡ ይሆናል። የመጠለያ ችግር፣ የዕለት ተለት መገልገያ ቁሳቁስ ዕጦት እና ሌሎችም ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት ይቸገራሉ።

የከተማ ፍልሰት እና ሕገ ወጥ ሥራዎች

ከገጠር ወደ ከተማ የሚሰደዱ ዜጎች ብዙውን ጊዜ ከተማ ውስጥም ሥራ በማጣት እንደሚቸገሩ ይነገራል። በተቃራኒው ደግሞ፣ ደመወዛቸው የማይቀመስ እየሆነ ነው በሚል የሚያማርሩ የከተማ ነዋሪዎችም አሉ።

ሀና የፋሲካን በዓል ከቤተሰቦቿ ጋር ለማክበር አዲስ አበባ በመጣች በሳምንት ጊዜ ውስጥ ‹ቦሌ ድልድይ› እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ስትንቀሳቀስ ከየት እንደመጣ ያላወቀችው ወጣት የጉዞ ሰነዶቿን የያዘ ቦርሳዋን ከእጇ ላይ መንትፎ ተፈተለከ። ልትከተለው ስትሞክር በአካባቢው የነበሩ ወጣቶች እንደሚያባርሩት በማስመሰል ግር ብለው በመሮጥ እሷን አዘናግተው፣ መንታፊውን እንዳስመለጡት

ትናገራለች። ጉዳዩን ለአካባቢው ፖሊስ ከጠቆመች በኋላ ፖሊስ የያዛቸው ተጠርጣሪዎች በሙሉ ከገጠር ወደ ከተማ ፈልሰው የመጡ ወጣቶች ነበሩ። ሀና ወደ መጣችበት አገር ለመመለስ የያዘችው ዕቅድ በዚህ ስርቆት ምክንያት ለሁለት ሳምንታት ያክል ለመዘግየት ተገድዳለች።

በሌላ በኩል፣ አቶ ተክለብርሃን የተባሉ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ያነጋገራቸው የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭ የቀን ሠራተኛ የዕለት ደሞዝ (“ጆርናታ”) ከመቶ ብር በላይ እንደሆነ እና የሠራተኛ እጥረት የሚገጥምበት ጊዜ ቀላል እንዳልሆነ ገልጸውለታል። “አንዳንዶቹ ከገጠር ወደከተማ የፈለሱት ወጣቶች ምንም አይሠሩም። በየዕለቱ የሚያጠፉትን ገንዘብ ከዬት እንደሚያመጡትም መገመት ከባድ አይደለም። በዚያ ላይ ከከተሜው ጋር የሚያመሳስላቸው ስለሚመስላቸው ወደጫት እና ሲጃራ ተጠቃሚነት ወዲያው ነው የሚገቡት” ይላሉ አቶ ተክለብርሃን።

ወ/ሮ አዜብ ከአቶ ተክለብርሃን የተለየ አመለካከት የላቸውም። የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን፣ ሥራቸውን ለቀው የወጡት የቤት ሠራተኛ በማጣት እንደሆነ ይናገራሉ። “ሙሉ ምግብ እና መጠለያዋ የተቻለላት የቤት ሠራተኛ እጅግ አነሰ ቢባል በወር 800 ብር እንዲከፈላት ትጠይቃለች። ይህ ደግሞ በመንግሥት ሥራ ደሞዝ የሚቀመስ አይደለም።” የሚሉት ወ/ሮ አዜብ፣ “የሚያዋጣ ሆኖ ስላላገኘሁት እኔ ሥራዬን ለቅቄ የቤት ሥራዎቹን እየሠራሁ በባለቤቴ ገቢ ለመተዳደር ወስነናል” ብለዋል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በተለይ ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በማኅበረ-ባሕላዊ ሁኔታዎች - ማለትም አላቻ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ የባል ሞት፣ እና የመሬት ባለቤትነት መብት ማጣት ምክንያቶች ሴቶች ወደአዲስ አበባ በገፍ ይሰደዳሉ። እነዚህ ወንዶች የሌሉባቸው ተጨማሪ ማኅበረ-ባሕላዊ ግፊቶች ናቸው የሴት ስደተኞች ቁጥር ከወንድ ስደተኞች ቁጥር የበለጠ እንዲሆኑ የሚያደርጉት። የቤት ሠራተኛ መሆን ያልቻሉት ወጣት ሴቶች ወደ ሴተኛ አዳሪነት ሲገቡ፣ በዕድሜ የገፉት ደግሞ ወደ ልመና ይሠማራሉ።

ስደት በየአምስት ዓመታት ዕቅዶቻችን ውስጥ

አዲስ አበባ በውልደት ከሚጨምረው የሕዝብ ቁጥሯ ባልተናነሰ፣ ማስተናገድ ከምትችለው በላይ ከገጠር በሚሰደዱ ዜጎችን ትቀበላለች። ለዚህ ዋነኛው ምክንያት ተደርገው የሚጠቀሱት የከተማዋ ከሌሎች ከተሞች የበለጠ ማደግ እና የኮንስትራክሽን ዘርፉ ያለተፎካካሪ ማበብ ነው። በተጨማሪም፣ የከተማዋ ነባር ነዋሪዎች የማይመርጧቸው የሥራ ዓይነቶች ከገጠር ለሚመጡት መቀበያ እና መላመጃ የሥራ ዘርፍ ስለሚሆን ነው። እንዲሁም፣ ከተማዋ ከአገር መውጣት ለሚፈልጉ በሙሉ

ሐተታ

ማዕከል መሆኗ ሌላኛው የገጠር ስደተኞችን የሚስቡ ገፀ በረከቷ ነው።

በእንግሊዝ መንግሥት የሚደጎመው የዕርዳታ ድርጅት (UKAID) የሠራው የኢትዮጵያ የስደት ፖሊሲ ጥናት እንደሚያመለክተው የአገር ውስጥ ፍልሰትን በተመለከተ የፖሊሲ ክፍተት አለ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የኢትዮጵያ ‹የስትራቴጂ ሰነዶች› እና በUSAID (2012)፣ በDFID (2012) እና በዓለም ባንክ (2012) የተሠሩ ጥናቶች የፍልሰት/ስደትን ጉዳይ ወይ በዝምታ ያልፉታል አልያም ደግሞ በአሉታዊ ጎኑ ብቻ ይጠቅሱታል።

በ1993 የፀደቀው ‹የዘላቂ ልማት እና የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ሰነድ› መንግሥት ካመቻቸው ዝውውር (ፍልሰት) ውጪ ያለው ፍልሰት በሙሉ በዘውጎች መካከል ውጥረት የሚያነግስ እና ለተፈጥሮ ሀብት መመናመን አደጋ የሚጥል እንደሆነ ተደርጎ ተጠቅሷል። በ1998 የፀደቀው ‹ድህነትን ለማጥፋት የተፋጠነ ዘላቂ ልማት ዕቅድ ሰነድ› ላይም ፍልሰት ተላላፊ የሆኑ እንደኤ.ች.አይ.ቪ. ያሉ በሽታዎችን በማሰራጨት የከተማ ድህነትን እና የሥራ አጥነት የሚያስፋፋ የልማት እንቅፋት እንደሆነ ተጠቅሷል። አንደኛው እና ሁለተኛው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ውስጥ ግን ስደት/ፍልሰት ምንም እንደሌለ ወይም እንደማያሳስብ ጉዳይ ከነአካቴው አልተጠቀሰም።

ጥቅም፣ ጉዳት እና መፍትሔከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት

ጉዳት ብቻ ያለው ጉዳይ እንዳልሆነ አጥኚዎቹ ይናገራሉ። ከተሜዎች የማይሠሯቸውን ሥራዎች ስደተኞቹ የሚሠሩ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ አብዛኛዎቹ ስደተኞች በአንጻራዊ የባሰ ድህነት ውስጥ ወደ ሚገኘው ቀዬያቸው የሚልኩት ገንዘብ የገጠሩን ሕይወት የማሻሻል ሚና እንደሚጫወት ጥናቶቹ ያመለክታሉ። በተጨማሪም 25 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች ወደ ትውልድ ቀያቸው የመረጃ እና ምክር (በሕግ ነክ፣ የሕፃናት ትምህርት፣ የገበያ ዋጋ ግምት፣ የጤና አገልግሎት እና የቤት ቴክኖሎጂ ጉዳዮች) በማቀበል የዕውቀት ሽግግሩን ያግዛሉ።

በሌላ በኩል ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት የፖሊሲ ክትትል ካልተደረገበት ለነባሩ ነዋሪም ይሁን ለስደተኞቹ የማይመች የኑሮ ክበብን ሊፈጥር ይችላል። የሥራ አጥነት እንዲሁም የወሲብ ንግድ እና ልመና እንዲስፋፉ ብሎም ለሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ መንስኤ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ መንግሥት አሁን እንደሚታየው በቸልታ ሊመለከተው አይገባም።

ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰትን የሚመለከት ፖሊሲ እንዲቀረፅ የሚመክረው የUKAID ጥናት ሦስት ዐብይ መፍትሔዎችን ይጠቁማል፤ ስደተኞቹ በሚያርፉባቸው ከተሞች ሠርተው ከማደር የሚከለክሏቸውን እንቅፋቶች እንዲቀረፉ ማድረግ፣ ስደተኞቹ ሠርተው ከሚያተርፉት ገንዘብ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲልኩ ማበረታታት እና የስደተኞቹን መሠረታዊ መብቶች ማስከበር።

Page 10: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

9ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

የማታለል ተግባር ነው የሚል ተምሳሌታዊ ትርጉም ይሰጠናል። እንግዲህ ይህ ክስተት የድኅረ ዘመናዊነት አስተምህሮ ዓይነተኛ ማሳያ ነው። አንድን ክስተት (አባይ በጣና ላይ የማቋረጡን ተፈጥሮአዊ ክስተት) የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ እንደሚረዱት ይነግሩናል ግጥሞቹ።

የድኅረ-ዘመናዊነት አቀንቃኙ ፈረንሳዊው ታላቁ ፈላስፋ ማይክል ፎኮ “የአንድን ነገር ምንነት በሚያስማማ መንገድ ማወቅ አንችልም” በሚል መነሻ “በተለይም ታሪክን ያነሳን እንደሆን የታሪክ ምንጮች ሁሉ የተዛቡና ምሉዕ ያልሆኑ በመሆናቸው፤ ሁሉም የታሪክ አተረጓጎሞች ዕኩል እውነትነት ያላቸው ናቸው። በመሆኑም ስላለፈው ታሪክ ደምድመን ይህ ነው የምንለው ነገር አይኖርም (the past […] [is] unknow-able)” በማለት ታሪክ መቼም ልንስማማበት የማንችለው ጉዳይ እንደሆነና ታሪክ ለብዝኃ-ዕይታ (Multiperspective) የተጋለጠ መሆኑን አፅንኦት ይሰጣል።

ይህ ግንዛቤ በሒደት እያደገ መጥቶ ወደ ንድፈ-ሐሳብ ደረጃ አድጎ በአሁኑ ወቅት ‹Standpoint (የመቆሚያ ቦታ) ንድፈ-ሐሳብ›ን ወልዶ እናገኛዋለን። ‹የመቆሚያ ቦታ ንድፈ-ሐሳብ› ታሪክን ጨምሮ አንድ ሰው የአንድን ጉዳይ እውነታነት የምት (የሚ)ገነዘበው ራሷ/ሱ ከቆመ(ች)በት ሁኔታ አንፃር ነው የሚል ሲሆን፤ የብዙ እውነቶች መኖርን ከመነሻው የሚቀበል ንድፈ-ሐሳብም ነው።

‘የሰሜንና የደቡብ ወግ’ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት “ታሪክ በቀድሞ

ዘመንና ባሁኑ ዘመን መካከል እንዳለ ውይይት ይቆጠራል” ይላሉ ‹ተረትና ታሪክ በኢትዮጵያ› በሚል ርዕስ በጻፉት ጽሑፍ። “ታሪክ የሰው ልጅ ሕሊና ነው” የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በበኩላቸው “ታሪክ የሚጻፈው በዋናነት ለዛሬና ለነገ እንጅ ለትናንት ተብሎ አይደለም” ይላሉ። ታሪክ በአሁኑ ወቅት የብዙ ኢትዮጵያዊያን በተለይም የልኂቃኑ የየቀን መወዛገቢያና የዛሬ ችግሮቻችን ምንጭ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል። ለዚህም መነሻ እየሆነ ያለው በአንድ በኩል “የአውሮፓ ታሪክ የዓለም ታሪክ ተደርጎ እንደሚወሰደው ሁሉ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ታሪክ የመላ ኢትዮጵያ ታሪክ ተደርጎ እየተወሰደ

ሐተታ

ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም የታሪክ ምሁር ሲሆኑ፤ በ1999 የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የታሪክ መማሪያ መጽሐፍትን ‘ታሪክ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ትምህርት ስለሆነ…’ በሚል (ሌሎች መማሪያ መጽሐፍት ጨረታ ወጥቶ ነው የሚዘጋጁት) ከአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ ምሁራን መካከል እንዲከልሱ ከተመረጡ ጥቂት ግለሰቦች አንዱ ናቸው። ዶ/ር ቴዎድሮስ እርሳቸው የተማሩበትን የብሔርተኝነት ጉዳይ ለታሪክ መነሻ በማድረግ የዐሥረኛ እና የዐሥራ ሁለተኛ ክፍል የታሪክ ማስተማሪያ መጽሐፍትን የመጀመሪያ ምዕራፎች አዘጋጅተው ለትምህርት ሚኒስትር የታሪክ ትምህርት ክፍል ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ቢያስገቡም፤ የታሪክ መጽሐፍቱ ከሌሎች ትምህርቶች በተለየ መልኩ ላለፉት ዐሥራ ሁለት ዓመታት ተከልሰው ለተማሪዎች ሊሰራጩ አልቻሉም። ከዚህም አልፎ የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ማኅበርን ለማቋቋምና የታሪክ ትምህርትን በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ለሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ለመስጠት ቀርበው የነበሩ ሐሳቦች ከመንግሥት በኩል ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ሊሳኩ ያልቻሉ መሆናቸውን በቁጭት ይናገራሉ። ይህ ለምን እንደሆነ የሚያብራሩት “እኛ አገር ታሪክና ፖለቲካን መነጠል አልተቻለም” በማለት ነው።

መንገደ ብዙው ‹ድኅረ-ዘመናዊነት› ‹Postmodernism› የሚለው የእንግሊዝኛ

ቃል እስከአሁን ወደ አማርኛ በቅጡ የተመለሰበት ቦታ ማግኝት አልቻልኩም። እንዲሁ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ግን ‹ድኅረ-ዘመናዊነት› ብንለው ያን ያህልም የትርጉም መዛባት የሚያመጣ አይሆንም። የ‹ድኅረ-ዘመናዊነት› አስተምህሮ አሁን ባለው ዓለም ለታሪክ፣ ለጥበብ፣ ለሕንፃ

ሥራ… አዲስ ዓይነት አተረጓጐም በመስጠት ለብዙ ውዝግቦችና ጭቅጭቆች መነሻ ሆኖ ቀጥሏል። አስተምህሮው ባጭሩ “አንድ እውነት የለም፣ ብዙ አተረጓጎሞች እንጅ” (There […] [is] no truth, only interpretations) በሚል ሐሳብ ሊጠቀለል ይችላል።

ለዚህ ጥሩ ማሳያ ሆኖ ያገኘሁት የአባይ ወንዝ ከመነሻው በጣና ሐይቅ ላይ አቋርጦ ማለፉን አስመልክቶ በሕዝብ የተገጠሙ ሦስት የተለያዩ ግጥሞችን ነው። የመጀመሪያው ግጥም፦

“አባይ በጣና ላይ፥ መሄዱ ለምን ነው፣ትንሹ ሲያጠፋ፥ ትልቁ ሊችል ነው።”

የሚል ሲሆን፤ ይሄም “ትንሹ አባይ በትልቁ ጣና ላይ ማቋረጡ ተምሳሌታዊ (sym-bolic) ነው። ተምሳሌትነቱም ‹መቻቻል›ን ያመላክታል” የሚል ሐሳብ የያዘ ነው። ሁለተኛው ግጥም ደግሞ፦

“አባይ በጣና ላይ፥ ሄደ ተንጎማሎ፣ አንተም ውኃ እኮ ነህ፥ እኔም ውኃ ብሎ።”

“አያችሁት ጎበዝ፥ ይሄን ነገር መውደድ፣አባይ በጣና ላይ ይፈልጋል መንገድ።”

ይላል። ይሄም “የአባይ በጣና ላይ አቋርጦ ማለፍ ተምሳሌትነቱ ‹መናናቅ› ነው” የሚል ነው። በሦስተኝነት የምናገኘው የሕዝብ ግጥም ደግሞ፦

“አባይ በጣና ላይ፥ ምነው ቀለደበት፣ለአንድ ቀን ነው፥ ብሎ ዘላለም ሔደበት።”

የሚል ሲሆን፤ አባይ በጣና ላይ መሔዱ

ብዝኃ-ዕይታ የሚፈትነው ‘የኢትዮጵያ ታሪክ’

ታሪክ እና አተራረኩ በኢትዮጵያ ልኂቃን ዘንድ የጋለ ሙግት ከሚቀሰቅሱ ርዕሰ-ጉዳዮች ውስጥ ይመደባሉ። ከዚያም በላይ የፖለቲካ ዝማሜዎች መሠረታዊ መነሻም ነው። ዘላለም ክብረት፣ ርዕሰ-ጉዳዩን በመምዘዝ፣ ከጥናቶች እና ምሁራን አንደበት ታሪክ እና አተራረኩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ለገጠማት ፈተና መፍትሔ ይፈለግለት ዘንድ የሐተታ ውይይት ርዕስ አድርጎ አቅርቦታል።

ወደሚቀጥለው ገጽ

Page 11: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

10 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ስምንት መቶ ዓመታት) ወቅት በተፈጠሩ እንደ አኲሱማዊት ‹ንግሥተ ሳባ› ያሉና ከተረትነት ባለፈ በማስረጃ እንደማትረጋገጠው እንደ ‹ዮዲት ጉዲት› ያሉ የታሪክ ተዋንያንን በመፍጠር ያደፈ ነው” ለሚሉት ሐሳብ ማረጋገጫ ነው።

የድኅረ-ዘመናዊነት ሊቃውንቱ ግን ተረት ቀመስ ‘ታሪክንም’ ሆነ የታሪክ ሊቃውንቱን (professional historians) አጥብቀው ይኮንኗቸዋል። ለዚህም መነሻቸው “የታሪክ ሊቃውንት የሚባሉት አሰልቺና የግል ስሜታቸውን አንፀባራቂ ሲሆኑ፤ በዓላማቸውም የፈለጉትን ቡድን ለማሞገስ፣ የጠሉትን ደግሞ ለማጉደፍ […] እንዲሁም ታሪክ ሕንፃ ይመስል ታሪክን ለባለሙያዎች በሚል ፈሊጥ የታሪክ ሊቃውንት ያልሆነውን ሰፊውን ሕዝብ ከመድረኩ ዘወር ማድረግን የሚመርጡ ናቸው” የሚል እንደሆነ ሊቁ ሐይደን ዋይት ይገልጻሉ።

ከዚህም ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት

የኢትዮጵያን ታሪክ የተለያዩ ሥልጣኔዎች ታሪክ አንድ ላይ እየኖሩበት ያሉ አድርጎ ከሚያየው ጀምሮ፣ ኢትዮጵያን አንድና አንድ ብቻ አድርጎ እስከሚያው ድረስ ተንሰራፍቷል። የታሪክ ሊቃውንቱም ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ መጥቶ አሁን ሁሉም የየራሱን ግንዛቤ በታሪክነት የሚያስቀምጥበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

ለዶ/ር ቴዎድሮስ ግን አሁን አሁን ጎልተው መታየት የጀመሩት የኢትዮጵያን ታሪክ ‹ሰሜን - ደቡብ›፣ ‹ሙስሊም - ክርስቲያን›፣ ‹Center - Periphery› እያሉ መክፈል አጀማመራቸው ኮሚኒስታዊ መሠረት ካለው ከ’ያ ትውልድ’ እንደሆነ ገልጸው፣ አሁን ደግሞ እርሳቸው ‹የዘውግ ጸሐፊዎች› ብለው የሰየሟቸው የታሪክ ጸሐፊዎች መገለጫ እንደሆነና “ይሄም ሥር

ታሪክ በአሁኑ ወቅት የብዙ ኢትዮጵያዊያን በተለይም የልኂቃኑ የየቀን መወዛገቢያና የዛሬ ችግሮቻችን ምንጭ ተደርጎ እየተወሰደ

ይገኛል። ለዚህም መነሻ እየሆነ ያለው በአንድ በኩል “የአውሮፓ ታሪክ የዓለም ታሪክ ተደርጎ እንደሚወሰደው ሁሉ፤ የሰሜን

ኢትዮጵያ ታሪክ የመላ ኢትዮጵያ ታሪክ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል” የሚል መሠረት ያያዘ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ

“የኢትዮጵያን ታሪክ ‹የሰሜንና የደቡብ› ብሎ መክፈሉ ታሪካዊ መሠረት የሌለው በብሔርተኝነትና በዛሬ ፖለቲካዊ አቋም የተበየነ

ነው” የሚሉ ሆነው እናገኛቸዋለን

ሐተታ

ይገኛል” የሚል መሠረት ያያዘ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያን ታሪክ ‹የሰሜንና የደቡብ› ብሎ መክፈሉ ታሪካዊ መሠረት የሌለው በብሔርተኝነትና በዛሬ ፖለቲካዊ አቋም የተበየነ ነው” የሚሉ ሆነው እናገኛቸዋለን።

ፕሮፌሰር ተሻለ ጥበቡ ‘The Mak-

ing of Modern Ethiopia 1896 - 1974‘ ባሉት መጽሐፋቸው ‹ከደብረ ቢዘን ኤርትራ እስከ ደብረ ሊባኖስ ሸዋ› ያለውን የኢትዮጵያ ታሪክ ‹የግዕዝ ሥልጣኔ› በማለት የሚገልጹት ሲሆን፤ “እኔ በደንብ የማውቀው ይሄን ስለሆነ ስለዚህ ሥልጣኔ እጽፋለሁ” ብለው ትረካቸውን ይቀጥላሉ። ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በበኩላቸው “በ19ኛው መቶ ዓመት የነበረው የኢትዮጵያ ስዕል የተሟላ የሚሆነው በስተደቡብ ያገሪቱ ክፍል የነበሩት ሕዝቦችና ግዛቶች ታሪክም አብሮ ሲወሳ ነው” ይላሉ። ከዚህ ተነስተን ፕሮፌሰር ተሻለ የሰሜኑን ‹የግዕዝ ሥልጣኔ› እንዳሉት ‹ከሆራ ሸዋ እስከ ቱርካና ቦረና› ያለውን ‹የገዳ ሥልጣኔ› ብንለው ሁለቱንም በሚፈለገው ዐውድ ለመረዳት እንችላለን። ፕሮፌሰር ባሕሩ ይሄን ቅይጥ “በመቶ ዓመቱ ሁለተኛ አጋማሽ (1850 - 1900) አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያን የፈጠረው የደቡቡና የሰሜኑ ውሕደት ነበር” በማለት ይገልጹታል።

የታሪክ ሊቁ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት “የታሪክ ትንተናና ጽሑፍ ዘለዓለማዊ እውነት የለውም። አዳዲስና አስተማማኝ መረጃዎች ሲገኙ በነሱ መሠረት ይስተካከላል፤ ጨርሶም ሊለወጥ ይችላል። በታሪክ ያለቀለት፤ ፍፁም እውነት የሚባል ነገር የለም። ሁልጊዜ አንፃራዊ እውነት (relative truth) ነው። […] ታሪክ ከእምነት ጋራ የሚለይበት ዋና ባሕርዩ ይህ ነው። […] ዋናው ነገር ከዚህ የለውጥ ሕግ ውጭ ምንም ነገር እንደሌለ መገንዘቡ ይበጃል።” በማለት ሲገልጹ፤ ከድኅረ-ዘመናዊነቱ ‹እውነት ተለዋዋጭና ብዙ ነች› ከሚለው ሐሳብ ጋር ስምም ሆኖ እናገኛዋለን።

አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እንደ ብሔራዊ ታሪክ (Official History) የሚወስደውን የታሪክ አካሄድም ብናይ ከብዙ ጎን ትችት የሚያገኝው ሆኖ እናገኛዋለን። የኢትዮጵያ መንግሥት ‹የኢትዮጵያ ታሪክ› ሲል በመንግሥታዊው ቋት (Ethiopian Governmental Portal) እና በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ውስጥ የምናገኘውን የኢትዮጵያ ታሪክ ስንመለከት “የንግሥ[…][ተ] ሳባ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ በሚገኘው በአኲሱም አካባቢ ይገኛል። አኲሱም ውስጥ ከቤተ መንግሥቱ ሌላ፣ ሌሎች በርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ሲገኙ ከነዚህ ውስጥም ንጉሥ ሚኒ[…][ል]ክ ከእየሩሳሌም ይዞት የመጣው የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ቦታ አንዱ ነው” በማለት ጀምሮ ሲወርድ ሲወራረድ የመጡትን ተረቶችና ታሪኮች ቀይጦ የሚያቀርብ ሆኖ እናገኘዋለን።

ይሄም የታሪክ ሊቃውንቱ (profession-al historians) “የኢትዮጵያ ታሪክ በተለይም በጨለማው ዘመን (ከ500 - 1300 ባሉት

የማይዝ (marginal view) ከመሆን አልፎ ዋናውን (Main Stream) የታሪክ መሠረት የሚንድ አይሆንም” ባይ ናቸው።

ብዝኃ-ዕይታ ለምን?“በታሪክ ጉዳይ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ

አመለካከት ለምን ይኖራቸዋል?” የሚለው ጥያቄ እንዲሁ ሲታይ ቀላል ይመስላል እንጂ ወደተወሳሰቡ ገለጻዎች የሚወስድ ነው። የታሪክ ጸሐፊዎች የታሪክ አረዳድ ልዩነትና ውዝግቦች የሚፈጠሩበትን ምክንያቶች ሲያስረዱ የታሪክ ባለሙያዋች የግል አረዳድ፣ የአሁኑ ጊዜ ፖለቲካና ባሕል ትናንትን ስለሚጫን፣ የታሪክ ባለሙያዎች የታሪክ አጠናን ዘዴ አቀራረብ፣ የተለያዩ የድጋፍ ማስረጃዎች በተለያዩ ባለሙያዎች ጥቅም ላይ መዋላቸው፣ በቂ ያልሆኑና የሚጋጩ ማስረጃዎች መኖር እና

በታሪክ ባለሙያዎች የተጠየቁት ጥያቄዎች በማለት ዘለግ ያለ ማብራሪያ ይሰጣሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው ለታሪክ ውዝግቦች በአብዛኛው መነሻ የሚሆኑት ጉዳዮች ሦስት እንደሆኑ ይገልጻሉ። “የመጀመሪያው የታሪክ ምንጭ አጠቃቀም ልዩነት ነው” የሚሉ ሲሆን፤ “ሁለተኛው በቂ ዕውቀት ሳይኖር ታሪክን መጻፍ ነው” ሲሉ፤ ሦስተኛው ደግሞ “የፖለቲካ ተፅዕኖ ናቸው” ይላሉ።

አሜሪካዊው የታሪክ ሊቅ ዊሊያም አፒላን የታሪክ ከላሾች (Historical Revi-sionists) ላይ በሠሩት ጥናት “የታሪክ ከላሾች የምንላቸው ያለፈውን ታሪክ መሠረተ ግንዶች በአዲስ መንገድ የሚያዩና አዲስ የሕዝብ ግንኙነቶችን የሚፈጥሩ አካሄዶችን የሚከተሉ የታሪክ ባለሙያዎች ናቸው” ይላሉ። ከቅርብ

Page 12: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

11ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

አጻጻፍ ዘዴ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና ተከልሶ ሊጻፍ ይገባዋል” የሚል ሐሳብ ይሰነዝራሉ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አዲስ ዓይነት የኢትዮጵያ የታሪክ አጻጻፍ አሁን ብቅ ያለ እንዳልሆነ ይገልጻሉ። “እኔ ዩኒቨርስቲ የገባሁበት 1969 በአጋጣሚ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልልቅ ቦታ የሚሰጣቸው እንደ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና ዶክተር ሥርግው ገላው ዩኒቨርስቲውን የተቀላቀሉበት ወቅት ነበር” የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ “እነዚህ የታሪክ ሊቃውንት የኢትዮጵያ ታሪክ ከልማዳዊው ተረት ቀመስ አጻጻፍ ወጥቶ በአዲስ መልክ ሁሉንም የኢትዮጵያ ክፍል ባቀፈ መልኩ እንዲጻፍ ጥረት ማድረጋቸው እኔም በቀጣይ ላዳበርኩት የታሪክ አጻጻፍ ስልት አስተዋጽኦ አድርጎልኛል” ይላሉ።

ዶ/ር ነጋሶ ይሄን አዲስ አተያይ ተጠቅመው ከተለምዶው የኦሮሞ ሕዝብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ገብቷል የሚለውን ተረክ (narrative) በማስተባበል የኦሮሞ ሕዝብ ላለፉት አንድ ሺሕ ዓመታት (ነጋሶ ይሄ አተያ በቀዳሚነት የኔ ነው ይላሉ) እዚሁ መሐል ኢትዮጵያ የቆየ መሆኑን የሚያሳይ የመመረቂያ ጽሑፍ ለዶክትሬት ማሟያቸው የጻፉ ሲሆን (መመረቂያው በኋላ በመጽሐፍ መልክ ታትሟል)፤ ዶ/ር ነጋሶ በዚህ መመረቂያ ጽሑፋቸው ላይ “በዚህ ሥራዬ ሆን ብዬ በነገሥታት እና በዐፄዎቹ ላይ ከማተኮር ይልቅ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተረሱና የተጨቆኑ ሕዝቦች ታሪክ ላይ አተኩሬያለሁ” ይላሉ። ነጋሶ ለዚህ

ሐተታ

ጊዜያት ወዲህ “ችግራችን የታሪካችን በአግባቡ ያለመጻፍ ነው” በሚል ምክንያት የኢትዮጵያን ታሪክ በአዲስ አገባብ እየጻፉ ያሉ ጸሐፍት እየበዙ መጥተዋል። እነዚህ ጸሐፍትም ታሪክን በአዲስ መልክ ለመጻፍ ለምን እንዳስፈለጋቸው በመጽሐፍቶቻቸው ይገልጻሉ። ይህ የታሪክ ከላሾች መብዛት ደግሞ ታሪክን የምንረዳበት ብዝኃ-ዕይታ (Multiperspectivity) እንዲኖረን ዋነኛ መግፍኤ እንደሆነ ምሁራን ያስረዳሉ።

ከነዚህ ‹የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ከላሾች› ልንላቸው ከምንችላቸው ግለሰቦች መካከል አሕመዲን ጀበል የኢትዮጵያን ታሪክ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንፃር በመጻፍ ግንባር ቀደሙ ናቸው። አሕመዲን በቅርቡ ‹3ቱ ዐፄዎች እና ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች፡ ትግልና መስዋዕትነት› በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው፦

“የግለሰቦቹ አዎንታዊና አሉታዊ ታሪክ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሚዛናዊ ሆኖ ባለመቅረቡ ለባለ ታሪኮቹ የተደበላለቀ ስሜት እንዲኖር በማድረግ በማኅበረሰቡ መካከል የልዩነት ምክንያት ሆኗል። የታሪክ ጸሐፍት ሊያሳዩን ከፈለጉት አንፃር አንደኛው የግለሰቦቹን ጀግንነት፣ የአገር ባለውለታነት እና ገድላቸውን ብቻ ሲያቀርብ ሌላኛው ደግሞ የተደበቀውን እና አሉታዊ ታሪካቸውን በማሳየት ስለጨቋኝነታቸው ሊጽፍ ይችላል። ሚዛናዊና ሁለቱንም ገጽታ ያስታረቀ ጽሑፍ በሌለበት የአንዱን ወገን ብቻ ያነበበ ሰው ስለ ግለሰቦቹ ከፊል ገጽታ ብቻ ይረዳል።” በማለት የዘመናዊት ኢትዮጵያ መሠረት ተደርገው የሚወሰዱትን ሦስት ነገሥታት ለሙስሊሙ የነበራቸውን አተያይ ከተለመደው ተረክ (Mainstream Nar-rative) በተለየ መልኩ ያቀርቡታል።

እንደ አሕመዲን ሁሉ የታሪክ ጸሐፊው ታቦር ዋሚም ‹የቅርብ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ከላሾች› ልንላቸው ከምንችላቸው ግለሰቦች መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በቅርቡ ‹የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች› በሚል ርዕስ የኦሮሞን ሕዝብ ማዕከል በማድረግ በጻፉት መጽሐፋቸው፦

“በኢትዮጵያ ታሪክ ሥም ሲቀነባበሩ የቆዩትና ዛሬም የሚቀርቡ ግሪኮ ሮማዊያኑ መነኮሳት ያቀነባበሯቸው የታሪከ ነገሥት፣ የክብረ ነገሥት፣ የፍትሐ ነገሥት ወዘተ ተረቶችና ከዐፄ ይኲኖ አምላክ ዘመን (1270 - 1285) በኋላ፣ በተለይም ከዐፄ አምደፅዮን ዘመን ጀምሮ የተጻፉት ታሪከ ነገሥትን መሠረት ያደረጉ፣ ከብሉይና ከሐዲስ ኪዳን ንግርቶች ጋር የተዛመዱ በነገሥታቱ የየግል ስሜት እርካታ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የነገሥታት ገድሎች ናቸው። አብዛኛዎቹ የውጭ አገር ጸሐፊዎችም እነዚህኑ ሰነዶች ወስደው በመተርጎም ወይም የራሳቸው የጥናት ውጤት አድርገው በማቅረብ የተረት ታሪክ ሲያቀርቡና ሲሸለሙበት ቆይተዋል። ከዚህም የተነሣ እስከዛሬ ድረስ እራሱን ችሎና ትኩረት አግኝቶ በስርዓት የተጠና የሕዝቦች ታሪክ በአገራችን አለ ለማለት አያስደፍርም።”

በማለት “ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የታሪክ

መነሻ የሆናቸው የሰፊው ሕዝብ ታሪክ ሲጻፍ አለማየታቸው እንደሆነ ይገልጻሉ።

የአውሮፓ ኅብረት አውሮፓ ካላት ሰፊና የተወሳሰበ ታሪክና የማንነት ስብጥር አንፃር የብዝኃ-ዕይታን የታሪክ አረዳድ እንደ መሪ ታሪክ ማስተማሪያ ዘዴ የአባል አገራቱ ይጠቀሙበት ዘንድ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የታሪክ ማስተማሪያ መመሪያዎችን (guide) በዚሁ የአረዳድ አግባብ ማዘጋጀት ጀምሯል። ይሄን የኅብረቱን መንገድ ያዩ የታሪክ ምሁራንም እርምጃውን ተግባቦትን የሚጨምር እንደሆነ ይገልጻሉ። “ከአውሮፓ የማይተናነስ የታሪክ እሰጣገባና ውዝግብ ያለባት ኢትዮጵያ ይሄን አዲስ ጎዳና ብትሔድበትስ?” ብሎ መጠየቅ እዚህ ላይ ተገቢ ይመስላል። ነገር ግን “የኢትዮጵያ ታሪክ አሁንም የፖለቲካው እስረኛ ነው” የሚለው የምሁራኑ አስተያየት ወደፊት እንዳንራመድ ያደርገናል።

ደብዛዛው ነገዶ/ር ቴዎድሮስ አሁን አሁን ብቅ እያሉ

ካሉት የታሪክ አጻጻፎች ባለፈ በአንዳንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የታሪክ መጽሐፍትን ለማቃጠል እስከ መጋበዝ ድረስ እንደተደረሰ ታዝበዋል። አሜሪካዊው ፍራንሲስ ፊዝጀራልድ የትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍትን አስመልክተው በጻፉት መጽሐፍ “በትምህርት ቤት ለተማሪዎች የሚሰጡ የታሪክ መጽሐፍት ዓላማቸው ተማሪዎችን አባቶቻችሁ ስለአገራችሁ ማወቅ አለባችሁ ብለው ያሰቡትን በመንገር መምራት እንጅ እውነትን ማሰስ አይደለም።” ይላሉ። በተጨማሪም ዶ/ር ቴዎድሮስ አሁን ባለንበት ሁኔታ የእኛ አገር ዓይነት የታሪክ ትምህርት በፖለቲካ ተበርዞ መደፍረስ ይታይበታል ባይ ናቸው። በዚህም ምክንያት እርሳቸው የተሳተፉበት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የታሪክ መጽሐፍት ተከልሰው መቼ ለተማሪዎች እንደሚሰጡም እርግጠኛ አይደሉም። ነገር ግን እንደመፍትሔ ብለው የምንግባባቸውን ታሪኮች ማጉላት የማንግባባቸውን ደግሞ አንዱ ያንዱን እውነታ በሚረዳበት መልኩ (Mutually Intelligible) ማሳለፍን ያቀርባሉ። ዶ/ር ነጋሶ በበኩላቸው ከነዚህ መፍትሔዎች ባለፈ ዕውቀትን መሠረት ያደረጉ የታሪክ አረዳዶችን ማጎልበትን እንደ መፍትሔ ይጨምራሉ።

አሁን አሁን “ታሪክ ምን ያደርጋል?” የሚለውን ጨምሮ “ታሪካችንን ብንተወው ይሻላል” የሚሉ ሐሳቦች እዚህም እዚያም ሲቀርቡ ይሰማል። ይህ ግን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ፣ በቅጡ ያልታሰበበት እና ዛሬ የትናንት ውላጅ መሆኑን የሚዘነጋ ሐሳብ ነው። የኖቤል ሎሬቱ ዊሊያም ፎልክነር ‘Requiem for Run’ በተባለው ሥራው ጋቪን ስቲቨንስ የተባለውን ጠበቃ ገፀ ባሕርይ “The past is never dead. It’s not even past” ሲል ያናግረዋል። የዛሬዋን ኢትዮጵያ የተመለከተ ሰው የፎልክነርን ነቢይነት አይቶ መገረሙ አይቀርም።

ዶ/ር ነጋሶ በዚህ መመረቂያ ጽሑፋቸው ላይ “በዚህ

ሥራዬ ሆን ብዬ በነገሥታት እና በዐፄዎቹ ላይ ከማተኮር

ይልቅ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተረሱና የተጨቆኑ ሕዝቦች ታሪክ

ላይ አተኩሬያለሁ” ይላሉ። ነጋሶ ለዚህ መነሻ የሆናቸው የሰፊው ሕዝብ ታሪክ ሲጻፍ

አለማየታቸው እንደሆነ ይገልጻሉ

Page 13: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

12 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ሕግ ፍትሕ አስተዳደር

አቶ ሞላ ዘገየ ባለፉት ሦስት የውይይት መጽሔት ተከታታይ እትሞች የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን፣ ለምን ሪፎርም እንደሚያስፈልግ እና ሒደቱ እንዴትና በማን ሊመራ እንደሚገባው የተለያዩ አገሮችን ተመክሮ ጠቅሰው ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል። መሠረታዊና ሁላችንም ልንወያይበት የሚገባው ርዕሰ ጉዳይ ይመስለኛል። በዚህች አጭር ጽሑፌ የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ እንዴት ከዴሞክራሲ ሽግግር እና የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን የፖለቲካ ልማት ከሚሉት ወሳኝ ፅንሰ ሐሳብ ጋር እንደሚያያዝ፣ በተለይ የምርጫ ስርዓት ሪፎርምን ጠቅሼ የተወሰኑ ሐሳቦችን ለመሰንዘር እሞክራለሁ። አቶ ሞላ የአገራችን የፖለቲካ ድርጅቶችን ሁኔታ ከተነተኑበት ነጥብ ጋር ብስማማም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያላማከለ ለውጥ ውጤታማ ይሆናል የሚል እምነት እንደሌለኝ ግን ከወዲሁ መግለጽ ይኖርብኛል።

የምርጫ ስርዓት እና የዴሞክራሲ ሽግግር

አቶ ሞላ በመጨረሻው ጽሑፋቸው የሜክሲኮ የሕገ መንግሥት ሪፎርም፣ በተለይ ደግሞ የምርጫ ስርዓቱ መሻሻሉ ለዚያች አገር የዴሞክራሲ ሽግግር ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ ጠቅሰዋል። እስማማለሁ። በሚክሲኮ የዴሞክራሲ ሽግግር ላይ የጻፉ እንደ ባርብራ ጌዲስ (Barbara Geddes -1994) እና ቢያትሪስ ማጋሎኒ (Beatriz Magaloni - 2006) ያሉ ምሁራንም በዚህ ላይ በሰፊው ጽፈውበታል። ያችን አገር ለበርካታ ዐሥርት ዓመታት ሲገዛ የቆየው የሜክሲኮ አብዮታዊ ፓርቲ (PRI) ከረዥም ጊዜ በኋላ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተሸንፎና ለሕዝብ ድምፅ ተገዥ ሆኖ ሥልጣኑን ለተመረጠው

የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ እና የዴሞክራሲ ሽግግር

ኃይል ማስረከብ የቻለው፣ ሪፎርም ስለተደረገ እና በሪፎርሙ ሒደት በፖለቲከኞች በራሳቸውና በፖለቲከኞችና በሕዝቡ መካከል መቀራረብ፣ መግባባትና መተማመን በመፈጠሩ ነው። ፓርቲው በወሰደው ገንቢ እርምጃ ምክንያት፣ የድርጅቱ መሪዎች እንደገና ራሳቸውን አደራጅተውና በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸናፊ ሆነው አገሪቱን በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ። ይህ ትልቅ አርኣያነት ያለው ሒደት በመሆኑ፣ አቶ ሞላ እንዳሉት ከሜክሲኮ ፖለቲከኞችና ከዚያች አገር የፖለቲካ ሽግግር መማር ብልህነት ነው።

ወደአገራችን የዴሞክራሲ ሽግግር ሒደት ስንመለስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 31 ስለመደረጃት መብት እና አንቀጽ 79 ስለፍርድ ቤቶች ነጻነት ይናገራሉ።

የምርጫ አስፈፃሚ የሆነው የምርጫ ቦርድም በዐዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ምርጫዎችን ሲመራ ቆይቷል። ይህ ቢያንስ በቅርጽ ደረጃ ለመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ የሚሆኑ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል ማለት ነው። ይሁን እንጂ አቶ ሞላ ደጋግመው እንደጠቀሱት፣ በአንድ በኩል የወጡትን ሕጎች በሥራ ላይ የማዋል ከፍተኛ ችግር የሚስተዋል ከመሆኑም በላይ፣ የሕጎች ፍትሓዊነትና የተቋማቱ ገለልተኛነትም ትልቅ ችግር ያለበት ነው። በፍርድ ቤቶችና በምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት ላይ ጥያቄ የሚነሳውን ያህል፣ የምርጫ ስርዓቱ የዴሞክራሲ ሽግግር እንቅፋት ስለመሆኑም ተደጋግሞ ይነሳል።

የምርጫ ስርዓቱን ነጥለን ብንመለከት፣ በእኔ አስተያየት በአገራችን የተቃዋሚ ፓርቲዎች አለመቀናጀት ወይም አለመተባበር፣ የፋይናንስ ችግር፣ ሐሳባቸውን የሚልጹበት መገናኛ ብዙኃን አለመኖር ወዘተ. እንዳለ ሆኖ፣ ዋናው እንቅፋት የምርጫ ስርዓቱ መሆኑ የሚያከራክር አይመስለኝም። እንደሚታወቀው የእኛ አገር ሕገ መንግሥት ከሌሎች አገሮች ከሚለይባቸው ነገሮች አንዱ የምርጫ ስርዓቱን መደንገጉ ነው። በሌሎች አገራት የምርጫ ስርዓት ብዙ ጊዜ በተራ ዝርዝር ሕጎች ነው የሚወሰነው። ምክንያቱም ልክ እንደ መሬት ፖሊሲ ከመንግሥት መንግሥት መለያየት የሚችል ጉዳይ ነው እንጂ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ አይደለም። የሆነ ሆኖ በእኔ አስተያየት ዋናው ችግር፣ የምርጫ ስርዓቱ በሕገ መንግሥት ደረጃ መደንገጉ ወይም አለመደንገጉ ሳይሆን፣ ይህን የምርጫ ስርዓት ይፈልግ አይፈልግ እንደሆነ ሕዝቡ አለመጠየቁና በነጻነት ሐሳቡን አለመስጠቱ ነው።

ብዙዎች በዚህ የአብላጫ ድምፅ የምርጫ ስርዓት ንዑስ ክፍል በሆነው ከፍተኛ ድምፅ የምርጫ ስርዓት አስቸጋሪነት ይስማማሉ። ይህ የምርጫ ስርዓት ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ሥልጣኑን በቀጣይነትና በቋሚነት እንዲይዝ ዕድሎችንና ሁኔታዎችን የሚያመቻች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲቀጭጩ የሚያደርግ የምርጫ ስርዓት በመሆኑ፣ ተመራጭነቱ እየተመናመነና በብዙ አገሮች እየጠፋ የመጣ የምርጫ ስርዓት በመሆኑ፣ ‘ዳይኖሰር’ የሚል ቅጽል ሥም እስከማትረፍ የደረሰ የምርጫ ስርዓት ነው። ስለዚሁ የምርጫ ስርዓት አስቸጋሪነት ‹ሕገ መንግሥት ምርጫና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ከትናንት ወዲያ እስከ

አቶ ሞላ ዘገዬ በዚሁ አምድ ላይ ባለፉት ሦስት ተከታታይ እትሞች “የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ ወቅታዊነት” በሚል ርዕስ ለዘላቂ ሠላም እና ሕገ መንግሥታዊነት የሚበጅ ያሉትን ምክረ ሐሳባቸውን ሲያካፍሉን ነበር። ኢዮብ ሲሳይ በአቶ ሞላ ሐሳብ ላይ የጎደለ የመሰላቸውን ማጠናከሪያ ሐሳብ እንደሚከተለው አስፍረውታል።

የእኛ አገር ሕገ መንግሥት ከሌሎች

አገሮች ከሚለይባቸው ነገሮች አንዱ የምርጫ

ስርዓቱን መደንገጉ ነው። በሌሎች አገራት የምርጫ

ስርዓት ብዙ ጊዜ በተራ ዝርዝር ሕጎች ነው

የሚወሰነው

Page 14: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

13ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ስርዓት ባልዳበረባቸው፣ በተለይ በአፍሪካ አገሮች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አለመተማመን አለ። ጠንካራና ገለልተኛ አገራዊ ተቋማት ስለማይገነቡ፣ በሥልጣን ላይ ያሉት አካላት ሥልጣናቸውን ቢለቁ በሠላም የሚኖሩበት ዕድል ስለመኖሩ ጨርሶ እርግጠኞች አይደሉም። በዚህ ምክንያት እስከሚችሉበት ጊዜ ድረስ፣ በኢኮኖሚያዊ ልማት እያሳበቡ፣ ግፋ ሲልም ኃይል እየተጠቀሙ ለመኖር ይሞክራሉ። ወደ ሥልጣን መውጫውም ሆነ ከሥልጣን መገለያው አመፅ በመሆኑ፣ በአመፅ ከሥልጣናቸው በሚወገዱበት ጊዜ መኖሪያቸው ስደት ወይም ወኅኒ ቤት ይሆናል። አገራችን ጨምሮ በአፍሪካ በአጠቃላይ የታየና አሁንም በስፋት የሚታይ ትልቅ ችግር ነው። ሕዝብ

የመከረበት ሕገ መንግሥት እና ጠንካራና ገለልተኛ አገራዊ ተቋማት ስለሌሉ የቱንም ያህል የኢኮኖሚያዊ ልማት ቢመጣ፣ የቱንም ያህል አስደናቂ የመሠረተ ልማት ግንባታ ቢካሔድ ከአደጋ አያመልጥም። የገንብቶ ማፍረስና አፍርሶ መገንባት አዙሪት የሚባለወም ይኸው ይመስለኛል።

ኢትዮጵያ ከዚህ አዙሪት እንድትገላገል ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። አቶ ሞላ እንዳሉት፣ በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና መንግሥታቸው በታሪክ ሊጠቀስ የሚችል አርኣያነት ያለው ተግባር የመፈፀም ዕድል አላቸው። “የዴሞክራሲ ተቋማት እየተገነቡ ነው፤ ለጋ ቢሆንም እያደገ ያለ ዴሞክራሲ አለን” ወዘተ. የሚለውን ዘወትር የሚሰማውን ምንም የማያሳምን አስተያየት ወደጎን ብሎ፣ ለአገርና ለሕዝብ ሲባል እውነታውን መጋፈጥ ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምና ጓዶቻቸው ሕዝብ የሚቀበለው ሕገ መንግሥት እንዲኖረን በሩን ከከፈቱና ገለልተኛ ተቋማት የሚገነቡበትን መንገድ ከጠረጉ፣ ትውልድ የሚዘክረው ‘ሌጋሲ’ እንደሚኖራቸው የሚያጠራጥር አይመስለኝም። የመንግሥት መሪዎች በምሳሌነት የሚጠቅሷቸው እነ ደቡብ ኮሪያና ታይዋንም ቢሆኑ ያደረጉት ይህንኑ ነው።

ሕግ ፍትሕ አስተዳደር

ነገ› በተሰኘው መጽሐፋቸው በዝርዝር የጻፉት ዶ/ር ነገደ ጎበዜ የምርጫ ስርዓቱ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 54/2 መሠረት ሕገ መንግሥታዊ በመሆኑና ሕገ መንግሥቱን የማሻሻሉ ጉዳይ ደግሞ በራሱ በሰነዱ ምክንያት እጅግ ውስብስብ ስለሆነ “…ስርዓቱን አስመልክቶ ያለው አማራጭ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ለቀቅ አድርጎ የቤት ሥራ ላይ ማተኮርና በአንድነት ቢቀርቡ ‘ማጆሪቲ’ የሚሆኑትን ተቃዋሚዎች ተበታትነው በመወዳደር ‘ማይኖሪቲ’ እየተባሉ በያሉበት ቀልጠው እንዳይቀሩ በአንድ በጋራ ፕሮግራም ዙሪያ በሕዝብ ፊት በጋራ መቅረብ ግዴታ የሚሆነው” ይላሉ።

ዓለማቀፍ የዴሞክራሲና የምርጫ ተቋም (IDEA) እንዳስቀመጠውም ከዚሁ የምርጫ ስርዓት ወደ ሌሎች በተለይ ወደ ቅይጥ የምርጫ ስርዓት የሚቀየሩ አገራት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ብዙዎቹ አገሮች ብሔራዊ እና አካባቢያዊ (የወረዳ ወዘተ.) ምርጫዎችን ለማካሔድ የተለያዩ ወይም ቅይጥ የምርጫ ስርዓቶችን ይጠቀማሉ። በአገራችንም የዴሞክራሲ ሽግግር እንዲመጣ ከምር የምንፈልግ ከሆነ፣ ከዚህ ከዚህ ዳይኖሰር የምርጫ ስርዓት መላቀቅ ይኖርብን ይመስለኛል። ለዚህም ግን አቶ ሞላ ደግመው ደጋግመው እንዳሳሰቡት ሕዝቡ እንዲጠየቅና በነጻነት እንዲወስንበት ያስፈልጋል።

የሕገ መንግሥት ሪፎርምና የፖለቲካ ልማት

ታዋቂው የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ ‹Political Order and Political Decay› በሚለው መጽሐፉ (2015፣ 23) የፖለቲካ ልማት፣ የፖለቲካ ተቋማት በጊዜ ሒደት የሚያሳዩትን ለውጥ (መሻሻል) እንደሚመለከት ይነግረናል። እንደ ፉኩያማ ገለጻ ዓላማውን ለማስፈፀም ኃይል የሚጠቀም፣ ኃይሉ በሕግ የተገደበና ተጠያቂነት ያለው አገረ-መንግሥት እንዲኖር ያስፈልጋል።

የዴሞክራሲ ችግር ባለባቸው አገሮች ያለው ዋናው አደጋ የመንግሥት ኃይል በሕግ አለመገደቡና ተጠያቂነት አለመስፈኑ ነው። ነጣጥለን እንያቸው። እንደሚታወቀው ሕገ መንግሥት በሥልጣን ላይ ያሉ አካላት ወይም ሌሎች [ጉልበት ያላቸው] ኃይለኞች፣ እንደፈለጉ እንዳይፈነጩ እና ሕዝብና አገር እንዳያምሱ ልጓም ለማበጀት የሚያገለግል መሣሪያ ቢሆንም፣ ዴሞክራሲያዊ ባልሆኑ አገሮች ከዚህ በተቃራኒው ሕገ መንግሥትም ይሁን ሌሎች ሕጎች የሚወጡት የኃይለኞችን ወይም የገዥዎችን ሥልጣን ለማስጠበቅ ነው። የሕግ የበላይነትና በሕግ መግዛት የተለያዩ ናቸው፤ በዴሞክራሲያዊ አገሮች ውስጥ ያለው የሕግ የበላይነት ሲሆን፣ ዴሞክራሲያዊ ባልሆኑት ውስጥ በአንፃሩ በሕግ መግዛት ማዕከላዊ ቦታ ይዞ ይገኛል። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዴሞክራሲያዊ በሆኑ አገሮች ውስጥ መንግሥትና የመንግሥት አካላት ለሚሠሩት

ማንኛውም ተግባር ተጠያቂነት አለባቸው፤ ይህ በማያሻማ መልኩ ሥራ ላይ ይውላል።

እነዚህን ነጥቦች ለመነሻ ያህል የጠቀስናቸው፣ የፖለቲካ ልማት እንዲመጣ የዴሞክራሲ ተቋማትን መገንባትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ፣ እነዚህ የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡና እንዲጠናከሩ ደግሞ ሕዝብ የወሳኝነት ሚና ሊኖረው እንደሚገባ ለመግለጽ ነው። በአገራችን እነዚህ ሁሉ ችግሮች በግልጽ የሚታዩ ናቸው። አቶ ሞላ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ነጻነቱ ተከብሮለት፣ ሳይፈራና ሳይሸማቀቅ መክሮ ዘክሮ ያፀደቀው ሕገ መንግሥት አግኝቶ አያውቅም። የሁሉም ነገር መቋጠሪያ ይህ በመሆኑ ደግሞ፣ የዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥትን

ፈተናችንን ሳንሻገር ወደ የትም መንቀሳቀስ አይቻለንም። ዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥት የሌሎች ዴሞክራሲያዊና በሕዝብ ተቀባይነት ያገኙ አገራዊ ተቋማት መሠረት በመሆኑ፣ ዛሬም ነገም ስለዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥት አስፈላጊነት እንድንወያይ፣ እንድንከራከርና መላ እንድንመታ ይስፈልጋል።

ሕዝብ በሕገ መንግሥቱና በአገራዊ ተቋማት ላይ መተማመን የሚኖረውና እነዚህን ተቋማት ተንከባክቦ ሊጠብቃቸው የሚችለው፣ ተቋማቱ እንከን የለሽ ሆነው ስለሚዘጋጁ ሳይሆን ስለመከረባቸውና ስለወሰነባቸው ነው። የሕገ መንግሥት ወይም የተቋማት እንከን የለሽነት በራሱ ትርጉም የለውም። ለዚህ ነው በሕገ መንግሥት ሪፎርም ሒደት ሕዝቡ የወሳኝነት ሚና እንዲጫወት ከተደረገ፣ በአንድ በኩል ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርገው የሚገነቡት አገራዊ ተቋማት ሕዝባዊ ተቀባይነት ያገኛሉ፤ በሌላ በኩል በሒደቱ በፖለቲከኞች መካከል ብቻ ሳይሆን በፖለቲከኞችና በሕዝቡ መካከል ውይይት፣ መቀራረብና መተማመን ይፈጠራል፤ ይህ ደግሞ በሥልጣን ላይ ያሉ አካላት እንደሜክሲኮ ፖለቲከኞች በምርጫ ቢሸነፉ፣ ሕገ መንግሥቱና ገለልተኛ የሆኑት አገራዊ ተቋማት እንደሚጠብቋቸው ስለሚገነዘቡ ከሥልጣናቸው ወርደው ሠላማዊ ሕይወት የሚመሩበትን ዕድል ይፈጥራል፤ አዲስ የዴሞክራሲ ሽግግር ምዕራፍ ይከፍታል የሚባለው።

እንደሚታወቀው በብዙዎቹ ዴሞክራሲያዊ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምና ጓዶቻቸው ሕዝብ የሚቀበለው ሕገ መንግሥት እንዲኖረን በሩን ከከፈቱና

ገለልተኛ ተቋማት የሚገነቡበትን መንገድ ከጠረጉ፣ ትውልድ የሚዘክረው ‘ሌጋሲ’ እንደሚኖራቸው

የሚያጠራጥር አይመስለኝም

ኢዮብ ሲሳይ የፖለቲካል ሳይንስ፣ የፒ.ኤች.ዲ. ተማሪ ናቸው፤ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected]

ሊገኙ ይችላሉ።

Page 15: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

14 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ሕግ ፍትሕ አስተዳደር

“በኛ ዘመንም ሆነ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ለሕግ እድገት ወሳኙ ነገር የሕግ ማውጣት፣ የሕግ ሳይንስ ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይሆን እራሱ ማኅበረሰቡ ነው” ~ ኢዩጀን ኸርሊች

ሕግ ከአንድ ማኅበረሰብ አስተሳሰብ፣ ባሕል፣ ማኅበራዊ ተቋማትና እሴቶች ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ከመኾኑ አንፃር ለተደነገገላቸው ሕዝቦች በልዩ ሁኔታ ከሚያገለግል በስተቀር የአንዱ አገር ሕግ ለሌላው አገር የማገልገል ዕድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ ሞንተስኪዩ “the spirit of the law” በሚለው መጽሐፉ ላይ አጥብቆ ይሞግታል። ነገር ግን የዓለም ታሪክ እንደሚያሳየው በተለያየ ጊዜና አጋጣሚ አገሮችና ሥልጣኔዎች ሕግንና የሕግ ተቋማትን ከሌሎች ወስደው ተግባር ላይ ሲያውሉ ይስተዋላል። የሩቁን ትተን ባለፉት ሁለት መቶ ዓመታት የነበረውን ሁኔታ እንኳን ብንመለከት ሦስት ዋና ዋና የሕግ ንቅለ-ተከላ (legal transplantations) መፈፀማቸውን በጉዳዩ ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ። በቅኝ ግዛት ወቅት በተለይም ፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ግዛቶቻቸው በሆኑት የአፍሪካ፣ ኤሽያና ላቲን አሜሪካ አገሮች ላይ ሕጎቻቸውን በኃይል የጫኑበት ሁኔታ አንዱ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ ከቅኝ ግዛት የተላቀቁ አገሮች በድጋሚ ገዢዎቻቸውን ጨምሮ ከአሜሪካና ሶቬዬት ኅብረት ሕጎቻቸውን የወሰዱበት አጋጣሚ ነው። ሦስተኛው ደግሞ በ1980ዎቹ የሶቬት የሶሻሊዝም ስርዓትን መፍረስ ተከትሎ የመካከለኛውና ምሥራቅ አውሮፓ፤ እንዲሁም ሌሎች ከሶሻሊስት ስርዓት ራሳቸውን ያላቀቁ አገሮች የሕግ ስርዓታቸውን በአዲስ መልክ ሲያዋቅሩ ሕጎችን ከምዕራብ አውሮፓና ከአሜሪካ የወሰዱበትን ሒደት የሚመለከት ነው።

አገራዊ እሴት አልባ የሕግ ንቅለ-ተከላዎች እና ፍትሕ ሕጎች የአገራዊ እሴቶችን ከግምት ውስጥ አስገብተው ካልተቀረፁ ለተፈፃሚነት ያስቸግራሉ በሚል የሚከራከረው ተሾመ ተስፋዬ ‹የኢትዮጵያ ሕጎች እና ሕገ መንግሥቶች አገራዊ እሴቶችን አቅፈዋልን? ካልሆነስ፣ ማቀፍ ይቻላቸው ይሆን?› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሕግ ተከላ እና ንቅለ-ተከላ ታሪካችንን ዳስሷል።

ሕግ በባሕሪው ከማኅበረሰብ ታሪክ፣ ርዕዮተዓለም፣ ሃማይማኖት፣ ባሕል፣ ማኅበራዊ ተቋማትና እሴቶች ጋር በፅኑ

የተቆራኘ በመሆኑ የአንድን አገር ሕግ ለሌላው አያገለግልም ከሚለው አንስቶ፤ ሕግ ራሱን ችሎ ሊቆም የሚችልና

የማኅበረሰብ መለወጫ መሣሪያ ስለሆነ የአንድ አገር ሕግ በሌላ አገር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፣ እስከሚለው ድረስ ፅንፍ

የረገጡ ክርክሮች ሲደረጉ ቆይተዋል

በአሁኑ ወቅትም ከሉላዊነት (globalization) ተፅዕኖ የተነሳ አገሮች ከሌላ አገር ብቻ ሳይሆን ከዓለምዐቀፍ ተቋማት ጭምር ሕግ በመገልበጥ የሕግ ስርዓታቸው አካል የማድረግ ሁኔታ ውስጥ በስፋት እንደሚሳታፉ ይታወቃል። ነገር ግን ሕግን

ከሌላ አገር በከፊልም ሆነ በሙሉ ገልብጦ የመውሰድ አስፈላጊነት እስከ አሁንም ድረስ ሲያከራክር ይገኛል። ሕግ በባሕሪው ከማኅበረሰብ ታሪክ፣ ርዕዮተዓለም፣ ሃማይማኖት፣ ባሕል፣ ማኅበራዊ ተቋማትና እሴቶች ጋር በፅኑ የተቆራኘ በመሆኑ የአንድን አገር ሕግ ለሌላው አያገለግልም ከሚለው አንስቶ፤ ሕግ ራሱን ችሎ ሊቆም የሚችልና የማኅበረሰብ መለወጫ መሣሪያ ስለሆነ የአንድ አገር ሕግ በሌላ አገር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፣ እስከሚለው ድረስ ፅንፍ የረገጡ ክርክሮች ሲደረጉ ቆይተዋል። ጉዳዩን ለማሳጠር ያህል በቅርቡ “The Transplant Effect” በሚል ርዕስ ባለፉት

ሁለት መቶ ዓመታት በተለያዩ 49 አገሮች ተሞክሮ ላይ ተመሥርቶ በሦስት የዘርፉ ባለሙያዎች በተደረገውና በሌሎችም ጥናቶች እንደተረጋገጠው የሕግ ንቅለ-ተከላ በአገሮች ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ፣ የወሳጁን አገርና ሕዝቦች ነባራዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ከሆነ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለመረዳት ይቻላል። በሌላ በኩል ሒደቱ በጥንቃቄ ከተከናወነና በተለይም ከዘመናዊ ሥልጣኔ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሕግ ስርዓትን ፈጥሮ ማዳበር ከሚወስደው ረጅም ጊዜ አንፃር ሲታይ ተዋሹን አገር ከሌላ አገር ልምድ እንዲወስድና በአጭር ጊዜ የሕግ ባለቤት አንዲሆን የሚያስችለው በመሆኑ ጠቀሜታ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ። ይህ በዓለምዐቀፍ ደረጃ ያለውን አጠቃላይ ስዕል የሚያሳይ ሲሆን

የዚህ ጽሑፍ ዓላማም በአገራችን የተፈፀሙ የሕግ ንቅለ-ተከላዎች በአገር በቀል እሴቶች ላይ ያስከተሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ በአጭሩ በማስቃኘት ውይይት መጫር ነው።

በኩር የሕግ ተከላበዘመናዊው የኢትዮጵያ የሕግ ታሪክ

ለመጀመሪያ ግዜ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ንቅለ-ተከላ የተከወነው በዐፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ነው። ከዚያ በፊት በነበረው ዘመን በአገሪቱ እንደ ፍትሓ-ነገሥት፣ ክብረ-ነገሥት፣ በ1930 የወጣው የወንጀል ሕግ ካሉት የተጻፉ ሕጎች

Page 16: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

15ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ወደ ሕዝቡ የዕለት ተዕለት ሕይወት ገብቶ የታቀደውን ተጨባጭ ለውጥ ሳይመጣ ስርዓቱ በደርግ ተተክቷል።

የደርግ ስርዓትም በወቅቱ በነበረው አገርዐቀፍና ዓለምዐቀፍ የፖለቲካ ትኩሳት በመገፋት የሶሻሊስት ርዕዮተዓለምን የስርዓቱ ማራመጃ መሣርያ አድርጎ ወስዷል። በዚህም የተነሳ በርካታ ሕጎችን ከሶሻሊስት አገሮች በመገልበጥ ተግባራዊ ለማድረግ ሞክራል። ከዚህ በተረፈ ግን በዐፄው ስርዓት ወጥተው የነበሩት ‹ኮዶች› ተፈፃሚነት ቀጥሏል። አገር በቀል እሴቶችን በሕግ ውስጥ ለማካተት ግን የወሰደው ተጨባጭ እርምጃ የለም።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በፀደቀው የ1987 ሕገ መንግሥት በቀደሙት ስርዓቶች የነበረው የአገሪቱ አሀዳዊ አወቃቀር ተቀይሮ ቋንቋን እና የብሔር ማንነትን መሠረት ያደረገ የፌደራል ስርዓት ተዘርግቷል። ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 34/5፣ 39/2፣ 78/5 ድንጋጌዎች ለመረዳት እንደሚቻለው በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ብሔር፣ በሔረሰቦችና ሕዝቦች ባሕላቸውን የመግለጽ፣ የመንከባከብና የማሳደግ መብት የተሰጣቸው ሲሆን የግልና የቤተሰብ ጉዳይን በተመለከተ የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ ባከበረ መልኩ በተከራካሪዎች ፈቃድ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ ሕጎች ተፈፃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ፣ ለዚሁ ዓላማ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ የዳኝነት ተቋማት ሊቋቋሙ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ይህ ካለፉት ስርዓቶች ጋር ሲነፃፀር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የአሁኑ ሕገ መንግሥት የሕግ ብዝኃነትን መቀበሉንና አገር በቀል የሕግ እሴቶች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚረዳ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን በሌሎች ጉዳዮች በተለይም በወንጀል ላይ ኅብረተሰቡ በተለይም በገጠር የሚኖረው ሕዝብ በረጅም ጊዜ የሕይወት ልምድ ያዳበራቸው የሕግ ግንዛቤና አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓቶች ለመጠቀም ያለውን ዕድል ሙሉ ለሙሉ የተዘጋ ነው ለማለት ይቻላል። በዚህም የተነሳ በአንዳንድ አከባቢዎች ሕዝቡ የመንግሥትን ሕግ ወደጎን በመተው በራሱ ባሕላዊ ሕጎች የሚጠቀምበት አጋጣሚዎች በርካታ መሆናቸውን፤ በተለይም በአፋር፣ ሶማሊያ፣ ጋምቤላ፣ አንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች ይህ ሁኔታ በስፋት እንደሚስተዋልና አንዳንዴም በመንግሥት ተቋማትና በባሕላዊ ስርዓቶቹ መካከል ግጭቶች እንደሚፈጠሩ ጥናቶች ያሳያሉ። በሌላ በኩል መንግሥት በየጊዜው የሚያወጣቸው ሕጎችን እንደ ሁኔታው ከተለያ አገሮችና ዓለምዐቀፍ ተቋማት ከመገልበጥ ባለፈ የአገሪቱን ነበራዊ ሁኔታና አገር በቀል እሴቶችን ለማካተት ተገቢውን ጥረት ስለማያደርግ የሕጎች ተፈፃሚነት ላይ ችግሮችን ማየት የተለመደ ነው።

ሕግ ፍትሕ አስተዳደር

በስተቀር በተለይም በገጠሪቱ የሚኖረው አብዛኛው ሕዝብ የሚተዳደረውና የሚዳኘው እንደሁኔታው ሃይማኖታዊና ምንነታዊ ትስስርን መሠረት ባደረጉ ባሕላዊና ልማዳዊ ሕጎችና የዳኝነት ስርዓቶች እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። በ1950 እና 1960ዎቹ ግን ንጉሡ አገሪቱ በተቀራረበ ጊዜ 4 መሠረታዊ (substantive) እና 2 የሥነ ስርዓት ሕጎች በአጠቃላይ 6 ኮዶች እንዲኖሩዋት ያደረጉ ሲሆን ይህም በሕግ ስርዓታችን ላይ መሠረታዊ የአቅጣጫ ለውጥ ማምጣቱ ብዙዎችን ያስማማል። ሕጎቹ በነባሩ አገራዊ እሴቶቻችን ላይ ያመጡትን ለውጥ ከመመልከታችን በፊት ለሒደቱ መነሻ የሆኑትን ታሪካዊ ምክንያቶች በአጭሩ እንመልከት።

ከአድዋ ድል በኋላ ኢትዮጵያ ዝናዋ እየገነነ በመምጣቱ የበርካታ የአውሮፓ አገሮችንና ጎብኚዎችን ቀልብ በመሳቧ ብዙ ልዑካንን ለማስተናገድ እንደቻለች የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በወቅቱ አውሮፓውያን የአፍሪካና ሌሎች ታዳጊ አገሮች የፍትሕ ስርዓቷ ኋላ ቀር ነው የሚል ግንዛቤ ስለነበራቸው በቅኝ በያዙዋቸው አገሮች የራሳቸውን የሕግ ስርዓት በግድ የመጫን፣ ሌሎችን ደግሞ ሕጋቸውን እንዲያዘምኑ ግፊት የማድረግና የራሳቸው ዜጎች በተለየ ሁኔታ በአውሮፓ ሕግና ዳኞች እንዲዳኙ ግፊት የማድረግ ልማድ ነበራቸው። በዚህ መሠረት አንድ የፈረንሳይ ልዑክ ኢትዮጵያ ሕጎቿን እንደ አውሮፓውያን እስክታዘምን ድረስ የፈረንሳይ ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲከሱም ሆነ ሲከሰሱ ጉዳያቸው በፈረንሳይ ሕግና ዳኞች እንዲታይ ስምምነት ከምኒሊክ ጋር በ1908 ያደርጋል። በዚህ መነሻነትም ሌሎችም የአውሮፓ አገሮች ተመሳሳይ መብት ያገኛሉ። ይህም የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነበር። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ “የሊግ ኦፍ ኔሽንስ” አባል ለመሆን በጠየቀችበት ወቅት የተነሳባት ተቃውሞ ኋላቀር መሆኗ ሲሆን ለዚህም በማሳያነት ከቀረቡ ጉዳዮች አንዱ ዘመናዊ ሕግ የላትም የሚል ነበር። ይህ ሁኔታ ከዚያ በኋላ ባሉት ግዜያትም በሰፊው ቀጥሏል። በዚህም የተነሳ ንጉሡ በአብዛኛው የውጭ ባለሙያዎች የተካተቱበት አርቃቂ ኮሚሽን በማቋቋም በምዕራባውያን አስተሳሰብ የተቃኙና በአብዛኛውም ከእነርሱ የተቀዱ ድንጋጌዎች የተካተቱባቸው ‹ኮዶችን› አውጥተዋል። ይህም የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅና አገሪቱን ለማዘመን በሚል ዓላማ እንደተከናወነ ንጉሡም ሆነ በሒደቱ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች በወቅቱ ገልጸው ነበር።

በአንጻሩ ሕጎቹ እንዲወጡ የተደረገው የክልል ገዢዎችን ሥልጣን ለማዳከምና የንጉሡ ሥልጣን ለማጠናከር ነው የሚሉም አሉ። የሆነው ሆኖ የሕጎቹ አጠቃላይ ይዘት ሲታይ በምዕራባውያን አስተሳሰብ የተቃኙና ከነርሱው የተቀዱ እንጂ አገር በቀልና አካባብያዊ የሆኑ ባሕላዊ፣ ሃይማኖታዊና ልማዳዊ እሴቶች ተካተዋል ለማለት አይቻልም። ይልቁንም እነዚህ ነባር እሴቶች ተፈፃሚነት እንዳይኖራቸው የሚከለክሉ መሆናቸውን ከድንጋጌዎቹ ዝርዝር ይዘት ለመረዳት ይቻላል። ሕጎቹ አገር በቀል

እሴቶችን ያላካተቱበትን መነሻ ምክንያትና ይህም በአገሪቱ የፍትሕ ሰርዓት የወደፊት ጉዞ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ከመነሻው የተለያዩ ምልከታዎች ነበሩ።

በወቅቱ በንጉሡም ሆነ ሕጎቹን ባረቀቁት ባለሙያዎች የተገለጸው የአገሪቱን የተበታተነና ኋላቀር የሆነውን ሕግ አስወግዶ የተማከለና ዘመናዊ የፍትሕ ስርዓት ለመገንባት እንደሆነ ተገልጿል። ሕጎቹ አገሪቱን ሊያዘምኑ እንደሚችሉ በብዙዎች ዘንድም ተስፋ ተጥሎ ነበር። ዳንኤል ኃይሉ የተባሉት ጸሐፊ [በወቅቱ] አገሪቱ ኋላቀር ስለሆነች ለመዘመን ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግ እንዳለባት፣ ይህም የአገሪቱን ሕዝብ አስተሳሰብ መቀየር፣ ከሕዝቡ አኗኗር ጋር በፅኑ ከተቆራኙ ጥቂት ባሕላዊ ሕጎች በስተቀር ሌሎቹን በዘመናዊ ሕግ መተካትና ማስወገድ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ይከራከራሉ። አያይዘውም አገሪቱ በወቅቱ ከነበረችበት የባሕል፣ የዕድገትና የፍትሕ ተቋማትና የሕግ ግንዛቤ አንፃር አንዳንድ ሕጎች ወዲያውኑ ተግባራዊ ባይሆኑ እንኳን አቅጣጫ በመጠቆም ሕዝቡን በሒደት ወደ ዕድገት ጎዳና እንደሚመሩ ይገልጻሉ።

በአንፃሩ ጆን ቤክስትሮም የተባሉት አጥኚ በከፊልም ቢሆን ከአቶ ዳንኤል የተለየ አቋም አላቸው። ጸሐፊው ሕጎቹ በሚረቀቁበት ወቅት ቋንቋ ካለመቻላቸው በተጨማሪ በአግባቡ ተጠንቶና በጽሑፍ ተደራጅቶ የተቀመጠ ነገር ባለመኖሩ ነባሩን ባሕላዊ ሕጎች በ‹ኮዶቹ› ውስጥ ለማካተት ለውጭ ባለሙያዎች አስቸጋሪ የነበረ መሆኑን ይገልጻሉ። አያይዘውም የአገሪቱ ባለሙያዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰቦች ፓርላማውን ጨምሮ የልኂቃኑንና የከተሜውን ሕዝብ ፍላጎት እንጂ የአብዛኛውን በተለይም የገጠሩን ሕዝብ ፍላጎት ስለማያንፀባርቁ፣ ነባሩ ባሕላዊ ሕግ በ‹ኮዶቹ› አለመካተቱን አስፍረው፣ ቢያንስ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በ‹ኮዶቹ› ድንጋጌዎችና በተግባር በሚኖረው የሕግ አተገባበር ረገድ ከፍተኛ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል ከፍተኛ ስጋታቸውን ገልጸው ነበር።

በእርግጥም እስካሁንም ድረስ ሕጎቹ በተፈለገው ደረጃ ሕዝቡ ውስጥ ሰርፀው በመግባት በዕለት ተዕለት ሕይወቱ ላይ ለውጥ አምጥተዋል ለማለት እንደማያስደፍር ብዙዎች ይስማማሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብዛኛው ሕዝብ በተለይም በገጠር የሚኖረው ሕይወቱን ይመራ የነበረው በሕጎቹ ሳይሆን በለመደው ባሕላዊና ሃይማኖታዊ ሕጎች ነበር። ለዚህም የሕጎቹ በበቂ ሁኔታና በሚገባው ቋንቋ ለሕዝቡ አለመድረስ፣ ሕጎቹን ለማስፈፀም የሚረዱ ተቋማት በበቂ ሁኔታ አለመደራጀትና የሕጎቹ ከኅብረተሰቡ ባሕልና እሴት ጋር አለመጣጣም በምክንያትነት ሊወሰዱ እንደሚችሉ ስለጉዳዩ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ከዘመናዊነት ጋር በእጅጉ የተቆራኙ እንደ ንግድ ሕግ ያሉ የሕግ ዘርፎች በአንፃራዊነት በተለይም በከተማ አከባቢ አፈፃፀማቸው የተሻለ መሆኑን ጥናቶች ያረጋግጣሉ። በጥቅሉ ሲታይ ግን ሕጉ

ጸሐፊው ተሾመ ተስፋዬ በኢሜይል አድራሻው [email protected] ይገኛል።

Page 17: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

16 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ምሥራቅ አፍሪካ

ከሽምቅ ተዋጊነት ወደአገር አስተዳዳሪነት ከተሸጋገረ በኋላ፣ በነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ተሸንፎና ለዐሥራ ስድስት ዓመታት በተቃዋሚነት ሲታገል ቆይቶ፣

ተመልሶ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኖ፣ የመንግሥት ሥልጣን ለመያዝ የበቃ አንድ ድርጅት አለ። የኒካራጓው የሳንዲኒስታ ንቅናቄ። ኒካራጓ የሳንዲኒስታ ንቅናቄ በተባለው ድርጅት እና በዚህ ድርጅት ዝነኛ መሪ፣ በዳንኤል ኦርቴጋ ምክንያት ስሟ በምሳሌነት ተደጋግሞ ይጠቀሳል። እንደአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ1961 የተመሠረተው የሳንዲኒስታ ንቅናቄ፣ ከ18 ዓመታት የተራዘመ ትጥቅ ትግል በኋላ፣ በ1979 የሶሞዛን አምባገነናዊ አገዛዝ አስወግዶ መንግሥታዊ ሥልጣን ያዘ፤ ቀጥሎም፣ በ1982 በምርጫ ካልሆነ በስተቀር መንግሥታዊ ሥልጣን መያዝ አይቻልም የሚለው የምርጫ ሕግ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ፣ በ1984 በተደረገው ብሔራዊ ምርጫ ንቅናቄው በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ፣ የድርጅቱ መሪ ዳንኤል ኦርቴጋ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኑ፤ በ1990 በተደረገው ምርጫ ንቅናቄው በመሸነፉ፣ ራሱን ለሕዝብ ምርጫ ውጤት ተገዥ አድርጎ ሥልጣኑን ለተቃዋሚው አስረከበ፤ በ1996 እና 2001 በተደረጉት ምርጫዎች በተከታታይ እየተሸነፈ፣ ለ16 ዓመታት በዋና ተቃዋሚ ድርጅትነት ከቆየ በኋላ፣ በ2006 በተደረገው ብሔራዊ ምርጫ አሸናፊ በመሆኑ፣ የድርጅቱ መሪ [ኦርቴጋ] ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣኑን

መልሰው ለመረከብ በቁ። ጠንካራ ድርጅት፣ አርቆ አሳቢ መሪ፣ እንግዳ የፖለቲካ ሒደት።

ጥያቄው ይህ የኒካራጓ ሁኔታ በሌሎች አገሮች በተለይ ደግሞ የሽምቅ ተዋጊዎች በነገሡበት የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ውስጥ ሊደገም የሚችልበት ዕድል አለ ወይ? የሚለው ነው። በትጥቅ ትግል አሸንፈው፣ የመንግሥት ሥልጣን ለመያዝ የበቁ ድርጅቶች በነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ቢሸነፉ፣ ለሕዝብ ምርጫ ተገዥ ሆነው ሥልጣናቸውን ለአሸናፊው ኃይል ሊያስረክቡ የሚችሉት እንደምን ባለ ሁኔታ ነው? የሚለው ጥያቄ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን የራስ ምታት ሆኖ እንደቀጠለ ነው። “የኒካራጓ ሁኔታ በሌላ አገር ይደገማል ማለት ያስቸግራል። ፈፅሞ አይቻልም ብሎ መከራከርም ግን አይቻልም፤” ይላሉ የውይይት መጽሔት አምደኛው ዶ/ር ዳንኤል ክንዴ። ምን ማለታቸው ነው?

አማጽያኑ በምርጫ ቢሸነፉ ሥልጣናቸውን ለተመራጩ ወገን ሊያስረክቡ ይችላሉ ወይ? ከሚለው አጨቃጫቂ ጥያቄ ይልቅ፣ እንደ ኒካራጓ ዓይነት ሒደት ሊፈጠር የሚችለው ምን ዓይነት ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው? በሚለው ነጥብ ላይ ማተኮሩ እንደሚሻል የሚገልጹት ዶ/ር ዳንኤል፣ “ከሽምቅ ተዋጊነት ወደ መንግሥታዊ ሥልጣን የሚመጡ ኃይሎች ራሳቸውን እንደመሲህና የሁሉም ችግሮች የመፍትሔ ምንጭ አድርገው ይቆጥራሉ፤ ‹ቁጥራችን ትንሽ፣ የታጠቅነው መሣሪያ እዚህ ግባ

የማይባል ሆኖ ሳለ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን ኃይል ያሸነፍነው ባለን ድርጅታዊ ጥንካሬ፣ የርዕዮተዓለም ጥራትና ሕዝባዊነት ምክንያት ነው› ይላሉ፤ አሸነፍነው የሚሉት ስርዓት በውስጡ የገጠመውን መበስበስና የዓለምዐቀፍ የኃይል አሰላለፉ የፈጠራቸውን ሁኔታዎች አይጠቅሷቸውም። ‹የጀግንነት ታሪካችን› የሚሉት እንዳይረሳ ሁልጊዜም የሞቱ ሰዎችና የተቃጠሉ ታንኮችን ምስል ያሳያሉ። ‹ትልቅ ነገር፣ ማንም ሊያምነው የማይችለው ገድል ፈፅመናል› ለማለት ሁልጊዜም ‹ታግለን የአፈና አገዛዙን እንጥለዋለን ብለን ስንነሳ ብዙዎች ተሳልቀውብን ነበር፣ የቀድሞውን አገዛዝ መጣል ከግንብ ጋር መላትም ነው ብለውን ነበር፣ ግን አሳካነው፤ አሁንም አገራችን የገጠማትን ችግር ሊፈታ የሚችል ከእኛ የተሻለ ኃይል የለም› ይላሉ። አይበገሬነታቸውን ማሳየት፣ ለሚገዙት ሕዝብም ሆነ ለዓለምዐቀፉ ማኅበረሰብ ጠንካራና ተወዳዳሪ የለሽ ሆነው መታየት፣ ‹ሁሉንም ማድረግ እንችላለን፤ ማንንም አንፈራም› ማለት ይፈልጋሉ። ተቀናቃኞቻቸውን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሌሎች አርፈው እንዲቀመጡ የማድረግ ስትራቴጂ አላቸው። በሌላ በኩል እነዚህ ድርጅቶች ‹መስዋዕትነት ከፍለን ስናበቃ ምንም ዓይነት አስተዋፅዖ ላላደረጉ ወገኖች ሥልጣኑን አሳልፈን አንሰጥም› ብለው የፖለቲካ ሥልጣኑን እንደ የደም ዋጋ መቁጠራቸው ደግሞ ተደጋግሞ የታየ ነው። በእኔ አስተያየት የድርጅቶችን አቋምና የፖለቲካውን ሁኔታ የሚወስነው የሕዝቡ ቁርጠኝነትና ፅናት ነው። በተራዘመና እልህ አስጨራሽ ሠላማዊ ትግል የራሱን ዕድል መወሰን የማይችል ሕዝብ በጥቂት አሸማቂዎች አገዛዝ ሥር ሊወድቅ ተረግሟል።” ሲሉ ያክላሉ።

እንደ ሳንዲኒስታ ንቅናቄ ዓይነት ድርጅትና እንደ ዳንኤል ኦርቴጋ ዓይነት አርቆ አሳቢ መሪ ሊገኝ የሚችልበት ዕድል ከሺሕ አንድ መሆኑን የሚገልጹት የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አቶ ኢዮብ ሲሳይ በበኩላቸው፣ አወንታዊ የፖለቲካ ሽግግር ሊኖር ይችላል አይችልም የሚለውን ለመመርመር፣ የፖለቲካ ድርጅቱ ታሪክና የመሪዎች አቋም፣ ሕዝቡ የራሱን

ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ዳንኤል ኦርቴጋን ፍለጋ

በትጥቅ ትግል ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ በምርጫ ሲሸነፉ ሥልጣኑን የሚለቁ ቡድኖች በዓለማችን እምብዛም አይታዩም፤ ይሁን እንጂ በኒኳራጓ ‹የሳንዲኒስታ ንቅናቄ› የተሰኘው ፓርቲ በዚህ መንገድ ሥልጣን ይዞ በምርጫ ሥልጣን መልቀቅም፣ መልሶ መያዝም እንደሚቻል አሳይቷል በሚል የጻፈው በሪሁን አዳነ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ በትጥቅ ትግል ሥልጣን የተቆጣጠሩ አገራት የኒኳራጓን ዓይነት ለውጥ ለየአገሮቻቸው ያሳዩ እንደሆን በዘረፉ የሚታወቁ ምሁራንን ጠይቋል።

Page 18: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

17ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

በትጥቅ ትግል አሸንፈው፣

የመንግሥት ሥልጣን

ለመያዝ የበቁ ድርጅቶች

በነጻና ፍትሐዊ ምርጫ

ቢሸነፉ፣ ለሕዝብ ምርጫ

ተገዥ ሆነው ሥልጣናቸውን

ለአሸናፊው ኃይል ሊያስረክቡ

የሚችሉት እንደምን ባለ

ሁኔታ ነው?

ምሥራቅ አፍሪካ

ዕድል በራሱ ለመወሰን ያለው የንቃተ ኅሊና ደረጃና ቁርጠኝነት እና የአገሮችን ጅኦፖለቲካዊ አቀማመጥ ሊጤን እንደሚገባ ያስገነዝባሉ። አቶ ሲሳይ እንደሚሉት ሽምቅ ተዋጊ ድርጅቶች የመንግሥት ሥልጣን ከያዙ በኋላም ያን ከትጥቅ ትግሉ ዘመን የወረሱትን ባሕል እንዲሁ በቀላሉ ይተውታል ማለት አይደለም። እንዲያውም ችግር በገጠማቸው ቁጥር በትጥቅ ትግሉ ወቅት የነበራቸውን ድርጅታዊ ጥንካሬ መጥቀስ ይቀናቸዋል። የትጥቅ ትግሉ የግድ የሚችላቸው ምሥጢር ጠባቂነት፣ የድርጅቱን ውሳኔ አለመጠየቅና ሳያቅማሙ መፈፀም፣ እነዚህን ግዴታዎች ተላልፈው በተገኙት ላይ የሚወሰደው ድርጅታዊ እርምጃ፣ ከድርጅቱ የተለየ አቋም ያላቸውን ኃይሎች በጠላትነት ፈርጆ ለመደምሰስ የሚደረገው እንቅስቃሴ ወዘተ. ሁሉ ድርጅቱ መንግሥታዊ ሥልጣን ከያዘ በኋላም ይቀጥላል። በሌላ በኩል ተደጋግሞ እንደታየው በትጥቅ ትግሉ የተሳተፈው ሠራዊት ወደአገር መከላከያ ሠራዊትነት ተቀይሯል ቢባልም፣ ከድርጅቱ ጋር ያለው ታሪካዊ ግንኙነት ይቋረጣል ማለት አይደለም።

የሳንዲኒስታ ንቅናቄ በአንጻሩ እነዚህን የብዙ ሽምቅ ተዋጊ ድርጅቶች ፈተናዎች በስኬት አልፏቸዋል። የድርጅቱ መሪዎች በትጥቅ ትግሉ አሸናፊ መሆን የቻልነው፣ አይበገሬ ስለሆንን ነው የሚል ዕብሪት ሰለባ ባለመሆናቸው፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የገቡትን ቃልኪዳን አላጠፉም። የፖለቲካ ሥልጣንን እንደ የደም ዋጋ ቆጥረው የአገር ሀብት ስላላጋበሱ ወይም ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመው ሕዝብ ስላላስለቀሱ፣ ኃላፊነታቸውን ቢለቁ ይደርስብናል የሚሉት መጥፎ ነገር የለም፤ አልነበረም።

“የሕዝቡ ንቃተ ኅሊና አድጎ፣ መብቱ በጥቂት እናውቅልሃለን ባዮች እንዳይነጠቅ በቁርጠኝነት መታገል እስካልጀመረ ድረስ፣ በሥልጣን ላይ ያሉ አካላት ምን ያህል ቸርና ቀናኢ ቢሆኑ፣ እንዲሁ እንደዘበት ሥልጣናቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ ማለት አይደለም።” የሚሉት አቶ ሲሳይ፣ “የሳንዲኒስታ ንቅናቄ መሪዎች አርቆ አሳቢነት በተግባር የተረጋገጠ ቢሆንም፣ የሕዝቡ የንቃተ ኅሊና ከፍታና ቁርጠኝነት ለፖለቲካ ሽግግሩ ያበረከተው አስተዋፅዖም ከፍተኛ ነው” ሲሉ ያብራራሉ።

አማጽያን የነገሡበት ቀጠናምሥራቅ አፍሪካ አማፅያን የነገሡበት

ቀጠና ነው። ኤርትራን፣ ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ዩጋንዳንና ሩዋንዳን የሚያስተዳድሩት በትጥቅ ትግል አሸናፊ ሆነው ሥልጣን የያዙ ኃይሎች ናቸው። ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል ሻዕቢያና ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓላቸውን በቅርቡ ያከበሩ ሲሆን፣ የዩጋንዳው ብሔራዊ አርነት ንቅናቄ ለሠላሳ ዓመታት፣ እንዲሁም የሩዋንዳው አርበኞች ግንባር ለ22 ዓመታት በሥልጣን ላይ ቆይተዋል። በአንድ ወቅት የምዕራቡ መገናኛ

ብዙኃን “አዲሶቹ የአፍሪካ ተስፋዎች”፣ “አዲሶቹ ተራማጅ መሪዎች” ወዘተ. በሚሉ የማሞካሻ ቃላት ሲገልጻቸው የነበሩት ፕሬዚዳንት ዮሪ ሞሴቬኒ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ፖል ካጋሜ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደታሰበው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን መመሥረት ባለመቻላቸው፣ ሲያደንቃቸው የከረመው የምዕራብ መገናኛ ብዙኃን መልሶ ሲወቅሳቸው ተስተውሏል።

ከጥር 21 ቀን 1978 ጀምረው በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ሞሴቬኒ፣ የብቸኛ ፓርቲ ዴሞክራሲ እገነባለሁ በሚል ሰበብ የመጀመሪያዎቹን ዐሥር ዓመታት ያለ ምንም ተቀናቃኝ በሥልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን፣ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ተፈቅዷል ከተባለበት ከ1988 ጀምሮ በተደረጉት አምስት ምርጫዎች ማሸነፋቸውን ሲያውጁ ቆይተዋል። ለሦስተኛ ጊዜ እንደማይወዳደሩ ለሕዝብ የገቡትን ቃል አጥፈው ተቀናቃኞቻቸውን እያዋከቡ፣ እያሰሩና እያሳደዱ በቅርቡ ለአምስተኛ ጊዜ “ተወዳድረው” መመረጣቸው ይፋ ሆኗል። የተረቀቀውን ሕገ መንግሥት መሳቢያቸው ውስጥ አስቀምጠው በመድበለ ፓርቲ ስርዓት ላይ የሚሳለቁትን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አምባገነናዊ አገዛዝ ወደጎን ብለን፣ የኢትዮጵያና ሩዋንዳ የፖለቲካ ሒደት በምናይበት ጊዜ ሁለቱ

አገሮች ያሉበት ደረጃ ከሞላ ጎደል ከዩጋንዳ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን እንገነዘባለን። በሁለቱም አገሮች የመድበለ ፓርቲ ስርዓት በቅርፅ ደረጃ ቢፈቀድም፣ በተግባር ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳልተገነባ፣ ይልቁንም ከሽምቅ ተዋጊነት አገር ወደማስተዳደር የተሸጋገሩት እነዚሁ ድርጅቶች ሲቪልም ወታደራዊም የሆኑ እና ከሽምቅ ተዋጊነት ሥነ ልቦና ያልተላቀቁ ድርጅቶች መሆናቸውን ለመገንዘብ አይከብድም።

ድርጅቶቹ የመድበለ ፓርቲ ስርዓትን እንደሚቀበሉ ቢያውጁም፣ ዴሞክራሲን ለመገንባት ያላቸው ቁርጠኝነት ለዜሮ የቀረበ በመሆኑ፣ በሲቪል ፖለቲካዊ ትግሉ ሲሸነፉ ወታደራዊነታቸው ይጋለጣል፤ ለሕዝብ የምርጫ ውጤት ከመገዛት ይልቅ ታንክና መትረየስ ተጠቅመው ተቀናቃኞቻቸውን ፀጥ ማሰኘት የሚቀናቸው፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ አውጭ የሚቆጥሩ፣ ሥልጣናቸውን ለማጋራት የማይፈልጉና የተለየ ሐሳብ የማይታገሱ ድርጅቶች ናቸው። የፀጥታ ኃይሉን የውጪ ተቃዋሚን ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ውስጥ የልዩነት ሐሳብ የሚያቀርቡ ወይም የተለየ አቋም የሚያራምዱ አመራርና አባላትን ፀጥ ለማሰኘት ይጠቀሙበታል።

ለመሆኑ ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ እንደ ሳንዲኒስታ ንቅናቄ ዓይነት የፖለቲካ ድርጅት እና እንደ ዳንኤል ኦርቴጋ ዓይነት የፖለቲካ መሪ ማግነት ያልተቻለው ለምን ይሆን?

ይህን ጥያቄ ለመመለስ በተለይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት እንደሚያስፈልግ የሚገልጹት ዶ/ር ዳንኤል፣ “ከሁሉ አስቀድሞ ግልጽ መሆን ያለበት እነዚህ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳና ሩዋንዳ ውስጥ በሥልጣን ላይ ያሉ ድርጅቶች መሪዎችና አባላት በከፍተኛ ደረጃ ሀብት በማከማቸት የተጠመዱ ኃይሎች ናቸው። ብዙ ገንዘብ በሰበሰቡ ቁጥር፣ ይበልጥ ከሕዝብ እየተነጠሉ፣ ይበልጥ የሕዝብን ጥያቄ ማዳመጥ እየተዉ መሔዳቸው ደግሞ የሚጠበቅ ነው። ዴሞክራሲ አደጋ የሚጋብዝ መስሎ ይሰማቸዋል። አንዱ ምክንያት ይኼ ነው። በሌላ በኩል እነዚህ ድርጅቶች ብሔረሰባዊ ማንነት መሠረት አድርገው የተደራጁ በመሆናቸው፣ ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ እንወክለዋለን የሚሉትን ወገን በጥቅማ ጥቅም ለመያዝ ስለሚሞክሩ፣ አደጋ ቢከሰት የሚጎዱት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የእኛ የሚሉት ሕዝብም እንደሚሆን ይገነዘባሉ። እንደሚታወቀው አፍሪካ ውስጥ ከፖለቲካ ሥልጣን መገለል ማለት፣ ከሀብትና ከኑሮ መገለል ማለት ከመሆኑም በላይ፣ ገዥዎች ከሥልጣን ሲወገዱ፣ የሚጎዱት ራሳቸው ብቻ ሳይሆኑ፣ የእነሱ ወገን የሆነ ሁሉ ነው። በዚህ ምክንያት እስከቻሉ ድረስ ኃይል እየተጠቀሙም ቢሆን በሥልጣን ላይ ለመኖር ይሞክራሉ እንጂ፣ ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ እነሱና ደጋፊዎቻቸው ሊጠብቃቸው ስለሚችለው ነገር አስተማማኝ ዋስትና ባላገኙበት ሁኔታ ሥልጣናቸውን በምንም ዓይነት አሳልፈው አይሰጡም” በማለት ያብራራሉ።

Page 19: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

18 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

መጽሐፍት

መንደርደሪያአሌክስ አብረሃም ስውር ደራሲ ነው፤

አንባቢው በአካልም ይሁን በምስል የማያውቀው በብዕር ሥም የሚጽፍ ደራሲ። አሌክስ አብረሃም በአካልም ሆነ በምስል መገለጥን የካደ፣ ነገር ግን ምስሎችን ለመለዋወጥ ተብሎ የተጀመረ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ (ፌስቡክ) ከአንባቢ ያስተዋወቀው፣ የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍም በሕትመት እንዲቀላቀል ያበረታው ደራሲ ነው።

ደራሲው ‹ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም› እና ‹ዙቤይዳ› የተባሉ የአጫጭር ተረኮች ስብስብ መጻሕፍትን፣ እንዲሁም ‹እናት፣ ፍቅር፣ ሀገር› የሚል የግጥሞች ስብስብ መጽሐፉን አሳትሟል፤ ሌሎች ገጣሚዎችን በማስተባበርም ‹መስቀል አደባባይ› የሚል የግጥም መጽሐፍ አሳትሟል። ከዚህም ባሻገር ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ ተከታዮችን ባፈራበት የፌስቡክ ገጹ ላይ ወጎቹን፣ ተረኮቹን፣ ግጥሞቹን፣ መጣጥፎቹን በየቀኑ ሊባል በሚችል ደረጃ ለአንባቢዎቹ ያካፍላል። እንዲያውም ፌስቡክ ወደ ኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ አንባቢያንን መልሶ አምጥቷል የሚባለው መላምት ትክክል ከሆነ፣ በዚህ ተግባር ውስጥ ትልቁን ሚና ከተጫወቱ ጥቂት ደራሲዎቻችን ቁንጮው አሌክስ እንደሚሆን እገምታለሁ።

አሌክስ በተለይ በሁለቱ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጻሕፍቱ እርስ በርሳቸው የተጋመዱ የተለያዩ ሐሳቦቹን እና ስሜቶቹን አጋርቷል። በድርሰቶቹ አማካይነት፣ በአስውቦ መግለጽ ከኀሊነቱ፣ በቋንቋ ሀብቱ (እና የአጠቃቀም ልኂቅነቱ)፣ እንዲሁም በምናቡም ጥልቀት በፈጠራቸው ታሪኮች እያዋዛ የሰላ

አሌክስ አብርሃም ታይታን የሚያደበዝዝ ስውር ደራሲ

‘የዶክተር አሸብር’ እና ‘ዙቤይዳ’ ንባብ

ፌስቡክ ላይ ራሳቸውን አስተዋውቀው ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኙ ከመጡ ጸሐፍት መካከል ‹አልክስ አብርሃም› በሚል ሥም የሚጽፈው ደራሲ ከግንባር ቀደሞቹ ተርታ ይሰለፋል። ቴዎድሮስ አጥላው የዚህን ደራሲ ሁለት መጽሐፍት አንብቦ የአሌክስ አብርሃም ድርሰቶች የአካላዊ ውበትን የመልካም ስብእና መገለጫ አድርጎ ያያቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ይነግረናል።

ማኅበራዊ ትችቱን ይሰነዝራል። እያሣሳቀ ይሄሰናል፤ እያሳሳቀ ያስፀፅተናል።

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ‹ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም› (2006) እና ‹ዙቤይዳ› (2007) በተባሉት መጻሕፍት ውስጥ ተደጋግመው ከሚሰሙ የደራሲው የሚመስሉ ድምፆች መካከል አንዱን፣ ይኸውም የአካላዊ ሰብእናን ነገር መዝዞ በአጭሩ መተንተን ነው። ይህ ጽሑፍ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከማደርገው ገና ያልደረሰ የግል ጥናቴ ተቀናብሮ የቀረበ ነው።

የመልክ እና ቁመና ውክልና ከወደ ኋላ

በየትኞቹም ባሕላዊ እና ኪነጥበባዊ ራስን መግለጫዎች ውስጥ አካል/ሥጋ እንደ መንፈስ መፈከሪያ ተደርጎ፣ የጭብጥ ማደሪያ ሆኖ ጉልህ ስፍራ ተሰጥቶት እናገኛለን። ባሕላዊ ገላን የማስዋብ ጥበባት፣ አካልን የማጠንከር ግዴታዎች፣ የአካል ጥንካሬ ወይም የቁመና ማማር ለትዕይንት የሚቀርቡባቸው ባሕላዊ ስርዓቶች፣ ወንዶችን ማደለቡ፣ የሴቶችን ብልት ወይም ከናፍር እና ጆሮዎች መተልተሉ፣ አንገት ማስረዘሙ፣ እግር አሰራው (foot binding)፣... ሁሉ አካለ ሰብእን (human body) በሰው ዓይን ተፈላጊ፣ ተመራጭ ማድረግን (መሆንን) ዋነኛ ገ’ዳቸው ያደረጉ ናቸው። ቅኔው (መወድሱ)፣ መልክዑ፣ ዘፈኑ፣ ስዕሉ፣ ሐውልቱ፣ ፊልሙ፣ ፎቶግራፉ፣ ልቦለዱ፣ ተውኔቱ፣ ማስታወቂያው፣... ሁሉ ቢያንስ ስለውክልናዊ ዋጋው ሲሉ ለአካለ ሰብእ ትኩረት ይሰጣሉ።

አካለ ሰብእ ተፈጥሯዊ፣ ወይም ሥነ

ሕይወታዊ ቅርፅ ብቻ አይደለም። አካለ ሰብእ በባሕላዊ/ በኪናዊ መንገድ ከሚታየው፣ ከሚዳሰሰው፣ ከሚሸተተው በላይ ሰፊ ትርጓሜ እንዲይዝ ተደርጎ የሚቀረፅ፣ ባይቀረፅም እንኳን በተፈጥሯዊ ወይም በማኅበራዊ ሥሪቱ ምክንያት ብቻ እንደዚያው ብዙ ትርጓሜዎችን (ሐሳቦችን፣ ስሜቶችን፣ አንድምታዎችን፣ ትውስታዎችን) ተሸክሞ የሚሔድ ምንባብ (text) ነው። Dani Cavallaro እንደሚለው `The physical form is not only a natural reality but also a cultural concept: a means of encoding society's values through its shape, size and ornamental attributes (Critical and Cultural Theory: Themathic Variations.London and New Jersey. 2001.97-8).

ተፈጥሯዊ ሥሪቱን የሚያዩ የማኅበረሰብ ዓይኖች (ዓይነ ልቡናዎችም ሊሆኑ ይችላሉ) በዚህ የአካላት ኅብረት ባቆመው ስጋ ላይ ከሚያነቡት ምንባብ የተነሳ ስሜታቸው ሊቀያየር፣ ሊፈርዱ፣ ሊፈርጁ፣ አቋም ሊይዙ፣ በድርጊትም አፀፋ ሊመልሱ ይችላሉ። (ለዚህ ነው ከኃላፊነታቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖረውም የመሪዎቻችን መልክ፣ ቁመና፣ አረማመድ… ትልቅ ጉዳያችን የሚሆነው፤ ለዚህ ነው “ይሄን ህዝብ እየቀጠቀጥንም ባይሆን፣ እየተንቀጠቀጥን እንገዛዋለን፣” አሉ ብለን ብስጭታችንን በቀልድ የምንወጣው።)

በእኔ ንባብ የአማርኛ ልቦለድ በአብዛኛው

Page 20: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

19ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4ወደሚቀጥለው ገጽ

መጽሐፍት

አስቀያሚ ሴቶችን ይጨቁናል። ቆንጆዎችን ተሸናፊ ያደርግ ይሆናል እንጂ፣ አስቀያሚዎችን አሸናፊ ሲያደርግ ማየቴን አላስታውስም። ዶ/ር ዮናስ አድማሱ “የዋሆቹ ፋና ወጊዎች” (The Humble Trailblazers) ከሚሏቸው ከነኅሩይ ወልደሥላሴ ጀምሮ፣ “ሥር ነቀል ለውጥ ፈላጊዎቹን” ጨምሮ፣ አሁን በዚህኛው ዘመን እስከተነሱት ድረስ፣ ያሉት የአማርኛ ልቦለድ ደራሲዎች በድርሰቶቻቸው ውስጥ ኪነት ቀብተው ለአንባቢ የሚልኳቸውን ሰናያት እሴቶች በተለይ የወንድ ዕይታ በማይስቡ ሴት ገፀ ባሕርያታቸው በኩል ሲያስተላልፉልን አይታዩም። ይልቁንም፣ በተለይ ቀደምት ታላላቅ የልቦለድ ሥራዎቻችንን ስንመለከት “መልክ ግብርን ይመራዋል” የሚል የጋራ መርሕ የሚከተሉ ይመስላሉ። (ምናልባትም ይህንን መልክን ከግብር/ ከባሕርይ ጋር አስማምቶ የማቅረብ ቅጥ ዓለማዊው ሥነ ጽሑፋችን ከገድላት የተዋሰው ሳይሆን አይቀርም።) ይህንን ሐሳብ በምሳሌዎች እንየው፡-

የመጀመሪያው የአማርኛ ልቦለድ ነው በሚባለው የአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ‹ጦቢያ› መጽሐፍ በምስቅልቅል ጀምራ በሥምረት የምትጠናቀቅ ተረክ ናት፤ በተለይ እንደ ዮናስ አድማሱ እና ታዬ አሰፋ ያሉት መጽሐፏን በጥልቀት ያጠኗት ሀያሲዎች እንደደመደሙት፣ ይህቺ መጽሐፍ ሁሉ በአንድ እምነት ተሳስሮ፣ በአንድ ንጉሥ ሥር አድሮ በሠላም የሚኖርበት ሀገረ መንግሥት የመመሥረት ርዕይ ሰንቃለች። የእኔም ጥናት ያረጋገጠልኝ ይህንኑ ነው።

ደራሲው ይህንን ታላቅ ርዕይ የሚያሸክሟቸውን ገፀ ባሕርያት በባሕርያቸው ወይም በሃይማኖታቸው ብቻ አልመረጧቸውም። በድርሰቱ መቼት መሠረትም በነገሥታት ዘርነታቸው (በደማቸው) ብቻ አልሾሟቸውም። ደራሲው ለተምኔታዊው መንግሥታቸው የመረጧቸውን ጦቢያን፣ ወንድሟን ዋሕድን እና ኋላ የሚያገባትን (የጦቢያ/ የኢትዮጵያ ባል የሚሆነውን) "የአረመኒ" ንጉሥ ለታሰበው መንግሥት የሚያስፈልገው ጽድቅ፣ ደም እና ደም ግባት አላብሰዋቸዋል።

ለምሳሌ ራሷን ኢትዮጵያን እንድትወክል የተቀረፀች የምትመስለው እና ኋላ ከወራሪው የ"አረመኒ" ንጉሥ ጋር ተጋብታ፣ በጋብቻዋ መንግሥት የምታረጋውን ጦቢያ የተባለችውን

ገፀ ባሕርይ ብንወስድ፣ ደራሲው የእሷን አእምሯዊ እና መንፈሳዊ ባሕርያት ለማሳየት ከተጉት ባልተናነሰ የስጋዋንም አነሁላይነት ይስሉልናል። የጦቢያን አመል የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ ከሚባሉት ከነኪሩቤል ጋር በንፅፅር የሚገልጥልን ተራኪ፣ የአካሏንም ነገር በጀመረበት መንፈሳዊ ንፅፅር “እንዲያው እግዚአብሔር ደስ ያለው ዕለት ተጨንቆና ተጠቦ ሠርቶ ነፍስ የዘራባት ትመስላለች እንጂ ጦቢያ እንደ ሰው የተፈጠረች አትመስልም ነበር” ብሎ ይቋጫል (አፈወርቅ፣ 48)። ገለጻዋ የሚጀምረው አጠቃላይ በሆነ ማራኪነቷን ገላጭ ዓረፍተ ነገር ነው። “እውነትም ጦቢያ እጅግ የተዋበች፥ እጅግ የተደነቀች፥ ላያት ሁሉ የምታነሆልልና የምታዘነጋ ነበረች፣” ይላል (ጦቢያ፣ ገጽ 47)። በፀሐይና በውርጭ የተጎሳቆለው ፊቷ፣ የጠፋ ወንድሟን ፍለጋ ስትሔድ በመንገድ አረመኔ እንዳይተናኮላት የደበቀችው ሴትነቷ እንኳን ያልሸፈኑትን የመልኳንና የቁመናዋን ፍፁም ውበት በዝርዝር እንተዋወቃለን።

“ዓይንዋ አስቀድሞ የብር አሎሎ መስሎ ከአጥቢያ ኮከብ ጋር የተፎካከረ ነበር። በዚያ ላይ ደግሞ ሽፋሽፍቷ እንደበልግ ሣር ተጨብጦ የሚታጨድ ይመስል ነበር። አፍንጫዋ ቀጥ ያለ፥ ከንፈሯ መፈንዳት የጀመረ የማለዳ ጽጌረዳ ይመስል ነበር። እንደ ወንድ የተቆረጠችው ጠጉርዋ እንደ ሰኔ ቡቃያ ወይም እንዳዲስ መሬት ጤፍ እየጋሸበ የሐር ነዶ መሰለ። በፀሐይና በውርጭ የተጎሳቆለው ፊቷ እያሸተ ሀጫ በረዶ ተመሰለው ጥርሷ ጋር ገና ከሩቅ እየጠቀሰ ከተሸሸገችበት ሴትነቷን ያሳጣባት ጀመር።” (ጦቢያ ገጽ 47)

በነገራችን ላይ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ይህንኑ የጦቢያን የተጋነነ የቁንጅና ገለጻ፣ ‹ዐጤ ምኒልክ› የተባለው መጽሐፋቸው ውስጥ ብዙም ሳያጓድሉ ለእቴጌ ጣይቱ ሲጠቀሙበት እናያለን። ጦቢያን በሥጋም በባሕርይም ይህንን ያህል ማግዘፋቸው (ይህንን ማግዘፍ ገንኖ የሚታየው በተጻራሪ ከቀረቡት ገፀ ባሕርያት ገለጻ አንጻር ነው)፣ ለእቴጌ ጣይቱ የሌላቸውን ሥጋዊ ውበት እስከ መስጠት የሚያደርሳቸው፣ (እሳቸው ብቻም ሳይሆኑ፣ ሌሎቹም ቀደምት “ታሪክ” ጸሐፊያን ለጀግኖቻቸው ሥጋዊ ውክልና መጨነቃቸው)፣ የሚያሳየን ለኅሩያኑ (ለተመረጡቱ) ፍፅምናን የማጎናፀፍ

አዝማሚያን ነው።በኋላም ቴዎድሮስ ገብሬ “ማኅበራዊ

ለውጥን” ግባቸው ያደረጉ ከሚላቸው የኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሥራዎች አንዱ የሆነው ‹የልብ አሳብ› ላይ ፅዮን ሞገሳ የተባለችውን ለፍፅምና የቀረበችው ገፀ ባሕርይ እና ‹ፍቅር እስከ መቃብር› ውስጥ ደግሞ የድርሰቱ የፍቅር ታሪክ፣ የፖለቲካ ስርዓት ሙግት፣ ዮናስ አድማሱ “የሰብእና መንጠፍ” (dehumanization) የሚሉት ጭብጦች እና ሌሎቹም ዋና ዋና ሐሳቦች የሚያጠነጥኑባትን ሰብለ ወንጌልንም በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። በዓሉ ግርማም ቢሆን፣ በ‹ከአድማስ ባሻገር› ጠይም ጣኦት ነኝ የምትለዋን ትምክህተኛዋን ቆንጆ ሉሊትን፣ በስተመጨረሻ ለአበራ ትንሳዔ የምትተጋ መልካም ሴት ሲያደርጋት ይታያል።

ይህንን ሰፊ ጥናት የሚጠይቅብኝን ትንተና በምሳሌነቱ አስይዤ፣ ወዲህ ወዳለንበት ዘመን እና ለዛሬ ወደ መረጥኩት ደራሲ ሥራዎች በፍጥነት ልመልሳችሁ።

የመልክና ቁመና ውክልና በአሌክስ ሥራዎች ውስጥ

ምንም እንኳን እንደ ቲፋኒ አትኪንሰን ያሉ ጸሐፊዎች “Contemporary culture loves body gazing'' (The Body. Palgrave: New York. 2005.p2) ቢሉም፣ እውነትም ዘመኑም “ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል” የሚል መርህ የያዘ የሚመስልበት እና ዓይነ ግቡነትን የሚያስቀድም ቢሆንም፣ አሌክስ አብረሃም ደራሲነቱ በሰጠው ፍንገጣ በአብዛኞቹ “ምግባር ከመልክ ይቅደም” ብሎ ከዚህ ከዘመኑ እውነታ ጋር ሲሟገት እና ከዚህ እውነታ ጋር ተስማምቶ ከሚኖረው ማኅበረሰብ ጋር ሲላተም እናገኘዋለን።

የአሌክስ ድርሰቶች ያሉት ቆንጆዎች በቁንጅናቸው ይከሽፋሉ፣ ወይም ስኬታቸው እንኳን በተራኪው ይንኳሰሳል። በዚህም የተነሳ ብዙ ጊዜ ደራሲው ቆንጆ ሴት አይወድም የሚል የአንባቢ አስተያየት ሲሰጥበት አስተውያለሁ። በእኔ ንባብ የአሌክስ ድርሰቶች ፀባቸው ከቁንጅና ጋር ሳይሆን ለቁንጅና ከተሰጠው ቦታ ጋር ነው። በሌላ አነጋገር ፀቡ ቁንጅናን አግንኖ ሰውን በዕይታው ከሚመዝነው ማኅበረሰብ ጋር ነው። ለምሳሌ “አልሐምዱሊላሒ ደህና ናት” የሚለው ተረክ ውስጥ አፍራህ ለምትባለው ቆንጆ ተማሪ የሚያዳሉትን መምህር አስታኮ ወገኖቹን ይሄሳል፡- “ግን እኮ እኛ ሐበሾች ብዙዎቻችን እናስመስላለን እንጂ ሴት አናከብርም፤ የምናከብረው ቆንጆ ሴትን ነው።” (ዙቤይዳ፣ ገፅ 7)

ሐበሾች ለዓይናችን ያማረውን ስናከብር ሌላውን እንንቃለን፤ ዓይነ ግቡዎችን በላያችን ላይ ስናሠለጥን፣ ሌሎችን እንጨፈልቃለን የሚል ሐሳብን በድርሰቶቹ ውስጥ ደጋግመን እናነባለን። ደራሲው ቆንጆዎች በቆንጆነታቸው ብቻ የተለየ ዕድል ማግኘታቸው፣ ወይም አስቀያሚዎች ቆንጆ ባለመሆናቸው ብቻ ዕድል መነፈጋቸው ፍትሐዊ አይደለም የሚል ትግል

የአማርኛ ልቦለድ በአብዛኛው አስቀያሚ ሴቶችን

ይጨቁናል። ቆንጆዎችን ተሸናፊ ያደርግ ይሆናል እንጂ፣

አስቀያሚዎችን አሸናፊ ሲያደርግ ማየቴን አላስታውስም

Page 21: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

20 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

መጽሐፍት

ውስጥ የገባ ይመስላል። ለምሳሌ አንደኛው ተረክ ውስጥ አንዲት ቆንጆ ለመቅጠር ሲባል፣ የኖሩ የቢሮው ሠራተኛ ያለጊዜያቸው ጡረታ እንዲወጡ ይደረጋል። ይህቺን በሁሉም ወንድ ሠራተኞች ዓይን ተወዳጅ የሆነች ቆንጆ ሴት፣ ተራኪው ጨቋኝ አድርጎ ያቀርባታል፤ ሰውን በሚታይ ምንትነቱ ብቻ የመቀበልን/የመግፋትን ጣጣ ይተረጉምባታል። “በአምባ ገነን እግሯ ምንም በሆነ ሴትነቷ፣ ፍትሕ ትረግጣለች፤ ያማረችው በሚስኪኖች እንባ ታጥባ ነው። ንፅህናዋ ንፁህ ነፍሳትን ትቢያ አድርጋ ነው። ያውም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሚስኪኖችን…” (ዶክተር አሸብር፣ ገፅ 144) ይህንኑ ሐሳብ “በክራንችና ጭብጨባ የቆመ ወንበር” በሚለው ምፀታዊ ተረክ ውስጥ አንድ ዘፋኝ “ተውረግረጊ የኔ ቆንጆ” ለተባለ ዘፈኑ ቪዲዮ የተቀረፀው ቪዲዮ ላይ የሞዴሏ ገላ እንዴት የተመፅዋቹን ችግር ጋርዶት እንደነበር ይነግረናል። ክሊፑ ላይ፣ “ተውረግራጊዋ ቆንጆ ለአበራ (የኔ ብጤው) ሳንቲም ልትመፀውት ጎንበስ ስትል ካሜራው የተራቆተ ታፋዋን ከጉልህ መቀመጫዋ ጋር የሚያሳይበት ትዕይንት ተካትቶ ነበር። የልጅቱ ሰፊ ዳሌና ራቁት ታፋ የአበራን ክራንች፣ የድንጋይ መቀመጫና የተቆረጠ ቀኝ እግሩን ከልሏቸው ነበር!!” (ዙቤይዳ፣ ገፅ 155)

አሌክስ ቆንጆዎቹን ሴቶች ከነአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ከነሐዲስ ዓለማየሁም በተቃራኒ በምግባር ያራቁታቸዋል። መልከ ቀና ምግባረ ቀና የሚያደርጋቸውን እናቶች ካልሆነ በቀር፣ ሴቶቹን በአካላዊ ውበታቸው መመካት፣ ስለ ቁንጅናቸው መጨነቅ፣ እሱኑ ማስጌጥ ሲጀምሩ ቀድሞ የሰጣቸውን ምግባር ሳይቀር ገፎ እርቃናቸውን ያስቀራቸዋል። በዚህ ረገድ ተራኪው በመልኳ ሲርድላት፣ በምግባሯ ሲያሞግሳት የነበረችውን ፋና የተባለች ቆንጆ ልጅ ከድህነት ለመውጣት ወደ ገላዋ መመልከት ስትጀምር ሴተኛ አዳሪ ያደርግና ያቀልላታል (ዶክተር አሸብር፣ ገፅ 21-43)። ፋና ቤተሰቧን ከረኀብ፣ ከሐፍረት እና ከጉስቁልና የምታወጣበት መሳሪያዋ፣ እንደ ተራኪያችን ከፋት ወይም ደስ አላት፣ በረዳት ወይም ሞቃት

የሚላት ቀርቶ በስሜት ሞቀች ወይስ በደነች የማትባልበት የሚሸጥ ገላነት ሕልውናዋ ሲሆን እናያለን። ሴቶቹ በተቃራኒው በመልካቸውና በቁመናቸው መመካት የወረወራቸው የሽንፈት ጉድጓዳቸው ውስጥ ሆነው አካላቸውን መርሳት ሲጀምሩ፣ ደራሲው በሌላ ማንነት የምግባር ትንሳዔ ያጎናፅፋቸዋል። ትኩረቷ ሁሉ ቁንጅናዋ፣ ቁንጅናዋን ያደመቀችበት ልብሷ ውድነት፣ ቁንጅናዋን የከበበችበት ሽቶ ምርጥነት የሆነባትን እና አሸብር የሚባለው ተራኪያችን “ዋጋ ቢስ” የሚላት ዛፒ ለዚህ ግሩም ምሳሌያችን ናት (ዶክተር አሸብር፣ ገፅ 200-237)።

በዚህ የታይታ ጉዳይ ደራሲው ማኅበረሰቡን ከመተቸት አልፎ ሲፋለመውም እናያለን። የደራሲው መሣሪያ በቃላት ሥጋ ያለበው አስቀያሚነት ነው። በአንዱ መጽሐፍ ውስጥ ሁለት የተለያዩ እንዲመስሉ የተለያዩ ሥሞች የተሰጧቸው፣ አንድነታቸው የገነነ ገፀ ባሕርያት “ከሰሀራ በታች” ውስጥ የምናገኛት ፍቅርተ (ዶክተር አሸብር፣ ገፅ 21-43) እና “አለሁላት” ውስጥ ያለችው ሀና ምንተስኖት (ዶክተር አሸብር፣ ገፅ 162-7) ናቸው። እነዚህ ሁለት ወጣቶች ሁለት ታሪኮች ውስጥ ይግቡ እንጂ ገለጻቸው ተመሳሳይ ነው፣ በአስቀያሚነታቸው ነቀፋ የሚያሸማቅቃቸው፣ መፈቀር ቀርቶ ማፍቀራቸው እንኳን የሚያሳፍራቸው፣ ነገር ግን አንደበታቸው የሚማርክ ተደርገው ነው የተመሰሉት። ይህንን የምግባር እሴት ለሁለቱም ሲደርብላቸው ስናይ፣ ቆንጆዎቹን በሰናይ ምግባር/ በቁምነገር ረገድ ሆነ ብሎ እንዳራቆታቸው እና ረጋፊ ሥጋቸውን ይዘው እንዲሰለፉ እንዳደረጋቸው እናረጋግጣለን።

በመጀመሪያው ተረክ ንግግሯ የማይጠገብ ያላትን ፍቅርተን ከሕፃንነቷ ጀምሮ የተገፋች፣ ኋላም ለተራ ሠላምታ እንኳን ወይ ሀብት ወይ መልክ ያስፈልጋል የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰች አድርጎ ሕመሟ እንዲሰማን ይጫነናል። ለስቃይዋ በተጠያቂነት እንድንፀፀት ይገፋፋናል። ይህቺኑ አስቀያሚ ከመቶ አርባ ገጽ በኋላ መልሶ በሌላ ሥም እና በሌላ አኗኗር ውስጥ አስገብቶ ያመጣት እና፣ ተራኪው (በጥልቀት ስንመለከተው አብዛኞቹ ተረኮች ውስጥ የሚመላለሰው አንድ ተራኪ እንደሆነ እንረዳለን) “ከሰሀራ በታች” ውስጥ ያለውን አፍቃሪነት፣ ደግነት፣ አዛኝነት፣ ከሚታየው ባሻገር የተደበቀውን የመመልከት ዝንባሌውን ይዞ የሀና ምንተስኖት ነጻ አውጪ ይሆንብናል። እንደ ማኅበረሰቡ በአስቀያሚነቷ አልገፋትም፤ እንደ አፈወርቅ “እንኳን ለቤተ መንግሥት ለተራበ ጅብም” ታስጠይፋለች ብሎ በክፉ መልኳ አልተረባትም፤ አሳምነው ባረጋ አንደመሰላት አስቀያሚ ገፀ ባሕርይ ደግሞ ቆንጆዋን ጓደኛዋን ወርሮ መያዣ የትሮይ ፈረሱ አላደረጋትም (የትሮይ ፈረስ፣ ገፅ 207)። ይልቁንም ከቤተሰቡም ከማኅበረሰቡም ተጋጭቶ ያገባታል፤ ሥምረት በጎደለው፣ በአስቀያሚ አካሏ ምክንያት ያለፍላጎቷ እንደ አስቀያሚ ገላ ብቻ ስትታይ ለኖረችው ሀና (ለፍቅርተም

ጭምር) የተነፈገችውን ወግ አጋንኖ ይሰጣታል። ማርገዟን ሁሉ ይነግረናል።

የአሌክስ አብረሃም አካል አልቦ ደራሲነት

የአሌክስ ፍልሚያ ከማኅበረሰቡ አስተሳሰብ ጋር ይመስላል፤ ሴቶችን ከሌሎች በተፈጥሮም ይሁን በትምህርት ካሏቸው እሴቶች አሳንሰን በአካላቸው/ ጊዜ በሚያረግፈው ገላቸው ብቻ ማየት ኢፍትሐዊ ነው ይላል። ድርሰቶቹ እንደሚያሳዩን ደራሲው ሰብእናቸውን ወደ ገላነት የሚያሳንሱትን ሴቶችም ሆነ፣ የሴቶቹን (የቆንጆዎቹንም ሆነ የአስቀያሚዎቹን) ሰብእና ወደ ገላነት አሳንሰው የሚያዩትን የወንድ ዓይኖች ይፀየፋል። ይህንኑም በተለያዩ ድርሰቶቹ ሲታገለው አይተናል።

አሌክስ ከድርሰቶቹም ውጭ በስውር መጻፉም የዚህ ትግሉ አንድ አካል ሊሆን ይችላል፤ ወይም ድርሰቶቹ በአካል ለመገለጥ ያለመፈለጉ ማሳያዎች ሊሆኑ ይችላሉ። በሥነ ጽሑፋችን ታሪክ በብዕር ሥም ጽፎ ማሳተም አዲስ ጉዳይ ላይሆን ይችላል (‹ሴተኛ አዳሪ› የሚለውን እናኑ አጎናፍር በተባለ የብዕር ስም የታተመ ቀዳሚ ሥራ ማስታወስ በቂ ነው)። ደራሲዎች በብዕር ሥም የሚጽፉትም እንደ የመጻፍ ነጻነት ማጣት ያሉ፣ ከገበያ ጋር በተያያዙ እና በሌሎችም የተለመዱ ምክንያቶች ይሆናል።

እስካሁን ለማሳየት የሞከርኳቸውን ሐሳቦች ሳሰላስላቸው ግን ሰውን በአካላዊ ቁንጅና እና ቁመናው መለካትን፣ መሾምን እና መጨቆንን የሚቃወሙ ድርሰቶችን የጻፈው ይሄ አሌክስ አብረሃም የተባለው ደራሲ ራሱን በአካል የማይገልጠው በዚሁ በድርሰቶቹ ውስጥ ተደጋግሞ በምናየው መርሑ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። መሰወሩ፣ ሰዎች ‹Ulysses› መጀመሪያ ላይ እንደምናገኘው አስቀያሚው ስቴፈን ዴዳሉስ “አሁን ይሄን መልክ ማነው ለእኔ የመረጠልኝ” በሚያስብለን፣ እኛ ባልሠራነው (ቆንጆም ይሁን አስቀያሚ) መልክና ቁመና ሳይሆን፣ ከእኛ በሆነው ዕውቀታችን፣ ምግባራችን፣ ክኅሎታችን ነው መታወቅ ያለብን የሚል ተቃውሞውን ማሰሚያው ይመስለኛል። አካል ይደብዝዝ አእምሮ እና መንፈስ ጎልቶ ይታይ የሚል ዓይነት ሐሳቡ ይሰማኛል።

በነገራችን ላይ ይሄ አካል አልቦነቱ ለእኛ ድርሰቶቹን እንተነትናለን ብለን ለምንነሳ አንባቢዎች፣ ለትንታኔያችን የደራሲውን የትርጓሜ ይሁንታ (his authority) ከመጠየቅ እና የድርሰቶቹን ጭብጦች በደራሲው እምነት፣ ፍላጎት እና የሕይወት ልምድ ላይ ከመገደብ ያድነናል። ዮሐንስ ከዪትስ ግጥም ወስዶ እንደሚለው ዳንሱን ከዳንሰኛው ነጥሎ ለማየትም ይረዳናል።

ቴዎድሮስ አጥላው የቋንቋ እና የሥነ ጽሑፍ ተመራማሪ ናቸው፡፡ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ይገኛሉ።

አፍራህ ለምትባለው ቆንጆ ተማሪ የሚያዳሉትን

መምህር አስታኮ ወገኖቹን ይሄሳል፡- “ግን እኮ እኛ

ሐበሾች ብዙዎቻችን እናስመስላለን እንጂ ሴት

አናከብርም፤ የምናከብረው ቆንጆ ሴትን ነው

Page 22: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

21ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ጎምዛዛው የልጅነት ጊዜየማርሸት ሲሳይ በ1960ዎቹ እንግሊዝ

ለትምህርት ከተላኩ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ውስጥ አንዷ ነበረች። እንግሊዝ ስትደርስ ነፍሰ ጡር የነበረችው የማርሸት በወቅቱ ከትዳር ውጭ መውለድን እንደነውር የሚቆጥረውን የእንግሊዝ ስርዓት መጋፈጥ ግዴታዋ ነበር። በእንግሊዝ ልጇን ወልዳ ወደ ት/ቤት ለመመለስ ለአጭር ጊዜ መፍትሔ አድርጋ የወሰደችው ልጇን ለማኅበራዊ አገልግሎት /Social worker/ መስጠት ነበር። ተመልሳ ልጇን እንደምታገኝ ተስፋ አድርጋ ነበር። ልጇን የተረከበው የማኅበራዊ አገልግሎት ሠራተኛ ግን ያለሷ ፈቃድ “ለምን ሲሳይ” የሚለውን የልጇን ሥም “ኖርማን ግሪንውድ” በሚል ቀይሮ ለአንድ ቤተሰብ እስከ ወዲያኛው በጉዲፈቻ ሰጠው።

እንደማንኛውም ሕፃን ደስተኛ ልጅ እንደነበር የሚናገረው ለምን፣ በጉዲፈቻ የሚያሳድጉት ቤተሰቦቹ ሁለት ልጆች ሲወልዱና ጥቁርነቱ እየገባው ሲመጣ ማንነቱ ጥያቄ ውስጥ ገባ። ዘጠኝ ዓመት እሰኪሞላው ጥቁር ሰው አይቶ አያውቅም፤ ዐሥራ ስድስት ዓመት እስኪሞላው ስለ ጥቁር ሰው የሚያውቀው ነገር አልነበረውም፤ ሀያ ሦስት ዓመት እስኪሞላው ‹ለምን› የሚለውን የሥሙን ትርጉም አያውቅም ነበር። ጥቁር የሆነው ሰይጣን ተጠናውቶት እንደሆነ የተነገረው ለምን፤ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲሞላው “ቤተሰቦችህ ነን” ሲሉት የነበሩት አሳዳጊዎቹ ያለ ማንም ጠያቂና ዘመድ ወደ ሕፃናት ማሳደጊያ /Child care/ ላኩት። ብቻውን እንደቀረና እንደተከዳ ገባው። ግራ መጋባት፣ ባዶነት፣ ብቸኝነት፣ ‹ማንነኝ? ከየት መጣሁ?› የሚሉ አስጨናቂና ግራ አጋቢ ስሜቶችና ሐሳቦች የልጅነት አዕምሮውን ሰቅዘው ያስጨንቁት ጀመር።

ዐሥራ ሰባት ዓመት እስኪሞላው

ለምን ባለቅኔው ለምን ሲሳይ ከኢትዮጵያ ወላጆች ተወለዶ፣ እንግሊዝ አገር በጉዲፈቻ

ያደገ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የአፈ እንግሊዝ ባለቅኔ ነው። መብራቱ በላቸው፣ የዚህን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ማንነት ራሱን በማነጋገር እና ሌሎችንም በመጠየቅ በዛሬው መጣጥፉ ያስነብበናል።

በቆየበት የሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ብዙ መከራ፣ መገለል፣ አካላዊና መንፈሳዊ በደል ደርሶበታል። በእንግሊዝ በዘመኑ እነዚህ የሕፃናት ማሳደጊያዎች የልጆችን ሕይወት ማበልፀጊያና መታደጊያ ሳይሆኑ በተቃራኒው የበደልና የጭቆና ቦታዎች ነበሩ። ለምን ከጊዜ በኋላ ይሄን የማሳደጊያ ቤት ድርጊት አጋልጧል። ብዙ ህፃናትንም ከሰቆቃ ታድጓል።

ማንነትን ፍለጋማንነቱን የተቀማውና የተከዳው ሕፃን

በግራ መጋባትና ‹ከየት መጣሁ? ማን ነኝ?› ብሎ በሚጠይቅበት ወቅት ነበር በ18 ዓመቱ የልደት ሰርተፊኬቱን ማግኘት የቻለው። የምሥጢሩን ቁልፍ አገኘው። ምሥጢሩንም መፍታት ጀመረ። ‹ለምን ሲሳይ› የሚለውን የተቀማውን ሥሙን አገኘው። እንደ ልጅ መንፈሳዊና አካላዊ እንክብካቤን የተነፈገና በሕፃናት ማሳደጊያ በደል የተማረረው ለምን እምቢተኛ መሆን ጀምሮ ነበር። በስሜቱ፣ በመንፈሱና በአካሉ የደረሰበት በደል፣ መገፋት፣ መከዳትና

መጨቆን ለከፋ የመንፈስ ስብራት ዳርጎት እንደነበር ያስታውሳል። ካለበት የተዘበራረቀ ሁኔታ ለማምለጥና ማንነቱን ፈልጎ ለማግኝት በሕይወት ላይ ማመፅ ነበረበት። በበረዷማው የእንግሊዝ ጎዳና በባዶ እግሩ እስከመጓዝ ደርሶ ነበር።

የልደት ምሥክር ወረቀቱ የምሥጢር መፍቻ ቁልፍ የሰጠው ተስፋ ግን የተሰረቀ ሥሙን ብቻ ሳይሆን እናቱ ስለሱ የጻፈችውን ደብዳቤ መመልከት አስችሎት ነበር። “እባካችሁ ልጄን መልሱልኝ በባዕድ ምድር በመገለልና በዘረኝነት ሲሰቃይ ማየት አልፈልግም” በሚሉና ልብን በሚነኩ ቃላት የተሞላውን የእናቱን ደብዳቤ ሲመለከት፣ ለምን በድቅድቅ ጨለማ ብቅ ያለች የብርሃን ፍንጣቂ እንደበራችለት ነበር የቆጠረው። ባገኛቸው የተለያዩ ብጭቅጫቂ መረጃዎች እየተመራ ጋምቢያ /Gambia/ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት /UN/ የምትሠራ ኢትዮጵያዊት እናቱን አገኛት። ትልቅ እፎይታ፣ ተስፋና የማንነት ፍለጋው ጉዞ ቀና መንገድ መጀመሩ ነበር።

ጎዳናው ወደ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰተት አድርጎ አስገባው። በዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት አውሮፕላን የነበሩት አባቱ አቶ ግደይ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ1972 በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው አልፎ ነበር። ይሠሩበት ከነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሕይወት መዝገባቸው ተገላበጠ። ቤተሰቦቻቸው እዛው ቦሌ አካባቢ እንደሚኖሩ ተነገረው። የጠፋበትን ማንነቱን ማግኝቱን ቀጥሏል። እህቶቹን አገኘ። ስለ አባቱ ታላቅነት ሰማ። ፎቶዎቹን ተመለከተ። በመልክ እንደሚመስለው አየ። አውሮፕላኑ ተከስክሶ የወደቀበትን፤ አባቱ የሞተበትን ቦታ ተጉዞ ተመለከተ።… ወደ መንፈሱ፣ ወደ ማንነቱ፣ ወደ ኢትዮጵያዊነቱ ተመለሰ። በቢ.ቢ.ሲ. የተሰራው የሕይወቱን ውጣ ውረድ የገለጸበት ‹ኢንተርናል ፍላይት› /Internal Flight / የተባለውን ዘጋቢ ፊልም ለተመለከተ፣ የለምን የሕይወት ጉዞ ልቦለድ እንጂ በእውኑ ዓለም ያለ አይመስለውም።

ግጥምና ለምን ምንና ምን ናቸው?ግጥም ከላይ ከኣርያም የተቀበላት

ልጅነቱን፣ ሕይወቱን፣ ማንነቱን፣ ስሜቱን፣ ሰውነቱን ባጠቃላይ የሰው ልጆችን መስተጋብር በጥልቀት የሚዳስስበት፣ የሚገልጽበትና

ወደሚቀጥለው ገጽ

አንድ ሰው

ፎቶ: lemnsissay.com

Page 23: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

22 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

አንድ ሰው

ለዓለም የሚመሰክርበት ብርቱ መሣሪያው ነው። “ግጥም ጥልቅ የሆነው የውስጥ ድምፃችን ነው” ይላል ለምን ስለ ግጥም ሲናገር። “የምጽፈው ይሄን ድምፅ በመጠቀም በዙሪያየ ያለውን ዓለም ለመግለጽና ለመተንተን ነው” ይላል። እጅግ ውስብስብና አስጨናቂ የልጅነት ጊዜን ያሳለፈው ለምን ሲሳይ ገና በለጋ ዕድሜው ነበር ገጣሚ ለመሆን የበቃው። በ21 ዓመቱ እንደ ጎርጎሳውያን አቆጣጠር በ1988 ‹ቴንደር ፊንገርስ ኢን ኤ ክሌንችድ ፊስት› /Tender Fingers in a Clenched Fist / የተባለውን የመጀመሪያ መጽሐፍ ለማሳተም የበቃው ለምን ለግጥም የተፈጠረ፤ ያለፈበትን፤ የኖረበትን፤ የተረዳውንና ያሰበውን ድንቅ በሆነ መንገድ የሚቀኝ ገጣሚ ነው ይሉታል፤ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች። ስምንት የግጥም መጽሐፎችን፣ ሰባት ቲያትሮችን፣ አራት የቢ.ቢ.ሲ. ሬዲዩ ድራማዎችንና የተለያዩ ዶክሜንተሬዎችን ያበረከተ የዓለማችን ድንቅና ዘርፈ ብዙ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ ነው።

ግጥሞቹን በመድረክ ሲያነባቸው ለተመለከተ በተጻፉበት መንፈስና ስሜት ውስጥ ራስን ማግኘት አይቀሬ ነው። ግሩም በሆነ የትወና ጥበብ ወደ ታዳሚው ሲያፈሳቸው መሳጭነት ብቻ ሳይሆን ግጥሞቹ የተጻፉበትን ስሜት እና በሙሉ ነፍሱና ማንነቱ እንደሚገጥማቸው መረዳት ይቻላል። ለዚህም ይመስላል በግጥሞቹ ላይ ኺሳዊ ግምገማ የሚሰጡ ባለሙያዎች “የለምን የግጥሞቹ ርዕሶች ቃላዊና /Oral/ ትወናዊ /Performance/ ቃና አላቸው” የሚሉት።

“የምጽፈው ሳልጽፍ መኖር ስለማልችል ነው” የሚለው ለምን የሕይወቱ ጉዞ ግጥም እና ቤተሰቦቹን ለማግኘት የተጓዘበት መንገድ እንደሆነ ያስረዳል። በመገለል፣ በብቸኝነት፣ በዘረኝነትና ማንነትን በመፈለግ ሲንከራተት የልጅነት ሕይወቱን ላሳለፈው ለምን፣ ታላቋ ብሪታንያ የክብር ቦታ ሰጥታዋለች። የእንግሊዝ ጎዳናዎች የለምንን የግጥም ሥራዎች ባደባባዮቿ ሰቅላ ለሕዝብ ታስነብባለች። የ2012

“እባካችሁ ልጄን መልሱልኝ በባዕድ ምድር በመገለልና በዘረኝነት ሲሰቃይ ማየት አልፈልግም” በሚሉና

ልብን በሚነኩ ቃላት የተሞላውን የእናቱን ደብዳቤ ሲመለከት፣ ለምን በድቅድቅ ጨለማ ብቅ ያለች የብርሃን ፍንጣቂ እንደበራችለት ነበር የቆጠረው

የለንዶን ኦሎምፒክ ዋና ገጣሚ አድርጋዋለች። ማንችስተር ዩኒቨርስቲ ለማንም የማይቸረውን ‹ቻንስለርነት› ሾማዋለች። የክብር ዶክትሬትም ሰጥታዋለች። የታላቋ ብሪታንያ ከፍተኛ ማዕረግ /Most Excellent Order of the British Empire (OBE)/ የተባለውን ሽልማት ከንግሥት ኤልሳቤት እጅ ተቀብሏል። አዲስ አበባ ኮሞሮስ መንገድ በሚገኝው የብሪቲሽ ካውንስል ‹ሌት ዜር ቢ ፒስ› /Let There Be Peace/ የተባለው ተወዳጅ ግጥም ሕዳር፣

አንድ ሰው

ፎቶ: lemns

issa

y.co

m

Page 24: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

23ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

በብሔራዊ ቲያትር የግጥም ሥራዎቹን አቅርቦ ነበር። በዚህ ዝግጅት ላይ ‹ጎልድ ፍሮም ዘ ስቶን› /Gold From The Stone/ እና ስለ ታላቁ የአድዋ ጦርነት የሚያወሳው ‹ዘ ባትል ኦፍ አድዋ› /The Battle Of Adwa/ የተባሉ ግጥሞቹን አቅርቦ ነበር።

በወቅቱ ለምን ሲሳይ ከአሜሪካ ሬዲዩ የአማርኛው ክፍል ጋር ባደረገው ቆይታ ሲናገር “‹ጎልድ ፍሮም ዘ ስቶን› /Gold From The Stone/ የተባለው ግጥም በሕይወቴ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። ገና ወላጆቼን፣ እናትና አባቴን፣ እህትና ወንድሞቼን፣ ባጠቃላይ ዘመዶቼን ፍለጋ ላይ በነበርኩበት በ20ዎቹ መጀመሪያ ከዚህች እንግሊዝ ከተባለች በውኃ ከተከበበች ትንሽ ሀገር ተነስቼ ዓለምን ማሰስ በያዝኩበት ዘመን የገጠምኩት ግጥም ስለሆነ ነው” ይልና፣ “ግጥሙ ሙሉውን ስለ እውነትና ስለ ማንነት የሚያወራ ነው” በማለት ግጥሙን እህቱና ሌሎች ቤተሰቦቹ በተገኙበት ማንበቡ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ይናገራል።

ስለ አድዋ ጦርነት የሚያወሳውን ግጥሙን በተመለከተ ሲናገር “ግጥሙ ከደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ የዘር መድሎ ማብቂያና የአድዋን ጦርነት በአፍሪካ ከቅኝ ግዛት አገዛዝ ፍፃሜ መጀመሪያ ጋር አዛምደው ከሚያጤኑት ማንዴላ ጋር ይቆራኛል” ይላል። “የግጥም ንባቤን ስለጦርነት ታሪክ በሚተርክ ጀምሬ አላውቅም። ይሁንና የአፍሪካ ኅብረት ሲከበር የአፍሪካ አንድነት ራሱ የነጻነት መሠረት መሆኑ እንደ ሌላው ነገር ሁሉ ጦርነትም የታሪካችን አካል በመሆኑ ነው። ማንነታችን በዚህ ብቻ አለመወሰኑ እንደ ገጣሚ ከሁሉ በላይ አስፈላጊው ነገር ነው።” በማለት ስለግጥሙ ይዘትና ዐውድ ይናገራል።

ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን በስፋት የሚጠቀመው ለምን ‹የማለዳ ትዊት› /Morning Tweet/ ብሎ በሚጠራው ልምዱ በየቀኑ የሚደንቁ ስንኞችን በትዊተርና ፌስቡክ ገጾቹ ለዓለም ያካፍላል። ለምን ሲሳይ በግጥሞቹ የሚያነሳቸው ርዕሰ ጉዳዩች ዓይነት፣ ጥልቀትና ስፋት ታላቅ ባለቅኔነቱን ይመሰክራሉ። እውነትን፣ ፍትሕን፣ ፍቅርን፣ ጭቆናን፣ የዘር መድሎን፣ ሐዘንን፣ ብቸኝነትን፣ ጦርነትን፣ ሠላምን፣ ቤተሰብን፣ ታሪክን፣ ማንነትን፣… በግጥሞቹ በመዳሰስ በመላው ዓለም ታላቅ ባለቅኔነቱን አስመስክሯል። እጅግ መሳጭ ከሆነው የሕይወቱ ጉዞ፣ የልጅነት ጊዜው፣ የቤተሰብና የማንነት ፍለጋው የሚቀዱት ቅኔዎቹ ሰብኣዊነቱን በጉልሕ ይመሰክራሉ። ታሪኩንና የሕይወቱን ጉዞ ሲተርክ ለደከሙ ጉልበትን፣ ላዘኑ መጽናናትን፣ ተስፋ ለቆረጡ መነቃቃትን የሚሰጥ ዓለምን በበጎ መመልከት የሚያስችል ስሜትን የሚፈጥር ነው። ነፍሱ ለሰው ልጆች እና ሰብኣዊነት ግድ የሚላት፣ የምትሳሳና የምትቃትት ናት። ባለቅኔው ለምን ሲሳይ።

መብራቱ በላቸውን በኢሜይል አድራሻው [email protected] ሊያገኙት ይችላሉ።

2008 በሐውልት ተቀርፆ ለተመልካች ክፍት ተደርጓል።

ዶ/ር ጄምስ ፕሮክተር እንደ ጎርጎሳውያን አቆጣጠር በ2009 በብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገጽ ላይ ስለ ለምን ሥራዎች ባሰፈሩት ሒሳዊ ትንታኔ ላይ ‹ሊስነር› /Listener/ ከሚለው እንደ ጎርጎሳውያን አቆጣጠር በ2008 ከታተመው መድብል ውስጥ ‹ቢፎር ዊ ጌት ኢንቱ ዚስ› /Before We Get Into This/ የሚለውን ግጥም በመጥቀስ ሲናገሩ “የልጅነት ፍቅር መቀማትንና የጉዲፈቻን አሰቃቂ ሕይወት ስሜት በሚነካና ጥልቀት ባለው መልኩ የገለጸበት፣ የሕዝብንና የግለሰብን ጉዳዩች ያገናኝበት ድንቅ ሥራ” ብለውታል::

“ሀሪ ፖተር፣ ሱፐር ማን፣ ሊዝቤት ስላንደር፣ ባት ማን፣ ሙሴ፣ ኦሊቨር ትዊስት እና ሌሎችም በታላላቅ ዘመን አይሽሬ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች የተጠቀሱ ዋና ገጸ ባሕሪያት ከወላጆቻቸው ተነጥለው ያደጉ ናቸው” የሚለው ለምን ሲሳይ “ደራሲዎች ከወላጆቻቸው ተነጥለው የሚያድጉ ልጆች፣ ቤተሰብ ለምንለው ተቋም መገለጫዎች ናቸው” በማለት በጉዲፈቻ የሚያድጉ ልጆች የአንድ ማኅበረሰብ፣ ቤተሰብ ባጠቃላይ የሰው ልጆች አንድ አካል መሆናቸውን ብሎም ታላላቅ ስብዕና ያላቸው ሰዎች የሚገኙበት መሆኑን በሥራዎቹና ባገኝው አጋጣሚ ሁሉ በማስገንዘብ በጉዲፈቻና በሕፃናት ማሳደጊያ የሚያድጉ ልጆች ጉዳይ ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ ታግሏል። ባጠቃላይ በሥራዎቹ ዘረኝነትን ተቃውሟል፤ የጉዲፈቻ በደሎችን አጋልጧል፤ ስለ ሠላም ዘምሯል፤ ስለፍቅር ሰብኳል፤ ስለ ብቸኝነት ተናግሯል፤ ዓለምን ዞሯል፤ የኦሎምፒክ አደባባዮችን ጨምሮ በታላላቅ አደባባዮች ድምፆቹን ከፍ አድርጎ በግጥም እንደሚባለው “ምላጭ ሲያብጥ፤ ውኃ ሲያንቅ” በሚያሳዩ ግጥሞቹ ዓለምን አስደምሟል።

የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ግጥምን ከሚመዝኑበት መንገድ አንዱና ዋነኛው የቃላት አጠቃቀሙና ጉልበቱ በግጥሙ ውስጥ ያለውን ኃይል በማየት ነው። ግጥም በተመጠኑ ቃላት የታመቀ ሐሳብ የሚገለጽበት የበለፀገ የፈጠራ ሥራ ነው። ዶ/ር ዮናስ አድማሱ በ2006 በታተመው ‹ጉራማይሌ› በሚለው መድብላቸው መግቢያ ቃላት በግጥም ውስጥ ስላላቸው ኃይል ሲናገሩ “…ቃላት ልዩ ኃይል አላቸው። የሚያውቁትን እንግዳ፣ አሮጌውን አዲስ ያደርጋሉ። የተበታተነውን ይሰበስባሉ፣ በበድኑም የሞቀ እስትንፋስን ለቅቀው ነፍስ ይዘራሉ፣ እንደ ሁኔታውም ዘላለማዊ ሕይወትን ያጎናፅፋሉ፤ ወይም እመቀ እመቃት ያወርዳሉ። በሥነ ጽሑፍ ዓለም ቃላት ሁሉን ቻይና ሁሉን አድራጊ ናቸው፤ በዚህ ልዩ ዓለም አልፋና ኦሜጋው እነሱው ናቸው…።” ይላሉ። ባለሙያዎችም የለምንን ሥራዎች የቃላት ጉልበት፤ የሐሳብ ምጥቀትና ጥልቀት ሲገልጹ “የቃላቱ ሁሉን ቻይነት፤ የምፀቱ ጉልበት፤ የአገላለጹ ኃያልነት የግጥሞቹን ዘላለማዊነት ይናገራሉ” ይላሉ።

‹ላንግስተን ሁውስ› /Langston Hughes/

በቀደሙት ዘመናት በአሜሪካን ሀገር የኖረ ጥቁር ገጣሚ፣ ማኅበራዊ አቀንቃኝ፣ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔትና የፖየቲክ ጃዝ ፈጣሪ፣ በግጥም ሥራዎች ላይ ተፅዕኖ እንዳሳረፈበት ለምን ሲሳይ ይናገራል። ነገር ግን ለምን ራሱን ከማንም ጋር ማወዳደር እንደማይፈልግና ወደላይ ወደ ከፍታው መውጣት ብቻ እንደሚፈልግ ይናገራል። ዝነኛ አባባልም አለው “ከዛፉ ጫፍ ብትወጣ የዛፉን ቅርንጫፎች ታገኛለህ። ከከዋክብቶቹ ላይ ብትወጣ ግን ዛፉን ታገኝዋለህ” የሚል።

እንደማሳረጊያበ2013 እንደ ጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር

በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ሲከበር ለምን ሲሳይ ከሌሎች ወጣት ገጣምያን በዕውቀቱ ሥዩምና ኤፍሬም እንዳለ ጋር በመሆን

ለምን ለግጥም የተፈጠረ፤ ያለፈበትን፤ የኖረበትን፤ የተረዳውንና ያሰበውን

ድንቅ በሆነ መንገድ የሚቀኝ ገጣሚ ነው

ይሉታል፤ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች። ስምንት የግጥም መጽሐፎችን፣

ሰባት ቲያትሮችን፣ አራት የቢ.ቢ.ሲ. ሬዲዩ

ድራማዎችንና የተለያዩ ዶክሜንተሬዎችን

ያበረከተ የዓለማችን ድንቅና ዘርፈ ብዙ የሥነ

ጽሑፍ ባለሙያ ነው

አንድ ሰው

Page 25: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

24 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ምስሎቻቸው በፊት ገጽ ከተገጠገጠ መጽሔት ወይም ጋዜጣ ለማሻሻጥ ይረዳሉ ተብሎ በግሉ ሚዲያ ከሚታመንባቸው ሰዎች አንዱ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ናቸው። በግሉ ሚዲያ ዘንድ የፕሮፌሰር መስፍን ስድብና ዘለፋ (በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጨምሮ) ለንባብ ማብቃት ትርፍ ያስገኛል፣ ገበያ ያደራል ተብሎ በይፋ የሚነገር ሲሆን ፕሮፌሰሩ ለምን ይሳደባሉ ብሎ ትችት ወይም ተቃውሞ አዘል ጽሑፍን ለግሉ ሚዲያ መላክ ደግሞ ገበያ ያሳጣናል ተብሎ ጽሑፉ ወደ ቅርጫት ይወረወራል። ለዚህ ይመስላል ‘ውይይት’ መጽሔት በመጀመሪያ እትሟ ለፕሮፌሰሩ በተዥጎደጎደ ልክ የሌለው ውዳሴ ታጅላ ብቅ ማለቱን የመረጠችው። እርግጥ ነው ‹ውይይት› መጽሔት ፕሮፌሰሩን ፍፁም ታጋይ አስመስላ ያቀረበቻቸው አንዳንድ ጋዜጦችና መጽሔቶች እጥፍ ባሉበት የአድርባይነት ጎዳና እስክትታጠፍ ‘የተቃውሞ ድምፅ’ መስላ ለመታየት ነው የሚሉ ሰዎችም አልታጡም። ይህን መሰል ሐሳብ የሰነዘሩ ሰዎች መጽሔቷ የገዥው ቡድን ቀንደኛ ደጋፊ የነበሩ ሰዎችን በጦማሪያኑ ካባነት ሸፍና ይዛለች የሚል ሐሳብ ስላላቸው ነው። ሁሉንም ጊዜ ይገልጠዋል።

ያም ሆነ ይህ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እውነተኛ ተፅዕኖ አሳዳሪ ሰው ናቸው ወይስ የመጽሔትና የጋዜጣ ማሻሻጫ ሰው? የሚለውን ጉዳይ በጥልቀት ማየት ይገባል።

ፕ/ር መስፍን እውነት ተፅዕኖ አሳዳሪ ናቸው?

የጃንሆይን እና የደርግን ዘመን እንተወውና ይኸኛው የሕ.ወ.ሓ.ት. መራሹ አገዛዝ ዘመን ፕሮፌሰር መስፍን ከመደበኛ ሥራቸው ወጣ ብለው የጎላ ቁም ነገር የሠሩበት ጊዜ ነበረ ማለት ይቻላል። እሱም የቀደሞውን ኢ.ሰ.መ.ጉ.ን (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን) በኋላም ሰ.መ.ጉ. (የሰብኣዊ መብቶች ጉባኤን) መሥርተው በመሪነት በቆዩባቸው ጊዜያት የፈፀሟቸውን ተግባራት የሚያጠቃልል ነው። ፕሮፌሰር መስፍን ኢ.ሰ.መ.ጉ.ን ‹ወያኔ› ሳይሆን ኢትዮጵያውያን አክሽፈውታል ቢሉም ይኸ ሥራ ከእሳቸው ታሪክ ውስጥ ዓብይ ሥፍራ የሚይዝ መሆኑን መካድ አይቻልም። ኢ.ሰ.መ.ጉ. ሲመሠረት በአገር ቤት 120 ብር እና ከዚያ

በላይ ገንዘብ ማዋጣት የሚችሉ አንድ መቶ ሺሕ አባላትን ለማሰባሰበ ታቅዶ 150 የሚሞሉ ማግኘት እንዳልተቻለ፣ በውጭ ደግሞ 500 ብር ማዋጣት የሚችሉ አንድ ሺሕ አባላት ለማሰባሰብ ታቅዶ መቶ ያልሞሉ አባላት ብቻ መገኘታቸውን በመግለጽ ኢ.ሰ.መ.ጉ. መክሸፉን ተናግረዋል። ይኸ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ያስነሳል። ኢ.ሰ.መ.ጉ. እንዲህ በአባላትና በገቢ ድርቅ የተመታ ከሆነ ፕሮፌሰሩ ተፅዕኖ አሳዳሪ ነበሩ ማለት ይቻላል? የፕሮፌሰሩ የሰብኣዊ መብቶች ጠበቃ ፊታውራሪ መባልስ በጣም የበዛ ሹመት አይሆንምን?

የግሉ ሚዲያ በአውራና በጀሌ ግለሰቦች በጭፍን መነዳት ስለሚፍገመገም በአንድ በኩል ኢትዮጵያ አልቆላታል ብለው ተስፋ ቆርጠው ተስፋ ለማስቆረጥ አደግድገው በተነሱ ወገኖች እየተሞላ መሆኑ ይፋ እየሆነ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ አውራዎችና ጀሌዎች ራሳቸውን በመታገል ላይ እንዳሉ ጀግኖች ቆጥረው ትግላቸው ያልተሳካው ሕዝብ ስለፈራና ስላንቀላፋ እነሱን መከተል ሳይችል በመቅረቱ መሆኑን እያወሩ ነው። ለነዚህ ታጋይና ጀግኖች ነን ባይ ግለሰቦች አውሮፓና አሜሪካ ሄዶ ማውራትም ትግል ሜዳ ውስጥ እንደ መግባት ተደርጎ እየተቆጠረ ነው። ይህ ዝቅጠት ነው።

ፕሮፌሰር መስፍንን የመሳሰሉ ሰዎች ለዚህ መሰሉ ዝቅጠት ዋና ተጠያቂዎች መሆናቸው የሚታበል አይደለም። ፕሮፌሰር መስፍን በሚጽፉትና በሚናገሩት ነገር ብቻ ሳይሆን በይፋ በተቀላቀሏቸው የፖለቲካ ድኖች ውስጥ በነበሩበት ወቅት እና ከፖለቲካ ውጭ ነኝ ብለው በተቀመጡበት ጊዜ ሁሉ በሠሩት የመሰሪነት ሥራ ለኢትዮጵያ የተቃውሞ ጎራ መድከምና መውደም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

የፓንክረስት ቤተሰብ እና የፕ/ር መስፍን ቤተሰብ

ስለ ሪታ ፓንክረስት፣ ስለ ልጃቸው ሪቻርድ ፓንክረስትና ስለ ልጅ ልጃቸው አሉላ ፓንክረስት የኢትዮጵያዊ ፍቅር ማሰብ ብቻውን ስለፕሮፌሰር መስፍን ብዙ ነገር ለማወቅ ይረዳል። ለአያትነት የበቁት ፕሮፌስር መስፍን ከልጆቻቸውና ከልጅ ልጆቻቸው ስንቶቹን ነው ኢትዮጵያዊ አድርገው ያሳደጉት? ሪታ ፓንክረስት፣ በልጅ እና በልጅ ልጅ ኢትዮጵያን በችግሯ ጊዜ ለመርዳት ከጎኗ

ሆነው ደፋ ቀና ብለዋል። ሪታ ፓንክረስት በልጅ እና በልጅ ልጅ ፖለቲካንና ስርዓትን ሰበብ ሳያደርጉ በመከራዋ ጊዙ ሁሉ ከኢትዮጵያ ጎን ቆመዋል፣ ለነጩ ጣሊያን አድርባይ ሳይሆኑ ወይም በዘረኛነት (በነጭ ወገንተኝነት) ሳይሸነፉ ለኢትዮጵያ ተሟግተዋል። የፕሮፌሰር መስፍን ልጆችና የልጅ ልጆችስ አሁን የት ነው ያሉት? ኢትዮጵያችን ከዚህ የከፋ ችግር ውስጥ ብትገባስ የፕሮፌሰሩ ልጆችና የልጅ ልጆች ከወገኖቻቸው ጎን ሆነው ደፋ ቀና ለማለት ተኮትኩተው ያደጉ ናቸውን?

ቁጥር አንድ ውይይት መጽሔት ፕሮፌሰሩን ላለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት የሳቸውን ያህል የታገለ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ በሕሊና ቢስነትና በጭፍን አጎብዳጅነት ተናግራለች። ባለፉት 50 ዓመታት በመጻፍና በመናገር ሳይሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የተሰዉ፣ የተጎሳቆሉ፣ የተጋዙ፣ እስከ አሁንም ጉልህ ተግባራዊ ሥራ በመሥራት ላይ ያሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ለውይይት መጽሔት ሰዎች እንዴት ተሰወረ? ለመሆኑ ከዶክተር መረራ ጉዲና እና ከፕሮፌሰሩ ማንኛቸው ናቸው በጽናትና በዓላማ በመታገል ዘመኑን የቆጠሩት? ማንስ ነው አወራሁ፣ ጻፍኩ እያለ ራሱን ያኮፈሰ?

ለኢትዮጵያ እቆረቆራለሁ የሚሉት ፕ/ር መስፍን በኃይለሥላሴ ጊዜ፣ በደርግ ጊዜ፣ በዚህ ዘመንም ብዙ ነገሮችን ‘ተናግሬ ነበር፤ ጽፌ ነበር’ በማለት ይናገራሉ። መጻፍም፣ መናገርም አንድ ነገር ነው፤ ጥሩ ነገር ነው። ነገር ግን መጻፍና መናገር ሁሉም ነገር ነው ማለት አይደለም።… በነዚህ ሦስት ስርዓቶች ውስጥ ስርዐቱን በማውገዝ የጻፉና የተናገሩ ፕሮፌሰሩ ብቻ አይደሉም። ከመሥሪያ ቤቶችና ከቀበሌ ስበሰባዎች ጀምሮ በጎ ነገርን የተናገሩና በጽሑፍ ያሳወቁ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸው የሚያጠራጥር አይደለም። ስለዚህ እኔ ጽፌ ነበር፣ ተናግሬ ነበር ተብሎ ሕዝቡ ዝም አለ ብሎ ሳያሰልሱ መዝለፍና መተቸት ተገቢ አይደለም።

ፕሮፌሰር መስፍን እሳቸው መጻፍና ማናገርን አቅማቸው የሚፈቅደው ሥራ አድርገው አይተው ኃላፊነታቸውን እንደተወጡ አድርገው እንደሚቆጥሩት ሁሉ ሌላውም የአቅሙን በማድረጉ ማክበሩን መርሳት የለባቸውም። እሳቸው ከመጻፍና ከመናገር አልፈው አለመሄዳቸውን የፍርሐት ወይም እየበሉ ለመኖር (ለሆዳምነት) ሲባል የተደረገ ሽሽት አድርገው እንዳላዩት ሁሉ ሌላውም አቅሙ እና ወቅቱ ከሚፈቅድለት መሥመር አልፎ ስላልሄደ ብቻ ሆዳም፣ ለማኝ፣ ጠማማ ወዘተ. እየተባለ መዘለፍ እንደማይገባው ሊረሱት አይገባም።

ፕሮፌሰሩ እና ቅንጅትፕሮፌሰር መስፍን ኢ.ሰ.መ.ጉ.ን

ጥለው በመውጣት ቅንጅትን መቀላቀላቸው ይታወሳል። ነገር ግን ፕሮፌሰሩ ተቀምጠው

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምተፅዕኖ አድራሽ ወይስ ዴሞክራሲ ደምሳሽ?

አንድ ሰው

‹ውይይት› መጽሔት በ1ኛ ዓመት፣ ቁጥር 1 እትሟ ‹ኩሩው ፕሮፌሰር እና እሳቤዎቻቸው› በሚል ርዕስ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ንግግሮች እና ሌሎችም ስለእርሳቸው ከተናገሩት የተቀዱ ሐሳቦችን ይዛ መውጣቷ ይታወሳል። አቶ ግዛቸው አበበ በላኩልን ጽሑፍ መጽሔቷ ይዛው የወጣችው ጽሑፍ ‹ለከት የሌለው› እና ‹ገበያ ለማግኘት የተደረገ ሙከራ› ነው በማለት አብጠልጥለውታል። ጽሑፋቸውን ከቦታ ጥበት አንጻር ከመጠነኛ አርትኦት ጋር እንደሚከተለው አትመነዋል።

Page 26: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

25ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ሲያዩት እንደመሰላቸው ፖለቲካው ቀላል እና ምቹ አልሆነላቸውም። በወራት ዕድሜ ውስጥ መጋቢት 29/1997 ዓም ላይ ‘…በሰኔ ተጠያቂነት ይመጣል… ሕዝብም ዝም ብሎ አያየንም… ከዚህ ቀን ጀምሮ በመካከላችሁ አልገኝም…’ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ከቅንጅት ሸሽተዋል። የደብዳቤው ግልባጭ ‘ቅንጅት ከየት ወዴት በተባለው መጽሐፍ ላይ ይገኛል። ፕሮፌሰር መስፍን በዚህ ዓይነት ምርጫ 1997 ከመምጣቱ በፊት ከቅንጅት አባልነታቸው ቢሰናበቱም የፈሩት አልቀረላቸውም። እሳቸውም በምርጫም አለመሳተፋቸውን አስታውሰው አመራር ተብለው ከመታሰር አለማምለጣቸውን በቁጭት ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ተረትና ምሳሌ አይወዱም እንጅ ‘ቀድሞ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ…’ የሚባለው እንደዚህ ማስተዋል ለሚጠይቅ ነገርን በሚመለከት አለመቸኮልን ለማሳሰብ መሆኑ ይታወቃል (ኢትዮ ምኅዳር ጋዜጣ፤ ሐምሌ 18/2007)።

ኢ.ሕ.አ.ፓ.ዎችንና የደርግ ተቃዋሚዎችንና የሚያንኳስሱት ፕሮፌሰር መስፍን እሳቸው ተቃዋሚ ሆነው ለወራት ዕድሜ መቆየት ፈተና ሆኖባቸው በደብዳቤ ተሰናብተዋል። ኢ.ሰ.መ.ጉ.ን ጥለው ወደ ፖለቲካ የገቡት ፕሮፌሰር መስፍን ስሜታዊ ሰው እንጅ ፅኑ አቋም ያላቸው ታጋይ ሆነው አልታዩም።

ላለፉት 50 ዓመታት ተወዳዳሪ የሌላቸው ታጋይ ተደርገው በውይይት መጽሔት የተካቡት ፕሮፌሰር መስፍን በቅንጅት ውስጥ የነበራቸው ቆይታ ከሴራ መጎንጎን ያልተለየ መሆኑን አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች ይናገራሉ። በቅንጅት ስብሰባዎች ላይ በይፋ ሊመከርበት የሚገባውን ነገር ወደ ቤታቸው እየወሰዱና የተወሰኑ ሰዎችን እየጠሩ ከመጋረጃ ጀርባ ሴራ ይጎነጉኑ ነበረ። ፕሮፌሰር መስፍን አቶ ልደቱ አያሌውን ለጋ እና ተሞክሮ የሌለው ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን በዕድሜውም ወጣት በነበረበት ጊዜ ከመላው አማራ ሕዝባዊ ድርጅት (መ.አ.ሕ.ድ.) ውስጥ እያለ የጀመሩትን የማዳፈን ሥራ ቅንጅት ውስጥም ደግመውታል። ከዚያም ዘወር ብለው ‘…ቅንጅት ውስጥ ገና ከመጀመሪያው ራሳቸውን ከፍ ከፍ አድርገው ለማሳየት የሚፈልጉ ለሥልጣን የሚስገበገቡ ግለሰቦች መታየታቸውና ለድርጅቱ ሳንካ መሆናቸውን በመጨረሻም ድጅቱን መናዳቸውን…’ የገለጹት ፕሮፌሰሩ ከነዚህ ሰዎች አንዱ አቶ ልደቱ አያሌው መሆናቸውን ነግረውናል። ሰው የዘራውን ያጭዳልና ፕሮፌሰር መስፍን በየጊዜው ወደ ቤታቸው እየጠሩ የተለየ ሴራ ለማራመድ ሲጠቀሙባቸው ከነበሩት ከአቶ ልደቱ አያሌው ከዚህ የተለየ ምን ቁም ነገር እንደሚጠብቁ ግልጽ ባይሆንም እሳቸው ራሳቸው ዞረው አቶ ልደቱን ወንጃይ ሆነው መገኘታቸው ደግሞ በጣም አስገራሚ ነው (ቅንጅት ከየት ወዴት? ገጽ 82-84፤ አገቱኒ፡ ገጽ 14)።

ፕሮፌሰሩ እና የፓርቲ ፖለቲካፕሮፌሰር መስፍን የጓዳ ሴራ የጀመሩት

መ.አ.ሕ.ድ. በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አማካኝነት በተመሠረተ ማግስት መሆኑን

ልብ ማለት እና ለምን ብሎ መጠየቅ ይገባል። ‹ቅናት ነው ወይስ ምቀኝነት?› በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ አንዳንድ ጠባብ ቡድኖችና ግለሰቦች አማራውን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጀው በየተገኘበት ጥቃት ሲፈፅሙበት አማራውን ከዚህ ግፍ ለመታደግ በሚል በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተጀመረ ስብስብ ወደ ፖለቲካ ቡድን ተቀይሮ ‘የመላ አማራ ሕዝቦች ድርጅት’ (መ.አ.ሕ.ድ.) የተባለ ፓርቲ መፈጠሩ ይታወቃል። ይህ ፓርቲ ገና ከመፈጠሩ ችግሮች የገጠሙት ከገዥው በድን ብቻ አልነበረም። አማራ የሚባል ሕዝብ የለም የሚሉት፣ በዚያን ጊዜ ከፖለቲካ ውጭ ነኝ፣ የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ነኝ ይሉ የነበሩት ፕሮፌሰር መፍስን ወልደማርያም እና እሳቸውን የመሳሰሉ ሰዎችም በመ.አ.ሕ.ድ. ላይ በጠላትነት ተሰልፈውበት ነበረ። ፕሮፌሰር መስፍን በግል ቤታቸው እነ ልደቱ አያሌውን እየጠሩ መ.አ.ሕ.ድ. ይናድ ዘንድ ትልቅ ሴራ ጎንጉነዋል። ሴራቸው ተሳክቶም አቶ ልደቱ አያሌው በመ.አ.ሕ.ድ. የአዲስ አበባ መዋቅር ውስጥ ከነበሩት ወጣቶች ብዙዎቹን ይዞ እንዲወጣና ‘የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ’ (ኢ.ዴ.ፓ.) የተባለው ፓርቲ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል። ይህ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሴራ በአብዛኛው በወጣት ተገንብቶ ለነበረው ለመ.አ.ሕ.ድ. ቀላል ምት አልነበረም (አገቱኒ፤ ገጽ 52)።

እንግዲህ ይህ ሁሉ እያለ ነው ፕሮፌሰሩ ‘የተጣመመው እንዲቃና’ ያለመሰልቸው የሠሩ ተደርገው በውይይት መጽሔት ቁጥር አንድ ላይ የተወደሱት። ይኸ ሁሉ ነው በመጽሔቷ ላይ ‘ፍየል ከመድረሷን’ ለመተረት የሚያነሳሰው።

በፖለቲካ ድርጅች ውስጥ ዋና አባል ሆኖ ለመንቀሳቀስ ፖለቲከኛ መሆንን የግድ ይላል። ፕሮፌሰር መስፍን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በመሳሰሉ አገራት ውስጥ ‘ፖለቲካ የለም’ የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል (ሕይወቴ እና የፖለቲካ እርምጃዬ፣ ኃይሉ ሻወል፤ ገጽ 86፤ ቅንጅት ከየት ወዴት? ገጽ 11)። ይህ አቋማቸው ኢ.ሰ.መ.ጉ.ን ጥለው ወጥተው ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ የገቡበትን ምክንያት ግራ አጋቢ እንዲሆን ያደርጋል። ፕሮፌሰር መስፍን የለም በሚሉት የፖለቲካ ባሕር ውስጥ ለመዋኘት መሞከር ውኃ በሌለው የመዋኛ ገንዳ በጭንቅላት ሶቶ (dive) ከመግባት ጋር የሚመሳሰል ነው።

ፖለቲካ የለም እያሉ ፖለቲከኛ በመሆን ግራ የሚያጋቡት ፕሮፌሰር መስፍን አትንኩኝ ባይ ሰው በመሆናቸው ከዲሞክራሲያዊ ባሕሪ ጋር አብረው ለመጓዝ ሲቸገሩ በተደጋጋሚ ታይቷል። በፖለቲካ ቡድኖች ላይ ሴራ የሚጎነጉኑት ‘እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ’ ከሚል መንፈስ ብቻ ሳይሆን ወደ አምባገነነንት ካዘነበለ ባሕሪያቸውም ከሚመነጭ ጎልቶ ለመታየት የመፈለግ ባሕሪያቸው ነው።

ሲሳተፉበት በነበረው አንድነት ይባል በነበረው የተቃውሞ ቡድን ውስጥ በተፈጠረ የሐሳብ ልዩነት ምክንያት ፓርቲው ስብሰባ ሲያካሂድ በቦታው ተገኝተው ከመሟገት ወይም ራሳቸውን ከስብሰባው አግልለው የሌሎችን የመሰብሰብ መብት ከማክበር ይልቅ ኢ.ቲ.ቪ.ን እና ፖሊስ አስከትለው ስብሰባው ወደሚካሄድበት ወደ ግዮን ሆቴል በመሄድ ስብሰባውን በኃይል

ማስበተናቸው የአንድ ቀን የኢ.ቲ.ቪ. የዜና ክፍል ሆኖ ታይቷል። ፕሮፌሰሩ ፖሊስ ጠርተው፣ ፖሊስ ኢ.ቲ.ቪ.ን ጠርቶ ይሁን፤ ፕሮፌሰሩ ኢ.ቲ.ቪ.ን ጠርተው፣ ኢ.ቲ.ቪ. ደግሞ ፖሊስ ጠርቶ የታወቀ ነገር የለም። ፕሮፌሰሩ አይነኬ ናቸው፤ እና ይህን በሚመለከት ብዙ ሲጻፍና እሳቸውም ሲጠየቁ አላየንም፤ አልሰማንም።

መተቸት እና ‘መትተቸት’ፕሮፌሰር መስፍን እሳቸው በማንም

ላይ የፈለጉትን ሁሉ እንደሚጽፉትና እንዳሻቸው እንደሚናገሩት ሌላውን በልበ ሰፊነት ለማስተናገድ ትዕግስት ያላቸው ሰው አይደሉም። ውዳሴና ማንቆለጳጰስ እየታከለባቸው ጥያቄዎች የማይደረደሩባቸውን ቃለ ምልልሶች አይቋቋሙም። በድክመታቸው ላይ ወይም በአንዳንድ አጠያያቂ አቋማቸው ላይ ያነጣጠሩ ቃለ ምልልሶች በቁጣ ተጀምረው ሳይቋጩ ሲቀሩ ታይተዋል። ፕሮፌሰር መስፍን ከመጽሐፎቻቸው ውስጥ በአንደኛው ላይ ‘ብታነቡት ይሻላል’ ብለው ያገለሏቸው ሰዎቸ አሉ። ይህ አባባል ፕሮፌሰሩ የእሳቸውን ሐሳብ የሚቃወሙ ሰዎችን ትችት ለመሸሽ መላ የዘየዱ ያስመስላቸዋል። ሞጋች ጥያቄዎች ይዞ ቃለ ምልልስ ሊያደርግላቸው የሞከረ አንድ ጋዜጠኛ ‘ቆጣ ብለው መለሱ… በሐሳብ መግባባት ባለመቻላችን ጥያቄዎቼን ሳልጨርስ ተለያይተናል’ ብሎ ጽፏል (ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? ገጽ 15)።

የፕሮፌሰሩ ዘለፋ እና የመክሸፍና የመፍረስ መርዶ በርካታ ተቃውሞዎችን መቀስቀሱ ይታወቃል። ፕሮፌሰር መስፍን ‘ለምን?’ ብለው የጠየቁ ሰዎችን እና ዘለፋውን አስመልክተው ትችታቸውን የሰነዘሩ ሰዎችንም መልሰው ለማዋረድ ሲሞክሩ ይስተዋላሉ። አስተያየት የሰጧቸውን የሚያውቋቸውንም ሆነ የማያወቋቸውን ሰዎች ሁሉ ‘…አንጎላችሁ በጭቃ የተሞላ ነው፤ ይህንን ጭቃ ዝቃችሁ ለጠፋችሁብኝ…’ ብለው ለማዋረድ ሞክረዋል (ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? ገጽ 19)። ፕሮፌሰሩ ‘የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ’፣ ‘ሐበሻው ሁሉ’ እያሉ በጅምላ ከሚሰነዝሩት ስድብና ዘለፋ የከፋ ‘ጭቃ’ ይኖር ይሆን?

ውይይት መጽሔት ዓይኗን በጨው አጥባ ፕሮፌሰሩ የሰው ትችት የማይቀበሉት የተችዎች የልኅቀት ደረጃ ከፕሮፌሰሩ የልኅቀት ደረጃ ጋር ስለማይመጣጠን ነው የሚል ሐሳብ አንፀባርቃለች። እያነጋገረ ያለው ነገር ፕሮፌሰሩ በመጽሔትና በመጽሐፋቸው ላይ ስድብና ዘለፋ፣ በአገርና በታሪክ ላይ ክሽፈትንና ውድቀትን ስለሚያሟርቱ እንጅ የሮኬት መሥራትን ወይም የኅዋ ምርምርን የሚመለከት አይደለምና መጽሔቷ በልኅቀት መቀለድ አይገባትም። ጎዳና ላይ ቆሞ አላፊ አግዳሚውንና የሚያውቀውንና የማያውቀውን ሁሉ በጅምላ የሚዘልፍ ጤነኛ አይደለምና ‘ሕዝብ ሁሉ’ ወይም ‘ሐበሻው ሁሉ’ እያሉ መዝለፍም ወፈፌነትን እንጅ ልኅቀትን አያሳይም።

አንድ ሰው

አቶ ግዛቸው አበበ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ይገኛሉ።

Page 27: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

26 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ትኩሳት

“ለለውጥ መላ የሌለው መንግሥት ራሱንም የሚያድንበት መላ አይኖረውም።” ኤድመንድ በርክ

ለመሆኑ ወቅቱ ስለአገራችን ነባራዊና መፃኢ ዕጣ ከምርና በቅን ልቡና የምንወያይበት አይደለምን? የሰፈነው የፖለቲካ ድባብስ ምን ያህል ይፈቅድልናል? ወይስ እንደ አንዳንዶች የውይይት ጊዜ አልፎበታል? በግንቦት 19 ቀን በ‹ካፒታል ሆቴል› ስለፌዴራሊዝም በተደረገ ጉባኤ ላይ ተገኝቼ ነበር። አንድ ምሁር፣ ‹በግንቦት ሃያ ዋዜማ የዘውግ አወቃቀራችንን ትክክለኝነት የሚያረጋግጠው በአገራችን ሠላም ማስፈኑ ነው› ሲሉ ብሰማ ደነገጥሁ። “ካድሬያዊነት” ተጭኖታል ብዬ ያሰብኩት ንግግራቸው ስላናደደኝ ‹ሠላም የሚሉት የእርስ በርስ ጦርነት አለመኖርን ብቻ ነው ወይ?› ብዬ በጽሑፍ ጥያቄ ብልክላቸውም መልስ ሳይሰጡኝ ቀሩ። ጉባኤው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ተጋዳላይ አቦይ ስብሓትና ሌሎችም ከነአጃቢዎቻቸው የተገኙበት በመሆኑ፣ አሁንም ገና ስለእውነተኛ ማኅበራዊ ሠላም የምንነጋገርበት ቀን አለመድረሱን ታዘብኩ። ብሔራዊ እርቅ ታንቆ የመውረድ አማራጭ ሆኖ መቅረቱም ታሰበኝ።

እውን ኢትዮጵያ ውስጥ አስተማማኝ ሠላም ሰፍኗልን?

ሕዝብና መንግሥት ሆድና ጀርባ ከሆኑ ከረምረም ብሏል። መንግሥትም ጠንቅቆ እንደሚያውቀው በመላ አገሪቱ ከፍተኛ እምነት ማጣት፣ ቅሬታና የታመቀ አመጽ አለ። እንደምንታዘበው ስርዓቱን የመቃወሚያ ለዘብተኛው መንገድ ሽሽት ሆኗል። ወታደሩም፣

ፖሊሱም፣ ሲቪሉም፣ ምሁሩም፣ ሁሉም መለዮውንና የመንግሥት ሥራውን እየጣለ በገፍ ወደ ውጭ አገራት መኮብለል ወይም በአገር ውስጥ በሌላ ሥራ ኑሮውን መግፋት ከመረጠ ቆየ። ይችን ታህል ያልጨከነው አብዛኛው ደግሞ ቀን እያወደሰ ማታ እያማ በያልፋል ተስፋ መኖር ቀጥሏል። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የሙጥኝ ባለው የፖለቲካ ብልጣብልጥነት አባዜ ለዘብተኛ አቋም የሚያንፀባርቁ ሀገር ወዳድ ዜጎች ወደጥግ እየተገፉና በሌላ ወገን እየተነቀፉ፣ በአገዛዙም በተቃዎሞውም ጎራ የማይጠፉት “ጽንፈኞች” በሕዝቡም፣ በፖለቲካ ክበቡም ዘንድ አድማጭ ጆሮ ቢያገኙና አልፎም ሥልጣን ለመንጠቅ ቢያሰፈስፉ የሚደንቅ አይሆንም።

በዚህች አጭር መጣጥፍ ለሐሳቤ መነሻ የሆነኝን የብሔራዊ እርቅ ጉዳይ በአገሪቱ ከሰፈነው የማኅበራዊ ሰላም እጦት አንጻር ለማየት እሞክራለሁ። ስለዚህም በመጀመሪያ ማነፃፀሪያ እንዲሆኑን ስለአገራዊ ግጭትና አመጽ መንስኤዎች ጥቂት ካልኩ በኋላ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) በምን ምክንያት የሠላሙን አጀንዳ በመዝጋት ረገድ የበለጠ ተጠያቂነት እንዳለበት ለማሳየት እሞክራለሁ። በመጨረሻም ለዚህ አስረጂ ከሆኑት ባሕርያቱ መካከል ሁለቱን በማብራራት እደመድማለሁ።

የማኅበራዊ ግጭትና አመጽ መንስኤዎች ምንድን ናቸው?የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁራን አበክረው

እንደሚያስተምሩት ከሁሉም በላይ በዜጎች መካከል በፖሊሲና በሕግ የተደነገገ ልዩነትን የሚፈጥር መዋቅራዊ መድልዎ በኅብረተሰብ ውስጥ ቅሬታን የሚያከርርና ለአመጽ የተመቻቸ

ነው። በተለይ ደግሞ የግጭትና አመጽ መሠረታዊ መንስኤ የሃብት ቁጥጥርና ክፍፍል ኢፍትሓዊነት ነው። ማርክሳውያን በግልጽ እንዳስቀመጡት ነባራዊው ኅብረተሰባዊ መዋቅር የባለሀብቶችን ባለቤትነትና ጥቅም ለማስጠበቅ የተቀየሰ ከሆነ፣ በሌላ አነጋገር የማኅበራዊ ተቋማት፣ የፖለቲካና ኤኮኖሚው ስርዓት ሥልጣን ያላቸው የሌላቸውን እንዲበዘብዙ የተመቻቸ ከሆነ፣ በገዥና ተገዥ፣ በሀብታምና ድኃ፣ ባለውና ባጣው መካከል መደባዊ ርቀት በመፍጠር፣ ተርታው ኅብረተሰብ ማኅበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ሥነ ልቡናዊ ባይተዋርነት እንዲሰማው ያደርጋል። ሰፊ ማኅበራዊ ልዩነት በፊናው ድህነትን፣ ድንቁርናን፣ እርዛትን፣ ችጋርን፣ በሽታን፣ ወንጀልንና ብሎም አመጽን ማፈንዳቱ አይቀሬ ይሆናል።

ሁለተኛ ዕድገት ወይም ልማት በራሱ ተፈላጊ ነገር ቢሆንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ የግጭት መንስኤ ይሆናል። በተለይም ልማቱ ፍትሓዊ ካልሆነ፣ ከፍተኛ ማኅበራዊ መድልዎ ወይም አንጻራዊ በደል ካስከተለ፣ ዜጎች የበይ ተመልካች መሆናቸው የሚሰማቸው፣ በገዛ አገራቸው የመሻሻል ሕልማቸውና ምኞታቸው የተጨናገፈና የመከነ፣ በዜግነታቸው በሚጠብቁትና በገሀድ በሚያገኙት መካከል ሊታገሱት የማይችል ክፍተት ካለ፣ ቅሬታ ሊፈጥርባቸውና ለአመጽ ሊያነሳሳቸው ይችላል።

ሦስተኛ መንግሥት ብሔራዊ እሴታዊ መግባባትን ሊፈጥር ካልቻለ፣ ራሱን ከአመጽ አዙሪት ሊያወጣና ዋነኛ ተግባራቱን ማከናወን ካቃተው፣ በዚህ ላይ ከአቅሙ በላይ የሆኑ አደጋዎች፣ ቀውሶችና ሴራዎች ውስጥ የተዘፈቀ ስለመሆኑ አጠቃላይ እምነት ካለ፣ ለቡድናዊ አመጽ የተመቻቸ ይሆናል።

አራተኛ በሕዝቦች መካከል የሚራገቡ እትብታዊና ደመነፍሳዊ ስሜቶች በማኅበረሰቦች መካከል አላስፈላጊ ፉክክሮችንና ከማንአንሼነትን በማጋጋልና መድልዎን በማባባስ የግጭቶችን አደገኝነት ይጨምራሉ። በሥልጣንና በሃብት የተፈጠሩ ልዩነቶችን ለማካካስና ብልጫ ለማግኘት የሚደረጉ መቀናቀኖችና ግጭቶች፣ በአንድ ሀገር ውስጥ ባሉ የተለያዩ ቡድኖች አጠቃላይ መስተጋብሮችና በማኅበራዊ ለውጥ ሒደቶች ውስጥ የሚንጸባረቁ የማያባሩ ጉዳዮች

የብሔራዊ እርቅን አጀንዳ ማነው የዘጋው?

ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም አንድ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ ‹በአገራችን ሠላም ሰፍኗል› የሚል አስተያየት ከአንድ ምሁር አንደበት ሲወጣ በመስማቱ ‹እውን በአገራችን ሠላም ሰፍኗል ወይስ አመጽ ታፍኗል?› በሚል በአገራችን ሠላም መስፈኑን የሚያጠራጥሩ ነባራዊ ፈተናዎች መኖራቸውን በሚከተለው መጣጥፉ ተንትኗል።

Page 28: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

27ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4ወደሚቀጥለው ገጽ

ትኩሳት

ይሆናሉ። አምስተኛ ሠላማዊ ሙግት ለዘብተኛ

የግጭት ዘይቤ ሲሆን፣ ቡድኖች በሠለጠነ መንገድ የሚፎካከሩበት፣ አንዱ የሌላውን ሐሳብ ለማስቀየር ወይም የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያገለግል፣ አመጽን የሚያመክን መላ ነው። ቅሬታን ለማስተንፈስ ወይም ለማስወገድ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ አማራጮች በተዘጉበት፣ ፖለቲካው በዜሮ ድምር ስሌት በሚካሄድበትና ተቃዋሚና ጠላት በተግባርም በቃልም ድንበራቸው በሚደበዝዝበት ሁኔታ፣ የአመጽ ቡድኖች ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም፣ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ፣ ጥቅማቸውን ለማስከበርና አቅማቸውን ለማደርጀት የሚጠቀሙበት ብቸኛ ብልሐት ይሆናል።

ስለዚህም ኅብረተሰብ በዘፈቀደ በጥቂት ‹ጸረ-ሰላም ኃይሎች› ሰበካ የሚነዳ ሳይሆን፣ የራሱን ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ጥቅም የሚያሰላ፣ ትእምርታዊና ባሕላዊ ወይም ሥነልቡናዊ እሴቶቹን ለማስከበር የሚቆም አስተዋይ ኃይል ነው። ዜጎች በመንግሥት ላይ እምነት ሲያጡ ወይም አደጋ፣ ተግዳሮትና ውርደት የደረሰባቸው መሆኑን ካመኑ ያምጻሉ። ዓላማቸው መብታቸውን ለማስከበር፣ ክብራቸውን ለማደስ ወይም ራሳቸውን ለመከላከል ነው።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ና ተፈጥሮአዊ የአመጻ ባሕርያቱ

ግጭት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የፈጠረው ጉዳይ አይደለም። አገዛዙ ራሱ በአመጽ ደርግን ገርስሶ ሥልጣን በተቆናጠጠበት ወቅት፣ የተረከበው ለሠላሳ ዓመታት ገደማ የክፍፍልና የጥላቻ መንፈስ የተዘራበት፣ ደም እንዲቃባና በጎሪጥ እንዲተያይ የተገደደ ሕዝብ ነበር። በእውነቱ በተለያዩ ውስጣዊና ዓለማቀፋዊ ክስተቶች ግጥምጥም ታሪክ የሥልጣን ሸክሞችን ያቃለለችለት፣ ሕዝብም እንደ ሙሴ ሊከተለው ተስፋ የጣለበት እንደ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ያለ አገዛዝ በአገሪቱ ታይቶ የሚያውቅ አይመስለኝም። ትልቁ ምፀት ይህንን ሐቅ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት.) ለመገንዘብ አለመቻሉና፣ ሠላም በተራበው አቅመቢስ ሕዝብ ላይ ራሱን

በግጭት አራጋቢነትና ዳኝነት በመደልደል፣ ከእያንዳንዱ ማኅበራዊ ስንጥቅ ለማትረፍና ሥልጣኑን ለማስጠበቅ መሰለፉ ነው። በአጭሩ ክፍፍልን፣ ግጭትንና አመጽን የሕልውናው መሠረት ማድረጉ ማለት ነው።

ሕ.ወ.ሓ.ት. ያልጠበቀው አገራዊ ኃላፊነት ሲወድቅበት በከፍተኛ የኃይል መዛባት ላይ የተመሠረተ ያንድ ወገን የንዑሳን መንግሥት አቆመ። ለአገራዊ አደራው የሚመጥን ማኅበራዊ መሠረትም፣ ችሎታም ፍላጎትም ስላልነበረው፣ ሳይውል ሳያድር ያዋጣኛል ባለው በተንኮልና በሴራ ዘይቤ ተሰማራ። በአሸናፊ ማናለብኝነት ዋና ዋና ተፎካካሪ ብሔረሰቦችን፣ አገራዊ ራዕይ ያላቸውን ነባርና አዲስ ቡድኖችን በመከፋፈል፣ በማገድና በመምታት ከጨዋታ ውጭ አደረጋቸው። በጥቂት የጎሳ ምልምሎችና የሥልጣን ተስፈኞች ታጅቦ የከፋፍለህ ግዛው ዓላማውን የሚያስፈፅምበትን ሕገ መንግሥት በብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዘይቤ መጫኑ የሠላም ምልክት አልነበረም። ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊቱን አላጠቆረበትም።

ነገር ግን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. እያደር የአገሪቱን ብሔራዊ ጦር በጠላትነት ፈርጆ በመበተን፣ ነባር መንግሥታዊ መዋቅራትን በተጓዳኝ የፓርቲና ሕዝባዊ ማኅበራትን በማዳከም ሙሉ በሙሉ በአንድ የዘውግ ቡድን ሥር መቆጣጠሩ። የጦር ኃይሎችንና የደኅንነትን፣ የቁልፍ ሚኒስቴር ቦታዎችን፣ በትልልቅ ከተሞች ውስጥ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንን፣ ከአገርዓቀፍ እስከ ጎጥ ያሉ የቤተ እምነት ኃላፊዎችን እና ከዞን እስከ ቀበሌ ያሉ የአስተዳደርና ፖለቲካ እርከኖችን ያለ አንዳች ሐፍረት በአንድ ብሔረሰብ አባላት እጅ ሲጠቀልል፣ ለይስሙላ ጣል ጣል የተደረጉ ሹማምንትን በታማኝ የሕ.ወ.ሓ.ት. ታኮዎች እያሾረ ሲቀልድና፣ በግልጽ ሀገሪቱን ጡንቻው ፈጥርቆ ለመግዛት ሲደላደልም አንድ ቀን ልብ ይገዛ ይሆናል የሚሉ የዋኾች አልጠፉም።

ሆኖም በይስሙላ ፌዴራላዊነት በቀጥታ የተማከለ የፋይናንስና የፖለቲካ ቁጥርር በማድረግ፣ ብዙኃኑን የአገሪቱ ብሔረሰቦች መብቶች በመግፈፍና በምልምሎች በማስረገጥ ለንዑሳን ምርጦች ልዕልና የቆመ በመሆኑ፣ ዛሬ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የብሔረሰቦች መብት ጠበቃ

ነኝ ቢል ማንም አያምነውም። እሱም ጉዳዩን በዘፈንና በማስታወቂያ ሰሌዳ ሙግት ገድቦ፣ ልማታዊ መንግሥት ነኝ ወደሚል ዜማ ዞሯል። ብዝኃነት የምትለው ዘይቤ ሁልጊዜም በግጭትና በተቃርኖ በከፋፍለህ ግዛው ስልት ለመዝለቅ የመጣጣሩ መሪ ቃል ናት። ማኅበራዊ ጥርጣሬንና ሽኩቻን ለማራገብ፣ መቻቻልና አብሮነት ለማደፍረስ በተደጋጋሚ ግልጽና ስውር ደባዎች መፈፀሙ፣ በየተጎራባች ብሔረሰቦች መካከል መቃቃርና ጥላቻ ሲካረር፣ ዜጎች በማንነታቸው የተነሳ በገዛ ሀገራቸው ሲበደሉ፣ ሲጋዙ፣ ሲባረሩ፣ ሲገደሉ፣ ንብረታቸው ሲቀማና ሲወድም በቸልታ ማየቱ፣ በተደጋጋሚ በሕዝብ ደም የታጠቡ ታማኝ ወንጀለኞችን ከመቅጣት ይልቅ ለዕድገት ማጨቱ የስርዓቱን ማንነት ይመሰክራል።

የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ዜጎች በጥርጣሬ ከማየት ባለፈ ጠባቦች፣ ትምክህተኞች፣ ፀረ-ሠላምና ፀረ-ልማት ኃይሎች፣ የሻዕቢያ ተላላኪዎች፣ ሽብርተኞች እያለ በጠላትነት በመፈረጅ በሥራና በሕይወት፣ በግልጋሎትና በግብር ግልጽ አድልዎ በማድረግ አዋክቧል። በአጠቃላይ የማኅበራዊ ታጋዮችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ የተቃዋሚ ኃይሎችን፣ የነጻው ጋዜጠኛ አባላትን በ“ሽብርተኝነት” በመፈረጅና በማንገላታት ግንባር ቀደም መሆኑ፣ እያንዳንዷን ማኅበራዊ ሕይወትና ተቋም ለመቆጣጠር ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከምና ለማጥፋት ቀን ተሌት መትጋቱ፣ ፍትሕን የጉልበተኞች ደንገጡር ማድረጉ የስርዓቱ ዓመጻዊ የአስተዳደር ዘይቤ ማሳያ ነው።

የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዋነኛ ችግሩም አቅመ ደካማነት ሲሆን፣ ይህም በአፈፃፀም፣ በቅቡልነት፣ በማኅበራዊ መሠረት ወዘተ. ይገለጻል። ከሁሉም በላይ የንዑሳን መንግሥት በመሆኑ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት አለበት። ይህን የድካምና የማቅለሽለሽ ስሜት ለመሸፈን ያለው አማራጭ ጠንካራና አይበገሬ መስሎ መታየት ነው። ‹ፈሪ ቀድሞ አስፈራሪ› እንዲሉ፤ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የጀግንነቱን ልክ በራሱ ለክቶታል፡፡ ስለዚህም ራሱን ‹የሕዳሴው ትውልድ› እያለ አለቅጥ በማቆላመጥና የአንድ ብሔረሰብ ጀግንነትን፣ የአንድ ግለሰብ ምልኪን በማራገብ አባዜ ተጠምዷል። ከዚህ በላቀ ግን የሥልጣኑ ምንጭ ከሕጋዊነት ይልቅ የደምና ጀግንነት ገድል በማድረግ ለሌሎች ከሁሉ የሚያዋጣው መንገድ ይህ መሆኑን ተምሳሌት በማኖሩ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የሠላሙን አጀንዳ ዘግቶታል።

ስለዚህም በአስገራሚ ማናለብኝነት፣ ግትርነትና አምባገነንነት ከሕዝብ በመካረር፣ በማስፈራራትና በብረት አለንጋ በመግረፍ ሩብ ምዕት ዓመት ዘልቋል። መሠረታዊ ለውጦችን ለማስተናገድ አሻፈረኝ ማለቱ፣ የዜጎችን ሐሳብ መናቁ፣ ደማቸውን ደመ-ከልብ አድርጎ ማስቀረቱ፣ በአፈናና በአውጫጪኝ መተማመኑ፣ ኃይልን የመጀመሪያም መጨረሻም አማራጭ አድርጎ በመውሰዱ ነው። በኃይል የወጣ በኃይል ይወርዳል የሚል ይመስላል። ከስርዓቱ

በይስሙላ ፌዴራላዊነት በቀጥታ የተማከለ የፋይናንስና የፖለቲካ ቁጥርር በማድረግ፣ ብዙኃኑን የአገሪቱ ብሔረሰቦች

መብቶች በመግፈፍና በምልምሎች በማስረገጥ ለንዑሳን ምርጦች ልዕልና የቆመ በመሆኑ፣ ዛሬ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.

የብሔረሰቦች መብት ጠበቃ ነኝ ቢል ማንም አያምነውም

Page 29: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

28 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ተፈጥሮ የመጣና ‹ለሕዝብ ስንዝር ስትሰጠው ክንድ ይመኛል› በሚለው ሸውራራ ብሒል ላይ የተመሠረተ መሆኑም አያጠራጥርም።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ፓርላማውን በአሳፋሪ ሁኔታ መቶ ፐርሰንት ጠቅልሎ (ጆሴፍ ስታሊን እንኳን በ1934 እ.ኤ.አ በ17ኛው የፓርቲው ጉባኤ ላይ ያገኘው ድምጽ 99 በመቶ ነበር) በሌላ በኩል የሕፃናት ፓርላማ እያለ ብላቴናዎችን መስበኩ፣ ሥነ ዜጋ እያስተማረ መብቱን የጠየቀውን ወጣት በጥይት መቁላቱ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ ምን ያህል ከጥበት ወደቧልታዊነት የመውረዱ መለኪያ ነው። አገሪቱ ሠላማዊ ሰልፍ እንኳን የማይፈቀድባት ብቸኛዋ የአፍሪካ አገር ሆናለች። ወኅኒ ቤቶች በፖለቲካ እስረኞች ተጣብበዋል፣ የሰብኣዊ መብት አያያዝ ከዓለም ጭራ አድርጎናል። በአጠቃላይ ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን ሐሳብ በመጥላት ሕዝብን ደፍጥጬ ሐሳቤን አስፈፅማለሁ፣ በኔ ርዕዮተዓለም የታረቀ አዲስና ታዛዥ ትውልድ እፈጥራለሁ ብሎ መታከቱ የሚሳካ አይሆንም።

ሠላም ዝም ብሎ አይመጣም፤ ከፍተኛ አስተዋይነት፣ ታጋሽነት/ሆደሰፊነት፣ አርቆ ተመልካችነትና ቅንነት ይጠይቃል። በአገሪቱ ሠላምና ፍትሕን ለማምጣት ያለው የመጀመሪያ አማራጭ የራሱን ጎደሎ አስተዳደር መጠገን ቢሆንም፣ ለዚህ የሁሉንም ወገኖች የጋራ

ተሳትፎ ለሚጠይቅ ግዳጅ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ቀና አይደለም። የሚጠበቅበትን ቢያንስ ሦስት ዋና ዋና ግዳጆች ማለትም አመጽን ከምንጩ ለመከላከል የተሻለ ዕኩልነት ለማስፈንና፣ የላቀ ማኅበራዊና ባሕላዊ መደጋገፍና መግባባት ለማበልፀግ በአግባቡ አልጣረም።

በአጭሩ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ስህተትን በተሻለ ስህተት እያረመ ለመሄድ የሚሞክር መሆኑን የአገዛዝ ታሪኩ ያሳያናል። የተደቀኑበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ከምር ገምግሞ የሰው ልጅን ተፈጥሮአዊ ባሕሪ በሠላማዊ እርምጃዎች በማሻሻል አመጽን ለመከላከልና ለማስቆም ይቻላል የሚል እምነት የለውም። በዚህ ፋንታ የያዘው ፈሊጥ የመቋቋሚያ ደኅንነትን ማጎልበትና እንዳስፈላጊነቱ ኃይልን ከጥቅም ቀይጦ በመጠቀም ንትርኮችን ለመፍታት መሞከር፣ አመጽ የሚከሰትበት ዕድል ለመቀነስና ከተነሳም ለማጥፋት ይበልጥ አስተማማኝ ነው የሚል ይመስላል። ዞሮ፣ ዞሮ ዓላማው ዴሞክራሲያዊና ፍትሓዊ ስርዓት

መገንባት ሳይሆን፣ የድለላ እና የቁጥጥር አገዛዝ ለመመሥረት ነው።

አፈናና ልማታዊ መንግሥት ለየቅልከላይ እንደተገለጸው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.

የኃይል አገዛዝ ዋነኛ ባሕሪው ቢሆንም፣ ጥሬ ጉልበት ሁልጊዜም አያዋጣም። ስለዚህም ከኃይል በመለስ የሚጠቀምባቸው ዘይቤዎችና ማስተባበያዎችን በጥንቃቄ አደራጅቷል። ከነዚህ አንዱ በልማታዊ መንግሥትነት ሥም የዘረጋው የአፈና ስርዓት ነው። የአፋኝነት አንዱ መገለጫው ዜጎች በመንግሥት ያልተፈቀዱ ማናቸውንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኙ መገደብ ነው። ሕዝብ በሚከፍልበት መገናኛ ብዙኃን ሕዝብን አክብሮ መረጃ ከመስጠት ይልቅ ሙሉ በሙሉ የእውነት በሮችን ዘግቶ በተሰለቸ የድለላ ወሬዎች መጠመዱ፣ ከፍተኛ አደጋ የደቀነ ርኀብን እንኳን በማድበስበስ ትዝብት ላይ መውደቁ፣ ዜጎች በይበልጥ ወደአሉባልታዊና አክራሪ ምንጮች እንዲሳቡ አስገድዷቸዋል።

ሁለተኛውና ግልጹ የአፈና ዘዴ ከመግባባት ይልቅ በጡንቻና በፍርሐት ለመግዛት የአገሪቱን ጥሪት በፖሊስና በደኅንነት ጋጋታ በማባከን መንግሥቱን የፖሊስ መንግሥት ማድረጉ ነው። በየስርቻው የተከላቸው ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ማኅበረሰብ ፖሊስ፣ ልዩ ግብረ ኃይል፣ ቅልብ ጦር፣ ፊዴራል ፖሊስ፣ አጋዥ ኃይል፣ ደንብ አስከባሪ፣ የአካባቢ ሚሊሻ፣ ከዚህ ጋር አንድ ለአምስት ጥርነፋ፣ ቡና ጠጡ ጋጋታ በተግባር ማኅበራዊ ቅሬታና ግጭት እየናረ እንጂ እየረገበ ያለመሄዱን ይመሰክራል። የማኅበረሰብ አጥኝዎች እንደሚሉት የፖሊስና እስር ቤት ዓላማ ወንጀል ለማጥፋት አይደለም። ወንጀል ችግርና ችጋር ባለበት አይጠፋም። ዋነኛ ዓላማው ዜጎችን በቅጣት አስፈራርቶ ለመለጎም፣ ወይም ደግሞ አስሮ ለማፈን ነው። የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በገዛ ወገኖቻቸው፣ ደመወዛቸውን በሚከፍሏቸውና በሕግ ከጥቃት እንዲጠብቋቸው አደራ በተሰጣቸው ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የኃይል ጥቃት በመፈፀምና፣ እንደተለመደውም ተጠያቂነትን በማምለጥ በማናለብኝነት መቀጠላቸው ማኅበራዊ ሠላም አያመጣም።

ሦስተኛውና በሰፊው የሚሠራበት የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. አፈና ዘዴ ጉቦና መደለያ ነው። ኪራይ ቸርቻሪነት የስርዓቱ አይነተኛ ባሕሪው በመሆኑ፣ ወደፊት ታሪክ ይህን አገዛዝ ‹ዘመነ መኳንንት› ብሎ ቢሰይመው አይገርመኝም። አገርን በግዙፍ የጉቦና የመደለያ ድርጎ ለማስተዳደር መሞከር አጥፍቶ ጠፊነት ነው። ነገር ግን አገዛዙ በሰፊው ሕዝብ አናት ላይ ፊጥ ያሉ ቢሊየነር ቅምጥሎችን የፈጠረ፣ እፍኝ ለማይሞሉ የስርዓቱ ልኂቃንና ጋሻ ጃግሬዎች ጥቅም የሚቸረችርና፣ ከዕለት ዕለት ኑሮው ገሃነም እየሆነ የሚጠበሰውን ብዙኃኑን ድሀ ኢትዮጵያዊ የረሳ የ“ኩላኮች”ና የከበርቴዎች ጠበቃ ሆኗል።

ለይስሙላ በየቢሮው ግድግዳ ‹የሥነ ምግባር መርሖች› አሽሞንሙኖ እያሰቀለ፣ በሌላ በኩል

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ቀና አይደለም። የሚጠበቅበትን ቢያንስ ሦስት ዋና ዋና ግዳጆች ማለትም አመጽን ከምንጩ ለመከላከል የተሻለ

ዕኩልነት ለማስፈንና፣ የላቀ ማኅበራዊና ባሕላዊ መደጋገፍና መግባባት ለማበልፀግ በአግባቡ አልጣረም

ትኩሳት

Page 30: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

29ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ሕዝብ በሚከፍልበት መገናኛ ብዙኃን ሕዝብን

አክብሮ መረጃ ከመስጠት ይልቅ ሙሉ በሙሉ

የእውነት በሮችን ዘግቶ በተሰለቸ የድለላ ወሬዎች መጠመዱ፣ ከፍተኛ አደጋ

የደቀነ ርኀብን እንኳን በማድበስበስ ትዝብት ላይ መውደቁ፣ ዜጎች

በይበልጥ ወደአሉባልታዊና አክራሪ ምንጮች እንዲሳቡ

አስገድዷቸዋል

ታማኝነት የሌለው አገዛዝ ሆኖ መገኘቱ፣ ቁልፍ ባለሥልጣናቱ በአደባባይ ኢትዮጵያንና ታሪኳ ላይ የሚያላግጡ፣ አገር ወዳድነትን ወደ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን አምላኪነት ያራከሱ፣ ከአቧራ አንስታ ያንቀባረረቻቸውን አገር በገደምዳሜ እስከማሰደብ የደረሱ መሆናቸው ከሥልጣኑ በላይ ምንም እሴት እንደሌላቸው የሚመሰክር ነው።

ሌላው ርዕሰ ጉዳይ በሚያስደነግጥ ሁኔታ አገርንና ሕዝብን ቤተ-ሙከራ ማድረጉ ነው። በተለይም የአገሪቱን የትምህርት ስርዓት በአካላዊ መስፋፋት ሽፋን በተግባር ማፈራረሱ፣ ለፈረንጅ የዕርዳታ ኮረጆ አሳልፎ መስጠቱ፣ ጥራዝ ነጠቅነትን በማስፋፋቱና ሁለገብ የሆነ ውድቀት የሚመረትበት ተቋም እንዲሆን መሰሪ ተንኮል ማድረጉ ይቅር የማይባል ሃጢአት ነው። ከአመክንዮም ሆነ ከኤኮኖሚክስ በተጣላ መልኩ የሚገነባቸው ዩኒቨርሲቲዎችን ከስኳር ፋብሪካዎች እንኳን አዋርዶ በማየት አመራሮቻቸው በፖለቲካ እጅ መንሻነት ለየዘውግ ቡድኑ በመልቀቅ የተራ ሹመኞች መቀለጃ አድርጓቸዋል። በተጨማሪም ከምርምር ማዕከልነት ይልቅ የፖለቲካ ወገንተኝነት የሚረጋገጥባቸው፣ ተማሪና መምህር የሚሰበክባቸው የመመልመያ ካምፖች እንዲሆኑ ማድረጉ፤ ምሁሩን በጣውንትነት በመፈረጅ ከተላላኪነት ባለፈ ለአገሩና ለወገኑ የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ መገደቡ፣ ግልጽ የሆነ የ‹ሜሪት› ስርዓት ባለመዘርጋት፣ ትምህርት ክህሎትና ልምድ ከፖለቲካ ታማኝነት በታች በመጣሉ፤ ተማሪውን በወጪ መጋራት በ‹ፎረም› ሥራ ዕድል ምንደኛ ማድረጉ ከትውልድ ማምከኛው ሰፊ ሴራ ጥቂቶቹ ናቸው።

ለማጠቃለል ከላይ የተዘረዘረው ይህ ሁሉ የዘውገኝነት ፣ የአመጽ አምላኪነት ፣ የከፋፋይነትና አፈና ሂደት የሥርዓቱን እድሜ በማራዘም መጠነኛ ፍሬ ማሳየቱ አይካድም። ሆኖም ዘላቂ መፍትሔ አያስገኝም፣ ለአገርም ለሕዝብም ፍፁም አይበጅም። መብት ለጠየቀ ጥይት ጭካኔ ከመሆኑም ሌላ የአመጽና ተቃውሞው አድማስ በየጊዜው እየሰፋ ከመንግሥት አቅም በላይ በመሆን ላይ ይገኛል። በተለይም በዚሁ ስርዓት ሥር ተወልዶ ያደገው ወጣት ክፍል የራሱ የሆነ አቋም እንዳለው፣ በሽንገላና በአእምሮ እጥበት እንዳልተኮላሸ ተስፋ አሳይቷል። ከእንግዲህ በተለመደው ዱለኝነት፣ ብልጣ ብልጥነትና ሴራ ጉንጎና እቀጥላለሁ ማለት ሩቅ የሚያስኬድ አይደለም፡፡፡ በበኩሌ አገር ወዳድነትን ወደ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን አምላኪነት የ25ኛ ዓመት ኢዮቤልዩውን ሲያከብር የምመኝለት ከርችሞ የዘጋውን የሠላምና የድርድር በር ለብሔራዊ እርቅና መግባባት ከፍቶ ይህንን ምስኪን ሕዝብ ከከፋ ሰቆቃ እንዲያድነው ነው። የከፋውን ማሰቡም ብልሕነት ነው።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም የሕግ መምህርና ተንታኝ ናቸው፡፡ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ይገኛሉ፡፡

ሥልጣን የግል ጥቅም ማስጠበቂያ እንዲሆን፣ ማኅበራዊ እሴቶች ፈርሰው ዋናው ነገር ይዞ መገኘት ነው የሚል አስተሳሰብ እንዲነግስ አበረታትቷል። ለወጣቱ ትውልድ ፖለቲካ በሐቅ ሳይሆን በማጭበርበር የሚጨበጥ፣ ዘላቂ የሕዝብና የአገር ጥቅም ሳይሆን ዘላቂ ሥልጣንና ከዚህ የሚገኝ ትሩፋትን መሠረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጡ፣ አድርባይነት፣ አጎብዳጅነት፣ ዋልጌነት፣ በማስፈኑ በአጠቃላይ ከጥቅማ ጥቅም ብሔራዊ መርሕና ራዕይ የሌለው መሆኑን ይመሰክራል። ታጋዩም ‹እንዳያልፍ የለም፤ ያ ሁሉ ታለፈ፤ ታጋይ የሕዝብ ልጅ ሚሊዮን ዘረፈ› እያለ ቢዘፍን አይገርመንም።

የአገሪቱን አንጡራ ሀብቶች ከሕዝብ በመንጠቅ በማናለብኝነት ለባለሟሎቹና ለባዕዳን ባለሀብቶች በመቸብቸቡ፣ በብድር በዕርዳታና በተለያዩ ልግስናዎች የሚገኙትን ሀብቶች በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ወገናዊናትና መድልዎ ከማሰራጨት በተጨማሪ ዓለም ጉድ እስኪል ድረስ መዋዕለ ንዋይ በሙስና ወደባዕዳን አገራት ሲሸሹ መቆጣጠርና ማስቆም የማይችል ወይም የማይፈልግ መሆኑ፣ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሕዝብን ለማገልገል ሳይሆን ራሳቸውን ለማገልገል በተሰለፉ ባለሥልጣኖች የተሞላ አገዛዝ መሆኑ ቁልጭ ያለ ማስረጃ ነው። ሙሰኞች ከመንግሥት ጋር መዋቅራዊ በመሆናቸው እነሱን መዋጋት በፍፁም ከኢ.ቢ.ሲ. ‹ዘጋቢ ፊልም› ምኞት የማያልፍ ነው።

አራተኛውና ከሁሉም የከፋው የአፈና ዘዴ ሕዝብን ከድህነት ጋር አብሮ ማኖር ነው። ይህ ደግሞ የለየላቸው አምባገነን መንግሥታት ዜጎችን ሰጥ ለጥ ለማሰኘት የሚጠቀሙበት አስተማማኝ ዘዴ ነው። ኤኮኖሚው በሁለት አሐዝ አደገ እየተባለ የሕዝብ ኑሮ ሲያሽቆለቁል ደንታ ቢስ መሆኑና ሹሮ እንኳን የቅንጦት ምግብ የሆነበት ጊዜ መደረሱ፣ በተግባር የአገሪቱ ከተሞች የፈረሱ ቤተሰቦች፣ መጠለያ ያጡ ወጣቶች፣ በሱስ የተጠመዱ ብላቴናዎች፣ በየመንገዱ የሚለምኑ ሕፃናትና ሴቶች መነኻሪያ ሲሆኑ በቂ እርምጃ አለመውሰዱ የዚህ መገለጫ ነው። ወጣቱን ትውልድ በአገሩ የሚኮራና ተስፋ የሰነቀ ከማድረግ ይልቅ ለባሕር ማዶ ግርድናና ለኮብል ድንጋይ ፈላጭነት ማጨቱ፣ አርሶ አደሩ በኩርማን ማሳው ተገድቦ በማዳበሪያ ዕዳ ተቀፍድዶ ከእጅ ወደአፍ የሆነ ኑሮውን እንዲገፋ ማስገደደዱ፣ በርኀብና በድርቅ የሚንጠራወዘውን ምስኪን እንኳን በአምስት ለአንድ አባዜ በማሰር፣ በፖለቲካ ታማኝነትና በብሔረሰብ መድልዎ በማድረግ ግፍ መፈፀሙ፤ የመንግሥት ሠራተኛው ከኑሮው ንረት በማታወጣው የይስሙላ ምንዳ መቀፍደደዱና በአስተዳደር ማሻሻያዎች ሰበብ አውጥቶ መጣሉ፣ ነጋዴው ነግዶ በማይወጣው የግብር ጫናና የአስተዳደር በደል በሙስና ከጨዋታ እንዲወጣና በጥቂት የስርዓቱ የበኩር ልጆች እጅ ኤኮኖሚው እንዲሰበሰብ ማድረጉ የስርዓቱን ኢሰብኣዊ ገጽታ ያሳያል።

በአጠቃላይ ከይስሙላ ዴሞክራሲያዊነት

ወደ ፈካሪ ልማትነት የተደረገው ሽግግር፣ እንደ መለኮታዊነትና ሶሻሊስታዊነት ከሥልጣን ማቆያ መላነት አላለፈም።

ራዕይ ለመቼና ለማን ?ሩብ ምዕተ ዓመታትን በሥልጣን

የመቆየት ዕድል ያገኘው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን ከምር የሚገመግም ከሆነ በደፈናው ከላይ የቀረበውን አስተያየት ‹የጠላት ወሬ ነው› ብሎ የሚጥለው አይመስለኝም። ለምስጋናው ሃያ አራት ሰዓት በየሚዲያው የሚዥጎደጎድ በመሆኑም፣ ጥፋቱን መንቀሳችን በጥቂቱ ሚዛን የሚያስጠብቅ ቢሆን ከሚል ምኞት ነው። አብዛኛውንም ነገር የመንግስት ባለሥልጣናት ራሳቸው በተለያየ መድረክ ተናግረውታል። ምናልባት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አገዛዙ ያላመናቸው፣ ሆኖም የስርዓቱ ምንግዴነትና ራዕይ አልባነት ከገነነባቸው ጉዳዮች መካከል አገርንና ትውልድን የሚመለከቱት ዋነኞች ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ደግሞ እጅግ ተቃርኗዊው አገሩን የማይወድ አገር መሪ የመሆን ዕዳ ነው። ከታሪክ፣ ከሕዝብ እሴት፣ ባሕልና ተቋማት ጋር ጠላትነት ማክረሩ ስርዓቱ ከተማሪው ንቅናቄ ያቆየው እርሾ ነው። ኢትዮጵያዊነትን ከአንድ ብሔረሰብ ለማቆራኘት መሞከሩ፣ ነገሩ ሲከሽፍ ደግሞ ከሕዝቦች ማንነት ጋር ለማጣላትና ለማራከስ መታከቱ የዘውገንኝት ቅርሱ ነው። የሀገሪቱን ጥቅም በተደጋጋሚ ችላ ማለቱ፣ ብሔራዊ ድንበሯን እንኳን ለማስከበር ብቃትና

ትኩሳት

Page 31: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

30 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ለማወቅ ፍላጎት ላለው ሰው ቀድመው ከሚመጡበት ጥያቄዎች ውስጥ “ኢትዮጵያ ለምን የፌዴራሊዝምን ስርዓት መረጠች?” የሚለው ጥያቄ አንዱ ነው።

ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ የተመረጠበት ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ። እነርሱም፣ ሀ) ያለፈውን አስተዳደራዊ ስህተት ለማረም ያስችላል ተብሎ በመታመኑ፤ ለ) አለመረጋጋት በኢትዮጵያ፣ በምሥራቅ አፍሪካ፣ በቀይ ባሕር እንዲሁም በሰሜን ምሥራቅ የሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ እንዳይከሰት ያደርጋል ተብሎ በመታመኑ፤ ሐ) በኢትዮጵያ የሚኖሩትን ከ80 በላይ የዘውግ ቡድኖች (ethnic groups) አብሮነትን ያጠናክራል ተብሎ በመታመኑ ነው።

እነዚህ ምክንያቶች ለኢትዮጵያ ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ ለመረዳት ደግሞ ከ1983 በፊት የነበረውን ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል።

ቅድመ ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያከ1983 የነበረው የኢትዮጵያ ሁኔታ የከፋ

ማኅበራዊ ኢፍትሓዊነት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ እና የፖለቲካ ጭቆና የተንሰራፋበት ነበር። በቋንቋ፣ በባሕል እና በሃይማኖት ላይ የተመሠረተ ማግለል ነበር። በውጤቱም፣ ብሶቶች እና አመፆች በተለያዩ አካባቢዎች ይከሰቱ ነበር። አመፆቹ እና ብሶቶቹ የተደራጁ የትጥቅ ትግሎችን ፈጥረዋል። በ1983 መገንጠል እና የራሳቸውን አካባቢያዊ መንግሥት መመሥረት የሚፈልጉ በርካታ ድርጅቶች

ነበሩ። እነዚህ የነጻነት ንቅናቄዎች ትልልቅ ቦታዎችን በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው ነበር። ከነዚህ ውስጥ የኤርትራ ነጻነት ግንባር (ኤ.ነ.ግ.) እና የኤርትራ ሕዝቦች ነጻነት ግንባር (ሻዕቢያ) በኤርትራ፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ሕ.ወ.ሓ.ት.) በትግራይ፤ የአፋር ነጻነት ግንባር (አ.ነ.ግ.) በአፋር፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢ.ሕ.ዴ.ን.) ኋላ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብ.አ.ዴ.ን.) በአማራ፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ.)፣ የኢስላማዊ ኦሮምያ ነጻነት ግንባር (ኢ.ኦ.ነ.ግ.)፣ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦ.ሕ.ዴ.ድ.) በኦሮሚያ፤የጋምቤላ ሕዝቦች ነጻነት ግንባር (ጋ.ሕ.ነ.ግ.) በጋምቤላ፤ የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ግንባር (ቤ.ሕ.ነ.ግ.) በቤኒሻንጉል፤ የሲዳማ ነጻነት ግንባር (ሲ.ነ.ግ.) በደቡብ ኢትዮጵያ እና የምዕራብ ሶማሊ ነጻነት ግንባር እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦ.ብ.ነ.ግ.) በኢትዮጵያ ሶማሊ ቦታዎችን ተቆጣጥረው ነበር። ሌሎችም ትንንሽ ድርጅቶች በአፋር፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ እና ኦሮሚያም ጭምር ነበሩ።

በዚያ ላይ፣ ሱዳን ውስጥ ጦርነት ነበር፤ ሶማሊያ አለመረጋጋት ውስጥ ነበረች። ስለሆነም፣ በአፍሪካ ቀንድ ያንዣበበው አደጋ ለሰሜን ምሥራቁ የሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ እና የቀይ ባሕር አካባቢ እንዲሁም የዓለምዐቀፉ የንግድ መሥመር ላይ ሠላም የማደፍረስ አደጋ ይጥላል የሚል ስጋት ነበር። የአራቱ ድርጅቶች (ሕ.ወ.ሓ.ት.፣ ብ.አ.ዴ.ን.፣ ኦ.ሕ.ዴ.ድ. እና ከድል

በኋላ የተቀላቀላቸው ደ.ኢ.ሕ.ዴ.ን.) ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.)፣ በኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ይመራ የነበረውን የወታደራዊውን ደርግ መንግሥት በግንቦት 1983 አሸንፎ መንግሥታዊ ሥልጣኑን ተቆጣጠረ። ነገር ግን በዚህ ብቻ ሠላም ወደ ኢትዮጵያ መረጋጋት ደግሞ ወደ አፍሪካ ቀንድ ይመጣል ማለት አይቻልም ነበር።

ጦርነቱን ለማቆም እና ለኢትዮጵያ ችግሮች ሠላማዊ መፍትሔ ለመፈለግ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በሐምሌ 1983 ከታጠቁም ካልታጠቁም፣ ከኢትዮጵያ የሠራተኞች ፓርቲ (ኢ.ሠ.ፓ. - በቀድሞው ወታደራዊ መንግሥት የተቋቋመ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ.) እና የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስታዊ ንቅናቄ (መ.ኢ.ሶ.ን) በስተቀር፣ የተቃዋሚ ደርጅቶች ጋር የሠላም ጉባኤ አድርጓል። ሻዕቢያ፣ ቀድሞውንም ኤርትራን በ1983 ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ ስለነበር ጉባኤው ላይ በታዛቢነት ነበር የታደመው። ጉባኤው የተካሔደው ሕ.ወ.ሓ.ት.፣ ሻዕቢያ እና ወታደራዊው መንግሥት በተገናኙበት አሜሪካ እና እንግሊዝ ያሰናዱት የለንደኑ ስብሰባ ላይ በተደረሰበት ስምምነት መሠረት ነው።

የሐምሌው የሠላም ጉባኤ ወሳኝ የሆኑ በርካታ ነጥቦች ላይ ውሳኔ ተደርጎበታል። የሚከተሉት ዋናዎቹ የጉባኤው ውጤቶች ነበሩ፤ ሀ) የሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ፀደቀ፣ ለ) በሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ላይ ተመሥርቶ የሽግግር መንግሥቱ ተቋቋመ፣ ሐ) ቻርተሩ ለተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት እስከ መገንጠል እና የራሳቸውን መንግሥት እስከ መመሥረት ድረስ ሰጣቸው፣ መ) የኤርትራ ሕዝቦች ከኢትዮጵያ ጋር በኅብረት መቀጠል ይፈልጉ እንደሆን ወይም መገንጠል ይፈልጉ እንደሁ የሚወስን ሪፈረንደም እንዲካሄድ ተወሰነ፣ ሠ) የኢትዮጵያ አገረ-መንግሥት ሥልጣኑ ኢ-ማዕካላዊ እንዲሆን እና በዘውግ ድንበሮች የተከፋፈሉ አዳዲስ የአስተዳደር ክልሎች ተቋቁመው የማዕከላዊው ሥልጣን እንዲከፋፈል ተደረገ፣ ረ) የሰብኣዊ መብቶች እንዲከበሩ ዋስትና ተሰጠ፣ ሰ) በዕኩልነት ላይ

የፌዴራሊዝም ፖለቲካ በኢትዮጵያ

የፌዴራሊዝም ስርዓት ጉዳይ በኢትዮጵያ አነጋጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥትን ፈርመው ያፀደቁት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገ መንግሥቱ የፀደቀበትን ሒደት ከተነተኑ በኋላ፣ ሕገ መንግሥቱ የተሻለ ሕዝባዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ይደረግ የሚለውን የመፍትሔ ሐሳብ የጠቆሙበትን ጽሑፋቸውን ልከውልን ወደአማርኛ መልሰን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

የአገር ነገር

Page 32: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

31ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

በውይይቱ የተሳተፉት በሙሉ ፌዴራሊዝምን

ቢደግፉም ቅድመ ሁኔታ የሌለውን የመገንጠል

መብትም ደግፈዋል። እነዚህ ሐሳቦች ለሕዝቡ ቀርበው

‹ሪፈረንደም› ቢደረግባቸው እና ሕዝቡ የሚለው ቢታወቅ

ጥሩ ነበር። ወይም አሁን ከ20 ዓመታት በኋላ ድጋሚ

ለሕዘቡ በ‹ሪፈረንደም› ቢቀርቡና የሕዝቡ ዳኝነት ቢሰማ የበለጠ ጥሩ ነበር

የአገር ነገር

ወደሚቀጥለው ገጽ

የተመሠረተ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ተወሰነ፣ ሸ) ቋንቋዎች እና ባሕሎች እንደሚከበሩ ዋስትና ተሰጠ፣ ቀ) የመገንጠል መብትን የምታከብር የተባበረች እና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለማቋቋም የሚያስችል ሕገ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲቀርፅ ተወሰነ።

የሽግግር መንግሥቱከጉባኤው በኋላ፣ የኢትዮጵያ የሽግግር

መንግሥት ነሐሴ 9፣ 1983 ተቋቋመ። የሽግግር መንግሥቱ በሐምሌው የሠላም ጉባኤ ላይ የተወከሉትን አብዛኛዎቹን ድርጅቶችን ወኪሎች ያቀፈ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም አቋቋመ። የሕ.ወ.ሓ.ት. ሊቀ መንበር አቶ መለስ ዜናዊ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና መራሔ መንግሥትነቱን ቦታ ሲወስዱ፣ የብ.አ.ዴ.ን. ሊቀመንበር አቶ ታምራት ላይኔ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይዘዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተቋቁሞ ነበር። የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሠራዊት የሕ.ወ.ሓ.ት. አባል በሆነው አቶ ስዬ አብርሃ የሚመራ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ሆነ። የሽግግር መንግሥቱ ውጤቶች፡- 1ኛ፣ አዲሶቹን ክልላዊ መንግሥታት የሚያቋቁም ምርጫ ማካሔድ፤ 2ኛ፣ የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ በሪፈረንደም አስወስኖ ኤርትራ ራሱን የቻለ አገረ-መንግሥት መመሥረቷ፤ 3ኛ፣ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ማቋቋሙ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) ሕገ መንግሥት እንዲፀድቅ በ1987 ምርጫ ማካሄዱ፤ 4ኛ፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ን የሚያቋቁመውን የመጀመሪያውን ምርጫ በነሐሴ 1987 ማካሄዱ ናቸው።

ሕገ መንግሥቱን የማዘጋጀቱ ሥራ በብዙ ደረጃዎች ውስጥ አልፏል። የመጀመሪያው ሕገ መንግሥቱን የሚያረቅ ኮሚሽን በ1984 ማቋቋሙ ነው። ይህ የተከናወነው መጀመሪያ የሽግግር መንግሥቱ የምክር ቤት አባል ያልሆኑ (የተወካዮች ምክር ቤቱ አባል ያልሆኑ ከ1983 በኋላ የተመሠረቱ ከ100 በላይ ድርጅቶች ነበሩ) የፖለቲካ ድርጅቶችን በሕትመት እና ኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች እንዲመዘገቡ በመጋበዝ ነበር። ለምክር ቤቱ አባልነት ካመለከቱት ድርጅቶች መካከል 7ቱ በሕግ የተመዘገቡት ተመርጠዋል (እነዚህም፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደ.ኢ.ዴ.ግ.)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢ.ብ.አ.ፓ.)፣ የ1984 መድረክ (መድረክ 84)፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ (ኢ.ሙ.ን.)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ቅንጅት (ደ.ኢ.ቅ.)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊግ (ኢ.ዴ.ን.ሊ) ነበሩ። በተመሳሳይ መንገድ 15 የሙያ ማኅበራት አባላትም በምክር ቤቱ ተመረጡ። እነዚህም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር (3)፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር (2)፣ የኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤት (3)፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (2)፣ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር (2) እና የተለያዩ የሴቶች ማኅበራት (3) ነበሩ።

ሌሎች ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶችም ምክር ቤቱ ውስጥ ተካትተዋል፤ እነርሱም፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት (ኢ.ዴ.ኅ. - የቀድሞው ንጉሣዊ ስርዓት ሰዎች ደርግን ለመታገል ያቋቋሙት ድርጅት ነው)፣ የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢ.ሕ.ዴ.ን.)፣ የከፋ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢ.ብ.ዴ.ድ.)፣ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦ.ሕ.ዴ.ድ.) እና የኢሳ /ጉርጉራ ነጻነት ግንባር ነበሩ። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የወከልነው የብ.አ.ዴ.ን. አቶ ዳዊት ዮሓንስ እና እኔ ከኦ.ሕ.ዴ.ድ. ብቻ ነበርን። ኦ.ነ.ግ. እና ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ኮሚሽኑ ከመቋቋሙ በፊት የሽግግር መንግሥቱን ጥለው ወጥተዋል። የኮሚሽኑ ማዕከል የተፈሪ መኮንን ቤተ መንግሥት ተደረገ። የኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ ቢሮ እና መሰብሰቢያ አዳራሹ ከአሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ ያለው የስብሰባ አዳራሽ ሆነ።

ኮሚሽኑ ለረዥም ጊዜ የወታደራዊው መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛ ሆነው የቆዩት ሊበራሉ የኢ.ብ.ዴ.ን. አቶ ክፍሌ ወዳጆን እንደ ሊቀ መንበር እና አብዮታዊ ዴሞክራቱ እና የረዥም ጊዜ የአሜሪካ ስደተኛውን አቶ ዳዊት ዮሓንስ [ምክትል]

አድርጎ መረጠ። አባላቱ የሚስማሙበት የሕገ መንግሥት ፅንሰ-ሐሳቦች ለሕዝባዊ ውይይት እንዲቀርቡ ስምምነት ላይ ተደረሰ። ነገር ግን፣ በአባላቱ መካከል ስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ነጥቦች ላይ ሕዝቡ ውሳኔ ይስጥ በሚለው ላይ መስማማት አልተቻለም። በዚህም መሠረት፣ ያለ ማንም ወገንተኝነት (non-partisan) ሰባት ምዕራፎች ያሉት የሕገ መንግሥት መሠረታዊ ፅንሰ-ሐሳቦችን የያዘ ሰነድ ተሰናዳ። ምርጫ ያላቸው ቅጾች በመሠረታዊዎቹ ፅንሰ-ሐሳቦች ዙሪያ (73 የሕገ መንግሥት ፅንሰ-ሐሳቦችን ከተለያዩ የሕገ መንግሥት አማራጮች ጋር) ለሕዝቡ፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሙያ ማኅበራት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶች፣ የትምህርት ተቋማት ተሰራጭተው ማኅበረሰቡ በመሠረታዊዎቹ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ላይ ያለው አስተያየት ለመሰብሰብ ተዘጋጀ። ከዚያም ሰነዶቹ በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተዘጋጅተው እና ለአካባቢ ነዋሪዎች የተለያዩ መድረኮች ተጠርተው 23,320 ቀበሌዎች እና በተለያዩ ተቋማት የተቀጠሩ ሠራተኞች፣ ሴቶች፣ ያገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና ሌሎችም ድርጅቶች ተሳትፈዋል። ልዩ መድረኮች ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩት በማመቻቸትም አመለካከትና አቋሞቻቸው ተመዘገበ። የየአካባቢው ውይይት ለሦስት ቀናት፣ በየቀኑ ከአራት እስከ ሰባት ለሚደርሱ ሰዐታት ተካሄደ። እንደኮሚሽኑ ሪፖርት፣ በውይይቶቹ ላይ የሰዉ ተሳትፎ፣ “በጥቅሉ፣ በመጀመሪያው ቀን ጥቂት የነበረ ሲሆን፣ በሁለተኛው ቀን ጨምሮ፣ በሦስተኛው ቀን የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል።” በወቅቱ ቁጥራቸው ትልቅ ሊሆን የሚችሉት ኢ.ሠ.ፓ.፣ ኢ.ሕ.አ.ፓ.፣ መ.ኢ.ሶ.ን. እና ኦ.ነ.ግ. ስብሰባዎቹ ላይ አንሳተፍም ብለው ነበር።

የሕገ መንግሥት አርቅቆትየፌዴራሊዝም ስርዓት የተመረጠበት

ዋነኛ ምክንያት ለዘውግ ቡድኖች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እና ቀላል የመገንጠል መብት ለመፍቀድ ነበር። ስለሆነም ከ73ቱ የሕገ መንግሥት ፅንሰ-ሐሳቦች መካከል ሁለቱ የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠልን የሚመለከቱ ነበሩ (እነዚህም አንቀጽ 39 እና አንቀጽ 40 ናቸው)። የራስን ዕድል መወሰንን በተመለከተ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ እና ሐራሪ ውስጥ የተሳተፉት ሰዎች ከ90 በመቶ በላይ ሐሳቡን ደገፉት። በአማራ፣ ቤኒሻንጉል እና የኢትዮጵያው ሶማሊ ክልል ሐሳቡ ከ72 እስከ 89 በመቶ በሚሆኑ ተሳታፊዎች ድጋፍ አግኝቷል። በአዲስ አበባ 67 በመቶ እና በጋምቤላ 59 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ብቻ ድጋፍ ሰጥተውታል። በአፋር (97%)፣ በሐረሪ (72%)፣ በኦሮሚያ (95%)፣ በትግራይ (92%) እና በአማራ (92%) ፌዴራል ስርዓቱን ደግፈውታል። 84% በጋምቤላ፣ 65% በሶማሊ ሐሳቡ ድጋፍ አግኝቷል። እንዲያም ሆኖ፣ በውይይቱ የተሳተፉት በሙሉ ፌዴራሊዝምን ቢደግፉም ቅድመ ሁኔታ የሌለውን የመገንጠል

Page 33: ሰኔ 4 /2008 - zehabesha.com · ሰኔ 4 /2008 ሐተታ ውይይት 21-22 9-11 ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ኃይሉ አድራሻ፤ አ.አ.፣ የካ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ

32 ውይይት ሰኔ 2008 1ኛ ዓመት ቁጥር 4

ትውስታ ነው። ትልልቅ ዘመናዊ እርሻዎችን፣ ኢንደስትሪዎችን፣ የመሠረተ ልማት አውታሮችን እንዲሁም ከተሞችን ለማስፋፋት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችም የግጭቶች መንስኤ ሲሆኑ ይስተዋላል። ሊደርቁ ያልቻሉ ታሪካዊ ቁስሎች ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ችግሮች ቅመም በመሆን ነገሮችን ሲያባብሱ ይስተዋላል። በአጠቃላይ የዴሞክራሲ አለማደግና የመድብለ-ፓርቲ ፖለቲካ አለመጎልበት የፌደራሊዝሙ ፈተና ሁነው እናገኛቸዋለን።የፌዴራሊዝም አስፈላጊነት ላይ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

ኢትዮጵያ የተባበረች ፌዴራል አገር ሆና እንድትቀጥል ብዙኃን ይፈልጋሉ። ተገንጣይ ንቅናቄዎች እየከሰሙ፣ ፌዴራላዊዎቹ እያበቡ ነው። የትጥቅ ትግል ንቅናቄዎች እዚህም እዚያም አሉ፤ ነገር ግን የመገንጠል ዓላማቸው ግብ አይመታም። ነገር ግን አሁንም የፌዴራል ስርዓቱን መረጋጋት የሚፈትኑት ሁኔታዎች አሉ። የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ልማቶች ከፍትሓዊ ሀብት ክፍፍል ጋር መጣመር አለባቸው። ይህ ካልሆነ፣ ብሶቶች ወደአብዮት ይገነፍሉ እና የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችን በኅብር የመኖር ፍቃደኝነት ሊበጠብጡት ይችላሉ። ሰብኣዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር አለባቸው።

ያም ሆነ ይህ፣ እንደመደምደሚያ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ለአፍታ ቁጭ ብለን ሕገ መንግሥታችን ከተረቀቀበት ጊዜ ጀምሮ፣ የፌዴራሊዝም ስርዓትነቱን ጉዳይ ጨምሮ፣ በርካታ አወዛጋቢ አንቀጾች እንደነበሩት ማሰብ አለብን። 100 በመቶ ዜጎች የሚቀበሉት ሕገ መንግሥት ይፀድቃል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ነገር ግን፣ ብዙኃን ኢትዮጵያውያን በሕገ መንግሥቱ ጉዳይ መግባባት ደረጃ ላይ የሚደርሱበትን መንገድ ማግኘት አለብን። ለዚህ ደግሞ የተመረጠው መፍትሔ፣ እኔ እንደማምነው፣ መጀመሪያ በአወዛጋቢ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ትርጉም ያለው ውይይቶች ማካሄድ ነው። ውይይቱ፣ አወዛጋቢ የሆኑትን ሕገ መንግሥታዊ አንቀጾች ወደ ማሻሻል የሚመራ መድረክ ለመመሥረት መሆን አለበት። ረቂቅ ማሻሻያው ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ይካተትና ሙሉ ሕገ መንግሥቱ ለሕዝበ ውሳኔ (‹ሪፈረንደም›) ይቀርባል። ይህ በኢትዮጵያ ያሉትን እና ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ሕገ መንግሥቱን ይቀበሉት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለመወሰን ዕድል ይሰጣቸዋል። እስካሁን ይህንን ዕድል አላገኙም። የዓለማችን አገራት ሕገ መንግሥቶች በዜጎች ሕዝበ ውሳኔ የፀደቁ እንዳልሆኑ አውቃለሁ። ነገር ግን የቅርብ ጊዜ የስኮትላንድ እና ካታሎኒያ ተሞክሮዎች እንደሚያስተምሩን ፍትሓዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ዘመናዊ የሆነ ሕዝበ ውሳኔ ማካሄድ የተሻለ ቅቡልነት ለሕገ መንግሥታችን ያስገኝለታል።

የአገር ነገር

መብትም ደግፈዋል። እነዚህ ሐሳቦች ለሕዝቡ ቀርበው ‹ሪፈረንደም› ቢደረግባቸው እና ሕዝቡ የሚለው ቢታወቅ ጥሩ ነበር። ወይም አሁን ከ20 ዓመታት በኋላ ድጋሚ ለሕዘቡ በ‹ሪፈረንደም› ቢቀርቡና የሕዝቡ ዳኝነት ቢሰማ የበለጠ ጥሩ ነበር።

የውይይቱ ውጤቶች ተሰብስበው ኮሚሽኑ ውስጥ ባሉ ባለሙያዎች ወደ ሕገ መንግሥታዊ አንቀጾች ተቀይረዋል። በዚሁ ግዜ፣ የውጭ የሕገ መንግሥት ዐዋቂዎች የራስን ዕድል በመወሰን፣ በፌዴራሊዝም እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የሌሎች አገር ተሞክሮዎችን አካፈሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ሥራቸውን ኮሚሽኑ እንዲወያይበት አቀረቡ። የተለያየ አቋም ባላቸው ሰዎች መካከል የሞቀ ውይይት ተካሄደበት። ከዚያም ድምፅ ተሰጠበት እና ሁሉም አንቀጾች ሊባል በሚችል መልኩ በአብላጫ ድምፅ ፀደቁ። በጥቂት አንቀጾቸ ጉዳይ ላይ ብቻ ምንም ዓይነት ማመቻመች (compromise) አልተደረገም፤ የሕዳጣን ቡድኖች ፍላጎት አልተተወም። በዚህ ረገድ ተቀናቃኝ የነበሩ ሁለት አቋሞች በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ተካትተው ለምክር ቤቱ ቀረቡ። ለምሳሌ አንቀጽ 39 (የራስን ዕድል በራስ መወሰን) እና አንቀጽ 40 (የንብረት መብት) ከነዚህ ውስጥ ይገኛሉ። የመጨረሻው እና 72 አንቀጾች የያዘው የሕገ መንግሥት ረቂቅ በመጋቢት 1986 ለምክር ቤቱ ቀረበ። ምክር ቤቱ 545 ሰዎች (አሁን 547 ናቸው) ያዘ። በግንቦት 1986 ምርጫው ተደርጎ፣ ከሕዳር እስከ ታኅሣሥ 1987 ድረስ ለስድስት ሳምንታት ጉባኤ ተካሔደ። የክልል ውክልናን በተመለከተ፣ ከሐረሪ 37፣ ከአዲስ አበባ 23፣ ከድሬ ዳዋ 2 ተወክለዋል።

መጨረሻ ላይ የፀደቀው 106 አንቀጾችን የያዘ ነው። ሁለቱ አንቀጾችን ማፅደቅን በተመለከተ በተደረገው ክርክር፣ የሕገ መንግሥት አርቃቂው ኮሚሽን እና በወቅቱ 515 አባላት የነበሩት ምክር ቤት አንቀጽ 39ን በተመለከተ 508ቱ ሲደግፉት 5ቱ ብቻ ተቃውመው 2ቱ በተዐቅቦ አሳልፈውታል። አንቀጽ 40ን በተመለከተ፣ በ3 ተዐቅቦ እና 496ቱ ደግፈውት አልፏል። 500 የሽግግር ምክር ቤት አባላት ፌዴራል ስርዓቱን ሲደግፉ፣ 5 ተቃውመው፣ 2 በተዐቅቦ አሳልፈውታል። በሚገርም ሁኔታ ግን፣ ከነሱ ውስጥ 24ቱ ነጻ ፍርድ ቤት መኖሩን ሲቃወሙ 494 ደግፈውት፣ በ9 ተዐቅቦ አልፏል። ያም ሆነ ይህ፣ ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ በኋላ፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ን የመመሥረቱ ሥራ ተጀመረ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫ በ1987 ተካሔደ። የተወካዮች ምክር ቤት በነሐሴ 1987 ተሰበሰበ እና የሕገ መንግሥቱን የአገሩ የበላይ ሕግነት ተቀበለ እና ሕገ መንግሥቱን ፈርሞ የሚያፀድቀውን ፕሬዚደንት መረጠ።

ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ የተቋቋመው የራስን ዕድል በራስ በመወሰን፣ የጋራ እና የተናጥል አመራር መርሖች ላይ ነው።

የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 47 የፌደሬሽኑ አባል ክልሎች በማድረግ 1. ትግራይ 2. አፋር

3. አማራ 4. ኦሮሚያ 5. ሶማሊ 6. ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ 7. የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች 8. ጋምቤላ እንዲሁም 9. ሐረሪን የያዘ ሲሆን፤ ከዚህም በኋላ የተጨመሩትን የአዲስ አበባና የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ይዟል። በሕገ መንግሥቱ እነዚህ ክልሎችናና የከተማ አስተዳደሮች የራሳቸው ሥልጣን ያላቸው ሲሆን፣ ተጠሪነታቸው ለፌደራል መንግሥቱ መሆኑ ደግሞ ሌላ ገጽታው ነው። የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (2 እና 3) የየክልሎቹና የከተማ አስተዳደሮቹ ነዋሪዎች ደግሞ በተወካዮቻቸው ይወከላሉ። ለሁሉም ክልሎች ዕኩል ሥልጣን የሚሰጠው የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 47 በንዑስ አንቀፅ 2 ላይ ለሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራሳቸውን ክልል የመመሥረት ሥልጣን ይሰጣል። የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 በበኩሉ የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶችን ሕገ መንግሥትን የመቅረጽና የማሻሻል ሥልጣንን ሰጥቶ መሥርቷቸዋል። እንዲሁም በአንቀፅ 61 እና 62 ላይ ሕገ መንግሥትን የመተርጎም ሥልጣንን ጨምሮ፤ በክልሎች መካከል በጀትን የመደልደልን ሥልጣን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ይሰጣል። ክልሎች ከፌደራል መንግሥቱ ተነጥለው የራሳቸውን ግብር የመሰብሰብ ሥልጣን ሕገ መንግሥቱ የሚሰጥ ሲሆን። የፌደራል መንግሥቱ በመንገድ፣ ኤሌክትሪክ እና ግድቦች ግንባታ በዋናነት በመሳተፍ ክልሎችን የራሳቸውን የክልል ሚሊሻ ማቋቋምን ጨምሮ በአካባቢያዊ ጉዳዩች ላይ ዋነኛ ተዋናዮች እንዲሆኑ አድርጓል።

መደምደሚያበአጠቃላይ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት

ብዙዎች እንደሚፈሩት አገሪቱን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን በማክበር እየበታተናት አይደለም። ለዚህም ጥሩ ማሳያው በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ይህ ነው የሚባል የእርስ በርስ ጦርነት አለመኖሩ ነው።

ነገር ግን የፌደራል ስርዓቱ ተግዳሮቶች የሉትም ማለት አይደለም። ለመጥቀስም ያህል ‹በፌደሬሽን ምክር ቤት ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በፌደሬሽን ምክር ቤት ያላቸው ውክልና ጥያቄ፣ የሀብት ክፍፍል ቀመር፣ የርዕዮተዓለም አለመግባባቶች የሚጠቀሱ ሲሆን፣ የርዕዮተዓለም ውዝግቡ የግለሰብ ወይንስ የቡድን መብት ይቅደም? በፌደራል ስርዓቱ እንቀጥል ወይስ ወደ ቀድሞው አሃዳዊ ስርዓት እንመለስ?› የሚሉ ጥያቄዎች ሲኖሩ፣ ፌደሬሽኑ በቋንቋና ብሔር ላይ መሠረት ያደረገ መሆኑ አሁን ያለው የቋንቋ ፖሊሲ… ላይም ጥያቄ የሚያነሱ አሉ። የብሔር ግጭቶችም በግጦሽ ቦታና በውኃ ምክንያት በተደጋጋሚ ይነሳሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማስፋት የተደረገው ጥረት በኦሮሞ ተማሪዎች፣ ገበሬዎች፣ የከተማ ነዋሪዎች እና በፖሊስ መካከል ትልቅ ግጭት መቀስቀሱም የቅርብ ጊዜ

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚደንት እና የታሪክ ተማራማሪ ናቸው። በኢሜይል አድራሻቸው

[email protected] ይገኛሉ።