ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46...

49
የኢ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008

Upload: others

Post on 12-Mar-2020

18 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008

Page 2: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴቶች

ተልዕኮ (Mission)

በመላ ሀገሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርትን በማስፋፋትና ተተኪ አትሌቶችን በብዛትና በጥራት

በማፍራት በአለም አቀፍ መድረኮች የአገራችንን ውጤታማነት ጠብቆ ማቆየት፤

ራዕይ (Vision)

በ2012 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት በአለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ምርጥ 5 ውጤታማ

ሃገሮች ተርታ ተሰልፋ ማየት፡፡

እሴቶች (Value)

ግልፀኝነትና ተጠያቂነት

መልካም ስምና ዝና

የላቀና ተደራሽነት ያለው አገልግሎት

ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት

ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት

ገለልተኝነት

ቅልጥፍናና ውጤታማነት

Page 3: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የዜና መፅሔቱ ስርጭት

ለባለድርሻ አካላት፣

መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣

ለአትሌቶች፣ ለአሰልጣኞች፣ ለዳኞች፣ ለማናጀሮች፣

ለአትሌቲክስ ስፖርት ቤተሰቦች፣

ዋና አዘጋጅ

ስለሺ ብሥራት

0911-637648/ 0116-479678

ዲዛይንና የለቀማ ሥራ

ልዑል ሰገድ እሸቱ

መረጃ አቅርቦት

ዮሐንስ እንግዳ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አድራሻ

ጉርድ ሾላ

ስልክ - 0116-479765/0116-479678

ፋክስ - 0116-450879

ድረ ገፅ www.eaf.org.et

ኢ-ሜል [email protected]

Facebook Ethiopian Athletics Federation or Ethiopian Ath Fed eaf

Page 4: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ማውጫ

ርዕስ ገፅ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት መልዕክት …………………………………………….

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ መልዕክት …………………………………………..

ዓመታዊ ክንውኖች ……………………………………………………………………………………………………

ማህበራት ማደራጃና ማዘውተሪ ስፍራዎች ………………………………………………

ትምህርትና ሥልጠና …………………………………………………………………………………….

ውድድሮች …………………………………………………………………………………………………

እናስተዋውቃችሁ ………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከየት ወደ የት?...………………………….…………..….

ኢትዮጵያ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ስፖርት /ከብራዛቪል እስከ ብራዛቪል/ …………..

አልኮል በአካል ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ………………………………………………………

ትውስታ …………………………………………………………………………………………………………….……

Page 5: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት መልዕክት፡-

የተከበሩ አቶ አለባቸው ንጉሴ - የኢአፌ ፕሬዝዳንት

ስፖርት ለአንድ ሃገር ህዝብ ሁለንተናዊ አቋም መሟላት አስፈላጊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታወቀና እየታመነበት

መጥቷል፡፡ ከዚህ አኳያ የአትሌቲክስ ስፖርትም ለሃገራችን ህዝብ ይሄንን ሚና ከሚጫወቱ ስፖርቶች ቀዳሚው ነው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እስከ አሁን ካከናወናቸው የለውጥ እንቅስቃሴዎች መካከል የመዋቅርና

የአደረጃጀት ጥናት ክለሳ፣ የአትሌቶች ስልጠና አሰጣጥ፣ የባለሙያዎችን አቅም የመገንባትና ውድድሮችን የማስፋፋት፣

የማህበራት አደረጃጀት፣ ክትትል፣ ድጋፍና የማብቃት ሥራዎች፣ መረጃ የማሰባሰብ፣ ማደራጀትና የግምገማ ሥራዎችንና ልዩ

ልዩ የኮሙኒኬሽን ተግባራትን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራቸው ይገኛል፡፡

ፌዴሬሽኑ የአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፉን ከመሰረቱ የማጠናከርና የማስፋፋት ራዕዩን በዘላቂነት ለማረጋገጥ

የሚያስችሉ የአሰራር ደንቦችና መመሪያዎችን ቀርፆ የሚመለከታቸው አካላት ገንቢ ሃሳብ ተካትቶ በጠቅላላ ጉባኤ አፀድቆ

ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ በዚህ እንቅስቃሴው የሃገራችንና የፌዴሬሽኑ የገፅታ ግንባታ፣ እንዲሁም በፋይናንስ አቅም ራስን

የመቻል አካሄዶች መታየት ችለዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ፌዴሬሽኑ የራሱ የሆነ ደረጃውን የጠበቀ፣ ለሃገሪቱም ሆነ ለፌዴሬሽኑ ቋሚ

የገቢ ምንጭና ሃብት ሊሆን የሚችል ህንፃ ከመገንባቱም በላይ የራሱ የሆነ ሆቴል ባለቤት መሆን ችሏል፡፡

በዚህም ፌዴሬሽኑ እንደ አዲዳስ ካሉ ስፖንሰር አድራጊዎችና ከልዩ ልዩ አካላት ከሚያገኘው ገቢ በተጨማሪ

ራሱን በራሱ ለማስተዳደርና የሃገሪቱን የአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ከሌሎች ሃገራት፣ አህጉራትና ዓለማት ጭምር ተፎካካሪና

ብልጫ ያለው አድርጎ ለማቅረብ በሚደረገው እንቅስቃሴ መልካም የሚባል ጅማሬ አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ ይሄንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠልና በመደገፍ ፌዴሬሽኑም ሆነ ባለድርሻ አካላት

ይህንን አላማ ተጋሪና ተባባሪ ትሆኑ ዘንድ በራሴና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስም የአክብሮት ግብዣዬን

አቀርባለሁ፡፡

Page 6: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አመሰግናለሁ!!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ መልዕክት፡-

አቶ ቢልልኝ መቆያ - የኢአፌ ጽ/ቤት ኃላፊ

የሃገሪቱን የአትሌቲክስ ስፖርት በበላይነት እየመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከተቋቋመበት ከ1941

ዓ. ም. ጀምሮ 67 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በነዚህ ዓመታት ከአትሌቲክስ ክንውኖች ጋር በተያያዘ በርካታ ተግባራትንም

አከናውኗል፡፡ ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞችም ሲስተዋሉ ቆይተዋል፡፡ ይሁንና ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት ያሉትንና የነበሩትን ጠንካራ

ጎኖች በመለየትና ችግሮቹን በመፈተሸ በሰው ሃብት አደረጃጀትና በአሰራር ልቆ ስልጠናንና የአገር ውስጥ ውድድሮችን

ለማስፋፋት፣ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ከምንግዜውም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የለውጥ ተግባራትን አጠናክሮ ወደፊት

የተሻለ አሰራርና አደረጃጀት በመፍጠር ወደ ተግባር መግባት እንዳለብን ተሰምሮበታል፡፡

ፌዴሬሽናችን እስከ አሁን ካከናወናቸው የለውጥ እንቅስቃሴዎች መካከል የተሻሻለ የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት

በማካሄድ ወደ ትግበራ ምእራፍ ላይ መገኘቱ በዋናነት የሚጠቀስ ሆኖ፣ የአትሌቶችን ስልጠና አሰጣጥ፣ የባለሙያዎችን አቅም

የመገንባትና አገር አቀፍ ውድድሮችን የማስፋፋት እንቅስቃሴዎች፣ የማህበራትና የክለቦች አደረጃጀት፣ ክትትል፣ ድጋፍና

የማብቃት ሥራዎች፣ የመረጃ አሰባሰብ፣ አደራጃጀትና የኢቫሉዌሽን ሥራዎች፤ እንዲሁም ልዩ ልዩ የኮሙኒኬሽን ተግባራት

በዋናነት በተሸለ አሰራር ማሳደግ ከሚጠቀሱ ተግባራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ፌዴሬሽኑ አሁን የተያያዘውን የአትሌቲክስ ስፖርት

ዘርፍ ከሥር መሰረቱ የማጠናከርና የማስፋፋት አላማ በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የBSC አተገባበር ስልጠና በማመቻቸት

የማስተግበሪያ ማንዋሎችና መመሪያዎችን ቀረፆ ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በአጠቃላይ ፌዴሬሽኑ በዚህ እንቅስቃሴው የአመለካከት፣ የክህሎትና የአሰራር ክፍተቶችን በመለየትና የመፍትሄ

አቅጣጫ በማስቀመጥ የፌዴሬሽኑን ገፅታ በመገንባት፣ እንዲሁም ፌደሬሽኑ በገቢ ከዚህ በፊት ከነበረው እንቅስቃሴ በላይ

በመስራት አቅሙን ማጎልበት ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም የክልልና ከተማ አስተዳደር የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች፣ የአትሌቲክስ የሙያ

ማህበራት፣ ክለቦችና ማናጀሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የፌዴሬሽኑን ራዕይ ለማሳካትየሃገራችንን

መልካም ገጽታ በልዩ ልዩ የአለም መድረክ ለማስታወቅ በርብርብና በመደጋገፍ መስራት እናዳለብን በራሴና በኢትዮጵያ

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!!

Page 7: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

ክቡር አቶ አለባቸው ንጉሴ፣ ፕሬዝዳንት

ዶ/ር ኢንጅነር መሰለ ኃይሌ፣ ም/ሬዝዳንት

አቶ መዓር አሊ፣ አቃቢ ነዋይ

የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥላሁን፣ አባል አቶ አብዱረሂም መሃመድ፣ አባል ዶ/ር በዛብህ ወልዴ፣ አባል ዶ/ር ሳምሶን ባዩ፣ አባል

Page 8: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አትሌት መሰረት ደፋር የኢት/አትሌቶች ማ/ ም/ፕሬ/ አባል አትሌት ስለሺ ስህን የኢት/አትሌቶች ማ/ፕሬ/ አባል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት

ከላይ አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ፅ/ቤት ኃላፊ፣ ከግራ የተከበሩ አቶ ዱቤ ጅሎ የአት/ስፖ/ማስ/ማል/የሥራ ሂደት

ዳይሬክተር፣ ከመሃል አቶ ዮሐንስ እንግዳ የኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት ተወካይ፣ ከቀኝ ወ/ሮ ሸዋይነሽ ገዛኸኝ

የፋ/ግ/ን/የሰ/ሃብ/አስ/የስራ ሂደት ዳይሬክተር ናቸው፡፡

Page 9: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የአመታዊ ክንውኖች አጫጭር ዜናዎች

ዜና አትሌቲክስ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ /ከጥቅምት 12 – 13/2007/

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከጥቅምት 12 – 13/2007 ዓ. ም. በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ

ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጠቅላላ ጉባዔው የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የስፖርት ሴክተር ኃላፊዎች፣ የአትሌቲክስ

ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ የክለብ ተወካዮች፣ የአሰልጣኞችና ዳኞች ማህበር ተወካዮችና የአትሌቶች ተወካዮች የተሳተፉ

ሲሆን በጉባዔው የ2006 በጀት አመት የሥራ ክንውን፣ የ2007 በጀት አመት እቅድና ልዩ ልዩ የአሰራር መመሪያዎች ላይ

ውይይት የተደረገና የማዳበሪያና ማሻሻያ ሃሳቦች ቀርበው ጸድቀዋል፡፡ ጉባዔው በቀጣይ ፌዴሬሽኑ ሊተገብራቸው የሚገቡ

ዋና ዋና ጉዳዮችን አድምቆ ያሰመረባቸው መሆኑም ያለፈው ዓመት ትውስታ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጉባዔው ሂደት

የፎቶ ኤግዚቢሽንና በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የበቆጂ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በተሳታፊዎችና በጋዜጠኞች

ተጎብኝቷል፡፡

የኢአፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በከፊል

Page 10: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የጉባዔው ተሳታፊዎች 1

የጉባዔው ተሳታፊዎች 2

የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን (CAA) ኢትዮጵያ ለ12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እያደረገች

ያለውን ዝግጅት ገምግሟል

ህዳር ወር 2007 ላይ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ወደ አዲስ አበባ የላከው ገምጋሚ ቡድን በኢትዮጵያ

አስተናጋጅነት በየካቲት ወር መጨረሻ ለ5 ተከታታይ ቀናት ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው 12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች

አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ ዝግጅቱንና ተያያዥነት ያላቸውን እንቅስቃሴዎች

ገምግሞ ተመልሷል፡፡ በውጤቱም የዝግጅቱ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑንና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት

ለሚመለከታቸው አካላት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

Page 11: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የCAA ምክትል ፕሬዝዳንትና የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) የኣለም አገር አቋራጭ ሩጫ ውድድር

ዳይሬክተር ሚስተር ዴቪድ ኦኮዮና ዋና ፀሐፊው ሚስተር ላሚን ፋቲህ፣ እንዲሁም በCAA የካውንስል አባልና የምስራቅ

አፍሪካ ሪጅን አትሌቲክስ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ኢንጂነር ሳዲቅ ኢብራሂም የተመራው ገምጋሚ ቡድን በአገሪቱ በነበረው የ3

ቀናት ቆይታ ዝግጅቱን ትኩረት ሰጥቶ ጎብኝቷል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ ቡድኑ በአዲስ አበባ በነበረው የ3 ቀናት

ቆይታ በዋናነት የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ አወቃቀርና የእቅድ ዝግጅት፣ እንዲሁም የውድድርና የማዘውተሪ ቦታዎች፣

የማሟሟቂያ ሜዳ፣ ሲኤኤ ከውድድሩ በፊት ለሚያካሂደው የኮንግረስና የካውንስል ስብሰባ አመቺ የሆነ መሰብሰቢያ

አዳራሽ፣ ማረፊያ ሆቴልና መሰል ጉዳዮችን ቅድመ ዝግጅት ተመልክቶ መመለሱን ገልፀዋል፡፡

ማህበራት ማደራጃና ማዘውተሪ ስፍራዎች

ማዘውተሪያ /ሰንዳፋ/

ከ14 አመታት በላይ እንደሆነው የሚነገርለት የሰንዳፋ በኬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ መንደር በወቅቱ ተጀምሮ በተቋረጠው

የገንዘብ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ ምክንያት የግንባታ ሥራው ሳይጀመር ለረጅም አመታት ቆይቶ ከ2006 አመተ ምህረት

መገባደጃ ጀምሮ ግን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በራሱ ጥረት ለዲዛይንና ለመጀመሪያ ደረጃ ግንባታ ሥራ በበጀተው

10 ሚሊዮን ብር ገንዘብ አማካይነት የአሸዋ ሜዳ፣ የሰልጣኝ አትሌቶች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያና መፀዳጃ ቤት ግንባታ

በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለማሰልጠኛ መንደሩ የኤሌክትሪክ አቅርቦት የተመቻቸለት ሲሆን የውሃና የመንገድ መሰረተ

ልማቱ በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ‹

‹‹

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰንዳፋ በኬ አካባቢ የሚገኘውና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የሚያስገነባው የሰንዳፋ በኬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ መንደር አሁን ያለበት ደረጃ ይህን ይመስላል፤

Page 12: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ማህበራት፤

የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር በይፋ ተቋቋመ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥር 25/2007 ዓ. ም. በአይነቱ የመጀመሪያና ለክልሎች/ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም

ለሌሎች የስፖርት ማህበራትና ፌዴሬሽኖች በመልካም ምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችለውን የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበርን

በይፋ አቋቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቶች ከዚህ በፊት ህጋዊ የሆነና የራሱ መተዳደሪያ ደንብና አሰራር ያለው ማህበር

ያልነበራቸው ሲሆኑ አሁን የተቋቋመው ማህበር ግን በመንግስት፣ በፌዴሬሽኑና በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች

ማህበር እውቅናና ህጋዊ ሰውነት ያለው ነው፡፡

በሂደቱም ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በውክልና የተመረጡ አትሌቶችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት

የማህበሩ ፕሬዝዳንት፣ ም/ፕሬዝዳንት፣ አቃቤ ነዋይ፣ ፀሐፊና 3 የማህበሩ አባላት ተመርጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በከፊል

በዚህ መሰረት፡-

1. አትሌት ስለሺ ስህን - ከኦሮሚያ ክልል - የማህበሩ ፕሬዝዳንት

2. አትሌት መሠረት ደፋር - ከአዲስ አበባ ከተ/አስ/ - የማህበሩ ም/ፕሬዝዳንት

3. አትሌት ማርቆስ ገነቲ - ከኦሮሚያ ክልል - የማህበሩ አቃቢ ነዋይ

4. አትሌት የማነ ፀጋዬ - ከትግራይ ክልል - የማህበሩ ፀሐፊ

5. አትሌት ሞስነት ገረመው - ከአማራ ክልል - የሥራ አስ/ ኮ/ አባል

6. አትሌት ግርማይ ብርሃኑ - ከሐረሪ ክልል - የሥራ አስ/ ኮ/ አባል

7. አትሌት ፋንቱ ማጊሶ - ከደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል - የሥራ አስ/ ኮ/ አባል በመሆን ተመርጠዋል፡፡

Page 13: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ትምህርትና ስልጠና

እ.ኤ.አ. 2014/15 በአህጉርና አለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ተካፋይ የሚሆኑ ብቁና ተፎካካሪ

አትሌቶችን ለማፍራት የሚያስችል የብሔራዊ ቡድን አትሌቶችና አሠልጣኞች መረጣ ቀዳሚው ስራ ነበር፡፡

በ2006 ዓ. ም. በነበሩ የሃገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ተካፋይ እና ውጤታማ አትሌቶችን በመምረጥ እንዲሁም

አመታዊውን ስልጠና በመገምገምና ውጤታማ የሆኑ አሠልጣኞችን በመለየት በተጨማሪም በተጓደሉ አሠልጣኞች

ምትክ በመቅጠር በድምሩ 30 አሠልጣኞችና በየኢቨንቱ የተለዩ 280 አትሌቶችን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ

በማካተትና በስልጠና ውስጥ እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡

የአሰልጣኝነት ስልጠና

የ2ኛ ደረጃ አሠልጣኝነት ሥልጠና በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ በኦሮሚያ ሻሸመኔ፣ በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ፣ በወሎ፣

በአክሱም እና በድሬደዋ ዩኒቨርስቲዎች ወንድ 143 ሴ 53 ድምር 196 አሠልጣኞች የተፈሩ ሲሆን የ1ኛ ደረጃ አሠልጣኝነት

ሥልጠና በጋምቤላ በአዳማ ከተሞች ወንድ 14፣ ሴት 31፣ በድምሩ 45 አሠልጣኞች ተፈርተዋል፡፡ በተጨማሪም ከክልሎችና

ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የ1ኛ ደረጃ የሌክቸረርነት ሥልጠና በአዳማ ከተማ ወንድ 19፣ ሴት 1፣ በድምሩ ለ20

ባለሙያዎች ተሠጥቷል፡፡ በተጨማሪም ከብሔራዊ ቡድን እና ከክለቦች ለተውጣጡ አሠልጣኞች ወንድ 38፣ ሴት 8፣

በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ 35፣ ሴት 9፣ በድምሩ ለ44 ባለሙያዎች

ተሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ ወንድ 249፣ ሴት 102፣ በድምሩ 351 ባለሙያዎች ማፍራት ተችሏል፡፡

የዳኝነት ስልጠና

የዳኞች ስልጠናን በተመለከተ በበጀት ከ9 ክልሎችና 2 ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡና 9ዐ ለሚሆኑ ዳኞች ስድስት

የዳኝነት ኮርስ ሌክቸረሮችን በመመደብ በሦስት ዙር የ2ኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠናዎችን

በመስጠት፤ ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ 60 ዳኞች አንድ ሌክቸረር ከIAAF በማስመጣት የአለም አቀፉን

አትሌቲክስ ማህበር የመጀመሪያ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና አግኝተው ለሁለተኛ ደረጃ ስልጠና እንዲያልፉ ከማድረግ

ባለፈ ከጥር 26 - 29/2007 ዓ. ም. በአዲስ አበባ የተካሄደውን 12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና

በአግባቡ መምራት የቻሉ ባለሙያዎችን ማፍራት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላ ወንድ 11፣ ሴት 2፣ በድምሩ 13

የ1ኛ ደረጃ፤ የዳኝነት ስልጠና፣ በሽሬና በደብረ-ብርሀን ወንድ 38፣ ሴት 13፣ በድምሩ 51 የ2ኛ ደረጃ የዳኝነት ስልጠና የተሰጠ

ሲሆን በድምሩ 214 ባለሙያዎች የሀገር ውስጥ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

ስልጠናውን ከወሰዱ የአትሌቲክስ ዳኞች በከፊል

Page 14: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ከታህሣሥ 5 - 20/2007 ዓ. ም. በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና ትግራይ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

በሚገኙ 26 የአትሌቲክስ ክለቦች፤ 36 ማሠልጠኛ ኘሮጀክቶች፣ 4 ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ በየክልሉ አትሌቲክስ

ፌዴሬሽኖችና በየዞኑ በሚገኙ የስፖርት ጽ/ቤቶች ላይ ያለውን የአደረጃጀት፣ ስልጠናና ውድድርን በተመለከተ

ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የተወጣጡ ባለሙያዎችና የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞችን ያቀፈ ግብረ ኃይል በመላክ

ሙያዊ ድጋፍ መስጠት ተችሏል፡፡

በውድድር ዘርፍ

3ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ውድድር ነሐሴ 20-25/2007 - አሰላ

በ3ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ውድድር 11ዱም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተካፈሉ ሲሆን ወንድ

171፣ ሴት 166፣ በድምሩ 337 አትሌቶች ተወዳዳሪ ሆነዋል፡፡

የውድድሩ ዋነኛ ዓላማዎችም፡-

1. በክልሎችና በከተማ አስተዳድሮች ለሚገኙ የታዳጊዎች ስልጠና ኘሮጀክት አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤

2. ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤

3. የታዳጊዎች አትሌቲክስ ኘሮጀክቶችን ስልጠና አፈፃፀም ለመመዘን ነው፡፡

በውጤቱ መሰረትም፡-

ተ.ቁ. ክልል/ከተማ አስ. ወርቅ ብር ነሐስደረጃ

ወ ሴ ድምር ወ ሴ ድምር ወ ሴ ድምር

1 ኦሮሚያ 8 8 16 6 6 12 7 10 17 1ኛ

2 አማራ 6 7 13 4 8 12 2 4 6 2ኛ

3 ትግራይ 2 - 2 4 - 4 5 2 7 3ኛ

ከላይ የተመለከተውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

16ኛው የኢትዮጵያ ሪሌይ ማራቶን ውድድር ጥቅምት 16/2007 - ባህር ዳር

ጥቅምት 16/2007 ዓ. ም. በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው 16ኛው የኢትዮጵያ ሪሌይ ማራቶን ውድድር በአጠቃላይ 19

ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች በ57 ወንድ፣ በ57 ሴት፣ በድምሩ በ114 አትሌቶች ተካፋይ ሆነውበት ነበር፡፡ ሪሌይ

ማራቶን ወንዶችና ሴቶች በመሰባጠር አንድ ላይ የሚወዳደሩበት ሩጫ ሲሆን እያንዳንዱ ክልል፣ ከተማ አስተዳደርና ክለብ

3 ወንድ፣ 3 ሴት፣ በጠቅላላ በ6 አትሌቶች ይወዳደራል፡፡ እነዚህ ተወዳዳሪዎች በሚያደርጉት የጋራ ጥረት ለውጤት

ይበቃሉ፡፡ በስፍራው ተገኝተው ሲያዩት ይበልጥ አጓጊ ውድድር እንደሆነም ይረዳሉ፡፡ በሩጫው ሂደት ታሱኪ የሚባል

ለቅብብል የሚገለገሉበትና በእጅ ውስጥ የሚጠለቅ ጨርቅ ይያዛል፡፡ ጃፓኖች የዚህ ውድድር ጠንሳሾች እንደሆኑም

ይነገራል፡፡

የውድድሩ ዓላማ

Page 15: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ለክልሎች፣ ከተማ አስተዳድሮችና ክለቦች የጐዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዕድል ለመፍጠር፣

ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣

ክልሎች፣ ከተማ አስተዳድሮችና ክለቦች በሪሌ ማራቶን ውድድር ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ የሚል ሲሆን፣

በውጤቱም መሰረት፡-

ተ.ቁ.

ክልል/ክለብ/ከተማ

አስተዳደር

1ኛ ሌግ5ኪ.ሜወንድ

2ኛ ሌግ5ኪ.ሜሴት

3ኛ ሌግ10ኪ.ሜወንድ

4ኛ ሌግ5ኪ.ሜሴት

5ኛ ሌግ10ኪ.ሜወንድ

6ኛ ሌግ7.195ኪ.ሜ

ሴት

ሰዓትውጤት42.195ኪ.ሜ

ደረጃ

1. ፌ/ማረሚያ

ቤቶች

13፡34.53

ሲሳይ

ኡምኔሳ

16፡04.01

ገነት

ኡዱቃድር

27፡49.88

ይግረም

ደመላሽ

15፡05.14

ሰንበሬ ተፈሪ

27፡58.03

ያሲን ሐጂ

22፡16.03

ሩቲ አጋ

2፡02፡48 1ኛ

2. መከላከያ 13፡09.08

ኢማና

መርጊያ

15፡07.49

ገነት ያለው

28፡26.63

ንጉሤ ጫላ

15፡46.74

ሽቶ ውዴሳ

28፡28.19

አታላይ

ይርሳው

22፡25.39

አባብል የሻነህ

2፡03፡24 2ኛ

3. አማራ ክልል 13፡09.28

አቤ ጋሻው

15፡40.13

አበበ እጅጉ

28፡05.84

ካሳሁን አበራ

15፡53.46

ፍርኑስ

ወርቅነህ

27፡58.83

ፅዳት አበጀ

22፡37.59

ስንታየሁ ለወጠኝ

2፡03፡26 3ኛ

4. ኢትዮጵያ ንግድ

ባንክ

13፡34.25

የኔው

አላምረው

16፡11.91

ምህረት

ደርቤ

27፡56.38

አዝመራው

መንግስቱ

15፡17.35

አለሚቱ

ሐሮዬ

28፡04.30

ልዑል

ገ/ስላሴ

22፡37.05

ሱቱሜ አሰፋ

2፡03፡42 4ኛ

5. ኦሮሚያ ክልል 13፡18.39

ታዬ ግርማ

15፡44.26

ፀሐይ ጫካ

28፡42.81

ተረፈ ደበላ

15፡24.18

ደራ ዳዲ

28፡24.85

አቡ ገለቶ

23፡05.88

ሚኪዳ አብደላ

2፡04፡41 5ኛ

6. ኢትዮጵያ

ኤሌትሪክ

13፡25.49

ንጋቱ ጌትነት

15፡03.17

አፈራ

ጉድፋይ

28፡58.82

ዘውዱ መኮንን

15፡57.71

አኸዛ ኪሮስ

28፡11.22

ፍቃዱ ሰቦቃ

23፡21.91

እታለማሁ ዘለቀ

2፡04፡59 6ኛ

16ኛው የሜ/ጀነራል ኃየሎም አርአያ መታሰቢያ 15 ኪሜ የጎዳና ሩጫ ውድድር - መቀሌ

የሜ/ጀነራል ኃየሎም አርአያ መታሰቢያ 15 ኪሜ የጎዳና ሩጫ ውድድር ለ16ኛ ጊዜ ህዳር 7/2007 ዓ. ም. በትግራይ ክልል

ርእሰ ከተማ መቀሌ የተካሄደ ሲሆን ከ9 ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከ10 ክለቦች የተውጣጡ 53 ሴቶችና 99

ወንዶች በድምሩ 152 አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ በውድድሩ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሴቶች አዲስ አበባ

በወንዶች አማራ ክልል፤ በክለቦች በሴቶች መከላከያ በወንዶች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊ ሲሆኑ በየውድድር ካታጎሪው

ከ1ኛ-6ኛ የወጡ አትሌቶች የገንዘብ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

አገር አቀፍ የሴቶች አትሌቲክስ ውድድር ታህሳስ 17 – 20/2007 - ድሬዳዋ

1ኛው ሀገር አቀፍ የሴቶች ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ከታህሣሥ 17-20/2007 ዓ.ም. በድሬደዋ ከተማ

አስተዳደር የተካሄደ ሲሆን እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች ተካፋይ የሆኑበት ውድድር ነው፡፡ ውድድሩ

Page 16: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

በዋናነት ዓላማው አድርጎ ተነሳው፡- ሴቶች በስፖርቱ ዘርፍ ቀጥተኛ ተሳትፎ እና እኩል ተጠቃሚነት መርህን በየደረጃው

ተግባራዊ በማድረግ፤ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ነው፡፡

የውድድር አይነቶች፡-

100 ሜትር፣ 200 ሜትር፣ 400 ሜትር፣ 800 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫና አሎሎ ውርወራሲሆኑ በውድድሩ ከ11 ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ 161 ሴት አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡ በሜዳሊያ ሠንጠረዥውስጥ የገቡት ግን የኦሮሚያና የአማራ ክልል አትሌቶች ብቻ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና

እድሜያቸው ከ16 – 19 አመት የሆናቸው አትሌቶች የሚካፈሉበት የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና

ውድድር ከ2004 ዓ. ም. ጀምሮ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ውድድር ነው፡፡ በርግጥ ከ2004 ዓ. ም. በፊትም የኢትዮጵያ

ታዳጊዎችና ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሚል ስያሜ ለ12 አመታት ሲካሄድ የቆየ ውድድር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከ2004

ዓ. ም. ጀምሮ ግን የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና መለየት አለበት እሚል አቋም ላይ በመደረሱ ራሱን ችሎ እንዲካሄድ

ተደርጓል፡፡

ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ይካፈሉበታል፡፡ በተጨማሪ ከክለቦችና ከብሄራዊ ቡድኑ እድሜያቸው በዚህ

ምድብ የሆኑ አትሌቶች ተካፋይ ይሆኑበታል፡፡ በዚህ ውድድር በመካከለኛና በረጅም ርቀቶች ተካፍለው አንደኛና ሁለተኛ

የሚወጡ አትሌቶች ኢትዮጵያ በምትካፈልበት በአፍሪካና በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመመረጥና ለመሳተፍ

እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-

በ1ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከቤንሻንጉል ክልል ውጪ ሁሉም ክልልና ከተማ

አስተዳደሮች ተካፋይ የነበሩ ሲሆን 385 ወንዶች፣ 315 ሴቶች፣ በድምሩ 700 የሚሆኑ አትሌቶች በየውድድር ዘርፎች

ተሳትፈዋል፡፡

በውጤቱም መሰረት፡-

የዋንጫ ተሸላሚዎች፡-

በሴቶች፡-

1) ጥ/ዲባባ- በ174 ነጥብ2) ኦሮሚያ- በ164 ነጥብ3) ኢት/ን/ባንክ- በ64 ነጥብ

በወንዶች፡-

1) ኦሮሚያ - በ180 ነጥብ2) ጥ/ዲባባ - በ176 ነጥብ3) ደቡብ - በ54 ነጥብ

Page 17: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

በአጠቃላይ ውጤት፡-

1) ጥ/ዲባባ - በ350 ነጥብ2) ኦሮሚያ - በ304 ነጥብ3) ደቡብ - በ95 ነጥብ

በ2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከጋምቤላና ኦሮሚያ ክልሎች ውጪ ሁሉም ክልልና

ከተማ አስተዳደሮች ተካፋይ የነበሩ ሲሆን 678 ወንዶች፣ 482 ሴቶች፣ በድምሩ 1,160 የሚሆኑ አትሌቶች በየውድድር

ዘርፎች ተሳትፈዋል፡፡

በውጤቱም መሰረት፡-

የዋንጫ ተሸላሚዎች፡-

በሴቶች፡-

1. መከላከያ - በ170 ነጥብ2. ፌ/ማ/ቤቶች - በ81 ነጥብ3. አማራ - በ69 ነጥብ

በወንዶች፡-

1. መከላከያ - በ115 ነጥብ2. አማራ - በ102 ነጥብ3. ጥ/ዲባባ - በ63 ነጥብ

በአጠቃላይ ውጤት፡-

1. መከላከያ - በ285 ነጥብ2. አማራ - በ171 ነጥብ3. ጥ/ዲባባ - በ158 ነጥብ

በ3ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከአዲስ አበባ፣ ከቤንሻንጉልና ከጋምቤላ ክልሎች ውጪ

ሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች የተካፈሉ ሲሆን 605 ወንዶች፣ 468 ሴቶች፣ በድምሩ 1,063 አትሌቶች በየውድድር

ዘርፎች ከጥር 7 – 10/2007 ዓ. ም. በኦሮሚያ ክልል፣ አሰላ ከተማ አረንጓዴው ስቴድየም ውድድራቸውን አካሂደዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ ተካፍለው ውጤታማ የሆኑ አትሌቶች በ2015 ማርች ወር ላይ ሃገራችን ኢትዮጵያ

ባስተናገደችውና አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ውጤቱ መሠረት፡-

1ኛ. ኦሮሚያ ክልል በ493 ነጥብ፣

2ኛ. መከላከያ ስፖርት ክለብ በ243 ነጥብ፣

3ኛ. አማራ ክልል በ119 ነጥብ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

Page 18: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር

የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር በ1976 ዓ. ም. በአዲስ አበባ ከተማ ጃን ሜዳ ውስጥ የጃን ሜዳ አገር

አቋራጭ ውድድር በሚል ስያሜ የተጀመረ ሲሆን፤ ዋነኛ አላማው ደግሞ ለአለም አገር አቋራጭ ውድድር ብቃት ያላቸውን

አትሌቶች ለመምረጥ፣ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራትና ለአትሌቶቻችን ሃገር አቀፍ የውድድር እድል ለመፍጠር የሚል ነው፡፡

የጃን ሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር ቀደም ሲል በ9 ኪ.ሜ. ወጣት ወንድና ሴቶች ላይ ብቻ ያተኩር የነበረ ሲሆን ቀስ በቀስ

በ4፣ በ6፣ በ9 እና በ12 ኪ.ሜ. ሲካሄድ ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት ግን በአለም አቀፉ የአገር አቋራጭ ሩጫ ውድድር ስታንዳርድ

መሰረት አዋቂ ወንድና ሴቶች፣ እንዲሁም ወጣት ወንድና ሴቶች በሚል የ12፣ የ8 እና የ6 ኪሎ ሜትር ውድድሮች በሚል

በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ቀደም ባሉት አመታት ከ5 በማይበልጡ ክለቦች አማካይነት እንደነ፡-

ወዳጆ ቡልቲ፣- ደረጀ ነዲ፣- መሃመድ ከድር፣

- አልማዝ ለማ፣- በላይነሽ በቀለና የመሳሰሉት

ወደ መካከለኛው ዘመን ደግሞ የክለቦች ቁጥር ወደ 11 አድጎ እንደነ፡-

- ቀነኒሳ በቀለ፣- ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም፣- ጌጤ ዋሚ፣- አብዮት አባተ፣

- ሃይሉ መኮንን፣- ሚሊዮን ወልዴ፣- ለኢላ አማን፣- እየሩሳሌም ኩማ የመሳሰሉት፣

ወደቅርቡ ዘመን ስንመጣ ደግሞ የተሳታፊ ክለቦች ቁጥር ወደ 42 አድጎ፣ እንዲሁም 9ኙ ክልሎችና 2ቱ ከተማአስተዳደሮችን በማሳተፍ እንደነ፣- እጅጋዬሁ ዲባባ- አየለ አብሽሮ፣- ሱሌ ኡቱራ፣

- አበራ ኩማ፣- መሰለች መልካሙ፣- መሃመድ አወል፣

- ብዙነሽ በቀለ፣ በላይነሽ ኦልጅራና የመሳሰሉት፣

አሁን ወዳለንበት ዘመን ስንመጣ ደግሞ እንደነ፡-- ቦንሳ ዲዳ፣- ገነት ያለው- ጎይተቶም ገ/ስላሴ፣

- ሙክታር እንድሪስ፣- ህይወት አያሌው፣

- ሃጎስ ገ/ህይወት የመሳሰሉትና ሌሎችም ስመ ጥርና ውጤታማ አትሌቶች በጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭውድድር የፈሩ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡

ለ32ኛ ጊዜ በተካሄደው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ላይም ታዋቂና ስመ ጥር የአገራችን አትሌቶችተሳትፈዋል፤

Page 19: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

በአንድ መቶ ብቻ ይቆጠር የነበረው የተሳታፊ አትሌቶች ቁጥር በአሁኑ ሰዓት በተለይም በ32ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናልአገር አቋራጭ ውድድር ላይ ወደ 1,239 አድጓል፤ የሴቶች ተሳትፎም ከ30 እና 40 በአሁኑ ወቅት ከ400 በላይ ማሳደግከመቻሉም በላይ የ9ኙ ክልሎችና 2ቱ ከተማ አስተዳደሮችና ከ40 በላይ ክለቦች ሙሉ ለሙሉ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ወደፊትደግሞ ፌዴሬሽኑ በዚህ ሳይወሰን ጥራትና ብዛት ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ሃገር ለመፍጠር ጠንክሮ ይሰራል የሚል ፅኑእምነት አለን፡፡

በ32ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ከ37 በላይ ክለቦች የብሔራዊ ቡድንንና ቬትራንን ጨምሮ፣ 9ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከግል ተወዳዳሪዎች ጭምር በ6 ኪሜ ወጣት ሴቶች 237፣ በ8 ኪሜ ወጣት ወንዶች 427፣በ8 ኪሜ አዋቂ ሴቶች 186፣ በ12 ኪሜ አዋቂ ወንዶች 389፣ ታዋቂዎቹን አትሌት ኢማና መርጋ፣ ህይወት አያሌው፣ ሃጎስገ/ህይወት፣ ገነት ያለው፣ አለሚቱ ሃሮዬ፣ በላይነሽ ኦልጅራና የመሳሰሉት በዚህ ውድድር ላይ ተካፋይ ሆነዋል፡፡

32ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ውጤት

ተ.ቁ. ካታጎሪ የግል አሸናፊ

ክልል፣ክለብ/ከተማአስተዳደር

ሰዓት ደረጃ የቡድን አሸናፊ ነጥብ ደረጃ

1.6 ኪሜወጣትሴቶች

ለተሰንበት ግደይ ትራንስ ኢትዮጵያ 20፡30.6 1ኛ ኦሮሚያ ክልል 36 1ኛዳግማዊት ክብሩ ፌዴራል ፖሊስ 20፡31.5 2ኛእታገኝ ወልዱ አማራ ክልል 20፡32.0 3ኛ አማራ ክልል 72 2ኛደራ ዲዳ ኦሮሚያ ክልል 20፡38.7 4ኛዘርፌ ልመንህ መከላከያ 20፡41.9 5ኛ መከላከያ 88 3ኛምህረት ተፈሪ መሰቦ ሲሚንቶ 20፡46.8 6ኛ

2.8 ኪሜወጣትወንዶች

ይሁንልኝ አዳነ መከላከያ 23፡31.7 1ኛ አማራ ክልል 30 1ኛያሲን ሀጂ ፌዴራል ማረሚያ 23፡32.6 2ኛአቤ ጋሻሁን አማራ ክልል 23፡32.8 3ኛ ኦሮሚያ ክልል 46 2ኛዮሐንስ መካሻ አማራ ክልል 23፡32.9 4ኛሐይማኖት አለው አማራ ክልል 23፡38.4 5ኛ ኢትዮጵያ

ኤሌክትሪክ 102 3ኛአዳነ ውለታው ብሔራዊ 23፡40.5 6ኛ

3.8 ኪሜአዋቂሴቶች

ገነት ያለው መከላከያ 26፡09.7 1ኛ ኢትዮጵያ ንግድባንክ 35 1ኛ

ማሚቱ ዳስካ ኦሮሚያ ፖሊስ 26፡17.1 2ኛሰንበሬ ተፈሪ ፌዴራል ማረሚያ 26፡27.9 3ኛ ኦሮሚያ ክልል 53 2ኛነፃነት ጉደታ ኦሮሚያ ክልል 26፡30.2 4ኛበላይነሽ ኦልጂራ ኢት/ንግድ ባንክ 26፡33.9 5ኛ መከላከያ 64 3ኛአለሚቱ ሀሮዬ ኢት/ንግድ ባንክ 26፡40.6 6ኛ

4.12 ኪሜአዋቂ

ወንዶች

ታምራት ቶላ ኦሮሚያ ክልል 35፡08.2 1ኛ ኦሮሚያ ክልል 18 1ኛቦንሣ ዲዳ ኦሮሚያ ክልል 35፡08.9 2ኛአፀዱ ፀጋዬ መከላከያ 35፡12.6 3ኛ መከላከያ 35 2ኛሐጎስ ገ/ሕይወት መስፍን ኢንጂነሪንግ 35፡18.9 4ኛተስፋዬ አበራ ኦሮሚያ ክልል 35፡20.3 5ኛ ኢትዮጵያ ንግድ

ባንክ 493ኛ

ሙክታር እድሪስ መከላከያ 35፡25.9 6ኛ

5. ቬትራን

አባተ አስታጥቄ ቬትራን 27፡08.5 1ኛአያሌው እንዳለ ቬትራን 27፡12.7 2ኛትዕዛዙ አበራ ቬትራን 28፡26.8 3ኛአድነው አበጋዝ ቬትራን 28፡52.7 4ኛምንአለ መኮንን ቬትራን 28፡57.1 5ኛይበልጣልቢያልፈው

ቬትራን 29፡11.4 6ኛ

Page 20: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ኢትዮጵያ ያዘጋጀችውን 12ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 3ኛ ሆና አጠናቀቀች

በኢአፌ የኮሙኒኬሽን ክፍል ባለሙያዎች የተዘጋጀው የሻምፒዮናው ሎጎ

እ.ኤ.አ ማርች 1/2015 ኢትዮጵያ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽንን ካውንስል ስብሰባ በድሮው የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ፣

እንዲሁም ማርች 2 እና 3/2015 ለተከታታይ 2 ቀናት የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ስብሰባን በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት

አዳራሽ ያስተናገደች ሲሆን በኮንግረሱ መክፈቻ እለት ክብርት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የኢፌዲሪ ም/ጠ/ሚ/ር ተገኝተው ንግግር

አድርገዋል፡፡

የሻምፒዮናው መክፈቻ

የእንኳን ደህና መጣችሁ እራት መስተንግዶ ደግሞ ማርች 2/2015 ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በካፒታል ሆቴል፣ በማግስቱ ማርች

3/2015 እንዲሁ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ/ር በተገኙበት በሸራተን አዲስ

Page 21: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ሆቴል የሚስተር ላሚን ዲያክ የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዝዳንትና የአፍሪካ አትሌቲክስ

ኮንፌዴሬሽን ካውንስል አባል ከካውንስል አባልነታቸው የመሸኛ ሥነ ስርዓት በሃገራችን ተስተናግዷል፡፡

ማርች 3/2015 ከማለዳው 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት የአትሌቲክስ ልኡካን ቡድን አባላት የብሔራዊ

ሙዝየማችንንና ታሪካዊ የሃገራችንን ስፍራዎች በአዲስ አበባና በአካባቢዋ በመዘዋወር እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡

ከማርች 5 – 9/2015 እ.ኤ.አ ለ5 ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ስቴድዮም በተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ

ሻምፒዮና ላይ 39 የአፍሪካ ሃገራት በ209 ሴት፣ በ145 ወንድ በአጠቃላይ በ354 አትሌቶች እና በ172 የልኡካን ቡድን

አባሎቻቸው ተካፋይ ሲሆኑ ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካ 1ኛ እና 2ኛ በመሆን ሻምፒዮናውን አጠናቀዋል፡፡ ኢትዮጵያም 6

ወርቅ፤ 12 ብር እና 10 ነሐስ በድምሩ 28 ሜዳሊያ በማግኘት ነው ውድድሯን በሶስተኝነት ያጠናቀቀችው፡፡ ኢትዮጵያ

በሰበሰበችው ሜዳሊያ ብዛት ከተሳታፊ ሃገራት ቀዳሚ ሆናለች፡፡ ኢትዮጵያ ከሰበሰበቻቸው 6 የወርቅ ሜዳሊያዎች 5ቱ

በሴቶች የተገኙ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በ12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ካሰለፈቻቸው አትሌቶች መካከል 2 አትሌቶች ከሜዳልያና

ከዲፕሎማ ውጪ ሲሆኑ 2 አትሌቶች ከውድድር ውጪ ሆነዋል፡፡ 76 አትሌቶች ከወርቅ /ከ1ኛ/ እስከ ዲፕሎማ /7ኛ/

ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡ በአጠቃላይ ይህ የተተኪዎችን የነገ ተስፋዎች አመላካች ውጤት ነው፡፡

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት በ5000 ሜትር

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ለሀገሩ ብቸኛውን በወንዶች የተገኘ ወርቅ አስመዝግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ሻምፒዮና፡-

በአትሌት ጫልቱ ሹሚ ረጋሳ 800 ሜትር ሴቶች፤

በአትሌት እታገኝ ወልዱ ማሞ 5,000 ሜትር ሴቶች፤

Page 22: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

በአትሌት የኋልዬ በለጠው ምትኩ 5,000 ሜትር ሴቶች ዕርምጃ ውድድር ፤

በአትሌት መዲና ንጉሴ በሪሶ 3,000 ሜትር ሴቶች፣ እንዲሁም

በአትሌት ዳዊት ስዩም ቢራቱ 1,500 መቶ ሜትር ሴቶች አማካኝነት ወርቅ ማግኘት ችላለች፡፡

አትሌት ጫልቱ ሹሚና ኮሬ ቶላ ወርቅና ብር በ800 ሜትር

አትሌት መዲና ንጉሴና ሹሩ ቡሎ ወርቅና ብር በ3000 ሜ

Page 23: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አትሌት እታገኝ ወልዱና ስንታየሁ ለወጠኝ ወርቅና ብር በ5000 ሜትር

ከ2 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በሞሪሸየስ ተካሂዶ በነበረው 11ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 22 ሜዳሊያ

በማግኘት በተመሳሳይ ሶስተኛ ደረጃ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡ ከተገኘው 7 የወርቅ ሜዳሊያ 6ቱ በሴቶች የተገኘ ነበር፡፡

አትሌት ዳዊት ስዩምና ባሶ ሳዶ ወርቅና ብር በ1500 ሜትር

በዚህ ውድድር ናይጀሪያ 12 ወርቅ፤ 8 ብር እና 7 ነሐስ በማግኘት የውድድሩ ፈርጥ ሆናለች፡፡ ናይጀሪያዎች በአጭር ርቀት

ውድድሮች ያሳዩት ብቃት ለበላይነት አብቅቷቸዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ 9 ወርቅ፤ 7 ብር እና 7 ነሐስ በማግኘት

በሻምፒዮናው ሁለተኛ ቦታን ተቆናጣለች፡፡ ሁለቱ ሀገራት በ11ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናም ተመሳሳይ

ውጤት ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡

Page 24: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ግብፅ እና ኬኒያ በቅደም ተከተል 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ በውድድሩ ከተሳተፉት 37 ሀገራት 18ቱ በሜዳሊያ

ሰንጠረዥ ገብተዋል፡፡ ውድድሩን 6ኛ ሆና ያጠናቀቀችው አልጄሪያ 13ኛውን የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እ. ኤ. አ.

በ2017 ለማዘጋጀት ሃላፊነቱን ከአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽንና ከኢትዮጵያ ተረክባለች፡፡ ኢትዮጵያ የተሳካ መሰናዶ

ማድረጓን ከተሳታፊዎች እና ዝግጅቱን ከሚመሩት አካላት እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሃገር ውስጥና የውጪ የሚዲያ ተቋማት

እማኝነት ማግኘት ተችሏል፡፡

ሻምፒዮናውን ከመክፈቻው ጀምሮ በየቀኑ ቁጥሩ ከ15,000 በላይ የሚገመት ህዝብ የተከታተለው ሲሆን ደማቅ የመክፈቻና

የመዝጊያ ስነ ስርአቶች ተካሂደዋል፡፡ በመክፈቻው እለት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት፣ በመዝጊያው

እለት ደግሞ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌዲሪ ም/ጠ/ሚ/ር ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡

የሻምፒዮናው መዝጊያ ሥነ ስርዓት በከፊል

መዝጊያ

Page 25: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

በዚህ ሻምፒዮና ላይ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ ጋራድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግ/ኩባንያ፣

ፀሐይ ሪል እስቴት፣ ኢትዮ - ቴሌኮም፣ ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ

ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር የነበራቸው የማይተካ የፋይናንስ፣

የቁሳቁስ፣ የጉልበትና የእውቀት ድጋፍ ለሻምፒዮናው በስኬት መጠናቀቅ ቀዳሚ ነበር፡፡

በአጠቃላይ ሻምፒዮናውን ለማካሄድ በኢፌዲሪ መንግስት፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ

ኮሚቴና በስፖንሰር አድራጊዎች አማካይነት ከ2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር /በወቅቱ የብር ምንዛሬ ከ40 ሚሊዮን ብር/

ያላነሰ ወጪ ተደርጓል፡፡

1ኛው ሃገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽንና ባዛር /በኤግዚቢሽን ማዕከል/

ክቡር አቶ አብዲሣ ያደታ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤግዚቢሽኑን ሲከፍቱ

ከመጋቢት 5 – 9/2007 ዓ. ም. ለ5 ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው የመጀመሪው ሃገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽንና ባዛር

የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ አብዲሣ ያደታና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ

ተጀምሮ መጠናቀቅ ችሏል፡፡

Page 26: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የፎቶ ኤግዚቢሽን 2007 ዓ. ም.

በፈለቀ ደምሴና በጂ.ኤም.ኤስ. ማስታወቂያና ፕሮሞሽን ድርጅቶች አስተባባሪነት የተጀመረው ይህ የስፖርት ኤግዚቢሽንና

ባዛር ለሃገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ ሲሆን አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን

ጨምሮ)፣ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም በርካታ ተቋማትና ድርጅቶች አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ፣

ምርቶቻቸውን መሸጥና ደጋፊ መመልመል የቻሉበት መልካም አጋጣሚ የተፈጠረበት ነበር፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች

እንዳስረዱት እንዲህ አይነቱ ጅምር ህብረተሰቡን ከሃገሩ ስፖርቶች ጋር ለማስተዋወቅ ሁነኛ መንገድ እንደሆነ

ከመግለፃቸውም በላይ በቀጣይ በተጠናከረና በተሻለ መንገድ ሊዘጋጅ እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡ በተጨማም አስተያየት

ሰጪዎቹ አንድ ሃገር አቀፍ የስፖርት ሙዚየም ቢኖር ለዜጎችም ሆነ ለቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው

ተናግረዋል፡፡

2ኛው ሃገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች የአትሌቲክስ ውድድር በባህር ዳር ከተማከመጋቢት 6 – 20/ 2007 ዓ. ም. ለ15 ቀናት ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር የአትሌቲክስ

ስፖርትን ጨምሮ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

1ኛ ኦሮሚያ ክልል - በ24 ወርቅ፣ 21 ብር፣ 11 ነሐስ በድምሩ 56 ሜዳልያ፣

2ኛ አማራ ክልል - በ10 ወርቅ፣ 8 ብር፣ 15 ነሐስ በድምሩ 33 ሜዳልያ፣

3ኛ ትግራይ ክልል - በ2 ወርቅ፣ 1 ነሐስ፣ በድምሩ 3 ሜዳልያ፣

4ኛ አዲስ አበባ ከ/አስ/ - በ1 ወርቅ፣ 4 ብር፣ 6 ነሐስ፣ በድምሩ 11 ሜዳልያ፣

5ኛ ደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል - በ3 ብር፣ 2 ነሐስ፣ በድምሩ 5 ሜዳልያ፣

6ኛ ጋምቤላ ክልል - በ1 ብር፣ 2 ነሐስ፣ በድምሩ 3 ሜዳልያ በማግኘት ከ1ኛ - 6ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን

አጠናቀዋል፡፡

Page 27: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

2ኛው አገር አቀፍ የተማሪዎች አትሌቲክስ ውድድር

2ኛው አገር አቀፍ የተማሪዎች አትሌቲክስ ውድድር ከመጋቢት 17-20/2007 ዓ.ም. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ

መንግስት በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ውድድር ከ11 ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ 204 ሴቶችና 241

ወንዶች በድምሩ 445 አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡ በውድድሩም ኦሮሚያ 24 ወርቅ፣ 21 ብር፣ 11 ነሐስ በድምሩ 56 ሜዳሊያ፤

አማራ ክልል 1ዐ ወርቅ፣ 8 ብር፣ 15 ነሐስ በድምሩ 33 ሜዳሊያ፤ ትግራይ ክልል 2 ወርቅ፣ 1 ነሐስ በድምሩ 3 ሜዳሊያ፤

አዲስ አበባ 1 ወርቅ፣ 4 ብር፣ 6 ነሐስ በድምሩ 11 ሜዳሊያ፤ ደቡብ ክልል 3 ብር፣ 2 ነሐስ በድምሩ 5 ሜዳሊያ፤ ጋምቤላ

ክልል 1 ብር፣ 2 ነሐስ በድምሩ 3 ሜዳሊያ በማስመዝገብ በአትሌቲክስ ውድድር በቅደም ተከተላቸው መሠረት ከ1ኛ-6ኛ

ደረጃ አስመዝግበዋል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ ቀን

የዓለም አትሌቲክስ ቀን ሚያዝያ 17 ቀን 2007 ዓ. ም. በ6 ክልሎች ከተማ አስተዳደሮች መካከል በታዳጊ ወጣቶች

ተካሂዷል፡፡ በዚህም አፋርና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፎቶ ግራፍና በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

41ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በቻይና ጉያንግ ከተማ መጋቢት 19/2007

2015 ቻይና ጉያንግ

ኢትዮጵያ 24 በሚሆኑ ወጣትና አዋቂ ሴትና ወንዶች የተወከለችባቸው አትሌቶቿ በውድድሩ ከተዘጋጁት 8 የወርቅ

ሜዳልያዎች 5ቱን በማስገኘት ከዓለም 1ኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አድርገዋታል፡፡

በወጣት ሴቶች ምድብ ኢትዮጵያ ከ1-3ኛ ያለውን ደረጃ፣

- በአትሌት ለተሰንበት ግደይ፣

- በአትሌት ዴራ ዲዳ፣

- በአትሌት እታገኝ ወልዱ፣

Page 28: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አትሌት ለተሰንበት ግደይ

በወጣት ወንዶች ምድብ 1ኛ ደረጃ፣

- በአትሌት ያሲን ሃጂ፣

አትሌት ያሲን ሃጂ

በአዋቂ ሴቶች ምድብ 2ኛና 3ኛ ደረጃን፣

- በአትሌት ሰንበሬ ተፈሪ፣- በአትሌት ነፃነት ጉደታ፣

Page 29: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አትሌት ሰንበሬ ተፈሪና ነፃነት ጉደታ

በአዋቂ ወንዶች ምድብ

- በአትሌት ሙክታር እንድሪስ

3ኛ ደረጃን በመያዝ 5 የወርቅ፣ 3 የብር፣ 3 የነሐስ፣ በድምሩ 11 ሜዳልያዎችን አግኝታ ከዓለም ሃገራት 1ኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

ወጣት ሴቶች

በወጣት ሴቶች ምድብ አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣ በወጣት ወንዶች ምድብ ደግሞ አትሌት ያሲን ሃጂ ወርቅ ያስገኙ ብቸኛ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 3 ወርቆች በወጣት ሴቶች በቡድን፣ በአዋቂ ሴቶች በቡድን እንዲሁም በአዋቂ

ወንዶች በቡድን የተገኙ ናቸው፡፡

Page 30: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

3ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና - አሰላ

3ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ከግንቦት 5-8/2007 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በአሰላ

ከተማ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ውድድር ከ10 ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከ26 ክለቦች የተውጣጡ

በወንድ 451 በሴቶች 355 በድምሩ 806 አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የውድድሩ አሸናፊ በሁለቱም ጾታ የኦሮሚያ

ክልል ሆኗል፡፡ ይሁንና በዚህ ውድድር አሁንም አፋጣኝ እርምጃ የሚሻው የእድሜ ችግር በጉልህ ታይቷል፡፡

44ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና - አዲስ አበባ ስቴድዮም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1963 ዓ. ም. ገደማ መካሄድ የጀመረ ውድድር ሲሆን ከ2000 ዓ. ም. ወዲህ ክልሎች፣ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች በአንድ ላይ በመሆን ውድድራቸውን የሚያካሂዱበት ትልቅ ሻምፒዮና ነው፡፡

የዘንድሮው ሻምፒዮና ለ44ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ዓላማው፡ -

በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮች፣ በክለቦችና በማሠልጠኛ ማዕከላት ለሚገኙ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤

ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤

ለብሔራዊ አትሌቲክስ ስልጠና አትሌቶችን ለመምረጥ፤

ከነሐሴ 28/2007 ዓ.ም. እስከ መስከረም 8/2008 ዓ.ም. ድረስ ብራዛቢል (ኮንጎ) በሚካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ለመምረጥ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በውድድሩ ከ10 ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከ30 ክለቦች የተውጣጡ ወንዶች 730 ሴቶች 552 በድምሩ1,282 አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል በውድድሩ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ /10/ ሪከርዶች የተሻሻሉ ሲሆን በሁለቱም ጾታየመከላከያ ስፖርት ክለብ አሸናፊ ሆኖ ተጠናቋል፡፡ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጋራድኃ/የተ/የግ/ኩባንያ በአይነት ስፖንሰር አድርጎት ነበር፡፡

በዝርዝር ውጤቱ መሰረትም፡-

ተ.ቁፆታ

ያስመዘገበዉነጥብ ደረጃ

ክልል/ከተማአስተዳደር/ክለብ

1.ሴቶች

82 3ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

125 2ኛ ኦሮሚያ ክልል

226 1ኛ መከላከያ

2.ወንደች

70 3ኛ አማራ ክልል እናፌ/ማረሚያ

191 2ኛ ኦሮሚያ ክልል

234 1ኛ መከላከያ

135 3ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Page 31: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

3. አጠቃላይወ/ሴ

316 2ኛ ኦሮሚያ ክልል

460 1ኛ መከላከይ

በዚህ ሻምፒዮና ላይ የተሻሻሉ ሪከርዶች፣ እንዲሁም 2 እና ከ2 በላይ ወርቅ ያመጡ አትሌቶች ነበሩ፡፡

ተ.ቁ የአትሌቱ ስም ጾታ

ክለብ የውድድት ዓይነት ውጤት

1. ሪከርድ ያሻሻሉ ቀድሞ የነበረ የተሻሻለ

አርዓያት ዲቦው ሴ ኢ/ን/ባንክ ከ/ዝላይ 1.67 ሜ 1.72 ሜ

አመለ ይበልጣል ሴ መከላከያ አሎሎ 12.06 ሜ 12.81ሜ

ቆንጅት ተሾመ ሴ ፌዴ/ማረሚያ 100 ሜ መሠ 14.46 14.19

እሌኒ ደመላሽ ሴ መከላከያ 400 ሜ መሠ 59.85 59.74

አልማዝ ንጉስ ሴ መከላከያ ዲስከስ 41.48ሜ 42.83 ሜ

መዝገቡ ቢራራ ወ መከላከያ ምርኩዝ 4.00ሜ 4.30 ሜ

ብሩክ አብርሃም ወ ኦሮሚያ መዶሻ 44.84ሜ 45.77 ሜ

በኃይሉ አለምሸት ወ መከላከያ 110 ሜ መሠ 14.03 13.73

በቀለ ለሚ ወ ኦሮሚያ ከፍታ ዝላይ 2.06 ሜ 2.07 ሜ

ፍሬዘውድ ተስፋዬኮሬ ቶላጋዲሴ ኢጃራጫልቱ ሹሚ

ኦሮሚያ 4X400 3፡41.57 3፡40.63

2. ሁለት ወርቅ ያመጡኚቦሎ ኡጉዳ ሴ መከላከያ ሱሉስ/ርዝመት

አልማዝ ንጉስ ሴ መከላከያ ዲስከስ/ጦር

ተስፋዬ ነዳሳ ወ መከላከያ ርዝመት/ሱሉስ

ሄኖክ ብርሃኑ ወ ኦሮሚያ 200/4X100

ጫልቱ ሹሚ ሴ ኦሮሚያ 800 ሜ፣4X400

3. ሶስት ወርቅ ያመጡ

ትግሰት ታማኙ ሴ ኢት/ንግ/ባንክ 200፣400፣4X100ሜ

Page 32: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የምሥራቅ አፍሪካ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና - ሱዳን/ካርቱም

ከሰኔ 6 - 7/20007 ዓ. ም. በሱዳን ካርቱም በተደረገው የምስራቅ አፍሪካ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሃገራችን ሶስት

የወንድ እና ሶስት የሴት አትሌቶችን በማሳተፍ የሚከተለውን ውጤት አስመዝግበው ተመልሰዋል፡፡

1. አዳነች አንበሳ በ1500 ሜትር 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ፣

2. አዲሱ ተስፋሁን በ3ዐዐዐ ሜትር 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ፣

3. ተማም ቱራ በ800 ሜትር 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ፣

4. ፋዬ ፍሬው በ100 ሜትር 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ፣

5. አዳነች አንበሳ በ800 ሜትር 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ፣

6. አብዱሰታር ከማል በ200 ሜትር 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ፣

7. ፋዬ ፍሬው በ200 ሜትር 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ፣

8. አገሬ በላቸው በ3000 ሜ ትር 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ፣

በአጠቃላይ ሃገራችን 5 ወርቅና 3 ብር ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ በ8 ሜዳልያዎች በሻምፒዮናው ላይ ከተካፈሉ 7 ሃገራት

መካከል ሱዳንን ተከትላ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቤጂንግ ቻይና ለሚደረገው 15ኛው የዓለም አትሌቲከስ ሻምፒዮና

በሁለቱም ጾታ በ10,000 ሜትር ሃገራችንን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ ሰኔ 10/20007 ዓ. ም. በሆላንድ ሄንግሎ

የሰዓት ማሟያ ሙከራ ውድድር አካሂዷል፡፡ በዚህ ውድድር ተካፍለው ሚኒማ ያሟሉ 3 ወንድና 3 ሴት በድምሩ 6

አትሌቶች፣ እንዲሁም ለማራቶን ውድድሩ 6 ወንድና 6 ሴት በድምሩ 12 አትሌቶች ተመርጠዋል፡፡

የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር - ሰኔ 21/2007 ዓ. ም. - ሃዋሳ

Page 33: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ሲሳይ ለማ እና አሸቴ በከሬ በኢንዶ ኢትዮጵያ ከተበረከተላቸው የኢንተርናሽናል ውድድር ግብዣ ሽልማት ጋር

31ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ሰኔ 21 ቀን 2007 ዓ. ም. በሀዋሳ ከተማ ተካሂዶ የኦሮሚያ ፖሊስ አትሌቶች የሆኑት

ሲሳይ ለማ እና አሸቴ በከሬ አሸናፊ ሆነውበታል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ክለብ አትሌቶች ፍፁም የበላይነታቸውን ባሳዩበት የሴቶቹ

ፉክክር ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉትን ደረጃዎች ተቆጣጥረው የጨረሱ ሲሆን በወንዶችም የ1ኛ እና 2ኛነቱን ስፍራ ወስደዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኢንዶ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው

በዘንድሮው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ላይ አሸናፊ የሆኑት ሲሳይ ለማ እና አሸቴ በከሬ በመጪው ፌብሩዋሪ

7/2016 በባርሴሎና በሚካሄድ የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ የሚካፈሉበትን ዕድል የኢንዶ

ኢትዮጵያ የጉብኝት ድርጅት በሽልማት መልክ አበርክቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከ1ኛ እስከ 10ኛ ለወጡ አትሌቶች በጠቅላላው የ120,000.00 ብር እና ለአንጋፋ

/ቬተራን/ ሯጮች ደግሞ የ5,000.00 ብር የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

በቡድን በተደረገው ፉክክር የነጥብ አሸናፊዎች በመሆኑ ረገድ የኦሮሚያ ፖሊስ እና ፌደራል ፖሊስ ክለቦች ስኬታማ የሆኑ

ሲሆን ኦሮሚያ ፖሊስ በሴቶች በ10 ነጥብ ፌደራል ፖሊስ በወንዶች በ39 ነጥብ አሸናፊ ሆነው የተዘጋጁትን ዋንጫዎች

ወስደዋል፡፡ በሁለቱም ፆታዎች በክልል፣ በክለብና በግል የተመዘገቡ በድምሩ ከ400 በላይ ሯጮች በተካፈሉበት የዘንድሮው

ውድድር ላይ በኢንዶ ኢትዮጵያ የጉብኝት ድርጅት አማካይነት ከስፔን የመጡ 33 የጤና ሯጮችና አንጋፋ (ቬተራን)

ተወዳዳሪዎች በ10 ኪ.ሜ. እና ግማሽ ማራቶን ተሳትፈዋል፡፡

ሲሳይ ለማ ውድድሩን በአሸናፊነት ሲጨርስ

Page 34: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

እሸቴ በከሬ ውድድሩን በአሸናፊነት ስትጨርስ

ለጀግናው አትሌት መታሰቢያ በተዘጋጀው የመጀመሪያ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ፣ የሶቭዬት ሕብረት እና የጅቡቲ አትሌቶች

ተካፋይ የነበሩ ሲሆን የውድድሩ ስያሜም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ‹የአበበ ቢቂላ ዓለም አቀፍ ማራቶን ውድድር› ይባል

እንደነበር ሆኖም ከግዜ በኋላ ውድድሩ አገራዊ መልክ ብቻ እንዲኖረውና ስያሜው ‹የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር›በሚል ተቀይሮ መካሄድ መቀጠሉ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ የኦሊምፒክ ድል ፈር ቀዳጅና የምንግዜም ኩራት የሆነው የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላን ገድል

ለመዘከር ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሄደው የማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች እየተከናወነ ዘንድሮ

ላይ የደረሰ ሲሆን የዘንድሮውን ጨምሮ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት ውድድሮች እያዘጋጀች የምትገኘው ሐዋሳ ከተማ 31ኛውን

ውድድርም በተሳካ ሁኔታ አስተናግዳለች፡፡

የ31ኛው የሻ/ል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውጤት

ወንዶች

1. ሲሳይ ለማ (ኦሮሚያ ፖሊስ) 2:14:42

2. ደሬሳ ጭምሳ (ኦሮሚያ ፖሊስ) 2:15:09

3. ዳንኤል አስጨንቅ (ፌደራል ፖሊስ) 2:15:33

4. ረጋሳ ምንዳዬ (ኦሮሚያ) 2:15:45

5. ደረጀ ተስፋዬ (መከለካያ) 2:16:5

ሴቶች

1. አሸቴ በከሬ (ኦሮሚያ ፖሊስ) 2:39:02

2. አበሩ መኩሪያ (ኦሮሚያ ፖሊስ) 2:39:06

3. መሰረት መንግስቴ (ኦሮሚያ ፖሊስ) 2:39:16

4. ጉልሜ ቶሎሳ (ኦሮሚያ ፖሊስ) 2:39:29

5. አመለወርቅ ፍቃዱ (ፌደራል ፖሊስ) 2:41:44

Page 35: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

9ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና - ኮሎምቢያ - ካሊ ከሐምሌ 8 – 12/2007 ዓ. ም.

ኢትዮጵያ በዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎዋና ውጤቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየተሻሻለ መምጣቱን

እስከ አሁን ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በዚህ መሠረት፡-

ወድድሩዓመትእ.ኤ.አ

የተደረገበት ከተማ ሀገር የውድድሩ ቀናትሜዳልያ አጠቃላይ ደረጃ

ወርቅ ብር ነሀስ ድምር በአፍሪካ በዓለም

1ኛው 1999 ባይዳጎዝ ፖላንድ 16 – 18 ጁላይ 0 4 0 4 3ኛ 17ኛ

2ኛው 2001 ደብሪስን ሀንጋሪ 12 – 15 ጁላይ 1 2 2 5 2ኛ 12ኛ

3ኛው 2003 ሸርብሪክ ካናዳ 9 – 13 ጁላይ1 1 1 3 2ኛ 12ኛ

4ኛው 2005 ማራካሽ ሞሮኮ 13 – 17 ጁላይ 1 1 1 3 4ኛ 11ኛ

5ኛው 2007 ኦስትራቫ ቼክሪፐብሊክ

11 – 15 ጁላይ 1 1 2 4 2ኛ 10ኛ

6ኛው 2009 ብሪክስተን ጣልያን 8 – 12 ጁላይ 1 1 4 6 2ኛ 9ኛ

7ኛው 2011 ሊል ፈረንሳይ 6 – 10 ጁላይ2 2 1 5 2ኛ 6ኛ

8ኛው 2013 ዶኔስክ ዩክሬን 10 – 14 ጁላይ3 3 2 8 2ኛ 3ኛ

9ኛው 2015 ካሊ ኮሎምቢያ 15 – 19 ጁላይ 2 3 3 8 2ኛ 4ኛ

10ኛው 2017 ኬንያ ናይሮቢ ወደፊት የሚካሄድ

በኮሎምቢያ - ካሊ በተካሄደው 9ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም የሚወክሏትን 20 ታዳጊዎች ከ6

የልኡካኑ አባላት ጋር ወደ ስፍራው ሸኝታ ነበር፡፡ በዚህ ሻምፒዮና ከላይ የተመለከተው ውጤት የተገኘ ሲሆን

ባለድሎቻችንም፡-

ተ.ቁ. አሸናፊ አትሌት ፆታ ርቀት ሜዳልያ1 ሹሩ ቡሎ ሴ 3,000 ሜ ወርቅ2 በዳቱ ሒርጳ ሴ 1,500 ሜ ወርቅ3 ሙሉጌታ አሰፋ ወ 1,500 ሜ ብር4 ጋዲሴ ኢጃራ ሴ 800 ሜ ብር5 ወገኔ ሰብስቤ ወ 2,000 ሜ መሰ ብር6 አገሬ በላቸው ሴ 2,000 ሜ መሰ ነሐስ7 አያልነሽ ደጀኔ ሴ 5,000 ሜ እርምጃ ነሐስ8 ተፈራ ሞሲሳ ወ 3,000 ሜ ነሐስ

9ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና - ኮሎምቢያ - ካሊ ከሐምሌ 8 – 12/2007 ዓ. ም.

ኢትዮጵያ በዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎዋና ውጤቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየተሻሻለ መምጣቱን

እስከ አሁን ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በዚህ መሠረት፡-

ወድድሩዓመትእ.ኤ.አ

የተደረገበት ከተማ ሀገር የውድድሩ ቀናትሜዳልያ አጠቃላይ ደረጃ

ወርቅ ብር ነሀስ ድምር በአፍሪካ በዓለም

1ኛው 1999 ባይዳጎዝ ፖላንድ 16 – 18 ጁላይ 0 4 0 4 3ኛ 17ኛ

2ኛው 2001 ደብሪስን ሀንጋሪ 12 – 15 ጁላይ 1 2 2 5 2ኛ 12ኛ

3ኛው 2003 ሸርብሪክ ካናዳ 9 – 13 ጁላይ1 1 1 3 2ኛ 12ኛ

4ኛው 2005 ማራካሽ ሞሮኮ 13 – 17 ጁላይ 1 1 1 3 4ኛ 11ኛ

5ኛው 2007 ኦስትራቫ ቼክሪፐብሊክ

11 – 15 ጁላይ 1 1 2 4 2ኛ 10ኛ

6ኛው 2009 ብሪክስተን ጣልያን 8 – 12 ጁላይ 1 1 4 6 2ኛ 9ኛ

7ኛው 2011 ሊል ፈረንሳይ 6 – 10 ጁላይ2 2 1 5 2ኛ 6ኛ

8ኛው 2013 ዶኔስክ ዩክሬን 10 – 14 ጁላይ3 3 2 8 2ኛ 3ኛ

9ኛው 2015 ካሊ ኮሎምቢያ 15 – 19 ጁላይ 2 3 3 8 2ኛ 4ኛ

10ኛው 2017 ኬንያ ናይሮቢ ወደፊት የሚካሄድ

በኮሎምቢያ - ካሊ በተካሄደው 9ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም የሚወክሏትን 20 ታዳጊዎች ከ6

የልኡካኑ አባላት ጋር ወደ ስፍራው ሸኝታ ነበር፡፡ በዚህ ሻምፒዮና ከላይ የተመለከተው ውጤት የተገኘ ሲሆን

ባለድሎቻችንም፡-

ተ.ቁ. አሸናፊ አትሌት ፆታ ርቀት ሜዳልያ1 ሹሩ ቡሎ ሴ 3,000 ሜ ወርቅ2 በዳቱ ሒርጳ ሴ 1,500 ሜ ወርቅ3 ሙሉጌታ አሰፋ ወ 1,500 ሜ ብር4 ጋዲሴ ኢጃራ ሴ 800 ሜ ብር5 ወገኔ ሰብስቤ ወ 2,000 ሜ መሰ ብር6 አገሬ በላቸው ሴ 2,000 ሜ መሰ ነሐስ7 አያልነሽ ደጀኔ ሴ 5,000 ሜ እርምጃ ነሐስ8 ተፈራ ሞሲሳ ወ 3,000 ሜ ነሐስ

9ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና - ኮሎምቢያ - ካሊ ከሐምሌ 8 – 12/2007 ዓ. ም.

ኢትዮጵያ በዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎዋና ውጤቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየተሻሻለ መምጣቱን

እስከ አሁን ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በዚህ መሠረት፡-

ወድድሩዓመትእ.ኤ.አ

የተደረገበት ከተማ ሀገር የውድድሩ ቀናትሜዳልያ አጠቃላይ ደረጃ

ወርቅ ብር ነሀስ ድምር በአፍሪካ በዓለም

1ኛው 1999 ባይዳጎዝ ፖላንድ 16 – 18 ጁላይ 0 4 0 4 3ኛ 17ኛ

2ኛው 2001 ደብሪስን ሀንጋሪ 12 – 15 ጁላይ 1 2 2 5 2ኛ 12ኛ

3ኛው 2003 ሸርብሪክ ካናዳ 9 – 13 ጁላይ1 1 1 3 2ኛ 12ኛ

4ኛው 2005 ማራካሽ ሞሮኮ 13 – 17 ጁላይ 1 1 1 3 4ኛ 11ኛ

5ኛው 2007 ኦስትራቫ ቼክሪፐብሊክ

11 – 15 ጁላይ 1 1 2 4 2ኛ 10ኛ

6ኛው 2009 ብሪክስተን ጣልያን 8 – 12 ጁላይ 1 1 4 6 2ኛ 9ኛ

7ኛው 2011 ሊል ፈረንሳይ 6 – 10 ጁላይ2 2 1 5 2ኛ 6ኛ

8ኛው 2013 ዶኔስክ ዩክሬን 10 – 14 ጁላይ3 3 2 8 2ኛ 3ኛ

9ኛው 2015 ካሊ ኮሎምቢያ 15 – 19 ጁላይ 2 3 3 8 2ኛ 4ኛ

10ኛው 2017 ኬንያ ናይሮቢ ወደፊት የሚካሄድ

በኮሎምቢያ - ካሊ በተካሄደው 9ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም የሚወክሏትን 20 ታዳጊዎች ከ6

የልኡካኑ አባላት ጋር ወደ ስፍራው ሸኝታ ነበር፡፡ በዚህ ሻምፒዮና ከላይ የተመለከተው ውጤት የተገኘ ሲሆን

ባለድሎቻችንም፡-

ተ.ቁ. አሸናፊ አትሌት ፆታ ርቀት ሜዳልያ1 ሹሩ ቡሎ ሴ 3,000 ሜ ወርቅ2 በዳቱ ሒርጳ ሴ 1,500 ሜ ወርቅ3 ሙሉጌታ አሰፋ ወ 1,500 ሜ ብር4 ጋዲሴ ኢጃራ ሴ 800 ሜ ብር5 ወገኔ ሰብስቤ ወ 2,000 ሜ መሰ ብር6 አገሬ በላቸው ሴ 2,000 ሜ መሰ ነሐስ7 አያልነሽ ደጀኔ ሴ 5,000 ሜ እርምጃ ነሐስ8 ተፈራ ሞሲሳ ወ 3,000 ሜ ነሐስ

Page 36: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ሲሆኑ ባለ ድሎቹ ታዳጊዎችና በቀጥታ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተገኙና ለዓለም አቀፍ ውድድሮች

እንግዶች ናቸው፡፡ ከላይ ከተመለከተው ውጤት ባሻገር በዚህ ሻምፒዮና ከ8 ያላነሱ ዲፕሎማዎችም ተገኝተዋል፡፡

አትሌት ሹሩ ቡሎ በ3000 ሜ እና በዳቱ ሒርጳ በ1,500 ሜ ሴቶች ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኙ

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መካፈልና ውጤታማ መሆን የጀመረችው እ. ኤ. አ. ከ1983 ጀምሮ በአትሌት ከበደባልቻ የማራቶን ድል ሲሆን ርቀቱን 2፡10፡27 በሆነ ሰዓት ፈፅሞ አውስትራሊዊውን አትሌት ሮብ ዲ ካስትሌን ተከትሎ 2ኛደረጃን ሲያገኝ ነበር፡፡ በመደበኛነት በየሁለት አመቱ፣ አልፎ አልፎም በየአራት አመቱ አንዴ በሚካሄደው በዚህ ሻምፒዮናበተለይም የአሁኑን ሳይጨምር ባለፉት 31 የውድድር አመታት ሃገራችን ኢትዮጵያ 22 የወርቅ፣ 19 የብር፣ 23 የነሃስ፣በድምሩ 64 ሜዳልያዎችን አግኝታ በአጠቃላይ እስከዛሬ በተካሄዱት 14 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ከአፍሪካ 2ኛ፣ከዓለም ደግሞ 7ኛ ደረጃን ይዛ ትገኛለች፡፡

ለ15ኛ ጊዜ የተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እ. ኤ. አ. ከኦገስት 22 – 30/2015 ለተከታታይ 9 ቀናት በቻይናዋ -ቤጂንግ ከተማ የወፍ ጎጆ ተብሎ በሚጠራው ዓለም አቀፍ ስቴድዮም ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያም በዚህ ሻምፒዮና ለውጤትያበቁኛል ብላ ያሰለፈቸቻቸውን 16 ወንድ፣ 17 ሴት፣ በድምሩ 33 አትሌቶች አዘጋጅታ ተካፍላለች፡፡

በውጤቱም መሰረት፡-

ኢትዮጵያ በ3 ወርቅ፣ በ3 ብር፣ በ2 ነሃስ፣ በድምሩ በ8 ሜዳልያዎች ከዓለም 5ኛ ደረጃን ይዛ ሻምፒዮናውን አጠናቃለች፡፡የአሁኑ ደረጃ ከ14ኛው የሞስኮ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንፃር በአንድ ደረጃ የተሻሻለ ሲሆን ከሜዳልያ አኳያ በ2 ነሃስዝቅ ያለ ነው፡፡

የሜዳልያ አሸናፊዎቻችን፡-

1. ገንዘቤ ዲባባ 1,500 ሜ በ4:08.09 ወርቅ፣2. አልማዝ አያና 5,000 ሜ 14:26.83 ወርቅ፣3. ማሬ ዲባባ ማራቶን በ2:27:35 ወርቅ፣

4. ሰንበሬ ተፈሪ 5,000 ሜ በ14:44.07 ብር፣5. ገለቴ ቡርቃ 10,000 ሜ በ31:41.77 ብር፣6. የማነ ፀጋዬ ማራቶንበ 2:13.08 ብር፣

Page 37: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

7. ሃጎስ ገ/ህይወት 5,000 ሜ በ13:51.86 ነሃስ፣ 8. ገንዘቤ ዲባባ 5,000 ሜ በ14፡ 44.14 ነሃስ፣

ያገኙ ሲሆኑ 8 አትሌቶች ከ4ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ የዲፕሎማ ባለቤት ሆነውበታል፡፡

አትሌት ማሬ ዲባባ በሴቶች ማራቶን የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት

ሶስቱ እንስት ጀግኖች በ5,000 ሜ ከ1ኛ - 3ኛ በመውጣት የጥንቱን ታሪክ ደግመዋል

ከግራ አልማዝ አያና 1ኛ፣ ከመሃል አትሌት ገንዘቤ ዲባባ 3ኛ፣ ከቀኝ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ 2ኛ

Page 38: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አትሌት ገለቴ ቡርቃ በ10,000 ሜ ሴቶች የብር ሜዳልያ ባለቤት

በግራ አትሌት የማነ ፀጋዬ በወንዶች ማራቶን የብር ሜዳልያ ባለቤት

በ8 ሚዳልያዎች ከዓለም የ5ኝነትን ደረጃ ይዞ ለተመለሰው የልኡካን ቡድንም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ

የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጂነር መሰለ ኃይሌና

ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

Page 39: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከየት ወደ የት?

የአትሌቲክስ ስፖርት በኢትዮጵያ መቼ፣ የትና እንዴት እንደተጀመረ የሚገልፁ ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ባይቻልም

ከ1890 ዓ. ም. ቀደም ብሎ በትምህርት ቤቶችና በወታደራዊ ካምፖች ይዘወተር እንደነበር ግን ይነገራል፡፡

ቀስ በቀስም አትሌቲክስ በሃገራችን አብዛኛው ሥፍራ እየተለመደና በህዝቡም ዘንድ እየተዘወተረ ስለመጣ ስፖርቱን

በበላይነት ሊመራ የሚችል ተቋም ‹‹ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን›› በሚል መጠሪያ በ1941 ዓ. ም. ተቋቋመ፡፡

የተቋቋመበት አጠቃላይ ዓላማ፡-

በአለም አቀፉ የስፖርት ህግ መሠረት በአንድ ሀገር በአንድ የስፖርት ዓይነት ሊኖር የሚችለው አንድ ሀገር አቀፍ ፌዴሬሽን ብቻ

በመሆኑ ፌዴሬሽኑ የሀገሪቱን ሕግና ደንብ ጠብቆ በሕዝብ፣ በመንግስትና በድርጅቶች ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ሀገር አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና

ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ተግባራትን የሚያከናውንና ከአጠቃላይ የህብረተሰቡ አትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴ በመነሳት በተለይ

የወጣቱን ትውልድ ግንዛቤና ተሳትፎ በማጠናከር የላቀ ችሎታ ያላቸው ምርጥ ስፖርተኞች እንዲፈሩ በማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ

የአገራችንን ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነት ማስፋት በሚል አጠቃላይ ዓላማ የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡

ተግባራቱም፡-

1. የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣው ማቋቋሚያ መመሪያ እንዲሁም በአለም አቀፍ

አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ሕገ ደንብ መሠረት በሀገሪቱ ውስጥ የአትሌቲክስ ስፖርትን በበላይነት ይመራል፣

ስለሚስፋፋበት ሁኔታ ስልቶችን ይቀይሳል፤

2. የአትሌቲክስ ስፖርቱን በሚመለከት የመንግስት ፖሊሲን፣ ሕግን፣ ደንብንና መመሪያዎችን ይፈፅማል፣ ያስፈፅማል፤

3. ደረጃቸውን የጠበቁ የአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲቋቋሙ ይደግፋል ዕውቅና ይሰጣል፤

4. የአትሌቲክስ ስፖርትን የሚመለከቱና ተዛማጅ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ ያሰራጫል፤

5. በሀገር ውስጥ ከአንድ ክልል በላይ በሚያሳትፍ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ከአንድ ሀገር በላይ የሚደረጉ የአትሌቲክስ

ውድድሮችን ያካሂዳል፣ ፈቃድ ይሰጣል፤

6. የአትሌቲክስ ስፖርት ክለቦች ስለሚደራጁበት ሁኔታ መመሪያ ያወጣል፣ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤

7. የታዳጊ፣ የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎ ስለሚያድግበት ሁኔታ ስልት ይቀይሳል፤

8. ምርጥ አትሌቶች እንዲፈሩና ዘመናዊ ስልጠና እንዲያገኙ ስልት ይቀይሳል፤

9. ከአለም አቀፍና ከሀገር ውስጥ የአትሌቲክስ ተቋማት ጋር በመተባበር ኮርሶችን፣ ሴሚናሮችን፣ ወርክሾፖችንና

ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፣ ዕውቅና ይሰጣል፤

10. የአትሌቲክስ ስፖርቱን በሚመለከት በአህጉራዊና አለም አቀፋዊ ውድድሮችና ስብሰባዎች ላይ ይሳተፋል፣ የተላለፉ

ውሳኔዎችንም ተግባራዊ ያደርጋል፤

11. የአሰልጣኞችንና የዳኞችን የመመልመያ መስፈርት ያዘጋጃል ደረጃ ያወጣል ፈቃድ ይሰጣል፤

12. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ የአትሌቲክስ ስፖርት እንዲስፋፋ ድጋፍ

ያደርጋል፤

13. የአትሌቲክስ ሰፖርትን ለማሳደግ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ይሳተፋል፤ የገቢ ማስገኛ ተቋማትንም

ያቋቁማል፤

Page 40: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

14. የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ይሰራል፤

15. ለኮሚሽን መ/ቤቱ በየጊዜው (በየሩብ ዓመቱ) የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል፤

16. የውስጥ መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በማውጣትና በጠቅላላ ጉባኤ በማስፀደቅ፣ በሥራ ላይ ያውላል፤

17. ኢትዮጵያ የተቀበለችውን የፀረ-ዶፒንግ ኮንቬንሽን ያከብራል ያስከብራል፤

18. በክልሎች ፌዴሬሽኖች እንዲደራጁ ድጋፍ ያደርጋል፣ እውቅና ይሰጣል፣ ለተፈፃሚነቱ መመሪያ ያወጣል፤

19. በአትሌቲክስ ስፖርት ዙሪያ የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ሰዎችና አካላት በተለያዩ መንገዶች ዕውቅና ይሰጣል፤

20. በአትሌቲክስ ስፖርት ዙሪያ ለሚነሱ አለመግባባቶችና ክርክሮች ዳኝነት ይሰጣል፤

21. በአመት አንድ ጊዜ የፌዴሬሽኑን የጠቅላላ ጉባኤ ያካሂዳል፤

22. ከስፖርት ጋር በተያያዙ የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ ይሳተፋል፡፡

23. ውል ይዋዋላል፣ ይከሳል፣ ይከሰሳል፡፡

ፌዴሬሽኑ በተቋቋመበት ወቅት የነበረውን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኮሎኔል ጌታሁን ተክለማርያም በበላይነት ይመሩና ያገለግሉ

እንደነበር፣ ከእኝህ ሰው በኋላ ደግሞ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው ተተክተው የአትሌቲክስ ስፖርቱን ይመሩ እንደነበር ይነገራል፡፡ የተለያዩ

አማተር አገልጋዮች ፌዴሬሽኑን በበጎ ፈቃደኝነት በመምራት አሁን ያለበት ደረጃ ያደረሱት ሲሆን አቶ ሙሉጌታ ኃይለማርያምን

ተክተው ክብርት ወ/ሮ ብሥራት ጋሻውጠና ከ1994 ዓ. ም. በኋላ እስከ 2004 ዓ. ም. ማብቂያ ድረስ ያገለገሉ ብቸኛዋ ሴት የፌዴሬሽኑ

ፕሬዝዳንት ነበሩ፤ እርሳቸውን ተክተው እስከ አሁን በመምራት ላይ የሚገኙት ደግሞ ክቡር አቶ አለባቸው ንጉሴ ናቸው፡፡

ከአህጉርና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አኳያም ፌዴሬሽኑ፡- ከዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር፣ ከአዲዳስ ኩባንያ፣ ከአፍሪካ

አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን፣ ከምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅንና ከአቻ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት ጋር መልካም የሚባልና

በአርዓያነት ሊጠቀስ የሚችል ግንኙነት ያደርጋል፡፡

ቀደም ሲል በተጠቀሰው ዓመትም ፌዴሬሽኑ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) አባል በመሆን ሲመዘገብ፣

ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን (CAA) እና በምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን (EAAR)

ውስጥ ከካውንስል አባልነት ባለፈ በአመራርነት እንድታገለግል ስለተመረጠች ስፖርቱ በአፍሪካ ደረጃም እንዲስፋፋ ያላሰለሰ ጥረት

ማድረጓን ቀጠለች፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከምሥረታው በኋላ ስፖርቱን በማሳደግና ክለቦችን በማቋቋም የተለያዩ ውድድሮችን ማካሄድ

በመጀመሩ በ1958 ዓ. ም. ‹‹የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አትሌቲክስ ሻምፒዮና›› በሚል የመጀመሪያውን አገር አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር

በወታደራዊ ካምፖች፣ በት/ቤቶችና በአንዳንድ ቡድኖች መካከል ማከናወን ቻለ፡፡

እየዋለ እያደረም የአትሌቲክስ ስፖርት በሃገሪቱ እያደገ በመምጣቱና በኣለም አቀፍ ውድድሮች ተሣታፊ ሊሆኑ የሚችሉ አትሌቶች

መጥቀው መውጣት በመቻላቸው እ.ኤ.አ. በ1956 ዓ. ም. በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ በተደረገው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአትሌት ባሻዬ ፈለቀ፣ በአትሌት ገብሬ ስንቄ፣ በአትሌት ዋሚ ቢራቱ እና በሌሎችም አትሌቶች አማካይነት

ተካፍላለች፡፡ ቀጥሎም እ.ኤ.አ. በ1960 ዓ. ም. በኢጣልያ ሮም ከተማ በተካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች አገራችን በማራቶን ሩጫ

ተሳትፋ በአትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ አሸናፊ በመሆን ለአፍሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳልያና ክብር

በማስመዝገብ በዓለም የአትሌቲክስ ስፖርት ታሪክ በቀዳሚነት ለመቀመጥ ቻለች፡፡

Page 41: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በአትሌቲክሱ ስፖርት በተለይም በረጅም ርቀት ሩጫ አሸናፊነት እየታወቀች የመጣችው ኢትዮጵያ ከ4

ዓመት በኋላ በጃፓን ቶኪዮ በተደረገው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የማራቶን ውድድር በፈር ቀዳጁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ

አማካይነት ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ልትደግም ችላለች፡፡

በአፍሪካም ሆነ በሃገራችን ከእነዚህ ፋና ወጊ ከሆኑት የአትሌቲክስ ድሎች በኋላ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ተተኪ አትሌቶች በዓለም

የኦሎምፒክ ጨዋታዎች፣ በዓለም ሃገር አቋራጭ፣ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎችና በሌሎችም ውድድሮች ላይ በመሳተፍ የአገራችን

ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርገዋል፡፡ እነ አትሌት ማሞ ወልዴ፣ ሽብሩ ረጋሳ፣ ቶለሳ ቆቱ፣ እሸቱ ቱራ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣

መሐመድ ከድር፣ ደራርቱ ቱሉ፣ በላይነህ ዲንሳሞ፣ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት

ደፋር፣…. ከብዙዎቹ ባለድሎቻችን መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በዚህም መሰረት ላለፉት 60ዎቹ አመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየአመቱ በሚያካሂዳቸው ከ10 በላይ የሃገር ውስጥ

ውድድሮች ላይ የመላ ሃገሪቱ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች እንዲሳተፉ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዘመናት ተከብሮ የቆየውንና በጀግኖች አትሌቶቻችን የሁልጊዜም ድል ያሸበረቀውን የአትሌቲክስ

ስፖርት ክብሩ ተጠብቆ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ተግቶ በመስራት በአሁኑ ወቅት በአመት ከ15 የማያንሱ

የአገር ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድሮችን የዓለም አቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የውድድር ካላንደር መሰረት እያደረገ

በማካሄድ በርካታ ተተኪና ወጣት አትሌቶችን ማፍራት ችሏል፡፡

በታሪካችን ውስጥ ያየናቸው በርካታ ስመ ጥር አትሌቶች ቢኖሩንም ከበርካቶች መካከል ለዋቢነት፤

ከፈር ቀዳጆቹ መካከል፡- አትሌት ባሻዬ ፈለቀ፣ ገብሬ ስንቄ፣ አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ሽብሩ ረጋሳ፣ ቶለሳ ቆቱ፣ እሸቱ ቱራ፣ ምሩፅይፍጠር፣ መሐመድ ከድር፣ ዮሐንስ መሃመድና የመሳሰሉት፤

ከተከታዮቹ፡- ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ በላይነህ ዲንሳሞ፣ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ቁጥሬ ዱለቻ፣ የመሳሰሉት፤

ከቅርቡ ዘመን፡- ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር፣ ስለሺ ስህን፣ ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም የመሳሰሉት፤

ከአሁኖቹ ደግሞ፡- መሃመድ አማን፣ አልማዝ አያና፣ ሙክታር እንድሪስ፣ ህይወት አያሌው፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ አለሚቱ ሃሮዬ፣ ሃጎስገ/ህይወት፣ ሶፍያ አሰፋ፣ የማነ ፀጋዬ፣ ቡዜ ድሪባ፣ መረሣ ካህሳይ፣ ዳዊት ስዩም፣ ያሲን ሃጂ፣ ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ፋንቱ ማጊሶ፣ ሞስነትገረመው፣ አለሚቱ ሃዊ፣ ጎይተቶም ገ/ስላሴና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

በአጠቃላይ ፌዴሬሽኑ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን፣ የማህበራት አደረጃጀትን፣ ስልጠናን፣ ተሳትፎንና ውድድሮችን በተመለከተ

እቅድ አዘጋጅቶ ዓለም አቀፍ ተፎካካሪነትና ውጤታማነትን ሊያመጣ በሚችል አካሄድ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡

Page 42: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች /ከብራዛቪል እስከ ብራዛቪል/

ሃገራችን ኢትዮጵያ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች መካፈል የጀመረችው እ. ኤ. አ. ከ1965 ጀምሮ ሲሆን እስከ አሁን ያሉትን 10

ተካታታይ የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ሙሉ ለሙሉ የተካፈለች ሲሆን እድገት ባለው መልኩ

ውጤታማ ናት፡፡

አጠቃላይ የአትሌቲክስ የተሳትፎ ጉዟችን ምን ይመስል ነበር? የሚለውን በተከታዩ ሰንጠረዥ እንመልከተው፡-

ጨዋታ

ዎች

እ.ኤ

አ.

አዘጋጅ

ወርቅ ብር ነሐስ ድም

ደረጃ

1ኛ

1965

ብራ

ዛቪል

0 01

ማሞ ወልዴ 5,000ሜ፣1

12ኛ

2ኛ

1973

ሌጎስ

2

ምሩፅ ይፍጠር10,000ሜ፣ ማሞወልዴ ማራቶን፣

3

ተገኝ በዛብህ 400ሜ፣ ምሩፅይፍጠር ፣5000ሜ፣ ለሊሳ በዳኔ

ማራቶን፣

3

ሙሉጌታ ታደሰ 400ሜ፣ ሽብሩረጋሳ 1,500ሜ፣ ዮሃንስ ሞሃመድ

3,000ሜ መሰ፣

85ኛ

3ኛ

1978

አልጀ

ርስ

1

ዮሃንስ ሞሃመድ5,000ሜ፣

1

ደረጀ ነዲ ማራቶን፣

2

መሃመድ ከድር 10,000ሜ፣ ግርማገብሬ ማራቶን፣

4

8ኛ

4ኛ

1987

ናይሮ

2

በላይነህ ዲንሳሞማራቶን፣ ሸምሱሃሰን 20 ኪሜ

ርምጃ፣

2

አበበ መኮንን 10,000ሜ፣ ደረጀ ነዲማራቶን፣

2

ከበደ ባልቻ ማራቶን፣ ዘውዴኃ/ማርያም 400ሜ መሰ፣

6

4ኛ

5ኛ

1991

ካይሮ

4

ፊጣ ባይሣ 5,000ሜ፣ ሸምሱ ሃሰን20 ኪሜ ርምጃ፣

ጠና ነገሬ ማራቶን፣ደራርቱ ቱሉ10,000ሜ፣

3

ደስታ አስግዶም 1500ሜ፣ ዘውዴኃ/ማርያም 800ሜ፣ ሉቺያ ይስሃቅ

3000ሜ መሰ፣

4

አለማየሁ ሮባ 1,500ሜ፣ ጫላከልሌ 10,000ሜ፣ ጌጤነሽ ኡርጌ1,500ሜ፣ ትዕግስት ሞረዳ 10,000

ሜ፣

11

3ኛ

Page 43: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

6ኛ

1995

ሃራሬ

1

ቁጥሬ ዱለቻ 1500ሜ፣

4

ሃብቴ ጅፋር 5000ሜ፣ ሃብቴ ጅፋር10000ሜ፣ አየለች ወርቁ 5000ሜ፣ እመቤት አቦምሳ ማራቶን፣

7

አየለ መዝገቡ 5000ሜ፣ ሸምሱ ሃሰን20 ኪሜ ርምጃ፣ ቁጥሬ ዱለቻ 800ሜ፣ ገነት ገ/ጊዮርጊስ 1500ሜ፣ ጌጤዋሚ 10000ሜ፣ እልፍነሽ አለሙ

ማራቶን፣ ጌጤ ኮማ 20 ኪሜ ርምጃ፣

12

6ኛ

7ኛ

1999

ጆሃን

ስበርግ

6

ሃይሉ መኮንን1500ሜ፣ አሰፋመዝገቡ 10000ሜ ቁጥሬ ዱለቻ1500ሜ፣ አየለችወርቁ 5000ሜ፣

ጌጤ ዋሚ 10,000ሜ፣ ሕይወት ግዛው

ማራቶን፣

3

ፊጣ ባይሳ 5000ሜ፣ መሪማ ሃሽም10,000ሜ፣ መሰረት ቆቱ ማራቶን፣

2

ሃብቴ ጅፋር 10,000ሜ፣ ኮሬአለሙ ማራቶን፣ 11

3ኛ

8ኛ

2003

አቡጃ

5

ቀነኒሳ በቀለ 5000ሜ፣ ስለሺ ስህን10000ሜ፣ ቁጥሬዱለቻ 1500ሜ፣

መሰረት ደፋር5000ሜ፣

እጅጋዬሁ ዲባባ10000ሜ፣

6

ሃይሉ መኮንን 5000ሜ፣ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም 10000

ሜ፣ ጋሻው መለሰ ማራቶን፣ ወርቅነሽኪዳኔ 10000ሜ፣ ታደለች ቢራ

ማራቶን፣ አምሳለ ያዕቆብ 20 ኪሜርምጃ፣

4

ለኢላ አማን ማራቶን፣ ደጀን ብርሃኑ10000ሜ፣ ጉዲሳ ሸንተማ

ማራቶን፣ ቴዎድሮስ ሽፈራው 3000ሜ መሰ፣

15

3ኛ

9ኛ

2007

አልጀ

ርስ

4

ድሪባ መርጋ ግማሽማራቶን፣ ገለቴ

ቡርቃ 1500ሜ፣መሰረት ደፋር5000ሜ፣

መስታወት ቱፋ10000ሜ፣

4

ታደሰ ቶላ 10000ሜ፣ መሰለችመልካሙ 5000ሜ፣ አፀደ ባይሳ

ግማሽ ማራቶን፣ መቅደስ በቀለ 3000ሜ መሰ፣

5

ታሪኩ በቀለ 5000ሜ፣ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም 10000

ሜ፣ ናሆም መስፍን 3000ሜ መሰ፣ነፃነት አጫሞ 3000ሜ መሰ፣

አስናቀች አራርሶ 20 ኪሜ ርምጃ፣

13

5ኛ

10ኛ

2011

ማፑ

6

ኢብራሂም ጀይላን10000ሜ፣

ብርሃን ጌታሁን3000ሜ መሰ፣

ለሊሳ ደሲሳ ግማሽማራቶን፣ ሱሌ

ኡቱራ 5000ሜ፣ሱሌ ኡቱራ 10000

ሜ፣ ማሬ ዲባባግማሽ ማራቶን፣

7

የኔው አላምረው 5000ሜ፣ ሮባ ጋሪ3000ሜ መሰ፣ ፋንቱ ማጊሶ 800ሜ፣ እመቤት አንተነህ 5000ሜ፣

ውዴ አያሌው 10000ሜ፣ ህይወትአያሌው 3000ሜ መሰ፣ ማሚቱ

ዳስካ ግማሽ ማራቶን፣

7

አባይነህ አየለ 5000ሜ፣ አዝመራውበቀለ 10000ሜ፣ ሲሳይ ኮርሜ3000ሜ መሰ፣ በቃና ዳባ ግማሽማራቶን፣ ትዝታ ቦጋለ 1500ሜ፣ብርቱካን አዳሙ 3000ሜ መሰ፣አይናለም እሸቱ 20 ኪሜ ርምጃ፣

20

2ኛ

Page 44: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

11ኛ

2015

ብራ

ዛቪል

6

መኮንን ገ/መድህን1,500 ሜ፣ፀበሉ ዘውዴ10,000 ሜ፣ሶፍያ አሰፋ 3,000ሜ መሰ፣ጌታነህ ሞላ 5,000ሜ፣ዳዊት ስዩም 1,500ሜ፣ማሚቱ ዳስካ ግማሽማራቶን፣

5

ህይወት አያሌው 3,000 ሜ መሰ፣አይናለም እሸቱ 20 ኪሜ እርምጃ፣ልዑል ገ/ስላሴ 5,000 ሜ፣ ወርቅነሽ

ደገፋ ግማሽ ማራቶን፣ በሱ ሳዶ 1,500ሜ፣

6

አስካለ ቲክሳ 20 ኪሜ እርምጃ፣አዱኛ ታከለ 10,000 ሜ፣ ኃ/ማርያምአማረ 3,000 ሜ፣ ጫልቱ ሹሜ 800

ሜ፣ ገለቴ ቡርቃ 10,000 ሜ፣የብርጓል መለሰ ግማሽ ማራቶን፣

17 2

አትሌት ፀበሉ ዘውዴና ጌታነህ ሞላ በ11ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ በወንዶች 10,000 ሜ እና 5,000 ሜ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቶች

11ኛ

2015

ብራ

ዛቪል

6

መኮንን ገ/መድህን1,500 ሜ፣ፀበሉ ዘውዴ10,000 ሜ፣ሶፍያ አሰፋ 3,000ሜ መሰ፣ጌታነህ ሞላ 5,000ሜ፣ዳዊት ስዩም 1,500ሜ፣ማሚቱ ዳስካ ግማሽማራቶን፣

5

ህይወት አያሌው 3,000 ሜ መሰ፣አይናለም እሸቱ 20 ኪሜ እርምጃ፣ልዑል ገ/ስላሴ 5,000 ሜ፣ ወርቅነሽ

ደገፋ ግማሽ ማራቶን፣ በሱ ሳዶ 1,500ሜ፣

6

አስካለ ቲክሳ 20 ኪሜ እርምጃ፣አዱኛ ታከለ 10,000 ሜ፣ ኃ/ማርያምአማረ 3,000 ሜ፣ ጫልቱ ሹሜ 800

ሜ፣ ገለቴ ቡርቃ 10,000 ሜ፣የብርጓል መለሰ ግማሽ ማራቶን፣

17 2

አትሌት ፀበሉ ዘውዴና ጌታነህ ሞላ በ11ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ በወንዶች 10,000 ሜ እና 5,000 ሜ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቶች

11ኛ

2015

ብራ

ዛቪል

6

መኮንን ገ/መድህን1,500 ሜ፣ፀበሉ ዘውዴ10,000 ሜ፣ሶፍያ አሰፋ 3,000ሜ መሰ፣ጌታነህ ሞላ 5,000ሜ፣ዳዊት ስዩም 1,500ሜ፣ማሚቱ ዳስካ ግማሽማራቶን፣

5

ህይወት አያሌው 3,000 ሜ መሰ፣አይናለም እሸቱ 20 ኪሜ እርምጃ፣ልዑል ገ/ስላሴ 5,000 ሜ፣ ወርቅነሽ

ደገፋ ግማሽ ማራቶን፣ በሱ ሳዶ 1,500ሜ፣

6

አስካለ ቲክሳ 20 ኪሜ እርምጃ፣አዱኛ ታከለ 10,000 ሜ፣ ኃ/ማርያምአማረ 3,000 ሜ፣ ጫልቱ ሹሜ 800

ሜ፣ ገለቴ ቡርቃ 10,000 ሜ፣የብርጓል መለሰ ግማሽ ማራቶን፣

17 2

አትሌት ፀበሉ ዘውዴና ጌታነህ ሞላ በ11ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ በወንዶች 10,000 ሜ እና 5,000 ሜ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቶች

Page 45: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

አልኮል በአካል ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ

ሳሙኤል ብርሃኑ

የት/ስልጠና ከፍ/ባለሙያ

ምግብና ውሃ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ በፊትም ይሁን በኋላ አስፈላጊ ለሆነው ኃይል ምንጭነት ወይም ሰውነት ያዘጋጀውን

ነገር ግን በእንቅስቃሴ ወቅት ያቃጠለውን ካሎሪ በመተካትና ብቃትን ጠብቆ ለመቆየት የሚጫወቱት ሚና እጅግ የበዛ ነው፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን በብዙ ስፖርተኞች እየተለመደ የመጣና የተቃጠለን ካሎሪ ለመተካት በሚል አልኮሆልን መውሰድ እንደትልቅ

አማራጭ እየተወሰደ ያለ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በአንፃሩ ግን አልኮሆልን ወስዶ ወደ እንቅስቃሴ መግባት ከምግብ እና ውሃ የሚገኘውን

ያህል ስነ - ምግባዊ ይዘት የሌለውና አስፈላጊውን ጥቅም ካለመስጠቱም በላይ የውሃን ቦታ ተክቶ ሊጫወት አይችልም፡፡

አልኮሆል ወስዶ ወደ እንቅስቃሴ መግባት የሰውነትን ሚዛን በማዛበት፣ የአይንና እጅ በቅንብር ድርጊትን

የማከናወን(Coordination) አቅም እንዳይኖር ማድረግ፤ በነገሮች ላይ ሚዛናዊ ውሳኔ ለመስጠት አቅም እንዳይኖር ማድረግ፤

ትኩረት ለማድረግ፤ ብርታትንና አወጥቶ ለመጠቀም፤ የጡንቻን ጥንካሬና ኃይል እንዲሁም ፍጥነትን ለመጠቀም፤ በአጠቃላይ

የተዛባ የአካልና የአእምሮ ሁኔታ እንዲኖር በማድረግ በስፖርት ላይ ያለው አሉታዊ ተጽእኖው የበዛ ነው፡፡

ከየትኛውም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በፊት፤ በእንቅስቃሴ ወቅት ወይም በኋላ ውሀን ወይም ስፖርታዊ ፈሳሽን መውሰድ

ሰውነትን ከጉዳት ከመታደጉም ባለፈ የሰውነትን ስብ በማቃጠልና የጡንቻ ሕዋሳትን በማዳበር፤ ኃይልን በብዛት ለማምረት

እንዲሁም ምግብን ለህዋሳት በአግባቡ ለማድረስና በአጸፌታው አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡

በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ስፖርተኛ ጠምቶት ስናይ ሰውነቱ ውስጥ ያለውን ፈሳሽ አሟጦ ተጠቅሞ ካለው ክብደት ከ1-2% ያህል

የቀነሰ መሆኑን ለማወቅ ይቻላል፡፡ ከዚህ በላይ አሳሳቢው እና ተያይዞ የሚከሰተው ብቃቱን ከ10-20% መቀነሱ ነው፡፡

ከእንቅስቃሴ ውጪም ሆኖ አልኮሆልን መውሰድ ለብቻው በአራት ሰዓታት ቆይታ ውስጥ የሰውነትን ውሃ /ፈሳሽ/ በ3% በመቀነስ

በፍጥነት ወደ ድርቀት ይመራዋል፡፡

በእንቅስቃሴ ወቅት ለኃይል ምንጭነት የተቃጠለውን ካሎሪ በመተካትና በፍጥነት ለማገገም አስፈላጊ የሆኑ ምግቦች በተለይ

ካርቦሃይድሬትና ፕሮቲን ላይ ትኩረት ማድረጉ ግድ ይላል፡፡ እነዚህ ምግቦች ላይ ትኩረት ማድረጉ ሰውነት በፍጥነት እያገገመና

ከፍ ወዳለ እንቅስቃሴ ለመግባት የሚኖረውን አቅም እንዲጎለብት ከማድረጉም በላይ የተፈለገው ግብ ላይ በፍጥነት ለመድረስ

ያስችላል፡፡ ይሁን እንጂ በተሳሳተ አስተሳሰብ ቶሎ ለማገገም በሚል አልኮሆልን ከእንቅስቃሴ በኋላ መውሰድ ፈጣን የሆነ የደም

ዑደት እንዲኖርና ህዋሳት እንዲነቃቁ ስለሚያደርግ ሰውነት በአግባቡ ከምግብ ያገኘውን ኃይል እንዳይጠቀም ስለሚያደርገው

የተዛባና ጊዜውን ያልጠበቀ የማገገም ሂደት (Improper recovery) እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህም ከሌሎች ንጥረ ምግቦች

በውህደት ሊገኝ የሚገባውን ጥቅም ያሳጣዋል፡፡

Page 46: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ከዚህም ባለፈ፡-

አልኮሆልን መውሰድ የደምን ቱቦ እንዲሰፋ በማድረጉ በእንቅስቃሴ ወቅት በሚፈጠር ግጭት አካል ላይ ጉዳት ላይ ቢደርስ ድም

በብዛት እንዲፈስና ለማቆምም አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርገዋል፤

በተለይ በተደጋጋሚ ጉዳት ለሚያጋጥማቸው አልኮሆል ተጠቃሚ አትሌቶች ወደ ትክክለኛው አቅማቸው ተመልሰው

የተለመደውን ተግባራቸውን ለማከናወን ረጅም ጊዜ ይወስድባቸዋል፤

በተለይ በጉዳት ምክንያት ማስታገሻ መድሀኒት እየወሰደ ያለ አትሌት አልኮሆልን ቢጠቀም ጨጓራው እንዲቆስል ከማድረጉም

ባለፈ ከመድሀኒቱ የሚገባውን ጥቅም እንዳያገኝ ያደርገዋል፤

አልኮሆል በተጨማሪም የሰውነትን የስብ ክምችት መጠን ይጨምራል፡፡ ሰውነት ከፍተኛ ስብነት ያለው ምግብን ተጠቅሞ

አልኮሆል መጠጥን ቢወስድ፤አልኮሆሉን በቀጥታ ለኃይል በማዋልና በአንጻሩ ከምግብ የተገኘው ስብ አከማችቶ በማስቀመጥ

ለአላስፈላጊ እና ያልተመጣጠነ የሰውነት ክብደት ይዳርጋል፤

በመሆኑም በአልኮል ሳቢያ በአካል ብቃት ላይ ከሚደርሰው ችግር ለመታደግ፡-

በብዛት ከመጣጠት ተቆጠብ/ቢ፣

ከመጣጣትህ/ሽ በፊት መጠንህን/ሺን እወቅ/ቂ፣

አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር ከማንኛውም የስፖርታዊ እንቅስቃሴ በፊት ከመጠጣት ተቆጠብ/ቢ፤ አስገዳጅ ሁኔታ

ከገጠመህ ግን ከሰባ ሁለት ሰዓታት በፊት ውሰድ/ጂ፣

በባዶ ሆድህ ከመጠጣት ተቆጠብ/ቢ፣

ከየትኛውም አልኮል አጠቃቀም በኋላ ብዛት ያለው አልኮሆል የሌለበትን የስፖርት መጠጥ ወይም ንፁህ ውሃ መጠጣትህን

አትዘንጋ/ጊ፣

ጉዳት ከደረሰብህ/ሽ ከ24 - 36 ሰዓታት በኋላ እንጂ በፊት አልኮል ከመጠቀም ተቆጠብ/ቢ፣

ለየትኛውም ጉዳት የተሰጠ ማስታገሻ መድሀኒቶችን እየወሰድክ/ሽ አልኮሆል አትጠቀም/ሚ፣

የአካል እንቅስቃሴ ከተሰራ በኋላ አልኮሆል ከተወሰደ መወሰድ ያለበት የፕሮቲን እና ካርቦሀይድሬት ምግቦችን ከወሰድክ/ሽ በኋላ

ነው፤

Page 47: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

ትውስታ

እ. ኤ. አ. ከ1960 – 2012 የ30ኛው ለንደን ኦሎምፒክ ድረስ ውጤታማ የነበሩ የኦሎምፒክ ረጅም ርቀት ሯጭ ጀግናአትሌቶችን በማስታወስ ታላቅ አክብሮት ለኢትዮጵያውያን ስመ ጥር ጀግኖቻችን!! በማለት ለቀጣዮቹ ጀግኖች መልካምምኞት እየተመኘን ቀዳሚዎቹን ቀጥሎ ባለው ውጤታቸው እናስታውሳቸዋለን:-

1) አበበ ቢቂላ …………………………(2 ወርቅ)

2) ማሞ ወልዴ…(1 ወርቅ፣ 1 ብር፣ 2 ነሃስ)

3) ምሩፅ ይፍጠር ………………….(2 ወርቅ)

4) ሞሐመድ ከድር ……………….(1 ነሃስ)

5) እሸቱ ቱራ ……………………….(1 ነሃስ)

6) ደራርቱ ቱሉ ………….(2 ወርቅ፣ 1 ብር)

7) ፊጣ ባይሣ …………………..(1 ነሃስ)

8) አዲስ አበበ ……………………(1 ነሃስ)

9) ፋጡማ ሮባ …………………..(1 ወርቅ)

10) ኃይሌ ገ/ስላሴ ……………….(2 ወርቅ)

11) ጌጤ ዋሚ ………….(1 ብር፣ 2 ነሃስ)

12) ገዛገኝ አበራ ………………….(1 ወርቅ)

13)ሚሊዮን ወልዴ …………………. (1 ወርቅ)

14) አሰፋ መዝገቡ …………………..(1 ነሃስ)

15)ተስፋዬ ቶላ …………………….(1 ነሃስ)

16) ቀነኒሣ በቀለ ………(3 ወርቅ፣ 1 ብር)

17) መሰረት ደፋር ……(2 ወርቅ፣ 1 ነሃስ)

18)ጥሩነሽ ዲባባ ……..(3 ወርቅ፣ 2 ነሃስ)

19) እጅጋዬሁ ዲባባ ………………(1 ብር)

20) ስለሺ ስህን …………………….(2ብር)

21) ፀጋዬ ከበደ …………………….(1 ነሃስ)

22)ቲኪ ገላና ………………………(1 ወርቅ)

23) ደጀን ገ/መስቀል ……………(1 ብር)

24) ሶፍያ አሰፋ …………………(1 ነሃስ)

25)ታሪኩ በቀለ …………………(1 ነሃስ)

Page 48: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የ2007 ዓ. ም. ደጋፊዎቻችንና አጋሮቻችን

ፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን

SΛMSUNG

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ስፖርት ኮሚሽንና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የ2007 ዓ. ም. ደጋፊዎቻችንና አጋሮቻችን

ፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን

SΛMSUNG

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ስፖርት ኮሚሽንና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የ2007 ዓ. ም. ደጋፊዎቻችንና አጋሮቻችን

ፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን

SΛMSUNG

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ስፖርት ኮሚሽንና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Page 49: ዜና መፅሔት ቅፅ 1፣ ቁ. 8/2008 · 2019-10-15 · በድምሩ 46 የአሠልጣኝነት የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በፊዚዮቴራፒ ሕክምና ወንድ

የፌዴሬሽኑ ሙሉ አድራሻ፡-

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ስልክ ፡- +251-116-479765/+251-116-450752

ፋክስ፡- +251-116-450879

ድረ - ገፅ፡- http://www.eaf.org.et

ኢ-ሜል፡- [email protected]

ፌስቡክ፡- Facebook Ethiopian Athletics Federation

ፖ.ሣ.ቁ.፡- 13336

ጉርድ ሾላ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣

የኮሙኒኬሽንና ሃብት አሰባሰብ ዳይሬክቶሬት፤

Ethiopian Athletics Federation

Communications & Marketing Directorate.