yxyr nbrt lw lw-#n x ym§md ¥hbrsÆê bx!t×ùà e trÙ» seasons ailing societies... ·...

94
yxyR NBrT lW_ lW-#N ym§mD ¥HbrsÆê E TRÙ» bx!T×ùÃ Forum for Environment (FfE) If we thke care of the Earth, the Earth will take care of us.

Upload: dangthuy

Post on 27-Jul-2018

213 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

yxyR NBrT lW_XÂlW-#N ym§mD ¥HbrsÆêE TRÙ»bx!T×ùÃ

Forum for Environment (FfE)

If we thke care of the Earth,the Earth will take care of us.

yxyR NBrT lW_XÂ

lW-#N ym§mD ¥HbrsÆêE TRÙ»bx!T×ùy

ዋና ተመራማሪፕሮፌሰር ዶ.ር ዛቢን ተሮጀር

ተባባሪ ተመራማሪዎችሔለን ግሬንዘባች ጁሊያ ፊትዝነርፈርደሪክ ዙር ኸይደ ክርሰቲን ሰፍሪንግሪጎር ኩህነርት አንድሬ ታየልበሪታ ላንግ ቴዎድሮስ ካሳሁንሳይመን ፔት አዳነ ከበደ

ትርጉምዳዊት ደስታ

ፕሮጀክት አሰተባባሪዎችማህሌት ታደሰ (FfE)አዳነ ከበደ (HoAREC/N)

አየለ ከበደ (HBF)

አሳታሚፎረም ፎር ኢንቫይሮንመትስልክ፡ +251 (0) 115 521 662/76ፋክስ፡ +251 (0) 115 521 034የመ.ሳ.ቁ 10386አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ሐምሌ 2004 ዓ.ም

የጥናት ውጤቱ ሰፋ ያለ ተደራሽነት እንዲኖረው በማሰብ ለማሳተም የሚያስፈልገውን ወጪ በገንዘብ የደገፈው የሃይንሪሽ ቦል ስቲፍቱንግ የኢትዮጵያ ቢሮ ሲሆን ለተደረገልን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

የዚህን መጽሀፍ ቅጂ በሙሉም ሆነ በከፊል በማሳተም ለማስተማሪ መጠቀም ይቻላል፡፡ ለዚህ ዓላማ መጠቀም የሚፈልግ ድርጅት ወይም ተቋም ለአሳታሚ ድርጅቶቹ ማሳወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህን እንጂ መጽሀፉን በማንኛውም ሁኔታ ለሽያጭ ማዋል ክልክል ነው፡፡

የዚህን መጽሀፍ የኤሌክትሮኒክስ ቅጂ በሚከተሉት ድረገጾች ማግኘት ይቻላል፡፡ www.hoarec.org www.boell-ethiopia.org www.ffe-ethiopia.org

ማውጫ ገጽምስጋና መግቢያ .................................................................................................................................................... 1 1. የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ልዩ ልዩ ገጽታዎች በኢትዮጵያ ............................................ 82. የአየር ንብረት ለውጥ እና የመላመድ ዘዴ ጥናትና ምርምር፡ አመክንዮና ንድፍ...................................................................................................................... 11 3. በጥናቱ የተገኙ አበይት እውነታዎች ........................................................................................ 16 3.1 የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ጥምር ገጽታ በኢትዮጵያ ................................... 16 3.2 በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ገጽታዎች ውስጥ ያለ የመንስኤ -ውጤት ግንኙነት 4. የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች በዋና ዋና የግብርና ዘርፎች ላይ ................................... 20 4.1 ቅይጥ የግብርና ሥርዓት በልዩ ልዩ የትኩረት ደረጃ .................................................. 20 4.1.1 የሰብል ምርት 4.1.1.1 የግብርና አካባቢያዊ ሁኔታ ለውጥ .............................................. 21 4.1.1.2 ከፍተኛ የምርት ማሽቆልቆል ........................................................ 22 4.1.1.3 የምርት ፈፅሞ መጥፋት ወይም መውደም ................................ 25 4.1.1.4 የሰብል በሽታዎች ............................................................................ 27 4.1.2 የእንሰሳት እርባታ ............................................................................................... 27 4.1.2.1 ዝቅተኛ የእንሰሳት ምርታማነት .................................................... 29 4.1.2.2 የእንሰሳት በሽታዎች ....................................................................... 31 5. “መቋቋም (Coping)” ወይስ “የመላመድ ዘዴ (Adaptation)” የመተዳደሪያን የማገገም ብቃት መታደግ ................................................................................. 34 5.1 የአየር ንብረት ለውጥ - የተደላደለን ተስማምቶ የመኖር ዘዴ የሚሸረሽር ኃይል የመላመድ ዘዴ ................................................................................... 36 5.2 ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ተላምዶ የመኖር ዘዴ ............................................................... 37 5.3 በማህበረሰባዊ ሽግግር ወቅት የሚያስፈልግ የመላመድ ዘዴ ..................................... 38 5.4 ተላምዶ መኖር፡- መተዳደሪያዎችንና የተቋማትን ገፅታዎች መለወጥ ............................................................................................................................... 40 5.4.1 የተዳከሙ ወቅቶች- ለክፍለ ዘመናት የቆመ ህግጋት ፈተና የኛንጋቶም ዘመን አቆጣጠር ................................................................. 41 5.4.2 የመላመድ ዘዴ እንደ መሠረታዊ ሽግግር/ለውጥ ስርዓትና የአርብቶአደሩ ነባራዊ እይታ.............................................................. 456. መደምደሚያ፡- የመላመድ ዘዴ አሉታዊ ተፅዕኖን ከመቀነስ ብቃት /ስርየት/ እና ከገንዘብ ድጋፍ ጋር ይያያዛል ................................................................. 48

መንስኤያዊ ጥናት 1፡ ድርቅ በምስራቃዊ ዞን - በብሪታ ላንግ ..................................................... 51መንስኤያዊ ጥናት 2፡ የኛንጋቶም ከፊል አርብቶ-አደር እይታ - በጁሊያ ፊዝነር፡፡ .................. 57መንስኤያዊ ጥናት 3፡ ወጥነት ያጣ ዝናብ በምእራብ - በሳይመን ፔዝ .................................... 72መንስኤያዊ ጥናት 4፡ ከልማድ መላቀቅ - የራያ አዘቦ ጨው ነጋዴዎች - በክርስቲያን ሰፍሪን .............................................................. 78መንስኤያዊ ጥናት 5፡ ወደፊት በቂ ውሃ ይኖር ይሆን? በአንድሬ ቴየሌ .................................... 82መንስኤያዊ ጥናት 6፡ በረዶ ጠባቂውን ያውቋቸዋል? - ሳይመን ፔዝ ....................................... 86 7. ማጣቀሻዎች .................................................................................................................................... 888. መሰረታዊ ቃላትና ፍቺዎቻቸው ............................................................................................... 88

ምስጋና

በአስራ ሶስትቱም የጥናት ማዕከላት የሚገኙት የግብርናና የገጠር ልማት ቢሮዎች ይህ የምርምር ስራ በተሳካ ሁኔታ ይጠናቀቅ ዘንድ ለተከታታይ ሶስት ወራት በመስክ ስራ በመሳተፍና ጥናቱን በማስተባበር ያደረጉት አስተዋፆ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች ስማችሁ ለተዘረዘረው የግብርናና የገጠር ልማት ባለሙያዎች በጥናቱ ሂደት በአስተባባሪነትና በአስተርጓሚነት በመሳተፍ ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ጥረት የአፍሪካ ቀንድ የአካባቢ ማዕከልና ጂ.አይ.ዜድ ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባሉ፡፡

1. አቶ ብርሃኑ ኃ/መስቀል2. አቶ አደራጀው ጎንፋ 3. አቶ ጂብሪል አብዱሌ 4. አቶ ዮናስ መኮንን 5. አቶ ሸምሰዲን ጁሀር 6. አቶ ሶያ ኩሩፓ 7. አቶ ደምሰው አለማው 8. አቶ እንዳለካቸው የሺጌታ 9. አቶ መለሰ በርሄ 10. አቶ ገብረአምላክ ፍሰሃ 11. አቶ ሎቡዋ ካኩታ 12. አቶ ለገሰ አሰፋ 13. 13. አቶ ሚኪያስ ወንድሙ

በተጨማሪም አቶ ዲንቃ ዘውዴ ከአፍሪካ ቀንድ የአካባቢ ማዕከል ለጥናትና ምርምሩ መሳካት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡

1

መግቢያ ባለንበት ዘመን የሙቀት መጠን መጨመርና የዝናብ ተለዋዋጭነት ሁኔታ በመላው ዓለም በሰፊው የሚታይና የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ክስተት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በታችኛው የማህበረሰብ ክፍል ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን ተገቢውን ትኩረት ካለማግኘቱም ባሻገር ገና በቂ ጥናትና ምርምር አልተደረገበትም፡፡

ከዚህ እውነታ በመነሳትም

• የአየር ንብረት ለውጥ በእርሻ ምርትና በሀገሬው የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች ምንድናቸው?

• ማህበረሰቡና እያንዳንዱ አርሶአደር እና አርብቶ አደር አዳዲሶቹን የአካባቢ ለውጦችና ሁኔታዎች እንዴት ይተነትናቸዋል? ለተግዳሮቶቹስ ምላሽ የሚሰጠው በምን መልኩ ነው?

ለሚሉትና ተያያዥነት ላላቸው ጥያቄዎች መልስ ለማፈላለግ የአፍሪካ ቀንድ የአካባቢ ማዕከል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር አንድ ዓመት የፈጀ የጥናትና ምርምር ስራ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ ይህ የጥናትና ምርምር ስራ በዋነኝነት የተካሄደው በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ብሔራዊ ፕሮግራም ባለቤትነትና በጂ.አይ.ዜድ. ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ድጋፍ ነው፡፡

‹‹በሁሉም ነገር ላይ የእርግጠኝነት ስሜት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣት››

‹‹ድሮ ዝናብ አዘል ደመና ከሰሜን ይመጣ ነበር፤ አሁን አሁን ግን ደመና ከየትኛውም

አቅጣጫ ሊመጣ ይችላል፤ ዝናብ የመምጣቱ ነገር ግን አስተማማኝ አይደለም፡፡››

አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶአደር የተናገረው

ብዙ ጊዜ የአየር ንብረት ለውጥ መረጃዎች የሚገኙት በላይኛው የአስተዳደር እርከን ደረጃ ነው፡፡ ለምሳሌ ከክልላዊ ተቋማት ይልቅ በአገር አቀፍ ደረጃ ወይንም ስለእያንዳንዱ ወር መረጃ ከመስጠት ይልቅ ዓመታዊ ጨመቁን (አማካዩን) ያስቀምጣሉ፡፡ በዚህ ደረጃ ብዙ ጊዜ በአማካይ የሙቀት መጠን ላይ የመጨመር ሁኔታ ማየት የሚቻል ቢሆንም በሌሎች የአየር ንብረት ገፅታዎች ላይ ተመሳሳይ ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ለውጥ አላሳየም፡፡ እንዲያውም የኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች መጠነኛ የዝናብ መጠን ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ ሆኖም ይህ መረጃ በዝናብ ስርጭትና መጠን ላይ የታየውን መሰረታዊ ለውጥ አያሳይም፡፡ ስለዚህ ከጥናቱ መሪ ጭብጦች አንዱ የአየር ሁኔታ ገፅታዎችና በግብርና ላይ የሚያስከትሉትን ውጤት ከአካባቢው ተዋናዮች እይታ አንፃር መዝግቦ ለመያዝ ነበር፡፡

2

በአስራ ሶስቱም ጥናቱ በተካሄደባቸው ቦታዎች የነበሩ አርሶአደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች አስተሳሰብ በሚደንቅ ደረጃ ተመሳሳይ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁሉም በየአካባቢያቸው ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ መኖሩን ይናገራሉ፡፡ ወጥነት ከሌለውና ወቅቱን ከማይጠብቀው የዝናብ ሁኔታ የተነሳ ግብርና አስቸጋሪና አስጊ እየሆነ መጥቷል፡፡ አያይዘውም ሁሉም በአንድ ቃል የሚመሰክሩት የሰብሎች የእድገት ጊዜ ማጠርን ነው፡፡ከሙቀት የሚመነጭ መጨናነቅ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታየው ውርጭ እና በማደግ ላይ ባሉ ሰብሎች ወሳኝ ወቅቶች ላይ የሚከሰተው ከፍተኛ የዝናብ እጥረት የአየር ንብረት ለውጥ እያባባሳቸው ያሉ አደገኛ ችግሮች ናቸው፡፡ የከፋው የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የአዝመራ ወቅት መለዋወጥና የበረዶ ማዕበሎች መከሰት ነው፡፡

የምስራቅ- ምዕራብ ልዩነት/ክፍፍል፡ ሁለት ዓይነት የአየር ንብረት ለውጥ በምዕራብ

‹‹የዝናብ እጥረት አይገጥመንም፤ ግን ወቅቱን ያልጠበቀና ከባድ ዶፍ ነው የሚዘንበው፡፡ አለያም ዘግይቶ ነው የሚጥለው፡፡ ዘንድሮ እስከ ሰኔ ድረስ ዝናብ አልነበረም፡፡ እንደ ደንቡ ዝናብ የሚጀምረው በሚያዝያ ነበር፣ እንግዲህ ዋናው ችግራችን ይሄ ነው፡፡››

በምዕራብ ኢትዮጵያ በአለፋ ወረዳ የሚገኝ አርሶአደር የተናገረው

በምስራቅ ‹‹የዝናቡ መጠን አነስተኛ በመሆኑ የድርቁ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነው፡፡ የዝናቡ ተለዋዋጭነት ሁሌም ቢኖርም ከዚህ ቀደም የነበረው የድርቅ ሁኔታ ግን እንደዚህ ከፍቶ አያውቅም፡፡››

በምስራቅ ኢትዮጵያ ሚደጋቶላ የምትገኝ አርሶአደር የተናገረችው

የአርሶ አደሮችንና የከፊል አርብቶ አደሮችን ትዝብት በአካባቢያዊ ልዩነት ላይ ተመርኩዘን ስንተነትን ሁለት የተለያዩ የአየር ንብረት ለውጥ ገፅታዎች ብቅ ይላሉ፡፡ የእነዚህ ሁለት ክልሎች መካፈያ ስምጥ ሸለቆን የተከተለ ሲሆን ከሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ተነስቶ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆችን በማካተት በማዕከላዊ ስምጥ ሸለቆ አድርጎ በመጨረሻ ወደ ደቡብ ምዕራብ ይታጠፍና በደቡብ ኦሞ አልፎ በሰሜን ኬንያ እስከሚገኘው የቱርካና ሐይቅ ይዘልቃል፡፡

በስምጥ ሸለቆ በስተምዕራብ የሚገኙ የኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢ አርሶአደሮች ዋና ዋና

3

ችግሮቻችን ብለው ከጠቀሱት መካከል የበረዶ ማዕበሎች፣ ድንገተኛና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እና እንደ ውርጭና ከፍተኛ ሙቀት የመሳሰሉትን ለግምት የሚያስቸግሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶችን ሲሆን በስተምስራቅ የሚገኙት አርሶአደሮችና አርብቶአደሮች ደግሞ ከመጋቢት እስከ ሰኔ የነበረው የበልግ ዝናብና በዝናብ የሚሞሉትና ለግብርና ስራ የሚያገለግሉ የውሃ ምንጮች በጣም መቀነስ ወይንም ጭራሽ የመጥፋት ሁኔታን በመጥቀስ ያማርራሉ፡፡

1.1 የግብርና ምርታማነት መቀነስና የማህበራዊ ትስስር መዳከም

እነዚህ ሁሉ የአካባቢ አየር ሁኔታ ለውጦች፡- የዝናብ እጥረትም ሆነ መብዛት፣ ውርጭ፣ በረዶ፣ ከፍተኛ ሙቀት ሁሉም በመሬት፣ በአፈር እና በውሃ ሀብት ላይ የነበረውን ጫና ያባብሱታል፤ በዚህም ሳቢያ የማህበረሰቡን ተጋላጭነት/ተጠቂነት ወደ ከፋ ደረጃ ያደርሱታል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ከምግብ ሰብል ምርትም ይሁን ከእንስሳት እርባታ አንፃር በግብርና ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያመጣል፡፡ የተፅእኖ ደረጃው ከቦታ ቦታ ጉልህ ልዩነቶች የሚታዩበት ቢሆንም የምግብ ሰብል ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳሉ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች አርሶአደሮች በተደጋጋሚ ያለምንም ምርት ባዶ እጃቸውን የሚቀሩበት ወቅትም አለ፡፡ በተጨማሪም ሰብሎችና እንስሳት ለበሽታዎችና ለተባዮች የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡

በሁሉም የጥናት ጣቢያዎች የሰዎቹ አኗኗር በቅይጥ የእርሻ ዘዴዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በዚህም እርሻና እንስሳት ርቢ እርስበርሳቸው የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ዝቅተኛ የሰብል ምርት የአንድን ቤተሰብ የምግብ አቅርቦት ከመቀነሱም በተጨማሪ ለእንስሳት መኖነት ይተርፍ የነበረን ተረፈ ምርት እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ የእንስሳቱ መዳከምም በተራው አርሶአደሩ ለሚቀጥለው የመኸር ወቅት መሬቱን በሚገባ ለማዘጋጀት ስለማይረዳው ውጤቱ የቀጣዩን የምርት መጠን ይጎዳል፡፡

‹‹የእንስሳት እርባታም ሆነ የሰብል ምርት ተነጣጥለው ሳይሆን በአንድ ላይ ሊቃኙ

የሚገባ የግብርና ዘርፎች ናቸው፡፡››

በምዕራብ ኢትዮጵያ በደጋ ዳሞት ውስጥ የሚገኝ በግ አርቢ የተናገረው

የጥናትና ምርምር ግኝቶች የአየር ንብረት ለውጥ በእነዚህ ተያያዥነት ባላቸው የሀገሪቱ የኑሮ ምሰሶዎች ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ውጤቶች ያመላክታሉ፤ እያሻቀበ ያለውን ተጠቂነት/ተጋላጭነት ሥር እየሰደደ መሄድ በተጨባጭ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በሁሉም ጥናቱ የተካሄደባቸው ቦታዎች እንደታየው በምግብ እህል ራስን አለመቻል የጋራ መገለጫ ሆኗል፡፡ ይህ ሁኔታ በታሪካቸው እስከ አለፉት አስር ዓመታት ድረስ የተትረፈረፈ ምርት

4

የነበራቸውን አካባቢዎችንም ያጠቃልላል፡፡

እ.አ.አ በ2015 ድህነትን በግማሽ ለመቀነስ ያለመውን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ የአየር ንብረት ለውጥ ወደኋላ ጎትቶታል፡፡ በቆላማው አካባቢ በተለይም ከባህር ጠለል ከ3000 ሜትር በላይ የሚገኙት ከፊል አርብቶ አደሮችና አርሶአደሮች ከተጠቂዎቹ ሁሉ በከፋ ደረጃ ላይ ያሉት ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች በህይወት መኖር በራሱ ጥያቄ ውስጥ የገባበት ወቅት ነው፡፡ 1.2 የመላመድ ዘዴ /Adaptation/ እና ማህበራዊ ሂደት

ጥናትና ምርምሩ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች በልማዳዊ የአኗኗር ዘይቤያቸው መቀጠል እንደማይችሉ ግልፅ ነው፡፡ የአሁኑን አኗኗራቸውን ከአዲሱ የአካባቢና የአየር ሁኔታ ለውጥ ጋር ማጣጣም ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የመላመድ ዘዴ የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ ለአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች መፍትሄ ለመስጠት ወቅታዊ እውቀት፣ ቴክኖሎጂ እና የገንዘብ ምንጮችን ለመጠቀም የሚያስችል አዲስ የተፈጠረ ቴክኒካዊ ሂደት አድርጎ የመውሰድ የተሳሳተ ግንዛቤ በሰፊው ይታያል፡፡

በዚህ ተቃራኒ የጥናት ውጤቶች እንደሚያሳዩት የመላመድ ዘዴ ብዙውን ጊዜ ማህበረሰቦች ራሳቸውን ከአዳዲስ የህይወት ሁነቶች ጋር እንዲያላምዱ የሚጠይቅና ነባር ማህበራዊና ተቋማዊ መዋቅሮች ወደ አዳዲስ መልኮች እንዲሸጋገሩ ግድ የሚል ውስብስብ ሂደት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ፀንተው የቆዩና ተቋማዊ መገለጫ የነበራቸው ማህበራዊ ገፅታዎች ተወግደው በምትካቸው ከተለመደው የአኗኗር ስልትና ማዕቀፍ የወጡ አዳዲስ ድርጅታዊ ገፅታዎች መጎልበትና መቋቋም ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡

1.3 ተጋላጭነት /Vulnerability/ እና የመላመድ ብቃት ማነስ

የመላመድ ዘዴ ተራ ሂደት አይደለም፤ እናም እንደ ትምህርት፣ ለቴክኖሎጂ ያለ ቀረቤታ፣ የገንዘብ ድጋፍ ያሉ በርካታ የሀብትና የመረጃ ምንጮችን ከመጠየቁም ባሻገር ጠንካራና ውጤታማ ማህበራዊ መዋቅሮችም ያስፈልጉታል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ ተጠቂነት/ተጋላጭነት፣ የመቋቋም አቅም እና የመላመድ ዘዴ ላይ የሚሰጡ ማብራሪያዎች በግልፅ የሚያመለክቱት፡-

1. በነባራዊው የተጋላጭነት እውነታዎችና 2. ክልላዊ (እንዳንዴም አካባቢያዊ) ተጨባጭ የአየር ንብረት ለውጥ ሁኔታዎችና

5

የሚከተለው ምሳሌ የዚህን ፅንሰሃሳብ ተግባራዊ ትርጓሜ ሊያብራራልን ይችላል፡፡ በመስኖ የሚለማ መሬት እምብዛም ከሌለባቸው አብዛኞቹ የትግራይ አካባቢዎች ጋር ሲነፃፀር በሰሜን ምዕራብ ትግራይ አካባቢ መደባይ ዛና ውስጥ የሚኖሩ አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው የመስኖ ዘዴዎችን በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ልምድና ዕውቀት የተጋላጭነት አውዱ አንድ አካል ነው፡፡

ገፅታዎች መካከል ያለውን ቁርኝት ነው፡፡

እነዚህ የኃይል ስብስቦች በጋራ እና በጥምረታቸው ማህበረሰቦች ከአካባቢያዊ ለውጥ ጋር ለመላመድ የሚያደርጉትን የማህበረሰቦች ውክልና ርቀት (ጥረትና የስኬት ደረጃ) ይወስናል፡፡

የተጋላጭነት እውነታ

• ለተፈጥሮ ሀብት ያለ ቀረቤታ • ኃይልና መረጃ• ትምህርትና ቴክኖሎጂ• ማህበራዊ ቁርኝት/መረብ• መድን • የሕዝብ ብዛት ጫና• የደን መመናመንና የአፈር መከላት• አጠቀላይ ሕብረተሰባዊ ተሀድሶ

ጥቅልተጋላጭነቶች/ተጠቂነቶች

የአየር ንብረት ለውጥ ገጽታዎች

• የዝናብ መጥፋት• ወቅቱን ያለመጠበቅ• ከፍተኛ(ሙቀት፣ቅዝቃዜ፣ ዝናብና የዝናብ እጥረት

የመላመድ/የመቋቋም አቅም

• ጥያቄው፡- ገበሬዎች/አርብቶአደሮች ማድረግ ያለባቸው ምንድነው? (መቋቋም- የአገር በቀል እውቀት ትንታኔና መረዳት ላይ የተመሰረተ ተቋም

ጭብጥ/እሳቤ፡ በፕሮፌሰር ዛቢን ትሮጀር

የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች

6

ምንም እንኳን እንደ መሬትና ሌሎች ሀብቶችን የማግኘት ሁኔታ፣ የትምህርት ተደራሽነት እንዲሁም ማህበረሰባዊ የኃይል ተዋረዶችን ከመሳሰሉ ማዕቀፎች አንፃር ሲታይ ከሌሎች አጎራባች ማህበረሰቦች ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ለየት ያለ የአኗኗር ዘይቤ በመደባይ ዛና ላሉ አርሶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን ለመላመድ ተጨማሪ ጠቀሜታ ይሰጣቸዋል፡፡

በመሬት አቀማመጣቸው ሲታዩ ሁሉም አካባቢዎች በተለይ በመኸር ጊዜ በሚከሰት የተራዘመ ደረቅ አየር፣ ድንገተኛ ዝናብና በረዶ በመሳሰሉ የዓየር ፀባይ ፅንፎችና ወጥነት በሌለው የዓየር ፀባይና በመሳሰሉት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች እኩል ይጠቃሉ፡፡ በውጤቱም ዝቅተኛ የሆነ የሰብል ምርት የሚገኝበት ሁኔታ ቢፈጠርም የመደባይ ዛና አርሶ አደሮች ግን የአየር ንብርት ለውጥን ለመላመድ የሚረዳቸው የመስኖ ሥራ ልምድ ስላላቸው ከሌሎቹ በተሻለ ሁኔታ ለውጡን ለመቋቋም አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ልምድ ከሌሎቹ የተጠቂነት አውዶች ጋር ተዳምሮ የአየር ንብረት ለውጥና ተያያዥ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ የመላመድ አቅማቸውን ያጎለብተዋል፡፡ ይህም ሁኔታ የመደባይ ዛና አርሶ አደሮች የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ከመቋቋም አንጻር ከሌሎቹም የተሻሉ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ለልማት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የኤክስቴንሽንና የማማከር ሥራ ሲሰራ ይህ ለየት ያለ ገፅታ ሊተኮርበትና ትምህርት ሊወሰድበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ተጋላጭነት በዚህ እንደምታ ሁልጊዜም አሉታዊ ተፅእኖዎችን ላያስከትል እንደሚችል ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ‹‹የተጋላጭነት እውነታም›› ከአንዳንድ የግብርና ቴክኖሎጂ ልምዶች ወይንም ከቋሚና ከታወቁ ማህበራዊ የደህንነት ስርዓቶች መገለጫ ከሆኑ ምክንያቶች ስብስብ አንፃር ሊታይ ይችላል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየላሉ ባሉት ሀገር በቀል የማህበራዊ ዋስትና መረቦች ምትክ ወደ ግለኝነት ያዘነበሉ የኑሮ ዘይቤዎች፣ በውጫዊ ተፅዕኖዎች በተቃኘ የፖለቲካ ምህዳር ወይንም ከስልጣን ክፍፍልና ከዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ጋር ተያይዞ በሚመሰረቱ አዳዲስ ተቋማት ሳቢያ የመላው አፍሪካ ማህበረሰቦች የሚያደርጉት የለወጥ ሽግግር የዚሁ የተጋላጭነት እውነታ ክፍሎች ናቸው፡፡

በማንኛውም ሁኔታ የህብረተሰቡ ክፍሎች በአየር ንብረት ለውጥ ወሳኝ ኃይላት ውስጥ የሚኖራቸውን የጋራ ውክልና ይወስናሉ ወይም ያመላክታሉ፡፡ ለማህበረሰቡ የሚኖራቸውን የውክልና ስፋት ልክ ይዘረዝራሉ፤ መልሰውም ይህንኑ በመተንተንና በህይውት ለመትረፍ በሚታትር ሁኔታ የመቋቋም ብቃታቸውን ማስተያያ ያደርጉታል፡፡

አፍሪካ በተለየ ሁኔታ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ናት፡፡ በነባራዊ ይዞታው መንግስታት በ2015 እ.አ.አ በግማሽ እንኳን ሊቀንሱት የማይችሉት የከፋ ድህነት፣ ፈጣን የህዝብ

7

ቁጥር መጨመር፣ እጅግ ዝቅተኛ የልማት ደረጃ፣ ዝቅተኛ የሥራ ኃይል ክፍፍል ብሎም በግብርና ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መወሰን አፍሪካንና ህዝቦቿን በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚመጡ ችግሮች በተለየ ሁኔታ ያጋልጧታል፡፡

በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ ክፍሎች ያሉ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች የተጋለጡ ማህበረሰቦች በምግብ እጥረት፣ በከፋ የአየር ሁኔታዎች ወይንም በበሽታዎች ምክንያት ለሚደርሱ ቀውሶች ተዳርገዋል፡፡ የገጠሩ ማህበረሰብ ለመረጃ፣ ለትምህርት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማወቅና ለመጠቀም እንዲሁም ለፋይናንስ ድጋፍ ያለው ድርሻ እጅግ አናሳ ነው፡፡ አርሶ አደሩ በእጁ የሚገኘው የእህል ክምችት በአንድ ወቅት የሚፈጠርን ችግር ተቋቁሞ ወደ ቀጣዩ የአዝመራ ወቅት ሊያሽጋግረው ይችል ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ የተራዘመ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ ሲባል ግን የውጭ ድጋፍ ማግኘት የግድ ይላል፡፡ ይህ ድጋፍ በአለም አቀፍ ደረጃ በሚኖር ስምምነት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተለወጡ የአካባቢ ሁኔታዎች የሚያስከትሉትን ተፅዕኖዎች ለመቋቋም የሚያስችሉ አካባቢያዊ መፍትሄዎችን የሚያስገኝ ሊሆን ይገባል፡፡ በአፋጣኝ የካሳ ክፍያ መልክ ይሁን ወይንም (በግጦሽ መሬት አስተዳደር ወይም በመልሶ ማልማት) በካርቦንማመቂያ /ማሰባሰቢያ/ ዘዴ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶች ለመደገፍ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ማስፈለጉ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ይህ ጥናት የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ ልዩ ገፅታዎች እጅግ ወሳኝ በሆኑት የግብርና ክፍሎች ማለትም በሰብል ምርትና በእንስሳት እርባታ ላይ የሚያደርሷቸውን ተፅእኖዎች በዝርዝር ይመረምራል፡፡

ይህንን ግብርና ተኮር ትንታኔ በኢትዮጵያ ካለው ከአጠቃላዩ ኢኮኖሚያዊ ልማት ጋር በማያያዝ ሰፋ ያለ የአየር ንብረት ለውጥ እውነታ ተዳስሷል፡፡ ውሃና የውሃ ተደራሽነት ያለውን ሁሉንአቀፍ ፋይዳ ከግንዛቤ በማስገባትም የጥናቱ አምስተኛ ምዕራፍ በዚህኛው የአየር ንብረት ለውጥ ገፅታ ላይ ያተኩራል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በልዩ ልዩ የግብርና ዘርፎች ላይ ከሚያሳድረው ተጽዕኖ በተጨማሪ በማህበረሰቡ የአኗኗር ሥርዓትና አጠቃላይ ገፅታ ጭምር ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ ጥናቱ የተለመዱ የዘርፍ ትንታኔዎችን ከተያያዥ የአኗኗር ሥርዓቶችና ከአካባቢያዊ የመቋቋሚያ ብልሀቶች አንፃር ያሉትን እይታዎችንም አጣምሯል፡፡

8

1. የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ልዩ ልዩ ገጽታዎች በኢትዮጵያ

በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን እውነታ ለመረዳት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቆ ለመረዳት መሞከር ተገቢ ይሆናል፡፡ እነርሱም ለመሆኑ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተከስቷል ወይ? በማህበረሰቡስ ኑሮ ላይ ይህ ለውጥ አሉታዊ ተፅእኖ አስከትሏል ወይ? ድርቅና ጎርፍስ የምንጊዜም የሀገሪቱ የአየር ሁኔታ መለዋወጥ መገለጫዎች አይደሉምን?

ከዓመታዊ የዝናብ መጠንና ሁኔታ ላይ የሚሰጡ የሥነ ልክ መረጃዎች በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መኖርና ክብደት ላይ ብዥታ ፈጥረዋል፡፡ በተለይ የተሻለ ምርታማና የኢትዮጵያን የዳቦ ቅርጫትነት መገለጫ ተደርገው የሚወሰዱት ደጋማ አካባቢዎች በአየር ንብረት ለውጡ ተፅዕኖ እንዳልደረሰባቸው ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ ሁልጊዜ የሚቀርበው ብዙም የጎላ ልዩነት የማያሳየው እንደውም በአንዳንድ የሀገሪቱ ምዕራብ ክፍሎች ላይ መጠነኛ መጨመር የሚያሳየው አማካኝ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ነው፡፡

በመሆኑም የዓለም ባንክ እኤአ በየካቲት ወር 2009 ባወጣው መረጃ ኢትዮጵያ በዓለም ካሉ ከአስራ ሁለቱ ዋነኛ የድርቅ ተጠቂ አገራት ሁለተኛ አድርጎ ሲያስቀምጣት በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ያወጣው መረጃ ደግሞ በወቅቱ ግልፅ የሆነ የሙቀት መጠን መጨመር ቢኖርም በዝናብ መጠንና ስርጭት ረገድ ምንም የጎላ ልዩነት አለመታየቱን ነው፡፡

ይህ አወዛጋቢ ጥያቄ እንዴት ይመለሳል?

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ እውነታውን ለመረዳት የሚቻለው የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑትን አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን ጠይቆ በየዕለቱም ሆነ በየወቅቱ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ያጋጠማቸውን ችግር መረዳት ሲቻል ነው፡፡ በግልፅ እንደሚታየው አርሶአደሮች፣ አርብቶአደሮች፣ ሚትሪዮሎጂስቶችና የአየር ንብረት ሳይንቲስቶች የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክተው የሚለኩት በእጅጉ የተለያዩ ነገሮችን ነው፡፡ አርሶአደሮችና አርብቶአደሮቹ የሚናገሩት ስለ ሁኔታው ተደጋግሞና አዘውትሮ ስለሚታየው እውነታ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በአጠቃላይ የዝናብ መጠን ሁኔታን ለመረዳት በተናጠል አማካይ ውጤቱ አይወሰድም፡፡ የዝናብ መጠን የሚታየው ከተፈለገበት ጉዳይ ማለትም-ሰብሎችና እንስሳቱ ከሚፈልጉት የውሃ መጠን ጋር ተያይዞ ነው፡፡ በተለይ አርሶአደሮችና አርብቶአደሮች በወቅቶችና ከወቅት ወቅት ያሉ እንደ ደረቅ ፀሐያማነት፣ ጎርፍ የሚያስከትል ዝናብ፣

9

በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የበረዶ ማዕበሎች የመሳሰሉ ለውጦችንና ልዩነቶችን ጠንቅቀው ያውቋቸዋል፡፡

በመሆኑም በመጀመሪያ እይታ ሳይንሳዊ መገለጫ የሌላቸውና የቀድሞውን ዘመን ወደ ማወደስ ያዘነበሉ ስነልቦናዊ እይታዎች ቢመስሉም የነዋሪዎቹ ግንዛቤዎች ግሩም ወጥነት ባለው ድምፀት የቀረቡ ገለፆዎች መሆናቸውን ይጠቁማሉ፡፡ ይህም የመረጃዎችን ተዓማኒነት ለማጠናከር በጥናትና ምርምር ቡድኑ ተወስዷል (በተጨማሪ ጄኒንግስ ኤስ እና የጄ. ማግራዝ እ.ኤ.አ 2009 ስራ ገፅ 12 እና ተከታዩን ይመልከቱ)፡፡

‹‹በረዶ ድሮም ነበር፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን አጥፊነቱ እየጨመረ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 የነበረው

በረዶ በህይወቴ ካየሁት ሁሉ እጅግ አስከፊው ነው፡፡ አንድ መንደር ምርቱን ሙሉ በሙሉ ያጣበት

ሁኔታ ተከስቷል››

በአማራ ክልል ደጋማ ክፍል ያለ አርሶአደር

10

የኛንጋቶም የአገር ሽማግሌ ከፊል አርብቶአደር

የኛንጋቶም አካባቢ ባልቴት

‹‹የወራቱ ስሞች እስካሁን አልተቀየሩም፤ ነገር

ግን ወራቱ ስለማንነታቸው የሚናገሩት ነገር

የለም፡፡ የቀድሞው ስሞቻቸው በነዚያ ወራት

በአካባቢው ምን እንደሚከሰት የሚጠቁም ነበር

አሁን ግን ምንም ነገር ስለማይነግሩን የወራቱ

ስሞች እንዲለወጡ እንፈልጋለን፡፡››

‹‹አስታውሳለሁ፡፡ ዝናቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ

እየቀነሰ ነው የመጣው፤ ለሶስት ወራት ያህል

በተከታታይ ይጥል የነበረው ዝናብ ወደ ሁለት

ወራት ቀነሰ፡፡ ሁሉ ነገር ተለውጧል፡፡ አሁን

ዓመቱን ሙሉ በጋ ነው፡፡ የክረምት ወራት

የሚባል ነገር እየጠፋ ነው፡፡››

‹‹አሁን አሁን ቀን የሚጨፍር ማንም

የለም፡፡ ሙቀቱ በፍፁም የሚቋቋሙት

አይደለም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ድክምክም ነው

የምትለው፡፡ ለዚያ ነው ክብረ በዓላቶቻችን

ሁሉ አሰልቺ የሆኑት፡፡››

የሰዎቹን ገለፃና አነጋገር ስንተነትን ሁለት

አጠቃላይ ድምዳሜዎች ላይ እንደርሳለን፡-

• ያለጥርጥር ማህበረሰቡ በአየር ንብረት ለውጥ

ሳቢያ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ሁኔታዎችም

ወደ ነበሩበት የማይመለሱ በመሆናቸውና

በተፅዕኖአቸው ምክንያት መሰረታዊ

ለውጦች እንደሆኑም አድርጎ ተርጉሟቸዋል፡

፡ የጥንቱ የወቅታዊነት ህግጋት አሁን

በዓመታዊው የአካባቢ ሁኔታ ላይ ምን

ማድረግ እንዳለባቸው ስለማያመላክታቸው

የዘመን አቆጣጠራቸውን እንኳን እንደገና

ለመሰየም ይፈልጋሉ፡፡

• ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በሁሉም

አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች አንድ

አይነት የአየር ንብረት ለውጥ ውጤቶችን

አልቀመሱም፡፡ የሚታዩት የአየር ንብረት

ለውጦች ማህበረሰቦቹን የሚገዳደሩበት ልዩ

ልዩ መንገዶችና የሚጠይቁት የመቋቋሚያ

ስልቶችም ከቦታ ቦታ የጎላ ልዩነቶች

አሏቸው፡፡

11

2. የአየር ንብረት ለውጥ እና የመላመድ ዘዴ ጥናትና ምርምር፡ አመክንዮና ንድፍ

እ.ኤ.እ. ከየካቲት 2009 እስከ የካቲት 2010 መጨረሻ ድረስ በነበረው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በጀርመን ሀገር ከሚገኘው የቦን ዩኒቨርሲቲ በመጡ ስምንት ጀርመናዊ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች፣ ከአዲስ አበባና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ ሶስት ተማሪዎችና ከየወረዳው ከተውጣጡ 18 የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የተዋቀረ የኢትዮ-ጀርመን የጥናት ቡድን ‹‹በአየር ንብረት ለውጥና መቋቋም›› ላይ ጥናትና ምርምር አካሂዷል፡፡ጥናቱ የተካሄደው በአሰራሶስት ጣቢያዎች ሲሆን በእያንዳንዱ ጣቢያም የተመደበው የጥናት ቡድን አንድ ጀርመናዊና አንድ ወይም ሁለት ኢተዮጵያዊን የያዘ ነበር፡፡ ይህን አደረጃጀትና ተጓዳኝ የመስክ ስራዎችን በድምሩ ስንመለከት በአጠቃላይ የሀያ አራት ወራት በተግባር የተፈተኑ የመስክ ስራዎችን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር እውን ለማድረግ ተችሏል ማለት ነው፡፡

ይህ ጥናትና ምርምር የተካሄደው በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የግብርናና የገጠር ልማት ሚኒስቴር ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ብሔራዊ ፕሮግራም ባለቤትነትና በጂ.አይ.ዜድ. ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ዘርፍ የገንዘብ ድጋፍ እና በሌሎች በጎአድራጊ ድርጅቶች ትብብር ነው፡፡

ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብ በመላው ዓለም ትኩረት ያገኘና በልዩ ልዩ ደረጃዎችም የተተገበረ ነው፡፡ ፅንሰ ኃሳቡ የተፈጥሮ ኃብቶች ምርታማነትን፣ ባህላዊና ስነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታዎቻቸው ለማህበረሰባዊ አገልግሎቶች ተጠብቀው እንዲቆዩ በማሰብ በዘላቂ አኳኋን ተጠቃሚነትን ግቡ ያደረገ ነው፡፡ (ሲዲኢ ኖቭ 2010) የእነዚህ ግቦች እውን መሆንና የእውነታቸው መጠን በተለያዩ ምክንያቶች የሚወሰን ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የህዝብ ብዛትና ተያያዥ የግብርና ስራ መስፋፋት ሁኔታ፣ ለማገዶ ፍጆታ የሚውል የእንጨት ምርትና የደን ምንጣሮ፣ ከልክ ያለፈ ግጦሽና የአፈር መሸርሸርና መከላትን የመሳሰሉት ሁኔታዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ከዚህ አንጻር እንግዲህ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች ደግሞ ከዚያም ያለፈና ተጨማሪ አባባሽ ኃይላት ናቸው፡፡ (ክለሳውን ይመልከቱ)

በልማትና በተጋላጭነቱ እውነታ መካከል ያለውን ቁርኝት ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር የበለጠ ለመረዳት ይቻል ዘንድ በአራት ክልላዊ መስተዳድሮች ማለትም በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ውስጥ የሀገሩቱን የስነምህዳር እና የአመራረት ስርዓት ልዩነቶችን የሚወክሉ አስራ ሶስት ጥናትና ምርምሩ የሚካሄድባቸው ጣቢያዎች ተቋቋሙ፡፡ (ጥናቱ የተካሄደባው ቦታዎች ካርታ ይመልከቱ)፡፡

12

በብሔራዊ ደረጃ በመከናወን ላይ የሚገኘው የዘላቂ የመሬት አስተዳደር መርሀ ግብር በምግብ እህል ራሳቸውን የቻሉና በበቂ ሁኔታ ከፍተኛ የግብርና ምርታማነት አላቸው በተባሉ የሀገሪቱ ክልሎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡ ይህም የተደረገው የገበያ ተወራራሽነትን እና ገበያ ተኮር ምርትን ለማስፋፋትና ለመደገፍ በዚህም ሳቢያ አሁን የተያያዝነውን የስነምህዳራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነት ሂደትን ለመግታት በሚል እሳቤ ነው፡፡

ከእነዚህ የዘላቂ የመሬት አስተዳደር ጣቢያዎች ውስጥ ዘጠኙ በዚህ ጥናትና ምርምር ተካተዋል፤ የስነምህዳርና የምርት ልዩነት እይታዎችን ለማስፋት ሲባል ሌሎች አራት ጣቢያዎችም ተጨምረዋል፡፡

የጥናትና ምርምር ጣቢያዎቹ ካርታ

13

ጥናቱ አራቱንም ዋና ዋና የኢትዮጵያ የግብርና ስነ-ምህዳራዊ ዞኖች የሸፈነ ነበር (በክፍል 3.1 ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ)፡፡

1. ደጋ ብርዳማ ሲሆን ከባህር ጣለል በላይ ከ2400 ሜትር በላይ ባሉ ከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ይገኛል፡፡ ይህ አካባቢ የግብርና ምርት ዓይነትን ይወስናል፡፡ በገብስና በእንስሳት ምርት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ከእነዚህ አካባቢያዊ ገደቦች የተነሳ የደጋ ገበሬዎች በበጎች እና በቀንድ ከብቶች እርባታ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ያተኩራሉ፡፡

2. ወይናደጋ ቀዝቃዛና ከባህር ጣለል በላይ ከ1500 እስከ 2400 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ባቄላና ሌሎች ጥራጥሬዎች፣ እንሰት የመሳሰሉት በርካታ የምግብ ሰብሎች የሚመረቱበት ምርታማው የግብርና ዞን ነው፡፡

3. ቆላ ሞቃታማና ከባህር ጣለል በላይ ከ600 እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸውን በጣም ደረቅ አካባቢዎች የሚወክል ነው፡፡ በተለይ ማሽላ በቆሎና ባቄላ በዚህ ዞን ይመረታሉ፡፡ ይሁን እንጂ የምርቱ መጠን እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡

4. በረሃ በጣም ሞቃታማና ደረቅ እንዲሁም ከባህር ጣለል በላይ ከ600 ሜትር በታች ከፍታ ያለውን አካባቢ የሚወክል ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ከፊልአርብቶአደሮችና አርብቶአደሮች ይኖሩበታል፡፡ ጥሩ በሚባሉ ወይንም ምንም አይነት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ባልደረሰባቸውና በቂ ዝናብ በጣለባቸው ዓመታት በዝናብ በሚለሙ ማሳዎች ላይ ማሽላ፣ በቆሎና ባቄላ ያመርታሉ፡፡

የጥናትና የምርምሩ ዋና ዓላማም በአየር ንብረት ለውጥ እንቅስቃሴ ሁኔታንና በአከባቢያዊ ልዩነቶች ማዕቀፍ ውስጥ ለውጡን ለመቋቋም ጥቅም ላይ የሚውሉ ብልሀቶችን በጥልቀት ለመረዳት ነበር፡፡

ሁሉም የጥናትና ምርምር ቡድኖች ተመሳሳይ የአጠናን ዘዴንና አቀራረብን ማለትም አሳታፊ ጥናትና ምርምር፣ የቅርብ ምልከታና በመጠኑ የተሰናዳ ቃለ መጠይቅ እንደመጠቀማቸው ለአብነት ከተወሰዱ ጣቢያዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማወዳደር ከድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡

14

ጥናቱ የተነሳው ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የደረሰባት ተፅዕኖ ጥቂት ወይንም በከፊል ነው የሚለው አስተሳሰብ የተዛባና አደናጋሪ ነው የሚለውን መላ ምት በማጠንጠን ነው፡፡ እንደመነሻ ሀሳብም የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ አለ የሚለውን አቋም ይዟል፡፡

ለውጡ ብዙ ገጽታዎች ይኖሩታል፤ አንዳንዶች እውነታዎች የሚትሮሎጂ ጣቢያዎች በሚያቀርቧቸው ጥቅል መረጃዎች ሊጋረዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ በሚትሮሎጂ ጣቢያዎች አሰራር መጨረሻ ላይ የምትለካው የዓመቱን አማካኝ የዝናብ መጠን በሚ.ሜ ነው፡፡ ይህ ውሃ በበረዶ መልክ እንደ ማዕበል አንዴ ይወርድና በኋላ ይቋረጥ ወይንም ከአደገኛና ረጅም የድርቅ ወራት በኋላ የወረደ ዶፍ ይሁን የሚታይና የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የሙቀትና የቅዝቃዜ ጽንፎችም በግልጽ የሚታዩ አይደሉም፡፡ ሌሊት አመዳይ/ውርጭ እስኪጥል እየቀዘቀዘ ቀን ቀን ከፍተኛ ሙቀት ቢፈጠርም አማካይ ውጤቱ የሚያሳየው ጥሩ የአየር ንብረት እንዳለ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ኑሮን የሚገፉትና በተጨባጭ ምን እየሆነ እንዳለ የሚያውቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ ናቸው፤ የባቄላ ቡቃያቸውን ብሎም ምርታቸውን የሚያወድመውን የበረዶ ማዕበልና በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳዎቻቸውን የሚጠራርገውን ድንገተኛ ዶፍ

ድንገተኛ ዝናብ በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች

15

በመሆኑም በጥናቱ ሂደት ነዋሪዎቹን ከልብ አዳመጥናቸው በመጨረሻም መረጃዎቻችንን እና ግኝቶቻችንን በዳሰሳዊ የመስክ ስራ ላይ የመረጃ ተአማኒነት ለማግኘት ፍቱን በሆነው የሶስትዮሽ ዘዴ አረጋገጥን፡፡

የጥናት መንገድ ፡- አሳታፊ ዘዴ

የሚቀምሱትና የሚያልፉበት እነሱ ናቸው፡፡ ወቅት ያመጣባቸውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችሉ መላዎችን ለመዘየድ የሚታገሉትም እነሱው ናቸው፡፡

16

3. በጥናቱ የተገኙ አበይት እውነታዎች

3.1 የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ጥምር ገጽታ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሁለት ንፍቀ ክበባት ከአየር ንብረት ተጽዕኖ ገጽታዎች አንጻር

ምዕራብ

የአየር ንብረት ለውጥ

መለያ ጠባያት(ባህሪያት)

• የዝናብ መዘግየትና

የክረምት ወቅቱን

አለመጠበቅ

• የሙቀት መጨመር

• በረዶ

• ንፋስ

• ከባድ (ዶፍ ዝናብ

• (አመዳይ/ውርጭ)

የአየር ንብረት ለውጥ

መለያ ጠባያት(ባህሪያት)

• የበልግ ዝናብ ማጠርና

መጥፋት

• የዝናብ መዘግየትና

የክረምት ወቅቱን

አለመጠበቅ

• የሙቀት መጨመር

ምስራቅ

ከአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ገጽታዎች አንጻር በምዕራብ እና በምስራቅ ኢትዮጵያ መካከል ቀስ በቀስ ልዩነት እየታየ ነው፡፡ ምዕራባዊው ክፍል በዝናቡ ወጥነት ማጣት፣ መምጫ ወቅቱ የማይታወቅ መሆንና የእጥረት ዝንባሌ በማሳየት መታወቅ ጀምሯል፡፡ ይህም ማህበረሰቡ ምን አይነት ሰብሎችን መቼ ማዝመር እንዳለበት እርግጠኝነት አሳጥቶታል፡፡ ከዶፍ ዝናብና ውርጭ ወይንም በረዶ በተጨማሪ የሙቀት መጨመርም ያሳያል፡፡ ስምጥ ሸለቆንና ተያያዥ ምዕራባዊ አካባቢዎችን የሚያጠቃልለው የምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ በበልግ ዝናብ እጥረት ወይንም በበርካታ ቦታዎች ፈጽሞ መጥፋት ፈተና ሆኖበታል፡፡

ጥናቱ በሚካሄድበት ወቅት ለሶስትና በአንዳንድ አከባቢዎች ለአምስት ዓመታት ዝናብ ያልጣለባቸውን ቦታዎች ለመመልከት ተችሏዋል፡፡ እነዚህ አከባቢዎች በክረምት ዝናብ ላይ ከሚደገፈው ከምዕራባዊው ክፍል ይልቅ ህይወታቸው በአመዛኙ የተመሰረተው በበልግ ዝናብ ላይ በመሆኑ ይህ የአየር ንብረት ለውጥ መለያ ጠባይ በማህበረሰቡ የኑሮ ህልውና ላይ ጠንካራ ተፅዕኖ አለው፡፡

17

‹‹የመስከረም በረዶ ራስ ምታት ነው የሆነብን ምክንያቱም ባዶ እጃችንን ነው የሚያስቀረን!›› በምዕራብ ኢትዮጵያ የደጋ ዳሞት አርሶአደር የተናገረው

‹‹ዝናቡ በማሳችን ላይ አንዴ ጢቅ(እንትፍ) ይልበታል፤ በማግስቱ ሙቀቱ ያው ነው እናም

የፀሐዩም ንዳድ ሳሩን ያበግነዋል!››

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የኛንጋቶም ከፊል አርብቶ አደር የተናገረው

በተወሰኑ የግብርና ሥነምህዳራዊ ዞኖች ውስጥ በተመረጡት የጥናትና ምርምር ጣቢያዎች የተገኘውን ይህን የምዕራብ-ምስራቅ የአየር ንብረት ለውጥ ገጽታዎች ማፈንገጥ/መለያየት አስቀምጦ ጉልህ ልዩነቶች ፈጥጠው ታይተዋል (ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ)፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖ ገጽታዎች ከግብርና-ሥነምህዳራዊ ክፍፍል አንፃር ሲታይ

የምርምር ጣቢያ

የበልግ ማ

ነስ/መ

ጥፋት

መዘግ

የት/ወ

ቅት አ

ለመጠበቅ

የሙቀት መ

ጨመ

ያልተስተ

ካከለ/ከባ

ድ ዝ

ናብ መ

ጨመ

ሞቃት ን

ፋስ

በረዶ

አመ

ዳይ/ው

ርጭ

የተራዘመ

ዝናብ

የዝናብ እ

ጥረት

የግብርና ስነምዳራዊ ዞን

አለፋ X X X X X ወይናደጋ፣ቆላ ሰሜን ምዕራብ

መደባይ ዛና X X X X X X ወይናደጋ

ደጋዳሞት X X X X X X X X X ደጋ፣ወይናደጋ ማዕከላዊ ደጋማ አከባቢዎች

ደገም X X X X X X ደጋ፣ወይናደጋ

ቀርሳ ማሊማ X X X X X X X ደጋ፣ወይናደጋ

ራያ አዘቦ XX X X X ወይናደጋ

ሸዋ ሮቢት X X X X ወይናደጋ፣ቆላ ስምጥ ሸለቆ

ቀዎት XX X X X X ወይናደጋ

ፋዲስ X X X X X ወይናደጋ ምስራቅ

ሚደጋ XX X X X ቆላ፣ወይናደጋ

ኛንጋቶም XX X X X በረሃ ደቡብ

18

ማህበረሰቡ በአብዛኛው ያጋጠመውን የአከባቢ ችግሮችና ፅንፍ የያዙ የአየር ሁኔታ ለውጦችን ከአለም አቀፋዊው የአየር ንብረት ለውጥ ሂደቶች ጋር አያያይዘውም፡፡ ስለዚህ በካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀትና በዓለም ሙቀት መጨመር መካከል ያለውን መንስኤ-ውጤት ግንኙነት ወደ ጎን ይለዋል፡፡ በእርግጥ የገጠሩ ማህበረሰብ ስለነዚህ ሂደቶች ምንም አይነት መረጃ የለውም፡፡

አንድ አርሶአደር ግን ስለ ዓለም አቀፉ ሁኔታና ያደጉ ሀገሮች ያለባቸውን ኃላፊነት በተመለከተ የሰማው ነገር እንዳለ ይናገራል፡፡

‹‹ነገሩ እንዴት እንደሆነ እርግጠኛ ባልሆንም ያደጉ ኃገራት የማይፈለጉ

ጋዞችን ወደ አየሩ እንደሚለቁ በሬድዮ ሰምቻለሁ!››

በአጠቃላይ አርሶአደሮቹ ችግሮቻቸውን የሚያብራሩት ኃላፊነቱን የራሳቸው በሚያደርግ አይነት ነው፡- ‹‹ደኖቹን መነጠርናቸው፤የስራችንን አገኘን ውጤቱም ይኽው ነው›› ወይንም ብዙ ሰዎች ኃይማኖታቸውን ወደ ፕሮቴስታንት ዕምነት ስለቀየሩ አሊያም ደግሞ ዝናብ መቼ እንደሚጥል ካለማወቃቸው የተነሳ አርሶአደሮች በበዓላት ቀን ጭምር ስለሚሰሩ በሀጢያታቸው ምክንያት የደረሰ የአምላክ ቁጣ አድርገው ይወስዱታል፡፡

ከዚህ በላይ እንደተገለጸው አርሶ አደሮቹ በተናገሯቸው ሀሳቦች ውስጥ አንዳንድ ትክክለኛ ሀቆች እንዳሉ መመልከት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዝናብ ያመጡ የነበሩት የነፋስ አቅጣጫዎች መቀየር እውነት ነው፡፡ የቅርብ ጊዜ ሳይንሳዊ ሞዴሎች እንደሚያሳዩት ወደ ምስራቅ የሚያቀኑ የአፍሪካ ምስራቅ ባህር ዳርቻ የከባቢ አየር ዝውውሮች የሚፈጠሩት በህንድ ውቅያኖስ መሞቅ ነው፡፡ ከለውጡ የተነሳ የበልግ ዝናብን ያመጡ የነበሩት እርጥበታማ ንፋሶች አሁን ወደ አፍሪካ አህጉር አይደርሱም፤ የዝናብ መጥፋት መንስኤ ተደርጎ የሚወሰደውም ይኽው ነው፡፡

3.2 በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ገጽታዎች ውስጥ ያለ የመንስኤ - ውጤት ግንኙነት

ከላይ በ‹‹መቋቋም ብቃት›› ላይ የተሰጠውን ዕቅድ ታሳቢ አድርገው ሲመለከቱት የሰዎች የተግባር ማዕቀፍ በተጋላጭነት የግንኙነት መረብ ይገለጣል፡፡ ከዚህ ዳራ በተቃራኒ በተጋላጭነት ላይ ያለ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ኢላማ የተደረጉትን ቡድኖች የመቋቋም አቅም ይወስናል፡፡ ቀጣዩ የትንተና ምስል ይህን ተጽዕኖ ይገልጣል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን የአየር ንብረት ለውጥ መለያ ፀባያት ምንነት ለአብነት ተወስደው ጥናትና ምርምሩ ከተካሄደባቸው ቦታዎች የአመራረት ስርዓት አንጻር ይተነተናል፡፡ ምስሉ

19

የልዩ ልዩ መለያ ጠባያትን የተጽዕኖ መጠን በሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሳዩትን ድግግሞሽ በማወዳደር ዳስሷል፡፡

የመንስኤ-ውጤት ግንኙነቱን የሚያሳየው የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎች የውሃ እጥረትን እንደ አመዳይ/ውርጭ እና በረዶ ያሉ ጽንፍ የያዙ የአየር ሁኔታን እንደሚያስከትሉ ነው፡፡ እነዚህ የአየር ንብረት መለያ ፀባያት ፍጹም አዲስና እጅግ የተለዩ አይደሉም፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን ድግግሞሻቸውና ብርታታቸው ጨምሯል፡፡ ይህም በሰብልና በመኖ ምርት መጠን ላይ መቀነስን አስከትሏል፡፡ በዚህ አንጻር በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ከሚያደርሱት እንደ ወባና ተቅማጥ ያሉ በሽታዎች በተጨማሪ የእጽዋትና የእንስሳት በሽታዎችም ላይ ጉልህ መጨመርን አስከትሏል፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ ከተካሄደባቸው ቦታዎች በተለይም ቀደም ሲል በምግብ ራሳቸውን የቻሉ ይባሉ ከነበሩት አካባቢዎች ውስጥ ቢያንስ ግማሹ በአሁኑ ሰዓት ወደ‹‹ረሀብ›› እና ‹‹ድህነት›› ቀጠናነት እንደተለወጡ ይደመድማል፡፡

የቀረ ወይም ያነሰ የበልግ ዝናብ

የክረምት መዘግየት፣መቀነስ ወይንም ወቅት አለመጠበቅ

የውሃ ሀብት እጥረት

የመጠጥ ውሃ ማነስ (እጥረት)

አካላዊ ድካም የከብቶች ምርታማነት

የከብቶች መሞት

ማህበረሰባዊ ህዳሴ

የኑሮ ደ

ህንነ

ትና ሀ

ይል ማ

ጣት

የምርታማነት መቀነስ

ግጭትና ስርቆት

ግራ የተጋባ/የተዋከበ እምነት

የስራ /የሙያ/ለውጥ

የትምህርት እጥረት

የተዛባ ማህበረሰባዊ ስርዓት

ስደት ጨለምተኝነት

የተጽዕኖ ልክ/ጠቀሜታ፡ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ዝቅተኛየተጋላጭነት ሁኔታ፣የህዝብ ቁጥር መጨመር፣የደን

መመናመን፣የአፈር መሸርሸር ወዘተ፡፡

የ8 የጥናት ጣቢያዎች የችግር ዛፍ (Problem Tree)

የገቢ መቀነስ

ረሃብ

ድህነት

የእህል ምርታማነትና የከብት መኖ መቀነስ

በሽታዎች (አዝርእት፣እንስሳትና ሰዎች)

ለእርሻ የሚውል ውሃ ማነስ (እጥረት)

የዕጸዋት ጥገኞችና የአረም መብዛት

የአፈር ለምነት መቀነስ

ትነት ከፍተኛ ምርት የመሬት መሸርሸር ጉዳት (የአዝርእት እና የንብረት)

የሙቀት መጨመር

ከባድ ዝናብ

ንፋስ የበረዶ ክስተቶች

ውርጭ የተራዘመ ዝናብ

20

ችግር አመልካች ምስሉ እንደሚጠቁመው ግልጽ የሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ መለያ ፀባያት ጥናት በተደረገባቸው አካባቢዎች ምርታማነትና የአኗኗር ሁኔታ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖዎች ጥቅል ገጽታ ሲያመላክት ቀጣዩ ክርክር በበለጠ ዝርዝር ገብቶና እያንዳንዱ የትኩረት ዘርፍ ከግብርና፣ ከጤና እና ከአኗኗር ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሰፊው ይመለከታል፡፡

4. የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች በዋና ዋና የግብርና ዘርፎች ላይ

4.1. ቅይጥ የግብርና ሥርዓት በልዩ ልዩ የትኩረት ደረጃ

በግልፅ እንደሚታየው የግብርና ምርት ስርዓቱ በሁለት ምሰሶዎቹ ላይ የቆመ ነው፡፡ እነርሱም የሰብል ምርትና የእንሰሳት እርባታ ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ በተጨባጭ ለሚታየው አካባቢያዊ እውነታ ከዝቅተኛ የገበያ ምርትና የገበያ ስብጥር ጋር ተዳምሮ አግባብነት ያለው መልስ ይመስላል፡፡ ከሰሜን ጫፍ ትግራይ እስከ ደቡብ ጫፍ ደቡብ ኦሞ ያሉት ሁሉም ጥናቱ የተካሄደባቸው ቦታዎች ይህን ቅይጥ የግብርና ሥርዓት መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ የትኩረት ደረጃቸው የየክልሉን ሥነ-ምህዳራዊ፣ አካባቢያዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ማዕቀፎችን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት በምግብ እርዳታና በአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ መሆኗ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ታሳቢ ስናደርግ እነዚህ ቅይጥ የግብርና ሥርዓቶች ለአየር ንብረት ጫናዎች የተጋለጡ በመሆናቸው ዓመቱን ሙሉ ምግብና የኑሮ ዋስትና ማረጋገጥ እንደማይችሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህ አጠቃላይ የተጋላጭነት አዝማሚያ የአየር ንብረት ለውጥ የህልውና መሠረት የሆነውን እና በሁለቱ ምሰሶዎች መካከል ያለውን ተያያዥነት በማናጋት ችግሩን ያባብሰዋል፡፡

ለትንታኔ ያመች ዘንድ እነዚህ እርስ በርሳቸው የተቆራኙ ምሰሶዎች በሚከተለው ዓይነት ተለይተው ይተኮርባቸውና በክርክሩ ሂደት ደግሞ ከመቋቋም ብቃት ጥያቄ አንፃር አብረው ይታያሉ፡፡

የሚከተሉት ገለፃዎች ኑሮአቸውን በአካባቢው የመሠረቱ ነዋሪዎችን ተግባራዊ ምላሾችን፣ ማስተካከያዎችን እና የመቋቋም አቅምን የግድ የሚሉ የአካባቢያዊ ለውጦችን ሁኔታ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ለአርሶአደሮቹ ወይም አርብቶአደሮቹ የልማት አማራጮችን የሚያቀርቡትና በአመራረት፣ በአፈር አጠባበቅ ወይንም በመስኖ አጠቃቀም ዘዴ ወይንም በሌላ የአስተራረስ ውሳኔዎች ላይ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይጠይቃሉ፡፡

21

ገለፃ የተደረገባቸው የጥናት ግኝቶች ቅደም ተከተል በመሠረቱ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ገፅታ አከፋፈል ጋር የሚስማማ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት፣ የባሰ ሁኔታ ትንታኔዎች የስምጥ ሸለቆና ምስራቅና ደቡብ ተያያዥ አካባቢዎችን የተፅዕኖ ገፅታ ያንፀባርቃሉ፡፡ ጥቂት የተሻለ ሁኔታን የሚያሳዩት ገለፃዎች ደግሞ በአየር ንብረት ለውጡ እምብዛም ያልተጎዱባቸውን አካባቢዎች ያመለክታሉ፡፡ በተመሣሣይ ሁኔታ ከላይ የተባለውን ለመድገም ያህል በጅማ አካባቢ ከሚገኝና መና ከሚባል ወረዳ በልዩ ስነ-ምህዳራዊ ፀጋ ቡና አብቃይ አካባቢ ከሚገኝ ጥናቱ ከተካሄደበት ቦታ በስተቀር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች በመላው ኢትዮጵያ ታይተዋል፡፡ በመሆኑም የመወያያ ርዕስ ሆነዋል፤ ምላሽ እየተሰጠባቸውም ይገኛል፡፡ በአብዛኛው እነዚህ ተፅዕኖዎች በኑሮና በኑሮ ዋስትና ላይ እንዳንዣበቡ አደጋዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

የክርክሩ አካሄድ እጅግ ግልፅ የሆነውን በሰብሎችና በእንሰሳት ምርታማነት ላይ የሚታየውን የቅያሬና ለውጥ አመክንዮ የተከተለ ሲሆን አርሶአደሮቹና አርብቶአደሮቹ የሚያቀርቧቸውን ምክንያቶች መሠረት በማድረግ ቅያሬና ለውጦቹን ከአየር ንብረት ለውጥ መገለጫ ፀባያት ጋር ያያይዘዋል፡፡

4.1.1. የሰብል ምርት

የሰብል ምርት በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ አርፎበታል፡፡ ከላይ እንደተመለከተው የዝናብ ወቅቶች ከነአካቴው ይጠፋሉ፣ በግማሽ ይቀንሳሉ፣ በበረዶ ወይንም በውርጭ/አመዳይ ይታጀባሉ፡፡ ወይንም ደግሞ የተዘሩትን ጠራርጎ በሚወስድና የደረሱ ሰብሎችን በሚያወድም የዝናብ ዶፍ ይረበሻሉ፡፡ ይህ አርሶአደሮች በልማዳቸው ላይ በመመርኮዝ አዝመራቸውን በሚመለከት ውሳኔዎቻቸውን እንዲከልሱ ወይም እንደገና እንዲያጤኑ የግድ ይላቸዋል፡፡ የሚከተለው ትንተና እጅግ ወሳኝ የሆኑ ለውጦችና ተፅዕኖዎች በሰብል ምርትና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ባላቸው ልዩ ትርጉም ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

4.1.1.1 የግብርና አካባቢያዊ ሁኔታ ለውጥ

እየጨመረ ከመጣው ሙቀት የተነሳ የግብርና ስነ-ምህዳራዊ ዞኖች በአጠቃላይ ወደ ላይ እያፈገፈጉ ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን አሁን አርሶአደሮች ድሮ ለበቆሎ ምርት ፈፅሞ ምቹ ባልነበረው ደጋማ አካባቢ ላይ በቆሎ ይዘራሉ፡፡ ይህ ለውጥ በመጀመሪያ ደረጃ አዎንታዊና ለማህበረሰቡ የምርጫ ልክና አማራጮችን የሚያሰፋ ነበር፡፡ አርሶአደሮች እነዚህን አጋጣሚዎች ይጠቀሙባቸዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደዚህ ያሉ ከመጠን ያለፉ ወደ ደጋ የሚደረጉ ሽሽቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አስቀድመው ገምተዋል፡፡ “በቅርቡ ሁሉም ቦታ ቆላ መሆኑ አይቀርም፡፡” ይህ ምንም እንኳን የተጋነነ ቢሆንም ጭንቀቱ

22

ተጨባጭ ነው፤ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ መሠረታዊ ለውጥ የመሆኑ ግንዛቤም ግልፅ ነው፡፡

በሌላ በኩል ድሮም ቢሆን ለኑሮም ሆነ ለሥራ አመቺ ያልነበሩት ቆላማና በረሃማ አካባቢዎች በአሁኑ ሰዓት ሙቀቱን ለመቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ አርሶአደሮች ስለሙቀት መጨመሩ ብዙ ያማርራሉ፡፡ የሚቋቋሙበት ሌላ ምንም ዘዴ ስለሌላቸው ራሳቸውንና የእርሻ ከብቶቻቸውን ለማዳን ሲሉ ለጥቂት ሰዓታት ብቻ በመስራት ለመከላከል ይሞክራሉ፡፡

“አረም ማረም አድካሚ ሆኗል፤ ስንሰራ ላብ በላብ እንሆናለን፡፡ አምና የነበረው ሙቀት አይጣል ነው፡፡ በግጦሽ መሬት ላይ ካየነው ተነስተን ልንነግርህ እንችላለን፡፡ ድሮ በጣም ብዙ ሳር ነበር፡፡ በዚያ ላይ ረግረግ የነበሩት ቦታዎች ሁሉ ደርቀዋል፡፡ እንዲህ ያለ ነገር ተከስቶ አያውቅም ነበር፡፡”

እንሰሳት - የቀንድ ከብት፣ በጎችና አህዮች እየጨመረ በመጣው ሙቀት የተነሳ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ይህም ከታች በዝርዝር ይተነተናል፡፡

4.1.1.2. ከፍተኛ የምርት ማሽቆልቆል

“ሰብሎች ዝናብ በሚፈልጉበት ወቅት ምንም ዝናብ አይኖርም፡፡ ደረቅ ያለ ሁኔታን በሚፈልጉበት ወቅት ደግሞ ዝናብ ይጥላል፡፡ በዚህ ሁኔታ አርሶአደር ሆኖ መቀጠል እንዴት እንችላለን”

በሌላው የዓለም ክፍሎችም እንደተለመደው በደንብ የታወቀው የአየር ንብረት ለውጥ መገለጫ ጠባይ መተንበይ የማይቻል የአየር ሁኔታ ክስተቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ክስተቶች ያልተጠበቁ ድንገተኛ ዝናብ መጣል፣ መቆራረጥ፣ ቶሎ ማቆም ወይንም በሰብሎች የእድገት ወቅት ማለትም እርጥበትና ዝናብ በሚፈልጉበት ወቅት ለሁለት ወይም ሶስት ሳምንታት ያህል ክው ብሎ መድረቅ ሊሆን ይችላሉ፡፡

ምንም እንኳን የለውጡ ውጤቶች ክብደት ቢለያይም በደጋማ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮችም ሆኑ በቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩት አርብቶ አደሮች ስለነዚህ ለውጦች ያማርራሉ፤ ይህን ሁኔታ ቀጥለን በዝርዝር የምናየው ይሆናል፡፡

23

በእነዚህ ባጠሩና በተስተጓጎሉ የእድገት ወቅቶች ምክንያት በተለይ ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈልጉ አዝርዕቶች ምርት በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሏል፤ ምርታማነታቸውም ክፉኛ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡

ይህ ለውጥ አርሶአደሮቹ በሚያደርጓቸው የአመራረት ውሳኔዎች ቅያሬ ላይ ይንፀባረቃል፡፡ ቅያሬው በመጀመሪያ በተዛማጅ የአዝርዕት ዝርያዎች ልዩነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

እስካሁን ተጨማሪ የተሻሻለ ዘር ሳይኖር አርሶአደሮች በሁለት የማሽላ ዝርያዎች መካከል ምርጫ አላቸው፡፡

ማሽላ ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈልግ፣ በድርቅ በቀላሉ የሚጠቃ፣ በበቂ ሁኔታ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ እና ጥሩ የገበያ ተፈላጊነት ያለው ነገር ግን አቀንጭራ (ስትሪጋ ሄርናቲካ) በተባለው ፀረ ሰብል አረም በቀላሉ ይጠቃል፡፡

ዘንጋዳ - ለመድረስ አጭር ጊዜ የሚፈልግ፣ ድርቅን በተሻለ ሁኔታ የሚቋቋም፣ ዝቅተኛ ምርታማነትና የገበያ ዋጋ ያለው ሆኖ በስትሪጋ ሄርናቲካ በቀላሉ የማይጠቃ

በውጤት - አልባ ማሳው ላይ የሚታይ አርሶ አደር

24

መና የቀረ እርሻ

የጤፍ ማሳ

ዘንጋዳን ማዝመር የሰብልን መና ሆኖ የመቅረት አደጋን መቀነሻ የሁልጊዜ ብልሀት ሆኗል፡፡ አርሶአደሮች የማሳቸውን ትንሽ ክፍል ለምናልባቱ በዘንጋዳ ሸፍነው አብዛኛውን ማሳ ማሽላ ይዘሩበት ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን በዝናብ መጥፋት ምክንያት እያጠረ የመጣውን የአዝመራ ወቅት ፍራቻ አርሶአደሮች ማሳቸውን ሙሉ በሙሉ ዘንጋዳ ሲዘሩና ባዶ እጃቸውን እንዳይቀሩ ሲያደርጉ ይታያል፡፡ ይህን ሲያደርጉ ገና ከጅምሩ የምግብ ዋስትናቸው ዓመቱን ሙሉ አብሯቸው እንደማይዘልቅ ሙሉ በሙሉ እያወቁ ነው፡፡

ከጤፍ አዝመራም ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ዘዴ ይታያል፡፡ አሁን አሁን በየማሳው

ይህ በአየር ንብረት ለውጥ አስገዳጅነት በጤፍ ዝርያ ላይ የተደረገው ቅያሬ ከምግብና ከመተዳደሪያ ዋስትና ጋር በተያያዘ ውጤቱ አደገኛ ነው፡፡ድሮ ጤፍ ለአብዛኛው ድኃ ቤተሰብ እንደ ዋነኛ የምግብ ፍጆታነት አይወሰድም ነበር፡፡

የምትታየው ቢንጄ የተባለችው ቶሎ የምትደርሰው ዝርያ ናት፡፡ ምክንያቱም ተመራጩና ከፍተኛ ምርት የሚሰጠውና በገበያም ተፈላጊ የሆነው ማኛ የተባለው የጤፍ ዝርያ በአሁኑ የአየር ንብረት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እንደሚወድም ስለተረዱ ነው፡፡

“ከዚህ በፊት አካባቢያችን ለምና በጤፍ ምርቱ የታወቀ ነበር፤ አሁን ግን ፍፁም ተቀይሯል፡፡ ለአርባ ቀናት የሚቆይ የክረምት ወቅት በቂ አይደለም፤ የተለመደው ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ነው፡፡”

25

ይልቁንም ዋጋው ዝቅተኛ በሆነው ማሽላ ለውጠው የምግብ ፍጆታቸውንና ዋስትናቸውን ያረጋግጡበት ነበር፡፡ አሁን ግን በዝቅተኛ ምርቷ በምትታወቀው የጤፍ ዝርያ ቢንጄ ይህ ብልኃት የሚያዋጣ አልሆነም፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ማለት ግን የሰብሎች መድረሻ ወቅት የማጠር አዝማሚያ ማለት ብቻም አይደለም፡፡ የማይፈለግና ባልተጠበቀ ወቅት የሚጥል ዝናብም ማለት ነው፡፡ የጥቅምት ዝናብ ፍፁም አጥፊ ነው፤ የደረሰው ጤፍ በቆልት መሆን ይጀምራል፡፡

በተመሳሳይ በመጠኑም ሆነ በአደገኝነቱ ታይቶ የማይታወቅ ያልተጠበቀ ጎርፍም የቅርብ ዓመታት ችግር ሆኗል፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት በደቡብ ኦሞ የሚኖሩ ኛንጋቶሞች በኦሞ ወንዝ ዳርቻዎች ዘርተውት የነበረው የማሽላና የበቆሎ ዝሪት በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች በጣለው ወቅቱን ያልጠበቀ ሁለተኛ ጎርፍ ተጠራርጎባቸዋል (ወንዝ -ሽሽ እርሻ 4.1.1.3 ይመልከቱ፡፡)

4.1.1.3. የምርት ፈፅሞ መጥፋት ወይም መውደም

“ይህ እርሻችን ነው፡፡ አሁን በማሳው ላይ አንዳች ነገር የለም፡፡ በዚህ ዓመት ሶስት ጊዜ ማሽላ አራት ጊዜ በቆሎ የዘራንበት ቢሆንም ምንም ምርት ማግኘት አልቻልንም፡፡”

ከላይ በተገለፀው የምእራብ-ምስራቅ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ገፅታዎች ልዩነት ጋር በተያያዘ በተለይ የበልግ ዝናብ ፍፁም መጥፋት መገለጫው በሆነው ምስራቃዊው ክፍል በአንዳንድ ጥናቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ማለትም በምስራቅ (ፈዲስ እና ሚዳጋቶላ ከሐረር በስተደቡብ) እና በደቡብ ቆላማ አካባቢዎች (ኛንጋቶም ከፊል-አርብቶአደር - በደቡብ ኦሞ ክልል ውስጥ) ለምርት አስፈላጊ የሆነው ከጥር እስከ ሰኔ የሚጥለው የበልግ ዝናብ ላለፉት አራትና አምስት ዓመታት ያህል አቁሟል፡፡ አርሶአደሮቹ አሳዛኝና ስለነገ ምንም ተስፋ የሚያደርጉት ነገር የሌላቸው ሆነዋል፡፡ አንዳንድ የሚዳጋቶላ አካባቢ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፡

“በማያቋርጥ ጥርጣሬ ውስጥ ነኝ - ለአየር ንብረቱ የሚስማማ ትክክለኛ ዘር ዘርቼ ይሆን?

ፍሬ ይገኝ ይሆን? ለወደፊቱ በአይናችን የምናየው ነው- በአካባቢው ምንም ጥሩ ነገር አይኖርም፤ ተስፋ የለውም!”

“ድሮ ጥሩ ምርት እናመርት ነበር፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2005 አንዳችን አራት ኩንታል (1 ኩንታል = 100 ኪ.ግ) አግኝተናል፡፡ ከአስራ ስድስት ዓመታት በፊት (እ.ኤ.አ በ1993)

26

የውሃ እጥረት

አንድ ሰው ከ1.5 ሄክታር መሬት ላይ 100 ዳሮታ (1 ዳሮታ = 50 ኪ.ግ) ማሽላ አምርቷል፡፡ ሁለት ጉድጓዶችን ሞልቶ ለሁለት ዓመታት በልቷል፡፡”

“በ1993 እ.አ.አ ሃያ ኩንታል ሽንኩርት አምርቻለሁ፡፡ ያንን ሸጨ ሁለት ላሞች፣ አንድ በሬና አዳዲስ ልብሶች ገዛሁበት፡፡ በዚህ ዓመት ግን ምንም የለም፡፡” እነዚህ ንግግሮች ሁሉ የሚያሳዩት አርሶአደሮች እጅግ የበለፀጉ ዘመናትን እንዳሳለፉ ነው፡፡ የዝናብ መጠን በሚዋዥቅበትና አዝመራ በሚከዳበት ወቅት የሚያጋጥመውን መጥፎ ሁኔታም ያውቁታል፡፡ ክፉ ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚያልፉም ያውቁበታል፡፡ ይሁንና አርሶአደሮችን አሁን የገጠማቸው ሁኔታ መላ የለውም፤ ፍፁም አዲስ ሆኖባቸዋል፡፡

“ዝናቡ ጥቂት ነው፤ ድርቁ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል፡፡ መዋዠቅ ሁሌም አለ፡፡ እንደ አሁኑ ያለ ድርቅ ግን ታይቶ አይታወቅም፡፡ ከምናውቀው የተለየ ነው፡፡”“የዝናብ ችግር ለአስርና አስራ ሁለት ዓመታት ያህል ዘልቋል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ግን እጅግ ብሶበታል፡፡ ምንም ዝናብ አልነበረም፡፡ የዝናብ ውሃ አጠራቅማለሁ እጅግ የባሰበት ዓመት ግን ይህኛው ዓመት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ቢያንስ ትንሽ ዝናብ አግኝተናል፤ አሁን ግን ምንም የለ፡፡ እንዲህ ያለ ለውጥ ከአያት ቅድመ አያቶቼ እንኳን ሰምቼ አላውቅም፡፡”

ዝናቡ በአብዛኛው ውሽንፍራማ ነው፤ ውሀውም ደረቁንና ሸክላማ አፈሩን ዘልቆ ወደ ውስጥ አይገባም፤ ይልቁንም ኃይለኛ ጎርፍ ይፈጠራል፡፡ አርሶአደሮቹና አርብቶአደሮቹ የዝናብ ማነስን ብቻ ሳይሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተከሰተውን እና በተለይ በበልግና በክረምት መካከል ባሉት ደረቅ ወራት በግልፅ የሚታየውን የሙቀት መጨመርም ተረድተዋል፡፡

27

መንስኤያዊ ጥናት 1፡- ገፅ 51 ላይ ባለው የሚዳጋቶላ (ከሐረር በስተደቡብ-ምዕራብ የሚገኝ ቦታ) ምስል እንደሚያሳየው የአብዛኛው ማህበረሰብ የምግብ ዋስትና ስጋት በማህበራዊ ዋስትና ላይ እየሰፋ የሚሄድ ተፅዕኖ አለው፡፡ የማህበረሰቡን እርስ በርስ መደጋገፍ ባህልን የመሸርሸር አቅም አለው፡፡

ተመሳሳይ የሆነ አሳዛኝ የህይወት ገፅታ በካንጋተን እና ቀጥሎም በኛንጋቶም ውስጥ በሉኩሉን ባለው ጥናቱ በተካሄደበት ቦታ ለማስተዋል ተችሏል፡፡ ነዋሪዎቹ ላለፉት አምስት ዓመታት ጭልጥ ብሎ ስለጠፋው የበልግ ዝናብና እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ ከነአካቴው ቀጣይነት የሌለውና ሊተነበይ የማይችል ስለሆነው ዝናብ ያማርራሉ፡፡ በአየር ንብረቱ ላይ ከታዩት ለውጦች የተነሳ የኛንጋቶም ህልውና የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ብለው ያስባሉ፡፡ እናም የዛሬውን ዘርፈ ብዙ ጫናዎችና አስከፊ ተፅዕኖዎች ቀርበን ስንረዳ ከሀሣባቸው ጋር መስማማትን የግድ ይላል፡፡

መንስኤያዊ ጥናት 2፡- ገፅ 57 ከላይ የሚገኘው የደቡብ ኦሞ የኛንጋቶሟ ሴትዮ የሞሩ ታሪክ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ቀድሞ የነበሩት ማህበራዊ ስርዓቶች ፈፅሞ የማይመለሱበትን አደገኛ ደረጃ ከሚያሳዩ መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

4.1.1.4 የሰብል በሽታዎች

“ሃራማዛፕ (ስትሪጋ ሄርናቲካ) ከዝናቡ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ዝናብ ካጠረን ከሶስትና አራት ዓመታት ጀምሮ ነው መታየት የጀመረው፡፡ ከዚያ በፊት ሃራማዛፕ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ድሮ ጥቂት ነበር ነገር ግን የዝናብ እጥረቱ እየባሰ ሲመጣ ተስፋፋ፡፡”

ከረጅም ፀሐያማ ወቅት፣ ከመሸጋገሪያ የድርቅ ወቅቶችና ከበረዶ ማዕበል የተነሳ ሰብሎች በአስከፊ ሁኔታ በበሽታዎች ይጠቃሉ፡፡ አንዱ የዚህ ክስተት ጥሩ ማሳያ እንደ አርሶአደሮቹ አስተያየት በሰብሎቹ ስሮች ላይ የሚጠመጠመው ስትሪጋ ሄርናቲካ (ፎቶውን ከላይ ይመልከቱ) ነው፡፡ በመሆኑም ስትሪጋን መንቀል ማለት ሰብሎቹን አብሮ መንቀል ስለሚሆን ማረሙ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

ስትሪጋ ሄርናቲካ - የመተዳደሪያ መሠረት አፍራሽ

28

ስትሪጋ ብዙ ዝናባማ በሆነው በምዕራቡም ሆነ የበልግ ዝናብ አጠር በሆነው ምስራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል ባሉት ጥናቱ በተካሄደባቸው ቦታዎች የጋራ ችግር ነው፡፡ በፋዲስና በሚዳጋቶላ ያሉ አርሶአደሮች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ ይህ አረም የጀመረው በምግብ እርዳታ ያገኙትን በቆሎ ከዘሩ በኋላ ነው፡፡ ለዚህ አባባል ተጨባጭ ማረጋገጫ ባይኖርም በደረቅ ወቅቶች ከሰብሎቹ ይልቅ ስትሪጋ ይለመልማል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም በምርታማነታቸው የተሻሉት የማሽላና የጤፍ ዝርያዎች በተለይ በስትሪጋ ይጠቃሉ (4.1.1.2 ን ይመልከቱ)፡፡

ሌላው ከበሽታ ጋር የተያያዘ ችግር በበረዶ ማዕበል የሚከሰተውና እንደ አርሶአደሮቹ አገላለፅ በአዝመራው ዓመት አጉል ወቅት ላይ የሚከሰተው የእንሰት በሽታ ነው፡፡ ይህ አደገኛ በሽታ በተለይ በኦሮሚያ ደጋማ አካባቢዎች ዋና ምግብ የሆነውን ዓመቱን ሙሉ የምግብ ዋስትና ከመስጠቱ የተነሳ ማህበረሰቡ እንደ ህይወት አድን የሚቆጥረውን እንሰትን የሚያጠቃ ነው፡፡

ዕፅዋቱ “አጠውልግ” (ባክቴሪያል ዊልት) በተባለ ባክቴሪያ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡ ባክቴሪያው የጥፋት ስራውን ለመፈፀም በእንሰቱ አካል ላይ የመግቢያ ያህል የምትሆነው ቁስል ይፈልጋል፡፡ ባክቴሪያው ድሮም የነበረና ለእፅዋቱም አስፈሪ ነበር፡፡ አሁን ግን አደጋው ከመቼውም ጊዜ በገዘፈ መልክ አፍጥጦ መጥቷል፡፡ በአየር ንብረት ለውጡ ምክንያት በተደጋጋሚ በሚከሰተው በረዶ የእንሰቱ ግንድ ስለሚበሳሳ ለባክቴሪያው ምቹ ሁኔታ ይፈጠርለታል፡፡

የእንሰት እርሻ እንሰት አጠውልግ ባክቴሪያ (እንሰት ባክቴሪያል ዊልት)

በኦሮሚያ ደጋማ አካባቢዎች ከሚገኘውና ጥናቱ ከተካሄደባቸው ቦታዎች አንዱ በሆነው በቀርሳ ማሊማ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የተትረፈረፈ የእንሰት ምርት ነበር፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ይህ ምርት እንደ እሴት ሰንሰለትና የልማት መሠረት ይቆጠር

29

ነበር፡፡ በመሆኑም ይህንኑ የበለጠ ለማጎልበት የእሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት ተቀርጾ የመጀመሪያ እርምጃዎችም ተወስደዋል ሕንፃም ተሰርቷል፡፡ በኋላ ግን በእንሰት ተክል ላይ መቁሰልን በሚያስከትለው በረዶ በታጀበው የአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ ትርፍ ማምረት እንዳልተቻለ ተደረሰበት፡፡ ከዚህ የተነሳም የእሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጄክቱ መቋረጡ የግድ ሆነ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው አርሶአደሮችና ቤተሰቦቻቸውም የባሰ የምግብ ዋስትና ማጣት ችግር እንደደረሰባቸው ይናገራሉ፡፡ “ህይወት አድን” በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ቀድሞ የነበረውን ተግባሩን እውን ማድረግ አልቻለም?

4.1.2 የእንሰሳት እርባታ

“በሬ ማለት እንደ መኪና ነው! እሱን መሸጥ የመጨረሻው አማራጭ ነው!”

ኢትዮጵያ በእንሰሳት ሀብት ብዛት በአፍሪካ ቀዳሚውን ቦታ ትይዛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በተደረገው የእንሰሳት ቆጠራ ኢትዮጵያ ከ28 ሚሊዮን የሚበልጡ የቀንድ ከብቶችን፣ 30 ሚሊዮን ትናንሽ አመንዣኪዎችን፣ ወደ 1 ሚሊዮን አካባቢ ግመሎችን፣ 4.5 ሚሊዮን የጋማ እንሰሳትን እና 32 ሚሊዮን ዶሮዎችን አስመዝግባለች (FAO/WFP Crop & Food Security Assessment Mission to Ethiopia, 2008)፡፡ የእንሰሳት ባለቤትነት 80 ከመቶ ለሚደርሰው የገጠሩ ማህበረሰብ መተዳደሪያ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው፡፡ ብዙ የቀንድ ከብት ቁጥር በአካባቢው ሁኔታ ላይ ጥፋት ስለሚያደርስ ከላይ የተገለፁት ቁጥሮች ያለጥርጥር እጅግ በጣም የበዛ ነው፡፡ ከልክ ያለፈ ግጦሽ የአፈር መከላትና መሸርሸርን ያስከትላል፡፡ ይህም ሁኔታ የሀገሪቱን አካባቢያዊ ሁኔታንና መተዳደሪያ ተጋላጭነትን ያፋጥናል፡፡ ማህበረሰቡ ግን ከብቶቹን ይፈልጋቸዋል እናም ከላይ በጥቅሱ እንደተመለከተው ብዙ የከፊል-አርብቶአደሮችና በደጋ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች ኑሮ የተመሰረተው በእንሰሳት ምርትና ምርታማነት ላይ ነው፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ መሠረታውያን መስመር ላይ እንሰሳትም ለአደጋ ተጋልጠዋል - የምርት ዝቅተኝነት፣ ለበሽታ ተጋላጭነት እና በጣም ለከፋ በአጭሩ የመቀጨት (የልጅነት ሞት) አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ከታች የቀረበው ክርክር አዳዲስ ተጋላጭነትንና የኑሮ ዋስትና ማጣት ቀስቃሽ የሆኑትን የእነዚህን ለውጦች መንስኤ ተያያዥነት ያሳያል፡፡

4.1.2.1 ዝቅተኛ የእንሰሳት ምርታማነት በመጀመሪያ ደረጃ የእንሰሳት ምርታማነት የሚወሰነው እንሰሳቱ በሚመገቧቸውና ሊያገኟቸው በሚችሏቸው የመኖ ጥራትና ብዛት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አብዛኛው እንስሳ

30

በግጦሽ የሚኖር ነው፡፡ ሌላው ተፈላጊ መኖም የሚመረተው በየማሳው ላይ ሲሆን ገለባ፣ ድርቆሽ፣ ጥራጥሬ ወይም ሌላ የመኖ ሳርና ቁጥቋጦዎችን የሚያካትት ነው፡፡

እያነሰ እንዲያውም እየጠፋ ከመጣው ዝናብ አንጻር እነዚህ የመኖ ምንጮችም እያሽቆለቆሉ ነው፡፡ የግጦች ቦታዎች በእንሰሳት ከመጨናነቃቸውም ባሻገር ከእርጥበት ማነስ የተነሳ ምርታማነታቸውም ቀንሷል፡፡ ከእርሻ ምርት በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆል ጋር ተያይዞ እንደሌላው የመኖ ሳርና ጥራጥሬ ሁሉ የገለባ መጠንም አሽቆልቁሏል፡፡

የድርቅ ወቅት እጅግ ሲረዝም አርሶአደሮቹ ከተለመደው መኖ ወጥተው ተጨማሪ ምግቦችን በአቅራቢያው ከሚገኙ ገበያዎች መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ለወተት ምርት የሚጠቅሙት ድቅል የቀንድ ከብቶች በተለይ ከፍተኛ ንጥረ ነገር ያላቸውን እንደ ፋጉሎ፣ ፍሩሽካ ወይም ሞላሰስ ያሉ ተጨማሪ መኖዎችን ከገለባ ጋር ተቀላቅለው እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፡፡ በተወሰነ ደረጃ ገበሬዎቹ ራሳቸው ከየወረዳው የግብርና ባለሙያዎችና ከልማት ጣቢያ ሰራተኞች በሚያገኙት እገዛ ሻል ያሉ የመኖ ዓይነቶችን ያመርታሉ፡፡ ሆኖም በዚህ ረገድ ካለው ድጋፍ ማነስ የተነሳ አብዛኛው አርሶአደር እነዚህን የመኖ አይነቶች የሚገዛና ከአብዛኛው ቤተሰብ የመግዛት አቅም ጋር የሚመጣጠን አይሆንም፡፡ እንዲሁም ገበሬዎቹ እንደቀድሞው ሳር አጭደው በመውሰድ ከብቶቻቸውን መመገብ አይችሉም፤ ምክንያቱም በፊት ያጭዱባቸው የነበሩት ተዳፋት አካባቢዎች አሁን ከሰውና እንሰሳት ንክኪ ተከልለዋልና፡፡

እንደ አማራጭ በተለይ በስምጥ ሸለቆና ተያያዥ አካባቢዎች ያሉ ገበሬዎች ቁልቋልን በመጥበስ ከብቶቻቸውን ይመግባሉ፡፡ የመጥበሱ ሂደት እሾኩን ከማስወገድ አንፃር አስፈላጊ ነው፤ አለበለዚያ ከብቶቹም ሊመግቡት አይችሉም፡፡ ገበሬዎቹ ይህን ስራ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ይገልፁታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ገበሬዎቹ ቁልቋሉን ቀኑን ሙሉ ሲሰበስቡ ውለው ማታ ወይንም ሌሊቱን መጥበስ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ቁልቋሉ እንደተቆረጠ በቶሎ መጠበስ ይኖርበታል፡፡ ከድካሙ ጋር ሲነፃፀር ጥቅሙ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ የከብቶቹም ህልውና የመነመነ ነው፡፡ አንድ ጊዜ ለመጥበስ የሚያስፈልገው ማገዶ በጣም ብዙ ስለሆነ ከዘላቂ የመሬት አስተዳደር አንፃር ድርጊቱ ጎጂ ነው፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት በርካታ ወረዳዎች በተለይ በስምጥ ሸለቶ አካባቢ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ከተከሰተው አስቸጋሪ የእንሰሳት ሁኔታ በመነሳት ገበሬዎች ከተጎዱ ወረዳዎች ወደ አጎራባች አካባቢዎች እንዲዘዋወሩ የሚፈቅድላቸው እና ለከብቶቻቸውም መኖና ውሃ የሚያስገኝላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይህም ብዙ ገበሬዎች የቤተሰብ አባሎቻቸውን እንስሳቱን እንዲንከባከቡ ከመኖሪያቸው ወደራቀ ቦታ እንዲልኩ ያስገድዳል፡፡ ማህበረሰቡ ግን ይህን የአርብቶአደር መሰል ህይወት አልለመደውም፡፡

31

ይህ በተራው የቤተሰብ ትስስር መረበሽንና በእርሻ ስራው ላይ የሰው ኃይል እጥረትን ያስከትላል፡፡ በአብዛኛው ገበሬዎቹ ከእንሰሳቱ ጋር የሚልኩት ልጆቻቸውን ነው ይህ ሁኔታ ደግሞ የመደበኛውን ትምህርት ሂደት ያደናቅፋል፡፡

ለእንሰሳት ምርታማነት መቀነስ ሌላው ምክንያት የሙቀት መጨመር ነው፡፡ በስምጥ ሸለቆ የሚገኙ አህዮችና የቀንድ ከብቶች እንዲሁም በቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ በጎች ከሙቀቱ የተነሳ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ለበሽታና ለሞት እጅግ የተጋለጡ ናቸው፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ አባባል በተለይ የኛንጋቶም በጎች ፀሐይ ላይ መውጣት አይፈልጉም፡፡ ወደ ፀሐይ ወጥተው ሳር ከሚፈልጉ ይልቅ በጥላዎች ስር መቆየትና ማረፍን ይመርጣሉ፡፡ በጎች ከፍየሎች በተለየ ሁኔታ የሚመገቡት ሣር ስለሆነ በጥላማ አካባቢ ምግባቸውን ሊያገኙ አይችሉም፡፡ የባሰ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው በረሃብ እስከመሞትም ይደርሳሉ፡፡

4.1.2.2. የእንሰሳት በሽታዎች ከዝናብ መዘግየት፣ ከበረዶ ማዕበልና ከውርጭ / አመዳይ ክስተቶች እንዲሁም ከልክ ያለፈ ግጦሽና ከአፈር መከላት ጋር ተየይዞ የእንሰሳት ምርት ተዳክሟል፡፡

“ከብቶቻችንን የምንመግባቸው ገለባ ነው፤ ሆዳቸውን ከመሙላት ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ጠቃሚ ንጥረ ነገር የለውም፡፡ ሌላ የምንመግባቸው ነገር የለም፡፡ እንዲያውም በጎች አፈርና የባህር ዛፍ ቅጠል መመገብ ጀምረዋል፡፡”

የኛንጋቶም አካባቢ በጎች

32

በተለይ በደጋና በወይና ደጋ አካባቢ ከመኖ አለመኖርና በተያያዥነት ከእንሰሳቱ መዳከም ጋር ተዳምሮ እንሰሳት ለበሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጋልጠዋል፡፡ ለዚህ አንዱ አብነት በበጎች ላይ የተከሰተው “ጥቁር እግር” ወይም “ጥምብስ” የተባለው ባክቴሪያ ወለድ በሽታ ነው፡፡ ከልምድ እንዳየነው ከገበሬዎች አንዳቸውም የዚህን በሽታ የህክምና ዳራ አያውቁም፡፡ የእንሰሳቱን በፍጥነት መበስበስ ብቻ ይመለከታሉ፡፡ የበጎቹን ቆዳ አይናቸው አካባቢ በቢላዋ በመብጣት ሊያክሟቸው ይሞክራሉ፡፡ ሆኖም ድርጊቱ አብዛኛውን ጊዜ የእንስሳቱን ሞት ያፋጥነዋል፡፡

መንስኤያዊ ጥናት 3፡- ለዚህ ዓይነቱ ምሳሌ ግልፅ ማብራሪያ ይሆን ዘንድ ገፅ 72 ላይ የተሰጠውን የደጋዳሞት /ፈረስ ቤት አካባቢ የሆነውን የበግ አርቢዎች ታሪክ ይመልከቱ፡፡

አሁን አሁን የተለመደውና በጣም አጥፊ የሆነው ሌላው በሽታ “ዋጅማ” ነው፡፡ “ዝናብ በዘገየባቸው ዓመታት ዋጅማ በየውሃው ዳር እየበዛ መጣ፡፡ ሌሎቹ የሳር ዝርያዎች እንደ ቀድሞው ፈጥነው የማደግ ኃይል የላቸውም፡፡ እንደዚያ ባሉት ዓመታት ዋጅማ በጣም ይበዛል፤ ስለዚህ ብዙ የቀንድ ከብቶች ይሞታሉ፡፡”

ድሮ ዋጅማ የመኖ ሣር ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ አርሶ አደሮቹ ለዚህ ክስተት ማብራሪያ ባይኖራቸውም አሁን አሁን ዋጅማ ወደ መርዛማነት የተቀየረ ይመስላል፡፡ ብዙ ጊዜ እንሰሳት የበሉት ምግብ ሲፈጭ ያስገሳቸዋል፡፡ ዋጅማ ከቀንድ ከብቱ ጨጓራ ውስጥ አረፋ በመፍጠር እንዳያገሱ ይከለክላቸዋል፤ ከዚህ የተነሳ ጨጓራቸው በአየር ስለሚሞላ ይነፋል፡፡ ማህበረሰቡ እውቀቱ ስለሌለው ባልተቀቀሉና ትክክለኛ ባልሆኑ መሣሪያዎች እንስሳቱን በባህላዊ ዘዴዎች በመብጣት እንስሳውን ለሞት በሚዳርገው ነገር ሊያክሟቸው ይሞክራሉ፡፡ የእንስሳት ሐኪሞች በስፍራው አይታዩም፤ በቀላሉ የሚገኙም አይደሉም፡፡

ክርር ባለው ደርቅ እንኳ ሳይቀር ዋጅማ ሲለመልምና ከሌላው ሳር በተሻለ ሁኔታ ሲያድግ የአየር ንብረት ለውጥ በተራዘመ ድርቅ አማካይነት በዋጅማ ምክንያት ለሚከሰተው ሞት ቁጥር መጨመር እንደመንስኤ ይቆጠራል፡፡

ዋጅማን ማከም

33

አልቅቶች በኩሬ ጭቃ ውስጥ

ሌላው የእንሰሳት በተለይም የቀንድ ከብቶች በሽታ የሚከሰተው ከወንዞች በሚፈጠሩ አነስተኛ ውሃ የያዙ ኩሬዎች አማካኝነት ነው፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ የቀንድ ከብቶቹና ሌሎች እንሰሳት ውሃ የሚጠጡት ከነዚህ ኩሬዎች ነው፡፡ በወቅቱ እነዚህ ኩሬዎች በውሃ የሚሞሉት በትክክለኛው ወቅት በሚዘንበው የዝናብ ውሃ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ጥገኛ ትላትሎቹ እንዲጠራረጉ ያደርግ ነበር፡፡ አሁን ግን ዝናቡ በቂ ስላልሆነ ኩሬዎቹ ብዙ ጊዜ በውሃ ጢም ብለው አይሞሉም፡፡

ስለዚህ ተባዮቹ በኩሬው ይቆያሉ፤ በብዛትም ይራባሉ፡፡ አንድ ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው በተለይ የቀንድ ከብቶችን የሚያጠቃው አልቂት ነው፡፡ ጥገኛ ተባዩ የከብቶቹን እግር ያጠቃል፤ ከብቶቹም በምላሳቸው በመታገዝ ከእግራቸው ላይ ለማላቀቅ ሲሞክሩ ምላሳቸው ላይ ይጣበቃል፡፡ የከብቶቹ ባለቤት ቶሎ ደርሶ ካላስወገደው ለሞት ሊያበቃቸውም ይችላል፡፡

ተጋላጭነት /ተጠቂነት

የደጋማ አካባቢዎች መተዳደሪያ ሁኔታዎች

• የተጎዳ የመተዳደሪያ ሁኔታ (ከፍታ)

• በከብት ርባታ ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት

• የህዝብ ብዛት ጫና • በከብት መንጋ መጨናነቅ• የአፈር ጨዋማነት

ጥቅል ተጋላጭነት / ተጠቂነት

• የዝናብ መዘግየትና መቀነስ• የዝናብ አመጣጥ ሁኔታ የማይተነበይ/የማይጠበቅ መሆኑ

• ፅንፍ የያዙ ሁኔታዎች /የጎርፍ /ዶፍ/ ዝናብ /በረዶ/ ውርጭ/ሙቀት

የመቋቋም ብቃት

ለእውነተኛ መቋቋም ያለ የመነመነ እድል የመተዳደሪያ ዋስትና እጦት መጨመር

በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የደረሰባት የደጋማ አካባቢዎች መተዳደሪያ ሁኔታ

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች

34

ከላይ እንደተገለፀው በእንሰሳት እርባታና በእርሻ መካከል ጠንካራ ትስስርና መደጋገፍ አለ፡፡ ይህንን በሚከተለው ምሣሌ አስረጅነት ማሳየት ይቻላል፡- ገበሬዎች ከብቶቻቸውን በተለይ የቀንድ ከብቶቻቸውን ካጡ የሚኖረው የፍግ እጥረት ብቻ ሳይሆን ለማሽላ እና ለጤፍ ማሳ ማዘጋጃ የሚረዱ በሬዎችም ችግር ይገጥማል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች የአጠቃላይ ዋስትና ማጣትና በመጨረሻም የምግብ ዋስትና ማጣት አደጋ ይጋረጥባቸዋል፡፡

ከላይ እንደተገለፀው በእንሰሳት እርባታና በእርሻ መካከል ጠንካራ ትስስርና መደጋገፍ አለ፡፡ ይህንን በሚከተለው ምሣሌ አስረጅነት ማሳየት ይቻላል፡- ገበሬዎች ከብቶቻቸውን በተለይ የቀንድ ከብቶቻቸውን ካጡ የሚኖረው የፍግ እጥረት ብቻ ሳይሆን ለማሽላ እና ለጤፍ ማሳ ማዘጋጃ የሚረዱ በሬዎችም ችግር ይገጥማል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች የአጠቃላይ ዋስትና ማጣትና በመጨረሻም የምግብ ዋስትና ማጣት አደጋ ይጋረጥባቸዋል፡፡ 5. 5. “መቋቋም (Coping)” ወይስ “የመላመድ ዘዴ (Adaptation)” የመተዳደሪያን የማገገም ብቃት መታደግ

የጥናት ሪፖርቱ “ተስማምቶ የመኖር ትርጉም - ከወቅታዊው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ጋር የተያያዙ አሻሚ አስተሳሰቦችና የቃላት አጠቃቀሞች” የሚል ንዑስ ርዕስ ተሰጥቶታል፡፡ ርዕሰ ጉዳያችን የሆኑትና ከመተዳደሪያ አንፃር ያየናቸው ሰዎች ተጠቂዎች እና ለረጅም ጊዜ ለውጫዊ ጫናዎች እና ለአስቸጋሪ ኃይላትና ሂደቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ ተጨማሪ የመተዳደሪያ ዋስትና እና ማገገሚያ ለማግኘት የሚታገሉ ናቸው፡፡ አስቸጋሪ ኃይላትንና ጫናዎችን መጋፈጥ እንዲሁም አሉታዊ ሁኔታዎችንና አደጋዎችን ማሸነፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ መቋቋም የለመዱት ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ በጊዜ ሂደት በተለመደው ለውጥን የመቋቋም ችሎታና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሚፈጠሩ ወቅታዊ ጫናዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

የማገገም ብቃት /ሬዚሊየንስ/ የሚለው ኃሳብ “የማህበራዊና ሥነ-ምህዳራዊ ስርዓቱ በራስ አደረጃጀትና ትምህርት አማካኝነት የሚገኝ የተስማምቶ መኖር ብቃት” ተብሎ ከተበየነ

35

የማገገም እርምጃ ወደ ተስማምቶ መኖር ይሸጋገራል ማለት ነው፡፡ ይህም ራስን እንደገና የማደራጀትና የማደስ ብቃት እንዲሁም ለራስ አደረጃጀትና ትምህርት የሚሆን እምቅ ችሎታ ማለት ነው፡፡ (በርኬስ ፣ ኮልዲንግ እና ፎኬ 2003-14)፡፡

በዚህ አኳያ ትኩረት የተሰጠው በማህበራዊ ተዋናዮቹ፣ ለፈጠራ ችሎታቸውና ለቅድመ ምላሽ እቅዳቸው ነው፡፡ አድጉር (2006 - 253) የማገገም ብቃት /ሬዚሊየንስ/ የሚለውን ፅንሰ ኃሳብ ”አዳዲስ ነገሮችን ለመስራት፣ ለፈጠራና ለልማት ለሚሆኑ መልካም አጋጣሚዎችን የመፍጠር እምቅ ችሎታ” ብሎ ይተረጉመዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የመላመድ ዘዴ እና መቋቋም አንድ ስርዓት ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ በሚሰጡ ብያኔዎችና ገለፃዎች ውስጥ “ተላምዶ መኖር የሚቻለው የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ውጤቶችን መጋፈጥ በመቻልና አሉታዊ ተፅዕኖዎቻቸውን ተቋቁሞ በመኖር ነው” የሚል አገላለፅን ልናገኝ እንችላለን (GTZ 2009 ፡ 9) ፤ ይህ አገላለጽ ግን ፍፁም ትክክል አይደለም፡፡

ከላይ ካየነው የአበያየን መቀላቀል በተቃራኒ ይህ ጥናት የሁለቱን እይታዎች ልዩነት እንደሚከተለው ያስቀምጣል፡፡

መቋቋም

ማህበረሰቡ ለመጣበት አንድ ዓይነት ጫና የሚሰጠውን ምላሽ ያመለክታል፡፡ በአጠቃላይ በልምድና በቀድሞ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ዘዴ እንጂ የማህበራዊ ሳይንስ ንግግርና ትንታኔ ውጤት አይደለም፡፡

የመላመድ ዘዴ

በተቃራኒው አንዳንድ ለውጦች (ለምሳሌ የአየር ንብረት ለውጥ) በደንብ በታወቁና በማህበራዊ ሂደት በተማርናቸው ብልሀቶች ምላሽ ሊያገኙ እንደማይችሉ እውቅና መስጠትን ይጠይቃል፡፡ ችግሮችና ጫናዎች ቅድመ መከላከያ ተቋም፣ አዳዲስ መፍትሄዎች እና ያልተሞከሩ ማለትም ከታች እንደሚቀርበው ሰፋ ያለ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎን የሚያካትቱ ስልቶችን ይጠይቃሉ (DFID 2010) ፡፡

ይህ በቃላት አጠቃቀም ላይ የተሰጠው ማብራሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ መሬት ወርደን ማህበረሰቡ ለመተዳደሪያ ዋስትናው የሚያደርገውን ትግል ስንመለከት ለደረሰ ችግር ምላሽ በመስጠትና ችግርን ቀድሞ ተንብዮ በመከላከል መካከል ይህን ያህል የጎላ ልዩነት የለም፡፡ ማህበረሰቦች ሁልጊዜ በጊዜ ሂደት ያዳበሯቸውንና በውል የሚታወቁ ችግር የመቋቋም ስልቶችን ይሞክራሉ ይፈትሻሉ፡፡ የአየር ንብረት ለውጡን መሠረታዊነት ከተገነዘቡ ግን አዳዲስ መፍትሄዎችን ይፈልጋሉ፡፡

36

5.1 የአየር ንብረት ለውጥ - የተደላደለን ተስማምቶ የመኖር ዘዴ የሚሸረሽር ኃይል

“እርከን መስራት ባህላችን ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ ስንሰራው ኖረናል፡፡ የድሮ እርከኖች ከአሁኖቹ ጋር ሲወዳደሩ በጣም ጠንካራ ነበሩ፡፡ ድሮ ተደጋጋሚ ድርቅ አልነበረም፡፡ ዛሬ ሰው ደክሟል፤ ለእርከን ሥራ የሚሆኑ ድንጋዮችን ወደ ማሳዎች ተሸክሞ ለመምጣት አይችልም፡፡ የድሮ እርከኖች የተሻሉ ነበሩ፡፡”

የመላመድ ዘዴን ጥያቄ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለማሸነፍ አስቀድሞ ከመከላከል ሥልቶችና ከውክልና አንፃር ለመመለስ ከመሞከራችን በፊት በመላመድ ዘዴ እና በአየር ንብረት ለውጥ መሠረታውያን መካከል ባለው ቁርኝት ላይ የተወሰነ ነገር እንበል፡፡ ትኩረታችን ፍፁምና በደንብ የተስተካከለ በነበረው ነገር ግን ከአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ የማይጠቅምና ዘመኑ ያለፈበትን አስቸጋሪ የአካባቢ ሁኔታን የመላመድ ብቃት ላይ ይሁን፡- ለአብነትም የኮንሶ ማህበረሰብን የእርከን ስራ እንውሰድ፡፡

በኢትዮጵያ የኮንሶ ማህበረሰብ ከአስቸጋሪ የአካባቢ ሁኔታ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ተላምዶ በመኖር ይታወቃል፡፡ ኮንሶዎች ከአርባ ምንጭ 80 ኪ.ሜ በስተደቡብ በሚገኘው አስቸጋሪ ተራራማ አካባቢ ኑሮአቸውን እንዲገፉ ስለተገደዱ ከእርሻ ስራቸው ትሩፋት የሚያስገኝላቸውን የእርከን ሥራ ስርዓት አዳብረዋል፡፡ ነገር ግን አሠራሩ በጣም አድካሚ እና በማህበረሰቡ ትብብር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም የማህበረሰቡ አባል የእርከን ሥራውን ትኩረት ሰጥቶ የሚሳተፍበት ተግባር ነው፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተጠቁት በተለይ የበልግ ዝናብ በተቋረጠባቸው ወይንም ባነሰባቸው በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ነዋሪዎች አሁን አሁን ለሁለትዮሽ ጥቅምና ለትብብር ያደርጉት የነበረውን ተባብሮ መስራት ቸል እያሉት ነው፡፡ በየማሳው በቀላሉ እንደሚታየው የዝናቡን መጠንም ይሁን ጊዜ መተንበይ የማይቻል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እርከኖችን መገንባትም ሆነ መጠገን አዋጪነት ያለው መስሎ ስለማይታይ ማህበረሰቡ ከዚህ ዓይነቱ ስራ የራቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ሌላኛው መገለጫ በሆነው አልፎ አልፎ በሚከሰተው ከባድ ጎርፍ በሚያስከትል ዝናብ መንስኤነት እርከኖች ተጠራርገው በአጭር ጊዜ ውስጥ ድራሻቸው ጠፍቷል፡፡

የፈራረሱ የኮንሶ እርከኖች

37

5.2 ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ተላምዶ የመኖር ዘዴ

በአጠቃላይ በጥናቱ ሂደት ካጋጠሙና ከታዩት ሁነቶች እንዲሁም ከተሰበሰቡት መረጃዎች ትንተና በመነሳት የአየር ንብረት ለውጥ ካለው የተጋላጭነት እውነታ ጋር ተዳምሮ አርሶአደሮችን ለምግብ ዋስትና ማጣት እንደዳረጋቸው ያለጥርጥር መናገር ይቻላል፡፡ በበርካታ ቦታዎች በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ መብላት ተጀምሯል፡፡ ይህም ማለት ሰዉ ምግብ የሚበላው ከቀኑ በአምስት እና አስራ አንድ ሰዓት ላይ ነው ማለት ነው፡፡ ዓላማውም የቁርስ ወጪን ከዝርዝሩ በማውጣት በቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ብቻ ይመገባል ማለት ነው፡፡

ይህ ጥናት ከተካሄደባቸው ቦታዎች በኢኮኖሚያዊ አቅሙ የተሻለ በሆነው በአለፋ አካባቢ እስካሁን ባለው ሁኔታ የአካባቢው ገበሬዎች ሊገነዘቡት በሚችሉት ደረጃ በስልተ ምርቱ ላይ ጫና አልተፈጠረም፡፡ ይህ ሁኔታ ግን የምስራች ተደርጎ ዘና የሚያሰኝ አይደለም፡፡ በአለፋም ቢሆን ምርት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ ቀድሞ ይደረግ እንደነበረው ምንም አይነት ትርፍ ምርት ከአለፋ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች አይጓጓዝም፡፡ በአለፋ ምርት መቀነስ ማለት በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ያለውን የረኃብ ሁኔታ መባባስ የሚያሳይ ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ብዙ ገፅታዎች ያሉት ብቻ ሳይሆን በርካታ ቁርኝቶችና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ሰፋ ያሉ ተፅዕኖዎች አሉት፡፡

በቅርቡ የምግብ ዋስትና የነበራቸው አካባቢዎች አሁን የምግብ ዋስትና ከማጣት ጋር እየተፋለሙና ያገኙትን አማራጭ ለመጠቀም እንደ ሴፍቲኔት ያሉ ፕሮግራሞችን እየሞከሩ ነው፡፡ የሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ግን የአርሶአደሮቹን የመቋቋሚያ ብልሀቶች በአሉታዊ መልኩ እየቀየራቸው ነው፡፡ የምግብና ገንዘብ ለስራ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ለአርሶአደሮቹ ተጨማሪ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ህዝቡ ግን የተቀበለውን ስንዴ ወደ ገበያ በማውጣት ይሸጥና በሚያገኘው ገንዘብ እጥፍ ማሽላ ይገዛበታል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን ገንዘቡ እንሰሳት ለመግዛት የተበደሩትን ዕዳ ለመክፈልም ይውላል፡፡ በአጠቃላይ ይህ የሚያሳየን የሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዳልሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም የእንሰሳት ምርታማነት ወደ ዜሮ የተጠጋና እንሰሳት መግዛትም ምርታማ ባለመሆኑ ነው፡፡

ይህ ምሳሌ የሚያሳየው አርሶአደሮች በሴፍቲኔት ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ነው፡፡ በሴፍቲኔት ፕሮግራም ከመታቀፍ ጋር ያሉት ችግሮች ግልፅ ቢሆኑም አርሶአደሮች ይህኛውን አማራጭ የተሻለ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ከዚያም በላይ የረጅም ጊዜ መፍትሄ አድርገውም ያዩታል፡፡ ይሁን እንጂ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ከመነሻው የታሰበው ለድርቅ ጊዜ የሚያገለግል የአጭር ጊዜ መፍትሄ እንዲሆን ነበር፡፡ አርሶአደሮቹም ይህንን ተቃርኖ ይገነዘቡታል፡፡ በተለይ ድሀ አርሶአደሮች ያለ ሴፍቲኔት መኖር እንደማይችሉ

38

ይናገራሉ፡፡ ይህን መሰሉ አረዳድ በማህበረሰቡ ውስጥ እንዳለ ሆኖ የሴፍቲኔት መርሀግብሩ የአርሶአደሮቹን የአዝመራ ወቅት ያገናዘበ አይደለም፡፡ እናም በሴፍቲኔት ፕሮግራም የሚሳተፉ አርሶአደሮች የሴፍቲኔት ስራዎች ከማሳ ዝግጅት እያዘገዩያቸው እንደሆነ በምሬት ይናገራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሴፍቲኔት የስራ መርሃግብር ከተሳታፊ አርሶአደሮች የግብርና ስራ ጋር ተቀናጅቶ የተዘጋጀ ባለመሆኑ በወረዳው ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡

የገጠማቸውን ጥቅል የግብርና ምርታማነት መውረድ ለመቋቋም አርሶአደሮች ዋና ስልት አድርገው የቀየሱት የራሳቸውን መሬት ወደ መስኖ እርሻነት መቀየር ወይንም ከሌሎች አርሶአደሮች ላይ የመስኖ አገልግሎት የሚያገኙ ማሳዎችን መከራየት ነው፡፡ ግቡ ለራሳቸው እንደ ጤፍና ማሽላ ያሉ ከእጅ ወዳፍ የሆነ ቀለብ ከማምረት አልፈው ገበያ ተኮር የሆኑ እንደ ሽንኩርት እና ሌሎች የሚሸጡ ምርቶችን ማምረት ነው፡፡ ይሁንና በመሬት ጥበቱ ምክንያትነትና በመስኖ መሬት አቅርቦቱ እጅግ አናሳ መሆን የተነሳ ካለፉት ዓመታት ወዲህ የመስኖ መሬት የኪራይ ዋጋ እያሻቀበ ይገኛል፡፡ ስኬታማ ሽንኩርት ማምረት መሬት ለመከራየት እና ማዳበሪያ እንዲሁም ተባይ ማጥፊያ መግዛት ለሚችሉ ኃብታም አርሶአደሮች የተተወ አማራጭ ይመስላል፡፡ ድሀ አምራቾች በዚህ ውድድር ውስጥ ይታገላሉ፤ በኋላም በሽንኩርት አምራችነት መቀጠል ወደማይችሉበት ደረጃ ይደርሳሉ፡፡ ስለዚህ ለድሀ አርሶአደሮች አማራጭ የሚሆኑ ሌሎች የገቢ ማግኛ ዘዴዎችን ማፈላለግ የግድ ይሆናል፡፡

“ላለንበት ሁኔታ አማራጭ የሚሆነው ከሸለቆው መስኖ መሳብ ነበር፡፡ መስኖ ብናገኝና እቃ ቢኖረን ማትረፍ እንችል ነበር፡፡ ውሃው አንዳንዴ ይኖራል፤ የሚያቁረው/የሚገድበው ምንም ነገር ስለሌለ ግን ይደርቃል፡፡ እንግዲህ አሁንም ዝናብ የማይኖር ከሆነ የሚኖረን ሌላው አማራጭ መሰደድ ወይንም እዚሁ መሞት ነው፡፡ ምንም አቅም ወይም መሳሪያ የለንም፤ በሸለቆው ውስጥ ያለው መሬትም ቢሆን ለሁሉም ማህበረሰብ የሚበቃ አይደለም፡፡ ከመንግስት ጋር የአላህንና የልዩ ልዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እርዳታ እንፈልጋለን፡፡”

“ማሽላና በቆሎ ከማምረት እንደ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎች ፍራፍሬዎችን ወደ ማምረት ለመለወጥ አቅጃለሁ፡፡ እነዚህ ትላልቅና በዚህ የአየር ንብረት በጥሩ ሁኔታ የሚለሙ ናቸው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ለዛፎች በቂ ውሃ መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብኛል፡፡”

5.3 በማህበረሰባዊ ሽግግር ወቅት የሚያስፈልግ የመላመድ ዘዴ

“ድሮ ሰው እርስ በርስ ይዋደድ ነበር፤ ያለንን እንካፈል ነበር፡፡ አሁን ከምግብ ማነስ የተነሳ ፍቅር ቀንሷል፡፡ ለአዛውንቶች የነበረው ክብር ሳይቀር እየቀነሰ ነው፡፡”

39

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የመላመድ ዘዴ ማለት አዳዲስ የግብርናና የአመራረት ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ ማለት ብቻ አይደለም፡፡ እንዲያውም ወደፊት የመላመድ ዘዴ ማለት ራስን ከአዲስ፣ ከግለኝነት የአኗኗር ዘይቤ ጋር ማስለመድ እንዲሁም ከአዲስና ካልተለመደ ህብረተሰባዊ ዳራ ራስን ማላመድ ማለት ይሆናል፡፡

በሁሉም ጥናቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡ እየቀነሰ ስለመጣው ማህበራዊ ትስስር፣ ኃላፊነትና መተሳሰብ በአንድ ቃል ያማርራል፡፡ ብዙ ጊዜ ምሬታቸውን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈጠረውን የምርት ብሎም ለየማህበራዊ ሁነቶቹ ምግብ ማቅረብ አለመቻላቸው በምክንያትነት ያቀርቡታል፡፡ የማህበረሰቡ አባላት ቀደም ሲል ይደረጉ የነበሩ አንዳንድ ማህበራዊ ጉዳዮችን ለማከናወን በቂ ገንዘብ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰርግና ልደት ዝግጅቶች ላይ እንኳን መሳተፍ አይችሉም ምክንያቱም ለአዘጋጁ ይዘው የሚሄዱት ምንም ነገር ስለማይኖራቸው ነው፡፡ ራሳቸውም ቢሆኑ ልዩ ዝግጅቶችን ከማድረግ ይቆጠባሉ፤ ምክንያቱ ደግሞ ለእንግዶቻቸው በቂና ጥሩ ድግስ መደገስ ስለማይችሉ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የቆዩት የማህበራዊ ዋስትና ስርዓቶች እንደ ደቦና ጂጊ የመሳሰሉት የመደጋገፊያ ስርዓቶች ቦታቸውን እየለቀቁ ነው፡፡ በቂ ምርት በሌለበት ቦታ የተሻሉት አርሶአደሮችም ቢሆኑ ለአጨዳ ማንንም አይቀጥሩም፡፡ ከዚህም የተነሳ የቀን ሰራተኞች በዓመት አንዴ ብቻ የሚገኝን ወሳኝ የስራ አጋጣሚ ያጣሉ ማለት ነው፡፡

ከዚህ አንፃር እጅግ ወሳኙ ነገር በጊዜ ሂደት እየተዳከሙ የመጡት እንደ ዕቁብ ያሉት ባህላዊ የባንክ ስርዓት እና ችግር ያጋጠመው እርዳታ የሚያገኝበት እንደ እርጥባን ያሉ በርካታ ባህላዊ ተቋማት ጉዳይ ነው፡፡

ጥቂት በሬዎች ብቻ ያሏቸው አርሶአደሮች ማሳዎቻቸውን በተገቢው ሁኔታ ማረስ ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ለምሳሌ የጤፍ ምርት ከዘር በፊት ጥሩ የማሳ ዝግጅትን ይፈልጋል፡፡ ማሳው የተሻለ ምርት እንዲሰጥ ከአራት እስከ ስድስት ጊዜ ድረስ መታረስን የግድ ይላል፡፡ በወቅቱ ካለው የእንሰሳት ቁጥር መመናመን ጋር ተያይዞ ደግሞ አርሶአደሮች ብቻቸውን ይህን ማድረግ አይችሉም፡፡

እንደ ልፍንቲ ወይም ሹኳር ያሉት ባህላዊ ተቋማት አስፈላጊነታቸው እየጨመረ ነው፤ ነገር ግን አደገኛ ጫና አለባቸው፡፡ ልፍንቲ የሚያገለግለው ገበሬው አንድ በሬ ብቻ ያለው ከሆነ ነው፡፡ በዚህ አይነቱ አሰራር ገበሬው ሌላ በሬ ከሌላ አርሶአደር ተውሶ አቀናጅቶ ያርሳል፡፡ በአርሶአደሮቹ መካከል የገንዘብ ክፍያ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም ገበሬው የሌላኛውን አርሶአደር መሬት ያርስለታል ወይንም ሁለቱም አርሶአደሮች አንድ አንድ በሬ

40

ያላቸው ከሆነ እነዚህኑ አቀናጅተው ተራ በተራ ያርሳሉ፡፡ አንድ አርሶአደር ጭራሽኑ በሬ የሌለው ከሆነ ሽኳር በሚባለው አሰራር በሬዎቹን ከሌላ አርሶአደር በመከራየት መሬቱን ያርሳል፡፡

አንዳንድ ጊዜ የገንዘብ ክፍያ አይጠይቅም፤ ለባለበሬዎቹ የቀን ስራ መስራትም እንደ ክፍያ ይቆጠራል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የተለመደው በሬዎቹን የፈለገው አርሶአደር የገንዘብ ክፍያ ይፈፅማል፡፡ የእንሰሳት ቁጥር እየተመናመነ በሄደበት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን ፍላጎት በጣም ስለጨመረ የሚጠየቀው ክፍያም ከፍ ብሏል፡፡ ስለዚህ ለብዙ አርሶአደሮች እነዚህን ባህላዊ ተቋማት ይዘው መቀጠልና መጠቀም ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ የእርሻ መሬታቸውን ለሀብታም አርሶአደሮች እያከራዩ መኖርን ይመርጣሉ፡፡

ሌላው በመሸርሸር ላይ ያለው ማህበራዊ ዋስትና ደግሞ ሥነ-ፆታን የሚመለከት ነው፡፡ ለምሳሌ ዛሬ ዛሬ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች በኛንጋቶም ማህበረሰብ ሴቶች መካከል በባህሉ ተጠብቆ የቆየው ግንኙነት አደጋ ተጋርጦበታል፡፡ እነዚህ ቁርኝቶች ብድር በመመላለስ ላይ የተመሠረቱ ግንኙነቶች ነበሩ፡፡ ሴቶች ወተትና እንደ ቅቤ እና እርጎ ያሉ የወተት ተዋፅኦዎችን እና ማሽላ በመለዋወጥ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ፡፡ አሁን ግን ወንዶቹ ከብቶቹን ይዘው ግጦሽ ወደሚገኝበት ተራራማ አካባቢ ስለሚሄዱና ሴቶች የእንሰሳትን ምርት ማግኘት ስለማይችሉ የተለመዱ የሴት ባልንጀርነታቸውን ይዘው መቀጠል አይችሉም፡፡ ከዚህ የተነሳ የባሎቻቸው ጥገኛ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥ ከደረሰው የምግብ ዋስትና ማጣት ጋር ተያይዞ ሴቶችና ህፃናት የበለጠ ተጋላጭ የሚሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በባህላቸው ህግጋት መሠረት ሴቶችና ልጆች እንደ በጎችና ፍየሎች ያሉ እንስሳትን በማሽላና በሌሎች የምግብ እህሎች እንዲለውጡ አይፈቀድላቸውም፡፡ ባሎቻቸው ከብቱን ይዘው ስለሚሄዱና በመለዋወጡ ሂደት ላይ የመደራደር ሚና ስለማይኖራቸው ሴቶች የመፍትሄ ተስፋ በሌለው ችጋር እየተጠበሱ ነው፡፡

5.4 ተላምዶ መኖር፡- መተዳደሪያዎችንና የተቋማትን ገፅታዎች መለወጥ

የአየር ንብረት ለውጥ ለዘመናት ፀንተው የኖሩትን ማህበራዊ ተቋማትና አሰራራቸውን እየተገዳደረ ነው፡፡ ህጎችና ደንቦች ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ አዳዲስ ስልጣናትና የአስተዳደር መዋቅሮች እንዲፈጠሩ የግድ ብሏል፡፡ የሚከተሉት ምሳሌዎች እነዚህን ህብረተሰባዊ ሽግግሮች ያሳያሉ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ለምሳሌ በኛንጋቶም እረኞች ተላምዶ የመኖር ምሳሌነት እንደተመለከተው ለተቋም ግንባታ ሂደት የውጭ ድጋፍን የግድ ይላል፡፡ በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ማህበረሰቡ ከአዳዲስ ተቋማዊ ማዕቀፎች ጋር በማስማማት ከማህበራዊው ሂደት ጋር የራሱን መውጫ ብልኃት ይቀይል፡፡

41

መንስኤያዊ ጥናት 6፡ ገፅ 86 ላይ ያለው ገለፃ “በረዶ ጠባቂ” ሰዎች አይተውት የማያውቁት የተፈጥሮ አደጋ ሲያንዣብብባቸው በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ከሁኔታው አንፃር አስተካክለው በራሳቸው ብያኔ የሚሄዱበትን አዲስ ሂደት ያሳያል፡፡

5.4.1. የተዳከሙ ወቅቶች- ለክፍለ ዘመናት የቆመ ህግጋት ፈተና የኛንጋቶም ዘመን አቆጣጠር

በተለይ ለአስቸጋሪ አካባቢያዊ ሁኔታዎች የሚሆን ስኬታማ የመላመድ ዘዴ መገለጫውን የሚያገኘው በትክክልና በተብራራ መንገድ በባህላዊ ዘዴ ከትውልድ ወደ ትውልድ በሚሸጋገር ተፈጥሮና አካባቢያዊ ሁኔታዎች በየወቅቱ በሚያሳዩት ልዩነት ገለፃ ነው፡፡ የአንድ ዓመት ዘመን አቆጣጠር ከግልፅ ተቋማዊ መምሪያው ጋር ዓመቱን በሙሉ የማህበረሰቡ ባህላዊ የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል፡፡ የአኗኗር ዘዴ ብቻ ሳይሆን ስለአጠቃላዩ ሥነ-ፍጥረት ያለንን መረዳት ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ በአንድ በተወሰነ ቀን ዘሮችን በመሬት ውስጥ ያኖራሉ፤ ያም ምትኃታዊ ነው፡፡ ብዙ ኃይልና የወደፊት ተስፋን እንዲሁም ስለ አዲስ ሰብል መብቀል ያለንን እርግጠኝነት ሁሉ ያካትታል፡፡

የተዳከሙት ወቅቶች ህልውናዊ ነውጥ ያስከትላሉ፡፡ ግለሰቦችም ሆኑ ማህበረሰቡ በአጠቃላይ በእምነት ስርዓቱ፣ በባህላዊ ልምምዶቹ ብሎም በማህበራዊ ግንኙነቱ ላይ እምነት የማጣት አደጋ አንዣቦበታል፡፡

የኛንጋቶም ዘመን አቆጣጠር 12 ወራት ሲኖሩት ከአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ጋር ሊነፃፀር ይችላል፡፡ የወራቱ ስሞች ከተፈጥሮ አመለካከቶችና ከማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ይያያዛሉ፡፡ ለምሳሌ ሎቾቶ ማለት “ጭቃማው ወር” ማለት ሲሆን ሉሱባን ማለት ደግሞ “የበዓላት ወር” ማለት ነው፡፡ ዓመቱ በሁለት ክፍለ ጊዜያት የተለየ ነው፡፡ አንደኛው አኮፖሮ (የጥጋብ ወቅት) ይባላል፡፡ እርሱም ከየካቲት እስከ ሐምሌ ያሉትን ወራት ይይዛል፡፡ የበልግ አዝመራ የሚሰበሰብበትና ግጦሽ እንደ ልብ የሚሆንበት ወቅት ነው፡፡ ማህበረሰቡ ከወተት ምርትና በአጠቃላይ ከምግብ ፍጆታው ብዙ ያተርፋል፡፡ ከሐምሌ እስከ ጥር ያሉት ወራት አካሙ (የርኃብ ወቅት) ይባላሉ፡፡ ይህ የዓመቱን የድርቅ ወቅት ይወክላል፡፡ በመስከረም መጨረሻና በህዳር መጨረሻ መካከል ኢሩጴ የሚባል አጭር የዝናብ ወቅት አለ፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ ደጋማ ክፍሎች የክረምት ወቅት ጋር የሚዛመደውና በየወንዞቹ ዳርና ዳር በሚኖረው ደለል ላይ ሰብል የሚዘመርበት ወቅት ነው፡፡

ከእንሰሳት አስተዳደርና ከግጦሽ ሳር እጥረት የተነሳ የቀንድ ከብቶች ብዙውን ጊዜ በአካሙ ይሰደዳሉ፡፡ አዛውንቶችና ህፃናት ትናንሽ አመንዣኪ እንስሳትን ይዘው በሰፈር ይቆያሉ፡፡ ይህ ግማሽ ዓመት የርኃብና የእጥረት ጊዜ ነው፡፡ ምንም ዓይነት የወተት ተዋፅኦና የሰብል ምርት አይገኝም፡፡ የርኃብ ጊዜ የሆነው አካሙ በሁለት ክፍሎች ይከፈላል- “የእንሰሳት

42

አካሙ” እና “የሰዎች አካሙ”፡፡ የኋለኛው የሚያመለክተው ከምርታማነት ማነስ ወይንም ከምርት መዳከም የተነሳ ሰዎች የሚራቡበትን ወቅት ነው፡፡

“የእንሰሳት አካሙ” ደግሞ የእንሰሳትን መከራ ብሎም የወተት እና የስጋ ምርት የሚጠፋበትን ወቅት ይመለከታል፡፡ ይህ ደግሞ በግጦሽ መጥፋት ወይንም በእንስሳት በሽታ መከሰት ሊመጣ ይችላል፡፡ ሁለቱ ዓይነት አካሙዎች በተለያዩ መመዘኛዎች ወይም ምክንያቶች ላይ ስለሚመሠረቱ በአንዴ የመከሰት አጋጣሚያቸው የመነመነ ነው፡፡ ሰብሎች ከግጦሽ ሳር ይልቅ ብዙ እና ወጥ የአየር እርጥበት ይፈልጋሉ፡፡ ሌላው የኛንጋቶም የአመራረት ስርዓት አስፈላጊ ክፍል እንሰሳት ምርት ላይ ለውጥ በማያመጣው በጎርፍ የሚወሰን ነው፡፡ አሁን አሁን ከአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ ግን ሁለቱም የአካሙ ዓይነቶች በተደጋጋሚ በአንድ ጊዜ ይከሰታሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ኛንጋቶሞች በሙቀት፣ በአየር እርጥበትና በጎርፍ ላይ ስለሚታዩ የቦታና የመጠን ለውጥ ይወያያሉ፡፡ እንደነሱ ግንዛቤ ሁሉም ልዩነቶች ምልክት ያሳዩት እ.ኤ.አ በ1989 ሲሆን ቀስ በቀስ የእርጥበትና የጎርፍ መጠኑ እያሽቆለቆለ መሄድን ይጠቁማሉ፡፡ በጣም የከፋ ለውጥ የታየው እ.ኤ.አ ከ1998 ጀምሮ ነው፡፡ ለውጡም የሙቀት መጨመርንና ጠንካራ የእርጥበት ሁኔታ/መጠን መዋዥቅን ያካትታል፡፡ ሁለቱን የዝናብ ወቅቶች ስናነፃፅር እጅግ በጣም የተጎዳው የበልግ ዝናብ (ማለትም አኮፖሮ) ነው፡፡

የዝናብ ሁኔታ ለውጥ እንደ አካባቢው ነዋሪዎች አገላለፅ

ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ መስ ጥቅ ሕዳ ታህ

ከ1989 በፊት

ከ1989-1998

ከ1998 በኋላ

አኮፖሮ የጥጋብ ወቅት አካሙ የርኃብ ወቅት መፍቻ

ዝናብ በየእለቱ

ዝናብ በየሁለት ወይም ሶስት ቀኑ

ዝናብ በየሁለት ወይም ሶስት ቀን (ብዙም የማያስተማምን)

ዝናብ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ

ዝናብ በሳምንት አንዴ

የዝናብ አስተማማኝ አለመሆን

ንድፍ ጁሊያ ፊዝነር

43

“አስታውሳለሁ! የዝናቡ ወቅት እያጠረ እያጠረ መጣ ሶስት የነበሩት የዝናብ ወራት /

አኮፖሮ/ ሁለት ሆኑ፡፡ አሁን አኮፖሮ የሚባል ነገር ጭራሽ የለንም፡፡”

“ዝናቡ እንደፈለገ ነው፡፡ አንዳንዴ ጭራሽ አይመጣም፡፡ አንዳንዴ ደግሞ በኃይል ይመጣና

ወዲያው ይቆማል፡፡”

ከመስከረም እስከ ህዳር መጨረሻ ያለችው ኢሩጴ የተባለችው አጭሯ የዝናብ ወቅት ብዙም አልተለወጠችም፡፡ አንዳንድ ኛንጋቶሞች ኢሩጴን ከበፊቱ ደከም ያለች ሲሉ ይገልጿታል፡፡ በአጠቃላይ ግን ማህበረሰቡ ይህችኛዋ አጭር የዝናብ ወቅት ከአኮፖሮ ይልቅ አስተማማኝ መሆኗን ይናገራሉ፡፡

“እንደ እውነቱ ኢሩጴን ነው አዲሱ አኮፖሮአችን ብለን መጥራት ያለብን፡፡ አኮፖሮ ጭራሽ

የለም ማለት ይቻላል፡፡”

ሌላው የለውጡ መገለጫ እ.ኤ.አ ከ1998 ጀምሮ እየጨመረ የመጣው ሙቀት ነው፡፡ ይህ ለብቻው ተነጥሎ የሚታይ ሳይሆን እየቀነሰ ከመጣው ከአየር እርጥበት ጋር ተያይዞ ነው፡፡

“ያለ ጥርጥር በጣም ይሞቃል፡፡ አየሩን ሊያቀዘቅዝ የሚችል ደመናም ሆነ

ዝናብ ፍፁም የለም፡፡”

በኦሞ ጎርፍ ጉዳይ ይህ የተለየ ነበር፡፡ ማህበረሰቡ በደጋማ አካባቢዎች ዝናብና በቆላማ አካባቢዎች ጎርፍ መካከል ያለውን ዝምድና በሚገባ ይረዳል፡፡ ይህ ስለአየር ንብረት ለውጦች ከመልክዓ ምድር አንፃር ሰፊ ግንዛቤን ፈጥሯል፡፡

ከጥቅል የማሽቆልቆል አዝማሚያ በተጨማሪ ያልተጠበቁ ኃይለኛ ጎርፎች በተለይ እየታዩ ነው፡፡ ሰብሉን ድራሹን ያጠፉና ኛንጋቶሞችን ለባሰ የምግብ ዋስትና ማጣት ያጋልጧቸዋል፡፡ የቅርብ ጊዜ ለውጦቹ ቀድሞ ከነበሩት ድርቆች ተለይተው ነው የሚቀርቡት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ረጃጅሞቹ ተከታታይ ደረቅ ወቅቶች እና አጭሩ የማገገሚያ ጊዜ ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ፡፡

“ርኃብና ድርቅ ለኛ አዲስ አይደለም፡፡ አሁን ግን ሁሉ ነገር አሁንም አሁንም እየተደጋገመብን

ነው፡፡”

በተጨማሪ የተለመደው የእንሰሳት አካሙ እና የሰዎች አካሙ መገናኛ ወቅት ዋናው

44

አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ኛንጋቶሞች ድርቅን በቀላሉ መቋቋም ቢችሉም የቅርብ ጊዜዎቹ ለውጦች ግን ልዩ ልዩ መተዳደሪያ ጥሪቶቻቸውን ባንዴ እያጠቁባቸው የማህበረሰቡን የመቋቋም ብቃት ወስነውባቸዋል፡፡

ጥንት ድርቅ የሚከሰተው በግጭት የተነሳ ሲሆን ተፅዕኖዎቻቸውም በመልክአምድር የተወሰነ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሁሉም ኛንጋቶሞች ለከፋ አካሙ በአንዴ አይጋለጡም ነበር፡፡ በታሪክ እንዲህ ያለ ሁኔታ ያጋጠመው ለጥቂት ጊዜያት ነው፡፡

ለውጦች የሚተረጎሙት ወይም የሚተነተኑት በሰብልና በእንሰሳት ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ ከሚያደርሱ ሌሎች ምክንያቶች ጋር በማወዳደር ነው፡፡ ከድርቅ ውጭ ያሉ ዋና ተፅዕኖዎች በሽታዎችና ተባዮች (ለምሳሌ አምበጣ እና ተምች) እና ግጭቶች ናቸው፡፡

“ድሮ ረኃብ ብዙ ጊዜ የሚያያዘው ከግጭት ጋር ነበር፡፡ አሁን ግን ግጭቶች በጣም ቀንሰዋል፤ ረኃብ ግን በጣም ጨምሯል!”

ከተፈጥሮ የሚገኘው ማስረጃ አይቀሬ ለሆኑት ለውጦች እንደ ማረጋገጫ ይወሰዳል፡- ብዙ ጊዜ የዝናብ መምጣትን የሚያበስሩት እንደ ሞሩ እና ማዪሎ ያሉት ወፎች ጠፍተዋል ወይም አይታዩም፡፡ እንዲሁም አሲፒንጉ፣ ንሂኮር ወይም ሎፑርካች የመሳሰሉት ብዙ ጊዜ በእርጥበታማ ሁኔታ የሚታዩት ነፍሳት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ለመሰብሰቢያ ጥላነት ያገለግል የነበረው የኢሴኮን ዛፍ በቂ ቅጠሎችን ማውጣት ትቷል፡፡ አሁን አሁን እንደጥላ ለማገልገል በሌሎች ዛፎች ቅጠሎች መጠቅጠቅ ይኖርበታል፡፡ እንደ ኢካዴሊ፣ ኢዬል እና ኢፓንጋይ ያሉ ዛፎች ተሰራጭተዋል (ጄኒንግስ እና ማግራዝ ስለተመሳሳይ ሂደቶችና ስለ ማህበረሰቡ እርግጠኝነት ማጣት የፃፈውን ማዛፓርታን እንደ አስረጂ ይጠቅሳሉ፡- 2009፡10)፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመልክአ ምድራዊው ሰፊ ተፅዕኖ የለውጥን ትርጉም ወይም ትንታኔ ተፅዕኖ ያሳድርበታል፡፡ የመለዋወጥ ግንኙነቶች በጎርፍም፣ በድርቅም ተፅዕኖ ያርፍባቸዋል፡፡

“ማንም በለውጥ ወይም በማካፈል የሚያግዘን የለም፡፡ ጎረቤቶቻችን ሁሉ ችግር ላይ ናቸው፡፡ ለውጡ ሁሉንም አካባቢ ያካለለ ነው፡፡”

በቅርብ ጊዜ የታዩት ለውጦች በአጠቃላይ ግራ መጋባትን እየፈጠሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ከአካባቢው የዘመን አቆጣጠር ጋር ሊጣጣሙ አይችሉም፡፡ የወራት አስፈላጊነት በተለይ ትርጉም እያጣ ነው፡፡

“ወራቱ ስማቸው አልተቀየረም እንጂ ስሞቹ ምንም መልእክት ማስተላለፍ ተስኗቸዋል!”

45

በተለይ የአኮፖሮ ወራት ቅደም ተከተል ከተፈጥሮ ለውጥ የተነሳ ተዘበራርቋል፡፡

ዛሬ እየተጨቃጨቅን ነው ምከንያቱም አሁን ያሉንን ወራት ስሞች እየተወያየንባቸው ነው፡፡ ተፈጥሮ ምልክት መሰጠቷን ትታለች፡፡ ምን እንደሚመጣ በምን እናውቃለን? የዘመን አቆጣጠራችንም ከአሁን በኋላ ዋጋ የለውም፡፡”

ኛንጋቶሞች በለውጡ ማብራሪያ ላይ የተለያየ ገለፃ አላቸው፡፡ በአዛውንቱና በወጣቶች መካከል ግልፅ ልዩነቶች ታይተዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ወጣቶቹ ምንም አይነት ማብራሪያ አይሰጡም ወይንም ደግሞ ግጭቶችን እንደ መንስኤ ይወስዷቸዋል፡፡

“እግዚአብሔር በምድራችን ላይ ስለፈሰሰው ደም ሁሉ እያለቀሰ ነው፡፡”

አዛውንቱ በውይይቶቻቸው በአጠቃላይ ማህበራዊና ባህላዊ ጥያቄዎች ለምሳሌ ስለ ኛንጋቶሞች ዋና አማካሪ ስለ ሎጉቲ ሞት በማንሳት ይነጋገራሉ፡፡ ሎጉቲ እ.ኤ.አ. በ1989 በደረሰው አስከፊ ግጭት ወቅት በስህተት ቸል ተብሎ ነበርና ከመሞቱ በፊት የኛንጋቶምን ማህበረሰብ ረግሞት ነው ማህበረሰቡ ለዚህ ውድቀት የበቃው የሚል መረዳት አላቸው፡፡ አዛውንቱ በተጨማሪ ለአያት ቅድመ አያቶች የተነፈገው አድናቆትና አክብሮት ዛሬ በተፈጥሮ ላይ ላለው ችግር መንስኤ እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ ወጣቶቹ ለውጦቹ የማይመለሱ መሆናቸውን ሲደመድሙ አዛውንቶቹ ያመነታሉ እናም ወደፊት ስለሚሆነው ነገር አስተያየት መስጠት አይፈልጉም፡፡ ይህ ተፈጥሮንና አካባቢያዊ ሁኔታን በመገንዘብ ረገድ በትውልዶች መካከል ያለውን ለውጥ ያሳያል፡፡ ወጣቱ ትውልድ ከአባቶቻቸው ይልቅ ለውጡ መሠረታዊ እንደሆነ አድርገው ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ኛንጋቶሞች አዲስ የተፈጥሮና የማገገሚያ ሚዛን ለማግኘት እንዲችሉ ወራቱን እንደገና መሠየም እንደሚያስፈልግ ይስማማሉ፡፡

5.4.2 የመላመድ ዘዴ እንደ መሠረታዊ ሽግግር/ለውጥ ስርዓትና የአርብቶአደሩ ነባራዊ እይታ

የመላመድ ዘዴ ያለ ጥርጥር የሚያነጣጥረው የመተዳደሪያ ዋስትናን እንደገና በማጠናከር እና በማገገም ብቃት /ሪዚሊየንስ/ ላይ ነው፡፡ ከላይ እንደተገለፀው የመላመድ ዘዴ ማለት አዳዲስና ከዚህ በፊት አገልግሎት ላይ ያልዋሉ ስልቶችን መጠቀም ማለትም ነው፡፡ በውጤቱም እነዚህ ስልቶች በአብዛኛው አዳዲስና ጥናት ሊደረግባቸው የሚገባ የተግባር መስክን እና አዳዲስ ማህራዊ ተቋማት መፈጠርን ያመላክታል፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ የኛንጋቶምን ጉዳይ እንደገና እጅግ ከፍተኛ አደጋ የተደቀነበት ማህበረሰብ ምሳሌ አድርገን እንውሰደው፡፡ በዚህ ተጨባጭ አደጋ በሞላበት አካባቢያዊ ሁኔታ ውስጥ ሁለት የተለያዩ የመላመድ ዘዴ ገፅታዎች እንመለከታለን፡፡

46

1. የከብቱን መንጋ ግማሽ ያህል ማሰማራት የሚችሉ ትልልቅ ልጆች ያሉት ኃብታሙ ሽማግሌ ልጆቹን ቲርጋ ወደሚባለው የተሻለ ግጦሽ ወዳለው ተራራማ ስፍራ ይልካል፡፡ ህይወት በብቸኛው የእንሰሳት መቆያ ቦታ ለወጣቶቹ አስቸጋሪ ናት፡፡ በህይወት ለመቆየት ከፍተኛ ትግል ያደርጋሉ፤ አንዳንዴም አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት ሲሉ እንሰሳት መሸጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ከመቅፅበት የከብቱ ዋጋና ስለከብቱ የነበራቸው አመለካከት ይለወጣል፡- ከክብር ወይም ማዕረግ ማሳያነት ወደ መገበያያ ገንዘብነት፡፡ ወጣት ወንዶች፡-

“በሎኩላን እንሰሳት ከሸጥክ ወይም ከለወጥክ ሰዎች ይኮንኑሃል፡፡ በቲርጋ ግን ምንም

አይነት ሌላ አማራጭ የለንም እና አዛውንቶቹም እንኳ ይህን ይረዳሉ፡፡

አንድ ሰው ብልጥ ከሆነ ጥቂት እንሰሳት ብቻ ኖረውትም የተከበረ ሊሆን ይችላል” ሲሉ

ይከራከራሉ፡፡

የኛንጋቶም አዛውንት

ወጣት የኛንጋቶም ጦረኛ ከሚወደው የቀንድ ከብት ጋር

47

የኛንጋቶም ቤተሰብ አባት ከብቶቹን ሲንከባከብ

እንሰሳትን ሊያሰማሩ የሚችሉ የደረሱ ልጆች የሌሉት የአዲስ ቤተሰብ አባት በቀድሞው አኗኗር ከመቀጠል ይልቅ ከብቶቹን ለማስወገድ፣ ጥቂት አመንዣኪዎችን ብቻ ለማስቀረት እና ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ይወስናል፡፡ እንዲህ ይላል፡-

“አዛውንቶቹ ሁልጊዜ ስለ እንሰሳት ያወራሉ! ነገር ግን ብዙ ወጣት ወንዶች ከአሁን

በኋላ እንሰሳትን መንከባከብ አይፈልጉም፡፡ ስራው በጣም ከባድ ነው፡፡ እኔ ጥቂት

አመንዣኪዎች ይበቁኛል፡፡ ልጆቼን ሴቶቹንም ጭምር አስተምራለሁ፡

ሁለቱም ማሳያዎች የማህረሰባዊ ሽግግር ወይም የለውጥ ሂደትን ያሳያሉ፡፡ በቲርጋ የሚቆዩት ወጣት ወንዶች ሁለተኛ ከፊል አርብቶ አደሮች አይሆኑም፡፡ አርብቶአደር ነው የሚሆኑት - እናም እንሰሳትን የማርባትና የመጠበቅ ስርዓቱን ወደ ገበያ ተኮር ሥራ ያሸጋግሩታል፡፡ ወጣት አባወራ በተቃራኒው የድሮ አኗኗሩን ከነአካቴው ትቶ በትምህርት አማካኝነት ወደ ዘመናዊነት ይሸጋገራል፡፡ በሁለቱም ሁኔታ የአገር በቀሎቹ ማህበራዊ ተቋማት ቅንብር እና ዋስትና የማይደረስባቸውና ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል፡፡ እነዚህ የወጣቱ ትውልድ ወኪሎች በውጭ ገፅታቸው የኛንጋቶምን ማንነት ሊያሳዩ ይችላሉ፤ በውስጣቸው ግን የተለወጡ ግለሰቦች ነው የሚሆኑት፡፡

ሁኔታው አዳዲስ ተቋማትን የግድ የሚል ነው፡፡ በቲርጋ ለሚኖሩት እረኞች የሚያገለግሉ የእንሰሳት ገበያና የእንሰሳት ህክምና አገልግሎቶች ይሁኑ ወይም ለቤተሰቡ አባት ልጆች የሚሆኑ የተሻሉ የትምህርት ስርዓቶች - የአዳዲስ ተቋማት መመስረት የግድ ነው፡፡ አዛውንቶቹ በዚህ በአዲሱ ስርዓት ውስጥ በከፊልም ቢሆን የራሳቸውን አስተዋፅኦ በፖለቲካ እና አዳዲሶቹን ተግዳሮቶች በሚቆጣጠሩ ሁኔታዎች በተተኩት የስልጣን መዋቅሮች እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል፡፡

48

ለህልውና የሚደረግ የማገዶ ለቀማ

ከዚህ ከግለሰብና እጅግ አስደናቂ ከሆነው ከደቡብ ኦሞ ከፊል አርብቶ አደሮች ሁኔታ በመነሳት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የመላመድ ዘዴ ማለት በብዙ መልኩ አዳዲስ ህብረተሰብአዊ መዋቅሮችን እና ተቋማትን መገንባት ማለት ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ያለ ጥርጥር የውጭ ድጋፍን የግድ የሚል ሂደት ነው፡፡

6. መደምደሚያ፡- የመላመድ ዘዴ አሉታዊ ተፅዕኖን ከመቀነስ ብቃት /ሚቲጌሽን/ እና ከገንዘብ ድጋፍ ጋር ይያያዛል

አሁን ፊታችንን ወደ እነዚህ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ወደአረፈባቸው አካባቢያዊ ሁኔታዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብናዞር ዘላቂ የመሬት አስተዳደርና የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚወሰዱ እርምጃዎች ለምሳሌ ቦረቦረሮች እንዲያገገሙ ማድረግና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የመሳሰሉት የአየር ንብረት ለውጥን የማስታገስ ውጤት አላቸው በሚለው አነጋገር መጀመር ይኖርብናል፡፡ ፎርች (እ.ኤ.አ 2009)

ማህበረሰቡ በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚፈጠሩ ክስተቶችን መቋቋም እንዲችሉ ጥቅም ላይ የዋሉ የተለመዱ የመሬት አስተዳደር ዘዴዎችን በትክክል አስቀምጧቸዋል፡፡

ይህን መሰል አበረታች ተሞክሮ ቢኖርም ለአስረጂነት በተወሰዱትና ጥናቱ በተካሄደባቸው ቦታዎች ያለው የተጋላጭነት ወይም የተጠቂነት እውነታ ከልዩ አካባቢያዊ የአየር ንብረት ለውጥ ገፅታ ጋር ተቆራኝቶ በጋራ የነዋሪዎቹን ከሁኔታዎቸ ጋር ተስማምቶ የመኖር ብቃት የማዳከምና ለምግብ ዋሰትና ማጣትና ለድህነት የማጋለጥ አዝማሚያ አለው፡፡ ይህ በተራው ከአጠቃላይ የዘላቂ የመሬት አስተዳደር ግብ ጋር በተቃራኒው የሚቆም ሁኔታ ነው፡፡

49

በተግባር እንደተማርነው ማንኛውም ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፕሮግራም በሚያደርገው የድህነት ቅነሳና በልማት ጥረቶቹ በእርግጥም ዘላቂ ሊሆን የሚችለው ለተጠቃሚዎቹ የሚያደርገው ድጋፍ እነዚህ የተጋላጭነት እውነታና የአየር ንብረት ለውጥ ገጽታ ያላቸውን አጥፊ ቁርኝት ለማጥፋት በግልጽ የተቃኘ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይህም በታወቁትና ለብዙ አካባቢዎች ምሳሌ በሆኑት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ላይ ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ ሊከናወን ይችላል፡፡

ውጤታማ ለመሆን ብሎም የዘላቂነትን ዓላማ እውን ለማድረግ የልማት ሀሳቦች የአየር ንብረት ለውጥ መሰረታዊያንን ከልማት ሀሳቡ ጽንሰ ሀሳቦችና ከተግባር እርምጃዎቻቸው ጋር መቀናጀት ይኖርባቸዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች፣ ተጋላጭነት እና ተስማምቶ የመኖር አቅም - እነዚህ ገጽታዎች ካሉበት ልዩ አካባቢያዊ አውድ አንጻር መፍትሔ ሊፈለግላቸው ይገባል፡፡ በዚህ ምክንያት ከለውጡ ጋር የመላመድ ዘዴን በማስፋፋት ሂደት እያንዳንዱ አውደ-ሁኔታ የራሱ የሆኑ የተለየ መፍትሔን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የመላመድ ዘዴዎችን በማስፋፋት ሂደት መገንዘብ የሚገባን አብይ ጉዳይ እያንዳንዱ አውደ-ሁኔታ የራሱ የሆነ የተለየ መፍትሄ የሚፈልግ መሆኑን ነው፡፡

በመጨረሻም የልማት አቅጣጫዎች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ለመላመድ የሚደረግ ድጋፍ የራሱ ውስንነቶች እንደሚኖሩት አስቀድሞ እውቅና ከመስጠት ጋር መጣመር ይኖርባቸዋል፡፡ አንዳንድ ትኩረት የተደረገላቸው ቡድኖች ምናልባትም እጅግ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ቡድኖች - አሁንም ሆነ ወደፊት ለዘላቂ የመላመድ ዘዴ ምንም አይነት እድል በማይሰጥ ሁኔታ በአየር ንብረት ኃይላት ይመታሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመተዳደሪያ ዋስትናቸው የሚያደርጉት ትግል በውጫዊ ዘዴና መሳሪያዎች መታገዝ ይኖርበታል፡፡

እዚህ ላይ ወደኋላ መለስ ብለን ዛሬ እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን የአኗኗር ወይም የመተዳደሪያ ስርዓቶች እንመልከት፡፡ ይህ የአኗኗር ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ በእንሰሳት እርባታ ላይ የተመሰረተና አሁን አሁን አናሳ ከሆነው የእንሰሳት ምርታማነት እና ከእንሰሳት መሞት የተነሳ መከራን የሚገፋ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ የእንሰሳት ቁጥር እንዳላት የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የአፈር መከላት፣ በረሀማነት፣ የአፈር መሸርሸር - እነዚህ ሁሉም በደንብ የታወቁ የእንሰሳት እጅግ መብዛትና ከተገቢው በላይ የሆነ ግጦሽ አስከፊ ውጤቶች ናቸው፡፡ ይሁንና አርሶአደሮችም ሆኑ አርብቶ አደሮች ዛሬም ሆነ ወደፊት ከብቶቻቸውን ይፈልጓቸዋል፡፡

50

በሌላ በኩል ሰዎች አስተሳሰባቸውን እየቀየሩ ነው፡፡ ከብዙ የመስክ ላይ ውይይቶች እንደተረዳነው ለምሳሌ ከኛንጋቶም ወጣት አርብቶ አደሮችና ከደጋማ አካባቢዎች አርሶአደሮች የመላመድ ዘዴ ስልቶች እንዳየነው ማህበረሰቡ የእንሰሳት ቁጥርን ጉዳይ እያሰበበትና ጥቂት ጤናማ እንሰሳት ቢኖሩኝ ይሻላል ወደሚለው ሀሳብ እያዘነበለ ነው፡፡ የተሻሻለ የግጦሽ መሬት አስተዳደር ከእንሰሳት ህክምና አገልግሎት ጋር አሁን ላለው ከፍተኛ የእንሰሳት ቁጥር የተሻለ አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በደንብ የተደራጀ የማደለብ ስራ በኢትዮጵያ ገበሬዎች ይተገበራል፡፡ /ለምሳሌ በሐረር አካባቢ) እና ከሌሎቹ አርሶአደሮችና ከአርብቶአደሮች ጋር በአሰራሩ ላይ መወያይት ይቻላል፡፡

እዚህ ላይ ‘አሉታዊ ተፅዕኖዎችን መቀነስ’ /Mitigation/ ከመላመድ ዘዴ /Adaptatiuon/ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊያገለግል ይችላል፡፡ የግጦሽ መሬት አስተዳደር ለወደፊቱ የካርቦን እዳ ማወራረሻ ዘዴ ተደርጎ እየተወሰደ ነው፤ እናም በተለይ ረጃጅም ስር ያላቸው የሳር ዝርያዎች በርካታ ካርቦንን ማከማቸት ይችላሉ /I.P.C.C., 2002፣ ናይልስ እና ሌሎች 2010፣ ስሚስ እና ሌሎች 2007/፡፡ አለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፎች /ለምሳሌ R.E.D.D./ ስላሉ አርሶአደሮችና አርብቶ አደሮች ከነዚህ አሰራሮች አስተማማኝ የሆነ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ንድፍ አሰራር /የካርቦን ገንዘብ የአየር ንብረት ለውጥ የመላመድ ድጋፍ G.E.F. ወዘተ/ በአካባቢያዊ እና በተጠቃሚ ቡድኖች አውድ ተደራሽና ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ይህ እንደገና ከዚህ በፊት የተባለውን የአዳዲስ ተቋማትንና የተቋማቱን ግንባታ አስፈላጊነት ጉዳይ የሚያጠናክር ነው፡፡

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለምሳሌ የግጦሽ መሬት አስተዳደር፣ ከአፈር ማሻሻያ እርምጃዎች ለምሳሌ የቀልዝ ዝግጅት ጋር የተቀናጀ የተከለሉ ቦታዎች አስተዳደር፣ ከውጪ የሚመጡ ድጋፎች አስተዳደር እና ለካርቦን እዳ ማወራረሻ የተዘጋጀውን ገንዘብ አጠቃቀም የሚቆጣጠርና የሚገመግም እንዲሁም አስፈላጊነቱን የሚያረጋግጥ አሰራርን የመሳሰሉት ሁሉ በማህበረሰቡ ውስጥ አዳዲስ ተቋማትን የግድ ይላሉ፡፡ ግኝት፣ ከልምድ መማርና ልማትን ማመቻቸት የመሰረታዊ ለውጥ ሂደቶችን ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ደግሞ መጀመር ያለበት በማህበረሰቡ ድርጅታዊና ተቋማዊ መዋቅሮች ውስጥ ነው፡፡

51

መንስኤያዊ ጥናት 1 - ድርቅ በምስራቃዊ ዞን በብሪታ ላንግ

የሐሊማ ታሪክ፡

‹‹በዚህ ጊዜ አንድ ላደርግ የምችለው ነገር ቢኖር መፀለይ ብቻ ነው››

መልካም ጅማሮ በሚዳጋ ቶላ

‹‹ምንጊዜም ሚዳጋ ቶላ ለመኖሪያ አስቸጋሪ ስፍራ ነው፡፡›› የ40 ዓመቷና የስድስት ልጆች እናት ሐሊማ እንደምታስታውሰው:: ‹‹ይሁን እንጂ›› ትላለች ‹‹መጀመሪያ ወላጆቼ ወደዚህ አካባቢ ሲፈልሱ የተትረፈረፈ ምርት የሚሰጥና ተስፋ ሰጪ መሬት ነበር፡፡››

ወደ ኋላ መለስ ብላ የወጣትነት ጊዜዋን ስትቃኝ አካባቢዋን የሸፈነውን ጥቅጥቅ ደንና ብዛት ያላቸውን ዛፎች ታስታውሳለች፡፡ አባቷ አስራ አምስት ላሞች፣ ሃያ አምስት ፍየሎችና በጎች፣ ስምንት መሬቱን የሚያርሱባቸው ብርቅዬ በሬዎች ባለቤት ነበሩ፡፡ ዝናቡም በበቂ ሁኔታ በዓመት ሁለት ጊዜ ሳያቋረጥ ስለሚዘንብ እሳቸውና ጎረቤቶቹ ጎተራቸውን በማሽላና ሌሎች እህሎች መሙላት ይችሉ ነበር፡፡ አንድ መልካም አዝመራ ሰፊውን ቤተሰባቸውን ለሁለት ዓመት ይቀልብ ነበር፡፡ ከብቶቹ ከተረፈ ምርቱ ስለሚቀለቡ የፋፉ ነበሩ፡፡ የሐሊማ እናት ህፃናቱን ለመመገብ በቂ ወተትና ማር ነበራት፡፡ ድጋፍ የሚሻ ሰው ከመጣም የእህል እርዳታ ያደርጉለት ነበር፡፡ በወቅቱ የሐሊማ ቤተሰቦች እንደ ማንኛውም በሰሜናዊ ሚዳጋ ቶላ የሚገኝ የቤርዛላ ማህበረሰብ የተረጋጋ ኑሮ ነበራቸው እንጂ ሀብታም አልነበሩም፡፡

‹‹ዛፎቹ ከተቆሩጡ አንስቶ የአየሩ ፀባይ መለወጥ ጀመረ፡፡›› ትላለች ሐሊማ ይህን አስተውላ ‹‹ዝናቡ አስተማማኝነቱ በቀረ ቁጥር ድርቅ በየዓመታቱ የተለመደ ሆነ፡፡››

52

ገና ለአቅመ ሄዋን እንደደረሰች የመቋቋም ዘዴ መጠቀም

ነገር ግን ሐሊማ እንዴት ለውጥ እንደመጣ ታስታውሳለች፡፡ ብዙ ብዙ ሰዎች ወደ ሚዳጋ ቶላ እየፈለሱ መጡ ብዙ ሕፃናትም ተወለዱ፡፡ የእርሻ መሬት ፍላጎትም እየመጨመረ በመሄዱ ወንዶቹ ዛፎቹን በመቁረጥ የእርሻ መሬት ማስፋፋት ጀመሩ፡፡ ዛፎቹ በሙሉ ሲወድሙ ሐሊማ ገና ጨቅላ ነበረች:: በወቅቱ አካባቢውን ስጋት ላይ ጥለውት የነበሩት የዱር እንሰሳት እንደ ጅብ፣ አንበሳና ዝሆን የመሳሰሉት ራቅ ወዳለው ወደ ጎበሌ ሸለቆ ተሰደዱ፡፡

በዓመታት ውስጥ የእርሻ ምርቱ በሚያስገርም ሁኔታ አሽቆለቆለ፡፡ በመንግስት የተቀጠሩ የአካባቢው የግብርና ቢሮ ተወካዮች የችግሩ መንስኤ መሬቱ ከሚገባው በላይ በመታረሱ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ሐሊማ ለዓቅመ ሄዋን ስትደርስና ብሎም ጋብቻ ስትመሠርት ለእሷና ለጎረቤቶቿ ድርቅ ብርቅነቱ አበቃ፡፡ በአንደኛው ዓመት ሐሊማና ባለቤቷ አብዱ ከምርት እጥረት የተነሳ ሲቸገሩ ለቀጣዩ ዓመት ደግሞ አብዱ በድርቅ ወራት አጠቃላይ ቤተሰቡን ሊመግብ የሚችል በቂ እህል ያመርታል፡፡ ስለዚህም ነበር ሐሊማና አብዱ የከብቶቹን ፍግ መሬታቸው ላይ እንደ ማዳበሪያነት ለመጠቀምና አልፎ አልፎ የመሬታቸውን ክፋይ እዳሪ ለማድረግ የወሰኑት፡፡ ይህን በማድረጋቸው በሚያገኙት ምርት የተሻለ ኑሮ መኖር አስችሏቸዋል፡፡ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ግን አንዳንዴ በእጇ የምትሰራውን የቃጫ ገመድ እንዲሁም በርበሬና ሌሎች የእህል አይነቶች ገበያ ወስዳ መሸጥ ነበረባት፡፡

ሐሊማ ይህን ሁኔታ እንዴት መወጣት እንዳለባት ታውቃለች፡፡ እጥረት በሚፈጠርበት ወቅት ለገዛ ልጆቿ እንኳ ወተትና ማር አትሰጣቸውም፡፡ ነገር ግን ለህፃናቱ ጥሩ ገንፎ፣ ለአዋቂዎቹና ለአሮጊት እናቷ እንጀራ በበርበሬ መመገብ የሚያስችል በቂ የእህል ክምችት በጎተራ ውስጥ ይኖራታል፡፡ ሐሊማና አብዱ ከግብርናው በተጨማሪ ገቢ ሊያስገኝላቸው የሚችሉ ሌሎች አማራጮችን ፈልገው በማግኘት ጥሩ ኑሮ ለመኖር በሚያስችላቸው ደረጃ የተቀናጁ ናቸው፡፡

ለሶስት ዓመታት የተዛባ ዝናብ፡ ‹‹መላው ቀዬ በረሃ ይመስላል››

ሆኖም የሚዳጋ ቶላ ሁኔታዎች በመጥፎ ሁኔታ በፍጥነት ተለዋወጡ፡፡ ማንም ምክንያቱን ሊናገር አይችልም፤ ይህም ሐሊማ፣ ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እርግጠኛ መሆን እንዲሳናቸው አደረገ፡፡ ብዙዎች ግን የአላህ ቅጣት ነው ብለው ያምናሉ፡፡

53

አሁንማ ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ጥቂት ምርት ሊያስገኝ የሚችል ዝናብ እንኳ ጠፋ፡፡ እርግጥ ነው ለጥቂት ቀናት ዝናብ ነበር፡፡ አንዳንድ እፅዋት ብቅ ብቅ እንዲሉ የሚረዳ ነበር፡፡ ነገር ግን ወዲያው ዝናቡም ቆመ እፅዋቱም ጠውልገው ዋጋ ቢስ ሆኑ፡፡

በዚህ ዓይነት ሁኔታ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ምርት ሊያስገኝ የሚችል ትክክለኛ የዝናብ ወቅት ሳይገኝ አለፈ፡፡ መሬቱ ተሰነጣጠቀ ውሃ ያቁሩ የነበሩ ጉድጓዶችም ሙሉ በሙሉ ደረቁ፡፡

‹‹መላው ቀዬ በረሃ መሰለ እኮ›› አሉ የሐሊማ አያት፡፡ ከዚህ ጋር ሊነፃፀር የሚችል ሁኔታ እሷም ራሷ አይታ አታውቅም፡፡

አብዱ ዝናቡ ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ምክንያት በእርሻው ላይ መማሰን ቀስ በቀስ እየሰለቸው መጣ፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ መሬቱን ቆፍሯል፣ አምስት ጊዜም አርሶታል፡፡ያስቀመጠውን ዘር አሟጥጦ ዘርቷል፤ በጣም ታትሯል፤ ነገር ግን ድካሙ ሁሉ ከንቱ ሆኖ ቀረ፡፡

እንሰሳት አልባ ሕይወት

ባለፈው ዓመት አብዱ የቤተሰቦቹ የእህል ክምችት ማለቂያው እንደተቃረበ ተመለከተ፡፡ ከብቶቹም ቢሆኑ ከጥቅማቸው ይልቅ ሸክምነታቸው እያመዘነ እንደመጣ

54

ተገንዝቧል፡፡ ደካሞቹ ጥጆች ቀደም ብለው ሞተዋል፤ የዓመቱ ሞቃት ወር የሰኔ ሙቀትም ከአቅማቸው በላይ ነበር፡፡ ሌሎቹም መኖና ውሃ ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን አልፋፉም፡፡

በተስፋ መቁረጥም ከብቶቹን መሸጥ ጀመረ፡፡ ይሁን እንጂ ጥሩ ዋጋ ሊያገኝላቸው አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ሌሎቹም የእሱ አይነት ሀሳብ ስለነበራቸው ከብቶቻቸውን አውጥተው ገበያውን አጥለቅልቀውት ነበርና፡፡ አብዱ ከሽያጩ ያገኘው ገቢ ቤተሰቡን ለጥቂት ወራት መቀለብ የሚችል ምግብና አስፈላጊ ቁሶች መግዛት የሚያስችል ብቻ ነበር፡፡

ሐሊማ የላሞቹና የፍየሎቹ ቁጥር መመናመኑን ስትገነዘብ እሷና ልጆቿ ተጨማሪ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል ነገር መፍጠር እንዳለባቸው ተገነዘበች፡፡ ስለዚህ ሁለት ትናንሽ ሴት ልጆቿን አሚናና ሰይናን ገመድ መስራት እንዲቻል ቃጫ ቆርጠው እንዲያመጡ አሰማራች፡፡

ሐሊማና ልጆቿ በቂ ገመድ መስሪያ ለማግኘት ለሰዓታት መጓዝ ነበረባቸው፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ብዙ ሴቶች የገመድ ምርት በማቅረብ ለመኖር ከሚያደርጉት ጥረት የተነሳ የቃጫ ዕጥረት መፈጠር ጀምሮ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ወደ ቤት ካመጡት በኋላ ቃጫውን ለመሰንጠቅና ለመፈልቀቅ ሰዓታት ይፈጃል፡፡ ሴቶቹ ስራው እስኪገባደድ ድረስ አጎንብሰው ለረጅም ሰዓታት መቆየት ግድ ስለሚላቸው በቀኑ መጨረሻ ጀርባቸውንና ጉልበታቸውን ሕመም ያሰቃያቸዋል፡፡ ልጆቹም ለረጅም ጊዜ በዚህ አይነት ሁኔታ መቆየት ስለማይችሉ ቀሪዎቹን ሐሊማና አያቷ ገመዱን ሲያመርቱ ልጆቹ ምግብ ማዘጋጀትና ቤት ማጽዳቱን ይያያዙታል፡፡

በቂ ገመዶች ከተሰሩ በኋላ ተለቅ ያለችው ልጇ ወይም ሐሊማ እራሷ ሚዳጋ ቶላ ገበያ ይዘው ይሄዳሉ፡፡ ለማህበረሰቡ ትርጉም የሚሰጥ ምርት ሳይኖር ጊዜው እየነጎደ ሲሄድ ገመድ ሻጮች ገበያውን እያጥለቀለቁት ሄዱ የገመድ ዋጋም እንዲሁ አሽቆለቆለ፡፡

55

ቤቱን በአግባቡ በመያዝ የሚረዷት ሁለቱ ትላልቅ ልጆቿ ከዲጃና ደሀብ ሲሆኑ እነርሱም በመንደሩ ወደሚገኘው ጉድጓድ በመሄድ ተራ ጠብቀው ጥቂት ጀሪካን ውሀ በአህያ ጭነው ለማምጣት ተሰማሩ፡፡

ልጆቹ በአካባቢያቸው ከሚገኘው ጉድጓድ ውሀ ማግኘታቸው አበቃ፡፡ ስለሆነም አለ ከሚባለው አንድ ብቸኛ ጉድጓድ ቀኑን ሙሉ ተሰልፈው ውለው ሁለት ጀሪካን ውሀ ለማግኘት ግብ ግቡ ከባድ ሆነ፡፡ ስለሆነም አህያ ቸል ሊሉት የማይችሉት ጠቃሚ የቤት እንሰሳ ሆነ፡፡ እንዲያም ሆኖ ውሃው እጅግ ጥራት የጎደለው ከመሆኑም በላይ የኩላሊት በሽታ እንደሚያስከትል በሰፊው ይነገራል፡፡ በየጥቂት ቀናቱ አንድ ትልቅ የመንግስት የውሃ ቦቴ እየመጣ የሕዝብ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውሀ ገንዳ ውስጥ ይገለብጣል፡፡ ነገር ግን ውሀው የሚበቃው ለከተማው ነዋሪዎች ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውሀ ለመቋደስ ከተፈለገ እዚያው ማደር ይጠይቃል፡፡ እንዲህ ሲያደርጉ ደግሞ ከተሜዎቹ ይሰድቧቸዋል፡፡

የውሃ ጉድጓዶች በሙሉ ስለደረቁ ምንም የሚጋሩት የለም፡፡ ሐሊማ ይህ የየቀኑ ፍልሚያ ስለሰለቻት ቤተሰቦቿን ረጅሙን መንገድ በመጓዝ ከጎበሌ ሸለቆ የወንዝ ውሃ መቅዳት እንዳለባቸው አሳመነች፡፡ ጉዞው ከቤርዛላ አምስት ሰዓት ይፈጃል፡፡ ወደ ወንዙ የሚያቀኑ ሌሎች ሰዎችም ስለነበሩ መንገዱን ማግኘት ቀላል ነበር፡፡ ሸለቆው የዱር እንሰሳት መኖሪያ ስለሆነ አደገኛ መሆኑን ሰምተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሁልጊዜ ጎላ ባለ ድምጽ እየዘፈኑና የተለያየ ደምጽ እያሰሙ በመሄድ ድንገት ሊያጠቃቸው የሚችል እንሰሳ ካለ ያባርራሉ፡፡ ነገር ግን በአንደኛው ቀን አንድ አጋጣሚ ተከሰተ፡፡ አንድ ዝሆን የሌላ መንደር ነዋሪ የሆነች ሴትን አጠቃ፡፡ ምን እንደሆነ ትክክለኛውን ነገር ሊያውቅ የቻለ ማንም የለም፡፡ ነገር ግን አስክሬኗንና በአጠገቧ ደግሞ የዝሆኑን ዳና አግኝተው ነበር፡፡

ከዚያን ጊዜ አንስቶ ወንድሞቻቸው ሐምሳና ጀማል አዲስ ግዳጅ ተሰጣቸው፡፡ ምንጊዜም ሜንጧቸውን ይዘው ከፍ ያለ ድምፅ እያሰሙ እህቶቻቸውን ያጅባሉ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወንዙ አካባቢ ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ሁኔታው ቀላል አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በደጋው አካባቢ ባለመዝነቡ የወንዙ ፍሰት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ስለዚህ ጥቂት ውሀ ለማግኘት ሴቶቹ መሬት መቆፈር ነበረባቸው፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ በላያቸው ከወደቀው ልፋትና ጫና ባሻገር እነርሱና ከጥቃት ሊጠብቋቸው የመጡት ወንዶች በድካምና ውሃን ባለማግኘት ስጋት ተያዙ፡፡

56

የሚያገኙትን እያንዳንዱን ገንዘብ ለምግብ ፍጆታነት ስላዋሉት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ተለቅ ያሉትን ወንዶች ልጆች ሐምሳና ጀማልን ወደ ትምህርት ቤት መላክ አልቻሉም፡፡ አብዱ የመጨረሻዋን ላም ፋዲስ ገበያ ወስዶ ቢሸጥም ያገኘው ገንዘብ ግን ጥቂት ሆነ፡፡ ልጆቹ ስራ ፈትነት ሰለቻቸው፡፡ ስራ ፈልገው እንዳይቀጠሩ ገና ለጋ ናቸው፡፡ እናታቸውንና እህቶቻቸውን እንዳያግዙ ልምዱ የላቸውም፡፡ ስለዚህ አብዛኛውን ጊዜ ከጓደኞቻቸው ጋር በከንቱ ያሳልፋሉ፡፡ከብቶቻቸው የሉም፤ ጥቂት ምርት እንኳ የሚያስገኝ ዝናብም የለም፡፡ የቀራቸው እንሰሳ ቢኖር አህያና ጥቂት ዶሮዎች ናቸው፡፡

በተመሳሳይ በቤት ውስጥ ያለው ሁኔታም እየከፋ መጣ፡፡ ከገመድ ስራ የሚገኘው ገቢ በቂ አልሆነም ስለዚህ ሐሊማ ገቢዋን ከፍ ለማድረግ ስለፈለገች ማገዶ ለቀማ ጀመረች፡፡ይህ ማገዶ ለቀማ አደጋ አለው፡፡ አንደኛ በአካባቢዋ የተረፉ ዛፎች የሉምና ወደ ጎበሌ ሸለቆ መውረድን ይጠይቃል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከልጆቿ ጋር እርስ በእርስ እየተጠባበቁ ይሄዳሉ፡፡ ተለቅ ያሉ ሴቶች ውሀ ለማምጣት አህያ ይዘው ሲጓዙ ሐሊማ የለቀመችውን እንጨት በገመድ አስራ በትከሻዋ ትሸከማለች፡፡ አንድ ቀን አምሽታ ወደቤቷ ስተገባ እንጨቱን የተሸከመችበት ገመድ ትከሻዋንና ደረቷን ሰርስሮ አቆሰላት፡፡ ለፋሻ መግዣ ወይም ለሕክምና ወጪ ገንዘብ ስለሌላት ቁስሏን የሸፈነችው በአሮጌ ጨርቅ ቅዳጅ ነበር፡፡

ከማገዶ ለቀማው ጋር የተያያዘ ሌላም ጫና ነበረባት፡- ሕግ፡፡ እከሌ ከእከሌ ሳይባል ማንም ሰው አንዲት ዛፍ እንዳይቆርጥ ታግዷል፡፡ መንግስት አለምአቀፍ ስምምነትን ለማስከበር ሰፊ መሬት ከልሎ በጥበቃ ስር አውሏል፡፡ ለዱር እንሰሳቱም እንዲህ ሆኗል፡፡

የውሃ ቦቴ መኪና ሲደርስ

57

ማንም የዱር እንሰሳ እንዳያድን የሕግ ከለላ ተደርጎላቸዋል፡፡ ይህም ብዙዎች የዱር እንስሳቱ ሕይወት ከእነርሱ ሕይወት ይልቅ የበለጠ ዋጋ የተሰጠው መስሎ እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ ስለዚህ ሐሊማ ብትያዝ ሊደርስባት የሚችለውን ትልቅ ችግር ስለምታውቅ በእጅጉ ትጠነቀቃለች፡፡ ይሁን እንጂ የእርሷና የቤተሰቧ በሕይወት መቆየት በማገዶው ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ልትተወው አትችልም፡፡

የአብዲን መመለስ መጠባበቅ

አብዲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሕንፃ ግንባታ ባለበት ወይንም ደግሞ በቂ ዝናብ በሚገኝበት አካባቢ በሀብታም እርሻ በመቀጠር ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ስራ ፍለጋ ወጥቷል፡፡ ሀብታሞቹ ገበሬዎች በገንዘብ ወይም ቢያንስ በእህል እንደሚከፍሉ ጎረቤቶቿ ነግረዋታል፡፡ አብዲ ሰርቶ ካገኘው አንድ ነገር ወደ ቤት መላክ ነበረበት፡፡ ነገር ግን ሐሊማ ምንም ነገር አልደረሳትም፡፡ የት እንዳለ ምን እየሰራ እንደሆነ አታውቅም፡፡ አንዳንድ ንብረቶቿን አካባቢዋ ወደሚገኝ ገበያ ወስዳ ሸጣለች፡፡ ባሏ ባይኖርም ብቻዋን በሕይወት ለመቆየት እየታገለች ነው፡፡ አያቷ ብቻቸውን ቤት ውስጥ እንዲውሉ ሆነዋል፡፡ አንዳንዴ ወጣ ብለው እህል ወይንም ቁራሽ እንጀራ ከጎረቤት ይለምናሉ፡፡ ጎረቤታሞች ያላቸውን መካፈል የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን አያቷ አቅመ ደካማ ስለሆኑ ራቅ ብለው አይሄዱም፡፡ አጎራባቾቻቸውም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ ዝናብ ከጠፋ ቆይቷል ስለዚህ ማንም ምንም የሚያካፍለው የለውም፡፡ በዚህ አይነት ምን ያህል ጊዜ መቀጠል እንደሚቻል ሐሊማ አታውቅም፡፡

በዚህን ጊዜ አንድ ልታደርግ የምትችለው ነገር ቢኖር መፀለይ ብቻ እንደሆነ ትናገራለች፡፡

መንስኤያዊ ጥናት 2- የኛንጋቶም ከፊል አርብቶ-አደር እይታ - በጁሊያ ፊዝነር፡፡

‹‹አሁን እየሆነ ያለው እያንዳንዱ ነገር ከአቅማችን በላይ ነው፡፡››

‹‹አርብቶአደርነት ማለት የሀብት እጥረትና የአየር ንብረት ጫና በበዛበት ሁኔታ ውስጥ

በአካባቢያዊ ስነምህዳር፣ በእንስሳትና በሰዎች መካከል ያለ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ

የተመሰረተ ጥብቅ ትስስር ነው፡፡ ይህም ትስስር ውስብስብ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃንና

በግጦሽ፣ በእንስሳትና በሰዎች መካከል ቀጣይ የስነምህዳር ሚዛን መጠበቅና ማስተዳደርን

ያካትታል፡፡››

ኖሪ እና ዴቪስ 2007፡7

58

ዛሬ በደንብ የዳበረው የአካባቢያዊ ስነምህዳር፣ የእንስሳትና በደቡብ ኢትዮጵያ በደቡብ ኦሞ የሚገኘው ከፊል አርብቶ-አደር የሆነው የኛንጋቶም ማህበረሰብ ግንኙነት ያለጥርጥር ተረብሿል፡፡ እንደ አንድ የኛንጋቶም አዛውንት አባባል አሁን እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ አርብቶአደሩን ከመቋቋም አቅሙ በላይ ወደሆነ ሁኔታ ውስጥ ከቶታል፡፡ ይህን አባባል በአግባቡ ለመረዳትና በጣም ከተከበረው የባሕላዊ የፖለቲካ ቡድን አባል ወደ ተጋባችው ሞሩ የተባለች የኛንጋቶም ሴት ታሪክ ከመዝለቃችን አስቀድመን ሶስቱን የከፊል አርብቶአደር ማህብረተሰብ አስደናቂ ምሰሶዎችን እንይ፡፡

ምሰሶ አንድ - እንሰሳት

የኛንጋቶም ባህል ከእንሰሳት እርባታ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ሲሆን ለኛንጋቶም የቤት እንሰሳ ማለት የባህላቸው አንዱ ምሰሶ ነው፡፡

‹‹የኛንጋቶም ባሕል ማለት የከብት ባለቤትነት ነው፡፡ ከብቶቻችንን ካጣን ባሕላችንንም አጣን፡፡››

እንሰሳት በኛንጋቶም ሕይወት ውስጥ በተለይም የቀንድ እንሰሳት ማለት ለወተት፣ሥጋና ሌጦ ምርት ጥቅም ከሚውሉ እንስሳት በላይ ናቸው፡፡ ከሀብት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ከበሬታም የሚለካው አንድ ቤተሰብ በሚኖረው የእንሰሳት ብዛት ነው፡፡ የጥሎሽ ክፍያ እንሰሳት ነውና ለጋብቻ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ በጥንቃቄ የሚደረግ የሚስት ምርጫና የእንሰሳት ባለቤትነት የወንዱ መለኪያ ነው፡፡

‹‹የብዙ ከብት ባለቤትነት መከበሪያ ነው፡፡››

‹‹ጠንካራ ወንድ ከብቶቹን ይዞ ርቆ ይሄዳል፡፡ ጠላትን ይፋለማል፣ ረሀብ አይፈራም፡፡

ከምንም በላይ ከብቶቹን ይወዳል፡፡››

የመጨረሻው ጥቅስ ፅናትን እንደ አዎንታዊ የጠንካራ ወንድ መገለጫ ይገልጻል፡፡ ከረሀብ ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታን በጽናት መጋፈጥ መቻልም አንዱ የጥንካሬ መገለጫ ነው፡፡ ኛንጋቶሞች ከቀንድ እንሰሳት ጎን ለጎን ጥቂት አመንዣኪዎችም (በግና ፍየል) አላቸው፡፡ እነርሱም በተለይ በችግር ጊዜ ለዓይነት ልውውጥ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ይህን የበግ፣የፍየልና የቀንድ እንሰሳት ልውውጥን ለማስቀረት በተቻለ መጠን ጥረት ይደረጋል፡፡

በእረኝነት መሰማራት ከጦርነት እና ራስን እንደ ጦረኛ ከማየት ጋር የተቆራኘም ነው፡፡ በተለይ የግጦሽ መሬት ለግጭት የተጋለጠ ነውና ከእንሰሳት ቀጥሎ ሁለተኛው አስፈላጊ

59

የወንድነት መገለጫ ጠመንጃ ነው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ እንሰሳትንና ማህብረሰቡን ከጥቃት መጠበቅ አንዱና በጣም አስፈላጊው የወንድ ሚና ነው፡፡

ከእህል በተጨማሪ የእንስሳት ተዋጽኦዎች በእለታዊ ፍጆታ ውስጥ አስፈላጊ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ትናንሽ አመንዣኪዎች (ፍየልና በግ) በአካሙ ወቅት (በድርቅ/በረሀብ ወቅት) ለእርድ ያገለግላሉ፡፡ በዚህ ወቅት የቀንድ ከብቶች ወደሩቅ ቦታ ሲወሰዱ ጥቂት ፍየልና በጎች ከአዛውንቶች፣ ሴቶችና ሕፃናት ጋር መንደር ውስጥ ይቆያሉ፡፡ በድርቅ ወቅት ፍየል (ሻል ባለ ጊዜ በጎችም ጭምር) ወተት ለመታለብ ተፈላጊ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለአምልኮ ሥርዓታዊ ወጎችም በጣም አስፈላጊ ናቸው (ለምሳሌ የዝናብ ልመና ሥነ-ስርዓት)፡፡ የቀንድ ከብት የሚታረደው እንደ ትላልቅ ሥርዓታዊ ወጎችና ሰርግ ላሉ በጣም ልዩ ለሆኑና ለተመረጡ ጉዳዮች ብቻ ነው፡፡ ለምግብነት እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑትና ብዙ ጊዜም ተቀላቅለው የሚቀርቡት የላም ወተትና ደም ናቸው፡፡ ከስጋ ጎን ለጎን ቅቤ ልዩ ማህበራዊ እሴትን ያስተላልፋል፡፡ እነዚህ የዕለት ተዕለት ምግብ ናቸው፡፡ በዋናነት ግን ለአዛውንቶችና በጣም ለተከበሩ ሰዎች የሚቀርቡ የምግብ ዓይነቶች ናቸው፡፡

ለኛንጋቶሞች እንስሳት የማንነት መለያ ናቸው፡፡ በሴቶች የሚለበሰው የበግና የፍየል ሌጦ ከየትኛው ጎሳ መሆናቸውን እንዲሁም የጋብቻ ሁኔታቸውን ይጠቁማል፡፡ የእንሰሳት ቀለምና የመንጎች ቅንብር አባወራው በማህበረሰቡ ውስጥ ስላለው ደረጃ ግልጽ የሆነ መረጃን ይሰጣሉ፡፡

በአጠቃላይ ከኢኮኖሚያዊ ተፈላጊነታቸው በተጨማሪ ሁሉም እንስሳት በተለይ የቀንድ ከብቶች ማሕበራዊና ስነ-ልቦናዊ ትርጉም አላቸው ማለት ይቻላል፡፡የእንስሳት ተዋጽኦ ባለቤት መሆን በራሱ፤ እንዲሁም ለፍጆታና ለጥቅም ማዋል የከፊል አርብቶአደሩ ማህበረሰብ ማንነት ዋነኛ ክፍል ነው፡፡

የኛንጋቶም የሌጦ ቀሚስ

60

ምሰሶ 2፡ የሰብል ምርት

ኛንጋቶሞች ዓመታዊ የእህል ምርት እንቅስቃሴአቸውን በሁለት የተለያዩ የግብርና ዑደቶች ማለትም በዝናብና በወንዝ ጎርፍ ላይ መስርተዋል፡፡ የዝናብ እርሻ በበልግ ዝናብ (አኮፖሮ) እገዛ በየካቲትና በግንቦት መካከል ይከናወናል፡፡ የወንዝ ዳር ደለል ግብርና የሚከናወነው በክረምት ወራት (ከሀምሌ-መስከረም) በደጋማው አካባቢ በሚዘንበው ዝናብ ምክንያት የኦሞ ወንዝ ጎርፍ ይዞት በሚመጣው የወንዝ ዳርቻ ለም አፈር ላይ ነው፡፡

ሁለቱ የግብርና ዑደቶች የአስተራረስ ዘዴ ጥቂት ልዩነት አላቸው፡፡ እጅግ በጣም አስፈላጊዎቹ አዝርዕት ማሽላ፣ ባቄላና በቆሎ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የወንዙ ዳርቻ ትምባሆ፣ ዱባና ቅል ለማብቀል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በአነስተኛ መጠን ከሚመረቱት ባቄላና በቆሎ ይልቅ ማሽላ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ ከዚያም በላይ በባሕላዊ ምክንያት የተለየ ተፈላጊነት አለው፡፡ ኛንጋቶሞች ማሽላን ቅዱስ ነው ይላሉ፡፡ ለተለያዩ ሥርዓታዊ ወግም ይጠቀሙታል፡፡ ከእንስሳቱ ባሻገር የማሽላ መኖርና ለፍጆታ መዋል ኩራታቸውና የማንነታቸው መገለጫ ጭምርም ነው፡፡

የኦሞ ወንዝ ዳርቻዎች

61

‹‹የምናገኘው ሁሉ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ማሽላ መብላት ካልቻልን ረሀብ ይሰማናል

እውነተኛ ኛንጋቶምነትም አይሰማንም፡፡››

በሌላ በኩል በቆሎና ባቄላ በሶስት ወር ከሚደርሰው ማሽላ ይልቅ በአጭር ጊዜ (በሁለት ወር) ይደርሳሉ፡፡ ይህም የማሽላ ምርት ከመድረሱ በፊት የረሀቡን ጊዜ ለማሳጠር የሚያገለግሉ አስፈላጊ የሰብል ዝርያ ያደርጋቸዋል፡፡

ምሰሶ 3፡ የኛንጋቶም ‹‹የመረዳዳት ባሕል››

በምሰሶ 2 እንደተገለጸው የእንሰሳት እርባታና የሰብል ምርት የኛንጋቶም ማህበረሰብ የማንነት ክፍል ናቸው፡፡ የእንሰሳት እርባታና የሰብል ምርት ከምግብ ዋስትና፣ ከባህልና ራሳቸውን ከሚገምቱበት ሚዛን አንፃር ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ከተገለፀው አስፈላጊነታቸው ባሻገር እንስሳትና ማሽላ ወዳጅነትን ለመመስረት አስፈላጊ መሳሪያ ናቸው፡፡ ኛንጋቶሞች እንስሳትና ማሽላን በመስጠትና በመቀበል በማህበረሰባቸው ውስጥ ጠንካራ ማህበራዊ የግንኙነት መረብን ይፈጥራሉ፡፡ ይህ የመስጠትና የመቀበል ግንኙነት በረሀብና በችግር ጊዜ አስፈላጊ መደጋገፍን አምጥቷል፡፡ ማኅበረሰቦቻቸውና አባሎቻቸው በተለያየ መልክአምድራዊ አቀማመጥ ላይ ስለሚገኙ ነዋሪዎቹ የሚገጥሟቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎችም እንዲሁ የተለያዩ ናቸው፡፡

አካሙ (ድርቅ) ሁሉንም ኛንጋቶሞች በተመሳሳይ ደረጃ አያጠቃም፡፡ ከፊሎቹ ኛንጋቶሞች በወንዝ ዳር እርሻ ላይ ሌሎቹ ደግሞ በእንስሳት እርባታና በዝናብ ላይ የተመሰረተ ስራ እርሻ የተደገፉ ናቸው፡፡ በድርቅ ወቅት የልውውጥ ግንኙነቱ ሕይወትን የማቆያ ትልቁ መንገድ ነው፡፡

‹‹ወዳጅ ሕይወትህን ይታደጋል፡፡ በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ልትቀርበው ትችላለህ፤ እርሱም

በአህያህ ማሽላ ይጭንልሀል፡፡ ምንም ነገር አይጠይቅህም ምክንያቱም አንተም እንዲህ

እንደምታደርግ ያውቃልና፡፡››

62

የኛንጋቶም የማካፈል ባሕል

‹‹ለወጣት ወንድ ለአዛውንቶች በሬ

ማረድ ክብር ነው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ

ለመከበርና ለመባረክ አስፈላጊ ነው፡፡››

በሰፈር ውስጥ ሁሉም የዕቃ ልውውጥና ስጦታ (የምግብ እርዳታን ጨምሮ) በወዳጆችና በዘመዳሞች መካከል ይከፋፈላል፡፡ እርድ ሲደረግ አባወራው በማህበረሰቡ ውስጥ ከሚገኙ ወዳጆቹ ጋር ይካፈላል፡፡

መደበኛ ምግብ እንኳን አቲያም በሚባለው በማህበረሰቡ መካከለኛ የመሰብሰቢያ ስፍራ በአንድነት ይበላል፡፡ እያንዳንዱ ወንድ እንደ ሚስቶቹ ቁጥር ብዛት በቅል ምግብ ሞልቶ ያበረክታል፡፡ አዛውንቶች

ከወጣቶቹ በለጥ ያለ ይሰጣሉ፡፡ በንጽጽር አልፎ አልፎ በሬ አርደው አዛውንቶችን የሚጋብዙት ወጣት ወንዶች ናቸው፡፡

ስለዚህ የተገኘው ምግብ ሁሉ በአካባቢ እንዲሁም በመንደር ደረጃ ይከፋፈላል፡፡ የምግብ እደላው የኛንጋቶም ህብረተሰብን ደህንነት ሚዛናዊ ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ የኛንጋቶሞች የመካፈል ባህል አስቸጋሪና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲገጥማቸው ራሳቸውን የሚያስተካክሉበት ትልቁ መሳሪያቸው ነው፡፡ ይህ ሁሉ ባህላዊ ሁኔታ የኛንጋቶም ማህበረሰብ የሚታወቅበትና ከዕለታዊ ኑሮአቸው ውስጥም የተዋሃደ ሚናን የሚጫወት ነው፡፡ ሰጥቶ መቀበል ከላይ እሰከታች ያለ የመቋቋሚያ ዘዴና የከፊል አርብቶአደሩ ማህበረሰብ ማንነት ዋና ክፍል ነው፡፡

ነገር ግን ዛሬ ኛንጋቶሞች በጠላትነት ከተሰለፉባቸው አስጨናቂ ውጫዊ ኃይላት ጋር ተፋጠዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ሕግ አስገዳጅነት ማሰማራት ወደሚፈልጉበት (ለምሳሌ የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ) አካባቢ ከብቶቻቸውን ለማሰማራት መከልከላቸው፣ በፕሮስፒስ ጁሊ ፍሎራ ዛፍ ወረራ ምክንያት የቀድሞ የባህል ማዕከል (ኪቢሽ)ን ማጣታቸው፣ ከቱርካና ማህበረሰብ ጋር እየጨመረ የመጣው የመሬትና የሀብት

63

ግጭት፣ መሬታቸው ለግብርና ኢንቨስትመንት ይወሰዳል ብለው መስጋታቸውና ዘመናዊነት ያመጣው ማዕበል ይገኙበታል፡፡ ኛንጋቶሞች በአየር ንብረት ለውጥ አስገዳጅነት ሊጠፉ ወደሚችሉበት ድንበር ተቃርበዋል፡፡

‹‹ዝናቡ በመሬታችን ላይ ትንሽ ጠብ ይላል፡፡ በቀጣዩ ቀን ያው እንደገና ይሞቃል፤

እናም ፀሐዩ ሳሩን ያበግነዋል፡፡››

የበልግ ዝናብ ከመጥፋቱ የተነሳ ኛንጋቶሞች ከበቆሎና ከባቄላ ይልቅ ለመድረስ ረጅም ጊዜ የሚወስደውን ማሽላ መዝራት አቁመዋል፡፡ በዝናብ ጥገኛ የሆነውን እርሻ ጨርሶ በመተው በኦሞ ወንዝ የዳርቻ እርሻ ላይ ተወስነዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በኦሞ ወንዝ አካባቢ የመሬት ፍላጎት ጫና በእጅጉ እየጨመረ ነው፡፡ ነገር ግን የወንዝ ዳር እርሻም ተስፋ የሚደረግበት ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች ዝናብ አስተማማኝነቱን በእጅጉ ባጣ መጠን የወንዝ ዳር እርሻ ምርታማነትም እያሽቆለቆለ መጣ፡፡ እንዲያውም በአዝመራ ወቅት ሁለት ሶስት ጊዜ የሚከሰተው ያልተጠበቀ ጎርፍ ሌላ ከፍተኛ አደጋን ጋርጧል፡፡

በዝናብ መጥፋት ሳቢያ የግጦሽ መመናመን ስላጋጠመ እንስሳቱን በተለይም የቀንድ ከብቶችንና በጎችን ደካማና ምርት አልባ አደረጋቸው (ከታች ያለውን ‹‹የመላመድ አቅም››/አዳፕቲቭ ካፓሲቲ/ ሰንጠረዥ ይመልከቱ)፡፡

በተጨማሪ ግጦሽ እየተመናመነ ሲመጣ እንሰሳትን ራቅ ወዳለና የተሻለ ግጦሽ ወደሚገኝበት ተራራማ አካባቢዎች መውሰድ የግድ ሆኗል፡፡ በድርቅ ወቅት ብቻ ግጦሽ ፍለጋ ራቅ ብሎ የሚኬድበት ዘመን አክትሟል፡፡ አሁን ከብቶቹና ምርታቸው ዓመቱን ሙሉ ለቤተሰቡ በቅርብ የማይገኙ ሆነዋል፡፡

በእነዚህ አዳዲስ ሁኔታዎችና አካሄዶች ውስጥ የመካፈል ባህል ቀስ በቀስ እየደበዘዘ መጥቷል፡፡ ኛንጋቶሞች የልውውጥ ግንኙነት ሊያደርጉበት የሚያስችሏቸው አስፈላጊ ቁሶች በእጃቸው የሉም፡፡ ግለሰቦች ለመኖር በየግላቸው እንዲፍጨረጨሩ ተገደዋል፡፡ እናም በህይወት ለመቆየት የምግብ እርዳታ እደላ እንዲቀርብላቸው ተደርጓል፡፡

64

ተጠቂነት/ ተጋላጭነት

• በጣም የተጋለጠ የአኗኗር ዘይቤ (አስከፊ በረሃማነት)

• በእጅጉ እንሰሳት እርባታ ላይ የተተገነ እርሻንም ለማካተት መጣር

• ከመጠን ያለፈ የእንሰሳት ብዛት/ መጨናነቅ

• የስጋት መስረፅ፤ ኦብፓ፣ ፕሮስፒስ፣የግብርና -ኢንቨስትመንት፣የሐብት ግጭቶች

የጥቃቱ ድምር ውጤት

የአየር ንብረት ለውጥ ገጽታዎች

• የበልግ ዝናብ መጥፋት (ለተከታይ ኣመታት)

• የኦሞ ወንዝ ዳርቻ እርሻና ምርታማነት መቀነስ

የመላመድ አቅም/ አዳፕቲቭ ካፓሲቲ/

• የእየጠፉ የመጡ የመተዳደሪያ መለኪያዎች፣ ‹‹ከመጋራት ባሕል›› ወደ ‹‹መጥፋት ታሪክ››

ንድፍ/እሳቤ፡ በፕሮፌሰር ዛቢን ትሮጀር

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች

65

ሞሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሞ ሸለቆ ውስጥ ከሚኖሩ 21 የከፊል አርብቶአደር ጎሳዎች

አንዱ ከሆነው የኛንጋቶም ጎሳ አባል ስትሆን ዕድሜዋም 45 ዓመት ነው፡፡ ሞሩ አንድ

ወንድና አራት ሴት በድምሩ አምስት ልጆች አሏት፡፡ ሞሩ በአንገቷ ላይ ከቡናማ የእንጨት

ዘር የተሰራ የአንገት ጌጥ ወይም ኤሊፋንት አድርጋለች፡፡ ይህ የአንገት ጌጥ በማኅበረሰቡ

ዘንድ እጅግ በሚከበረው የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ ወንድ ያገባች መሆኑን ያመለክታል፡፡

ነገር ግን ባለቤቷ ሕመምተኛ ስለሆነ ቀድሞ እንደሚያደርገው ቤተሰቡን መደገፍ አልቻለም፡፡

ሞሩ፤ የዝሆን ቤተሰብ ሚስት

66

ሞሩ ምንግዜም ማለዳ ጎህ ሳይቀድ ትነሳለች፡፡ ላሞቿን አልባ ለባሏና ለልጆቿ ቁርስ ታዘጋጃለች፡፡ በቂ ምግብ ከተዘጋጀና ከተረፈ እርሷም ትበላለች፡፡ በቀን ብዙ ጊዜ የሀያ ደቂቃ የእገር ጉዞ በማድረግ ከኦሞ ወንዝ ውሃ ታመላልሳለች፡፡ አንዳንዴ ሎፒንያንግ የተባለችው ወጣቷ ሁለተኛዋ የባሏ ሚስት ትረዳታለች፡፡

በድርቅ ወቅት ሞሩ ትንሽ መሬት በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ታርሳለች፡፡ የራሷ የሆኑ እንስሳት የሏትም፤ ነገር ግን ባለቤቷ የሁለት ላሞችና የአምስት ፍየሎችን ምርት እንድትጠቀም ፈቅዶላታል፡፡ ይህ በኛንጋቶም ባሕል የተለመደ ነው፡፡ ወተቱን በመናጥ ቅቤ ታወጣለች፡፡ ሞሩ በወተት ተዋጽኦዎች ትደሰታለች ምክንያቱም ልውውጡ በሴቶች መካከል ወዳጅነትን ያፈራልና፡፡ በችግር ጊዜ ወዳጆች ረሀብን ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት ሊያስታግስ የሚችል ነገር ይልካሉ፡፡ ሞሩ ይህ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በተግባር ታውቃለች፡፡

ነገር ግን ላሞቹ ቀድሞ ይሰጡት ከነበረው ወተት ያነሰ መስጠት ጀመሩ፡፡ ስለዚህ ሴቶቹ ግንኙነታቸውን የሚያስተሳስር ነገር አጡ፡፡ ሞሩ ራሷ ከሁለት የቅርብ ወዳጆቿ ጋር የነበራት ግንኙነት ተቋርጧል፡፡

ዛሬ የሞሩ ልጅ ታገባለች፡፡ ለዚህ ልዩ ቀን ሞሩ ጎሳዋን የሚጠቁም ቀለም ያለውን ባሕላዊ የሌጦ ቀሚስ መልበስ ፈልጋለች፡፡ ይሁን እንጂ ቀሚሱ ቆርፍዷል፡፡ ለማለስለሻ የሚሆን ቅቤ የላትም፡፡ ይህ ሁሉም የኛንጋቶም ሴቶች የሚጋሩት ችግር ነው፡፡ የደረቀው ጫፍ ገላቸውንና ተረከዛቸውን እየሞዠቀ ስለሚያሳምማቸው ወንዶቹ ቢቃወሙም ሴቶቹ ከጨርቅ የተሰራ የምዕራባውያን ቀሚስ መልበስ ጀምረዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ በኛንጋቶም ባሕላዊ ጋብቻ ላይ ሞሩ መልበስ ያለባት ሌጦ ነው፡፡ ምንአልባት የቆረፈደው ሌጦ እንደልቧ አያስጨፍራት ይሆናል፡፡ “ያም ሆነ ይህ ውጪ ያለው ሙቀት አድካሚ ነው” ስትል አሰበች ሞሩ፡፡

የኛንጋ

ቶም ሴ

ቶች ሲ

ጨፍሩ

67

በእድሜ እጅግ የሚበልጣትን ሰው የምታገባዋን ልጇን ትመለከተቻት፡፡ ሞሩ ለልጇ የተመኘችላት

ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ አዲሱ የልጇ ባለቤት ግን የሞሩ ባለቤት ጥሩ ወዳጅ ነው፡፡ በእርግጥ ቀሪውን

ቤተሰባቸውን በደንብ ይረዳል፤ እጥረት ሲፈጠር ወዳጅነትን ጠብቆ ማቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡

ኛንጋቶሞች በድርቅ ወራት መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ያውቁታል፡፡ ሞሩ ላለመሞት

ሌጦ እስከመብላት የደረሰችበት የፅኑ ረሀብ ወቅት ልምድ አላት፡፡ ኛንጋቶሞች ደጋግመው

በሚተርኩት ታሪካቸው ውስጥ እንደሚታየው ረሀብ እና ረጅም ድርቅን አሳልፈዋል፡፡ ስለዚህ

ኛንጋቶሞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መኖርን ተለማምደዋል፡፡ ቤተሰቦች በተለያየ ጊዜ የተለያዩ

የውሃ ምንጮችን/መገኛዎችን በመጠቀም መሬትን ያለማሉ፡፡ የሚያረቧቸው እንስሳትም የተለያዩ

ሰለሆኑ ለአካባቢያዊ ሁኔታዎች የተለያየ ምላሽ አላቸው፡፡ የኛንጋቶም ሕዝብ ችግርን በአግባቡ

ለመወጣት ይተባበራል፡፡ ነገር ግን ሁኔታው ተለወጠ፡፡ አሁን አሁን ድርቁም ማቆሚያ የለውም፡፡

በኛንጋቶም የቀን አቆጣጠር የወራቱ ስሞች አካባቢያዊ ሁኔታዎችንና የጋራ ክንዋኔዎችን

ያንፀባርቃሉ፡፡ ለምሳሌ መጋቢት ምንጊዜም ጭቃማ ነው፡፡ ለዚህ ነው ሎኮቶ ወይም ‹‹ጭቃው››

ሲሉ የጠሩት፡፡ አንዳንዴ ሞሩ በዚህ ወር ወደ እንስሳቱ ማደሪያ በጣም ሳትጨቀይ ለመድረስ

አነስተኛ ድልድይ ትገነባ ነበር፡፡ በሚያዝያ ሳር ማደግ ይጀምራል፡፡ ስለዚህ ይህ ወር ሎቲማ ተብሎ

ይጠራል፤ ‹‹ሳሩ እያደገ ነው›› ማለት ነው፡፡ ከአስር ዓመት በፊት ዝናቡ በአንድ ጊዜ መጣ፤

ይህን ወቅት ኛንጋቶሞች ‹‹ታላቁ ጎርፍ›› ሲሉ አቲኪፒ ብለው ሰየሙት፡፡ ከአቲኪፒ ጀምሮ ዝናቡ

ባሻው ጊዜ መምጣት ጀመረ፡፡ ወጥነቱና አስተማማኝነቱ ቀረ፡፡ ሞሩ ሁኔታው ሁሉ ተምታቶባታል፡፡

የወራቱ ስም እየተቀያየረ ከመጣው አካባቢያዊ ሁኔታ ጋር በጭራሽ አይጣጣምም፡፡ ሞሩ ‹‹የቀን

መቁጠሪያው መስራት አቁሟል›› ስትል አብረዋት ለነበሩት ሴቶች ተናገረች፡፡

ከ1998 በፊትአኮፖሮ አካሙ

የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ መስ ጥቅ ኅዳ ታህ ጥር

ፍየሎች

በጎች

የቀንድ ከብቶች X X X X

ከ1998 በኋላ አኮፖሮ አካሙ

ፍየሎች

በጎች X X X X

እንሰሳት X X X X

የወተት ምርታማነት

መግለጫ

ከፍተኛ አነስተኛ የለም

ንድፈ/እሳቤ፡ በጄ. ፊዝነር

X

68

የዝናቡ ወቅት በየካቲት ጀምሮ በሰኔ ያበቃ ነበር፡፡ ኛንጋቶሞች ይህን ወቅት አኮፖሮ (የጥጋብ ወቅት) ብለው ይጠሩታል፡፡ የደጋማ አካባቢ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወቅቱን በልግ ይሉታል፡፡ በዚህ ጊዜ ኛንጋቶሞች በዝናቡ በመታገዝ የእርሻ ስራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡ እንስሳቱ በቂ ሳር ስለሚያገኙ ብዛት ያለው ወተት ይሰጡ ነበር (ሰንጠረዡን ይመልከቱ)፡፡ ማህበረሰቡም በዚህ ወቅት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ያዘጋጃል፡፡ በየትኛውም ሥፍራ ያሉ ኛንጋቶሞች ለጭፈራና መረጃ ለመለዋወጥ ይሰበሰቡ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ዝናብ ከመጥፋቱ የተነሳ እንዲህ ያሉ በዓላት እየቀሩ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ ሁሉም ነገር ተለውጧል፡፡

በየዓመቱ ለስድስት ወራት በሚዘልቀው ደረቅ ወቅት መሬቱ እንደ ድንገተኛው ነፋስ ደረቅ ፀሐዩም የሚያቃጥል ነው፡፡ ሞቃታማው ንፋስ አሸዋውን አስነስቶ ዛፎችን እየሰባበረና ቁጥቋጦዎችን እያስተኛ እያፏጨ ይሄዳል፡፡

ኛንጋቶሞች አካሙ ብለው በሚጠሩት በዚህ የድርቅ ጊዜ ወጣት ወንዶች ቤተሰቦቻቸውን ትተው ለከብቶቻቸው ውሃና ሳር ፍለጋ ርቀው ይጓዛሉ፡፡ ሴቶች፣ ሕፃናትና አዛውንቶች ከበጎችና ከፍየሎች ጋር በመንደር ይቀራሉ፡፡

የኛንጋቶም እረኞች

የሞሩ ቤተሰብ ብዙ እንሰሳት ስላሏቸው እንደ ሀብታም ይታያሉ፡፡ እርሷ ባትቆጥራቸውም ምንአልባት 150 እንስሳት ይኖራቸዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ባሏ ስለታመመና የሚንከባከባቸው አንድ ወንድ ልጃቸው ብቻ ስለሆነ እንዴት አድርገው እንስሳቱን መያዝ እንደሚችሉ ግራ ተጋብተዋል፡፡ ይህን ሀሳብ ለባሏ ባታካፍለውም ቤተሰቡ ጥቂት እንስሳት ብቻ ቢኖረው ስትል ተመኝታለች፡፡ በማህበረሰቡ ባህልና ወግ መሠረት በተከታታይ እንስሳትን መሸጥ ወይም መለወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ የሚገጥመው ጉዳይ ነው፡፡ ኛንጋቶሞች በረኃብ

69

የኛንጋቶም ጦረኞች

ወቅት እንኳን አንዲትን ላም ለማረድ ከመወሰናቸው በፊት የላሞችን ደም በመጠጣት ሕይወታቸውን ለማቆየት ይጥራሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሞሩ በችግሮቿና ከሀሳቦቿ ብዛት የተነሳ እንቅልፍ ታጣለች፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት አምስት የኛንጋቶም ወንዶች እንሰሳት ለመዝረፍ በመጡ የጎረቤት ጎሳዎች ተገድለዋል፡፡

ሞሩ ወንድ ልጇ ቢገደልባት ምን እንደምታደርግ በማሰብ ትጨነቃለች፡፡ እንስሳቱን ማን ይንከባከባል? ቤተሰቧን ማን ይንከባከባል? በኛንጋቶም ባህል ሴት የራሷ መብት የላትም፡፡ ቤተሰቦቿን ለመመገብ እንኳ ፍየል መሸጥ ወይ መለወጥ አይፈቀድላትም፡፡

ነገር ግን ሁሉም ኛንጋቶሞች የዚህ ችግር ሰለባ ናቸው ስትል አሰበች፡፡ የግጦሽ መሬት እየጠበበና የከብቶቹም ጤንነት እያሽቆለቆለ መጥቷል፡፡ ኛንጋቶሞች የድርቅና የእርጥበት ጊዜያትን ሁኔታ በመከታተል በተደጋጋሚ ለግጦሽ መዘዋወርን ለምደዋል፡፡ ነገር ግን ከዝናብ እጥረት የተነሳ ለለውጥ የሚሆን በቂ የግጦሽ መሬትም ጠፍቷል፡፡ ይህም ዘመናትን ተሻግረው የዘለቁትን የመቋቋሚያ ብልሀቶች መና አሰቀርቷቸዋል፡፡ ሁሉም በየዕለቱ እየተባባሰ በመጣው የአካባቢው ሁኔታ ውስጥ በህይወት ለመቆየት በሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮች ላይ ይወያያሉ፡፡ እያንዳንዱ የማህበረሰብ አባል በጭንቀት ያጉረመርማል፡፡

70

ትናንት ሞሩ ጥቂት ወጣት ወንዶች ሲጨቃጨቁ በጨረፍታ ሰምታለች፡፡ መንደራቸውን ለቀው በቀላሉ ሳር ወደሚገኝባቸው ተራራዎች ከብቶቻቸውን ይዘው በመሄድ አዲስ ሕይወት በመጀመር አማራጭነት ላይ ተወያይተዋል፡፡

ወጣቶቹ ይህን ሲነጋገሩ ከአንድ ጎረቤቷ ጎጆ በስተጀርባ ቆማ ነበር፡፡በወንዝ ዳርቻ የሚገኙ እርሻዎቻቸውንና አዛውንቶችን ጥለው ለመሄድ እንኳ ተነሳስተዋል፡፡ ‹‹ወጣቶቹ ይህን ለማድረግ እንዴት ደፈሩ?›› ስትል በንዴት አሰበች፡፡ ‹‹አዛውንቶችን የመንከባከብ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ደግሞስ ለባህላዊው ወግ እና ለምግባቸው ማሽላ ከየት ያገኛሉ?›› ይህ አዲስ የህይወት ዘይቤ ማንንም እንደማይረዳ ሞሩ ተጠራጥራለች፡፡

ወንድ ብትሆን ኖሮ አብዛኛውን የቤት እንስሳ ወደ ኬንጋተን ገበያ በመውሰድ ትሸጥ ነበር፡፡ ኬንጋተን በኛንጋቶም ወረዳ ዋና ከተማ የሚገኝ የገበያ ቦታ ነው፡፡ እንደእርሷ ፍላጎት ባህላቸውን መጠበቅ የሚያስችል ያህል አስቀርታ ሌሎቹን በመሸጥ ቤተሰቧን በመመገብ ዳግም አትራብም ነበር፡፡ ጥቂት ወጣቶች እንስሳትን አንድ በአንድ መሸጥ ጀምረዋል፡፡ አንዳንዶቹማ ከብቶቻቸውን ወደየዘመዶቻቸው ልከው እነርሱ ከፍየሎችና በጎች ጋር ቀርተዋል፡፡ እነርሱም ብዛት ያላቸው የቀንድ ከብቶችና መንጎቻቸውን ማስተዳደርና ከፊታቸው የተደቀነውን አስከፊ ሁኔታ መጋፈጥ አስቸግሯቸዋል፡፡ ይህ የሞሩ ቤተሰብ ችግር ብቻ አይደለም፡፡ “ነገር ግን ወንድም እንኳ ቢሆን” ስትል አሰበች “አዲስ የኑሮ ዋስትና አማራጭ ለመፈለግ በጣም አስቸጋሪ ነው::”

ሁሉም የድሮ ነገር የተሻለ ነበር ማለት ግን አይደለም፡፡ እንዲያውም ላለፉት ጥቂት ዓመታት ኛንጋቶሞች ሰፋ ያለ የፖለቲካ ችሎታና ተሳትፎ ጋር የተሳሰረ የራሳቸው አካባቢዊ አስተዳደር መስርተዋል፡፡ ማህበረሰቡ የተሻለ የጤናና የትምህርት ዕድል አግኝቷል፡፡ ሞሩ ጭራሽ የሴቶች ማህበር ኃላፊ ሆናለች፡፡ ወደ ካንጋቴን በመመላለስ በምግብ እርዳታ ስርጭት ጊዜ ሴቶችን ታግዛለች፡፡

የምግብ እርዳታ- ይህ አሁን ኛንጋቶሞች የተተገኑበት ነገር ነው፡፡ ሞሩ የምግብ እርዳታውን አትወደውም፡፡ በእርዳታ መልክ የሚሰጣቸው በአካባቢው ያልተለመዱ የእህል ዓይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የእህል ዓይነቶች በእጅ ለመፍጨት አስቸጋሪ ከመሆናቸው ባሻገር ሲበሉም አይጣፍጡም፡፡ በመሆኑም ሞሩ በፍጹም አትወዳቸውም፡፡ እንደውም አንድ ቀን ባለቤቷ “ይህን ጭቃ አትስጪኝ” ሲል ቅሬታ ቢያሰማም ሌላ ልትሰጠው የምትችለው አማራጭ አልነበራትም፡፡ሞሩ የወጣትነት ጊዜዋን ታስታውሳለች፡፡ በዓላትን ትወድዳቸው ነበር፡፡ መጨፈር፣

71

መዝለልና መዝፈን ትወድ ነበር፡፡ አሁን አዛውንቶች አዝነዋል፡፡ ሥርዓታዊ ወጉን ለመፈጸምም አፍረዋል፡፡ ሌሎች አዛውንቶችን ለመጋበዝ በቂ የሆነ ማሽላ ወይም ወተት የላቸውም፡፡ የጥንቱ የልውውጥ ስርዓትና ግንኙነትም አብቅቶለታል፡፡

ሞሩን ያሳሰባት የአየር ሁኔታው መለወጥ ብቻ አይደለም፡፡ የኛንጋቶም ባሕልም እየተለወጠ መሆኑ ጭምር እንጂ፡፡ የአየር ሁኔታው ደረቃማና ለመኖር አስቸጋሪ እየሆነ ሲመጣ ማህበረሰቡ ወጉን እየጣለ አዳዲስ የሕይወት ዘይቤዎችን ለመቀበል የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

ነገ ሞሩ እንደ ገና በሕይወት ለመቆየት የምታደርገውን የዕለቱን ፍልሚያ ትጀምራለች ቤተሰቧንና ባሕሏን ለማቆየት፡፡ ነገር ግን ለጊዜው ይህን ሀሳብ ከህሊናዋ ገፋችው እና የልጇን ሰርግ ለመታደም ከጎጆዋ ወጣች፡፡

‹‹የምንለዋወጠው ምንም ነገር

የለም፡፡ የምግብ እርዳታ እደላ

ላይ ብቻ እንገናኛለን፡፡››

ከሩቅ ለመጣ እንግዳ የሞሩ ባለቤት አንድ ጊዜ የተናገረው፡፡

የምግብ እርዳታ ስርጭት

72

መንስኤያዊ ጥናት 3፡- ወጥነት ያጣ ዝናብ በምእራብ - በሳይመን ፔዝ

የአስሬ ታሪክ፡- “የተዛባና የተናጋ የአየር ሁኔታና ሕብረተሰብ መገለጫ”

በመንደሩ ውስጥ ሁሉም ‹‹ባሪያ›› ብለው ይጠሩታል፡፡ ትክክለኛ ስሙ መለስ ነው፡፡ መለስ የተወለደው በደጋዳሞት ወረዳ ዋና ከተማ ፈረስ ቤት ሲሆን አሁን አስራ አምስት ዓመቱ ነው፡፡ ቅጽል ስሙ የተሰጠውም ቤተሰቡን ለመደገፍ የተገኘውን ማንኛውንም አይነት ሥራ በመስራት ስለሚታወቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ እ.ኤ.አ ከመስከረም 2009 ጀምሮ ባሪያና ቤተሰቦቹ ጠፉ፡፡ የቅርብ ዘመዶቹን ጨምሮ ምን እንደደረሰባቸው ማንም አያውቅም፡፡ በአንድ ጀምበር አንድ ሰው ሲሰወር ይህ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ጀምሮ እንዲሁ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚ ብዙ ሰዎች ወይም ሙሉ ቤተሰብ በአጠቃላይ ይሰወራሉ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ስለ ጥንቆላ ወይም አስማት ያወራሉ፡፡ አዛውንቱ አስሬ ግን እንዲህ ያለውን ወሬ አይቀበሉትም፡፡ አስሬ መላ ሕይወታቸውን በዚሁ በጮቄ ተራራ ላይ ነው ያሳለፉት፡፡ ከአካባቢው ጋር እጅግ የተዛመዱ ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ችግሩ እየሰፋና ፈርጀ ብዙ እየሆነ መምጣቱን አስተውለዋል፡፡ እድሜያቸው በትክክል ስንት እንደሆነ ባያውቁትም የንጉስ ኃይለስላሴን በዓለ ሲመት ያስታውሳሉ፡፡ በወቅቱ ህፃን ቢሆኑም ህይወታቸው እጅግ መልካም ነበር፡፡ የፈረሰ ቤት አካባቢ በሰፊ ጫካ የተከበበ ነበር፡፡ የአስሬ አባት ምግብ አጠር ሲላቸው አደን ይወጡ ነበር፡፡ ብዙ የዱር እንሰሳት ነበሩ፡፡ የደጋው ነዋሪዎች በደቡባዊ ጎጃም ሸለቆ አቦሸማኔዎች እንደነበሩ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና አስሬ ስለ ዱር እንሰሳት ደንታ የላቸውም፡፡ የእሳቸው ፍላጎት ምንጊዜም በግ ማርባት ነው፡፡

የደጋዳሞ

ት በ

ጎች

73

የጮቄ ተራራ ገበሬዎች በግ በማርባት የታወቁ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ነዋሪዎቹ እንሰሳትን እንዴት አድርገው መያዝ እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው፡፡ የወረዳው ከተማ ፈረስ ቤት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህን ስም ሊያገኝ የቻለበትም በቂ ምክንያት አለው፡፡ በአካባቢው አሉ ከሚባሉ ጥቂት ፈረስ አርቢ ቦታዎች አንዱ በመሆኑ ነው፡፡

አዛውንቶቹ የቀድሞውን መለስ ብለው በትዝታ ሲቃኙ ባለፉት ጥቂት አስርተ ዓመታት ኑሮአቸው ትልቅ ለውጥ አስተናግዷል፡፡ በመላው አገሪቱ የህዝብ ብዛት መጨመር ያሳደረው ጫና ቤተሰቦች ቀደም ሲል ይተዳደሩበት በነበረው እንሰሳት ርቢ ብቻ መዝለቅ አልተቻላቸውም፡፡ በመጀመሪያ ቀስ በቀስ የተመናመነውን ጫካ መነጠሩ፤ በመቀጠልም ተራራውን፡፡ የእርሻ ስነ-ምህዳሩ አቅሙ የሚያወላዳ ባይሆንም አርሶአደሮቹ በዛፍ የተሸፈነውን መሬት ሁሉ ሊያለሙ ሞከሩ፡፡ አመቺ ባልሆነው የደጋማ አየር ንብረት መብቀል የቻሉት ጥቂት የሰብል ዓይነቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ዛሬ ዋነኛዎቹ የሰብል ዓይነቶች እንደ ድንች፣ ስንዴ፣ ፋባ ቢንስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በቆሎና ትሪቲካሊ ሆነዋል፡፡

መሬት ማረስ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ገበሬዎቹ በእርሻና በእንሰሳት እርባታ መካከል ያለውን ትክክለኛ ሚዛናዊ ግንኙነት ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡ በመሆኑም በሁለቱ የግብርና ስርዓቶች መካከል ያለውን ውስጣዊ ትስስር መረዳት በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ አስሬ በአጽንዖት ሲናገር ‹‹በእንሰሳት ርቢ ብቻ ልንኖር አንችልም እንዲሁም ያለእንስሳቱ መሬቱን ማልማት አይሆንም መሬቱን አርሶ ለዘር ዝግጁ ለማድረግ በሬዎች ያስፈልጉናል፡፡ የሚያመነዥኩ እንሰሳትም ድንቅ የሆነ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ይሰጣሉ›› ይላሉ፡፡ ሌላው አርሶአደር አክለውም ‹‹እንሰሳት ርቢንና እርሻን ለያይቶ ማቅረብ ትርጉም አይሰጥም እንደ አንድ ሊታይ የሚገባው ስርዓት ነው›› ይላሉ፡፡

የጥምበስ በሽታ (Blackleg Disease)

በአካባቢው ነዋሪዎች ጥምበስ ተብሎ በሚጠራው አደገኛና ትኩሳታማ በባክቴሪያ አምጭነት የሚከሰት የቀንድ ከብቶችና የበጎች በሽታ ነው፡፡ ጥምበስ በአብዛኛው የሚከስተው ክሎስትሪዲየም ቻውቮይ በሚባል የባክቴሪያ ዓይነት ነው፡፡ብዙጊዜ ባይሆንም ክሎስትሪዲየም ሴፕቲከም ወይንም ክሎስትሪዲየም ኖቪ የተባሉት ሕዋሳትም ለበሽታው መንስኤ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች በዘር መልክ በአፈር ውስጥ ለረጅም ጊዜ በህይወት መቆየት ይችላሉ፡፡ በአመዛኙ ከብቶቹ እነዚህን ህዋሳት ከሳር ጋር ወደ ሆዳቸው ያስገቧቸዋል፤ በሚያሙለጨልጨው የምግብ መፍጫ ስርዓተ አካላት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ በዚህ መልክ ባክቴሪያዎቹ በደም ዝውውር ስርዓት ውስጥ ገብተው በዋና ዋና (ብዙ ጊዜ በእግር) ጡንቻዎች ውስጥ ይከማቻሉ፡፡ በወረርሽኝ መልክ እስኪገለጥ ድረስ ያለምንም ምልክት በሰውነት ውስጥ መቀየት ይችላል፡፡ የበሽታው ወረርሽኝ በቅርብ ጊዜ የአፈር ስርዓቱ በተረበሸባቸው አካባቢዎች በሰፊው መታየቱ የአፈር መከላት የተዳፈኑትን የባክቴሪያ ዘሮች ይቀሰቅሳቸው ይሆናል የሚል ግምትን ያሳድራል፡፡ በበጎች ላይ የሚከሰተው ጥምበስ ከመቆሳሰል ጋር ይያያዛል፡፡ በህይወት የሚተርፉት እንስሳትም እጅግ ጥቂት ናቸው፡፡ በሽታው በጎቹን በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሞት ያበቃቸዋል፡፡

74

በእንሰሳት እርባታ ስርዓቱ ላይ የሚከሰተው ችግር በቀጥታ ከእህል ማምረት ስርዓቱ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ከእንሰሳት ጋር የተያያዘ ችግር ካለ ምርት ከመቀነሱ በፊት ያለው የጊዜ ጥያቄ ብቻ ነው፡፡ አስኔና ወዳጆቻቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግሩ እያደገ መምጣቱን ተመልከተዋል፡፡‹‹በሁለቱ መካከል ያለው መደጋገፍ አንድ ቦታ ሚዛኑን ስቷል፤ በተለይም የበጎች ምርት ላይ፡፡ ትልቁ ችግርም የኸው ነው››ይላሉ፡፡ በጎች ለደጋማው አካባቢ ነዋሪዎች እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በጎች እጅግም ከማይመቸው የአየር ሁኔታ ጋር የተላመዱ ናቸውና፡፡ ባለፈው አስር ዓመት ጊዜ ውስጥ አስከፊው ደዌ ብቅ አለ፡፡ጥምበስ የበግ አርቢዎችን የወደፊት እጣ ፋንታ ስጋት ላይ የጣለ ተላላፊ የሆነ ከባክቴሪያ የሚመጣ የበጎች በሽታ ነው (ሳጥኑን ይመልከቱ)፡፡

አስሬ ጥቡ በምሬት ሲናገሩ ‹‹ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጎቻችን ሲሞቱ ለማየት ተገደናል›› ይላሉ፡፡ እሳቸው ብቻም አይደሉ ዛሬ ሁሉም ስለጥምበስ በሽታ ይናገራሉ፡፡ እያንዳንዱ አርሶአደር ለዚህ በሽታ ቢያንስ አንድ ከብቱን ገብሯል፡፡ አንድ ሽማግሌ “ጥምበስ ፈጣን ገዳይ ነው፤ አንድ በግ በአንድ ወይም በሁለት ቀን ውስጥ ይገላል፡፡ አንዳንዴ የበሽታውን ምልክት የምናየው ዘግይተን ስለሆነ ሲሞቱ ከማየት በቀር ምንም ማድረግ አንችልም፡፡አንዱ ጎረቤቴ በዚህ ሳምንት ውስጥ ሁሉንም በጎቹን አጥቷል” ሲሉ በመረጃ ደግፈው ይናገራሉ፡፡

ዋና ዋና ችግሮቻቸውን በመመልከት የደጋ ዳሞት አርሶአደሮች የአየር ንብረት መለወጥ ትልቁን ሚና እንደተጫወተ ደርሰውበታል፡፡ በቅርብ የተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛናዊነትን አቃውሷል፡፡ ‹‹የአየር ሁኔታው ከሚዛናዊነት ውጭ ሆኗል›› ሲሉም አስኔ ያማርራሉ፡፡ በእርግጥ በደጋዳሞት ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ዝርዝር ከብዙዎቹ ስፍራዎች ይልቅ ዘለግ ያለ ነው፡፡ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙት ችግሮች የሚጀምሩት በዝናብ አመጣጥ ሁኔታ ላይ ነው፡፡

75

እጣፈንታው የተገላቢጦሽ የሆነ ይመስላል፡፡መምጣት በሚገባው ጊዜ ዘግይቶ ከመጣ በማያስፈልግበት ወቅት ቀደም ብሎ መውጣት/ማባራት ይገባው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ እናም በዚህ ስፍራ ለረጅም ጊዜ የሚጥለው ዝናብ በእህል ምርቱ ላይ አደገኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ እንግዲህ ክረምቱ እጅግ ረጅምና ከሐምሌ አጋማሽ እስከ ነሐሴ መጨረሻ ያለው ደግሞ እጅግ በጣም ኃይለኛ ነው፡፡

በደጋዳሞት ብዙውን ጊዜ ነጎድጓድና በረዶ አስከትሎ የሚመጣው ኃይለኛ ዝናብ ከነአስከፊ ጥፋቱ የተለመደ ሆኗል፡፡ በተለይ በነሐሴ መጨረሻ እና መስከረም መጀመሪያ እህል የማውደም አቅሙ ቀላል አይደለም፡፡ አስሬ ጥቡ በዚህ ሳቢያ የደረሰውን ጉዳት ሲገልጹ ‹‹የተዛባው የዝናብ አመጣጥ የእርሻን ስራ ከማሰተጓጎሉ ባሻገር ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ በአስከፊ ሁኔታ እህላችን በበረዶ በተደጋጋሚ ተበላሽቶብናል›› በማለት ያስረዳሉ፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በተቃራኒም ጥቂት አዎንታዊ ውጤቶችን መመልከታቸውንም አልሸሸጉም፡፡ ቀደም ሲል ነዋሪዎች የበግ ለምድ/አጎዛ ይለብሱ ነበር፡፡ ዛሬ ራሳቸው አስሬ እንኳን አንድ ይኖራቸው ይሆን? አያውቁም፡፡ ሙቀት እየጨመረ ስለመጣ ሙቀት ሰጪው የበግ ለምድ/አጎዛ አላስፈላጊ ነው፡፡ ቀድሞ የማያመርቱትን የእህል አይነት ማምረት ጀምረዋል በቆሎ የሚመረተው ቆላ በሚገኘው በደምበጫ ነበር፡፡ የበቆሎ እርሻ ከዓመት ወደ ዓመት ወደ ደጋው ሲሸጋገር እያየን ነው፡፡ ነገር ግን የሙቀቱ መጨመር አሉታዊ ውጤትም እያሳየ ነው፡፡ ሞቃታማ ንፋስ ለደጋዳሞት አዲስ ክስተት ነው፡፡ ይህ ንፋስ በበጋ ወቅት የውሀ ትነትን ያፋጥናል፡፡ በመጨረሻም ዕጽዋቶችን በማድረቅ ፍሬያማነትን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈረሰ ቤት በስተደቡብ ድንጋይ በር በምትባል መንደር የወባ በሽታ ዜና ተሰማ፡፡ የደጋዳሞት ነዋሪዎች ይህ በሽታ ሲያጋጥማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ስለሆነ በወቅቱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ምንም አይነት

አስሬ በቁጭት ‹‹ባልጠበቅነው መንገድ የዝናቡ ሁኔታ ተቀየረ፡፡ ከሃያ ዓመታት በፊት በዝናቡ ላይ እንተማመን ነበር፡፡ የበልግ ወራት ጥቂት የዝናብ ቀናትን በየካቲትና በሚያዝያ ወር መካከል ያመጣልንና ክረምቱ ደግሞ በትክክል በሰኔ ወር አጋማሽ ይጀምራል፡፡ ዛሬ መሬታችንን አዘጋጅተን የዝናብን መምጣት በከንቱ እንጠባበቃለን›› ይላሉ፡፡

ፈረስ ቤት አካባቢ የበረዶ ማዕበል ከወረደ በኋላ

76

ግንዛቤ አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም አስሬ በአጭሩ ‹‹በተወሰነ ደረጃ የሙቀቱ መጨመር ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ከፍ እያለ እንዳይሄድና አሉታዊ ተጽዕኖው ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን እንፈራለን” ሲሉ ያጠቃልላሉ፡፡ ‹‹በግ አርቢዎች በጥመበስ በሽታና በአየር ንብረት ለውጥ መካከል ያለውን ግንኙነት ለይተው አውቀዋል፡፡ ‹‹በደረቅ ወራት ቁጥሩ እንደሚያሻቅብ ደርሰንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ ጥቂት መኖ ብቻ ስለሚኖር በጎቹ ደካማ ይሆናሉ፤ ለበሽታም ይጋለጣሉ፡፡ ለረጅም ጊዜ በሚዘልቅ ድርቅ፣የምግብ እጥረትና በጥመበስ መዛመት መካከል ግንኙነት እንዳለ ገምተናል፡፡” ‹‹በተጨማሪም በሚሞቱት በጎችና በአየር ንብረት ለውጡ መካከል ሌላም ተጽኖአዊ ግንኙነት አለ፡፡

በደጋዳሞት ወጥነት በሌለው ዝናብ ሳቢያ በተፈጠረ የመሬት መከላትና በነፋስ የመሬት መጠረግ በመከሰቱ የለም አፈር መሸርሸር ሁኔታው እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ ከአካባቢው የግብርና ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ከወረዳው ጠቅላላ ስፋት 60 በመቶ የሚሆነው መሬት ለምነቱን አጥቷል፡፡ በአካባቢው ለተከሰተው የአፈር ለምነት መመናመን መንስኤ ተብለው የሚጠቀሱትም የሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ማለትም ጫካን መመንጠር፣ ያለማሰለስ ማረስ እና የተፈጥሮ ሁኔታ መለዋወጥ ማለትም በከባድ ዝናብ፣ ነፋስ፣ ወዘተ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ምክንያትነት የተከሰተው ወጥነት የሌለው ኃይለኛ ዝናብ ለለም አፈሩ

የአፈር መሸርሸር ለጥምበስ መከሰት ምቹ ሁኔታ እንደሆነ ይገመታል

የተራዘመ የደረቅ ወቅትተጠቂነት/ተጋላጭነት

ከፍተኛ የመሬት ከፍታውሱን እድገት

ጥምበስ (በባክቴሪያ የሚመጣ የበግ በሽታ)

በእንሰሳት ርቢ ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት

አነስተኛ በልግ

የክረምት መዘግየት/ መዛባት

ውርጭ እና በረዶ

የምርት መቀነስ የመኖ ማነስ

በበሽታዎች በቀላሉ

የበጎች መሞት

ድህነት ብድር

ማህበራዊ ትራንስፎርሜሽንና

ፍልሰት

ጭብጥ/እሳቤ፡ በፕሮፌሰር ዛቢን ትሮጀር

የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች

77

መሸርሸር ሌላው መንስኤ ነው፡፡ እናም በተጨማሪም የአፈሩ መጎሳቆል የጥመበስ በሽታ ተሸካሚ ህዋስን አነቃቅቶታል፡፡

ጥምበስ በማህበራዊ ስርዓቱ ላይ ጭምር ከፍተኛ የሆነ መሰረታዊ ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) አምጥቷል፡፡ እየጨመረ በመጣው በጥምበስ ችግር ምክንያት ብዙ ቤተሰቦች የገንዘብ ችግር ሥጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ጥሩ ተቋማዊ የደህንነት መረብ (ሴፍቲኔት) ተመስርቶ ስለነበር መጀመሪያ ላይ ጉዳዩ እንደ ትልቅ ችግር አልታየም ነበር፡፡ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም አርሶአደሮች በግ መግዛት እንዲችሉ ብድር ለመስጠት ዝግጁ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የጥምበስ አምጪ ባክቴሪያ ሳይታይ ለዓመታት በአፈር ውስጥ በህይወት መቆየት ይችላል፡፡ ስለዚህ የአዳዲሶቹ በጎች በደዌው መጠቃት የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነበር፡፡ብዙዎቹ ሊረሱት በማይችሉት አንድ ቀን ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የወሰደውን ገንዘብ መመለስ ያልቻለ የአካባቢው አርሶአደር በፖሊስ ተያዘ፡፡ አርሶአደሮቹም ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ብድር በመውሰዳቸው በራሳቸው ላይ ያመጡት አደጋ ታወቃቸው፡ አደጋውን ለመቀነስም ጓደኛሞችና ጎረቤታሞች የቁጠባ ቡድን መሰረቱ፡፡ ስምንት እየሆኑ በአንድ የቁጠባ ቡዱን ተደራጁ፡፡ አንድ ቤተሰብ ብድሩን መክፈል ካቃተው ቡድኑ ይከፍላል፡፡ በየቡድኑ ውስጥ የእኩያሞች ሕብረት ጫና ወዲያው እያየለ መጣና ቡድኖቹን ከንቱ አደረጋቸው፡፡ መጨቃጨቅ የተለመደ ሆነ፤ጓደኛሞችም ወደ ባላንጣነት ተለወጡ፡፡አስሬ ጥቡ ይህ ለውጥ አስግቷቸዋል፡፡ ‹‹በዚህ ለውጥ ምከንያት እያንዳንዱ ደሀ ሆነ፤ ቀድሞ ማህበረሰቡ ይረዳዳ ነበር፡፡ ዛሬ ሁሉም ደሀ ስለሆነ መደጋገፍ ቀርቷል›› ይላሉ፡፡

በመለስ ቤተሰብም ላይ ተመሳሳይ ነገር ደርሶበታል፡፡ የበግ መንጎቻቸውን እስካጡባት ዕለት ድረስ የተሳካላቸው በግ አርቢዎች ነበሩ፡፡ ቤተሰቡም በመልካም አቋም ላይ የሚገኝ ሲሆን ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ በመቻላቸው የመለስ አባት ይኮሩ ነበር፡፡ በአንድ ጀምበር ግን ከአስራ ሰባቱ በጎቻቸው አስራ አራቱን አጡ፡፡ ከዚህ በኋላ ለትምህርት ቤት የሚሆን ገንዘብም ጠፋ፡፡ መለስ ቤተሰቡን ለመርዳት ብሎ ትምህርቱን ሲያቋርጥና ስራ ሲጀምር የአስራ ሶስት ዓመት ልጅ ነበር፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ባሪያው እየተባለ ይጠራ ጀመር፡፡

የመለስ ቤተሰብ ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ብድር ወስደው አባትየው እንደገና በግ የማርባት ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በመልካም ሁኔታ መከናወን የጀመረም መሰለ፡፡ እቅዱም ከፍተኛ የክርስቲያን በዓል በሆነውና እያንዳንዱ ቤተሰብ ለክብረበዓሉ በግ ስለሚያስፈልገው የበግ ዋጋ በሚንርበት በመስቀል በዓል ወቅት በጎቹን ለመሸጥ ነበር፡፡ ከሽያጩም እዳቸውን ለመክፈል አስበው ነበር፡፡

78

ታዲያ መለስ በየዕለቱ እንደሚያደርገው መስቀል ከመድረሱ ጥቂት ቀናት በፊት አንድ ምሽት ላይ በጎቹን ሰብስቦ ሲያጉር ሁሉም ነገር ሰላም ነበር፤ የተለየ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ በማግስቱ ግን አምስቱ ሞተዋል፡፡ በቀጣዩ ቀን ሶስቱ ተደገሙ፡፡ ቤተሰቡ ከሁለት በጎችና ከክምር እዳው ጋር ቀረ፡፡ መለስ ቀሪዎቹን ሁለት በጎች ገበያ ወስዶ ሸጣቸውና አመሻሹ ላይ ቤታቸውንና ማህበረሰቡን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጥለው ኮበለሉ፡፡

ምርጫው በመታሰርና በመሰደድ መካከል ያለ ምርጫ ነበር፡፡ ላንዳንዶች የመለስ ውሳኔ ቀላል ይመስላቸዋል፡፡ ለአስሬ ጥቡ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የማህበሩ አዛውንት፣ አቶ አስሬ ስለሁኔታው ሲናገሩ ድምጻቸው ተስፋ የመቁረጥና የማዘን ስሜታቸውን ያሳብቅባቸዋል፡፡

‹‹የአየሩ ፀባዩ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰባችንም ሚዛኑን አጥቷል፤ ከእነዚህ ጫናዎች

የተነሳ ማንም ቀዬውን እርግፍ አድርጎ ሊሄድ አይገባም፡፡

ሰዎች እንደዛፍ ናቸው፡፡ መሬታችን ላይ ስር ሰደናል ማንም ስሩን ወይንም ስሯን

ማጣት የለበትም፡፡››

መንስኤያዊ ጥናት 4 - ከልማድ መላቀቅ - የራያ አዘቦ ጨው ነጋዴዎች በአዲስ ጎዳና መጓዝ አለባቸው በክርስቲያን ሰፍሪን

በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሚገኘው አርሶአደር ብርሃኑ መንገሻ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከስድስት ግመሎቹ ሶሰቱን አጥቷል፡፡ ተስፋ በቆረጠ አነጋገር ‹‹ምርቱ ውጤታማ ስላልሆነ እንሰሳቱን በደንብ ለመቀለብ አልቻልንም›› ይላል፡፡ ብርሃኑ የሚኖርባት በራያና አዘቦ ወረዳ ውስጥ የምትገኘው መሆኒ ቀበሌ ላለፉት አስር ዓመታት ዝናብ በተገቢው ሁኔታ ባለመዝነቡ ለተከታታይ አስከፊ ድርቅ ተጋልጣለች፡፡

ድሮ በዓመት ሁለቴ ያመርቱ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በዓመት አንዴ ብቻ ሆኗል፡፡ቀድሞ የነበረው የዝናብ አመጣጥ ተቀይሯል፡፡ ክረምት የሚጀምረው ዘግይቶ ነው፡፡ ከድሮው ጋር ሲነፃፀር ዶፍ የሚዘንብበት አጋጣሚ በጣም ጨምሯል፡፡ የውሀ መገኘት ሁኔታም እንዲሁ ተለውጧል፡፡ በመደበኛው አካሄድ አርሶአደሮች በየዓመቱ ሁለት ቶን እህል ያመርቱ ነበር፡፡ ይህም ቤተሰባቸውንና የቤት እንሰሳቱን መግቦ ጎተራቸውን ይሞላ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እ.ኤ.አ በ2009 አብዛኛው አርሶአደር ደረቃማው የበጋ ወቅትን ለማሳለፍ የማይችል ከመቶ ኪሎ ግራም ያነሰ እህል ነው ያመረቱት፡፡

79

የራያና አዘቦ ወረዳ የሚገኘው በምስራቅ አፍሪካ ታላቁ ስምጥ ሸለቆ ጫፍ ከባህር ጠለል በላይ በ1700 ሜትር ከፍታ ላይ ነው፡፡ በወረዳው ያሉት ትናንሽ መንደሮችና ከተሞች የሚገኙት ለጥ ባለው እና 3000 ሜትር ከፍታ ባላቸው ደጋማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተከበበው አምባ ላይ ነው፡፡ የአካባቢው ሁኔታ ለግብርና ስራ ምቹ ነው፡፡ ከደጋማ አካባቢዎች የሚፈሱት ወንዞች ለጥሩ የአፈር እርጥበትና ለምነት ተፈላጊ የሆኑትን በቂ ውሀ እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ያመጡለታል፡፡

የምርቱ ሁኔታ ምንጊዜም ተለዋዋጭ ነውና የዚህ አካባቢ አርሶአደሮች መተዳደሪያ በግብርና ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም፡፡

ለጥቂት የመንደሩ ነዋሪዎች ጨው አስፈላጊ የገቢ ምንጭ ነው፡፡ ብርሃኑ መንገሻን ያገኘሁት በመንደሩ ከሚኖሩ አርሶአደሮች ጋር ሲወያይ ነው፡፡ ሁሉም የጨው ነጋዴዎች ናቸው፡፡

ራያና አዘቦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የጨው አቅርቦት ዋንኛ ምንጭ ከሆነው በሰሜናዊ ምስራቅ አፋር ከሚገኘው የጨው ሀይቅ በእንሰሳት የሁለት ሳምንት ጉዞ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ በርካታ ትውልዶችን ላስቆጠረ ዘመን የግመል ባለቤት የሆኑት ራያዎች ግመሎቻቸውን ይዘው ወደ በረሀ በመውረድ በመቀሌ ከተማ ለሚገኘው ዋናው ገበያ ጨው ያቀርባሉ፡፡ሥራው አስቸጋሪ ነገር ግን የሰብል ምርት ገቢንና የገበሬውን ሕይወት ለማጠናከር ትርፋማ አማራጭ ነበር፡፡ ዛሬ ብርሃኑና ጓደኞቹ ወደ ጨው ሀይቅ ስለሚደረገው ቀጣዩ ጉዞ እየተወያዩ ነው፡፡ ብዙዎች ተስፋ ቆርጠዋልና ለመጓዝ አይዳዳቸውም፡፡ እንደ ብርሀኑ ሁሉ ሌሎቹም በድርቅ ምክንያት ግመሎቻቸውን አጥተዋል፡፡ ከዚያም በላይ ሰዎቹም ሆኑ እንስሶቹ ደካክመዋል ወይም ድካም የተሰማቸው መስለዋል፡፡

ጉዞው በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል በኤርትራ ድንበር አጠገብ ወደሚገኘውና አስቸጋሪ አካባቢያዊ ሁኔታ ወዳለው ደንከል በረሀ ይወስዳቸዋል፡፡ በዚያ የሶስት ሚሊዮን ዓመታት ጂኦሎጂካዊ ክንዋኔ በፕላኔታችን ላይ ልዩ የሆነ መልክአ ምድር ፈጥሯል፡፡ በአንዳንድ የምድር ረባዳማ ስፍራዎች ቅድመ ውቅያኖሶች ደርቀው አሁን

የእርሻ ማሳ

80

ያለውን ቅሪታቸውን ከበስተኋላቸው ትተው አልፈዋል፡፡ የአሰሌ ሀይቅ በአሁኑ ጊዜ ግግር ጨው (አሞሌ) በሰው ኃይል እየተቆፈረና ከጨው ቋጥኝ ላይ እየተቀረፈ ወደ ግዙፍ የአገሪቱ ገበያ የሚጓጓዝበት ብቸኛው ስፍራ ነው፡፡

ሌሎቹን ተጓዦች መጠባበቅ የጨው ቁፋሮ በደናክል

አካባቢው ከመኪና መንገድ በጣም የራቀ ስለሆነ በሺህ የሚቆጠሩ ግመሎች በየቀኑ ጨው ተጭነው ለሶስት ተከታታይ ቀናት በመጓዝ በረሀውን አቋርጠው ወደ ትልቁ ቤራኤሌ ከተማ ይደርሳሉ፡፡ ጨዉ ከዚህ በመኪና እየተጫነ ወደ ከተሞች ይወሰዳል፡፡የራያና አዘቦ አርሶአደሮች ይህን ከባድ ልፋት መታገስ አይፈልጉም፡፡ በቤታቸው ያለው የምግብ ክምችት ለዓመታት በተከሰተው ድርቅ እያሽቆለቆለ ስለመጣ የሚመገቡት በቀን አንድ ጊዜ እንጀራ ብቻ ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ በእርግጠኝነት አስቸጋሪውን ጉዞ ለማድረግ በቂ አይደለም፡፡ በዓመት ውስጥ ይህን ጉዞ ብዙ ጊዜ ያደርግ የነበረው አርአያ ተስፋይ ‹‹በርሀብ መሞትን እፈራለሁ›› ሲል ነግሮኛል፡፡ ሀብታም አርሶአደሮች ሳይቀሩ የጨው ንግድን መጠራጠር ጀምረዋል፡፡ የትርፉ ዝቅተኝነት ስራው ብዙዎችን እንዳይስብ አድርጎታል፡፡ እጅግ ብዙ ግመሎች ሞተዋል፡፡ እናም የግመሎቹ ብዛት ባነሰ ቁጥር ሊያጓጉዙ የሚችሉት አነስተኛ ጨው ይሆናል፡፡ ይህም ትርፉን ጥቂት ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም የመንገድ ግንባታና የመኪና መበራከት ልማዳዊው በግመል የማጓጓዝ ስራ ጊዜው እንዲያልፍበትና የጨው ዋጋም እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡

“ትርፍ የማናገኝበት ከሆነ ይህን ማድረግ ለምን እንቀጥላለን?” ሲሉ አርሶአደሮች ራሳቸውን ይጠይቃሉ:: አርሶአደሮቹ የራሳቸውንና የእንሰሶቻቸውን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡ በዚህም ሳቢያ የመጨረሻ የሕይወት ዋስትናቸው ማክተሙን ይረዳሉ፡፡የተፈጠረውን ሁኔታ ለመጋፈጥ ማህበረሰቡ አማራጭ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን ምን አማራጭ አለ? በዚህ ጊዜ በግብርናው ላይ ያለው ጫናም አሻቅቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2050 የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በእጥፍ አድጎ 160 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ ግብርናው ይህን ሁሉ የህዝብ ቁጥር በፍጹም ሊሸከም አይችልም፡፡

81

አሁን ነዋሪዎቹ ለችግሮቻቸው ዘላቂ መፍትሔ ማየት አልቻሉም፡፡ ብዙዎቹ አርሶአደሮች ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው ልማዳቸው መለያየታቸው ይጸጽታቸዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ቅፍለት (ጨው ከበረሃ በግመል ማጓጓዝ) የማይቻል ነው፡፡ ከመንግስት እርዳታ እየጠበቁ ነው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ በምግብ እርዳታው በቂነትና በስርጭቱ ፍትሀዊነት ላይ ቢያማርሩም እንደ ሴፍቲኔት ያሉት የምግብ ለስራ ፕሮግራሞች ተጨማሪ እርዳታ በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ ብርሃኑ የኑሮ ትግሉን መቀጠል መፈለጉ ግልጽ ነው፡፡ ‹‹ሁሉም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፤ እናም የተሻለ ቀን እንደገና ያመጣልናል›› አለ ፈገግ እያለ፡፡

የብርሀኑን ጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት አንዳንድ አርሶአደሮች ግመሎቻቸውን አምጥተው ለብርሃኑ ይሰጡታል፡፡ እርሱም ግመሎቹን ይዞ እንደገና ይጓዛል እንደገና ይሞክራል፡፡ ለእርሱ ተጨማሪ ገንዘብ ለማገኘት መልካም አጋጣሚ ነው ምክንያቱም ከትርፋቸው የተወሰነ መቶኛ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ ያጋሩታልና፡፡

ከአርሶአደሮቹ መካከል የብርሃኑ ቁርጠኝነት ለየት ያለ ነው፡፡ በአጠቃላይ ተስፋ መቁረጥና የረዳት አልባነት ስሜት ተንስራፍቷል፡፡ ባለፉት ዓመታት የተተገበሩት ብዙዎቹ የልማት እርምጃዎች ፍሬአልባ ሆነዋል፡፡ ስለዚህ አርሶአደሮቹ በልማዳዊው አካሄድና በዘመናዊነት መካከል ተወጥረዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀው የጨው ንግድ በአሁኑ ጊዜ እንደማያዋጣ ግልጽ ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ የጨው ንግዱ ስራ አሁንም ማንነታቸውንና ማህበራዊ ስፍራቸውን እየቀረጸ ይገኛል፡፡ የጨው ንግዱ ከከዳቸው ማህበራዊ መረጋጋት ይናጋል፡፡ ሀዘንና መከፋት በማህበረሰቡ ህይወት ላይ ይሰፍናል፡፡ እነኚህ ማንነቶች ከተዳከሙ ዘመናዊ እድገትን ተግባራዊ ማድረግም ያዳግታል፡፡

ሀይማኖትም የአርሶአደሮቹ አስተሳሰብ መነሻ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ቄሶቹ የወቅቱን ቀውስ አርሶአደሮቹ ለእግዚያብሔር ማደርን ስለቀነሱና መጽሐፍ ቅዱሳዊ በዓላትን ስለሻሩ ከእግዚአብሔር የመጣ ቅጣት እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ እነዚህም ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ ተስፋ በማድረግ ወደ ሀይማኖት መመለስን እንደመፍትሄ ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ሀይማኖት አርሶአደሮቹ ከያዙት አዲስ አሰራር ጋር የተለያየ ነው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ ለመጣው አዲስ አካሄድ ሊሰጡት የተገባውን ትኩረት ይከለክላል፡፡

በመሆኒ መንደር ከሚገኙት የግብርና ባለሙያዎች አንዱ የሆነው መለስ በርሄ በአርሶአደሮቹ ቁርጠኝነት ማጣት ላይ ቅሬታ አለው፡፡ ‹‹በማህበረሰቡ ውስጥ የተተገበረው የመልሶ ማልማት አብዛኛው ጥረት ከሽፏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አርሶአደሮቹ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር ስለገጠማቸው በልማት እርምጃዎቻችን ውስጥ በተገቢው ሁኔታ አይሳተፉም” ሲል ይናገራል፡፡ ችግኞችን ከመድረቅ ለማዳን በተከለለውና የአፈር መከላትን ለመከላከል ተብሎ ተራራው ላይ ወደ ተተከሉት ዕጽዋት ከብቶቻቸውን በዘፈቀደ ያሰማራሉ፡፡ አብዛኛው

82

ያለፈው ዓመት የልማት ሥራዎች ወድመዋል፡፡ በተራራው ግርጌ ያሉት የእርሻ ማሳዎች ከተራራው በሚወርደው ጎርፍ ለምነታቸውን እያጡና ዋጋ ቢስ እየሆኑ ስለሆነ ደኑን መልሶ ማልማት ለአካባቢው አስፈላጊ እርምጃ ነው፡፡

ሀይማኖት፣ ረሀብና በአርባ ቀን እድል ማመን ለገበሬው ግንዛቤ እንዲህ መሆን ምክንያት ሆነዋል፡፡ መለስ ግን ወደ ፊት የሚያስኬድ መንገድ እንዳለ ያምናል፡፡ እንደርሱ አመለካከት ማህበረሰቡ ሊከተለው የሚገባ ሞዴል ያስፈልገዋል፡፡ የተሻሻለ ግብርናን ተግባራዊ ማድረግ የሚያውቁ ጥቂት አርአያ መሆን የሚችሉ አርሶአደሮች የግብርና ቢሮ ሀሳብን ተግባራዊ በማድረግ በደንብ ተሳክቶላቸዋል፡፡ “ሌሎችም ደግሞ ፈጣን አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት መጀመራቸውን እያየን ነው” ይላል መለስ፡፡

አቶ አባዲ የአዲሱ አስተሳሰብ አንዱ ተግባሪ ነው፡፡ የዛሬ አስር ዓመት በከፋ ሁኔታ ላይ የነበረውን የአባቱን መሬት ተረከበ፡፡ ከእኔ ጋር ከመገናኘቱ ጥቂት ሳምንታት ቀድሞ የጨረሰው ባለቆርቆሮ ክዳን ቤት ኩሩ ባለቤት ሆኗል፡፡ ‹‹ያለፉት ዓመታት ቀላል አልነበሩም›› አለ ሲያወጋኝ “ነገር ግን አንዳንድ ለውጦችን በማድረግ ጥቂት ገንዘብ ማጠራቀም ቻልኩ፤ ሶስት የንብ ቀፎዎች አሉኝ፡፡ ማሩን ገበያ ለማውጣት ለምግብ ወይም ለሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች የሚሆነኝን ገንዘብ አገኛለሁ፡፡” አባዲ ከቤቱ ጓሮ የሚገኘውን መሬት በመጠቀም እድገት ማምጣት የሚያስችለውን በግብርና ቢሮ የተሰጠውን ስልጠና ከሁለት ዓመት በፊት ወስዶ አመርቂ ውጤት አምጥቷል፡፡

ሁሉንም ያማከሉ የግብርና አማራጮች ለአርሶአደሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው!

መንስኤያዊ ጥናት 5፡ ወደፊት በቂ ውሃ ይኖር ይሆን? በአንድሬ ቴየሌ

ተወልደ ወደ ጠባቧ ግቢው ሲገባ አሁንም የማለዳው ቅዝቃዜ እንዳለ ነው፡፡ ሚስቱ ሀይማኖት እና ሁለቱ ልጆቻቸው እንዳደረጉት ከትንሿ የፕላስቲክ ማስታጠቢያ ውስጥ ከሚገኘው ውሃ ጥቂት ወስዶ ታጠበ፡፡ ዛሬ ማለዳ አንድ እፍኝ ውሀ ለእጁና ለሰውነቱ በቂ ነው፡፡ ውሀ በእጅጉ ውስን በሆነበት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሚገኘው ገጠራማ የትግራይ ክልል የእጅና ገላ መታጠቢያ ውሀን ቤተሰቡ የሚያውቀው በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ ነው፡፡ መደባይ ዛና ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በግምት 600 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አካባቢ ትገኛለች፡፡ እዚህ በሌሎች በርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደሆነው ሁሉ ለሳምንታት ዝናብ አልዘነበም፡፡ አሁን የጥቅምት አጋማሽ ነው፣ የአጨዳ ጊዜ አልፏል፡፡ ነገር ግን ተወልደ በእርሻው ላይ ያለውን አዝርዕት ጥቂት ዘግየት ብሎ ለማጨድ አስቧል፡፡“እስካሁን ፍሬው ሙሉ ለሙሉ አልደረሰም” አለ፡፡ በማከልም “ምናልባት በእግዚአብሔር

83

ፈቃድ በሚቀጥሉት ቀናት ጥቂት ዝናብ እናገኝ ይሆናል:: በእርግጥ መቼ እንደሚዘንብና መቼ እንደማይዘንብ አናውቅም” አለ፡፡ ብዙሀኑም ሆነ ሌሎች በአካባቢው ያሉ አርሶአደሮችም እንዲህ ነው የሚያስቡት፡፡ ‹‹ዝናቡ በፈለገው ጊዜ መምጣቱና መሄዱ ብቻ አይደለም›› ይላል ተወልደ ‹‹ከዚያም በላይ በአለፉት ዓመታት የዝናቡ መጠንም እያነሰ እየቀነሰ ነው የመጣው፡፡ ከአስር ዓመታት በፊት ገበሬው ከግንቦት እስከ መስከረም ባለው የዝናብ ወራት ይተማመን ነበር፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን የዝናቡ ወቅት ማጠሩ ግልጽ ሆነ፡፡ ዛሬ ገበሬው ከሰኔ እስከ ነሐሴ ባለው የዝናብ ጊዜ ውስጥ ለማምረት እንዲችል ራሱን ማሰተካከል አለበት፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ ዝናብ አለ ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ አብዛኛዎቹን ሰብሎች ለማዝመር ደግሞ የዝናቡ ጊዜ እጅግ አጭር ነው፡፡

“ለዓመታት ሙቀቱ እየጨመረ እየጨመረ መጥቷል›› አለ ተወልደ ወደ እርሻው ስንሄድ ከፊታችን ያለውን ወንዝ እያሳየን፡፡ “ቀደም ባሉት ጊዜያት ቢያንስ ጥቂቶቻችን ዝናብ በቂ ባልሆነ ጊዜ ሰብሎቹ እስኪደርሱ ድረስ ወንዙን በመጥለፍ እርሻችንን እናጠጣ ነበር፤ ዛሬ ግን ይህ የማይቻል ነው፡፡”

‹‹ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በጣም ሞቃት ስለነበር ወንዙ በሚያዝያና ግንቦት ፈጽሞ ይደርቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ ከሙቀቱ ማየል የተነሳ በቤታችን ውስጥ እንኳን መቀመጥ አልቻልንም፡፡›› እንደማንኛውም የትግራይ አርሶአደር ተወልደ መጀመሪያ የሚዘራው ጤፍ ነው፡፡ ሲናገርም ‹‹ከዓመታት በፊት እኔም የመስኖ ቦይ ገነባሁ፤ የወንዙ መጠንም መልካም ነበር፡፡ የእርሻ ማሳዬን ጭምር በወንዙ ውሃ አጠጣ ነበር፡፡ ዛሬ ይህም አልተቻለም” ይላል፡፡ ለተወልደ ድርቅ ማለት አብዛኛውን ጊዜ ርሀብ መሆኑ በዓመታት ውስጥ የተለመደ ሆኗል፡፡ ‹‹ቤተሰቤና እኔ የምንመገበው ከቀድሞው ያነሰ ነው፡፡ የአሁኑ አዝመራ ምርት ካልያዘልን ያለን አማራጭ በክልሉ ያሉ ብዙዎች እንደሚያደርጉት ከውጭ የሚመጣ የምግብ እርዳታን ተስፋ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ እርሻቸው በዝናብ ላይ እንደተመሰረተውና የወንዝ ውሃ በቀላሉ እንደማያገኙት ሌሎች አርሶአደሮች ሁሉ ተወልደ ለውሀ ማቆር የሚሆን ጉድጓድ ቆፍሯል፡፡ ‹‹ከበፊቱ ይልቅ አብዛኛው አርሶአደር የውሀ ማጠራቀሚያ ኩሬ ቆፍሮ ይጠባበቃል፡፡ ነገር ግን የውሀ ማቆሪያ ጉድጓዱ በቂ ዝናብ ከሌለ ምን እናደርግበታለን?›› ሲል ተወልደ ይጠይቃል፡፡

‹‹ዝናብ ቢዘንብም እንኳን ውሀው በፍጥነት ይሰርጋል፡፡የቀረውም ጥቂት ውሀ ከሙቀቱ የተነሳ ይተናል፤ ጉድጓዱን የምሸፍንበት ፕላስቲክ ሸራ ለመግዛት ደግሞ አቅም የለኝም፡፡››

84

የፈራረሰ የውሃ ጉድጓድ

የጎርፍ ውሃን ማስቀረት፣ የመሬት መከላት

‹‹ቀደም ሲል ስለተቆፈሩት የውሀ ጉድጓዶች ተመሳሳይ ነገር ማለት ይቻላል፡፡ እሰካሁን ውሀ የሚሰጡት

በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው፡፡››

ከዝናብ መጥፋት ወይም እጥረት ሳቢያ የከርሰምድር ውሃው ጠለል/ ከፍታ ቀንሷል፡፡ እንደገና አስተማማኝ ውሃ ለማግኘት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ያስፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን አሁንም ዋናው ችግር ገንዘብ ነው፡፡ “እንዲህ አይነት ጉድጓድ ለመቆፈር ገንዘብም ሆነ ቴክኖሎጂው የለንም›› ይላል ተወልደ፡፡ ‹‹ውሀ ለማጠጣት እንጠቀምባቸው የነበሩ አሮጌዎቹ ጉድጓዶች ቀስ በቀስ ፈራርሰዋል፤ ምንም ማድረግ አንችልም››፡፡

በፍጥነት እየቀነሰ የሚሄደውን የከርሰ ምድር ውሀ ለማሻሻል የወረዳው የአፈርና የውሀ ጥበቃ ክፍል እርምጃ ወስዷል፡፡ ውሀ በብዛት በሚጎርፍበት ገደላማ አካባቢዎች ላይ ስፋታቸው በግምት ሁለት ሜትር ጥልቀታቸው በአማካኝ ግማሽ ሜትር የሆነ ባለአራት ማዕዘን ጉድጓዶች በመቆፈር በፍጥነት የሚያልፈውን ውሀ በመቀበል ወደ ምድር እንዲሰርግ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡

ነገር ግን ይህን ቴክኖሎጂ በትርፋማነት ለመጠቀም ዝናብ በበቂ መጠን መዝነብ አለበት፡፡እንደ ኢትዮጵያ ባሉ 90 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ባላቸው ሀገሮች ውሀ ህዝብን ለመመገብ የሚጫወተው ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡ በግምት 85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የገጠር ነዋሪና ከግብርና ምርት ስርዓት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ነገር ግን ከሚታረሰው መሬት ውስጥ የመስኖ ተጠቃሚ የሆነው ከአምስት እስከ ሰባት በመቶ ብቻ ነው፡፡ ችግሩ የውሀ እጥረት ቢሆንም ያለውም ቢሆን በአግባቡ ጥቅም ላይ አይውልም፡፡

‹‹በሌላ በኩል ድንገተኛ ዝናብ ደግሞ አፈራችንን ጠራርጎ ይወስደዋል፡፡ በእውነት ክፉ ነው!

መሬቱ ተጎሳቁሎ አፈሩ ከጥቅም ውጭ እየሆነ በቀላሉ ከማሳችን ላይ ተጠራርጎ ይሄዳል፡፡

85

ባህላዊ የድንጋይ ካብ/መደብ/

በተጨማሪም የውርስ ሕጉ የኢትዮጵያን አርሶአደሮች እንቅልፍ አሳጥቷል፡፡ አንድ ቀን ተወልደም ሶስት ሄክታር መሬቱን ለልጆቹ ለአሰፋና ለኃይለመስቀል እኩል ያካፍላል፡፡ ቤተሰቡ አንድ ሄክታር ተኩል የሚሆን የእርሻ መሬት ብቻ ይዞ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የግብርና ምርት ውስን ኑሮ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በቋሚነት ማዳበሪያን መጠቀምና በመስኖ እርሻን ማልማት ከቀድሞ ይልቅ በጣም አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል፡፡ መሬትን እዳሪ አድርጎ ማቆየት አይታሰብም፡፡ የመደባይ ዛና ማዳበሪያ ፍጆታ ብዛት በአገሪቱ ካለው አማካይ ፍጆታ 50 በመቶ ይልቃል፡፡ በተመሳሳይ የዚህ አካባቢ አርሶአደሮች በአማካይ ከየትኛውም የኢትዮጵያ አርሶአደር በላይ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ይጠቀማሉ፡፡ የዋጋው ከፍተኛነት ደግሞ በገበሬው የአኗኗር ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖውን አሳርፎበታል፡፡

“አንድ ልከኛ አርሶአደር የምርት ውጤቱ ሳይዛባ ባለበት እንዲቀጥል ለማድረግ የሚፈልገው የማዳበሪያ መጠን በአሁኑ ሁኔታ ከአቅም በላይ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ለሚቀጥለው ዓመት የሚሆን ማዳበሪያ ለመግዛት ካለችን ምርት ላይ ከፊሉን ሸጠናል፡፡ የማዳበሪያ ዋጋ ደግሞ ከዓመት ዓመት እያሻቀበ ነው›› ይላል ተወልደ፡፡ እሱ በግሉ የእርሻውን ድንበር ድንጋይ በመካብ አስከፊውን የአፈር መከላት ለመከላከል እየጣረ ነው፡፡ የጠብታ መስኖ መሳሪያና ምርጥ ዘር በብቃት እንድናመርት ይረዱን ነበር፡፡ ነገር ግን ለዚህ ቴክኖሎጂ የሚሆን ገንዘብ የለንም፤ በቂ መያዣ ካላቀረብክ በእርግጠኝነት ማንም ብድር አይሰጥህም፡፡ ለዚህ ሁኔታ መነሻም በህጉ ማዕቀፍ ውስጥ ሳይገኝ አይቀርም፡- ለልጆቻቸው የሚያስተላልፉት የእርሻ መሬት እንደ እውነቱ ከሆነ የራሳቸው አይደለም፡፡መሬቱ ለምንም ጠቀሜታ ይዋል የመሬቱ እውነተኛ ባለቤት የኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡ ገበሬው መሬቱን መጠቀም ይችላል፤ ነገር ግን ብድር ለማግኘት መሬቱን እንደመያዣ ማቅረብ አይችልም፡፡ የመኖሪያና ቤቱና ያሉት ቁሳቁሶች ደግሞ ለመያዣነት የሚበቃ ዋጋ ኖሯቸው ብድር ሊያስገኙለት አይችሉም፡፡

በኢትዮጵያ የግብርና ምርት ውስጥ በጠብታ መስኖ ማልማት ሙሉ በሙሉ ፀንቶ እስኪተዋወቅ ድረስ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም፡፡ እስከዚያ የትግራይ አርሶአደር እርዳታን ከማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት) ተስፋ በማድረግ ይቀጥላል፡፡ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ የዚህ ማህበር ግብ የትግራይን ህዝብ ችግር ማቃለል ነው፡፡ በሱዳን

ድንበር ያሉትን ስደተኞች ከመርዳት ባሻገር ማረት የውሀ ጉድጓዶችንና የከርሰምድር ውሀን እና ሌሎች ውሀ የሚያስገኙ ዘዴዎችን በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ ማረት ገበሬው በጓሮ አትክልት፣ በንብ በማነብና በእንሰሳት በማድለብ እንዲሰማራም ድጋፍ ያደርጋል፡

86

፡ ነገር ግን በመጨረሻ ማረትም ቢሆን ለክልሉ ዝናብ ማዝነብ አይቻለውም፡፡ እናም 4.5 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በአየር ንብረት መለወጥ ምክንያት ኑሮው እንደተቃወሰ ግምት ውስጥ በማስገባት አርሶአደሮች በኑሮአቸው ላይ የሚታይ ፋይዳ ያለው መሻሻል እስኪመጣ መጠበቅ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

‹‹አንድ ቀን ዝናቡ ጨርሶ ቀጥ እንዳይል እግዚአብሔር ይርዳን፤ምክንያቱም

ዝናብ እስካለ ድረስ መቼስ ተስፋ ይኖረናል›› ይላል ተወልደ፡፡

መንስኤያዊ ጥናት 6፡ በረዶ ጠባቂውን ያውቋቸዋል? -በሳይመን ፔዝ

በድንገት ሰማዩ ጠቋቁሯል፡፡ ድቅድቅ ያለው ደመና ከበድ ያለ የአየር ሁኔታ እየመጣ እንደሆነ ስለሚጠቁም በአለፋ ወረዳ የሻሁራ መንገዶች ያለ ሰው ሁሉ ወደ ቤቱ ለመግባት ጥድፊያ ላይ ነው፡፡ በሻሁራ ቅዳሜ የገበያ ቀን ነው፡፡ ነገር ግን ድንገተኛውና ያልተጠበቀው ዝናብ ወከባና ሁካታ የተሞላውን የገበያ እንቅስቃሴ በጊዜ በተነው፡፡

ቤታቸው መድረስ ያልቻሉት ሰዎች በትንሿ ገበያ ዋና መንገዶች ዳር ባሉ ሻይ ቤቶች ውስጥ ተጠልለዋል፡፡ ታደሰ ጎንፋና አብራሃም ፍሰሃ ከሻይ ቤቱ በር አጠገብ ተቀምጠው በኃዘን ደመናውን ያጤናሉ፡፡ አብረሃም አስተያየቱን በመቀጠል ‹‹ትንሽ ቆይቶ በረዶ ይዘንባል›› አለና ሻይ አዘዘ፡፡ በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ማጉረምረም እየተዛመተ ሄደ፡፡ ሁሉም ሰው በረዶ ይፈራል፡፡ በተለይ ነሐሴ ውስጥ ከዘነበ ምርቱን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ ይችላል፡፡ ‹‹ላለፉት ሰባት ዓመታት በረዶ ዓይነተኛ ችግር ሆኖብናል፡፡ ምንም እንኳን በረዶ ለዚህ አካባቢ ያልተለመደ ባይሆንም ድግግሞሹ ግን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡» በማለት ታደሰ አከለበትና ሁሉም በሃሳቡ ተስማሙ፡፡ የበረዶው በከፍተኛ ደረጃ መደጋገም ዋነኛ ችግር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በ1998 ዓ.ም የአንድ መንደር ምርት ሙሉ በሙሉ ነበር የወደመው፡፡

ሻሁራ ከፍተኛ የግብርና አቅም ያለው አካባቢ ነው፡፡ ለወትሮው ከ1900 እስከ 2000 ሚ.ሜ የሚሆን በቂ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ነበረው፡፡ ላለፉት ጥቂት አስርተ ዓመታትም ትርፍ አምራች የሆነ አካባቢ ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ነዋሪ ሲናገሩ እንዲህ አሉ ‹‹አሁን አሁን የምናመርተው ከቤተስቦቻችን ፍጆታ አያልፍም፡፡ ከአሁን ወዲያ ለሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችና ክልሎች ለመሽጥ የሚያስችል ትርፍ ምርት ሊኖረን አይችልም፡፡»

ከዚያም በረዶው መውረድ ጀመረ፡፡ በቆርቆሮው ላይ የሚስማው ጩኸት ሊታገሱት የማይቻል ነው፡፡ በሻይ ቤቷ ውስጥ ያሉት አርሶአደሮችም በጉዳዩ ላይ በሀዘን መወያየት ጀመሩ፡፡ ከዚያም አብረሃም እንዲህ ብሎ ጮኸ ‹‹የበረዶ ጠባቂ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?››

87

ምላሽ ሳይጠብቅ ማብራራቱን ቀጠለ፡፡ ‹‹የሚኖሩት በብቸኝነት ነው፤ የምታዩአቸውም አንዳንድ ጊዜ ነው፡፡ ሁለት አይነት የበረዶ ጠባቂዎች አሉ፤ በረዶውን የሚያመጡና ከበረዶው የሚጠብቁአችሁ፡፡ ቀደም ብሎ በዚህ ወረዳ ሦስት በረዶ ጠባቂዎች ብቻ ነበሩ፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቁጥራቸው እንደ አሸን እየፈላ ነው፡፡ ዛሬ ወደ ሁለት መቶ ይጠጋል፡፡ በረዶ ማዝነብ መሬቱን ከበረዶ ከመጠበቅ ይልቅ ይቀላል ይባላል፡፡ ስለዚህ ልትከፍሏቸው ፈቃደኛ ከሆናችሁ አባዛኞቹ በእርሻችሁ ላይ በረዶ ያዘንቡላችኋል፡፡››

ምንም እንኳን አንድ በረዶ ጠባቂ የሚያደርገው ምን እንደሆነ እርግጠኛ የሚሆን ሰው ባይኖርም ሁሉም ስለዚህ አዲስ የስራ መስክ አስቀድሞ ያውቃል፡፡ እንደሚናፈሰው ወሬ ከሆነ በረዶ ጠባቂ በሚጠበቀው መሬት ከፍተኛ ቦታ ላይ በተተከለ ማማ ዣንጥላ ስር ተቀምጦ መፅሀፉን ይደግማል፡፡ በሻይ ቤቷ ውስጥ ካሉ አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም የተሻለ ጥበቃ ለማግኘት የበረዶ ጠባቂዎችን በሚስጥር ገንዘብ ከፍለዋል፡፡ በሚስጥር ነው ታዲያ፤ ምክንያቱም በእውነት በእግዚአብሔር የምታምን ከሆነ እንደዚህ አይነት የጥንቆላ ዘዴዎችን መጠቀም አትፈልግም፡፡

በረዶ ጠባቂዎቹ የሚከፈላቸው ከመኸር በኋላ ሲሆን አንዳንዶቹ ጥሩ ገንዘብ ያገኛሉ፡፡ እንዲያውም ከበረዶ ጠባቂዎቹ አንዱ ከአርሶአደሮቹ በተቀበለው ክፍያ አይሱዙ መኪና ገዝቶ አሁን ነጋዴ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አርሶአደሮቹ በእነዚህ ሰዎች ላይ የበለጠ ተጠራጣሪ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ለበረዶ ጠባቂዎቹ ከፍለውም በረዶ በሚዘንብበት ጊዜ በበረዶ ጠባዊዎቹና በሚቃረኑአቸው ኃይላት መሀል በጣም የበዛ ፍክክር እንዳለ ጠርጥረዋል፡፡ ‹‹ለበረዶ ጠባቂ ገንዘብ እንከፍላለን ነገር ግን በእነርሱ ላይ ልንተማመንባቸው አልቻልንም፤ ምናልባትም የእኛ መንደር ከበረዶ ትድን ይሆናል፤ ነገር ግን ሌላ መንደር ደግሞ ይወድማል፡፡ ታዲያ በረዶ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ማለት እንዴት እንችላን?››

በእርግጥም ሰፊ ውድድር በመካሄድ ላይ ነው፡፡ አንዳንድ መንደሮች ለበረዶ ጠባቂዎች ከአሁን በኃላ ገንዘብ ላለመክፈልና በእግዚአብሔር ላይ ከተመሠረተ እምነት ጋር ለመጣበቅ ወስነዋል፡፡ አብረሃም እንዲህ ሲል ተናገረ ‹‹በጠንቋይና በእግዚአብሔር መካከል ግራ ተጋብተን ነበር፤ አሁን ግን መንደሩ በሙሉ በእግዚአብሔር ለማመን ወስኗል፡፡ በእግዚአብሔር ካመንክ በረዶ ጠባቂውን አትፈልገውም፡፡»

የበረዶው ዶፍ እንዳለቀ በሻይ ቤቷ ያሉት አርሷደሮች ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡ አብርሃም የእረኛ ዱላውን አንስቶ መግቢያው በር ላይ እንደቆመ እንዲህ አለ ‹‹የሆነው ሆኖ በስተመጨረሻ በረዶ ጠባቂዎቹን ገንዘብ የሚከፍሉ አንዳንድ አርሶ አደሮች ይኖሩ እንደሆነ ምን ታውቃለህ?››

የአየር ንብረት ለውጥ በአለፋ ወረዳ እያደገ ያለ አዲስ የስራ ዘርፍ የፈጠረ ይመስላል!

88

7. ማጣቀሻዎች

8. Glossary/መሰረታዊ ቃላትና ፍቺዎቻቸው Adaptaion: የመላመድ ዘዴ

Mitigation: አሉታዊ ተፅዕኖን መቀነስ

Coping: መቋቋም

Livelihood: መተዳደሪያ

Integration: ትስስር

Social Cohesion: ማህበራዊ ትስስር

Social structure: ማህበራዊ መዋቅር

Vulnerability: ተጋላጭነት

Resilience፡ የማገገም ብቃት

yxF¶µ qND yxµÆb! ¥:kL _MrT xÄ!S xbÆ †n!vRs!tE xÄ!S xbÆ x!T×ùÃyxyR NBrT lW_ m§mD SRyT PéG‰MSLK q$_R +251 (0) 11 655 0226 +251 (0) 11 810 6713ÍKS +251 (0) 11 123 9469x!(»YL [email protected]

Printed by: http://www.masterprintingpressplc.com