ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር...

29
ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ተደብቀው የኖሩ፡ አዳዲስ ምሥጢራትን የገለጠችባቸው፣ ከዮሓንስ ኢትዮጲስ ለቀረቡ፡ ተከታታይ ጥያቄዎች፡ የተሰጡ መልሶች። ኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን፡ ከእንግሊዝኛው ዝግጅት፡ ወደኢትዮጵያኛው እንደተረጐመው፤ አብርሆትና አርትዖት፡ በኪዳናዊ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ (ንቡረ-እድ) + + + ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፩ደኛ ጥያቄ፡- ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾኑ፡ ማረጋገጫዎ ምን እንደኾነ ልጠይቅዎ ግድ ይለኛል? የትኛው መጽሓፍ ቅዱስ፡ ይህን ይናገራል? ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ከኾነ፣ "የጥንቶቹ አይሁድ፡ ከኢትዮጵያውያን ጋር፡ በአካል ተመሳሳይ ነበሩ፤" ማለት ነው? ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡- በጥያቄዎ ላይ፡ ሌላ ጥያቄ እንጨምራለን። ጥያቄያችን፡ ቀላልና ግልጽ ሲኾን፡ እርስዎ ከጠየቁን ጋር፡ ተመሳሳይ ነው። ልዩነቱ፡ ጥያቄያችን ያነጣጠረው፡ እርስዎው እራስዎ ላይ መኾኑ ነው። ለጥያቄያችንም፡ እውነተኛውን ምላሽ እንዲሰጡን፡ በትሕትና እንጠይቅዎታለን። ጥያቄያችንም፡ "እርስዎ ራስዎ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾንዎ፡ ማለትም፡ ስለእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ማንነትዎ፡ ማረጋገጫዎ ምንድን ነው?" የሚል ነውና፡ እባክዎ! ለዚህ ጥያቄያችን፡ የተሟላ መልስዎን ይስጡን? ይኽን የጠየቅንዎ፡ በጥያቄዎ ላይ ላነሡት ርእስ፡ በመጻሕፍታችንና በኅዋ ሰሌዳችን፥ እንዲኹም፡ በፌስቡካችን ላይ፡ በዝርዝር የቀረበ ሰፊ ማብራሪያ ስለሚገኝ፡ ትክክለኛውን ግንዛቤ ለማግኘት እንደሚረዳዎ፡ ለመጠቆም በማሰብ ነው።

Upload: trinhtuyen

Post on 13-Mar-2018

327 views

Category:

Documents


23 download

TRANSCRIPT

Page 1: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡

ተደብቀው የኖሩ፡ አዳዲስ ምሥጢራትን የገለጠችባቸው፣

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ ለቀረቡ፡

ተከታታይ ጥያቄዎች፡ የተሰጡ መልሶች።

ኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን፡

ከእንግሊዝኛው ዝግጅት፡ ወደኢትዮጵያኛው እንደተረጐመው፤

አብርሆትና አርትዖት፡ በኪዳናዊ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ (ንቡረ-እድ)

+ + +

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፩ደኛ ጥያቄ፡-

ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾኑ፡ ማረጋገጫዎ ምን እንደኾነ ልጠይቅዎ ግድ

ይለኛል? የትኛው መጽሓፍ ቅዱስ፡ ይህን ይናገራል? ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ከኾነ፣

"የጥንቶቹ አይሁድ፡ ከኢትዮጵያውያን ጋር፡ በአካል ተመሳሳይ ነበሩ፤" ማለት ነው?

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡-

በጥያቄዎ ላይ፡ ሌላ ጥያቄ እንጨምራለን። ጥያቄያችን፡ ቀላልና ግልጽ ሲኾን፡

እርስዎ ከጠየቁን ጋር፡ ተመሳሳይ ነው። ልዩነቱ፡ ጥያቄያችን ያነጣጠረው፡ እርስዎው

እራስዎ ላይ መኾኑ ነው። ለጥያቄያችንም፡ እውነተኛውን ምላሽ እንዲሰጡን፡ በትሕትና

እንጠይቅዎታለን።

ጥያቄያችንም፡ "እርስዎ ራስዎ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾንዎ፡ ማለትም፡

ስለእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ማንነትዎ፡ ማረጋገጫዎ ምንድን ነው?" የሚል ነውና፡

እባክዎ! ለዚህ ጥያቄያችን፡ የተሟላ መልስዎን ይስጡን?

ይኽን የጠየቅንዎ፡ በጥያቄዎ ላይ ላነሡት ርእስ፡ በመጻሕፍታችንና በኅዋ

ሰሌዳችን፥ እንዲኹም፡ በፌስቡካችን ላይ፡ በዝርዝር የቀረበ ሰፊ ማብራሪያ ስለሚገኝ፡

ትክክለኛውን ግንዛቤ ለማግኘት እንደሚረዳዎ፡ ለመጠቆም በማሰብ ነው።

Page 2: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፪ተኛ ጥያቄ፡-

ጥያቄዎን ለመመለስ፡ በመጀመርያ፡ ኢትዮጵያዊነት የዘር ሓረጌ ነው። ወላጆቼም

ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊት ናቸው። እንዲኹም፡ የኢትዮጵያው ሃይማኖታዊ ሥነ-

ምግባር፡ ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር የተቆራኘ እንደኾነ በማመን፤ ኹሉን የኢትዮጵያን ባህል እደግፋለሁ። ይህም፡ የምዕራባውያን ተጽዕኖ ያደረባቸው፣ በእየራሳቸውም፡

"ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ነን!' የሚሉት ወገኖች፡ እንደጎጂ ባህል

የሚመለከቱትን፥ ወይም የሚንቁትን፡ ምሳሌ ለመጥቀስ ያኽል፡ "ያለዕድሜ ጋብቻ"ን ጨምሮ ይኾናል።

ምክንያቱ ግልጽ ባይኾንም፡ ኢትዮጵያ ውስጥ (እና በተቀረው የአፍሪቃ

አህጉር)፡ የግብረ ሰዶም ርእዮተ ዓለም እንዲስፋፋ፡ ጥረት የሚያደርጉት ሰዎች፡

ያለዕድሜ ጋብቻ እንዲቆም የሚሞግቱት፡ እነርሱ እራሳቸው ስለመኾኑ

(አገልግሎታቸውም ለሰይጣን እንደኾነ)፡ እኒሁ፡ የኢትዮጵያ ሰዎች፡ መገንዘብ

ተስኗቸዋል። የግብረ ሰዶማዊ መብት ደጋፊ የኾነን፡ ማንኛውንም ግለሰብ፡

ወንድ/ሴት፡ "ያለዕድሜ ጋብቻ"ን በተመለከተ፡ አቋሙ ምን እንደኾነ ቢጠየቅ፡ በእርግጥ፡ ድርጊቱ አግባብ አለመኾኑን እና/ወይም ጎጂ ስለመኾኑ፡ ምክንያቱን ሊናገር

ወይም ሊያብራራ ይቻለዋል። በምዕራቡ ዓለም፡ "ያለዕድሜ ጋብቻ" እንዲቆም፡ ጥረት

የሚያደርጉት፡ በተዘዋዋሪ ደግሞ፡ ግብረ ሰዶም እንዲስፋፋ የሚፈጽሙት፡ የአንድ

ሳንቲም፡ ኹለት ገጽታዎች ናቸው። እኔ የተረዳኹት፡ ከክርስትና እና ከኢትዮጵያዊነት ተቃራኒ የኾነው የምዕራቡ

ባህል፡ ሰይጣናዊ ስለመኾኑ ነው። መልሴ፡ ከዚህ አስተሳሰብ፡ ፈቀቅ ያለ ኹኖ ቢገኝ፡

ይቅርታ እጠይቃለሁ። ይኹን እንጂ፡ ጉዳዩ አግባብ ስለመኾኑና የጠበቀ ግንኙነት

እንዳለው አምናለሁ። እና ባጭሩ፡ እውነተኛ የኾነ ኢትዮጵያዊ / የኾነች ኢትዮጵያዊት፡ ኢትዮጵያዊ

ነክነት ያለውን፡ ማንኛውንም ባህል፡ ምዕራባውያን ቢስማሙም ባይስማሙም፡

ሊቀበሉት ይገባል። በእኔ አስተያየት፡ ለራሳቸው አገር ባህል፥ ወይም አኗኗር ዘይቤ፡ ተፃራሪዎች የኾኑት፡ እነዚያ የኢትዮጵያ ሰዎች፡ ማንነታቸውን የካዱ ናቸው። እኔ ግን

በበኩሌ፡ የኢትዮጵያን ባህል ሳላዛባ፡ ኹሉን እጠብቃለሁ።

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡-

ለመልስዎ፡ እግዚአብሔር ይስጥልን!

ዳሩ ግን፤ አጋጣሚ ኹኖ፡ የጥያቄያችንን ቍም ነገር አላገኙትም። የዚህም ዋና

ምክንያት፡ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ገላጭ የኾኑትን መጻሕፍት ባለማንበብዎ፥

በኅዋ ሰሌዳችንና በፌስ ቡክ ገጻችን የሚተላለፉትንም መልእክቶች፡ ባለመመልከትዎ

ይኾናል።

Page 3: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

እውነታው ይህ ከኾነ፡ ከኹሉ ይልቅ፡ ይበልጥ፡ ለዚህ ርእሰ ነገር፡ ቅድሚያን

በመስጠት፥ ይህንም እንደመሥፈርት በመውሰድ፡ መጻሕፍቱን እንዲያነብቡና ኅዋ

ሰሌዳችንን፥ የፌስ ቡክ መድረካችንን እንዲጎበኙ እናበረታታዎታለን።

ምናልባት፡ ይህን ግዳጅ ያጠናቀቁ ከኾነ፡ ያልተፈጸመው፡ ሌላው ተከታዩ

ግዳጅ፡ "ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት ስለመኾኗ፥ ከዚህ አንጻር ደግሞ፡

ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምንነት፡ ገና በትክክል አልተረዱም!" የሚለው

ይኾናል። ወይንም፡ ኹሉን አውቀውና ተረድተው፡ "እውነታውን አልተቀበሉትም!"

ማለት ይኾናል።

የዚህ ኹሉ፡ ምክንያቱ፡ የትኛውም ይኹን የትኛው፡ እስከአኹን ለውይይት

የቀረበው አሳብ፡ ለአጠቃላይ ግንዛቤ፡ በቂ፥ ወይም፡ ተመጣጣኝ እንደሚኾን በማመን፥

ምርጫውንና ውሳኔውንም፡ በአግባቡ፡ ለእርስዎው በመተው፡ ወደሌሎቹ ጥያቄዎችዎ

እንዘልቃለን።

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፫ተኛ ጥያቄ፡-

ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣው ትውፊታችን፡ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ፡

ከእስራኤል ጉዞው፡ ወደኢትዮጵያ ሲመለስ፡ ክርስትናን ለአገራችን ሰብኳል። ሐዋርያው ማቴዎስ፡ ተመሳሳዩን እንደፈጸመም ይታወቃል። ታድያ እውነታው ይህ ከኾነ፡

አብዛኞቹ "ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊት ነን!" የሚሉት ወገኖች፡ በንጽጽር ቅርብ

ለኾኑት ምዕራባውያን የወንጌል መልእክተኞች፡ ቅድሚያውን መስጠታቸው ለምንድን ነው?

ይህ የኾነበት ምክንያት፡ እነዚህ ክርስቲያኖች፡ የኢትዮጵያን፡ የክርስትና

ዝክረ ታሪክ አያውቁም ማለት ነው። እውነተኛ ስለኾነችው ቤተ ክርስቲያን የተሰበከው፡

በማቴዎስና በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበረ። ታድያ! እዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ፡ ምን ደረሰ? እኔ የማምነው ጥቃት እንደተፈጸመባት ነው።

ከዚህ የሚከተለው ሓተታ የተወሰደው፡ ‘ኢትዮጵያ፡ ያልታወቀች አገር፤

ስለባህሏና ስለታሪኳ መመሪያ’ በሚል ርእስ፡ ስቱዋርት መንሮ-ሄይ (Stuart Munro-Hay)፡ ከጻፈው መጽሓፍ፡ ከገጽ ፳፬ ላይ ነው።

“አጼ ዘርዓ ያዕቆብ (፩ሺ፬፻፴፬-፷፰)፡ የለየለት ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ነበረ።

ሚስቱ፡ እቴጌ ጽዮን ሞገሳ (Seyon Mogasa)፡ በግርፋት፡ ሕይወቷ ሊያልፍ

በቅቷል። ምክንያቱ፡ እርሱን፡ ከዙፋኑ ለማውረድ፡ በታቀደው ሴራ ውስጥ፡

"ተካፍላለች!" ተብሎ የቀረበባት ክስና ውቅስ፡ በእርሱ ላይ የፈጠረበት ንዴት ገንፍሎ

ነው። ልጁ በዕደ ማርያም፡ ስለእናቱ ሞት በማዘኑ፡ ቅጣት ደርሶበታል።

“ዘርዓ ያዕቆብ፡ የተቀናቃኞቹን ኅሊና እንኳ ሳይቀር፡ ለመቆጣጠር

ሞክሯል። ወቅቱ፡ ሃይማኖት ነክ የኾኑ ጥያቄዎች ተነሥተው፡ ውይይትና ክርክር

የሚደረግበት፥ አፍታ ሳይቆይ ደግሞ፡ ንጉሠ ነገሥቱ፡ እምነትን በተመለከተ፡

Page 4: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ለሚደነግገው ትዕዛዝ፡ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ላልኾኑት፡ ጭካኔ የነገሠበት ዘመን ነበር።

ማንኛውም ዓይነት ተቃውሞ፡ መኮላሸት ነበረበትና። “የኾነ ኾኖ፡ ዘርዓ ያዕቆብ፡ በሃይማኖትና በባህል ረገድ፡ ከፍተኛ

አስተዋጽኦን አበርክቷል። በተለይ፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡ በኢትዮጵያ ቤተ

ክርስቲያን ዘንድ፡ በአምልኮ ደረጃ እንድትመሰገን፡ በርካታ መርሓ ግብሮች እንዲዘጋጁ

አስደርጓል። ጥንታዊ ስለኾነው ሥርወ መንግሥት የሚመሰክሩ፡ የብራና መጻሕፍትና ሥዕሎች፡ ጥቂት በኾኑ አብያተ ክርስቲያን ብቻ (እንደዘገባው ከኾነ) ዛሬ ድረስ

ይገኛሉ።”

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡-

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት በመኾኗ፥ ኢትዮጵያውያንና

ኢትዮጵያውያትም፡ የእግዚአብሔር፥ ራሷም፡ የእግዚአብሔር እናት እና ኢትዮጵያ

የኾነችው፡ የድንግል ማርያም ልጆች በመኾናቸው፥ በጠቅላላው፡ ለኖሩበት፡ የ፯ሺ፭፻፯

(የሰባት ሽህ አምስት መቶ ሰባት) ዓመታት የነፃነት ህልውና ዘመን፡ መንፈስ ቅዱስ

ከኾነው፡ ከራሱ ከእግዚአብሔር በቀር፡ አንድም የሰው አስተማሪ፥ ሰባኪ፥ ሓዋርያ፥

ወይንም፡ የምሥራቹ ቃል (የወንጌል) መልእክተኛ፡ ጨርሶ አስፈልጓት አያውቅም።

እንዲያውም፡ በዚህ ኹሉ ዘመን፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡

እውነተኞችና ታማኞች ነቢያትና ሓዋርያት፥ አስተማሪዎችና ሰባኪዎች፥ የምሥራቹ

ቃል (የወንጌል) መልእክተኞች ኾነው፡ ወደተቀሩት የዓለም ሕዝቦች በመኼድ፡

ተመሳሳዩን አገልግሎት የፈጸሙት፡ እነርሱው፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት

ናቸው።

መቸም፡ በዚህ ረገድ፡ እርስዎም፡ በሃይማኖት ያወቁትና የተቀበሉት እውነታ

አለ፤ ይኸውም፡ በበላይነትና ባጠቃላይነት፡ ኹሉን ዐቀፍ በኾነው፡ በዚህ

ኢትዮጵያዊነት፡ ማለትም፡ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ ሃይማኖት ጸንተው

የሚኖሩ ሰዎች ኹሉ፡ ስማቸው የተመዘገበበትና የሚመዘገብበት፡ የሕይወት መጽሓፍ

እንዳለ የሚያረጋግጠው መለኮታዊው ቃል ነው።

በዚህ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የአገልጋዮች ስም

ዝርዝር በተመዘገበበት የሕይወት መጽሓፍ ውስጥ የተካተቱት የእምነት መሪዎች፡

ማንነታቸው፡ በመጽሓፍ ቅዱስ፡ በክብር የተወሳው፡ የቅዱሳኑና የቅዱሳቱ ስም ብቻ

አይደለም፤ ነገር ግን፡ ስማቸው፡ በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ሳይጠቀስ የቀረውንና

ከመጽሓፍ ቅዱስ ውጪ በኾኑት፡ በዓለም ሃይማኖቶችም ዘንድ ተጠቅሶ የሚገኘውን፡

ለምሳሌ፡ በአይሁድ፥ በቡድሃ፥ በሒንዱ፥ በክርስትናና በእስልምና፥ በሌሎችም

እምነቶች ዘንድ የታወቁትን ግለሰቦች ስም ጭምር፡ ያጠቃለለ ነው። (ራእ. ፭፥ ፩፤ ፳፥

፲፪-፲፭።)

ይህ የእግዚአብሔር እውነታ፡ እዚህ ላይ፡ አርአያ ኹነው፡ ለአብነት

በቀረቡት፥ ስማቸውና ምግባራቸው፡ ከዚህ በታች፡ ባጭር በተወሳው፡ በስመ-ጥሩዎቹ

ሰዎች ዜና መዋዕል፡ በበለጠ ታውቆ፡ ሊረጋገጥ ይቻላል። ከእነዚህም፡ ከብዙዎቹ

Page 5: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

"የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ልጆች" መካከል፡ የጠቀስናቸው ጥቂቶቹ፡

እኒኸውልዎ፦

፩ደኛው፡ አብርሃምን፡ ስለአምልኮተ እግዚአብሔር አስተምሮና

ባርኮ፡ ለግርዛት ቃል ኪዳን ያበቃው፡ ኢትዮጵያዊው መልከ ጼዴቅ ነው፤

፪ተኛው፡ ሙሴን፡ ስለአምልኮተ እግዚአብሔርና ስለኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ያስተማረው፥ ሴት ልጁንም ሲጳራን የዳረለት፡

ኢትዮጵያዊው ካህን ዮቶር ነው፤

፫ተኛዪቱ፡ የቅዱሱ ኪዳን ሃይማኖቷንና የእግዚአብሔር የኾነውን፥

እነርሱም፡ በሙሴ አማካይነት፡ ተሰጥቷቸው የነበረውን ሥርዓተ መንግሥቷን፡

ለአይሁዶችና ለንጉሣቸው፡ ለሰሎሞን በማዘከር፡ የቀድሞውን እንዲያጸኑት ለማድረግ፥

ከዚህም በላይ፡ ታቦተ ጽዮንና የዳዊት፡ የቃል ኪዳን ዘር፡ ወደኢትዮጵያ ተመልሰው

የሚመጡበትን መንገድ ለመክፈትና ለማመቻቸት፡ እግዚአብሔር፡ መንፈሷን

አነሣሥቶ፡ ቅማያቷ፡ ኢትዮጵያዊው መልከ ጼዴቅ ወደቈረቈራትና ኹለተኛዪቱ አገሯ

ወደኾነችው፡ ወደኢየሩሳሌም እንድትጓዝ ያደረጋት፥ እዚያም፡ ወላጁ፡ እስራኤላዊው

ዳዊት ከኾነው፡ ወላጂቱም፡ ኢትዮጵያዊቷ ቤትሳባ ከኾነችው፡ ከንጉሥ ሰሎሞን፥

"እብነ መለክ"፥ በሕዝባዊ አጠራርም፡ "ምኒልክ" የተባለውን ልጇን የወለደችው፡

ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ማክዳ ናት፤

፬ተኛዎቹ፡ ራሳቸውን፡ የአብርሃም፥ የይስሓቅና የእስራኤል ልጆች

በማድረግ፥ በሌሎችም ዘንድ፡ "ዕብራውያን" ተብለው በመጠራት፡ "የእግዚአብሔር

ሕዝብ ነን!" የሚሉት አይሁድ፡ በተለያየ መልክና በተደጋጋሚ ይዞታ፡ የፈጸሙት፡

የኃጢኣታቸው ጽዋ፡ ሞልቶ በመፍሰሱ፡ ትዕግሥትና ምሕረት፡ የባሕርይ ገንዘቦቹ

የኾኑት አምላካቸው እግዚአብሔር፡ በንስሓ ይመለሱለት ዘንድ፡ ሊገሥፃቸውና

ሊመክራቸው፥ ሊያስጠነቅቃቸውና "እምቢ!" ካሉም፡ ለቅጣት የሚጠብቃቸው ፍዳ፡

ምን ዓይነት እንደኾነ ሊያሳውቃቸው፡ ከመኻላቸው ያስነሣቸው፡ ኢትዮጵያዊው ነቢየ

እግዚአብሔር ኤርምያስና በዚያ ተልእኮ፡ ከእርሱ ጋር የተባበሩት፡ ኢትዮጵያውያኑ ደቀ

መዛሙርቱ፡ አቤሜሌክና ባሮክ ናቸው።

እኒሁ፡ ዐንገተ ደንዳኖቹ አይሁድ፡ የኃጢኣታቸው ጽዋ፡

እንዲያ ሞልቶ በመፍሰሱ፡ በባቢሎን፡ ለ፸ (ሰባ) ዓመታት፡ ያን የሚያህል፡ የፈተና

ነበልባል የነደደባቸው፥ ያን የሚያህልም፡ የመከራ ማዕበል ያጥለቀለቃቸው፡

እንዲያው፡ ያለበቂ ምክንያት አልነበረም።

ስማቸው፡ ከላይ በተጠቀሰውና እየራሳቸውን፡ ለፍጹሙ

ኢትዮጵያዊነት ባበቁት፥ በቀደምት ቅማያቶቻቸው፡ በአብርሃም አማካይነት፡

ከአምልኮተ ጣዖት፥ በሙሴ አማካይነት፡ ከግብፅ ባርነት፥ በዳዊት አማካይነት ደግሞ፡

ከአረማዊው የአገዛዝ ቀንበር፡ ነጻ የወጡበትን፡ ቀደም ብሎ፡ ከፈጣሪያቸው

የተደረገላቸውን፡ ያን ኹሉ፡ መለኮታዊ ትድግና፡ በመዘንጋታቸው እንጂ።

Page 6: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

በመዘንጋታቸውም ብቻ አይደለም፤ ከዚያ፡ እጅግ ከባሰው፡ ከከባዱ ኃጢኣታቸው

የተነሣ ጭምር እንጂ።

እርሱም፡ ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት

የተቀበሉትን፡ ቅዱሱን ኪዳን፡ በተደጋጋሚ በማፍረስ፡ የፈጸሙት፡ ታላቁ፡ የክፋትና

የክህደት፥ የዓመፅና የአመንዝራነት ኃጢኣታቸው ነው።

ይህም እውነታ፡ በዛሬው፡ የኢትዮጵያና የዓለም የሰው ዘር

ትውልድ ዘንድ፡ በብርቱ ሊታወስና ሊጤን ይገባል፤ ያስፈልጋልም።

፭ተኛው፡ ከእኒያ፡ ስማቸው፡ ከላይ ከተወሳው ቅዱሳንና ቅዱሳት

የዘር ሓረግ፥ በተለይም፡ ፫ተኛዪቱ ባለተራ ቍጥር ከኾነችው፡ ከኢትዮጵያዊቷ

ንግሥት፡ ከማክዳ እና ከእስራኤላዊው ንጉሥ፡ ከሰሎሞን እስከተወለደው፡ "እብነ

መለክ"፥ ወይም፡ "ምኒልክ" እስከተባለው ልጇ እየወረደ፡ በመጨረሻ፡

ለኢትዮጵያዊው ኢያቄምና ለኢትዮጵያዊቷ ሓና ከደረሰው፡ ከቅዱሱ ኪዳን ዘር፡

ለእግዚአብሔር አብ፡ ሙሽሪትነት፥ ለእግዚአብሔር ወልድ፡ እናትነትና ለእግዚአብሔር

መንፈስ ቅዱስ፡ መቅደስነት የበቃችው፡ ራሷም፡ "ኢትዮጵያ" የኾነችው፡ ድንግል

ማርያም ተገኘች።

፮ተኛው፡ የሰውን ልጅ ለማዳን፡ ከሰማይ የወረደው፡ ኢየሱስ

መሢሕ፡ እግዚአብሔር እም፡ ቀደም ብላ፡ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከተዋሓደቻት፡

ከዚችው፡ ኢትዮጵያዊት ድንግል ማርያም፡ መለኮት በተዋሓደው ሰውነት (ትስብእት)፡

ተወለደ።

፯ተኛው፡ ከእርሷም፡ "ኢትፈነውኩ፡ ዘእንበለ ኀበ አባግዕ፡

ዘተሓጕላ፡ ዘቤተ እስራኤል!" ማለትም፡ "ከእስራኤል ወገን ወደኾኑ፡ ወደጠፉት በጎች

ብቻ እንጂ፡ ወደሌላ አልተላክሁም።" በሚል ቍርጥ ቃል፡ እነዚህኑ፡ ፈጽመው

የጠፉትን፡ የእስራኤልን ቤት ልጆች ብቻ ለማዳን ሳይኾን፡ በፈጣሪው ላይ፡ የአምልኮ

አመንዛሪ፥ ከሃዲና ዐመፀኛ ኾኖ የተገኘውንና በዓለሙ ኹሉ የተበተነውን፡ መላውን

የሰውን ልጅ፡ በዘለዓለም ቤዛነቱና መድኃኒትነቱ፡ የመጨረሻው አማናዊው ኢትዮጵያዊ

ነቢይና መልእክተኛ፥ መምህርና ሓዋርያ፥ መድኅንና እረኛ፥ ሊቀ ካህናትና ንጉሠ

ነገሥት ኾኖ መታደጉ፡ ይህን የእግዚአብሔርን እውነታ፡ የበለጠ ያጎላዋል፤

ያጸናዋልም። (ማቴ. ፲፥ ፭-፯; ፲፭፥ ፳፬።)

ይህ ዝክረ ነገር ሲታሰብና ሲወሳ፡ በኋለኛው ዘመን፡ ዘግየት ብለው የደረሱት፡

ቡድሀን፥ መሓመድንና መኀትመ ጋንዲን የመሰሉት፡ ሌሎች ግለሰቦች፡ ከዚሁ ጎራ

የሚመደቡ ስመ ጥር ተምሳሌቶች ይኾናሉ።

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፬ተኛ ጥያቄ፡-

ኢትዮጵያ፡ መምህር፥ ወንጌል ሰባኪና ሓዋርያት፡ ፈጽሞ አስፈልጓት የማያውቅ

ከኾነ፡ ከእነዚህም ጋር ንኪክነት ካልነበራት፡ ይህ ማለት ታድያ! መጽሓፍ ቅዱስ አያስፈልጋትም ማለት ነውን?

Page 7: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

በጽሑፍዎ ውስጥ፡ ከዚህ በታች ያሠፈሩት የመልእክት ይዘት፡ ምን ማለት

እንደኾነ እርግጠኛ አይደለሁም። ይኸውም፡ “በበላይነትና ባጠቃላይነት፡ ኹሉን ዐቀፍ

በኾነው፡ በዚህ ኢትዮጵያዊነት፡ ማለትም፡ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ

ሃይማኖት ጸንተው የሚኖሩ ሰዎች ኹሉ፡ ስማቸው የተመዘገበበትና የሚመዘገብበት፡

የሕይወት መጽሓፍ እንዳለ የሚያረጋግጠው መለኮታዊው ቃል ነው።

“በዚህ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋዮች ስም

ዝርዝር፡ በተመዘገበበት የሕይወት መጽሓፍ ውስጥ የተካተቱት የእምነት መሪዎች፡

ማንነታቸው፡ በመጽሓፍ ቅዱስ፡ በክብር የተወሳው፡ የቅዱሳኑና የቅዱሳቱ ስም ብቻ

አይደለም፤ ነገር ግን፡ ስማቸው፡ በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ሳይጠቀስ የቀረውንና

ከመጽሓፍ ቅዱስ ውጪ በኾኑት፡ በዓለም ሃይማኖቶችም ዘንድ ተጠቅሶ የሚገኘውን፡

ለምሳሌ፡ በአይሁድ፥ በቡድሃ፥ በሒንዱ፥ በክርስትናና በእስልምና፥ በሌሎችም

እምነቶች ዘንድ የታወቁትን ግለሰቦች ስም ጭምር፡ ያጠቃለለ ነው።” የሚለው ነው።

ለእርስዎ ያለኝ ከበሬታ እንደተጠበቀ ኹኖ፡ ይህ ይትበሃልዎ ግን፡ ከክርስትና እምነት ጋር ፈጽሞ የማይስማማ፥ በመልእክትዎ እንደጠቀሱት፡ አረማዊ ከኾነው

የዓለም ሃይማኖትም ጋር የማይዛመድ ነው። የእነዚህ ሃይማኖት መምህሮች (ማለትም

እርስዎ የጠቀሷቸውን፡ ቡድሃን፥ መሓመድንና መኀትመ ጋንዲን የመሰሉት)

ያስተማሩት እምነት፡ መጽሓፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ አይደለም። ትምህርቱም ቢኾን፡ እርስ በእርሱ የሚቃረን ስለኾነ፡ በእግዚአብሔር መንፈስ

የተነሣሣ አለመኾኑ ይታወቃል። ክርስትና፡ ስለአንድ ጉዳይ በማንሣት፡ "ይህን

ይመስላል!" ሲል፡ ቡዲዝም፥ ሒንዱይዝምና እስልምና ግን የሚናገሩት፡ ፈጽሞ ከዚህ የተለየ ነው።

ስለዚህ፡ እርስዎ በመልእክትዎ፦ “በበላይነትና ባጠቃላይነት፡ ኹሉን ዐቀፍ

በኾነው፡ በዚህ ኢትዮጵያዊነት፡ ማለትም፡ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ

ሃይማኖት ጸንተው የሚኖሩ ሰዎች ኹሉ፡ ስማቸው የተመዘገበበትና የሚመዘገብበት፡

የሕይወት መጽሓፍ እንዳለ የሚያረጋግጠው መለኮታዊው ቃል ነው። በዚህ፡

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋዮች ስም ዝርዝር፡ በተመዘገበበት

የሕይወት መጽሓፍ ውስጥ የተካተቱት የእምነት መሪዎች፡ ማንነታቸው፡ በመጽሓፍ

ቅዱስ፡ በክብር የተወሳው፡ የቅዱሳኑና የቅዱሳቱ ስም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን፡

ስማቸው፡ በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ሳይጠቀስ የቀረውንና ከመጽሓፍ ቅዱስ ውጪ

በኾኑት፡ በዓለም ሃይማኖቶችም ዘንድ ተጠቅሶ የሚገኘውን፡ ለምሳሌ፡ በአይሁድ፥

በቡድሃ፥ በሒንዱ፥ በክርስትናና በእስልምና፥ በሌሎችም እምነቶች ዘንድ የታወቁትን

ግለሰቦች ስም ጭምር፡ ያጠቃለለ ነው።

“...ይህ ዝክረ ነገር ሲታሰብና ሲወሳ፡ በኋለኛው ዘመን፡ ዘግየት ብለው

የደረሱት፡ ቡድሀን፥ መሓመድንና መኀትመ ጋንዲን የመሰሉት፡ ሌሎች ግለሰቦች፡

ከዚሁ ጎራ የሚመደቡ ስመ ጥር ተምሳሌቶች ይኾናሉ።” በማለት እንዳቀረቡት

ይትበሃል፡ ኹሉም እምነቶች፡ የአንዲቷ ሃይማኖት መገለጫዎች ኾነው መገኘት

አይቻላቸውም።

Page 8: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ጨርሶ፡ የክርስትና እምነት ያልኾነውን፡ ይህን አደናጋሪ ሃይማኖታዊ

ትምህርት፡ ከወዴት እንዳገኙት፡ እኔ አላውቅም። ፪ ዮሓንስ ፩፥ ፱-፲፩። “ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው

እግዚአብሔር የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት። ማንም

ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም

አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።”

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡-

ከላይ እንደተገለጸው፡ እስካኹን እየተነጋገርንበት ባለው፡ በአጠቃላዩ የውይይት

አርእስት ውስጥ፡ በእርስዎ በኩል፡ ቀደም ብለው፥ በማከታተልም ላቀረቧቸው

አስተያየቶችና ትችቶች፡ በእኛ በኩል፡ የተሰጡ ምላሾች አድርገው ይቀበሏቸው ዘንድ፡

ከዚህ በታች የሠፈሩትን መሠረታውያንና መነሻ የሚኾኑ መረጃዎችን፡

አቅርበንልዎታል፦

አንደኛ፤ እባክዎን፡ እዚህ ላይ፡ ሊያውቁትና ሊገነዘቡት የሚገባዎት ቁምነገር፡

እርስዎ፡ አኹን፡ ውይይትዎን እያካኼዱ ያሉት፡ የሚታየውን ምድራዊ ዓለምና

የማይታየውን ሰማያዊ ዓለም በሚያጠቃልለው፡ በመላው፡ የእግዚአብሔር ፍጥረታተ

ዓለማት ላይ፡ ሰፍና ከምትገኘው፡ ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ጋር ብቻ

መኾኑን ነው።

በዚህም፡ አዎ! በቅዱሱ ኪዳን፡ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሃይማኖትን

መሠረት ያደረገችውና በዚያ የተዋቀረችው፡ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡

በውስጧ፡ በመጽሓፍ ቅዱስ የሚመሩትን ብቻ ሳይኾን፡ የማይመሩትን የዓለም

ሃይማኖቶች ጭምር፡ ለምሳሌ፡ ጣዖት አምላኪን፡ ይሁዲን፡ ቡዲስትን፡ ሒንዱን፡

ክርስቲያንንና እስላምን፥ የመሳሰሉትንም ያካተተች ኾና፡ ከኹሉ ይልቅ፡ ጎልቶና በልጦ

በሚገኝ ብቅዓት፡ በመላው ፍጥረተ ዓለም ላይ የሰፈነችና ኹሉን አቀፍ የኾነች፡

መለኮታዊት አቋም ናት።

የሰይጣን ህልውና እና ምድራዊው የሥልጣን ክልሉ እንኳ ሳይቀር፡

በዚህ፡ ምንም በማይሳነው፥ ኹሉን ቻይና ወሰን በሌለው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት፡ ቁጥጥር ሥር ነው። ከተፈጠረውና በህልውና ካለው፡ ከማንኛውም

የፍጥረት አባል መካከል፡ ከዚህ የቍጥጥር እውነታ ውጪ ያፈነገጠ፡ አንዳችም ነገር፡

ከቶ የለም።

ለዚህም ነው፡ በአጠቃላይ፡ በመላው ዓለም ከሚገኙ ሃይማኖቶችና

ሥልጣኔዎች፥ በተለይም፡ ከአሕዛብና ከአይሁድ፥ ከክርስቲያኖችና ከእስልምና እምነት

ተከታዮች መካከል ወጥተው የሚንከራተቱ መጻተኞች፥ ለስደተኝነት መከራም

የተጋለጡ ሰለባዎች ኹሉ፡ በሃይማኖት ሰበብ፡ ይህን የመሰለው ችግርና መሰደድ

በደረሰባቸውና በሚደርስባቸው ጊዜ ኹሉ፡ ከአሳዶጆቻቸው ጥቃት የሚታደግ፡

አስተማማኝ መጠለያን፥ ዋስትና ያለውን ጥበቃም ለማግኘት፡ ወደኢትዮጵያ፡

Page 9: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

የእግዚአብሔር መንግሥት ያመሩና ይጓዙ፥ ይደርሱም የነበሩት፤ ዛሬም እንኳ ሳይቀር፡

በዚሁ ኹኔታ፡ እያደረጉ ያሉት። እርሷም፡ ተገቢውን ጥገኝነት፥ በተሟላ መልክና

ይዘት ታበረክት የነበረው፤ ዛሬም፡ እያበረከተች ያለችው።

በግእዝ፥ በኢትዮጵያኛና በእንግሊዝኛ ተጽፈው የሚገኙት፡

የኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያት፡ የቅዱሱ ኪዳን ጸሎቶች፥ ሌሎቹም ቅዱሳት

መጻሕፍት፡ ይህን መለኮታዊ እውነታ፡ በበለጠ አጉልተውና አጽንተው ያረጋግጣሉ፦

"ነአምን፡ በአሓዱ አምላክ፡ እግዚአብሔር አብወእም፡ አኀዜ

ኵሉ፥ ገባሬ ሰማያት ወምድር፡ ዘያስተርኢ፥ ወዘኢያስተርኢ።

"ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እግዚአብሔር ጸባዖት! ፍጹም ምሉእ

ሰማያተ፥ ወምድረ።"

"ኹሉን በያዘ፥ ሰማይንና ምድርን፥ የሚታየውንና የማይታየውን

በፈጠረ፡ አንድ አምላክ፥ አባትና እናትም በኾነው፡ በእግዚአብሔር እናምናለን።

"ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! አሸናፊ እግዚአብሔር! በሰማያትና

በምድር፡ ፍጹም የመላ ነው።" "We Ethiopians believe in One God, The Father and Mother,

Almighty Who possesses all, Maker of the Heavens and Earth, the visible

and the invisible.

"O Holy! Holy! Holy! God The Invincible Who is Wholly

Omnipresent in All Heavens and Earth!

አዎን! እንግዴህ፡ ከዚህ ቀጥለን፡ ስለመላው ፍጥረተ ዓለም ሠሪነቷና

ባለቤትነቷ፥ ስለስፍነቷና መጋቢነቷ፡ እንዲህ እያልን የምንናገርላት፡ ይህች ናት፡

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

-ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ/ት እና ኢትዮጵያዊነት፡ በአካል፥

በሰብኣዊነትና በነፃነት፡ እስከዛሬ የኖሩበት ዘመን፡ የ፯ሺ፭፻፯ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ

ሰባት) ዓመታት ዕድሜን ያጠቃለለ ሲኾን፡ አኹንም፡ በዘለዓለማዊነቱ ይቀጥላል፤

-ኢትዮጵያ፡ የቅድስት ድንግል ማርያም አርአያ፥ እንዲኹም፡

የእግዚአብሔር አብ ሙሽራ፤ የእግዚአብሔር ልጅ እናት እና የእግዚአብሔር መንፈስ

ቅዱስ ቤተ መቅደስ ናት፤

-ኢትዮጵያዊ/ት፡ ወንድ/ሴት፡ የእግዚአብሔር አምሳል የኾነውና

በእግዚአብሔር፡ “ከእኛ እንደአንዱ ኾነ” የተባለለት ሰውነት ነው፤

-የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት አካልነት ተገልጦ ያለ ነው።

ኹለተኛ፤ ራሷን፡ በሚያሳዝን ኹኔታ፡ በአራተኛው ምዕተ ዓመታት፡ በግብጽ

የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደተመሠረተችና የእርሷ ቅርንጫፍ ኾና፡

ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተቋቋመች የምትታወቀው፥ እስከዛሬና ዛሬ፥ ወደፊትም፡ በዚህ

መልኩ ልትቀጥል የወሰነችበት፡ ይህ ቆይታዋም፡ እስካኹን፡ ፩ሺ፮፻ ዓመታትን ያህል

ብቻ ያስቆጠረ ስለመኾኑ፡ በራሷ አረጋግጣ የሚነገርላት፥ እርስዎም፡ የኢትዮጵያ

Page 10: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማለት የሚጠሯት አይደለችም፡ ኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት።

አዎን! ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ በእነዚህና እነዚህን

በመሰሉ አስከፊና አስቸጋሪ ዕድሎች የተሰነካከለችውና የተበከለችው፡ የኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አለመኾኗን፡ በተጨማሪ መግለጹ፡ እጅግ

አስፈላጊ ቁምነገር ይኾናል።

ይኸውም፡ ይህችው፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ

ክርስቲያን፡ ቀደም አድርጋና በጊዜ ኺደት፡ ራሷን፡ ለአይሁዳዊው ትምህርትና ወግ

በማስገዛት፥ እውነተኛ ማንነቷንም፡ ለኦሪቱ ቀንበር አሳልፋ በመስጠት፥ እንዲያውም፡

በዘመነ ብሉይ ኪዳን እንደተቆረቆረች፡ አምና በመቀበልና ዛሬ ድረስ፡ በዚሁ ጎራ

ውስጥ ተዘፍቃ፡ ስትማቅቅ የኖረችበትን ዘመን፡ እንደገናናነት በመቍጠር፡ ይህ፡

የተገዢነት ማንነቷ ዕድሜ፡ ለ፫ሺ (ሦስት ሽህ) ዓመታት መብቃቱን፡ በዐዋጅ

ማረጋገጧን እንደቀጠለች የሚነገርላት መኾኑ ነው።

አዎን! ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ እውነተኞቹና

ታማኞቹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር

የተጋቡትንና ለብዙ ሺሆች ዓመታት ጠብቀው ያቆዩትን፡ ቅዱሱን ኪዳን፡ ባኹኑ

ሰዓት፡ በማናለብኝነት ድፍረት ጥሳና በገሃድ ዓመፅ ክዳ፡ ሰይጣናዊ ለኾነው፡

ለውሳጣዊውና ለአፍኣዊው፡ የዓለማውያኑ መንግሥታት ኃይል፡ በአሳፋሪ ኹኔታና

ሙሉ ለሙሉ፡ እጇን የሰጠችው፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

አይደለችም።

ሦስተኛ፤ እርስዎ፡ እንዲህ አዳንቀው እየተናገሩለት ያለው ባህል፡ ከቶ፡

የትኛው ይኾን? በአኹኑ ሰዓት ያለውን፡ "ኢትዮጵያዊ/ት ነኝ!" የሚለውን ሰው፡

ወንዱንም፥ ሴቲቱንም ስላፈራው ባህል ይኾን? እርሱም፡ ራሱን፡ ለባዕድ ያስገዛውንና

ከኢትዮጵያዊነት ውጪ፡ ልዩ ጕድ ፍጡር የኾነውን ኢትዮጵያዊ/ት? ወይስ፡ "ዘመናዊ

ነኝ!" የሚለውን የተቀረውን ኢትዮጵያዊ ትውልድ?

የእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት ባሕርይ ያልኾነውን፡ ተገዢነትን እንጂ፡

ነፃነትን የማይወድ፡ የበታችነት ስሜት ያደረበት፥ የቅዱሱን ኪዳን ተዋሕዶ

ሃይማኖቱንና ኢትዮጵያዊ ማንነቱን፡ በይፋ ክዶና ቀይሮ፡ ሓሰተኞቹ መንፈሳውያንና

ሥጋውያን ከኾኑት፡ ከባዕዳን የሃይማኖት ድርጅቶችና የመንግሥታት ኃይላት ጋር

የወገነውን፡ አጎብዳጅ ትውልድ ያስገኘውን፡ ባህል ነው፡ እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ ባህል"

የሚሉት?

ከራሱ ጕሥቍልናና የሙስና ዝቅጠት አልፎ ተርፎ፡ ይህን ዓይነቱን፡

ርካሽና አዋራጅ የኾነ ባዕድ ባህሉን፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ሕዝብ

ላይ፡ በረቂቅና በገሃድ ተፅዕኖ ለማዛመት በትጋት የሚራወጠውን፡ ይህን አስጠቂ

ትውልድ ያፈራውን ባህል ነው፡ እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ ባህል" የሚሉት?

Page 11: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ኧረ፡ ለመኾኑ፡ የትኛውን ዓይነት ባህል ነው፡ እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ

ባህል" የሚሉት?

በኦሪታውያኑ አይሁድ አማካይነት፡ ከዛሬ፡ ሦስት ሽህ ዓመታት ጀምሮ፥

በኦርቶዶክሳውያኑ ግብፆች አማካይነት ደግሞ፡ በቀደመው፡ የአምልኮ ባዕድ ቍስል

ላይ፡ ሌላ ጽኑ ቍስልን በመጨመር፡ ከዛሬ ሽህ ስድስት መቶ ዓመታት አንሥቶ፡

በቅዱሱ ኪዳን፡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች የኾኑትን፡ ኢትዮጵያውያንን እና

ኢትዮጵያውያትን፡ ለክፎና ተፃርሮ፡ ለዚህን ያህል ዘመን፡ እንዲህ፡ እንደዛሬው፡

እያናከሰና እያባላ፡ በነፍስና ሥጋ፥ በመንፈስም፡ ሲጠናወታቸውና ሲያሽመደምዳቸው፥

ሲያጥመነምናቸውና ሲያማቅቃቸው የኖረውን፡ የርኩሱን መንፈስ፡ ሰይጣናዊ ባህል

ነው፡ እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ ባህል" የሚሉት?

ታዲያ! የቱን ነው? እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ ባህል" የሚሉት?

የዛሬውን ትውልድ ጨምሮ፡ በእነዚያ፡ እየራሳቸውን፡ "ኢትዮጵያውያን

እና ኢትዮጵያውያት ነን!" እያሉ በሚጠሩት ትውልዶች ዘንድ፡ በአይሁድ

ኦሪታዊነቱ፡ ለሽህ አራት መቶ ዓመታት፥ በግብፃውያኑ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንነቱ

ደግሞ፡ ለሽህ ስድስት መቶ ሰባት ዓመታት፥ በድምሩ፡ ለሦስት ሽህ ሰባት ዓመታት፡

የተኖረበትን ነው? እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ ባህል" የሚሉት?

ያን፡ በግልም ኾነ በጋራ፥ በቤተሰብም ኾነ በኅብረተሰብ፥ በብሔረሰብም

ኾነ በአገር ደረጃ፡ አኹንም እንኳ፡ በእርስዎና በእኛ መካከል እየኾነ ባለው ዓይነት፥

እንዲህ፡ በስድብና በነቀፌታ፥ በጥላቻና በቂም በቀል ብቻ ካልኾነ በቀር፥ አዎን!

በመጨረሻውም፡ እርስ በርስ፡ ደም በመፋሰስና በመተላለቅ ካልኾነ በቀር፡ እስከዛሬና

ዛሬም ድረስ፡ በእኒሁ፡ "ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ነን!" በሚሉት፡

ሓሳውያን መካከል፥ በሰላምና በፍቅር፡ ለመቀራረብና ለመገናኘት፥ ቍጭ ብሎና

"እህ!" ተባብሎም በመደማመጥ፥ በጨዋነትና በሥርዓት፡ ለመነጋገርና ለመወያየት፥

ጽሑፍ ለመለዋወጥም ያልተቻለበትን፡ ይኼን መሰሉን፡ የችግር ኹኔታ ነው? እርስዎ፡

"ኢትዮጵያዊ ባህል" የሚሉት?

እንግዴህ፡ "ዘቦ ዕዝን፡ ሰሚዓ ለይስማዕ!" ማለትም፡ "የሚሰማ ጆሮ

ያለው፡ ይስማ!" ያለውን፡ የመምህራችንን፡ የመሢሕ ኢየሱስን ቃል፡ እርስዎም ኾኑ፡

እርስዎን የመሰሉት ኹሉ፡ ሰምታችሁ የምትፈጽሙት ከኾነ፡ ይኼ እውነታ፡ ምን

ዓይነቱን፡ ለሦስት ሽህ ዓመታት ተደብቆ የኖረ የጉድ ምሥጢርን እንዳወጣ፡ እስኪ

እንንገርዎ! (ማቴ. ፲፩፥ ፲፭።)

ይኼም ምሥጢር፡ እንደዛሬዎቹ አስመሳዮችና ግብዞች፡ "ሀገረ

እግዚአብሔር፥ ሕዝበ እግዚአብሔር፥ መንግሥተ እግዚአብሔር" በተባለችው፡

በኢትዮጵያ ምድር ላይ፡ ያለማቋረጥ በተካኼዱት፡ እነዚያን፡ ከላይ የተጠቀሱትን

በመሰሉት፡ አሠቃቂና ዘግናኝ፥ አስነዋሪና አሳፋሪ በኾኑት፡ የግድያና የዕልቂት

ድርጊቶችና ጦርነቶች የተሞላው ዜና መዋዕል፡ የሰዎች ደም ፈስሶ፡ ያን ጠጥቶ

መርካትን የሚወድደው፡ የርኩሱ መንፈስ፡ የክፋትና የጭካኔ፥ የጥፋትና የሞት ሥራ

Page 12: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

የተፈጸመበትና የተከሠተበት እንጂ፡ የመንፈስ ቅዱስ አለመኾኑን፡ ያለውልውል

ያረጋግጠዋል።

ለመኾኑ፡ እንዲህ ዓይነቱ ጕሥቍልና፡ እስከዛሬና ዛሬም፡ በዚሁ

መልኩ እንዲቀጥል እየተደረገ ያለው፡ ከቶ በማን ይመስልዎታል? እየራሳቸውን፡

በሓሰት፡ "ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ነን!" የሚሉትን ኹሉ፡ አካትታ

የያዘችው፡ በኢትዮጵያ ምድር፡ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፡ ቅርንጫፍ

የኾነችው፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኾኑት፡

ግብፃውያንና ኢትዮጵያውያን መነኮሳት አይደለምን? በእርግጥ፡ ነው እንጂ።

ይህ ግልጽ እውነታ፡ በእውነተኞቹ፡ የቅዱሱ ኪዳን

ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ዘንድ፡ በይፋ የሚታወቅ ነው። ይህን እውነታ፡

እስካኹን፡ እርስዎ አላወቁት እንደኾነ፡ እንግዴህ ወዲህ፡ ማወቅ ብቻ አይደለም፡

በጥብቅ ሊገነዘቡትም ይገባል።

እንግዴህ፡ እርስዎ፡ "ኢትዮጵያዊ ባህል" የሚሉት፡ ይህን ዓይነቱን

ከኾነ፡ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ በዚህ ረገድ፡ በፍጹም ቍርጠኛነትና

እርግጠኛነት የምትሰጥዎ፡ ቀጥተኛና ግልጽ መልስ፡ "የለም! አይደለምና፡ ስለዚህ፡

አትቀበለውም!" የሚል ነው።

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዘንድ፡ ይህ ዓይነቱ ባህል፡

የእግዚአብሔር ጠላቶች የኾኑ ባዕዳን የፈጠሩትና እነርሱ፡ በእውነተኞቹ የኢትዮጵያ

ልጆች ላይ፡ በተጽዕኖ ያኖሩት በመኾኑ፡ "እርሱ፡ የሰዎች ሥርዓት ያስገኘው፡

ሰይጣናዊው ልማድ ነው።" ብለን፡ በአጽንዖት እንናገራለን።

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ በጽኑ ተመሥርታ የቆመችበትና

ተገድግዳ የተደመደመችበት፡ የኹለንተና ህልውናዋ ጕልላታዊ ባህል፡ በቅዱሱ ኪዳን

ተዋሕዶ ሃይማኖት ከተገለጸው፡ ከእግዚአብሔራዊው እውቀትና ሥርዓተ ሕይወት ብቻ

የመነጨ በመኾኑ፡ ለልጆቿ ያሳወቀችውና የምታሳውቀው፡ ኢትዮጵያዊው ባህል፡

ይኸው፡ የመንፈስ ቅዱሱ ብቻ መኾኑ፡ ምንጊዜም ሊታመንበት ይገባል።

አዎን! ይህን ኹሉ ኃጢአትና ዓመፃ ያነሣሡትና የፈጸሙት፡ ሌሎች

ሳይኾኑ፡ በቅድሚያ፡ ላለፉት ሦስት ሽህ ዓመታት፡ በኢትዮጵያ የሰፈኑት፡ የብሉዩ

ኪዳን ተከታዮች የኾኑት፡ ኦሪታውያኑ አይሁድ ሲኾኑ፥ በቀጣይነትና በተደራቢነት

ደግሞ፡ ላለፉት ዐሥራ ስድስት ምእተ ዓመታት፡ የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ

የኾኑት፡ ኦርቶዶክሳውያኑ ግብፆች፥ በመጨረሻም፡ "ኃያላን ክርስቲያን መንግሥታት"

በመባል የሚታወቁት ናቸው።

እነዚህ ኹሉ ሥጋውያንና መንፈሳውያን የጥፋት ኃይላት፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ለኾነችው፡ ለኢትዮጵያ፡ አካሎቿ የኾኑትን፡ ራሷን፡ ኢትዮጵያን፥

የኢትዮጵያን ልጆችና ኢትዮጵያዊነትን፡ ከምድረ ገጽ ለመደምሰስ፡ እስከዛሬ ድረስ፥

ዛሬም፡ ይኸው ሲጥሩ ሲግሩ ይገኛሉ።

Page 13: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

አራተኛ፤ ስለዚህ፡ "የለም! አይኾንም! ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት፡ ይህን ዓይነቱን አስተሳሰብና ድርጊት፡ በየትኛውም መልክ ቢቀርብላት፡

ከቶ አትቀበለውም። በተቃራኒው ግን፡ ታወግዘዋለች!" ብለን እንደመድማለን።

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፡ እያንዳንዱ ሕያው

ኢትዮጵያዊ፥ እያንዳንዷም ሕያውት ኢትዮጵያዊት፡ ያው፡ በእየራሳቸው፡ ኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ናቸው። ይህም ማለት፡ አዎን! "እያንዳንዱ ሕያው

ኢትዮጵያዊ፥ እያንዳንዷም ሕያውት ኢትዮጵያዊት፡ ያው በእየራሳቸው፡ የሕያው

እግዚአብሔር መለኮታዊ ባህል፡ ሕያው መገለጫ፥ እንዲሁም፡ በቅዱሳት መጻሕፍት

የታቀፉትን፡ ሰባቱን ቃል ኪዳናት የያዘው፡ የ“ቅዱሱ ኪዳን” ሕያው መዝገብ

ናቸው!" ማለት ነው።

ከዚህ የተነሣ፡ ይኸው እያንዳንዱ ሕያው ኢትዮጵያዊ፥ ይህችው

እያንዳንዷ ሕያውት ኢትዮጵያዊትም፡ ማንኛውም ዓይነት፡ ሰብኣዊ ጽንሰ-ሐሳብ

ከፈጠረው፡ ተገዢነትን፥ ጭቆናንና ባርነትን እስከመቀበል፥ ራስንና ማንነትንም

እስከመካድ ከሚያደርሰው፡ ይህን ከመሰለው ሰይጣናዊ ባህል፡ ፈጽመው የነጹ ናቸው።

ይህ ብቻ አይደለም። ሕያው የኾነው ኢትዮጵያዊ፥ ሕያውት የኾነችውም

ኢትዮጵያዊት፡ ያው እርሱ፡ ራሱ፥ እርሷ፡ ራሷም፡ በእየራሳቸው በሚገኙበት ሰብአዊ

አካል፡ ሕያዉ የእግዚአብሔር መጽሓፍ ቅዱስ ናቸው።

ለዚህ እኮ ነው፡ በእግዚአብሔር መንግሥት፡ "የኢትዮጵያ ልጆች"

የተባሉት፥ በእየራሳቸውም፡ መጽሓፍ ቅዱስ፡ ሕያው የኾነበትን ሰብአዊ አካል

የተላበሱት፡ እውነተኞቹ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ሰው

የጻፈው መጽሓፍ ቅዱስ፡ ፈጽሞ አስፈልጓቸው የማያውቀው። እንዲህም፡

የተባለላቸው። ይህንም እውነታ፡ እግዚአብሔር፡ እንዲህ በሚለው ቃሉ ተናግሮታል፦

“እምድኅረ እማንቱ መዋዕል፡ ይቤ እግዚአብሔር፦ "እወዲ

ሕግየ፡ ውስተ ኅሊናሆሙ፤ ወእጽሕፎ፡ ውስተ ልቦሙ። ወእከውኖሙ አምላኮሙ፤

ወእሙንቱኒ፡ ይከውኑኒ ሕዝብየ። ወኢይምህር እንከ፡ እኍ፡ ወእኅዋሁ፡ እንዘ ይብል፦

'አእምርዎ ለእግዚአብሔር!' እስመ ኵሎሙ የአምሩኒ፤ ንኡሶሙ፥ ወዐቢዮሙ።"”

ማለትም፡ “ከእነዚያ ወራት በኋላ፡ እግዚአብሔር፡ እንዲህ

አለ፦ "ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ። በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔም፡ አምላክ

እኾናቸዋለሁ። እነርሱም፡ ሕዝብ ይኾኑኛል። እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥

እያንዳንዱም ወንድሙን፡ 'እግዚአብሔርን እወቅ!' ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ

እስከታላቁ ድረስ፡ ኹሉ ያውቁኛልና።"” (ኤር. ፴፩፥ ፴፩-፴፬፤ ዕብ. ፰፥ ፰-፲፪፤ ፲፥

፲፭-፲፮።)

አምስተኛ፤ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፡ ኢትዮጵያውያንና

ኢትዮጵያውያት፡ ከእንግዲህ ወዲህ፡ እየራሳቸውን፡ "አግዓዚ፥ ዐምሓራ፥ ወይንም

ክርስቲያን" በማለት አይጠሩም። የሚሉት፡ በቀላሉ፡ እየራሳቸውን፡ "ኢትዮጵያዊ"፥

ወይም፡ "ኢትዮጵያዊት" ብለው፡ በመጥራት ብቻ ነው።

Page 14: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ይህ የኾነበት ምክንያት፡ "አግዓዚ፥ ዐምሓራ፥ ወይም፡ ክርስቲያን"

የሚባለው፡ ቀድሞ፡ አረማዊ፥ ወይም፡ አሕዛብ፥ ወይም፡ ጣዖት አምላኪ፥ ወይም፡

ኢ-አማኒ (በእግዚአብሔር የማያምን)፥ ወይም፡ እንዲያውም፡ ይሁዲ፥ ወይም፡ እስላም

ከኾነው መካከል እንኳ ሳይቀር፡ ስለክርስቶስ ተምሮና አውቆ፡ የተማረውንና

ያወቀውንም፡ ተቀብሎትና አምኖበት፡ የጥምቀቱ ሥርዓት ተካኺዶ ሲጠናቀቅ፡

"አግዓዚ፥ ዐምሓራ፥ ወይም፡ ክርስቲያን" የሚል ስያሜ ስለሚስሰጠው ነው።

እንዲህ እንደመኾኑ፡ ይህ፡ አማናዊ ምክንያት፡ በእርግጥ፡

ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያውያትን ብቻ ለይቶ፡ ከዚህ ውጪ የሚያደርጋቸው

ከመኾኑ በስተቀር፡ አግዓዚዎች፥ ዐምሓሮች፥ ወይም፡ ክርስቲያኖች የነበሩትንና

ያልነበሩትን፥ የኾኑትንና ያልኾኑትን ኹሉ፡ በእርግጥ አካትቶ የሚመለከት እንደኾነ

መገንዘቡ፡ ለማንም አያዳግትም።

አዎን! መመሪያቸው፡ ብሉይ ኪዳን ከነበረው፡ ከአይሁድ ኦሪታዊ

እምነት አስቀድሞ፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ዓለምን የፈጠረውንና

የሚያስተዳድረውን፡ አንድ አምላክ የኾነውን፡ እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበረ። ይህም

ማለት፡ እነርሱ፡ የእግዚአብሔር አማኞችና እግዚአብሔርን የሚያመልኩ፡

የእግዚአብሔር ልጆችና ካህናት (አገልጋዮች) ናቸው። ይህ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ

በተጨማሪ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋዮችና ወራሾችም ናቸው እንጂ።

አብርሃምን አስተምሮ፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት እንዳበቃው፡

እንደኢትዮጵያዊው ካህን ንጉሥ፡ እንደመልከ ጼዴቅ፥ ለሙሴም፡ ተመሳሳዩን ምግባር

ፈጽሞለት፡ ለዚያ የኢትዮጵያዊነት ታላቅ ጸጋና ክብር እንዳበቃው፡ እንደኢትዮጵያዊው

ካህን ንጉሥ ዮቶር ኹሉ፡ ማለት ነው።

"ንግሥተ ሳባ" በሚል ስያሜ፡ በገናንነትዋ፡ እጅግ ታዋቂና ተደናቂ

የኾነችው፡ ንግሥት ማክዳ፡ ከላይ የተጠቀሱት፡ ስመ ጥሩዎቹ ቀደምቶቿ፡

እንዳደረጉት ኹሉ፡ እርሷም፡ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ለነበረው፡ ለእስራኤላዊው ንጉሥ

ሰሎሞን፡ ዘለዓለማዊ ሕይወቱን በሚመለከት፡ ላበረከተችለት፡ የተትረፈረፈ

ኢትዮጵያዊ ጸጋና በረከት፡ ሌላዪቱና መልካሚቱ፡ ኢትዮጵያዊት ተምሳሊት ናት።

እንዲህ እንደመኾኑ፡ ለመላዎቹ፡ የአዳምና የሔዋን ልጆች የተሰጡትን፡

ሦስቱንም፡ የቃል ኪዳን ማኅተሞች፡ ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥተው፡ በመቀበልና

በመጠበቅ፥ እስካኹንና አኹንም፡ በምድር ላይ፡ በእግዚአብሔር እምነትና አምልኮ

ጸንተው የሚገኙና የቀጠሉ፡ በእርግጥ፡ የቅዱስ ኪዳኗ ኢትዮጵያ ልጆች ብቻ ናቸው።

እኒህ፡ ሦስቱ፡ የቃል ኪዳን ማኅተሞች የተባሉት፦ የመጀመሪያው፡

በነፍስ፡ ማለትም፡ በቀደመው ዘመነ ልደት (ጥንተ ተፈጥሮ) ያገኘነው ኪዳነ ልቦና፥

ወይም፡ ኪዳነ ነፍስ፥ ኹለተኛው፡ በሥጋ፡ ማለትም፡ በመካከለኛው ዘመነ ኦሪት

ያገኘነው፡ ብሉይ ኪዳን፥ ወይም፡ ኪዳነ ሥጋ፥ ሦስተኛው፡ በመንፈስ፡ ማለትም

በፍጻሜ ዘመነ ምሕረት ያገኘነው፡ አዲስ ኪዳን፥ ወይም፡ ኪዳነ መንፈስ ናቸው።

Page 15: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ከእነዚህ፡ ከሦስቱ፡ መለኮታውያት የቃል ኪዳናት ማኅተሞች የተነሣ

ነው፡ እኒሁ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ገና ከፍጥረት ጀምሮ፡

“የእግዚአብሔር ልጆች” በመባል ተለይተው የታወቁት፤ ኋላም፡ “የኢትዮጵያ

ልጆች” የሚለው ስም የተሰጣቸው፤ በመጨረሻም፡ ዛሬ፡ በቀላሉ፡ “ኢትዮጵያውያን

እና ኢትዮጵያውያት” በመባል የሚታወቁት። (ዘፍጥ. ፮፥ ፩-፬፤ አሞ. ፱፥፯።)

ስድስተኛ፤ እውነታው፡ ይህ ኾኖ ሣለ፡ ነገር ግን፡ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ

በኾኑት ክርስቲያኖች ዘንድ፡ በክርስትና ስምና በእምነቱ ረገድ፡ በመላው ዓለም

እየተካኼደ ባለው፡ የተለያየ፡ አሳፋሪና ነውር የተመላበት፡ የግብዝነት ድርጊት

ምክንያት፡ የራሱ፡ የክርስትና፡ የስም አጠራሩና የሃይማኖቱ ነገር፡ ምን ያኽል

እንደተዋረደና እንደተናቀ፡ አጠያያቂም እንደኾነ፡ በውኑ አስተውለውታልን?

እስኪ፡ በዚህ ረገድ፡ አንድ ምሳሌን፡ ለናሙና ያኽል እናቅርብልዎ!

ይኸውም፡ እጅግ በዝቶ ከሚገኘውና ከክርስትና ተግባር ጋር ጨርሶ ተዛማጅነት

ከማይኖረው፥ ኾኖም፡ በጭካኔ ከተፈጸሙ በርካታ ድርጊቶች መካከል የሚገኘውን፡

አንዱን ዝክረ ነገር ብቻ ነው፦

ያም፡ በአንድ ወገን፡ በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ፡ እራሷን፡

ከኃያላኑ ክርስቲያን አህጉር፡ አንዷ አድርጋ፥ "ክርስቲያናዊ" በተባለ መንግሥትና

በብሔራዊ ቤተ ክርስቲያን የምትመራው፥ የምትተዳደረውም፡ የሕዝበ ክርስቲያን

አገር፥ እንዲሁም፡ የጋራ ብልጽግና አገሮች ንግሥተ ነገሥታትና የተባበሩት የደሴቲቱ

ነገሥታት፡ የበላይ ገዢ የኾነችው፥ "ታላቋ ብሪታንያ" በመባልም የምትታወቀው

እንግሊዝ የፈጸመችውን ያሳያል።

በሌላው ወገን ደግሞ፡ "ሒንዱዎች" በሚባሉት፡ በሕንድ አገር፡

የትእልፊት አእላፋት ሕዝብ ላይ፡ በእንግሊዝ የተፈጸመባቸውን የሚያሳይ ሲኾን፡

እኒህን፡ የድርጊቱን ኹለት ገጽታዎች፡ ከፊት ለፊታችን አስቀምጠን፥ በቅዱሱ ኪዳን

የኢትዮጵያዊነት ፍትሕ ሚዛናችንም፡ አነጻጽረን ተመልክተን፡ ርቱዕ ብያኔያችንን፡

በየኅሊናችን እንሰጥ ዘንድ፡ ከእርስዎም፥ ከእኛም ይጠበቃል።

ይህን በተመለከተ፡ እስኪ፡ ከዚህ የሚከተለውን፡ አንድ ቀላል ጥያቄ

ላቅርብልዎ! ጥያቄውም፡ ከላይ ለተነሣው ጉዳይ፡ በእርስዎ በኩል፡በራስዎ፡ ያልተዛባና

የማያዳላ፡ ሚዛናዊ አእምሮዎ፡ በትክክል የሚሰጡት መልስ ነው። ጥያቄውም፡ እንዲህ

የሚል ነው፦ በትስብእት፡ የድንግል ማርያም ልጅ ኾኖ፡ በሰውነት በተገለጠው፡

በእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ዓይን፡ እውነተኛው ክርስቲያን፡ የትኛው ነው ይላሉ?

የእግዚአብሔር ፍጡራን መኾናቸው ቀርቶ፡ በቅኝ ግዛት ሰለባነት፡

በሕንድ የትውልድ አገራቸው የሚኖሩ፡ የትእልፊት አእላፋት ሒንዱዎችን በመወከል፥

እንዲሁም፡ በክርስቶስ ሰውነት ለተከሠተችው መለኮታዊት እውነት፡ በታማኝነት ጸንቶ

በመገኘት፡ ራሱን በሰማዕትነት አሳልፎ የሰጠው፡ መኀትመ ጋንዲ፡ ከወገቡ በታች

Page 16: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ብቻ፡ ቍራጭ ጨርቅን አገልድሞ፡ በዳኝነቱ ሚዛን ፊት፡ ባዶ እግሩን፡ በአንድ በኩል

ቆሟል።

በሌላው በኩል ደግሞ፡ ክርስቲያናዊት የኾነችውን፡ ታላቋ

ብሪታንያንና ሕዝቧን በመወከል፡ በእነዚያ ጥቁ ሕዝቦች ላይ፡ የተለያየ ግፍን

የፈጸመው፡ ክርስቲያኑ ንጉሥ ጆርጅ፡ በወርቅ የተንቈጠቈጠ የግርማ ሞገስ ልብሱን

ተጎናጽፎና ጫማውን ተጫምቶ፥ ዘውዱንም ደፍቶ፡ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይታያል።

ታዲያ! በእርስዎ የዳኝነት ሚዛን፡ ምን አሉ? እባክዎን! እስኪ

ይንገሩኝ? ከኹለቱ ሰዎች የትኛው ነው እውነተኛው ክርስቲያን? ራሱን፡ “ክርስቲያን”

በማለት የጠራው፡ እንግሊዛዊው ንጉሥ ጆርጅ ነውን? ወይስ፡ ክርስቲያን አለመኾኑ

ተረጋግጦ፡ “ሒንዱ” የሚለው፡ መለያ ስያሜ የተሰጠው፡ ሕንዳዊው፡ መኀትመ

ጋንዲ?

እንግዲህ፡ እውነተኛው ክርስቲያን፡ ማንኛቸው ስለመኾናቸው፡

ለይቶ ለማወቅ ያስችለን ዘንድ፡ በዚህ ረገድ፡ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ የሰጠውንና

አግባብነት ያለውን፡ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን፡ መለኮታዊ መመሪያ ልንመለከተው

ያስፈልገናል። ይህ፡ የእግዚአብሔር ቃል፡ እውነተኛው ክርስቲያን፡ በአጋጣሚ

የመረጥነው፡ የስም ክርስቲያኑ፡ ነገር ግን፡ ቅኝ ገዢው፥ ጨቋኙና ጨፍጫፊው፡

እንግሊዛዊው ንጉሥ ጆርጅና እርሱን የወከለው፡ የእንግሊዝ ሕዝብ ስለመኾኑ፡

ወይንም፡ እንዲሁ፡ በአጋጣሚ የመረጥነው፡ ታማኙ ሒንዱው የሕንድ መሪ፡ መኀትመ

ጋንዲና እርሱ የተወከላቸው፡ ቅኝ ተገዢዎቹ፥ ተጨቋኞቹና ተጨፍጫፊዎቹ፡

ሒንዱዎቹ፡ የሕንድ ሕዝብ ስለመኾናቸው ለይቶ ለማወቅ ያስችለናል።

አግባብነት ያለው፡ መለኮታዊው የኢየሱስ ክርስቶስ መመሪያ፡

እንዲህ ይነበባል፦

“ተዐቀቡኬ! እምሓሳውያነ ነቢያት፡ እለ ይመጽኡ

ኀቤክሙ፡ በአልባሰ አባግዕ፤ ወእንተ ውሥጦሙሰ፡ ተኵላት መሰጥ እሙንቱ።

ወእምፍሬሆሙ፡ ተአምርዎሙ።

“ይቀሥሙሁ እምአሥዋክ፡ አስካለ!? ወእምአሜከላ፡

በለሰ!? ከማሁኬ! ኵሉ ዕፅ ሠናይ፡ ፍሬ ሠናየ ይፈሪ፤ ወእኩይሰ ዕፅ፡ ፍሬ እኩየ

ይፈሪ። ኢይክል፡ ዕፅ ሠናይ፡ ፍሬ እኩየ ፈርየ፤ ወኢዕፅ እኩይ፡ ፍሬ ሠናየ ፈርየ።

ኵሉ ዕፅ፡ ዘኢይፈሪ፡ ፍሬ ሠናየ፡ ይገዝምዎ፤ ወውስተ እሳት ይወድይዎ።

ወእምፍሬሆሙ እንከ! ተአምርዎሙ።

“አኮ ኵሉ ዘይብለኒ፡ "እግዚኦ! እግዚኦ!" ዘይበውእ

ውስተ መንግሥተ ሰማያት፣ ዘእንበለ ዘይገብር ፈቃዶ፡ ለአቡየ ዘበሰማያት።

“ወብዙኃን ይብሉኒ፡ በይእቲ ዕለት፦ "እግዚኦ! እግዚኦ!

አኮኑ በስምከ ተነበይነ? ወበስምከ፡ አጋንንተ አውጻእነ? ወበስምከ፡ ኀይላተ ብዙኀ

ገበርነ?"

Page 17: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

“ወይእተ ጊዜ፡ እብሎሙ፦ "ግሙራ ኢየአምረክሙ።

ረኃቁ እምኔየ ኵልክሙ፡ እለ ትገብሩ ዓመፃ!

ማለትም፡ “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፥

በውስጣቸው ግን፡ ነጣቂዎች ተኵላዎች ከኾኑ፡ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።

ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።

“ከእሾህ፡ ወይን፥ ከኵርንችትስ፡ በለስ ይለቀማልን?

እንዲሁ፡ መልካም ዛፍ ኹሉ፡ መልካም ፍሬ ያደርጋል፤ ክፉም ዛፍ፡ ክፉ ፍሬ

ያደርጋል። መልካም ዛፍ፡ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ፡ መልካም ፍሬ

ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬን የማያደርግ ዛፍ ኹሉ፡ ይቆረጣል፤ ወደእሳትም

ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።

“በሰማያት ያለውን፡ የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፣

"ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!" የሚለኝ ኹሉ፡ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

“በዚያ ቀን፡ ብዙዎች፡ "ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ፡

ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ፡ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ፡ ብዙ

ተአምራትን አላደረግንምን?" ይሉኛል።

“የዚያን ጊዜም፡ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥

ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” (ማቴ. ፯፥ ፲፭-፳፫።)

እንደ ተጨማሪ ምሳሌ፡ ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት

ጋር፡ የበለጠ ተቀራራቢነት ለሚኖረው፡ ለቡድሃ ሃይማኖት፡ ተመሳሳይ የኾነ መግለጫ

ሊሰጠው ይችል ይኾናል። በተለይ፡ ስለሕይወት እና ስለመለኮታዊ መንግሥት፡ ያለው

ጽንሰ ሓሳብ፥ ስለተግባራዊነቱም፡ ከምሥራቅና ከምዕራብ ክርስቲያን አገሮችና

ከአብያተ ክርስቲያናቶቻቸው ጋር ሲነጻጸር ማለት ነው።

ሰባተኛ፤ እየተነጋገርንበት ስላለው ጉዳይ፡ መነሣት የሚገባው፡ የቀረ፡ አንድ

ቁም ነገር አለ። ይኸውም፡ መሥራቹና መሪው፡ መሓመድ የኾነው፡ የእስልምና

ሃይማኖት፡ እንደሌሎቹ ሃይማኖቶች፡ በምድር ላይ የመከሠቱ ምሥጢራዊ ዓላማ ነው።

የቀደሙት፡ "ክርስቲያኖች" የተባሉት የዓለም ሕዝብ ወገኖች፡ በአንድ

በኩል፡ መንፈሳውያንና ሃይማኖታውያን ተቋማት የኾኑትን አብያተ ክርስቲያኖቻቸውን፥

በሌላው በኩል ደግሞ፡ ሥጋውያንና ዓለማውያን ድርጅቶች የኾኑትን

መንግሥቶቻቸውን፡ በአንድነት አስተባብረው ይዘው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ላይ፡ ምን ሊያደርጉ፡ ዐቅደውና ዓልመው እንደነበረ፡ ሊያውቁ ይሻሉ?

ያም ዕቅዳቸውና ዒላማቸው፡ ፈጽሞ ሰይጣናዊ እንደነበረ፥ ዛሬም፡

እየኾነ እንዳለ፡ እርስዎ፡ እውነታውን፡ በእርግጥ፡ ተረድተው፥ ጉዳዩንም፡ በትኵረት

ተመልክተው፡ ሊያብሰለስሉት ይፈልጋሉ?

የሚፈልጉ ከኾነ፡ ይህን ርእሰ ነገር በሚመለከት ያለው፡

እግዚአብሔራዊው እውነታ፡ ይኼውልዎ! የዚያ፡ ከላይ የተጠቀሰው ውጥን ዓላሚዎችና

ደጋፊዎቻቸው፡ ያን፡ እኩይ የዘመቻ ዓላማቸውን፡ በቅድስት ኢትዮጵያ ላይ ለመጀመር

Page 18: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ተዘጋጅተው የነበረበት ጊዜ፡ በ፬ኛውና በ፭ኛው ክፍለ ዘመን ገደማ ሲኾን፡ ያም ዘመን፡

አስነዋሪው የእነርሱ ኃያልነት፡ ከመጨረሻው ከፍተኛ የልዕልና ደረጃ የደረሰበት ጊዜ

እንደነበረ ይታወቃል።

በዚያ ዘመቻቸውም፡ ዓላማቸው፡ የእግዚአብሔር መንግሥት

ኢትዮጵያን፡ ቢቻል፡ እንደዛሬው ኹሉ፡ በበጎ ጎኑ አንጻር ሲመለከቱት፡ ሙሉ

በሙሉ፡ የእነርሱ የግዛት አካል አድርገው ለመጠቅለል፥ ምናልባት ግን፡ ያ ምርጫቸው

ሊሳካላቸው ሳይችል ቢቀር፡ በክፉ ጎኑ አንጻር በተመለከቱበት ዓይናቸው፡ እርሷን፡

ከምድረ ገጽ፡ ፈጽመው ለመደምሰስ እንደነበረ፡ እርስዎ፡ ይህን እውነታ ሲገነዘቡ፡

ከኢትዮጵያዊነትዎ የተነሣ፡ በእርግጥ፡ በውስጥዎ፡ ከፍተኛ፡ የመንፈስ ማዕበላዊ ነውጥና

ሁከት፥ ድንጋጤና ሽብር ተነሣሥቶ፡ እንደሚያጥለቀልቅዎ ይታመናል።

አዎን! ዘመቻው የተጀመረው፡ በአንድ ወገን፡ በሮማዊው የካቶሊክ

ቤተክርስቲያን ንጉሠ ነገሥታዊ መንግሥት፥ በሌላኛው ወገን ደግሞ፡ በባዛንቲኑ የግሪክ

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ንጉሠ ነገሥታዊ መንግሥት፡ ጥምር አዝማችነት ሲኾን፥

የእግዚአብሔርና የድንግል ማርያም ልጅ የኾነውን፡ ኢየሱስ ክርስቶስን "አንቀበልም"

በማለት፡ ለአረማውያኑ ሮማውያን፡ አሳልፈው ለስቅላት ሞት የዳረጉትን አይሁድን

ጭምር ያስተባበረ፥ አረማውያንንም ሳይቀር ያሳተፈ ነበረ።

ከላይ ለተወሳው፡ በመላው የዓለም አብያተ ክርስቲያናትና የዓለም

መንግሥታት ኅብረት ለተቀነባበረው፡ ለዚህ፡ "ሃይማኖታዊ" ተብዬው ጠንቀኛና

የርኵሰት ዘመቻ፡ በቀዳሚ መሪነት፡ ቀንደኛዎቹ መንገድ ጠራጊዎችና አቀናጆች

ኾነው፡ የፊታውራሪነቱን ሚና ይዘው የሚያጋፍሩት፥ ዛሬም፡ እያጋፈሩ ያሉት፡ የግብፅ

ቅብጣዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን "ጳጳሳት" የተባሉት፡ የበላይ ኀላፊዎቿ ናቸው።

በዚያን ጊዜ የተከሠተው ይህ ድርጊት፡ ከዚያን በፊት፡ ከብዙ ዘመናት

አስቀድሞ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፡ ተመሳሳይ የኾነ ውጤትን

እንዲያመጣ ታቅዶ፡ የተፈጸመ ሌላ የዘመቻ ሴራ እንደነበረ፣ ያም የዘመቻ ሴራ፡

በተወሰነ ደረጃ ተሳክቷል ለማለት የሚያስደፍር፡ በአይሁድ የተካኼደው እንደነበረ፡

እዚህ ላይ፡ ሊጤን ይገባል።

እንዲያው ለመኾኑ፡ ከላይ የተጠቀሱት፡ እነዚህ፡ የጥፋት

አውጠንጣኞችና ሴረኞች፡ ሰላማዊና ታማኝ፥ እግዚአብሔርን አምላኪና አፍቃሪ

በኾነው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ደግ ሕዝብ ላይ፡ ይህን መሰል፡

እጅግ ከባድና ተንኮልን ያዘለ፥ ጽኑዕ ኃጢኣተኛም የሚያደርግ፥ ሥውር የጥቃት ደባን

ለመፈጸም፡ እንዲህ፡ በጥምረት ያነሣሣቸው ምክንያት፡ ከቶ ምንድን ነው?

ለዚህ የከረረ ጥላቻ፡ አሳማኝ የኾነ፡ ብቸኛና ምክንያታዊ ምላሽ ሊገኝ

የሚችለው፡ ከሌላ ሳይኾን፡ ከዚህ ከሚከተለው፡ መለኮታዊ እውነት ነው። ይኸውም፦

ኢትዮጵያ፡ ምንጊዜም፡ በማይናወጸው ቆራጥ አቋሟ፡

"እስመ ለእግዚአብሔር መንግሥት፤ ወውእቱ ይኴንኖሙ ለአሕዛብ።"

ማለትም፡"መንግሥት፡ ለእግዚአብሔር ናትና፤ እርሱም፡

አሕዛብን ይገዛል።"

Page 19: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ማለትም፡ "For THE KINGDOM IS THE LORD'S, and

He rules over the nations." የሚለውን መለኮታዊ ቃል፡ ከኹሉ አብልጣ፡ ያላንዳች

ማመንታት፡ እስከ ዘለቄታው ድረስ በመከተል፡ “የእግዚአብሔር መንግሥት” ኾና

ለመኖር፡ ባደረገችው ምርጫዋ፡ በመጽናቷ ብቻ ነው። (መዝ. ፳፩፥ ፳፰። Ps. 22/28.)

አዎን! በዚህ፡ በመለኮታዊው እውነት መሠረት፡ የቅዱሱ ኪዳን

ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ብቻ፡ እየራሳቸውን፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ምንነታቸውና ማንነታቸው አጽንተው፥ በዚህ አቋማቸውም፡ ፍጹም

ታማኞች ኾነው፡ በእውነተኛነታቸው ሲቀጥሉ፡ ከላይ እንደተገለጸው፡ በምድር ላይ

ያለው፡ በአጠቃላይ፡ መላው የሰው ዘር ወገኖች፥ በተለይ ግን፡ የተቀረው፡ የክርስቲያኑ

ዓለም ተብዬዎቹ፡ በእርሱ፡ በራሱ፡ በእግዚአብሔር የተመሠረተውን፡ ይህን፡

መለኮታዊ የሥርዓተ መንግሥት አቋም ትተው፡ ፈጽመው ገሸሽ አሉ።

ይህ ብቻ ሳይኾን፡ ከላይ የተጠቀሱት፡ እነዚያው፡ መላው የክርስቲያኑ

ዓለም ሕዝቦች፡ ባለመለያየት ተባብረው፡ በመለኮታዊው ሥርዓት፡ አንዲት

የኾነችውን፡ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን፡ ለኹለት በመክፈል፡

አንደኛውን፡ “መንፈሳዊ” ወይም “ቤተ ክርስቲያን” ብለው በመሠየም፡ በቤተ ክህነት

የማዕርጋት መዋቅር እንዲመራ ሲያደርጉ፥ ኹለተኛውን ደግሞ፡ “ሥጋዊ” ወይም

“ዓለማዊ አገዛዝ” በሚል ስያሜ በመጥራት፡ ኢአማንያን በኾኑ የጨዋዎች መንግሥት

እንዲካኼድ አድርገዋል።

"የቀደሙት ክርስቲያኖች" ተብለው የሚጠሩት፡ እነዚያ የክርስቲያኑ

ዓለም ወገኖች፡ ያደረጉትን፡ ያን፡ ተመሳሳይ፡ የጥቃት ዘመቻ፡ በሃይማኖታዊ

አቋምነታቸው፡ "ኦርቶዶክስ፥ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት" የተባሉት የዛሬዎቹ

መሰሎቻቸው አብያተ ክርስቲያናት፡ ባኹኑ ሰዓት፡ ከቀደሙት እንዳዩትና

እንዳስለመዱት፡ አቻዎቻቸውና ተባባሪዎቻቸው ከኾኑት፡ ከዓለማውያኑ የመንግሥታቱ

ድርጅቶች ጋር በመመሣጠር፡ ተዳምረው፡ የጥፋታቸው ጥንተ ዒላማና ሰለባ

በኾነችው፡ በዚያችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፡ በአዲስ መልክ

እያካኼዱ እንደሚገኙ ያውቃሉን?

ይህኛውን አዲሱን ዘመቻ፡ ከቀድሞው ለየት የሚያደርገው፥ ደግሞም

በጣሙን የሚያስገርመው፡ ትብብሩ፡ አይሁድን፥ አሕዛብንና አረማውያንን ብቻ

ሳይኾን፡ በይበልጥና በገሃድ፡ በኢትዮጵያ፡ የግብፅ ቅብጣዊት ኦርቶዶክስ ቤተ

ክርስቲያን ቅርንጫፍ የኾነችውን፡ የዛሬዪቱን፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ

ክርስቲያንን ጨምሮ ያካተተ መኾኑ ነው።

በሰው ልጅ ህልውና ውስጥ፡ እስከዛሬ ባለፈው፥ አኹን ባለውና

ወደፊትም እየተከታተለ በሚደርሰው የዘመን ኺደት፡ ግፍ የተመላበት የክፋትና

የኃጢኣት፥ ይህን ዓይነቱም ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙና ኹኔታውም ከዕለት

ወደዕለት እየተባባሰ መቀጠሉ፡ ለምንድን ነው?

መልሱ፡ ከዚህ በታች በሠፈረውና በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ላይ፡ እስከዛሬ ሲፈጸም የኖረውን፥ ዛሬም፡ እየተካኼደ ያለውን ደባና

Page 20: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ጥቃት አጋልጦ በሚያሳየው፡ እንዲህ በሚለው፡ የእግዚአብሔር ቃለ ትንቢት ውስጥ

ተጽፎ ስለሚነበብ፡ ይህንኑ፡ በአንክሮና በተዘክሮ፥ በትኵረትና በተመሥጦ መመልከት

ነው፦

"ለምንት አንገለጉ አሕዛብ? ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ? ወተንሥኡ

ነገሥተ ምድር። ወመላእክትኒ ተጋብኡ ምስሌሆሙ ኅቡረ፤ ላዕለ እግዚአብሔር፥

ወላዕለ መሢሑ፦ 'ንበትክ እምኔነ ማእሰሪሆሙ! ወንገድፍ እምላዕሌነ አርዑቶሙ!'

"ወእግዚአብሔር ይሣለቅ ላዕሌሆሙ፤ ሶበ ይነብቦሙ በመዓቱ፥

ወበመዓቱ የሀውኮሙ።

"'አንሰ ተሠየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ፤ በጽዮን፡ በደብረ መቅደሱ፤

ከመእንግር ትእዛዞ ለእግዚአብሔር። እግዚአብሔር ይቤለኒ፦ ‹ወልድየ አንተ! ወአነ

ዮም ወለድኩከ! ሰአል እምኔየ፡ እሁበከ አሕዛበ፡ ለርስትከ። ወምኵናኒከኒ እስከአጽናፈ

ምድር። ወትርዕዮሙ በበትረ ኀጺን፤ ወከመንዋየ ለብሓ ትቀጠቅጦሙ።›'

"ወይእዜኒ፡ ነገሥት ለብዉ! ወተገሠፁ ኵልክሙ፡ እለ ትኴንንዋ

ለምድር! ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሀት! ወተሓሠዩ ሎቱ በረዓድ! አጽንዕዋ

ለጥበብ፡ ከመኢይትመዐዕ እግዚአብሔር! ወኢይትትሀጐሉ እምፍኖተ ጽድቅ! ሶበ

ነድደት ፍጡነ መዓቱ።

"ብፁዓን ኵሎሙ፡ እለ ተወከሉ ቦቱ።"

ማለትም፡ "አሕዛብ ለምን ጕባኤ አደረጉ! 'የእግዚአብሔር

ወገኖች ነን!' የሚሉ ሕዝቦችስ ተሰባስበው፡ ለምን፡ ስለከንቱ ነገር ይነጋገራሉ? እነዚህ

የምድር መንግሥታት፥ ከእነርሱም ጋር ገዢዎችና ባለሥልጣኖች በአንድነት ተባብረው፦

"ኑ! እኛን ያሠሩበትን ገመዳቸውን፡ ከእኛ እንበጥስ! በላያችን ያኖሩትንም ቀንበር፡

አውርደን እንጣል!' እያሉ፡ በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ፡ በክህደትና በዓመፅ

ተነሣሡ!

"በሰማያት የሚኖረው እግዚአብሔር ግን፡ ይሥቅባቸዋል፤

ይሣለቅባቸዋልም። በቍጣው ይናገራቸዋል፤ በመዓቱም ያውካቸዋል። የእግዚአብሔርን

ትእዛዙን እነግራቸው ዘንድ፡ የመቅደሱ ተራራ በኾነችው፡ በጽዮን፡ በላያቸው፡ ንጉሥ

አድርጎ ለሾመኝ ለእኔ፡ እርሱ እግዚአብሔር፡ እንዲህ ይለኛል፦ 'አንተ፡ እኔ ዛሬ

የወለድሁህ ልጄ ነህ! ለምነኝ! አሕዛብን፡ ለርስትህ፥ ግዛትህንም፡ እስከምድር ዳርቻ

እሰጥሃለሁ። ደጋጎቹን፡ በመልካሙ በትረ መንግሥትህ ትጠብቃቸዋለህ፤ ክፉዎቹንም፡

እንደሸክላ ሠሪ ዕቃ ትቀጠቅጣቸዋለህ።'

"እንግዴህ፡ እናንት፡ የዓለም መንግሥታት መሪዎችና ሕግ

አስፈጻሚዎች የኾናችሁ ኹሉ፡ ልብ አድርጉ! በምድር ላይ ባሉ አህጉር ኹሉ፡

አማካሪዎችና ሕግ አውጪዎች፥ ሕግ ተርጓሚዎችና ፈራጆች የኾናችሁ ኹሉ፡ ተገሠፁ!

ኹላችሁም፡ ለእግዚአብሔር፡ በፍርሃት ተገዙ! በፍርሃት በመገዛታችሁም፡ ደስ ይበላችሁ!

ከእርሱ የእውነት መንገድ በመውጣታችሁ፡ እርሱ እንዳይቈጣ፥ ቍጣውም ፈጥና፡

በላያችሁ እንዳትነድድባችሁ፡ የእግዚአብሔርን እውቀትና ጥበብ አጽንታችሁ ያዙ!

"በእግዚአብሔር የታመኑና የተማመኑ ኹሉ፡ ብፁዓን ናቸው።"

Page 21: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

"Why do the nations rage? And the people plot a vain

thing? "The kings of the earth set themselves, and the rulers take counsel

together, against The Lord and against His Anointed, saying, 'Let us break

Their Bonds in pieces and cast away Their Cords from us!'

"He Who sits in the Heavens shall laugh; The Lord shall

hold them in derision. Then He shall speak to them in His wrath, and distress

them in His deep displeasure:

"'Yet, I have set My King on My Holy Hill of Zion. I will

declare the decree: The Lord has said to Me, ‹You are My Son; today, I have

begotten you. Ask of Me; and I will give You the nations for Your inheritance,

and the ends of the earth for Your possession. You shall break them with a

rod of iron; You shall dash them to pieces like a potter's vessel›'

"Now therefore, be wise, O kings! Be instructed, you

judges of the earth! Serve The Lord with fear! And rejoice with trembling;

Kiss The Son, lest He be angry, and you perish in the way, when His wrath is

kindled but a little.

"Blessed are all those who put their trust in Him." (መዝ.

፪፥ ፩-፲፪። Ps.2/1-12.)

ስምንተኛ፤ ይህን በመሰለ ወሳኝ ወቅት ነበረ፡ መሓመድ፡ እስልምናን አንግቦ፥

ኃይልን ታጥቆና ሰይፍን ጨብጦ፡ በዐረብ ምድረ በዳ እንዲነሣ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ኢትዮጵያ፡ ፈጣሪዋና አምላኳ የኾነው፡ እግዚአብሔር፡ የፈቀደው።

ለምን ፈቀደ? መሓመድ፡ በዐረብ ምድረ በዳ፡ እስልምናን አንግቦ፥

ኃይልን ታጥቆና ሰይፍን ጨብጦ፡ ለምን፡ በድንገት ተነሣ? እንዲነሣ፡ መንሥኤ

የኾነው ምክንያትስ፡ ከቶ ምንድር ነው?

አዎን! የእዚህ ጥያቄ መልስ፡ አንድ እና አንድ ብቻ ነው። እርሱም፦

በመጀመሪያ፦ በቀጥታ፡ በእግዚአብሔር ላይ፡ በጠላትነት

በመነሣሣት፡ በቅድስት ድንግል ማርያም እና በተወዳጅ ልጇ በኢየሱስ መሢሕ፡ የሥጋ

መሥዋዕትነትና የደም ቤዛነት ታድሳ የጸናችውን፥ ይህችን፡ ለ፯ሺ፭፻፯ ዓመታት

ዕድሜ የበቃችውን፥ ጥንታዊቷን፥ የዛሬዪቷንና ዘለዓለማዊቷን፡ ኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥትን፡ በአስፈሪው የእልቂት ዘመቻቸው፡ ሊያጠፏት

የተዘጋጁትን፡ ከላይ የተገለጹትን፡ የጥፋት ግብረ-ዐበሮች ለመቅጣት፥

በመጨረሻም፡ ይህችኑ፡ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን፡

ከእነዚሁ፡ የክፋት አበጋዞች፡ ሠውሮ ለመጠበቅ እና ተከላክሎ ለማዳን መኾኑን፡

"ኢትዮጵያዊ/ት ነኝ!" የሚለውን፡ ይህን፡ የዛሬውን ከሃዲና ዐመፀኛ፥ አመንዛሪና ክፉ

ትውልድ ጨምሮ፡ ለመላው የዓለም ሕዝብ ኹሉ፡ በይፋ የታወቀ ይኹን!

አዎን! ከዚህ የተነሣ፡ ዕድሉ ኾኖ፡ ለእስልምና መሥራችነትና መሪነት

የተመረጠው መሓመድ፡ ሃይማኖታዊ ምግባሩን፡ በሥራ ላይ ለማዋል መሠረት

ያደረገው ቋሚ መመሪያ፡ "እግዚአብሔር፡ የኹሉ በላይ፥ ገዢና መሪ ነው!"

Page 22: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

የሚለውን መለኮታዊዉን ሥርዓተ መንግሥት በመከተል ሲኾን፤ ማለትም፡ ራሱ፡

የእስልምና ሃይማኖት፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት ተቋም፡ እንዳለ ተቀብሎ፡

ሥርዓቱን፡ ለራሱ፡ እንደመሠረታዊ መመሪያ በማድረግ፡ ሙሉ በሙሉ፡ መጠቀም

ብቻ ሳይኾን፡ እስከዛሬ ድረስ፡ ይህንኑ ተልእኮውን፡ ለተቀረው ዓለም በሙሉ፡

እያስፋፋ መኾኑ፡ በይፋ ይታወቅ!

ለምን? ምክንያቱ፡ መሓመድ፡ ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት

ጋር፡ እጅግ ቀደም ያለና ሥር የሰደደ፡ የማንነት መሠረትና የሥጋ ዝምድና ብቻ

ሳይኾን፤ ስለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ጥልቅና ሰፊ የኾነ፡ አጠቃላይ

እውቀት ስለነበረው ነው።

ለዚህ ነበረ፡ በትውልድ አገሩ ውስጥ፡ ገና በመጀመሪያ፡በሃይማኖት

ተቃዋሚዎቹ በኩል፡ ጥቃት ሲደርስበት፡ ቤተሰቡንና ተከታዮቹን፡ ራሱ

ወደሚያውቃትና ወደሚያምንባት፥ ለእነርሱም፡ የተሟላ መጠለያን እንደሚያገኙ

ወዳረጋገጠላቸው፡ ወደኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሸሹ የመራቸው።

መመሪያው፡ በዚህ ብቻ አላበቃም። መሓመድ፡ በእርሱ ጊዜ ለነበሩት፥

ለወደፊቶቹም ተከታዮቹና አማኞቹ፡ እጅጉን አጥብቆ፡ በጽኑ የአደራ ኑዛዜ፡

የሰጣቸው፡ የትእዛዝና የማስጠንቀቂያ ቃል አለ። ይኸውም፡ "ኢትዮጵያውያንና

ኢትዮጵያውያት፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ያላቸውን

እውነተኛነታቸውንና ታማኝነታቸውን እስካላጓደሉ ድረስ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት እና በእነርሱ ላይ፡ መቼም ቢኾን፡ ‘ጂሃድ’ የሚሉትን የሃይማኖት ጦርነት

እንዳያውጁባቸው፥ ነገር ግን፡ እኒሁ፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡

መለኮታዊው` ጥበቃና ክለላ በማይለያት አገራቸው፡ የሚኖሩትን፡ መልካሙን

ህልውናቸውን ይቀጥሉ ዘንድ፡ በእግዚአብሔር ሰላም እንዲተዉዋቸው፡ የሚያሳስበው

ቃሉ ነው።"

ኢትዮጵያንና የእስልምናን መነሣት በሚመለከት የተገለጸው፡ ይህ

መለኮታዊ እውነታ፡ በእርግጥ እውን ኾኖ፡ በገሃድና በግዝፈት የተፈጸመ ስለመኾኑ፡

በማንም ዘንድ፡ ሊካድ የማይቻል፡ ታሪካዊ ክሥተት ነው። ይኸውም፡ የጥፋቱ

ዐድመኞች በኾኑት፡ በእነዚሁ በክርስቲያኑ ዓለም አገራት ላይ፡ የተመዘዘው፡ ይህ

እስላማዊ ሰይፍ፡ እያንዳንዳቸውን፡ በተከታታይ፡ አንድ በአንድ፡ እየቀላ፡ ከሥልጣኑ

ሥር ሲያንበረክካቸውና ሲዘርራቸው፡ በይፋ መታየቱና መረጋገጡ ነው።

ለመኾኑ፡ ይህ ዓይነቱ አስደንጋጭ፡ የቅጣት መቅሠፍታዊ ማዕበልና

ነበልባላዊ የእሳት ቃጠሎ፡ እያየለ የተካኼደባቸው፡ የየክርስቲያናቱ አገራት ግዛቶችና

ይዞታዎች፥ እንዲኹም ከተሞች፥ ማእከላትና ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚታዩባቸው

መዲናዎች፥ አብያተ ክርስቲያናትና የንጉሠ ነገሥታት መንግሥታት ምድሮች፡ እነማንና

የትኞቹ ናቸው?

እነርሱማ፡ ከየመን ጀምሮ፡ የዐረብ አገርን ያካተተውን፡ የመካከለኛውን

ምሥራቅ፥ የሃይማኖት እምብርት የኾነችውን፡ ኢየሩሳሌምን፥ ግብፅንና ዝነኛዋን፡

Page 23: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

የክርስትና ትምህርት ማዕከል የኾነችውን፡ የእስክንድርያን ከተማና ልብያን ጨምሮ፡

መላውን፡ የሰሜን አፍሪቃ አህጉርን፥ ደግሞም፡ ፋርስንና አካባቢዎቿን፥ እንዲሁም፡

በከፊል እስከሕንድ የሚዘልቀውን፥ "ታናሽ እስያ" የሚባለውን፡ የቅርብ ምሥራቅን፥

እንዲያውም፡ የሮማ እና የግሪክ፡ ንጉሠ ነገሥታዊ፡ ሰፊ ግዛት የኾነው፡ የባዛንቲን

መንግሥት፡ መናገሻ ከተማን፡ ቍስጥንጥንያን፥ እርሷም፡ ኋላ፡ ስሟ ተቀይሮ፡

እስከዛሬ፡ የእስላማዊዋ ቱርክ፡ መዲና የኾነችውን፡ ‘ኢስታንቡል’ን፡ አጠቃልለው

ይዘው የነበሩት ናቸው።

አዎን! እነርሱማ፡ እንደዛሬዎቹ መሰሎቻቸውና ወራሾቻቸው ኹሉ፡

በሰይጣናዊው ፈሊጣቸውና በረቀቀው ዕብሪታቸው፥ ዐምባ-ገነንነታቸውና

ማናለብኝነታቸው፥ ግፋቸውና ጭቆናቸው፡ የዋሁን፡ የእግዚአብሔርን ሰብኣዊ ፍጥረት፡

ይገዙ የነበሩት፡ እየራሳቸውን፡"ክርስቲያን እና አይሁድ ነን!" የሚሉት ወገኖች

ናቸው።

እኒህ ኹሉ አገሮችና የሕዝብ ወገኖች፥ አብያተ ክርስቲያናትና

መንግሥታት፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን ለማጥቃትና ለማጥፋት፡

በአንድነት ተባብረው፡ ደባን የፈጸሙ፥ ሊፈጽሙም የተዘጋጁ ኾነው፡ በመለኮታዊው

የዳኝነት ዓይንና የፍርድ ሚዛን፡ ስለተገኙ፡ ርኅራኄና ምሕረት ባልነበረው፥ አኹንም፡

በሌለው፥ ገና እንደተመዘዘና ሊቆራርጥ እየተምዘገዘገ ባለው፡ በኃያሉና በብርቱው

እስላማዊ ሠይፍ ሥር፡ አንድ በአንድ፡ በመከታተል ሊወድቁ ችለዋል።

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን፡ ይኸው፡ በምንም ሳትነካ፡

የማንነቷንና የምንነቷን አምላካዊ ህልውናዋን፡ በመለኮታዊው ሥርዓቷ፡ እነሆ! እስከዛሬ

ጠብቃና አጽንታ ኖራለች። እንደዚሁ ኹሉ፡ ዛሬና ወደፊት፥ ለዘላለሙም ትኖራለች።

ከጠላቶቿ ለሚደርስባት፡ ለዚሁ ለማያቋርጠው የግፍ ጥቃቷ፡

እውነተኛውን መለኮታዊ ፍርድ ለሰጠውና ለሚሰጠው፡ ለእግዚአብሔር፡ ምስጋና

ይድረሰውና፡ አዎን! ለዚህ መለኮታዊ እውነታ፡ ሙሉ ማስረጃ የሚኾነው ማረጋገጫ፡

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ እስካኹን ድረስ፡ ከተቃዋሚዎቿ

የሚደርስባትን ጥቃት ተቋቁማ፥ ሙሉ ነጻነቷንና ሰላሟን፡ አጽንታ በመጠበቅ፡

ህልውናዋን ለመቀጠል መቻሏ ነው።

አዎን! የእነዚሁ፡ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎች፡ የቀደሙት

መሰሎቻቸውና አውራሾቻቸው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ

ስለፈጸሙት፥ ነገር ግን፡ ሳይሠምርላቸው ስለቀረው ጥቃት፡ አንዳችም ጸጸት

ሳይሰማቸው፡ ዛሬም፡ ተመሳሳዩን ዓይነት ጥቃት ለመፈጸም ለሚቃጡት፡ በዓለም

ዙሪያ፡ ክርስቲያን እንደኾኑ ለሚነገርላቸው ወገኖች ኹሉ፡ ተደጋግሞ ሊነገራቸው

የሚገባ፡ አንድ ቍም ነገር አለ፤ ይኸውም፡ ያው፡ የኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት አምላክ፡ በዚህ ረገድ፡ ያንኑ፡ መለኮታዊ የዳኝነት ፍርዱን፡ እንዳለፉት

ጊዜያት ኹሉ፡ ዛሬም፡ ፍትሓዊና ርቱዓዊ በኾነው መልኩና ይዘቱ፡ መስጠቱን

የማያቋርጥ መኾኑ ነው።

Page 24: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

እዚህ ላይ፡ በቀላሉ፡ ሊጠቀስ የሚያስፈልገውና የሚገባው፥ አግባብነት

ያለውም፡ አንድ፡ ዋናና አጓዳኝ የኾነ ጉዳይ አለ፤ ይኸውም፡ አውሮጳ ውስጥ

የሚገኘውና ተቀማጭነቱ ጀኔቫ የኾነው፡ የዓለም መንግሥታት ማኅበር፡ በቅርቢቱ፡

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ሰጪነትና ራሷን፡ "ዩናይትድ ስቴትስ" ብላ

በሰየመችው፡ በሩቂቱ አሜሪካ ተባባሪነት፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ

ያካኼደውን፡ ተመሳሳይ የወረራ ዘመቻን የሚያወሳውና የአጭር ጊዜ ትዝታ ኾኖ

የቆየው ዝክረ-ነገር ነው።

ይህ፡ በዚህኛው ጊዜ፡ በዚህ ረገድ የተከሠተው፡ የመለኮታዊው ዳኝነት

እውነታ፡ ያን የሚያህለውንና ያን የመሰለውን፡ ታላቅና አሠቃቂ የሕይወት ዕልቂትንና

የንብረት ውድመትን ያስከተለውን፡ የኹለተኛው የዓለም ጦርነት መነሣትን የሚመለከት

ይኾናል። አዎን! በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፡ የግፍ ወረራንና

ጥቃትን በፈጸሙት፡ በእነዚሁ፡ ክፉ አድራጊዎች ላይ የተገለጠው፡ መለኮታዊው

የዳኝነት ፍርድ፡ በሌላ ሳይኾን፡ የራሳቸው በኾኑት፡ በጀርመኑ የናዚ መሪ፡ በአዶልፍ

ሂትለርና በጣሊያኑ ፋሺስት መሪ፡ በቤኒቶ ሙሶሎኒ፥ እንዲሁም፡ በንጉሠ ነገሥታዊው

የጃፓን ጦር፡ ወታደራዊ ጀብደኞች፡ ኅብረት፡ ተወጥኖና ተካኺዶ፡ መጠናቀቁ ነው።

ከቀድሞው ስሕተቱ ያልተማረው፡ መንፈሳዊውና ሥጋዊው የዓለም ዐቀፍ

ኅብረተሰብ፡ ዒላማውና ሰለባው በኾነችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት

ላይ፡ ዛሬም፡ ያንኑ፡ የማያቋርጠውን፡ ተመሳሳይ፡ የጠላትነት አጥቂ ዘመቻውን፥

እንዲያውም በጠነከረና በረቀቀ መንገድ፡ በጽኑ እያፋፋመ እንደሚገኝ፡ ይኸው፡ የዓይን

ምስክሮች ኾነን፡ እንመለከታለን።

ነገር ግን፡ የዛሬዎቹ ሤረኞች፡ በአንድ በኩል፡ በካቶሊክ ቤተ

ክርስቲያንና ራሳቸውን "የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት (ሸንጎ)" ብለው

በሚጠሩት ሲደገፉ፤ በሌላ ጎኑ ደግሞ፡ ከዚህ ቀደም፡ "የዓለም መንግሥታት ማኅበር"

በመባል ይታወቅ ከነበረውና ከፈረሰው፥ በምትኩም ከተቋቋመው፡ የተባበሩት

መንግሥታት ድርጅት ጋር በመተባበር፡ ኹለቱም፡ ምድራውያን የዓለም ዐቀፍ

ተቋማት፡ ያንኑ፡ የጥንቱን፡ የቅዠት ሕልማቸውን፡ እውን ለማድረግና ኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥትን ለማፈራረስ፡ ባለ፥ በሌላቸው፡ የጋራ ኃይላቶቻቸው፡

በፍጹም ውሕደትና በገሃድ፡ ይኸው፡ ሲጥሩ ይታያሉ።

እኛ ግን፡ በአሜሪካ ምሥራቃዊ ውቅያኖስ ዳርቻ በምትገኘው፡ በ‘ኒው

ዮርክ’ ከተማ፡ (እንደእነርሱ የቀን አቆጣጠር)፡ በSeptember 11, 2001 በደረሰው

አሠቃቂ የዕልቂት አደጋ፡ የተከፈተው፡ የመለኮታዊው የፍርድና የቅጣት ማኅደር፡

የችሎቱን ብያኔ፡ በተግባራዊነት ፈጽሞ፡ እስኪዘጋና ወደዘላለማዊው ቤተ መዛግብቱ

እስኪመለስ ድረስ፡ የኺደት ውጤቱን ከመጠበቅና ከመመልከት በቀር፡ ሌላ ማማረጫ

አይኖረንም።

ይህች፡ የ‘ኒው ዮርክ’ ከተማ፡ የእግዚአብሔር ቃል፡ እንዲህ በሚል፡

ሥዕላዊ ማብራሪያ፡ የሚገልጻት ናት፦

Page 25: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

“ወመጽአ አሓዱ፡ እምነ እልክቱ ሰብዓቱ መላእክት፡ እለ

ይፀውሩ፡ ሰብዓተ ጽዋዓተ፤ ወይቤለኒ፦ "ነዓ! አርኢከ፡ ደይና፡ ለእንታክቲ ዘማ

ዐባይ፡ እንተ ትነብር፡ ውስተ ማያት ብዙኅ። ...ወዛቲ ብእሲት፡ እንተ ርኢካ፡ ሀገር

ዐባይ፡ ይእቲ፡ እንተ ትነግሥ፡ ላዕለ መንግሥታተ ምድር።”

ማለትም፡ “ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ፡ ከሰባቱ መላእክት

አንዱ መጥቶ፡ 'ና! በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን፡ የታላቂቱን ጋለሞታ

ፍርድ አሳይሃለሁ። …ያየሃትም ሴት፡ በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ፡ ታላቂቱ

ከተማ ናት።” (ራእ. ፲፯/፩-፲፰; ፲፰/፩-፳፬.)

ዛሬም፡ ጠብ ወዳጅ በኾነውና ማንነቱ፡ ቀደም ብሎ በተገለጸው፡

በመላው የዓለም ኅብረተሰብ ላይ፡ ከላይ የተወሳው፡ መለኮታዊው ፍርድ፡ የቅጣት

በትሩን እያሳረፈና ይህንኑ ተልእኮውን እየቀጠለ ይገኛል። አዎን! በኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፡ ወረራንና ጥፋትን ለማድረስ በቃጣውና ተቃዋሚ

በኾነው፡ በዚሁ፡ የዓለም ኅብረተሰብ ላይ፥ የእርሱ ደጋፊና ተባባሪ በኾነውም ወገን

ኹሉ ላይ፡ ይኸው፡ የእስልምና ኃይል፡ የቅጣት ሰይፉን በመምዘዝ፡ የመቅጣት

ግዳጁን፡ እነሆ! አኹንም እየፈጸመ መኾኑ፡ በግልጽ ይታያል።

ከላይ የተጠቀሰው መለኮታዊ ፍርድ፡ የተፈጸመባት ዕለት፡

እንደኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር፡ በመስከረም ፩ ቀን፥ ፲፱፻፺፬ ዓመተ ምሕረት፡ መኾኑ፡

ይህም፡ Ethiopia: The Classic Case በተሰኘውና በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ኀላፊነት፡ ለኅትመትና ለሥርጭት በበቃው መጽሓፍ ውስጥ የተነገረው፡

የማስጠንቀቂያ መልእክት፡ እንዲህ፡ ቀደም ብሎ በተላለፈ፡ ወደሰባተኛው ዓመት

ሲቃረብ መከሠቱ፡ አመልካችነቱ፡ የባለራእዩ ቃል፡ ጊዜውን ጠብቆ መፈጸሙን

የሚያረጋግጥ ኾኗል።

ዘጠነኛ፤ እንግዲህ፡ እስልምና፡ መለኮታዊ ለኾነው ዓላማ እንዴት እንደዋለ፡

ማስተዋል ነው። ይኸውም፦

፩. በአጠቃላይ፡ በመላው ዓለም፡ አረማውያንን፥ ጣዖት አምላኪዎችንና

አሕዛብን፣ በተለይ ግን፡ እየራሳቸውን፡ እንደሃይማኖተኞች ሕዝቦች በመቍጠር፥

ከሰብአውያን ፍጡሮች መካከልም፡ "እኛ፡ 'አይሁዳውያንና ክርስቲያኖች' ተብለን፡

የምንጠራ ነን!" እያሉ፡ በግብዝነት የሚመጻደቁት ዐንገተ-ደንዳኖች፡ በኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፡ በግትርነት ለሚያካኺዱት፡ የክህደትና የዓመፅ፥

የአምልኮ ምንዝርናና የሥልጣን ብልግና ኃጢኣታቸው፡ ተገቢውን ተግሣፅና ቅጣት

ለመስጠት ነው። ይህም፡ በአንድ ጎኑ፡ ከዚህ የሚከተለው፡ የተቀደሰ ዓላማ እንዳለው፡

መመልከት ነው። ይኸውም፦

፪. እኒሁ የክፋት ሠራዊት፡ የዓለማቱ ኹሉ ፈጣሪና ባለቤት፥ ጠባቂና

መጋቢ በኾነችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ስለሠሩት በደል፡

በየበኩላቸው፡ እየራሳቸውን በመመርመር፡ ንስሓ የመግባት ምግባርን ይፈጽሙ ዘንድ፥

ቀጥሎ፡ እውነተኛዎቹን፡ የቅዱሱ ኪዳን ተዋሕዶ ሃይማኖቷንና ሕይወቷን፡ በእምነት

Page 26: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ይቀበሉ ዘንድ፥ በመጨረሻም፡ በዚህ ረገድ፡ ኹሉም፡ የሚገባቸውን ግዳጅ፡ በተግባር

ላይ በማዋል፡ ወደቀድሞው ሥርዓቷ እንዲመለሱና ይህም፡ በመላዋ የምድር ገጽ

እንዲሰፍን፡ በአጽንዖትና ባስቸኳይ ለማሳሰብ ነው። እናም፦

፫. እግዚአብሔር፡ ለመላው የሰው ዘር፡ መልካም ህልውና እና ተድላ

ሲል፡ መሥርቶ፡ ያቋቋማትና ለዓለሙ ኹሉ ገሃድ ያደረጋት፡ ኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት፡ በተቀደሰው የምንነት አቋሟና የማንነት ህልውናዋ፡ ምንም

ዓይነት ጥቃት ሳይደርስባት፡ ተከልላና ተጠብቃ፡ ለመኖር እንደምትችል፡ ይህችን፡

የእግዚአብሔር እውነት፡ አምነው ለመቀበል፥ በተግባርም ለመፈጸም፡ "እምቢ!" ላሉት

ኹሉ፡ በአጽንዖት ለማስገንዘብ ነው።

ነገር ግን፡ እነዚሁ፡ ከላይ የተጠቀሱት፡ የኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት ተፃራሪዎች፡ ይህን የማስጠንቀቂያ ደወል ሰምተው፡ ተገቢውን ለመፈጸም፡

አኹንም፡ ፈቃደኛ ባይኾኑ፥ ማለትም፡ በዚኹ፡ በተጠመዱበት፡ የጥፋት ዓላማቸው፡

እንደጸኑ ኾነው፡ የተነሣሡበትን የደባ ተግባር፡ እስካኹን እየኾነ በሚታየው መልክና

ይዘት፡ በእርሷ ላይ፡ በእምቢተኝነት፡ መቀጠላቸውን ባያቆሙ፡ መጨረሻቸው፡ ምን

እንደሚኾን፡ አስቀድመው ሊያውቁትና ሊገነዘቡት ይገባቸዋል፤ ይኸውም፦

በጠንቀኛውና በመሠሪው፡ የክፋት ኃይል የሚካኼደው፡ የመላው

የክርስቲያኑ ዓለም፡ ግብዝነት፣

ደግሞም፡ የፀረ-እግዚአብሔርና የጭካኔ አበጋዝ የኾነው፡ የዓለም

ዐቀፉ ይሁድና፡ ልበ-ደንዳናነት፣

እንዲሁም፡ ሃይማኖተ-ቢሱና ሥርዓተ-አልበኛው ሰብኣዊው ወገን፡

በምድር ኹሉ፡ እያስፋፋና እየጎዳበት ያለው፡ የአምልኮተ እግዚአብሔር ንቀት፡ እነዚህ

ኹሉ፡ የክፉው ዲያብሎስ የተግባር ውጤቶች፡ የሚጠብቃቸው ጽዋ፡ ፈጽሞ

በማያጠያይቅና በማያጠራጥር ኹኔታ፡ የመጨረሻው መደምሰስ መኾኑ ነው።

ይህንም እውነታ፡ የእግዚአብሔር ቃል፡ እንዲህ ሲል ያረጋግጠዋል፦

“ወሶበ ኀልቀ ፲፻ ዓመት፡ ይትፈታሕ ሰይጣን፡ እምነ ሞቅሑ።

ወይወፅእ፡ ያስሕቶሙ ለአሕዛብ፡ እለ ውስተ አርባዕቱ መአዝኒሃ ለምድር፤

ወያስተጋብኦሙ፡ ለጎግ ወለማጎግ፡ ከመ ያስተቃትሎሙ፤ ወኍልቆሙሰ፡ ከመ ኆጻ

ባሕር።

“ወዐርጉ፡ ውስተ ስፍሓ ለምድር፤ ወዐገትዋ ለትእይንቶሙ፡

ለቅዱሳን፣ ወለሀገር ቅድስት [ኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር]። ወእምዝ፡

ወረደት እሳት፡ እምሰማይ፥ እምኀበ እግዚአብሔር፤ ወበልዐቶሙ።

“ወለዝክቱኒ ሰይጣን፡ ዘያስሕቶሙ፡ ወደይዎ ውስተ ዐዘቅተ

እሳት፥ ወተይ፡ ኀበ ሀሎ፡ ዝክቱ አርዌ፣ ወሓሳዌ ነቢይ፡ ከመ ይደየኑ፡ መዐልተ፥

ወሌሊተ፣ እስከ ለዓለመ ዓለም።

ማለትም፡ “ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእሥራቱ

ይፈታል፤ በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን

Page 27: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

እንዲያስታቸው፥ ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር

አሸዋ የሚያህል ነው።

“ወደምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሠፈርና የተወደደችውን

ከተማ [ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን] ከበቡ። እሳትም ከሰማይ

ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው።

“ያሳታቸውም ዲያብሎስ፡ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ

ወዳሉበት፡ ወደእሳቱና ወደዲኑ ባሕር ተጣለ። ለዘላለምም እስከ ዘላለም፡ ቀንና ሌሊት

ይሠቃያሉ።” (ራእ. ፳፥ ፯-፲።)

ከዚህ በኋላ፡ እስላማዊው ሃይማኖት፡ መለኮታዊ ተልእኮውን፡ እንዲህ፡

ፈጽሞ ሲያበቃ፡ በመሣሪያነቱ፡ ጠቃሚ፥ በአገልግሎቱም፡ ውጤታማ ኾኖ የተገኘውን፡

የተመዘዘ ኃያል ሠይፉን፡ ወደሰገባው ይመልሳል። ተአማኒነቱንና ተገዢነቱንም፡

በመጨረሻ፡ በራሱ የፍላጎትና የስምምነት ውሳኔ፡ ለመለኮታዊው ፈቃድና ለኢትዮጵያ፡

የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የቅዱሱ ኪዳን ተዋሕዶ ሃይማኖት በማብቃት፡ እንግዴህ

ወዲህ ወደማይታሰብበት፡ ወደ"ኀበ አልቦነቱ"፣ ማለትም፡ ወደ"አለመኖርነቱ"

ይጎዳኛል። በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት መቅደስም ሥር፡ በሰላምና

ለዘላለም ይሠወራል።

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ በዚህ ምንነቷና ማንነቷ፡

በሥጋዊውና በነፍሳዊው፥ በመንፈሳዊውና በኹለንተናዊው ህልውናዋ፡ ጥንቱኑ፡

በመነሻው፡ በመለኮታዊው ኅሊና ታስባና በዕውቀቱ ተዘጋጅታ፣ በጥበቡም ተመሥርታ፡

እስከዛሬ በጸናችበትና ወደፊትም፡ ለዘለዓለም በምትቀጥልበት አቋሟ፡ በማይታየው፡

ረቂቁ ዓለም በኩል፡ የሚጠብቋትና የሚከላከሉላት፡ ቅዱሳኑ የሰማይ ሠራዊተ መላእክት

ናቸው።

በሚታየው፡ በግዙፉ ዓለም በኩል ደግሞ፡ የሰዎች፡ የዓለም መንግሥታት

እንደሚያደርጉት፡ በጦር መሣሪያ ሳይኾን፡ ለሕዝቧ፡ ሰላማዊ አገልግሎትን፡

ያለአንዳች የኃይል መሣሪያ፡ በፍቅር ብቻ ከሚያበረክቱት፡ የደኅንነት ጥበቃ፥

የሥርዓት አስከባሪና የረድኤት ሰጪ ዘበኞቿ ጋር፡ በተጨማሪ፡ ተመሳሳዩን፡ የልማትና

የዕድገት ሰላማዊ አገልግሎታቸውን፡ ያለአንዳች የኃይል መሣሪያ፡ በፍቅር ብቻ፡

ለሕዝቧና ለፍጥረቷ የሚያበረክቱላት፡ የከተማና ብሔራዊ፣ የሕግና የክብር፣ የምድርና

የአየር፥ የባሕርና የጠረፍ ጥበቃ፥ በጠቅላላም፡ የአገር መከላከያ ሠራዊቶቿ ናቸው።

ከዚህ የተነሣ፡ እንደሰዎቹ፡ የዓለም መንግሥታት ጦር ኃይሎች፡ ለዚህ

ዓላማ ማስፈጸሚያና ለተግባሩ ማካኼጃ፡ ያስፈልጓት የነበሩትን፡ ልዩ ልዩ የጦር

መሣሪያ ምርትን በማሳደግ ረገድ፡ ይደርስ የነበረውን፡ የጥበብ ሙስናን፥ የሰው

እልቂትንና፣ የገንዘብ ብክነትን ለማስወገድ ችላለች። ለሰዎቹ፡ የዓለም መንግሥታት፡

የጦር ኃይሎች ግዳጅ ማካኼጃና ማስፈጸሚያ፡ ሊመደብ የሚያስፈልገው ዕውቀትና

ጥበብ፥ ሰውና ጕልበቱ፥ ገንዘቡና ንብረቱም፡ ለእርሷ፡ አላስፈለጓትም፤

አያስፈልጓትምም። ያን ኹሉ ዕውቀትና ጥበብ፥ ሰውና ጕልበቱንም፥ ገንዘቡንና

ንብረቱን ጭምር፡ እርሷ፡ ኹሉንም፡ ለሕዝቧ፡ ሥጋዊና ነፍሳዊ፥ መንፈሳዊና

Page 28: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

ኹለንተናዊ ሕይወት ማዳበሪያ፣ ለሥነ ፍጥረቷም እንክብካቤ ብቻ እንዲውል

አድርጋለች።

አሥረኛ፤ ለማጠቃለል ያኽል፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት

ኃላፊነት፡ ለዕትመት የበቁትን መጻሕፍት፥ እንዲሁም፡ በኅዋ ሰሌዳችንና በፌስቡካችን

ላይ ሠፍረው የሚገኙትን የቅዱሱ ኪዳን መልእክቶችና ሰነዶች፡ እንዲያነብቧቸውና

እንዲመለከቷቸው፡ በድጋሚ፥ በአጽንዖት አሳስብዎታለሁ።

ምናልባት፡ ይህን ማሳሰቢያ፡ ተግባራዊ ማድረግ፡ የሚያዳግትዎ ቢኾን፡ ቢያንስ

ቢያንስ፡ በኅዋ ሰሌዳችን ዋና ገጽ ላይ፡ “ሃይማኖት” በሚለው ክፍል ውስጥ

የሚገኙትን፡ አራት የጸሎት ክታቦችን መመልከቱ ይጠቅምዎታል።

እነዚህም፦

፩ኛ. የኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያት የሃይማኖት ጸሎት።

፪ኛ. የኢትዮጵያውያትና የኢትዮጵያውያን፡ የቃል ኪዳን ጸሎት።

፫ኛ. ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ለእግዚአብሔር

የሚያቀርቡት፡ የምስጋና ጸሎት።

፬ኛ. ኢትዮጵያውያትና ኢትዮጵያውያን፡ ለድንግል ማርያም

የሚያቀርቡት፡ የሰላምታ ጸሎት።

እንዲሁም፡ ከዚህ በተጨማሪ፡ በተከታታይ የወጡትን ቃለ ዐዋዲዎች

(የአዋጅ ቃሎች) ያጠቃለለ ይኾናል።

ከላይ የተዘረዘሩት ሃይማኖታውያን ጽሑፎች፡ ለእያንዳንዱ ግለሰብ

ስለኢትዮጵያ፥ ስለኢትዮጵያ ልጆችና ስለኢትዮጵዊነት፡ ወሳኝ የኾኑ ቁምነገሮችን

በሚመለከት፡ የበለጠ ግንዛቤን ለማስጨበጥ የሚያስችሉ ከመኾናቸው በላይ፡ በዚሁ

ዙሪያ፡ የተሟላ እውቀትን እንደሚያስገኙም ይታመናል። በመጨረሻ፡ በዚህ ረገድ፡

የተገኘውን እውቀት፡ ተግባራዊ በማድረግ፡ ራስን፡ ለ"ፍጹሙ ኢትዮጵያዊነት"

ማብቃት ይቻላል።

በቀላሉ ሊገነዘቧቸው ለሚቻሉ፥ ደግሞም፡ ማስተዋልን ለሚጠይቁ፡ ከባድና

በርካታ ጥያቄዎች፡ የተሰጡት መልሶቻቸው፡ በኅዋ ሰሌዳችንና መድረኮቻችን፥

እንዲሁም፡ በመጻሕፍታችንና በክታቦቻችን ዓምዶች ላይ ይገኛሉ።

ለእነዚህ፡ ቅድሚያን በመስጠት፡ እነርሱን መመልከቱ፡ አንባቢን መርዳት ብቻ

ሳይኾን፡ ከዚህ በላይ እንደተከሠተው፡ ተመሳሳይ የኾነ፡ የጥያቄና መልሱ ቅብብሎሽ፡

የሚወስደውን ጊዜ ከመቆጠቡ ጋር፡ ከኹለቱም፡ ማለትም፡ ጥያቄውን ከሚያቀርበውና

ምላሹን ከሚሰጠው ወገን፡ አላግባብ ሊባክን የሚችለውን ጉልበትና ወጪ፡ ማዳኑ

ጭምር፡ በጣሙን ጠቃሚ መኾኑ፡ እሙን ነው።

አለዚያ፡ ለእርስዎ እንደተደረገው ኹሉ፡ እንግዳና አዲስ የኾነውን፡ እያንዳንዱን

ግለሰብ፡ በተመሳሳይ ኹኔታ ማስተናገዱ፡ እጅግ አስቸጋሪና ለሥራ አፈጻጸም አመቺ

እንደማይኾን፡ በማንም ዘንድ ይታወቃል። ስለዚህ፡ ስለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

Page 29: ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ethiopiathekingdomofgod.org/sites/default/files...ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር

መንግሥት፡ የጠለቀ እውቀት ለማግኘትና ይህንም፡ ወደራስ ማንነት ለማሥረፅ፡ አዲስና

እንግዳ የኾነ፡ ማንኛውም ግለሰብ፡ በተቻለ መጠን፡ ድግግሞሹንና ብክነቱን

በማስቀረት፡ ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉ፡ እጅግ አስፈላጊ መኾኑን

በዚህ አጋጣሚ፡ እንደገና ልናሳስብ እንወድዳለን።

የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያ አገልጋይ፦

ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ።