ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል...

31
የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀ 1959 – 2009 ነሐሴ 2009

Upload: hadan

Post on 20-Feb-2018

283 views

Category:

Documents


23 download

TRANSCRIPT

Page 1: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር

ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀ

1959 – 2009

ነሐሴ 2009

Page 2: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት
Page 3: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት እንክብካቤ የተደረገ የ50 ዓመት ጉዞ

ምሥረታ

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር የ50

ዓመታትን ጉዞ መለስ ብሎ ትውስታዎችን ማሰላሰል፣ ተሞክሮዎችን መቃኘትና ስኬቶችን መዳሰስ

አይቀርም፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር መንግሥታዊ፣ ሃይማኖታዊ እና እንዲሁም አትራፊ

ያልሆነ በ1959 ዓ/ም የተመሠረተ በአካባቢ ጥበቃና ግንዛቤ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሆነ አገር በቀል

ተቋም ነው፡፡

ይህ ማህበር በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያ ዝንባሌ በነበራቸው 32 በጎ ፈቃደኛ

መሥራች አባላት እንደተመሠረተ የማህበሩ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡ በ1959 ዓ/ም የጄኔራል ዊንጌት

ትምህርት ቤት ርዕሠ መምህር የነበሩ ሚስተር አለን ኢ. ኪንግ (Mr. Alan E. King)፣ በወቅቱ የዱር

እንስሳት ጥበቃ መ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ለነበሩት ለሻለቃ ግዛው ገድለ ጊዮርጊስ ስለማህበሩ መመሥረት

አስፈላጊነት ባቀረቡት መነሻ ሀሳብ መሠረት መጀመሪያ በማህበራዊ ክበብነት የተመሠረተ ሲሆን፣

እያደርም በአካባቢ ጥበቃና በብዝሀ ሕይወት እንክብካቤ ዘርፍ ላይ የሚያተኩር ማህበር እንዲሆን

በተደረገው ጥረት እውቅናን ማግኘት ችሏል፡፡

ማህበሩ የመንግሥትን ድጋፍ እንዲያገኝ በዶ/ር ብርሀነ ጥዑመልሳን በጊዜው የብሔራዊ ላቦራቶሪና

ምርምር ተቋም ረዳት ዳይሬክተር እና የማህበሩ ም/ፕሬዚዳንት ጠያቂነትና የቅርብ ክትትል ግርማዊ

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በጥቅምት ወር 1961 ዓ/ም የማህበሩ የበላይ ጠባቂ ሆኑ፡፡ ግርማዊነታቸው

ለማህበሩ የገንዘብ ዕርዳታ ያደረጉ ሲሆን እርሳቸው ባቀረቡት ሀሳብ መሠረትም የማህበሩ ስያሜ ቀድሞ

"የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ታሪክ ማህበር" ይባል የነበረው "የዱር እንስሳት" የሚለው ሐረግ ታክሎበት፣

"የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር" የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ

የማህበሩን አባላት በቤተመንግሥታቸው በተቀበሉበት ወቅት ከተናገሩት የሚከተለው ይጠቀሳል፡፡

"የኢትዮጵያን እንስሳትና ዕፅዋት በተፈጥሮ አካባቢያቸው መጠበቅ፣ እናም

ከሚደርስባቸው የጅምላ ውድመት ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች፣ በቅንነትና በሥነ

ውበት ተቆርቋሪነት ስሜት በመነሳት የሚደረጉ ክንውኖች ብቻ ሳይሆኑ የሀገሪቱን

ቅርሶች በዘዴ በመጠበቅና በመንከባከብ ለሚቀጥሉት ተውልዶች እንዲተላለፉ የማስቻል

ድርጊት ነው” ፡፡

Page 4: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ማህበሩ ከተመሠረተ ከስምንት ዓመታት በኋላ የማህበሩ አባላት ቁጥር 71 ደርሶ ነበር፡፡ ከነዚህም

ውስጥ 67ቱ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የውጪ አገር ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን

የማህበሩ አባላት ግን አራት ብቻ ነበሩ፡፡ የውጪ ዜጎች ቁጥር ለምን ይህን ያህል እንደበዛ በሰነዶች

የተደገፈ ማስረጃ አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ጉዳዩ በአጋጣሚ የተከሰተ ነው ማለትም አይደለም፡፡

ንጉሠ ነገሥቱ የማህበሩ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ ሲጠየቁ ይሁንታቸውን የማግኘቱ ምስጢር፣ ማህበሩ

እንዲቋቋም ወሳኝ ሚና ከተጫወቱ የውጪ ዜጎች መካከል የተወሰኑት ለከፍተኛ ሥራ ወደ አገራችን

መምጣታቸውንና ከዚህም የተነሳ ንጉሠ ነገሥቱን ብዙም ሳይቸገሩ ማግኘት ይችሉ እንደነበር

የሚያመለክት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ እነዚህ የውጪ ዜጎች ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ምክንያትም

ይሁን ለጉብኝት የተለያዩ የአገሪቱን አካባቢዎች የማየት ዕድል ማግኘታቸው በአገሪቱ የተፈጥሮ ውበት

እንዲደመሙና ተገቢው እንክብካቤ ካልተደረገ ሊደርስ የሚችለው አደጋ ቀላል እንደማይሆን የተረዱ

መሆኑን ያመለክታል፡፡ ምንም እንኳን በ1960ዎቹ ለአካባቢ ጥበቃ የተሰጠው ግምት በአጠቃላይ ዝቅተኛ

ቢሆንም፣ በምዕራባውያን ዘንድ የተሻለ ግንዛቤ ነበር፡፡ በቁጥር አነስተኛ የነበሩት ኢትዮጵየውያን

ለማህበሩ መመስረት ያበረከቱት ወሳኝ ጥረት እንደተጠበቀ ቢሆንም፣ አብዛኛዎቹ የማህበሩ አባላት

የመጡት ስለተፈጥሮ ጥበቃ የተሻለ ግንዛቤ ከነበረበት ከአውሮፓ መሆኑ፣ ሀሳቡን ከማፍለቅ ጀምሮ

ለማህበሩ ምሥረታ የተጫወቱት ሚና ጉልህ እንደነበረ መጥቀሱ ተገቢ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ከተመሠረተበት 1959 ዓ/ም ጀምሮ በቢሮ ደረጃ

ተጠናክሮ እስከተዋቀረበት 1985 ዓ/ም ድረስ ለ26 ዓመታት በአስር የሥራ አሲኪያጅ ኮሚቴ አባላት

እየተመራ ወርሃዊ ስብሰባዎችንም ፈቃደኛ በሆኑ አባላት መኖሪያ ቤቶች ሲያካሄድ እንደነበረ

ከመዛግብት ለመረዳት ተችሏል፡፡ ይህ ሁኔታ ፈታኝና አሰልቺ ቢሆንም የማህበሩ አባላት የመሠረቱት

ማህበር ዘላቂ እንዲሆን የማድረግ ዓላማቸውን ሊገድበው አልቻለም፡፡ በማህበር ደረጃ የተቋቋመውን

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር የበለጠ አጠናክሮ በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤና

አካባቢ ጉዳይ ላይ እንዲያተኩር ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ የዚህ ጥረት ግንባር ቀደም ተዋንያን የአዲስ

አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የሕትመት ክፍል ኃላፊ የነበሩት (በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ)

ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ እና፣ የሥነ ሕይወት ትምህርት ክፍል መምህራን እንደነበሩ ለመረዳት

ተችሏል፡፡ ምሁራኑና ሌሎች አባላትም ማህበሩን በማጠናከር ሂደት ውስጥ ከሰጡት ልዩ ትኩረት

ዋነኛው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን አጠናክሮ ማቋቋም፣ የማህበሩን የትኩረት አቅጣጫ መከለስና ራዕዩ

እንዲሳካ በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ማድረግ ነበር፡፡ በፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ሊቀመንበርነት

የተጠናከረው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመነጋገር የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ

ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ጽ/ቤት ቦሌ መንገድ የቀድሞው ካራማራ ሆቴል አጠገብ በሚገኝ

ሕንፃ ውስጥ በ1985 አቋቋመ፡፡

Page 5: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ይህንን የ50 ዓመታት የምሥረታ በዓል የምናከብረው የማህበሩ መሥራች አባቶች በመሐከላችን

በሌሉበት ነው፡፡ ብዙዎቹ ዛሬ በሕይወት የሌሉ ሲሆን፣ በሕይወት ያሉትም ቢሆኑ ርቀውና መምጣት

በማይችሉበት የዕድሜ ክልል ውስጥ ናቸው፡፡ ከመሥራቾች አንዱ አውስትራሊያዊው ሚስተር አለን

ኪንግ ሲሆኑ፣ የምሥረታውን ሃሳብ ከመጠንሰስ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከማህበሩ ጋር ያላቸውን

ግንኙነት ሳያቋርጡና ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን መግለጽ ተገቢ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና

የተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ለእኝህ ወደር ለሌላቸው የድርጅቱ መሥራች፣ እውነተኛ ወዳጅ፣ ተቆርቋሪና

ባለውለታ ያለውን አድናቆት ይገልጻል፡፡

ከላይ በመግቢያው እንደተገለጸው የማህበሩ ባለአደራ ኮሚቴ በበጎ ፈቃደኝነት በመነሳሳትና በሂደትም

ያጋጠሙትን መሰናክሎች በፅናት ለማለፍ ያደረገው ጥረት ባይታከልበት ኖሮ የኢትዮጵያ ዱር

እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር አሁን ያለበት ደረጃ ላይ መድረስ ይቅርና ህልውናም ላይኖረው

ይችል ነበር፡፡ የኮሚቴው አስደናቂ ተግባራት ሁሌም መዘከር ያለባቸው ሲሆኑ፣ እኛም ጠንክረን

በመሥራት ህልማቸውን ዕውን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

የማህበሩ የወቅቱ አደረጃጀት

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና የተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ዋና የበላይ አካል የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን፣

ድርጅቱ በበጎ ፈቃደኛነት በሚያገለግሉ ሰባት አባላት ባሉት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሚመራ ነው፡፡

የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ በየአራት ዓመቱ ከማህበሩ አባላት ጠቅላላ ጉባኤ ውስጥ የሚመረጥና

በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሲሆን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚከናወኑት ግን በዋና

ዳይሬክተር በሚመራ የጽሕፈት ቤቱ የቅጥር ሠራተኞች ነው፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ድምፅ አልባ የቦርድ

ፀሐፊ በመሆንም አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በፕሮጀክቶች መብዛትና ማነስ ላይ ተመርኩዞ፣ የሠራተኞች

ቁጥር ክፍና ዝቅ የሚል ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ 15 መደበኛና 1 ጊዜያዊ በድምሩም 16

ሠራተኞች አሉት፡፡

የ50 ዓመት ክንውኖችና ስኬቶች

ማህበሩ የሥራ እንቅስቃሴ የሚያደርገው በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ሲሆን ዓላማውንም ለመተግበር

የመንግሥትና ሌሎች ተቋማት እገዛና ትብብር እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ማህበሩ

ከመንግሥትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠርና በመተባበር ይሠራል፡፡

ማህበሩ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ ጉዳዮች አብሮ

የመሥራት ባህሉን አዳብሯል፡፡ የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ሚኒስቴር፣ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት

ልማት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት

Page 6: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ኢንስቲትዩት፣ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ሕይወት

ትምህርት ክፍል፣ የክልል መንግሥታት የግብርና ቢሮዎች፣ በአዲስ አበባና በክልል የሚገኙ የትምህርት

ቢሮዎችና ት/ቤቶች፣ የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢያዊ ጥምረት ማዕከል፣ የሥነ ሕዝብ፣ ሥነ ተዋልዶና

አካባቢ ጥምረት በኢትዮጵያ እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ማህበሩ በአገር ውስጥ አብሯቸው

ከሚሠራቸው ድርጅቶች መሃከል ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በማህበራዊ ክበብነት ከተቋቋመ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ

እንቅስቃሴዎቹ ያነጣጠሩት ትኩረት በሚሹ የአካባቢ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶችና ተፈጥሮንና

ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት ላይ ነበር፡፡ በሂደትም፣ ከፊል ሳይንሳዊ ይዘት ያለውን "ዋሊያ" የተሰኘ

መጽሔት የማሳተምና ማሠራጨት እንቀስቃሴ ተጀመረ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ስለአካባቢ እንክብካቤና

የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ አስፈላጊነት የግንዛቤ ትምህርት የሚሰጥ “አጋዘን” መጽሔት እንዲሁም ሌሎች

ተዛማጅ ሕትመቶችን አሳትሞ ለትምህርት ቤቶችና ለሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎች የማሰራጨት

ተግባራት ይከናወኑ የነበሩት በተወሰኑ በጎ ፈቃደኛ አባላት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት የማህበሩ እንቅስቃሴ በይዘቱም ሆነ በመጠኑ እየሰፋ መምጣትና ማህበሩም

በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ግንኙነትና ተቀባይነት እየገዘፈ መምጣት ሥራውን በበጎ

ፈቃደኞች ብቻ ከዳር ማድረስ እንደማይቻል በግልጽ አሳየ፡፡ ይህም ሁኔታ የማህበሩን የዕለት ተዕለት

ሥራ የሚተገብር የራሱ ቅጥር ሠራተኞች ያሉት ቋሚ ጽሕፈት ቤት ማቋቋም አሰፈላጊ መሆኑን

አመላከተ፡፡ በመሆኑም፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ጥበቃ ላይ የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ አገር በቀል ደርጅትነት እውቅና አግኝቶ በሚያዚያ ወር

1984 ዓ/ም በመለያ ቁጥር 054 በአገር ውስጥ ሚኒሰቴር ተመዘገበ፡፡

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና የተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ቋሚ ጽሕፈት ቤት ኖሮት በ1985 ከተቋቋመና

በግልጽ የተቀመጡ የአካባቢና የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ፣ የአካባቢ ትምህርት ግንዛቤና የማህበረሰብ

ተደራሽነት እና የክትትልና ምርምር መርሐ ግብሮች ከተቀረፁ በኋላ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

ከ1985 ዓ/ም ወዲህ ባሉት ጊዜያትም ማህበሩ ካከናወናቸው ተግባራትና ከተገኙ ስኬቶች መካከል

የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

እ. ኤ. አ. ጁን 1992 ሪኦ ዴ ጃኔሮ ከተካሄደው የአካባቢ ጉባኤ በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ

የዓለም የአካባቢ ቀን እንዲከበር በተወሰነው መሠረት፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ

ታሪክ ማህበር የትምህርት ቤት የአካባቢ ክበባትን በማስተባበር በዓሉ እንዲከበር ፋና ወጊ ሚና

ተጫውቷል፤

Page 7: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ከ400 በሚበልጡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጆች

እና በአካባቢ ማህበረሰቦች የተፈጥሮ ክበባትን በማቋቋም የአካባቢ ትምህርት በአገሪቱ እንዲስፋፋ

በማድረግ ረገድ በቀደምትነት ይፈረጃል፤

ከ40 በሚበልጡ የተለያዩ የአካባቢ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በራሪ ጽሑፎች፣ ፖሰተሮች፣ የክበባት

መመሪያዎች፣ መጽሔቶች፣ የትምህርት አጋዥ ጽሑፎች እና መጻሕፍት፣ በማሳተም

እንዲሠራጩ የተደረገ ሲሆን፤ ከነዚህ የሕትመት ውጤቶች መካከል፣ በአካባቢ ጉዳዮች ላይ

ትምህርታዊና የምርምር ሥራዎችን ይዞ የሚወጣ ከፊል ሳይንሳዊ የሆነው "ዋሊያ" መጽሔት

እና ተማሪዎችና ወጣቶች ስለአካባቢ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ለአካባቢ ተቆርቋሪ ሆነው

እንዲያድጉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተው "አጋዘን" መጽሔት ጉልህ ሥፍራ የሚሰጣቸው

ናቸው፤

በአገራችን ብቻ በሚገኙ ብርቅዬ አዕዋፍትና ሌሎች ዝሪያዎች በሚገኙባቸው 69 ቁልፍ የሆኑ

ሥፍራዎች ሰፊ የጥናት ዳሰሳ በማድረግ እና በአፍሪቃ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያን ዋና

የአዕዋፍት መኖሪያ ሥፍራዎች ዝርዝር መረጃ የያዘ መጽሐፍ እንዲታተተም ተደርጓል፤

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የአካባቢ ተንከባካቢ ድርጅቶች መቋቋም ተምሳሌት ሲሆን፣

የአንዳዶቹ ድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች እና ቁልፍ ሠራተኞች በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ዱር

እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ባቋቋማቸው የትምህርት ቤቶች የተፈጥሮ ክበባት አባል

የነበሩ ናቸው፤

ከ3.5 ሚሊዮን የሚበልጡ የተላያዩ አገር በቀል እና የውጪ ዕፅዋት ዝሪያ ችግኞችን በማፍላትና

በማሠራጨት በትምህርት ቤቶች፣ በተለያዩ የመንግሥት መ/ቤቶች ፣ በቤተ ክርስቲያናትና

ገዳማት ቅጥር ግቢ ውስጥ እና በተራቆቱ መሬቶች እንዲተከሉ ተደርጓል፤

በአገሪቱ ውስጥ የተመረጡ 23 ሐይቆችና ውሀ አዘል መሬቶች ለነዋሪና ስደተኛ አእዋፍየሚሰጡትን ጥቅምና የሚደርስባቸውን አካባቢያዊ ተፅዕኖ ለማጥናት ለ12 ዓመታት ያላሠለሰክትትልና ምርምር ተደር¹ል፡፡

ከበርጋ ወፍ አፍቃሪዎች ማህበር እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ከአስተዳደር አካላት ጋር

በመሆን በበርጋ ውሃ አዘል መሬት የምትገኘውን ለአደጋ የተጋለጠች ብርቅዬ የበርጋ ወፍ

(White-winged Flufftail) የተሻለ ጥበቃ እንዲደረግላት ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፤

እንደ ዓለም አቀፍ የአዕዋፍት ድርጅት (BirdLife International) አባልነቱ፣ የኢትዮጵያ ዱር

እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በአገራችን የሚገኙ ለአደጋ የተጋለጡ ብርቅዬ አዕዋፍትን

አስመልክቶ ተገቢ የጥበቃና የምርምር ሥራ ከመሥራት አኳያ በአገሪቱ ውስጥ ብቸኛ ድርጅት

ነው፡፡ ለአደጋ የተጋለጡ ብርቅዬ አዕዋፍትን አስመልክቶ በምን መልክ መጠበቅ እንደሚገባቸው

የሚያመላክቱ በርካታ አስተዳደራዊ መርሃ ግብሮችንም ማዘጋጀት ችሏል፤

Page 8: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

በ24 ቤተ ክርስቲያናትና በ15 ገዳማት አጸዶች ውስጥ በተደረገ የዕፅዋት ዳሰሳ ጥናት፣ 223

አገር በቀል ዛፎች የተለዩና የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 120 የሚሆኑት ዝርያዎች

ለአካባቢው ህብረተሰብ በተለያየ መልክ ጥቅም እንደሚሰጡ ተረጋግጧል፡፡ ለ5 ቤተ

ክርስቲያናትና ገዳማትም የአስተዳደር ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

ሀገር በቀል ዕውቀት /Indigenous Knowledge/ የሀገሪቱን ዕፅዋት ከመጠበቅ አንፃር ያለውን

የጎላ አስተዋጽኦ ለማስረፅ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ በአራት የጋሞ ዞን ደጋማ አካባቢዎች በ544

የተቀደሱ ሥፍራዎች (Sacred Forest Sites) - ከእነዚህ ውስጥ 100ዎቹ ደኖች ናቸው -

ጥናት ተካሂዷል፡፡ ይህ ጥናት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙት “የተቀደሱ” ሥፍራዎች

ለደን እና ሌሎች ብዝሐ ሕይወት ጥበቃ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አመላካች ሆኗል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ስኬቶች የማህበሩ ዐበይት የሥራ ክንውኖች ቢሆኑም፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና

ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በመቶዎች በሚቆጠሩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአካባቢ

ትምህርት እና ግንዛቤን በማስፋፋት መርሐ ግብር ያከናወናቸው ተግባራት ይበልጥ የሚያኮሩና

ሊሠመርባቸው የሚገቡ ናቸው፡፡ ከሁሉም ተግባራት በላይ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ልብና

አእምሮ በመግዛት ለአካባቢያቸው ተቆርቋሪ ሆነው ተገቢውን ጥበቃ ሲያደርጉ ማየትን የመሰለ የሚያረካ

ነገር የለም፡፡ በኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር የአካባቢ ትምህርትን ከማስፋፋት አኳያ

የተከናወኑ ቀደምት ተግባራትም አሁን ድረስ በየትምህርት ቤቶቹ አሻራቸው ይታያል፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ባለፉት በርካታ ዓመታት ያከናወናቸው ስኬታማ

ተግባራት የሚያኮሩ ቢሆኑም፣ ማህበሩም ሆነ ሌሎች በአካባቢ ጥበቃ ሥራ የተሠማሩ መሰል ድርጅቶች

ከቶ ሊዘናጉ አይገባም፡፡ ገና ረጅም ጉዞ የሚቀረን ሲሆን፣ የሚጠብቁን ሥራዎችና ተግዳሮቶች የዚያኑ

ያህል ብዙ ናቸው፡፡

ጥምረት መፍጠር፣ የአካባቢ ቡድኖችን ማቋቋም እና የግንኙነት መረቦችን ማስፋት

ማህበሩ ከውጪ ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር መረጃዎችንም ሆነ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ

እንዲቻል በስፋት ተንቀሳቅሷል፡፡ በመሆኑም በ50 ዓመቱ የማህበሩ ጉዞ ለማህበሩ ዓላማ ግብ መምታት

እገዛ ሲያደርጉ ከነበሩትና አሁንም እገዛ እያደረጉ ካሉ ድርጅቶች ውስጥ የስዊድን ዓለም አቀፍ ተራድዖ

ድርጅት፣ የካናዳ ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

የገንዘብ ተቋም፣ በርድላይፍ ኢንተርናሽናል፣ የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ የኔዘርላንድስ ኤምባሲ፣ የፈረንሳይ

ኤምባሲ፣ የፊንላንድ ኤምባሲ፣ የቤልጂየም ኤምባሲ፣ የኖርዌይ የግብርና ልማት ባለሥልጣን፣

ክሪስተንሰን ፈንድ፣ ሚደልፐንት ዌትላንደስ ትረስት፣ የአሜሪካን ዓሣና ዱር እንሰሳት አገልግሎት፣

ካውንተር ፓርት ኢንተርናሽናል፣ ኮንሰርቬሽን ኢንተርናሽናል፣ የጀርመን ተፈጥሮ ጥበቃ ድርጅት

Page 9: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

/NABU/፣ የእንግሊዝ በርድላይፍ ድርጅት (RSPB)፣ ትሪ ኤይድ ዩኬ፣ ትሪስ ፎር ሲቲስ፣ ብሪቲሽ

በርድ ፌር፣ ክሪቲካል ኤኮሲሰተም ፓርትነርሺፕ ፈንድ (CEPF)፣ ዳርዊን ኢኒሼቲቭ እና ዌትላንድስ

ኢንተርናሽናል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ማህበሩ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን በሚያከናውንባቸው አካባቢዎች ሁሉ፣ ከየአካባቢው

ማህበረሰብ የተውጣጡ የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖችን በማቋቋምና በታቀዱ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ

በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይመደባል፡፡ ለአብነት ያህል በምዕራብ ሸዋ ዞን በአድአ

በርጋ ወረዳ የተቋቋመው የበርጋ ወፍ አፍቃሪዎች ማህበር እና በምራብ አርሲ ዞን በአርሲ ነጌሌ ወረዳ

የተቋቋመው የአብጃታ ሻላ የአካባቢ ተንከባካቢ ማህበር ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህም ቡድኖች በብዝሀ

ሕይወት ሀብት ላይ ክትትልና ጥበቃ በማድረግ ረገድ አጋዥ መሆናቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡

ፕሮጄክቶች በሚተገበሩበት ወቅት ስለአካባቢ ጥበቃ አስፈላጊነት ያላቸው ግንዛቤ ስለሚያድግና ተጠቃሚ

እንደሚያደርጋቸውም ስለሚረዱ ፕሮጄክቶቹ ከተጠናቀቁ በኋላ ቀጣይነት ያለው ሥራ ሲያከናውኑ

ይታያሉ፡፡

ማህበሩ መንግሥታዊ ካልሆኑ የልማት ድርጅቶችና ሌሎች ድርጅቶችም ጋር የግንኙነት መረቦች

በመፍጠር የግንኙነት ትስስሮች እንዲኖሩት ለማድረግ ችሏል፡፡ ከድርጅቶቹም መካከል፣ በርድላይፍ

ኢንተርናሺናል፣ ኢስት አፍሪካ ኢንቫይሮሜንታል ኔትዎርክ፣ ዌትላንድስ ኢንተርናሽናል፣ ሚድልፐንት

ዌትላንድ ትረስት፣ የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢያዊ ኔትወርክ፣ የሥነ ሕዝብ፣ ሥነ ተዋልዶና አካባቢ

ጥምረት፣ አልበርታይን ሪፍት ኮንሰርቬሽን ሶሳይቲ፣ ማውንቴይን ፓርትነርሺፕ ፎረምና እና ሌሎች

ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው አገር በቀል የሆኑና፣ ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ የሚያደርጉ

መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ማህበሩ ባለው የግንኙነት መረብም በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ብሔራዊ የአካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናቶች አቢይ

ኮሚቴዎችና ግብረ ኃይሎች አባል በመሆን የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ናሺናል

ባዮዳይቨርሲቲ እስትራቴጂ ኤንድ አክሽን ፕላን (NBSAP)፣ ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ፣ ናሽናል ፍላወር

አሊያንስ፣ ሴንትራል ሪፍት ቫሊ ዎርኪንግ ግሩፕ፣ ሸካ ፎረስት አሊያንስ አድቮከሲ ግሩፕ እና ማን

ኤንድ ባዮስፊር ብሔራዊ ግብረ ኃይል የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በአቢይ

ኮሚቴና ግብረ ኃይል አባልነት አገልግሎት ከሰጠባቸውና ከሚሰጥባቸው ድርጅቶች ውስጥ የሚጠቀሱ

ናቸው፡፡

የወፎች ጥናት

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በወፎች ጥናት ላይ የተሠማራ

መንግሥታዊ ያልሆነ ብቸኛ ተቋም ነው፡፡ በዐበይት የአዕዋፍ መገኛ ቦታዎች / Important Bird Areas

Page 10: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

/ ፕሮግራም አማካኝንት በ69 ሥፍራዎች ላይ ጥልቅ ጥናት በማከናወን የስጋት ምንጮችንና ሊወሰዱ

የሚገባቸውን የመፍትሔ አማራጮችን በመለየት ጠቃሚ መረጃዎችን አጠናቅሮ በመጽሐፍ መልክ

አቅርቧል፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለወፎችና ከወፎች ጋር ተዛማጅነት ያለው ዕውቀትና

ግንዛቤ እያደገ ይገኛል፡፡ በርካታ የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎችም የማስተርስና የፒ. ኤች. ዲ የመመረቂያ

ጥናት ሥራዎቻቸውን ከኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ጋር በመተባበር በአእዋፍ

ላይ በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ምስጋና

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር (ኢዱእተታማ) 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል

በምናከብርበት በዚህ ወቅት የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ያደረጉትን አሰዋፅኦ መዘከር ተገቢ ነው፡፡

ከሁሉም በማስቀደም ማህበሩ ህልውና እንዲያገኝ ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ላበረከቱት መሥራች አባላትና

ባለአደራ ኮሚቴ አባላት ከፍ ያለ አድናቆትና ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በይበልጥ ደግሞ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ለሆነው መንግሥታዊ ያልሆነ የአካባቢ ጥበቃ ማህበር እንዲመሠረት ሀሳብ

በማፍለቅ ግንባር ቀደም ሚና ለተጫወቱትና ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ የማህበሩ የቦርድ ሰበሳቢ

ለነበሩት ሚስተር አለን ኢ. ኪንግ ልዩ ምሥጋናችንን እንቸራለን፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት በንቃት በመሳተፍ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕት አድርገው በበጎ

ፈቃደኝነት ሲሠሩ ለቆዩ የቦርድ አባላት የላቀ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በአባላቱ፣ ተመሳሳይ ዓላማ ባላቸው

ባለድርሻ አካላት፣ ለድርጅቱ በቁርጠኝነት ሲያገለግሉ በቆዩ ሠራተኞችና የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች

በመታገዝ የቦርድ አባላቱ የማህበሩን ገፅታ በመገንባት አሁን ካለበት ደረጃ አድርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዱር

እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ዓላማውንና ተግባራቱን እዳር ለማድረስ ባደረገው እንቅስቃሴ የቦርድ

አባላቱ መተኪያ የሌለው ሚና የተጫወቱ ሲሆን፣ የነርሱ ግልጽና ጠንካራ አመራር ባይታከልበት ኖሮ

ማህበሩ አሁን ካለበት ደረጃ ሊደርስ አይችልም ነበር፡፡

አካባቢን መጠበቅ፣ ብዝሐ ሕይወትን መንከባከብ እና የማህበረሰቦች ኑሮ እንዲሻሻል ማድረግ ሙሉ

በሙሉ የመንግሥት ሃላፊነት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድርሻ

መንግሥትን ማገዝና ክፍተቶችን መሙላት ነው፡፡ እንደ ኢዱእተታማ ያሉ ማህበራት በተጨባጭ

የሚታይ ስኬታማ ሥራ በመሥራት ሃላፊነታቸውን መወጣት የሚችሉት የመንግሥት መልካም

ፈቃድና የህብረተሰቡ ተቀባይነት ሲታከልበት ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ

ማህበር ለመንግሥት በአጠቃላይ እና አግባብነት ላላቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ስለመልካም

ፈቃዳቸው፣ አመቺ የሥራ ሁኔታን በማመቻቸትና ተገቢውን ድጋፍ በመስጠታቸው ባለውለታው

መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ ከልብ የመነጨ ምስጋናም ያቀርባል፡፡ በየአካባቢው አጋሮቻችን የሆኑት

Page 11: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ማህበረሰቦችና የፕሮጄክቶች ተጠቃሚዎች ዓላማችንን በመደገፍ ላደረጉልን ትብብር ጥልቅ የሆነ

አድናቆት አለን፡፡

የልማት አጋሮቻችን ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ ባያደርጉልን ኖሮ የማህበራችን

ህልውና ሊረጋገጥ አይችልም ነበርና፣ ለነዚህ አካላት ከልብ የመነጨ ጥልቅ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

ከግለሰብ እስከ ባለአደራ በጎ አድራጎቶች፣ ከኤምባሲዎች እስከ መንግሥታት እና መንግሥታዊ ካልሆኑ

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እስከ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች እና ሌሎችም እስካሁን ላደረጉልን ድጋፍ

ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለወደፊቱም ትብብራቸውና አጋርነታቸው ቀጣይነት እንደሚኖረው ፅኑ እምነት

አለን፡፡

የመጨረሻውና ነገር ግን ከሁሉም በላይ፣ ዓለም አቀፍ የአዕዋፍ ድርጅትና አባላቱ ማህበሩን በገንዘብ፣

በገጽታ ግንባታ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ የቴክኒክ አቅም እንዲኖረው በማድረግ ረገድ ላበረከቱት ድጋፍ

ባለውለታችን መሆናቸውን ሳንገልጽ አናልፍም፡፡ የዓለም የአዕዋፍ ድርጅት አባል የሆነውና የጀርመን

የተፈጥሮ ጥበቃ ማህበር (NABU)፣ ኢዱእተታማ ለሚተገብራቸው በፕሮጄክት ላልታቀፉ ተግባራት

መደጎሚያ የሚሆን ከግዴታ ነፃ የሆነ ድርጅታዊ ድጋፍ በመስጠት ላደረገልን ከፍተኛ ድጋፍ ልዩና የላቀ

ምስጋና እያቀረብን፣ ይህም በደቡብና ሰሜን ዓለም አቀፍ የአዕዋፍ አጋር ማህበራት መካከል የተደረገ

የትብብር ተምሳሌት መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡

Page 12: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

የኢዱተታማ አጭር የፎቶገራፍ ዘገባ

A SHORT PICTORIAL REVIEW OF EWNHS

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለማህበሩ ድጋፍ ያደርጉነበር

H.I.M Haileselassie I was very supportive of theSociety

ሚስተር አለን እና ሚስ ሔልጌ ኪንግ የዕድሜ ልክ የማህበሩደጋፊዎች ናቸው

Mr. and Ms. Alan King seen here are life timesupporter of the Society

ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ለኢዱእተታማ ተቋማዊይዘት መሪ ሚና ተጫውተዋል

Prof. Shibru Tedla played a leading role ininstitutionalizing EWNHS

Page 13: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

.

የዓለም የአካባቢ ቀንና ሌሎች የአካባቢ ጥበቃበዓላትን በማክብር ኢዱእተታማ ፋና ወጊ ነው

EWNHS is a pioneer organization in thecelebration of World Environment Day (WED)& other Environment events

ሕብረተሰቡ ለተፈጥሮ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ ኢዱእተታማ የግንዛቤ ሥራዎችን ይሠራል

Awareness raising about nature conservation is an important programme area of EWNHS

በተለያዩ መንገዶች ህብረተሰቡ ስለአካባቢ ግንዛቤ እንዲኖረው ጥረት ተደርጓል

Conservation Out-reach Programme Activities

Page 14: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

የተጎዳ ስርዓተ ምህዳር እንዲያገግም የተከናወኑ ሥራዎች - አቢጃታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ አካባቢእና ሊበን ወረዳ ጉጂ ዞን

Rehabilitation of fragile eco-system around Abijata Shalla NP & Liben Woreda Guji Zone

የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ሥራዎች

Conservation Activities

Page 15: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

በኢዱእተታማ የተካሄ የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ውጤት እያሳዩ ነው

EWNHS Conservation efforts are showing a difference

Page 16: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ሊበን ላርክLiben Lark

ዞሪትPrince Ruspoli’sTuraco

ዋይት ቴልድ ሰዋሎWhite tailed swallow

ኢዱእተታማ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥበቃና እንክብካቤ ከሚያደርግላቸው ለጥፋት የተጋለጡ

ብርቅዬ የአገራችን ወፎች ጥቂቶቹ

A few endangered bird species of Ethiopia whose conservation EWNHS has prioritized

Page 17: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

በማህበራዊ አገልግሎት እና ኑሮን በማሻሻል ረገድ የተከናወኑ ተግባራት

Social Services and Livelihoods improvement Activities

ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለትምህርት ቤቶች፣ ለፕሮጄክት ተጠቃሚዎችና ለእንስሳት

Clean Water for Schools, Project Beneficiaries, and Livestock

Page 18: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ኢዱእተታማ በአንዳንድ ት/ቤቶች በጣም የተጎዱ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባትም ሆነ በመጠገንየመማር ማስተማር ሂደት የተሻለ እንዲሆን እገዛ አድርጓል

EWNHS has supported schools to improve the teaching learning environment by

constructing & repairing dilapidated class room buildings – Bufata Arjo Elementary School,

Central Rift Valley (West Arsi Zone)

Page 19: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

በአዲስ አበባ የደጋ ፍራፍሬ ዛፎችን በማስተዋወቅ ረገድበኢዱእተታማ የተሳከ ሥራ ተከናውኗል

EWNHS has successfully promoted temperate fruit trees inAddis Ababa

የማህበረሰብ አካባቢ ተንከባካቢ ቡድኖች በገቢማስገኛ ተግባራት በመሳተፍ አባሎቻቸውንተጠቃሚ አድርገዋል

Community Conservation Groups havebenefited their members through incomegeneration activities

Page 20: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

ETHIOPIAN WILDLIFE & NATURAL HISTORY SOCIETY

GOLDEN JUBILEE ANNIVERSARY ISSUE

1966 – 2016

August, 2017

Page 21: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

FIFTY YEARS OF DEDICATION TO CONSERVATION

Birth of EWNHS

On 21 June 1966, a group of keen environmentalists and advocates of sustainable use of

natural resources, most of whom were expatriates, formed the nucleus for what is to be the

first indigenous environmental NGO in Ethiopia. The Ethiopian Wildlife and Natural History

Society (EWNHS), which was initially conceived as a Social Club, was evolved into a non-

governmental, not-for-profit and non-religious, membership based indigenous environmental

NGO in September 1966, in Addis Ababa, Ethiopia. The 32 founding members selected and

formed a Caretaker Committee of 10 individuals, namely, Miss P. Allen, Dr. Birhane Teoume-

Lessane, Brother Alfred Kinzing, Mr. P. Walshe, Mr. J. M. Dobson, Dr. F.P. Lisowski, Mr. St.

Mandalidis, Mr. J.H.C.Talbot, Major Gizaw G/ Giorgis and Mr. Alan E. King from among its

ranks.

Gradually, the number of members grew to 71, out of which the Ethiopian nationals were only

4. One might ask as to why the majority of the members are expatriates. It has not been

possible to come across historical documents, which substantiate why so many expatriates

happened to be in the fore-front of such an initiative. On the other hand, this of course

may not be accidental. The fact that the initiators went as far as succeeding to win the

heart and mind of the Emperor as the Society’s patron could be an evidence in itself

that some of the expatriate members in the Caretaker Committee had easy access to the

Imperial Court in connection with some important mission in the country. In that respect,

they also obviously had the opportunity to visit some parts of the country and must have

been amazed by the natural beauty of the country and the potential threats ahead. On

the other hand, although the environmental agenda was a low key affair in the 60s in

Ethiopia, it was still better understood in the western world where most of the Caretaker

Committee members came from. Hence, while the few Ethiopians did play crucial roles,

due credit should be given to our expatriate friends for their initiative that eventually led to

the establishment of EWNHS.

Considerable efforts were made to gear the Society towards a more focused nature

conservation endeavours. In this respect a sterling effort was made in the late 1970s, by

Professor Shibru Tedla the then Head of Research and Publication of Addis Ababa University

Page 22: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

(AAU), and Lecturers of the Biology Department (AAU). Their key activities include among

others, strengthening the Executive Committee, revising the Society’s areas of operation, and

establishing a Secretariat which is entrusted with the responsibility of fulfilling its vision and

mission. Accordingly, the Executive Committee led by Professor Shibru Tedla, in consultation

with AAU, opened the Society’s Office in a building near the former Kara Marra Hotel on Bole

road, in 1993.

From its establishment in 1966 until it was reorganized and structured at secretariat level

in 1993, the Society was run by an Executive Committee consisting of ten members, for

about 26 years. Meetings were held at residentials of members who volunteered to host.

Although there were challenges, the commitment of members to sustain the Society had

always prevailed. Four years after it was legally registered, Executive Committee

members, particularly Dr. Birhane Teumelisan Co-director of the National Laboratory &

Research Institute and V/President of the Society made a passionate appeal to His Majesty

Emperor Haileselassie to be the Society’s patron. And in November 1968 the Society was

accorded the honour and privilege of His Majesty’s patronage. The Emperor’s guidance

was immediate. Besides financial support, His Majesty gave a directive to change the

Society’s name from "Ethiopian Natural History Society" to "Ethiopian Wildlife and Natural

History Society", to indicate the importance of wildlife conservation. The Emperor’s

passion for conservation was reflected in his speech, when he received the Society’s

Executive Committee members. The following is an excerpt from the speech:

"The protection of Ethiopia’s animals and plants in their natural habitats is

not motivated only by sheer concern and passion for their beauty; but is

rather an effort aimed at conserving and taking care of the country’s

heritage for the next generation."

We are celebrating this anniversary without the founding members, who have either

passed away long ago, or are too frail to join us. One of the founding members, Mr.

Alan E. King who lives in Adelaide, Australia, is still supporting EWNHS to this date. The

Ethiopian Wildlife and Natural History Society is heavily indebted to him, and as such, his

unparalleled support to the Society should be acknowledged.

Page 23: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

With this short prelude, it is important to underline that without the initial initiative and

voluntary commitment of the Caretaker Committee, who single handedly tackled the

obstacle on the way, EWNHS may not be what it is today, or might not have even been

in existence. We must always remember the wonderful job they did, and work hard to

fulfill their wishes.

Achievements

The establishment of EWNHS by the founding members is in itself a great achievement.

For a long time the Society’s activities were confined to indoor functions such as panel

discussions on salient environmental issues, presented by professionals; and outdoor

excursions to natural and historical sites. Besides indoor/outdoor activities, the publication

of Walia, a quasi-scientific journal, which featured important environmental topics, was an

achievement worth mentioning. All these activities were run voluntarily by members.

In course of time, however, it became evident that the volume of activities and the

recognition the Society accorded both nationally and internationally became too demanding

to be handled by volunteers alone. Hence, it became imperative to establish a permanent

Secretariat, and hire fulltime staffs (currently 15) who work in collaboration with the

volunteers. With subsequent transformation, the Caretaker Committee was institutionalized

evolving EWNHS into an officially registered Indigenous Non-state Environmental Society,

with a permanent Secretariat and salaried staff, in September 1993.

Depending on situations and financial availability, the Ethiopian Wildlife and Natural

History Society carry out its activities in different parts of the country in collaboration with

government organizations and other partners. The Society has forged a strong working

relationship with a number of government ministries and agencies. Some of our partners

include among others, Ministry of Environment, Forest and Climate Change; Ministry of

Agriculture and Natural Resources; Ethiopian Wildlife Conservation Authority; Ethiopian

Biodiversity Institute; Oromia Forest and Wildlife Conservation Enterprise; Addis Ababa

University, Biology Department; Horn of Africa Regional Environmental Center and

Network; Population, Health and Environment Consortium Ethiopia (PHE); Regional

Bureaus of Agriculture; Schools; and Community Organizations.

Page 24: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

The achievements of EWNHS have been growing with its transformation into a

permanent Secretariat, and clearly defined programme areas, namely, Environmental

Protection and Biodiversity Conservation; Environmental Education, Awareness Raising

and Community Outreach; and Monitoring and Research. Currently, the Society is run by

voluntarily serving Board of Management of seven members. The Board of Management

is selected from among members at the Annual General Meeting, every four years.

While the Board focuses on policy issues, the day to day activities are carried out by

salaried staff headed by Executive Director. The Executive Director is at the same time

a non-voting Board member, serving as its secretary.

The following are some of the achievements of EWNHS since 1993:

EWNHS pioneered the celebration of World Environment Day (WED) with

school Nature Clubs, following the decision of United Nations Conference for

Environment and Development in Rio de Janiero in 1992;

Pioneered in promoting Environmental Education within Ethiopia, working

through Nature Clubs established in over 400 Elementary & Secondary Schools,

Teacher Training Colleges and Communities distributed throughout the country.

It has organized 21 Regional Environmental Education Workshops for 345

Teachers and other experts;

Published over 40 assorted thematic environmental support publications,

including brochures, posters, factsheets, resource materials, club guides,

booklets, books and magazines to various target audiences;

Promoted the transfer of environmental knowledge and awareness via two of its

publications, “WALIA”, a quasi scientific journal, and “AGAZEN”, which features

short reading materials on environment for students and the youth;

Conducted an intensive assessment and identified 69 key sites within Ethiopia

that are extremely important for conservation of endemic and threatened birds

and other taxa, and published a book on the Important Bird Areas (IBAs) of

Ethiopia, a first inventory of its kind in Africa;

Served as spring board for establishment of quite a number of successful

conservation institutions in Ethiopia, as some Executive Directors and key staff

Page 25: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

members of these institutions used to be Members of School Nature Clubs

established by EWNHS in the past;

Raised and distributed over 3.5 million seedlings of assorted indigenous and

exotic plant species to be planted in school and sacred grounds, and highly

degraded landscapes;

Played decisive roles in improving the conservation status of the White-winged

Flufftail, a globally Endangered bird species, by conserving its paloustrine

wetland habitat, using the Site Support Group (SSG) at Berga IBA site as entry

point to the wider community and local government stakeholders;

Carried out intensive monitoring at 23 selected Wetlands that are Important as

feeding and resting stages for migratory bird species for 12 years in the

row, as integral part of African Waterfowl Census scheme;

As a member of BirdLife International, championed in taking the leading role in

conservation and research of endemic and threatened birds of Ethiopia,

including Northern Bald Ibis, White-winged Flufftail, Liben Lark, Abyssinian Bush-

crow, White-tailed Swallow, Prince Ruspoli’s Turaco, etc. In the research front, 2

MSc and 2 PhD studies were facilitated;

Developed quite a number of Management Action Plans for Conservation of

threatened bird Species – White-winged Flufftail, Liben Lark, etc.;

Carried out Rapid Biodiversity Assessment at 24 Churches & 15 Monasteries to

investigate species richness. To that effect, 223 indigenous woody plants have

been identified and recorded, of which 120 species have been found to be

used by local people for different purposes. Forest Management Plan was also

developed for 5 Churches and Monasteries;

As part of promoting Indigenous Knowledge, it has been possible to identify

544 sacred sites in the Gamo Highlands of south Ethiopia, of which 100 were

Sacred Forests, both natural sites and burial cemeteries that have been

designated by local communities as conservation entities; and

Successfully implemented several Complex and Multi-dimensional Projects thatinvolved stakeholders of different perspectives, including Global EnvironmentFacility (GEF) IBA Project, Migratory Soaring Birds (MSB) Project, Royal

Page 26: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

Netherlands Embassy (RNE) Project, Ethiopian Sustainable Tourism Alliance (ESTA)Project, Critical Ecosystem Partinership Fund (CEPF) Project, etc.

While the achievements stated above speak for themselves, it is important to underline

that EWNHS is more importantly proud of pioneering Environmental Education and

Awareness-raising programmes in hundreds of elementary and secondary schools.

Nothing is more rewarding in conservation, other than wining the hearts and minds of

thousands of youngsters to live in harmony with their environment. Indeed, the

environmental education activities initiated by EWNHS in few schools have further

flourished with the establishment of nature clubs in hundreds of schools throughout the

country.

Although EWNHS has made commendable achievements over the years, there should

not be room for complacency, be it on the part of EWNHS or any other conservation

organization for that matter, as we have still a long way to go and multifaceted

challenges to resolve.

Partnership, Establishment of Local Conservation Groups and Net-working

During 50 years of its existence, the Ethiopian Wildlife and Natural history Society has

worked in collaboration with a number of foreign partners, implementing projects and

sharing information and experiences on conservation. Foreign partners which have been

supporting the Society include among others, European Union; GEF-UNDP; British

Embassy; French Embassy; Finland Embassy; Royal Netherlands Embassy; Belgium

Embassy; Swedish International Development Authority (Sida); Canada International

Development Authority (CIDA); Finland International Development Agency (FINNIDA);

Norwegian Agricultural Development Agency; Maurice Laing Foundation; Walt Disney

Company Foundation; Disney Wildlife Conservation Foundation; Middelpunt Wetland

Trust; IUCN-EARO; DFID; Christensen Fund; US Fish and Wildlife Service; US Forest

Service; Counterpart International; Conservation International; Family Health International

(FHI360); Birdlife International; Norwegian Ornithological Society (NOF); Finish Ornithological

Society (SOUMI); Spanish Agency for International Development & Cooperation (AECID); Royal

Society for Protection of Birds (RSPB); Naturschutzbund Deutschland (NABU); Tree Aid UK;

Page 27: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

Trees for Cities; British Birdfair; Critical Ecosystems Partinership Fund (CEPF); Darwin

Initiative; and Wetlands International.

The Ethiopian Wildlife and Natural History Society has also been working in

collaboration with local partners. The Society is among the front-runners in creating

Local Conservation Groups (LCGs), grass-root conservation partners, which have been

playing supportive roles in nature conservation. The Berga SSG/LCG in West Shewa

Zone and the Abijata Shalla Environmental Degradation Mitigating Group in West Arsi

Zone (Central Rift Valley) are such LCGs, which are active in biodiversity monitoring and

conservation in their respective localities.

The Society has also been active in networking with like-minded conservation

organizations. Some of the network members include BirdLife International Secretariat;

Albertine Rift Conservation Society (ARCOS); Mountain Partnership Forum; Wetlands

International; Middelpunt Wetland Trust; Horn of Africa Regional Environment Centre &

Network; and PHE Consortium Ethiopia.

The Ethiopian Wildlife and Natural History Society is one of the few known sources of

information on birds and wildlife studies. Because of this, the Society is often selected

to serve as a member of various committees and task forces on environmental

matters. Nile Basin Initiative; National Flower Alliance; Central Rift Valley Working

Group; Sheka Forest Alliance Advocacy Group፣ National Biodiversity Strategy and

Action Plan (NBSAP) Technical Team and Man and Biospherte National Task Force

are some of the main committees and task forces to which EWNHS is/has been a

member.

EWNHS is the only NGO that is working on the study of birds in Ethiopia. In

connection with this, the knowledge and awareness about birds in Ethiopia has

progressed significantly. Through the IBA programme, the Society has indicated its

concerns and the necessary precautionary measures to be taken in all the 69 IBAs in

the country.

Page 28: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

Acknowledgements

At this point in time of celebrating the 50th year anniversary of the Ethiopian Wildlife

and Natural History Society (EWNHS), it would be proper to recognize the contributions

of various individuals and institutions. At the outset, we would like to extend our utmost

appreciation and sincere thanks to the founding members and Caretaker Committee

Members who have been instrumental for the very survival of the Society. Moreover,

we cannot express enough thanks to Mr. Alan E. King who has inspired the nucleus

idea that led to the establishment of a non-state conservation institution in Ethiopia, the

current EWNHS. He has also been the chairperson of the Board of Management for

many years.

We are hugely grateful and indebted to the past and active Board of Management

Members of the Society for investing their own financial resources and sacrificing their

precious time on voluntary basis. Underpinned by members, like-minded partners,

dedicated employees and volunteers, Board Members built the profile of the Society

and guided it to the stage where it is now. Nobody has been more important to

EWNHS in the pursuit of its objectives and activities than the Board Members, without

whose genuine guidance the Society would have not been what it is now.

Protection of environment, conservation of biodiversity and ensuring of improved

livelihoods of communities is absolutely the mandate of Government. Civil society

organizations are there to assist government and fill gaps. For any civil society

organization, like EWNHS, to be successful on the ground and discharge its

responsibility, the good will of Government and acceptance by communities/beneficiaries

is extremely crucial. EWNHS is deeply indebted to the Government in general and the

line ministries in particular for their good will, provision of working environment and

support. Our deep appreciation goes out also to the local communities/beneficiaries for

consenting to our objectives and partnering with us.

We would like to express our deep and sincere gratitude to development partners,

without whose financial support and technical backstopping, the existence of the Society

for 50 years would not have been realized. They are too many to enumerate here from

Page 29: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

individuals to trusts & foundations, embassies to Governments and from International

NGOs to International Development Agencies. We gratefully acknowledge the funding

kindly granted to us thus far and look forward for future collaborative partnerships.

Finally, yet importantly, we owe a huge debt of appreciation to BirdLife International

Secretariat (and its members) for the support they extend to the Society in terms of

fundraising, image building and all-rounded technical capacity building. A special and

profound gratitude goes to NABU, BirdLife Partner in Germany, for extending

institutional support to EWNHS as non-restricted funds for meeting core activities of the

Society, while at the same time becoming an example of north-south collaboration

between BirdLife partners.

Page 30: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት

EWNHS Membership Registration Form

I. Personal details1. Dr/ Mr/Mrs/Ms: _____ 2. Full Name: _______________ _____ 3. Sex (M/F) : ______ 4. Date of Birth (d-m-y)*: _____________ 5. Place of Birth* :_______ ____ 6. Nationality: _____________ 7. Qualification (Dip, BA, MA, BSc, MSc,etc.): ____ ___8. Field of Study: ________ _______ 9. Occupation:_____________ 10. Organization: ______________________11. Position: _________________________.

II. Contact Address12. Country: ____ ____ 13. State: _____ __ ____ 14. City/Town: __ ______15. Subcity: _________ 16. Kebelle: _____ 17. H. No*: _________ 18. P. O. Box:____ __ 19. Tel (Office):_____ _ 20. Tel (Home):______________21. Mobile: _____ ____ 22. Fax: ______ _______ 23. E-Mail: ___________ _ 24. Website:______________

* Optional

III. Membership CategoryPlease tick the membership category that most suits you:Membership Category Subscription Fee1. Ordinary Member Birr60.002. Family Member (Ethiopians) Birr125.003. Elementary School Students (Grades 1-6) Birr5.00 4. Secondary School Students (Grd 7-12) Birr10.005. Colleges and University Students Birr15.00 6. Nature/Wildlife Clubs, Schools & CBO Birr45.007. Institutions (NGOs, GOs, Colle. & Univ.) Birr100.008. Corporate members (profit making org) Birr500.009. Supporting Members (Resident Expatriates

& Ethiopians by Birth) US$20.0011. Life Members (Resident Ethiopians) Birr1500.0012. Life Members (Resident Expatriates) Birr2500.00

IV. For Membership Categories No. 6-8 only:

I, the undersigned, confirm my Institution’s interest and commitment to be a member of the Ethiopian Wildlife and NaturalHistory Society and pledge to fulfill the membership requirements, including the payment of the annual membership fee.

____________________________Membership authorized by Position ________________________

Signature__________

V. Mode of Payment for all Membership Categories

I wish to pay:1. by cash on the date of the General Annual Meetings2. directly at the EWNHS Office 3. by cash to a collector assigned by EWNHS 4. as bank transfer to the dedicated bank account of EWNHS5. as postal money order

Date of Application: _______________Signature: ________________________(For Membership Categories other than 6, 7 and 8)

Please tear off and return the completed form to the EWNHS Secretariat in person, the scanned copy by E-mail([email protected]) or by post (EWNHS, P. O. Box 13303, Addis Ababa, Ethiopia).

Page 31: ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የተዘጋጀphe-ethiopia.org/admin/uploads/attachment-2634-EWNHS 50th... · ለአካባቢና ብዝሀ ሕይወት